በትሕትናው ልዕልናን ላገኘ፣ ለፍጥረታት ባለው ርኅራኄ የአምላክ እናትን ለሚመስል፣ የተቸገሩትን ፈጥኖ መርዳት ልማዱ ላደረገው፣ የእግዚአብሔር ሠራዊት አለቃ፣ ደግ እና ሰውን ወዳጅ ለሆነው መልአክ ለቅዱስ ሚካኤል ዓመታዊ በዓል እንኳን በሰላም አደረሰን።
ቅዱሳን መላእክት በአንድ ኃጢአተኛ ወደ እግዚአብሔር መመለስ የሚደሰቱትን ያህል፣ ባልተመለሰው ኃጢአተኛ ደግሞ እንዲሁ ያዝናሉ። በአንዱ ኃጢአተኛ መመለስ የተሰማቸውን ደስታ ፈጣሪያቸውን በማመስገን እንደሚገልጹ፣ ባልተመለሰው ኃጥእ የተሰማቸውን ኃዘን ደግሞ አምላካቸውን "ማረው፣ ይቅር በለው" ብለው በመለመን ያሳያሉ። (ያዕ 5፥13) ቅዱስ ሚካኤል አሁን እንዴት እንደ ሆንን አይቶ ይዘንልን፣ አዝኖም ይለምንልን፣ ለምኖም ያስምረን!!!
ዲያቆን አቤል ካሳሁን
ሰላም ጎዶኞቼ !!
በዲያቆን አባይነህ ጋባዥነት ዛሬ ወደ ጽዋ ቲዩብ እየሄድኩ ነው። በዚያ እንገናኝ !!
https://youtube.com/channel/UCRMvaTDo4oZhDjqaUljwFog
ሻሎም ! ሰላም
የኢየሱሰ ክርስቶስ ስሞች ክፍል አንድ
1. ሁሉን ቻይ - “ያለውና የነበረው የሚመጣውም ሁሉንም የሚገዛ ጌታ አምላክ፡— አልፋና ዖሜጋ እኔ ነኝ ይላል። ራዕ1:8
2. አልፋ እና ኦሜጋ - “እኔ አልፋና ኦሜጋ ፣ ፊተኛውና መጨረሻው ፣ መጀመሪያ እና መጨረሻው እኔ ነኝ” ራእይ 22:13
3. ኢየሱስ “ እነሆም፥ ትፀንሻለሽ ወንድ ልጅም ትወልጃለሽ፥ ስሙንም ኢየሱስ ትዪዋለሽ። ሉቃ 1:31
4. የእምነታችን ፈጻሚ - " የእምነታችንንም ራስና ፈጻሚውን ኢየሱስን ተመልክተን፥ በፊታችን ያለውን ሩጫ በትዕግሥት እንሩጥ፤ ዕብ. 12 2
5. ክንድ - “ “የያዕቆብንና የዮሴፍን ልጆች፥ ሕዝብህን በክንድህ አዳንሃቸው።” መዝሙር 76፥1
6. የሕይወት እንጀራ - “ኢየሱስም እንዲህ አላቸው፦ የሕይወት እንጀራ እኔ ነኝ፤ ወደ እኔ የሚመጣ ከቶ አይራብም በእኔ የሚያምንም ሁልጊዜ ከቶ አይጠማም።”የሐ 6:35
7. የእግዚአብሔር ልጅ - “እነሆም ፣ ከሰማይ የመጣ ድምፅ“ በእርሱ ደስ የሚለኝ የምወደው ልጄ ይህ ነው ”አለ። ማቴ. 3:17
8. ሙሽራው - “ኢየሱስም አላቸው- “ ሙሽራው ከእነርሱ ጋር እስከሆነ ድረስ የሰርጉ ተጋቢዎች ሊያዝኑ ይችላሉን? ሙሽራው ከእነርሱ የሚወሰድበት ቀናት ይመጣሉ በዚያን ጊዜም ይጦማሉ ፡፡ ማቴ. 9 15
