"ታድላ" ቢሉላት
"እንዲህ ምትፅፍላት"
መልሴ
እኔ - ታደልኩ ኝ
ስለርሷ - ጻፍኩ ኝ
➤ከወደዱት በቅንነት ይቀላቀሉን!
👇👇👇👇👇👇
@liulzemaryam
@liulzemaryam
☝☝☝☝☝☝☝
#ኤልያስ_ሽታሁን
የወደደ ፍቅሩን
ሸረሪትም ድሩን
እንደማያስነካ
እንዲዚያ ነኝ በቃ::
ወዶገባ ሆኖ ምርኮኛ ትካዜው
እንዲሳካ ብሎ
እውነቱን ሸጦ ነው አፍቃሪ ለጊዜው።
“እሺ” ቢል ቢዋረድ ቢናቅም ቢዘበት
"ምንም አያመጣም" ብለሽ አትሳቂበት::
ለወናፍ ዐፍ ሁሉ ቢሆን መዘበቻው
የመጣበት ቀን ግን
በፍቅሩ ልክ ነው የአፍቃሪ ጥላቻው።
➤ከወደዱት በቅንነት ይቀላቀሉን!
👇👇👇👇👇👇
@liulzemaryam
@liulzemaryam
@liulzemaryam
☝☝☝☝☝☝☝
ደስ የሚል ግጥም
➤ከወደዱት በቅንነት ይቀላቀሉን!
👇👇👇👇👇👇
@liulzemaryam
@liulzemaryam
@liulzemaryam
☝☝☝☝☝☝☝
#መወድስ_ለአንተ
➤ከወደዱት በቅንነት ለሁሉም እንዲደርስ share ያድርጉ
👇👇👇👇👇👇
@liulzemaryam
@liulzemaryam
@liulzemaryam
☝☝☝☝☝☝☝
#ግጥም_ስጽፍልሽ
➤ከወደዱት በቅንነት ለሁሉም እንዲደርስ share ያድርጉ
👇👇👇👇👇👇
@liulzemaryam
@liulzemaryam
@liulzemaryam
☝☝☝☝☝☝☝
#እሺ_በይኝና
➤ከወደዱት በቅንነት እባኮ ለሁሉም እንዲደርስ share ያድርጉ
👇👇👇👇👇👇
@liulzemaryam
@liulzemaryam
@liulzemaryam
☝☝☝☝☝☝☝
#ስትኮላተፊ
➤ከወደዱት በቅንነት እባኮ ለሁሉም እንዲደርስ share ያድርጉ
👇👇👇👇👇👇
@liulzemaryam
@liulzemaryam
@liulzemaryam
☝☝☝☝☝☝☝
#ምን_እየሆንኩ_ልጠብቅሽ
➤ከወደዱት በቅንነት እባኮ ለሁሉም እንዲደርስ share ያድርጉ
👇👇👇👇👇👇
@liulzemaryam
@liulzemaryam
@liulzemaryam
☝☝☝☝☝☝☝
ብቸኛ ሰው የለም፡፡
ኤልያስ ሽታኹን
* * * * * *
ይሄ ሁሉ ሰው ስለብቸኝነት
የተዘፈነ የሚሰማው
የተገጠመ የሚያነበው
የተሳለ የሚቃርመው
ወዶ ይመስልሀል?
ከሰው ጋር የጠመመ በምንም ላይቀና
ከብቸኝነት ውሰጥ ምን ደስታ አለና?
ምንም:፡
ብቻ እንዲሁ
ከአብሮነት ስቃይ
ዕንባ ያላባባይ
በአብሮነት ተዛዝሎ
ከመክረም ተቋስሎ
እያለ አሸሸ
ስንቱ ራሱን ዋሸ?
ወዶ ይመስለሀል?
ከአድማስ እስከ አድማስ
ሰው ሀዘኑ ሲማስ
እንዲያው ከራሴ ጋር ልሁነው ልንደደው
ብቸኝነት ዜማን
ለሀገሩ በሙሉ ማነው ያስለመደው?
