killuminati2 | Unsorted

Telegram-канал killuminati2 - ንቂ ኢትዮጵያ

1139

እዚ ገፅ ላይ የምናነሳቸዉ ነገሮች ፩ ስለ ኢሉሚናቲ ፪ ስለ 5G ፫ ኢትዮጵያ ላይ ስለሚደረጉ ሴራዎች ፬ ስለ GMO ፭ ስለ ግብረሰዶማዊነት ፮ ስለ ማይክሮ ቺፕ 1% CONTROL THE WORLD 4% ARE SELL OUT PUPPETS 90% ARE ASLEEP 5% KNOW AND ARE TRYING TO WAKE UP THE 90% THE 1% DONT WANT THE 5% WAKING UP THE 90%

Subscribe to a channel

ንቂ ኢትዮጵያ

👉ድምፃዊ አቤልና ኢሉሚናቲ

አለምአቀፍ የሙዚቃ ኢንደስትሪ ላይ ስሙ በገናናነት የሚነሳው ኢትዮጵያዊው ድምፃዊ አቤል ወይም በመድረክ ስሙ The Weeknd (xo) ነፍሱን ለአጋንንቱ አለም የሸጠ ስለመሆኑና በርካታ ተከታዬቹን እያሳተ ስለመሆኑ በማስረጃ የተደገፈ ትንተና የተሰጠበትን ይህን አጭር ቪዲዬ በበመልከት ራሳችንና ልጆቻችንን በዘፈን ስም እየተሰራጩ ካሉት ከሰይጣን አምልኮ መዝሙሮች እንጠብቅ።

በዚህ ጊዜ ካልነቃን አሰፍስፎ በሚጠብቀን አውሬ እራሳችንንም ሆነ ልጆቻችንን ነው ምናስበላውና #እንንቃ።
ፈጣሪ ሀገራችንን ከክፉ ይመልስልን!

#day_7_tube

Читать полностью…

ንቂ ኢትዮጵያ

ሔዋን ገ\ወልድ በኢሉሚናቲ ተጠልፋለች!! | ሔዋን እና ግብረ-ሰዶማውያኑ ሙዚቀኞች | ጋዜጠኛ አብይ ይልማ ያጋለጠው ምስጢር | Haleta tv

Читать полностью…

ንቂ ኢትዮጵያ

የኢትዮጵያን የቴሌኮም ዘርፍ የተረከበው ሳፋሪ ኮም እና ቀጣይ ዕቅዱ

- ዲጂታላይዜሽንን በኢትዮጵያ ለማስፋፋትና ሀገሪቱን በሰይጣን ቁጥጥር ስር ለማንበርከክ በቅርቡ ስራውን የሚጀምረው ሳፍሪኮም የመጨረሻ እቅዱ በዩሃንስ ራዕይ የተጠቀሰውን ትንቢት ማስፈፀም ነው።

የዩሃንስ ራዕይ 13:-16-18

"ታናናሾችና ታላላቆችም ባለጠጎችና ድሆችም ጌታዎችና ባሪያዎችም ሁሉ በቀኝ እጃቸው ወይም በግምባራቸው ምልክትን እንዲቀበሉ ፥ የአውሬውም ስም ወይም የስሙ ቁጥር ያለው ምልክት የሌለበት ማንም ሊገዛ ወይም ሊሸጥ እንዳይችል ይደረጋል። ጥበብ በዚህ አለ። አዕምሮ ያለው የአውሬውን ቁጥር ይቁጠረው ፤ ቁጥሩም የሰው ቁጥር ነውና ፥ ቁጥሩም 666 ነው። "

Читать полностью…

ንቂ ኢትዮጵያ

አደገኛው የ 5ጂ ቴክኖሎጂ በኢትዮጵያ::
ባለፈው ሳምንት በኢትዮጵያ ስራ የጀመረው የ5ጂ ኢንተርኔት ቴክኖሎጂ እጅግ አደገኛ የሆነ አላማ በዚህች አጭር ቪዲዬ ገለፃ ተደርጎበታልና ተከታተሉት።
#የግዮን_ምንጭ

Читать полностью…

ንቂ ኢትዮጵያ

ስለ NIKE ጫማ ማወቅ ያለብን

✅Nike በአለማችን ተወዳጅ የሆነው Brand ጫማ ስያሜውን ያገኘው ከጥንት የግሪክ አማልክት የ Pallas(Titan) እና የStyx ልጅ ከሆነችው Nike ነው ፡፡Styx መሬትንና የሲዖልን መግቢያ የሚከፍል ወንዝ ነው ብለው ግሪኮች ያምኑ ነበር፡፡
Nike የጥንታዊ ግሪኮች ጣዖት የነበረች ሲሆን የፍጥነት የጥንካሬና የድል አምላክ ብለው ያመልኳት ነበር፡፡መመለኳም አሁን ድረስ ቀጥሏል፡፡

Nike በ Zeus(የጥንት ግሪክ ዋና አምላክ) የፍጥነት የጥንካሬና የድል አምላክ ለዘላለም እንደሆነች ቃል ስለተገባላት አምላክነቷ አሁንም ድረስ ቀጥሎ በእሷ ስም የተሰየሙት ምርቶች የሚከተሉት ናቸው፡
1.Honda motor cycles የ Nike'ን ምልክት እንደ አርማ/logo ይጠቀማል፡፡
2.በአሜሪካ anti aircraft missile system የ nike'ን ምልክት ይጠቀማል፡፡
3.በዋነኛነት የ nike ጫማ አምራች የ nike'ን ምልክት ይጠቀማል፡፡

✅ ስለዚህ አብዛኞቻችን የምንጠቀመው Nike ጫማ ሰይጣንን የሚወክል ስለሆነ ልንጠነቀቅ ይገባል፡፡በዙ ሰወች "ካላመለኩት ምን ችግር አለው" ይሉ ይሆናል ነገር ግን እኛ የእግዚአብሔር ተከታዮች እንጂ የሰይጣን አደለንም፡፡ ሰይጣን አምላኪዎቹ ኢሉሚናቲዎች ብዙ በጀት መድበው ይህንን ሁሉ የሚከውኑት የሚያመልኩትን ሰይጣን ከፍ ከፍ ለማረግና የዓለም ህዝብን በማወቅም ሆነ ባለማወቅ የሱ አቀንቃኝ ለማረግ ነው።

አሁን አሁን ላይ ለእኛ ለክርስቲያኖች ጊዜው ከባድና በፈተናዎች የተሞላ ነው::እያንዳንዷን እርምጃችን ቆም ብለን ማሰብ ይገባናል፡፡ምክንያቱም እኛ ግሎባላይዜሽን በሚባል በዘመናዊ ባርነት የታጠርን ሰወች አብዛኛው እንቅስቃሴያችን በእኛ ሳይሆን የሰይጣን ጭፍራ በሆኑ ሀገሮች የተወሰነ ስለሆነ ነው፡፡የሚሰጡንን ቀጥታ እንቀበላለን ለምን ብለን አንጠይቅም። የእነሱን እንቀበላለን የእኛን እንንቃለን የእነሱ የሆነው ሁሉ ይጥመናል፡፡ ነገር ግን ምን ያህል ስለምንከተላቸው ሰወች ፣ ስለ አለባበሳቸው ፣ ስለምንመገበው ምግብ ፣ ስለምንጠቀመው ቴክኖሎጂ እናውቃለን?

አሁንም ለመንቃትና ለማስተዋል ጊዜው አረፈደም!

#ፀረ_ኢሉሚናቲዝም

Читать полностью…

ንቂ ኢትዮጵያ

ኦርቶዶክስን በኦርቶዶክሳውያን የማዳከም አዲስ ስልት!

....የቀጠለ

(5) ከዚኽን በፊትም በተለመደው የፖለቲካ ሴራ አካሔድ መሠረት ቅዱስ ፓትርያርኩን ከመንበር አውርደው በሌላ ተረኛ ለመተካት ባለሥልጣናቱ ፊት ለፊት መምጣቱን አልፈለጉትም፡፡ እናም፥ መጀመሪያ ቅዱስነታቸውን እነርሱ ‹‹ጁንታ›› ከሚሉት አካል ጋር ፈርጀው ለማሸማቀቅ፣ በምእመኑ ዘንድ ለማስጠላትና ‹‹በፈቃዳቸው ለቀቁ›› ለማስባል ሞከሩ፡፡ ‹‹እኔም ኦርቶዶክሳዊ
ነኝ›› የሚሉ፣ በተግባር ግን ያልኾኑ ‹‹መምህራን›› እና አክቲቪስቶችን ከጀርባ ‹‹አይዟችሁ!›› እያሉ በጸያፍ አገላለጾች አስሰደቧቸው፤ ከልክ በላይም አፍ አስከፈቱባቸው፡፡ የቅዱስ ሲኖዶስን
ዋና ጸሐፊ ‹‹አይወክሉንም!›› የሚል መግለጫ አስሰጡ፡፡ ኦርቶዶክሳዊ ኹሉ ግን በሚገርም ኹኔታ እንደ አንድ ቃል ተናጋሪ፣ እንደ አንድ ልብ መካሪ ኾኖ ‹‹ከአባታችን ጎን ነን!›› ብሎ አሳፈራቸው፡፡ ይኽንን የሕዝቡን ሥነ ልቡና ያስተዋሉት ፖለቲከኞቹ ከቅዱስነታቸው ጋር የ ግል ቅራኔ ያላቸውንና የሥልጣን ጥም ያሰከራቸውን ‹‹ጳጳሳት›› በኅቡዕ አደራጅተው መንቀሳቀስ ይዘዋል፡፡ ‹‹ደኅንነቶች ነን›› በሚሉ ሰዎችና ለተረኛው መንግሥት እንቀርባለን በሚሉ ‹‹አባቶች›› አማካይነት ‹‹መንግሥት የሚፈልገው ይኽንን ነው›› ብለው እያስወሩ በአባቶችን ውሳኔ ላይ ከወዲሁ ጫና ለማሳደር እየተሞከረ፣ ቤት ለቤትም ቅስቀሳዎች እየተደረጉ መኾኑ እየተሰማ
ነው፡፡ ገና ቅዱስ ሲኖዶሱ ሳይሰበሰብም፡- ‹‹ቅዱስ ፓትርያርኩ በሌሉበት ምልዓተ ጉባኤ እንደሚካሔድ፣ እንደራሴ እንደሚሾም›› ማስወራት ይዘዋል፡፡ የእኛን አባቶች እየተዋጓቸው ያሉት በእኛው አባቶች ነው የሚያስብለውም ይኸው ነው!

(6) ሕገ ቤተ ክርስቲያንን በማርቀቅና በማጽደቅ ሒደት ውስጥም የግለሰቦች ፍላጎትና የውጭ አካላት እጅ እየገባ እንደኾነ ተሰምቷል፡፡ ገና ሕጉ በቅዱስ ሲኖዶስ ታይቶ ሳይጸድቅ ‹‹የማስፈጸሚያ ሰነድ›› የሚል ረቂቅ በአዲስ አበባ ሀገረ ስብከት ውስጥ ባሉት የወቅቱ ፈላጭ
ቆራጮች አማካይነት ሌላ አጀንዳ ማስቀየርያ መዘጋጀቱም ታውቋል፡፡ ስሙን ‹‹ሕገ ቤተ ክርስቲያን›› እያሰኙት የቤተ ክርስቲያንን ጥቅም ለግለሰቦች ፍላጎት አሳልፎ የሚሰጠውን አካሔድ ግን ‹‹ሕጋዊ›› ለማስመሰል የሚሔዱበት ርቀት ያስተዛዝባል! ሌላው ቀርቶ ‹‹እኛ
መነኮሳት ነን፤ ንብረታችን ኹሉ የቤተ ክርስቲያን እንጂ የእኛ መኾን የለበትም›› የሚል ሐሳብ የሰጡ ሊቃነ ጳጳሳትን እንኳን ምን ያኽል ሲያገልሏቸው እንደነበር የምናስታውሰው ነው!

(7) የኦርቶዶክሳዊት ቤተ ክርስቲያን ሲኖዶሳዊ አንድነትና መዋቅራዊ ጥንካሬ ለጎሣ ፖለቲካቸው የመከፋፈል ሴራ አልመች ሲል የ16ኛውን መቶ ክፍለ ዘመን እሾኽ (‹‹ቅብዓት›› የሚባል ኑፋቄ)
በ21ኛው ክፍለ ዘመን መልሰው ለመትከል ምሥራቅ ጎጃምን የሚያስጨንቋትም አሉ፡፡
በየትኛውም የኦርቶዶክሳዊት ቤተ ክርስቲያን ታይቶና ተሰምቶ በማይታወቅ ሥርዓት ‹‹ጳጳሳት›› እንደተሾሙ ተነገረ፡፡ የቅዱስ ሲኖዶስን ምልዓተ ጉባኤ ትኩረት ለመሳብና አጀንዳውንም ለማስቀየርም ሲሉ ‹‹የጳጳሳቱ በዓለ ሢመት ተዘጋጅቷል›› ብለው የጥሪ ካርድ በተኑ፡፡ ይኽ ኹሉ ሲኾንና ከመደበኛው የቤተ ክርስቲያኒቱ መዋቅር ተደጋጋሚ አቤቱታ ለመንግሥት መዋቅሮች ሲቀርብ ግን ጆሮ ዳባ ልበስ ብለዋል፤ በአጥፊው ፋንታም ሰላማውያኑ ታስረዋል፡፡ ‹‹ተለያይቶ
የነበረውን ሲኖዶስ አንድ አደረግሁ›› ብለው የሚመጻደቁት አካላት ‹‹ሌላ ሲኖዶስ›› ለመፍጠር ለምን እንደሚሯሯጡ ግን ግልጽ አይደለም!
ኦርቶዶክስን በራሳቸው በኦርቶዶክሳውያን አማካይነት የማዳከም ስልት፤ አዲሱ የአጽራረ ቤተ ክርስቲያን ሴራ!

