የማይጠገበው የሸይክ ሙሐመድ አንሲ ዳዕዋ ነገ ማለትም ጁሙዓ ረመዳን-5-1445 ዓ.ሒ ከቀኑ 7:30 youtube.com/@Islam_mindset ዩቲዩብ ቻናላችን ላይ ገብተው በጥሞና ብታዳምጡ ተጠቃሚ ይሆናሉ።
Читать полностью…ረመዳን - 3 (part-1)
የረመዳን ጉዞ
ረመዳን አይቆምም ይጓዛል! ነገር ግን እኛ አለመቆማችንን እርግጠኛ እንሁን። ምክንያቱም ረመዳን የመጨረሻይቱ ቀን ላይ አብረነው መጓዛችንን ይመሰክርልናል አልያም አለመጓዛችንን ይመሰክርብናል። በቀላሉ እንዳንሸወድ አብዘሀኞች እንደተሸወዱት ማለት ነው... ገና ነው ረመዳን ብለው ሳያስቡት እንዳለቀባቸው ማለት ነው። ከሰዓታቶቹ እና ከቀናቶቹ ጋር አብረን ከረመዳን ወር በኢባዳ እንጓዝ, ያኔ ነው ረመዳን እኛን የሚለውጠን...ካልሆነ ግን ረመዳንን በማይረባ ነገር ለውጠነዋል!
t.me/@mind_islam
#ጀዛኩሙሏህ_ኸይረን
#ቤተሰብ_ይሁኑ
ረመዳን - 1
በረመዳን ለመጠቀም ዘንድ ረመዳንን የእውነት በውስጣችንን ልናውቀው በአዕምሯችን ልናስተነትነው ይገባል።
ረመዳን ብሎ ማለት.. በደማችን ውስጥ የሚዘዋወረውን ዋና ጠላታችን የሚታሰርበት ወር ነው!..
ረመዳን ብሎ ማለት ከሱ በፊትም ሆነ በኋላ ምንም አይነት መመሪያ የማይበልጠው የአላህ ንግግሩ ቁርአን የወረደበት ቀን ነው...
ረመዳን ማለት ውስጣችንን በጠንካራ ጉትጎታ የምታሳስተን ነፍስያችን በረሀብ የምትከስምበት ወር ነው...
ረመዳን ብሎ ማለት አላህ በእያንዳንዱ ለሊት በሱ የእውነት ላመኑ ባሮቹን ከጀሀነም እሳት ነፃ የሚልበት ቀን ነው...
ረመዳን ብሎ ማለት አላህ ከወራቶቹ ሁሉ ያላቀው ወር ሲሆን አላህ ዘንድ ከፍ ማለት ከፈለክ በረመዳን ደረጃህን ከፍ አድርግ!...
ረመዳን ብሎ ማለት በውስጡ የቀናቶች ንጉስ የሆነችን ቀን ለይለቱል ቀድርን በውስጡ የያዘ ወር ነው...
...እናም ይሄንን ሁሉ መጠቀም ካልቻልክ ከተረገሙት ውስጥ መሆንህ አረጋግጠሀል...አላህ የረመዳን ትሩፋቶችን ከሚጠቀሙት ያድርገን......
t.me/@mind_islam
#remedan
#Remedan
ግዜ ሰጥተህ የምታሳልፋቸው ,የምትፈፅማቸው ,እንዲሁም የምትጨነቅለት አልያም የምትደሰትበት ነገር ሁሉ ስላንተ ይናገራል።ከዚህ ሁሉ ነገር ግን አንተ በምትሰራቸው ነገሮች ምን ያህል ደስተኛ ነህ ,ምን ያህሉስ ፈልገኸው ትፈፅመዋለህ፤ ምን ያህሉስ ደስ ብሎህ ትከውነዋለህ። የራስህን ማንነት የምታውቀው በዚህ ምልክት ነው። ምክንያቱም አላህ ስለ ሙናፊቆች በቀላሉ ሲገልፅልን ሶላትን ሲሰግዱ እንኳ ዉስጣቸውን እየደበራቸው ነው ብሎ አይደል! ...ሁሌም ቢሆን አስታውስ!
