livurlif | Other

Telegram-канал livurlif - Live your life ሕይወትህን ኑራት

18499

Everyone in this world created for a reason it's up to us to find out why and work for it and serve the universe. Work smarter❗ Stay positive and Rich❗ 🎖

Subscribe to a channel

Live your life ሕይወትህን ኑራት

መጠበቅ በጣም ከባድ ነገር ነው...

⭐️ባል እና ሚስት ልጅ ለመውለድ አስበው:: ፈጣሪያቸውን ለምነው ከብዙ ጥረት በኃላ ሚስት ማርገዝዋ ሲታወቅ ትልቅ ደስታን ይጭራል:: ግን ሁሉም ገና መጀመሩ ነው ረጅም ጉዞ አለ... 9 ወራትን መጠበቅ አለባቸው ሁለቱም:: ምንም ያህል ቢጓጉም ያልጊዜው ሆዷን ቀደው ልጁን ሊያወጡት አይሞክሩም አይችሉምም:: እና ለስኬት የሚያስፈልጉ እንደ ማንኛውም ባህሪዎች ወይም ልማዶች መጠበቅ አንዱ ነው:: ለዛም መጠበቅን መለማመድ በጣም አስፈላጊ ነው :: ቀላል ነገር አይደልም አንዳንዴ ራስን ማሞኘት ይመስላል ምንም በሌለበት ትልቅ ነገር ተመኝቶ እየሰሩ መጠበቅ::

⭐️ መጠበቅ ወስጥ ያለው ትልቅ ነገር እምነት ነው:: እምነት ደሞ ማረጋገጥን አይፍልግም:: ካረጋገጥን በኃላ የሚመጣ እምነት እምነት አይባልም:: እምነት ያለምንም ማረጋገጫ ይሚቀድም ነገር ነው::
..... ....አምኖ ወጤት እስኪመጣ ጠብቆ ለመቆየት ደሞ ፅናት ይጠይቃል:: አንዳንዴ ምንም ተስፋ ሰጪ ነገር እናጣለን እና የእውነት ፅናታችን እና እምነታችን ሚፈተነው ያኔ ነው:: ምን ያህል ነው መጓዝ የምንችለው?  ምን ያህል ነው መጠበቅ ምንችለው?

አንድ ተረት ልንገራቹ....😊

👵ተረት ተረት👴
..........

⭐️ ሁለት ዋሽንት🪈🪈 ሚጫወቱ ልጆች ነበሩ:: እና ሁለቱም በጣም የሚያምር እና መሳጭ ሙዚቃዎችን 🎶🎶🎵ይጫወቱ ነበር... ነገር ግን በተለየ መልኩ አንደኛው ልጅ ዋሽንቱን በሚጫወትበት ሰዓት ሁሌም 🌧🌧ዝናብ🌧🌧 ይዘንብ ነበር እና ሰዉ ይህ ነገር በጣም ስለሚያስደምመው እና ስለሚደንቀው እሱን ልጅ አብልጠው ይወዱት ነበር :: ግን ሁሌም ጥያቄ🤔 ይሆንባቸዋል እንዴት ተምሳሳይ ነገር እየተጫወቱ የሁለቱም ሙዚቃ እያማረ ለአንዱ እየዘነበ ለአንዱ አይዘንብም?  እና የሆነ እለት ዋሽንት ሲጫወት የሚዘንብለትን ልጅ ለመጠየቅ ወሰኑ የተለየ የሚያረገው ነገር ካለ ለማወቅ... እናም ጠየቁት... የልጁ መልስ በጣም አስገራሚ ነበር:: እኔኮ የተለየ ነገር ስለማረግ አይደለም የሚዘንበው: ዋሽንቴን የምጫወተው እስኪዘንብ ድረስ ስልሆነ ነው:: አላቸው ይባላል... በዚህ ልጅ እና በዛኛው ያለው ልዩነት በፅናት የመጠበቅ እና ያለመጠበቅ ነው::

💡@livurlif
💡@livurlif
💡@livurlif

ሼር ማረግ መብታቹ ነው 😊

Читать полностью…

Live your life ሕይወትህን ኑራት

ሰህተት አንድን ከዚህ በፊት አድርገነው የማናውቀውን(እንዴት እንደሚደረግ የማናውቀውን) ነገር ለማድረግ በምንሞክርበት ሰዓት የሚፈጠር እክል ሲሆን
ጥፋት ደሞ አንድ ሰው እያወቀ ትክክል ያልሆነ ነገር ሲሰራ የሚፈጠር ክስተት ነው::

