.......... የጊዜ ዋጋ
UNITED GOD KINGDOM
“ጊዜ ከሁሉ ነገር በላይ እጅግ የሚያስፈልገን ነገር ሆኖ ሳለ ከሁሉ ነገር በላይ በተበላሸ ሁኔታ የምንጠቀምበት ነገር ነው” - William Penn
• የአንድን አመት ዋጋ ለማወቅ ከፈለግህ ክፍሉን የደገመን ተማሪ ጠይቀው፤
• የአንድን ወር ዋጋ ለማወቅ ከፈለግህ ካለወሩ የተወለደን ሕጻን የወለደችን ሴት ጠይቃት፤
• የአንድን ሳምንት ዋጋ ለማወቅ ከፈለግህ በየሳምንቱ የሚወጣን ጋዜጣ አሳታሚ ጠይቀው፤
• የአንድን ቀን ዋጋ ለማወቅ ከፈለግህ የወሳኝ ፈተናን ውጤት ነገ ለመስማት የሚጠብቅን ተማሪ ጠይቀው፤
• የአንድን ሰአት ዋጋ ለማወቅ ከፈለግህ ለመገናኘት የተቀጣጠሩ ትኩስ ፍቅረኞችን ጠይቃቸው፤
• የአንድን ደቂቃ ዋጋ ለማወቅ ከፈለግህ አውቶቡስ ለትንሽ ያመለጠውን ሰው ጠይቀው፤
• የአንድን ሰከንድ ዋጋ ለማወቅ ከፈለግህ ከአደጋ ለጥቂት ያመለጠን ሰው ጠይቀው፤
• የአንድን ሚሊ ሰከንድ ዋጋ ለማወቅ ከፈለግህ በኦሎምፒክ ሩጫ ለጥቂት የተቀደመን ሯጭ ጠይቀው፡፡
ሰው ለምንም ነገር የሚከፍለው በገንዘብ ሳይሆን በጊዜ ነው፡፡ ይህ እውነት ቀድሞውኑ ገንዘቡን ካለመኖር ወደ መኖር ያመጣው “ጊዜ” የተባለው ነገር የመሆኑን እውነታ ጠቋሚ ነው፡፡ ጊዜ በአለም ላይ ውድ ከተባሉ ነገሮች ቀደምተኛውን ስፍራ የያዘ ጉዳይ ነው፡፡ ጊዜውን ያባከነ ሰው ሕይወቱን ያባከነ ሰው ነው፡፡
ጊዜን በአግባቡ ባለመጠቀም ምክንያት ሰዎች ገንዘብን ይከስራሉ፣ ወዳጅነትን ያበላሻሉ፣ ከዚያም አልፎ፣ አንዳንድ ጊዜ፣ በሞትና በሕይወት መካከል የሚወስን ገጠመኝ ውስጥ ራሳቸውን ይጨምራሉ፡፡ የጊዜ አጠቃቀማችን ሁኔታ ተጽእኖው እጅግ ብዙ ነው፡፡ ይህ የሆነበት ምክንያት ጊዜ አንድና አንድ በመሆኑ ነው። ጊዜ አንዴ ካለፈ በፍጹም ተመልሶ አይመጣም፡፡ ጊዜ በብዙ እድሎች የተሞላ ሃብት ነው፡፡ ጊዜ እንዲሁ ሲያልፍና ሲባክን ከዚያው ጋር አስገራሚ እድሎችና ሌሎች ውብ ነገሮች አብረው ያልፋሉ፡፡
ጊዜ በተሰኘው ሃብትህ ላይ ያለህን አመለካከት ስታስተካክለውና የጊዜ አጠቃቀም ብቃትህን በሚገባ ስታዳብር በብዙ ትግል ለመፍታት ሞክረህ ያልፈታሃቸው ችግሮችህ የት እንደገቡ ሳታውቅ ተስተካክለው ታገኛቸዋለህ፡፡
⭐️ሊንኩን በመጫን Forward ያድርጉ..
⭐️@Kingdeom
⭐️@Kingdeom1
ሰናይ ቀን🙏🙏🙏Jeson Habtishe.
UNITED GOD KINGDOM
😇Jesus The Son Of Man
.....Introduction
🤔..ሰው ማነው?..
ይህንን ጥበባዊ መልእክት፣በጥሞና እና በማስተዋል እንድትሰሙት እና Share እንድታደርጉት ተጋብዛችኋል።
@Kingdom
@Kingdom1
ሊንኩን በመጫን ይቀላቀሉ።
Jeson.
....የምታጣው፣ነገር ከሌለ የምታገኘውም፣አይኖርም።...በሂይወታቸው አሽናፊ፣የሆኑ ሰዎች የሚያጡት ነገር ብዙ ነው።...
Jeson
👉@Kingdeom1
👉@Kingdeom...ሊንኩን በመጫን ይቀላቀሉ።...❤
የህይወት ወሳኝ ጥያቄዎች
ከዚህ በታች ያሉት ጥያቄዎች መነሻ ሀሳቦች እንዲሆናችሁ ብዬ ነው ያቀረቡኩት እናንተ የራሳችሁን ጥያቄ መፍጠር ትችላላችሁ።
1.በህይወቴ ላሳካው የምፈልገው አላማ እና ራዕይ ምንድን ነው?? ከአምስት ወይም ከአስር አመት በኋላ ራሴን የት ማግኘት እፈልጋለሁ ??
2.አሁን ያሉኝ ሕልሞች እና ግቦች ከጥቂት አመታት በፊት ከነበረው በጣም የተለዩ ናቸውን? ከተለዩ ለምን?
3.አሁን ባለው ህይወቴ ከቀጠልኩ ከአምስት እና ከአስር አመት በኋላ ምን አይነት ህይወት ሊኖረኝ ይችላል??
