liulzemaryam | Unsorted

Telegram-канал liulzemaryam - ከጥበብ እልፍኝ

-

በዚህ ቻናል አስደሳች ግጥሞች፦በድምፅ በፅሁፍ አስተማሪ ታሪኮች ትረካዎች ወግ እና ሌሎች የጥበብ ስራዎች ያገኙበታል። . . ምኞት አይከለከልም ያሉትን ሰምቼ ሞቴን ተመኘውት መኖሬን ጠልቼ #💚💛❤ @jape16

Subscribe to a channel

ከጥበብ እልፍኝ

አንቺን ሚያስጨንቅሽ ፣ የኔ ፎቶ ማብዛት
እኔ ምጨነቀው
ካሜራዬን ሽጬ ፣ ጠብመንጃ ለመግዛት😂
።።።
አንቺን የሚገርምሽ ፣ የኔ ግምባር መውጣት
እኔን የሚገርመኝ
ሊጥ ለመስረቅ ታግሎ ፣ የሚሞት እልፍ ወጣት😂
።።።
አንቺ የምትዪኝ
ያንተ አዲስ አበባ ፣ ከእጄ ላይ ወድቋል
እጅህን ቶሎ ስጥ ፣ ጦርነቱ አልቋል
እኔ የምነግርሽ
እጅሽን አልሻም ፣ በሊጥ ተጨማልቋል
ሸገር ስትናፍቅሽ ፣ መቀሌሽ ርቋል 😂
።።።።
ባፍሽ የምትነግሪኝ
ሁሉንም ሀይማኖት ፣ እንደምትወጂ
በተግባር የማይሽ
መስጅድ ቤተስኪያን ውስጥ ፣ ነው ስትፀዳጂ።
።።።
አንቺ ምትነግሪኝ
ጌታ ፈጣሪሽን ፣ እንደምትፈሪ
እኔ ግን የማውቅሽ
መኖክሴ አይቀርሽም ፣ በቡድን ስትደፍሪ
።።
ታዲያ እኔና አንቺ ፣በምን እንግባባ
ያንቺ ናፍቆት መሳቅ ፣ የኔ እውነት እምባ
እኔ ምልሽ ዘራፍ ፣ የምትይኝ እምበር
ትግልሽ እኔን ማፍረስ ፣ ትግሌ አንቺን ለመቅበር
የኔ ተስፋ አንድነት ፣ያንቺ ተስፋ አንድ ቀን
ቋንቋ እንዴት ያግባባን ፣ ኑሮ እያራራቀን?!😂



➤ከወደዱት በቅንነት ይቀላቀሉን!
👇👇👇👇👇👇
@liulzemaryam
@liulzemaryam
@liulzemaryam
☝☝☝☝☝☝☝

Читать полностью…

ከጥበብ እልፍኝ

🇪🇹🇪🇹ትንሳኤሽ ናፍቆናል🇪🇹🇪🇹

✍ልዑል


✅ድንቅ ሀገራዊ ግጥም ነው ተጋበዙልኝ🇪🇹🇪🇹🇪🇹



➤ከወደዱት በቅንነት ይቀላቀሉን!
👇👇👇👇👇👇
@liulzemaryam
@liulzemaryam
@liulzemaryam
☝☝☝☝☝☝☝

Читать полностью…

ከጥበብ እልፍኝ

✅ነጽር🙏

✍ልዑል


😭😭ፈጣሪ አምላክ የጦብያን መከራ በቃ ብሎ ይታረቃት😭😭


#Reposte

➤ከወደዱት በቅንነት ይቀላቀሉን!
👇👇👇👇👇👇
@liulzemaryam
@liulzemaryam
@liulzemaryam
☝☝☝☝☝☝☝

Читать полностью…

ከጥበብ እልፍኝ

✅ነጽር(ተመልከት)🙏

✍ልዑል

ልክ እንደ ዛፍ ፍሬ ነፍስ እየረገፈ
እህልና እንስሳ እየተረፈረፈ
አድባሬው በሞላ ሬሳ ታቀፈ።

እናቶች አነቡ
ህፃናት ተራቡ
ምድርህ ረሰረሰች
በደም አየታጠበች።

ሰሜኑ ታጠነ በባሩዱ ሽታ
ቦረና ተራበ በጥም ተንገላታ
ወለጋ ረገፈ የሰው ዘር በጅምላ
ሬሳም ቀባሪ አጣ በአውሬ አየተበላ።

ነፍሰጡር እናቶች በግፍ ተገደሉ
ጨቅላ ህፃናቶች በእሳት ተቃጠሉ
ረገፉ እንደ ቅጠል በእርሃብ ጠኔ
አልባሽ አጉራሽ አቶ አለቀ ወገኔ።

በበቀል ሴስነው ፀብን ያረገዙ
የጥልን ጦር ታጥቀው ክፋት እየነዙ
የጦቢያን መከራ ስቃዮን አበዙ

አቤቱ🙏

ታዲያ እስከ መቼ ግራህን ትሰጠን?
ታዲያ እስከ መቼ ፊትህን ትነፍገን?
እስከመቼ ታዲያ ሬሳ ታቅፈን?
በረሃብ ቸነፈር በጥም እናልቃለን?

መንሹ በእጅህ ነው ሁሉን ልታጠራ
ነጽር(ተመልከት) አቤቱ ታደገን ሀደራ!



➤ከወደዱት በቅንነት ይቀላቀሉን!
👇👇👇👇👇👇
@liulzemaryam
@liulzemaryam
@liulzemaryam
☝☝☝☝☝☝☝

Читать полностью…

ከጥበብ እልፍኝ

ይድረስ ..ለማይደርስልን መንግስት


በላይ በቀለ ወያ

እንደምነህ መንግስት ፥ እኛ አለን በደህና
ባመቻቸህልን ፥ የለውጥ ጎዳና
ሺዎችን ገብረን ፣ ለአንድ ብልፅግና
ከሶስት አመት በላይ
እየተሰበርን ፣ " ሰበር" በሚል ዜና
ተራ እየጠበቅን ፣ ለሞት ተሰልፈን
ግፍኛን ተቃውመን ፣ ግፈኛን ደግፈን
ደብዳቤ እየላክን ፣ በደማችን ፅፈን
እኛ አለን በስጋት ፣ እኛ አለን በተድላ
በቀን ሶስት ግዜ
ቁርስ ምሳና ራት ፣ መከራ ስንበላ
አንተ ግን እንዴት ነህ?
እንደምነህልን ፣ ካልንህስ በኋላ?!
እኛ አለን በድሎት
እኛ አለን በፀሎት
ከገዳያችን ጋር ፣ ቀብር ስናስፈጥም
ስንኖር ኢትዮጵያዊ
ስንሞት ምን እንደሆንን ፣ ባናረጋግጥም
እኛ አለን በተአምር ፣ እኛ አለን በደህና
እየተገደልን
"ስልታዊ ማፈግፈግ" ፣ በሚል ፍልስፍና
አንተ ግን እንዴት ነህ?
እልፎች ሚቃወሙህ ፣ እልፎች ሚደግፉህ
እልፎች ሚያወድሱህ ፣ እልፎች የሚነቅፉህ
እንዴት ነው መንግስትህ
ከአዲስ ምእራፍ ጋር ፣ የተመሰረተው?
አንድ አንተን ለማፅናት ፣ ስንቶች ነን ምንሞተው?



