kene_tobeya | Unsorted

Telegram-канал kene_tobeya - ቅኔ እና ጦቢያ

-

▬▬▬▬▬▬▬▬▬▬▬▬ በብራና ዘመን ቀለምን ቀምመን እንዘርፋለን ቅኔ ለፍቅር የሚሆን። #ቅኔ_እና_ጦቢያ #በብራና_ዘመን_ለምን_ተላለፍነ!! በወጣቱ ገጣሚ እና ፀሀፊ አማኑኤል ደርበው ▬▬▬▬▬▬▬▬▬▬▬▬ ያግኙን፦ለሀሳብ አስተያየት 👉 @poet_amanbot 👉 @aman0777

Subscribe to a channel

ቅኔ እና ጦቢያ

የሆነ ምሽት


በ በዕውቀቱ ስዩም


ይሄ ንፍጣም ቫይረስ ወደ አገራችን ከመግባቱ ሁለት ወር
አስቀድሞ የነበረውን ጊዜ እንደ ጉድ ጨፈርኩበት! ዛሬ እንዲህ
ተጨማድጄ ልቀመጥ ያኔ እየዞርኩ የክለብ ምንጣፍ በዳንስ
ሳጨማድድ አመሽ ነበር!
የዚያን ቀን ምሽት ከጊድዮን ጋር ነበርሁ፤ ባለትዳር ነው፤
የሚስቱና (ዛዮን) የሶስት ልጆቹ ፎቶ በስልኩ ስክሪን ላይ ወለል
ብሎ ይታያል ፤ እኔ ስለጎተጎትኩት ፤ ሚስቱም “ እስቲ ዛሬ ወንድ
ይውጣህ ! አምሽተህ ና” ብላ ስለገፋፋችው ነው እንጂ ጌድዮን
በተፈጥሮው’ መዝናናት የተሳነው’ ሰው ነው፤
“ምን ላምጣላችሁ?” አለችን አስተናጋጂት ኤደን!
“ዘፈን የለም እንዴ ዛሬ?” ስል ጠየቅሗት የምንፈገውን ካዘዝኳት
በሗላ።
“አራት ሰአት ላይ እንጀምራለን’
“እነማን አሉ?
“ኩኩ ሰብስቤ ! አለማየሁ ! ወንድሙ ጂራ “
“ አሹስ ?”
አሹ የታወቀ ተወዛዋዥ ነው፤ የሰማንያ አራቱን ብሄረሰቦች
ውዝዋዜ አሳምሮ ይችላል ፤( ሶስቱ ብሄሮች ከኤርትራ ናቸው)፤ ‘
“ሰውነቱ አጥንት ያለውኮ አይመስልም ይሉታል ‘ አድናቂዎቹ!!
“ አሹ እንደታመመ አልሰማህም እንዴ?” አለችኝ በትካዜ፤
“ምን ገጠመው?”
‘’ በቀደም እለት አቶ ወርቁ አይተነው አምስት መቶ ሺ ብር
ሲሸልሙት በድንጋጤ ከመድረክ ወድቆ ፤ አሁን ሼክ አላሙዲን
እያሳከሙት ነው”
ጉዋደኛየ ጊድየን ሚስቱን ስልክ ለማናገር መሸተኞችን እየጣሰ
ወጣ፤ ባልና ሚስቱ የሚያወሩትን መገመት አያቅተኝም ፤
“ ዛይየ” ይላታል
“ወይ አባቱ”
“ ሶስተኛ ቢራ ልጨምር ነበር ፤ይደብርሻል ?”
“ እንዴ ልትዝናና አይደል እንዴ ከቤት የወጣኸው? እንዲያውም
ከስምንት በታች ጠጥተህ ከመጣህ እዚች ቤት አትገባትም ”
የጌድዮንና የዛየንን ጋብቻ እንዲሰጣችሁ እየትመኘው ታሪኩን
ልቀጥል፤
ትንሽ ቆይቶ የክለቡ ፀጥታ አስከባሪ አቦሌ ወደ ተቀመጥንበት
ጠረጴዛ መጣ፤
“ ስራ እንዴት ነው” አልኩት፤
“ ” አሼወይና ነው፤ “
“ አንተ እዚህ ቤት ከተቀጠርክ ጊዜ ጀምሮ ያጥንት ህክምና
ክሊኒኮች ስራ እንደበዛባቸው ሰምቻለሁ “ ብየ አሟሟቅሁለት።
አቦሌ መጠነ -ሰፊ ፈገግታ አሳየኝ “ እንዴት ባለ ብቃት እየሰራሁ
እንዳለሁ ለመታዘብ ከፈለግህ ትንሽ መጠበቅ አለብህ፤ ዋናው
የጥሎ ማለፍ ድብድብ የሚጀምረው ከምሽቱ አምስት ሰአት ላይ
ነው” አለኝ፤
“ እስከዚያ እንኳን የምንቆይ አልመሰለኝም ”
አቦሌ ቅር አለው፤ ግን ወድያው ዞር ብሎ አዳራሹን ከዳር
እስከዳር ቃኘው ፤ወድያው ፊቱ በደስታ በራ “ ኦኬ! ያን ኤደንን
ካልሳምኩ እያለ እሚወራጨውን ረጅም ሰውየ አየኸው?” አለኝ።
“ አው”
“ አንድ ጥፊ አይነስቡ ስር በስሱ እገባለታለሁ ፤ ሶስቴ
ተሽከርክሮ ወደ ምስራቅ ከወደቀ ዘንድሮ በኢትዮጵያ ጥጋብ
ይሆናል ”
አራት ተኩል ላይ እኔና ጌድዮን ከክለቡ ወጥተን በቅርቡ ወደ
ተከፈተ ሌላ ክለብ ሄድን ፤ መንፈቀሌሊት ገደማ ያልጠበቅነው
ነገር ተከሰተ ! መደበኛው መብራት ጠፋና ባለህብረቀለም
መብራት ክፍሉ ውስጥ መንቀዥቀዥ ጀመረ፤ አንዲት ገላዋ
በሁሉም አቅጣጫ ሞላ ሞላ ያለ ቆንጅየ ሴትዮ ከሙታንታ በቀር
እርቃን ሆና ወደ መድረክ ወጥታ ምሶሶውን እየታገለች
መወረግረግ ጀመረች ፤ ደንበኞች ማውካት ማጨብጨብ
ጀመሩ! ፤ እኔም ግራ እግሬን በቀኝ እግሬ ላይ ጭኜ ትእይንቱን
ለማጣጣም ተሰናዳሁ ፤ ጉዋደኛየ ግን አልተመቸውም፤
ኮሌታየን ጭምድዶ እያካለበ ይዞኝ ወጣ፤ ጥቂት ጨዋ
ታዳሚዎች እያጉረመረሙ ተከተሉን!
በረንዳው ላይ ቁጭ ብለን ቢራ እየጠጣን ስናወራ ፤አንድ
ሽማግሌ ከክለቡ ወጡ፤በጣም ተናደዋል፤ በሽበት የተሞላውን
የእርጎ ጣባ የመሰለውን ራሳቸውን እየነቀነቁ ከፊታችን ትንሽ
ተንቆራጠጡ ፤ ሲጃራቸውን አቀጣጠሉና አንዴ ስበው ጭሱን
ወደ ሰማይ ተኮሱት ‘በእድሜየ ማምሻ ላይ እንዲህ ያለ ጉድ
ታሳየኝ !’ የሚሉ መሰለኝ! ትውልዱን ወክየ ግብዳ ድንጋይ
ተሸክሜ እግራቸው ላይ ለመውደቅ ከጀለኝ
“ ዘገነነዎት አይደል አባት?”
አላቸው ጉዋደኛየ፤
“ በጣም እንጂ !” አሉ ሽሜው” ስንት ሽንኩር ሽንኩር የመሳሰሉ
ኮረዶች እያሉ ይቺን ደባደቦ ፈትተው ይለቁብናል ? ”

