kuzibo | Unsorted

Telegram-канал kuzibo - ሳቅና ቁምነገር

88

☞የTelegram ቻናላችን በቀልድ ስመ ጥር በቀዳሚነት የሚጠቀስ ሽንት አሽጨራሽና ጥርስ የማያስከድን በቀልድ በቁምነገር የብቃት ማረጋገጫ ያለው ቻናል ነው ♥Contact us @sakna kum neger bot የተመረጡ የአማርኛ ቀልዶች ምስሎች: ቪዲዮዎች: አስገራሚ እውነታዎች፡ወቅታዊ መረጃዎችና:ልዩ ልዩ ፅሑፎች የሚያገኙበት ቻናል!! @ሳቅና ቁም ነገር t.me/kuzziBot

Subscribe to a channel

ሳቅና ቁምነገር

እነ ጃዋር መሐመድ ከእስር ይፈቱ በማለት የካቲት 6 ቀን 2013 ዓ,ም ጅማ ዩኒቨርሲቲ ተማሪዎችን ባስመረቀበት መድረክ የጠየቀውን ተመራቂ ፍርድ ቤት ቢያሰናብተውም እስካሁን ከእስር እንዳልተለቀቀ ጠበቃው ተናገሩ።

የመሐመድ ዴክሲሶ ጠበቃ ለዶይቼ ቬለ እንዳሉት ደንበኛቸው በመድረኩ የተናገረው የመናገር ነጻነት አንዱ ማሳያ ቢሆንም ሁከት በማነሳሳት እና ከታጣቂ ኃይሎች ጋር ግንኙነት አለው በሚል ወንጀል ተጠርጥሮ በፖሊስ ታስሯል። የኢትዮጵያ ሰብዓዊ መብቶች ኮሚሽን በኦሮሚያ ክልል የፍርድ ቤቶች ትዕዛዝ አለመከበሩ እንዳሳሰበው ባመለከተበት መግለጫው ፍርድ ቤት የጅማ ዩኒቨርሲቲ ተመራቂው እንዲለቀቅ የሰጠው ውሳኔ እንዲከበር ጠይቋል።

(ዶይቼ ቬለ/DW)

Читать полностью…

ሳቅና ቁምነገር

ለ 12ኛ ክፍል ተማሪዎች ሰበር ዜና ‼️

የ 12ኛ ክፍል ፈተና ከየካቲት 29 እስከ መጋቢት 2 ይሠጣል ተብሏል።

በኦንላይን ሊሰጥ የነበረው የ12ኛ ክፍል ፈተና በወረቀት ሊሰጥ መሆኑ ተገለፀ።

ትምህርት ሚኒስቴር በዚህ ጉዳይ ዙሪያ መግለጫ እየሰጠ ይገኛል። በዚሁ መግለጫ ላይ ፈተናው ከየካቲት 29 እስከ መጋቢት 2 ይሠጣል ተብሏል። ዝርዝር መረጃ ይዘን እንመለሳለን።
@KuziBo

Читать полностью…

ሳቅና ቁምነገር

የህወሃት ሊቀመንበር የሆኑት ደብረ ፅዮን ገብረ ሚካኤል (ዶ/ር) ከሁለት ወራት ዝምታ በኋላ በትናትናው ዕለት፣ ጥር 22፣ 2013 ዓ.ም በድምፂ ወያነ ትግራይ ፌስቡክ ገፅ በቀጥታ ለትግራይ ህዝብ መልዕክት አስተላልፈዋል።

ደብረ ፅዮን ገብረ ሚካኤል (ዶ/ር) በትግራይ ላይ የተከሰተውን ወታደራዊ ግጭት ተከትሎ በተቋረጠው ድምፂ ወያነ ትግራይ የፌስቡክ ገፅ በቀጥታ ለ13 ደቂቃዎች በድምፅ ባስተላለፉት መልዕከት ክልሉ ላይ ደርሷል ስለተባሉ ውድመቶች፣ ቀጥሏል ስላሉት ትግል ሁኔታ እንዲሁም ለትግራይ ህዝብና ለአለም አቀፉ ማህበረሰብ ጥሪ አቅርበዋል።"የትግራይ ሴቶች በተናጠልና በደቦ ይደፈራሉ። የትግራይ ሰዎች ሰብዓዊና ዲሞክራሲያዊ መብቶችና ነጻነቶች በከፋ መገለጫና አኳሃን ይጣሳሉ፣ ይገፈፋሉ። የትግራይ መንደሮችና ዓብያተ እምነቶች፣ የትግራይ ሰራዊት ይኑርበት አይኑርበት ሳይገዳቸው የቦምቦችና የመድፎ ዒላማ ይደረጋሉ። ውድና መተኪያ የሌላቸው ቅርሶችም ይወድማሉ፣ ይዘረፋሉ። በሚልዮን የሚቆጠር ህዝብ እንዳለ ከቀየው ወጥቶና ተፈናቅሎ የመከራ ኑሮ ይኖራል።" ብለዋል።