4.ለስኬት የሚያስፈልገው ፅኑ ፍላጎት ፣ ቁርጠኝንት እና ትጋት አለኝ ወይ፤ ከሌለኝ ለምን?
5.ህይወቴ ውስጥ ደስታ፣ ሰላም እና ፍቅር አለ ወይ? ከሌለኝ ለምን?
6.በህይወቴ የተሰጠኝ ፀጋ ፣ክህሎት ወይም ተሰጥዖ ምንድነው?? እንዴትስ ልጠቀምበት አስቤያለሁ??
7.በምኖርበት ማህበረሰብ ውስጥ ምን አስተዋጽኦ አድርጌያለሁ? ከዚህ በኋላስ ምን ለማድረግ አስቤያለሁ?
8.መጥፎ ልማዶች(ሱስ) አለብኝ ወይ?? እንዴት ነፃ መሆን እችላለሁኝ?
ሌሎችን ለማስተማር ሼር ያድርጉ
Important questions of life
The questions below are meant to be a starting point for you, you can create your own questions.
1. What is the purpose and vision I want to achieve in my life?? Where do I want to find myself in five or ten years??
2. Are my dreams and goals different now than they were a few years ago? If different, why?
3. If I continue with my current life, what kind of life will I have in five or ten years?
4. Do I have the strong will, commitment and dedication needed for success? If I don't have it, why?
5. Is there happiness, peace and love in my life? If I don't have it, why?
6. What is the grace, skill or talent given to me in my life? How am I supposed to use it??
7. What have I contributed to the society I live in? What do I plan to do next?
8. Do I have bad habits? How can I be free?
Share to teach others
Jeson Habtishe...
🤔🤔 ወይ መፍቀድህን አቁም ወይም ንጭንጭህን አቁም!
አንድን ነገር መቆጣጠር ስትችል እንዲሆንብህ እየፈቀድክ ከዚያ ደግሞ በሁኔታውና በውጤቱ መነጫነጭ ታላቅ አባካኝነት ነው፡፡ አንድ ነገር እንዲሆን የምትፈቅድ ከሆነ በዚያ ምክንያት ስለሆነብህ ነገር መነጫነጭ ማቆም አለብህ፡፡ በአጭሩ፣ እንዲሆን ስለፈቀድከው ነገር አትነጫነጭ፡፡ በኋላ እንድትነጫነጭ የሚያደርግህን ነገር ደግሞ መጀመሪያውኑ መፍቀድን አቁም፡፡
አንድ ነገር እንዲሆንብህ አንተው እየፈቀድክ በኋላ ስትነጫነጭ ሁለት ነገር ነው የምትከስረው፡- የሆነብህ ነገር ያመጣው ክስረትና ከዚያም በመነጫነጭህ ምክንያት የምታባክነው የጊዜና የስሜት ብክነት፡፡
ለምሳሌ፣ “ሁል ጊዜ ገንዘብ ተበድሮኝ አይመልስም” . . . “ሁል ጊዜ እቃ እየወሰደ አያመጣም” . . . “ሁል ጊዜ ሚስጥሬን ስነግራት ለሌላ ሰው ትናገርብኛለች” . . . “ሁል ጊዜ ይቅርታ ትጠይቀኝና መልሼ ሳምናት ያንኑ ጥፋት ትደጋግማለች” እና እነዚህን መሰል ንጭንጮች ካሉበህ ወይ ተግባርህን አቁም፣ ወይም ደግሞ በተግባርህ ቀጥልና ንጭንጩን አቁም፡፡
አንዳንድ ጊዜ ከአቅማችን በላይ በሆነ መልኩ ነገሮች እንዲሆኑ የመፍቀዳችን እውነታ እንደተጠበቀ ሆኖ፣ አንድን ነገር እየፈቀድን ስንነጫነጭ ግን ወይ አስመሳይነት ነው ወይም ደግሞ አጠቃላይ የህይወት ሂደት ግንዛቤ የጎደለን አይነት ሰዎች ነን፡፡
የሆነብህን ወይም ሰው አደረገብኝ ብለህ የምታስበውን ነገር በሚገባ አጢነው፡፡ ሁኔታው ወደመሆን እንዲመጣ ፈቃድ የሰጠኸው አንተ ከሆንክ ያለህ ምርጫ ከሁለቱ አንዱ ነው፤ ወይ መፍቀድን ማቆም ወይም ደግሞ መነጫነጭን ማቆም፡፡
❤️UNITED GOD KINGDOM❤️
በዶ/ር ኢዮብ
Jeson Habtishe...
❤️@Kingdeom
❤️@Kingdeom1
...ብዙ ሰዎች ህልማቸውን፣መኖር ያቃተቸው ሰዎች ምን ይሉኛል፣በሚል ይሉኝታ ነው።..ሰዎች አናንተን ከመተቸት፣ከማስፈራራት፣ከሀሜት፣ከፋገራ፣ያለፈ ምን ሊያደርጓቹ ይችላሉ..?እንግዲህ ስጋን፣መግደል የምሚችሉትን አትፍሩ።......ህልማችሁን ለመፍጠር የምትንቀሳቀሱበት ጊዜ አሁን ነው።
...Many people say to me, "What do people say to me who have failed to live their dreams?"...What can people do to you other than criticize, threaten, gossip, defecate...? So don't be afraid of those who can kill your dreams. Now is the time to get creative.
JESON Habtisge...ሼር ያድርጉ
...This world, your existence, is the beginning and the end. What you are living for once and for the last time. You have no chance to be created again. Give yourself enough time and listen to your inner self, why you were created.
...ይችህ አለም፣የመኖራችሁ፣ መጀመሪያም፣መጨረሻም ናት።እየኖራችሁ ያላችሁት ለአንዴ እና ለመጨረሻ ጊዜ ነው።ድጋሚ የመፈጠር እድል የላችሁም።ለራሳችሁ በቂ ጊዜ ስጡና፣ለምን እንደተፈጠራችሁ ውስጣችሁን አዳምጡ። Jeson Habtishe..
