loveyuolema | Unsorted

Telegram-канал loveyuolema - ISLAMIC SCHOOL 2

8667

✍ ጅልከሆንክ ጅል ተከታይ ጀንትል ከሆንክ አስከታይ ትሆናለህ..! ጅልም ጀንትልም ካልሆንክ ደግሞ አርፈህ በራስህ ዓለም ትኖራለህ..! አንባቢ እንሁን፡፡ለውጥ ከራስ ቢጀመር ...የቸገረን ጥሩ መካሪ ሳይሆን፤ የሰማነውን መተግበር ነው ያቃተን!ጅህልና በሽታ ነዉ፡፡ 🎖For any comment T.me/Anws_bot

Subscribe to a channel

ISLAMIC SCHOOL 2

ከሰዎች ጋር ስትሆን መላኢካ ብቻህን ስትሆን ሰይጣን አትሁን።ልብ በል አላህ ብቻህን ስትሆንም ይመለከተሀል!
/channel//mind_islam

Читать полностью…

ISLAMIC SCHOOL 2

ሰላትን እያቆራረጥክ ከሰገድክ አዕምሮህ መስራቱን አቁሟል።ሰላትን መስገድ ካቆምክ የምታስበው በስሜትህ ነው።ራስህን ፈትሽ ሙስሊም መሆንህን..
/channel//mind_islam

Читать полностью…

ISLAMIC SCHOOL 2

በዱንያ ስንኖር እና ችግራችን ሲቃለል ሁሌ ጤና ሆነን ሞት ወደኛ የማይመጣ ይመስለናል። ጥበበኛ ማለት በዱንያ ሲስፋፋለት በከይር ነገር ላይ ለመሳተፍ የሚጣደፍ ሰዉ ነው።ምክንያቱም ሞት በዛው ፍጥነት ወደሱ እየመጣ መሆኑ ያውቃልና!
/channel/mind_islam

Читать полностью…

ISLAMIC SCHOOL 2

ሁሉም ነገሮችን አጢናሀቸው ከሆነ ያንተን ግዜ እና ሰዓት ለመውሰድ ይሻማሉ ይሽቀዳደማሉ።አንተ ብልጥ ከሆንክ ግን ከሁሉም ነገር ሰዓት እና ግዜህን ቀንሰህ ለቁርአን ትሰጣለህ። ያኔ አላህ በቃላቱ እያናገረህ መሆኑን ትረዳለህ።ይሄንን አትርሳ!

Читать полностью…

ISLAMIC SCHOOL 2

"ነብያዊ ስኬት!" በሚል ርዕስ ወደናንተ ተዘጋጅቶ የቀረበ ቪዲዮ ሲሆን የስኬትን ትርጉም ወደ ነብያቶች ህይወት በመመለስ ትርጉሙን ከአኗኗራቸው ጋር በማያያዝ ዉዥብር የሌለበትን ትርጉም የሚሰጥ ነው።በተለይም በአብዘሀኛው የኢስላም ዕይታ እንደመሆኑ መጠን የነብዩ ሙሐመድን(ሰ.ዐ.ወ) የስኬት ጣራን እንደምሳሌ እየጠቀሰ ተመልካቾችን ወዳለፈው ወርቃማ የነብይነት ዘመን በመመለስ ራሳቸውን እንዲገመግሙ ይጋብዛል። በስተመጨረሻም ስኬትን ልንጎናፀፍ ዘንድ መጀመሪያ ማድረግ ያለብን ምን እንደሆነ ሀሳብ ይሰጣል። ቪዲዮ ሰዎችን ይገነባል ብላችሁ ካሰባችሁበት ሼር እና ላይክ እንዲሁም ሰብስክራብ በማድረግ ቤተሰብ ይሁኑ።በሌሎችም የማህበራዊ ሚዲያዎቻችን የተለያዩ ትምህርቶችን እና ማስታወሻዎችን ይከታተሉ።
youtube.com//@UCf1l3HUhbvYevpMWRDPVhjg
tiktok.com//@islam_mindset
t.me//@mind_islam
instagram.com//@nura_husu
facebook.com//@Islam_Mindset
ያገኙናል።እናመሰግናለን!

......................................Islam_Mindset....................

Читать полностью…

ISLAMIC SCHOOL 2

ኢብኑ ተይሚያህ(አላህ ይዘንላቸው) እንዲህ አሉ:-

"በአላህ ላይ መወከል(መመካት) ግዴታ ነው።ከትላልቅ ግዴታዎች ዉስጥም ይመደባል፤ልክ አንድን ኢባዳ ለአላህ ብቻ ጥርት አድርጎ እንደሚሰራው ሁሉ!, ረሱልን ሰ.ዐ.ወ እንደመውድ ይመስል። በርግጥም በአላህ ላይ መመካት ልክ እንደ ትጥበት እና ዉዱዕ እንደመፈፀምም በተለያዩ የቁርአን አናቅፅቶች ትዕዛዙም መጥቷል።እንዲሁም ከአላህ ዉጪም መመካት በጥብቅ ተከልክሏል
قال تعالى: {فاعبُدهُ وتوكّل عليه}

