legit_doubler_channe | Unsorted

Telegram-канал legit_doubler_channe - Bezibezita

-

@Tomas098 @Bezibezita አስደናቂ እውነታዎችን አዳዲስ ያልተሰሙ ነገሮች እንዲሁም የተለያዩ ግጥሞች እዚህ አሉ

Subscribe to a channel

Bezibezita

ጥንወት

ጥንወት ተጠናውቶኝ
ድንግዝግዝ አድርጎኝ
በሀሳብ አናውዞኝ
ናላዬን ወዝውዞኝ
አመል ሆነሽብኝ
እኔ ያንቺ ሱሰኛ
እየቃዥሁ አለሁ
ጠዋት እና ማታ
ማለዳ ስነቃ
ሲጋራ አጨሳለሁ
በጭሱ ተስለሽ
ውብ ሆነሽ አያለሁ
ሱሰኛ ሆኛለሁ
ደሞ ወደማታ
አረቄ እጠጣለሁ
በስካር መንፈስ ውስጥ
እቅፌ ውስጥ ገብተሽ
ስዳራሽ አድራለሁ
ሱሰኛ ሆኛለሁ
ጠዋት እና ማታ
አንቺን አስባለሁ

ዳዊት ንጉሴ


@getem0
@getem0

Читать полностью…

Bezibezita

(Santa_¥e)

እውነት እልሀለሁ
እውን አንተን መሳይ የዋህ ፍቅሩን ክዶ፣
የጠላህ እንደሆን ልቤ ሌላ ለምዶ😒፣
ምህረት ያሳጣው...
ለሰሚ ማይመች ሀያል ቅጣት ይቅጣው፣
ዘላለም አለሙን አፍቃሪ ያሳጣው😏፣

እውነት እልሀለሁ
አንተን የያዙ እጆች ሌላ ሰው ካቀፉ
ያለአንዳች ስስት ከአካላቴ ጎለው
ተነጥለው ይጥፉ፣
ነፍሴን የሚያስቷት የሚያጎድፏት ሁሉ
ላንተ ፍቅር ሲባል ተቆርጠው ይጣሉ😔

እውነት እልሀለሁ
በውጫው ውበት ነፍሴ ተመክታ🤦‍♀
ካንተ በላይ ቆንጆ...ሞልቷል ያልኩህ ለታ
ከስቼ ጠቋቁሬ እንደፅጌ🥀 ልርገፍ፣
በምንገድ ስታየኝ ሌላ ሴት መስዬህ
እያየኸኝ እለፍ😒፣

እውነት እልሀለሁ
የመጨረሻዬ ነህ....
ብዬ የገባሁትን ፅኑ ቃሌን ጥሼ🤔
የከዳሁህ እንደሁ ማተቤን በጥሼ፣
እሱ አይለመነኝ......የጠላሁህ ጊዜ፣
ጭንቄን ያበርክተው ይዋጠኝ ትካዜ፣