9. የማዕዘን ራስ - “ግንበኞች የናቁት ድንጋይ እርሱ የማዕዘን ድንጋይ ሆነ”። መዝ. 118 22
10. አዳኝ - “ ከሙታን ያስነሣውን ልጁን ከሰማይ እስኪመጣ መጠበቅ ፣ ከሚመጣው ቁጣ የሚያድነን ኢየሱስን” 1 ተሰ 1 10
11. ታማኝ እና እውነተኛ - “ሰማይ ሲከፈት አየሁ ከእኔም በፊት ነጭ ፈረስ ነበረ ፣ በላዩም ታማኝ እና እውነተኛ ይባላል። በፍትህ ይፈርዳል እንዲሁም ይከፍላል ፡፡ ” ራእይ 19 11
12. መልካም እረኛ - “እኔ ጥሩ እረኛ ነኝ። መልካሙ እረኛ ነፍሱን ስለ በጎቹ ያኖራል ፡፡ ” ዮሐ 10 11
13. ታላቁ ሊቀ ካህናት - “ስለዚህ ፣ እኛ ሰማያትን የሚያልፍ ታላቅ ሊቀ ካህናት የእግዚአብሔር ልጅ ኢየሱስ ስላለን ፣ ኑዛዛችንን አጥብቀን እንያዝ ፡፡ ዕብ. 4 14
14. የቤተክርስቲያኗ ራስ - “እናም ሁሉንም ከእግሩ በታች አስገብቶ በሁሉ ላይ የበላይ አድርጎ ለቤተክርስቲያን ሰጠው።” ኤፌ. 1:22
15. ቅዱስ አገልጋይ - “… እናም ለመፈወስ እጅህን ስትዘረጋ ባሮችህ ባሪያዎችህ በሙሉ ቃልህ እንዲናገሩ ፍቀድላቸው በቅዱስ አገልጋይህም በኢየሱስ ስም ምልክቶች እና ድንቆች ይከናወናሉ ፡፡ ” ሐዋ 4 -30
16. እኔ ነኝ - “ኢየሱስም አላቸው። እውነት እውነት እላችኋለሁ ፣ አብርሃም ከመወለዱ በፊት እኔ ነበርኩ። ዮሐ 8 58
17. አማኑኤል - “… ወንድ ልጅ ትወልዳለች ስሙንም አማኑኤል ብላ ትጠራዋለች ፣ ትርጉሙም‹ ከእኛ ጋር እግዚአብሔር ›ማለት ነው ፡ 7 14
18. በቃላት ሊገለጽ የማይችል ስጦታ - “ ለማይነገር ስጦታው እግዚአብሔር ይመስገን ፡፡ 2 ቆሮ. 9 15
19. ፈራጅ - “እርሱ በሕያዋንና በሙታን ላይ ፈራጅ ሆኖ የሾመው እርሱ ነው።” የሐዋርያት ሥራ 10:42
20. የነገሥታት ንጉስ - “እነዚህ በጉን ይወጋሉ ፤ በጉም የጌቶች ጌታ እና የነገሥታት ንጉስ ስለሆነ ድል ይነሣል ፣ ከእነርሱም ጋር ያሉት የተጠሩና የተመረጡ የታመኑም ድል ይነሣሉ። ራእይ 17:14
21. የእግዚአብሔር በግ - “በማግስቱ ዮሐንስ ኢየሱስን ወደ እርሱ ሲመጣ አይቶ“ እነሆ የዓለምን ኃጢአት የሚያስወግድ የእግዚአብሔር በግ ”አለ ፡ ዮሐ 1 29
