lewetatoch_mekir | Unsorted

Telegram-канал lewetatoch_mekir - 🌴ለወጣቶች ምክር🌴

-

🔖ይህ የወንድማችሁ Mohammed ebnu seid ቻናል ነው። በዚህ ቻናል ውስጥ ብዙ አይነት ትምህርቶችን ለማድረስ እና ለማስተማር እሞክራለሁ ። ኢንሻአላህ ስህተቴን በቁርአን በሀዲስ ላረመኝ አላህ ይዘንለት እቀበላለሁ @Dear_ibnu_seid አድርሱኝ 🔖 አላህ ዱንያዬም አኼራዬንም እንዲያሳምርልኝ ዱአ አድርጉልኝ ። @Lewetatoch_mekir 👈👈join ይበሉ

Subscribe to a channel

🌴ለወጣቶች ምክር🌴

በስልክህ ጉዳይ የውመል ቂያማ አላህ ፊት ትጠየቃለህ ።

እያንዳንዱ ስለፃፍከው ፅሁፍ
በስልክ ስለምትመለከተው ነገር
ሼር፣ ላይክ፣ ኮመንት ስላደረገው
ስለምትደዋወለውና ስላወራኸው
ስለእያንዳንዱ ትጠየቃለህ።

መልካም ስትሰራበት ከነበረ በጥሩ ትመነዳለህ። ክፋ ከነበረ ደግሞ የእጅህን ታገኛለህ።

የዛኔ ቁጭት በማይጠቅምበት ቀን ዋ! ጥፋቴ ምናለ ስልክ ባልነበረኝ ምናለ ሚዲያ የሚባል ባላወቅኩኝ ብለህ ከምትመኝና ከምትፀፀት ዛሬውኑ የስልክና የሚዲያ አጠቃቀምህ አስተካክል።

በስልክህ ሰበብ ጀነት ልትገባ አልያም የጀሀነም እሳት ልትወርድ መሆኑን አስበህ ምርጫህን አስተካክል።

‏سيسألك الله عن هذا الجهاز الذي بين يديك!


--------------------
mohammed ebnu seid
-----------------------------
🍀🍀🍀
በቴሌግራም ይ🀄️ላ🀄️ሉን!
➢👇👇👇

@Lewetatoch_mekir
@Lewetatoch_mekir

Читать полностью…

🌴ለወጣቶች ምክር🌴

ወጣትነት በሚያልፍ ቀንና በሚመጣ  ምሽት መሀል መገኘት ነው!

ምነው ለዝች ለኩንትራት ኑሮ ወንጀል መስራታችን በዛ? ከአሏህም ከሰውም መጣላታችን መዛሳ? ለሚደበዝዝ ስሜት የፈካውን ዐለም (አኼራን) አጨለምንውሳ!? ከቶ ምን ይሻለን ይሆን?

ውዱ ነብያችን ﷺ መፍትሄውን ሲነግሩን የሚከተለውን ይላሉ ፦

كُنْ فِي الدُّنْيَا كَأَنَّكَ غَرِيبٌ أَوْ عَابِرُ سَبِيلٍ "

"ዱንያ ላይ ስትኖር እንደ እንግዳ ወይም እንደ አላፊ መንገደኛ ሁን።"

1ኛ, ዱንያ ላይ እንግዳ ሁን" እንግዳ ማለት: የሰጡትን በልቶ፣ እዚህ ተኛ በተባለበት ቦታ ላይ የሚተኛና የታዘዘውን በአግባቦ ታዞ የሚያድር ሰው ነው!። አንተም የሰማያትና የምድር ባልተቤት ለሆነው (ለአሏህ) ታዘህና የሰጠህን ሲሳይ ተመግበህ ለትእዛዛቱ የምታድር ባርያው ሁን!።

2ኛ, እንደ አሏፊ መንገደኛ ሁን" መንገደኛ ሰው ማለት: ወግ የማያበዛ፣ ለሚሄድበት ነገር ቶሎ መድረስን የሚሻና ምንገዱን ከሚያቀላጥፍለት ነገር ውጭ ምንም ነገር የማይፈልግ ሰው ነው። አንተም እንደምንገደኛ ቃላቶችህ የተገደቡ፣ ከጀነት ውጭ ምንም ነገር የማትመኝና ጀነት ለመግባት የሚያግዝህን መልካም ስራን ከመስራት የማትቦዝን ትሁት ሰው ሁን!።

--------------------
mohammed ebnu seid
-----------------------------
🍀🍀🍀
በቴሌግራም ይ🀄️ላ🀄️ሉን!
➢👇👇👇

@Lewetatoch_mekir
@Lewetatoch_mekir

Читать полностью…

🌴ለወጣቶች ምክር🌴

◼️ወንጀሉ ላሳሰበው ሰው ትልቅ ብስራት !!
➖➖➖➖➖➖➖➖➖➖➖➖➖

👉የአረፋ ቀን ፆም የሁለት አመት ወንጀል ያብሳል።

♦️ትንሽ ሰርቶ ብዙ ማትረፍ ማለት ይህ ነው።

✅ ከአቡቀታዳህ ተይዞ እንደተወራው የአላህ መልእክተኛ - ﷺ - ስለ አረፋ ቀን ፆም ተጠይቀው እንዲህ አሉ፦ {ያለፈውንም የወደፊቱንም (የሁለት) አመት ወንጀል ያብሳል}።

📚ሙስሊም ዘግቦታል።

ይህ ሀቂቃ ለተጠቀመበት ሰው ትልቅ እድል ነው።

↪️የአረፋ ቀን ማለት፦
◾️ሰዎች ከጀሀነም ነፃ የሚወጡበት
◾️ወንጀሎቻቸው በብዛት የሚማርበት
◾️ዱአቸው ይበልጥ ተቀባይነት የሚያገኝበት
◾️አረፋ ተራራ ላይ በቆሙት ባሮቹ አላህ የሚፎክርበት
◾️የሀጅ ዋና ሩክን የሆነው አረፋ ተራራ ላይ የሚቆምበት
◾️አላህ እዝነቱ ለባሮቹ የሚቸርበት የአመቱ ምርጥ ቀን ነው።

↪️ ይህንን ወሳኝ ቀን፦
💦ቀኑን በመፃም
💦ዱአ በማብዛት
💦ቁርአን በመቅራት
💦ዚክር በመዘከር
💦ሶደቃ በመስጠት
💦ተክቢራ በማብዛትና
👉በሌሎችም መልካም ስራ ላይ ሆነን ልናሳልፈው ይገባል።

✅ ይህንን ታላቅ እድል ቀጣይ አመት ላታገኘው ትችላለህና ዛሬ ላይ በአግባቡ ተጠቀምበት።

--------------------
mohammed ebnu seid
-----------------------------
🍀🍀🍀
በቴሌግራም ይ🀄️ላ🀄️ሉን!
➢👇👇👇

@Lewetatoch_mekir
@Lewetatoch_mekir

Читать полностью…

🌴ለወጣቶች ምክር🌴

ጨረቃ በመታየቷ የዙልሒጃ ወር ነገ ሰኞ  አንድ ብሎ ይጀምራል! በዚህም የኢድ አል አድሃ አረፋ በዓል ሰኔ 21 ዕለተ ረቡዕ እንደሚከበር ታውቋል!

ከነገ ጀምሮ ያሉትን 10ቱን ቀናት በኢባዳ እናሳልፈው!

--------------------
mohammed ebnu seid
-----------------------------
🍀🍀🍀
በቴሌግራም ይ🀄️ላ🀄️ሉን!
➢👇👇👇

@Lewetatoch_mekir
@Lewetatoch_mekir

Читать полностью…

🌴ለወጣቶች ምክር🌴

ጅሀድ በጥሩ ንያና ሱናውን በጠበቀ መልኩ፣ ልክ በሰይፍና በመሳሪያ እንደሚሆነው ሁሉ፣ በንግግርና በጹሑፍም ይሆናል። ስለዚህ በምንናገረውና በምንፅፈው ንያችንን እናስተካከል! ሱናውን በጠበቀ መልኩ እንታገል! ከዚህ ውጭ ዲንን ሱናን ከፍ ለማድረግ በቻሉት የሚታገሉ ሰዎችን ወኔያቸውን ግባቸውን ለመገደል፣ ዝቅ ለማድረግ እንዲሁም የጥመት አፍካር (አስተሳሰቦችን) ከፍ ለማድረግ፣ ሶፋችንን ወይም ፍራሻችን ላይ ተቀምጠን ጅሀድ በሰይፍ ነበር እንጅ! እያልን ከመፃፍ ይልቅ በምንችለው ትንሽ ብንሞክር ይሻል ነበር።  የሰይፉንም አላህ ትክክለኛ መስፈርቱን አሟልቶልን አንገታችን የሚሞሸለቅ ያድርገው! ጉዳዩ ጀነት ነው ከተገኘ ምንም ቢሰጡት ከምንም ጋር አይሰተካከልም። ችግሩ መስፈርቱ መሟላቱ ላይ ነው።

--------------------
mohammed ebnu seid
-----------------------------
🍀🍀🍀
በቴሌግራም ይ🀄️ላ🀄️ሉን!
➢👇👇👇

@Lewetatoch_mekir
@Lewetatoch_mekir               

Читать полностью…

🌴ለወጣቶች ምክር🌴

ሙሲባውን አላህ እንዲመለስልን በዱዓእ እንበርታ!