ግና ፍቅረይ...
አዲስ ቆንጆ ለምዶ ቀድሞ የሸፈተው
ያንተው ልብ እንደሆን😳ሌላዋን የሻተው

ተጨማሪ ወዷል ቢሉኝ🙄 እውነት እልሀለሁ
ደስታህ ደስታዬ ነው 😁 ቆሜ እድርሃለሁ።።
...
🙈🙈🙈

✌️✌️
#No_malekakes😌

@Axelym
@Axelym
@Axelym

Читать полностью…

Bezibezita

የማለዳ ራእይ!
(በእውቀቱ ስዩም)
ናፍቆትሽ ፀናብኝ
ብየ ስልክልሽ
‘አይዞህ ' አይባልም
መከሰት ነው እንጂ በገሀድ ወይ በህልም !
ካጨሽ አሰናብቺ
ትዳር ካለሽ ፍቺ
ለኔ ለምመኝሽ ሁሉን ነገር ስጪ
የህሊና ቀጪ
የልቦና ስሜት
ይሉንታና ሀሜት
ያገር ሰው ሽሙጥም
ከምኞቴ አይበልጥም ::
ተሊቀመላኩ
ክንፍ ተበድረሽ
ነፋስ ቀድመሽ በረሽ
ባለሁበት አገር
እንደ ሸዋዚንገር
ብረት ለበስ ጡንቻ
ባንድ ርግጫ ብቻ
የቤቴን በር ሰብረሽ
ዐይነ ርግብሽ ወድያ
ቀሚስሽ ወደ ላይ
ወደኔ በጥድፍያ
ወዳልጋው በዝላይ
በጀርባየ ሁኘ
ከእግሮቼ መካከል የጠላ ምልክት
አንቺ ጆሮ ሆነሽ
እኔ ሎቲ ሆኘ-ተጣጥሞ ስክት !
እንዲህ እያሰበ ገላየ ሲቸገር
መጣሁ ትያለሽ ስል
“አይዞህ “ ብሎ ነገር፤
የማለዳ ራእይ፤ ምኞቴን በማመን
በገሀድም ይሁን፤ ወይም በሰመመን
አሳትፊኝ አልሁ እንጂ
ከገላሽ በረከት፤ ከሙቀት ከለዛው
የቃል ምፅዋትማ ሞልቷል በየታዛው!
@tobiya7

Читать полностью…

Bezibezita

የራስ ተፈሪያን እንቅስቃሴ እና የትውልድ ቦታ ራስ ተፈሪያን የጃማይካዊያን ነው የ ራስ እንቅስቃሴ አብዛኞቹ ተከታዮቹ ጃማይካዊያን ናቸው። ነገር ግን የራስ ተፈሪያን እንቅስቃሴ መንፈሳዊነት የተፈጠረበት ቦታ ኢትዮጵያ ነው። በአማርኛ "ራስ" ማለት አለቃ እንደማለት ሲሆን ተፈሪ ደግሞ ያው የ አፄ ሀይለስላሴ ስም ነው ። እንቅስቃሴው አፄ ሀይለስላሴን እንደ ፈጣሪ ስጦታ ይቆጥራቸዋል ። ለበለጠ መረጃ የኢትዮጵያን ሰንደቅዓላማ ቀለማትን ይመልከቱ

Читать полностью…

Bezibezita

ይህም አለ እንዴ🤔 እንቅልፍ ከወሰዳት እስከ ሁለት ወር የማትነቃው የ 17 አመቷ ኮሎምቢያዊት ወጣት

Читать полностью…

Bezibezita

👉አምፖልን የፈለሰፈው ቶማስ ኤዲሰን ጨለማን ይፈራ ነበር ።

Читать полностью…

Bezibezita

🇪🇹ማግሰኞ መስከረም ፳፮ ፳፻፲፫ ዓ.ም
━━━━━━━━━━━━━━━━━━━━━━━


እረኛ ይሉታል ፥ የአለሙን ጌታ
ፍለጋ ላይ ቢያዩት ፥ አንድ በጉ ጠፍታ ።

​​ ┈┈┈┈•◦●◉❖◉●••┈┈ ┈
✍🏽© ቤተልሔም ጌታነህ
╰══•••┈ ┈ ┈•◦●◉❖◉●••┈┈ ┈

ምንጭ ➸ የግጥም አብዮት
ለመቀላቀል 👉🏽 @poemandquote
አስተያየት 👉🏽 @poemandquotebot
┏─━─━─━─━≪♡≫━─━─━─━─┓
❘ ❝ ሰው፡ከሆኑ፡በቂያችን፡ነው። ❞ ᴀ ❘
┗─━─━─━─━≪♡≫━─━─━─━─┛

Читать полностью…

Bezibezita

በ ሐገረ እስራኤል የራሷ ቦታ ያላት (ዴር ሱልጣን ) ብቸኛዋ ሐገር ኢ ት ዮ ጵ ያ ነች ።ይሄንን ቦታ ምዕራባዊያንና አንዳንድ የምስራቅ ሀገራት ለመውሰድ ቢሞክሩም እንዳልተሳካላቸው ታሪክ ይዘክራል።