t.me/kene_tobeya

Читать полностью…

ቅኔ እና ጦቢያ

" #ሰው_ፍቅር_ናፍቆት"

#አዲስ_አበባ
✿ በጃዕፋር መፅሐፍት መደብር ( ለገሀር )
✿ በኤዞፕ ( ፒያሳ )
✿ በኮሜርስ
✿ በሜክሲኮ ቡክ ኮርነር
✿ አምስት ኪሎ አካባቢ ባሉ መሸጫዎች ይገኛል፡፡
#ናዝሬት
✿በምንተስኖት መፅሀፍት
✿በዳሪክ አዳማ
@heranawi
@hernawi
@heranawi

Читать полностью…

ቅኔ እና ጦቢያ

( #ሰው__ፍቅር__ናፍቆት )

ሽልማት የሚያሸልም ውድድር

ሰላም ዳግም ሔራን ነኝ… በባለፈው የወጣውን #ሰው_ፍቅር_ናፍቆት የተሰኘውን መፅሀፌን ለብዙ አንባቢያን ለማድረስ በማሰብ ለቴሌግራም ወዳጆቻችን ሽልማት ያለው ውድድር አዘጋጅተናል።
#የውድድሩ_አይነት

ከዚህ ፎቶ ጋር የተያያዘውን መልዕክት በተለያዩ ግሩፖች ና ቻናሎች ላይ ሼር በማድረግ ብዙ ተመልካች (view) ማግኘት ሲሆን……

#ሽልማቱ_ደግሞ

1, አንደኛ 100 k ተመልካች ላገኘ
5 ጊ.ባ ኢንተርኔት ፖኬጅ እና አንድ
"ሰው ፍቅር_ናፍቆት" መፅሀፍ

2, ሁለተኛ ከፍተኛ ተመልካች ላገኘ
4 ጊ.ባ ኢንተርኔት ፓኬጅ አንድ
" #ሰው_ፍቅር_ናፍቆት " መፅሀፍ

3, ሶስተኛ ከፍተኛ ተመልካች ላገኘ
3 ጊ.ባ. ኢንተርኔት ፓኬጅ አንደ
" #ሰው_ፍቅር_ናፍቆት " መፅሀፍ

4, አራተኛ ከፍተኛ ተመልካች ላገኘ
2 ጊ.ባ. ኢንተርኔት ፓኬጅ አንድ
" #ሰው_ፍቅር_ናፍቆት " መፅሀፍ
5, አምስተኛ ከፍተኛ ተመልካች ላገኘ
1 ጊ . ባ ኢንተርኔት ፓኬጅ አንድ
" #ሰው_ፍቅር_ናፍቆት " መፅሀፍ

ውድድሩ ነገ ሃሙስ ማታ 2 ሰዓት ይጀመራል!!

#ለመወዳደር_የምትፈልጉ_በዚህ_በኩል_አናግሩኝ @dagiamen12

Join and share……………👇👇
@heranawi
@heranawi
@heranawi

Читать полностью…

ቅኔ እና ጦቢያ

ሔራን📖📖:
( #ሰው__ፍቅር__ናፍቆት )
:
#ፎቶ___ አማኒ( የ ፍካት ቤተሰብ)

#የእርሶንም_ቅጂ_ይላኩልን
@dagiamen12
ወይም
0942459046 ቴሌግራም!!
:
#አዲስ_አበባ
✿ በጃዕፋር መፅሐፍት መደብር ( ለገሀር )
✿ በኤዞፕ ( ፒያሳ )
✿ በኮሜርስ
✿ በሜክሲኮ ቡኩ ኮርነር
✿ አምስት ኪሎ አካባቢ ባሉ መሸጫዎች ይገኛል፡፡

#ናዝሬት
✿በምንተስኖት መፅሀፍት
✿በዳሪክ አዳማ
✿ወልዴ መፅሀፍት መሸጫ ይገኛል
*…………………………………………**
Join and share……………………👇👇
@heranawi
@heranawi
@heranaei

Читать полностью…

ቅኔ እና ጦቢያ

ቡና
እጣን
እኔ
እና
የእናንተ መፅሀፍ!!
#በነገራችን_ላይ…እኛም ሰው ፍቅር ናፍቆትን በቁጥጥር ስር አውለናታን
#የእርሶንም_ቅጂ_ይላኩልን 📷
@dagiamen12
ወይም
…0942459046 ቴሌግራም!
በጃፋር መፅሀፍት ………ለገሃር
በኤዞፕ መፅሀፍት…………ፒያሳ
በኮሜርስ መፅሀፍት ………ሜክሲኮ

Читать полностью…

ቅኔ እና ጦቢያ

"ሰው ፍቅር ናፍቆት!"
#ጃፋር_መፅሀፍት…ለገሃር
#ኤዞፕ_መፅሀፍት_ፒያሳ…ይገኛል!
@heranawi
@dagiamen12
@heranawi

