kehiwotmahder | Unsorted

Telegram-канал kehiwotmahder - የሶላ ደብዳቤ እና ሌሎችም ... 💌

-

የጥበብ ዋርካ ወደሆነው ገፃችን እንኳን በደህና መጣችሁ🤗 እባክዎን በዚህ የገፅ ዋርካችን አረፍ ይበሉ አረፍ ብለው በጥሩ አቀራረብ አዋዝተን የምናቀርበውን ግጥሞች ፤ ድርሰቶች ፤ ደብዳቤዎችን ያድምጡ ። በፔጃችን ፍቅርን በጥበብ ቋንቋ እንሰብካለን << ጥበብ የፍቅር መግለጫ ነው ፤ ፍቅር ደግሞ የጥበብ መገለጫ ነው >> #ጦጵያ #ቶጵያ 👇 #ዕድል_ፈንታዬ_ኢትዮጵያ_ሁኚልኝ_ሳሌም 💚💛❤

Subscribe to a channel

የሶላ ደብዳቤ እና ሌሎችም ... 💌

እድል እና መልስ እንደሚሹ ልቦች እና እድል ነፍገው ጥያቄውን እንዳላደመጡ ልቦች የሚያሳዝን ምን ይኖር ?

ውዴ
ላንቺም ለኔም ላይበጅ ረፍዶ ከማዘን
እድል ስጭኝ እና ልንገርሽ የውስጤን


ፅፌ ካልሰደድኩት መሀል
ከሶላ ✍🏾

Читать полностью…

የሶላ ደብዳቤ እና ሌሎችም ... 💌

ብትሄጂ ያለአንቺ ልኖር ብገደድም እንኳን አማራጭ የለኝምና እቀበላለሁ

ቢሆንም ግን አትሂጂ


ከመራቅሽ በላይ በትዝታ መኖርን እፈራለሁና


ያለተቋጩ ሀሳቦች
ከሶላ ✍🏾

Читать полностью…

የሶላ ደብዳቤ እና ሌሎችም ... 💌

ሕይወት ግራ መኖር ሽንቁር
ፍላጎቷን ልሳን የላት አትናገር!

ላትናገር...
እኔም ተውኩኝ መልሷን ልሻ
በዝምታ ማለፍ ብቻ የኔ ድርሻ


ገጣሚ ፦ ሶላ ✍🏾

Читать полностью…

የሶላ ደብዳቤ እና ሌሎችም ... 💌

Inspired by Rami 💁‍♀

፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨

እንደኔ ያለ ሰው
ከ12ቱ ወራት
ለድካም ከማትሆን ከ52 እሁዳት ከአመት እለታት
ቀኑን ዘሎ ዘሎ አንዷን ነው ሚቆጥራት


ውዴ
የሌላውን ባላውቅም
ስፍራዋን ሳትስት በምስራቅ እያለች
እፍኝ ለአይኖቼ ፀዳል ከሰወረች ከፀሀይ ወጋገን
እውነት እልሻለሁ
ለኔ ላንዱ ምስኪን  ሻማሽ ነው ብርሀን
ሌላውን ባላውቅም
የእውነትን ሻማ
ውሸት በንፋሷ ሽው አርጋ ስቀማ
እሰይ በሚል አለም በበዛበት ሌባ
እውነት እልሻለሁ
ለታረዘው ልቤ ልደትሽ ነው ካባ

እውነት እልሻለሁ

ደምድሜ ባላውቅም
ውሸት ላሳወረን ለኛ ግብዝ አለም


ከልደትሽ ውጭ የእውነት ቀን የለንም

ከልደትሽ ውጭ ሌላ ቀን የለንም


ሶላ ✍🏾


@Ammelakuletters
@Ammelakuletters
@Kehiwotmahder

Читать полностью…

የሶላ ደብዳቤ እና ሌሎችም ... 💌

እንኳን ላንቺ ቀርቶ
መሰናበቻዬን ለማላውቀው ለቀን
.
.
የምጨነቅበት የለኝም ሰቀቀን



ከሶላ


@Ammelakuletters
@Ammelakuletters
@Ammelakuletters

Читать полностью…

የሶላ ደብዳቤ እና ሌሎችም ... 💌

Viral ግጥም ( don't try to laugh)