22. የዓለም ብርሃን - “እኔ የዓለም ብርሃን ነኝ ፤ የሚከተለኝ ሁሉ በጨለማ አይመላለስም የሕይወት ብርሃን ግን ይኖረዋል” ዮሐ 8 12
23. የይሁዳ አንበሳ - “ከእንግዲህ ወዲህ አታልቅስ; እነሆ ፣ ከይሁዳ ነገድ አንበሳ ፣ የዳዊት ሥር ፣ ጥቅልሉንና ሰባቱን ማኅተሞቹን ይከፍት ዘንድ ድል ነሥቷል ፡፡ ራእይ 5 5
24. የሁሉም ጌታ - “በዚህ ምክንያት ደግሞ እግዚአብሔር ከፍ ከፍ አደረገው ፣ ከስምም ሁሉ በላይ የሆነውን ስም ሰጠው ፣ ስለዚህም በሰማይና በምድር ካሉ ሁሉ በኢየሱስ ስም ይንበረከኩ ዘንድ። ለእግዚአብሔር አብ ክብርም ከምድርም በታች ምላስም ሁሉ ኢየሱስ ክርስቶስ ጌታ እንደ ሆነ ይመሰክር ዘንድ ነው። ፊል. 2 9-11
25. ክርስቶስ ቀ- “አንድ እግዚአብሔር አለና በእግዚአብሔርና በሰውም መካከል አንድ መካከለኛ ደግሞ አለ እርሱም ሰው የሆነ ክርስቶስ ኢየሱስ ነው ፡፡ 1 ጢሞ. 2 5
26. መሲህ - “መሲሑን አገኘነው” (ማለትም ክርስቶስ) ፡ ዮሃንስ 1:41
27. ኃያል - “በዚያን ጊዜ እኔ እግዚአብሔር አዳኛችሁ ፣ ቤዛህ ፣ የያዕቆብ ኃያል እንደሆንሁ በዚያን ጊዜ ያውቃሉ።” ነው 60 16
28. ነፃ የሚያወጣው - “ስለዚህ ልጁ ነፃ ካወጣችሁ በእውነት ነፃ ትሆናላችሁ” 8:36
29. ተስፋችን - “ ተስፋችን ክርስቶስ ኢየሱስ።” 1 ጢሞ. 1: 1
30. ሰላም - “ሁለቱን ቡድኖች አንድ ያደረገው እርሱም የጠላትን መለያየትን ግንብ ያፈረሰ እርሱ ራሱ ሰላማችን ነውና” ኤፌ. 2 14
31. የነቢይ ነቢይ “ኢየሱስም አላቸው። ነቢይ በትውልድ አገሩ ፣ ከዘመዶቹም ከቤተሰቡም በቀር ክብር አይሰጥም አላቸው። ማርቆስ 6 4
32. ቤዛ - “ እኔን ግን የሚቤዠኝ ሕያው እንደ ሆነ፥ በመጨረሻም ዘመን በምድር ላይ እንዲቆም፥
ኢዮብ 19:25
33. ትንሳኤ- “ኢየሱስ ክርስቶስ በቅዱሳት መጻሕፍት መሠረት ስለ ኃጢአታችን እንደ ሞተ ፣ እንደ ተቀበረ ፣ በቅዱሳት መጻሕፍት መሠረት በሦስተኛው ቀን እንደተነሣ ፡፡ 1 ቆሮ. 15 3-4
34. አለት - “ከተከተላቸው ከመንፈሳዊው ዓለት ጠጥተዋልና ፣ ዓለትም ክርስቶስ ነበር” 1 ቆሮ. 10 4
35. መስዋእትነት - “ይህ ፍቅር ነው ፤ እግዚአብሔርን እንደወደድን አይደለም ፤ እርሱ ግን እኛን እንደ ወደደን ስለ ኃጢአታችንም ማስተስሪያ አድርጎ ልጁን እንደ ላከ ነው እንጂ። 1 ዮሐንስ 4 10