➤ከወደዱት በቅንነት ይቀላቀሉን!
👇👇👇👇👇👇
@liulzemaryam
@liulzemaryam
@liulzemaryam
☝☝☝☝☝☝☝

Читать полностью…

ከጥበብ እልፍኝ

-በሞቷ ፊት ለፊት-

በቀደም ደወለች
አወጋች አወጋሁ
በስተመጨረሻ
ደና ሰንብች ብዬ የስልኬን አፍ ዘጋሁ፤

ከዚያ ቀናት አልፈው
ወራት እንደቅጠል እግሬ ስር ረግፈው
ልጅ ሆና የማውቃት እናቷን አከለች
ዘጠኝ ወር አርግዛ ሞት ተገላገለች፤

ምን አሽዋ ቢያልቡ
ነፋስ ቢጋልቡ
ደመናውን ጠርበው ሐውልት ቢያስገነቡ
ሞትና ክስመት ነው የተፈጥሮ ግቡ
ብዬ እንዳልፅናና
በሞቷ ፊት ለፊት ሀሳብ ሁሉ መና
ምክር ሁሉ ኦና
እንባን አይገድብም የሰው ፍልስፍና።

[ በእውቀቱ ስዩም ]

[ ይህ ግጥም ለመውለድ ወደ አንቡላንስ ገብተው በቃሬዛ ለሚወጡ የሀገሬ እናቶች መታሰቢያ ይሁንልኝ ]


➤ከወደዱት በቅንነት ይቀላቀሉን!
👇👇👇👇👇👇
@liulzemaryam
@liulzemaryam
@liulzemaryam
☝☝☝☝☝☝☝

Читать полностью…

ከጥበብ እልፍኝ

▻ፍካሬ ፍያታዊ ዘየማን

.
በእርግጥ!
እውራኑን ስታበራ ፣ ሽባውን ስትተረትር
ሙታንን ስታስነሳ ፣ ዲዳውን ስታናግር
አይቼህ ነበረ ባይኔ
ሆኖም አላምንህም!
የሀስማተኞች እንጂ ፣
ያምላክ መገለጫው ፣ ይህ አይደለም ለኔ፡፡
።።።፣፣።።።፣።።።።።።።።።፣፣፣፣።።።።።።።
በእርግጥ!
ነፋሳትን ስታዛቸው ፣ በባህር ላይ ስትራመድ
ከጭንጫ ውሃ ስታፈልቅ ፣ መና ከሰማይ ስታወርድ
አይቼህ ነበረ ባይኔ
ሆኖም አላምንህም!
የሀስማተኞች እንጂ ፣
ያምላክ መገለጫው ፣ ይህ አይደለም ለኔ፡፡
።።።።።።፣፣፣፣፣፣።።።።፣፣፣፣፣።።።።።።።።
አንተ አምላክ ነኝ ባይ
አይሁድ በጨርቅህ ላይ ፣ እጣ ሚጣጣሉ
ከቀኝህ ሰቅለውኝ...
መስቀልህን ባየው ፣
ከመስቀልህ ዘንዳ ፣ ቁማርተኞች አሉ፡፡
ለካስ እስከዛሬ...
የካብከውን ስንድ ፣ በመላ ዘመኔ
ባንተ ላይ ቆማሪ...
ወንበዴ ነኝና ፣ ሽፍታ አረመኔ
ዳግመኛ ስትመጣ...
በመንግስትህ አስበኝ"
ያምላክ መገለጫው ፣ ምህረት ነው ለኔ!!!



➤ከወደዱት በቅንነት ይቀላቀሉን!
👇👇👇👇👇👇
@liulzemaryam
@liulzemaryam
@liulzemaryam
☝☝☝☝☝☝☝

Читать полностью…

ከጥበብ እልፍኝ

✅ይቅር በይኝና ልጅሽ ይታረቀኝ



ሰማይ ሆኖ ሆድሽ
አድማስ ሆኖ ክንድሽ
ታቅፈሸው አየሁ የሰራኝን ጌታ
የት ነው የኔ ቦታ?
በሆድሽ የያዝሽው
ፍቅር ነው
ደግ ነው
ምህረት ነውና
ዓይንሽ ለማየት እኔ ማን ነኝና፡፡
አዛኝቱ ሆይ
ወለላይቱ ሆይ
ማር እንደሚጣፍጥ አያሻኝም መቅመስ
ስጋ በልቻለሁ ካንቺ ቤተ-መቅደስ::
* ወዮ ትንቂኝ ይሆን
ወዮ ትርቂኝ ይሆን
ምን በስጋ ብረክስ ምን ዳግም ብበድል
በማርያም ጣቴ ነው ጥልን የምገድል፡፡
ስምሽን ስናገር ከነውሬ ብዛት ምላሴ ኮልታፋ
ይቅር በይኝና ይብቃኝ ላንቀላፋ፡፡
እማዬ አዘንኩኝ
እናቴ ወድቅኩኝ
ብቻዬን አይደለም ስንት ሰው ገደለኩኝ፡፡
ነፍሰ በላው እኔ  ብዙ ያሳዘንኩሽ
ልክ እንደናቴ እጅ ተኝተሽ በሳምኩሽ
እንደናቴ ዓይን ሰርቄ ባየሁሽ፡፡
ምን ትመስይ ይሆን?
ምን እያልሽኝ ይሆን?
እንደልጀነቴ እንደትዝታዬ
እንደዳቤ ቁራሽ እንደፍልሰታዬ
ምነው በቀረሁኝ ከእቅፍሽ እማማ
ስምሽን ልጥራ እንጂ የት አለሁ እኔማ፡፡
ካንቺ ጋር ጠፍቼ
እብሰለሰላለሁ ከራሴ ጠፍቼ
እንገበገባለሁ  ራሴን ሰምቼ
ትነግሳለች ሲሉኝ
የለሁም ከእቅፏ ለሌላ ዘምቼ፡፡
ችግሬን ብቻ ሳይ መልክሽ ይጠፋኛል
መልክሽን  ብቻ ሳይ ችግር ይረሳኛል፡፡
ለውርደት አታርጊብኝ አታርጊብኝ ለውርደት
ከሲኦል ያቃጥላልና የክፉ ሰው አንደበት፡፡
* "ኦ ወዮ ትንቂኝ ይሆን
    ኦ ወዮ ትርቂኝ ይሆን
    ዘማዊ ሆኜ አሳዝኜሽ ይሆን"
እንዳለ ጸሎቱ
እኔም እልሻለሁ
ነውር ቁመት ካለው
ልኬ ነው አውቃለሁ፡፡
በደል ገጽ ካለው
ገጼ ነው አውቃለሁ፡፡
ኃጢያት ቁጥር ካለው
እኔ ነኝ አውቃለሁ፡፡