የኔ የከንፈር ጣዕም ተወዳጅ ቀይ ሎጋ
እኔ 'ወድሻለሁ እንደ አ**ስጋ

ባይሽ የማልጠግብሽ የውበት ቀለሜ
እሳሳልሻለሁ እንደአርቲስቶች እድሜ

ብቻ አንቺ ከመጣሽ ካላልሽኝ ለመቼ
ለቲክታክ አላንስም
አግቢኝ እልሻለሁ ዱቄት ተቀብቼ

ከሶላ


@Ammelakuletters
@Ammelakuletters
@Ammelakuletters

Читать полностью…

የሶላ ደብዳቤ እና ሌሎችም ... 💌

<<መልካም አዲስ አመት እንዲሆን አልመኝም!>>


ድርሰት ፦ ከሶላ



በተፈጥሮዬ አዲስ ነገር እወዳለሁ ... አዲስ ስፍራ፣አዲስ እውቀት፣አዲስ ምግብ ቤት.. እንዲሁም ዛሬን! ምክንያቱም ዛሬ ትናንት ያልነበረች ነገም የማትደገም ብቸኛ እና አዲስ ስለሆነች .... አዲስ ሰውም መተዋወቅ እወዳለሁ።  በተለይ እንዳንቺ ቆንጆ የሆነች ሴት! በርግጥ በስራዬ እና በውሎዬ ዙሪያ ብዙ ቆንጆዎች ብትዋወቅም ቆ-ንጆ-ሪ(ቆንጆ እና እንጆሪ) የሆነች  ጎረቤት ሲኖረኝ ግን የመጀመሪያዬ ነው።  ስለአንቺ ባሰባሰብኩት ጥናታዊ መረጃ አዲስ ተከራይ ነሽ ።
ከማላውቀው ባህሪሽ በስተቀር ለኔ አዲስ በመሆንሽ ብቻ እንድወድሽ እገደዳለሁኝ !ግን ምን አይነት መውደድ .... ?

  የዘመኑ ሳይንስ እንደሚለው የአንድ ሰው የፊት ገፅ በአለም ላይ 9 ጊዜ ተደጋግሞ ይገኛል ይላል ... የእኛ አምላክ ፈጣሪ ግን ሁሉን በጊዜው ፈጥሮ ጨረሰ እንጂ የሚፈጥረው የሚያልቅበት አምላክ አይደለም .... በቅርበት የማውቃቸው አንዳንድ የሰፈሬ ልጆች ስለውበትሽ ስነግራቸው ቁንጅናሽን ለማጣጣል << ምን ታካብዳለህ የሷ አይነት 9 አሉ >> ቢሉኝም  ለኔ ግን የሚፈጥረው በማያልቅበት እጅ የተሰራስሽ አምሳያ የሌለሽ ብቸኛ ቆንጆ ነሽ።  በርግጥ ነፍስ እና ስጋ ባይኖረውም አንቺን ሊመስል የሚችል አንድ አለ እርሱም በመስታወት የምታዪው የራስሽ ውብ ምስል ነው! 


እርሜን በምወደው ዛሬ ባይሽ ወደድኩሽ ! እርሙን ዛሬ ቁንጅናሽን ቢመለከት ፤ ጎረፈ ይሄ ሁሉ አዲስ ስሜት ....