t.me/@mind_islam
#join
#ቤተሰብ_እንሁን
ለውጥ የሚጀምረው ከማሰብ መቻል ነው። ከዚያም ወደ ተግባር ይለወጣል። ነገር ግን አብዘሀኞቻችን እንዳለመታደል ሆኖ በደመነፍስ ተግብረን እንደገና ስለፈፀምነው ተግባር እናስባለን።ለዚያ ነው የማንለወጠው..! ደመነፍስን የምትነዳው ልባችን ናት። የምናስበው ደግሞ በአዕምሯችን ነው። አላህ የሚመለከተው ልባችንን እንዲሁም ተግባራችንን ነው።የኛ ተግባር መሆን ያለበት አዕምሯችንን ከልባችን ጋር ማያያዝ ብቻ ነው። ያኔ ማሰብ ከምንተገብረው ተግባራችን ቀዳሚ መሆኑን እናውቃለን።
t.me/@mind_islam
#ጀዛኩሙሏህ_ኸይረን
አላህ ላከበረው፣ላዘጋጀው የተከበረው የረመዷን ወር መዘጋጀት በአላህ ላመነ የአላህ ባርያ ግድ ነው። ኢንሻአላህ በተለያዩ የሶሻል ሚዲያ ቴሌግራምን ጨምሮ ጠቃሚ የሚሆኑ ትምህርቶችን በደናንተ የምናደርስ ይሆናል።
ኢንሻአላህ...
እናንተም የአጅሩ ተካፋይ ሊሆኑ ዘንድ ሼር ያድርጉ!
t.me/@mind_islam
#ጀዛኩሙሏህ_ኸይረን
ረሱል ሰ.ዐ.ወ ሰውን ነው ሰው አድርገው የገነቡት!
መጀመሪያ ሰው መሆንህን አሰብ..ምክንያቱም ውስጥህን አትዋሽምና!
ከዚያም ሰው ሆነህ ስትገነባ አላህ ያዘዘህን ትተገብራለህ...ካልተገነባህ ግን ትፈርሳለህ!
ያንተ ጥንካሬ በተገነባሀው ልክ ይወሰናል።
t.me/@mind_islam
#አጫጭር_ማስታወሻዎች_እንዲደርሳችሁ_ቻናሉን_ጆይን_ያድርጉ #ሊንኩን_ሼር_በማድረግ
#ቻናሉን_እናሳድገው
ህይወት የግዜ ጥርቅም ነው። ስንኖርበት ቀስ በቀስ ይቀንሳል። በመቀነሱም ውስጥ የሚያስደስት እና የሚያሳዝን ሁኔታዎችን እናሳልፋለን። ሁሉም ግዜያቸውን ጠብቀው ነው የሚከወኑት,የሚያስደስቱት ክንውኖች እኛ ስለፈለግን አይፈጥኑም፣እኛን የሚያስከፉ ነገሮች እኛ ስለጠላናቸው አይንጓደዱም! በዚህ መሀል ግን ጥሩም አገኘን መጥፎ ብቸኛ ማጣፈጫው ነገር ትግዕስት ነው። ታጋሾች እንሁን! እንመነዳበታለን ከአላህ!... ያውም ያለ ሂሳብ.
t.me/@mind_islam
#አጫጭር_ማስታወሻዎች_እንዲደርሳችሁ_ቻናሉን_ጆይን_ያድርጉ
#ከላይ_ያለውን_ሊንኩን_ሼር_በማድረግ
#ቤተሰብ_እናብዛ
#ጀዛኩሙሏህ_ኸይረን
ህይወታችን ኢስላም ይሁን። ያኔ እኛ የፈለግነውን ሙስሊም ሳንሆን አላህ የፈለው ሙስሊም እንሆናለን። መንገዳችን የኛ መላመት ሳይሆን ቁርአን ይሆናል።እኛ የፈጠርነው ወንድማማችነት ሳይሆን አላህ የሚፈልገው ወንድምነትን እንወልዳለን። ..ግን እውን ህይወታችን ኢስላም ነው?!