አላህም እንዲህ ብሏል [ እርሱን ብቻ አምልክ፣ በሱም ብቻ ተመካ]"

@islam_mindset

Читать полностью…

ISLAMIC SCHOOL 2

"የአላህ ደጋግ ባሮች በኢባዳ ላይ ሆነው ስለ ወንጀላቸው እያስታወሱ ያለቅሳሉ፤ አንተ በወንጀል ላይ ሆነህ ትስቃለህ!"
ኢብኑል ጀውዚይ

Читать полностью…

ISLAMIC SCHOOL 2

"ከሰዎች ሁሉ በላጭ ሰው ማለት የረሱልን ሱና የተገበረ ነው ሰዎች የረሷትን!"

ሙሐመድ ኢብኑ ኢስማኢል አል-ቡኻሪ

Читать полностью…

ISLAMIC SCHOOL 2

"ትንሽ ተሰርቶ ብዙ ማትረፍ!"

አሰላሙአለይኩም ወራህመቱላሂ ወበረካቱ!

አላህ አዛኝ ከመሆኑ የተነሳ ለባሮቹ ብዙ እዕሎችን በዱንያ ቀናቶች ውስጥ የተለያዩ ትሩፋቶችን አስቀምጧል። ይሄንን ያደረገው ለሚወደው ባርያው በትንሽ እድሜው ብዙ ኢባዳዎች እንዲፈፅም ሊፃፍለት ዘንድ ነው። አላህ ልዩ ያደረጋቸው ኢባዳዎች ለአንድ በአላህ ላመነ ባርያው ወንጀሎቹን ከመሞቱ በፊት ሊያስምሩት፤አልያም አላህ ዘንድ ደረጃው ከፍ እንዲል ዘንድ ሊሆን ይችላል። ነገር ግን አላህ እነዚህን ትሩፋቶች እሱ ለሚወዳቸው,አልያም ላዘነላቸው ወይም በሰፊው እዝነቱ እንዲገቡ ለፈለገው ብቻ ነው እንዲተገብሩት ሀይል እና ብርታት የሚሰጣቸው...ታዲያ ያኔ አንድ የአላህ ባርያ ይህንን ትሩፋት ከአላህ ተቸረው ማለት ትንሽ በህይወት ኖሮ ብዙ አተረፈ ይባላል!
ራሳችንን እንጠይቅ ..
ትርፍ ካመለጣቸው ውስጥ ነን ወይንስ የአላህ ትርፍ ሱስ ከሆነባቸው ውስጥ ነን?!🤔

ርዕሱን ከወደዱት ሼር ያድርጉት!
ጀዛኩሙሏህ ኸይረን!
t.me//@mind_islam

Читать полностью…

ISLAMIC SCHOOL 2

"ትልቅን ነገር መያዝ!"

አሰላሙአለይኩም ወራህመቱላሂ ወበረካቱ!
እኛ የሰው ልጆች አላህ ትልቅ አድርጎን ከፍጥረታቶቹ ሁሉ አብልጦናል። በፍጥረታት አለም ላይም የበላይ አድርጎናል። ነገር ግን ትልቅ እና ዋጋ ያለው ሆኖ መፈጠር ብቻ እንኳን አላህ ዘንድ ይቅርና በዱንያም ደረጃ ሊያስገኝ አይችልም። ትልቅን ነገር አስቦ የታሰበውን መተግርበር ግድ ይላል። በሚያሳዝን ሁኔታ ግን ዘመናችን ትልቅን ነገር ማድነቅ እንጂ ትልቅን ነገር ሰዎች በአብዘሀኛው ሲሰሩ አይታይም። የትንሽ ሰው ምልክቱ ከሞት በፊት ላለው ነገር ብቻ የሚያስብ ሲሆን የትልቅ ሰው ምልክቱ ሞትን አንድ ቀን እንደሚገናኘው አውቆ ከዚያ በኋላ ላለው ህይወት ትኩረት የሰጠ ነው። ለዚህም ነው ቁርአን ወደኛ የመጣው! ታላቅነትን ሊያስተምረን ከሞት በፊት ስንኖር ከሞት በኋላ ላለው ነገር የሚጠቅመንን ስራ እንድንሰራ እና ከሞትንም በኋላ ትንሽ ሰው ሆነን እንዳንሸበር እና እንዳንፈራ! ያኔ ትልቅ ነገር ያዝ ይባላል። በዚሁ ሚዛን ሌላ ነገር ከያዝን ምናልባችም ትልቅ የሆን እየመሰለን ትንሽ ሆነን እንኖራለን።ይህ የሚገባን ከዚች ህይወት ሰንለያይ ብቻ ነው።  ከዛ በፊት ግን አላህ ትላልቅ ናቸው ከተባሉት ባሮቹ ውስጥ እንመደብ! ትላልቅ ለመሆን እንደዘመኑ መስፈርት የበዛበት ጉዳይ ሳይሆን በአላህ ከልባችን አምነን ጥሩ ስራን ብቻ እንስራ! ስንሰራም ከዱንያ ፈልገን ሳይሆን ከአኪራ ብቻ እንደምንመነዳ አስበን ስንነሳ ትልቅ ነገርን ያዝን ይባላል። ወላሁ አዕለም!..
ttps://t.me/@mind_islam
https://instagram.com/ islamic_mindset_official
islamic_mindset_official" rel="nofollow">https://tiktok.com/@islamic_mindset_official
islamic_mindset_official" rel="nofollow">http://youtube.com/@islamic_mindset_official
http:// facebook.com/@huseros

Читать полностью…

ISLAMIC SCHOOL 2

" ሁሌ አንርሳ!"

