kene_tobeya | Unsorted

Telegram-канал kene_tobeya - ቅኔ እና ጦቢያ

-

▬▬▬▬▬▬▬▬▬▬▬▬ በብራና ዘመን ቀለምን ቀምመን እንዘርፋለን ቅኔ ለፍቅር የሚሆን። #ቅኔ_እና_ጦቢያ #በብራና_ዘመን_ለምን_ተላለፍነ!! በወጣቱ ገጣሚ እና ፀሀፊ አማኑኤል ደርበው ▬▬▬▬▬▬▬▬▬▬▬▬ ያግኙን፦ለሀሳብ አስተያየት 👉 @poet_amanbot 👉 @aman0777

Subscribe to a channel

ቅኔ እና ጦቢያ

ለአንድ ዘፋኝ፣ልድት፡
ይሄ ሁሉ፣ጩኸት፡
ምንድን ነው?፣ማካበድ፡
እንደዚህ ማሸርገድ፡፡

"ጎጃም ያረሰውን፣ለጎንደር ካልሸጠ፡
ጎንደር ያረሰውን፣ለጓጃም ካልሸጠ፡
የሸዋ አባት ልጁን፣ለትግሬ ካልሰጠ፡
የሀረር ነጋዴ፣ወለጋ ካልሸጠ፡፡"
እያለች በስንኝ፣ዜማ ም'ደረድር፡
እንዳሻን እንዳ'ኖር፣ተቧድነን በሰፈር፡
ዘፈኗ አልጣመንም፣ለኛ ለሆድ አደር፡፡

"የማያረጅ ውበት፣የማያልቅ ቁንጅና፡
የማይደረቅ የማይነጥፍ፣ለዘመን የፀና፡፡
ከጥንት ከፅንስ አዳም፣ገና ከፍጥረት፡
የፈሰሰ ውሀ፣ፈልቆ ከገነት፡
ግርማ ሞገስ፡
የሀገር ፀጋ፣የሀገር ልብስ፡፡"
ከኛ በላይ አባይን፣ልቃ በማሞገስ፡
የግሏ አ'ርጋዋለች፣በዚህም ትከሰስ፡፡

"አደዋ ዛሬ ናት፣አደዋ ትላንት፡
መቼ ተነሱና፣የወዳደቁት፡
ምስጋና ለነሱ፣ለአደዋ ጀግኖች፡
ለዛሬ ነፃነት፣ላበቁኝ ወገኖች፡፡"
ወራሪ ይርዳል፣በዚህ አስፈሪ ዜማ፡
አደዋ ዛሬ ናት፣ማለቷን ሲሰማ፡
ለባንዳ'ማ ጭራሽ፣ለጆሮው አይስማማ፡፡

"አንተ ልጅ አንተ ልጅ፣አንተ ልጅ ያሙሀል፡
ልብ ይበላል እንጂ፣አይሰጥም ይሉሀል፡፡
በዚ'ች በማተቤ፣እምልልሀለው፡
ፍቅርን ካልሰጠኸኝ፣እሞትብለሀለው፡፡"
በስርቅርቅ ድምፇ፣እንዲህ እያዜመች፡
ስንቱን ደንዳና ልብ፣በፍቅር አቀለጠች?።

ስለሀገር ስዘፍን፣በቅኔ አመሳጥራ፡
ፍቅርን ስታዜም፣ሒወትን ጨምራ፡፡
ለኛ አይመቸንም፣እንዲህ ያለ ነገር፡
ጥበብን ማበርከት፣ትውልድ የሚሻገር፡፡
ማታ የሚረሳ፣ጠዋት አስጨፍሮ፡
ይህን ነው የለመደው፣የኛ የአድማጭ ጆሮ፡፡

እና ለዚ'ች ዘፋኝ፣ማከበድ ምንድን ነው?:
ለንግስቷ ልደት፣ይህ ነው የሚገባው?:
እጅጉን እናካብድ፣ማካበድ ያንሳታል፡
ስሟም እጅግ አየው፣ብዙ ይገባታል፡፡

ሙዚቃ መልካም ልደት፡፡
✍ (አድናቆት ክፍሌ የብርቱካን)

#የግጥም_ቃና
👇👇👇
@ilovvll
@ilovvll 👈ቤተሰብ ይሁኑ

Читать полностью…

ቅኔ እና ጦቢያ

ደመና

በአፍላነት ሸብቶ ልጅ እያለ ገና፣
ሲደካክም ጠቁሮ ሲጫነው እርጅና፤
ለራሱ እያነባ ይሞታል ደመና።

©ያብባል ጌትነት

@kene_tobeya

Читать полностью…

ቅኔ እና ጦቢያ

( ዝምታዬ መሀል)
:
ከአዲስ ቀን ጅማሪ
ደግሞ እስከ ማለቂያው
ነፍስን በምታርድ…ስጋን በምታ‘ቀፍ
ስንክሳር ባጠራት
ጥልፍልፋም ህይወት
ሐሰት ተሞካሽቶ…ሀቂቃ እንዲነቀፍ
:
:
ሲተጋ የሚውል
ዕልፍ አውርቶ አዳሪ
አሸን ተናጋሪ…በሞላበት መንደር
ልሳን ሳያወጡ
በዝምታ ውሎ… በዝምታ ማደር
:
:
ባይቻል ቢከብድም
:
:
ሳወራ አትናገር
ዝም ስል በል በርታ…እያለ ‘ሚመክረኝ
ከተናጋሪ ዓለም
በዝምታ አክናፍ …ዝም አ‘ርጎ ‘ሚያበረኝ
:
:
እኔነት ከምለው
ከነፍሴ ሸራ ላይ
ህመም የተኳለ…ሰላምን የሰለ
ዝምታዬ መሃል
ዝም ብዬ ምሰማው…ብዙ ዝምታ አለ!!
:



ዬ… ሆይ እወድሃለሁ♥!!
…………………………………………**
[ ዳግም ሔራን #ሰው_ፍቅር_ናፍቆት]
Join and share
@heranawi
@heranawi
@heranawi ይቀላቀሉን🙏🙏

Читать полностью…

ቅኔ እና ጦቢያ

አንቺ እየሩሳሌም
የዳዊት ከተማ
የህዝቦችሽ ብርሃን
መጣልሽ በግርማ
-
ሆሳዕና በዓርያም
እያሉ ዘመሩ
ህፃናት በየሩሳሌም

እንኳን አደረሰን!