*     *      *      *      *       *      *

* መልክአ ኤዶም




➤ከወደዱት በቅንነት ይቀላቀሉን!
👇👇👇👇👇👇
@liulzemaryam
@liulzemaryam
@liulzemaryam
☝☝☝☝☝☝☝

Читать полностью…

ከጥበብ እልፍኝ

የፍቅር ፀብ
( በላይ በቀለ ወያ )

ባብሮነታችን ውስጥ
ጥላቻ ባይኖርም - መናናቅ ነበረ
በመናናቃችን
መለያየት መጣ - አብሮ መኖር ቀረ
አብሮ መብላት ቀረ
አብሮ መዋል ቀረ
አብሮ ማደር ቀረ
ቀረ
ቀረ
ቀረ
ሁሉም ነገር ሲቀር - ናፍቆት ተጀመረ
በናፈቅሽኝ ጊዜ - እንዲህ ስል ነበረ
እንኳን ተለያየን - እንኳን አብረን በላን
እንኳንም ናፈቅሽኝ - ፍቅር ነው ያጣለን፡፡
ባብሮነታችን ልክ
መናናቅ ልብ ላይ - ያኔ የተሰቀለ
አሁን የሚታየኝ
ናፍቆት የምንለው - ናፋቂ ፍቅር አለ፡፡
እንኳን ተለያየን!


➤ከወደዱት በቅንነት ይቀላቀሉን!
👇👇👇👇👇👇
@liulzemaryam
@liulzemaryam
@liulzemaryam
☝☝☝☝☝☝☝

Читать полностью…

ከጥበብ እልፍኝ

ወሩ መሥከረም ነው...
ቀኑ በሃያ አንድ ፣ በኢትዮጵያ አቆጣጠር
እንጦጦ ማርያም...
የ'መብርሐንን ፣ በአሏን ለማክበር
ከክርስቲያኖች ቤት...
አርፍጄ እንደደረስሁ ፣ታቦት ወጥቶ ነበር፡፡
፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡
ከታቦቱ አጠገብ...
አውደ ምህረቱ ላይ ፣ ካህኑ ይሰብካል
አንዳንዱ ምእመን ፣
ተአምር ያዘለ ..
ብጫቂ ወረቀት ፣ ለካህኑ ይልካል
ደግሞ ሌላ ተአምር...
ለካህኑ ጆሮ ፣ ዲያቆኑ ያንሻኩካል፡፡
፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡
ካህኑ!
"ታ'ምር ነው ምእመናን ፣ አንድዜ እልል በሉ
አንኳኩ ይከፈታል ፣
ጠይቁ ይሰጣል ፣ ይላልና ቃሉ
"አፀደ ማርያም"
የተባለች እናት ፣ የማርያም ምስክር
ልጇን አስተምራ ፣ በስቃይ በችግር
ካንዱ ይንበርስቲ...
ተመርቆ ወጥቶ ፣ ያለ ሥራ ሲኖር
አምና በዚህ ሰዓት...
ከደጇ መጥቼ ፣ ተማፅኛት ነበር
ፀሎቴን ሰምታለች!
ልጄም ሥራ ይዞ ...
መቶ ዶላር ልኳል ፣ ካሜሪካን ሀገር፡፡"
እንዲህ እንዲያ እያለ
ስብከቱን አቋርጦ ፣ ተአምር ሲናገር...
በሴቶች እልልታ ፣ በወንዶች ጭብጨባ
የኢትዮጵያዊት ስለት...
ካሚሪካን ሀገር ፣ ተልኮ ሲገባ
ጥያቄ አምጣለሁ ፣ ዐይኔ እስኪያረግዝ እንባ፡፡
፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡
አላለሁ...
ምንድነው እዚህ ሀገር ፣ ተምሮ መመረቅ?
እርግማን አይደል ወይ...
ሰው ሀገር ለመሥራት ፣ ተቸግሮ ማወቅ?
።፣፣፣፣፣።።።፣።፣፣
ምኑ ነው እውቀቱስ...
የተማሩት ነገር ፣ ላገር ካልጠቀመ
ምንስ ነው መቸገር....
ወድቀው ከፍ ያረጉት ፣ ሰው ሀገር ከቆመ?
ወይስ አልተቻለም...
እዚሁ ተምሮ ፣ እዚሁ ሀገር መስራት?
የተማረው ሁሉ...
ጥሏት ከነጎደ ፣
ማነው ይችን ሀገር ፣ የሚያስተዳድራት?
፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡
ምንድነው እማምላክ
የሠው ሀገር ገንዘብ ፣ የሰው ሀገር ፍራንክ
በእልልታ ታጅቦ ፣ ከደጅሽ ሚመጣ?
በማለት እያማጥኩ...
ጥያቄ እየወረድኩ ፣ ጥያቄ ስወጣ...
።።።።፣፣።።።።
አውደ ምህረቱ ላይ ፣ የካህኑ ስብከት
ከታቦቱ ፊት ላይ....
"ተቃጠልኩኝ " የሚል
"አሰናብቺኝ " የሚል
በሰው ላይ ያደረ ፣ ያጋንንት ጩኸት
ከታቦቱ ዙርያ...
"አይኔ ነሽ ብርሃኔ
እመቤቴ ማርያም ፣ አብሶማ ለኔ"
እያለ ሚዘምር ፣ ክብ የሰራ ወጣት
ይህንን እያየሁ
ብዙ ጥያቄዎች ፣ ሳምጥ ሳጠራቅም
አንድ አይነ ስውር ሰው...
ፊቴ ተደቀነ ፣ ምፅዋት ሊለቅም፡፡
፡፡፡ ፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡
ምነው እመብርሀን
ታደዪ ይመሥል...
አይኔ ነሽ እያለ
አብሶማ እያለ ፣ ወጣቱ ሲዘምር
ምን ይሰማው ይሆን...
ከደጅሽ የመጣ ፣ ምስኪን አይነስውር?
ስል እጠይቃለሁ ፣ ደግሞ እታዘባለሁ
ጥያቄ እያማጥሁ ፣ እንባ እወልዳለሁ፡፡
እዘኝ አዛኝቱ!
እዘኝ አዛኝቱ!!