t.me/@mind_islam
#አጫጭር_ማስታወሻዎች_እንዲደርሳችሁ_ቻናሉን_ጆይን_ያድርጉ
#ከላይ_ያለውን_ሊንኩን_ሼር_በማድረግ
#ቤተሰብ_እናብዛ
#ጀዛኩሙሏህ_ኸይረን
ሰዓታቶች በማለፍ ቢመርሙም ሙዕሚን በልቡ አላህን በማስታወስ ያጣፍጣቸዋል።ይህ አላህን ማስታወሱ ከልቡ መንጭቶ ምላሱ ላይ ሲያደርገው ዚክር ይባላል። አላህ በማስታወስ ግዜያችንን እናጣፍጥ!
t.me/@mind_islam
#አጫጭር_ማስታወሻዎች_እንዲደርሳችሁ_ቻናሉን_ጆይን_ያድርጉ
#ጀዛኩሙሏህ_ኸይረን
የህይወትን ደረጃ በትክክል የሚያውቁት ህይወትን የተነጠቁ ናቸው። ያ ማለት በመቃብር ያሉ ሰዎች ናቸው።እነዚያ በመቃብር ውስጥ ያሉ ሰዎች አይሆንላቸውም እንጂ ቢሆንላቸው በህይወት መመለስ፤እኛ በህይወት እየኖርን ፍፁም ከምንጓጓለት የተለየ ነገር ነው መተግበርን የሚመርጡት!...ግን አይሆንም! እኛ በህይወት ያለነው ግን እድል አለን። እነርሱ የፈለጉትን ለመፈፀም።እድላችንን አናባክነው።ከሁሉ በፊት ሰዓታችንን በኢባዳ እናሳልፈው ሌላው ግዜውን ጠብቆ ይመጣል።ኢባዳ ግን ያልፋል እንጂ እንደሌላው ግዜውን ጠብቆ አይመጣም!
t.me/@mind_islam
#ጀዛኩሙሏህ_ኸይረን
#አጫጭር_ማስታወሻዎች_እንዲደርሷችሁ_ቻናሉን_ጆይን_ያድርጉ
#ሊንኩን_ሼር_በማድረግ
#ቤተሰብ_እናብዛ
ነግቶ ሲመሽ እና መሽቶ ሲነጋ አላህን ከልብህ አመስግን።ምክንያቱም አመስጋኞች በጣም ጥቂት ናቸው። ከጥቂቶቹ ሁን!
t.me/@mind_islam
ስንወለድ ከሁሉም ነገር ነፃ ሆነን ተወለድን፤ስናድግ ሁሉንም ነገር ለመሰብሰብ ፈለግን፤ስንሞት ሁሉንም ነገር ጥለን እንሞታለን፤ ከዚያም አላህ ስለሁሉም ነገር ይጠይቀናል። ...አስታውሱ!
t.me/@mind_islam
በዚች አለም ዉስጥ ውድ ነገሮች እዚያም እዚህም ይገኛሉ። ነገር ግን ከህይወት በላይ ውድ ነገር የለም። በዚህ ዉድ ነገር አላህን ካልተገዛንበት ምናልባች ዘላለም ብንፀፀት እንኳን አናገኘውም። ለዚህም መጀመሪያ በማሰብ ይጀምራል። ከዚያ...ወደ ውሳኔ!
t.me/@mind_islam
የሰራነውን መገምገም
ከአሱር ሶላት እስከ መግሪብ ሰዓት ባሉት ግዜያቶች ስራችንን የለሊቱን እና የቀኑን ዘወር ብለን መመልከትን ልምድ ይኑረን። ምክንያቱም የተሳሳትነው ነገር ካለም እስከ መግሪብ ኢስቲግፋር የምንለበትን የተዋቡ ሰዓታቶች አሉን። የምናስታውሰው ስህተት ከሌለም ይበልጥ በኢባዳ ቀኑን መጨረስ ትልቅ ትሩፉት እናገኝበታለን። ራሳችንን በረመዳን መገምገም የምንችልበት ወር እንዲሁም እኛም ራሳችንን በመገምገማችን ትልቅ እድለኞች መሆናችንን እናስተንትን።
t.me/@mind_islam
ረመዳን - 1 (part 2)
የረመዳን የመጀመሪያው ቀን ሊያልፍብን ሰዓታቶች ቀርተውታል። ይበልጥ በዱዓ,በዚክር እንዲሁም ቁርአን በመቅራት ከአሱር እስከ መግሪብ ያለውን ግዜ እንጠቀምበት። ምክንያቱም ይቺ ግዜ አላህ ዘንድ ትልቅ ቦታ አላት። የማታ አዝካሮችን በማለት ዛሬ እንጀምረው፣ ዱዓ አድርጉልን ያሉ ወንድሞችን እና እህቶችን ዱዓ እናድርግላቸው፣ ቁርአን ቢያንስ አንድ ጁዝ እንቅራበት እንዲሁም በጥሩ እንሰናበተው...አደራ በመዳከም እና በማይጠቅሙ ነገሮች በነዚህ ሰዓቶች እንጠንቀቅ። ምክንያቱም ስራዎች የሚመዘኑት በመጨረሻ መሆናቸውን አንርሳ!
