እድል እና መልስ እንደሚሹ ልቦች እና እድል ነፍገው ጥያቄውን እንዳላደመጡ ልቦች የሚያሳዝን ምን ይኖር ?
ውዴ
ላንቺም ለኔም ላይበጅ ረፍዶ ከማዘን
እድል ስጭኝ እና ልንገርሽ የውስጤን
ፅፌ ካልሰደድኩት መሀል
ከሶላ ✍🏾
ብትሄጂ ያለአንቺ ልኖር ብገደድም እንኳን አማራጭ የለኝምና እቀበላለሁ
ቢሆንም ግን አትሂጂ
ከመራቅሽ በላይ በትዝታ መኖርን እፈራለሁና
ያለተቋጩ ሀሳቦች
ከሶላ ✍🏾
ሕይወት ግራ መኖር ሽንቁር
ፍላጎቷን ልሳን የላት አትናገር!
ላትናገር...
እኔም ተውኩኝ መልሷን ልሻ
በዝምታ ማለፍ ብቻ የኔ ድርሻ
ገጣሚ ፦ ሶላ ✍🏾
Inspired by Rami 💁♀
፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨
እንደኔ ያለ ሰው
ከ12ቱ ወራት
ለድካም ከማትሆን ከ52 እሁዳት ከአመት እለታት
ቀኑን ዘሎ ዘሎ አንዷን ነው ሚቆጥራት
ውዴ
የሌላውን ባላውቅም
ስፍራዋን ሳትስት በምስራቅ እያለች
እፍኝ ለአይኖቼ ፀዳል ከሰወረች ከፀሀይ ወጋገን
እውነት እልሻለሁ
ለኔ ላንዱ ምስኪን ሻማሽ ነው ብርሀን
ሌላውን ባላውቅም
የእውነትን ሻማ
ውሸት በንፋሷ ሽው አርጋ ስቀማ
እሰይ በሚል አለም በበዛበት ሌባ
እውነት እልሻለሁ
ለታረዘው ልቤ ልደትሽ ነው ካባ
እውነት እልሻለሁ
ደምድሜ ባላውቅም
ውሸት ላሳወረን ለኛ ግብዝ አለም
ከልደትሽ ውጭ የእውነት ቀን የለንም
ከልደትሽ ውጭ ሌላ ቀን የለንም
ሶላ ✍🏾
@Ammelakuletters
@Ammelakuletters
@Kehiwotmahder
እንኳን ላንቺ ቀርቶ
መሰናበቻዬን ለማላውቀው ለቀን
.
.
የምጨነቅበት የለኝም ሰቀቀን
ከሶላ
@Ammelakuletters
@Ammelakuletters
@Ammelakuletters
Viral ግጥም ( don't try to laugh)
የኔ የከንፈር ጣዕም ተወዳጅ ቀይ ሎጋ
እኔ 'ወድሻለሁ እንደ አ**ስጋ
ባይሽ የማልጠግብሽ የውበት ቀለሜ
እሳሳልሻለሁ እንደአርቲስቶች እድሜ
ብቻ አንቺ ከመጣሽ ካላልሽኝ ለመቼ
ለቲክታክ አላንስም
አግቢኝ እልሻለሁ ዱቄት ተቀብቼ
ከሶላ
@Ammelakuletters
@Ammelakuletters
@Ammelakuletters
<<መልካም አዲስ አመት እንዲሆን አልመኝም!>>
ድርሰት ፦ ከሶላ
በተፈጥሮዬ አዲስ ነገር እወዳለሁ ... አዲስ ስፍራ፣አዲስ እውቀት፣አዲስ ምግብ ቤት.. እንዲሁም ዛሬን! ምክንያቱም ዛሬ ትናንት ያልነበረች ነገም የማትደገም ብቸኛ እና አዲስ ስለሆነች .... አዲስ ሰውም መተዋወቅ እወዳለሁ። በተለይ እንዳንቺ ቆንጆ የሆነች ሴት! በርግጥ በስራዬ እና በውሎዬ ዙሪያ ብዙ ቆንጆዎች ብትዋወቅም ቆ-ንጆ-ሪ(ቆንጆ እና እንጆሪ) የሆነች ጎረቤት ሲኖረኝ ግን የመጀመሪያዬ ነው። ስለአንቺ ባሰባሰብኩት ጥናታዊ መረጃ አዲስ ተከራይ ነሽ ።
ከማላውቀው ባህሪሽ በስተቀር ለኔ አዲስ በመሆንሽ ብቻ እንድወድሽ እገደዳለሁኝ !ግን ምን አይነት መውደድ .... ?