በትግራይ ክልል ከተከሰተው ቀውስ ጋር በተያያዘ የፌደራል ጠቅላይ ዐቃቤ ሕግና የፌደራል ፖሊስ በበርካታ የህወሓት ወታደራዊና ፖለቲካዊ አመራሮች ላይ የእስር ትዕዛዝ ማውጣታቸው ይፋ ማድረጋቸው የሚታወስ ነው። ከነዚህም አመራሮች አንዱ የህወሃት ሊቀ መንበር ደብረ ፅዮን ሲሆኑ በአሁኑ ወቅት ያሉበት አይታወቅም።ለእስር ማዘዣው ዋነኛ ምክንያቶቹ በትግራይ ክልል በሚገኘው በአገር መከላከያ ሠራዊት የሰሜን ዕዝ ላይ ጥቃት በመፈፀም፣ የአገር ክህደት ወንጀል በመፈፀም፣ የመከላከያ ሠራዊትና የፖሊስ አባላት እንዲታገቱ አድርገዋል በሚል ተጠርጥረው ነው።

(BBC)
@KuziBo

Читать полностью…

ሳቅና ቁምነገር

ቀዳማዊት እመቤትወ/ሮ ዝናሽ ታያቸው 13ኛውን ት/ቤት ለመመረቅ አፋር ክልል ገቡ፡፡
@KuziBo

Читать полностью…

ሳቅና ቁምነገር

👉 ለአስተያየትዎ @KuzziBot

Читать полностью…

ሳቅና ቁምነገር

ቤተ መፅሐፍት |world books
ይህን ለሌሎች ጋደኛቻችሁ ሼር በማረግ ተባበሩን::ሌሎችም የተለያዮ መፅሐፍት እንዲያገኙ እናድርግ።
ሼር ሼር ሼር


https://t.me/joinchat/AAAAAE5AFvEWhd2AFbBGZw

Читать полностью…

ሳቅና ቁምነገር

" Rabelem igma num miyanammay,
Rabah bicsita num miyan (dagoh)"

t.me/httpsDiiniKeeAnaakara

Читать полностью…

ሳቅና ቁምነገር

የዩኬ አዲሱ የኮሮናቫይረስ ዝርያ ከቀደመው የከፋ ነው ተባለ

የዩኬ አዲሱ የኮሮናቫይረስ ዝርያ ከቀደመው የከፋ ነው ተባለ

@KuziBo

Читать полностью…

ሳቅና ቁምነገር

በአፋር ክልል የበረሃ አንበጣ ዳግም መከሰቱን የክልሉ እርሻ፣ አርብቶ አደርና ተፈጥሮ ሃብት ልማት ቢሮ አስታወቀ‼️

በቢሮው የበረሃ አንበጣ መከላከል ግብረ-ሃይል አስተባባሪ ዶክተር አያሌው ሹመት ለኢዜአ እንደገለጹት በክልሉ አፋምቦ፣ ዱብቲና አይሳኢታ ወረዳዎች ጥር 9 ቀን 2013 ዓ.ም የአንበጣ መንጋው ዳግም ተከስቷል።መነሻውን ከጅቡቲና ሱማሌ ያደረገው የአንበጣ መንጋ በሌሎችም የክልሉ ወረዳዎች እየተስፋፋ መሆኑን ተናግረዋል።

በክልሉ ሚሌ፣ ጭፍራ፣ ጉሊናና ቴሩ ወረዳዎች የአንበጣ መንጋው የተስፋፋባቸው መሆናቸውንም ጠቅሰዋል።አሁን ላይ በክልሉ የግብርና ስራዎች የሚከናወኑበት ወቅት በመሆኑ የአንበጣ መንጋው ከእንስሳት መኖ በተጨማሪ በሰብል ላይ ጉዳት እንዳይደርስ ህብረተሰቡን በማሳተፍ በባህላዊ መንገድ የመከላከል ስራ እየተካሄደ መሆኑን ተናግረዋል።

መንጋው እስካሁን ያደረሠውን ጉዳት ለማወቅ መረጃ እየተሰበሰበ መሆኑንም ገልጸው፤ መንጋውን ለመቆጣጠር በሰውና በተሽከርካሪ ኬሚካል ለመርጨት አስቸጋተሪ በመሆኑ አካባቢዎች ከግብርና ሚኒስቴር ጋር በመነጋገር በአውሮፕላን የታገዘ ርጭት ለማካሄድ ጥረት እየተደረገ መሆኑን አስተባባሪው አስታውቀዋል።በክልሉ ካለፉት ሁለት አመት ወዲህ በተደጋጋሚ የበረሃ አንበጣ ተከስቶ በሰብል፣ በእንስሳት መኖና ቁጥቋጦዎች ላይ ጉዳት ማድረሱ ይታወሳል።
@kuziBo

Читать полностью…

ሳቅና ቁምነገር

ጆ ባይደን በሹመት ቀናቸው የትራምፕን ፖሊሲዎች ለመሻር መዘጋጀታቸው ተገለጸ

ሙስሊም በሚበዛባቸው 7 ሀገሮች ላይ የተጣለውን የጉዞ እገዳ ማንሳት በሹመታቸው ቀን ከሚወስኗቸው ጉዳዮች አንዱ ነው፡፡ በሚሊዮኖች የሚቆጠሩ ፈቃድ የሌላቸው ሰዎች ዜግነት የሚያገኙበት ዕድልም ይፈጠራል ተብሏል፡፡