ውድዬ ... አምላክ አንቺን ይስጠኝ ብዬ እምላለሁ ከዚህ በፊት የመውደዴን አይነት ባላውቀውም ይህ አይነት መውደድ ግን ለኔ እንግዳ ነው

ግን.... ስለአንቺ ብዙ እንዳስብ  ብዙ እንዳሰላስል ያደረገኝ በአይምሮዬ የሚመላለስ  አንድ ጥያቄ አለ ...  አስከአሁን ከአሁንም እስከዚህች ቅፅበት ደረስ  አዲስ ሰውን መተዋወቅ የምወድ እንደሆንኩ  ባውቅም አንቺን ግን  ሳልተዋወቅሽ ለምን  ወደድኩሽ 


ዛሬን ልኬት በማይገኝለት  መልኩ ወደድኩሽ እሺ ነገስ እንዴት ልሆን ነው? ከነገወድያስ? ስተዋወቅሽስ? ተጋብተን ልጆች ስንወልድስ???


መልካም አዲስ አመት እንዲሆን አልመኝም ቀርቤሽ ሁሌ እንደአዲስ የምወድሽ እንድትሆኚ እመኛለሁኝ እንጂ !



ስላነበቡት እግዚአብሔር ያክብርልኝ
ተፃፈ በሶላ መስከረም 1 2016


@Ammelakuletters
@Ammelakuletters
@Ammelakuletters

Читать полностью…

የሶላ ደብዳቤ እና ሌሎችም ... 💌

( ክፉ ሰው ቶሎ አይሞትም ጥሩ ጥሩው እንጂ ለሚለው አባባል ምን አልባት መልስ ከሆነ ብዬ የፃፍኩት ነው። << ሰው ከነኃጥያቱ እና ከነክፋቱ የሚወደው አምላክ ያለው እድለኛ ፍጡር ነው ... >> )

፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨

እግዜሩ ድንቅ ነው
የክፉውን ዕድሜ ረጅም ያደርጋል
ለምስኪኑ ደግሞ ጥቂት ኑሮ ይሰጣል

እንዴት ?

የየዋውን ነፍሲት
አምላክ አሳጥሮ በቶሎ የሚያስቀብር
ህያው እንዲኖር ነው በሰማዩ መንበር
በአንፃሩ ጌታ የከፋው ፍጡሩን ያስኖረው በመቶ
እንዲድን ሽቶ ነው በንሰሀው ጠርቶ


ከሶላ ✍

@kehiwotmahder
@kehiwotmahder
@kehiwotmahder

Читать полностью…

የሶላ ደብዳቤ እና ሌሎችም ... 💌

ከደብዳቤዎቼ ቅንጭብጭብ ፦ ፩


~ ልክ የጥቅምት ነፋስ እነደነካው የእህል ዘር  ፀጉርሽ መለስ ቀለስ እያለ ሲወዛወዝ ሳይ ከአይኔም አልፎ ሀሳቤ እና ቀልቤ ወዲህ እና ወዲያ ይንከራተታሉ



~ ከረጅም ጊዜ በኋላ የምትወደው ሰው መጥቶ ያሳለፍነውን ሁሉ እንዳልተፈጠረ አድርገህ አስበው ሲልህ ባዶ ህይወት ይከብሀል ። በርግጥ ይህን ስሜት ከዚህ በፊት የማውቀው ቢሆንም በርሷ ሳየው እንደአዲስ ሆኖ ለምን እንደሚሰማኝ አላውቅም!


~ የተደሰትንበትን ዕለቶች አልረሳቸውም ፤ ካንቺ ያተረፍኩት ቀሪ ትዝታዎቼ ናቸው!


