ገንዘብ ሲገኝ ሊያስደስት ይችል ይሆናል። ያስደስት እንጂ የውስጥን እርካታና መረጋጋትን በፍፁም አይሰጥ።ለዛ ነው ገንዘብ የሌላቸው ሰዎች ገንዘብን ሲያገኙ በፊት ላይ ከነበሩበት አላህ የሚወደው ቦታ የምናጣቻው። ገንዘብ ያላቸው ከሌላቸው ሰዎች ይበልጥ ሩጫ እና ጭንቀት ውስጥ ይገባሉ።አላህ ያዘነላቸው ሰዎች ሲቀሩ!...እንዲሁ ገንዘብ ሲታጣ ሊጠብ እና ሊያጨናንቅ ይችል ይሆናል። ነገር ግን አያስደነግጥም። ምክንያቱም መታጣቱ ቋሚ አይደለም።ግዜውን ጠብቆ ይመጣል። በነዚህ በሁለቱ ተቃራኒ ጎኖች አንድ ሙዕሚን ገንዘብን ሲያገኝ የሁሉ የበላይ እንደሆነ አያስብም...ሲያጣም ከሁሉ የበታች እንደሆነም አይሰማውም። ሙስሊም ገንዘብ ሲያገኝ ሆነ ሲያጣ አንድ አይነት ባህሪ ብቻ ነው ያለው... እሱም በአላህ ፈተና ላይ እንደሆነ ያስተነትናል።
ISLAMINDSET
Pi is a new digital currency developed by Stanford PhDs, with over 55 million members worldwide. To claim your Pi, follow this link https://minepi.com/nurahusu4646 and use my username (nurahusu4646) as your invitation code.
Читать полностью…ብዙዎች ነፃ መውጣትን ከጉልበት እና ከገንዘብ ጋር አያይዘው ይመለከቱታል። ጥቂቶች ደግሞ ከሞት በኋላ አላህ ቃል ስለገባው ጀነት እና ከቅጣት መዳንን ነፃ መውጣትን በማሰብ ነፃ ነን ይላሉ።ነገር ግን የተወሰኑ ሰዎች በዱንያ ላይ የማያልፍን ነገር በሚያልፈው ሰዓታቸው ስራን ሰርተው ነፃ የወጡ ሰዎች አሉ።ነፃ መውጣት ማለት አላህ በባሮቹ ላይ ግዴታ ካደረገው በላይ ትሩፋቶችን ጨምሮ መስራት ነው።ለዛ ነው እነዚያ የተወሰኑ ሰዎች ሳይሞቱ ዱንያን ላይ አላህ ጀነት ውስጥ የሚያስቀምጣቸው።...ምንኛ ያማረ ነፃነት ነው! አላህ ይወፍቀን!
ISLAMINDSET
ሰዎች በህይወት ኖረው እንደሞቱ ይቆጠራሉ። በተቃራኒው ደግሞ ሞተው በሰዎች መሀል ይኖራሉ። የሰዎችን ደረጃ የሚወስነው ለሰዎች ስብዕናቸው ሲሆን በአላህ ፊት ደግሞ ዚክር(አላህን በምላሳቸው ማስታወስ)ስንችሉ ብቻ ነው። ለዚያም ነው "እነዚያ አላህን የሚያስታዉሱ እና የማያስታዉሱ ምሳሊያቸው በህይወት እንደሚኖሩ እና እንደሞቱ አምሳያ ናቸው ያሉት ነብዩ ሙሐመድ (ሰለላሁአለይሂ ወሰለም!)