Читать полностью…

ቅኔ እና ጦቢያ

( ብትኖሪም ባትኖሪም)
:
ከነፍስ የተቀዳው
ሳቅሽ ሳቁን ወልዶ : ደስታ እያሳቀፈው
ስንቱን ወዝ አልባ ቀን
በፈገግታሽ ብርታት : ጠንክሮ ካ‘ለፈው
:
ከአፍቃሪሽ ልቤ
አለነት ሲጎድል : ሲያንስ ከሙላቱ
እንባ እየታቀፈ
ከፅልመት ቢጠቁረ : ጠፋቶበት ቅላቱ
:
:
ወዘናው ቢከፋ
ፀዲል እሱነቱ : ገፁ ቢከረፋ
ሀዘን ያቆሰለው
ያልጠገግው ቁስለት : ዳግም ቢገለማ
ወጋገንማ ፍቅርሽ
ከበዓቱ ጠፎቶ : ቢወርሰው ጨለማ
:
እርሱ ላፍታ አያዝን
በልክ የለሽ ስፍር : ተስፋውን አይመዝን
ያልጠፋ አንቺነትሽን
የትግኝ ቃል ይዞ : ለማግኘት አይባዝን !
:
:
አየሽ ሀቁ እንዲህ ነው
ያጣሽ ይህ የኔ ልብ
የሚኖረው ኑረት
ውስጣዊ ልሳኑን : ምሥጢሩን ስንፈታው
የአለች ቃል_ኪዳን
እምነት እና እውነቱ : እንዲህ ነው አንድምታው
:
:
እንዴት አልሽ መሰል?
እንደዚህ ልበለሽ

ተመልከች የኔ ሴት
ኦናነት ካጠረው
ከምንም እኔነት : ያንቺነትሽ ሙላት
ባል‘ታለመ መሄድ
በደንገቴ ዕጦት : ከሙላት ቢያጎላት
:
እንዲህ እንደ እኔ ላለ
ህመም ለፀነበት : ለታደለ ህቅታ
አንሶ የማታየት
የጎደለ ጉድለት : ዝቅ ያለ ዝቅታ
:
በዝቃዊ እርካብ
ከ ከፍ ላይ ደርሶ : ገዝፎ ለመገለጥ
ሳቅን የጋረደን
ጭጋጋሙን ዋይታ : በሀሴት ለመብለጥ
:
ዋዜማ ነውና
ምን ህመሜ ከፍቶ : ሀዘኔ ቢፀና
አልፎ በማወራው
በለቅሶዬ ላለቅስ : በሀዘኔ አላዝንም
የአፍቅሮቴን ልኬት
በመሄድሽ ስፍር : በአጉል አልመዝንም
:
ይህ ማለት ምንደን ነው
:
ትላንት አለኝ ያልኩት
ዛሬ ተለይቶኝ : አሁን የናፈኩት
የነበር መውደድሽን
ከክደትሽ በፊት : ቀድሞ ስላወኩት
:
አንቺን ተከትሎ
ከኋላ በመጣ : በመለየት እውነት
ግዝፈቱ ዝቅ አይልም
ተሸርፎ አይጣልም : የልቤ ላይ እምነት…!!
:
እናም ፍቅር_ዓለሜ
ብትኖሪም ባትኖሪም
ኃያሉ መውደድሽ : ልቤ ላይ ይኖራል
ጨለማ ቢመስልም
ላምባው አንቺነትሽ : ለ ነፍሴ ይበራል!
:
:
#እስከ_መቼ………… #እንጃ
ብቻ ግን ትላንቴ_ሆይ
ዛሬም





ሁ!
…………………………………………**
©ዳግም ሔራን ( ቅዱሱ እብድ)
( ሰው ፍቅር ናፍቆት በቅርብ ቀን)
Join and share………………………👇👇
@heranawi
@heranawi
@heranawi ይቀላቀሉን 🙏🙏

Читать полностью…

ቅኔ እና ጦቢያ

እመጓ
ዶክተር አለማየሁ ዋሴ
@kene_tobeya

Читать полностью…

ቅኔ እና ጦቢያ

ገላና ገላ
t.me/kene_tobeya

Читать полностью…

ቅኔ እና ጦቢያ

" ትዝታ ይብቃ "
ገጣሚ: አንባቢ …ዳግም ሔራን
[ #ከሰው_ፍቅር_ናፍቆት
የግጥም መፅሀፍ ላይ የተወሰደ ]

ሰው ፍቅር ናፍቆት
[ #በቅርብ_ቀን]
Join and share…………………👇👇
@heranawi
@heranawi
@heranawi

Читать полностью…

ቅኔ እና ጦቢያ

#ከትናንት_የተጫረ_‘ሳ ት...✍

እንደሰበዓሰገል ፡ ኮከብ ፡ ምሪት
እንደመከተል – የሰጠሽኝ ፡ ምልክት
የዐይንሽ – የቃልሽ ፡ ምሥጢር
ለዛኔው ፡ እኔ ፡ ቢጠጥር፤
ሳይገባኝ
ስቀቴ ፡ እንደመራኝ
ወርቅሽን ፡ በሰም ፡ ፈክሬ
ሲገባኝ
እሳቱ ፡ ተረፈኝ ፡ ዛሬ።
ለካ…
ወደድኩሽ ፡ ብዬ ፡ ስመናቀር
ሞትኩልህ ፡ ብለሽኝ : ነበር።

---- // ----
ገጣሚ፦ መ ዘ ክ ር ፡ ግ ር ማ

t.me/kene_tobeya

Читать полностью…

ቅኔ እና ጦቢያ

# እረፉ "
ዘመመ ብላችሁ የሰዉ ቤት አትግፉ
እሾህ ለማሳመር አበባ አታርግፉ ::
" # እረፍ "
ቆሜለሁ ለማለት አጥሬን አትደገፍ
ለአመዳም ወዘናህ ቆዳየን አትግፈፍ ::
" # እረፍ "
በመስመርህ ፍካ በድንበርህ ለምልም
በየአልጋህ እደር በየእንቅልፍህ አልም ፡፡
" # እረፊ "
በኩረጃ ንባብ ትርጉም አትግደፊ
በሰባራ መርፌ የሰዉ ልክ አትስፊ ::
ማን እንደሰለፈኝ — ማን እንደሰበረኝ
ጠያቂ አጣሁ እንጂ— መልስማ ነበረኝ
ምክንያት ታመመ — መፍትሔ ታመመ
ከጥያቄዉ በፊት — መልሱ እየቀደመ
.
ሌብነት ገነነ
ግርግር ገነነ
ብልጭልጭ ገነነ
ድንግርግር ገነነ
ኪሳራ ገነነ
ደላሎች ገነኑ ደላሎች ጀገኑ
ባልዋለ ገበያ ዋጋ እየተመኑ ፡፡

እያያ ፈንገስ
t.me/kene_tobeya

Читать полностью…

ቅኔ እና ጦቢያ

ያንተ ልጅ ሲበላ
የኔ ልጅ ያለቅሳል

ያንተ ቤት ተከድኖ
የኔ ቤት ይፈርሳል

ያንተ መሬት ታርሶ
የኔ ዳዋ ለብሷል

ወይ ካንተ ወይ ከኔ
ያንዳችን ቀን ደርሷል
ግዜ መሀንዲስ ነው
ይሰራል ያፈርሳል
(ከሚድያ)