36. አዳኝ - “ዛሬ በዳዊት ከተማ አዳኝ ተወልዶላችኋልና እርሱም ክርስቶስ ጌታ ነው።” ሉቃስ 2 11
37. የሰው ልጅ - “የሰው ልጅ የጠፋውን ሊፈልግና ሊያድን መጥቶአልና።” ሉቃስ 19 10
38. የልዑል ልጅ - “እርሱ ታላቅ ይሆናል የልዑል ልጅም ይባላል። ጌታ እግዚአብሔር የአባቱን የዳዊትን ዙፋን ይሰጠዋል። ” ሉቃስ 1 32
39. ከሁሉ በላይ ፈጣሪ - “በሰማያትም በምድርም ሁሉ ፣ የሚታዩ እና የማይታዩ ፣ ዙፋኖች ወይም ገዥዎች ወይም ገዥዎች ወይም ባለሥልጣናት ሁሉም በእርሱ ተፈጥረዋል በእርሱ እና ለእርሱ ሁሉም ነገሮች ተፈጥረዋል ፡ እርሱ ከሁሉ በፊት ነው በእርሱም ነገሮች ሁሉ ተጣመሩ… ” ቆላ 1 16-17
40. ሕይወት - “ኢየሱስም“ እኔ ትንሳኤ እና ህይወት እኔ ነኝ ፤ በእኔ የሚያምን ቢሞቱም እንኳ በሕይወት ይኖራል ”አላት ፡ ዮሐንስ 11:25
41. በር - “እኔ በሩ ነኝ ፡ ማንም በእኔ በኩል ቢገባ ይድናል ወደ ውስጥም ይወጣል ወደ ውጭም ግጦሽ ያገኛል ፡፡ ዮሐንስ 10: 9
42. መንገድ - “ኢየሱስ መለሰ ፣“ እኔ መንገድና እውነት ሕይወትም ነኝ ፤ በእኔ በቀር ወደ አብ የሚመጣ የለም ” ዮሐ 14 6
43. ቃል- “በመጀመሪያ ቃል ነበረ ፣ ቃልም በእግዚአብሔር ዘንድ ነበረ ፣ ቃልም እግዚአብሔር ነበረ።” ዮሐንስ 1: 1
44. እውነተኛ የወይን ግንድ - “እኔ እውነተኛ የወይን ግንድ እኔ ነኝ ፣ የወይኑም ገበሬ አባቴ ነው” ዮሐንስ 15: 1
45.
ነጭ ነጯን መነጋገር ጀምረናል !!
https://www.youtube.com/watch?v=oFcK6WLmAuU&feature=share
መረጃ tv ላይ ገና አልተጀመረም ታገሱ ። በመረጃ tv ዩቲዩብ እና ፌስቡክ ቀጥታ እያስተላለፈ ስለሆነ እዛ ላይ ሲጨርስ በ tv ይተላለፋል ።
ታገሱ!
ላልተማከለው አደረጃጀት ልምድ እንለዋወጥ!
-------------------------
ባለፈው እንደተወያየነው ራሳችንን፣ ቤተሰባችንንና አብያተ ክርስቲያናትን ከጥቃት ለመከላከል ባልተማከለ ደረጃ መደራጀታችንን ከቤተሰብ እንድንጀምር ተመካክረን ነበር፡፡