👉ከ ‹‹ግንጊልቻ›› መጽሐፍ፣ ምዕ.4፥ ገጽ.89-92 ላይ ባለው ሐሳብ መነሻነት የተጠናቀረ

Читать полностью…

ንቂ ኢትዮጵያ

ውሎ አዳር በጎንደር

(ታመነ መንግስቴ ነኝ)

ስሆነው ፣ሳደርገው የዋልኩትን በሰንበት ላውጋችሁ!

ይችን እሁድ የምትሰኝ ዕለት ፈጣሪ እኛን አበጅቶ እርፍ ብሎባታል ሲባል እሰማለሁ፣አንብቤማለሁ።

"ብታምኑም ባታምኑም ጦር ግንባር ሳለሁ ሁልጊዜ ጠዋት ጠዋት ለኢንጅነር ክፍሌ ሆሮ ደውየ የግድቡን ሁኔታ እጠይቅ ነበር" እንዳሉት የአገሬ መራሔ መንግስት(ሀሳብዎ ላይ ተሳስቸ ያላሉት ነገር ብየ ተሆነ እርስዎ ተሳስተው 'የኤርትራ ጦር አልገባም' እንዳሉት ይቁጠሩት) እኔም 'ብታምኑም ባታምኑም እሁድ የእረፍት ዕለት ናት' ብያችሗለሁ።

ግን ግን ጠቅላያችን "ነገርዮሹ ስራዎት መስሎኝ? ለምን ማሳመን አስፈለገዎት_እያ!?"

ደሞስ ኢትዮጵያ ውስጥ ምን የሚሉት አለማመን ነው? አሁን እኒህ የመኪናችን ዘዋሪ እስላሙ፣ጠዋት ቁርጥ ስንበላ'ቁርስ በልቻለሁ' ያሉን ኦርቶዶክሱ ጓዴ መኪና ውስጥ መተኛትን ተልባቸው መያዛቸውን ለማረጋገጥ 'ማርያምን?' ሲላቸው 'ማርያምን' ብለው የለም? ቢራስ አብረን አልጠጣንም? ይህችን እንቆቅልሽ አገር ምን ማድረግ ይሻላል? ማሳደግ😀

ውሎ አዳር በጎንደር፦

"ምን ተሰራ ፤ምን ተወራ
ጎንደር በጀግኖች ጎራ?
ይበሰራ፣
እውቀት ሐቅ ይነገራ።"

በሚል ዘፈን ተጀመረ።የመፃፍ ጸጋየን ተጠቅሜ "የጎንደር ወዳጆቸ ጋሽ ንዋይ"ጎንደር የወርቁ ልጅ ዘውዴ ናት እናቴ!" ያለላትን በሙሉ ስሟ ዘውዴ ወርቁ የምትሰኘን የጎንደር እናት ፈልጋችሁ አገናኙኝ❤" ብየ ለመንኩ።ልመናየን የሰማው እግዜር(እግዜር ግን ያነባል?) ቃልኪዳን(ቃልየ ብየ ስሟን አላቀልም) የዘውዴን ምትክ ፍቅርን አገናኙኝ።ፍቅር እኮ የባለከዘራው እህት ናት።እዚያ ቤት ያጎረሰችኝን ልጅ እግዜሩ መና ያውርድላት።እግዜሩ ግን ሳልሞትበት ለአፋር ሕዝብ የሚያጠግብ ውሃም ይስጠው።

ቀኑን ሙሉ ስንፈልገው የዋልነው ሰውየ ደመቀ ዘውዱ አይደለም? እኔስ ቤቱን፣ሚስቱን፣ልብሱን፣ጉርሱን አይቸ"እንደሰው ነው የምትኖር ጋሸ!?" ብየ ብደነቅበት "እህ እንደምን ልኑር?" አለኝ።

እኔማ እንደ 'ከንቲባ' አዳነች አበቤ ብየ ነበር።እናንተ 'እዳነች አበበች'የምትሉ ነገር ሰንጣቂዎች ግን ለአማራ ሕዝብ ምን አድርጋችሁለታል?

"አማራው ያጣው መሪ ነው።መሪዎች ለራሳቸው ክብር እንጅ ለሕዝቡ አይጨነቁም።"ብላችሁስ 'ማን አለህ'? ልትሉኝ አይደል?

'ደመቀ ዘውዱ' ልበላችሁና ዳግም አስከብቡት! እናንየ 'ጎንደር ባለ ማተብ ነው፤በደመቀ ዘውዴ እና ወልቃይት ጠገዴ አይደራደርም።'

የልቅ እንየ ታከለ የባህል አዳራሽ ብቅ ብለን እንመለስ። እዚያ 'ዶፔል ቢራ 22 ብር' ተብሎ ዋጋው በር ላይ የተፃፈለት ምን ያህል አስቀያሚ መጠጥ ቢሆን ነው? ጣፋጭ መጠጥና ልባም ጎንደሬ እማ 'ሽሽግ' ተደርገው እንደ መይሳው ካሳ ላለው የአገር ዋልታ ይሰጣሉ።የራስ አሊ እናት ተዋበችን ለዳግማዊ ቴዎድሮስ የዳሩለት እኮ ዋጋዋን ለጥፈው አይደለም!

'አንች በቀሚስ የምትዋቢው ጎንደሬ ወዳጀ እነበብሻለሁ!?"

"እኔን ጎንደር ጎንደር እኔን ጎንደር ያርገኝ
የበሉት ሲስማማ የፈለጉት ሲገኝ"

የባለከዘራው እህት ቤት የበላሁት እዚህ የማይፃፍ ነገር ተስማምቶኛል።እንደምሳ በልቸው እነሆ ራትም ሆኖኛል።ኤርምያስ አመልጋ ለምን በ24 ሰዓት አንዴ ብቻ እንደሚበላ ተገለጠልኝ ልበል እንዴ? ይልቅስ 'ከኤርምያስ አመልጋ ጋር ማዕከላዊ እስር ቤት ነበርኩ" ያለኝን መኩሪያ የሆነ ፋኖ_ሻለቃ ጠዋት ቃለ መጠይቅ አድርጌ አለሁ።

አዝማሪ አማረን...!

እንየ ታከለ ቤቷ ሞልቶባታል።ባልደረባየ"እናንተ ፈስሳችሁ ነው?" ያላቸው ጎንደሬዎች(ተሌላም አገር ሊመጡ ይችላሉ።አርብ ዕለት አዘዞ ጥይቱ እንደፈነዳ ዘብ(Police )ጣቢያ ተመቶ ሁለት ሰውም ሞቶ ገብተን ወላ ሐድያ ወላ ወላይታ ብቻ ሴቶች ለስደት ሊያመልጡ ሲሉ ተይዘው አላየንም እንዴ?) በሩን አልፈው መንገዱን እየዘጉት ነው።

ተስፋ ቆርጠን('ክርስቲያን ተስፋ አይቆርጥም'ሲባል እሰማለሁ።እስላምስ? እሱም አይቆርጥም።አብሮን የነበረው ሰውየ እስላም መሆኑን ተላይኛው አንቀጽ ጥፌ የለም እንዴ?) ስንጓዝ "ባላገሩ " የሚሉት የአዝማሪ ቤት አገኘን።

"እኔን ጎንደር ያርገኝ"

እዚያ ቤት ገብተን የገበየነውንስ ታልሞትኩ ተድሉ በሗላ አወጋችሗለሁ።ተሞትኩም አትደነቁ ሌላ ታመነ ወይም ሌላ እገሌ ያወጋችሗል።

"ከሰማይ በታች አዲስ ነገር የለም።" ጎንደርም በላሊበላ ዘመን ዝም ብላ ጋራ እና ሸንተረር ነበረች።ሗላ "እሽሩሩ ጎንደር"ተባለች።የፋሲል ግቢን አሃለች።አሁንም ደርግና ወያኔን ተቋቁማ እየቆዘመች፣እያስቆዘመችኝ አለች።

t.me/Gazetaw

Читать полностью…

ንቂ ኢትዮጵያ

https://images.app.goo.gl/4jJJ84b8S3Mn3Vv17

Читать полностью…

ንቂ ኢትዮጵያ

ወደ ቤቴ ኑ!

ታመነ መንግስቴ ውቤ ነኝ።

ጊዜ፣ቦታ እና ሁኔታ ተገጣጥመው የምወደውን ሞያ ጋዜጠኝነትን ወርቅ ከሸለምኩት በሗላ ከጀግኖቹ የአገሬ ልጆች ጋር በጦር ግንባር ተገኝቻለሁ።

ይህ ጦርነት ከአስር ዓመታት በሗላ " አደይ መቀሌ"፣"እናቴ አዲስ አበባ" የሚሉ ዘፈኖች እንደሚደመጡበት ሃቅ ነው።

እስከዚያ ግን የሞት አቃቂር እያየን አለን።

ለሁሉም ከሸዋ ጣርማ በር እስከ ወሎ ጫፍ ዋጃ_ጥሙጋ፣ከሰቲት ሁመራዋ ማይጋባ እስከ አዲ አርቃይ ተጎራባች ጨው በር በጀማሪ ጋዜጠኛ ዐይን ያየሁትን፣የሰማሁትን፣ቀጥሎ በሚመጡ ጊዚያት በፈጠርኳቸው ግንኙነቶች የምፈትሻቸውን ሃቆች ለመቋደስ ወደ #እዚህ ቤት /channel/Gazetaw ብቅ በሉ።

በተለይ በፌስቡክ በኩል የጓደኝነት ጥያቄያችሁን ያልመለስኩላችሁ ወዳጆቸ ቤቴን ብታንኳኳት በሩስያ ሰራሹ ቴሌግራም ጥዑም ሃሳቦችን እንጋራለን።


እናም እዚህ ቤት /channel/Gazetaw ብላችሁ አንኳኩ።ክፍት ናት።

ታመነ መንግስቴ ከወሎ ግንባር!

Читать полностью…

ንቂ ኢትዮጵያ

"ውድ አንባብያን!

"ክረምት እና ንባብ" በሚል መሪ ቃል ዋልያ ኢቨንትስ ከሐምሌ 15_ነሀሴ 10 ድረስ የሚቆይ የመጻሕፍት አውደ ርእይ ማዘጋጀቱ ይታወቃል።

በዚህ መሰናዶ ነባርና አዳዲስ መጻሕፍት በቅናሽ ዋጋ ከመገኘቱ በተጨማሪ በእያንዳንዱ ውሎ/ምሽት ልዩ ልዩ የጥበብ ዝግጅቶች ይከናወናሉ።

ከእነዚህ ክንውኖች አንዱ አንጋፋ ደራስያን ልምዳቸውን የሚያካፍሉበት ነው። ስለሆነም ሐምሌ 29:2013 ዓ.ም በዕለተ ሐሙስ ከአስራ አንድ ሰዓት ጀምሮ ደራሲ አንዳርጌ መስፍን ተጋባዥ እንግዳ ሆነው የሕይወት ልምዳቸውን ያካፍላሉ።

ኑ! ከ "ጥቁር ደም" እና ከሌሎችም ልቦለዶች ደራሲ ጋር ማለፊያ ወግ እናውጋ!

አድራሻ:- አራት ኪሎ ከቱሪስት ጀርባ ኢክላስ ህንጻ። ለበለጠ መረጃ 0966252525::"

ይሄ መድረክ ከተዓምር በታች ያለ ተዓምር ነው ሰዎቸ!

እኔ ዕድሜ ለባምላኩ ገዛኸኝ ይሁንና ሁለት ምሽቶችን ታድሜ እየተፈወስኩ ተመልሻለሁ።

ነገም አብራችሁን ማዝገም ለምትሹ
መልዕክቶቻችሁን፦

በጓዳ @GazetawBot ላይ

ለእኔ ለአባወራው @Tamen1234 እያላችሁ ላኩልኝ።

የቤታችንን በር @Gazetaw አንኳኩ፤ክፍት ናት!

Читать полностью…

ንቂ ኢትዮጵያ

መንገሪያ!


ከነገ ቅዳሜ _ሐምሌ 3 /2013 ዓ.ም ጀምሮ በእዚህ ቤት ይተላለፍ የነበረው የደብዳቤና ጦማር ቀን እንደተጠበቀ ሆኖ ከዘ_ፍጥረት እስከ ምፅዓት ከኢትዮጵያ እጣ ፋንታ ጋር የተቋጠረው የዓባይ ጉዳይ የሚዳሰስበት "የዓባይ ነገር"የተሰኘ ዝግጅት እንደምንጀምር እናሳውቃለን።

እናንተ የቤቱ ሰዎችም በዚህ አምድ ስር ታላቁን ወንዝና ተፋሰሱን ከየ አንፃሩ እየተመለከታችሁ መሶባችንን ሙሉ እንድታደርጉ ትለመናላችሁ!


ሐምሌ_2_ቀን_2013 ዓ.ም

ታመነ መንግስቴ ፤አዲስ አበባ _ኢትዮጵያ



የሻታችሁን ሁሉ፦

በጓዳ @GazetawBot ላይ

ለእኔ ለአባወራው @Tamen1234 እያላችሁ ላኩልኝ።

የቤታችንን በር @Gazetaw አንኳኩ፤ክፍት ናት!

Читать полностью…

ንቂ ኢትዮጵያ

ልባሽ አለበሱን

(በታመነ መንግስቴ)

ከአፄ ፋሲል በፊት፤እንደዋዛ አሰሱን
በምኒልክ ዘመን፤ዳግመኛ ከለሱን
ፋሽስት ሆኑና፤ያው ትንሽ ቀመሱን
አሁን ሰምሮላቸው፤ ልባሽ አለበሱን።

ግጥሙ ግጥም ነው።ተውት!