➤ከወደዱት በቅንነት ይቀላቀሉን!
👇👇👇👇👇👇
@liulzemaryam
@liulzemaryam
@liulzemaryam
☝☝☝☝☝☝☝

Читать полностью…

ከጥበብ እልፍኝ

▻ድምጽሽ ሰትሰማ

እንደ ናርዶስ ሽቱ እንደ ንጽህ ዕጣን፣
እንደ ጥኡም ዜማ እንደ ቅዱስ ቁርባን፣
እንደ ሊቆች ጥበብ ልክ እንደ ቅዳሴ፣
እንደ መላዕክቱ ምስጋና ውዳሴ....

ህይወቴ ቃልሽን ድምጽሽን ስትሰማ፣
ሐሴት ይሞላታል እፁብ ድንቅ ግርማ።

ድምጽሽን ስትሰማ በደመና ቋት ላይ፣
ክንፍ አበቅላ በራ በአርያም ሰማይ......

ከጻድቃን ሰማዕታት ከቅዱሳን ጋራ፣
ቅዱሱን የአምላክ ስም ፍፁም ስትጣራ.....

ባርነትን መርጣ ለጌታዋ በክብር፣
ትህትናን ተሞልታ በማይታበይ ፍቅር...

ስትቦርቅ በደስታ ይሰማኛል በ'ውነት፣
ቃልሽ ብስራት ሆኗት ፍስሀና ሐሴት።


✍ልዑል


➤ከወደዱት በቅንነት ይቀላቀሉን!
👇👇👇👇👇👇
@liulzemaryam
@liulzemaryam
@liulzemaryam
☝☝☝☝☝☝☝

Читать полностью…

ከጥበብ እልፍኝ

..……
ብዙን ከመመኘት የደፈነው ልቤን
ከአመንዝራነት የጋረደው ዓይኔን
ከሐጢያት ጎዳና ያወጣኝ ጎትቶ
ከዕድፍ ስሜት ውስጥ የለየኝ አንጽቶ
ካንተ ያገኘኹት ሁሉን የሚረታው
የኔ ውብ ሙሽራ ያንተ ውብ ፍቅር ነው!
እናም ሙሽራዬ ይህ ግዙፍ ስሜት
እስከ ዕድሜ ዘመኔ እስካለልኝ ዕለት
እንዲኖር እሻለው በሐሴት ልኖርበት!

✍️🙋
➤ከወደዱት በቅንነት ይቀላቀሉን!
👇👇👇👇👇👇
@liulzemaryam
@liulzemaryam
@liulzemaryam
☝☝☝☝☝☝☝

Читать полностью…

ከጥበብ እልፍኝ

"ሠርግ አማረኝ"
(absurd wedding)
እንዳልኩሽ አልቀረሁም፡፡
አገባሁ እኮ፡፡
ያውም ላንቺ በገዛሁት ቀለበት፡፡(ዕምነት)
ያውም ላንቺ በገዛሁት ነጭ ሱፍ፡፡(ተስፋ)
ያውም ላንቺ ለጫጉላ በተከራየሁት ቤት፡፡(ፍቅር)
:
:
እና ከመጣሽ ....ሠርግ ልጠራሽ ነበር፡፡
ብቻዬን የደገስኩት፡፡
ብቻዬን ...ሠርግ፡፡
የራሴን ጉልበት ስሜ
ከራሴ ቤት ወጥቼ ራሴ አልቅሼ ራሴን አባብዬ
("ወግ ነው ሲዳሩ ማለቀስ" ብዬ)፡፡
ወግ ላይ ነኝ፡፡
ሰው ይታያሻል አይደለ?
ሲያረግድልኝ፡፡
የኔ ሠርግ ለየት የሚለው ጥቁር በጥቁር ያልለበሰ አለመግባቱ ነው፡፡
(ሞትና ሠርግ አንድ ነው)
የዚህ ሠርግ ልዩ መሆኑ ሙዚቃ የለም፡፡ በቃ የቀጥታ ስርጭት ሙሾ ነው፡፡ ሙሉ ባንድም አለ፡፡
የእናቴ እጅ እና ደረት፡፡ (ሲደቃ)
ይሰማሻል?
እናቴ:- "ለኔ ያርገው"
ሕዝቡ:- "እሰይ"
እናቴ:- "እኔ ልውደቅልህ"
ሕዝቡ:- "እሰይ"
እናቴ:- "ካልገባሁ ከመቃብር"
ሕዝቡ :- "አናስገባም ለቅሶኛ (እናቴን) እደጅ ተኛ፡፡ "
ያው
ከሠርጌ በፊት በላኩልሽ ጽሑፍ
"ብቻሰው ይኑር ብዬሽ የለ"
(ረሳሽው እንዴ)
ሠርጌ ላይ
የሚያለቅሱ
የሚያላቅሱ
የሚያለቃቅሱ
የሞተባቸው ትዝ ያላቸው
"የኔስ ቢሞትብኝ ምን ይውጥኝ?" የሚሉ
አዛኞች
እነ እማማ ድንቁ
እነ እማማ ሰልፌ
አጽናኞች
እነ ዘዉዱ
እነ ነስሓ አባት
አስመሳዮች
በሠርጉ የቀኑ
እነ "የቀድሞ ፍቅረኛ ነን" ባይ
"ቀመሶናል" ባይ
"አናቀውም እንዴ" ባይ
ሁሉም ለሠርጉ የበኩሉን አዋጥቷል፡፡
ሁሉም ገምቷል የቻለውን፡፡
እንዲያውም መዳፌን ላስነበብ ሄጄ የሆነ ቀን ሰውየው እጄን ቢያየው አነሰችበትና፡፡ "ይህ መዳፍ ለመነበብ አልደረሰም" አለኝ፡፡ "እና ዕድሌን እንዴት ልወቅ?" አልኩት
"እጅህ እንዲህ ካነሰ ዕድልህን ገምተው" ያለኝን ትዝ አለሽ፡፡
በቃ እሱ እንደገመተው ሆነ፡፡
የዛሬ....
ግምት ወ ሐሜት
"ትናንት እኮ አይቼው ነበር"
"ስንት ነገር አብረን ልንሰራ ነበር"
"ያው የሴት ጣጣ ነው"
"ሱስ ነው መቼም"
"ያስታውቅ ነበረ፡፡ ስለሞት ያወራ ነበር"
"ሰይጣን ነው"
ሌላም ሌላም....
ትመጫለሽ ሠርጌ ነው
:
:
:
አንገቴን ከገመድ የዳረኩበት ቀን፡፡

* * * * * * * * *
(ነፍስ ይማር አይባልም ራሱን ላልማረ)