የሰው ልጅ ባህሪዎች ብዙ ናቸው::ተሳሳችነቱ እና አጥፊነቱ ከነሱ መሃል ናቸው:: ሁለቱም ትክክል ያለመሆንን ሁኔታ ሲያሳዩ የመጀመሪያው አብዛኛው ሰው ላይ የሚታይ ነገር አይደለም ምክንያቱም አዲስ ነገር ለመሞከርብዙ ሰው ስለሚፈራ አርፎ ጎመን በጤና ብሎ ካለማወቁ ጋር መቀመጥን ይመርጣል ወይም የማውቀው በቂዬ ነው ባይ ነው::

ሁለተኛው በብዛት በተደጋጋሚ ሰዎች ላይ የሚታይ ባህሪ ነው:: ራሳችንን እንፈትሽ እስኪ ሕይወታችን ላይ ትክክል እንዳልሆነ ውስጣችን እያወቀ (እየነገረን) ግን ማድረጋችንን የምንቀጥለው ምን ያህል ነገር አለ?? ራሳችንን ሳንዋሽ ከፈተሽን የምናረገ አብዛኛው ነገር እንደዛ እንደሆነ እንረዳለን:: ለምን ግን ያንን ነገር እኮ ማድረግ አንፈልግም በማረጋችንም ደስተኛ አይደለንም ካለፈ በኃላ ብዙ ጊዜ ራሳችንን ስንወቅስ እንገኛለን:: ታዲያ ለምንድነው የምናረገው??
ሕይወታችን ላይ የምናከናውነው ተግባራችን አብዛኛው የፈለግነው ሳይሆን ያመንበት ነው የሚሆነው:: እዚህጋ እንዴ እኔ እኮ ያኛው ነገር ትክክል እንዳልሆነ አምኛለሁ ልንል እንችላለን:: ነገር ግን ትክክል እንዳልሆንን አውቀናል እንጂ አላመንም:: ምንድነው ልዩነታቸው...?
በኑሮአችን ከ75% በላይ የሚሆነው ተግባራችን የሚሆነው አስበን በምናረገው ሳይሆን ባመነበት እና ወስጣችን በሰረፀው (program) በተደርገው መልኩ ነው ይለናል ቤተሰብ ሳይንስ:: ማለት...? ሰፊ ነው ታሪኩ ከጀመርነው ማለቂያ የለውም ለናንተ ልተወው እና እንድትጎግሉት...
አብዛኛው ተግባራችን አስበን በምናረገው ካልሆነ የሚወሰነው⭐️ ልብ ⭐️ ሊባል የሚገባ ነገር ነው ማለት ነው:: ያመንበትን ነገር ውስጣችን የሰረፀውን ራሳችንን ወደሁዋላ አርገን ልናጤነው ይገባል ማለት ነው :: ምን አይነት ሃሳቦች እምነቶች አመለካከቶች ናቸው ውስጣችን ያሉት...? ስለምናረገው ነገር ያለን ሃሳብ እምነት አመለካከት ላይ ይወስናል ድርጊታችን ወይም የሚመጣው ውጤት ወደ ውስጥ ጠልቆ ማየትን ይጠይቃል:: ቆም ብሎ ምንድነው እየተካሄደ ያለው🤔🤔 ራስን መፈተሽ🙇🙇‍♀... ዝም ብለን ራሳችንን እናጥናው ምን ያህሉ የምንፈልገው ነው ምን ያህሉ የማንፈልገው? በዛን ሰዓት ያለንን ስሜት አመለካከት እንቃኘው ራሳችንን jugde ሳናረግ ጥፋቶቻችንን መቃኘት ልማድ ይኑረን እና ቀስ🚶‍♀🚶‍♀🚶🚶 በቀስ ደሞ ትክክል እንዳልሆነ እና ምን ያህል አፀያፊ ተግባር እንደሆነ ለራስ መንገር በተደጋጋሚ... በተደጋጋሚ ... "እዚህ ጋር ወቀሳ ሳይሆን እንደ ምክር ቢጤ ብናረገው"........በመቀጠል እንዴት መቀየር እንደሚቻል መፍትሄ ወይም መፍቻ ቁልፎችን🔑🔑🗝🗝🔑🗝 ማስቀመጥ:: በሚቀጥለው ተመሳሳይ ነገር ሲፈፀም ትኩረት በመስጠት ነገሩን ረጋ ብሎ ማየት እና ከመክፈቻ ቁልፎቹ መሃል አንዱን🗝 በማንሳት ቀሎ የታየንን መክፈት:: ሙሉ በሙሉ በአንድ ሙከራ ከጥፋት መፅዳት የማይታሰብ ነገር እንደሆነ ግልፅ ነው...ግን በሆነ መንገድ ጥፋቱን መቀነስ::