እንጂ
ዘር የሌለው
የሰው ደም ያልሳበው
ሳቅን ፍንጣቂ
የዕንባውን ጭማቂ
የሚያይለት ያጣ
ብቸኝነት ዕጣ
ብሶት ቆፈን ወርሶት
በየጥቃቅኑ ሆድ አንጀቱን ብሶት
ገና ፈገግ ሲል
ጠፍንጎ እየያዘው ብቸኝነት ከፍንጅ
ብቻውን ተፈጥሮ
ብቻውን የሞት የታለ የሰው ልጅ?
ብቸኛ ሚባለው
ወይ እኛ የተውነው
ቢወርደን ዕንባውን
ወይ እኛን ትተውን
እንደሆን ነውና
ብናበጥር ዘሩን
አውጥተን ብናየው ከሀዘኑ ቀለም
የተተወ እንጂ ብቸኛ ሰው የለም፡፡
➤ከወደዱት በቅንነት ይቀላቀሉን!
👇👇👇👇👇👇
@liulzemaryam
@liulzemaryam
@liulzemaryam
☝☝☝☝☝☝☝
ሰንበት-
* * * * *
የመመለስ መንገድ ባይሆንም ለጌታ
መጣል ግን አይከፋም "የነበርን" ቦታ፡፡
የሰንበት ቀንና ሰንበት ትምርትቤት
ትዝታ የሌለው ባይኖርም አንዳች ቤት
በልጅነት ድሮ
"አሾረው ነበረ" የደብሩን ከበሮ::
በጊዜ በዕድሜ እየደበዘዙ
"ዘምሬ ነበረ" ማለት የሚያበዙ
"ከነበር" ፉከራ ጀርባ ተቀምጠን
አታውቁም ከመባል ፍርሃት ሮጠን
ሰንበት ትምህርትቤት
መልዕክተ ዩሐንስን
መልክአ ኢየሱስን
"ዘልቄ ነበረ"
የሚለው ሰው ቁጥር ያውም በተውሶ
ሰንበት መማርና
ሰንበት ማክበር ቀረ "ነበርን" ከልሶ፡፡
"ነበርን" በንባብ
"ነበርን" በወርድ
"ነበርን" በዜማ
ስናጠና ከርመን እንደሠርግ ዘፈን
ለእግዜርም ለሰውም "ነበር" የተረፈን
ሙዳይ ምጽዋትን የመያዝ ትህትና
አሁን ቀይረነው
በሚይዙ ሰዎች ውስጣችን ሳይቀና
ልክ እንደጅልነት
ልክ እንደልጅነት
ሰፍረነው ሲያበቃ
"እኛም እንዲህ ነበር"ን ማለት ሆነ በቃ፡፡
ትህትናን ሰበርን
ትናንትን ቀበረን
ስናጠናው አለን መልክአ "ነበርን"፡፡
➤ከወደዱት በቅንነት ይቀላቀሉን!
👇👇👇👇👇👇
@liulzemaryam
@liulzemaryam
@liulzemaryam
☝☝☝☝☝☝☝
ብቸኛ ሰው የለም፡፡
ኤልያስ ሽታኹን
* * * * * *
ይሄ ሁሉ ሰው ስለብቸኝነት
የተዘፈነ የሚሰማው
የተገጠመ የሚያነበው
የተሳለ የሚቃርመው
ወዶ ይመስልሀል?
ከሰው ጋር የጠመመ በምንም ላይቀና
ከብቸኝነት ውሰጥ ምን ደስታ አለና?
ምንም:፡
ብቻ እንዲሁ
ከአብሮነት ስቃይ
ዕንባ ያላባባይ
በአብሮነት ተዛዝሎ
ከመክረም ተቋስሎ
እያለ አሸሸ
ስንቱ ራሱን ዋሸ?
ወዶ ይመስለሀል?
ከአድማስ እስከ አድማስ
ሰው ሀዘኑ ሲማስ
እንዲያው ከራሴ ጋር ልሁነው ልንደደው
ብቸኝነት ዜማን
ለሀገሩ በሙሉ ማነው ያስለመደው?
እንጂ
ዘር የሌለው
የሰው ደም ያልሳበው
ሳቅን ፍንጣቂ
የዕንባውን ጭማቂ
የሚያይለት ያጣ
ብቸኝነት ዕጣ
ብሶት ቆፈን ወርሶት
በየጥቃቅኑ ሆድ አንጀቱን ብሶት
ገና ፈገግ ሲል
ጠፍንጎ እየያዘው ብቸኝነት ከፍንጅ
ብቻውን ተፈጥሮ
ብቻውን የሞት የታለ የሰው ልጅ?