-
#የግጥም_ቃና
👇👇👇
@ilovvll
@ilovvll 👈ቤተሰብ ይሁኑ

Читать полностью…

ቅኔ እና ጦቢያ

#ላለመሰበር

ገና ሌት ነው ስትወጭ
ስንብት ቃልሽም የለ
በለጋነት ለፈጠርሽው
የፀሀይ ገፅ አልተሳለ

ይወጋል አንቺው እያደር
ከእልፈትሽ የቀረው ስንጥር

ጣርሽ ሲገን ያልገባው ክፋይሽ ዘመን በሳው
ወደ ኋላ ሲክለፈለፍ ያረፈበት አሁን ከዳው

እሰይ!! ይሄም ይፈተሽ
ጠሀይ ያልነካው ገላ ታሽቶ አጥንቱ ባይፀና
ከመዳፍሽ ነው እውነት ወይስ ከሌት ደመና

ብቻ ትናንት አሁን ነው
መሸሽ አይሻም ካንቺ ማለፍሽን አያጎላም
ባክኖ ሸርተት እያለ ለስብራት አያደላም።

አማኑኤል ደርበው

t.me/kene_tobeya

Читать полностью…

ቅኔ እና ጦቢያ

ሰም እና ወርቅ
" ዋጋችን ስንት ነው? "
#ሐሙስ_ሚያዚያ_7 በብሔራዊ እንገናኝ!!
Join and share………………………👇
@heranawi
@heranawi
@heranawi

Читать полностью…

ቅኔ እና ጦቢያ

መቼ ነው ሚፈታ!?

ቀመር ተለውጦ ፣ ሲሄድ መንገድ ዞሬ
ስጋዬን ቀልቤው ፣ ለሰው በላው አውሬ
እንደ ፎቅ መስታወት ፣ ፊቱ አቅለጥልጦ
የኔን ወዝ ደቅኖ ፣ እንደሸንኮር መጦ
የሱ የደም ግባት ፣ ወዘናው አማረ
ኪሎዬን ቀንሶ ፣ ኪሎውን ጨመረ።

ልክ እንደ ቀይ ባህር ፣ የየብስ ላይ ስፋት
ልክ እንደ ሰሃራ ፣ የሰማይ ስር እሳት
ልክ እንደ ራስደጀን ፣ የመሬት ከፍታ
ልክ እንደ አፋር ዳሎል ፣ የምድር ዝቅታ
ፋፍቶ ቢጠበድል
ረዝሞ ቢንቀዋለል
ቢወጠር ቢያስካካ
'ማን ሊነካኝ!' ብሎ ፣ ከግዜር ቢለካካ !!
ስንቱን በጉያዋ ፣ አፍና እንዳሊያዘች
ዛሬስ ከብዷት ኖሮ ፣ ምድሪቷም ቃተተች።

ታዲያ…
እኮ ታዲያ…!!
ሰሚ ሸንጎ የለሽ ፣ እኔዋ አህያ
ያው እንደጣለብኝ
እንጀፈረደብኝ ፣ ብቻዬን አውላላ
የጫነብኝ ቀንበር ፣ ማነቆው ሳይላላ
የዚን ጥንብ መዓት፣
ሸክም ተሸክሜ ዝንት አለም ልኖርነው !?
ወይስ ደግሞ ዳግም…
አንድ ቀን ቀን ወቶ
ያ'መታት ሸክሜን አስኪፈታልኝነው !?


(ከመሠለ ከልካይ) መጋቢት ፳፻፲፫ ዓ.ም

Читать полностью…

ቅኔ እና ጦቢያ

🔥የ ክብሪት ልጅ


ለሰጠሁት መንሻ ላኖርኩት ከፍታ
የወለድኩት ጀግና የወለድኩት ሽፍታ
የለገሰኝ ምላሽ የቸረኝ ውለታ
ከናቱ ሆደ ወጥቶ እናቱን ሚመታ
የክብሪት ልጅ መሆን ንድድ ያለው ለታ
🔥
🔥
አንዴ በዲሞፍተር ሁለቴ በሞፈር
ተኩሶ ልቤ ላይ አርሶ የኔን አፈር
ወዛም ገፅታዬ እንዳልሆነ ሲቀር
ተጋዳላይ ትግራይ ተጋዳላይ ሃገር
ሴት ልጅሽ ትደፈር የወንድ እድሜ ይጠር
🔥
🔥
ቅባት ሰርጎት እሱ ብመስለው አመዳም
በጉንፋኑ ጊዜ እንዳልሆንኩ ጤናዳም
ቆጥሮኝ እንደ እሾህ ፈርዶኝ እንደ አጋም
የሳቀለት ጥርሴን እያለ ልጋጋም
የደረቀው ምድሩን አጠጣው የኔን ደም
🔥
🔥
እንዳልሆንኩት ሁሉ የድንበር ላይ ታቦት
ህዝቤን እንደ ሰንጋ ልጄን እንደ ጠቦት
ከሰሜኑ ባህር የጅብ ወዳጅ ከቦት
አርዶ ይበላኛል ሲጠግብ ርቦት
🔥
🔥
ጄሪካን ባዘለ የቀይ ባህር ቁምጣ
አጋድሞኝ መደብ ላይ ከላይ እታች ጣጣ
ተራውጦ ሲጠግብ ነፍሴ እንድትወጣ
ብና ጠጡ ጓዴ ሰይፉን ይዞ መጣ
🔥
ቢቆጣ ጎፈሬው በራሴው መላጣ
ወቶልኝ ነው እንጂ ያልመረጥኩት እጣ
አይዞህ ባይ ወገኔን እንዴት አንድስ ልጣ
🔥
🔥
አለሁ የሚለኝስ ከናካቴው ይጥፋ
የምሳሌው ክርኖች በላዬ ሲከፋ
አይቶኝ እንዳላየኝ ቢያልፈኝ አልከፋ
ወገብ መቸበቡ ያስቆረጠኝ ተስፋ
🔥
🔥
ከሆዴያወጣሁት ከጎኔ ተንፋቆ
በፈጠረው እሳት ከትናንቱ ደምቆ
የተላከውን ቃል ከጉያው ሸምቆ
ጁን_ ጁን_ እያለ ከመራው ሰው ልቆ
በሳቅ ፈካ ፊቱ መደብደቤን አውቆ
🔥
🔥
በልጆቼ እሳት እኔው ከጠፋሁኝ
ምናለበት ታድያ
ወይ ያኔ ወይ ያኔ እናቱን ባልሆንኩኝ