ይህን ሂደት እየደጋገምን በሁሉም ቁልፎች🔑🔑🗝🗝🔑🗝 ሁሉንም ጉድለት ከፍተን ማረም እስክንችል ድረስ መቀጠል ከዛም አዲስ እምነቶች እና አመለካከቶችን መገንባት:: ባለፍነው መንገድ ተንተርሰን አዲሱ እምነት ሕይወት እስኪዘራ ድረስ በሁኔታዎች ሁሉ ለራስ እየደጋገሙ መንገር በመጨረሻም ሳናውቀው ራሳችንን ከጥፋት ርቀን ወይም የምንፈልገውን ነገር በመተግበር ላይ እናገኘዋለን::

ቀላል አይደለም
.....................................ሒደት ነው
ተስፋ ባለመቁረጥ የሚያረጉት የፅናት ጉዞ...
እያንዳንዱ ለውጥ ይህንን ሒደት ያስተናግዳል በጣም ባጭሩ...
በመሃል አቋርጠን አይሆንም ብንል አዎ አይሆንም ምክንያቱም አልጨረስነውማ:: አንድ ሰው መድረሻውን የሆነ ቦታ አርጎ መንገድ ጀምሮ ሲጓዝ ከርሞ ደክሞት ወይ በሆነ ምክንያት አቋርጦ ቢመለስ እዛ ቦታ መድረስ አይቻልም ማለት ይቻላል? ይህ ነው በአብዛኛው እየተፈጠረ ያለው

እና መልካም ጉዞ ከፅናት ጋር ... ፅናት ጎረቤታቹን አይደለም 😊❤️

💡@livurlif
💡@livurlif
💡@livurlif

ሼር ማረግ መብታቹ ነው 😊

Читать полностью…

Live your life ሕይወትህን ኑራት

@livurlif

Читать полностью…

Live your life ሕይወትህን ኑራት

@livurlif

Читать полностью…

Live your life ሕይወትህን ኑራት

📍የተሻለ አለህ

በአውሎ ንፋስ ውስጥ ብትሆን፣ ዶፍ ዝናብ ቢወርድብህ፣ ዋጋህ ያነሰበት፣ መኖርህ የማይቆጠርበት፣ አበርክቶትህ የማይታይበት፣ ስራህ የማያፈራበት፣ ማንነትህ የማይመረጥበት ስፍራ ብትኖር እንኳን ፈጣሪ አብሮህ ካለ ሁሌም የተሻለ ከፍ ያለ ነገር አለህ።

🔷ምንም እንኳን እምነታችን ቢጎድል፣ ክፋታችን ቢበዛ፣ ሃሳባችን ቢያንስ፣ ምግባራችን የወረደ፣ ስራችንም አሳዛኝ ቢሆንም ፈጣሪ ግን ጥሎ አይጥለንም።፣ ትቶ አይተወንም ሁሌም ይመለከተናልና መቼም ችላ አይለንም። የተውን ሰዎች ይኖራሉ፣ ያገለሉን፣ የተጠየፉን እንዲሁ እንደዋዛም የናቁን ሰዎች ይኖራሉ ዋናው ነገር ግን በፈጠረን አለመገፋታችን አለመረሳታችን ነው።

♦️የተሻለ አለህ! ከዛሬው የላቀ፣ ከትናንት የገዘፈ፣ ከአሁንህ ያየለና ከፍ ያለ ስፍራ ይኖርሃል። የማይቀየሩ የሚመስሉ ከባድ ሁኔታዎች ይቀየራሉ፤ ይወርዱ የማይመስሉ ሸክሞች፣ ይፈቱ ያልመሰሉ ችግሮች፣ ይስተካከሉ ያልመሰሉ ውጥንቅጦች ይወርዳሉ፣ ይፈታሉ፣ ይስተካከሉ።

እምነትህ ቢፈተን ግራ አትጋባ ይልቅ ለተሻለ ክብር እንደታጨህ አስተውል፤ በፈተናህ ብዛት አትደናገር ይልቅ የድልህ ቀን ቅርብ እንደሆነ አስተውል። በጫናዎች ብዛት የማትሸበር፣ ለምድራዊ ፈተና የማትበገር፣ ከፈጣሪህ ውጪ እንዳልሆንክ አስተውል።

🔷አንዳንዴ ማሳለፍ እየቻልን አቅፈናቸው የምንቀጥላቸው ብዙ ኮተቶቻችን ጣእሙን ማየት እንዳንችል ሁሉ ነገራችንን ዘግተንባቸዋል። ለማማረር እንጂ ለማመስገን ስንፈናል ለማዘን እንጂ ለመደሰት ጉልበት አጠተናል። መቆየት በማይገባን ቦታ ላይ በመቆማችን ማሳለፍ የሚገባንን አላፊ ሃሳቦችን እንዳያልፋ መንገድ ዘግተንባቸዋል እሰኪ ነቅነቅ እንበል እናሳልፋቸው የሚመጡት ሁሉ እንደአመጣጣቸው እንሸኛቸው አኛም ከቆምንበት አስተሳሰብ ስናልፍ ሁሉም ጊዜያዊ መሆኑን እናውቃለን።