እንደተነጋገርነው የተደራጁ ቡድኖች በስም ለይተውን፣ የአገዳደላችንን መንገድ መርጠውልን፣ ልጆቻችንን በፊታችን አርደው፣ ሚስቶቻችንንና እህቶቻችንን በፊታችን ደፍረው፣ በዶለዶመ ቢላ ከማንጅራታችን ሊያርዱን የሚጠብቁት አጋጣሚዎችን ብቻ ነው ብለን ነበር፡፡
ይኸው ከሰሞኑ በቤንሻንጉል ጉሙዝ ዘግናኙን አገዳደላችንን አሳይተውናል፡፡ የቀሪውን ሕሊና በሚያቀውስ ጭካኔ ሊገሉን፣ ተራፊው የሚጎርሰው እንዲያጣ ያለንን ሁሉ በእሳት ሊያጋዩት የቤታችንን በር ሰብረው መግባታቸውን ቀጥለዋል፡፡
አሁንም በጉባ ወረዳ ሞታችንን ለመከላከል ማንም ከጎናችን አልቆመም፡፡ ይኸው አሁንም ሬሳችን እንኳ አፈር ናፍቆታል፡፡ ከግድያ የተረፉ እናቶቻችንና ልጆቻችን ከአውሬ የተረፈ በድናችንን ለመቅበር በመማጸን ቀሪ እንባቸውን እየጨረሱ ነው፡፡ በጥቅምትም በሰኔም የሆነው፣ ቅዱስ ሲኖዶስም በጥናት አረጋግጦ የነገረን፣ አሁንም በቤንሻንጉል የሆነው ይኸው ነው፡፡
ወንድሜ! እህቴ! አራጆቹ አሁንም በበራችን ቆመዋል፡፡ ራሳችንን ከመከላከል ውጪ አማራጭ የለንም ማለታችን ትክክል ነው፡፡ አራጆቻችን ለብዙ ዓመታት በአስተሳሰብ፣ በኢኮኖሚና በስልጣን ሲደራጁ የቆዩ በመሆናቸው ይሕን የሚመጥን አደረጃጀት ለመፍጠር ጊዜ ይወስዳል፡፡
“እስከዛው ግን ራሳችንንና ቤተሰቦቻችንን እደጃፋችን ከቆመው የአራጅ ቡድን ኢሰብአዊና ዘግናኝ ጭፍጨፋ እንዴት እንከላከል?” ብለን ተወያተን ነበር፡፡ “ራሳችንን በራሳችን እናደራጅ” ብለንም ነበር፡፡ ሁሉም ወጣት የተዋሕዶ ልጅ “በመጀመሪያ ራሱን ለመከላከል ባልተማከለ ሁኔታ ይደራጅ ” ብለን ተስማምተን ነበር፡፡
ወንድሜና እህቴ! የእኛና የቤተሰቦቻችንን ደጃፍ ለመከላከል የመጀመሪያዎቹ እኛ ብቻ ነን፡፡
አራጆቹ ይኸው አሁንም በደጅህ/ሽ ቆመዋል፡፡ የአንተ/ቺ እና የቤተሰብህ/ሽ ደህንነት ባንተ/ቺ የመከላከል አቅም ይወሰናል፡፡
ምን ታደርጋለህ/ሽ?
ትጮሃለህ?
ስልክ ትደውላለህ?
ለማን?
ወደ የት?
በመስኮት ዘለህ ትሸሻለህ?
ህጻናቱንና አረጋውያኑን ትተህ?
ደግሞስ ወዴት?
ወንድሜ፣ እህቴ አራጆችህ መፈናፈኛ እንዳይኖርህ አድርገው ሊያርዱህ እያንዳንዷን ቀዳዳ ደፍነው በቤትህ ዙሪያ አሉ፡፡
ያለህ አማራጭ የግፍ ጽዋቸውን መጠጣት አሊያም ራስህን በጀግንነት መከላከል ብቻ ነው፡፡
ስለዚህ ራሳችንን በየቤታችን ልናደራጅ የተስማማነው ለዚህ ነው፡፡