የዘመኑ ሳይንስ እንደሚለው የአንድ ሰው የፊት ገፅ በአለም ላይ 9 ጊዜ ተደጋግሞ ይገኛል ይላል ... የእኛ አምላክ ፈጣሪ ግን ሁሉን በጊዜው ፈጥሮ ጨረሰ እንጂ የሚፈጥረው የሚያልቅበት አምላክ አይደለም .... በቅርበት የማውቃቸው አንዳንድ የሰፈሬ ልጆች ስለውበትሽ ስነግራቸው ቁንጅናሽን ለማጣጣል << ምን ታካብዳለህ የሷ አይነት 9 አሉ >> ቢሉኝም ለኔ ግን የሚፈጥረው በማያልቅበት እጅ የተሰራስሽ አምሳያ የሌለሽ ብቸኛ ቆንጆ ነሽ። በርግጥ ነፍስ እና ስጋ ባይኖረውም አንቺን ሊመስል የሚችል አንድ አለ እርሱም በመስታወት የምታዪው የራስሽ ውብ ምስል ነው!
እርሜን በምወደው ዛሬ ባይሽ ወደድኩሽ ! እርሙን ዛሬ ቁንጅናሽን ቢመለከት ፤ ጎረፈ ይሄ ሁሉ አዲስ ስሜት ....
ውድዬ ... አምላክ አንቺን ይስጠኝ ብዬ እምላለሁ ከዚህ በፊት የመውደዴን አይነት ባላውቀውም ይህ አይነት መውደድ ግን ለኔ እንግዳ ነው
ግን.... ስለአንቺ ብዙ እንዳስብ ብዙ እንዳሰላስል ያደረገኝ በአይምሮዬ የሚመላለስ አንድ ጥያቄ አለ ... አስከአሁን ከአሁንም እስከዚህች ቅፅበት ደረስ አዲስ ሰውን መተዋወቅ የምወድ እንደሆንኩ ባውቅም አንቺን ግን ሳልተዋወቅሽ ለምን ወደድኩሽ
ዛሬን ልኬት በማይገኝለት መልኩ ወደድኩሽ እሺ ነገስ እንዴት ልሆን ነው? ከነገወድያስ? ስተዋወቅሽስ? ተጋብተን ልጆች ስንወልድስ???
መልካም አዲስ አመት እንዲሆን አልመኝም ቀርቤሽ ሁሌ እንደአዲስ የምወድሽ እንድትሆኚ እመኛለሁኝ እንጂ !
ስላነበቡት እግዚአብሔር ያክብርልኝ
ተፃፈ በሶላ መስከረም 1 2016
@Ammelakuletters
@Ammelakuletters
@Ammelakuletters
( ክፉ ሰው ቶሎ አይሞትም ጥሩ ጥሩው እንጂ ለሚለው አባባል ምን አልባት መልስ ከሆነ ብዬ የፃፍኩት ነው። << ሰው ከነኃጥያቱ እና ከነክፋቱ የሚወደው አምላክ ያለው እድለኛ ፍጡር ነው ... >> )
፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨
እግዜሩ ድንቅ ነው
የክፉውን ዕድሜ ረጅም ያደርጋል
ለምስኪኑ ደግሞ ጥቂት ኑሮ ይሰጣል
እንዴት ?
የየዋውን ነፍሲት
አምላክ አሳጥሮ በቶሎ የሚያስቀብር
ህያው እንዲኖር ነው በሰማዩ መንበር
በአንፃሩ ጌታ የከፋው ፍጡሩን ያስኖረው በመቶ
እንዲድን ሽቶ ነው በንሰሀው ጠርቶ
ከሶላ ✍
@kehiwotmahder
@kehiwotmahder
@kehiwotmahder
ከደብዳቤዎቼ ቅንጭብጭብ ፦ ፩
~ ልክ የጥቅምት ነፋስ እነደነካው የእህል ዘር ፀጉርሽ መለስ ቀለስ እያለ ሲወዛወዝ ሳይ ከአይኔም አልፎ ሀሳቤ እና ቀልቤ ወዲህ እና ወዲያ ይንከራተታሉ
~ ከረጅም ጊዜ በኋላ የምትወደው ሰው መጥቶ ያሳለፍነውን ሁሉ እንዳልተፈጠረ አድርገህ አስበው ሲልህ ባዶ ህይወት ይከብሀል ። በርግጥ ይህን ስሜት ከዚህ በፊት የማውቀው ቢሆንም በርሷ ሳየው እንደአዲስ ሆኖ ለምን እንደሚሰማኝ አላውቅም!