👉👉 ወደፊት ተመልከት🧐🧐🧐
UNITED GOD KINGDEOM
በአዲስ የህይወት ጎዳና ላይ መራመድ ትችላለህ፡፡ አሁን በመጣልህ ማስተዋል ተጠቅመህ የዛሬውን እና የነገውን ህይወትህን መለወጥ እንደምትችል እመን፡፡
ትኩረትህ በትናንት ላይ ሳይሆን በነገ ላይ ይሁን፡፡ ያለፈውን የህይወት ዘመንህን ቆርጠህ መጣል አትችልም፤ የህይወትህ ታሪክ ነው፡፡ ሆኖም አቅጣጫህን ወደ ኋላ ሳይሆን ወደፊት ማድረግ ትችላለህ፡፡
በአዕምሮህ ነገን እና ወደፊትን ከተመለከትህ ትናንት ከአንተ ኋላ ይሆናል፤ በአዕምሮህ ትናንትን የምትመለከት ከሆነ ደግሞ ፊትህ ወደ ትናንት ጀርባህ ደግሞ ወደ ነገ ይሆናል፡፡ አንተ ትናንትን በማሰብ ሳይሆን ነገን በማሰብ ደስተኛ ልትሆን ትችላለህ፡፡ በትናንትህ ውስጥ የሚታጨድ መልካም ነገር የለም፤ በነገ ውስጥ ግን ደስታን ሊያመጣ የሚችል ተስፋ አለ፡፡ ትናንት ጨለማ ነው፤ በነገ ውስጥ ግን የህይወት ብርሃን ተስፋ ይኖራል፡፡ ስለዚህ "ከእኔ ትናንት ይልቅ የእኔ ነገ ተስፋ አለው" የሚል እይታ ይኑርህ!
ሰናይ ቀን🙏🙏🙏
@Kingdeom1
@Kingdeom
UNITED GOD KINGDEOM
🌎🌍🌏🌍🌎🌎🌍🌏🌎🌍🌏
ስላም ለእናንተ ይሁን የተከበራችሁ የUNITED KINGDOM ቤተሰቦች፣ላልተወሰነ ጊዜ በተፈጠሩ አንዳንድ ምክንያቶች በጉሩፑ ውስጥ፣የነበረንን እንቅስቃሴ፣አቁመን ነበር። ነገር ግን ይህ የተፈጠረው ክፍተት የተስተካከለ ስለሆነ፣ ቀድሞ ይሰራ እንደነበረው አስተማሪ እና ገንቢ ምክሮች፤እና ሀሳባዊ ትምህርቶች፣በአዲስ ይዘት እና አቀራረብ፣ወደ እናን የምናቀርብ መሆናችንን ስንገልፅ፣በደሰታ እናሳውቃለን።....
አሁን ባለን አሰራር መሰረት፣አስተማሪ እና ገንቢ፣ሀሳብ በውስጣችሁ፣ያለ ወንድሞች እና እህቶች ይህንን አድል፣እንድትጠቀሙ የጋበዝን መሆናችንን እናሳውቃለን።.....
ለበለጠ መረጃ ..👉0992088207
በመደወል፣መስራት የምትችሉ መሆናችንን እናሳውቃለን።...
👉 @Kingdeom
👉 @Kingdeom1
ሊንኩን በመጫን አሰና ሼር በማድረግ ቤተሰብ ይሁኑ።...
🤔..በክርስቲያንኖች ህይወት ውስጥ፣ሴይጣን መኖር አይችልም
፣ነገር ግን ..👉እርሱን የሚጋብዙት እነርሱ ናቸው።..የስጋ ስራ፣ሴ
ይጣንን ወደ ህይወታችን የምንጋብዝበት የጥሪ ካርድ ነው።..
..🤔ሰዎች ስለ አንተ፣የሚያስቡት ነገር ያንተ ጉዳይ አይደለም።.
..ብዙ ሰዎች ውስጣዊ፣ቅንነትህን እና የዋህነትህን ሳያውቁ ብዙ፣
ነገር ስለ አንተ ይላሉ።እውነታው ግን ሰዎች ስለ አንተ የሚያወሩት
እነርሱ የሚያስቡትን እንጂ፣አንተ የሆንከውን አይደለም። ...
🤔ቆንጆ ብትሆን፣..ይሄ ሴሴኛ፣ወይም ባለጌ ይሉሀል
🤔የፊት ገፅታህ ባያምር፣ይሄ ደግሞ፣አስጠሊታ፣ምኑምየማያ
ምር ይሉሀል።
🤔ገንዘብ ቢኖርህ፣🤑 ይሄ ደግሞ ግፈኛ፣ምን አለበት ለድ
ሆች ቢሰጥ ይሉሀል፣ ሆዳም ይሉሀል።
🤔የምትሰራው ነገር ቢበላሽብህ፣ወይም ብትከስር በቃ አይነሳም
ባዶ ሆነ ይሉሀል።...ፈጣሪ እየቀጣው ነው ይሉሀል።
🤔አምሮብህ ብትለብስ ምን አዘነጠው፣ይሉሀል
🤔ልብስ ሳይኖርህ፣ያገኘኸውን ብትለብስ፣ይሄ ለማኝ ይሉሀል
🤔ስትበላ ለምን፣በላህ .....!..ሳትበላ ስትቀር ደግሞ የሰው
ምግብ የማይበላ፣ጋኔን ያለበት ይሉሀል።
🤔ተጫዋች ስትሆን፣ልበ ቢስ ቁም ነገር የሌለብህ ይሉሀል።
🤔ቁም ነገረኛ ስትሆን ደግሞ፣ምን አዋቂ ነኝ ይሉሀል።
🤔ከእህትህ ወይም ከወንድምሽ ጋር ስትዝናኑ ቢያዩ፣ፍቅረኛ
እያለችው ይልከሰከሳል ይሉሀል።
😍ነገር ግን ከሰዎች፣እሚጠቅምህን እና ውስጥህን እንድታሳ
ድግ እሚረዳህን መልካም ምክር፣ተቀበል።
...ራስህን ሁን...ለማንም ስትል የምትጀምረው እና የምትጨርሰ
ው ነገር አይኑር።👉..ውስጥህን ልብህን ብቻ ተከተል።
❤❤❤@Kingdeom
@Kingdeom1...ሊንኩን በመጫን ይቀላቀሉ።
🌎UNITED GOD KINGDEOM🌎
በተስፋ መሞላት!