ጆ ባይደን ከ 3 ቀናት በኋላ 46ኛው የአሜሪካ ፕሬዝዳንት ሆነው ይሾማሉ! የፓሪሱን የአየር ንብረት ስምምነት እንደገና መቀላቀል እና ሙስሊም በሚበዛባቸው ሀገሮች ላይ የተጣለውን የጉዞ እገዳ ማንሳት በቅጽበት ከሚቀየሩ የትራምፕ ፖሊሲዎች መካከል መሆናቸውን የአሜሪካ ሚዲያዎች ዘግበዋል፡፡

በትራምፕ ፖሊሲ በሜክሲኮ ድንበር እየተያዙ ከወላጆቻቸው የተለዩ ህጻናትን ዳግም ከወላጆቻቸው ጋር እንዲገናኙ ማድረግም ፣ ባይደን በፍጥነት የሚተገብሩት ተለዋጭ ፖሊሲ እንደሚሆን ተገልጿል፡፡ ከኮሮናቫይረስ ጋር በተያያዘ ፣ ማስክ ማድረግን ጨምሮ ሌሎች አስገዳጅ ህጎችን ሊያጸድቁ እንደሚችሉም የኋይት ሀውስ ኃላፊው መረጃ ያመለክታል፡፡

በመጀመሪያ የስልጣን ቀናቸው ከሚያሳልፏቸው ውሳኔዎች በተጨማሪ ፣ በ100 ቀናት የስልጣን ጊዜያቸው ፣ በርካታ ስደተኞችን ተጠቃሚ የሚያደርግ አዲስ የስደተኞች ህግ ለኮንግረሱ እንደሚያቀርቡ ይጠበቃል፡፡ በዚህም አሁን ላይ በአሜሪካ የሚገኙ በሚሊዮኖች የሚቆጠሩ ህጋዊ የመኖሪያ ፈቀድ የሌላቸው ስደተኞች የሀገሪቱን ዜግነት የሚያገኙበት መንገድ እንደሚከፈትላቸው ነው የሲኤንኤን ዘገባ የሚያሳየው፡፡ (አልአይን)
@KuziBo

Читать полностью…

ሳቅና ቁምነገር

ጎልልልልልልልልል ቼልሲ ሜሰን ማውንት ነው ያስቆጠረው

ፉልሀም 0 vs 1 ቼልሲ

SHARE" @KuziBo

Читать полностью…

ሳቅና ቁምነገር

በመተከል በግፍ የተገደሉ ኢትዮጵያውያን ‼️

Читать полностью…

ሳቅና ቁምነገር

🏴󠁧󠁢󠁥󠁮󠁧󠁿 የእ/ዝ ፕሪሚየር ሊግ 19ነኛው ሳምንት ጨዋታ
ፉልሃም 0 vs 0 ቼልሲ

@kuziBo

Читать полностью…

ሳቅና ቁምነገር

ከካፒቶል ጥቃት በኃላ የትራምፕ ተቀባይነት መቀነሱን ከህዝብ በተሰበሰበ ድምፅ ማረጋገጥ ተቻለ

በዋይት ሀውስ ለአራት ዓመታት ያህል ቆይታ ያደረጉት ፕሬዝዳንት ዶናልድ ትራምፕ ስልጣናቸውን ሊለቁ ቀናቶች ብቻ በቀሩበት በዚህ ጊዜ ተቀባይነታቸው በሀገረ አሜሪካ ቀንሷል።በካፒቶል የደረሰው ጥቃት ደግሞ ዋንኛ ምክንያት ሆኗል።

ሶስት ተቋማት የትራምፕን ተቀባይነት በተመለከተ ከህዝብ ድምፅ ሰብስበዋል።በሁለቱ ድምፅ የሰበሰቡ ተቋማት ባገኙት የህዝብ ድምፅ ግኝት መሰረት በድጋሚ በምርጫ እንዳይወዳደሩ ሊታገዱ እንደሚገባም አመላክተዋል።

የህዝብ ድምፅ የሰበሰቡት ፒው ሪሰርች፣ዋሽንግተን ፖስት ከኤቢሲ ኒውስ ጋር በመጣመርና ሮይተርስ ናቸው።በፒው ሪሰርች ግኝት መሰረት የትራምፕ ተቀባይነት 29 በመቶ ቀንሷል።

አንዳንድ ሪፓብሊካን የካፒቶል ጥቃት ቢያወግዙም አሁንም ያለ አንዳች ማስረጃ ምርጫው ተጭበርብሯል የሚለውን የትራምፕን ክስ የሚደግፉ ግን በርካቶች ናቸው።

በስምኦን ደረጄ
#ዳጉ_ጆርናል

Читать полностью…

ሳቅና ቁምነገር

❌ አቶ አስመላሽ ወልደስላሴ

Death picture(የአስክሬን ፎቶ)