~ የተደሰትንበትን ዕለቶች አልረሳቸውም ፤ ካንቺ ያተረፍኩት ቀሪ ትዝታዎቼ ናቸው!
~ ፍቅርሽን ካጀበው ውቅያኖስ በላይ ዙሪያዬን የከበቡኝን ኮከቦች በሀሳብ መስኮት አሻግሬ እያየሁ ካንቺ ሰገነት ያደርሱኝ ዘንድ እማፀናቸዋለሁ
~ አልተሻለኝም!መጥተሽ በነበረ ጊዜ ህመሜን ብረሳም መድሀኒቴን ግን አላገኘውም
... ይቀጥል?ላል .... ❤️
@Ammelakuletters
@Ammelakuletters
@Kehiwotmahder
@Kehiwotmahder
(Inspired by sofi's poem)
ደሳሳ ደርባባ የሰናፍጭ ቤቴን ፣ ሊነሱኝ ከያዙ
ከጣራዬ ብሶች ፣
ከቀዳዳው በላይ አፍራሾች ከበዙ
በቤቱ ያሰበኝ ፣ የዘለዓለም አምላክ
የበለጠ ሊሰጥ ፣ በማይዘልቀው ቤቴ ፈተና ከላከ
የኢዮብን ትዕግስት ፣ 'ስክማረው ድረስ ወይኩን ፍቃድከ !
እንዲህ ነው የምለው
.
.
.
አሜን ነው የማውቀው ።
.... ከሶላ 🫡
@Ammelakuletters
@Ammelakuletters
@Ammelakuletters
ምርጥ ለቤትዎ እና ለኩሽናዎ ምቾት እና ውበት የሆኑትን የKENWOOD & ሌሎች የአውሮፓ ሀገር ምርቶችን ከእኛ ለእናንተ ከእቃዎቻችን በጥቂቱ👇
፨hand mixer
፨food processer
፨meat grinder
፨mini chopper for our kids
፨Blend classic(glass blender)
፨Multi fry pressure cooker
አቅሞን ያገናዘበ ስለሆነ ያነጋግሩን
የቴሌግራም ገፃችንን ይጎብኙ👇
/channel/kegnalenante
ስልክ፡ 0973412834
ከሶፊ እና ከሶላ 😱
፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨
አምጡልኝ ብዕሬን፥ሕመሜን ልከትብ
በቃላት ነጠብጣብ
ተስፋዬን ልቀጥል በፈጠርኩት ምናብ...
ግና ግን እናንተ
ለበሽታው ሰሪ ታለ ጤና አዳም
አትበሉት ግዴለም
ዘመናት ቢቆጠር ቢዳሰስ ዘለአለም
መድሀኒት ለአለም
ከፈጣሪ እንጂ ከፍጡር አይደለም!
Re-edit
@Kehiwotmahder
@Kehiwotmahder
@Kehiwotmahder
For those who are searching their happiness
ለራስህን የምትሻውን ደስታ የምታገኘው ባለህበት ስፍራ እንጂ ለመሆን በምትፈልግበት ቦታ አይደለም
ከሶላ ( #street_note's )
@Ammelakuletters
@Ammelakuletters
@Ammelakuletters
እኔ ፦ እንግዳ ስሜት ተሰምቶሽ ያውቃል...?
እሷ ፦ ሁሉም ስሜት መጀመሪያ እንግዳ ነው ❤️🩹
@Ammelakuletters
@Kehiwotmahder
<< በህይወቴ ትልቅ የተማርኩበት ሰው መደገፊያ ሊሆን አይችልም በተለይ እግዚአብሔርን ለቀህ ሲሆን >>
ወጣት ቤዛዊት ጥላሁን (በዶንኪ ቲዩብ የ"አንድ ሰው ህይወት" ፕሮግራም ላይ ቀርባ የተናገረችው አንገቴን ያስደፋ እወነት )
ልትሄጂ በወሰንሽበት በመጨረሻው መጀመሪያ ቀን ...
.....
ስትሄጂም አንቺን ሳስብ ምንአልባት የማዝን እንጂ ህይወቴን ሙሉ አንቺን የማስብ እና የማዝን የመሰለሽ ቀን ....
.....
የራስሽን ብርሀን ስትወስጂ ብርሀኔ እንዳንቺ የሚደበዝዝ እንጂ የሚጠፋ የመሰለሽ ቀን....
.....
በራቅሽኝ መጠን ልክ የምርቀው ከአንቺ እንጂ ከራሴ እንዳልሆነ ያልገባሽ ቀን ...
......