Читать полностью…

Bezibezita

​​​​​​​​​​​​​​​​​​​​​​​​​​​​​​​​​​​​​​​​​​​​​​​​​​​​​​​​​​​​​​​​​​​​​​​​​​​​​​​​​​​​​​​​​​​​​​​​​​​​​​​​​​ ​​​​​​​​​​​​​​​​​​​​​​​​​​​​​​​​​​​​​​​​​​​👤 Getish Mamo
🎵
Zufanu New | ዙፋኑ ነው
━━━━━━━━━━━
⇝ RELEASED DATE :
#OCT2, 2020🔥
⇝ TYPE :
#Single
⇝ Quality: 480P
⇝ FORMATS :
#Mp3 + #Video
⇝TG CHANNEL
: @AASHADDIS
━━━━━━━━━━━━

Читать полностью…

Bezibezita

የቃል ፍቅር ብቻ


ከእውነት አለም እርቆ፣
ከውሸት አለም ጠልቆ፣
ያለ መስሎ የሌለ፣
ባስመሳዮች አፍ ላይ የዋለ፣
የቃል ፍቅር ብቻ አለ።
ከልብ ያላደረ፣
በውሰጥም ያልኖረ፣
የቃል ፍቅር ብቻ አለ፤
ታማኞችን ያቆሰለ።

✍kirub

Читать полностью…

Bezibezita

✍ በአሜሪካዊው ሳይካትሪስት ዶክተር አለን ፍራንሲስ "ወንዶች ስለ ሴቶች ሁሉን ነገር ያውቃሉ" በሚል ርዕስ የተፃፈው መፅሀፍ በ1988ት የተመረቀ ሲሆን ይህ መፅሀፍ በውስጡ 128ት ገፆች አሉት ! የሚገርመው ታዲያ በመፅሀፉ ውስጥ የሚገኙት 128ቱም ገፆች ግን አንዲትንም ፊደል ያልተፃፈባቸው ነጭ ወረቅት መሆናቸው ነው ፤ ርዕስ ብቻ ያለው ይህ መፅሀፍ በሚልየን ጥራዞች የተሸጠ ሲሆን ለ30 ጊዜ ታትሞ ለአንባቢያን ለገበያ የቀረበ ሲሆን በሚልየን ዶላር ደረጃ በየአመቱም ገቢም ያስገባል !! ግን አንባቢያን ምኑን ሊያነቡት ነው መፅሀፉን የሚገዙት 🤔🤔😄

Читать полностью…

Bezibezita

#አቶደኝም_አትበል 🙅‍♀💐
አቅም እየከዳኝ ቃላትን ለማውጣት
አፌ እስከሚያያዝ ቸግሮት ማስረዳት
ዕልፍ የሆነ ግዜ እንደዛ ስወደህ
አግዝፌ ከማንም ብቻየን ሳፈቅርህ
ያ ሁሉ ባይገባህ ላንተ ስል የሆንኩት
ዛሬ ሄድኩ ብለህ
አቶደኝም አትበል ቅስሜን አታንኮትኩት
* በያኔው ግዚያችን *
ላንተ የነበረኝ መውደድና ስሜት
ልኩም አይገኝም የሚሰፈርበት
ላፍታ ማይቋረጥ ምላሽ የማይጠብቅ
ላላጠፋው ጥፋት ይቅርታ ሚጠይቅ
ወረት ሳይዳስሰው ከድሜየ ሚዘልቅ
ከኔ ደስታ በላይ ላንተ የሚቦርቅ
ልዩ ነበርኮ ከቃልም የሚርቅ
ገደሉን ሜዳ ነው ብትል እንኳ ማምን
በሄደበት ሁሉ አብሮ የሚያስመንን
አብረን ሁነን እንኳ ተቀምጠህ ጎኔ
የሚያስናፍቅ ነበር እያየሁህ ባይኔ
እንቅልፍንኳ ወስዶህ ደርሶ የሚጨንቀኝ
ነቅተህ እስከማይህ ትግስት የሚያሳጣኝ
ሰው የለም እስከምል በቃ ካንተ በቀር
ነበርኮ የኔ ላንተ የነበረኝ ስሜትና ማፍቀር
እናም እባክህን
ዛሬ ሄድኩ ብለህ አትበል አቶደኝም
ለጆሮም ይቀፋል ግራ ነው ለሰሚም