የዛሬው ጨዋታችን በአንዲት የደቡባዊ አፍሪካ አገር ላይ የተሰራን ትዕይንተ ዶሴ(Documentary Film) መሰረት አድርጎ የተዋዛ ነው።

ርዕሱ በፈረንጅ አፍ"T_Shirt Travels"ይላል።በእኛ አፍ መተርጎሙ አስፈላጊ አልመሰለኝም።ለነገሩ መተርጎሙም ከባድ ነው።ብዙዎቹን የእንግሊዝኛ ቃላት በማደንቀው የአማርኛ ቋንቋ ለመክተብ ስታትር እንዲህ ተራራ የሆኑ ቃላት ይገጥማሉ።"Shirt"ን "ካናቴራ" ማለት ባይሳነኝም "T"ን "ቲ"ማለት ተገቢ አይመስለኝም።ነገሩ ከነገሬ ጋር ስለሚገናኝ እንጅ በቋንቋ ላይ አንድ ቀን እንደምንጨዋወት አልዘነጋሁኝም(አትርሱብኝና ቋንቋ መደባለቅ ለማይምነት መቅረብ መሆኑን በሆነ አፍታ አሳያችሗለሁ)!

እንዳልኳችሁ ትዕይንተ ዶሴው የተሰራው በደቡባዊት አፍሪካ ውስጥ ባለች አንድ እባብ የመሰለ ካርታ ያላት አገር ነው።በልጀነታችን ከምንሰማቸው አስቂኝ ቀልዶች መካከል የሆነ ተማሪ ዋና ከተማዋን ሲጠራ "ልዑል ካሳ" ማለቱ ነበር።ለስሟ የቀረበ መጠሪያ ያለው ወንዝ ያጠጣታል።ምናልባትም የአፍሪካ ትልቁ ፏፏቴ በዚያ ይገኛል።ስሟን መንገር "አታውቁም"ማለት ይሆንብኛል😀

አገሪቱና ዋና ከተማዋ ብሎም ወንዟ ማን እንደሆኑ እየገመታችሁ መጨዋወታችንን እንቀጥልማ__

"ኧረ እርየ እርየ _ኧረ እርየው መላ
ጎጃም ተገበየ__ፍቅርና ተድላ"ይላል ቆምጫጫው ጎጀ።
(ተነገሬ ጋር ምን ያገናኘዋል? ምንም😀)
ትዕይንተ ዶሴው ሲጠቃለል"አፍሪካ ማለት ነፃነቷን መልሳ በማጣት ላይ ያለች የምዕራቡም የምስራቁም ዐለም የቆሻሻ ማራገፊያ ናት።"ማለት ይመስለኛል።

ጉድ እኮ ነው ሰዎቸ__
አሜሪካዊያን ለብሰውትም፣አጥበውትም፣ጥለውትም ፣አንስተውትም፣መልሰው ጥለውትም ቤት እያጣበበ ያስቸገራቸውን "ውራጅ"ጨርቅ በየ መንገዱ"ስጡን"ለሚሏቸው ሰዎች ይቸሯቸዋል።በትዕይንተ ዶሴው ላይ እንደሚሉት"ምንም ልብስ ለሌላቸው ሰዎች የሚሰጥ፣ለአሜሪካ የጦር ኃይል በነፃ የሚለገስ "ይመስላቸዋል።በአፍሪካ ምድር ሁነኛ የገንዘብ መከመሪያ መሆኑን ማን ይነግራቸዋል?

የማወጋው ወግ ግር ያላችሁ በስድስት ኪሎና አካባቢዋ፣በመገናኛ መንገድ፣በሜክሲኮ አካባቢ፣በዚህ በአራዳ መንደር(Piazza)"በረረች፣በረረች፣ሱሪ በሞቶ፣ጫማ በሞቶ "የሚሉ ቀማኞችን ታውቃላችሁ? በቃ ይሄንን ነው የምላችሁ።

እናንተ ሆየ(ራሴ እንዴት እንደተንገላታሁ ልንገራችሁ።ከቴስ ከጎዳና ገዝቸ መሰላችሁ? ከመርካቶ ዘግኘ እኮ ነው ጉድ የሆንኩላችሁ።ተምወደው ተወዳጀ ጋር አንድ መልከ መልካም ኮት_Jacket_[ኮት =ኩታ__ይችንም አንድ ቀን እናወጋታለን] ገዛሁላችሁ።ተዚያማ ሲያቀብጠኝ በምናምን ቀኑ አጠብኩላችሁ።ተዚያ ቀለሙ ምን ሆነ ልበላችሉ? ነጭ፣ቀይ፣ቢጫ፣ጥቁር፣የማላውቀው በቃ ጉድ ሆንኩላችሁ።)

"ዋጋው በጣም ተራ ሆኖ ነው" ታላችሁ።አባ ይሙት ትሳሳታላችሁ።ማነው 900(ዘጠኝ መቶ) ብርን ተራ ነው ያላችሁ? ይሄ ብር የብዙ አዲስ አበቤ ተቋማት ጥበቃዎች ደመዎዝ መሆኑን ለማታውቁ ልንገራችሁ።አንዳንዶቹ ግን ሲበዛባቸው ነው(ስለነሱም አንድ ቀን እናወጋለን😁)

ተዚህ ጉደኛ ኮት በሗላ ልብስ ማመን ተሳነኝ(በቃ ጥቁር ሱሪ ገዝቸ ከማጠብ ወያኔ ተሸንፋለች፣መቀሌም አትገባም የሚለውን የባጫ በደሌ😁 መግለጫ ማመን ቀለለኝ።)

ሰዎቸ እየቀለድኩ አይደለም።"ቀልድና ቅዘን"አገራችንን ሲያበላሽ እያየሁ አልቀልድም።መራሄ መንግስት ዐቢይ አህመድ በመደመር መፅሐፋቸው ገጽ_66 ላይ፦
"ብዙ በጭቆና ውስጥ የሚኖሩ ሕዝቦች የጭቆናቸውን ሕመም የሚቋቋሙትና ኑሯቸውን የሚያስቀጥሉት ራሳቸውን በቀልድ እየደለሉ ነው።"ይላሉ።እስማማለሁ።

ካስፈለገ"ዐለምን ለመለወጥ የሚሰሩ ሰዎች አይቀልዱም።እነማን ናቸው ዐለምን የለወጧት
ታውቃለህ? ስሚዝ አዳምስ፣ሪካርዶ፣ካርል ማርክስ እነዚህ ዓለማዊ ፈላስፋዎች ናቸው።እና አይቀልዱም።ያለ ጩኸት ዝም ብለው ዐለምን ይለውጣሉ።"የሚለንን የበዓሉ ግርማ ኦሮማይ ላይ የተሳለ ገጸ ባህርይ እጨምርላችሗለሁ።እናም 'ቀልድና ንቅዘት(ቅዘን ላለማለት) አገር ያበላሻል'እላችሗለሁ።

ጨዋታችን እንደ አገሬ ቦተሊካ የተሳከረበት እንዳይሆን እንዲህ እንጠቅልለውማ❤

"ዘመነ ሉላዊነት ብዙ ሕዝቦችን እያገለለ፣ዳር እየጣለ እና ካላቸው ነገር እየነጠለ ነው"ሲሉ በቁጭት የሚናገሩት የ"T_Shirt Travels" ትዕይንተ ዶሴ ቃለ መጠይቅ ተደራጊ ኡርባን ጆሃንሰን ናቸው።እሳቸው የUNICEF የምስራቅና ደቡብ አፍሪካ ክልላዊ ሃላፊ እንደሆኑ ልብ ይሏል።

በዚሁ ትዕይንት ውስጥ እንግዳ የሆኑ አንዲት ሳተና ሴት አፍሪካዊትም"ነፃ ገበያ ነፃ ገበያ ይላሉ(ምዕራባዊያንን ነው) ግን ነፃው ገበያ ለማን ነው?" ብለው ይጠይቃሉ።

ለዚህ ነው የአፍራካ ነፃነት ከብዙ አስርት ዐመታት በሗላም አጠራጣሪ የሆነው።ዛሬም ዳግማዊ ኃይለሥላሴ፣ዳግማዊ ኩዋሚ ንኩርማህ፣ዳግማዊ ከተማ ይፍሩ፣ዳግማዊ ጁሊየስ ኒሬሬ፣ዳግማዊ ጸጋየ ገብረ መድኅን ያስፈልጋሉ።"አፍሪካ ቀዳሚውን የሰው ልጅ ስልጣኔ በዐባይ ሸለቆ ላይ የጀመረች የካም እና ኩሽ ምድር፣በሗላም እናንተ ባሪያ እያደረጋችሁ እስከምትፈነግሉት ታላቁ ቄስ ዮሐንስ(Priester John) የነገሰለት፣መንሳ ሙሳ በቲንቡክቱ ቀየ ወርቅ የነሰነሰለት፣ለሾና ሕዝብ አገሩን "ታላቋ" ዚምባቡየ እያለ ታሪክ የሰገደለት ኃያል ዘውግ የሚኖርባት የምድር ዕምብርት ናት እንዲሉ።

አፍሪካና አፍሪካዊያን(ኢትዮጵያዊያንም መጠነኛ ኩራታችንን ተወት አድርገን እንደ አፍሪካዊ ማሰብ አለብን።ከሰሞኑ ስማቸውን የዘነጋሁት ምሁር'ኢትዮጵያ ብቸኛዋ ቅኝ ያልተገዛች አገር ምናምን ስንልኮ በተገዙት የአፍሪካ ወገኖቻችን ቁስል ላይ እንጨት እየሰደድን ነው'ያሉበትን ንግግራቸው በጣም ወድጀዋለሁ።በተቻለን መጠን አፍሪካን አክብረን ልንመራት ይገባል።ታላቁ ንጉስ ቀኃሥ በመንግስታቱ ማህበርና የተለያዩ አገሮች ዞረው ዞረው በመጨረሻ እንደማይሆን ሲረዱ "የአፍሪካ አባት"መሆናቸውን መዘንጋት የለብንም።)

ስለሆነም አፍሪካና አፍሪካዊያን በሚያኮራው ማንነታችን ሊያሳፍሩን ቢጥሩም ልናፍርላቸው ፈፅሞ አይገባም።ልባሻቸውን እና በቅንዝር የተሞላ ጥቅስ ያጥለቀለቀው ሹራባቸውን አውልቀን ጥለን የእኛን ባህላዊ ልብሶች በብዛት በማምረት መልበስ እንችላለን።

እኛን የጎደለን ስነ ልቦናዊ ብስለት ነው።እንመልከት፣እናንብብ፣እንጠይቅ፣እምቢ እንበል።
(ኤዲያ ላወጋችሁ ያሰብኩት ብዙ ነበር።አሁን ባስበው ረጅም ጡፍ አታነቡም።ደሞ ይሄ ወንፊት የመሰለ ማህበራዊ መገናኛም ተረዘመ ያፈሰዋል።ዴሞ "ነገር ቢያበዙት በአህያ አይጫንም"ና ለዛሬው ይበቃናል።ትዕይንተ ዶሴውን ተመልከቱት፣የአገሪቱን፣የዋና ከተማዋንና የወንዙን ስም አሁኑኑ ምንም ነገር ሳታዩ እዚሁ ላይ ገምቱና ከሃሳቦቻችሁ ጋር በተለመዱት አድራሻዎቸ ላኩልኝ!
የምወዳችሁ ነኝ!)


የሻታችሁን ሁሉ፦

በጓዳ @GazetawBot ላይ

ለእኔ@Tamen1234 እያላችሁ ላኩልኝ።

የቤታችንን በር @Gazetaw አንኳኩ፤ክፍት ናት!

Читать полностью…

ንቂ ኢትዮጵያ

ምሽት 12:00 ላይ "የጋራ ነው"የሬዲዮ ዝግጅት በአዋሽ FM 90.7 መደመጥ ይጀምራል።


ስለ ደግነት አርማዋ እማማ አበበች ጎበና መነጋገራችን እንደተጠበቀ ሆኖ፦


👉ሰሞነኛ የታሪክ አጋጣሚዎችን በምናወሳበት አፍታ በሐምሌ ወር ተወልዶ በሰኔ ስለሞተው "የወራሪዎች ንጉስ "ጨዋታ ይዘናል።

👉ባህልና ወግ ላይ
"አሻም አሻም"እያለ ለኢትዮጵያዊ ባህልና ጋዜጠኝነት ሲተጋ ኖሮ በጎልማሳነቱ ስላጣነው ጋዜጠኛ ካሳሁን አሰፋ ጉዳይ ይኖረናል።

👉በኪነ ጥበብ ሰዓታችንም ወደ ወሎ ተጉዘን በዚያ ከ"እሪኩም ዘመዳ" እስከ ሸህ ሁሴን ጅብሪል ትንቢት አዘል ግጥሞች ምጥን ዝግጅት ይዘናል።

👉በፖለቲካ እና ማህበራዊ ጉዳዮች ዳሰሳ ጊዜ ወደ ልበ ተራራዋ ትንሽየ አገር ኩባ እናመራለን።

👉ከእናንተ አድማጮች ጋር ለመወያየት የመረጥነውም "ዘመናዊነት እና ኢትዮጵያ ምንና ምን ናቸው?" የሚል ርዕስ አለን።

ክቡራትና ክብራን ከእናንተ ጥሞና እና ተሳትፎ እንጠብቃለን።

አጫጭሮቹን መልዕክቶቻችሁ በድምፅም እየቀረፃችሁ፦

👉6804 ላይ ላኩልን።

በቀጥታ የስልክ መስመርም፦

011 5 54 33 16 ወይም የመጨረሻውን 19 እያደረጋችሁ ደውሉልን።


ሃሳባችሁን በማህበራዊ መገናኛውም፦

በጓዳ @GazetawBot ላይ

ለእኔ@Tamen1234 እያላችሁ ላኩልኝ።

የቤታችንን በር @Gazetaw አንኳኩ፤ክፍት ናት!

