knowelg | Unsorted

Telegram-канал knowelg - Ethio dreams

-

ማንኛውም አስተያየት በ @Geberye_1 አድርሰን

Subscribe to a channel

Ethio dreams

ስልክ ጢርርር

📱"አቤት"

☎️"አንተ ምናባህ ሆነህ ነው እንደዚህ የጠፋኸው!?"

|ቃ ቃ ቃ ሽንኩርት
ስትከትፍ

📱"ምን ባክሽ ስራ እያሯሯጠኝ ..." ▣ ..."

☎️" "ስልክ መደወል እስኪያቅትህ ድረስ ስራ በዝቶብህ?"

📱"ያው ታውቂው የለ የአዲስ ስራን ነገር...ዛሬ ግን በምን ትዝ ብዬሽ ደወልሽ?''

☎️"እእእ...ቅድም ሶደሬ ላይ የሆነ ፊልም እያየሁ እኮ.. ልክ እንዳንተ ለፍላፊ የሆነ ካራክተር ሲመጣ ትዝ አልከኝና የታባቱ ጠፍቶ ይሆን ብዬ ደወልኩልህ...

📱" [ትሽሽሽሽ የምታቁላላው ሽንኩርት ላይ ውሃ ጠብ ስታደርግ

፨📱 "እእእ እንደዛ ነው?"

☎️"አዎ"

📱"አለሁ ምን እሆናለሁ... የት ሆነሽ ነው አንቺ? አሁንም እዛው ቤት ነሽ አ?''

☎️"አዎ እዛው ነኝ...ምናባህ አንተ እኮ ልምጣ ልትል ይሆናል አታፍርም!"

[ስታማስል...ሽሮ እየሰራች ነው።

📱"ኧረ አይደለም... ጨዋታውን ካመጣሺው ግን መጥቼ ባይሽ ደስ ይለኛል"

☎️"አ አ...አይቻልም"

📱"ለነገሩ ተዪው ... ልምጣ ብልም መንገዱ ራሱ ትዝ አይለኝም"

☎️ "ወገኛ...በእንትና ሱቅ ጋር ታጥፈክ የእንትናን ፀጉርቤት እልፍ ብለክ ያለው ት/ቤት ጎን እንደሆነ ጠፍቶክ ነው?"

📱 "አሃ አሁን መጣልኝ... ከመጣሁ ስለቆየሁ ጠፍቶብኝ ነበር... እና በቃ ልምጣ አ?''

☎️ " "ኖ ኖ አይቻልም አልኩህ እኮ"

📱"ለነገሩ ተዪው...ይሄኔ ባልሽ ሶፋ ላይ ተከምሮ ኢሳት እያየ ነው"

☎️"ውይ የመቼህን?? ተፋታን እኮ... እሱም እዛው ሞያሌ ገባ እኔም ልጆቼን ለእናቴ ሰጥቼ ብቻዬን ፈልሰስ እልልሃለሁ"

📱"የምርሽን ነው?? በስማም የሚገርም ነው!.... እና በቃ ልከሰታ?''

☎️ "አይቻልም አልኩህ እኮ ሰውዬ!"

📱"እሺ ገባኝ"

☎️ "ምኑ ነው ሚገባህ??"

📱 "ደህንነቴን ለማረጋገጥ ብቻ እንደደወልሽ"

☎️""እና ሌላ ምንህን ፈልጌ እደውላለሁ!?ናፍቀኸኝ??"

[ወጥ በማማሰያ ስትቀምስ አፏ ላይ ይሰማል።

📱 "አልናፈቅኩሽም?"

☎️"እና ብትናፍቀኝስ??"

📱 "ከሰይጣን ፈጥኜ ልምጣ አ??"

☎️"ኦኦኦ ሰውዬ አይቻልም አልኩልህ እኮ!"


📱"እሺ"

°°°

••••

☎️"ስማማ"

📱"ወዬ"

☎️"ያቺን የምትወዳትን ሽሮ እኮ እየቀመምኩ ነው"

📱"ጎበዝ" "

☎️ከሰብለ ባልትና እንጀራ ገዝቼ መጥቼ አቅርቤ እስክበላ ከደረስክ ትበላለህ”

📱"እና ልምጣ???" 🙄

☎️ "...አዎ ግን ማደር አይቻልም...መጥተህ መመለስ ነው! በዛ ላይ ከብየዳ ቤት ቀጥታ ፍየል ፍየል እያልክ እንዳትመጣ. እዚህ ውሃ ስለጠፋች እዛው ታጥበህ ና!"