ሁሉም ያልፍ የለ ትላንትናም አልፏል ዘሬም ታልፋለች ነገም ትቀጥላለች እኔም አንተም እናልፋለን ምክንያቱም ሁሉም ያልፋል።ሁሉን የፈጠረ፣ ሁሉን የያዘ፣ በሁሉ ውስጥ ያለው አምላክህ ባንተ ውስጥ ስለመኖሩ አትጠራጠር፤ ለተሻለው ስፍራ እንደሚያበቃህ እምነት ይኑርህ።

🔑ማሰብ ላይ በርታ፤ መስራት ላይ ጠንክር፣ አምላክህን ይዘህ ፈተናህን ተጋፈጥ፣ በፀሎትህ ፅና፣ ምስጋናህን ደጋግመህ አቅርብ፣ ካንተ በላይ የሚሰራብህ፣ ተአምር የሚያደርግብህ ፈጣሪህ አብሮህ እንደሆነ አስብ። ብቻህን የሆንክ ቢመስልህ እርሱ ከጎንህ አለ፤ የተገፋህ ቢመስልህ በእርሱ እቅፍ ውስጥ ነህ፤ የወደክ ቢመስልህ እርሱ ያነሳሃል፤ በሚገባህ ስፍራም በክብር ያቆምሃል።

ውብ አሁን ❤️

@EthioHumanity
@EthioHumanity

✍@EthioHumanitybot

Читать полностью…

Live your life ሕይወትህን ኑራት

@livurlif

Читать полностью…

Live your life ሕይወትህን ኑራት

@livurlif

Читать полностью…

Live your life ሕይወትህን ኑራት

@livurlif

Читать полностью…

Live your life ሕይወትህን ኑራት

🫧🫧🫧🫧🫧🫧🫧🫧🫧🫧🫧🫧🫧🫧🫧🫧🫧

አንዳዴ በእምነት ፅንቶ እንደመቆየት ሚከብድ ነገር የለም ጭንቅላት ሚሰብከውን አሉታዊ ስብከት አለማዳምጥ እና ወድፊት መጓዝ....😑
🕳🕳🕳🕳🕳🕳🕳🕳🕳🕳🕳🕳🕳🕳🕳🕳
ምንም እንኳን ነገሮች ቢከብዱ ብታጣ እጅህ ባዶ ቢሆንም ወደ ህልሜ እየትቃረብኩ ነው ብሎ ማመን? Wooow በጣም ትልቅ ፅናትን ይጠይቃል።
🕳🕳🕳🕳🕳🕳🕳🕳🕳🕳🕳🕳🕳🕳🕳🕳
ግን የሚገርመው ወሳኙ እና አስፈላጊው እምነት ነገሮች አልጋ ባልጋ በሆኑበት ጊዜ ያለን ሳይሆን
ጭንቅላታችን ህልማችን ሊሳካ የማይችልበትን የሚታይ የሆኑ በጣም ብዙ ምክኒያቶች በሚያሳየን ሰአት ይቻላል ብለን የማይታዩትን ምክንያቶች በማየት ትንሿን ብርሃን አይተን በኣላማችን መፅናት ስንችል ነው ከምንፈልገው እና ከሚገባን ስኬት የምንደርሰው።


@livurlif
@livurlif
@livurlif

Читать полностью…

Live your life ሕይወትህን ኑራት

📍ወዳጄ ሆይ

ሥር የሰደዱ ዛፎች ነፋስን ይቋቋማሉ ፣ ወደ ታች የጠለቁ መሠረቶች ብዙ ፎቅ ይሸከማሉ ። ሰውም በሳል ሲሆን በፈተና ይጸናል ፣ ፈተናና ነፋስ ያልፋሉና ። ነፋሱ ዘንበል ቢያደርግህም እንዲሰብርህ መፍቀድ የለብህም ። ብዙ ጫናዎችን ለመሸከም እውቀትና ማስተዋልን ገንዘብ አድርግ ። አንተም እንደዛፉ ስር ስደድ ጠንካራነት እውቀት አለው ፣ በጥበብ ይናገራል ፤ ተግባር አለው ። ጠንካራነት ስሜት ሳይሆን ተግባር ፣ ፉከራ ሳይሆን ድርጊት ነው ። ጠንካራነት ሞራልም ምግባርም ነው።