Читать полностью…

ንቂ ኢትዮጵያ

ጥበብ፣ጋዜጠኝነትና ስነ ፅሁፍ መሻታችሁ የሆነ እነሆ አውድማ አለላችሁ።

ግቡና የአገራችን ምርጡ የሀሳብ ገበያ እናድርገው።

/channel/litjournalism የምትለዋን ማስፈንጠሪያ በመጫን ዝለቁ።

Читать полностью…

ንቂ ኢትዮጵያ

"እረኛየ"ን ለፍቅር እና ልቦና ውቅር

(በታመነ መንግስቴ)

እግዚያብሔር ይመስገንና የእኔ ቀየ አድማሷ ሰፊ ነው።እኛ ቤት በላይ ካለችው አፋፍ ቁጭ ላለ ዐይኑ እስከሚደክም የሰማዩን ጥግ ይታከከዋል።

ልጅ እያለን ይኼ ሁሉ ውበት እያየነው የማይታይ ነበር።የልቦና ውቅራችንም እንደ አሁኑ ጠበቅ ያለ አልነበረም።

እኛ ትዕይንተ መስኮት አናውቅም።ሬዲዮም ቶሎ አላደመጥንም።መፅሐፍ ማንበብ አይታሰብም።

እናም ዐለም አድማሱ እስከሚጋርደን ብቻ ነበረች።ደስተኛም ነበርን።ምክንያቱም ሁሉንም ዐለም በዐይናችን እናየዋለና😂

አለማወቅ ደጉ፤አለመመራመር
ማወቅ ነው ስቃዩ፤ፍላጎት ሲጨምር።


ባለፈው ዓመት Covid_19 መጣ።ለሳምንታት ሰማይዋን ሳላይ በኑሮዋ ከምኳትንባት ሸገር ወደ ተወለድኩባት መንደሬ ሉባ ጊዮርጊስ ሄድኩኝ።ቀን ከመፅሐፍት ጋር እውላለሁኝ።ወደ ማታ አፋፍ እሆንና የእነሴን ሜዳ እስከ ደቡብ ጎንደር እያየሁ ሰፋ ባለ ምናብ እንዲህ እላለሁኝ።

"እነሴን በስዕል


እንደ ጣና ሐይቅ የተንጣለለ ሜዳ! በሜዳው ላይ የተዘራ የሚመስል የዕፅዋት ሽፋን___


ፀሐይ ያለ ስስት የምታሞቀው ተፈጥሮ፣ታላቁን የዓባይ ወንዝ ከሰማዩ ስር የሚፈስ የሚያስመስል የመሬት ገፅታ፣ታሪካዊቷን የሞጣ ከተማ ለዓመል ያህል ከቆንጆ ልጅ ደረት ላይ እንደተጣበቀች አብረቅራቂ እንቁ ያቀማጠለ ከባቢ!


እነሴ የጎጃም ግርማ_የጎጃሜነት አርማ ሆኖ በጥቅምት ወር የመጨረሻዎቹ ቀናት ይታየኛል!

(ይመስለኛል በጥቅምት ወር 20ዎቹ 2013 ዓ.ም ገደማ የከተብኳት ትዝታ ናት)


የሸገር እና የከተማይቱ ኢትዮጵያ ልጆችም "እረኛየ"ንበቀናነት ተመልከቱት።ምናብን አስፍቶ አገር ያስወድዳል።

እኛ ገጠሬዎቹ ናፍቀናችሁ እንደመጣነው እናንተም ናፍቃችሁን ትመጡ ዘንድ ለልቦና ውቅራችሁ አንድ ቤት ውስጥ የሚቀረፁ ኮልኮሌ ትዕይንቶችን ተውና እንዲህ ያሉትን ተመልከቷቸው።

አገሬ ፈለክ ናት፤እንዲያው ሁለመና
የእሷን የተቸረው፤በዓለም የለምና!


አስተያየት ያላችሁ፦


በጓዳ @GazetawBot ላይ

እኔ ለአባወራው @Tamen1234 እያላችሁ ላኩለልኝ።

የቤታችንን በር @Gazetaw አንኳኩ፤ክፍት ናት!

Читать полностью…

ንቂ ኢትዮጵያ

የኢትዮጵያ የሙዚቃ ኢንደስትሪ በኢሉሚናቲ ቁጥጥር ስር እየወደቀ ይገኛል። በአሁኑ ሰዓት በዓለም ላይ እየተስፋፋ የሄደው በሙዚቃ ሰይጣንን የማስመለክ ስልት በሀገራችንም ተግባራዊ ለማረግ ከፍተኛ በጀት በሚስጥር ማህበራቱ ተመድቦለት ከፍተኛ ስራዎች እየተሰራ ይገኛል።

በኢትዮጵያ ዛሬ ላይ በማወቅም ሆነ ባለማወቅ ነፍሳቸውን ለሰይጣን የሸጡና የሰይጣን አገልጋይና ዘማሪ ሆነው ትውልዱን እያሳቱ የሚገኙ የሙዚቃ ሰዎች ብቅ ብቅ እያሉ ይገኛሉ። እነዚህን ሙዚቃዎች ደጋግመን ባየንና በሰማን ቁጥር ነብሳችንን እያስኮነናትና ለአጋንንቱ አለም ተገዢ እየሆንን ነው ምንሄደው።

ከላይ ባለው ቪዲዮ ላይ የጃኖ ባንድ አባል የነበረችው ሔዋን ገ/ወልድ አዲስ የሙዚቃ ስራ እንዴት ከአጋንንቱ አለም ጋር የተሳሰረ ስለመሆኑ #በአብይ_ይልማ ተተንትኖ ቀርቦበታልና በጥሞና እዩት ለሌሎችም ሼር በማረግ ወጣቱን ትውልድ ከጥፋት ለመታደግ የቡኩላችንን እናበርክት።

Читать полностью…

ንቂ ኢትዮጵያ

ከዚህ በፊት የቅዱስ ጊዎርጊስ ቢራ መወገዝ እንደሚገባ ፅፈንላቹ ነበር። አሁን ደሞ ቅዱስ ዮሃንስ ቢራን ይዘው መጥተዋል። በአሜሪካ አንድ የሀበሻ ሬስቶራንት ውስጥ ለገበያ የቀረበው ይህ ቢራ በቀጥታ የቅዱስ ዮሃንስን በረከት ከሀገራችን ሊያሳጣ የሚችልና ለመቅሰፍትም የሚያደርስ ነው።

የሰማዕታት ስዕል በኦርቶዶክስ ሀይማኖት ትልቅ ትልቅ ስፍራ ያለው ነገር ነው። እንኳን ቢራ ላይ ሊታተምና በየመንገዱ ሊጣል ቀርቶ ትንሽ የቆሸሸ ስፍራም አይቀመጥም። እጅግ ከባድ የሆኑ ነገሮችን እያቀለልን በማለፋችን ነው አሁን ለደረስንበት ውድቀት የደረሰነው። ውድቀታችንን ብቻ ከማየት ባለፈ የውድቀታችንን ምንጮች ፈልገን ማድረቅ ስንችል ነው ከችግሮቻችን ወጥተን ወደ ቀደምት ልዕልናችን የምንመለሰው።

ለሀገራችን ችግሮቻችን አንዱ ምንጭ የኢትዮጵያን ባለውለታ የሰማዕቱ ቅዱስ ጊዎርጊስን ስዕለ አድኖ በዚህ ደረጃ አርክሰን ከቆሻሻ ጋር መጣላችን ነው። ያለፈው ትውልድ የሰራውን ስህተቶች አዲሱ ትውልድ በንቃት እያረመ ካልሄደ በስተቀር መቀመቅ ነው ተያይዘን የምኖርደው።

👉ይህን ጽሁፍ ያነበበ ለነፍሱ ይወስን!

ቢያንስ እኛ ቢራውን ባለመጠቀምና ሌሎችን በማንቃት ግዴታችንን እንወጣ!

Читать полностью…

ንቂ ኢትዮጵያ

ዘመን አመጣሾቹ ቢትኮይን (beast coin) እና ክሪፕቶ ከረንሲ ምን ማለት ነው? እንዴትስ ይሰራል?

ኢሉሚናቲዎች ለመጨረሻው የዲጂታላይዜሽን ጥቅለላ ይህን መገበያያ እንዴት ሊጠቀሙበት አስበው እንዳመጡት የሚያብራራ ቪዲዬ ነውና አድምጡት።

ስለ አውሬው የወደፊት ገንዘብ በቂ ግንዛቤ ይያዙ!

#የግዮን_ምንጭ

Читать полностью…

ንቂ ኢትዮጵያ

ቅዱስ ጊዮርጊስ - ቢራ ወይስ ሰማዕት?

የቅዱሳን ስዕል አድህኖ በክብር መቀመጥ ሲገባው የቅዱስ ገዮርጊስ ስዕል ግን

1/ በየጠርሙሱ ተለጥፎ የሰካራም እጅ ያለ ንጽህና በድፍረት ይጨብጠዋል።

2/ ስዕል አድህኖው በየመጠጥ ቤቱ እየወደቀ ይረገጣል። ከቆሻሻ ጋር ተጠርጎ ይጣላል።

3/ በስሙ ታቦት መቀረጽ ሲገባው የሚያሰክር መጠጥ ሆኖ ስሙን ለማርከስ ተሰርቷል

4/ ኢትዮጵያ ከሰማዕቱ የምታገኘውን ክብርና ጥበቃ ለማሳጣት በ1915 ዓ.ም ጣሊያኖች አቅድው አቋቋሙት።

የሚገርመው መጠጡን የሚጠጣው የኦርቶዶክስ ተዋህዶ ተከታዩ ነው።
አንዳዴ እንደቀላል የምናያቸው ነገሮች ከፍተኛ የሆነ ጥፋቶች ናቸውና እንንቃ።

ይህን ጽሁፍ ያነበበ ለነፍሱ ይወስን!

Читать полностью…

ንቂ ኢትዮጵያ

የኢትዮጵያ ዋና ስር መሠረታዊ ችግር - አንቀጽ 39

ምዕራባውያኑ ስለ አንቀጽ 39 በፈረንጆቹ አቆጣጠር በ2014 ዓ.ም የሰጡት የሴራቸውን ማብራሪያ አድምጡት። ሀገሪቱን በብሔር ብሔረሰብ መብት ማስከበር ስም በህገመንግስቱ እንዲካተት የተደረገው በማር የተለወሰ መርዝ አንቀፅ አደገኝነት በሰፊው ተብራርቶበታልና አድምጡት ሼርም ተደረጋጉት። አዲሱ ትውልድ ሊነቃና ካለፈው ታሪኩ ሊማር ይገባዋልና።

Читать полностью…

ንቂ ኢትዮጵያ

ኦርቶዶክስን በኦርቶዶክሳውያን የማዳከም አዲስ ስልት!