ቢያንስ አምስት ተልዕኮዎች ወስደን ነበር፡፡
1. የህሊና ዝግጅት፡፡
“ተቀምጠህ በጥንቃቄ አስብ፡፡ በማንኛውም ሰዓት አራጆቹ ከቤትህ ደጃፍ ይደርሳሉ፡፡ ይህን በመቀበል “ለመከላከል ምን አለኝ?” ብለህ/ሺ ራስህን ጠይቅ፡፡”
2. የግብዓት ዝግጅት፡፡
በምንድን እከላከላለሁ? ብለህ/ሺ ጠይቅ/ቂ፡፡ ይህንንም አሟላ፡፡ ምንም ሊሆን ይችላል፡፡ ያሳመነህንና አቅምህ የሚፈቅደውን ያህል አዘጋጅ፡፡
3. የከባቢ ዝግጅት::
የቤት እና የግቢ ሁኔታም ለዚህ የመከላከል መንገድ እንዲመች ሆኖ መዘጋጀት አለበት፡፡ የኃይል ሚዛን ቢከብድህ ማፈግፈግ መቻል አለብህ፡፡ በየት በኩል? እንዴት? ይህን መልስ፡፡
4. የቡድን ዝግጅት ፡፡
ድንጉጥ ህጻናት፣ ርብትብት አዛውንት ይዘህ የመከላከል ግጥሚያ ልታደርግ አትችልም፡፡ ከእነሱ ጋር ተደራጅ/ጂ፡፡ እንደየሁኔታቸው ዝግጁ አድርጋቸው፡፡
5. ከጥቃት በኋላም ሕይወት መቀጠል አለባት፡፡ እናም ሀብትህና የህልውና ሰነዶችህን በአንድ ቅርጫት ውስጥ አለማስቀመጥህን አረጋግጥ፡፡ እሳት የማይበላው፣ አራጆችህ የማይደርሱበት ስፍራ ይኑርህ፡፡
ይህ ዝግጅት ገና የመጀመሪያው ነው፡፡ በቀጣይ ወደጎረቤት አደረጃጀት ያድጋል፡፡ 2013 የተስፋ ዘመን የሚሆንልን በዚህ መንገድ ራሳችንን ለመከላከል ዝግጁ መሆናችንን ስናረጋግጥ ብቻ ነው፡፡ ስለዚህ ባለፉት 2 ሳምንታት በየቤታችን ምን አደረግን?
ዳይ!
በነጻነት ሀሳብ እንለዋወጥ፡፡
አምላካችን የኛና የቤተሰባችንን ደም ከስንፍናችን እንዳይጠይቅ ራሳችንን አዘጋጅተን ማጠናቀቅ አለብን፡፡
እናም የዛሬው ውይይታችን ልምድ የምንለዋወጥበት ነው፡፡ በአምስቱ ነጥቦች ራሱን በቤቱ ውስጥ በማደራጀት የሰራ ምዕመን ተሞክሮውን ያጋራን፡፡ በሕሊና ራስህንና ቤተሰብህን እንዴት አዘጋጀህ/ሽ? በምን መንገድ ለመከላከል ተዘጋጀህ/ሽ? የራስህንና የቤተሰብህን አካላዊ ዝግጅት እንዴት ፈጠርክ/ሽ? በነጻነት ልምድ እንለዋወጥ!
(ከዚህ ሃሳብ ውጪ አስተያየት የምትሰጡትን በፍፁም አናስተናግድም::)
@maedotzeorthodox
እንኳን ደስስ ያለን !!
*~★★~*
• ከተቻለ ዛሬ ወደ ማታ በፌስቡክ Live ለመግባት እሞክራለሁ። ኣ
#ETHIOPIA | ~ እልልልልልልልል ተመስገን አባቴ መድኃኔዓለም። ከምስጋና በቀር ምን ይከፈልሃል?