ብቸኛ ሚባለው
ወይ እኛ የተውነው
ቢወርደን ዕንባውን
ወይ እኛን ትተውን
እንደሆን ነውና
ብናበጥር ዘሩን
አውጥተን ብናየው ከሀዘኑ ቀለም
የተተወ እንጂ ብቸኛ ሰው የለም፡፡
➤ከወደዱት በቅንነት ይቀላቀሉን!
👇👇👇👇👇👇
@liulzemaryam
@liulzemaryam
@liulzemaryam
☝☝☝☝☝☝☝
እኛም እንደ እረኞቹ በቤተልሔም መገኘትን ወደድን እንደ ሰብዓ ሰገል እጅ መንሻ ማቅረብን ሻትን እንደ ላም አህያ እስትንፋስ ብንለግሰው አልን እንደ ዮሴፍ በድንቅ የመላእክት ጉባዔ መታደምን ናፈቅን… እንዲሁ ወዶን ሳይፀየፈን በደላችንን ሊሽር ሰው ሆኖልናልና እንኳን ደስ አለን!
መልካም በዓል!
👇👇👇👇👇👇
@liulzemaryam
@liulzemaryam
@liulzemaryam
☝☝☝☝☝☝☝
✅የመወለድ ናፍቆት!
ግፈፈው ጥላውን
አሁን ያጠላውን ...
ህዝቤ ይተራመስ ይሯሯጥ ለግፊያ
አይኔ አይቶ ይሳቅ ወዝ ያለው ገበያ
ይጢስብን እጣን.. .
ቁጣህ እንዳይነካን...
እንኳን አደረሰህ ይበለኝ ጎረቤት
ለሊት ላይ ይሰማኝ የመቅደስ ማህሌት
ይጩህ ደጄ ላይ በግ
ይድረስ የበዓል ወግ
ይከፋፈል ቅርጫ ቆሞ አባወራ
እናቶች ያስምሩት የማጀቱን ስራ
ተሰዶ የኖረው ይግባ ዲያስፖራ
ጦር የፈታው ወሬ ደርሶ አይወራ
ህፃናት ያውሱን የጃቸውን ምስል
ተወልደህ ውለደን አዲስ እንድንመስል
ገና ሆይ ልደት ሆይ
ይሄን ክፉ ዘመን መጥተህ አትሽርም ወይ?
➤ከወደዱት በቅንነት ይቀላቀሉን!
👇👇👇👇👇👇
@liulzemaryam
@liulzemaryam
@liulzemaryam
☝☝☝☝☝☝☝
ትናንትና ማታ
(በዕውቀቱ ሥዩም)
ላሟሟሽ ሲገባኝ፣እንዳሞሌ አጥቤሽ
በመጨረስ ፋንታ
ለነገ ቆጥቤሽ
አስተርፌሽ ለሰው
የጸጸት ሱናሚ ፤ዓለሜን አመሰው፡፡
ምነው ቢቻል ኖሮ
ፈገግታሽን ቋጥሮ
ሙዳይ ውስጥ መደበቅ
ጃንደረባ ቀጥሮ
ጭንሽን ማስጠበቅ
ክፍት ልቤን ይዤ፤ ዝግ ደጅሽን ጠናሁ
በሰበብ ወድጄሽ ፤ያለሰበብ ቀናሁ፡፡
ፍቅር በተባለ፤ ግራ- ገቢ ነገር
ከጨመተው አገር
ከሰከነው ቀየ
መናፍቅ ይመስል፤ ባዋጅ ተነጥየ
እንደካፖርቴ ቁልፍ፤ ልቤን የትም ጥየ
የትም ስከተልሽ
የትም ሆኖ እድልሽ፤
ሁሉ ያንች ወዳጅ
ሁሉ ባላንጣየ
መፈቀር ሆኖ ጣሽ፤ መቅናት ሆኖ ጣየ
ላንቺ ብስል ፍሬ፤ ለኔ ገለባ ግርድ
ላንቺ እቅፍ አበባ፤ ለኔ እቅፍ ሙሉ ብርድ
ማነው የበየነው ፣ይህን ግፈኛ ፍርድ፡፡
➤ከወደዱት በቅንነት ይቀላቀሉን!