📱"እህህ... ሽሮ ልበላ ብቻ አይደል የምመጣው… በብብቴ አልጎርስ ወጥ አልጨልፍ

☎️"አፈር ብላ!!🤬🤬🤬🤬🤬 ...ከፊቴ እንጀራ ልትቆርስ ስትዘረጋ አፍንጫዬ ብብትህን ማሽተቱ ይቀራል??"

📱"እእእ...እሺ በቃ ለቅለቅ ብዬ ስምዘገዘግ ነው ምመጣው"

☎️"ደግሞ ሽሮ መብያህን እንዳትረሳ!"

📱"እሱን ብረሳ ቀኜ ትርሳኝ”

☎️"" "ኧረ ሽሮ ያለቃሪያ ስለማትወድ ቃሪያውን ነው ያልኩህ አንተ ከውካዋ"

📱"ቃሪያውን ነው እንዴ? እሺ መንገድ ላይ ከሚመድቡት ገዝቼ ይዤ እመጣለሁ" "

☎️"ደግሞ የሚያቃጥለውን መርጠህ ግዛ... ጎመን ጎመን የሚል ይዘህ እንዳትመጣ!"

📱"እሺ"😋"

☎️ስማኝ ደግሞ"

📱"እ?"

☎️"ኮንዶምም እንዳትረሳ!”

*ስልክ ንግግሩን ሲያዳምጡ የነበሩ የቴሌ(ሳፋሪኮም) ኦፕሬተሮች*:

Girum👏❤️😂

Читать полностью…

Ethio dreams

የአላማ ሰው መሆን!

"ወዴት መሄድ እንደምትፈልግ ካላወክ የትኛውም መንገድ የሚወስድህ ይመስልሀል" የሚል አባባል አለ። በጣም የሚገርም እውነት የያዘ ነው፤ ህልም ያስፈልግሀል፤ የአላማ ሰው መሆን አለብህ!

እርግጠኛ ነኝ ሁሌም የአይምሮ ሰላም እየተሰማህ መኖር ትፈልጋለህ፤ ወዳጄ አንድ ነገር አርግ 'አጥብቀህ የምትፈልገውን የህይወትህን ጥግ አሁን እወቀው!'

እርካታ የሞላበት ሀሙስ ተመኘንላችሁ🙏
@knowelg
የእናንተው ምርጥ ጓደኛ!

Читать полностью…

Ethio dreams

Ethio dreams
ትልቅ ተመኝ!

የሰው ልጅ ትልቁ ድክመቱ ትልቅ አስቦ አለመሳካቱ አይደለም ትንሽ አስቦ ተሳክቶለት ማቆሙ ነው፤ አንተ አጥብቀህ ፈልገኸው ፈጣሪ ያልሰጠህ ነገር የለም! ካለ ደግሞ ወይ ጊዜው አልደረሰም ወይ የተሻለውን ሊሰጥህ ነው።

ወዳጄ ትልቁ ቦታ ይገባሀል! ትልቅ ተመኝ፣ ትልቅ ጠይቅ ከዛ እሱን ለማግኘት የምትችለውን ያህል ሞክር በተረፈው አምላክ ይጨመርበታል!

ድንቅ ረቡዕ ተመኘንላችሁ🙏
@knowelg
የእናንተው ምርጥ ጓደኛ!

ያመንክበትን አድርገው !

አንተ የታየህ ሁሉም ሰው ይታየዋል ማለት አይደለም ለምን ሀሳቤን አልተቀበሉትም ብለህ ራስህን አትረብሽ መጥፎ ሰው ሆነው ሳይሆን አንተ የታየህ ስላልታያቸው ነው ። ትልቁ ስህተት መሳሳት ሳይሆን ከዚህ በላይ ማድረግ እችል ነበር ብሎ መጸጸት ነው ፤ ያመንክበትን አድርገው።