~ ፍቅርሽን ካጀበው ውቅያኖስ በላይ ዙሪያዬን የከበቡኝን ኮከቦች በሀሳብ መስኮት አሻግሬ እያየሁ ካንቺ ሰገነት ያደርሱኝ ዘንድ እማፀናቸዋለሁ


~ አልተሻለኝም!መጥተሽ በነበረ ጊዜ ህመሜን ብረሳም መድሀኒቴን ግን አላገኘውም




... ይቀጥል?ላል .... ❤️



@Ammelakuletters
@Ammelakuletters
@Kehiwotmahder
@Kehiwotmahder

Читать полностью…

የሶላ ደብዳቤ እና ሌሎችም ... 💌

One of my fav letter's 👏👆👇

Читать полностью…

የሶላ ደብዳቤ እና ሌሎችም ... 💌

One of my fav poem 😘👆

Читать полностью…

የሶላ ደብዳቤ እና ሌሎችም ... 💌

(Inspired by sofi's poem)


ደሳሳ ደርባባ የሰናፍጭ ቤቴን ፣ ሊነሱኝ ከያዙ
ከጣራዬ ብሶች ፣
ከቀዳዳው በላይ አፍራሾች ከበዙ

በቤቱ ያሰበኝ ፣ የዘለዓለም አምላክ
የበለጠ ሊሰጥ ፣ በማይዘልቀው ቤቴ ፈተና ከላከ

የኢዮብን ትዕግስት ፣ 'ስክማረው ድረስ ወይኩን ፍቃድከ !


እንዲህ ነው የምለው
.
.
.
አሜን ነው የማውቀው ።

.... ከሶላ 🫡


@Ammelakuletters
@Ammelakuletters
@Ammelakuletters

Читать полностью…

የሶላ ደብዳቤ እና ሌሎችም ... 💌

ምርጥ ለቤትዎ እና ለኩሽናዎ ምቾት እና ውበት የሆኑትን የKENWOOD & ሌሎች የአውሮፓ ሀገር ምርቶችን ከእኛ ለእናንተ ከእቃዎቻችን በጥቂቱ👇

፨hand mixer
፨food processer
፨meat grinder
፨mini chopper for our kids
፨Blend classic(glass blender)
፨Multi fry pressure cooker


አቅሞን ያገናዘበ ስለሆነ ያነጋግሩን

የቴሌግራም ገፃችንን ይጎብኙ👇
/channel/kegnalenante

ስልክ፡ 0973412834

Читать полностью…

የሶላ ደብዳቤ እና ሌሎችም ... 💌

ከሶፊ እና ከሶላ 😱

፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨

አምጡልኝ ብዕሬን፥ሕመሜን ልከትብ
በቃላት ነጠብጣብ
ተስፋዬን ልቀጥል በፈጠርኩት ምናብ...

ግና ግን እናንተ
ለበሽታው ሰሪ ታለ ጤና አዳም
አትበሉት ግዴለም
ዘመናት ቢቆጠር ቢዳሰስ ዘለአለም
መድሀኒት ለአለም
ከፈጣሪ እንጂ ከፍጡር አይደለም!


Re-edit

@Kehiwotmahder
@Kehiwotmahder
@Kehiwotmahder

Читать полностью…

የሶላ ደብዳቤ እና ሌሎችም ... 💌

For those who are searching their happiness


ለራስህን የምትሻውን ደስታ የምታገኘው ባለህበት ስፍራ እንጂ ለመሆን በምትፈልግበት ቦታ አይደለም

ከሶላ ( #street_note's )


@Ammelakuletters
@Ammelakuletters
@Ammelakuletters

Читать полностью…

የሶላ ደብዳቤ እና ሌሎችም ... 💌

አንዳንድ ትዝታዎች ዘልአለማዊ ናቸው 🖤

Читать полностью…

የሶላ ደብዳቤ እና ሌሎችም ... 💌

I found this 🙏🏾 in sofoniyas nebiyu ig story

Читать полностью…

የሶላ ደብዳቤ እና ሌሎችም ... 💌

እኔ ፦ እንግዳ ስሜት ተሰምቶሽ ያውቃል...?