ISLAMINDSET
የሙዕሚን መሳሪያ
ዘመናችን ከየትኛውም ግዜ እና ሰዓት በላይ ቀላል ምቹ ቢሆንም ከየትኛውም ዘመን በላይ ግን የሰው ልጆች ደም እንደ ወንዝ ዥረት በየቦታው እየፈሰሰ ይገኛል። በተለይም በአላህ አንድነት ጥርት አድርገው ባርነታቸውን ባረጋገጡት ሙዕሚኖች ደግሞ በጣም ባስ እያለ መጥቷል።ነገር ግን በአንፃራዊ ሰላም ላይ ያሉ ሙዕሚኖች ድቅድቅ ባለ የድሎት ዝንጋቴ ላይ መሆናቸውን በተለያዩ የህይወት ገጠመኞች ሲታይ ይስተዋላል። ለዚያም ይመስላል አላህ በተለያዩ የዱንያ ህይወት ላይ በቀጥታም ሆነ በተዘዋዋሪ ፈተና ውስጥ የሚያስገባን! የሰላምን ትንፋሽ ተነፍገው በጥበት ላሉ ለወንድሞቻችን እና ለእህቶቻችን የነሱን ህመም ህመማችን ነው ብለን ከየትኛውም የአጀንዳ እንቅስቃሴ ነፃ ሁነን ልባችን ተቃጥሎ ዱዓ የማናረግላቸው..ምክንያቱም አላህ የሱን መሳሪያ በግልፅ ነፍጎናል። የሙዕሚን ዋነኛው መሳሪያ እና አስተማማኙ ዱዓ ብቻ ነው። ልባችን ተቃጥሎ ከውስጣችን ዱዓ ስናደርግ የኛም ህይወት ይቀላል።
አላህ ከልባቸው ዱዓ ከሚያደርጉት ባሮች ያድርገን!
#gaza
#dua
#islamindset
አላህ እኛ ሙስሊሞችን ደረጃ የሚሰጠን በስብስብ ብዛታችን ሳይሆን በዉስጣችን ባለው የተቅዋ ጥንካሬያችን ብቻ ነው።በሚያሳዝን ሁኔታ ግን ይሄንን ዘንግተነዋል።ለዚህም መረጃው እንደ ገለባ በዝተን በመካከላችን ፍሬ መታጣቱ በቂ ነው። አላህ ብቸኛን ሰው ከህዝብ መንጋ ስብስብ እንደሚበልጥ በራሱ ንግግር በሚገባን መልኩ አሰቀምጦልናል።ማስተንተኛ አዕምሮ ካለን! ስለዚህ የራሳችንን ትልቁን የቤት ስራችንን ሳንጨርስ ሌላ ስራዎች አንጀምር።ምክንያቱም እንሰበራለን። ሁላችንም በመጀመሪያ ተቅዋችንን እንመርምር! የሙስሊም ትልቁ አጀንዳ ስብስብን ማጠናከር ሳይሆን ተቅዋን በልብ መጠንከር የሚችልበትን መንገዶችን መስራት እና መዘርጋት ነው። ይህ የዛሬው መልዕክታችን ነው አላህ ከመጥፎ ነገር ሁሉ ይጠብቃችሁ...!
#አሚን..
t.me/@mind_islam
#share
#like
#ቤተሰብ_ይሁኑ
" የረመዳን እንግዳ ነን!?"
ጠይቃችሁ ታውቃላችሁ አስተውላችሁ እንደሆነ ረመዳን ሲገባ መስጂዶች ይጨናነቃሉ።እስከዛሬ የመጀመሪያው ሶፍ ላይ ሲሰግዱ የነበሩ ሰዎች በረመዳን ላይ በረመዳን እንግደኞች ተነጥቀው ሲቸገሩ ይስተዋል ነበር። የሚገርመው ነገር ረመዳን ሳይወጣ እንግዳነታቸውን ጨርሰው በፊት ለነበሩት ሰጋጆች አስረክበው ይወጣሉ። ካላመናችሁ መስድጅ ገብታችሁ አረጋግጡ። ዲንን ዱንያ አድርገን በመያዝ እና የረመዳን እንግዳ አንሁን።ቢያንስ እንኳን ህሊናችንን እንታዘዘው!ራሳችንን እንታዘበው,ባርነታችንን በቃል ብቻ ሳይሆን በተግባር ሳንሞት እናረጋግጥ!