👇👇👇👇👇👇
@liulzemaryam
@liulzemaryam
@liulzemaryam
☝☝☝☝☝☝☝
✅ ትንሳኤሽ ናፍቆናል
ንጋት ነበር ጥንቱን ያኔ በዚያ ዘመን
ዘመን ዘመን ወልዶ ክፋት ተንኮል ሳይገን
ንጋት ነበር ጥንቱን በዚያ ዘመን ያኔ
ሳይጠናወት የጎጥ መንፈስ ጠኔ
ያኔ ንጋት ነበር
በጦቢያ ምድር
ፍፁም ድንቅ ፍቅር
የአብሮነት ህብር
እውነት የቀመረው ስውር ድንቅ ሚሲጢር።
ንጋት ነበረች ጦብያ .....
የብርሃኗ ፀዳል ለአለም የምያበራ
ለአፍሪቃ ትምክት ስሟ የምፈራ
ለዜጎቿ ደጀን ግብሯ የምያኮራ።
ንጋት ነበር ያኔ
ጎዳውሙሉ ነው ማጀቷ አልገደለም
ወተት ይፈልቀዋል ወንዟ አልነጠፈም።
ከፍ ካለው ሰማይ ደመናው ያጎራል
ወቅቱ ሳይዛነፍ ዝናሙ ይዘንባል
አይሰስትም ከቶ ምድሯ እህል ያበቅላል።
ፍቅር ነበር ያኔ
ከአማራ ምድር ላይ ጤፍ እየታጨደ
ከደቡቡ መንደር ሰንጋ እየታረደ
ገብሱ ከኦሮሚያ ለጥማችን ማርኪያ
ቅመሙ ከትግረይ ለጥፍጠት መለኪያ
አፋር ቤንሻንጉል ጋምቤላ ሱማሌ ፍቅር እያዜሙ
ሐረር እና ድሬ ከውቢት ሸገር ጋር አብሮ አየተመሙ
አንድ ኢትዮጲያ ብለን የፍቅር ገበታ በአንድ ተቆድሰናል
በሀገር ፍቅር ወኔ ጠላት መክተናል
ያኔ
እውነት አደራጀን
ፍቅር አወዳጀን
አብሮነቱ ዋጀን
ግና ዛሬ
ጥላቻ ፈረጀን
ጎጠኝነት ፈጀን
አለቅን ገረጀን።
የሀገር ፍቅር ወኔ የታለ የጥንቱ
ጠላት ሚያርበደብድ የትገባ ህብረቱ
ስለምን
በፍቅር ያዜምነው ቅኝቱ ፈረሰ
በህዝብ ህሊና ውስጥ ክፋት ተፀነሰ
በሰውነታችን ልክ እሾህ አሜኬላ ስለምን ፀደቀ
ያቆምነው መሰረት እንዴት ባለ ታምር ወደቀ ደቀቀ
ጦቢያዬ ትንሳኤሽ ናፍቆናል ነፍስ ዘርተሽ በኛ
ከፍ በይ ከፍ ይበል ሰንደቅሽ ሰንንደቅሽ ዳግመኛ
ትንሳኤሽ ናፍቆናል የቀደመው ክብርሽ
ብቅ በይ በምስራቅ ኢትዮጲያ ወዴት ነሽ።
✍ልዑል
➤ከወደዱት በቅንነት ይቀላቀሉን!
👇👇👇👇👇👇
@liulzemaryam
@liulzemaryam
@liulzemaryam
☝☝☝☝☝☝☝
#እንዴት_ታዘዘላት?
➤ከወደዱት በቅንነት ይቀላቀሉን!
👇👇👇👇👇👇
@liulzemaryam
@liulzemaryam
@liulzemaryam
☝☝☝☝☝☝☝
#አንቺ_ምን_ይገድሽ
➤ከወደዱት በቅንነት ይቀላቀሉን!