#እኔ_ለወገኔ

#የግጥም_ቃና
👇👇👇
@ilovvll
@ilovvll 👈 ቤተሰብ ይሁኑ

Читать полностью…

ቅኔ እና ጦቢያ

ለኑረት ዋስትናው :ለትንሹ ኩራት
ምን እንኳ ቢመረጥ……ትልቁ ቢቀጠር
ለትልቅ እውነት : ለጋን እሱነቱ
ደጋፊ ማንነት………ያፈልጋል ጠጠር !!
……………………………………**
[ #ሰው_ፍቅር_ናፍቆት]
በቅርብ ቀን #ከሔራን
Join and share…………………👇
@heranawi
@heranawi
@heranawi

Читать полностью…

ቅኔ እና ጦቢያ

የደንቆሮ፡ድንቁርና ብልህ፡ለመምሰል፡ሲሞክር ይገለፃል።


🗣 ክቡር ዶ/ር ሀዲስ አለማየሁ


t.me/kene_tobeya

Читать полностью…

ቅኔ እና ጦቢያ

" #ሰው_ፍቅር_ናፍቆት"

#አዲስ_አበባ
✿ በጃዕፋር መፅሐፍት መደብር ( ለገሀር )
✿ በኤዞፕ ( ፒያሳ )
✿ በኮሜርስ
✿ በሜክሲኮ ቡክ ኮርነር
✿ አምስት ኪሎ አካባቢ ባሉ መሸጫዎች ይገኛል፡፡
#ናዝሬት
✿በምንተስኖት መፅሀፍት
✿በዳሪክ አዳማ
@heranawi
@hernawi
@heranwi

Читать полностью…

ቅኔ እና ጦቢያ

ሔራን📖📖:
"
#ሰው_ፍቅር_ናፍቆት"

#አዲስ_አበባ
✿ በጃዕፋር መፅሐፍት መደብር ( ለገሀር )
✿ በኤዞፕ ( ፒያሳ )
✿ በኮሜርስ
✿ በሜክሲኮ ቡክ ኮርነር
✿ አምስት ኪሎ አካባቢ ባሉ መሸጫዎች ይገኛል፡፡
#ናዝሬት
✿በምንተስኖት መፅሀፍት
✿በዳሪክ አዳማ
@heranawi
@heranawi

Читать полностью…

ቅኔ እና ጦቢያ

" #ሰው_ፍቅር_ናፍቆት"

#አዲስ_አበባ
✿ በጃዕፋር መፅሐፍት መደብር ( ለገሀር )
✿ በኤዞፕ ( ፒያሳ )
✿ በኮሜርስ
✿ በሜክሲኮ ቡኩ ኮርነር
✿ አምስት ኪሎ አካባቢ ባሉ መሸጫዎች ይገኛል፡፡

#ናዝሬት
✿በምንተስኖት መፅሀፍት
✿በዳሪክ አዳማ
✿ወልዴ መፅሀፍት መሸጫ ይገኛል
*……………………………

Читать полностью…

ቅኔ እና ጦቢያ

( #ሰው__ፍቅር__ናፍቆት )
አዲስ መፅሀፍ እንዲህ እየተነበበ ይገኛል
@heranawi
@heranawi
@heranawi

Читать полностью…

ቅኔ እና ጦቢያ

ለምን አልፈጠርክም?

ኤፍሬም ስዩም (ሶልያና)

#የግጥም_ቃና
👇👇👇
@ilovvll
@ilovvll 👈 ቤተሰብ ይሁኑ

💚መልካም💛ቀን❤

Читать полностью…

ቅኔ እና ጦቢያ

ዌል ***
የከፍታው ዘመን በርግጥ ተጀምሯል
ብራችን ዋጋ አጥቶ ዶላር እጅግ ንሯል
ከሌለን ተወስዶ ላለው ተጨምሯል
ወዛችን ተሟጦ አመዳም ሆነናል

#የግጥም_ቃና_በመክሊት_የ16ቷ
👇👇👇
@ilovvll
@ilovvll 👈 ቤተሰብ ይሁኑ

Читать полностью…

ቅኔ እና ጦቢያ

"እመጓ ቆላ ሆይ!"
"አንቺ የተባረክሽ ምስጢራዊ ምድር!
ሶርያው አባ አድሪል ቅዱሱን ቅርስና ቃል ኪዳን በሆዷ ይዛለች ብሎ የተቀኘልሽ፤
አንቺ የቅርብ ሩቅ ማዕከላዊ ምድር ስትሆኚ በተራሮች የተከለልሽ አዘቅት፤
አንቺ መላእክት የሚረብቡሽ ስትሆኚ ሰወች ግን የናቁሽ፤
አንቺ አለምን የሚያስቀና ግሩም ቃል ኪዳን ያለሽ ስትሆኚ ራስሽን ደብቀሽ ተራ
ሆነሽ የኖርሽ መናኝ፤
አንቺ ሁሉም ስለራሱ ሲያወራ፣ ለዘመናት ዝም ያልሽ ልጉም ሙዳይ፤
ቫቲካን ስታቅራራ፣ ቆጵሮስ ስትጮህ፣ እስክንድሪያ ስታመሰጥር፣ ኢየሩሳሌም
በጸጸት ስትቃትት፣ ለንደን ያለስጦታዋ ስትቦተልክ፣ ፈረንሳይዋ ማርሴይ በምኞት
ስትቃዥ ምንም የማይመስልሽ አርምሞን የመረጥሽ አሳቻ ታዛቢ፣
የእህቶችሽን የአክሱምን፣ የግሸንን፣ የላሊበላን፣ የጣና ቂርቆስን ያክል እንኳን
ፊትሽ የማይፈታ የተቋጠርሽ ሸማ! ዓለም ሁሉ ወደ እነርሱ ሲጎርፍ ቅናት
የሌለብሽ ልዝብ ደርባባ፤"
መልካም ቀን!!
ዶ/ር አለማየሁ ዋሴ ከፃፈው እመጓ መፅሀፍ በትንሹ የተወሰደ።
t.me/kene_tobeya