ሁሉም ነገሮች የሚሆኑት በምክንያት ነው፤ ስለማትቀይራቸው ነገሮች አብዝተህ አትጨነቅ! እንደዛ እያደረክ ከሆነ ግን ንፋስን እየተከተልክ ነው፤ ስለዚህ የትም አትደርስም! ወዳጄ ሌላውን ትተህ ስለምትቀይረው ነገር ብቻ አስብ፤ ያኔ መንፈስህ ይረጋጋል ጭንቀት ይራገፋል ተስፋ ትሞላና ሁሉን ነገር ትቀይራለህ።
ለአስተያየት @sideinfo📩
@kingdeom
👉ብሩህ ቀን ይሁንላችሁ🙏
ሀያሉ ማንነትህ!
የህይወት ፈተናዎች የሚደጋገሙት ማን እንደሆንክ ይበልጥ እንድታውቅ ነው፤ በተለይማ መቋቋም ሲያቅትህ ሊበረቱ ይችላሉ።
ብረት እንደ ጋለ ነው የሚቀጠቀጠው ምክንያቱም ያኔ የምንፈልገውን ቅርፅ ለማስያዝ ይመቻል። አንተም በደስታህ ወራት ፀባይህን ህይወትህን ማሻሻል ላይታይህ ይችላል ትዘናጋለህ፤ ፈጣሪ ሊያነቃህ ፈተናዎችን ይልካል ካልሰማህ ሌላም ይጨምራል እንደ ጋለ ነው ሚቀጠቀጠው ያልኩትን አትርሳ።
ታዲያ ምን ይሻላል? መፍትሄው ፈጣሪ ምን ሊያስተምረኝ ነው ብሎ ማሰብ፤ ከዛ በዚህ ከባድ ፈተና ውስጥ ግዙፉና ሀያሉ ማንነትህ ሲወጣ ታየዋለህ! የምድራችን ታላላቆች ይሄን ነው ያደረጉት።
ለአስተያየት @sideinfo📩
@Kingdeom1
የማይጠገብ ቅዳሜ ተመኘሁላችሁ
የመጨረሻው ዘመን
ክፍል-3
...እኛ በምድር ላይ ያለን
የክርስቶስ አካል የሆንን ቤተክርስቲያን እዚህ እስካለን ድረስ በክርስቶስ የተሰራውን ስራ እየገለጥን የምንኖር የትንሳኤው አካሎች ነን፡፡ በ1ኛ ቆሮ 15 ላይ እኔ ደግሞ የተቀበልሁትን ከሁሉ በፊት አሳልፌ ሰጠኋችሁ እንዲህ ብዬ፦ መጽሐፍ እንደሚል ክርስቶስ ስለ ኃጢአታችን ሞተ፥ ተቀበረም፥ መጽሐፍም እንደሚል በሦስተኛው ቀን ተነሣ፥ ብሎ እንደሚናገረው በእየሱስ ሞትና ትንሳኤ የተሻሩ እና የተገለጡ ሕይወቶች አሉ፤ ቤተክርስቲያን በምድር የትንሳኤን ሕይወት በምድር እየተለማመደች ስትመጣ ጌታ እየሱስ በመስቀል ጣር ያስወገዳቸው የጨለማው የህይወት ስርአቶችን ወደ ክርስቶስ ፍፁም ሙላት በማደግ እያሸነፈች ስትመጣ ድህነት፣ ሃጢያት፣ ሞት በስጋ ይሻራሉ፡፡
ሞት በሰው በኩል ስለ መጣ ትንሣኤ ሙታን በሰው በኩል ሆኖአልና። ሁሉ በአዳም እንደሚሞቱ እንዲሁ ሁሉ በክርስቶስ ደግሞ ሕያዋን ይሆናሉና። ነገር ግን እያንዳንዱ በራሱ ተራ ይሆናል፤ ክርስቶስ እንደ በኩራት ነው፥ በኋላም በመምጣቱ ለክርስቶስ የሆኑት ናቸው፤ በኋላም፥ መንግሥቱን ለእግዚአብሔር ለአባቱ አሳልፎ በሰጠ ጊዜ አለቅነትንም ሁሉና ሥልጣንን ሁሉ ኃይልንም በሻረ ጊዜ፥ ፍጻሜ ይሆናል። ጠላቶቹን ሁሉ ከእግሩ በታች እስኪያደርግ ድረስ ሊነግሥ ይገባዋልና። 1ኛ ቆሮ 15፡21-25
በዚህ ክፍል እንደምናየው ጌታ እየሱስ አንድ ቀን እንደተቀጠረለት እናያለን ጠላቶቹን የእግሩ መረገጫ እስኪያደርግ ድረስ … ይላል ያን ጊዜ ፍጻሜ ይመጣል፡፡ እየሱስ ያለሸነፈው ጠላት የለም ነገር ግን ቤተክርስቲያ በእርሱ ያላትን እምነት እያደገ ሲመጣ በተራዋ ሞትን ታሸንፋለች፡፡ እስካሁን ድረስ ከእየሱስ በስተቀር ሞትን በስጋው ያሸነፈ የለም፤ ነገር ግን በመጨረሻ ቤተክርስቲያን ሞትን በስጋዋ ታሸንፋለች ያን ጊዜ ለአካሉ ማለትም ለቤተክርስርስቲያን ፍጻሜ ይመጣል፡፡