በተለይም ከአሱር በኋላ ባለው ጊዜ ዱዓእ ሙስተጃብ ነው ተብሏልና!


--------------------
mohammed ebnu seid
-----------------------------
🍀🍀🍀
በቴሌግራም ይ🀄️ላ🀄️ሉን!
➢👇👇👇

@Lewetatoch_mekir
@Lewetatoch_mekir

Читать полностью…

🌴ለወጣቶች ምክር🌴

ፍትህ የሃገር ዋልታና ማገር ነው። ፍትህ በህዝቦች ውስጥ ለሚኖር ግጭትና መቃቃር አቋራጩ የመፍትሄ መንገድ ነው። ማስተዋል ለቻለ እስከ አፍንጫው ከታጠቀ ጦር በላይ ለሃገር እድገትም ይሁን ዘላቂ ሰላም የሚያስፈልገው ፍትሃዊ አስተዳደር ነው። ዳሩ ምን ዋጋ አለው? አፍሪካውያን ከታሪክ የምንማረው ከታሪክ አለመማርን ነው። ቤታቸው ፈርሶ ጎዳና ላይ የወደቁ ወገኖቻችን እንባ ዛሬ ከምናየው የከፋ ለሁላችንም የሚተርፍ መከራ እንዳያመጣብን ያስፈራል። አላህ ይሁነን።

--------------------
mohammed ebnu seid
-----------------------------
🍀🍀🍀
በቴሌግራም ይ🀄️ላ🀄️ሉን!
➢👇👇👇

@Lewetatoch_mekir
@Lewetatoch_mekir

Читать полностью…

🌴ለወጣቶች ምክር🌴

📱 በስልክህ ጉዳይ የውመል ቂያማ አላህ ፊት ትጠየቃለህ ‼️

እያንዳንዱ ስለፃፍከው ፅሁፍ
በስልክ ስለምትመለከተው ነገር
ሼር፣ ላይክ፣ ኮመንት ስላደረገው
ስለምትደዋወለውና ስላወራኸው
ስለእያንዳንዱ ትጠየቃለህ።

መልካም ስትሰራበት ከነበረ በጥሩ ትመነዳለህ። ክፋ ከነበረ ደግሞ የእጅህን ታገኛለህ።

የዛኔ ቁጭት በማይጠቅምበት ቀን ዋ! ጥፋቴ ምናለ ስልክ ባልነበረኝ ምናለ ሚዲያ የሚባል ባላወቅኩኝ ብለህ ከምትመኝና ከምትፀፀት ዛሬውኑ የስልክና የሚዲያ አጠቃቀምህ አስተካክል።

በስልክህ ሰበብ ጀነት ልትገባ አልያም የጀሀነም እሳት ልትወርድ መሆኑን አስበህ ምርጫህን አስተካክል።

‏سيسألك الله عن هذا الجهاز الذي بين يديك!


--------------------
mohammed ebnu seid
-----------------------------
🍀🍀🍀
በቴሌግራም ይ🀄️ላ🀄️ሉን!
➢👇👇👇

@Lewetatoch_mekir
@Lewetatoch_mekir

Читать полностью…

🌴ለወጣቶች ምክር🌴

ውዷ እህቴ እስቲ ይህቺን ስሚኝ....‼️

እንደ ሸንኮራ አገዳ ናት ሁሉም ከመጠጠ ቦሃላ የሚጥላት...!!

ውድ እህቴ ዛሬም ነጌም በመጨረሻው አለም ለስኬት የሚበቁት የሱን ትዕዛዝ የሰሙና የተከተሉ ናቸዉ።  አለህ አንቺን ለስኬት የሚያበቁ ድንጋጌዎችን ደንግጎልሻል።

ከሱ ውጪ ያሉት ደግሞ አላማቸው ሒጃብሽን ማስጣልና ማስወርወር ነው። ይህን የሚያደርጉት አላማቸውን ለማሳካት ሲሉ ነው። ስለዚህም እኩይ አላማ ብለውም ገንዘባቸውን ይበትናሉ። ጊዜያቸውን ይሰዋሉ። *ይህ ሁሉ ትግል አንችን ከአለህ መንገድ ለማስወጣት ነው* ።... *የእርቃን መፅሄቱ ...የወሲብ መናሃርያ ኢንተርኔቱ...የቴሌቬዥን ሙሰልሰሉና ፊልሙ...ሒጃብን የማጣጣል ዘመቻው ...በማህበረ ሰብ መካከል ዝሙት ይስፋፋ ዘንድ ነው።*

👌ውዷ እህቴ እምቢ በያቸው በሂጃብሽ ሙጭጭ በይ አደራሽን...
እንደምታውቂው መናፍቃን አላማቸው ርካሽ ነው። *ሒጃብሽን ጥለሽ በአደባባይ ስትወጪ አንቺን በማየት ሊረኩ ፣ ስጋዊ ፍላጎታቸውን ሊያጣጥሙ ነው። ዳንስሽን ፣ ተሰጥኦሽን ፣ ቁመናሽን አውጪው አትደብቂው...እያሉ የሚጎታጉቱትም ለዚሁ ነው። ገላሽን ማቀራመት ይፈልጋሉ።ሴሰኞች ናቸው። በመሆኑም መስተንግዶ ላይ ካልሆንሽ ፣ ማስታወቂያ ቆመሽ ካላስነገርሽ አይጥማቸውም።*
ገላሽ በአደባባይ መታየቱ ለነሱ እርካታ... *ላንቺ ደሞ ውርደት መሆኑን እወቂ።* እየተሟገቱ ያሉት ለመብትሽ ሳይሆን ለመብታቸውና ለስሜታቸው መሆኑን እወቂ...ተረጂ...

👌የሚገርሙ ናቸው...የሴት ልጅን መብት እንኳን በአግባቡ ያወቁ አይመስሉም ።እውን የሴት ልጅ መብት እርቃን መውጣት ፣ ሸቀጥ ማስተዋወቅ ፣ ገበያ መውጣት ፣ አደባባይ መታየት ነውን?አይደለም ይህ ሁሉ አንቺን ማጃጃያ ነው።
ስለ ውብ ወጣት ሴቶች እንጂ ስለዕድሜ ስለገፉ አሮጊቶችና ባላቸው ስለሞተባቸው ሴቶች ሲያነሱ አናይም...ወይም ደግሞ ልጆች የእናቶቻቸውን መብት እንዲጠብቁ ሲጎተጉቱ አይታዩም።

የሚፈልጉት ጥፋትን ብቻ ናው። የሚከተሉትም ጭፍን ስሜታቸውን ነው። የሚኖሩትም ለራሳቸው ጥቅም ነው። የሚገርመው ደግሞ የማህበረሰቡ ዕድገትና ስልጣኔ በዚህ መልኩ እንዲፋጠን ይናገራሉ።
ይህ ምንግዜም የመናፊቃን ባህሪ ነው።እነርሱ የመናፍቃን ራስ የሆነው ዐብደላህ ኢብኑ ሰሉል የልጅ ልጆች ናቸው።እነርሱ እኮ ናቸው እናታችንን አኢሻን ረዲአላሁ አንሃ በዝሙት የቀጠፉት። ያኔም ምክንያታቸው ይኸው ነበር።