አስላሙአለይኩም ወራህመቱላሂ ወበረካቱ!
አላህ ለሰው ልጆች ትላልቅ ተዓምራት ሰጥቷቸዋል! ሁሉም ነገሮች ካስተነተነው ተዐምር ነው። ነገር ግን የአዕምሮ ተዐምር እጅጉን ይበልጣል። ለምን ቢባል የአዕምሮ ተዐምሩ የሰው ልጆች ተሸክመውት ከመዞር ውጪ ምን ያህል ልዩ መሆኑን እስካሁን መገመት እንጂ ማወቅ አልቻሉም። ለምሳሌ ብናነሳ አይን ልዩ ተዐምር ነው ግን ተዐምርነቱ የሚታዩ ነገሮችን ማየት ላይ ይወሰናል። ጆሮም መስማት የሚችሉ ነገሮች ላይ ይወሰናል። ምላስ ነገሮች መቅመስ ላይ ይወሰናል። ከአዕምሮ ውጪ ሁሉም የአላህ ፀጋ የሚሰሩት ነገሮች ወሰናቸው ይታወቃል። ወደ አዕምሮ ስንመለስ ግን ሚስጥሩ ሁሌም አይታወቅም።ሁሌ አዲስ ነገረን ያመነጫል። አዲስን ነገር ይፈጥራል። ነገር ግን ይሄንን ስራውን ሁሌ ቦታ ከሰጠነው የእውነት የአላህ ባርያ መሆናችን አይቀሬ ነው። ሁሌ ባሰበ እና ልዩ ነገሮችን ለመፍጠር ሲነሳ የአላህ ተዓምር መሆኑን ማሰብ አንርሳ! የሰው ልጆች ለዚህ ህይወት ሲባል አዕምሯቸውን ተጠቅመዉ ልዩ የሆኑ ነገሮችን ለአለም እያበረከቱ ይገኛል። ግና እነዚህ ሰዎች ያንን የፈጠሩትን ልዩ ነገሮችን በሞት እንሚለዩት ቢያውቁትም ቢረዱትም ከሞት በኋላ ላለ ነገር አዕምሯቸውን አሳምነውት ለዚች ህይወት እንደለፉት ሁሉ ለዚያም ከሞት በኋላ ላለው ህይወት እስካለፉ ድረስ አዕምሯቸውን አልተጠቀሙበትም። ....ራሳቸውን በማመፃደቅ ግን የተጠቀሙበት ይመስላቸዋል!

ይጠቅማል ብላችሁ ካሰባችሁ ለብዙ ሰዎች እንዲደርስ ሼር ያድርጉት!

#ኢስላሚክ_ማይንድset

http;/t.me/@mind_islam

Читать полностью…

ISLAMIC SCHOOL 2

"የደስታችን ቀን!"

አሰላሙአለይኩም ወራህመቱላሂ ወበረካቱ!..

ቀናቶችን አላህ በራሱ ሀይል እና ብልሀት ይገለባብጣቸዋል። አንዱን ቀን ከፊሉን ብርሀን አድርጎ ከፊሉን ብርሀን አሳጥቶት ጨለማ ያደርገዋል። ቀናቶችን ሲፈልግ ደረጃ ያላቸው ሲያደርጋቸው ሌሎችን ቀናቶችን ተራ ቀኖች ያደርጋቸዋል። አንዳንዱን ቀናቶች ሞቃት ሲያደርጋቸው አንዳንዶቹን ደግሞ ብርድ እና ዝናባማ ያደርጋቸዋል። የአላህ ተዐምራቶች አያልቁበትም! ነገር ግን እነዚህ የአላህ ተዐምራቶች ሲገለባበጡ በህይወት ያለ ሰው በምን መልኩ ነው የሚያልፋቸው የሚለው የሰውነቱን ማንነት ይገልፀዋል።አላህ ወራቶችን እንዳሳወቀን ሁሉ ከወራቶች ደግሞ ረመዳንን አልቆት እኛ እንድንፆመዉ ነገረን እንዴት እንደምነፆመውም በነብዩ ሙሐመድ ሰ.ዐ.ወ አማካኝነት አስተማረን ረመዳን ሲያልቅ ደግሞ የመደሰቻ ቀን ብሎ አወጀለን። ነገር ግን "የኢድ ሚስጥሩ ምንድን ነው?" ብለን ጠይቀን እናውቅ ይሆን! ኢድ ማለት በኔ እሳቤ አንድ ሙስሊም ቀኑን ነብዩ ሙሐመድ ሰ.ዐ.ወ እንዳሳለፉት እያሳለፈ ወደ ኋላ በረመዳን የሰራቸውን ኢባዳዎችን ዘወር በሎ በመመልከት ከኢድ በኋላ ለመቀጠል የሚዘጋጅበት ቀን ነው።
ምክንያቱም በረመዳን ያመለጠው ነገር ካለ ተፀፅቶ ወደ ኢባዳ እንዲገባ አልያም በረመዳን የተቻለውን አቅሙን ተጠቅሞ በኢባዳ ካሳለፈም እንዲቀጥል እና እንዲጨምር ዘንድ ነው ባይ ነኝ።