(መልዕክቱ የሚጠቅም ነው ብላችሁ ካመናችሁበት ለሌላ ሰው እንዲደርስ ያድርጉ)
t.me/mind_islam
#ጀዛኩሙሏህ_ኸይረን
ያንተ ማንነት ለነገሮች ቦታ በምትሰጠው ነገር ይወሰናል።ለጊዜውም ቢሆን...!
ለነገሮች ቦታ መስጠት ማለት ደግሞ ውድ የሆነውን ሰዓትህን በምሰጠው ነገር ማሳለፍ ማለት ነው። ምንድን ነው የምታሳልፈው ሰዓትህን ራስህን ጠይቅ...!?
@islam_mindset
ረመዳን- 12 -1445 ዓ.ሒ
በዚች ህይወት ስትኖር ዋጋ ያላቸውን ነገሮች ስትገዛ በብር ነው። በዱንያ ላይ ብር ነውም ያለው! ነፍስህ ከሰውነትህ ስትለያይ ግን ብር ስራውን አቁሞ በሌላ ይተካል። እርሱም ሀሰና ይባላል።የአኪራ ገንዘብ ነው! ሚዛኑም የሚንቀሳቀሰው በሀሰናት ነው የመጨረሻይቱ ቀን ላይ!ሙዕሚን የሚለየው እዚህ ነጥብ ላይ ነው...ነፍሱ ከሰውነቱ ሳትለየው የዱንያውን ብር ወደ አኪራው ብር(ሀሰናት)ብቻ ለመቀየር ይሰራል። ምን ብሩን ብቻ..ጊዜውንም ጉልበቱንም ወደ ሀሰናት የሚቀይሩ አጋጣሚዎችን ሁሉ ይጠቀምባቸዋል።ሙናፊቆች እና ካሃዲያን ግን ለዚህ በፍፁም አልታደሉም።
t.me/@mind_islam
" የድግግሞሽ ፀጋ"
በህይወት እስካለን ድረስ ፍጥረተ አለሙ ሲደጋገም እንመለከታለን። ለሊት ከቀኑ እንዲሁም ቀኑ ከለሊት፤ ብርዱ ከሙቀቱ እንዲሁም ሙቀቱ ከብርዱ፤ አመት ከአመት አንዳይነት ወራቶች በኛ ላይ ይመላለሳሉ። የአላህ ድንጋጌዎችም እንደዚሁ ናቸው። በየቀኑ አምስት አውቃት ሶላቶችን ሰዓታቸውን ጠብቀን እንሰግዳቸዋለን፣ በየአመቱ ዘካ ግዴታ የሚሆንበት ሰው የአመቱን ግዜ ጠብቆ ይሰጣል፣ እንዲሁም ረመዳን በየአመቱ ይመላለሳል። ሀጅም ወሩን ጠብቆ ይመጣል። ይሄ ግን የሚሆነው በህይወት ላለ ሰው ብቻ ነው። ምክንያቱም የሞቱ ሰዎች በነሱ ላይ የመጨረሻይቱን ቀን መጠባበቅ ብቻ ነው ስራቸው! የስራ መዝገባቸውም ተጠቅሎ ተቀምጧል። መጥፎ የሰሩትን ነገር ሊያካክስ የሚችል ስራ መስራት አይችሉም፤ ጥሩ የሆነውንም ስራ ይበልጥ እንስራ ብለው አይንቀሳቀሱም። ከዚህ የምንረዳው አላህ በኛ ላይ ከዋላቸው ፀጋዎች መሀል የጊዜ ድግግሞሽ ፀጋ መሆን ነው። ምክንያቱም አላህ አንድን ፀጋ ደጋግሞ ሰጠን ማለት ምናልባችም ደጋግሞ እድል እየሰጠን ነው ካለንበት ወንጀላችን እንድንመለስ አልያም ወደሱ ይበልጥ እንድንቃረብ!
t.me/@mind_islam
#ቤተሰብ_ይሁኑ
ነገ ቅዳሜ ማለትም ረመዳን-6 ከቀኑ 8:00 ላይ በዩትዩብ ቻናላችን የሼኽ ሙሐመድ አንሲ ትምህርት ይውሰዱ።
youtube.com/@islam_mindset ያገኙናል!