እሷ ፦ ሁሉም ስሜት መጀመሪያ እንግዳ ነው ❤️‍🩹


@Ammelakuletters
@Kehiwotmahder

Читать полностью…

የሶላ ደብዳቤ እና ሌሎችም ... 💌

<< በህይወቴ ትልቅ የተማርኩበት ሰው መደገፊያ ሊሆን አይችልም በተለይ እግዚአብሔርን ለቀህ ሲሆን >>
                        


       ወጣት ቤዛዊት ጥላሁን  (በዶንኪ ቲዩብ የ"አንድ ሰው ህይወት" ፕሮግራም ላይ ቀርባ የተናገረችው አንገቴን ያስደፋ እወነት )

Читать полностью…

የሶላ ደብዳቤ እና ሌሎችም ... 💌

ልትሄጂ በወሰንሽበት በመጨረሻው መጀመሪያ ቀን ...
.....
ስትሄጂም አንቺን ሳስብ ምንአልባት የማዝን እንጂ ህይወቴን ሙሉ አንቺን የማስብ እና የማዝን የመሰለሽ ቀን ....
.....
የራስሽን ብርሀን ስትወስጂ ብርሀኔ እንዳንቺ የሚደበዝዝ እንጂ የሚጠፋ የመሰለሽ ቀን....
.....
በራቅሽኝ መጠን ልክ የምርቀው ከአንቺ እንጂ ከራሴ እንዳልሆነ ያልገባሽ ቀን ...
......
መሄድሽ ለኔ ስጠብቀው የነበረ የምስራች እንጂ መርዶ እንዳልሆነ የዘነጋሽ ቀን....


ያን ቀን ሂጂ ሂ ...


እኔም ከማይጠቅሙኝ ሁሉ አድነኝ የሚለውን የዘውትር ፀሎቴ እንደተሰማ ልነግርሽ ባልኩት ቀን .... ለካ




ም!!!

                                                           
                        
                                                           
     ያልተቋጩ ሀሳቦች
ከሶላ ✍🏾


@Ammelakuletters
@Ammelakuletters
@Ammelakuletters                                                     
                                                            
                                            

Читать полностью…

የሶላ ደብዳቤ እና ሌሎችም ... 💌

መ...ለ...የ...ት እና መ...ለ...ያ...የ...ት ❤️‍🩹


ጥሁፍ ፦ ከሶላ🫡

Ft. Gossaye ... የቦሌው ጎዳና ሽር 'ምንልበት ፣ እኔን መልሶኛል አንቺን ሸኝቼበት 🧎🏿



🔴፦ የጥሁፉ የመጨረሻው ቃል " እንዳትይኝ " ላልቶም ጠብቆም ይነበብ


Video & Audio editor ፦ sofii 🙏


ይህ Video እና ቀጣይም እንዲለቀቅ ከፈለጉ 👍 ይጫኑ


@Ammelakuletters
@Ammelakuletters
@Kehiwotmahder
@Kehiwotmahder

Читать полностью…

የሶላ ደብዳቤ እና ሌሎችም ... 💌

<< መልካም አዲስ አመት እንዲሆን አልመኝም >>

አጭር ድርሰት በሶላ

ነገ ይጠብቁን


@Ammelakuletters
@Ammelakuletters
@Ammelakuletters

Читать полностью…

የሶላ ደብዳቤ እና ሌሎችም ... 💌

አንዳንዴ ከሚያመን ከበሽታው በላይ የማስታገሻውን መድሀኒት (painkiller) መልመድ በይበልጥ ይጎዳናል ... ልክ አንቺን መልመዴ ከቁስሌ በላይ እንደጎዳኝ ....

#Nomore_pain_killer 💊
#No_more_አንቺ 💔


  WOW ...  ከልቤ ስትርቂ ህይወት እና መኖር ተጀመረ


ተጣፈ ፦ በሶላ ✍🏾

Photo credit ፦ sophi


@Ammelakuletters
@Ammelakuletters

@Kehiwotmahder
@Kehiwotmahder

Читать полностью…

የሶላ ደብዳቤ እና ሌሎችም ... 💌

የሶላ ደብዳቤ
ክፍል ገፅ-በገፅ
💔

<< ይበርዳል ... >>

" በእውኑ ፍቅር እና አንድን ሰው ማፍቀር ይለያያልን ?"