አላማችን ግብረገብነትን በማህበረሰቡ መካከል ማስፋፋት ነው ይላሉ።እውነቱ ግን የጥፋትና የውዥንብር ሃይል እንደነበሩ ነው። አለህ ያጠፋትን እሳት ለማንደድ የሚጥሩ ።ሴቶችን በመግዛት በዝሙት ስራ ያሰማሯቸው ፤ ገቢያቸውንም ይወስዱባቸው ነበር። አለህ በቁርአኑ ወህይ አውርዶ አጋለጣቸው።
የዘኑነ መናፍቃንም እንዲሁ ናቸው።የእስልምና ነገር አይዋጥላቸውም።ሒጃብን ይወብቅሻል ይላሉ።ኒቃብሽ እንደሚከብድሽ ይናገራሉ።ፊትን መሸፈን ትንፋሽ እንደምያሳጣ ይነግሩሻል። ሱሪ ለመራመድ ቀላል እና አመች ነው ይሉሻል።
  
መናፍቃን ሰውነታቸው እስልምና ውስጥ ቢኖርም ልባቸው ከሃድያኑ ጋ ነው።የሚማርካቸውም ሆነ የሚስባቸው የምዕራቡ ዓለም ሥልጣኔ ነው።ወደዝያ ለመድረስ ደሞ ሒጃብ ማውለቅን እንደመስፈርት ያቀርባሉ።
መሰልጠን ልብስን መጣል ነው ይላሉ። ሀገራቸው ሄዶ የጎበኛቸው የነርሱን ርካሽ ህይወትና ያሉበትን የሞራል ዝቅጠት በአጭር ግዜ ውስጥ መረዳት ይቻላል።
 
በአውሮፕላን ማረፍያ ጣብያዎች ውስጥ ሴት ልጅ ተላላኪ ሆና ስታገለግል ፣ የፅዳት ሰራተኛ ሆና ስትሰራ ፣ የሽንት ቤት ጠራጊ ሆና ስትተዳደር ትታዘባላችሁ።ቆንጆ ከሆነች ደግሞ ቦታዋ በርና ሄቴል ነው...ወንዶችን ለማማልለ።

አንደኛው ሰክሮ ይለፈድድባታል ፣ ሌላኛው ሰውነቷን ካልዳበስኩ ይላል።ሌላኛው የገቢ ምንጩ አድርጎ ይከራያታል። ሁሉም ጉዳያቸውን የጨረሱ እንደሆነ አያዝኑላትም። በጥፉ ብለዋት ነው የሚያባርሯት ሃጃቸው ከወጣላቸው "ምን ትጠብቅያለሽ ?" ይሏታል። ዕድሜዋ ሲገፋ ደሞ የአዛውንቶች መንከባከቢያ ቦታ አለ እዛ ወስደው ይወራውሯታል።እስር ቤት ይመስላል።ከመቃብር የሚተናነስ አይደለም።

 ልብ በይ እህቴ እነሱ የሚሉት ነፃነት ይህ ናው እንግዲህ። ወላሂ እኛ እዚህ ሆነን ፍሊፒንስ ስላለችው ሙስሊም ሴት እንታመማለን።ካሽሚር ለምትገኘው እህት እንቆስላለን...እነርሱ ሀገር ያለችው ሴት ግን አታሳስባቸውም። መጫወቻቸውና የሌሎች መጫወቻ ናት ሁሉም ወዲህና ወዲያ የሚቀባበላት። እንደ ሸንኮራ አገዳ ናት ሁሉም ከመጠጠ ቦሃላ የሚጥላት።
--------------------
mohammed ebnu seid
-----------------------------
🍀🍀🍀
በቴሌግራም ይ🀄️ላ🀄️ሉን!
➢👇👇👇

@Lewetatoch_mekir
@Lewetatoch_mekir

Читать полностью…

🌴ለወጣቶች ምክር🌴

. 人 ★* 。 • ˚* ˚
. (__ _)*ኢድ ሙባረክ*★
. ┃口┃ *ተቀበለሏሁ ሚና*
. ┃口┃★ *ወሚንኩም *˛•
. ┃口┃★ 。* •★ 。•˛˚˛*
. ┃口┃ •˛˚˛* 人 •˛˚ *
. ┃口┃ .-:'''"''''"''.-.
. ┃口┃ (_(_(_()_)_)_)


🛍አሰላሙ አለይኩም ወረህመቱላሂ ወበረካትሁ 🛍
ውድ የተከበራችሁ ለወጣቶች ምክር የቻናላችን ተከታዮች በሙሉ እንኳን #ለኢድ አል-ፊጥር በሰላም አደረሳችሁ 🛍🛍

🎁እንደዚሁም ለአብሮነት ኢስላሚክ ግሩፕ ተከታታይ በሙሉ እንኳን #ለኢድ አል-ፊጥር በሰላም አደረሳችሁ 🎁

🎈እንደዚሁም በጣም የምወዳችሁ ለሀገሬ ልጆች ወሎ ባቲ ለምትኖሩ እና እንደዚሁም በመላው አለም ለይ ለምትኖሩ ሙስሊም እህት እና ወንድሞች በሙሉ እንኳን #ለኢድ አል-ፊጥር በሰላም አደረሳችሁ 🎈