📍ወዳጄ ሆይ

ፊት የልብ አደባባይነውና ሁሉን ቅሬታህን ፊትህ ላይ አታስነብብ፡፡ ጠላቶችህ ፊትህን እንጂ ልብህን እንዲያዩ አትፍቀድ፡፡ ለስድባቸው ስድብን አትመልስ ጆሮ ሰጥቼ ሰምቻችኀለሁ ማለት ነውና፡፡ ለአሳማሚዎችህ በቸኛው ማለፊያ ታምሞ አለመጠበቅ ነው ። ታመህ ካልጠበቀቻው ፣ ጆሮ ሰትጠህ ዝቅ ካላልክላቸው የሚያሳምምህ የለምና፡፡ ከራስህ ጋር ሳትመክር ከሰው ጋር አትመካከር፡፡ ለአንድ ሀሳብ የሶስት ቀን እድሜ ስጠው፡፡ ባዕድ ባለበት ስለቤትህ አታውራ፡፡  ለግቢህ አጥር ፣ለቤትህ በር፣ለህይወትህ ሚስጥር ይኑርህ፡፡ የተሻልክ ሳይሆን የበለጥክ ሁን፡፡

📍ወዳጄ ሆይ

መሬትህ በሚሸከመው መጠን ቤትህን ሥራ ፣ ወዳጅህ በሚችለው መጠን ምሥጢር ንገረው ፣ ተማሪህ ባደገበት መጠን መግበው ። የሌላው የሆነችውን ሴት ላንተ አትመኝ ። ያንን ጥላ ስትመጣ አንተን ጥላህ መሄድ እንደምትችል እያስተማርሃት ነው ። አንቺም የሌላውን ባለትዳር አትመኚ ።

📍ወዳጄ ሆይ

ብትታመም በአገርህ ትታመማለህ ። አገርህ የታመመች ከሆነች ግን ዓለም ዝግ ይሆንብሃል ። ተሰደህም ለመከበር አገር ያስፈልግሃል ። ከሰላም የበለጠ ሀብት ፣ ከማስተዋል የበለጠ ሥልጣኔ ፣ ከፍቅር የበለጠ ደስታ የለም ። ያለ ፈጣሪ እየተስፋፉ ያሉ ሰዎች እየጠበቡ ነው ። ልብስ ጸድቶ ልብ ከቆሸሸ የመንፈስ ነጻነት ገና አልመጣም ። የድሮ ሰው ልቡ ንጹሕ ፣ ልብሱ አዳፋ ነበር ። የዛሬ ልጅ ልብሱ ንጹሕ ፣ ልቡ ሸርታታ ነው

📍ወዳጄ ሆይ

የሰብዊነት ሥራ ለሰው ሁሉ የሚደረግ የደግነት ስራ ነው፣ ደግ ለመሆን ጥግ አትያዝ ። ከሥርህ ያለው አንተ የማትችለውን የሚችልልህ ነውና አክብረው ። ቆጥረህ ከሰጠህ ስጦታህ ይረክሳል ። ደብቀህ ከሰጠህ ስጦታህ ሲወራ ይኖራል ። ከፍ ስትል ልታይ ካልክ ሁሉም ሰው ስትወድቅ ያይሃል ። በከፈትክለት መጠን ጠላት ይገባል ። ሰይጣን አስገድዶ ሳይሆን አዘናግቶ የሚገድል ጠላት ነው ።

💡እናም ወዳጄ

የታወከ ሌሊት ሲገጥምህ በሰላም ስላደርክባቸው ሌሊቶች አለማመስገንህን አስብ ። ቀኑ መብትህ ሳይሆን ስጦታህ ነውና አመስግንበት ። እሰይ ነጋ ማለት ሲገባህ ደሞ ነጋ አትበል ።ሲያነጋልህ ምንም ክፈያ ላላስከፈለህ ጌታ የማለዳ ምስጋና ለማቅረብ አትዘግይ ። ወጥቶ የመግባት ዋጋው ትልቅ ነውና የምሽት ጸሎትህንም አታስታጉል ። እያጣጣርክ ስለ ጤና ከመጸለይ በጤናህ ፈጣሪህን አመስግን ።

ውብ ጊዜ❤️

@Ethiohumanity
@Ethiohumanity

✍ @EthiohumanityBot

Читать полностью…

Live your life ሕይወትህን ኑራት

〰〰〰〰〰〰〰〰〰〰〰〰〰〰〰

☀️ መቀበል የቻለ ወይም የተለማመደ ሰው ብልህ የሆነ ሰው ነው በዬ አምናለው ለማለት የፈልኩት ያለበትን ሁኔታ ያልበትን ነገር የተሰጠውን ሰውነት የተሰጠውን ማንነት የተሰጠውን ቤተሰብ ያለበተን አካባቢ ያለበተን መኖሪያ ቤት የተሠጠውን አየር የሚሰራውን ሥራ ትዳሩን የተሰጡትን ልጆች የተለያዩ ሁኔታዎች ሊሆኑ ይችላሉ የማንፈልገው ሁኔታ እንኳን ቢሆን የሚታየን ነገር የሚያማርር ብቻ እንኳን ቢሆን እነሱን መቀበል መቻል የኖርብናል