(ከታች ያለውን ሊንክ በመጫን ቤተሰብ እንሁን!)
t.me/@mind_islam
ረመዳን ግዜውን ጠብቆ ለሚጠቀምበት ብዙ ትሩፋቶችን በውስጡ ይዞ ሊገባ ሰዓታቶችን እየቆጠረ ይገኛል። ይሄ ሁሉ ግን በህይወት ለደረሰ ብቻም ሳይሆን ለሚጠቀምበት መሆኑን እንገንዘብ። ረመዳንን ከሚጠቀሙበት እንዲሁም ከሚጠቅማቸው ውስጥ አላህ ያድርገን!....አሚን.
t.me/@mind_islam
" ጥንካሬ ሲተረጎም!"
ብዙዎቻችን በብዙ መልክ ጥንካሬን የምንለካበት ሚዛን ይኖረናል። አንዳንዶች ተሳስተን, ሌሎቻችን ደግሞ ልክ ልንሆን እንችላለን። በብዙ እይታዎች አንፃር!.. አንዳንዶች ጥንካሬን ባልተረጋገጠ ታሪክ ስንለካ፤ ሌሎች ደግሞ ባለንበት ዘመን በሚከወነው እውነታ ይመዝኑታል።ጥንካሬን ከሀብት እና ከማጣትም ጋር የሚመዝኑም አይጠፉም። ከዚህም ባስ ሲል... ጥንካሬን ከጀግንነት ጋር በማያያዝ... ክብረትን እና ዝናን ማገኘት የመጨረሻው ቁንጮ ነው ብለው የሚያስቡ ሙስሊሞችም ከምንግዜውም በላይ ተበራክተዋል። ይሄ ሁሉ አስተሳሰብ ከእምነታችን መላላት መሆኑን ሙስሊሞች ልብ ልንል ይገባል።በተለይ ወጣቶች! የሰው ልጅ በእምነት የሚኖር ፍጡር ነው።ሌሎች ፍጡሮች ለአላህ ተገዢነትን ብቻ እንጂ የኔ እምነት ይሄ ነው ብለው አይናገሩም አይወያዩም ብሎም በዕምነታቸው ምክንያት አይጋደሉም፣ መስዋት አይከፍሉም። የሰው ልጅ ግን ለዚህ ታድሏል።ጥንካሬ የሚመዘነው በእምነት ብቻ ነው። እኛ ሙስሊሞች በኢማናችን ልክ ነው ጥንካሬያችን! ለአላህ ባለን ቅርበት እና ርቀት ብቻ ነው የምንለካው። የዘር እና የቀለም፤የጎሳና የጎጥ፣የተራነት እና የባለስልጣንነት በኢስላም ላይ ቦታ እንደሌለው ምሳሌ አድርገን ልንወስድ የሚገባን, የነብይነት ህይወታቸው የ23 አመት ጉዞ ብቸኛ መመዘኛችን መሆኑን እንወቅ፣እንገንዘብ። ከጥቃቅን እስከ ትላልቅ የእለት ከእለት ዉሏችን በቁርአን አንቀፆች እና በሀዲሶች ይለካ! ዉስጣችንንም እንመርምር ፣የማይነጥፍ እና የማይዛነፍ ሚዛን ለጥንካሬያችን እናስቀምጥ። እንደ ተምሳሌታችን ነብዩ ሙሀመድ(ሰ.ዐ.ወ) ጥንካሬን በወህይ እውቀት እንገንባ! እምነታችን፣ኑሮአችን፣ትምህርታችን፣መረዳዳታችን፣ሰራችን፣ትግላችን ሁሌም በዲነል ኢስላም ይመዘን።ያኔ ጠንካሮች እንሆናለን። የተረሳውንም ጥንካሬን ለትውልድ እናስተምራለን እናሳያለን!..
