kehiwotmahder | Unsorted

Telegram-канал kehiwotmahder - የሶላ ደብዳቤ እና ሌሎችም ... 💌

-

የጥበብ ዋርካ ወደሆነው ገፃችን እንኳን በደህና መጣችሁ🤗 እባክዎን በዚህ የገፅ ዋርካችን አረፍ ይበሉ አረፍ ብለው በጥሩ አቀራረብ አዋዝተን የምናቀርበውን ግጥሞች ፤ ድርሰቶች ፤ ደብዳቤዎችን ያድምጡ ። በፔጃችን ፍቅርን በጥበብ ቋንቋ እንሰብካለን << ጥበብ የፍቅር መግለጫ ነው ፤ ፍቅር ደግሞ የጥበብ መገለጫ ነው >> #ጦጵያ #ቶጵያ 👇 #ዕድል_ፈንታዬ_ኢትዮጵያ_ሁኚልኝ_ሳሌም 💚💛❤

Subscribe to a channel

የሶላ ደብዳቤ እና ሌሎችም ... 💌

በህይወትህ ዙሪያ ቦታ የሰጠካቸው አብዛኛው ሰዎች ራስህን ችለህ ቆመህ ማየት ያስፈራቸዋል !


ለዚም ራስህን ችለህ እንዳትቆም ምርኩዝ ይሆኑልሀል እንጂ ራስህን ችለህ የምትቆምበትን አቅም እና ጥንካሬን አያሳዩህም


አሰሳ 1 : ራስህን ችለህ መቆም እንደምትችል ለራስህ አሳየው !

አሰሳ 2 : ለራስህ መሆን በቂ ነው


ነጠብጣብ ቀለም ፤ ያልተቋጩ ሀሳቦች ( ከሶላ )



@Ammelakuletters
@Ammelakuletters
@Ammelakuletters

Читать полностью…

የሶላ ደብዳቤ እና ሌሎችም ... 💌

ላንድ ተበዳይ ሰው የሚወደውን ከመለየት በላይ ሌላ ፍራቻ ያለው አይመስልሽም አደል? ለዛ ተበዳይ ሰው ከመለየት በላይ አዲስ ሰው ወደ ህይወቱ ማስገባት እንዲሚያስፈራውስ ታውቂያለሽ? ....

እኔ ግን የፈራውት እሱን አይደለም! የሁልጊዜ ጥያቄሽን ነው ...



አዲስ ሰው በህይወቴ ካስገባሁ በኋላ መጥተሽ እንዴት በሌላ ሰው ትተካኛለህ እንዳትይኝ ?


ከሶላ ማህደር ✌️


@Ammelakuletters
@Ammelakuletters
@Ammelakuletters

Читать полностью…

የሶላ ደብዳቤ እና ሌሎችም ... 💌

በህሊና ቋጥኝ
፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨

በህሊና ቋጥኝ ዘልቀው ሲራመዱ
ዳገቱን ለመግፋት ቁልቁል ከወረዱ
ሰማይ ደመና አዝሎ ተስፋን ካረገዘ
በኑሮ አንሳንሳር ላይ ብዙ ከተጓዘ
ሰው የለኝም ብለህ ፍለጋ አትውጣ
ከጠበከው ቦታ ራስህን ስታጣ
በምኞት ጉዞ ላይ ዙሪያህን ብቃኝም
ከአንተነትህ በላይ ሰውም አታገኝም !

ከሶላ

Читать полностью…

የሶላ ደብዳቤ እና ሌሎችም ... 💌

አታርቂያት ከቶ ❤️‍🔥

ከሶላ ✍
፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨


የአንቺ እንዳልሆን ሲፈርድ ሆነሽ ቀናተኛ
ባለፈው ያየዋት፣
በጣም ነው ምታምረው የልብሽ ጓደኛ
እያልኩ ስነግርሽ፣
አንቺን ያልኩ ይመስል መስታወት ታያለሽ
ቁንጅና ሳይኖርሽ እንዳለሽ እያሰብሽ

ይልቁንስ ቀንተሽ፣
ቆንጆ ጓደኛሽን
እንዳልወዳት ፈርተሽ አታርቂያት ከቶ
ገና ድሮ ድሮ
ስታስተዋውቂኝ ውበቷ ገዝቶኛል ልቤን አሸፍቶ



አታርቂያት ...
ከቶ አታርቂያት አንቺ ግን እንዳሻሽ
ትርጉሙ ሌላ ነው ነይ ብዬ ስቀጥርሽ

ትርጉሙ ይሄ ነው
በርግጥ
እንቺን እንኳን ቢሆን መጀመሪያ ማውቀው
እውነቱን ልንገርሽ
የምወደው እሷን ያልኩት ግን አንቺን ነው!