🔞🔞 ከ 18 አመት በታች ያላችሁ ባታዩት ይመረጣል🔞🔞

@kuziBo

Читать полностью…

ሳቅና ቁምነገር

#EthiopiaElection2013

የአማራ ብሔራዊ ንቅናቄ (አብን) ነገ እሁድ በአዲስ አበባ ፣ በባሕር ዳር፣ ጎንደር፣ ደሴ እና ደብረ ብርሃን ከተሞች የምርጫ ቅስቀሳ ማስጀመሪያ መርኃ ግብር እንደሚያካሂድ አስታውቋል።

ፓርቲው በአዲስ አበባ አብሮ ለመስራት ከተስማማቸው ፓርቲዎች ጋር (ባልደራስ ለእውነተኛ ዴሞክራሲ ፓርቲ፣ የመላው ኢትዮጵያ አንድነት ድርጅት፣ የኢትዮጵያ ብሄራዊ አንድነት ፓርቲ) በጋራ የምርጫ ቅስቀሳ ማስጀመሪያ መርኃ ግብሩን ለሚመለከተው የመንግስት አካል በደብዳቤ ማሳወቁንም ገልጿል።

👉@KuziBo

Читать полностью…

ሳቅና ቁምነገር

የማይካድራው ጭፍጨፋ በርካታ ንፁሃን የተገደሉበት ዓለም አቀፍ የሽብር ወንጀል ሆኖ ተመዘገበ‼️

ወንጀሉ ቦኮሀራም በተመሳሳይ ወር በናይጄሪያ ላይ ከፈፀመው የሽብር ወንጀል ይበልጣል ተብሏል።

ህወሓት አደራጅቶታል በተባለው እና “ሳምሪ” በተሰኘው ኢ-መደበኛ የወጣቶች ቡድን በማይካድራ የተፈጸመው ጭፍጨፋ በርካታ ንፁሃን የተገደሉበት ዓለም አቀፍ የሽብር ወንጀል ሆኖ ተመዘገበ፡፡

ወንጀሉ የተመዘገበው በዓለም አቀፉ የፖሊስ ተቋም ኢንተርፖል ነው፡፡ በዓለም አቀፍ ደረጃ ባሳለፍነው ህዳር ወር የተፈጸሙ የሽብር ወንጀሎችን ዝርዝር ያወጣው ተቋሙ የማይካድራው ጭፍጨፋ በርካታ ንፁሃን ዜጎች ህይወታቸውን ያጡበት ኢሰብዓዊ ድርጊት ነው ሲል አስቀምጧል፡፡

ጭፍጨፋው በመላው ዓለም ከተፈጸሙ 10 ተመሳሳይ የሽብር ወንጀሎች ቀዳሚው ነው ያለም ሲሆን ቦኮሀራም በተጠቀሰው ወር በናይጄሪያ ከፈፀመው የሽብር ወንጀል እንደሚበልጥ ነው የገለጸው፡፡

የተቋሙ የሽብር ወንጀል መከላከል ዳይሬክቶሬት ጭፍጨፋው ማንነትን መሰረት አድርጎ የተፈጸመ ነው ማለቱንም ነው ከፌዴራል ፖሊስ የተገኘው መረጃ የሚያመለክተው፡፡

ዳይሬክቶሬቱ 600 ንጹሃን መጨፍጨፋቸውንም ይፋ አድርጓል።

ጥቅምት 30 ቀን 2013 ዓ.ም በማይካድራ እና በአካባቢው የተፈጸመው ጭፍጨፋ በወቅቱ በስልጣን ላይ በነበረው የአካባቢው መስተዳድር የጸጥታ መዋቅር አስተባባሪነት መፈጸሙን የኢትዮጵያ ሰብዓዊ መብቶች ኮሚሽን (ኢሰመኮ) ኅዳር 15 ቀን 2013 ዓ.ም ባወጣው የመጀመሪያ ደረጃ ቀዳሚ ሪፖርት ማስታወቁ የሚታወስ ነው፡፡
@KuziBo

Читать полностью…

ሳቅና ቁምነገር

"...የኮሮና ክትባት በሚያዝያ ወር ወደ ሀገር ውስጥ ይገባል" - ጤና ሚኒስቴር

የኮሮና ቫይረስ መከላከያ ክትባት እስከ መጪው ሚያዝያ ወር ወደ ሀገር ውስጥ እንደሚገባና 20 ከመቶ ለሚሆኑ ተጋላጭ የህብረተሰብ ክፍሎች እንደሚዳረስ የጤና ሚኒስቴር አስታውቋል።

የክትባት ስራውን የሚያስተባብር ግብረሃይል በብሄራዊ ደረጃ መቋቋሙ ተገልጿል።

በጤና ሚኒስቴር የክትባትና ተያያዥ ጉዳዮች የሚኒስትሯ (ዶ/ር ሊያ ታደሰ) ከፍተኛ አማካሪ ዶክተር ሙሉቀን ዮሃንስ ፥ ከጤና ሚኒስቴር ፣ ከጠቅላይ ሚኒስቴር እና ከፕሬዚዳንት ፅህፈት ቤት ጋር በመቀናጀት የኮሮና መከላከያ ክትባትን ወደ ሀገር ውስጥ ለማስገባት ዘርፈ ብዙ ዝግጅቶች እየተከናወኑ ይገኛሉ ብለዋል።