መሄድሽ ለኔ ስጠብቀው የነበረ የምስራች እንጂ መርዶ እንዳልሆነ የዘነጋሽ ቀን....
ያን ቀን ሂጂ ሂ ...ጂ
እኔም ከማይጠቅሙኝ ሁሉ አድነኝ የሚለውን የዘውትር ፀሎቴ እንደተሰማ ልነግርሽ ባልኩት ቀን .... ለካ
የ
ለ
ሽ
ም!!!
ያልተቋጩ ሀሳቦች
ከሶላ ✍🏾
@Ammelakuletters
@Ammelakuletters
@Ammelakuletters
መ...ለ...የ...ት እና መ...ለ...ያ...የ...ት ❤️🩹
ጥሁፍ ፦ ከሶላ🫡
Ft. Gossaye ... የቦሌው ጎዳና ሽር 'ምንልበት ፣ እኔን መልሶኛል አንቺን ሸኝቼበት 🧎🏿
🔴፦ የጥሁፉ የመጨረሻው ቃል " እንዳትይኝ " ላልቶም ጠብቆም ይነበብ
Video & Audio editor ፦ sofii 🙏
ይህ Video እና ቀጣይም እንዲለቀቅ ከፈለጉ 👍 ይጫኑ
@Ammelakuletters
@Ammelakuletters
@Kehiwotmahder
@Kehiwotmahder
<< መልካም አዲስ አመት እንዲሆን አልመኝም >>
አጭር ድርሰት በሶላ
ነገ ይጠብቁን
@Ammelakuletters
@Ammelakuletters
@Ammelakuletters
አንዳንዴ ከሚያመን ከበሽታው በላይ የማስታገሻውን መድሀኒት (painkiller) መልመድ በይበልጥ ይጎዳናል ... ልክ አንቺን መልመዴ ከቁስሌ በላይ እንደጎዳኝ ....
#Nomore_pain_killer 💊
#No_more_አንቺ 💔
WOW ... ከልቤ ስትርቂ ህይወት እና መኖር ተጀመረ
ተጣፈ ፦ በሶላ ✍🏾
Photo credit ፦ sophi
@Ammelakuletters
@Ammelakuletters
@Kehiwotmahder
@Kehiwotmahder
የሶላ ደብዳቤ
ክፍል ገፅ-በገፅ 💔
<< ይበርዳል ... >>
" በእውኑ ፍቅር እና አንድን ሰው ማፍቀር ይለያያልን ?"
@Kehiwotmahder
@Kehiwotmahder
@Kehiwotmahder
የሶላ ደብዳቤ
ክፍል ገፅ-በገፅ 🤗
" ከጀንበሯ ጋር ጠልቃለች 💔 "
The owner of this story was my friend & written by me .
👂💌 @Ammelakuletters
ሰው አለኝ 💝
ከሶላ ✍
Tamerat desta ( Kalkidan alegn ) 👑
@Kehiwotmahder
@Kehiwotmahder
@Kehiwotmahder
ሰላም ለእናንተ ይሁን (ዮሐ 20:26)
የትንሳኤ ግጥም ከሶላ
<< ዛሬም ሳትዘነጋን ሳትተወን ላፍታ
ዳግም ቶሎ ናልን ስንል ማራናታ >>
እንኳን ለጌታችን ለመድኃኒታችን ለእየሱስ ክርስቶስ ብርሀነ ትንሳዔ በሰላም አደረሳችሁ
@Kehiwotmahder
@Kehiwotmahder
@Kehiwotmahder
ከሶላ እና ሶፊ
.....ዘመን ሲመሽ #2
ጊዜ ሲሸሽ.......
በአባቶቻችን ፍክት ብሎ የነበረው ብርሀን መሽቶ ይታየኛል።ንጋት ይናፍቃል... ንጋት እንኳን ቢኖር እንዳናይ የአይናችን ጉድፍ ሰውሮታል...መልካም ሆነን ተፈጥረን ሳለ መልካሙን መንገድ አልመረጥንም...መልካምነት እምቢኝ፤ክፋት ይግዛን አልን። ሳይሰሩ ውጤት ብቻ ናፋቂ፤ክፋት ዘርቶ መልካም ጠባቂ።የድሎት እና የሆዳችን ተገዢ ከህሊናችን አጉድለን ኪሳችንን የምንሞላ፤ባደረግነው የማንፀፀት ሀፍረት የሌለን ልበ ደንዳና ድፍኖች ሆነናል። የዘራነው ዘር የወፍ ሲሳይ ሆኗል... ትርፋችን ብኩንነት ነው....