እነሆ፥ አንድ ምሥጢር እነግራችኋለሁ፤ ሁላችን አናንቀላፋም ነገር ግን የኋለኛው መለከት ሲነፋ ሁላችን በድንገት በቅጽበተ ዓይን እንለወጣለን፤ መለከት ይሸነፋልና ሙታንም የማይበሰብሱ ሆነው ይነሣሉ እኛም እንለወጣለን። ይህ የሚበሰብሰው የማይበሰብሰውን ሊለብስ ይህም የሚሞተው የማይሞተውን ሊለብስ ይገባዋልና። ዳሩ ግን ይህ የሚበሰብሰው የማይበሰብሰውን ሲለብስ ይህም የሚሞተው የማይሞተውን ሲለብስ፥ በዚያን ጊዜ፦ ሞት ድል በመነሣት ተዋጠ ተብሎ የተጻፈው ቃል ይፈጸማል። 1ኛ ቆሮ 15፡51-54
ቤተክርስቲያን ድህነትን ሃጢያትን ሞትን መጥላት ያለባት ምድራዊ ስለሆነች ወይም ምድርን ስለምትወድ ሳይሆን በክርስቶስ የተሸነፉትን የትንሳኤውን ህይወት በምድር ላይ እየገለጠች በመምጣት በመጨረሻ የሚሻረውን ሞትን ወደ ማሸነፍ እንድትደርስ ነው፡፡ ንጥቀት ላይ የምትደርሰው ቤተክርስቲያን የጌታን ፍጻሜ ታያለች
ለአስተያየት @sideinfo
@Kingdeom1
-share አድርጉት እየጠቀመችሁ ከሆነ::
👉ብሩሁ ቀን ይሁንላችሁ🙏
...አዲስ የሆነ፣ህይወት በእድል አይመጣም።ህይወታችሁን አዲስ አድርጎ መፍጠር፣የእናንተ ድርሻ ነው።...የምታስቡትን፣ደጋግማችሁ እስካሰባችሁ፣ድረስ...የምትሰሩትን ደጋግማችሁ፣እስከሰራችሁ ድረስ አትለወጡም።ኑሮአችሁም አይቀየርም።
...በምትኖሩት ህይወት፣ደስተኛ ካልሆናችሁ፣የምታስቡትን እና፣ልምድ የሆነ ድርጊታችሁን፣ቀይሩ።የራሳችሁን ህይወት፣ሙሉ በሙሉ ሀላፊነት፣ውሰዱ።በሆናችሁት ባደረጋችሁት፣ስህተት፣ማንንም ተወቃሽ አታድርጉ።ምክንያቱም ስለፈጠራችሁት፣ስህተት፣ኑሮአችሁ አሁን ስላለበት ሁኔታ፣ሌላውን እስከወቀሳችሁ ድረስ፣አትለወጡም።
Jeson Habtishe.
The Year Of Prosperity 💎💎💎💎💎💰💰
...ሴይጣን ሀጢአት፣የሆነበት ""በስህተት ነቅቶ፣ነው።...
..ዙፋን ላይ ቁጭ፣በማለት፣እግዚአብሔርን መሆን የሚቻል መስሎታል።
..ተራራ ቁጭ፣በማለት እግዚአብሔርን፣መሆን የሚቻል መስሎታል።
..✨⭐️ከከዋክብት በላይ፣በመሆን፣እግዚአብሔርን መሆን፣የሚቻል መስሎታል።
..ሴይጣን እግዚአብሔርን፣በማየት" ነቃ"..የነቃው ግን በስህተት ነው።
...እንደ ቀልድ፣የምናያቸው፣ታላላቅ ሀይማኖቶች፣ከአንድ ሰው ነው የጀመሩት።ከሰውዬው ሲጀምሩ፣ሰውዬው፣ያለ ክርስቶስ ነቅቶ ነው፣የጀመረው።
...ክርስቶስ ሳይበራለት፣ሰው ከነቃ፣ሀይማኖት ይፈጥራል።ሰዎች ቀላል እንዳይመስሉአችሁ፣ሀይማኖት መፍጠር ይችላሉ።
...ሀይማኖት ባህርይው እንደዚህ ነው፣መጨረሻው፣ሞት በሆነበት፣አለም ላይ የሚመላለስ ሀሳብ ነው።
...ሀይማኖተኞች ጥቂቶቹ ነቅተዋል፣ብርሀናቸው ግን እንደ ጨለማ የጨለመች ናት።
...🛌አንተ የምትተኛ ንቃ፤ከሙታንም ተነሳ ክርስቶስ ያበራልሀል።
Jeson Habtishe
👉@Kingdeom1
👉@Kingdeom...ሊንኩን በመጫን ይቀላቀሉ።...❤
....don't be like hypocrites when you pray....sometimes there is an answer to the question we ask God.
....ስትፀልዩ እንደ ግብዞች አትሁኑ።....አንዳንዴ እግዚአብሔርን በምንጠይቀውም ጥያቄ ውስጥ፣እኛም የምንመልሰው መልስም አለ።
Jeson Habtishe...
🏃♀️🏃♀️🏃♀️ መንቀሳቀስ 🏃♂️🏃♂️🏃♂️
..UNITED GOD KINGDOM ...