የእቅድ እና አጠቃላይ የዝግጅት ስራን በሚመለከት የክትባቱን ሥራ የሚያስተባብር ግብረሃይል ከልማት አጋር ድርጅቶች ፣ ከመንግስት ኤጀንሲዎች ፣ ከጤና ሚኒስቴር እንዲሁም ከተለያዩ ባለድርሻ አካላት ተውጣጥቶ በብሔራዊ ደረጃ መቋቋሙን ገልጸዋል፡፡

EPA
@KuziBo

Читать полностью…

ሳቅና ቁምነገር

ከህውሃት ታጣቂ ሃይል ጋር በመሰለፍ ሲዋጉና ሲያዋጉ የነበሩ 18 ከፍተኛ መኮንኖች በቁጥጥር ስር ዋሉ

ከህውሃት ታጣቂ ሃይል ጋር በመሰለፍ ከመቀሌ እስከ ቆላ ተንቤን ሲዋጉና ሲያዋጉ የነበሩ 18 ከፍተኛ መኮንኖች በመከላከያ ሠራዊትና የፌዴራል ጸጥታ ሃይሎች የጋራ አሰሳና ፍተሻ ስራ በቁጥጥር ስር ውለዋል።

ከቡድን ጋር በማወቅም ይሁን ባለማወቅ የተሰለፉ ሃይሎች በሰላማዊ መንገድ እጃቸውን ለመንግስት እንዲሰጡም በድጋሚ ጥሪ ቀርቧል።

የመከላከያ ኢንዶክትርኔሽን ዋና ዳይሬክተር ሜጀር ጀኔራል መሀመድ ተሰማ ለኢዜአ አንደገለጹት 18ቱ ከፍተኛ መኮንኖች በቁጥጥር ስር የዋሉት የመከላከያ ሰራዊትና የፌደራል ጸጥታ ተቋማት በቅንጅት ባካሄዱት አሰሳና ፍተሻ ነው። via ENA
@KuziBo

Читать полностью…

ሳቅና ቁምነገር

🔆ለቴሌግራም አዲስ ገቢዎች ቴሌግራምን ልናስተዋውቃችሁ ነው አብራችሁን ሁኑ።

1.user_name ቢኖራችሁ ይመረጣል፤ ስልክ ቁጥራችሁን መስጠት ባትፈልጉ ይህን username ቢሰጡት ማንም እናንተን በቀላሉ ማግኘት ይችላል።

⚠️ setting ውስጥ ማግኘት ትችላላችሁ።

2.የሆነ ሰው እያዋራችሁ ስልክ ቁጥሩን ለማወቅ ከፈለጋችሁ ቀላል ዘዴ ልንገራችሁ። 👇

🤔እናንተ ብቻ ስልክ ቁጥራችሁን ላኩለት ያ ሰው ቁጥራችሁን contact ወይም dialer ውስጥ ካስገባው የእሱ ቁጥር በቀጥታ ለናንተ ይታያችኋል።

⚠️ስልኳን አልሰጥ ላለች ሁላ ቁጥራችሁን ስትልኩ ዋሉ አሏችሁ ደሞ 😜

3.አዲስ Chanel (በፌስቡክኛ page የምንለውን) ወይም group ለመክፈት ከፈለጉ new group ወይም new channel የሚለውን በመጫንና ያላችሁን contact add በማድረግ ማስጀመር ትችላላችሁ።. . 👇👇👇

4.ብዙ አይነት ቴሌግራም አፕ አለ ለምሳሌ telegram, plus, mobogram, supergram, multigram...

እነዚህ 👆 ሁሉም የየራሳቸው feature አላቸው።

5.የሆነ ሰው አካውንት ውስጥ ስትገቡ start secret chat የሚል ይመጣል ከ normal chat ጋር ልዩነቱ ምንድነው?

✔️ከ 1ቀን በኋላ መልእክቱ ከእናንተም, ከተላከለትም ሰው, ከቴሌግራም ሰርቨርም ላይ ይጠፋል። ❌

✔️እናንተ የላካችሁለትን መልእክት ለሌላ ሰው ለማስተላለፍ(forward) ማድረግ አይችልም።

6. ፌስቡክ ላይ የምትጠቀሙበት chat off (ቻት ላይ እንደሆናችሁ ሌላ ሰው እንዳያውቅ ማድረጊያ) እዚህም አለ።

✅Setting ➡️ privacy and security ➡️ last seen

እዚህ 👆 ውስጥ በመግባት...

✔️ሁሉም ሰው እንዲያያችሁ (everybody)

✔️ስልካችሁ ላይ ስልካቸው የተመዘገበ ሰዎች ብቻ እንዲያያችሁ (only contacts)

✔️እንዲሁም ማንም እንዳያያችሁ (nobody) ማድረግ ትችላላችሁ።. . .