Читать полностью…

ቅኔ እና ጦቢያ

#ገላና_ገላ

እንዲያው አንዳንዴ ቁጭ ስል ሩቅ መንደር የተሰየሙትን ባልጀሮቼን ማስታወስ እወዳለሁ።እናም ዛሬ ወዳጆቼን ሳስታውስ ብርዷ ሰውነትን ሰንጥቆ ሲገባ አረቂ በመለኪያ ለፈውስ ይዛ የምትቀበለንን ሀገረ ደብረ ብርሃንን አስታወስኩ።ጥቂት የማይባሉ ወዳጄች አሉኝ።አንደኛው ወዳጄ ደግሞ የመጀመሪያ ልጁን ከተገላገለ ሰንበትበት ብሏን።ብዘገይም መሌ እንኳን ደስ አለህ። እናንተም መጥሀፉን አድናችሁ አንብቡ ልመናም ትዕዛዝም ነው።

መላኩ ደምሴ(ገላና ገላ)
t.me/kene_tobeya

Читать полностью…

ቅኔ እና ጦቢያ

ደራሲ ና አንባቢ

ሱራፌል ጌትነት
ሱራ ቢራቢሮ🦋

✍ @surabirabiro 🦋

Читать полностью…

ቅኔ እና ጦቢያ

ንፁህ፡ፍቅር
ሊኖር፡የሚችለው
በምክንያቶችና
በመሥፈርቶች
ካልታጀበ፡ብቻ፡ነው።

🗣 ኦሾ

t.me/kene_tobeya

Читать полностью…

ቅኔ እና ጦቢያ

ይሄም ያልፋል!!!

@ilovvll
@ilovvll 👈 ቤተሰብ ይሁኑ

💚መልካም💛ቀን❤

Читать полностью…

ቅኔ እና ጦቢያ

ጎዳናው ይገርማል?!

ጋዜጠኛ፣ ገጣሚና ደራሲ ~ #በረከት በላይነህ

ይገርማል መንገዱ
እግረኛው ይገርማል

ሸራ ጫማ ባ'ይነት
በነጫጭ ካልሲ
በሲኪኒ ሱሪ
ከመምህሩ ጋራ
አይስክሬም ሚልስ
የሀይስኩል ተማሪ
.
ፀባይኛ ወጣት
ጃንቦ ተከልሎ
በምርቃና ሆኖ
ሀሳብ የሚፈትል
አንዲት ሙ......ደኛ እናት
በ'ድሜ ከልጆቼ አንሳለው የምትል
ፒዛውን የሚገምጥ
ጭማቂ የሚመጥ
አራዳ አባወራ
በሚስቱ ትከሻ
በልጆቹ ምላስ
ቅምጥ የሚጣራ
.
አንድ ፍሬ ሴቶች
በተገዛ ቅንድብ
በተገዛ ፀጉር በተገዛ ጥፍር
በውሰት ወዘና የተብለጨለጩ
ማኪያቶ ከበው
ለውስኪ ሚንጫጩ
ጅናም ጅንሳም ወንዶች በሴቶች ጫጫታ የሚቁለጨለጩ
.
ይገርማል ጎዳናው ይገርማል መንገዱ....
.
ድንቡሽቡሽ ህፃናት
በቶም ኤንድ ጄሪ ሱስ
ቀልባቸው የከሳ
በአይፎኑ አጮልቆ
ያንጀሊናን ከንፈር የሚስም ጎረምሳ
.
ቀውጢ ዳያስፖራ
.
የሎቲው የቁምጣው የቲሸርቱ ጥለት የተንዘረፈፈው
አማርኛ ሲሸሽ "what's happen" የጠለፈው
.
ነቄ ብላቴና
.
ከዮፍታዬ ቀዬ
ካ'ዲስ አለማየሁ
ከመዝገቡ መንደር
የአዲስ አ'ባ ጥሪ
በቁምጣ ያበረረው
ከቅኔ ተጣልቶ
ከግዕዝ ተኳርፎ ሎተሪ ሚያዞረው
.
ፀዴ ብላቴና
.
ከባላገር ዘመን
ከጨለማ ዘመን
ወደ ብርሃን ጥግ ተሸጋገርኩ ብሎ
በሸንኮራ ምርኩዝ ከተማ ሚያካልል መቋሚያውን ጥሎ
ነብሱ እየሰለለች
በከተሜነት ወግ ባ'ራዳነት ልምሻ
ሲያዘግም የሚውል
ሊስትሮውን ጭኖ በታቦት ትከሻ
.
ፎቆቹ
.
በመስታወት ቁመት በቆርቆሮ ገፆች
ባ'ልሙኒየም ጥራዝ የተብረቀረቁ
የጌቶቻቸውን እድሜ ሚያሳብቁ
ሁሉም........ ሁሉም......ሁሉም ጥግ ናቸው
ለወደቀ ወገን ይራራል ልባቸው
.
ሁሉም
...... ሁሉም
.
ከዘለለት ጥድፊያ
ከሰርክ ውጣ ውረድ በተረፈች አንጀት
ለወደቀ ወገን ምርኩዝ ማበጃጀት
ሁሉም...... ሁሉም ይችላሉ
ስለ'ግዚአር ላለ ይመፀውታሉ
.
እኔ ግን........ እኔ ግን .........ቆጥራለው
የ'ድሜ ክቡር ጀንበር
በጎዳና ፅልመት ሲዋጥ አስተውላለው
ጡረታ መንገድ ዳር ሲከፈን አያለው
.
ቆጥራለው.....ቆጥራለው
.
ቆጥራለው አዛውንት
በየአቀበቱ በየቁልቁለቱ
ማረፊያ ፍለጋ የሚንከራተቱ
ቆጥራለው አዛውንት ከልጆቻቸው ፊት
የልመና መዝገብ የገለጡ አሮጊት
ቆጥራለው በየመንገዱ ዳር
እርጅና ሙሽራው ለምፅዋት ሲዳር
ቆጥራለው በየሸንተረሩ በየተፋሰሱ
አቀርቅሮ ሲያዘግም እርጅና ሞገሱ
ቆጥራለው በ'ያደባባዩ
የሽማግሌ አይኖች የልጅ ፊት እያዩ
ቆጥራለው በየሰርጣሰርጡ
በልመና ጉልበት ከሞት ሲፋጠጡ
የ'ርጅና መዳፎች እሾህ ሲጨብጡ
.
ቆጥሬ..... ቆጥሬ.......ቆጥሬ
በለማኝ አዛውንት ብዛት ተሳክሬ
የማሰንበቻ ስንቅ ከኪሴ ቆንጥሬ
ያፅድቆቴን ዋጋ በሳንቲም መንዝሬ
ባ'ዛውንት ምርቃት ከሀገር ከቀዬው ትርፌን ሳመሳስል
በጎዳናው ቀለም ፃድቅ መልኬን ስስል
ጎልቶ ሚታየኝ ግን የሚያሳፍር ምስል
በቀላል ጥያቄ የነተበ ምስል
.
ጥያቄ
.
የዲጄ ኳኳታ የደናሽ ጋጋታ
የድራፍት እርካታ ያ'ረቄ ድንፋታ
ባጣበበው መንገድ
እንደምን ይቻላል
ላ'ያት ሳንቲም ሰጥቶ በ'ርካታ መራመድ?
.
ለወጣት ሹክሹክታ ለገደል ዝምታ
ላስመሳይ ጫጫታ ላድርባይ እሪታ
በተሰራ መንገድ
እውነት ቀላል ነው ወይ
ላ'ያት ሳንቲም ሰቶ በ'ርካታ መራመድ?
.
ለቡቲክ ሰልፈኛ ለካፌ 'ድምተኛ
ለውስኪ ጭሰኛ ለበርገር ምርኮኛ
በተሰራ መንገድ
እንደምን ይቻላል
ላ'ያት ሳንቲም ሰቶ በ'ርካታ መራመድ?
.
አያት....አያት...አያትነት ማለት
በደማቅ አሻራ የሸመኑት ጥለት
ለተራኪ እድሜ የተሰጠ አንደበት
ባ'ባት በ'ናት ፅናት የማይደክም ጉልበት
በልጅ ልጅ መነፅር የማያረጅ ውበት
በልጅ ልጆች ጥበብ የሚታደስ እውቀት
.....................................የሚታደስ እውነት
አያት ሆኑ ማለት
ድርብ አባትነት
ድርብ እናትነት
.
በተለይ እዚህማ.......
በዚህች አይነት ሀገር
ጎጆዋን ላቆመች
በተጋድሎ ካስማ
ባርበኝነት ማገር
በዚህች አይነት ሀገር
ጥያቄና መልሷን
ባ'ዛን በቅዳሴ በምትሰራ መንደር
በዱአ በፀሎት
በምናኔ ምርኩዝ በከረመች ሰፈር
የአያትነት ዋጋው በልኩ ቢሰፈር
ለሳንቲም ምርቃት ባልተሻማን ነበር!
.
ታሪክ በመዳፉ ስላደላደለው
ሁሉም ኢትዮጵያዊ ንጉስ አያት አለው
የልጅ ልጆች ስባት ባያመነምነው
ያያቶቻችን መልክ ሁሌም አንድ አይነት ነው
.
እላለው... እላለው....
.
የልጆች ምፅዋት ያ'ያቶች ልመና
ያ'ባቶች ግርግር በሞላው ጎዳና
መንገዱ አይልቅም
ጎዳናው አያልቅም
ይሰፋል ይረዝማል ይሄዳል ይጓዛል
እግረኛው ሞኝ ነው
ሳንቲሙን ዘርዝሮ
ከወደቁ አዛውንት ምርቃት ይገዛል
.
መንገዱ ያስፈራል
መንገዱ ይጨንቃል
ልጆች ሳቅ ሲያንቃቸው
አያት እምባ ይጨምቃል
መንገዱ ያሰጋል መንገዱ ያረጃል
ከዘናጭ ልጆች ጎን እርዛት ያዘለ አያት ይወለዳል
.
ሰጪ ካለቀሰ ተበዳሪ ስቆ
ጌታ ከለመነ አማኙ 'ግር ወድቆ
ልዑል ከዘመረ ንጉሱ ተዋርዶ
ገፁ ተመሳቅሎ ሽፋኑ ካማረ
ወለሉ ተንቆ ምንጣፍ ከከበረ
ባ'ገርኛ ስሌት ማነው ያልከሰረ?
.
እላለው........እላለው
.
ከየጎዳናው ገፅ ጥያቄ አነሳለው
ጥያቄ እጥላለው
እርጅና ለማምሻው ጎዳናን ካመነ
አያት ከልጅ ልጁ ሳንቲም ከለመነ
ባገርኛ ስሌት ማነው ያልመከነ?
.
በ'ግዚኦታ ዘመን በምዕላ ዘመን
እመንገድ ዳር ወድቆ ትራፊ መለመን
በጥሞና ዘመን የሚያስቡት ማጣት
በማውረሻ እድሜ የሚሰጡት ማጣት
በማልበሻ ዘመን በ'ርዛት መቀጣት
በለጋሽነት ወቅት በማጉረሻ ዘመን
በጥማት መገረፍ በርሀብ መመንመን
ከሆነ እጣችን
ይጠየቅ ትርጉሙ የልጅነታችን
ይፈተሽ መንገዱ የልጅ ልጆቻችን