ትርጉሙ ይሄው ነው ሌላ እንዳይመስልሽ
ይልቅ ከወደድሽኝ
እሷን ቅጠሪልኝ ነይ ብዬ ስቀጥርሽ


ግና ግና ቀንተሽ፣
ቆንጆ ጓደኛሽን
እንዳልወዳት ፈርተሽ አታርቂያት ከቶ
ያኔ ድሮ ድሮ
ስታስተዋውቂኝ ውበቷ ገዝቶኛል ልቤን አሸፍቶ



@Kehiwotmahder
@Kehiwotmahder
@Kehiwotmahder

Читать полностью…

የሶላ ደብዳቤ እና ሌሎችም ... 💌

እመነኝ ስትይኝ

ከሶላ ✍

፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨

ድቡልቡል አይኖችሽ ከአይኔ ገጥመውኝ
እንደጠራ ኩሬ በጥዑም ልሳንሽ እመነኝ ስትይኝ
እወድሽ ጀመረ
ፍቅር ማለት ማመን ለልቤው እያልኩኝ



በሌላኛው እለት ሆነን በቀን ቅዱስ
በጥቅምቱ ንፋስ ተውበሽ በቀሚስ
ሳይሽ ውበትሽ አፍዞኝ
ከተክለቁመናሽ ትኩስ ፍቅር ይዞኝ
አንቺም የኔው ንዝረት ተሰምቶሽ መሰለኝ
በድንገት ስበሽኝ ከንፈሬን ስትሚኝ
ጠበበኝ ምድሪቷ
የወደድኳት አለም ኧረ የትአባቷ!

ግና ምን ይበጃል
ይሄ ሁሉ ስሜት ለአንቺ ቀልድ ኖሯል
መውደዴን ስነግርሽ ጠልተሽኝ ሞተሻል


ዳሩም አልጠፋኝም ሀገር ሙሉ ያውቃል
የሚያምንሽ ስታጪ እመነኝ ብለሻል
አላምንም እንዳልል ከንፈሬን ስመሻል
ዳሩም ግን አትሚኝ!
ውስጥሽ ቢነግርሽም ወደሽኝ እንዳጣሽ
እውነቱን ታውቂያለሽ
እንኳንስ ለልቤ ለህልሜም ሩቅ ነሽ


እስኪ ልጠይቅሽ ለራስሽ መልሽው
የሄደው ልብሽን በምን አስማቴ ነው ቀርቤ ምጎዳው?

እኔ አላውቅም ...


@Kehiwotmahder
@Kehiwotmahder
@Kehiwotmahder

Читать полностью…

የሶላ ደብዳቤ እና ሌሎችም ... 💌

ምስኪኗ የእናቴ መንታ ኢትዮጵያዬ 💔

#Ethiopian_Challenge

፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨


ውዲቷ ኢትዮጵያ

የመጣብሽ ማዕበል ፣
ስላነዋወጠሽ ፈፅመሽ አትፍሪ
በሞገድ መሀከል ፣
ድሮም ፈተና አለው እስክትሻገሪ 💚💛❤️


                    ከሶላ ✍


የክቡር ዶክተር ቴዎድሮስ ካሳሁን/ቴዲ አፍሮ/ ( አርማሽ [ቀናበል] ) ተጋበዙልኝ ❤️

ኢትዮጵያውነትን የሚገልፅ ፅሁፍ ያለው #Ethiopian_Challengeን ይቀላቀሉ👇

@sola1612

፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨
@Kehiwotmahder
@Kehiwotmahder
@Kehiwotmahder

Читать полностью…

የሶላ ደብዳቤ እና ሌሎችም ... 💌

አጋጥሞኝ ስለማያውቅ ነው እንጂ ሰው መርዳት < እፈልጋለሁ > አትበል ይልቅ የተቸገረውን እና አጣውት ያልከውን ሰው ካለበት < ፈልገህ > እርዳው


        
                           ከሶላ የቆየ ማህደር ✍

በምስሉ ላይ ያለችው ነጭ ነጥብ ትርጉም አላት! ምን ይሆን ግን ትርጉሙ...?


በቅርቡ በአዳዲስ ስራዎች ለመምጣት እሞክራለሁ እስከዛው ቻናሌን share በማድረግ አብረን እናሳድገው






     @Kehiwotmahder
     @Kehiwotmahder
     @Kehiwotmahder

Читать полностью…

የሶላ ደብዳቤ እና ሌሎችም ... 💌

ዓለም እና አንተ ! 💔

፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨

ዓለም ክብ ነች ፤ ሰው ደግሞ ተራማጅ ... በዓለም ክብነት ሳቢያ የሰው ልጅ ይሽከረከራል ወይንም የሰው ልጅ የመሄዱ እና የመምጣቱ ሂደት ዓለምን ያሽከረክራል ... እንግዲያ  ዓለም ጫፍ ከሌላት ሰው ደሞ መንገደኛ  ከሆነ ዛሬ ጥለነው የሄድነው ፣ የናቅነው ፣ በችግሩ የሳቅንበት ፣ በጉድለቱ የተጠቀምንበት ፣ የጣልነው ጥለነውንም እንዳይነሳ እጃችንን የነሳነው ላይ ቢጥለንስ ?  በትናንትናችን እንዳንቆጭ <<ነገ ላይ ትናንት በምትሆነው ዛሬ>> መልካሙን ሰርተን እንለፍ !