👇👇👇👇👇👇
@liulzemaryam
@liulzemaryam
@liulzemaryam
☝☝☝☝☝☝☝
ማርያም "አራራይ"
~ ~ ~ ~ ~
እግዜር እሳት
ሰው ለማዳን የለበሳት
ወርቅ ልብሱ የመለኮት
ዓይኗ ትሁት አንበርክኮት
ሲድህ ታየ አምላክ ህፃን
ማርያም አጥባን ዳግም ነጻን::
ግን
ንግሥት እንበል እንጂ ለደስታ ቃሉ
ማርያም እና ሀዘን ይተዋወቃሉ::
እመእምላክ
ንጹህ ዜና ፍቅር ገድል
እርሷ ብቻ ሰው ሳትበድል
ሸማ ታለብሳለች ሐር ትህትና
ታስማማለች አሉ ወርቅ ሴት ናትና::
ግን
ንግሥት እንበል እንጂ ለደስታ ቃሉ
ማርያም እና ሀዘን ይተዋወቃሉ::
እመአማን
የነፍስ ልብስ ሸማ የክት
ሰው የመሆን ሴት ምልክት
ባህር ትሁት እምነት ወንዟ
አሳመረው አዳም ወዛ
ነፍስ ጩኸት "አድህነኒ"
ምስጢር ማርያም "ይኩነኒ"
ሆነ አንዴ ላይደገም
ለሰው የለም ሁሌ መርገም::
ግን
አንድ ቀን ያይደለ እድሜ ልኳን ሁሉ
ማርያም እና ሀዘን ይተዋወቃሉ::
አለቅሰች ሲጎትቱት ከምን ትግባ ሲገርፉባት
ዓይኗ እያየ ነበር ልጇን የገፉባት::
ሲጠጣ ከፊቷ አይታለች ሀሞቱ
ቆማ ታዘበችው ሞትን እስከሞቱ::
ወርቅ ልጅ ቀብራለች ተፈትና በእሳት
መከራ ያውቃታል ሰው ባያስታውሳት::
ብርቅ ልጅ ተሰቅሎ
እርቃኑን ተገድሎ
ቆማ ስላየችው ሀዘን እንደድግስ
የከፋው ሰው ካለ ማርያም እቅፍ ያልቅስ::
ድንኳን መሐል ሆነው ሁሉም ይስቃሉ
ለምን አትበሉ
ማርያም እና ሀዘን ይተዋወቃሉ::
እርሷ
እንደደሀ ተናነስች
የልጇን ደም እያፈሰች::
እርሷ
ዓለም አይቶ ተላለፋት
እግዜር ብቻ ችሎ ጻፋት::
እርሷ
ንጋት ለሰው ብርቅ ወጋገን
ምድር ያለች የእግዜር ወገን
እርሷ
አይደርስ ቅድስና
አይልኬ ልግስና
ዜማ ሰማን ከርሷ ቀዳን
አራራይ ናት የሰው መዳን::
➤ከወደዱት በቅንነት ለሁሉም እንዲደርስ share ያድርጉ
👇👇👇👇👇👇
@liulzemaryam
@liulzemaryam
@liulzemaryam
☝☝☝☝☝☝☝
#ይቅናሽ
➤ከወደዱት በቅንነት ለሁሉም እንዲደርስ share ያድርጉ
👇👇👇👇👇👇
@liulzemaryam
@liulzemaryam
@liulzemaryam
☝☝☝☝☝☝☝
#ይቅርታ
➤ከወደዱት በቅንነት ለሁሉም እንዲደርስ share ያድርጉ
👇👇👇👇👇👇
@liulzemaryam
@liulzemaryam
@liulzemaryam
☝☝☝☝☝☝☝
ምን ያህል ወደደከኝ?
➤ከወደዱት በቅንነት እባኮ ለሁሉም እንዲደርስ share ያድርጉ
👇👇👇👇👇👇
@liulzemaryam
@liulzemaryam
@liulzemaryam
☝☝☝☝☝☝☝
#አንቺ
➤ከወደዱት በቅንነት እባኮ ለሁሉም እንዲደርስ share ያድርጉ
👇👇👇👇👇👇
@liulzemaryam
@liulzemaryam
@liulzemaryam
☝☝☝☝☝☝☝
መኖር አይደለም ወይ?