ግድ የለም እንመን

እንመን

በሰውኛ ስሌት ውጤቱ ሲሰራ
ትውልድ ያደኸያል ያያቶች ኪሳራ
በልጅ ልጆች ዓለም
እንደጉድ ቢደለቅ ቢዘመር ቢዘፈን
አባት ይወራጫል ባ'ያቶች መታፈን
.
አባት ሆይ
.
ለልጆችህ ርዕዮት
ትላንቱን የረሳ ተስፋ ሲደራረት
ህልሜ ነው ይልሀል ያ'ያቶቹ ቅዠት
ከልጅህ አንደበት
ቋንቋ እንደዶፍ ቢዘንብ
ትርጉም ቢንፎለፎል ሺ ቃላት ቢጎርፍም
የልጅ ልጅ አግባቢ ግማሽ ገፅ አይፅፍም
ከልጆችህ ባህር
አሳ የሚያጠግቡ ለአሳ ሚስማሙ
እፅዋት ተክሎች
እንደጉድ ቢራቡ እንደጉድ ቢያብቡ
ገበታው አይሞላም ተቀዷል መረቡ
.
ግድ የለም እንመን........እንመን
.
የስኬት ክብደቱ
የምቾት አይነቱ
የነገ ውበቱ ባሻው ቋት ቢለካ
በምንም ቢሰፈር ባሻው ቃል ቢነገር
ጀግና ልጅ አትወልድም
አያቶቿን ገድላ የምትሸልል ሀገር
.
ከፎቆቹ ጥላ....
ከያስፓልቱ ገላ ሲታተም ድምቀቴ
በመስታወት አጀብ ሲጠገን ጉልበቴ
ይኸው አነበብኩት
አያቶቼ ፊት ላይ ተፅፏል ሽንፈቴ
በመኪና ብዛት
በመስታወት አይነት ሲለካ ፍጥነቴ
በግንብ አጥር መአት
በፎቆች ጋጋታ ሲሰላ ስኬቴ
ይኸው ይታየኛል
አያቴ ገፅ ላይ ተስሏል ውድቀቴ
።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።ተስሏል ሽንፈቴ!