👉 Rewrite
                                           
ከሶላ


@Kehiwotmahder
@Kehiwotmahder
@Kehiwotmahder

Читать полностью…

የሶላ ደብዳቤ እና ሌሎችም ... 💌

<< ግራ እጄ እና ቀለበት ጣቷ... >>

ደራሲ ፦ ሶላ ✍

፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨
ዛሬ ደግሞ አርፍዳለች ... ካወኳት ጀምሮ እስከ ትናንት ድረስ የሚያረፍድ ሰው አልወድም ስትለኝ አልነበር ...ወይስ ለሷ ማርፈድ ማለት ቀድማ ስትገኝ ብቻ ነው ! ... መቅረት የሚሉት ነገር ስላለ በማርፈዷ አላማረርኩም... እኔን ያስጨነቀኝ ምን እንደምጋብዛት ነው ... አስተናጋጁ ያመጣልኝን አንድ ማኪያቶ ለ45 ደቂቃ ሳቆይ Takeaway እንዳልለው ፈርቶ ይሆን እጄን ልታጠብ ብዬ እንዳልሮጥ ብቻ አስተያየቱ ደስ አይልም ... አሁን የትኛው የአማኑኤል ታማሚ ነው ለማኪያቶ እጄን ታጥቤ ልምጣ የሚል ! ... አይኑ ስላስፈራኝ ልጋብዛት ያሰብኩትን ማኪያቶ እንዲደግመኝ አዘዝኩት ... ምን ሲቆላኝ ነው ላግኝህ ስትለኝ እሽ ያልኳት ?  አስተናጋጁ ያቀረበልኝን ልጎነጭ ጎንበስ ስል << የማያልፍለት ድሀ ሀብታም ይጋብዛል ! >> ብላ  በፈገግታ ዲዛይን በተሰራልኝ ማኪያቶ ላይ ስትስቅ ምስሏ ታየኝ ... ከፈገግታው ዲዛይን ስር የሚታየው ነጭ ወተት ጥርሷን ስለሚመስል ማኪያቶውን ሳይሆን እርሷን ያመጣልኝ መሰለኝ .

 
ሰዓታት አርፍዳ መጣች ... ላቅፋት ሁለት እጄን ስሰድ ቀኝ እጄን ጨብጣ የጉንጯን ከንፈር ከጉንጬ አሳሳመች ... የድርሻውን ስላጣ ግራ እጄ ቅር ቢለውም ሌላ ቀን እምደማስቀድመው ስነግረው ተረጋጋ ... እርሷ ግን መረጋጋት አልቻለችም  ... አስር ጊዜ ፀጉሯን ትፈትላለች ... ለአጭር ሰከንድ ታየኝ እና ለደቂቃ ግራ ጣቶቿን ታየዋለች ... አዲስ ጥፍር ቀለም ገዛች እንዴ እያልኩ አይኗን ተከትዬ ጣቷ ላይ ማፍጠጥ ጀመርኩ ... አዲስ ነገር አልታይ አለኝ ... አስተናጋጁ ሊታዘዛት ሊመጣ ሲል በእጇ ምልክት መለሰችው .... ቀለበት ጣቷን እየዳበሰች በድንገት ካፏ << ላገባ ነው >> የሚል ቃል አወጣች ... ጋብቻ የሞት ጥላ ስለሚመስለኝ ደነገጥኩ ... ጨርሼ ስላልሰማዋት ነው እጂ ስለ ጊልዶ ዘፈን ነው የምታወራው ብዬ ራሴን ላረጋጋ ሞከርኩ  ... ደገመችው << አልሰማከኝም ላገባ ነው እያልኩህ ነው ! >>
<< ሰምቼሻለሁ >>

<< እና ምን ይዘጋሀል >> ( ያገባችን መስሏት ልትጨቃጨቀኝ ነው እንዴ? )

<< ማንን እንደምታገቢ ግራ ቢገባኝ ነው >> ቀጠልኩና

<< ልጁ ግን ማነው ?>> አልኳት

<< አታውቀውም ! >>

<< ስለማላውቀውማ ነው የጠየኩሽ ! >> ስላት ፊቷን ወደ ካፌው በረንዳ ወርውራ አንድ ወጣት ጠቆመችኝ ... ጀርባውን አየሁት .... በልጅነታችን በጭቃ እንደምንሰራው ብይ የተድቦለቦለ 4በ4 የሆነ አጭር ነገር ነው ... በጣም ከማጠሩ የተነሳ እሷ ያደረገችውን ሂል ጫማ እንኳን ቢጫማ ወገቧ ላይ አይደርስም ... የኋላውን ገፅ ካየሁ በኋላ የፊተኛው ገፁን መገመት ጀመርኩ


ከኋላ በኩርኩም ቢባል የሚረግፍ ትልልቅ አይን ፣ እንደ እኔ ከችግር የሚሰፋ አገጭ ፣ የድሮ የቴሌቪዥን ጀርባ የሚመስል ቦርጭ ያለው ሆኖ ታየኝ ... ከሀሳቤ ስመለስ ማውራቷን አንዳላቆመች አስተዋልኩ .


<< ወጌን ሳላይ ፤ ሳላገባ እድሜዬ እኮ ሊሄድ ነው >>

<< ከዚህ በላይ >>  ብላት ታንቀኛለች  ...  መልስ አልሰጠዋትም ... ደግማም አልጠየቀችም .... ከካፌው ጫጫታ በዝምታ የምንተነፍሰው አየር ወደ ጆሮዬ ይወርዳል ... የትዝታዋን ካሴት መታ መታ አድርጌ ከፈትኩ ... ድንገት መናገሯ እንጂ ለማግባት መውሰኗ ስህተት መስሎ አልታየኝም ....