@Kehiwotmahder
@Kehiwotmahder
@Kehiwotmahder

Читать полностью…

የሶላ ደብዳቤ እና ሌሎችም ... 💌

የሶላ ደብዳቤ
ክፍል ገፅ-በገፅ 🤗

" ከጀንበሯ ጋር ጠልቃለች 💔 "

The owner of this story was my friend & written by me .

👂💌 @Ammelakuletters

Читать полностью…

የሶላ ደብዳቤ እና ሌሎችም ... 💌

ሰው አለኝ 💝

ከሶላ ✍

Tamerat desta ( Kalkidan alegn ) 👑

@Kehiwotmahder
@Kehiwotmahder
@Kehiwotmahder

Читать полностью…

የሶላ ደብዳቤ እና ሌሎችም ... 💌

ሰላም ለእናንተ ይሁን (ዮሐ 20:26)

የትንሳኤ ግጥም ከሶላ

<< ዛሬም ሳትዘነጋን ሳትተወን ላፍታ
ዳግም ቶሎ ናልን ስንል ማራናታ >>

እንኳን ለጌታችን ለመድኃኒታችን ለእየሱስ ክርስቶስ ብርሀነ ትንሳዔ በሰላም አደረሳችሁ

@Kehiwotmahder
@Kehiwotmahder
@Kehiwotmahder

Читать полностью…

የሶላ ደብዳቤ እና ሌሎችም ... 💌

ከሃሳቤ በላይ 😊

✍ከሶላ😷

"እንኳንስ የዛሬው የነገውም ያልፋል🙌።"

💚👂😃 @Ammelakuletters

Читать полностью…

የሶላ ደብዳቤ እና ሌሎችም ... 💌

ከሶላ እና ሶፊ


.....ዘመን ሲመሽ #2
ጊዜ ሲሸሽ.......