🌙በመጨረሻ ለመላው ኢስላምና ተከታይ እህት ወንድሞቼ እንኳን #ለኢድ አል-ፊጥር በሰላም አደረሳችሁ ማለት እፈልጋለሁ 🌙

🖊ወንድማችሁ mohammed ebnu seid ነኝ 🗞 @Dear_mahammi 🌹ከወሎ ባቲ🌹

Читать полностью…

🌴ለወጣቶች ምክር🌴

ዘካ የሚሰጠው ለምን አይነት ሰው ነው?
~~~
የዘካ ባለሐቆች 8 ናቸው። በቁርኣን እንዲህ ተዘርዝረዋል:–

(إِنَّمَا الصَّدَقَاتُ لِلْفُقَرَاءِ وَالْمَسَاكِينِ وَالْعَامِلِينَ عَلَيْهَا وَالْمُؤَلَّفَةِ قُلُوبُهُمْ وَفِي الرِّقَابِ وَالْغَارِمِينَ وَفِي سَبِيلِ اللَّهِ وَابْنِ السَّبِيلِ ۖ فَرِيضَةً مِنَ اللَّهِ ۗ وَاللَّهُ عَلِيمٌ حَكِيمٌ)

"ግዴታ ምጽዋቶች (የሚከፈሉት) ለድሆች፣ ለምስኪኖችም፣ በርሷም ላይ ለሚሰሩ ሰራተኞች፣ ልቦቻቸውም (በእስልምና) ለሚለማመዱ፣ ጫንቃዎችንም (በባርነት ተገዢዎችን) ነፃ በማውጣት፣ በባለ እዳዎችም፣ በአላህ መንገድም በሚሰሩ፣ በመንገደኛም ብቻ ነው፡፡ ከአላህ የተደነገገች ግዴታ ናት፡፡ አላህም አዋቂ ጥበበኛ ነው፡፡" [አተውባ: 60]

መጠነኛ ማብራሪያ

① ድሃ ማለት:– ለመኖር (ልብሱ፣ ጉርሱ፣ ትዳር ለመመስረት፣ ለመማር፣) ምንም ነገር የሌለው ወይም ትንሽ ነገር ያለው ማለት ነው። እነዚህን ፍላጎቶች ለማሟላት ዘካ ሊሰጠው ይችላል።

② ምስኪን ማለት: – ለመኖር የሚሆን ነገር በተወሰነ መጠን ያለው ሲሆን የሚበቃው ግን አይደለም።

③ ዘካ ላይ የሚሰሩ ሰራተኞች:– ዘካ እንዲሰበስቡ በመሪ የሚላኩ ሰዎች ናቸው። ዘካ ሶስት ነገሮችን ይፈልጋል። መሰብሰብ፣ መጠበቅና ማከፋፈል። በሶስቱም ዘርፍ ላይ የሚሰማሩ ሰራተኞች ሃብታም ቢሆኑ እንኳ ዘካ ይሰጣቸዋል።
ልብ በሉ! ለዚሁ ስራ በመንግስት የሚሾሙትን እንጂ የግለሰቦች ወኪሎችን አይመለከትም። ደሞዝተኛ ሰራተኛም እዚህ ውስጥ አይገባም።  

④ ልቦቻቸው (በእስልምና) የሚለማመዱ ማለት ሁለት አይነት ናቸው።

አንደኛ፡- ሙስሊም ያልሆነ ሰው ነው። ሙስሊም ባይሆንም ለተሻጋሪ ፋይዳ ሲባል ነው ሊሰጠው የተፈቀደው።
– ቢሰጠው ይሰልማል ወይም ሌላ ፋይዳ ይገኝበታል ተብሎ ተስፋ የሚጣልበት ከሆነ፣
– የሚያደርሰው ጉዳት ኖሮ በዚህ ማስቆም የሚቻል ከሆነ

ሁለተኛ፡- ሰለምቴ ነው።
– በዲኑ እንዲጠነክር ወይም ለሌላ ሰው መስለም/ መጠንከር ሰበብ ይሆናል ተብሎ ከተገመተ
– በሙስሊሞች ላይ ጉዳት የሚያደርስ ሆኖ በዚህ ማስቆም የሚቻል ከሆነ። [መጅሙዑል ፈታዋ፣ ኢብኑ ተይሚያ: 28/290]

⑤  እራሳቸውን ከአሳዳሪዎቻቸው በመግዛት ነፃ ለማውጣት የሚጣጣሩ ባሪያዎች ዘካ ከሚገባቸው ናቸው።

የተጠለፉ/ የተማረኩ ሙስሊሞችን ማስለቀቅም ከዚሁ ውስጥ ይካተታል።

⑥ ባለ እዳ:– የተጣሉ ሰዎችን ለማስታረቅ አስቦ እዳ የገባ ሰው ሃብታም እንኳን ቢሆን ዘካ ሊሰጠው ይችላል።
በራሱ ጉዳይ እዳ የተጫነው ከሆነ በኑሮው ባይቸገር እንኳ እዳውን ለመክፈል ሊሰጠው ይችላል።

⑦ በአላህ መንገድ የሚሰራ ማለት:– ለጂሃድ ዘማች ማለት ነው። ለትጥቅ፣ ለስንቅና አጠቃላይ ዝግጅት ዘካ ይሰጣል።

⑧ መንገደኛ:– አገሩ መግቢያ ከዘካ ገንዘብ ይሰጠዋል።
                  
--------------------
mohammed ebnu seid
-----------------------------
🍀🍀🍀
በቴሌግራም ይ🀄️ላ🀄️ሉን!
➢👇👇👇

@Lewetatoch_mekir
@Lewetatoch_mekir

Читать полностью…

🌴ለወጣቶች ምክር🌴

♨️አስፋሪዋ የጀሃነም እሳት ቃጠሎዋ የዱንያውን በ69 እጥፍ ይበልጣል። ቁርኣኑን አድምጡት🔊

የስራ ሚዛኖቻቸው የቀለሉባቸው ከሳሪዎች  ዘውታሪ የጀሃነም ቅጣት ምንኛ የከፋ እንደሆነ  አላህ ሱረህ አልሙዕሚኑን 104 እስከ 111: ገልፆልናል።

【104】تَلْفَحُ وُجُوهَهُمُ النَّارُ وَهُمْ فِيهَا كَالِحُونَ
ፊቶቻቸውን እሳት ትደበድባቸዋለች (ትገርፋቸዋለች) ።እነርሱም በውስጧ የተኮማተሩ ናቸው።

【105】أَلَمْ تَكُنْ آيَاتِي تُتْلَىٰ عَلَيْكُمْ فَكُنتُم بِهَا تُكَذِّبُونَ
በእናንተ ላይ አንቀፆቼ   የሚነበቡላችሁና የምታስተባብሉ አልበራችሁምን።

【106】قَالُوا رَبَّنَا غَلَبَتْ عَلَيْنَا شِقْوَتُنَا وَكُنَّا قَوْمًا ضَالِّينَ  
ይላሉ "ጌታችን ሆይ  መጥፎነታችን አሸነፈችን።ጠማሞችም ህዝቦች ነበርን።"

【107】رَبَّنَا أَخْرِجْنَا مِنْهَا فَإِنْ عُدْنَا فَإِنَّا ظَالِمُونَ
"ጌታችን ሆይ ከእርሷ (ጀሃነም) አውጣን። ወደ ጥመታችን ከተመለስን አኛው ነን በዳዮቹ።"

【108】قَالَ اخْسَئُوا فِيهَا وَلَا تُكَلِّمُونِ
አላህ አለ: በውስጧ ተዋርዳችሁ ኑሩ አታናግሩኝም።

【109】إِنَّهُ كَانَ فَرِيقٌ مِّنْ عِبَادِي يَقُولُونَ رَبَّنَا آمَنَّا فَاغْفِرْ لَنَا وَارْحَمْنَا وَأَنتَ خَيْرُ الرَّاحِمِينَ
እነሆ ከባሮቼ መካከል
" ጌታችን ሆይ አምነናልና ማረን እዘንልንም አንተም ከአዛኞች ሁሉ በላጩ አዛኝ ነህና"  የሚሉ አካላት ነበሩ።

【110】فَاتَّخَذْتُمُوهُمْ سِخْرِيًّا حَتَّىٰ أَنسَوْكُمْ ذِكْرِي وَكُنتُم مِّنْهُمْ تَضْحَكُونَ
መቀለጃ አድረጋችሁ ያዛቿቸው።
እኔንም ከማስታወስ እስከሚያስረሷችሁ ድረስ።በእነርሱም የምትስቁ ነበራችሁ።

【111】إِنِّي جَزَيْتُهُمُ الْيَوْمَ بِمَا صَبَرُوا أَنَّهُمْ هُمُ الْفَائِزُونَ
እኔ ዛሬ የመታገሳቸውን ዋጋ ከፈልኳቸው። ስኬታማ ማለት እነርሱ ናቸው።

ጥቆማ
👉የጠማሞችን ቅጣት የሚፈራ መንገዳቸውን ይጠንቀቅ።
👉የአማኞችን ስኬት የሚፈልግ መንገዳቸውን ይከተል።

🤲ጌታችን ሆይ አምነናልና ማረን እዘንልንም አንተም ከአዛኞች ሁሉ በላጩ አዛኝ ነህና🤲