Читать полностью…

Bezibezita

ተኩስ 😍👮‍♂
መጀመሪያ ጊዜ የተኮስከው ጥይት
በሰው እጅ ነው አሉ ለዛውም በሴቲት
ማስታወሻ እንዲሆን ነበር ለካ ኃላ
ድሮ በምትወድህ እሁን በምትጠላ
የተኮሱት ሁሉ መቼ ሰውን ሊገል
መጨረሻው ሆነ በፍቅር ላይ በቀል
ታዲያ ይህን ግዜ እንዲሆን በቃልህ
ሁለተኛ ተኩስ መሣሪያው ይቅለልህ
@bezibezita

Читать полностью…

Bezibezita

🇪🇹ሐሙስ መስከረም ፳፩ ፳፻፲፫ ዓ.ም
━━━━━━━━━━━━━━━━━━━━━━━



አትውረድ እንባዬ ፥ ማረፊያ የለህም
እንደ ራሔል እንባ ፥ ውጣ ወደ አርያም ።

Читать полностью…

Bezibezita

A
👤 Abbush Zeleke
👤 Abby Lakew
👤 Abdu Kiar
👤 Abeba Desalegn
👤 Abebe Teka
👤 Abel Mulugeta
👤 Abinet Agonafir
👤 Abrham Gebremedhin
👤 Abraham Negussie
👤 Abonesh Adnew
👤 Ada Kassaye
👤 Ahmed Teshome
👤 Aklilu Seyum
👤 Alemayehu Eshete
👤 Alex Olompia
👤 Ali Birra
👤 Aster Aweke
👤 Aster Kebede
👤 Asnakech Worku
👤 Aregahegn Worash
B
👤 Bethelhem Dagnachew
👤 Betty G
👤 Bezuayehu Demissie
👤 Bisrat Surafel
👤 Buze Man
D
👤 Dan Admassu
👤 Dawit Mellesse
👤 Derege Degefaw
👤 Dj Rophnan
E
👤 Eden Gebreselassie
👤 Elias Asefa
👤 Endegna/የኛ+(እንደኔ😉)
👤 Ephrem Tamiru
👤 Esubalew Yetayew
👤 Eyob Mekonnen
F
👤 Fasil Demoz
👤 Fikeraddis Nekatibeb
G
👤 Gedion Daniel
👤 Genet Masresha
👤 Gete Anley
👤 Gigi
👤 Gili Yalo
👤 Gossaye Tesfaye
H
👤 Haileye Taddese
👤 Haile Roots
👤 Hamelmal Abate
👤 Hana Shenkute
👤 Haymanot Girma
👤 Helen Berhe
👤 Henok Abebe
👤 Hibist Tiruneh
👤 Hirut Bekele

Читать полностью…

Bezibezita

ስቀሽ … አበረድሽኝ

ከጥም ቆራጭ ምንጭሽ ፥ ልጠጣ ጎምጅቼ
ላታልልሽ ዝቼ
ጢሜን ተላጭቼ
ጫማዬን አጥድቼ
በሚያሽበለብል ቃል ፥ ምላሴን ገርቼ
ለበአሌ ላርድሽ ፥ ቢላዋየን ስዬ
ሁዳዴን የጦመ ፥ መልካም ሰው መስዬ
እንደ አታላይ ተኩላ
ሊነጥቅ ሊበላ
ለምድ እንደለበሰ ፥ በበጎች መካከል
ሳር መጋጥ ጀምሮ ፥ መንጋውን ለመምሰል
በዚያው እንደቀረ ፥ ከሰርዶ ተዋዶ
ጨዋታ ወግሽን ፥ ዠሮየ ተላምዶ
ፍቅር አልብሰሽኝ
ውሀ ልሰርቅሽ ስል ፥ እርጎ አበድረሽኝ
ነድጄ መጥቼ ፥ ስቀሽ አበረድሽኝ