...ግብይይቱ ግን ተፋፍሟል.... የማይሸጥም የለም! የተሰረቀ ህንፃ ይሸጣል፤ታሪክ፤ቅርስ እና ማንነት በረከሰ ዋጋ ይሸጣል ። (በዚህም ይሄ ትውልድ ታሪክን አዛብቶ እውነትን ይራባል!)፤ሰው በቁሙ ይሸጣል። የሚገርመው ገዢው! የሚገዛው ወንድሙን፣ሻጩም የሚሸጠው የገዛ ወንድሙን ነው።
#2_ዘመን_ሲመሽ_ጊዜ_ሲሸሽ
የምንፈጥረው ችግር ተበራክቷል...ሰማዩ የምድሩን። ግፍ ያንፀባርቃል...ሀሩር ፀሀይ(እጅግ የሚለበልብ)፣ጭጋግ፣ቁጣ አዘል መብረቅ፣ውርጭ ከክፉ ስራችን የተጠመቀ መራር ፅዋችን ነው።ሁለት አይነት ሰው ሆነናል! ግራ የገባን እና ምንም ያልገባን... ወዴት እንደምንሄድ ያልተገነዘብን፤ ወደፊት እየረገጥን ወደኋላ የሚንራመድ፤ መድረሻውን ስንል መነሻው ጠፍቶን መሀል ቤት የቀረን ሆነናል። ልክ እንደኛ መንገድ የጠፋበትን እንከተላለን....
መብታችን ይከበር ለሚለው ሰልፍ ወተን ነዳጅ ተወደደ! ይቀነስልን!!! የሚለው ሰልፍ ላይ ተሰልፈን እንመለሳለን።...ሰፊ ቤተ-መቅደስ እያለን በጠባቡ አለም እየተጋፋን ነው...ቀኝ እጃችንን ግራ፣ግራ እጃችንን ቀኝ ልናደርግ እንፈልጋለን።የምንፈታተነውን አናውቀውም...ኑሯችን መልክ ብቻ ነው...ግብረገብነት ከህሊናችን ተፍቆ ጥላቻ በደማቁ ተፅፏል(ፍቅራችን ከጥቅም አይዘልም።) ለውጣችን ቁልቁል ነው።በክፋት ጎዳና ላይ ስለሆንን በእኛና በእኛ መካከል ፈጣን ዝግመተ ነውጥ ይታይብናል። ከራሳችን ጋር እንኳን ሰላም የለንም።
#2_ዘመን_ሲመሽ_ጊዜ_ሲሸሽ
ከአፅናፍ እስከ አፅናፍ በጥላቻ ደለል ተደፍነናል...ለተደረገ መልካም ነገር እንጂ ለተደረገው መጥፎ ነገር ሀላፊነቱን የሚወስድ ጠፍቷል...መልካሙን የኔ መጥፎውን የእናንተ ይላሉ።ማንን ማመን እንዳለብን ጨንቆናል ሁሉም በመረጃ አስደግፎ ይዋሻል...
የሚሉንና የምናየው ነገር ለየቅል ነው...በዳዩን ልኮ ሊያፅናን ይመጣል...(የማፅናናት ወይስ የመበደል ፍቅር ያለው???)
ከአካላችሁ አንዱ የናንተ አይደለም...ስለራሳችሁ ከእናንተ በላይ እኛ እናውቃለንም ይሉናል...(ጆሮዬ ነው ወይስ አፍንጫዬ የእኔ ያልሆነው...? )
ከአካላችሁ አንዱ ሲጎል ለውስጣችሁ ሰላም የምታደርጉት መስዋትነት ነው...ወንድማችንን እንዳንወድ ዘረኝነት ጠምዶ ይዞናል...ትስስራችን የመልካም ባህል ትውፊቶቻችን አፈር በልቷቸዋል ጤና ይስጥልኝ ትተን ጤና ይንሳልኝ፤ምነው በደፋልኝ ማለት ከጀመርን ሰነባብተናል... ልባችንም፤ዘመናችንም የክፋት እና የኅጥያት ማደርያ ሆኗል።
ሶፊ ያለው እውነቱን ነው "የደከመ ላይ የሚበረታ እንጂ የደከመን የሚያበረታ ጠፍቷል..."
መመደብ ትወዳላችሁ...
እኔንስ ማን ትሉኛላችሁ ?
"ኤሎሄ...! "
በፍፁም ቀላል አይደለም ለምትለው ህይወትህ በፍፁም ቀላል አትሁንለት!
.
.
.
.
ነጠብጣብ ቀለም ፤ ያለተቋጩ ሀሳቦች ( ከሶላ )
@Ammelakuletters
@Ammelakuletters
@Ammelakuletters