* * * * * *
ህያውነት እምቢ ልሁን የሙት ወዳጅ
የት ደርሶ ያውቅና? ትንሳኤን አሳዳጅ::
እምቢ ባይ ትንሳኤ
አርፎ መተኛት ነው ሙት የለው ጉባኤ::
ኗሪ ነው ጣጠኛ
አንዴ በጉባኤ
አንዴ በሱባኤ
የሚጨቀጭቀው የገዛ ናላውን
ቢጠየቅ ላይመለስ ትናንት የበላውን፡፡
ኗሪ ነው ጣጠኛ
አንዴ በዕምነቱ
አንዴ በእውነቱ
አንዴ በዕውቀቱ
እየቀባጠረ ስሌት መሳይ ተረት
ሞቱን ይራገማል የሽረት የወረት፡፡
በትርጉም በቃላት መኖር ከሚጠብህ
ሞት እንኳ በገባህ ትንሳኤው ቀርቶብህ::
ሞትህን ነው ማጥበቅ ደጉን ወዳጅህን
ማሳመርስ ጠርጎ መቃብር ደጅህን
እሱ ጋር ጽናበት
መቃብርም መቅደስ ነው መኖር ለቻለበት፡፡
እንዲያው ላመል እንጂ ሞት የምንፈራ
መኖር አይደለም ወይ? የሰው ልጅ መከራ...
➤ከወደዱት በቅንነት ይቀላቀሉን!
👇👇👇👇👇👇
@liulzemaryam
@liulzemaryam
@liulzemaryam
☝☝☝☝☝☝☝
ኤልያስ ሽታኹን
* * * * * *
እኔ
በፀጉሮችሽ መሐል እልፍ ፂም ባገኝም
የት ነበረች ብዬ ሳስብ አልገኝም
እኔ
የሺ ወንድ ጠረን ብስብም ከአንገትሽ
እከራከራለሁ አይደለም ካንጀትሽ
እኔ
በጡቶችሽ ጫፎች እያየሁ አሻራ
እጠርግልሻለሁ ቆጥሬ እንዳቧራ
ይልቅስ የእኔ
ስጋቴ
ፍርሃቴ
ያ ሁሉ ተባዕት እንዳያስጨንቁሽ
ያ ሁሉ ተባዕት ቀምሰው እንዳይርቁሽ
የሚያብሰከሰከኝ ሲስሙ እንዳያንቁሽ
(ነበር)
እኔ
ሁሉን ደስታ አይተሽ
እንደፀሀይ ገላ ሙቀሽ
ስትጨርሺ
እንዳላይሽ አዝነሽ
እንዳንላይሽ ደርቀሽ
(ነበር)
እንጂ
ያዘንሽ ቀንም ከአጠገብሽ አለሁ
የደስታሽን ቀብር አብሬ እውላለሁ
ያንቺን የሀዘን ቀን እንደኔ ቆጥሬ
እንጀመር እላለሁ መውደድን ከዛሬ
ከዛሬ
ከአሁን
ከቅፅበት
ህይወት ስታበቃ እኛ እንጀምረበት
እላለሁ፡፡
እላለሁ
እንዳዲስ እንጀምር እንዳልተለመደው
ይሰፋል እላለሁ የተቀዳደደው
ይፀናል እላለሁ የተንገዳገደው
እላለሁ፡፡
እንደማቱሳላ
አኑረኝ
ቀኔን ሳላሰላ
አክርመኝ፡፡
ላቧን እስክትጨርስ
በወንድ እንክትርስ
ዓይኗ እስከሚሟሟ
እስከሚደባለቅ እውንና ህልሟ
አኑረኝ እላለሁ
አክረመኝ እላለሁ
እድሜ ስጠኝ ብዬ እለማመናለሁ
ለምን
ሁሉም የጣለሽ ቀን እኔ አነሳሻለሁ፡፡
(እስከዛ ግን አለሁ)
➤ከወደዱት በቅንነት ይቀላቀሉን!