✍✍tomi

ከወደዱት ለወዳጆ ያጋሩ:-
@bewketuseyoum19
@bewketuseyoum19

Читать полностью…

ቅኔ እና ጦቢያ


☀️ባቦ 💧 ጋያ☀️

ታዘብኳት መንፈሴን ፣ ሆና ከጣራው ስር
ክንፎቿን ዘርግታ ፣ ለመብረር ብትሞክር።

ወደዳር ወጥቼ
ከትንፍጉ መሃል
ትንፋሼን አውጥቼ
አየሩን ስቀበል
በሰመመን ቃኛ
ቁጭ ብዬ ስመሰጥ ፣ ሳስብ ሳሰላስል
ቀዘፍኩት ባህሩን ፣ ሃይቋ ላይ ሆኜ
እንደሳቄ ሁሉ
አለም እንዳለፈች ፣ ውስጤን አሳምኜ።



(ከመሠለ ከልካይ)

ይቀላቀላቀሉን፦
@kene_tobeya
@kene_tobeya

Читать полностью…

ቅኔ እና ጦቢያ

ሁሉንም ትቻለሁ፥
አቅሜ ደክሟል አንዴ፣
ቀና ልል ስታገል፥ ከጠፋ መንገዴ፤
ተይው እርሽው ይቅር፥
በ'ሬት ተበርዟል፥ መፈጠር ጣዕሙ፣
የህይወት ስራስር፥
የመኖር ሽፋኑ፥
ሀዘንን ከትቧል፥ ሞት ሆኗል ቀለሙ...

አማኑኤል ደርበው(አማን)
t.me/kene_tobeya

Читать полностью…

ቅኔ እና ጦቢያ

ዛሬ በግሩም ቡና
ሸጋ ቆይታ ይኖረናል!

ሁላችሁም ተጋበዙልኝ🙏
Join and share…………………👇👇
@heranawi
@heranawi
@hetanawi

Читать полностью…

ቅኔ እና ጦቢያ

የግጥም ብሂል

(ከመሰለ ከልካይ)

ሁሉም ነገር የሚመራው ወይም የሚመራበት ሕግ አለ። ለምሳሌ ጊዜ። ጊዜ በተወሰነ ስልተምት የተቀኘ ፣ ማታ እና ቀን በሚባሉ የአንድ ሙሉ ቀን እኩሌታዎች የተከፈለና ሁሌም በቋሚነት ክረምት ከበጋ ሳይነጥፍ እንደሚፈስ ጅረት እራሱን የቻለ ሚዛናዊ ፍሰት ያለው ቀመር ነው። ስለዚህ ጊዜ የሚመራበት ህግ ጥብቅ እና ሕያው ነው።

ግጥምም ሲፃፍ ወይም ሲደረደር ይበልጥ ስሜትን የሚጭር አንዳች ሃይልን እንዲጎናፀፍ ፣ መሰረታዊ የስነግጥም ሕግጋትን የተከተለ መሆን አለበት።

ለምሳሌ ምት እና ምጣኔን አንስተን ባጭር እንመልከት። ስለምት ካነሳን ስለቀለም ማንሳታችን የማይቀር ጉዳይ ነው። (ከዚህ በፊት የቀለምን መሰረታዊ ሕጎች ከግጥም አንፃር ለማየት እንደሞከርን አይዘነጋም ።) አንድ ሙሉ ቀን በእኩል 12 ሰዓቶች ንጋት እና ፅልመት ተብሎ ለሁለት እንደሚከፈል ሁሉ ግጥምም በሐረጉች ውስጥ ባሉት እኩል የቀለም መጠኖች ይከፈላል።

ምት ደግሞ እንደልብ ትርታ ሁሉ ዋናውና እይቀሬው የግጥም ባህሪ ነው። ከግጥም የሚፈለገውን ምት (ሚዚቃዊ ቃና ) ማግኘት የሚቻለው በሀረጎች ውስጥ ባሉት የቀለም ሜትሮች መሰረት ነው። ስለዚህ ግጥም ሲፃፍ ምቱ የጠበቀ እንዲሆን ፣ በተወሰነ የጊዜ ፍሰት ውስጥ በአንድ ትንፋሽ ተነበው የሚያልቁ ሕረጎችን በያንዳንዱ ስንኝ ውስጥ ማዋቀር ሲቻል ነው። ይህ ካልሆነ ግጥሙ ዋናው እና አይቀሬ ባህሪውን ያጣል ማለት ነው።

ባጠቃላይ አንድ ግጥም ሲፃፍ በጥቂቱ የሚከተሉትን መሠረታዊ ፅንሰሃሶቦችን ማካተት ይኖርበታል።
✅የቀለም ምጣኔውን የጠበቀ ፣
✅ምት ያለው ፣
✅በዘይቤ የተቀኘ ፣
✅እምቅ እና ምስል ከሳች የሆነ… ወዘተ።