#የግጥም_ቃና
👇👇👇
@ilovvll
@ilovvll 👈ቤተሰብ ይሁኑ

Читать полностью…

ቅኔ እና ጦቢያ

ኪዳን ያጣ ቃል

ከደጃፍሽ ነበርኩ
ቃልሽን ጥበቃ ኪዳን እየቋጨሁ፣
ረግጠሽኝ ስታልፊ
ያመታት ነፍሰ ጡር ቃል ኪዳኔን ፈጀሁ፡፡
በንቀትሽ ምጣድ የፆም ፍቅሬን ስገድፍ
ልብሽ ምን ሽቶ ነው?
ከዘላለም እውኔ ፍም እጦት የሚልፍ
ምን 'ረስቶ ቃል ሰንኮፍሽ ደንገጡር
ደርሶ እያገረሸ ባመሸበት 'ሚያድር
(ይደረው ግድ የለም)
(ይወቀው ግድ የለም)
(ልብሽ የኔ አይደለም)
በናፍቆት ስጠበስ ስሸት ቃልሽ ጠፍቶ ኑሮ እንደዘለለኝ
አካሌን ተይና
ልቤንም ተይና
ከነ ግንጥል ግብርሽ ከልብሽ ደጅ ነኝ!


መላኩ ደምሴ
t.me/kene_tobeya

Читать полностью…

ቅኔ እና ጦቢያ

"ሰው ነው በለኝ"

አንዴ!!!
እስኪ ከዘር ውጣ፣
ሰው ታቷል በረብጣ፤

ዛሬ ህይወቱን ያጣ፣
የሞት ፅዋ የጠጣ፤
ሰው ነው ባለ እጣ።
.
.
አማራ አይደለም!
ኦሮሞ አይደለም!
ትግራይም አይደለም!!!

አልያም ቤኒሻንጉል.....

የሞተው ወንድምህ፤
የጠፋች እህትህ፤
አባት ያጣው ልጅህ!

እንጂ........
መተከል አይደለም!
ወይም ያማራ ህዝብ!
ሰው! ሰው! ነው፤
ሰው ነው በየሜዳው፦
ደጅ ወቶ የቀረው....

አፈር ገፊ ህዝብ ነው.....

በዘር ፈንታ ያለግብሩ
በዘሩ! አይደል ድፍት ያለው

አትበል ወንድሜ!
ይነሳል ህመሜ
.
.
.
አንዴ! አንዴ ብቻ...
ሰው ነው! በለኝ ውስጤ ይርካ፣


ወገኔ ነው! በለኝ እና
ልቤ በአንተ ቆሞ ይመካ።


እኔ አልክድም፦
አዎ አካል ነው፣
እኔ አልምልም፦
እሱ እውነት ነው፣
አላስረዳም እሱ ኢት ነው።


አንተም እንዲህ በለኝ፦
የልቤን ዝማሬ በጆሮዬ አድርሰኝ...
.
.
.
"ሰው ነው ወንድም አለም ሌላ እንዳይመስልህ፥
ልብህ እንዳይዘነጋ ሚስጥር ግን ላስታውስህ.......

አያ ጅብ ከሌለ ውሻ አይጮህም ከቶ፣
ማደግ ብቻ አይደለም አንዳዴም ያረጃል ሰዉም ስጋ በልቶ።"

በለኝ ነቃ! ልበል ወገን አለኝ ልበል!!!