➤ከወደዱት በቅንነት ይቀላቀሉን!
👇👇👇👇👇👇
@liulzemaryam
@liulzemaryam
@liulzemaryam
☝☝☝☝☝☝☝

Читать полностью…

ከጥበብ እልፍኝ

#የፍቅር_መልዕክት_፫
❤❤❤❤❤❤❤
ሁሌም ከ እንቅልፌ ስነቃ የልቤን ጤነኝነት የማረጋግጠው ስላንቺ ሲያስብ ነው። አው ልቤ ጤነኛ ስለሆነ አንቺን አለማፍቀር አይችልም።
ምክንያቱም ፍቅርሽ ፈዋሽ መድህን ነውና።

❤አፈቅርሻለው❤


➤ከወደዱት በቅንነት ይቀላቀሉን!
👇👇👇👇👇👇
@liulzemaryam
@liulzemaryam
@liulzemaryam
☝☝☝☝☝☝☝

Читать полностью…

ከጥበብ እልፍኝ

#አትሄድም ብየ

#ገጣሚ-በድሉ ዋቅጅራ

#አቅራቢ-ልዑል ዘ-ማርያም

➤ከወደዱት በቅንነት ይቀላቀሉን!
👇👇👇👇👇👇
@liulzemaryam
@liulzemaryam
@liulzemaryam
☝☝☝☝☝☝☝

Читать полностью…

ከጥበብ እልፍኝ

(በላይ በቀለ ወያ)
.
.
ክፉም ንጉስ መጣ
ደግም ንጉስ መጣ
ብቻ ግን ያልፋሉ ፣ ሁሉም እንደመልኩ
ይብላኝ ከህዝብ ጋር
ለሚጣሉ ህዝቦች ፣ መሪ እያመለኩ !!!


➤ከወደዱት በቅንነት ይቀላቀሉን!
👇👇👇👇👇👇
@liulzemaryam
@liulzemaryam
@liulzemaryam
☝☝☝☝☝☝☝

Читать полностью…

ከጥበብ እልፍኝ

🇪🇹🇪🇹🇪🇹ተነሱ🇪🇹🇪🇹🇪🇹

✍ልዑል


✅ድንቅ ሀገራዊ ግጥም ነው ተጋበዙልኝ🇪🇹🇪🇹🇪🇹



➤ከወደዱት በቅንነት ይቀላቀሉን!
👇👇👇👇👇👇
@liulzemaryam
@liulzemaryam
@liulzemaryam
☝☝☝☝☝☝☝

Читать полностью…

ከጥበብ እልፍኝ

✅ነጽር🙏

✍ልዑል


😭😭ፈጣሪ አምላክ የጦብያን መከራ በቃ ብሎ ይታረቃት😭😭



➤ከወደዱት በቅንነት ይቀላቀሉን!
👇👇👇👇👇👇
@liulzemaryam
@liulzemaryam
@liulzemaryam
☝☝☝☝☝☝☝

Читать полностью…

ከጥበብ እልፍኝ

ኤልያስ ሽታኹን

ማሰብና ማመን ወደአፍሪቃ መጡ
በውጊያ ምክንያት
መቆም አቃተቸው እንኳ ሊቀመጡ፡፡
ሁሉ ውጊያ ላይ ነው
በየስም አጠራር
በጦር አመራር፡፡
የጥቁር ዘር ታሪክ በሞት የዘመነው
ክላሽ እንደቆሎ ማነው ያዘገነው?
ብለው ሊጠይቁ
በውጊያ መካከል ሞትን ሲጋፈጡ
የሚተኩስ እንጂ
ቆም ብሎ ሚያወራ አንድ ጥቁር አጡ፡፡

* አንዱን እንደምንም
ጠየቁት አቁመው
ስሙን ረስቶታል ስሙ የቡድን ነው፡፡
ገና ነው
ህፃን ነው
እንኳንና መግደል
ቁራሽ አለመስጠት የሚመስለው በደል ::
ነበር፡፡

* ህፃን ነው ተማሪ
የአስኳላ ጀማሪ
ጠላትና ወዳጅ እንደተምታታበት
ጥያቄው ሳይገባው ጠላት ደረሰበት፡፡

* አንዷን እጇን ያዟት
ለመኗት
ዘከሯት
እሺ ብላ ቆመች
ምላሹ ሲከብዳት አዙራው ደገነች፡፡
አንበረከካ
አስራ
ትታቸው ሮጠች
ጦርነት ስራ ነው አፍሪቃም አይደለች፡፡

ሐበሻ ብልሁ
ሐበሻ በእልሁ
እየለዋወጠ የሞቱን አሟሟት
ቁጭ ብሎ ያያል
በነጴጥሮስ ሀገር ጭካኔን ሲሾሟት፡፡

ሐበሻ ብልሁ
ሐበሻ በእልሁ
የሆዱን ለጀርባው አዙሮ እያዘለ
በቀን የሰራውን
ማታ ይሰማዋል ዜና ነው እያለ ፡፡
ሐበሻ ብልሁ
ሐበሻ በእልሁ
እምነቱን ለገዳም
ሀጢያቱን ለአዳም
ወስዶ እየለደፈ
ፆሙን ይቀበላል ሰው እየገደፈ፡፡
ማመንና ማሰብ
ወደአፍሪቃ መጡ
መቆም አቃታቸው እንኳን ሊቀመጡ፡፡
ሰውና ጠምነጃ ፀንቶ ትዳራቸው
ሞትን እንዲወልዱ ማነው ያስተኛቸው፡፡
ባሩድ ባለጉልበት እየተጀመረ
እየተካረረ
በፀብ በክርክር
ለመኖር ይላል የሟቾች መፈክር፡፡
በመላው አፍሪቃ ተፅፎ ምታየው
ትልቁ መፈክር እንደዚህ የሚል ነው፡፡
ማሰብ እንኳን ካሰብክ ማሰላሰል በውል
እንያንዳንህ ዜጋ
ከመነጽርህ ጋር ጠመነጃህን ወልውል፡፡

እረ የኛስ ሊቅ
እረ የኛስ ምሁር
ካልደፈራረሰ አይጠራም እያሉ እያደፈረሱ
እድሜ ለመፈክር
የወለዱ ሁሉ በባሩድ ታረሱ፡፡
ሞት በጥቁሮች መሬት የተበራከተው
እድሜ ለመፈክር
ቆም ብሎ ማሰብ ስለሚያስገድል ነው፡፡
እንዲያ ነው መናናቅ
እንዲያ ነው መራራቅ
በነፍስም በስጋም በመንፈስ ሳይኖሩ
እንደምን ቻልንበት ጦርን መወርወሩ፡፡
የለንም ከስጋ
የለንም ከመንፈስ
እንዲያው ብቻ