"ግጥም ሶስቱን መሰራታዊ የግጥም ባሕሪያትን (ምጣኔ ፣ ምት እና እምቅነት) እስካሟለ ድረስ እዲህ መሆን አለበት ወይም እንዲያ መሆን የለበትም ተብሎ በድንጋጌ መወሰን አይቻልም። ይልቁንስ ደራሲው የራሱን የፈጠራ ችሎታ አክሎበት በጥንቃቄ በተመረጡ ቃላት ፣ በክረምት ደጃፍ ስር እንዳቆረች ትንሽ ኩሬ ያለውን ጥልቅ ሃሳብ አንደ ቀይ ባህር አግዝፎ ፣ እንደ ምሽት ጨረቃ ጮራ ያለችውን ረቂቅ ስሜት እንደቀትር ፀሃይ አድምቆ የማሳየት ጥበብ ነው።"
🗝ፀጋዬ ገ/መድሕን "እሳት ወይ አበባ"
🗝ሃሪይ ሾው(Harry show) "Dorway to poetry"
በተሰኙት መፃፎቻቸው ከትበውት እናገኛለን።

ስለዚህ አንድ ሰው አንድን ግጥም አንብቦ ማስተካከያ ወይም እርማት ለመስጠት ብቁ ነው ለመባል የግጥምን 'ሳይንስ ' አብጠርጥሮ ማወቅ አለበት።

ለምሳሌ:-

፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨
ጨመዳ

ጨመዳ፣
የዱሩ ባለጦር የግልቢያው
ራስ ሜዳ
የአምባው አንጃግሬ የቁንዲያት ባለዳ
ና እንጂ በማለዳ!
ናፍቀው ቆዝመዋል ጓዳና ጎርጓዳ።

ሰው አየኝ አላየኝ ብለህ ሳትገላምጥ
የዱሯ ላምህን ና እንጂ እናማምጥ፤
ቢያዩህም ኮራበል እንዳትደነግጥ
ከቶ የምን መፍራት ለማንም እርምጥምጥ፤
ጨለማስ ለምንህ በቀን ይሻልሃል
የፅልማሞት ጉቶ ጠልፎ ይጥልሃል።

በልና እንጂ ወንድሜ!
ደሞ መጦቅ ፈርቶ ለዬትኛው እድሜ?
ምን ይራቅ ምንይጠር ሁካት ሳትፈጥር
ፈጠን ፈጠን ብለህ ከየጋጣው ስርስር
የቤቱን ውሃ ልክ አርገው ቆፈር ቆፈር፤
ምንስ ቢጓጉጥህ የአምባው ሰረሰር
የቁንዲያት ባለዳ አይደለህ ባለጦር!?

©ከቅኔ_በጡሊ_መሰለ_ከልካይ_ገፅ174
፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨

የይህን ግጥም ዋቢ በማድረግ…

"ግጥሙ ምት አለው ወይ? " (ይህን ለመመለስ…የቀለምን ሕግ ማወቅ አለበት ፤ በተለይ ሳድስ ፊደሎችን በተመለከተ…)

"ግጥሙ ምስል ለመከሰት ፣ ረቂቁን ለማግዘፍ ፣ ድብዝዙን ለማድመቅ ፣ የማይዳሰሰውን እንዲታሰስ ለማድረጎ …እንዲቻለው ዘንድ ምን አይነት የፈጠራ ዝንባሌ ተስተውሎበታል?" (ይህን ለመመለስ… ዘይቤን ከነአይነቶቹ ማወቅ አለበት።)

"ግጥሙ እምቅ ነው አይደለም?" (ይህን ለመመለስ…ፍካሪያዊ ፍቺ ያላቸውን ብዙ የአማሪኛ ቃላት ማወቅ አለበት። እንደገጢሚውም ሁሉ የምርጥ ቃላት አዳኝ መሆን አለበት።)
እና ብዙ… ሌላ… ሌላ… ሌላም…


#ዋሕድ

ለግጥም አፍቃሪያን በሙሉ ያጋሩ።
የሚከተለውንም ሊንክ በመጫን ይቀላቀሉን።
👇👇
@kene_tobeya
@kene_tobeya

Читать полностью…

ቅኔ እና ጦቢያ

~አንቺ ምን አለብሽ!~
.
.
.
ጠለል የለሽ ልቤ ፥ አንቺን አንቺን ብሎ
ባ'ሳብ ሰረገላ ፥ ሄዶሽ ተከትሎ
በፍቅርሽ ቢለከፍ ፥ አንጅግራው ነሁልሎ…

አንቺ ምን አለብሽ
ከቤትሽ ቁጭ ብለሽ
እኔው አጣጥሬ
ልሙትልሽ እንጂ፣
ሞግጌ ጠውልጌ
በፍቅርሽ አዋጂ።
.
.
.
ሰወች መሃል ሳለው ፥ እራሴን አግልዬ
በባይተዋር ኑሮ ፥ ባብድ ጨርቄን ጥዬ…

አንቺ ምን አለብሽ
ከቤትሽ ቁጭ ብለሽ
ያመለከሽ ልቤ
ይባክንልሽ እንጂ፣
ያልታደለው ፍጥረት
ባ'ርባ ቀኑ ፍርጂ።
.
.
.
የፍቅርሽ ነበልባል ፥ የቁም ስቃዩ ጭንቅ
ከድስኩሩ አዘቅት ፥ ጥሎኝ ከመቀመቅ
ባልበላውት እዳ ፥ ታስሬ ብማቅቅ…

አንቺ ምን አለብሽ
ከቤትሽ ቁጭ ብለሽ
የ'ናት ያ'ባትሽን
ፀጉር አበጥሪ፣
እኔን ፈርዶብኛል
የፍቅር ፈጣሪ።
.
.
.
ፀአዳ አይኖችሽ ፥ ባይኖቼ ተስለው
አርቄ እንዳላይ ፥ ታላንቺ ሌላ ሰው
ልቤ ቢበረግግ ፥ እስኪርቀው ጥላ
ማያት እንስት ሁሉ ፥ አንቺን ተመስላ…