⭐️የመጀምሪያው መክንያት
ምንም አይነት አስከፊ ሁኔታ ላይ ብንሆን እኛ ያለን ነገር ሕልም የሆነባቸው እና እንዲኖራቸው ሚፀልዩ ብዙ ሰዎች አሉ ያ ማለት በእጃችን ትልቅ ሀብት እንዳለ ሊሰማን እና ልናመሰግን ይገባል
ሁለተኛ ደግሞ ወደምንፈልገው ቦታ ወይም ሁኔታ ለመድረስ ያልንበተን ቦታ እና ሁኔታ መቀበል እና መረዳት ይኖርብናል ምክንያቱም አሁን ባለን ነገር ተጠቅመን ነው ለወደፊት እንዲኖረን የምንሻውን የሌለንን ነገር መፍጠር የምንቸለው

☀️ መቀበላችን ያለንበትን ሁኔታ ለመቀየር ንፁህ አእምሮ እንዲኖረን ይርዳናል

☀️ ሁሉም ነገር የሆነበት ምክንያት አለው ነገርግን ምንም ነገር ቢሆን እኛን ለማደግ እንዲረዳን እንደ ማገልገያ መጠቀም መቻል እንጂ እያማረርን እንዲያዘቅጠን መፍቀድ አይኖርበንም

☀️ ካለብን ችግር ካለንበት ሁኔታ ለመሸሽ ከመሞክር ይለቅ ተቀብለነው ተጋፍጠነው ማለፍ መቻል ይኖርብናል

☀️ ከሁሉም በላይ ደግሞ አንደኛ ምክንያት በዬ ያስቀምተኩት ላይ ትኩረታችንን ብናረግ እመርጣለው ማለትም ምንም አይነት ሁኔታ ላይ ብንሆን ከኛ የባሰ ሁኔታ ላይ ያሉ በዙሃን አሉ እንሱን በማሰብ ለምቀየር ወይም የተሻለ ነገን ለመያዝ ያለንን ነገር ተቀብለን ላለን ነገር መስጋና ማቅረብ እንዳለብን መገንዘብ እና መለማመድ የኖርበናል
❤️❤️❤️ ያመስገነም የጨመርለታልና ❤️❤️❤️

@livurlif
@livurlif
@livurlif

Читать полностью…

Live your life ሕይወትህን ኑራት

〰〰〰〰〰〰〰〰〰〰〰〰〰〰〰〰

🔘 ሁሉም ድርጊት ራሱን በትዝታ መልክ መግለፁ እና የሰራነው ሰራ በትውስታ መልክ እንድሚመጣብን ግልፅ ነዉ

🔘 ለዛም አሁን እያደረግን እየሰራን ያለውን ነገር ልብ እንበለው መልካም ተግባር ነዉ ወይስ ተቃራኒው::

🔘 ከዛሬ የሆነ ቀን ወራት ወይም አመታት ቡሃላ ስናስታውሰው የምንደሰትበት ነዉ ወይስ ምናፍርበት?

🔴 እያንዳንዱን ድርጊታችንን ልብ እንበል

🔘 ስንቶቻችን ነን ካረግነዉ ነገር ትዝታ ጋር መላቀቅ ያቃተን ራሳችንን ይቅር ማለት ያቃተን?

🔘 አንድን ነገር ከመከወናችን በፊት ቆም ብለን እናስብ በዚህ ተግባሬ ኮራበታለው ወይስ አፍርበታለሁ

🔘 ከሆነ ቡሃላ ከመቀበል እና ራስን ይቅር ከማለት ወጪ መቀይር የምችለው ነገር አይኖርም:: አሁን ላይ ግን መምረጥ ይቻላል... 😊