ባለፉት የታሪክ ገጽታዎቻችን ውስጥ በጉልበትና በይፋዊ ተቃርኖ ኦርቶዶክስን ከኢትዮጵያ ለማጥፋት ሲደረጉ የነበሩ እንቅስቃሴዎች ኹሉ አልተሳኩም፤ እንዲያውም የበለጠ ሲያጠናክሯትና ሲያስፋፏት ተስተዋሉ እንጂ፡፡ ለምሳሌ፡- በግራኝ አህመድ ወረራ ዘመን
ኦርቶዶክሳውያኑን በግዳጅ የማስለም ድርጊቶች ተፈጽመው ነበር፤ ሕዝቡም ወደ እስልምና ሲገባ አምኖበት ሳይኾን ተገዶ ስለነበር ጊዜ እስኪያልፍ በትዕግሥት ሲጠባበቅ ቆይቶ ነበር፡፡ እናም፥ ቅድስት ቤተ ክርስቲያን እነዚያ የመከራ ዘመናት ሲያልፉ ሃይማኖታቸውን እንዲክዱ
ተገደው የነበሩ ምእመኖቿን መልሳ ወደ ጉያዋ ለመሰብሰብ እንዲያስችላት ‹‹አንቀጸ አሚን›› የተባለ የማስተማሪያ መጽሐፍ አዘጋጅታ፣ ‹‹መጽሐፈ ቄዴር›› የተባለ የማጥመቅያ ሥርዓትም
ሠርታ ተልእኮዋን መልሳ ለማጠናከር ችላለች። ኦርቶዶክሳዊነትን ለማክሰም የተሠራ ሴራ ጭራሹን እንዲጠናከር ዕድል መፍጠሩን ይኽ አንዱ የታሪክ ምስክርነት ነው፡፡
በኋላ በጣልያን ወረራ ጊዜም ካቶሊኮች የእስልምናውን ክንፍ በመደገፍ ሁለቱ ‹‹የጠላቴ ጠላት ወዳጄ ነው›› በሚመስል መርሕ ተባብረው ኦርቶዶክሳዊት ቤተ ክርስቲያንን ለማዳከም ሲሠሩ ነበር፡፡ ለምሳሌ፡- በካቶሊኮቹ ሴራ ‹‹ሁለቱ እሾሆች›› የተባሉ ቅባትና ጸጋ በኢትዮጵያ ምድር በተተከሉ ጊዜ ኦርቶዶክሳዊት ቤተ ክርስቲያን እነርሱን ለመንቀል ትግል ላይ ስትጠመድ እስልምናው ደግሞ ድምጹን አጥፍቶ ውስጥ ውስጡን ሲስፋፋ እንደነበር ተዘግቧል፡፡ በዚኽ ታሪካዊ ተሞክሮ መሠረት ደግሞ የጋራ ጠላትን እንዴት በትብብር መዋጋት እንደሚቻል ልምድ ተቀስሞበታል፤ ይበልጥ አዘምኖና አጠናክሮ መቀጠል እንደሚያስፈልግም የታመነበት ይመስላል፡፡
አሁንም በግላጭ ኦርቶዶክሳውያንን አስገድዶ ለመጠምዘዝ መሞከር የማይታሰብ ነውና ሌላ ስልት አስፈለጋቸው! ይልቁንም፥ ተፈጥሯዊ በኾነ መንገድ (biological strategy) ቤተ ክርስቲያኒቱ ራሷን በራሷ እንድታጠፋ ኹኔታዎችን ማመቻቸት አዲሱ ስልት ተደርጎ የተያዘ ይመስላል፡፡ ይኽ ስልት አንድ እንዲጠቃ የተፈለገው ተቋም ራሱን በራሱ እንዲያጠፋ መርዳት (helping the institution to self-suicide) የማድረጊያ ዘዴ ነው፡፡ ይኽ ተፈጥሯዊ
የመባሉም ምስጢር ችግሩን በሚመስል መፍትሔ የመከላከል ስልትን ስለሚከተል ነው፡፡
ለምሳሌ፡- በሥነ-ሕይወታዊ የጥናት ዘርፍ ትላትሎችን ከግብርና ሰብል ጥቃት ለመከላከል ሲፈለግ ለሰብሉ ጎጂ ያልኾኑ፣ ነገር ግን ትላትሎቹን የሚበሉ ሌሎች እንስሳት የማርባት ዘዴ
ማለት ነው፤ በዚኽ የተፈጥሮ ሚዛን (ecological balance) ይጠበቃል፡፡ ከሌሎች ስልቶች የበለጠም ውጤታማ ነው (ኬሚካልን የመሰሉ መፍትሔዎች ለጎጂ ተባዮች ተረጭተው
ጠቃሚዎቹንና ሰብሎችን ጭምር የሚያደርቁ ‹‹ጅምላ ጨራሽ›› ከመኾናቸውም በላይ ለአየር
ብክለት ስለሚያጋልጡ አይመከሩም)፡፡ ተባዮቹን የሚመስሉ ሌሎች ተጻራሪ ተባዮች ሲኾኑ ግን ተመሳሳይ የአኗኗር ዘይቤ ስላላቸው በቀጥታ ከመገናኘታቸውም በላይ ጎጂዎቹ ተባዮችን አዘናግተው (ዘመድ መስለው) እንዲያጠቁአቸው ዕድል ይሰጣቸዋል፡፡
ይኽንኑ ኹኔታ ወደ ተቋም ስናመጣው የኢትዮጵያ ቤተ ክርስቲያንን ፊት ለፊት በመንግሥታዊ ሥልጣን ተጠቅመው፣ በሰይፍ አስፈራርተውና በሃይማኖታዊ ጉዳዮች ተከራክረው ማሸነፍ
እንደማይቻል ከታሪክ የተረዱት አካላት አንድነቷን ለመክፈል መጠቀም የጀመሩት አዲሱ ስልት መኾኑ ነው፡፡ ይኽ ስልት በኢትዮጵያ ቤተ ክርስቲያን ላይ በቀጥታና በይፋ የሚሰነዝረውን ጥቃት በይፋ ሳያሳውቅ (ለትችት በማያጋልጠው፣ ነገር ግን የተሻለ ውጤታማ በሚያደርገው መልኩ) እንዲያዳክማት የሚያስችላቸው ነው፡፡
ይኽ ተፈጥሯዊ ስትራቴጂ ‹‹ራስን በራስ እንዲያጠፋ የመርዳት›› መርሕን ስለሚከተል ቤተ ክህነቱ እንደተጻራሪ ክንፍ በፈረጃቸው የእስልምናና ሌሎች የፕሮቴስታንት ቤተ እምነቶች ከመገዳደር ይልቅ በውስጡ ባሉት ሰዎቹ ተጠቅሞ፣ ስያሜውን በሚመስል ዘዴ፣ የራሱን ተልእኮ
የሚያፋጥንለት የሚመስለውን አሠራር መዘርጋት ይበልጥ ውጤታማ ያደርገዋል፡፡ መዋቅርን በመዋቅር፣ ጳጳስን በጳጳስ፣ ቤተ ክህነትን በቤተ ክህነት፣ ሲኖዶስን በሲኖዶስ፣ ማኅበራትን በማኅበራት፣ አሠራርን በአሠራር ተክቶ ከመጀመሪያው አቅጣጫዋ ወደ ሚፈለገው መሥመር ማስቀየስ፤ በሒደትም ግብዓተ መሬቷን ለመፈጸም እንደማለም ያለ ስልት ነው፡፡
ይኽ ከሰሞንኛ ኹኔታዎች አንጻር ምን ምን ነገሮችን እንድናስተውል ያደርገናል?

(1) ትናንት ‹‹የኦሮሚያ ቤተ ክህነት›› እያሉ ሲያጨናንቁን የነበሩ ‹‹ኦርቶዶክሳውያን›› ወንድሞቻችን ዘግይተው ደግሞ በመስቀል አደባባይ ጉዳይ፥ ‹‹ሙስሊም ወንድሞቻችን
ቢያፈጥሩበት ምን ችግር አለበት?›› እያሉ ሲከራከሩን አስተውለናል፡፡ የገዛ ወገኖቻችን ከተቀናቃኞቻችን ጎን ኾነው ሞገቱን፤ ኦርቶዶክሳውያንን በኦርቶዶክሳውያን መዋጋት ይሏል ይኽ
ነው!

(2) ይኽንኑ ጉዳይ ቅድስት ቤተ ክርስቲያን በጠቅላይ ቤተ ክህነቷ አማካይነት ተቃውሞ ስታቀርብ መንግሥት ደግሞ የእርሷኑ ሌላ መዋቅር (የአዲስ አበባ ሀገረ ስብከትን) ተጠቅሞ
‹‹ይቅርታ›› አስጠየቀ፤ በመዋቅራችን አማካይነት መዋቅራችንን አጠቃው ማለት ነው!

(3) ለኦርቶዶክሳዊ ቀኖናት ደንታ የሌላቸውና ከመሰል እሴቶች ሊያንሸራትቱን የሚሹ ተሓድሶዎች ‹‹ኦርቶዶክሳውያን›› መስለው፣ ለትግራይ ሕዝብም እንደተቆረቆሩ አስመስለው
በበዓለ ሃምሳ ጾም ዐወጁ፡፡ ይኽንን ሲያደርጉ ግን ‹‹የገዳም አባቶችና የትግራይ ሊቃነ ጳጳሳት አዘዋል›› እያሉ ነው፡፡ ከእኛው ጾምና ትእዛዘ አበው ጋር ታክከው የእኛኑ ቀኖና ለመናድ የሚደረግ ሌላኛው እንቅስቃሴ!

(4) በውስጣችን ኾነው፣ ለሀገርና ለቤተ ክርስቲያንን አሁናዊ ጭንቀት መፍትሔ እንዳገኙ አስመስለው ‹‹ደጉ ንጉሥ ቴዎድሮስ ይገለጣል!›› የሚሉንም በዝተዋል፡፡ ለዚኽ ማሳመኛቸው
ደግሞ ‹‹ፍካረ ኢየሱስ›› እና ‹‹የገዳም አባቶች መልእክት›› የሚሉ የማግባቢያ አካሔዶችን ይጠቀማሉ፡፡ ገዳማውያኑ ግን በአንድነት ኾነው ‹‹መልእክቱ ከእኛ አይደለም!›› ማለታቸውን ልብ ይሏል፡፡

ይቀጥላል...

Читать полностью…

ንቂ ኢትዮጵያ

የብልፅግና ፓርቲና የብልፅግና ቤተክርስቲያን ምስል
የብልፅግና ቤተክርስቲያን ምስል ቢጫ፣ሰማያዊና ቀይ ሰዎች እጃቸውን ወደ ላይ ዘርግተው የሚዘሉ ሰዎች አናት ላይ መስቀል ከነ ፈነጠቀው ጸዳሉ ይስተዋላል፡፡ በአንፃሩ የብልፅግና ፓርቲና ሁለት እጆች ተዘርግተው ሰማያዊ፣ ቢጫና ቀይ ሰዎች በሰማየ ሰማያቱ ላይ የፈነጠቀውን የፀሐይ ብርሃን አይተው ሲጨፍሩ ይስተዋላል፡፡ የሁለቱም ቀለማቶች አንድ ዓይነት መሆናቸው ሰማያዊ፣ ቢጫና ቀይ ቀለማት መሆናቸውና ሦስት እጃቸውን ወደላይ አድርገው የሚዘሉ ሰዎች መሆናቸው ዝም ብሎ ገጠመኝ ሊሆን አይችልም እንላለን፡፡ የብልፅግና ቤተክርስቲያን የተጀመረው በአስራ ዘጠነኛው ክፍለዘመን የአዲስ ሃሳብ አፋላቂዎች ንቅናቄ ሲሆን በ1950 እኤአ በሃገረ አሜሪካ በመዳን ቅሪቶች ዘመን የብልፅግና ቤተክርስቲያን ነገረ መለኮት ተጀመረ፡፡ (www.Prosperity church logo)1 ድረ-ገፅ አይተው ትዝብትዎን ያጋሩ፡፡

የብልፅግና ፓርቲና ልዩ ልዩ የኃይማኖት እምነት ተቆማት
የብልጽግና መንፈሳዊ ትምህርት (ነገረ መለኮት) አስተምህሮት መሠረት ክርስቲያኖች ደህንነታቸው መጠበቅ አለበት ምክንያቱም መንፈሳዊና አካላዊ ህይወት የማይነጣጠሉና የማይለያዩ ተጨባጭና ነባራዊ ሁኔታ አላቸው፡፡ የምዕመናኖች ደህንነታቸው የሚተረጎመው አካላዊ ጤና እና በኢኮኖሚ ብልፅግና ይገለፃል፡፡ የብልጽግና ነገረ መለኮት መምህሮች አትኩሮቱን ለግለሰብ ሥልጣን መስጠት በመንፈሳዊና አካላዊ ጥምረት በጎ ጎን በመገንባት ያሳልፋል፡፡ ክርስቲያኖች በተፈጥሮ ላይ ሥልጣን ተሰጥቶቸዋል ምክንያቱም ክርስቲያኖች በእግዚአብሄር አምሳያ ስለተፈጠሩ ነው፡፡ በዚህም ምክንያት ክርስቲያኖች መንፈሳዊ ዓለማቸውን በማለማመድ በአካባቢያቸው የሚገኙ ቁስአካላዊ ነገሮች መጠቀም መቻል አለባቸው፡፡ የብልጽግና መንፈሳዊ ትምህርት መሪዎች ያለ አንዳች ፀፀት ኃጢአታችንን እንዲያስተሰርይልን፣ ከበሽታ ደዌን ለመፈወስ፣ ከድህነት አረንቆ ለመላቀቅ፣ ከመንፈሳዊ እርኩስነት ለመንፃት፣ ድህነትና በሽታ በህብረተሰቡ ዘንድ እንደእርግማን ስለሚቆጠር በእምነትና በእውነት ይህን የተሳሳተ አስተሳሰብ መስበር እንችላለን፡፡ ”Prosperity theology teaches that Christians are entitled to well-being and, because spiritual and physical realities are seen as one inseparable reality, interprets well-being as physical health and economic prosperity.[47] Teachers of the doctrine focus on personal empowerment,[48] promoting a positive view of the spirit and body. They maintain that Christians have been given power over creation because they are made in the image of God and teach that positive confession allows Christians to exercise dominion over their souls and material objects around them.[48] Leaders of the movement view the atonement as providing for the alleviation of sickness, poverty, and spiritual corruption;[49] poverty and illness are cast as curses which can be broken by faith and righteous actions.” 2

የዘመናዊ ሽብርተኛነት ታሪካዊ አጀማመር ከፈረንሳይ አብዬት ጋር ይያያዛል፡፡ በዘመኑ የሽብርተኛነት ሥር መሠረቱ መንስዔው ሥልጣኔ አሊያም የባህል ግጭቶች፣ ዓለም አቀፋዊ ትሥሥር፣ ኃይማኖታዊ ግጭቶች፣ የእስራኤልና የፓልስታይን ግጭት፣ አሊያም የራሽያ አፍጋኒስታን መውረር በሃገራት መህል የተከሰቱ ሽብርተኞነት ያካትታል፡፡ የዘመናዊ ሽብርተኛነት በግለሰብ ደረጃ በስብዓናችን ላይ የሚከሰት ብስጭት፣ የመገለል ስሜት፣ አሉታዊ የማንነት ጥያቄ፣ ራስን ማፍቀርና ማምለክ ንዴት እና ወይም የግብረገብነት ፈሪሃ እግዜብሄር ጋር ያለ ግንኙነት መላሸቅ ስሜቶች ይካተታሉ፡፡ በሃገራችን ኃይማኖታዊ ግጭቶች ወደ ዘርና ኃይማኖት ፍጅት (ጀጆኖሳይድ) ተሸጋግሮል፡

Читать полностью…

ንቂ ኢትዮጵያ

መርሳ እና ወልድያ ነፃ የወጡ ዕለት

(ከጦር ግንባር ዘጋቢው ታመነ መንግስቴ ማስታወሻ የተቀነጨበ)

ጋዜጠኝነትን እንደ እንጀራ ከቆጠርከው የተፈጨ አሸዋ የተቀላቀለበት እንጀራ ነው።እየጣመህ ይሰብርሃል።ሞያው ፍፁማዊ ነፃነት ይፈልጋል።በዚያው ልክ የባለሞያው ፍፁማዊ ምክንያታዊነት ፍቱን ነው።
እንዲህ ከሆነ ጋዜጠኝነት በፍቅር የሚያሰክር ሸሞንሟና ሞያ ቢሰኝ አልበዛበትም።

ዛሬ ሲነጋጋ ወደ ውጫሌ፣ውርጌሳ እና መርሳ ሄደን እኒያን ወሎየዎች ማየት እንዳለብን ሃሳብ አመጣሁ።ብቸኛው በእኔ ውሳኔ የሆነ ነገር ነው።ላለፉት 14 ቀናት የምሰራው ሁሉ በአለቆቸ ፈቃድ ላይ ብቻ የተመሠረተ ነበር።

ትናንት ማታ አሳስቄ ተሳካልኝ...!