አንቺ ምን አለብሽ
ከቤትሽ ቁጭ ብለሽ
ሚስኪኗ እናቴ
ትጨናነቅ እንጂ፣
በእንጭጭ ሲቀረው
ያላት አንድ ልጂ።


በፍቅርሽ አበሳ ፥ በናፍቆትሽ ለቅሶ
የአልጋዬ ትራስ ፥ አንሶላው በስብሶ
ብርድ ብርድ እያለኝ ፥ በሕመም ስቃትት
አይኔም ሳይከደን ፥ በስቃይ በጭንቀት
ሌትም እንቅልፍ የለኝ ፥ እንዲው ነው ሚነጋ
በፍቅርሽ ሰመመን ፥ ስዞር ቆላ ደጋ።

💔 💔
🕴🕴🕴🕴🕴🕴🕴
🕴🕴🕴🕴🕴🕴🕴
🕴🕴🕴🕴🕴🕴🕴
💔 💔

አሁንስ ብቻዬን ፥ አቅቶኛል ፍቅርሽ
ማርከሻውን ስጪኝ ፥ ቆሚያለው ከደጅሽ፤
የመሳፍንት ሃረግ ፥ ያለብሽ እመቤት
የጌቶች ልጅ ሆነሽ ፥ የጉልት ባለቤት
ደሃዋ እናቴን ፥ ንቀሽ ባትፈሪ
አሻፈረኝ ብለሽ ፥ ብታንገራግሪ
ወዮልሽ በሗላ፣
የድህነት አምላክ ፥ ያይሻል ፈጣሪ።


ከመሰለ ከልካይ
#ከወደዱት_ለወዳጆ_ያጋሩ
👇👇
@kene_tobeya
@kene_tobeya

Читать полностью…

ቅኔ እና ጦቢያ

ትላንታዊ ዝለት!
ገጣሚ:አንባቢ…ዳግም ሔራን
( #ሰው_ፍቅር_ናፍቆት )
:
:
Join and share……………👇👇
@heranawi
@heranawi
@heranawi

Читать полностью…

ቅኔ እና ጦቢያ

የግጥም የቀለም አመጣጠን

ግጥም የቀለም ምጣኔው (የመነሻና የመድረሻ ሀረጎቹን (ዘመናዊ ግጥም ካልሆነ) ለማንበብ የሚወስድብን ጊዜ) እኩል መሆን አለመሆኑን ማወቅ የምንችለው በያንዳንዱ ስንኝ ውስጥ ያሉትን የሃረግ ቀለሞች ቁጥር ማወቅ ስንችል ነው። በአይን አይተን ብቻ ስለምጣኔው እርግጠኛ መሆን አንችልም። መገመት ግን እንችል ይሆናል።

ቀለም ፦ ተነባቢና አናባቢ ቃላት ተከታትለው በመምጣት የሚፈጥሩት የቋነቋ መዋቅር ነው።
ወይም ስድስቱ የአማሪኛ አናባቢዎች ፣ ማለትም |ኧ| |ኡ| |ኢ| |ኣ| |ኤ| |ኦ|(ከ'እ' በስተቀር) ለብቻቸው በመቆም የሚፈጥሩት ብያኔ ነው።

አበይት የቀለም ህጎች
(የሳድስ ሕጎች
)

፩. ሳድሶች (ስድስተኛ የአማሪኛ ፊደሎች) በቃል መጀመሪያ ከመጡ ሁሌም እንደቀለም ይቆጠራሉ። ጠብቀው ስለሚነበቡ።

፪. ሳድሶች በቃል መጨረሻ ከመጡ እንደቀለም አይቆጠሩም። ላልተው ስለሚነበቡ። ይህ ሕግ ግን አንዳንድ ጊዜ ሊሻር ይችላል። ለምሳሌ በስንኝ መድረሻው ሃረግ በመጨረሻው ቃል መደምደሚያ ሆሄ (ቤት መምቻ ወይም መድፍያ ፊደል) እንደየደረሲው ፍላጎት እና የሃረጎቹ ምጣኔ መሰረት ቀለም የሚሆኑበትም ሁኔታ አለ።

ምሳሌ፦
እሷ ብትወደኝ ፣ ተያይተን ድንገት
ልቤ ተረታላት ፣ እኔም ወደድኳት።

🗝እንደቀለም የተቆጠረው '/ '
🗝ቀለም ያልሆነው '×'

ሀረጎቹ በቀለም ሲተነተኑ
👇👇
/ / / / / / × / /× /× /× / /
እሷ ብትወደኝ ፣ ተያይተን ድንገት 6/6
/ / / / / /× / / × / / × / /
ልቤ ተረታላት ፣ እኔም ወደድኳት። 6/6
ግጥሙ በሃረግ 6 ቀለም አለው። (የወል ቤት ነው።)
ከላይ እንደምንመለከተው 'ት' ሳድስ ቢሆንም በቃላቱ ውስጥ ተረግጦ ነው የተነበበው። ስለዚህ እንደ ቀለም ይቆጥራል።
በተጨማሪ ሳድሶች በሕግ '፫'👇👇 መሰረት ቀለም የሚሆኑበት ሌላም መሰረት አላቸው።

፫. ሁለት ሳድሶች በአንድ ቃል ውስጥ ተከታትለው ከመጡ የመጀመርያው ሳድስ ድምፅ በቀጣዩ ስለሚዋጥ ሁልጊዜም ሁለተኛው ሳድስ ጠብቆ ስለሚነበብ እንደቀለም ይቆጠራል።