በአባቶቻችን ፍክት ብሎ የነበረው ብርሀን መሽቶ ይታየኛል።ንጋት ይናፍቃል... ንጋት እንኳን ቢኖር እንዳናይ የአይናችን ጉድፍ ሰውሮታል...መልካም ሆነን ተፈጥረን ሳለ መልካሙን መንገድ አልመረጥንም...መልካምነት እምቢኝ፤ክፋት ይግዛን አልን። ሳይሰሩ ውጤት ብቻ ናፋቂ፤ክፋት ዘርቶ መልካም ጠባቂ።የድሎት እና የሆዳችን ተገዢ ከህሊናችን አጉድለን ኪሳችንን የምንሞላ፤ባደረግነው የማንፀፀት ሀፍረት የሌለን ልበ ደንዳና ድፍኖች ሆነናል። የዘራነው ዘር የወፍ ሲሳይ ሆኗል... ትርፋችን ብኩንነት ነው....
...ግብይይቱ ግን ተፋፍሟል.... የማይሸጥም የለም! የተሰረቀ ህንፃ ይሸጣል፤ታሪክ፤ቅርስ እና ማንነት በረከሰ ዋጋ ይሸጣል ። (በዚህም ይሄ ትውልድ ታሪክን አዛብቶ እውነትን ይራባል!)፤ሰው በቁሙ ይሸጣል። የሚገርመው ገዢው! የሚገዛው ወንድሙን፣ሻጩም የሚሸጠው የገዛ ወንድሙን ነው።
#2_ዘመን_ሲመሽ_ጊዜ_ሲሸሽ
የምንፈጥረው ችግር ተበራክቷል...ሰማዩ የምድሩን። ግፍ ያንፀባርቃል...ሀሩር ፀሀይ(እጅግ የሚለበልብ)፣ጭጋግ፣ቁጣ አዘል መብረቅ፣ውርጭ ከክፉ ስራችን የተጠመቀ መራር ፅዋችን ነው።ሁለት አይነት ሰው ሆነናል! ግራ የገባን እና ምንም ያልገባን... ወዴት እንደምንሄድ ያልተገነዘብን፤ ወደፊት እየረገጥን ወደኋላ የሚንራመድ፤ መድረሻውን ስንል መነሻው ጠፍቶን መሀል ቤት የቀረን ሆነናል። ልክ እንደኛ መንገድ የጠፋበትን እንከተላለን....
መብታችን ይከበር ለሚለው ሰልፍ ወተን ነዳጅ ተወደደ! ይቀነስልን!!! የሚለው ሰልፍ ላይ ተሰልፈን እንመለሳለን።...ሰፊ ቤተ-መቅደስ እያለን በጠባቡ አለም እየተጋፋን ነው...ቀኝ እጃችንን ግራ፣ግራ እጃችንን ቀኝ ልናደርግ እንፈልጋለን።የምንፈታተነውን አናውቀውም...ኑሯችን መልክ ብቻ ነው...ግብረገብነት ከህሊናችን ተፍቆ ጥላቻ በደማቁ ተፅፏል(ፍቅራችን ከጥቅም አይዘልም።) ለውጣችን ቁልቁል ነው።በክፋት ጎዳና ላይ ስለሆንን በእኛና በእኛ መካከል ፈጣን ዝግመተ ነውጥ ይታይብናል። ከራሳችን ጋር እንኳን ሰላም የለንም።
#2_ዘመን_ሲመሽ_ጊዜ_ሲሸሽ
ከአፅናፍ እስከ አፅናፍ በጥላቻ ደለል ተደፍነናል...ለተደረገ መልካም ነገር እንጂ ለተደረገው መጥፎ ነገር ሀላፊነቱን የሚወስድ ጠፍቷል...መልካሙን የኔ መጥፎውን የእናንተ ይላሉ።ማንን ማመን እንዳለብን ጨንቆናል ሁሉም በመረጃ አስደግፎ ይዋሻል...
የሚሉንና የምናየው ነገር ለየቅል ነው...በዳዩን ልኮ ሊያፅናን ይመጣል...(የማፅናናት ወይስ የመበደል ፍቅር ያለው???)
ከአካላችሁ አንዱ የናንተ አይደለም...ስለራሳችሁ ከእናንተ በላይ እኛ እናውቃለንም ይሉናል...(ጆሮዬ ነው ወይስ አፍንጫዬ የእኔ ያልሆነው...? )
ከአካላችሁ አንዱ ሲጎል ለውስጣችሁ ሰላም የምታደርጉት መስዋትነት ነው...ወንድማችንን እንዳንወድ ዘረኝነት ጠምዶ ይዞናል...ትስስራችን የመልካም ባህል ትውፊቶቻችን አፈር በልቷቸዋል ጤና ይስጥልኝ ትተን ጤና ይንሳልኝ፤ምነው በደፋልኝ ማለት ከጀመርን ሰነባብተናል... ልባችንም፤ዘመናችንም የክፋት እና የኅጥያት ማደርያ ሆኗል።


ሶፊ ያለው እውነቱን ነው "የደከመ ላይ የሚበረታ እንጂ የደከመን የሚያበረታ ጠፍቷል..."

መመደብ ትወዳላችሁ...

እኔንስ ማን ትሉኛላችሁ ?


"ኤሎሄ...! "

Читать полностью…

የሶላ ደብዳቤ እና ሌሎችም ... 💌

በፍፁም ቀላል አይደለም ለምትለው ህይወትህ በፍፁም ቀላል አትሁንለት!
.

.

.

.
ነጠብጣብ ቀለም ፤ ያለተቋጩ ሀሳቦች ( ከሶላ )


@Ammelakuletters
@Ammelakuletters
@Ammelakuletters

Читать полностью…
Subscribe to a channel