በየ አመቱ...በየ ወሩ...በየ ሳምንቱ...በየቀኑ...በየሰዓቱ..በየደቂቃው እንዲሁም በየሴኮንዶች አላህ በኛ ላይ እዝነቱን ፀጋው ምህረቱን ይውልልናል። ልባችን ከድንጋይ በላይ ስትደርቅ ከሰጠን ይልቅ በአብዘሀኛው ያልሰጠን ነገር እንዳለ እያስመሰልን አላህን"አልሀምዱሊላህ!!!" ከማለት እንኮራለን።ነገር ግን ልባችን የመርጠቧ ምልክት የትኛውንም የዱንያ ህመም ላይ እንሁን አላህ በሰጠን ፀጋ ስለምንሽር "አልሀምዱሊላህ!!" ከማለት አናርፍም። ምክንያቱም ፀጋውን በውስጡ ላመነ ሰው "አልሀምዱሊላህ!" እንዲ ያስገድደዋል። እንዳለመታደል ሆኖ ግን የአላህ አመስጋኝ ባሮቹ ትንሽ ሆነው በፀጋው የሚክዱት በዙ!
አላህ ከጥቂት ባሮቹ ያድርገን!...ምክንያቱም አመስጋኝ ባሮቹ ጥቂት ናቸውና!
➙ መልካም የጁሙኣ ግዜ ይሁንልን።
ISLAMINDSET
ትልቅ ሰው ማለት ራሱ የሚድንበትን መንገድ ለማግኘት ሰበብ የሚያደርግ ነው። ብዙዎች ራሳቸውን ለማዳን ሁሌም ይሯሯጣሉ።ነገር ግን "ከምንድን ነው የምናድነው!?" የሚለው ጥያቄ ይለያያቸዋል።ሰዎች እዚህ ላይም ነው የሚለያዩት! ሙስሊም በባዶ ተስፋ ሳይሆን የኢኺራ እርግጠኝነትን(የቂንን) በልቡ ስላረጋገጠ, ሩጫው ሰላረጋገጠው አለም ብቻ ነው። አላህም ባረጋገጠው ኒያ መሰረት ይመነደዋል። ምክንያቱም ሙኽሊስ ባሪያው መሆኑን በተግባር ለአላህ አሳይቷልና!
ISLAMINDSET
"በአንድ ቀን ውስጥ ሱበሀነላህ ወቢሀምዲሂ 100 ግዜ ያለ ሰው ወንጀሉን አላህ ይምርለታል።ወንጀሉ እንደ ባህር አረፋ ቢበዛም!" ነብዩ ሙሐመድ (ሰ.ዐ.ወ).
ISLAMINDSET
የአይናችን ተዓምሩ በብርሃን ነፀብራቅ የነገሮችን ምስል በቀለማቸው አማካኝነት መመልከት ማስቻሉ ነው። እንደዚህ አይነቱ ብርሃን የትኛውም ፍጥረት አይን እስካለው ድረስ መመልከት ይችላል። የልብ ብርሃን ግን ለአይን ከሚሰጠው ብርሃን ፍፁም የተለያየ ነው። ይሄም ብርሃን ያለው በቁርአን ውስጥ ብቻ ነው። የቁርአንን ብርሃን ያገኘ አይኑም ልቡም ይመለከታል። ያጣው ግን አጥቶታል። ለዛ ነው ብዙዎች በአይናቸው ማየት ችለው በልባቸው መመልከት ያቃታቸው!