✍ ናትናኤል ጌቱ
@getem0
@getem0

Читать полностью…

Bezibezita

"ታጥቋል" በተባለ በየዕለት መሳደድ፣
"ባልታወቀ" ገዳይ በካራ መታረድ፣
"ነፍስ ይማር" እያሉ ሞትን መለማመድ።
ሰለቸን! ..... ታከተን!
መረረን! ..... ሰቀቀን!
ደከመን! .... አመመን!

ሜሮን ጌትነት
@getem
@getem
@getem

Читать полностью…

Bezibezita

. ተ ረ ት ተ ረ ት .
-----------------------------
ተረት ተረት
የላም በረት
አንድ ሰው ነበረ
በሀብቱ የከበረ
ውልደቱም እድገቱም የሆነ አሜሪካ
ባለው ነገር ሁሉ ጭራሽ የማይረካ
ሲሞላለት ሆዱ 'ሀምበርገሩን' በልቶ
'ጋዴሚት' ይለዋል አልጋው ላይ ተኝቶ።

ተረት ተረት ...
አንድ ሰው ነበረ
በጣም የተማረ
በቃኝን የማያውቅ የጣልያን ተወላጅ
ሁሌም ለአዲስ ነገር ጠዋት ማታ 'ሚባጅ
'ፒዛና ፓስታውን' ጥርግርግ አድርጎ
ይተኛል ጥሩ እንቅልፍ 'ባፋንኩሎ' ብሎ።

ተረት ተረት ...
አንድ ሰው ነበረ
ህልሙ የሰመረ
ጀርመን ነው ሀገሩ
'ምርጥ ዘር' ነው ዘሩ
'ቮግ ቮረስቱን' በልቶ ሞልቶለት አዱኛ
'ሻይሰ' ብሎ ነው ሁሌም የሚተኛ።
ተረት ተረት ...
አንድ ሰው ነበረ
የተመራመረ
ጃፓን ተወለደ
በሮቦት አደገ
ቀን ሲሰራ ውሎ
ሩዙን ቀቅሎ
'ሱሺ' ጠግቦ በልቶ
'ባጋይሮ' ብሎ ያነጋል ተኝቶ።

ተረት ተረት ...
አንድ ሰው ነበረ
አጥቶ የተቸገረ
ኢትዮጵያ ተወልዶ ኢትዮጵያ ያደገ ኩራት ነው 'ራቱ ዛሬም ሆነ ነገ
ቢጠግብም ባይጠግብም ቆሎውን ቆርጥሞ
'ተመስገን' ይለዋል መደብ ላይ ተጋድሞ።

ተረት ተረት ...
እግዜር ከመንበሩ ወደ ምድር ወርዶ
ይጎበኝ ነበረ በየቤቱ ሄዶ
ከእነኚያ ከአራቱ ቆዳቸው ከነጣ
ከየአንደበታቸው መልካም ነገር ቢያጣ
ጥቁሩ ሲያመሰግን የፈለገው ሞልቶ
ያጎደለባቸው አንድ የሆነ ነገር እንዳለ ገምቶ
ሊጨምርላቸው ነጮቹጋ ሄደ አበሻውን ትቶ።

ተረቴን መልሱ
አፌን በዳቦ አብሱ።
-------------------------------
©✍ በሜሮን ጌትነት
@getemmmmmm
@getemmmmmm
@getemmmmmm

Читать полностью…

Bezibezita

አምፖልን እና ሌሎች ተጨማሪ 1500 አስገራሚ የፈጠራ ውጤቶችን አሁን ላለንበት አለም ያበረከተው ቶማስ ኤዲሰን ይሄንን ሁሉ ድንቅ የፈጠራ ዉጤት ሲያበረክት የቀለም ትምህርቱ ግን ከ አራተኛ ክፍል የዘለለ አልነበረም።