--------------------
mohammed ebnu seid
-----------------------------
🍀🍀🍀
በቴሌግራም ይ🀄️ላ🀄️ሉን!
➢👇👇👇

@Lewetatoch_mekir
@Lewetatoch_mekir

Читать полностью…

🌴ለወጣቶች ምክር🌴

ይህን ታላቅ ወር ለመፆም አላህ አድሎህ እርሱ እንደሚፈልገው በአግባቡ ፆመህ አሳልፈው!!
———
አላህ (ተባረከወተዓላ) እንዲህ ብሏልና:-

فَمَن شَهِدَ مِنكُمُ الشَّهرَ فَليَصُمه
«ከእናንተም ወሩን ያገኘው ሰው ይፁመው» አል-በቀረህ 185

እናንተ ሙስሊሞች ሆይ! ከእናንተ ውስጥ ግዴታ የሆነውን የተከበረውን የረመዷን ወርን ለመፆም አላህ ያደረሰው በአግባቡ ይጠቀምበት። ጊዜውን ሀራም በሆኑና በተለያዩ ወሬና ዛዛታ ሊያቃጥለው አይገባም!። እያየን ነው ትላንት አብረውን የነበሩ ሰዎችን ዛሬ ሞቱ እየተባልን ነውና ቆም ብሎ ሊያስተውል ይገባል። በነሱ ሊማር ይገባል!። በረመዷን ወር ላይ መልካም ለመስራት ምን ያህል ጓግተውና ናፍቀው እንደነበረም እናስተውል።

በጫት፣ ኢስላማዊ የሚል ከንቱ ስያሜ በተለጠፈላቸው ፊልምና ድራማ፣ በነሺዳ፣ ጊዜያችሁን የምታባክኑ ሰዎችም አላህን ፍሩት!! መንዙማና ነሺዳን እንሰማለን ብላችሁ ወንጀል አትሸምቱ!! ይልቅ ቁርኣን መቅራት ባልተመቻችሁ ወቅቶች ቁርኣን ከፍታችሁ አድምጡ!! በዚህ ወር ላይ ስንትና ስንት መልካም ስራ ሊሰሩበት እየናፈቁ ትተው የሄዱና ያልታደሉ ሰዎችን አስታውሱ። እናንተ ለዚህ ትልቅ ፀጋ ስትታደሉ ሀራም በመስራትና ጊዜያችሁን በአጋጉል ነገር አታቃጥሉት!! በጊዜ መጠየቅ አለና ተገቢ ያልሆነን ነገር በመስራት ማሳለፋችሁን ትታችሁ፣ የቢድዓን ተግባራትንም ርቃችሁ፣ በቂርኣት በዚክርና በተለያዩ ሸሪዓ በደነገጋቸው የአምልኮ አይነቶች አሳልፉት!!።
✍🏻ኢብን ሽፋ (t.me/ibnshifa)

--------------------
mohammed ebnu seid
-----------------------------
🍀🍀🍀
በቴሌግራም ይ🀄️ላ🀄️ሉን!
➢👇👇👇

@Lewetatoch_mekir
@Lewetatoch_mekir

Читать полностью…

🌴ለወጣቶች ምክር🌴

​​ዛሬ የረመዳን ጨረቃ 🌙🌙እየተጠበቀ ነው ከታየ ነገ ረመዳን ይገባል ማታ ተራዊህ እንሰግዳለን። ካልታየ ሐሙስ አንድ ብለን እንጀምራለን ።
​​
ስለዚህ ተውበት አድርገን ውስጣችንና ላያችንን አፅድተን እንቀበለው።

አላህ እንዲህ ይላል:- "የአደም ልጆች ስራቸዉ ሁሉ ለራሳቸዉ ነዉ፤ፆም ብቻ ሲቀር👌 ፆም የእኔ ነዉ ምንዳዉንም የምከፍለዉ እኔ ነኝ" (ረሱል ሶለላሁ አለይሂ ወሰለም)

ረመዷን ተቃርቦ በአንድ እጅ የሚቆጠሩ ቀናቶች ቀርተዉታ .. ሰሞኑን በገባሁኝ ቁጥር online የይቅርታ መልዕክቶች በብዛት ገብተዉልኝ አገኛለሁኝ ።

ይቅርታ ብላችሁ ለላካችሁልኝ በሙሉ ለአላህ ስል ይቅር ብያችኋለሁኝ  🙏
እኔም የሰዉ ልጅ ተሳሳች ነዉ እና በተለያዩ ምክንያቶች ያስቀየምኳችሁ እህት ወንድሞቼ ይቅር እንድትሉኝ በአላህ ስም እጠይቃችኋለሁኝ 🙏

ወንድሙን ለአንድ አመት ያክል ያኮረፈ ሰዉ ልክ ደሙን ያፈሰሰበት ያክል ነዉ። ረሱል (ሶለላሁ አለይሂ ወሰለም) ይሄ ሀዲስ ሁሌም ያስፈራኛል እናም ሁላችንም በዚህ ታላቅ ወር ይቅር ልንባባል እና አላህን ደግሞ በአጠፋናዉ ወንጀል መሀሬታዉን ይንጠይቅ እና ልንማፀን ይገባል ። «አላህን ይቅርታ የጠየቀ እርሱ ይቅርታውን ይቀበለዋል»። ረሱል (ሶለላሁ ዓለይሂ ወሰለም)

So ይህንን ታላቅ  እና የእዝነት ወር  ሁላችንም አዉፍ እንባባል ። ካላናገረኝ አላናግርም !!
አዉፍ ካላለኝ አልልም !! ይህ የተበላበት ኋላቀር አስተሳሰብ ነዉና  እንርሳዉ።

ረመዳንን ፡- በኢባዳ / በቁርአን / በዱአ / በኢስቲግፋር / በተዉበት ፣ ከሚያሳልፉትና ሙሉ ምንዳዉን አጊኝተዉ ከሚያልፉ ባሮቹ ያድርገን አሚን 🤲

"ረመዳን መቶ ያልተጠቀመ ሰዉ አላህ ከእዝነቱ ያርቀዉ" (ረሱል ሶለላሁ አለይሂ ወሰለም) አላህ ከሚጠቀሙበት ያድርገን🤲

✍️ሁላችሁም ይህንን መልዕክት ለምታነቡ በሙሉ አዉፉ በሉኝ ።

--------------------
mohammed ebnu seid
-----------------------------
🍀🍀🍀
በቴሌግራም ይ🀄️ላ🀄️ሉን!
➢👇👇👇

@Lewetatoch_mekir
@Lewetatoch_mekir

Читать полностью…

🌴ለወጣቶች ምክር🌴

⇛ወደ አላህ ከመቃረብ ዉጭ  ደስታ እና እርካታ!! ይኖራል ብለህ መቼም እዳታስብ!!!
   ጌታችን አላህ እንዲህ ይለናል

الَّذِينَ آمَنُوا وَتَطْمَئِنُّ قُلُوبُهُمْ بِذِكْرِ اللَّهِ ۗ أَلَا بِذِكْرِ اللَّهِ تَطْمَئِنُّ الْقُلُوبُ

(እነሱም) እነዚያ ያመኑ ልቦቻቸውም አላህን በማውሳት የሚረኩ ናቸው፡፡ ንቁ! አላህን በማውሳት ልቦች ይረካሉ፡፡  
    
ሱረቱል ነጅም
--------------------
mohammed ebnu seid
-----------------------------
🍀🍀🍀
በቴሌግራም ይ🀄️ላ🀄️ሉን!
➢👇👇👇

@Lewetatoch_mekir
@Lewetatoch_mekir

Читать полностью…

🌴ለወጣቶች ምክር🌴

ጉቦ / ሙስና
~
በዚህ ዘመን ጉቦ በከፍተኛ ሁኔታ ተሰራጭቷል። በተለይ በመንግስታዊ ተቋማት ሰዎች በትክክለኛ መንገድ ሄደው ሐቃቸውን የሚያስከብሩበት መንገድ በጣም የጠበበ ሆኗል። እንደ ባንክ፣ ከፍተኛ የትምህርት ተቋማት፣ ... ባሉ ትልልቅ የግል ተቋማት ራሱ ቀላል የማይባል የጉቦ ጥፋት ይገኛል። እንዲያውም በብዙ ሴክተሮች ውስጥ ከጉዳይ አስፈፃሚ እስከ ሃላፊ የተዘረጋ ራሱን የቻለ የጉቦ መረብ አለ። የሚመጣውን የጉቦ ገንዘብ እንደ ስልጣን ተዋረዳቸውና እንደ ተሳትፏቸው ይከፋፈሉታል።
አንዳንድ ቦታዎች ላይ በጉዳይ አስፈፃሚዎች በኩል አድርጎ ሃላፊዎችና ሰራተኞች የሚከፋፈሉት ለጉቦ የሚወጣው ገንዘብ መጠን ለትክክለኛው ጉዳይ ከሚጠየቀው ክፍያ እጥፍ በላይ የራቀ ነው።