7.በቴሌግራም ማንኛውንም አይነት ዶክመንት መላክ ትችላላችሁ።

⚠️ከታች ያለውን attachment ምልክት በመንካት 👆

8.ቴሌግራም በየደቂቃው backup ስለሚይዝ ስልክዎ 📱 ቢጠፋ፣ ቢበላሽ 😭 መረጃዎ እንዳለ ይቆያል።

9.አሁን ያሉበትን ቦታ ⤴️ ለሌሎች ማጋራት ይችላሉ።

⚠️ከታች ያለውን attachment በመንካት 👆

10.ቴሌግራም በራሱ ምንም አይነት አሰልቺ ማስታወቂያዎችን ለተጠቃሚዎቹ አይልክም። ❌

⚠️(AD-free)

11.አፑን ለራስዎ እንደሚመችዎ theming ውስጥ በመግባት personalize ማድረግ ይችላሉ።

_________________________.

12.ቴሌግራምዎን ከእርስዎ ውጭ ማንም እንዳይከፍተው password 🔑 መስጠት ከፈለጉ 👇

💢Setting ➡️ privacy and security ➡️ passcode lock ➡️ on ያድርጉና password ይስጡት ከዛም ✔️

13.አንዳንድ ሰዎች ያለፍላጎትዎ ግሩፕ/ቻናል ላይ እያስገቡዎት ከተቸገሩ 👇

💢Setting ➡️ privacy and security ➡️ groups/channels ➡️ no one ✔️

14👉 Telegram ሲከፍቱት ያለእርስዎ ትእዛዛት audio, video, document download እንዳያደርግ 👇

💢 Setting ➡️ data and storage ➡️ auto download media off ❌

15. እርስዎ ባያዙትም 😡 ቴሌግራም ላይ ያዩዋቸውን ፎቶዎች 📸, ቪድዩዎች 🎥... አፑ በራሱ የስልክዎን 📲 storage በመጠቀም ያስቀምጣል፤ ቦታ እንዳይጨናነቅብዎ ለማጥፋት ❌

💢Files ➡️ internal storage ➡️ telegram ...delete

________________________

⚠️መረጃዎችን ለወዳጅዎ 👥 ያጋሩ።

@kuziBo

Читать полностью…

ሳቅና ቁምነገር

▶️ አልካትራዝ ወህኒ ቤት
---------------------------
"የ ጠ ፉ ት እ ስ ረ ኞ ች"

ግሩም ትረካ

@Worldbook0

Читать полностью…

ሳቅና ቁምነገር

🗣እኛ ስለንባብ
@worldify
<<ንባብ ያልታከለበት ግንዛቤ ግልብ ያደርጋል።>>
ደራሲ በአሉ ግርማ

<<መጽሐፍትን ማንበብ ታሪክህን በሚገባ እንድታውቅ ያደርግሀል። ታሪክህን ስታውቅ ደግሞ ራስህን ታውቃለህ ።>>
አምባሳደር ዘውዴ ረታ

<<ማንበብ የአዕምሮ ምግብ ነው፤ዋናው የአዕምሮ ምግብ ! >>
ደራሲ ስዩም ገ/ህይወት

<<ማንበብ ህይወትን የምንቀይርበት ትልቅ መሣሪያ ነው።ያለንባብ ህይወትን በአግባቡ መምራት አይቻልም።>>
አሰልጣኝ ሠውነት ቢሻው

<<ማንበብ የዕውቀት ብርሃን ነው። ስለዚህ ባነበብን ቁጥር ውስጣችንም ሆነ በዙሪያችን ያለው ውጫዊ ነገር በሙሉ በብርሃን የተሞላ ይሆናል። >>
ስአሊ አንዷለም ሞገስ

<<በዚች ጥንታዊት ሀገር መጻሕፍትን መፃፍ ብቻ ሳይሆን ማንበብ፣ማስነበብ፣ማፃፍ፣ሲነበቡ መስማት ጭምር የተከበረ ነገር ነበር ። >>
ዲያቆን ዳንኤል ክብረት

<<ማንበብ እኮ ሁሉን ነገሮች ያንተ እንዲሆኑ ያደርጋል።ስታነብ ትዝናናለህ። ማንበብን ተከርሎ ደግሞ ስለሁሉም ነገር ማወቅና መረዳት ትጀምራለህ። >>
ድምጻዊ ፀሃዬ ዮሀንስ

<<ማንበብ ያልኖርነውን ትላንት ዛሬ ላይ መኖር እንድንችል ያደርጋል። ካልኖርንበት ዘመን ጓደኞች እንዲኖሩንና ዘመናቸውን የኖርንበት ያህል እንድሰማን ያደርጋል።>>
ገጣሚና ጋዜጠኛ ዳዊት አለሙ

<<መጽሐፍ ያጣ አዕምሮ ውሀ ያጣ ተክል ማለት ነው።ሰው ራሱን አውቆና ችሎ እንዲኖር መጽሐፍ ማንበብ በእጅጉ ይጠቅማል።>>
መምህር ንጉሴ ታደሰ

<<ማንበብ አዕምሮን አያስርብም።የሚያነብ ሰው ዘወትር በአስተሳሰቡ ንቁና በአስተሳሰቡየበለጸገ ነው።>>
ጋዜጠኛ ገነነ መኩሪያ ሊብሮ)