አንደኛ ቀን ተመኘን🙏
@knowelg
የእናንተው ምርጥ ጓደኛ 😊

Читать полностью…

Ethio dreams

ብዙ ጊዜ ሞባይል ስንገዛ የምንገዛውን ሞባይል ጥራት ለመለየት ስለምንቸገር በቅርብ ያገኘነውን ሰው በመጠየቅ በምስክርነት እንወስናለን ፡፡
የስሞች መብዛትም አንዱ ችግር ነው፡፡ሳምሰንግ ፣ኖኪያ፣ ኤልጂ፣አፕል፣ወዘተ ወዘተ እየተባለ ይሄ ያ ይበልጣል ሙግትም አለ፡፡
እስቲ ለዛሬ ከሞባይል ቀፎ መሰረታዊ ማወዳደሪያ መስፈርቶች ውስጥ ጥቂቶቹን እንይ፡፡
የመጀመሪያው የሞባይል ቀፎ ማወዳደሪያ ኦፕሬቲንግ ሲስተሙ ነው። ለምሳሌ ሳምሰንግ አንድሮይድን ና ቴክኖ አንድሮይድን ይጠቀማሉ እንበል፡፡ ኦፕሬቲንግ ሲስተማቸው አንድሮይድ መሆኑ በሞባይል ቀፎዎች መሀል ያለውን ያገልግሎት ጥራት፣ ከዘመነው
(አፕዴት ቴክ ) ጋር ያለውን መግባባትና ችሎታ፣ለቫይረስ ያለመጋለጥ ብቃትን ጨምሮ ከከባድ ድረ ገጽና አፕሊኬሽን ጋር ተጣጥሞ የመስራት አቅሙን ማሳየቱ ጥቂቶቹ መገለጫዎቹ ናቸው፡፡
ባጠቃላይ የሞባይል ቀፎን ባሕርይ ወሳኝ ምዕራፍ ኦፕሬቲንግ ሲስተሙ ነው፡፡ ከሞባይል ቀፎ አንፃር አንድሮይድ ባሁኑ ወቅት ከዊንዶው እና ማክ የተሻለ የኪስን አቅም ባማከለ መልኩ ተቀባይነት እያገኘ ነው፡፡
ሁለተኛው ማነፃፀሪያ ደግሞ ዋይ ፋይ፣ ብሉቱዝ፣ ዩኤስቢ፣ ጂፒኤስ፣፣ ቱጂ፣ ስሪጂ፣ ፎር ጂ
የመሳሰሉትን መያዙና በተጨማሪም
ሁለትና ከዚያ በላይ ሲም መቀበሉ ሲሆን ከዚህም በላይ ኖርማል ሲም ጂ ኤስ ኤም እና ruim (cdma sim ) ባንድ ላይ መያዙ ነው፡፡
የፋይል አደረጃጀት ስርአታቸው ለአጠቃቀም ቀላል መሆንና እንደፈለግነው መቀየር መቻሉና ምቹ መሆናቸው ደግሞ ሌላው መለኪያ ነው ፡፡
ለምሳሌ ተች ስክሪን፣ ስክሪን ጋድጌትስን መቀይር መቻሉና በፋይል ማናጀር በምንፈልገው መንገድ መቆጣጠር በሚያስችል መንገድ ‘እንደዚህ ሁንልኝ’ ስንለው የሚሆንልን ስማርት ፎን ደስ አይልም ?
ሶሰተኛው ማነፃፀሪያ የራሱ የሞባይሉ ሜሞሪ ( ፎን ወይም ኢንተርናል ሜሞሪ) ምንለው
ነው፡፡ ይህ ሜሞሪ አቅሙ በጨመረ
ቁጥር ዋጋውም አብሮ መጨመሩ እሙን ሲሆን ለቀፎዎች የዋጋ ልዩነት መሰረትም አንዱ
ምክንያት ነው፡፡
ቀፎዎች የምንከትላቸውን የውጭ ሜሞሪዎችና አብሮአቸው የተሰራውን ሜሞሪ ባንድ
አይነት ስለማይጠቀሙ በፍጥነት፣ በጥራትና
በአቅማቸው ላይ የሚያመጣው ልዩነት ትልቅ ነው፡፡ ቀፎዎች (TIF card)ቲፍ ካርድና
ኤስዲ(SD card) ካርድን(ሞባይላችን ላይ
ምንከታቸው ሜሞሪዎች ማለቴ ነው) ሲጠቀሙ ፍጥነታቸው ዝቅተኛ ከመሆኑም በላይ
የሚጭኑት አፕሊኬሽን ውስንና ቀጥታ ፍሰት
(Real Time access) ነው፡፡ ስለዚህ ቀፎ ስንገዛ የራሱን ሜሞሪ አቅም ማስተዋል ግድ
ይላል፡፡
አራተኛው የሞባይል ቀፎ ማወዳደሪያ ‘ፎን ክሎክ’ የሞባይል ቀፎውን ሲስተም ሃርድዌር
ፍጥነት ሚወስን ነው።ለምሳሌ ድረ ገፅ
ላይ አንድ ሞባይል ያለምንም መቆራረጥ ከዩቱብ ወይንም ከኛው ድሬትዩባችን ላይ ቪዲዮ
ቢያጫውት የክሎክ ፍጥነቱንና
የቢዩልት ኢን ሜሞሪን(phone memory) ጥራት ያሳያል፡፡
በተጨማሪ ቪዲዮ ኮሊንግ ያለችግርና (ፍሪዝ) በእስካይፒ መጠቀም ከቻልን በርግጥም
የቀፎዎችን ግሩም ጥራት ያሳየናል፡፡ እዚህ
ጋር ከግንዛቤ ውስጥ እንዲገባልኝ ምፈልገው አሁን ያለው የአገራችን የኔትዎርክ ችግር
በቀፎው እንዳይሳበብ የኔትዎርኩን ሁኔታም
ማየት መልካም መሆኑን ነው፡፡
አምስተኛ የባትሪ ጥራትና ቆይታ ነው ፡፡ አንዳንድ ሞባይሎች ባትሪ ሙጥጥ አያረጉ ‘‘እረ
የቻርጀር ያለህ!’’ እያሰኙ ስንቱን
አስጨንቀዋል፡፡ በርግጥ የሞባይል አቅምና ያገልግሎት ጥራት በጨመረ ቁጥር ባትሪ
አጠቃቀምም አብሮ ቢጨምርም ብዙ
ሞባይል አምራቾች የሞባይል ባትሪ ጥራትን በማሻሻል እነዚህ ቀፎዎች ለ18 ሰኣት
አንዲያገለግሉ አርገው ሰርተውልናል፡፡
ሌላው ባትሪን በተመለከተ ማየት ያለብን የተሻለ ሞባይል ለመግዛት የባትሪ ማኔጅመንት
ፕሮቶኮል አውቶማቲክና ማኑዋል አማራጭ
እንዳለው ማጣራት ነው፡፡
የባትሪ ቀበኛ ከሆኑት ስክሪን ብራይትነስና ቫይብሬት ቴክኖሎጂን ጨምሮ ከጀርባ ሳናያቸው
የሚስሩ አፕሊኬሽኖች መኖር፣ ቫይረስና
አንቲ ቫይረስ ማኔጅ ማድረግና የመሳሰሉትን መቆጣጠሪያ ሶፍት ዌር መጫን የባትሪን
ቀይታ ለማራዘም የምጠቁመው ተጨማሪ
መፍተሄ ነው።
በመጨረሻም የተሻለ ሞባይል ለመያዝ ከላይ ከጠቀስኳቸው በተጨማሪ ኢሜይል፣የጽሑፍ
መልዕክት፣ካሜራ ጥራት፣ ምቾት፣ሰክሪን
ስፋትና የተመረተበትን ቀን ማረጋገጡ ጠቃሚ ነው፡፡
@knowelg