ደሴ የግዷን ከ38 ቀናት የእብዱ ውሻ ንክሻ ዱካኳ እየነቃች ነው።የሚያሳዝነው ቀድማ ከከፈተቻቸው የአገልግሎት ዘርፎቿ ጫት ቤትና መጠጥ ቤት ይፈጥናሉ።"ዐለም ለምኔ"ብለው የሚቅሙት ማኘክ ጀምረዋል።ከሳምንት በፊት ደሴ _ፒያሳ ያገኘሗቸው የዕድሜ ባለሃብት"የአሁኑ ትውልድ ጫትን እንደ ባህል አደረገው"እያሉ ሲቆጩ ነበር።ብዙ ወሎየዎች በጦርነቱ መደፈራቸውን ይናገሩና ሲጨርሱ"ጫቱን ትታችሁ ለሕልውናችሁ ታገሉ"ይላሉ።

ደሴን ትተናት ወደ ሐይቅ ነዳን።ሐይቅን አልፈናት ሚሌ ወንዝ ላይ ነን።እዚህ ሐይቅን መዲናው ያደረገው የተሁለደሬ ወረዳ ያልቅና ባለ ቅኝቱ አምባሰል ይጀምራል።አምባሰል ወሎየዎቹን በምልዓት ከሚወክሉ አካባቢዎች አንዱ ነው።ዋና ከተማው ያው _ውጫሌ ናት።ውጫሌ በኢትዮጵያ ታሪክ ያላት ቦታ ከሰማይ በታች የሚገኝ ተዐምር ነው።

የኢትዮጵያ ታሪክ ሀሁ የማይገባው ሁሉ አድዋን ያውቀዋል።አድዋ ጓደኛየ ሳሙኤል ታዴ"የሰው ልጆች ድል"የሚለውን የጥቁር ሕዝብ ጀብዱ የምትመሰክር ምድር ናት።እናም ስለ አድዋ ጦርነት፣ድልና ነፃነት ለማውጋት የ1881ን(?) የውጫሌ ውል መንተራስ ግድ ነው።

ያኔ የሸዋው ንጉስ ዳግማዊ ምኒልክ ጣሊያን ወደ መሐል አገር እየገሰገሰ መሆኑን ተረዱ።እንደገባቸው ልጓም ማስያዣ አንድ ውል መፈራረም ነበረባቸው።ይህም ይሆን ዘንድ ከጊዜው የኢጣሊያ መንግስት ተላላኪ ፔትሮ አንቶሎኒ ጋር እዚህ አለንበት ቀየ አካባቢ "ይስማ ንጉስ"ተብሎ ተፈራረሙ።

የውጫሌ ውል ትርጉመ ብዙ ነው።በተለይ አንቀፅ ሶስት እና አንቀፅ 17 ከዚያ ወዲህ በተፈጠረችው ኢትዮጵያ ታሪክ ላይ ነጭና ጥቁር ነጥብ አሳርፈዋል።

አንቀፅ ሶስት የአሁኗን ኤርትራ የዚያን ጊዜዋን ሃማሴን ከኢትዮጵያ አካል ላይ የቆረጠ ቃል አለበት ተብሎ ይታመናል።እኔ እና ትውልዴ የተማርንበት የ10ኛ ብሎም 12ኛ ክፍል መፅሐፍ እዚህ ጉዳይ ላይ በጉልህ ያሰምራል።

አንቀፅ 17ን እንኳን እኛ ሰው በሙሉ ያውቀዋል።ይህ አንቀፅ የጫረው እሳት ተቀጣጥሎ ጥቁር ሕዝቦችን በተለየ፤የሰው ልጆችን ባጠቃላይ ባለድል አድርጓል።

ለሁሉም ለሁሉም ከሌላው ጣሊያን ጋር እየተዋጋን አሁን ውጫሌ ነን።

በግራ በኩል "ውጫሌ 17"የሚሰኝ ትምህርት ቤት መግቢያው ይታየኛል።አደነቅሗቸው።ታሪክን እንዲህ ማስታወስ መቸስ ልባምነት ነው።ለነገሩ መኪናችንን የሚዘውራት ኃይሌም"...ውጫሌ እኮ ጣይቱ እምቢ ያለችበት ቦታ ነው"ሲለን ነበር።ሃቅ አለው።እቴጌይቱ ያንን መናኛ ፈረንጅ"...እኔ ሴት ነኝ።ጦርነት አልወድም።ግን የአገሬን በጠላት እጅ መውደቅ ከማይ ጦርነትን እመርጣለሁ።ከፈለግህ ጦርነቱን የዛሬ ሳምንት አድርገው።እጠብቅሃለሁ"ያሉት እዚህ ነበር።

የዛሬ ረፋዷ ውጫሌ ከእብዱ ውሻ ወያኔ እጅ ነፃ ሆናለች።እስከ ትናንት ታህሳስ 8 ቀን 2014 ዓ.ም እዚህ እንደነበሩ ያገኘናቸው ባላገሮች ነገሩን።መቸስ በመንደሩ ያልተተኮሰ የጦር መሳሪያ የለም።ቀየው ደቋል።ሰዎቹ ደንግጠዋል።ዝምታ ላይ ናቸው።

እኛ በመገስገስ ላይ ነን።የወሎ ምድር የተራራ እና ሸንተረር አወደ ርዕይ ይመስላል።ልቅረፅ ቢል የመቅረፀ ምስል(ካሜራ) ባለሞያ የሚያደክሙ ተራሮች ይታያሉ።ውርጌሳን እንዳለፍን ወደ ዝነኛዋ ኒኒ በር ተጠጋን።

ኒኒ በርን ደሴ ሆኘ ከራሴ ስም በላይ ደጋግሜ ስሟን አድምጫለሁ።ሲበዛ ስልታዊ ቦታ ናት።ይህችን ማነቂያ የያዘ ተዋጊ ልዩ ብልሃት አያስፈልገውም።ተራራ ሸንተረሩ ጠላትን ተዋግቶ አድክሞ ያቀብለዋል።በዓሉ ግርማ በኦሮማይ የናቅፋን ተራሮች"ገዳይ መሬት...እግዜር ተበሳጭቶ በክርኑ የደቆሳቸው"እያለ እንደፃፈው ኒኒ በርም እንዲያ ናት።

ከሁለት አንገተ መለሎ ኮረብታዎች መሃል እንደ ቀዳዳ ሆና የተፈጠረችው ኒኒ ልባችን የጓጓላትን መርሳ ከተማ ለማየት ማጮለቂያ ናት።ይህችው የምድር ትዕንግርት የመዓት ኢትዮጵያዊያን እና ኢትዮጵያዊያት ወንድሞቸን ደም የማገች፣አጥንት የሳገች ቦታ ናት።ቢያንስ ላለፉት ሰባትና ስምንት ቀናት ቅልጥ ያለ ጦርነት ይካሄድባት ነበር።ደሴ አኪም ቤት(?) በገፍ እየመጡ ቁስላቸው ሲያሳቅቀኝ የነበሩ አዳጊ ወጣቶች የረገፉት እሷ ዘንድ ሳይሆን አይቀርም።

ሳይሆን ባይቀርም ልባችን መርሳ ስለሆነ እና እንደ እሷ ያሉ"ገዳይ መሬቶች"ብዙ ስለሆኑ መኪናችንን ነዳናት።መርሳም ገባን።ኮከብ የሌለባት አረንጓዴ፣ብጫ ቀይ ሰንደቃችን እንዳስከበረችን አለች።አሁን በነፃዋ የሰሜን ወሎ ፈርጥ መርሳ ከተማ በኩራት መኪናችን ላይ ሆና መውለብለብ ጀምራለች።ሕዝቡ ቤቱን ትቶ ጎዳና ወጥቷል።ሲያየን ፍቅር ያቅበጠብጠዋል።የነፃነት ጣዕም ያንቀጠቅጠዋል።የደስታ ስሜት ይንጠዋል።

ረፋድ አምስት ሰዓት ገደማ ሆነ።መሐል መርሳ መነሐሪያው ፊት ለፊት ተከስተናል።ወሎየዎቹ በደስታ ስካር ላይ ናቸው።ፍፁም ሳይኖራቸው ፍፁም ይለግሱን ጀመር።ዐይኔን በእያቅጣጫው እየወረወርኩት ነው።መከላከያው መኪናው ላይ ሆኖ እንጀራ በሚጥሚጣ ይበላል።የሚያበሉት ስድስት ወር ወያኔ የበላቸው የከተማዋ ነዋሪዎች ናቸው።እኛ መኪናችን ውስጥ ሳለን የብርቱካን በረዶ ወረደብን።በቃ ያዘንቡብናል።በመኪናችን መስኮት የተለገሱን ብርቱካኖች እንደ ነፃነት ጥዑም ነበሩ።ዐይኔ በጋዜጠኝነት መነፅር ይህንን ፍፁማዊ የሕዝብ ደስታ ስላየች በፍስሐ ተጥለቅልቄያለሁ።

አሁን ከመኪናችን መውረድ አለብን።የምንሰራበት ማኅበራዊ መገናኛ ግርግር ይወዳል።ቡና ቤተንዋይ(Buna Bank) መርሳ ቅርንጫፍን ለምስል መቅረጫ(Camera)ችን ዐይን ሰጥተን የኒያን ደጋግ ወሎየዎች እየየ ልንሰማ ነው።በመሐል እንዲህ ሆነ።

"ጁንታ ጁንታ"ተባለ።የተማረከ የእብዱ ውሻ ወያኔ ታጋይ አለ።ምድረ ወታደር፣የከተማ ነዋሪ ምናልባትም መለያ የቀየረ ሰላይ ሁላ ከቦታል።አንድ" መቶ አለቃ ነኝ "ያለን የመከላከያ ሰራዊት አባል መቅረጸ ምስልና የድምፅ ማጉያ(Microphone) እንደያዝን ሲያይ በትዕዛዝ መልክ፦
"ኑ ቃለ መጠይቅ አድርጉለት" አለን።ያኔ በደስታ ሰክሬ ስለነበር እንዳለው ለማድረግ ተዘጋጀሁ።አሁን ሳስበው ለካስ በወታደር ቤት ትዕዛዝ እንጅ "እባክህ"ማለት ነውር ነው።


ለሁሉም በዚህ የዘመቻ ጉዞየ ለመጀመሪያ ጊዜ የጠላትን ተዋጊ ቃለ መጠይቅ ላደርግ ነው።መጀመሪያ ባልደረባየ(ምስል ቀራጩ) "አይዞህ ወንድሞችህ ነን"አለው።

(የወያኔን ምርኮኛ ጉዳይ ይዠ በሁለተኛው ክፍል እመለሳለሁ።ታሪኩ የተፈጸመው ልክ የዛሬ ሁለት ወር ታህሳስ ዘጠኝ ቀን በዋለችው ዕለተ ቅዳሜ ነው!)

t.me/Gazetaw

Читать полностью…

ንቂ ኢትዮጵያ

የኔ "ሰው"ናትናኤል ዲበና

(በታመነ መንግስቴ)

ልጁ በአዲስ አበባ መካነ አዕምሮ የሕትመትና በይነ መረብ(Print and Web) ጋዜጠኝነትን ይማራል።

መቼስ አስተዋይነት፣አድማጭነት፣ቅንነት እና ርቱዕ አንደበት የእሱ ናቸው።

ከናቲነት ጋር አብሮ መስራት ሲመቸኝ!አይኮሰኩስም።ጥንቅቅ ያለ ቀጫጫ ነው😁

አሁን Etv ላይ"ነገን ዛሬ"በሚሰኝ የወጣቶች ዝግጅት አፍታ እንግዳ ሆኖ አየሁት።ደስስስ አለኝ።

በዕየለቱ ሳይረግጣት በማይውላት "አረንጓዴ ሰው ይገኝባታል" በሚባልላት አራት ኪሎ ሲኳትን ምስል ቀራጩ አንስቶታል።

ሌላዋ ናቲየ የሚወዳት ቦታ ስድስት ኪሎ አንበሳ ግቢ ጋ ያለችዋ ፒፕሲ የጋዜጣ እና መፅሐፍ ማንበቢያ እንዲሁም መሸጫ ጓዳ ናት።እዚያ ናቲነትን መፈለግ አያከስርም።

ይሄ በብዙኃን መገናኛ ዕውቀቱ(ስለ ኢትዮጵያ መገናኛ ብዙኃንና ባለሙያዎቻቸው ከዊኪፒዲያ በላይ አምኘ የምጠይቀውና የጠየኩትን የሚሰጠኝ ትጉህ ተወዳጀ ነው)የሚያስደምመኝ የዘመኔ ስጦታ በቃለ መጠይቁ አፍታ፦

"በሚዲያ ውስጥ ገብቶ እንደ ጥላ የሚያልፍ ጋዜጠኛ መሆን አልፈልግም"ብሏል።

በአስር ጣቴ ፈርሜ አምነዋለሁ።ቸር ይግጠመው!


የቀጫጫውን የEtv ቆይታ ለመታደም https://www.facebook.com/100003435445465/posts/3127578597366624/ ላይ ግቡ።

ወደ መሃል አለላችሁ!