እንኳን አላህ ለመደሰቻችን ቀን ለኢድ-አል ፊጥር በኢማን፣በአፊያ ፣በሰላም ሙስሊም ወንድሞቼ እና አህቶቼ አደረሳችሁ።

#ኢስላሚክ_ማይንድset
t.me//@mind_islam
Instagram.com//@islamic_mindset_official
tiktok.com/@islamic_mindset1
youtube.com//@islamic_mindset1

Читать полностью…

ISLAMIC SCHOOL 2

"የአስተሳሰባችን ካብ!"

አሰላሙአለይኩም ወራህመቱላሂ ወበረካቱ!

የሰው ልጅ ሲፈጠር አሳቢ እና ያሰበውን ነገር ተግባሪ ተደርጎ ነው። በዚህ ሂደት ላይ ህይወቱን ለመገንባት ይጣጣራል... አንዳንዶች ያሰቡትን ሳያጎድሉ በተግባር ሲተገብሩት ይታያል!ሌሎች ደግሞ ያሰቡትን ትንሽ ይተገብሩት እና ይተውታል። ሌሎች ከናካቴው በሀሳብ ጀምረው በሀሳባቸው የሚቋጩም አይጠፉም። ይሄ የሚያመለክተው የሰው ልጅ ማንኛውንም ተግባር ሊፈፅም ሲል እንደሚያስብ ነው። በዚህ አስተሳሰብ" ሳላስበው ነው የፈፀምኩት" የሚለው ቃል ትርጉም አልባ ነው። እኛ ማለት የአስተሳሰባችን ካቦች ነን። ይሄ አንድ የሚደንቅ ነገር ቢሆንም ሌላው ግን መታየት ያለበት የአስተሳሰቦቻችን ብሎኬቶች ምንድን ናቸው!? የሚለውን መመለስ ነው። ነገሮች ባጠቃላይ እንደ ሀሳብ መጥፎም ሆነ ጥሩ የየራሳቸው ምክንያቶች አሏቸው። ነገር ግን እነዚህ የተለያዩ ሀሳቦች በምናምንባቸው እና በተቀመጠላቸው ሚዛን ሲመዘኑ ውድቅ ይሆናሉ... አልያም ያልፋሉ! ስለዚህ የእኛ አስተሳሰባችን በምን የተመዘነ እና የተቃኘ መሆኑን መመርመር ይጠበቅብናል። የአስተሳሰቦቻችን ጥልቀት እና ድርጊቶች የኛን እምነት(ኢማንን) ይገልፃሉ። ከዚህም በላይ አንዳንዴም ልንቆጣጠራቸው የማንችለው ድርጊቶች አሉ። ቅፅበታዊ እና ድንገታዊ ሲሆኑ! እነዚህ ድርጊቶች የኛን የአስተሳሰብ ብሎኮችን ያመላክታሉ። ይሄንን አጀንዳ ለማንሳት የፈለግነው ምክንያት በአፋችን አብዘሀኛው ሙስሊም በተለይም ወጣቶች ኢስላምን እንደምንተገብር እናስባለን ግና እንደምናስበው ነን!? የሚለውን ትኩረት እንድንሰጥበት ነው። የአስተሳሰባችን ባንዲራ ቁርአን እና ሀዲስ መር ሳይሆን ቁርአን አልያም ሀዲስን እኛ ልንገልፀው አንችልም...ምክንያቱም እንደሚገባው በሀሳባችን አላብላላነውም የሀሳባችን አካል የእውነት አላደረግነውም። ምን ያህል እንደምናስበው ነን? ኢስላምን እንደምናውቀዉ እያሰብነው ነው!?🤔
እነዚህን ሁለት ነገሮችን ግዜ ሳንሰጥ በወጣትነታችን ህይወት  መመለስ ይኖርብናል። አላህ አስተሳሰቦቻችንን እንድናስተካክል በጣም ብዙ እድሎች እንደሰጠን እናስብ እና እንተግብረው። በአላህ ፈቃድ ስንተገብረው ከቅጣት ነፃ ከሚሆኑት ባሮቹ እንሆናለን።...ጀዛኩሙሏህ ከይረን!