👇👇👇👇👇👇
@liulzemaryam
@liulzemaryam
@liulzemaryam
☝☝☝☝☝☝☝
* * * * * * *
አንቺን በሰማሁት ብሰማው አምላኬን
ዓለም ባላወቀኝ ቁመትና መልኬን፡፡
የቀበርኩትን ልብ እንዳይነቃ በዛር
ናፍቀኸኛል ስትይ ነቃ እንዳላዛር
ነቅቼልሻለሁ
ቀጣዩ ምንድነው?
ናፈቀኸኛል
ናፍቀኸኛል
ናፍቀኸኛል መባል
ታውቂያለሽ ያባባል::
የወንድ ልጅ ነገር እስከዚህ ይሞኛል
አታምኚኝም እንጂ
ናፍቀኸኛል መባል ራሱ ናፍቆኛል፡፡
ልተኛበት አንዴ ቃልሽን መልሽው
እንቅልፌን ወስዶታል ናፈቀኸኛል ያልሽው፡፡
➤ከወደዱት በቅንነት ይቀላቀሉን!
👇👇👇👇👇👇
@liulzemaryam
@liulzemaryam
@liulzemaryam
☝☝☝☝☝☝☝
#አንቺ ባለ ዶሮ
እስቲ ልጠይቅሽ ንገሪኝ ግድ የለም
ይሄ ሞያሽ ምንጩ ከእናትሽ አይደለም
መመጠን መከለስ
ማጠብ ማቁላላቱን በሙሉ ትተሽው
ማረዱን ብቻ
መገንጠሉን ብቻ.......ከወዴት ተማርሽው?
➤ከወደዱት በቅንነት ይቀላቀሉን!
👇👇👇👇👇👇
@liulzemaryam
@liulzemaryam
@liulzemaryam
☝☝☝☝☝☝☝
✅አበበና ጫላ
አጀንዳ ስታጣ ፣ በስም አትጣላ!
አንተም ጩቤ ጨብጥ ፣ አንተም በሶ ብላ🤪
ጨቡዴ ሁን ሀጎስ ፣ አቶቴም ሁን ሺፋ
ማንም ይበሉህ ማን ፣ ሲጠሩህ አትጥፋ
አቤት በል በኩራት ፣ ክብርህን አትጣው
መልአክ ቢሆንም ፣ ስምን የሚያወጣው
እኛ ግን እኛ ነን ፣ ሀያል ያልበገረን
አለማወቅ እንጂ ፣ የሚያከራክረን
እንዳልተገዛን ነው ፣ ስማችን ሚነግረን።
።።።
አሁን ለምሳሌ
ምኒሊክ ተወልዶ ፣ ባይጠገን ቅስሜ
ምኒልክ ተወልዶ ፣ ባይፈታ ህልሜ
በላቶቪች ነበር ፣ በላይ ሚሉት ስሜ!
➤ከወደዱት በቅንነት ይቀላቀሉን!
👇👇👇👇👇👇
@liulzemaryam
@liulzemaryam
@liulzemaryam
☝☝☝☝☝☝☝
"ደህና ነህ አትበይኝ"
ደህና መሆን ማለት
በጭንቀት ተራራ በናፍቆት ቁልቁለት
ድካም በበዛብት በብቸኝነት ቤት
መዳከር አይደለም....
ደህና መሆን ማለት....
ሣቅሽ በሌለበት በተቆጣ ሀገር
ደሥታ በቸገረው በሚያሣዝን ሠፈር
መንደርተኛ ተብሎ መቆጠር አይደለም
ደህና መሆን ማለት.....
ከተትረፈረፈው ከሚማርክ ገላ
ወይም ከሚያሠክረው ከጠላው አተላ
አንችን እያሠቡ መጎንጨት አይደለም
ደህና መሆን ማለት....
የትም በማያደርሥ መንገድ መመላለሥ
በማታውቂው ሥፍራ ትኖሪያለሽ ብሎ
...... ..........ሀገር ምድሩን ማሠሥ
መቅበዝበዝ አይደለም.....
ደህና መሆን ማለት
ከ ጫጫታ መሀል...
ፍዝዝ ብሎ ቁሞ ድምፅሽን መናፈቅ
አንቺን እያሠቡ...
ውብ ተፈጥሮን ትቶ ፈራሽ ጣኦት ማድነቅ
መሥለምለም አይደለም..
እናማ የኔአለም..