#ዋሕድ

የቀለምን ፅንሰሃሳብ ማወቅ ለሚገባቸው የስነፁፍ ቤተሰቦች ሁሉ ያጋሩ።
👇👇
@kene_tobeya
@kene_tobeya

Читать полностью…

ቅኔ እና ጦቢያ

በፍቅር ሱባኤ
በረሀብ በረሀ በስጋ ጠውልገን
በፍቅር ሰማይ ስር ከሚያፈሰው ዝናብ በመንፈስ አብበን
ከንፈራችን ደርቆ አየተዛዘንን
አናርሰው ነበር እየተቃመስን
እስትንፋስ ሳይቀረን እየተዋዋስን

ከቤታችን ጀርባ ባለች ትንሽ ደብር ከሚካኤል እቤት
አንዳችን ላንዳችን ስንፀልይ ውለን
ባገኘናት ጉርሻ አፋችን አብሰን
በፍቅር ሱባኤ ደስተኞች ነበርን

ትዝ ይልሻል ወዴ?
ክረምትና በጋን
የአልጋችንን ቦታ ሳንቀይር ረስተን
ሁሌ በጋ መስሎን
ዝናብ የጣለ ቀን
አልጋችን እርሶ እረጥቦ ገላችን
ተቃቅፈን ያደርነው እያንቀጠቀጠን
ለሌላ ያየ ሰው የችግር ቢመስልም
ለኛ ፍቅር ነበር

ደግሞ ለበዓል ቀን ፊታችን ሲያበራ
ለስላሳ እንጀራ በወጥ ተፈትፍታ ቤታችን ስትገባ
ሙቀቱ ሲያጅበን የጠጅ እና የጠላ
ሰው ሆንን እያልን
አቅም በአንድ ቀን እንደተላበስን
ስንጮት ያደርነው ቀኑ እስኪነጋ እንቅልፍ ሳየጥለን
የዛች ቀኗን ማግስት ከአልጋችን ወለን
ላንነሳ ምለን

ያሳለፍነው ሁሉ እውነት ትዝ ይልሻል
አውቃለሁኝ ውዴ አዎን አስታውሰሻል
ከቤታችን መሀል የጣልሽው ትዝታሽ አግኝቶ ነግሮሻል
ድሮስ ያለ ፍቅር አሁን ያለሽ ሁሉ መቼ ይጠቅምሻል
ልብሽ ከኔ ኋሏ ብዙ ጠይቆሻል

ያኔ ግን
ከኔ ጋራ ሳለሽ ደሀ እንኳ ብኖንም
ቤታችንን በግንብ ባናንፅ ባናሽቆጠቁጥም
ሆዳችን ለሁሌ ጠግቦልን ባያድርም
የኔና ያንቺ ህይወት አንድ ቀን ተሳስቶ አማሮን አያውቅም

✍ @abelyohannes12


#የግጥም_ቃና
👇👇👇
@ilovvll
@ilovvll 👈ቤተሰብ ይሁኑ

Читать полностью…

ቅኔ እና ጦቢያ

እቀናለሁ አዎ
አጥንት ያነቅዛል ሲል ባይገባንም ውሉ
ቅናት ይሉት ነገር ተሰጥቷል ለሁሉ፡፡
አዎን እቀናለሁ
ያልቀኑበት ነገር ሲነጠቅ ስላየሁ፡፡
ብቻ ወድሽ የለ እኔ ምን አውቅና
ራሴን የማገኝ በሆንሽው ስቀና፡፡
ይኸውልሽ ጉዴ
ከከንፈርሽ በታች
ባለው ጥቁር ነጥብ ስቀና እያየሽኝ
እንደማላቅ ነገር ማርያም ስማኝ አልሽኝ፡፡
ለምን
ለምን ከንፈርሽ ጋር
ለምን አንቺን መርጣ
ለምን
ለምን
ለምን
ለምን ሳመችሽ ስል ብዬ ደፋ ቀና
አትፍረጂ ፍቅሬ
አፍቃሪ አይመርጥም በፍቅሩ ሲቀና፡፡
(እኔ ምን አቃለሁ
ብቻ ወድሻለሁ!!)

ኤሊያስ ሽታኹን

t.mt/kene_tobeya

Читать полностью…

ቅኔ እና ጦቢያ

ሃዘኔ ሲወለድ

ሃዘኔ እንደተወለደ በክብካቤና በፍቅር እየኮተኮትኩ አሳደግሁት።
ሃዘኔም ቀስ በቀስ እንደማንኛውም ህይወት ያለው ፍጡር አደገ። ጠንካራና መልከመልካም እንዲሁም ደስተኛ ሆነ።
እኔና ሀዘኔ በጣም እንዋደዳለን።በዙሪያችን ያሉትንም እንወዳቸዋለን።ውዴታችን የሚመጣው ሃዘን ደግ ልብ ስላለውና የእኔ ልብ ደግሞ ለሀዘን ቅርብ በመሆኗ ነው።

እኔና ሃዘኔ ተቀምጠን ስናወጋ ቀናትና ሌሊት ሳይታወቁ ያልፋሉ።ሃዘኔ አንደበተ -ርቱዕ ሲሆን እኔም ከርሱ ጋር በመሆኔ አንደበተ -ርቱዕ ሆኛለሁ።

ሁለታችን ስናዜም ጎረቤቶቻችን በመስኮቶቻቸው በኩል ብቅ ብለው ያደምጡናል።ግጥምና ዜማችን ማራኪ በመሆኑ ሰምተው ይደሰቱብናል።

እኔና ሃዘኔ በእግራችን ስንጓዝ የመንገደኞች ዐይን እኛ ላይ ያርፋል።ስለእኛ መልካም ቃላት ሲያወሩ ይሰማናል። ደግሞም የሚቀኑብን ሰወች ነበሩ።
ምክኒያቱም ሃዘን ማንንም የሚያስቀና መልካም ነገር በመሆኑ እኔም ስለምኮራበት ነበር።