ጉቦ በኢስላም እጅግ የተኮነነ ቆሻሻ ተግባር ነው። ዐብዱላህ ብኑ ዐምር - ረዲየላሁ ዐንሁ - እንዲህ ይላሉ፦
لَعَنَ رَسُولُ اللَّهِ صَلَّى اللَّهُ عَلَيْهِ وَسَلَّمَ الرَّاشِيَ وَالْمُرْتَشِيَ
"የአላህ መልእክተኛ ﷺ ጉቦ ሰጭንም ጉቦ ተቀባይንም ተራግመዋል።" [አቡ ዳውድ፡ 3580] [ቲርሚዚይ፡ 1337]
ስለዚህ ጉቦ፡
* የአላህን ቁጣ የሚያስከትል፣ ከእዝነቱ የሚያርቅ ከባድ ወንጀል ነው።
* የዱዓእን ተቀባይነት ያሳጣል።
* የሰዎችን ሐቅ መጋፋት፣ በበደል ላይ መተባበር፣ የሰውን ልጅ ክብር ማርከስ አለበት።
* በጉቦ የተገኘ ገንዘብ ቆሻሻ ገንዘብ ነው። የሰዎችን ገንዘብ ያለ ሐቅ መብላት ነው።
* ጉቦ ደካሞች ሐቃቸውን የሚያገኙበትን መንገድ የሚያጠብ፣ ስግብግብ ሃብታሞች ሌሎችን እንዲገፉ መንገድ የሚጠርግ ጥፋት ነው።
* ጉቦ ፍትሃዊ የሃብት ክፍፍል እንዳይኖር፣ የሃገር ሃብት በጥቂቶች እንዲያዝ በማድረግ ኢኮኖሚን የሚያዛባ ደዌ ነው።
* ጉቦ ሰብአዊነትንና መተዛዘንን የሚያጠፋ፣ ጭካኔና ስግብግብነት የሚያስፋፋ እኩይ ተግባር ነው።
* ጉቦ በተንሰራፋበት ሃገር ውስጥ ፍትህ ከዜጎች በጣም ይርቃል። ሰላም ይጠፋል። ተጠያቂነት አይኖርም። ኢኮኖሚውም፣ ፖለቲካውም ይበለሻሻል። ሞራልና ግብረ ገብነት ምናልባት ካልጠፋ በእጅጉ ይቀጭጫል።
ስለዚህ የጉቦ ጥፋት ዳፋው ከግለሰቦች አልፎ ሃገርና ህዝብ ላይ ከባድ ተጽዕኖ አለው ማለት ነው። ከነዚህ ምድራዊ ቅጣቶች ባሻገር እንደ ሙስሊም ኣኺራዊ ቅጣት እንዳለውም ልናስታውስ ይገባል።

ከዚህ የጉቦ ውግዘት ተለይቶ የሚወጣው ሰዎች ሐቃቸውን ለማግኘት ህጋዊ አማራጭ በማጣታቸው የራሳቸውን ሐቅ ለማስከበር ሲሉ ብቻ የሚሰጡት ገንዘብ ነው። በርግጥ በየትኛውም ሁኔታ፣ ጉዳት ቢደርስ እንኳ ጉቦ ጋር መነካካትን የከለከሉ ዓሊሞች በተጨባጭ አሉ። ነገር ግን ፈፅሞ ከጉቦ ጋር አልነካካም ቢሉ አንዳንዴ ህይወትን የሚፈትን፣ ህልውናን አደጋ ላይ የሚጥል ችግር ሊገጥም ይችላል። ስለሆነም ሌሎችን ለመጉዳት ሳይሆን የራስን ሐቅ ለማስከበር ወይም ከራስ ላይ ጉዳትን ለመከላከል እስከሆነ ድረስ ገንዘብ መስጠት እንደሚቻል ከጥንት ጀምሮ በርከት ያሉ ዓሊሞች ገልፀዋል። ለምሳሌ ያክል ሶንዓኒንና ኢብኑ ተይሚያን መጥቀስ ይቻላል።

Ibnu Munewor

--------------------
mohammed ebnu seid
-----------------------------
🍀🍀🍀
በቴሌግራም ይ🀄️ላ🀄️ሉን!
➢👇👇👇

@Lewetatoch_mekir
@Lewetatoch_mekir

Читать полностью…

🌴ለወጣቶች ምክር🌴

. 人 ★* 。 • ˚* ˚
. (__ _)*ኢድ ሙባረክ*★
. ┃口┃ *ተቀበለሏሁ ሚና*
. ┃口┃★ *ወሚንኩም *˛•
. ┃口┃★ 。* •★ 。•˛˚˛*
. ┃口┃ •˛˚˛* 人 •˛˚ *
. ┃口┃ .-:'''"''''"''.-.
. ┃口┃ (_(_(_()_)_)_)


🛍አሰላሙ አለይኩም ወረህመቱላሂ ወበረካትሁ 🛍
ውድ የተከበራችሁ #ለወጣቶች ምክር የቻናላችን ተከታዮች በሙሉ እንኳን #ለኢድ አል-አደሃ #በሰላም አደረሳችሁ 🛍🛍

🎁እንደዚሁም #ለአብሮነት ኢስላሚክ ግሩፕ ተከታታይ በሙሉ እንኳን #ለኢድ አል-አደሃ በሰላም #አደረሳችሁ 🎁

🎈እንደዚሁም በጣም የምወዳችሁ #ለሀገሬ ልጆች ወሎ #ባቲ ለምትኖሩ እና እንደዚሁም በመላው አለም ለይ ለምትኖሩ ሙስሊም እህት እና ወንድሞች #በሙሉ እንኳን #ለኢድ አል-ፊጥር በሰላም አደረሳችሁ 🎈

🌙በመጨረሻ ለመላው #ኢስላምና ተከታይ እህት ወንድሞቼ እንኳን #ለኢድ አል-አደሃ በሰላም #አደረሳችሁ ማለት እፈልጋለሁ 🌙

🖊ወንድማችሁ mohammed ebnu seid ነኝ 🌹ከወሎ ባቲ🌹

Читать полностью…

🌴ለወጣቶች ምክር🌴

«🍃ዘምዘም ውኃ የመጠጣት
       አደብና ዱዓእ


▪️የዘምዘም ውኃ የተባረከ፣ ምድር ላይ ካሉ ውኃዎች ሁሉ የላቀና በላጩ፤ ለተራበ ሰው ምግብና ለታማሚ ፈውስ እንደሆነ ነቢዩ ﷺተናግረዋል።
አላህ ዘምዘምን ከቦታዎች ሁሉ መርጦ ከተከበረው ቤቱ (ከዕባህ) ዘንድ ማድረጉም የዘምዘምን ክብር ከሚያሳዩ ነገሮች መካከል አንዱ ነው።

▪️ዘምዘምን በጥሩ ኒያህ (መልካምን ነገር  አቅዶ) መጠጣት ተወዳጅ ተግባር ነው።ለምሳሌ ኢማንና የዲን ዕውቀትን፣ ጥሩና ደጋግ ልጆችን፣ ጤንነትን፣ ሰፊና ንጹሕ ሲሳይን ወዘተ ማግኘትን አቅዶና ነይቶ፣ እንዲሁም ዱዓእ አድርጎ መጠጣት ይገባል።
ታላቁ ሰሓቢይ ዐብዱሏህ ኢብኑ ዐባስ ዘምዘም ሲጠጡ የሚከተለውን ዱዓእ ያደርጉ እንደነበረ ዳረቁጥኒይና ሌሎችም ዘግበዋል፥
"اللهم إني أسألك عِلما نافعا ورزقا طيبا وشِفاءً مِن كلِ داء"
አላህ ሆይ ጠቃሚ ዕውቀትን፣ ሰፊ/መልካም ሲሳይን፣ ከበሽታዎች በሙሉ ፈውስን እጠይቅሃለሁ"::

ዘምዘም ሲጠጣ:-
▪️1/ቀድሞ ቢስሚላህ ማለት፣
▪️2/ቀድመው ሁለት ጊዜ ትንንሽ ፉት እያሉ በመቅመስ ሶስተኛው ላይ በደምብ ግጥም አድርጎ መጠጣት፣
▪️3/ ሲጠጡ በዛ አድርጎ (ጠግቦና ሆድን ሞልቶ) መጠጣት፣
▪️4/ጠጥተው እንደጨረሱ ከላይ የተገለጸውን ወይም ተመሳሳይና የግል ጉዳይን የሚገልጽ ዱዓእ ማድረግ ይመረጣል።
በርካታህ ሊቃውንት ሰሒሕ/ትክክለኛ ባሉት ሐዲሥ እንደተነገረው "ዘምዘም ውኃ ለተጠጣለት ዓላማ ይሆናል"። መካህ ሐረም ከሚገኘው ዘምዘም ውጪ ዓለም ላይ የትም ተመሳሳይ ትሩፋትና ጥቅም ያለው የተባረከ ውኃ የለም። ሊኖርም አይችልም።»

ኡስታዝ አሕመድ ሸይኽ ኣደም
@ ዛዱል-መዓድ

--------------------
mohammed ebnu seid
-----------------------------
🍀🍀🍀
በቴሌግራም ይ🀄️ላ🀄️ሉን!
➢👇👇👇

@Lewetatoch_mekir
@Lewetatoch_mekir

Читать полностью…

🌴ለወጣቶች ምክር🌴

እራቁት ሰዉ በዝቷል!

ባስተሳሰብ ዘቅጦ መለየት ተስኖን
ሰዉ ይሆን ይሄ ሰዉ እያለን ተገርመን
ስንት ቀን አለፈ ስንት ሌሊት ሸኘን፡፡
ስሙ ትልቅ ሆኖ ስራዉ ግን ይገርማል
ስንቱ ከላይ ለብሶ ዉስጥ ራቁት ሆኗል..
እሱን ቤት ይቁጠረዉ.…..….
በውድ የተገዛ ጨርቅ ነገር ለብሷል