መልካም አዳር

@livurlif
@livurlif
@livurlif

Читать полностью…

Live your life ሕይወትህን ኑራት

If you have your God by ur side that's all you need to have❤️
@livurlif

Читать полностью…

Live your life ሕይወትህን ኑራት

@livurlif

Читать полностью…

Live your life ሕይወትህን ኑራት

@livurlif

Читать полностью…

Live your life ሕይወትህን ኑራት

ልዩነት
ትልቁ ውበታችን ልዩነታችን ነው ባይ ነኝ:: በጣም ሰፊ ቃል ነው:: ጥቂቱን ብቻ እናንሳ እና አንተን የመሰለ አንድም ሰው እንደሌለ አስበህ ታቃለህ አንቺስ ውዴ..? አስባቹ ሊሆን ይችላል ግን ደግማቹ አስቡት እስኪ አንድም አንተን ወይም አንቺን የሚመስል የለም ልዩ ነህ /ልዩ ነሽ :: አሁን ላይ ትልቁ ወረርሽኝ ሌላውን ለመምሰል የሚደረግ ጥረት ነው :: መቼም የማይሳካ እያደር ህመም የሚፈጥር በሽታ:: ዓለም(አለምን እየወከሉ ያሉ የሆኑ ህዝቦች) ለብዙ ነገር ያስቀመጡት መስፈርት አለ:: እና አብዛኛው ሰው እሱን መስፈርት ለማሟላት እና ሙሉ ለመሆን እየሞኮረ ያለ ይመስለኛል:: እስኪ እኔ ማነኝ ምንድን ነውስ ሚያስደስተኝ ፍላጎቴስ ምንድነው...? እኔ እኔን የተቀበልኩ ቀን ነው ቀኑ ያበራልኝ ሴትነቴን መልኬን ቀለሜን ፅጉሬን አቋሜን ድምፄን መላው አካላቴን ማንነቴን... :: ሌላውን በመምሰል ወይም ለምን ይሄ እንድዛ አልሆነም ብሎ በማሰብ ብዙ ጊዜዬን የማባክን ሰው ነበርኩ:: ዓለሙም ባስቀመጠው መስፈርት ይሄ ይጎልሻል ይሄ ይቀራል ሊል ይሞክራል... Really ማነው ያለህ ቆይ ያልኩት ጊዜ ነው ነገር አለሙ የተቀየረው:: በራስ መተማመን ቀና ማለት መጣ አረ ልታይ ልታይ እራሱ ሳልል እቀራለው... አምላካችን የሰውን ልጅ አሳምረን ፈጠርነው ብሎ ሲያበቃ ማን ወንድ ነው ከሰው ላይ አቃቂር ሊያወጣ ሚነሳ...? ሁላችንም በልዩነታችን ውብ ነን:: ሌላን ለመምሰል በሞከርን ሰዓት ወረርሽኙ ያገኘናል::  ልዩ መሆን እንዴት ደስ ይላል በማንኛውም መንገድ በማንነት በሃሳብ በአመለካከት ባካሄድ በባህል በብሄር በዘር በሃይማኖት በቀለም...  በሁሉም ነገር

💡@livurlif
💡@livurlif
💡@livurlif

ሼር የማረግ መብታቹ በህግ የተጠበቀ ነው 😊

Читать полностью…

Live your life ሕይወትህን ኑራት

አንዳንድ ጊዜ ሁሉም አንድ ሆነው እኛ በምንለይበት ሰዓት የተሳሳት ነው እኛ እንደሆንን ይሰማናል:: ዞር ብለን ስናየው ደሞ የአላማችን ጥንካሬ እና ትልቅነት አስፈላጊነት ሁሉንም ነገር ሲሸፍን እናያለን:: አላማችን ብለን በያዝነው ጉዞ ላይ ተቃዋሚው ሲበዛ ይታያል:: እርግጠኛ መሆን ያለብህ ነገር አላማህ ከፈጣሪ ጋር የማያጋጭህ መሆኑን ብቻ ነው:: ሃሳብህ ከራስህ አልፎ ሌላውን ለመጥቀም ከሆነ በዓላማህ ፅና:: አንተ ብቻ ነህ ውስጥህ ያለውን የምታቀው እና ውጤቱም የሚታይህ:: ለምን ወይም እንዴት ማየት ተሳናቸው ብለህ ለማስረዳት አትሞክር:: ጉልበትህን መጨረስ ነው ትርፉ አንተ ካየከው ይበቃል:: የሚያስፈልገውም እሱ ነው ሁሉም ነገር ፈተና ነው:: አላማ ከፈጣሪ እስከሆነ ድረስ ምን ያህል ብቁ ነው ይህ ሰው ምን ያህልስ መሄድ ይችላል የእውነት ይፈልገዋል እየጠየቀ ያለውን የሚሉ እና የመሳሰሉ ጥያቄዎች ናቸው እየመጡ ያሉት በነዛ ተቃዋሚዎች ምክንያት:: አሁን ላይ ቢቃወሙህም ግን ወደመድረሻህ እያደረሱህ ነው በፅናት ከቀጠልክ:: አንድ አባባል አለ ሁሉንም ማስደሰት ከፈለክ መሪ ሳይሆን ice cream ሻጭ ሁን ይላል::