Читать полностью…

ንቂ ኢትዮጵያ

#.. እመ.... #

ያደኩበት ቀበሌ.. የአባቴን ጠቦቶች ለቅሞ የወዳጆቼን ሀገር ሊረሽን ወረደ ፡፡
አዬ እመብርሃን....
እዛም ስለት አለብሽ ፡ እዚም ፀሎት አለብሽ ... ታቦት ስመው ከወጡ ልጆችሽ መሃል ሁለት ቡድን እንጂ ሁለት አምላክ የለም አይደል ?
እንግዲህ ለማን ትለመኛለሽ ፡ እንግዲህ ለማን ትጠየቂያለሽ .....
ሳይነጋ መሸብን ፡፡
ሰሜን ሊጀግን ፡ ደቡብ ሊረሽን ፡ ምስራቅ ሊፋለም ይወርዳል ፡፡ ሰው ሳያንስ እንስሶች በካራ ስለት ያልቃሉ፡፡
በለምለም ሳር መማለድ ቀረ ፡፡ ደናቁርትን የሚታገል ህዝብ ፊት ለስርየት የሚታረድ ቄስ ጠፋ ፡፡ ለሽንገላ የቆመ ሼህ ናፈቀን ፡፡ በቃ... ሁሉም ስለ ጎጡ ፆመ ፡፡

...ዝንት ዓለም ዱላ ፡ ዝንት ዓለም ካራ ፡፡
የመቆም ጥቅም ሳይገባን የምንወድቅለት ሀገር ይናፍቀናል ፡፡
አየሽ ድንግል... ታመን አልጨረስንም ፡ ዘፍነን አልታደስንም ፡፡
" በሉ እንሂድ !! " .... እንላለን
" እንውጋቸው !! እንበላቸው !! " አይደርስብን ዘመን የለም ፡፡ ይኸው... ይመጣል ያልነው ምፅዓት በኛ ክፋት ተቀደመ ፡፡ አፈ ሙዝ እሩምታው እስኪንጠፈጠፍ ብንጀግንም.. አሻግረሽ የነገን ለቅሶ አሳዪን .... በቃ በይን እመብርሃን ፡፡ በቃን............ ሰው ማስታረቅ ትቷል ፡ ሰው መሸነፍ ትቷል ፡፡ በቃን....
አምና ለሳቀው ብላቴ .. ፡
አምና ለሳቀው ወታደር.. ... ለሀገሬው ... ለተገፋው ፡ ለሚገፋው!! ... ይማማር ዘንድ ፊደል ሁነሽ ድረሽለት ፡፡
በቃ በይን እመብርሐን ፡፡
የትግራይ ወዳጆቼ... ሳሚ ፡ ሀዱሽ ፡ ገሬ ፡ ክብሮም ፡ ኤልሳ ፡ አንድ ቀን በደህናው ቀን እንገናኛለን ♥ ፡፡
#ጌታነህ ደጉ

Читать полностью…

ንቂ ኢትዮጵያ

የዛሬ ዓመት ገደማ የተከተበ___

'ጉራ ብቻ'
(በታመነ መንግስቴ)

ያው የማከብረው ወዳጀ መምህር ሀብታሙ አለማየሁ አንድ ማስፈንጠሪያ(Link) ላከልኝ።Egypt Independant የተሰኘ ገፀ ድር ጉራ ተሸክሟል።"ኢትዮጵያ እና ግብፅ ጦርነት ቢገጥሙ ማን ያሸንፋል?" ዓይነት የሰይጣን ንፅፅር ውስጥ ለመግባት ሲንደረደር የአገሩ ርዕሰ ብሔር አብደል ፈታህ አል ሲሲ የአየር ኃይል መኮነኖቻቸውን "ለየትኛውም የአገር ውስጥ ወይም የድንበር ባሻገር ተልዕኮ ተዘጋጁ"እያሉ ማሟሟቃቸውን ወሽክቷል።

ይቀጥልና የግብፁ ውጭ ጉዳይ ምሉክ ሳሚ ሽኩሪ ስለ እኛው አቻቸው አቶ ገዱ ዓረፍተ ነገሮች"ጠብ አጫሪነትና"እና "አበሳጭነት" መናገራቸውን ፅፏል።ከዚያም ከዓለም ዐቀፉ የጦር መሳሪያ ሃይል ድረገፅ አገኘሁት ያለውን የኢትዮጵያና ግብፅ ንፅፅሮሽ ያስቀምጣል።ለአብነት፦

ሀ.የግብፅ ዓለም ዓቀፍ የጦር አቅም ዘጠነኛ ሲሆን የኢትዮጵያ 60ኛ ተብሏል።

ሁ.የግብፅ ዓመታዊ የጦር ኃይል ገንዘብ ድልድል(በጀት) 11.2 ትዕልፊት(ቢሊዮን) ሆኖ የኢትዮጵያው 350 አዕላፍ(ሚሊዮን) ተገምቷል።

ሂ.የግብፅ ወታደሮች ቁጥር 920ሺ ተገምተው የእኛዎቹ 160ሺ ላይ ተቀምጠዋል።

እንግዲህ ነፃነትን ለ2ሺህ ዓመታት ተነፍጋ በቱርክ፣እንግሊዝ፣ሮማ፣ፋርስ፣እና ኢትዮጵያ ስትገዛ በኖረችውና ነፃነትን በማታውቀው አገረ ግብፅ ያለ የሚመስለው 'Egypt Indepndant' የፃፈውን እንመነውና ወደ እኛ ጉዳዮች እንምጣ፦

'ከነገራችን ጋር' የኢትዮጵያው የውጭ ጉዳይ ምሉክ አቶ ገዱ አንዳርጋቸው የያዙት መንገድ አይከፋም።ግብፅን እንደማንፈራትና በተለይ በሁለት እጆቿ ልታፍስ መቃጣቷን መቃወማቸው ያስመሰግናቸዋል።_ ሰውየው ደመ ሞቃት ስለመሆናቸው ራሳቸው ለዘመን መፅሔት በሰጡት ቃለ ምልልስ ውስጥ አንብቤያለሁ።

ቢሆንም ከዘመን አይሽሬው የኢትዮጵያ ላዕከ መንግስት(Diplomat) አክሊሉ ሃብተወልድ ጋር የሚነፃፀር ብልጠት ያስፈልጋል።አክሊሉ በማስታወሻቸው እንደፃፉልን ኤርትራን ለማስመለስ ባደረጉት እልህ አስጨራሽ ትግል ውስጥ ረፍት አልባ ሆነው ለህመም ሳይቀር ተዳርገዋል።የዚያኔ ኢትዮጵያን በስም እንኳ በደንብ ከማያውቋት አገራት መሪዎች ጋር በፈጠሩት መልካም ግንኙነት የተባበሩት መንግስታት ድርጅት ጠቅላላ ጉባኤ ላይ የኤርትራን ወደ ኢትዮጵያ መቀላቀል ደግፈው እጅ እንዲያወጡልን አድርገዋቸዋል።

ጋሽ አክሊሉ ሃብቴ ዛሬ "የጥቁር እንቁ" የምንለውን የጋምቤላ ምድር ወደ እናት አገሩ የመለሱት በጥበብ ነው።ኦጋዴንን፣የባቡሩን ባለቤትነት፣ ኢትዮጵያን ራሷን ያስረከቡን በከፍተኛ የተግባቦት ብቃት ነው።ከእነ አቶ ገዱ ይሄ እና ከዚህ በላይ ይጠበቃል።

የእኛ ትውልድ ሃውልት የህዳሴ ግድብ ነው።ግብፅ "ጦርነት" የምትለው 'ጉራ ብቻ' ነው።ምክንያቱም ዘመኑ አይፈቅድማ! የምወደው ነገራተሰብ(ጋዜጠኛ) ዮርዳኖስ አበበ እንደሚለው "በዚህ ዘመን በአንድ ጦርነት የሚመጣን ኪሳራ 20 ዓመት አይመልሰውም።" ጦርነቱ ከሆነም እንዲሁ በጉራ ደረጃ እና የአገር ውስጥ ባንዳዎቻችንን በመመልመል ነው።ስለዚህ ለጊዜው በአጥንት መናከሱን ትተን ወደ ጅቡ መጮህ አለብን።

ጅቡ ብዙ ነው።እነ አሜሪካም የእኛን ጉዳይ ለራሳቸው ይፈልጉታል።ያ ታላቅ ሰው-አክሊሉ ሃብቴ እንደፃፉት"ሁሉም ለየራሱ ጥቅም እንጅ በፖለቲካ 'ጀስቲስ'(ፍትሕ) እንደሌለ የታወቀ ነው።"

በዚህም ተባለ በዚያ እኛ መራብ አንፈልግም።ግዮን ኢትዮጵያን "ይከብ" ዘንድ በአምላኩ ታዝዟል።አሁንም ጋሽ አክሊሉ ሃብቴ ኦጋዴንን ሊነጥቋቸው ለቋመጡ እንግሊዞች"ሳንዋጋና ሳንሸነፍ ልትወስዱት አትችሉም!" እንዳሏቸው እኛም "ሳንዋጋና ሳንሸነፍ የዓባይን ግድብ ውሃ ሙሌት ልትከለክሉን አትችሉም!" ብለናል።

"ጉራ ብቻ'' የለቀቀብኝን ገፀ ድር ማስፈንጠሪያ እነሆ፦https://egyptindependent.com/is-an-egypt-ethiopia-war-an-option-a-comparison-between-the-egyptian-and-ethiopian-armies/

Читать полностью…

ንቂ ኢትዮጵያ

ትግራይ፦የታሪክ ወለፈንድነት* እና ሰሞነኛ ጣጣ

(በታመነ መንግስቴ)

እኔ በመራሄ መንግስቱ ዐቢይ አህመድ ፅሕፈት ቤት አልታደምኩም።በነዚያ ነጫጭ ወንበሮች ላይ አልተቀመጥኩም።ከሰውየው ዘንድ ፍርፋሪም አልቀመስኩም።በአሸናፊው አንደበታቸው ተረትቸም አላጨበጨብኩም።ግን ዘመኔ የመረጃ ነውና ሰውየውም ያሉትን ጋዜጠኞቹም የሆኑትን ታዝቤያለሁ።በሚከተለው መጠነኛ የልጅ ትንታኔየ ሰሞነኛውን የተከዜ ማዶ ጣጣ ከታሪክም፣ከተረክም፣ከዛሬም ከነገም አንፃር እመለከተዋለሁ።

ስሙን የደበቅሁለት ዘፋኝ ተወዳጀ እንደነገረኝ ከሰሞኑ በአዲስ አበባ ዳንኪራ ቤቶች"እምበር ተጋዳላይ"መቀንቀን ጀምሯል።በዚህም የተነሳ የመዲናይቱ ቀውጢ መጨፈሪያዎች ገበያቸው ተመናምኗል።ብልፅግናውን ፍራቻ የማስደለቅ ቅስማቸው ኮስምኗል።

ከተከዜ ማዶ ደግሞ ምናልባትም የቀበሮ ደስታ ቢጤ ሆኗል።በዚያ መራሔ መንግስት ዐቢይ አህመድ በገደምዳሜው"ወጋን"ያሉት ትግሬ "ታጋዮቹን"በፌሽታ እየተቀበለ ይመስላል።

የኒያ ደጋግ ሰሜነኞች እጣ ፋንታ በቀናነት ለተመለከተው እጅጉን ያሳዝናል።ያ_ምድር ላለፉት ቢያንስ 5 መቶ ዓመታት የቀውጢ ጦርነቶች ሁነኛ መድረክ ሆኗል።እናም እነ በዓሉ ግርማ እንደሚሉትና ታሪክም ደጋግሞ እንደሚነግረን ቦታው የ"አድር ባዮች"ምድር ሆኗል።

ላይኞቹ አንቀፆች መራራ መሆናቸው ይነበበኛል።ነገር ግን የሐበሻ ጀብዱ ተርጓሚ ተጫነ ጆብሬ መኮንን ስለ ጉዳዩ ጠይቄያቸው እንደመለሱልኝ"ተፈርቶ አይኖርም"ና ሃቅ ሃቁን ብንነጋገር ያግባባን ይመስለኛል።

በዓሉ ግርማ የሰዎቹን ስነ ልቦና ከተረዱት ጋር ተነጋግሮ ሊፅፈው ችሏል ተብሎ በሚገመተው"ኦሮማይ"የተሰኘ ታሪካዊ ልቦለዱ ውስጥ፦

"ሰለሞን ለመናገር ብሎ የሚናገር ሰው አይደለም።ከተናገረ ስለሚናገረው ነገር ካንጀቱ ስለሚናገር አድማጭ ይስባል።"ብሎ ባስተዋወቀን ገጸ ባህርይው አማካኝነት በገጽ _83_ላይ ከመረብ ማዶ ስላሉት ትግሬዎች ስነ ልቦና ሊነግረን ይሞክራል።
"___በኤርትራ ክፍለ ሀገር ታሪክ ውስጥ የበላይነትን ያገኛል ተብሎ የሚገመተውን ኃይል ተቀብሎ የማስተናገድ ዝንባሌ አዲስ ነገር አይደለም።በ400 ዘመን የትግል ታሪክ ውስጥ አንዱ ኃይል ሲሄድና ሌላው ሲመጣ ማየት የተለመደ ነገር ሆኖ ቆይቷልና አድርባይነት ሁለተኛ ተፈጥሮ ሊሆን ምንም አልቀረውም።መጠራጠር ይበዛል።የ"ቶማሶች"ቁጥር ቀላል አይደለም።"

ደራሲው ለመረብ ማዶ ሰዎች የከተበው ሃቅ ለተከዜ ማዶዎቹም የሚሰራ ይመስላል።መከላከያው መቀሌ ሲገባ "ጁንታው ጨቁኖን ነበር"ብሎ እነ ደፂ ከጫካ ወደ ከተሞች ሲጠጉ "እምበር ተጋዳላይ" ማለት ከአድር ባይነት በምን ይለያል? በአገር መከላከያ ሰራዊት ላይ ጨክኖ መተኮስ፣"አንድ ቄስ የማስተማሪያ ድምፅ ማጉያና ክላሽንኮብ"ይዘው መውተርተር ምን ይባላል? ኢትዮጵያንና ኢትዮጵያዊነትን መጥላት ከዚህ በምን ይለያል? እኒህን ጥያቄዎች ለመመለስ የአራት ኪሎው ባለሟል እንዳሉትም "የጥሞና ጊዜ ያስፈልጋል!"