ሳቋ እና ስትስቅ የሚሰምጠው ጉንጫ ፤ ጨዋታዋ ፤ ቁም ነገሯ ፤  ደስ ይለኝ ነበር ... ዳሩ ግን ፍቅር ጋር  አይደርስም .

<< ዝም አልክ ምነው ?>> አለች ከንፈሯን ጣል አድርጋ

<< ይገርማል አንድ ምሽት የህይወታችንን አቅጣጫ ለወጠች ማለት ነው ?>> አልኳት

<< ይገርማል አይደል  ህይወት  ግራ ነች >> አለችኝ
በአንድ ምሽት ሀሳቧን ምን እንዳስቀረው መጠየቅ አልፈለኩም ፤  እንድትቀይርም አልጠብቅም

<< ይህቺ ምሽት ባትኖርስ በእኔ እና አንቺ መሀል ምን ይፈጠር ነበር ?>> አልኳት

<< አላውቅም ፤ ህይወት እና ነገ እኮ አይታወቁም !>> ብላ በመስኮቱ ማዶ አይኗን አሻግራ ተመለሰች ... አይኗን ታዘብኩ .



<< መቼም አይናችንን ጨፍነን የምናልመው እና ስንገልጥ የምኖረው ለየቅል ነው ... እኔ ገና አልነቃሁም ፤  አንቺ ግን ስለነቃሽ መኖር መጀመር አለብሽ >> አልኳት በውስጤ ... ቀና ብላ ስታየኝ ውስጤን የሰማችው መስሎኝ ፈገግ አልኩላት .



የእርሷንም የእኔንም እጆች አየሁ ... ቀኝ እጆቻችን ላይ የሰላምታችን አሸራዎች ተቀርፀዋል .... የተቀሩትን እጆቻችንን አስተዋኩ ፤ የኔ ግራ እጅ ለሰላምታ ይናፍቃል ... የሷ ቀለበት ጣት ግን አዲስ ደስታ ፤ ህይወት እና የነገን የተስፋ ይናፍቃል ... ህይወት ግራ አይደለች


<< የሱንስ አላውቅም ... አንቺ ግን ዛሬ  ያረፈድሽው የሰርጌ ቀን እስኪደርስ ልለማመድ ብለሽ ነው ?>> አልኳት ፤ ሶስታችንም አንድ ላይ ሳቅን ፤ አስተናጋጁ ግን ተኮሳትሮ እንዳየኝ ነበር .


    እኔም እንዳንተ አላዘንኩም ሄጄ ልበለው ?

፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨


#ስላነበባችሁት_ከልብ_አመሰግናለሁ


@Kehiwotmahder
@Kehiwotmahder
@Kehiwotmahder

Читать полностью…

የሶላ ደብዳቤ እና ሌሎችም ... 💌




<ና> ያለህ ሆይ ና

፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨

ሰው እና አለም እውነትን ስላወራህ ይጠሉሀል ፤ ውሸትን ስላወራህ ግን ይወዱሀል ... ህሊናህ ደግሞ እውነትን እጥብቃ ትወዳለች ፤ በአንፃሩ ደሞ ውሸትን አጥብቃ ትጠየፋለች ... ህሊና የምንለው የእውነት ሚዛን የአምላካችን ምሳሌ ነው . ታድያ ሰው ይወደዋል ከምንለው ውሸት እና ከአምላካችን ፍፁም መውደድ የቱ ይበልጣል ? ( ይህን ጥያቄ ለህሊናችን እንጠይቀው ) እናስተውል ሰው የሚወደን እነርሱን መስለን ስለምንዋሽ ነው አምላክ ግን የሚወደን ፍቅሩ እውነት ስለሆነ እና ስለሆነ ብቻ ነው .



ህሊና እውነትን የምትወድ የአምላክ አብነት ናት

ከሶላ ( ከከረመ ማህደሬ የተገኘ )


@Kehiwotmahder
@Kehiwotmahder
@Kehiwotmahder

Читать полностью…

የሶላ ደብዳቤ እና ሌሎችም ... 💌

አልልሽም ይቅር ! 🙅‍♂

ከሶላ ✍

፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨

እመጣለሁ ብላ እንደ ፀና ሀውልት አስቁማኝ ስትቀር
ድንገትም ከመጣች በስልኬ ደውላ ሌላውን ስትቀጥር
እንደልጅ እቃቃ መስልሆሽ ይሆን ፍቅር?

ይቅር .. ይቅር ይቅር <አልልሽም ይቅር!>
ቀድሞም በመምጣትሽ

.

የተረፈኝ የለም  ከሰላምታሽ በቀር 💔


@Kehiwotmahder
@Kehiwotmahder
@Kehiwotmahder

Читать полностью…

የሶላ ደብዳቤ እና ሌሎችም ... 💌

ኢትዮጲያዊት ሞናሊዛ ከሚለው ድርሰቴ ተቆርጦ የተወሰደ

ደራሲ እና አቅራቢ ፦ ሶላ ✍

@Kehiwotmahder
@Kehiwotmahder
@Kehiwotmahder

Читать полностью…

የሶላ ደብዳቤ እና ሌሎችም ... 💌

<< ኢትዮጵያዊት ሞናሊዛ >>

ድርሰት ፦ ሶላ ✍


🔴ማሳሰቢያ ፦ በመጀመሪያ ድርሰቱን እስከመጨረሻው ተከታተሉት ፤ ቀጥሎ ታሪኩን በምናባችሁ ሸራ ላይ ትስሉታላችሁ ፤ ከዛም በዳቪንቼ ምናባችሁ ሸራ ላይ የሳላችኋትን ሞናሊዛ በፅሁፍ @sola1612 ላይ አድርሱኝ እኔም በዚሁ ገፅ ለአንባብያን አደርስላችኋለሁ