ጠቃሚ ነው ብላችሁ ካሰባችሁ ሌሎች ትምህርቶች እንዲደርሳቸው ቻናላችንን ለምትወዱት ሰው ያጋሩ!

#ኢስላሚክ_ማይንድset!
t.me//@mind_islam
Instagram.com//@islamic_mindset_official

Читать полностью…

ISLAMIC SCHOOL 2

https://www.youtube.com/live/a_DpQGc3j1c?feature=share

Читать полностью…

ISLAMIC SCHOOL 2

"ራስህን የመመልከት ጥበብ!"

አሰላሙአለይኩም ወራህመቱላሂ ወበረካቱ!
እንደምን አላችሁ ውድ ወንድሞች እና እህቶች ፤ አባቶች እና እናቶች በዛሬው እለት የመረጥነው ርዕስ ሰፊ መሆኑ እርግጥ ነው። ነገር ግን በዛሬ የምክክር ፕሮግራማችን ልንወሳሳ የፈለግነው በኢስላም ደረጃ ላይ ራሳችንን መመልከት ነው። የቀን ከቀን ዉሏችን በጠቅላላ ራሳችንን የምንመለከትበት ቢሆንም በዘመናችን ራሳችንን ከመመልከት ይልቅ ራሳችንን ረስተን ሰውን የምንመለከትበት መንገዶች እንደ ፀጉራችን መብዛታቸው የማይካድ ነው። ይሄንን ለማስተካከል ዘንድ በመጀመሪያ ለራሳችንን ጠጣር በሆኑ ነገሮች ጠጠር ያሉ  ጥያቄዎችን ማንሳት ይኖርብናል ራሳችንን መመልከት ከፈለግን ! ይሄም ምንድን ነው ከተባለ ነብዩ ሙሀመድ ለምንድን ነገር ነበር ትኩረት ይሰጡ የነበረዉ በህይወታቸው ሲኖሩ? ብለን መጠየቅ ይጠበቅብናል። በተዘዋዋሪ ይሄንን ራስህን ጠየክ ማለት ተምሳሌት አድርገህ የያዝካቸውን  የመጨረሻ ነብይህን  ሙሀመድ(ሰ.ዐ.ወ)  መስታወትህ አድርገሀቸዋል ማለት ነው።ያኔ ራስህን የመመልከት ደረጃ ላይ ደርሰሀል። ረሱል ሰ.ዐ.ወ በህይወታቸው መጀመሪያ ላይ ለታላቅ ተልዕኮ ከመታጨታቸው በፊት በመጀመሪያ የከወኑት ራሳቸውን ከተበላሸ ማህበረሰብ ተገለው በስፋት ራሳቸውን መመልከት እና የዚህን አለም ሚስጥር ለመመርመር ብሎም የሰው ልጅ ለምን እንደተፈጠረ በእውነት ማወቅ ነበር። ከሰው ልጆች ዉስጥ ደግሞ ነብዩ ሙሀመድ ናቸው። የመነጠላቸው ሚስጥር የተበላሸ የመሀይማን እውነታ በርሳቸው ዘመን ሰለጎለበተ ነበር። ልክ አሁን እንዳለንበት ዘመን ማለቴ ነው። ግና ሲታሰብ አሁን ያለንበት ዘመን ሳይብስ አልቀረም ባይ ነኝ። በዚህ ከማህበረሰብ የመነጠል ሂደት በይበልጥ ራሳቸውን መመልከት እና ከብልሹ ማህበረሰብ የተበላሸ ሰው ላለመሆን ነው። ነገሩ እንደዚህ ከሆነ እኔ እና አንተ ስለራሳችን ብቸኛ ሆነን የምንመለከትበት ግዜና ቦታ ማመቻቸት ይጠበቅብናል። ራስን ለመመልከት ዘንድ ማለት ነው! በዚህ ራስን በመመልከት ሂደት የምታስበውን፣ የምትፈፅመውን፣ ለመፈፀም ያልቻልከውን ጥሩም ሆነ መጥፎ ነገር ምንም ሳይደበቅ ይታያል። ብልጥ እና ብልህ ከሆንክ ስለ መጥፎ የሰራሀቸውን ነገሮች እንዴት እንደምታስተካክላቸው አልያም እንደምትተዋቸው ትወስናለህ። አላህ ካዘነልህ ደግሞ ልትፀፀትም ችለህ አይንህ ሊያነባ  ይችላል። ይሄ ደግሞ ጥላ በሌለበት ጥላ ከሚጠለሉ ሰዎች መሀል መሆንህን ነብይህ ሙሀመድ ሰ.ዐ.ወ ነግረውሀል። ምክንያቱም ለብቻህ ሆነህ መጥፎ ወንጀሎችን አላህ የከለከላቸውን ነገሮች አስታውሶ ማልቀስ መፀፀት እንደዘመናችን በካልኩሌሽን የሚገኝ ሳይሆን የኢማን ነበልባል መኖሩ ቅርወት የሌለው ነገር ነው! ይሄ ሁሉ እንግዲህ ማለትም ራስህን ስትመለከት አንተነትህን ከአላህ ጋር ያለህን ግንኙነት የማስተካከል እና የማጥበቅ እድል ይኖራሀል፤ ራስህን ስትመለከት ከሰዎች ጋር በምን አይነት መልኩ ግንኙነት መፍጠር እና በምንስ አይነት ግንኙነትህ መቋረጥ እንዳለበት ታውቃለህ። ልብ በል ራስህን ስትመለከት በመጀመሪያ አላህ ግዴታ ያደረገብህን ነገር ከመመልከት ጀምር..ከዚያም ወደ ሱና ኢባዳዎች...ከዚያም ወደ ፀባይህ ተመልከት! ፀባይህን ስትመለከት ያንተን ፀባይ በሌሎች ሰዎች እንዳለ አስበህ መዝን!..እንደዚህ በየጀረጃው መመልከትህን ቀጥል...!