ከላይ ደረብ አርጎ እዉነት ነዉ አጊጧል፡፡
ከለበሰዉ በላይ እርቃን ይታየኛል
እኔ በኔ እይታ እራቁት ሰዉ በዝቷል፡
ገንዘብ ብቻ ኖሮት ሙሉ የመሰለ
ከላይ ለስም ለብሶ ስንት እራቁት አለ፡፡

--------------------
mohammed ebnu seid
-----------------------------
🍀🍀🍀
በቴሌግራም ይ🀄️ላ🀄️ሉን!
➢👇👇👇

@Lewetatoch_mekir
@Lewetatoch_mekir

Читать полностью…

🌴ለወጣቶች ምክር🌴

🤲 ያ አላህ ........☝️ ሙስሊሞችን አዛውንቶች ሳይቀሩ ያለ ርህራሄ ያሳደዱ፣ ያንገላቱ፣ የደበደቡ፣ የገደሉ የሆኑ ግፈኛ አረመኔዎችን ከነአዛዦቻቸው በዕውቀትህና በችሎታህ ቁጠራቸው፤ እንደገደሉንም ተራ በተራ ለያይተህ ግደላቸው፤ አንድኛቸውንም እንኳ እንዳታስቀር።

🤲 ያ አላህ ለሌሎች አምባገነኖች መመከሪያና የጠላት መሳቂያ አድርጋቸው።

🤲 ያ አላህ! በገዳዮቻችን ላይ አስደናቂ የሆነ ተዓምራትህን ሳይውል ሳያድር አሳየን።

🤲 አላህ ሆይ! በጠላቶቻችን ላይ ልዩ በሆነው እርዳታህ እርዳን፤ ልባችንንም አሽርልን፤ ልጇን ወይም ባሏን የተነጠቀች እናትንም አንተው አፅናናልን፤ የአልጋ ቁራኛ የሆኑ ቁስለኞችንም ፈውሳቸው።

🤲  ያ አላህ! እንባችንን አንተው እበስልን፤ ጠላቶቻችን ይህ አይነቱን በደል ዳግም እንዳይፈፅሙብንም ነገሮችን አታመቻችላቸው።

🤲 ሁሉንም ነገር ለማድረግ ቻይ የሆንከው ጌታችን ሆይ! አንባገነኖች ላይ ፈጣን የሆነ የበቀል መቅሰፍትህን አውርድባቸው።

ኣሚን ኣሚን ኣሚን

--------------------
mohammed ebnu seid
-----------------------------
🍀🍀🍀
በቴሌግራም ይ🀄️ላ🀄️ሉን!
➢👇👇👇

@Lewetatoch_mekir
@Lewetatoch_mekir

Читать полностью…

🌴ለወጣቶች ምክር🌴

ወዳጄ ሆይ መቆም ከፈለክ ሌሎችን አትጣል ‼️

💡የምትሔድበት የስኬት መንገድ ሺህ ጊዜ ይርዘም እንጂ ቶሎ ለመድረስ ብለህ አቋራጭ መንገድ አትጠቀም። ልብህ በእውነት ላይ ተረማምደው በሰዎች ትከሻ ላይ ተንጠልጥለው ፣ በአቋራጭ ባደጉ ሰዎች እንዳይቀና ! የግፍንም እንጀራ እንዳትበላ ተጠንቀቅ ፣ትግስትን ገንዘብህ አድርጋት አላል ለአንተ ያዘጋጀዉ ነገር አለውና። በዕውነት ፣ በሃቅና በራስ አገዝ አዋጭ መንገድ ከተራማድክ እመነኝ በያንዳንዱ እርምጃህ ስኬትህን እየገነባህ ነው።

ሀሴትህ በቀናነትህ መጨምር ይበዛል፣ ከክፋት ትርፍ አይሰበሰብም፡፡ የምትሆነው ብታጣ እንኳ ጨካኝነትን ብቸኛው ምርጫህ አታድርግ፡፡ የሚመረጥ ስላጣህም የማይመረጥ አትምረጥ ፣ የምትመርጠው ከሌለ አለመምረጥም ጥሩ ምርጫ ነው፡፡ ማስተዋልህን ባለማስተዋል አትጠቀምበት፡፡

ወዳጄ ሆይ ......!!

ከብረህ ሳለም ቀለህ መኖርን አትውደድ፡፡ በከፍታ እንጂ በዝቅታ እያሰቡ መኖር አይመጥንህም ጭካኔ የሕሊና ሰላምህን ያቀነጭራል፡፡ የውስጥህንም ሰላም ያመክናል፡፡ጊዜአዊ እንጂ ዘላለማዊ የዚህች ምድር ነዋሪ አይደለህምና በደጉ ጊዜህ መሰልህን አትበድል፡፡

📍ነገ የአንተ ዕጣ ፈንታ ምን እንደሚሆን በውል አታውቅምና ነግ በእኔ ማለትን እወቅ፡፡ በቁንጮነት ዘመንህ የፍጡራንን መብት አትግፈፍ፡፡ የሌላው ውድቀት የአንተን መቆም አያረጋግጥምና ፣ መከራ በታጨቀባት በዚህች ጠፊ ዓለም መልካምነትን የመሰለ ሰላም ሰጪ ተግባር የለም፡፡ በመሆኑም ዛሬህ ላይ ነገ የማትፀፀትበትን ምግባር አብዛ፡፡

ነፃ የሆነ ነፃነት እንዲሰማህ ፤ በጭንቀት የታጨቀ ኑሮህን በቅንነት ቀይር፡፡ ከሁካታ እርካታ አይመነጭም እፎይታ ለሚሰጡህ ተግባሮች ራስህን ስጥ፡፡

         ውብ ምሽት❤️

--------------------
mohammed ebnu seid
-----------------------------
🍀🍀🍀
በቴሌግራም ይ🀄️ላ🀄️ሉን!
➢👇👇👇

@Lewetatoch_mekir
@Lewetatoch_mekir

Читать полностью…

🌴ለወጣቶች ምክር🌴

መስጂድ ፈርሶ የሚመሰረት ከተማ አይኖርም!

Читать полностью…

🌴ለወጣቶች ምክር🌴

እናንተ የአላህ ባሮች!
ዱንያ እንዲህ ናት! -

የመተላለፊያው አገር እንጂ ዘላለማዊ ቤት አይደለችም። ጅማሮዋ ችግርና መከራ ናት ፣ ፍፃሜዋም ጥፋት፣ ሐላሏ ሒሳብ አለበት ፣ ሀራምዋም ቅጣት ነው ። በርሷ የተብቃቃ ፈተና ይፈተናል። ድሀ ለሆነ ሰው የሀዘን ምንጭ ናት።
እርሷ ወላሂ! ወቢላሂ! ወተላሂ! ከመቀነስ በቀር ለማንንም አትሞላም፣ ለማንም ሰፊ አትሆንም… ጥበትን እንጂ አላስተናገደችም፣ ከማሳዘን በቀር ማንንም አታስደሰትም፣ ከማልቀስ በቀር እምብዛም አታስቅም፣ ምንም ያህል ትልቅ ብትሆን ትንሽ ናት! ምንም ያህል ረጅም ብትሆን አጭር ነች።

ዱንያ ማለት አላህ በቁርኣኑ እንደገለፃት ናት!
“ቅርቢቱ ሕይወት ጨዋታና ዛዛታ፣ ማጌጫም፣ በመካከላችሁም መፎካከሪያ፣ በገንዘቦችና በልጆችም ብዛት መፎካከሪያ ብቻ መሆንዋን እወቁ፡፡” (አልሀዲድ:20)
ታዲያ እናንተ የአላህ ባሮች ሆይ! አስተውሉ!ምንም ያህል ጌጥ ፣ ጉራ እና በንብረት ብዛት ፉክክር ቢቀድማት  ዞሮ ዞሮ ማሳረጊያዋ ወደ  ቢጫነት(መጠውለግ) እና ፍርስራሽ ነው።  ነብያችን - የአላህ ሰላትና ሰላም በእሳቸው ላይ ይሁንና - ስለ እሷ እንደተናገሩት ።
"ዱንያ በትንኝ ክንፍ ከአላህ ጋር ብትስተካከል ኖሮ ለካፊር ከእርሷ  አንድ ጉንጭ ውሃ ባላጠጣው ነበር"
(ቲርሚዚ ዘግበውታል)

ከሸይኽ ስዑድ ሹረም ኹጥባ የተወሰደ

--------------------
mohammed ebnu seid
-----------------------------
🍀🍀🍀
በቴሌግራም ይ🀄️ላ🀄️ሉን!
➢👇👇👇

@Lewetatoch_mekir
@Lewetatoch_mekir

Читать полностью…

🌴ለወጣቶች ምክር🌴

አላህ ዘንድ የቀለለ ሰው የሰዎች ውዳሴ አይጠቅመውም
~
በሰው እጅ እሳትም ሆነ ጀነት የለም። ስለሆነም የሰዎች ጭብጨባና አድናቆት ግብ ሊሆን አይገባም። አላህ ከፍ ያደረገውን የምቀኞች ክፋት አያወርደውም። አላህ ዝቅ ያደረገውን ጭብጨባና ከንቱ ውዳሴ አይሰቅለውም። ስለሆነም የሰዎች ውግዘት ጭንቀትህ፣ ውዳሴያቸው ደግሞ መሻትህ አይሁን። ይልቁንም ለትእዛዙ በማደር ጌታህ ዘንድ ከፍ ለማለት ጣር። ኢማሙል አውዛዒይ - ረሒመሁላህ - እንዲህ ይላሉ፦