t.me/@mind_islam
youtube.com/@islam_mindset
tiktok.com/@islam_mindset
fb.com/@islam_mindset
#ፎሎው_ያድርጉ
#ቻናሉን_እናሳድገው
#ቤተሰብ_እንሁን
#እንጠቀማለን_ኢንሻአላህ
ሙዕሚን የረመዳን ቀናቶች ወደሱ በቀረቡ ግዜ ልቡ በሀሴት እና በብርሀን ትፈካለች።ምክንያቱም በያንዳንዱ የረመዳን ቀናቶች ውስጥ ምን እንዳለ ያውቃልና!
@t.me/@mind_islam
#ሊንኩን_ሼር_በማድረግ
#ቻናሉን_ያሳድጉት
እኛ ሰዎች ጥሩ ነገርን ለመፈፀም አልያም ከመጥፎ ነገር ለመራቅ የመጨረሻችን እንደሆን ከተሰማን እና ካወቅን ከውስጣችን ያንን ነገር ለመተግበር አልያም እድላችንን ለመጠቀም እጅጉኑ ትኩረት እሰጥበታለን።እንበልና ያሁኑ ጁሙዓ የህይወታችንን የመጨረሻው ጁሙዓ መሆኑን ብናውቅ ምን እያደረግን እንደምናሳልፈው እንገምት።የመጨረሻው ጁሙዓ አለመሆኑም ምንም ማረጋገጫ የለንም...!
(ሶሉ አለ ነቢ ያሙስሊሚን!)
t.me/@mind_islam
#ሊንኩን_ሼር_በማድረግ #ቻናሉን_እናሳድገው
አሁን ላይ የምንተገብረው ተግባራችን የሆነ ሰዓት አወቅነውም አላወቀነውም አስበንበታል። ጥሩ የምንተገብር ከሆነ ይበልጥ ወደፊት ጥሩ ለመተግበር አሁን ማሰብ ይጠበቅብናል። መጥፎ ነገር ላይ ካለን አሁን ላይ ማቆምን መምረጥ እና መወሰን ይኖርብናል። ሳይታሰብ የሚፈፀም ነገር የለም።
t.me/@mind_islam
#አጫጭር_ማስታወሻዎች_እንዲደርሳችሁ_ቻናሉን_ጆይን_ያድርጉ
#ጀዛኩሙሏህ_ኸይረን
ግዜያቶች ባለፉ ቁጥር "ቅድም!" ከሚለው ቃል እየመሰረቱ ከኛ ወደ ኋላ ይሰወራሉ። የሚመጡት ግዜያቶች ደግሞ"በኋላ" ከሚለው ቃል ጀምሮ ወደ ፊት ይጠብቁናል። ልብ እንበል እኛ ግን "አሁን" ላይ ነን። ያ ማለት ለሚያልፈው "ቅድም" አሁን ላይ መስራት ያለብንን የምንወስንበት፤ ለሚመጣው "በኋላ" የምንዘጋጅበት ግዜ ነው። አላህ የሚጠይቀን ስለዚህ ጉዳይ ነው። አሁንን እንዴት እንዳሳለፍነው!
t.me/@mind_islam
#አጫጭር_ማስታወሻዎች_እንዲደርሳችሁ_ቻናሉን_ጆይን_ያድርጉ
#ጀዛኩሙሏህ_ኸይረን
ብቻችንን ስንሆን ምንድን ነው የምናስበው፣የምናወራው፣የምንተገብረው እንዲሁም የምንመኘው, ምክንያቱም እኛ ማለት ብቻችንን የምንሆነን ነን። አላህም ምንዳችንን የሚሰጠን በማንነታችን ደረጃ ነው። የሙዕሚን ደረጃው ብቻውን ሲሆን ይበልጥ ጥፋቶቹን እያስታወሰ ወደ አላህ ያለቅሳል እንጂ ይበልጥ አላህ የተከለከለውን አይተገብርም!