/channel/mind_islam
http://youtube.com/islamic_mindset1
http://tiktok.com/islamic_mindset1
http://instagram.com/islamic_mindset_official

ጀዛኩሙሏህ ከይረን!
አሰላሙአለይኩም ወራህመቱላሂ ወበረካቱ.

Читать полностью…

ISLAMIC SCHOOL 2

የሰዉ ልጅ ልክ እንደ እንሰሳ በቂያማ ቀን አፈር ሁን አይባልም። ይቀጥላል ህይወቱ! ነገር ግን በዘመናችን ይሄንን የረሳን ይመስላል..አላህ ይዘንልን!!
/channel//mind_islam

Читать полностью…

ISLAMIC SCHOOL 2

ይመለስናል እንጂ ሁሉም ነገር በዚች ዱንያ ሳለን ግዜያዊ ነው ያልፋል ነገር ግን እነዚያ ያለፉት ነገሮች አላህ ዘንድ ደረጃ ታገኝባቸዋለህ አልያም ትቀጣባቸዋለህ።ማስተንተን እና መምረጥ ያንተ ድርሻ ነው።
/channel//mind_islam
(ሊንኩን ሼር በማድረግ አሻራዎን ያሳርፉ!)

Читать полностью…

ISLAMIC SCHOOL 2

ሰዎች በአሁን ግዜ ወደፊት ምን መሆን እንደሚፈልጉ እና ምን መሆን እንዳለባቸው ሲራቀቁ መመልከት በብዛት እንታዘባለን።ከራሳችን ጀምሮ ነገር ግን አሁን ላይ ምን እንደሆን ራሳችንን አንረዳም ምክንያቱም ያለፉ ዘመናቶች እና ትርክቶች በፎርጂድ ካሴት አዕምሯችንን ስለሞላነው ይሆናል።ለዛም ነው ትክክለኛውን የሶሀብችን ብሎም የነብዩን ሰ.ዐ.ወ ታሪክን የማናጠናው! አላህ ይዘንልን!
@islam_mindset

Читать полностью…

ISLAMIC SCHOOL 2

በጥልቀት ሰዎችን የተመለከተ ሰው አብዘሀኛውን አላህን ከማስታወስ የተዘናጉ ሆነው ያገኛቸዋል። የሚጠቅማቸውን እና የሚጎዳቸውን በቅጡ መለየት ላይ ጥሬ ሆነው ያገኛቸዋል። በተግባራቸው አኪራቸውን አበላሽተው ዱንያቸው ቢስተካከልላቸው የሚመርጡ ሰዎችን ያገኛል። ነገር ግን የዚህ ሰው ትልቅነት የሚመዘነው ራሱ እንዳያቸው ሰዎች ውስጡን ሲመረምር ብቻ ነው። እንደምታያቸው እና እንደምትታዘባቸው ሰዎች ነህ!?

@Islam_Mindset

Читать полностью…

ISLAMIC SCHOOL 2

https://youtu.be/wJ22mql5xQU

Читать полностью…

ISLAMIC SCHOOL 2

"አንድም ሰው የለም በህይወት ሳለ ሀዘን እና ደስታ ቢፈራረቅበት እንጂ፤ ነገር ግን ደስታን አላህን ማመስገኒያ አድርጉት, ሀዘንን ደግሞ ትዕግስት አድርጓት!"
ኢክሪማ (ረዲየላሁ አንህ)

Читать полностью…

ISLAMIC SCHOOL 2

"አላህ እንሰሳ ሳይሆን ሰው አድርጎ ፈጥሮህ፤በህይወት አኑሮህ ወደሱ እንድትቃረብ እድሉን ሰጥቶህ መጠቀም ካቃተህ እንዴት አላህ በዱንያ ሳለህ ይርዳህ ከዚህ በላይ!"
@islam_mindset