እስከፍፃሜው መልካም ንባብ 😊

@Kehiwotmahder
@Kehiwotmahder
@Kehiwotmahder

Читать полностью…

የሶላ ደብዳቤ እና ሌሎችም ... 💌

አሜን

ከሶላ ✍

Background music ፦ Dawit tsege 👑

<< የጠዋት ውበትሽ ወፎችን ጠራቸው
ለእልፍ አእላፍ ኮከብ ጨረቃን ሆንሻቸው >>

@Kehiwotmahder
@Kehiwotmahder
@kehiwotmahder

Читать полностью…

የሶላ ደብዳቤ እና ሌሎችም ... 💌

ከግዑዙ ጨለማ በላይ አንተ ጨለማ አትሁን! 💔

ከሶላ ✍


@Kehiwotmahder
@Kehiwotmahder
@Kehiwotmahder

Читать полностью…

የሶላ ደብዳቤ እና ሌሎችም ... 💌

መራራ ግን ጣፋጭ እውነት #1 😤👉💙



ሰዎችን ስትወድ ለደስታህ ምክንያት ታገኛለህ ፤ ራስህን ስትወድ ግን ደስተኛ ትሆናለህ!


ነጠብጣብ ቀለም ፤ ያልተቋጩ ሀሳቦች ( ከሶላ )



@Ammelakuletters
@Ammelakuletters
@Ammelakuletters

Читать полностью…

የሶላ ደብዳቤ እና ሌሎችም ... 💌

ከህይወት ማህደር
ክፍል ገፅ-በገፅ ከሶላ ( @sola1612 )
It was pall lately...🙁
👂🚶 @Ammelakuletters

Читать полностью…

የሶላ ደብዳቤ እና ሌሎችም ... 💌

😁ቆንጆ ነኝ❤️
ከበላይ በቀለ ወያ👏 በሶላ🤠
...All of ma people's are beautiful...especially me😋.



👂👑 @Ammelakuletters

Читать полностью…

የሶላ ደብዳቤ እና ሌሎችም ... 💌

የሶላ ደብዳቤ የናፈቀው እስኪ 👍

( ላይኩ ከ25 ሲያልፍ እለቀዋለሁ )

Читать полностью…

የሶላ ደብዳቤ እና ሌሎችም ... 💌

ሰው ከአንድ እናት የተወለደው ወንድም ወይም እህቱን ምንም ቢበድሉ እና ቢከፉ የአንድ እናት ልጆች ነን ብሎ ይቅርታ ያደርጋል ፤ ከመውደድም አይሰንፍም! ከአንድ እናት ላልተወለዱት የፍጥረታት ሁሉ አባት እና እናት ከሆነው ጌታ የተገኙት እና የአንድ አምላክ ልጆች የሆኑት ወንድም ወይም እህቱ ግን ቢበድሉት ይጠላቸዋል ቢያስከፉትም ለመጥላት ከቶ አይዘገይም!

ከሶላ ✍



@Kehiwotmahder
@Kehiwotmahder
@Kehiwotmahder

Читать полностью…

የሶላ ደብዳቤ እና ሌሎችም ... 💌

ወደፊት አብረን በምናሳልፋቸው የፍቅር ቀናቶች ውስጥ ከቶ አልጎዳሽም ብዬ ቃል አልገባልሽም ነገር ግን እመኚኝ ልጎዳሽ አልመጣሁም !

የሶላ ደብዳቤ ✍

( ሰሞኑን በአንድ ግጥም እመጣለሁ )

Share & Add ማድረግ ተረስቷል👇👇👇

@Kehiwotmahder
@Kehiwotmahder
@Kehiwotmahder

Читать полностью…

የሶላ ደብዳቤ እና ሌሎችም ... 💌

አጋጥሞኝ ስለማያውቅ ነው እንጂ ሰው መርዳት < እፈልጋለሁ > አትበል ይልቅ የተቸገረውን እና አጣውት ያልከውን ሰው ካለበት < ፈልገህ > እርዳው


        
                           ከሶላ የቆየ ማህደር ✍




በቅርቡ በአዳዲስ ስራዎች ለመምጣት እሞክራለሁ እስከዛው ቻናሌን share በማድረግ አብረን እናሳድገው






     @Kehiwotmahder
     @Kehiwotmahder
     @Kehiwotmahder

Читать полностью…

የሶላ ደብዳቤ እና ሌሎችም ... 💌

ሰው ምንም ቢበድልህ ፣ ቢያስከፋህ ፣ ቢጠላህ በአፈጣጠሩ ብቻ ውደደው! ምክንያቱም ሰውን የአምላኩ አምሳል እና እንዳ'ንተ ድንቅ ፍጡር ስለሆነ ብቻ ልትወደው እንጂ ከተፈጠረ በኋላ ያደረገውን መጥፎ ተግባር እያነሳህ ልትጠላው የተገባ አይደለምና!

፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨

ሰውን ስትወድ አምላክህ ይቀርብሀል ፤ ሰውን ስትጠላ ከአምላክህ ትርቃለህ!

                                              ከሶላ ✍

@Kehiwotmahder
@Kehiwotmahder
@Kehiwotmahder

Читать полностью…

የሶላ ደብዳቤ እና ሌሎችም ... 💌

በነገው አሀዱ 2014 << ግራ እጄ እና ቀለበት ጣቷ >> ከሚለው ድርሰቴ ጋር ቀጠሮ ይያዙ

@Kehiwotmahder
@Kehiwotmahder
@Kehiwotmahder

Читать полностью…

የሶላ ደብዳቤ እና ሌሎችም ... 💌

ህሊና 🤯

ከሶላ ✍

" የሰው ልጅ በሙሉ እኩል ያለው ነገር ቢኖር ሕሊና ነው!... እንጠቀምበት!!! "
.
@Ammelakuletters
@Ammelakuletters
@Ammelakuletters

Читать полностью…

የሶላ ደብዳቤ እና ሌሎችም ... 💌

     << ኢትዮጵያዊት ሞናሊዛ >>

         ክፍል ~ ፪ ( የመጨረሻው ክፍል )

  ደራሲ ፦ ሶላ ✍

፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨

አውደርዕዩን የታደሙት ሰዓሊውን ተከትለው ሲሄዱ እኔ አንድ ስዕል ላይ አፍጥጬ ቀረሁ ... በአውደዕርዩ በአካል ካየዋቸው እንዳንድ ቆንጆዎች ሁሉ ይህ ስዕል በእጅጉን ያምር ነበር .


በአረንጓዴ ቢጫ ቀይ በተሞሸረ ጥልፍ ሀበሻ ቀሚስ የተዋበች ከአንድ ሀይቅ ዳር እግሯን የምትታጠብ የቀይ ዳማ መልክ ያላት ኢትዮጵያዊ ልጃገረድ አየሁ ...
የደም ግባቷ ወዝ እንደጥላ በሀይቁ ላይ ያንፀባርቃል ... በሙሴ በትር የተከፈለ ይመስል የፀጉሯ አከፋፈል ያምራል ... በእጇ እየጨለፈች ቀኝ እግሯን ስታለብሰው የሚታየው ውሀ በሀይቁ ላይ ከሚንሸራሸረው ውሀ በእጅጉን ይነጣል ... ሎሚ ተረከዟን የተጫማው ጎማ ጫማዋ ሌላ እንይጫማበት ከጎኗ ሆኖ የእግሯን ታጥቦ መመለስ ይጠባበቃል  ...  የአንገቷ መስቀል ማህተም እና የግምባር ንቅሳቷ ለአምላኳ ሰርክ እንደምትታመን ያመሳክራሉ ... ከሀይቁ ፣ ከዛፉ ፣ ከሰማዩ ጋር ተጣምራ ሌላ አዲስ ተፈጥሮ ትመስላለች ... ውበቷን ላየ የእግዜር  ድንቅ ፍጡር ማለቱ የማይቀር ነው ... ወደድኳት ፤ የማውቃት ያህል ተሰማኝ ፤ የወፍራም ፍቅር ውልብታ መታኝ .  




ፊቷን ፣ እጇን ፣ ፀጉሯን ዳብሼው የማውቅ ፣ በትንፋሿ የተነፈስኩ ፤ በእግሯ የተራመድኩ ፣ በአይኗ ያየሁ ፣ በምላሷ የቀመስኩ ፣ በአካሏ አካል የሆንኩ ፣የልቧን ትርታ በጆሮዎቼ ያደመጥኩ ያህል ተሰማኝ ... ስዕሏን ከአይኔ አልፌ በልቤ ማየት ጀመርኩ ... ተመኘው ፤ ምናለ ጥበብ ድርብ ችሎታ ሰጥታኝ ወበቷን በሸራው ላይ እኔ ብቻ ባስቀመጥኩኝ ... ምናለ ልቤስ ላይ ብትቀመጥ ፤ ለዚህች << ኢትዮጵያዊት ሞናሊዛ >> ዳቪንቼን ብሆናት ምን አለበት ? ስትስቅም ስታለቅስ እንደምትማር ከልቤ በሚመጣው መልኳ ኢትዮጵያዊ ሞናሊዛዬን ብስል ምን ነበር ? ምናለ ጥበብ አገናኝታ ብታጣምረን ፤ እኔ በምኖርበት ዓለም ትኖር ይሆን ወይስ እኔ ካለፍኩ በኋላ ትፈጠራለች ? ይሄኔ እኮ ስንቴ ተላልፈናል ... ታክሲ ውስጥ ፣ መንገድ ላይ ፣ የስራ ማስታወቂያ ላይ ፣ ብቻ አንድ ቦታ ተላልፈን ይሆናል ማን ያውቃል ? ግን ም .. ና .. ለ ብዬ ሳልጨርስ << ሰላም ነው ?>> የሚል ድምፅ ጎተተኝ ፤ ሰዓሊው ነበር .