በነፍስ ጠፍተናል
የፈጠረን አምላክ በስም እስኪረሳን
እድሜ ለመፈክር
ለፍቅር ተኝተን ለቀብር ተነሳን ፡፡
ቆም ብሎ ማደግ
ሰከን ብሎ መኖር
አበቦች በለጡን
እንስሶች በለጡን
እሾህዎች በለጡን
ሞት ሆነን በቀልን ባሩድ እያጠጡን፡፡
ወከባ እያጠጡን
ጥድፊያን እያጠጡን...
የሞት ወርቅ በላን
የሞት ብር በላን
የሞት ነሀስ በላን
ከእናታችን ጉያ ጫካ ነው የደላን፡፡
እወራረዳሁ
በክላሽ ያፅናኑት
በመውዜር ያዳኑት
ጠባሳው እንዲሽር ሬት ቀብተውት
አበስነው ይሉሀል ጭራሽ አብሰውት::
እወራረዳለሁ
ግድ የለም እንስከን
ግድ የለም አንስከር
ህይወት ምን ቢያቅረን
ሞት እንኳን ይምከረን፡፡
እወራረዳለሁ
የሚወደቀው ሰው ነው
የሚሞተው ሰው ነው
የሚረግፈው ሰው ነው
እንደጫካ ቅጠል
የኛ እኮ አኗኗር
ከችግር ለመውጣት ከችግር መቀጠል፡፡
እወራረዳለሁ
ያለበደላቸው
ያለነውራቸው
ተስፋቸው ተቀብሮ ህልማቸው በሞተው
የአፍሪቃ ወንበር
እንባ ላይ ሆኖ ነው መፅናት የሚያቅተው፡፡
እንዲያ ነው ሲርቁት
እንዲያ ነው ሲንቁት
ሁሉን ገዢ አላህ ሁሉን ገዢ እግዜር
ሰላም ላምጣ ይላል ጠመኔጃና መውዜር፡፡
እንዲ ነው ሲንቁት
እንዲያ ነው ሲርቁት የዓለማትን ጌታ
ላስታርቃችሁ ይላል ሰይጣን በቄስ ቦታ፡፡


➤ከወደዱት በቅንነት ይቀላቀሉን!
👇👇👇👇👇👇
@liulzemaryam
@liulzemaryam
@liulzemaryam
☝☝☝☝☝☝☝

Читать полностью…

ከጥበብ እልፍኝ

ኤልያስ ሽታኹን

ተፈጥሮ አዘነች
ቀን አዘነበለች
ያ ምስኪን ገበሬ ሆዱ አለው ባር ባር
አወየው ቦረና የከረዩ አድባር....

ሁለት ሀዘን መሐል ተቀመጠች በርዷት
ቀብር ቀረች አሉ ሁሉን እያረዷት፡፡
በየሰሜን መርዶ
በየደበቡ መርዶ
በየምስራቅ ሀዘን
በየምዕራብ ሀዘን
አንድ ሰው ስንት ነው በአንድ ሰው ሲመዘን፡፡
የሰውና በሬው ደም ተቀላቀለ
ነፍስ ተሸቀለ፡፡

የኛ ፀብ ተረፈ ለሞት እስኪያበቃ
ተኳረፉ አሉ ቦረና ዋቃ
የኛ ፀብ ተረፈ ስንቱን ውኃ አስጠማ
ተኳረፉ አሉ ወሎና ከራማ
የኛ ፀብ ተረፈ ለወሬም እንዳይሆን
ተኳረፉ አሉ አክሱምና ፅዮን

ምን አማላጅ አለ
ይቅርታ ከሌለ?
ምን ተስፋ ይታያል....?

ከመሬቱ ጋራ ከምትካሰሱ
ወደላይ እረሱ
ወደላይ ጠርጥሩ
ሰማይ አበጥሩ

እውነት ይሄ ነገር የምድር እጅ ነው?
እውነት ይሄ ነገር ፀቡ የሰው ልጅ ነው?...
እዛጋ ነው መልሱ ለዚህ ሁሉ ስቃይ
ምድር እንዲህ ስትሆን የት ሄዶ ነው ሰማይ?
እንጃ ...

* * * * * * *
(ያለ ነውራቸው ስለሚቀጡት ሁሉ እንድረስላቸው)



➤ከወደዱት በቅንነት ይቀላቀሉን!
👇👇👇👇👇👇
@liulzemaryam
@liulzemaryam
@liulzemaryam
☝☝☝☝☝☝☝

Читать полностью…

ከጥበብ እልፍኝ

#ኑ ሰማይ እንስራ

ከጡት የነጠቁት ጨቅላ ልጅ ይመስል
ማኩረፍ ነው አባዜው የሀገሬ ምስል
ያኮረፈ አንጀት
አይመለስ ላንገት፡፡
አባወራውም ዝም
እማወራውም ዝም
አይነቅዝም
እየተባባሉ
የዚህ ቤት ስለቶች ስንቱን በጎች በሉ፡፡
ይልቅስ
ለማረስ ቢሳሉ
ለማጨድ ቢሳሉ
ለማረም ቢሳሉ በወጉ በወጉ
የምስኪን በጎችን አንገቶች ባልወጉ፡፡
እየተብሰልኩ
እየተንገበገብኩ
የምለማመነው
ቆይ ሀገር ምንደነው?
ቆይ አድባር ምንድነው?
በሚል ጥያቄ ነው?

ከአክሱም የረዘመ
ቃየልን ያረመ
ከአባይ የዘለቀ
ሰዶምን የናቀ
አዋሽን ያከለ
ፅዮንን ያከለ
ጊቤን የሸሸገ
ጣናን ላይ ያረገ
ባሮን የከበበ
ፍቅራችን የት ገባ
ልባችን እንደምን ከድብ ጋር አደባ?
ይናፍቃል አይደል
የፀጋዬ ሀገር
ይናፍቃል አይደል
የደበበ ሀገር
ዘመን ተከትለን
ወደላይ ሰርተናት
ከሰው አይን ገብታ በዘር እንዳያጥሯት
የኔና አንቺን ሀገር
እንደላሊበላ ወደታች በሰሯት፡፡

ወደስምጡ
ይምጡ
ይምጡ
ይቀመጡ
ሀሳብ ይቁምና
መንዙማ ይጠጡ ቅዳሴ ይጠጡ፡፡
ህምም እና መዝመም
እንጂማ
ደመና ነን ያሉ
መዝነብም እንዳለ ለምን ይረሳሉ?
የትኛው ደመና
ዘላለም ቆየና፡፡
ሊቁ ምን ሆኖ ነው ደመና ሚያብራራ
ይልቅስ እንዲያውም
ሀገር ሚያስጠልል ኑ ሰማይ እንስራ፡፡