Читать полностью…

Bezibezita

#ችግሬ

እርም ያባቴን ሥጋ
ለዓለም ብተጋ
ዓለም በቃኝ ብዬ
ላልመለስ ምዬ
ምዬ ተገዝቼ
ላልመለስ ዝቼ
ሁሉን ነገር ትቼ
አንተንም 'ረስቼ
ይዤ ጾም ጸሎቴን
ውዳሴ ስግደቴን
ልመንን እልና
ታስገድፈኛለህ በ'ልሜ ትመጣና::

Читать полностью…

Bezibezita

#ሳይኮሎጂ እንደሚለው
ቢጫ ቀለም የሚወዱ ሰዎች
በጣም ሀይለኞችና የውሳኔ ሰዎች
የመሆን ዕድላቸው ሰፊ ነው
$@♥

Читать полностью…

Bezibezita

╭─┅┅─┅─┅─═┅❀┅═─┅─┅─┅┅─╮
「❝ የዋህ፡ሰዎች
ልባቸው፡ንፁህ፡ነው።
በሰዎች፡ዘንድ፡ግን
ተቀባይነት፡አይኖራቸውም። ❞」
╰─┅┅─┅─┅─═┅❀┅═─┅─

Читать полностью…

Bezibezita

"ብሉይ ኪዳን "
ሊቀ ነቢያት ሙሴን የአመራርነት ጥበብ ያስተማረው #ኢትዮጵያዊ_ዮቶር ነው ። ስለዚህ ለእስራኤል ከፈርዖን ነፃ መውጣት የኢትዮጵያ ከፍተኛ ሚና አለበት ማለት ነው።
❤️👉 ቴዲ አፍሮ በጥቁር ሰው አልበሙ ላይ የየቶርን ኢትዮጵያዊነት ለመጥቀስ ሞክሯል።



"የዮቶር እርስት ውብ ሀገር ኢትዮጵያ ነች❤️❤️❤️🇪🇹🇪🇹።

Читать полностью…

Bezibezita

📢Join us 👉🆔 @Aashaddis

Читать полностью…

Bezibezita

👉✍✍✍✍✍✍
👉እንደ ጣት አሻራ ሁሉ የ እያንዳንዱሰው የምላስ አሻራ የተለያየ ነው
👉ፈረንሳይኛ ከ 600ዓመታት በላይ የ እንግሊዝ ብሔራዊ ቋንቋ ሆኖ አገልግሏል
👉ኤልቪስ ፕሪስሊ 8ኛ ክፍል ሳለ በ ሙዚቃ ትምህርት ዝቅተኛ ውጤት C ነበር ያገኘው
👉አንድ አማካይ የ 4አመት ህፃን በቀን ውስጥ ከ400 በላይ ጥያቄዎችን ይጠይቃል
👉ቀንድ አውጣ ለ3 አመታት እንቅልፉን ሊለጥጥ ይችላል
👉ዝሆኖች መዝለል የማይችሉ ብቸኛ እንስሳት ናቸው
👉አንዳንድ ድመቶች ለሰዎች አለርጂክ ናቸው
👉አብርሃም ሊንከን የአሜሪካ ፕሬዚዳንት ከመሆኑ በፊት የ ሀገሩ የነፃ ትግል ሻምፒዮና ነበር በ300 ገደማ የነፃ ትግል ግጥሚያዎች ላይ ተሳትፎ በ አንዱ ብቻ ነው የተሸነፈው
👉በ16ኛው እና በ17ኛው ክ/ዘመን ቱርክ ውስጥ ቡና ሲጠጣ የተያዘ ሰው ልሞት ይዳረግ ነበር
👉🙄የዛሬ 3ሺ አመት ገደማ ግብፃዊያን የሚሞቱት በ30 አመት እድሚያቸው ነበር
👉ኮካኮላ መጀመሪያ ሲፈጠር ቀለሙ አረንጓዴ ነበር