<< እ ህ ህ ሰላም ነው >> አልኩት ታዳሚው በሙሉ ወጥተው እንዳለቁ ለማስተዋል እየጣርኩ

<< ከቅድም ጀምሮ እያስተዋልኩህ ነበር ስዕሉን ወደከው ነው ?>>

<< አዎ ወድጃታለው ማለቴ ታምራለች ታውቃታለህ ?>>

<< አልገባኝም ? >> አለኝ

ትኩረቴን ከኢትዮጵያዊቷ ሞናሊዛ ሳልነቅል << እኔም አልገባኝም... >> አልኩት

<< ስለምኑ ነው የምታወራው ? >>

<< ስለርሷ >>

<< OK ስለሳልኳት ልጅ ነው የምትለው? >> አለኝ

<< አይደለም ተስለህ ስለሳልካት ልጃገረድ >> አልኩት

<< እርሷስ አትገባህም ...>>

<< ለምንድነው የማታገባኝ ? >>

በግርምት ሳቀና << ማለቴ የወንድሜ ሚስት ነች >>

<< ብትሆንስ >> ብዬው

ድንገት ባነንኩና << ምን አልከኝ ?>> አልኩት

<< የወንድሜ ሚስት ነች ነው ያልኩህ  የስዕሌን ሀሳብ ስለምትመስል ነው የተጠቀምኳት >> አለኝ
ሰዓሊው ድሬድ ያልሆነ ፀጉሩ የገባ ትዑት ቢጤ ይመስላል ...


የሰው እንደሆነች ብሰማም ውበቷ አንደታየኝ ነው ፤ ለሷ ብቻ የተከፈተው የአይኔ ልዩ ክፍል ማየቱን ፤ አይቶም ማድነቁን አላቆመም ነበር .




<< እና ከርሷ ስር ማለቴ ከስዕሉ ስር ተይዟል አይባልም ?>> አልኩት ... አሁን እንዲ ማን ያስባል ¡ ...
እንዲመልስልኝ ጊዜ ልሰጠው አልፈለኩም ... ተስፋዬን ስለሰበረው ስለ ስዕሉ አስተያየት ሳይጠይቀኝ  << ምንም አትልም ! ማለቴ የስዕል ችሎታህም እርሷም ... ወደፊት ግን አሻሽል  እሺ >> ብዬ አንድ እርምጃ ተራምጄ ቀልቤን የሰወረችው ይህች ኢትዮጵያዊት ሞናሊዛ በሌላ ዳቪንቼ ልብ ውስጥ እንደሆነች ትዝ ሲለኝ መለስ አልኩና << ለርሷም እንድታሻሽል ንገራት >> አልኩት ጨከን ብዬ .

<< ምኑን? >> አለ

<< ፊቷን >>

የርሷ ለመሆን ባልታደለው ውስጤ << አንቺ ባልሽ ላይ ስትደርቢ ትንሽ አታፍሪም ! በይ ከልቤ ሹልክ ብለሽ ውጪ >> ብዬ ከማዕከሉ ተሰወርኩ .



አንዳንዴ ውበት እና መውደድ ይምታታብናል ልበል ? ... መጀመሪያ ማየት የምንችለው ውጫዊውን ስለሆነ ልክ ውበትን እንዳየን በፍጥነት ወደድን እንላለን ... በርግጥ ውስጣዊውን ማየት እንችልም ማመን እንጂ ...  እውነተኛ የመውደድን ጣዕም ከልብ እየቀመስን ስንመጣ ደግሞ ይሄማ ውበት ነው እንላለን .




<< መባቻህን እንድታይ እግሮችህን አክንፍ ፤ በመጓዝ ስላለ በመሄድ ተንሳፈፍ >> ነበር አይደል አይምሮዬ ያለኝ ፤ እንዲህ ለማለት ፈልጎ ይሆን ?



መሬት አየረገጥክ በመሄድህ ብቻ ፣
አይገኝም ስፍራ የሚሆን መባቻ
ይልቅ መንታ እግርህን አስበህ አስነሳ ፣
ደርሶ እንዳይሆንክ መድረሻህ አበሳ !




ይህች << ኢትዮጵያዊት >> በእውነትም ነበረች ፤ እርሷን ባይሆንም ውበቷን ወድጄዋለሁ ፤ እነሆ ውበቷም በልቤ ህያው ሸራ ላይ ተስሎ ይገኛል .

፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨

ስላነነቡት እናመሰግናለን ፤ በቅርቡ << ግራ እጄ እና ቀለበት ጣቷ >> በሚለው ድርሰቴ እንገናኛለን


@Kehiwotmahder
@Kehiwotmahder
@Kehiwotmahder

Читать полностью…

የሶላ ደብዳቤ እና ሌሎችም ... 💌

<< ኢትዮጵያዊት ሞናሊዛ >>

ደራሲ፦ ሶላ
፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨

እንደተለመደው የምሄድበት የለም ... ብዙ ጊዜ ሄጄ የምደርስበት ነገር ስሌለ መጓዝ አልጀምርም ! ... ዛሬ ግን << መባቻህን እንድታይ እግሮችህን አክንፍ ፤ በመጓዝ ስላለ በመሄድ ተንሳፈፍ >>  የግጥም መድብል አይምሮዬ ሰዉም ይመስል መሄድ አሰኝቶኛል ... ትርምሱ ይረብሻል ... መኪናውም ሰዉም ተጨናንቋል ... በዚህ ጭንቅንቅ  ለስራ የታደለው ሰራተኛ በታክሲ ፣ አለቃው ደግሞ በመኪናው ሆኖ በመስኮት እየተፋጠጡ ቢሮ እኩል እንደሚደርሱ አልጠራጠርም .... የምበላው የሌለኝ ጊዜ ቶሎ ቶሎ ይርበኛል ... ዛሬ ደሞ ትንሽ ከመሄዴ ደክሞኛል ... መዳረሻ ስለሌለኝ ይሆናል  ... እግሬን ከትርምሱ ገታ አድርጌ ፊት ለፊት ወደታየኝ የስእል አወደርዕይ ማዕከል አመራሁ .