✍መክሊት (የ16ቷ)
06-5-2013
#የግጥም_ቃና
👇👇👇
@ilovvll
@ilovvll 👈 ቤተሰብ ይሁኑ

Читать полностью…

ቅኔ እና ጦቢያ

መስኮት



የቀሰቀሰኝ የሙልጭታ ድምጽ ነው –የማዳለጥ። ማታ ራት
በልተን፥ እዚያው የተውነውን ሳህን በዕንቅፍ ልቧ ሳትረግጠው
አልቀረችም። አስታውሳለሁ በዕንቅልፍ ልቧ የመሔድ ችግር
እንዳለባት የነገረችኝ እንደቀልድ ነበር።
–ደግሞ እንዳትደነግጥ በዘረመላችን ያለ ነው። እናቴም ስሊፕ
ዋከር ነበረች ሂሂሂ… ብላ ስትነግረኝ የምሯን አልመሰለኝም
ነበር።
(ዐምደኛ ለሆንኩበት መጽሔት ‘ የዘረመል ሂያጆች ‘ የሚል ርዕስ
ያለው ጽሑፍ አዘጋጅቼ የነገረችኝ ሰሞን አስነበብኩ።)
እንዲህ ስትለኝ አፏ አከባቢ የከሸፈ ፈገግታ ነበር። ወዲያው ገጿ
የተዘቀዘቀ ነጠላ የለበሰ መሰለ –ጨዋታ ቀየረች። አንድ ፊት
ላይ ይሄን ሁሉ አይነት ኪነት መመድረክ ትንሽ አይከብድም?
እያዘነች ለምን ትስቃለች? እየሳቀችስ ለምን ታዝናለች? ከእሷ
በቀርስ ሂሂሂታንና ምፅታን ኩታ ገጠም ማድረግ የቻለ ማነው?
በሰማሁት ድምጽ እንደባነንኩ እጆቼን አንሶላው ውስጥ ሰደድኩ
— አልነበረችም። መብራቱን አብርቼ ስመለከት ግርግዳውን
እየዳሰሰች ነበር። ተነስቼ ወደ አልጋው ጫፍ አቅፌያት
ተመለስኩ። ደረቴን ተንተርሳም ለደቂቃዎች በተቀመጥንበት
በዝምታ ቆየች። የፖስታ ስጎ የረገጡ የእግር ጣቶቿን አያለሁ።
ጣቶቿ የሚበሉ የፓስታ ክርታስ መስለዋል። የራስ ጸጉሯን
በቀስታ እፈትላለሁ። ኅሊናዬ ውስጥ የቢትልስ ‘ ዌን ማይ ጊታር
ጀንትሊ ዊፕስ ‘ ይፈስሳል። (ይሰማት ይሆን? ማለት ወደ ኅሊናዬ
እንደማዘንበል ብላለች) የጸጉሯ ዛሎች እንደ በገና አውታር
ናቸው። ጣቶቼ ጸጉሯ ውስጥ ሲርመሰመሱ ያላቸው ዜማ
ምንድነው?? ኖታውስ እንደምንድነው??
— ታውቃለህ… መስኮት እየፈለግኩ ነበር – መስኮት።
— መስኮት??
–አዎ መስኮት። አልገርምም??
በእንቅልፍ ልቧ ለምን መስኮት ትፈልጋለች?? . . .ግራ ቢገባኝ
ክፍሌን አየሁ። ተራ የወንደላጤ ቤት ነው። ተራ ያስባለው
የመስኮት አለመኖር አይደለም። በር እንጂ መስኮት ምን
ያደርግልኛል? እንዲህ ስል የመስኮት አስፈላጊነት ምንድነውም
ማለቴ ነው[?] ከበር የማይገኝ፥ ከመስኮት ብቻ የሚገኝ ልዩ
ጥቅምስ ምንድነው?? ማናፈሻ ነው?? ወይስ የአደጋ ጊዜ
መውጫ ነው?? ለጽዳት ከሆነ ክፍሌን እንደ ሴት አጸዳለሁ። ”
እንደ ሴት ” አባባሌ አይጥምም። ጽዳትን ሴት ላይ ታግ
ማድረግ ይመስላል። ጽዳት ግን ግርድና አይደለም። ፌሚኒስቶች
የሚታገሉት? ይህቺ ሐገር የሴት ልጅን ታሪክ ከማዕድ ቤት ድስት
ጋር ሰቅላ ስላኖረች ነው። የሉሲያውያን ታሪክ ቢፈለግ? ተደብቆ
የሚገኘው የጠለሸ የድስት ቂጥ ላይ እንደ ነቁጥ ሰፍሮ ነው።
አብዮቱ ሞር ኩሽናዊ ነው –ከዚያ አልወጣም።
” እንደ ሴት አጸዳለሁ” ስል የሚገባቸው አሉ። እንደ ሴት
የሚለው ቃል ግራ ዘመምና ቀኝ ዘመም አለው –በዚህም
ተከፍለናል። ” እንደ ሴት ” ስትል ለብዙ ይተነተናል። ” እንደ ሴት
” የሚለው ቃል የሕብረተሰቡ መስፈሪያ ነው። አንዱን ከአንዱ
የሚያነሱበት፥ የሚያነጽሩበት፥ የሚመዝኑበት –ማስተዛዘያቸው
ነው። እንደ ሴት ያደርገዋል ካሉህ –ጄንትልሜን አይደለህም። ”
እንደ ሴት ” ለወሬ አመላላሾች ነው። እንደ ሴት ከተባለ
ለአድሃሪያን ነው። እንደ ሴት ለልክስክስ ነው። እንደ ሴት –ጓዳ
ጓዳውን ለሚል ነው። እንደ ሴት ለሚልፈሰፈስ ነው –ቆፍጠን
ላላለ። የሴት ልጅ ዲሲፕሊንድ ላልሆነ የሚለጠፍ ታርጋ ነው።
ግለሰብ፥ ግሩፕ፥ ሶሳዪቲ፥ ካንትሪ –የሴት ልጆች ናቸው። እዚህ
ጋር የትርጉም መጠፋፋት አለ። ተቃርኗዊነትን በሁለት ጽንፍ
ይዘናል። እምዬ የሚባል ንጉስ የነበራት ” እናት ሐገር ኢትዮጵያ
” ልጆቿን ” የሴት ልጆች ” እያለች ስትሳደብ ማየት ምን አይነት
ሽሙጥ ነው?? በራስ ላይ ኩሸት አይሆንም??
ወንደ ላጤነት ሲባል በቆሸሸ ካልሲ ውስጥ የጠለቀ እግር
በዓይኑ ውልብ የሚልበት መዓት ሰው አለ። ቢያንስ የእኔ
የወንደላጤነት ዌይ እንደዚያ አይደለም። ይሄን ቤት ያገኘልኝ
ደላላ ሲደውልልኝ፤ ክፍሉን ለመጀመሪያ ጊዜ መጥቼ አየሁት።
ደስ የሚል ቤት ነው። ለሥራ ቦታዬም ቀረብ ይላል። ተስማምቼ
ይሆነኛል ስለው? …ቤቱ መስኮት እንደሌለው አውቅ ነበር።
ዕውር አይደለሁም። የመስኮት አለመኖር ግን የአንድን ቤት
ሙሉነት አያጎድለውም። በአዲስ አበባ የሚከራይ ቤት ማግኘት
ብቻውን ሥራ ነው። በዚያ ላይ ‘ መስኮት ያለው ‘ ምናምን
እያልኩ ብቀናጣ በእንቅርት ላይ ጆሮ ደግፍ እንደመመኘት ነው።
ሆሆ ! አስቀድሜ….
–ስፔሻሊ መስኮት ያለው ቤት ፈልግልኝ ብዬው ቢሆን ትንሽ
ዊርድ አይሆንም?
ደላላው….
–ምናልባት ካልሲውንና የበላበትን ማጠብ የማይወድ ቁናሳም
ተከራይ ቢሆን ነው… ብሎ ቢያስብ በማን ሊፈረድ ነው?
መልሶ ዕንቅልፍ እንደወሰዳት ባይም ማረፍ አልቻልኩም። ዓይኔን
ለመጨፈን ስሞክር ቤቴ ውስጥ ያጣሁትን መስኮት ኅሊናዬ
ውስጥ እያገኘሁት ተቸገርኩ። መልሼ ገለጥኩት፥ መልሼ
ከደንኩት። ትርጉም ለመስጠት ሞከርኩ።
መስኮት . . .መውጪያ መፈለጓን ያሳያል? ከምን ማምለጥ
ፈልጋ ይሆን?? . . .መስኮት. . . ከውጪ ወደ ውስጥ ማሾለኪያ
ሊሆን አይችልም? ሌላኛው ሰው ማነው? . . .መስኮት ስትፈልግ
ወደ ቀጣዩ የሕይወት ክፍል የሚያሸጋግረንን ሌላ ቤት እንፈልግ
ማለቷስ ይሆን?? ትዳር፥ ልጅ፥ ቤተሰብ???
ያን መመስረት እንደማልፈልግ ነግሬያታለሁ። እነዚህ ነገሮች ላይ
እየተሽከረከርኩ –የድካም ዕንቅልፍ ወሰደኝ።
ነግቶ አይኔን ስገልጥ ለባብሳ ጨርሳ ጆሮ ጌጧን እያደረገች
ነበር። የተኛሁበት መጥታ ጉንጬን ስማኝ ቦርሳዋን ይዛ ወጣች።
ቃል እንዳልተናገረች፥ እኔም ” ማዕዜ ትመጺ ኃቤየ? ” (ወደ እኔ
መቼ ትመጪያለሽ?) እንኳን እንዳላልኳት ያወቅኩት በሩ ከተዘጋና
ከረፈደ በኋላ ነው። በሩን ስትዘጋው እንደመጨለም አለ።

እሱባለው አበራ
t.me/kene_tobeya

Читать полностью…
Subscribe to a channel