አሁን ግን ሃዘኔ ሞተብኝ።እነሆ እኔም ብቻየን ማሰላሰልና መብሰክሰክ ጀመርኩኝ

አሁን በምናገርበት ሰዓት ቃላቴ ለጆሮዬ ይከብዱኛል።ሳዜም የሚሰማኝ ጎረቤት የለም።በጎዳናው ስራመድ የሚያየኝ የለም

ስተኛ ብቻ እንዲህ የሚሉ የሃዘን ቃላት ይሰሙኛል:_ "አያችሁት - እዛ ጋር ሃዘኑ የሞተበት ሰውዬ ተኝቷል።"

ካህሊል ጂብራን
t.me/kene_tobeya

Читать полностью…

ቅኔ እና ጦቢያ

አለም ጨረቃ ላይ ለሚኖረው ይዞታ በሚፎካከርበት በዚህ የ 21ኛው ክፍለዘመን #ኢትዮጲያውያን ሁሉን ነገር በዘር መነፅር እያየን ሮጠው ያልጠገቡ <ህፃናት> እና የሶቪየት ህብረት እንደፈራረሰች ባልሰሙ አዛውንቶች መጫወቻ ሆነን መቅረት የለብንም!!!

ወጣቶች፣ ማስተዋል የጀመራችሁ ታዳጊ ህፃናት እንዲሁም ሙሉ ኢትዮያውያን በሙሉ
እባካችሁ እየሞቱ ያሉት ዜጎቻችን ናቸው!

#ጥቁር የአፍሪካ ፈርጦች ናቸው!!!

ምንም የማያውቁ አፈር ገፊ ወገኖቻችን ናቸው!
እነሱም መስዋዕትነት የተከፈለባቸው ሰዎች! ናቸው!!

እኔ አምላክ ስለፈጠረው ሰውነት እንጂ
አካላት ስለፈጠሩት ብሄር አይመለከተኝም!

እና እባካችሁ አማራዎች ተገደሉ ብለን ጥግ አንያዝ ድምፃችንን እናሰማ ቀን ምን ይዞ እንደሚመጣ አናውቅም ሁላችንም ወረፋችንን የማናውቅ ሰልፈኞች ነንና
ባለተራ ሳንባል ዲሞክራሲ ፈሶበት ፍትህ የጎደለበት ሀገር ለትውልድ ጥለን ተወቃሾች እንዳንሆን!
#አስታውሱ ታሪክ መቼም ቢሆን አይረሳንም መቼም!
የዛኔ #ተወቃሽም #ተሞጋሽም የመሆን ምርጫው የኛ ነው የኛ ብቻ!!!

✍መክሊት የ16ቷ ነበርኩኝ

💚ሰላም💛ለሀገራችን❤ ይሁን
💚ሰናይ💛ምሽት ❤

@ilovvll
@ilovvll 👈 ቤተሰብ ይሁኑ

Читать полностью…

ቅኔ እና ጦቢያ

ይሰማኛል...

ያቃጭላል ድምፃቸው
ያለመቆም ይንጫጫል
ታቁሮ ደም ለመብጣት በሹል ጎኑ ይሳላል

እረፍት አልባ
የግፍ ጩኸት
በበላዩ ስንኩልኩል ፍርድ
በደም አድፎ የትም ሲነጉድ

ያቃጭላል
ሆድ ይቆርጣል
ልብ ይበሳል
ያጣጥራል
በሰው ምግባር ሰው ይረክሳል።

አማኑኤል ደርበው
t.me/kene_tobeya

Читать полностью…

ቅኔ እና ጦቢያ

ዛሬ ይመረቃልና #እንዳትቀሩ ተብላችኋል
በሙሉዓለም የባህል ማዕከል
ቴቄል
#አዲስ_መጽሐፍ_በሦስት_ደራሲያን
ርእስ ፦ ቴቄል
ይዘት ፦ ወግጥም
እልፍ ኃይል ታድዬ፥ ሙሉ ቢሆን ቤቴ፣
አንቺን ካላደለኝ፣
በሚዛን ሲሰፈር፥ባዶ ነው ሕይወቴ።
ዳንኤል ከበደ
ትዝታ ያዘለው፥
ይኼ ከንቱ አካሌ፥ ድካምን አያውቅም፣
ዘመን ብጠብቅህ፥ የቱም ለኔ አይደንቅም።
ሙሉወርቅ ተስፋ
አትመን ያልሽኝን
አምኛለሁ በቃ፣
ላልጨለመበት ሰው
ምኑ ናት ጨረቃ?
አማኑኤል ደርበው

t.me/kene_tobeya

Читать полностью…

ቅኔ እና ጦቢያ

ወህኒ

(ይስማዕከ ወርቁ)

ካቻምና በመስቀል ድፎ ባርኬአለሁ።
ዘንድሮ በጩቤ አጥንት ወግቻለሁ።

ለምን እንዳትሉ፤
በቃ ሆነ በሉ፤
የሰው ልጅ ጠባዩ የሰው ልጅ አመሉ ።

አምና ደግ ነበርኩ ፣ ክፉ ሰው ዘንድሮ
ትናንትና ምሁር ፣ ዛሬ ግን ደንቆሮ ።

ለምን እንዳትሉ ፤
በቃ ሆነ በሉ ፤
የሰው ልጅ ጠባዩ የሰው ልጅ አመሉ ።

መሆን አምሮኝ ያውቃል፤ ፖለቲከኛ ሰው ፣ ኃያል የጦር መሪ ፤
ተመኝቼም ነበር ለመሆን አዝማሪ ፤
ገጣሚ ለመሆን ስንኝ ቋጥሬአለሁ ፤
ደራሲ ለመሆን ተስዬም አውቃለሁ ፤
ሞዴል አርሶአደርም ለመሆን ፈልጌ ፣
አስጠምጄ ነበር ከ 4 ኪሎ ግርጌ ።
ኢንጂነር ዶክተርም ልሆን ነበር እኮ ፤
እንደዚህ ሆንኩ እንጂ ነገር ሌላ ታኮ ።