* * * * * * *


➤ከወደዱት በቅንነት ይቀላቀሉን!
👇👇👇👇👇👇
@liulzemaryam
@liulzemaryam
@liulzemaryam
☝☝☝☝☝☝☝

Читать полностью…

ከጥበብ እልፍኝ

እንደ ቀልድ ፈገግ******


በላይ በቀለ ወያ
.
አንቺ እንደምን አለሽ? ፣ እኔን'ኳን አሞኛል
ደህና ነኝ ብልሽም ፣ ሳቄ ይቀድመኛል።
ኑሮ እንዴት ይዞሻል ፣ ባለሽበት ሀገር
እኔ ባለሁበት...
ኢምንት ጉዳይ ነው!
እየሳቁ ውሎ ፣ እየሳቁ ማደር።
ውሸት ነው አትመኝ....
እዚህ ሀዘን የለም ሳቅ ነው የተረፈን
ስላቅ ነው ትርጉሙ...
ሀገር ለቆ ሄዶ፣
"ሀገሬን ሀገሬን" ፣ ብሎ እንደመዝፈን።
............................................
ይልቅ አንቺ እንዴት ነሽ? ፣ እኔ አለሁ ታምሜ
ይህን ምፅፍልሽ ፣ ነው ሀኪም ፊት ቆሜ።
ምን አሳቀህ አልሽኝ?
"ምንህን ነው ሚያምህ"...
ብሎ ቢጠይቀኝ
ባኪሙ ጥያቄ ፣ ውስጤ ተገረመ
ምኑን ሀኪም ሆነ...
ማወቅ ከተሳነው ፣ ምኔ እንደታመመ?
...........................................
ሃሃሃሃሃሃሃሃሃ
ልነግርሽ እኮ ነው
ምን ብዬ ልንገርሽ?....
ልነግርሽ ያልሁትን ፣ ሳቄ እያፈነው።
ሃሃሃሃ
😁
እናም እልሻለሁ...
ልነግርሽ ያልሁትን ፣ አልቻልኩም መናገር
ቁም ነገራችንን...
ሳቅ ነው የሚያፍነው ፣ ባለሁበት ሀገር

[ በላይ በቀለ ወያ ]


➤ከወደዱት በቅንነት ይቀላቀሉን!
👇👇👇👇👇👇
@liulzemaryam
@liulzemaryam
@liulzemaryam
☝☝☝☝☝☝☝

Читать полностью…

ከጥበብ እልፍኝ

ካ'ናት ስንወጣ
ፀሐይ አመላቸው ፣ ማቅለጥ ማውረድ ላይተው
"ቅቤ ተገፍቶ ነው
አናት ላይ የወጣው " ፥ በማለት ተርተው
ረግተን ቢያገኙን ፣ ቅቤ አረጉን ገፍተው።
።።።
እስከመቼ ይሆን
ቀልጦ ወውረድ ላይቀር ፣ ለመገፋት መርጋት
ፍራሹ እሾህ ነው ፣ ብርድ ልብሱ ውጋት
ጦርነቱ ችጋር ፣ ሀገሪቱ ስጋት
ምን ላይ ተተኝቶ ፣ ይታለማል ንጋት?!


➤ከወደዱት በቅንነት ይቀላቀሉን!
👇👇👇👇👇👇
@liulzemaryam
@liulzemaryam
@liulzemaryam
☝☝☝☝☝☝☝

Читать полностью…

ከጥበብ እልፍኝ

. ✅ቃልና ህይወት

(ልዑል)

እውነት ሳይገለጥ ረቆ፥ጎልቶ ሳይጠና፣
ሰማያት ሳይዘረጉ የምድር መሰረት ሳይፀና፣
ፍጥረታት ሳይኖሩ ቃል ነበር በቅድምና።

ሰማይ ያለ ካስማ ምድር ያለ መሰረት፣
በሐለወት ጥበብ ሳይፈጠር ፍጥረት....

ብርሃናት ሳይበሩ ንውጽውጽታ ሳይደመጥ፣
ቃል ነበር ቃል ሆኖ ረቆ ሳይገለጥ።

የመዳፉ ፍጥረት ህይወት ሲያጣ ከስሞ፣
ከአምሳሉ ሲቃረን ከክደት ጋር ገጥሞ.....

ይህ ቃል ስጋ ሆነ ከመርገም ሊቤዠን፣
የረቀቀው ጎላ የራቀን ቀረበ ከሞት ሊታደገን።

ቃል ህይወት ሆነ በስጋ ተገልጦ፣
ከንግስና ይልቅ ባርያነትን መርጦ።





➤ከወደዱት በቅንነት ይቀላቀሉን!
👇👇👇👇👇👇
@liulzemaryam
@liulzemaryam
@liulzemaryam
☝☝☝☝☝☝☝

Читать полностью…

ከጥበብ እልፍኝ

# ኤፍሬም_ስዩም እንደፃፈው
# ኑ_ግድግዳ_እናፍርስ_2008

# የማርያም_ንግስ_እለት ።
.
አዳፋ ነጠላ በቀጠነ ገላ ፥ ነፋስ የሚጥለው
የነተበ ጫማ. ጥቁር ያዘን ቀሚስ ፥ ኑሮ ያጨቀየው
ለብሳ የተገኘች .........
ከቤተክርስቲያን አፀድ ፥ ቆማ ከዋርካ ስር
አንዲት ምስኪን ባልቴት .....ትለማመን ነበር
,
አደራሽን ማርያም
አደራሽን ማርያም
እበላው የለኝ መሶቤ ተራቁቷል
እለብሰው የለኝም ጀርባዬ በርዶታል።
,
ወድቃ እየተነሳች
እምባ እያፈሰሰች
ተስፋዋ ማርያምን ትለማመን ነበር
ከቤተክርስቲያን ጓሮ ቆማ ከዋርካ ስር።
,
የደብሩ አለቃ
ካባ ላንቃ ለብሶ ምጣህቱን ደርቦ
ልክ የሌለው ቦርጩ ወደፊት ተስቦ
የንግሱን ምዕመን ወደፊቱ ስቦ
ጮክ ብሎ ያወራል
ጮክ ብሎ ያስተምራል።
,
1
የመቅደሱ ቀለም ሊታደስ ይገባል
2
የካህናት ደመወዝ ሊጨመር ግድ ይላል
3
ደጀ ሠላም ወንበር እጅጉን ያንሰናል ......
.
እናም.......
በዚህ ታላቅ ደብር ይህ ችግር ስላለ
ለማርያም የሚሆን እጃቹ የት - አለ?
እያለ።.....
ህዝቡን ያስተምራል
ህዝቡን ይደልላል።......
ለንግሱ የመጡ.....
ባለ ብዙ ብሮች
ብዙ ባለጠጎች....
ጥለት የለበሱ ፥ በሽቶ የራሱ
ቆመው የነበሩ....እፊት ከመቅደሱ
ቀለም እንዲቀባ እንዲታደስ ደብሩ
ለደጀ ሠላሙ ደግሞም ለወንበሩ
በሺ .....የሚቆጠሩ
ብሮች ወረዋሩ....
.
የደብሩ አለቃ ግንባር በጣም ውዛ
የሚወረወረው ብሩም በጣም በዛ።
.
የዛች የምስኪን ነፍስ
ያች ታላቅ መቅደስ
ቆማ ከዋርካ ስር
ተስፋዋ ማርያምን ትለማመን ነበር::
,
ኣደራሽን ማርያም
አደራሽን ማርያም
እበላው የለኝም መሶቤ ተራቁቷል
እጠጣው የለኝም ማድጋዬ ጎድሏል
እለብሰው የለኝም ጀርባዬ በርዶታል
አንቺ ነሽ ተስፋዬ የኔስ ተስፋ ሞቷል
ወድቃ እየተነሳች
እምባ እያፈሰሰች።
,
,
ግና ግን ለዛሬ ፥ ለክብርሽ እንዲሆን
ተቀበይ ስጦታ ውሰጂ አምሃዬን
የሟች ባሌን ማስታወሻ የኣንገት ሃብሌን::