😊አመሰግናለሁ መልካም ጊዜ ❤️

💡 @livurlif
💡 @livurlif
💡 @livurlif

Читать полностью…

Live your life ሕይወትህን ኑራት

@livurlif

Читать полностью…

Live your life ሕይወትህን ኑራት

@livurlif

Читать полностью…

Live your life ሕይወትህን ኑራት

@livurlif

Читать полностью…

Live your life ሕይወትህን ኑራት

@livurlif

Читать полностью…

Live your life ሕይወትህን ኑራት

✨የውስጥህን ስሜት የምታቀው አንተ እና ፈጣሪህ ብቻ ናቹ አካባቢህ ላይ ያለው ሰው መረዳት ባለመቻሉ ብዙ አትዘንበት ከስንት አንድ በተመሳሳይ ሁኔታ ላይ ያለፈ ሰው ካገኘህ ልትረዳዱ ትችላላቹ እሱም ግን ደረጃ አለው

⚡️ሁላችንም በተለያየ ሁኔታ ላይ ማለፋችን አንዳንችን ከአንዳችን እንድንማር የተደረገ የፈጣሪ ስራ ይመስለኛል::

🔘 እኔ እንደተረዳሁት... እውነታውም ይመስለኛል...

✨ችግር ብለን በጠራነው ሁኔታ ውስጥ ማለፋችን እና ያለንበትን ሁኔታ ሚረዳ ሰው አለመኖሩም የፈጣሪ ስራ ይመስለኛል::

⚡️ወደሱ ፊታችንን አዙረን መፍትሄያችንን የምፍትሄዎች ሁሉ ባለቤት ከሆነው ከሱ እንድንጠይቅ በዛውም ዝምድናችንን እንድናጠነክር ፈልጎ ሳይሆን አይቀርም::

ምን ትላላችሁ...?


@livurlif
@livurlif
@livurlif

Читать полностью…

Live your life ሕይወትህን ኑራት

@livurlif

Читать полностью…

Live your life ሕይወትህን ኑራት

@livurlif

Читать полностью…

Live your life ሕይወትህን ኑራት

@livurlif

Читать полностью…

Live your life ሕይወትህን ኑራት

@livurlif

Читать полностью…

Live your life ሕይወትህን ኑራት

Just take the first step

@livurlif

Читать полностью…

Live your life ሕይወትህን ኑራት

@livurlif

Читать полностью…

Live your life ሕይወትህን ኑራት

Do you?

@livurlif

Читать полностью…

Live your life ሕይወትህን ኑራት

ምልካም ቀን ይሁንላችሁ
Have a blessed day😊
ክዌሎ ቃለመጠየቅ በተደረገለት ቦታዎች ሁሉ ማለት ይቻላል ደጋግሞ የሚያነሳትና ከራሱ የሕይወት ተሞክሮ አንጻር ትልቅ ቁምነገር ያላት አንዲት መልእክት አለችው
"አንድ ሰው በመጀመሪያ ደረጃ የልጅነት ህልሜ ይሳካል ብሎ ማመን አለበት" የሚለው ክዌሎ "ሲቀጥል ሕልምህን ለማሳካት የመጀመሪያውን እርምጃ ውሰድ:: ከዛ መላው ሁለንተና(universe) ህልምህን እንድታሳካ በጥምረት ሆኖ ያረብልሀ ይተባበርሃል" ይላል:: ለክዌሎ ሕልም እንዳይሳካ እንቅፋት የሚሆነው ነገር "የእወድቅ ይሆን ፍርሃት ነዉ" ይላል:: "እሱን አስወግድ" ሲል ይመክራል::
የ68 ዓመቱ ክዌሎ ከሞትክ በኃላ እንዴት መታወስ ትሻለህ ተብሎ ለቀረበለት ጥያቄ:
"እኔ ከሞትኩ በኃላ አለም እንዴትም አርጎ ቢያስታውሰኝ ግድ የለኝም:: ግን ስሞት መቃብሬ ላይ እንዲፃፍ የምፈልገውን ልንገርህ... He died while He is alive ( በመኖር ላይ ሳለ ሞተ ) የሚል ፅሁፍ ሀውልቴ ላይ እንዲሰፍር እፈልጋለሁ:: ምክንያቱም ምን መሰለህ" ይላል ስመጥሩ ደራሲ አብዛኛው ሰው የሚሞተው በቁሙ ነዉ:: ከመሞቱ በፊት"

Paulo Coelho the writer of "The alchemist"

ግሩም የአለማችን ታሪኮች ከተሰኘ መፅሐፍ የተወሰደ ገፅ 15

@livurlif

Читать полностью…
Subscribe to a channel