ስኬትና ውጤት ያለ እንቅስቃሴ አይገኝም ፡ ነብር ካልተወረወረ አይዝም፣ ቀስት ካልተስፈነጠረ አያድንም፣ ሰይፍ ካልተሰነዘረ አይገድልም።
👉 ተንቀሳቀስ
👉 አትተኛ ለረጅም ጊዜ የተኛ ውሃ ይሸታል።
👉 በቦታው ለዘመናት የቆየ ድንጋይ አንድ ቀን ይፈለጣል።
👉 ሽቶ ጫን ጫን ሲሉት ነው ጥሩ እሚሸተው።
👉 ሰንደል ሲያቃጥሉት ነው አከባቢን እሚያውደው።
የሰው ልጅም በችግሮች ሲደበደብ ካልሆነ ጥሩ ጠረን አይወጣውም። ያለ ጥረትም ከስኬት ጫፍ አይደረስም ህይወትን የታገላት ነው የሚያሸንፋት።
ህይወት ሩጫ ናት። የስኬት ገበያ ሁሉ ውድድር አለው። መጀመረያ የጨሰ ነው ሇላ ብርሃን የሚወጣው። ፈጥነህ ከመኝታህ ተነስ ተሽቀዳደም የዛሬን ውሀ እንደዛሬ ጠጣው እንደትላንት ከጠጣኸው መምረሩ አይቀርም። አስተውል ያደረ ይበላሻል ያደረ አፋሽ ላለመሆን ፈጥነህ ቀንህን ተመስገን ብለህ ጀምር!
መልካም ምሽት..❤❤
@Kingdeom1
@Kingdeom....ሊንኩን በመጫን ይቀላቀሉ።....
...Change does not happen by chance or chance....Your life starts from inside you. Your lifestyle and actions are created by the thoughts that your mind holds. You don't have to, turn your thoughts into actions, if you can't, you'll stay where you are. jeson habtish...
...ለውጥ በአጋጣሚ እና በእድል አይሆንም።...
ህይወትህ የምትጀምረው፣ከውስጥህ ነው።አኗኗርህ እና ድርጊትህ
የሚፈጠረው፣አእምሮህ በተያዘበት ሀሳብ ልክ ነው።የምትኖረውን
ኑሮ ለመቀየር፣ከፈለክ የምታስበውን፣እና የምትውላቸውን ሰዎች መቀየር አለብህ።....አንድ ነገር መርሳት፣የለብህም፣የምታስበውን
ነገር ወደ ድርጊት መለወጥ፣ካልቻልክ ባለህበት ትቀራለህ።
Jeson Habtishe....
🤯🤯ውስጣዊ፣ የእውቀት ዕድገት
🕊🕊🕊🕊🕊🕊🕊🕊🕊🕊🕊
ነገሮችን የምንረዳው በእውቀታችን መጠን ነው፡፡እውቀታችን የሚያድገው በንባባችን ልክ ነው፡፡ የአረዳድና የገጠመኝ መለያየት እስካለ ልዩነት አይቀርም፡፡ ከንባብ ተፋተህ ፤ከእውቀት ተራርቀህ ከከረምክ በተራ ጉዳዮች አእምሮህ ተወጥሮ ይውላል፡፡ የዘር ፣የቀለም ፣የእኔነት ፣የደም ፣የሃይማኖት ነገሮች ራስ ምታት ይሆኑብሃል፡፡
@Kingdeom
@Kingdeom 1
ግንዛቤህ እያደገ ከመጣ ከእኔነት ጣጣ ትፋታለህ፡፡ በህይወት ውስጥ ለቁምነገር እንጂ ለተራ ነገሮች መጨነቅ ታቆማለህ፡፡
ይበልጥ የሚያውቅና እየመጠቀ የሚሄድ ሰው ሰላማዊ ፣ትዕግሥተኛ ፣አንድነትን ፈላጊ፣ከእኔነት የሚጣላ ይሆናል፡፡ በሁሉም ነገር የኔ ሃሳብ ብቻ ነው ትክክል የምትል ከሆነ ጤና ጎድሎሃል፡፡ በንባብ ታከም፡፡
የተለያዩ አመለካከቶችንም ተቀበል፡፡ ተወያይ ፤ያንተንም ሃሳብ በአማራጭነት አቅርብ፡፡ የሌላውንም ስማ ፣ ሌላውም እኮ መመዘኚያ አለው፡፡ ሃሳብህን በትህትና አቅርብ፡፡ በትምክህት አትወጣጠር ግትር አትበል፡፡ እልህና ግትር ያለ ባህሪህ አይደለም ሃሳብህን ራስህንም ያሽቀነጥርሃል፡፡ ብስለት ያለው ሰው በጥበብ ነው የሚያስረዳው፡፡ ባዶ ሰዎች ለታይታ ይሮጣሉ፡፡ ዝም ያለ ሁሉም አዋቂ አይደለም፡፡ ለሰዎች መልካም የሆነውን በዝምታ ወይም በጥድፊያው ሳይሆን በሥራው ታገኘዋለህ፡፡
ሰናይ ቀን🙏🙏🙏አመሰግናለሁ ..
UNITED GOD KINGDEOM
🌎🌏🌍🌍🌏🌎🌎🌏🌍🌍🌏🌎
@Kingdeom
@Kingdeom1
Jeson Habtishe
ሼር ማድረግን፣አይርሱ
Everything starts from within.... Be calm. Give yourself enough time to listen to yourself, and be calm instead of being driven by your disturbing emotions..