እንደ ኩሩ ኢትዮጵያዊ በኢትዮጵያ ታሪክ ውስጥ ከማደንቃቸውና ከሚያሳዝኑኝ ነገስታት መካከል ትግሬው ቆራጥ መሪ ዮሐንስ አራተኛ ይገኙበታል።የእሳቸው በድልም በእድልም የተዋዛ የግዛት ዘመንና በመጨረሻ ለኢትዮጵያ ቁራሽ መሬት ሲሉ አንገታቸው በመሃዲስት እጅ መቆረሱ ከጥፋታቸው በላይ እጅጉን ይጎላብኛል።

ይሄንን እያሰላሰልኩ በትግራዋይ ጀግንትና የኢትዮጵያ ስልጣኔ እምብርትነት ስኮፈስ አስቀያሚዎቹ የከሃዲነት አጋጣሚዎች እንደ ሰኔ መብረቅ ብልጭ ይሉብኛል።

የሐበሻ ጀብዱ መፅሐፍ ተርጓሚ ተጫነ ጆብሬ መኮንን በተገኙበት የአዲስ አበባ መካነ አዕምሮ የመፅሐፍት አውደ ርዕይ መድረክ ላይ አስተናባሪ የነበሩት ታላቁ የስነ ፅሁፍ አስተማሪ ሊቀ ምሁሩ ደረጀ ገብሬ በዕለቱ ሲመክሩን"ታሪክ መማሪያ እንጅ መማረሪያ"ስላልሆነ በዚሁ መፅሐፍ ገጽ_307 ላይ ተከትቦ ብዙ ያነጋገረን አንቀፅ ከዚሁ የተከዜ ማዶ ሰዎች ጣጣ ጋር በእጅጉ ይቆራኛል።

የዚህ ተወዳጅ መፅሐፍ ደራሲ አዶልፍ ፓርለሳክ የኢትዮጵያው የገበሬ ጦር በብዙ አጋጣሚዎች ድልን በጣሊያን ላይ ተቀዳጅቶ ዳግማዊ አድዋን ሊያበስር ሲል እንከን እየሆኑ በአገራቸው ታሪክ ላይ ቀፋፊ ቀለም ያስቀመጡትን ሰዎች በስም ይጠቅሱና

"___በማይጨው ጦርነት በዚያች ቀውጢ ሰዓት በሰሩት ስራ እኔም "አረመኔዎች" ናቸው ከማለት ወደሗላ አልልም።" ሲሉ እጅጉን ያዝኑባቸዋል።

በጉዳይ ላይ ብቻ ከተርጓሚው ጋሽ ተጫነ ጆብሬ ጋር መጠነኛ ክርክር ለማድረግ ሞክረናል።በዚያች አፍታ ከተሰነዘሩ የታዳሚያን ዕይታዎች መካከል የማረከኝና በዚህ ፅሁፍ ውስጥም ጎልቶ ቢነበብ የሚያግባባን "ባንዳነት ከGeographical Location አንፃር"ቢታይ ሲሉ አንድ ሰው ያነሱት ሃሳብ ተመችቶኛል።

የነገሩን ሁነኛነት ለመፈተሽ ባደረግሁት ጥረት የዚሁ መፅሐፍ ደራሲ በተጠቀሰው ገጽ ላይ ከብስጭታቸው ቀጥለው"ራያዎች በዘር ኦሮሞዎች ናቸው ይባላል"ያሉበት አገላለፅ ቀን የከፋ ለታ የትኛውም "ኢትዮጵያዊነት ሱሴ ነው"የሚል ብሔር አገሩን አሽቀንጥሮ ከመጣው ጋር አሸሸ ገዳሜ ሊል እንደሚችል ማሳያ ይሆናል።

"ቀን ዘመድ እኮ ልዠ
እናትና ልዡን የሚያስተቃቅፈው የቀኑ ማማር ነው።"ስትል የአያቴ ምሽት የነገረችኝ በኑረት የተፈቸነ ሃቅም በእንዲህ ያሉ ተጠየቆች ይሰራል።

"ብሔርም ባዕዳ ነው፤ይገለባበጣል

አብሽሪ ኢትዮጵያ፤የአንች ቀን ይመጣል።"**


በዚህም ተባለ በዚያ የኢትዮጵያ መከላከያ ሰራዊት ትግራይን ለቆ መውጣቱ በአንፃራዊነት ለሁሉም ይበጃል።መራሔ መንግስት ዐቢይ አህመድ ለጋዜጠኞቹ ሲነግሩ እንደሰማነው ሕዝበ ትግራዋይ የመከላከያን ጣዕም" ቢያንስ በወር ውስጥ ቢበዛ በሁለት"ሊረዳው ይችላል።እስካሁን ግን ለብዙ ክፍለ ዘመናት ታሪክ እና ዕድል ፊታቸውን አዙረውበት መጠነኛ የአገር ክህደቶችና በትህነግ(TPLF) ስብከቶች የተማረከ ይመስላል።

"ከድህነት ነፃ እስካልወጣን ድረስ ባንዳነት አይጠፋም።"የሚለው የጋሽ ተጫነ ጆብሬ መኮንን ሃሳብ ለሁሉም ኢትዮጵያዊያን ይሰራል።የራበው ታማኝ ውሻ ጎን ሲርቀው ማጀት ማማተሩ ወይም ጎረቤት ሄዶ ተከርቸም መሆኑ መች ይቀራል?

ስለዚህ ዘመቻችን ድሕነት በሚባል ሁነኛ ጠላት ላይ ቢሆን ይሻላል።ጠብመንጃው ስራ ይባላል።ስራ ሰውን ሳይሆን እንጀራን ያበላል።

ይቆየን!


*.ወለፈንድነት___Paradox ለሚለው ቃል አንፃራዊ ፍች እና ግራ አጋቢ፣የሚያምታታ
ማለት ነው።

**.ግጥሙ ፦ሰውነት ባዕዳ ነው፤
ይገለባበጣል
አብሽሪ ቲኑየ፤
የአንች ቀን ይመጣል"

ከሚለው የትህትና መኩሪያ ግጥም ቃላት ብቻ ተቀይረው የተወሰደ ነው።



ሃሳባችሁን ፦

በጓዳ @GazetawBot ላይ

ለእኔ@Tamen1234 እያላችሁ ላኩልኝ።

የቤታችንን በር @Gazetaw አንኳኩ፤ክፍት ናት!

Читать полностью…

ንቂ ኢትዮጵያ

ሰው ሁሉ ቅኔ ነው፤ራሱን ይቀኛል
የእኔን ትቸዋለሁ፤የአንተ ይበቃኛል።
አያ ሙሉጌታ፦
ተቀድሰህ ንገስ፤በልባችን ዙፋን
ሁሉ እየተንጫጫ፤መሪው ገዥው ጠፋን።

ታመነ መንግስቴ

ለባለ ቅኔው ሙሉጌታ ተስፋየ

Читать полностью…

ንቂ ኢትዮጵያ

እነሆ ትንታግ ፀሐፊ እየመጣ ነው።በላይሁን ፍስሃ(ዝጎራ ቤል) በአካል ስታገኙት አይናገርም።ሲፅፍ እንዲህ ነው።የልቤ ሰው በዓሉ ግርማ፣የአደፍርስ ወላጅ ዳኛቸው ወርቁ ዝምተኛ ነበሩ አሉ።

"(በዝጎራ ቤል)

ሳያት ደምሴ (እናናዬ):-

"ጥበቧ ት/ቤት እየገባችብኝ አስቸግራኝ እሷን መልሻት መምጣቴ እኮ ነው፡፡"

መዓዛ:-

"እናናዬ ታዲያ እኮ ጥበቧ ት/ቤት መግባቷ እኮ ጥሩ ነው፥ጥበብን ፈልጋ ነው፡፡
እሷ ከዚያ ጠፍታ አይደለም እንዴ የተሸበርነው!?"👏👏👏👏👏

የሚገርም ቅኔ! ትክክለኛ አገላለጽ!

"እረኛዬ" ተከታታይ ድራማ ማስደመሙን ቀጥሏል፡፡ ከርዕሱ ብነሳ #እረኛ የሚለው ቃል ብቻውን ህልቆ መሳፍርት ትርጉሞችንና ምሳሌዎች ያሉት ሦስት ፊደል የያዘ ቃል ነው፡፡ ጥቂቶቹን ለማስታወስ ያክል:- ጠባቂ፥ መሪ፥ አቅጣጫ ጠቋሚ፥ አራቂ፥ ዘብ፥ ወዘተ…

በእረኛ ከሚመሰሉ ጥቂቶቹ ደግሞ:- #እግዚአብሔር (በክርስትና ዕምነት እንደሚታወቀው)፥ የሀገራት መሪዎች፥ የጥበብ ሰዎች(መልካም የሆኑ ልማዶችን ህዝብ እንዲያተኩርባቸው አጽንዖት በመስጠት)፥ መምህራን፥ ግለሰቦች(ራስን መግዛት መቻል ወይም ራስን ወደ ትክክለኛ መንገድ መምራት መቻል) ወዘተ………

ስለ ርዕሱ ይህችን ታክል ካልኩኝ ከላይ መግቢዬ ላይ ከትዕይንቱ ላይ ቀንጭቤ ወደወሰድኳቸው ዓ.ነገሮች ልለፍና የተወሰነ እንድል ይፈቀድልኝ🙏

አመሰግናለሁ!!!

#ጥበብ ለአንድ ማህበረሰብ ሁለንተናዊ ዕድገት(መሻሻል) ጉልህ ሚና እንዳላት መናገሩ ለቀባሪ እንደማርዳት ነው ብዬ አስባለሁ(4ቱ ባህሪያተ ስጋ እና 3ቱ ባህሪያተ ነፍስ ለተቸረው ሰው ለሆነ ሰው ሁሉ)፡፡
ነገር ግን አውቆ ጥቅም ላይ ማዋልና አውቆ ዝም ማለት ለየቅል እንደሆኑም መረዳቱ ጠቃሚ ይመስለኛል፡፡

የቀደሙት አባቶቻችን የጥበብን ጠቀሜታ በአግባቡ ተረድተው በተግባር ሲከውኑት ኖረዋል በተለያዩ አስቻይ ባልሆኑ ሁኔታዎች ውስጥ ሆነው፡፡ ደመናን ጠቅሰው ከቦታ ቦታ ይጓጓዙ እንደነበር እንሰማለን(ሐሽማልን ያነበበ እጅ ያውጣ እስኪ🤚) ከነገራችን ላይ(ከታሜ እንደተዋስኳት ይሰመርልኝ) ስለጦርነት ሲነሳ አባቶቻችን፥ ስለጥበብ ሲነሳ አባቶቻችን፥ ስለ ሀገራችን ጥንተ ገናናነት ሲነሳ አባቶቻችን ወዘተ…… ስቅታ ገደልናቸው እኮ😔 እኛስ ባለፈው መኩራትን ብቻ ጀብድ አድርገን ታሪክን ሳንሰራ ታሪክ በመጥቀስ ከተሰፈረልን የዕድሜ ዘመን እየቀነስን የምንኖረው???

በዘመናችን ትምህርትና ጥበብ እሳትና ጭድ የሆኑ ያክል ት/ቤቶቻችን ጥበብን ተጠይፈው #ሸምድደህ ትፋው(ታመነ መንግስቴ እንደሚለው) ቲዎሪዎችንና የባዕዳንን አሰስ ገሰስ ቆልለው ትውልዱን አስገድደው እየደፈሩት ነው ብል ቀለል አድርጌው እንደሆነ እንጂ ያጋነንኩት አይመስለኝም፥ ከዚህ በላይ ገላጭ ሐረግ ባገኝ ደስ ባለኝ ነበር!፡፡

እናማ ሀሳቤን ጠቅለል ለማድረግ ያክል እየዘራን ያለነው ዘር(አረ ምንባላበትን እያልኩ አደለም ሆይ መቼም ህዝቤ #ዘር የሚለውን ቃል ሲሰማ 5ቱ ብቻ ሳይሆኑ ራሱ የፈጠራቸውንም የስሜት ህዋሳት አቁሞ ነው ሚሰማህ)፥ እየበቀለ ያለው ቡቃያ፥ እያጨድን እና እየከመርን ያለነው ነዶ፥ እያስፈጨን ያለነው እህል፥ እያቦካን እና እየጋገርን የምንበላው እንጀራ ወዘተ…… እያቃረን ለጤናችንም ለመንፈሳችንም ሰላም ያልሰጠን #ጥበብ ስጋዎቿ ከሆኑት ት/ቤቶቻችን ተነጥላ እርቃኗን ስለቀረች ነው፥ ፈላጊና ተፈላጊ የፍየልና ቅዝምዝም ሁኔታ አጋጥሟቸው ነውና ልብ መለቱ አከፋም፡፡ እናስተውል፡፡

ቸር ሰንብቱልኝ👋 እረኛዬን ተመልከቱ እንጂ አትዩ(የሁለቱን ልዩነት መቼም አይጠፋችሁም፡፡"


(ደግሞ "ከነገራችን ላይ"ሳይሆን "ከነገራችን ጋር"እንደምል አትርሳ ዝጎራ ቤል😂)


አስተያየት ያላችሁ፦


በጓዳ @GazetawBot ላይ

እኔ ለአባወራው @Tamen1234 እያላችሁ ላኩልኝ።

የቤታችንን በር @Gazetaw አንኳኩ፤ክፍት ናት!

Читать полностью…

ንቂ ኢትዮጵያ

"እረኛየ"ን ለፍቅር እና ልቦና ውቅር

እንዲህ ባለ መንደር ማደግ ምናብን ያሰፋል።

የሸገር እና የከተማይቱ ኢትዮጵያ ልጆችም "እረኛየ"ንበቀናነት ተመልከቱት።ምናብን አስፍቶ አገር ያስወድዳል።

እኛ ገጠሬዎቹ ናፍቀናችሁ እንደመጣነው እናንተም ናፍቃችሁን ትመጡ ዘንድ ለልቦና ውቅራችሁ አንድ ቤት ውስጥ የሚቀረፁ ኮልኮሌ ትዕይንቶችን ተውና እንዲህ ያሉትን ተመልከቷቸው።

አገሬ ፈለክ ናት፤እንዲያው ሁለመና
የእሷን የተቸረው፤በዓለም የለምና!

Читать полностью…
Subscribe to a channel