ደህና ነህ?? እያልሽኝ ትመጫለሽ እያልኩ
አንቺን እየጠበኩ...
አንቺን ያሣፈረ መርከብ የሌለበት
ዕልፍ አባይ ጎረፈ
ጠረንሽን ያልያዘ ዕልፍ አየር ነፈሠ
ዕልፍ ቀን አለፈ
.
.
እናም ቃሌን ሥሚ
ደህና ነህ እያልሽኝ ዝምምምም ከሆነ መልሤ
ዝምታየን ሥሚ...
ደህና ባልሆነ ሀገር..
መቅረትሽ ሢጨመር...
ደህና ነኝ እያለ
እንዴት ልቤ ዋሽቶ ምላሤ ይናገር!!
➤ከወደዱት በቅንነት ይቀላቀሉን!
👇👇👇👇👇👇
@liulzemaryam
@liulzemaryam
@liulzemaryam
☝☝☝☝☝☝☝
ያንን ለሊት ልታነጊ ከድቅድቅ ስር
ስታመሺ
ጨዋነቱ መች ጎሎ ነው ዝም ያለሽን
ምትረብሺ
( አቤት አንቺስ )
ካፈጣጠር ብዙ እርቀሽ መመለስን
ስትሰውሪ
ክንፍም አለሽ አዎ አውቃለው በእርምጃ
ነው የምትበሪ
(አጀብ ለኔ)
ከጥላሽ ጋር ውል የገባው መገለጥሽ
ሚናፍቀኝ
ሁሉንሽም አወኩኝ ስል ፍፁምነት
ሚጨርሰኝ
አወይ ለኔ....
አንቺን ብዬ ዳር ለያዝኩኝ
መመለስሽን ፍለጋ መሄድሽን የቀጠርኩኝ
መጨረስ ነሽ ዝንተ አለሙን
የመንጠፍጠፍ መውረድ ደራሽ
ሊያሳይ ነው የከተብሽ ገነት አይደል
ያንቺ ስፍራሽ
የማለዳ የወፍ ዜማ ጉም የያዛት ነሽ
ወገግታ
የመሳካት ነሽ አንኳሩ የስለቴ ዋና ቦታ
ስፀልይ ነው የምጀግን ስረጭሽ ነው
ምበረታ
ፀበል ፈውስ ለድክመቴ የአምላክ ቃሉን
ማስታወሻ
የእኔ እምነት ትክክል ነው የክርክር
ማጣቀሻ
የመአበል የዝምታው የማለቆች
መንቀራፈፍ
ወጀብሽን ስታበዢ በኪዳንሽ የምንሳፈፍ
መውረድ ነፅቶ መበከልን እዛ ጥሎ
ከደግ ጋር እያወጉ ቅድ ስናን ተመስሎ
ደሞ ደርበብ መቀዛቀዝ
ከብዙ ጋር ምንም አለ በመድመቅ
ውስጥ ሚደበዝዝ
ከሰራሽኝ ሰው መሆን ላይ አፍቃሪነት
ሲሽኮረመም
የኔን ማለፍ ፈቅጄ ነው በጣሮች ውስጥ
አንቺን ማክም
****************
(ካሊድ አቅሉ)
➤ከወደዱት በቅንነት ይቀላቀሉን!
👇👇👇👇👇👇
@liulzemaryam
@liulzemaryam
@liulzemaryam
☝☝☝☝☝☝☝
#ለካስ
ማበጠር ቸግሮኝ ገለባን ከፍሬ፣
እንዲው እንደባከንኩ መልስ አጥቼ ኖሬ፣
ለዚው ጥያቄዬ ለሚወብቅና ለሚያንቀጠቅጠኝ፣
ተመስገን ነው ዛሬ ግዜ ምላሽ ሰጠኝ።
፡
፡
ይኸው የግዜው መልስ ...
፡
፡
ስንዴን ከእንክርዳዱ የምንለይባቸው
ገንዘብና ዝናም ለካስ ወንፊት ናቸው።
#ሄኖክ_ብርሃኑ.....✍
➤ከወደዱት በቅንነት ይቀላቀሉን!
👇👇👇👇👇👇
@liulzemaryam
@liulzemaryam
@liulzemaryam
☝☝☝☝☝☝☝