ISLAMINDSET
ዱንያ የሰው ልጆች ይሄን ያክል ትኩረት አድርገውባት ለፍተውባት ካልሞላች ያውም ከ40-60 አማካኝ እድሜ ለመኖር አኪራ ሳይለፋበት ይገኛል ብሎ የሚያስብ ካለ ተሳስቷል። አዕምሮው ራሱ ባልተገነዘበው ነፃ ሀሳብ ታሟል። ለሁሉም ህመም ደግሞ መድሀኒት አለው። ለደነዚህ አይነቱ በሽታ መድሀኒቱ ቁርአን ማንበብ እና በጥልቀት ማስተንተን ነው።
ISLAMINDSET
ኢብኑ ጀዉዚ(አላህ ይዘንላቸውና) እንዲህ ብለዋል፡-
"ከቅጣት ሁሉ ከባዱ ቅጣት በሐጥያት ላይ መዘዉተር
፤መንፈሳዊነትን መራቅ ፤ ኢማንን መገፈፍ ፤ ከአላህ ጋር የማዉራትን ጥፍጥና አለመታደል ፤ ቁርአንን መርሳትና ኢስቲግፋር ችላ ማለት ነዉ፡፡
ዱንያ ላይ ከቀልብ በሽታ ይልቅ በሰዉነት ላይ የሚደርሰዉ በሽታ ቀላል ነዉ!"ብለዋል
#viral
#foryou
#fb_page
#islamindset
#like
#share
የተወዳጁን ኡስታዝ ሼይክ መሐመድ አንሲን ትምህርት በተከታታይ ወደናንተ በአላህ ፈቃድ በዩትዩብ ቻናላችን ይደርሳል። ቻናሉ ለብዙ ሰዎች እንዲደርስ ሼር ያድርጉት!
እንዲሁም ሰብስክራይብ በማድረግ የቻናሉ ቤተሰብ ይሁኑ።
youtube.com/@islam_mindset
ረመዳን-15-1445 ዓ.ሒ
ህይወት ትጠቀለላለች...ያውም ሳናስብበት ሳንጨነቅለት..ሳናስተነትነለት! ለዚህም ማሳያ እስካሁን ያሳለፍነውን ዘመናቶች እና ግዜያቶችን ዘወር ብለን መመልከት ብቻ በቂ ነው።ከህይወት ግን የሚያስፈራው ነገር ቢኖር መቼ ከሞት ጋር እንደምንላተም አለማወቃችን ነው። ምክንያቱም ሞት ለመምጣቱ መስፈርት የለውም። ከዚህም አለፍ ስንል ደግሞ አለመዘጋጀታችን እና ዘላለም እንደምንኖር ማስመሰላችን አሰፈሪ ያደርገዋል። ጠንቃቃዎች እንሁን ..ወደ አላህ በቻልነው አቅም እንቃረብ!
@islam_mindset
ረመዳን -8 ሰኞ ከቀኑ 7:15 በዩትዩብ ቻናላችን ትምህርቱን ይከታተሉ።
"ዱዓ ስታደርግ..." በሚል ዝግጅት ወደናንተ የቀረበ ሲሆን ዝግጅቱ በረመዳን 7 - 1445ዓ.ሒ በሼኽ ሙሐመድ አል-አንሲ አማካኝነት የሚካሄድ ሲሆን ሰፊ ነጥቦችን ሼኹ ይዳስሳሉ። በዋናነት ስለ ዱዓ ሚስጥራቶች እና እስከዛሬ አስበናቸው የማናቃቸውን ነጥቦችን ከህይወታችን ጋር በማያያዝ የዱዓ ሚስጥራቶችን ያብራርሉናል። ፕሮግራሙን ሼር እና ላይክ እንዲሁም ፔጃችንን ሰብስክራይብ በማድረግ ቤተሰብ ይሁኑ!
http;//youtube.com/@UCf1l3HUhbvYevpMWRDPVhjg
http;//tiktok.com/@islam_mindset
----------------------------------------------------