Читать полностью…

Ethio dreams

ያገለገለ Smartphone
ያገለገለ ሳይክል መሸጥ የምትፈልጉ ሰዎች በውስጥ ላኩልን ብዙ ፍላጎት አለ 👍
@Hulgebe_bot

Читать полностью…

Ethio dreams

🚲🚲🚲🚲🚲
📌 1 ወር አገልግሏል

💵ዋጋ 8000 ብር

ፈላጊው ብቻ
👇👇👇
@Hulgebe_bot

Читать полностью…

Ethio dreams

ያገለገለ Smartphone
ያገለገለ ሳይክል መሸጥ የምትፈልጉ ሰዎች በውስጥ ላኩልን ብዙ ፍላጎት አለ 👍
@Hulgebe_bot

Читать полностью…

Ethio dreams

ከላይ በፎቶ የምታዩት New HD Phone Screen Magnifiers ነው።
ዋጋ 1800ብር
Call 0934340368
Free delivery
  ▪︎በ ስልኮ ፊልምም ሆነ የተለያዩ ነገሮችን ሲያዩ የሚያዩትን ነገር 3x አተልቆ ያሳያል።
▪︎Video ሲያዩ አይኖ ላይ ሊደረስ የሚችልን ጉዳት የሚቀንስ።
▪︎የሚያዩት ነገር የተለየ ጥራት እና ውበት እንዲኖረው የሚያስችል ምርጥ ቴክኖሎጂ።
¶በማንኛውም ቦታ ይዘውት ሊንቀሳቀሱ ይችላሉ።
¶ለሁሉም ደንበኞቻችን ያሉበት ቦታ ድረስ በነጻ እናደርሳለን።for more info👉👉@Ygwlg

Читать полностью…

Ethio dreams

✍ውድ የቻናላችን ቤተሰቦች ለተፈጠረው ቺግር ይቅርታ እየጠየቅን የቻናላችን ስም ተቀይሯል ማለትም ሁለገብ የጥያቄ እና መልስ ሚለው ወደ Ethio አገናኝ እናም ከዚህ ሰከት ጀምራችሁ ማንኛውም መሸጥ ወይም መግዛት የምትፈልጉትን ነገር ላኩልን።

Читать полностью…

Ethio dreams

እጅግ በጣም ጥሩ መሆን !