Читать полностью…

ISLAMIC SCHOOL 2

በሶሻል ሚዲያችን በዩትዩብ በአጭር ግዜ ውስጥ ብዙ እይታ ካፈሩት ቪዲዮዎቻችን አንዱ "አላህ መርጦሀልን?" በሚል ርዕስ የተዘጋጀው ስራችን ነው። በርግጥም የአብዘሀኛውን ህይወትን እና ባህሪ የሚነካ እንደመሆኑ መጠን ለመታየት ምክንያት ሊሆን ይችላል። በዩትዩብ ቻናላችንን በመጎብኘት የተለያዩ አስታዋሽ መልዕክቶችን ይከታተሉ!
እናመሰግናለን!
@islam_mindset

Читать полностью…

ISLAMIC SCHOOL 2

https://youtu.be/O3GyKzUz7mo

Читать полностью…

ISLAMIC SCHOOL 2

youtube// @arebgenda_mesjid ​
t.me// @arebgendamesjid
Instagram // arebgenda_mesjid
tik tok //arebgenda_mesjid
Facebook //mesjid5043

በመጎብኘት የማህበረሰብ ሚዲያዎቻችንን በሚለቀቁ ትምህርቶች እና ጠቃሚ ምክሮች ይከታተሉ።
የአረብ ገንዳ መስጂድ ወጣቶች የሚዲያ ማዕከል

Читать полностью…

ISLAMIC SCHOOL 2

      " ጊዜን እንዴት እንቅደመዉ! "


አሰላሙአለይኩም ወራህመቱላሂ ወበረካቱ!

ውድ ሙስሊም ወንድሞች እና እህቶች አባቶች እና እናቶች እንደምን አላችሁ። ዛሬ ደግሞ ስለ ህይወታችን እንነጋገራለን። ስለማይቆመው እና መሄዱን ስለማያቋርጠው፤ ህይወት የሚለው ቃል ትርጉም የሚያገኘው ጊዜ ሲኖረው መሆኑን ምን ያህል ግን አስተውለናል። በህይወት የሚኖሩ ሰዎች ህያው ሲባሉ ግዜ አልቆባቸው በህይወት የማይኖሩ ግና አሁን በመቃብር ውስጥ ያሉት ሰዎች ሙታን ይባላሉ። ልዩነቱ ግዜ መኖር እና አለመኖር መሆኑ በአይናችን የምናየው እውነት ነው።። ጊዜ እስካለን ድረስ ስራ መስራታችን አይቀሬ ነው። ግና እየሰራን ያለነው ስራ እና አሰራራችን ጊዜን ተጠቃሚ አልያም ጊዜን አባካኝነታችንን ያመላክታል። በኢስላም ስራን ስንመዝን እና በዓለማዊ ህይወት ስራን ስንመዝን  ስንመዝን ፍፁም ለየቅል ሆኖ እናገኘዋለን። ነገሩ እንዲህ ነው!.. ለዓለማዊ ነገሮች ስራ ስንሰራ አንድ ቀን የሰራነው ይቆማል ከዚያም ቤተሰቦቻችን አልያም ቅርብ የሆኑ ሰዎች ወይም ሌሎች ሰዎች  ስራውን ያስቀጥሉታል ለራሳቸው ሲሉ ማለት ነው።ምክንያቱም ስራውን የምንሰራው እኛ በህይወት እስካለን ድረስ ነው። ህይወታችን ደግሞ አላቂ ነው። ህይወታችን ካለቀ በኋላ የምንኖረው እና የምንጓዘው መንገድ ደግሞ ምን ያህል እንሆነ ለመገመት እንኳን ከግምት በላይ ነው። ስለዚህ ግዜያችንን የተጠቀምንበት እየመሰለን ለዓለማዊ ስራ ብቻ አዋልነው ማለት የተሰጠን ግዜ ለረዝሙ ጉዞ ስንቅ አልሆነንም ...በሌላ ቋንቋ ግዜያችን ባክኗል ማለት ነው። ባጭሩ ግዜያችንን ቀደምነው ማለት ሳይሆን ለዘላለም ቀደመን ማለት ነው። ነብዩ ሙሀመድ (ሰ.ዐ.ወ) በሀዲሳቸው የአኪራ አንድ ቀን ለዱንያ አንድ ሺ አመት መሆኑን ነግረውን ነበር። የአኪራውን አንድ ቀን ከዱንያው አንድ ቀን ጋር ሲነፃፀር 1/1000 አልያም የዱንያ አንድ ቀን ለአኪራ 0.001 መሆኑን ማወቅ ይጠበቅብናል። ነገሩ እንዲህ ከሆነ የዚች አለም ቀናቶች ምንም አይደሉም ማለት ነው። አላህ ለጥሩ ነገር ልባችንን ያጠንክረው እና ግዜአችንን ለመጪው አለም አልያም ለአኪራ ግዜያችን አደረግነው ማለት ማብቂያው ለማይታወቀው ረዝም ጉዞ ስንቅ ያዝን ማለት ነው። በነገራችን ላይ በዚች አለም ስንኖር ለመኖር ዘንድ ስራ መስራት ይኖርብናል። ነገር ግን ልባችንን ጥለን ቢያንስ እንኳን ግዴታ የሆኑብንን ኢባዳዎች መተግበር ሊሳነን አይገባም። ቅድሚያ ለዲነል ኢስላም መሆን ይገባል። ያኔ በሚያልቀው ግዜ የማያልቀውን የዘላለምን ግዜ እንዲቸረን ከአላህ ሰበብ ይሆንልናል። በዚህ ብቻ ግዜን መቅደም እንችላለን ብልጥ ከሆን ማለቴ ነው!