ﺇﻥّ من الناس مَن يُحِبُّ الثّناء عليه، ﻭﻣﺎ يُساوي عند الله جناح بعوضة
"ከሰዎች ውስጥ መወደስን የሚወድ አለ። አላህ ዘንድ ግን የትንኝ ክንፍ አያክልም።" [ሒልየቱል አውሊያእ፡ 8/255]

#ከደጋጎቹ_ቀዬ

--------------------
mohammed ebnu seid
-----------------------------
🍀🍀🍀
በቴሌግራም ይ🀄️ላ🀄️ሉን!
➢👇👇👇

@Lewetatoch_mekir
@Lewetatoch_mekir

Читать полностью…

🌴ለወጣቶች ምክር🌴

የዛሬዋን ለሊት  እንደቀልድ  ልናሳልፋት አይገባም ‼️

ከወሬ ከአሉ ባልታ ርቀን ፣ ይቺን ሌሊት በኢባዳ  ልናሳልፋት ይገባል ።  ምናልባትም  ቀጣይ  ረመዳን  ስለመድረሳችን ምንም ዋስትና የለንም !! የመጨረሻችን ሊሆን  ይችላል ።

እሄ የተከበረ ወር ፣ ያስጠቀመውን አስጠቅሞ  ሊያልቅ  ቀናቶች ቀርተውታል ።
በዝችው ባለችን ሰአት ስራችንን እናሳምር 
🤲አላህ  እኛንም  እናንተንም   ከመልካም ባሪያወቹ ያድርገን  🤲 ዱአችንንም  ሙስተጃብ  ያድርግልን  ።

ተበራቱ  በዱአ በቂረአት  በዚክር

--------------------
mohammed ebnu seid
-----------------------------
🍀🍀🍀
በቴሌግራም ይ🀄️ላ🀄️ሉን!
➢👇👇👇

@Lewetatoch_mekir
@Lewetatoch_mekir

Читать полностью…

🌴ለወጣቶች ምክር🌴

#ውዶቼ_ዱዓችሁ_በጣም_ያፈልገኛል_ወላሂ 💔

ሰከንዶች ወስዳችሁ ከልባችሁ ዱዓ አድርጉልኝ 🤲
ትልቅ ትንሽ ብዬ የምንቀውና የማበላልጠው ሰው የለም !
የምርም ይሄንን ያነበበ ሰው ሁሉ ዱዓ ያደርግልኛል ብዬ በማሰብ ነው የለጠፍኩት ።

Читать полностью…

🌴ለወጣቶች ምክር🌴

•••••••••፨🌺አፍጡር ላይ የሚባል ዱዓ🌺፨••••••••••



ذَهَبَ الظَّمَأُ وَابْتَلَّتِ الْعُرُوْقُ وَثَبَتَ اْلأَجْرُ إِنْ شَاءَ اللهُ.

••••••••••••••፨🌺ትርጉም፨🌺••••••••••••••
ጥማችን ተቆርጧል፡፡ የደም ሥሮቻችን ረጥበቃል፡፡ የአላህ ፈቃድ ከሆነ ምንዳም ተረጋግጦልናል፡፡ ’

اَللَّهُمَّ إِنِّيْ أَسْأَلُكَ بِرَحْمَتِكَ الَّتِيْ وَسِعَتْ كُلَّ شَيْءٍ أَنْ تَغْفِرَ لِيْ.
••••••••••••••••፨🌺ትርጉም፨🌺•••••••••••

አላህ ሆይ! ምህረትን ትለግሰኝ ዘንድ ሁሉንም ነገር ባዳረሰችው እዝነትህ እማፀንሐለሁ፡፡’

--------------------
mohammed ebnu seid
-----------------------------
🍀🍀🍀
በቴሌግራም ይ🀄️ላ🀄️ሉን!
➢👇👇👇

@Lewetatoch_mekir
@Lewetatoch_mekir

Читать полностью…

🌴ለወጣቶች ምክር🌴

ረመዳን ሙባረክ ። እንኳን ለ1444 ዓመተ ሂጅራ የተከበረው ረመዷን ወር በሰላም አደረሰን ። ወሩ የምህረት እና አላህ ከእሳት ነፃ ከሚላቸው ባሮቹ ተርታ የምንመደብበት የአፊያና የሰላም ወር አላህ ያድርግልን።

--------------------
mohammed ebnu seid
-----------------------------
🍀🍀🍀
በቴሌግራም ይ🀄️ላ🀄️ሉን!
➢👇👇👇

@Lewetatoch_mekir
@Lewetatoch_mekir

Читать полностью…

🌴ለወጣቶች ምክር🌴

የሚስት ዘመዶች ፊት ሰለ ስሜት፣ ሰለ ወሲባዊ ነገሮች ማውራት አደብ አይደለም!። በተለይ ሰለ ልጃቸው ከሆነ ብልግናም ጭምር ነው። ዓሊይ ኢብን አቢ'ጧሊብ የረሱልን ልጅ "ፋጢማን" ሰላገባዋት ረሱልን ሰለመዚይ መጠየቅ ፈርቼ "ሚቅዳድ ኢብኑ ዐምርን" እንዲጠይቅልኝ ላኩት ይላል።

ኢብኑ ዑሰይሚን፦ ከዚህ ሐዲስ ከምንይዛቸው ጥቅሞች ውሥጥ ብለው በሶስተኛ ደረጃነት ያስቀመጡት፦
أن من الأدب أن لايذكر الرجل عند أقارب زوجته مايتعلق بالفروج والشهوة.
አንድ ሰው: የሚስቱ ቅርብ ዘመዶች ዘንድ ስለብልትና ከስሜት ጋር ተያያዥ ነገራቶችን አለማውራቱ ከአድብ ነው!።
[ተቢሁል አፍሃም,ቢሸርሒ ዑምደቲል አህካም 81]

--------------------
mohammed ebnu seid
-----------------------------
🍀🍀🍀
በቴሌግራም ይ🀄️ላ🀄️ሉን!
➢👇👇👇

@Lewetatoch_mekir
@Lewetatoch_mekir

Читать полностью…

🌴ለወጣቶች ምክር🌴

🥀:::::ትዳር::::::🌹

በሸይኽ ኢብኑ ዑሰይሚን አንደበት
[አላህ ይዘንላቸው]
      

«አንድ ባል ሚስቱን በጥሩ አያያዝ ተኗኗራት የሚባለው ከሷ ጋር በአንድ ፍራሽ ላይ አንድ ለሃፍ [ኮምፎርት፣ ብርድ ልብስና የመሳሰሉትን የመኝታ ልብስ በጋራ ] ለብሶ መተኛቱ ነው።

   ምክንያቱም የመልእክተኛው [ሰለላሁ ዐለይሂ ወሰለም] ፈለግ ይኸ ነበርና።

  ነገር ግን እነዚያ ባሎቹም ለብቻቸው፣  ሚስቶችም ለየብቻቸው የሚተኙ ሰዎች፤ አንዳንዴም ከዚህ በከፋ ሁኔታ እሱ በተለየ ክፍል እሷም በተለየ ክፍል የሚተኙ (የሚያድሩ) ከሆነ ያለምንም ጥርጥር ይኸ ከትዳር ጓደኛ ጋር በመጥፎ ሁኔታ መኗኗር " سوء المعاشرة" ይባላል።»

[ይኸ ደግሞ አላህ ያዘዘንን በመልካም ሁኔታ የመኗኗር ኑዛዜን ይጥሳል።]

  አላህም እንዲህ ብሏልኮ☞

”هُنَّ لِبَاسٌ لَّكُمْ وَأَنتُمْ لِبَاسٌ لَّهُنَّ“
«እነርሱ ለናንተ ልብሶች ናቸው፤ እናንተም ለነርሱ ልብሶች ናችሁ፡፡»

✍አልበቀራህ☞187 : البقرة 
--------------------
mohammed ebnu seid
-----------------------------
🍀🍀🍀
በቴሌግራም ይ🀄️ላ🀄️ሉን!
➢👇👇👇

@Lewetatoch_mekir
@Lewetatoch_mekir

Читать полностью…
Subscribe to a channel