ስዕል ባልችልም የተሳለን ግን ፎቶ ማንሳት እችላለሁ ... ያለፈን ነገር ማንሳት እንጂ ፎቶ ማንሳት በጣም እወዳለሁ ... በተለይ ተፈጥሮን ... ጠዋት ጠዋት ከተራራው አናት ብቅ የምትል እና ሊመሻሽ ሲል በአድማስ የምትጠልቅን ፀሀይ ፣ ጨረቃ የምትሸምነውን ክዋክብት ፣ ንቦች የሚስሟትን ፅጌሬዳ ፣ አንዳንዴንም ቆነጃጅንት ሴቶችን ማንሳት ደስ ይለኛል ...  ስልክ ከሚሉት ነገር ሁሉ  ሰልፊ ካሜራን አልወድም !



ሰአሊው ከፊት ሆኖ ስለሳላቸው ስዕል ማብራሪያ ሲሰጥ እኔ ደግሞ በሜካፕ ተስለው የታደሙትን የእስቶችን ምስል ማብራሪያ ለራሴ እሰጣለሁ ... ለፊታቸው ሜክአፕ 10,000 ቢያወጡ ፣ ለፀጉራቸው ሂውማንሄር 15,000 ቢያወጡ 25,000 ብርርርርር ይሆናል ...  ጉድ ነው ዘንድሮ !  ታድያ << ተፈጥሮ ላልሰጠቻቸው ነገር ይሄን ሁላ ካወጡ ተፈጥሮ ለሰጠቻቸው ነገር ምን ያህል ያወጣሉ ?>>  .... የራሴን ሀሳብ ስዕል ስጨርስ የሰዓሊውን ስዕል መቃኘት ጀመርኩ ... አንዳንዶቹ አብስትራክት ስዕሎች ህይወቴን ሲመስሉ የተቀረው ደግሞ የማይፈታውን ፊቴን ይመስል ውስብስብ ያለ ነው ... አውደርዕዩን የታደሙት ሰዓሊውን ተከትለው ሲሄዱ እኔ አንድ ስዕል ላይ አፍጥጬ ቀረሁ ... በአውደዕርዩ በአካል ካየዋቸው እንዳንድ ቆንጆዎች ሁሉ ይህ ስዕል በእጅጉን ያምር ነበር .

ይቀጥል?ላል ...


@Kehiwotmahder
@Kehiwotmahder
@Kehiwotmahder

Читать полностью…

የሶላ ደብዳቤ እና ሌሎችም ... 💌

<< ኢትዮጵያዊት ሞናሊዛ >>

ድርሰት ፦ ሶላ 👉 😃

ነገ ምሽት ይጠብቁን 🙏

@Kehiwotmahder
💚 ❤️
@Kehiwotmahder
💛 💛
@Kehiwotmahder
❤️ 💚

Читать полностью…

የሶላ ደብዳቤ እና ሌሎችም ... 💌

ጃኬቴ 🤔

ከሶላ ✍

እንደቢራቢሮ ( ቴዲ አፍሮ 👑 )

@Kehiwotmahder
@kehiwotmahder
@Kehiwotmahder

Читать полностью…

የሶላ ደብዳቤ እና ሌሎችም ... 💌

<< ነፍስ በምን ትከብራለች ?>>

፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨

እግዚአብሔር እኛን ከሁለት ነገር ዋጀን .... ከአፈር እና እፍ ብሎ ከሰራን ትንፋሹ ... እፍ ብሎ የሰራት ነፍሳችን ከህያው ትንፋሹ ስለሰራት ሞት አይረታትም .... ስጋችንን ደግሞ ከፈጠረው አለም ተውሶ ስለሰራት ከምድር አታልፍም ፤ ትሞታለች ... ታድያ አምላክ ከፈጠረው አለም አፈርን ተውሶ የሰራት ስጋችን ወደ አፈር ተመልሳ በዚሁ ምድር የምትቀር ከሆነች ስለምን ጥላቻ እንሰንቃለን ? ስለምን ሀብትን እናስበልጣለን ? እስከመቼስ ይዘን ለማንሄደው ነገር እንደክማለን ?
የፈጠረን እንዲሁ ስላከበረን ከከበረ ትንፋሹ የከበረ ነፍስ እንደሰጠን ካወቅን የፈጠረንን ለምን አናከብር ? ትዕዛዙንስ ለምን አንጠብቅ? በትንፋሹ የዋጃትን ነፍስ ለምን አናከብር ? << ነፍስ በምን ትከብራለች ?>>

<< በክርስቶስ ፍቅር። >> ፍቅር እግዚአብሔር ነውና


ከሶላ ማህደር ✍


@Kehiwotmahder
@kehiwotmahder
@Kehiwotmahder

Читать полностью…
Subscribe to a channel