<<ዕውቀቴን ሁሉ ያገኘሁት በማንበብ ነው። በአጭሩ ማንበብ አዋቂ ብቻ ሳይሆን ሙሉ ሰው ያደርጋል።>>
ደራሲ ጳውሎስ ኞኞ

🗣 እነሱ ስለንባብ

<<የኔ ምርጥ ጓደኛ ብዬ የምቀርበው ሰው ያላነበብኩትን መጽሐፍ እንካ አንብብ ብሎ የሚሰጠኝ ነው።>>
አብርሐም ሊንከን

<<ዘወትር ባነበብኩ ቁጥር ውስጤ የነበረውና ያለው ትልቁ የመቻል አቅም ይቀሰቀሳል።>>
ማልኮም ኤክሥ

<<ለአንድ ሠው መጽሐፍ ስትሸጥ የሸጥከው ብዙ ወረቀቶችን የተጻፈበትን ቀለምና ጥራዙንም አይደለም። ለርሱ የሸጥክለት ዋናው ነገር ሙሉ የሆነ አዲስ ህይወትን ነው።>>
ክርስቶፈር ሞርሌይ

<<በዚህ ዘመን በየትኛውም ሁኔታ በጣም ጊዜ የለኝም።እረፍት የለኝም ብለህ የምታስብ ቢሆን እንኳን ለማንበብ የግድ ጊዜ መስጠት አለብህ።ይህን አላደረክም ማለት ግን በገዛ ፍላጎትህ ራስህን አላዋቂ እያደረከው ነው ማለት ነው።>>
ኮንፊሽየሥ

<<መጽሐፍትን በሚገባ ማንበብ ማለት በድሮ ዘመን ይኖር ከነበረ በጣም አስተዋይ ሰው ጋር መወያየት ማለት ነው።>>
ሬኔ ዴካርቴሥ

<<ማስቲካ ለማምረት ከምናወጣው ወጪ በላይ ለመጻሕፍት ብዙ ወጪን ባናወጣ ኑሮ ይች ሀገራችን እንዲህ የሰለጠነችና የዘመነች አትሆንም ነበር >>
አልበርት ሀባርድ(አሜሪካዊ)

<<ከየትኛውም ነገር በላይ ትልቁንና ከፍተኛውን ደስታ የማገኘው ሳነብ ነው።>>
የፋሽን ዲዛይነሯ ቢልብላሥ

<<መጽሐፍን ከማቃጠል የባሰ በርካታ ወንጀሎች አሉ። ከነዚህ መሃል መጽሐፍትን አለማንበብ አንዱ ትልቁ ወንጀል ነው።>>
ጆሴፍ ብሮድስኪ

<<ዛሬ ያነበበ ነገ መሪ ይሆናል።>>
ማርጋሪት ፉለር

<<መጽሐፍ የማያነብ ሠው ጭራሽ ማንበብ ከማይችል ሰው በምንም አይሻልም።>>
ማርክትዌን

<<አንድ መጽሐፍ ባነበብን ቁጥር እዚህ ምድር ላይ በሆነ ቦታ ለኛ አንድ በር እየተከፈተልን ነው።>>
ቬራናዛሪያን

<<ማንበብ ከምንገምተው በላይ ዘላቂ የሆነ ደስታን ነው የሚሰጠን።>>
ላውራቡሽ
ምንጬ፦ንባብ ለህይወት ቅጽ ፩ (በኃብታሙ ማሞ ካሣዬ)
Join us:@KuziBo

Читать полностью…

ሳቅና ቁምነገር

ሱዳን በሶስተኛ ወገን የተደገሰላትን የጦርነት ወጥመድ በመተው ችግሩን በድርድር ለመፍታት ቁርጠኛ መሆን አለባት‼️
🗣ጀነራል ብርሃኑ ጁላ

ሱዳን በሶስተኛ ወገን የተደገሰላትን የጦርነት ወጥመድ ወደ ጎን በመተው የድንበሩን ጉዳይ በድርድር ለመፍታት ቁርጠኛ መሆን እንዳለባት የኢፌዴሪ ጦር ሃይሎች ጠቅላይ ኢታማዦር ሹም ጀነራል ብርሃኑ ጁላ ተናገሩ።
@KuziBo

Читать полностью…

ሳቅና ቁምነገር

ጆ ባይደን የትራምፕን ትዕዛዝ በመተላለፍ የኮቪድ-19 ጉዞ ገደብ እንደሚቀጥል አስታወቁ‼️

በነገው ዕለት ስልጣን የሚረከቡት የአሜሪካው ተመራጭ ፕሬዚዳንት ጆ ባይደን ቃል አቀባይ በዩናይትድ ኪንግደም፣ በአውሮፓ ህብረትና በብራዚል የተጣለው የጉዞ ገደብ እንደሚቀጥል አስታውቀዋል። ፕሬዚዳንቱ ይህንን ውሳኔ ያስተላለፉት የጉዞ ገደቡ ይነሳ የሚለውን የትራምፕን ትዕዛዝ በመተላለፍ ነው።