➤ከወደዱት በቅንነት ይቀላቀሉን!
👇👇👇👇👇👇
@liulzemaryam
@liulzemaryam
@liulzemaryam
☝☝☝☝☝☝☝

Читать полностью…

ከጥበብ እልፍኝ

እምዬ ኢትዮጵያ ፣ ብትደላም ብትከፋም
ምላስ ናት ለህዝቧ ፣ ከአፋችን አትጠፋም።
።።።
አፍ በሚባል ዋሻ...
ምላስን የሚያህል ፣ ስጋ ተሸክሞ
ስጋ ባለመብላት ፣ ማንስ ያውቃል ፆሞ?!
:::::::::
ፍስክ ምላስሽን ፣ ባፍሽ ተሸክመሽ
ከዋናው የደም ምንጭ ፣ ልቤ ላይ ታትመሽ
ፆመኛ ነኝ ስትይ ፣ ታስገርሚኛለሽ፡፡
፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡
ወደ ነፍሴ ገዳም ፣ ስትገቢ መንነሽ
ዓለም በቃኝ ስትይ ፣ የኔው ዓለም ሆነሽ
ታስገርሚኛለሽ፡፡
፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡

(በላይ በቀለ ወያ ✍️)


➤ከወደዱት በቅንነት ይቀላቀሉን!
👇👇👇👇👇👇
@liulzemaryam
@liulzemaryam
@liulzemaryam
☝☝☝☝☝☝☝

Читать полностью…

ከጥበብ እልፍኝ

ሀገሩን በሙሉ ፥ ጨለማ ሲወርሰው
እድሜ ለአንቺ ፍቅር
መብራት ጠፋ ብዬ ፥ አልጮህም እንደሰው።
ወድሃለሁ ስትይ
ብርሀን ያፈልቃል ፣ ነዝሮት ሰውነቴ
አለም ይታየኛል ፣ እንኳን ጠባብ ቤቴ😂





➤ከወደዱት በቅንነት ይቀላቀሉን!
👇👇👇👇👇👇
@liulzemaryam
@liulzemaryam
@liulzemaryam
☝☝☝☝☝☝☝

Читать полностью…

ከጥበብ እልፍኝ

የሴተኛ አዳሪ ልጅ ነኝ
(በላይ በቀለ ወያ)
.
.
ያባቴን ማንነት ፣ ድንገት ስጠይቃት
እንባና ትዝታ ፣ እየተናነቃት
እንዲህ ትለኛለች...
"አንተን በመሀፀን ፣ እኔን በእርግዝና
ልጁን እና ፍቅሩን ፣ ክዶ ሄዱዋልና
አንተን ለማሳደግ...
ታክቶኝ የለመድኩት ፣ የብዙ ሰው ገላ
አንተን ካሳደገህ...
ሁሉም አባትህ ነው!
ከፍሎኝ የሚተኛ ፣ ወንድ አዳሪው ሁላ።"
ብላ የምትነግረኝ
የሴተኛ አዳሪ ፣ የተከፋይ ልጅ ነኝ ።
፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡
ይሄ ነው ታሪኩዋ...
ሴት አዳሪነቱዋን፣ ቀድሞ ያስጀመራት
የሆነ ዘመን ላይ ፣ ፍቅረኛ ነበራት
"የዘላለሜ ነሽ" ብሎ የሚነግራት ፡፡
፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡
የሆነ ዘመን ላይ...
"አረገዝኩ" አለችው ፣ ማስረገዙን ካደ
ዘላለም ስታምነው...
እኔን በመሐፀን ፣ እሷን በችግር ላይ ፣ ጥሎ ተሰደደ።
፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡
የሆነ ዘመን ላይ...
እኔ ተወለድኩኝ ፣ እሱዋ ተቸገረች
እኔን ለማሳደግ....
ከብዙ ወንዶች ጋር ፣ መተኛት ጀመረች።
፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡
ከዛን ቀን ጀምሮ....
ሲመሽ ትወጣለች ፣ በፍጥነት ተኩላ
ማልዳ ትመጣለች ደክሙዋት ተጎሳቁላ
አንተን ካሳደገህ...
ከፍሎ ተኚ ሁሉ ፣ አባትህ ነው ብላ።

➤ከወደዱት በቅንነት ይቀላቀሉን!
👇👇👇👇👇👇
@liulzemaryam
@liulzemaryam
@liulzemaryam
☝☝☝☝☝☝☝

Читать полностью…

ከጥበብ እልፍኝ

#ገጣሚ-ኤልያስ ሽታሁን

#አቅራቢ-ልዑል ዘ-ማርያም

➤ከወደዱት በቅንነት ይቀላቀሉን!
👇👇👇👇👇👇
@liulzemaryam
@liulzemaryam
@liulzemaryam
☝☝☝☝☝☝☝

Читать полностью…

ከጥበብ እልፍኝ

#የፍቅር _መልዕክት_፪

የኔ አለም🌍
አንቺን ማግኘቴ "መታደል ነው" እያልኩ አንዳንዴ አስባለው። ግን ወድያው እንደተሳሳትኩ ይገባኛል።
ምክንያቱም አንቺን ማግኘት ከእድል በላይ ነው። የእውነት አንቺን ማግኘት ከእድልም ይልቅ መባረክ፣መመረጥ ነው። ፈጣሪም ሲወደኝ በሐሴት እኖር ዘንድ አንቺን አደለኝ።

❤❤❤

➤ከወደዱት በቅንነት ይቀላቀሉን!
👇👇👇👇👇👇
@liulzemaryam
@liulzemaryam
@liulzemaryam
☝☝☝☝☝☝☝

Читать полностью…
Subscribe to a channel