አሰላሙአለይኩም ወራህመቱላሂ ወበረካቱ! 

/channel/@mind_islam
https://instagram.com/ islamic_mindset_official
islamic_mindset1" rel="nofollow">https://tiktok.com/@islamic_mindset1

Читать полностью…

ISLAMIC SCHOOL 2



​​👉ለመላው የእስልምና እምነት ተከታዮች እንኳን ለ1444ኛው የኢድ-አልፈጥር በዓል አደረሰን😍

ኢድ ሙባረክ!🌙

Читать полностью…

ISLAMIC SCHOOL 2

"ዝንባሌ "

አሰላሙአለይኩም ወራህመቱላሂ ወበረካቱ! የዛሬው የምክር ፅሁፋችን ለየብቻችን ለራሳችን የምንጠይቅው ርዕስ እንደሆነ ግልፅ ነው። ዘመናችን በአስተያየት በአመለካከት አረም የበዛበት ግዜ ነው። ይህ ሌሎች ትርጉሞች የመስጠት አቅም ቢኖረውም እዚህ ላይ ልንረዳ የሚገባን ነገር ሰዎች እንደመሆናችን መጠን አስተያየት እና ምልከታ ብሎም አመለካከት መኖራችን አይቀሬ ነው። ነገር ግን  ይህ በመለኪያ ሚዛን መመዘን ካቃተን ዝንባሌዎቻችን ከሚዛኑ በልጧል ማለት ነው።ልብ እንበል ነብዩ ሙሀመድ ሰ.ዐ.ወ መልዕክተኛ ሆነው ከአላህ ሲላኩ ሰዎች በመጀመሪያ የጥሜትን መንገድ የጀመሩት በዝንባሌያቸው መገታታቸው መሆኑ መረሳት የለበትም። እኛ 360 ጣኦታትን ትተን አንድን አምላክ እናምልክ እንዴ ማለታቸው ታላቁ የነሱ ዘመን መገለጫ ሲሆን በኛ ዘመን ደግሞ 360 ጣኦት በላይ ለመቁጠር አዳጋች በሆነ መልኩ በምክንያት የተረጋገጠ በሚመስል እውነታ በውስጡ እውነትን ሳይዝ ውሸት እውነት በመሰለ ጥሩነቱ በሀቅ ያልተመዘነ  ዝንባሌያችን  የኛ ዘመን ጣኦት መሆኑ እርግጥ ነው። ዝንባሌ እምነትን የመግለፅ አቅም አለው። ሁሉም ሰው በዝንባሌው ውሎ በዝንባሌው ያድራል። ያለ ዝንባሌ በህይወት የሚኖር ሰው የለም። ሁላችንም የእያንዳንዱ የቀን ውሏችን የምንውልበት መንገድ የኛን ዝንባሌ በምንውልበት ቦታ ይገለፃል። የምንማረው ትምህርት ዝንባሌያችንን ያመለክታ ዝንባሌያችን ግን በተግባር ይረጋገጣል። ስለዚህ ራሳችንን መመልከት ማለት ተግባራችንን እንጂ እውቀታችንን መሆን የለበትም። ምክንያቱም የምንተገብረው ተግባር ለተማርነው እውቀት ዝንባሌያችን የምንገልፅበት መሆኑን እንረዳ... እያንዳንዱ ሰው በራሱ ከሚውልበት ቦታ ሌሎችም ሌላ ቦታ ይውላሉ... ያድራሉ። ወደድነውም ጠላነውም.. ነገር ግን በምንውልበት ቦታ አላህን ማስታወስ እና የአላህን ተዕምር መመልከት ከዚያም ሱናቸውን በእያንዳንዱ እንቅስቃሴያችን መተግበር የቻለ ሰው ትልቁ ትክክለኛው የዝንባሌ ጣራ መሆኑን እንረዳ! ለዚህም ነው ነብዩ ሙሀመድ ሰ.ዐ.ወ ያሉት ( ማናችሁም አላመም የውስጥ ስሜቱ እኔ ለመጣሁበት መንገድ ወዶ መከተል እስካልቻለ ድረስ...)  ብለዉ የወህይ ቃላታቸውን ለኛ የሰጡን...
ዝንባሌያችን ከየትኛው ይሁን!?

የቴሌግራም ቻናላችንን join ይበሉ ሌሎችም እንዲደርሳቸው ሼር ያድርጉት።
t.me//@mind_islam

Читать полностью…

ISLAMIC SCHOOL 2

https://www.youtube.com/live/EfuhBv84e_o?feature=share

Читать полностью…

ISLAMIC SCHOOL 2

https://youtu.be/LjPDEGiV13E

Читать полностью…
Subscribe to a channel