በያዝነው ሳምንት ሰኞ ዋይት ሃውስ የጉዞ ገደቡ ጥር 18፣ 2013 መነሳት አለበት የሚል ውሳኔ አሳልፎ ነበር። ይህም ማለት ተመራጩ ፕሬዚዳንት ጆ ባይደን ስልጣን ከያዙ ከስድስት ቀናት በኋላ ማለት ነው። ነገር ግን የጆ ባይደን ቃለ አቀባይ ጄን ፕሳኪ በበኩላቸው ወቅቱ የጉዞ ገደብ የሚላላበት አይደለም በማለት በትዊተር ገፃቸው ላይ አስፍረዋል።

Читать полностью…

ሳቅና ቁምነገር

አባይ ወልዱ እና ዶ/ር ሰለሞን ኪዳኔ በአእምሮ ጭንቀት ሕመም ጦር ኃይሎች ሆስፒታል ገቡ፡፡

@kuziBo

Читать полностью…

ሳቅና ቁምነገር

🔴 አስከሬን ሲቀበር የሚያሳይ Video
@KuziBo

Читать полностью…

ሳቅና ቁምነገር

ሁለተኛው አጋማሽ ተጀመረ

Читать полностью…

ሳቅና ቁምነገር

በመተከል ዞን ዘጠኝ ሰዎች ተገደሉ!

በዛሬው እለት ጥር 8/2013 በመተከል ዞን ቡለን ወረዳ በኤኮንቲ እና በቁጂ ቀበሌ ዘጠኝ ንፁሀን ዜጎች መገደላቸውን የአዲስ ማለዳ ታማኝ ምንጮች ተናገሩ።

ማንም ሰው መሳሪያ ይዞ እንዳይንቀሳቀስ እና የሰአት ገደብ በተጣለበት መተከል ዞን ዛሬም ግድያ ተፈፅሟል ሲሉ ለአዲስ ማለዳ ተናግረዋል።

የተገደሉትም ዜጎች መሳሪያ መያዝ ክልክል መሆኑን ተከትሎ ራሳቸውን መከላከል በማይችሉበት ሁኔታ ወደ እርሻ ቦታቸው በማቅናት ሳሉ መገደላቸውን ነው የአዲስ ማለዳ ምንጭ የተናገሩት።
@kuziBo

Читать полностью…

ሳቅና ቁምነገር

ትግራይ፡ ከፍተኛ የህወሓት አመራሮች አዲስ አበባ ውስጥ ፍርድ ቤት ቀረቡ

ባለፈው ሳምንት ትግራይ ውስጥ ተይዘው ወደ አዲስ አበባ ከተወሰዱት ከፍተኛ የህወሓት አመራሮች መካከል አቶ ስብሐት ነጋንና አቶ አቶ አባይ ወልዱን ጨምሮ ዛሬ አርብ ፍርድ ቤት ቀረቡ።

https://www.bbc.com/amharic/news-55681378

Читать полностью…

ሳቅና ቁምነገር

👥 Member /Follower Plus 📡

📣 #በቀላሉ_የቴሌግራም_ቻናል_እና_የግሩፖትን_ሜምበሮች_ማሳደግ_ይፈልጋሉ❓

✔️ እንግዳውስ በትክክል የሚያሳድግ BOT እናስተዋውቆ።
 ̄ ̄ ̄ ̄ ̄ ̄ ̄ ̄ ̄ ̄ ̄
🔗 ሪፈራል ሊንኮን ለሌሎች በመጋበዝ ነጻ ሜምበር የሚያገኙበት ምርጥ BOT ነው።
👤 #አንድ_ሰው_የርሶን_ሪፈራል_ሊንክ_ነክቶ_ወደቦቱ_ሲገባ እና የኛን ቴሌግራም ቻናል ሲቀላቀል #15_የቴሌግራም_ሜምበሮችን _ያገኛሉ።

❗️ያስተውሉ: ሜምበሮቹን ወደቻናሎት ማስገባት የሚችሉት #በርሶ_ሪፈራል_ሊንክ_የተቀላቀሉት_ሰዎች_ድምር_100_ሲደርሱ_ብቻ_ነው።

♻️ ከዚያማ በፈለጉት ሰዓት ማስገባት ይችላሉ።

💵 በክፍያ ማሳደግ ከፈለጉ ደግሞ
🔘 #ለ1000_offline_members (Offline አካውንቶች) ዋጋ 90 ብር ብቻ።
⭕️ #ለ1000_Active_members (Online ተጠቃሚዎች) ዋጋ 90 ብር

⤵️
/channel/Buy_members_Ethio_bot?start=r0314555416
〰〰〰〰〰〰〰〰〰〰
⤴️ በዚህ ሊንክ በመግባት እርሶም የአገልግሎቱ ተጠቃሚ መሆን ይችላሉ።
 ̄ ̄ ̄ ̄ ̄ ̄ ̄ ̄ ̄ ̄ ̄ ̄
ㅤ ㅤ ㅤㅤㅤㅤ ㅤ ㅤ ㅤㅤㅤ

Читать полностью…
Subscribe to a channel