እቺ አለም ለጥሩ ሰው ቦታ የላትም ፤ ይሄ ሲባል ግን ለክፉ ሰው ነው ቦታ ያላት ማለት አይደለም። ብዙ ሰዎች በስራ ህይወታቸው ፣ በፍቅር ህይወታቸው እኔኮ ጥሩ ሰው ነኝ እንዴት ይሄ ለኔ ስለሚሉ ነው ። ትልቅ ስኬት ላይ መድረስ ከፈለግክ እጅግ በጣም ጥሩ መሆን ይጠበቅብሃል ከጥሩነት አልፈህ ብዙ ማወቅ ብዙ መጠየቅ ወሳኝ ነው ! ጥሩነት እንዳያስርህ ።

ምርጥ የሆነ ዋዜማ ተመኘንላችሁ 🙏
@knowelg
የእናንተው ምርጥ ጓደኛ 😊

Читать полностью…

Ethio dreams

ማቆም የለም!

ከዚህ በፊት ሰዎች በተለያየ አጋጣሚ ደጋግመው አሞኝተው ሸውደውህ ይሆናል፤ እና ሞኝ ነህ ማለት ነው? አይደለህም! በዚህ አለም ለአላማህ ስትሮጥ ደጋግመህ መውደቅ ወይ መሳሳት ያለ ነው፤ እኔኮ ህይወቴ በስህተት የተሞላ ነው፤ ለስኬት አልተፈጠርኩም ማለት የለብህም።

ወዳጄ ከወደቅበት መልሰህ ትነሳና የሚፈልጉትን ዋጋ ከፍሎ ማሳካት ምን ማለት እንደሆነ ለራስህ ታሳየዋለህ! ይሄን ሳታደርግ ማቆም የለም!

ልዩ ምሽት ተመኘንላችሁ🙏
@knowelg
የእናንተው ምርጥ ጓደኛ!

Читать полностью…

Ethio dreams

ሰላም ሰላም ወድ የ ኢትዮ ድርምስ ቤተሰቦች ..... ተመለሰናል.... ሼር ማድረግ አትርሱ ... እናመሰግናለን 🙏🙏🙏🙏🙏

Читать полностью…

Ethio dreams

ዛሬ በብዛት ተፈላጊ የሆኑ ነገሮች👇
Wireless Mic
Camera
Samsung Phone
Camera stand
መጋዘን ጎተራ አካባቢ
ሳይክል
ባጃጅ
PC
Hard disk
Flash 64GB and above

ያገለገሉ ዕቃዎችን ይሽጡ/ይግዙ👇
@Hulgebe_bot

Читать полностью…

Ethio dreams

ማንኛውም የሚሸጥ እቃ ካሎት ይላኩልን🙏
👇
@Hulgebe_bot

Читать полностью…

Ethio dreams

ዛሬ በብዛት ተፈላጊ የሆኑ ነገሮች👇
Wireless Mic
Camera
Samsung Phone
Camera stand
መጋዘን ጎተራ አካባቢ
ሳይክል
ባጃጅ
PC
Hard disk
Flash 64GB and above

ያገለገሉ ዕቃዎችን ይሽጡ/ይግዙ👇
@Hulgebe_bot

Читать полностью…

Ethio dreams

ማንኛውም የሚሸጥ እቃ ካሎት ይላኩልን🙏
👇
@Hulgebe_bot

Читать полностью…

Ethio dreams

👉ምናገናኛቸው እቃዎች አዲስ እንዲሁም ለተወሰነ ጊዜ ተጠቅማችሁ መሸጥ ለምትፈልጉ ሲሆን ለምሳሌ mobile,Tablet,personal computer, shoes ወዘተ ናቸው። ከታች ባለው ሊንክ መሸጥ ወይም መግዛት የምትፈልጉትን ነገር መላክ ትችላላችሁ 👇👇
@Ygwlg

Читать полностью…
Subscribe to a channel