t.me/@mind_islam
#አጫጭር_ማስታወሻዎች_እንዲደርሳችሁ_ቻናሉን_ጆይን_ያድርጉ
#ሊንኩን_ሼር_በማድረግ
#ቤተሰብ_እናብዛ
#ጀዛኩሙሏህ_ኸይረን
ሁሌም ቢሆን በአላህ ላይ ጥሩ ተስፋ ይኑረን። ያጠፋነውን ወንጀላችንን ከልባችን ይቅር በለን እንበለው። ይቅር እንዳለን እናስብ እና በኢባዳ እንጠንክር።በኢባዳ ስንጠነክር ልክ ነገ መሞቱን እርግጠኛ እንደሆነ ሰው እንሁን!
t.me/@mind_islam
#ጀዛኩሙሏህ_ኸይረን
#አጫጭር_ማስታወሻዎች_እንዲደርሳችሁ_ቻናሉን_ጆይን_ያድርጉ
#ከላይ_ያለውን_ሊንኩን_ሼር_በማድረግ
#ቤተሰብ_እናብዛ
አላህ በሱ ላመኑ ባሮቹ ካላመኑት ይበልጥ ያዝንላቸዋል፤ይወዳቸዋል፤እንዲሁም ክብር ይሰጣቸዋል።በየግዜውም ቢሆን ወደሱ እንዲቀርቡ እድል ይሰጣቸዋል። የሚሰጣቸውም እድል መሽቶ መንጋትን እንዲሁም ነግቶ መምሸትን በህይወት ማየት ነው። በጁሙዓ ቀን በህይወት መኖር አንዱ ትልቁ የአላህ እድል ነው። ለተጠቀመበት ከሌሎች ቀናቶች ይለያል!
[ አላሙመ ሶሊ አላ ሙሐመድ..❤]
t.me/@mind_islam
#ሊንኩን_ሼር_በማድረግ
#ቤተሰብ_እናብዛ
#አጫጭር_ማስታወሻዎች_እንዲደርሷችሁ_ቻናሉን_ጆይን_ያድርጉ
#ጀዛኩሙሏህ_ኸይረን
የአላህ ዉዴታህ በቀነሰ ቁጥር የዱንያ ውዴታህ ይጨምራል።በተቃራኒው የዱንያ ፍቅርህ በቀነሰ ጊዜ የአላህ ወዴታ ይጨምራል። በረሱልም ዘመን እንዲህ ነበር ካስተነተነው!
t.me/@mind_islam
በሰዎች ዘንድ ስትሆን መላዒካ ብቻህን ስትሆን ሰይጣን አትሁን። ያንተ ደረጃ በአላህ ዘንድ ብቻህን ስትሆን መሆኑን አስታውስ!
t.me/@mind_islam
ሁሉም በግዜው ይከወናል።ከዋኙ አላህ ሲሆን እኛ ደግሞ በአላህ ላይ ጥሩ ሀሳብ እና ትግዕስት ማድረግ ብቻ ነው። ሁሌም ይሄንን አስታውሱ !
t.me/@mind_islam
#ሼር_በማድረግ
#ቤተሰብ_እናብዛ
ክፍል-2
ነግቶ ሲመሽ እንዲሁም መሽቶ ሲነጋ አላህ ወደሱ እንድትቃረብ እድል እየሰጠህ መሆኑን አጢን።ከትላንትናው በተሻለ ዛሬ አላህን ብቻ አምልክ፤ከትላንትናው በተሻለ ዛሬ አላህ ከከለከለው ነገር ራቅ፤ከትላንትናው በተሻለ ዛሬ ላይ ያበላሸኸውን አስተካክል።ምክንያቱም ቀብር ውስጥ አሁን ላይ ሆነው ያንተን እድል የሚፈልጉ አሉ!
#ሼር_በማድረግ
#ቤተሰብ_እናብዛ!
t.me/@mind_islam
...................Islam-mindset......................