Jason Habtishe
ሁሉም ነገር የሚጀምረው ከውስጥህ ነው።...የተረጋጋህ ሁን።በአእምሮህ ውስጥ በሚፈጠሩ የተረበሹ ስሜቶችህ ከመመራት ይልቅ ራስህን ለማድመጥ፣እና የተረጋጋ ለመሆን ለራስህ በቂ ጊዜ ስጥ።
...Jeson Habtishe
❤UNITED GOD KINGDEOM❤
# ማንነትን አለመዘንጋት
🦆🦆🦆🦆🦆🦆🦆🦆🦆🦆
"ዳክዬዎች በሚኖሩበት ሥፍራ ውስጥ የሚኖር አንድ ባለ ረጅም አንገት ፍጡር ነበር። ይህ ፍጡር ቡናማ ላባዎች ነበሩት ዳክዬዎችን ለመሆን የተቻለውን ጥረት ቢያደርግም ዳክዬዎችን ለመሆን አልቻለም። እደነሱ መሄድ፣ እደነሱ መናገርና እደነሱ መዋኘት አልቻለም። ከጥረቱም ባለፈ ራሱን እንደ ዳክዬ አድርጎ መመልከት ጀመረ። ሆኖም በአንድ አጋጣሚ የሱን ዓይነት ሰጎን ሲያይ ዳክዬ የመሆን ልፋቱ ከንቱ እደሆነ ተገነዘበ።
@Kingdeom
@Kingdeom1
አሁን በምትመሩት ህይወት ደስተኛ ያልሆናችሁበትን ማንኛውንም ነገር የመለወጥ ኃይሉ አላችሁ። ወደዚህ ዓለም ስትመጡ የማያልቅ ፍላጎትንና ፈጣሪ መንፈስን ይዛችሁ እንደሆነ አትዘንጉ! እነዚህ ጥንካሬዎች አሁንም ድረስ አላችሁ። ከእናንተ የሚጠበቀው ፈልጎ ማግኘት ብቻ ነው። ለመጪው ህይወታችሁ ስኬት የሚረዷችሁን ቁልፎች ለማግኘት ያለፈ ህይወታችሁን ተመልከቱ። በመቀጠልም ፍላጎቶቻችሁን ለማሳካት ምንም ዓይነት ገደብ እንደሌለባችሁ በማመን ወደፊት ተጓዙ። በርግጥም እስካላመናቹ ድረስ የምትፈልጉትን ለማሳካት ገደቦች የሉም።
ወላጆቻችንና መምህራኖቻችን በቀና ስሜት ከምንፈልገው የስኬት ጫፍ እንዳንደርስ የይምሰል ገደቦችን በመፍጠር ተፅዕኖ አድርገውብን ሊሆን ይችላል። እነዚህ አሉታዊ እምነቶቻችንን መለወጥ እንችላለን። የምትፈልጉትን ትምህርት ለመማርና ዝንባሌዎቻችሁን መቀየር ትችላላችሁ። አሁንም በርካታ የፈጣሪነት ክህሎት ስላላችሁ የፈጠራ ክሕሎቶቻችሁን ተጠቀሙባቸው። እናንተ ዳክዬ ለመሆን የሚጥረውን ሰጎን አይደላችሁም።
አዎንታዊና ትክክለኛውን መንገድ ምረጡ። ላለፉት መሰናክል የሆኑባችሁን ነገሮች በማወቅ መንገዳቹን ጀምሩ። ወቀሳ፣ ፀፀትና የጥፋተኝነት ስሜቶች በነበራችሁበት ስለሚያስቀራችሁ አስወግዷቸው። ጥልቅ ፍቅርና ፍላጎት ባላችሁ ነገር ላይ በማተኮር በህይወታችሁ ለማግኘትና ለማሳካት የምትፈልጓቸውን ምርጥ ነገሮች ሁሉ አግኙ። እራሳችሁን መሆናቹን ለቅፅበትም ቢሆን አትዘንጉ።
ሰናይ ቀን🙏🙏🙏
😍UNITED GOD KINGDEOM😍
Jeson Habtishe..
ሼር ማድረግን፣አይርሱ...
........👉ስጋን ሳይሆን አእምሮን አግቡ።...ቁመናን ሳይሆን ስብእናን አግቡ።..........................
ዳሌን ሳይሆን የተዋበ ልብን አግቡ።..🏃♀️🏃♂️................
............ገንዘብ ያለው ሁለ፣ሀብታም አይደለም።.....የተረጋጋ ውስጣዊ ስብእና እንጂ፣ገንዘብ ብቻውን የተረጋጋ ህይወትን አይፈጥርም።........
............ገንዘብ የሌለው ሁሉ ደሀ አይደለም።....ረዳቱቱ እንድትሆኚለት፣አምኖ ወደ ህይወቱ የጋበዘሽ ሰው፣የናጠጠ ደሀ እንኳ
ቢሆን፣በአንቺ ምክንያት ታላቅ ሰው ሆኖ መነሳት ይችላል።.............
👫👫👫👫👫👫👫👫👫👫👫👫👫👫👫👫👫👫👫
JESON Habtishe
🤔.ሰዎች ስለ እኔ ምን፣ይሉ ይሁን..? በሚል ሀሳብ ውስጥ ሆነህ
እስረኛ አትሁን።ሁሉም ሰው በራሱ የህይወት ትግል ውስጥ፣የተ
ጠመደ ነዉ።.ወጣት ሳለህ፣ሰዎች ስለ እኔ ምን፣ይሉ ይሁን በሚሉ
ሀሳቦች ተጠምደህ ትጨነቃለህ፣ እውነታው ግን በህይወት ማብቂ
ያ በእርጅናህ ጊዜህ ላይ፣ማንም ስለአንተ እንደማያስብ እና እንደ
ማይጨነቅ እወቅ።...ሰዎች ስለ አንተ የሚያስቡት ነገር፣የአንተ ጉዳይ አይደለም።...