ለምን እንዳትሉ፤
በቃ ሆነ በሉ ፤
የሰው ልጅ ጠባዩ የሰው ልጅ አመሉ ።

አንድ ሰው አንድ ነው ከንግዲህ አትበሉ ፤
የሰው ልጅ ወህኒ ነው ፤
እልፍ አዕላፍ ሰዎች ታስረው የተጣሉ ፣
መውጫ አጥተው ነው እንጂ፣አንድ ሰው ውስጥ አሉ።


✍️ #ይስማዕከ ወርቁ

Читать полностью…

ቅኔ እና ጦቢያ

ሰውን የምትቀርበው ሌላ ስለሆነ ነው። ሁሉን ነገር ስታውቅ ሌላ መሆኑ ይቀራል። ትንሽ የማይታወቅ ነገር አስቀር👌

💚ሰናይ💛ምሽት ❤

#የግጥም_ቃና
👇👇👇
@ilovvll
@ilovvll

Читать полностью…

ቅኔ እና ጦቢያ

#ቴቄል
አዲስ መፅሀፍ
የወግ እና ግጥም ስብስብ
ተፃፈ-በአማኑኤል ደርበው
-ዳንኤል ከበደ
-ሙሉወርቅ ተስፋ
መገኛ:_
፨በአዲስ አበባ ሜክሲኮ ሀሁ መጻሕፍት መደብር
፨ባህር ዳር በሁሉም መጻሕፍት መድብር
፨በደብረ ታቦር
እንዲሁ በቅርቡ በሌሎች ከተሞች
t.me/kene_tobeya

Читать полностью…

ቅኔ እና ጦቢያ

ትህትና የመልካም ህይወት መሰረት ናት፡፡ሰዎችን ዝቅ ብሎ ማገልገል ወደ ከፍታ የምታወጣ መሰላል ናት፡፡ለራሳችሁም ሆነ ለሌሎች ትሁት ሁኑ፡፡ስትኖሩ መረን አትልቀቁ፡፡ህይወታችሁ በስነ ምግባር እና በበጎነት የታጠረ ይሁን፡፡ንግግራችሁ ለጆሮ ይጣፍጥ፡፡ሀሳባችሁ የሞተን መንፈስ ያንቃ፡፡ስራችሁን ምንጊዜም በታማኝነት ፈጽሙ፡፡ከምትሰሩት ስራ በስተጀርባ ተንኮል አይኑር፡፡ለሰዎችም ሆነ ለፍጥረት ሁሉ መልካም ሁኑ፡፡"ሞኝ!" ብትባሉም ደግነታችሁን አታቁሙ፡፡አለም የእናንተን መልካምነት አጥብቃ ትፈልጋለች፡፡ ኢትዮጵያም የእናንተን አገልግሎት፣ ደግነት፣ ትህተናና መስጠት የምተናፍቅበት ጊዜ አሁን ነው፡፡ ሰው በጠፋበት ጊዜ መልካም ሰው ሁኑ፡፡ ሰዎችን አድኑ፡፡የበጎነት ብርሃናችሁ በአለም ያብራ፡፡በአገራችሁም ይፈንጥቅ፡፡በቀን ቢያንስ ለአንድ ጊዜ መልካም ነገር ማድረግን ተማሩ፡፡ዛሬ ይህንን ፖስት ሼር በማድረግ ጀምሩ፡፡ሰዎችን በጠዋቱ አነቃቁ፡፡
#መልካምቀን

Читать полностью…

ቅኔ እና ጦቢያ

ሰው ፍቅር ናፍቆት
:
:
ከነገ ጀምሮ በድሬ ደዋ
ግሩም ቡና ይገኛል!
:
:
Join and share……………👇
@heranawi
@hrranawi
@heranawi

Читать полностью…

ቅኔ እና ጦቢያ

ክልክል ነው

ማጨስ ክልክል ነው
ማፍዋጨት ክልክል ነው
መሽናት ክልክል ነው
ግድግዳው በሙሉ
ተሰርቶ በክልክል
የቱ ነው ትክክል?
ትንሽ ግድግዳና ትንሽ
ኃይል ባደለኝ
"መከልከል ክልክል ነው"፤
የሚል ትዕዛዝ አለኝ።

@ilovvll
(በእውቀቱ ስዩም)
የ፤ሣት ዳር ሀሳቦች፣

#በግጥም_ቃና
👇👇👇
@ilovvll
@ilovvll 👈 ቤተሰብ ይሁኑ

💚ሰናይ💛ግዜ ❤

Читать полностью…

ቅኔ እና ጦቢያ

ትዝታ ይብቃ!
ገጣሚ ዳግም ሔራን
( #ሰው__ፍቅር__ናፍቆት )
:
:
Join and share…………👇
@heranawi
@heranawi
@heranawi

Читать полностью…

ቅኔ እና ጦቢያ

በምናልባት ኑሮ…

አይቦዝን አንቀልባው
አይሞላም ጉድጉዋዱ
ሺሆች ሞተው ሲያድሩ
ሺሆች ተወለዱ
ይመሻል ይነጋል ፣ ያው እንደልማዱ

ማን በገላገለኝ ፣ የጄን ሰአት ሰብሮ
በምናልባት አገር ፣ በምናልባት ኑሮ
የመጣው ይምጣ እንጂ ፣ ማን ያቅዳል ደፍሮ


ከ"ማለዳ ድባብ" (በእውቀቱ ስዩም)
ለወዳጆ በማጋራት ይቀላቀሉን።
👇👇
@kene_tobeya
@kene_tobeya

Читать полностью…

ቅኔ እና ጦቢያ

#ቴቄል

ጉዞ ወደ እናንተ...

ከነገ ጀምሮ በሁሉም #የባህር_ዳር መፅሀፍት መደብር
እንዲሁም በቅርቡ...
#በአዲስ_አበባ
#በናዝሬት
#በደብረ_ብርሃን
#በደብረ_ታቦር
#በድሬዳዋ እንዲሁም በሌሎች ከተሞች
t.me/kene_tobeya

Читать полностью…
Subscribe to a channel