Читать полностью…

Bezibezita

እናቱን ለሚወድ ❤❤ ከወደዳችሁት የ ባላገሩን ምርጥ ሁሌም አደርሳለሁ የተወደዳችሁ

Читать полностью…

Bezibezita

#አልወድህም_አሁን 🤷‍♀
መያዝ ስችል ያኔ እያለ በጆችህ
የጣልከውን ፍቅር ትርጉሙ ቀሎብህ
ዛሬ ከረፈደ ገብቶህ መውደድ ጥቅሙ
ማግኜት ብትሻም አሁን የለም አቅሙ
በሌሎች ተወስዷል ያንተን በሚያልሙ
እናም እባክህን የትናንቱ ጓዴ
ዘወር በልልኝ ጥፋ ከመንገዴ
እንኳን ለይቅርታ የሚሆን ላብሮነት
ፍላጎትም የለኝ ጭርሱን ለማውራት
ያኔ የምታቀው ላንተ ያለኝ ቦታ
ተቀይሮ ገብቷል ከጥላቻ ተርታ
በቃ ይሄው ብቻነው የምነግርህ እውነት
በል ዋጠው እንግዲ ቢመርም እንደሬት
#keri

Читать полностью…

Bezibezita

ሀኪሙ .........😔
ሀኪም ድረስልኝ እምዬ ታማለች
አንዴ ሻል ሲላት ደግማ እየታመመች
እራሷን ነው ሲባል እግሯን ያማታል
እግሯን ሲሉ ደግሞ ሆዷን ይቆርጣታል
ሀኪሙ ...........😒😒😒
እጆችህ መድሀኒት ሲባል ሰምቻለሁ
ምስኪኗን እማዬን ላንተ ሰጥጫለሁ

ምን ሆና ነው አሉኝ መታመሟን አይተው
በጣሙን ከስታለች ልጆቿ ወፍረው
እንዴት አይወፍሩ ደሟን እየጠጡ
ልትሞት ስትል አይተው ጥለው ፈረጠጡ
ታዲያ በዚህ መሀል ምንም የማላውቀው
የምወዳት ልጇ እኔ ተሰቃየው



...............እባክህ ሀኪሙ 😔😔😔
እውነት ሀኪም ከሆንክ እጆችህ መድኃኒት
እናቴን ዳስልኝ በፈዋሽ መድሀኒት
በይቅርታህ በምህረት







መታሰቢያነቱ አሁን ትንሽ ካርታ ሆና ለቀረችው እናታችን
እናት ኢትዮጵያ 🇪🇹❤️

Читать полностью…

Bezibezita

J
👤 Jah Lude
👤 Jacky Gossee
👤 Jano Band
👤 Jonny Ragga
👤 Jossy(Yoseph Gebre)
K
👤 Kirubel Assefa
L
👤 Lij Michael
M
👤 Mahmoud Ahmed
👤 Mahlet G/Giorgis
👤 Manalemosh Dibo
👤 Maritu Legesse
👤 Markon
👤 Madingo Afework
👤 Melkamu Meaza
👤 Melkamu Tebeje
👤 Michael Belayneh
👤 Mikaya Behailu
👤 Minyeshu Kifle
👤 Muluken Melesse
N
👤 Neway Debebe
👤 Nati Haile
👤 Nhatty Man
S
👤 Sami Dan
👤 Sayat Demissie
👤 Seleshe Demissie
👤 Shewandagne Hailu
T
👤 Tamrat Desta
👤 Teddy Afro
👤 Teddy Yo
👤 Tesdenia G/Markos
👤 Tesgaye Eshetu
👤 Teshaye Yohannes
👤 Theodros Tadesse
👤 Tibebu Workyie
👤 Tigist Fantahun
👤 Tilahun Gessesse
Y
👤 Yabu Jc
👤 Yehunie Belay
👤 Yeshi Demelash
Z
👤 Zeritu Kebede
👤 Ziggy Zaga
🌐 Join A ቃልኪዳን Tube More!!!😉

Читать полностью…

Bezibezita

Ye ethiopian artists discography👇

Читать полностью…
Subscribe to a channel