🤔..ብዙዎቻችን በህይወታችን ውስጥ፣ብዙ ስህተትን ውድቀትን
አሳልፈናል..አንዳንዶቻችን በመጠጥ፣ስካር..አንዳንዶቻችን በዝሙ
ት ሀጢአት፣እና እርኩሰት..ብዙዎቻችን ደግሞ መተው ስንችል፣መ
ተው ባቃተን ሱስ ውስጥ፣ገብተናል..በporno ግራፊ፣ከጓደኛችን
ከምንወደው ሰው ጋር መተው ያቃተን፣የተለያየ ወሲብ፣የእርኩሰት
ልምምድ ውስጥ ወድቀን ይሆናል።
🤔ለማንም ማውራት የማትችላቸው፣ነገር ግን ከብዙ ሰዎች፣ደብ
ቀህ፣የምትይዛቸው ብዙ ሚስጥሮች አሉሁ።..ህይወትህ እንዲቀየ
ር ብዙ አስበህ፣ከገባህበት እስራት ነፃ ልትሆን አቅቶህ ተስፋ ቆር
ጠህ ይሆናል።..ግን አንድ ሀሳብ ልስጥህ..😎😎
...ወደ ውስጥህ ተንፍስ፣ለሌሎች ከምትሰጠው ጊዜ ባሻገር፣ለራ
ስህ በቂ ጊዜ ስጥ። ከእውነተኛ ማንነትህ ጋር፣ተነጋገር።..ሰዎች እንዳያውቁት ከምትፈራው፣ማንነትህ ጋር በግልፅ፣ተነጋገር።
ውስጥህን ተከተል፣ ሌሎችን ለመምሰል ስትል የጣልከውን፣እወነ
ተኛ ማንነትህን፣አንሳው። በራስህ አትፈር።.ለሌሎች ለመኖር ስታስ
ብ አስቀድመህ፣ራስህን ሆነህ ኑር።...
ሼር ማድረግን አይርሱ...Share ያድርጉ..
Jeson Habtishe..
❤@Kingdeom1
❤@Kingdeom
👆👆Join us
🌎UNITED GOD KINGDEOM🌍
ወደ አምላክ ተጠጋ!
አለም ካከበረው ፈጣሪ ያከበረው ይበልጣል ምክንያቱም ሰዎች ውጪህን ያያሉ ፈጣሪ ግን ልብህን ያያል፤ ከአምላክህ ጋር ስትጣበቅ ጉድለት የለም፤ ሰዎች መረጋጋትህን አይተው ያከብሩሀል፤ ሳር ቅጠሉ ላንተ ያጎነብሳል፤ ከምንም በላይ ህሊናህ ከዚህ አለም ጭንቀትና ፍርሀት በሰላም ያርፋል።
መዝናናት ጊዜያዊ እረፍት ይሰጥህ ይሆናል፤ ከሰዎች ጋር ስትቀላቀል ችግርህን ለጊዜው ትረሳው ይሆናል፤ ግን ወዳጄ የዚህን አለም አድካሚ ሸክም ከአይምሮህ የምታወርደው ወደ ፈጣሪህ ስትጠጋ ብቻ ነው!
👉ለየቱም አስተያየት
@sideinfo📩📩
@kingdeom1
የሚገርም ሰንበት ይሁንላችሁ
ዛሬ በእጅህ ነው!!🖐
ትላንት ትውስታ ነው፣ ነገ ተስፋ ነው። ግን ዛሬ ለምትፈልገው አላማ ትዕዛዝህን እየጠበቀ ነው። እና የምትፈልገውን ነገር ለማሳካት ከዛሬ የተሻለ ጊዜ የለም!!
ለአስተያየት @sideinfo📩
@Kingdeom1
መልካም የግዜ አጠቃቀም
አንተ ትለያለህ!
ራስን በመውቀስ ህይወት አይቀየርም! እንደውም ብሶብህ ስህተትህን መደጋገም እጣ ፋንታህ ነው የሚሆነው፤ ራስህን አትውቀስ!
ቀንህ እንዲያምርና ደስ ብሎህ እንድትውል ከፈለክ እስከዛሬ ያለፍካቸውን የህይወት ፈተናዎች አስብ፤ አንተ ባትሆን ኖሮ እነዛን ከባድ ጊዜያት ማን ያልፍ ነበር?! ስለዚህ ድንቅ ነህ ወዳጄ! አንቺም እኮ የማይታሰበውን ነው ያለፍሺው ስለዚህ እህቴ አንቺም ልዩ ነሽ!
ለአስተያየት @sideinfo📩
👉@kingdeom1
🙏 ልዪ አርብ ይሁንላችሁ🙏
የመጨረሻው ዘመን
ክፍል- ሁለት
።።።።።።።
👉የጌታ መምጣት ምልክት
ባለፈው ሳምንት እንደተመለከትነው የመጨረሻው ዘመን ከቤተክርስቲያን አንጻርና ከዓለም አንጻር በሁለት ከፍለን ለይተን ማየት ይኖርብናል፡፡ የመጨረሻው ዘመን ለዓለም ስጋት፣ ፍርድ ጦርነት፣ጭነቀት ሲሆንባት ለቤተክርስቲያን ግን ክብር፣ ሌላ ሕይወት የመሲሁ ዳግም ምጽዓት እንደሆነ ማወቅ አለብን፡፡
👉ቤተክርስቲያን በመጨረሻው ዘመን በጭንቀት፣ በፍርሃት በውርደት አትጨርስም፤ ቤተክርስቲያን በአሸናፊነት በድል እና በመጨረሻ የመንግስት ወንጌል ይሰበካል የተባለው ነው የሚፈጸምባት፡፡ ቤተክርስቲያን ሃይላት እና ስልጣናትን ሳትሽር ለዓለም በክብር ሳታበራ መጨረሻው አይመጣም፤ በጣም ብዙ ሰዎች መጨረሻው የሚመጣ የሚመስላቸው ለዓለም የተነገረውን ትንቢት በማየት ጦርነት፣ረሃብ፣የዕውቀት መብዛት ነው፡፡ ነገር ግን እነዚህ በዓለም ላይ ላሉ ሰዎች ምልክት እና ለቤተክርስቲያን ደግሞ የምጥ ጣር መጀመሪያ ናቸው፤ ነገር ግን እስከ መጨረሻው የሚፀና የትንሳኤውን መንግስት በምድር ገልጠን ነው መጨረሻው የሚመጣው፡፡....✍✍
፦ይቀጥላል።
ለአስተያየት @sideinfo
@Kingdeom1
share አርጉት እየጠቀማችሁ ከሆነ
ብርሩ ቀን ይሁንላችሁ🙏