… ማዕዶታችን … “ ማዕዶት ዘኦርቶዶክስ ተዋሕዶ የትናንቱ ለነገ ማኅበራችን ” በፈቃደ እግዚአብሔር የመሠረትነው ማዕዶታችን። ቀደም ሲል ከቤተ ክህነቱ ከቅዱስ ሲኖዶሳችን፣ ዛሬ ደግሞ በወርሀ ጥቅምት በዕለተ ማክሰኞ በበዓለ ገብረ መንፈስ ቅዱስ፣ በዝቋላው አንበሳ፣ በምድረ ከብዱ ኮከብ በአቡኤ ጣዲቁ ዓመታዊ በዓለ ንግሥ በጻድቁ አማላጅነት በዕለተ ቀናቸው ከኢትዮጵያ መንግሥት ከቤተ መንግሥቱ ከማኅበራት ማደራጃ የዕውቅና ሰርተፍኬቱ በይፋ ተቀብሎ ሥራህን በይፋ ጀምር ተብሏል።
• ሰርተፊኬቱን የማዕዶታችን የቦርድ አባል፣ የኢትዮጵያ ዕንቁዋ ሴት በግሌ የእኔ እህት አትሌት ደራርቱ ቱሉና የማዕዶታችን ዋና ሥራ አስኪያጅ አቶ ዮናስ በግንባር ቀርበው ተቀብለዋል።
•••
እንግዲህ … እግዚአብሔርም፣ ቤተ ክህነትም፣ ቤተ መንግሥቱም ያሰብነውን፣ ያቀድነውን እንሠራ ዘንድ ያለ ምንም ግርግርና ክርክር ጥርጥርም ፈቅደውልናል። እንኳን ደስ ያለን። እንኳን ደስስ ያላችሁ። ሌላ ምን ይባላል። ኡፋ…ኣ።
•••
ድምጽ ያጠፋነው፣ ወሬም ያላበዛነው፣ በትእግስት የሠራነው ሥራ ፍሬ አፍርቷል። ምስጋና ለእግዚአብሔር፣ ምስጋና ለቅዱሳን ፓትርያርኮቻችን፣ ምስጋና ለቅዱስ ሲኖዶሳችን፣ ምስጋና ለጠቅላይ ቤተ ክህነቱ የሕግ ክፍል፣ ምስጋና ለማኅበራት ማደራጃ ሠራተኞችና የሥራ ኃላፊዎች በሙሉ።
… ምስጋና ለማዕዶት ዋና ሥራ አስኪያጅ ለዮኒዬ፣ ምስጋና ለማዕዶት ዘኦርቶዶክስ የቦርድ አባላት በሙሉ። የቀረውን በቀጣይ እመለስበታለሁ። አሁን አውቀን ፈተና ለመቀነስ ሲባል የሌለን እስኪመስል ድረስ የጠፋንበትን የቴሌግራም ግሩፕ እንቅስቃሴ እንደ አዲስ እናቀጣጥለው። ሁላችሁም ግሩፓችሁን አንቀሳቅሱት። ዳይ ፍጠኑ ወደ ሥራ።
… አሁን ቢሮዎች ይከፈቱ። የባንክ አካውንቱ ይከፈት። አባላት በይፋ ለመመዝገብ ተዘጋጁ። አምላኬ ሆይ እንደው ምን አባቴ ልሁንልህ። ለአንተ ውለታ ምንስ ባደርግ፣ እንዴትስ ባመሰግንህ እረካ ይሆን? ብቻ ተመስገንልኝ።
• ስለ አሐዱ ባንክ
• ስለ እኔ ዩቲዩብና
• ስለ ሳታላይት ተሌቪዥን ደግሞ ሌላ የምስራቾች አሉኝ። ዛሬ ዕለቱ የደስታ ማብሠሪያ ብቻ ነው።
¶ድልና ትንሣኤ ለኢትዮጵያ ሀገራችንና ለተዋሕዶ ሃይማኖታችን ! ውድቀትና ጥፋት፤ ለሁለቱም ጠላቶች ይሁን። አሜን። አራት ነጥብ።
•••
"ጌታ ሆይ! ከዚህ በፊት በሆነው ፤ አሁንም እየሆነ ባለው እና ወደፊትም በሚሆነው ነገር ፤ ክብሩን ሁሉ አንተ ውሰድ ።" አሜን. !
"ድንግል ሆይ እናቴ ! አዛኝቱ አማላጅቱም ሆይ ዛሬም እንደትናንቱ ቅደሚ ከፊት ከኋላዬ "
ይህንንም ራሴው በእጄ ጻፍኩት። +49 1521 5070996 ደግሞ የቴሌግራም፣ የቫይበር፣ የኢሞና የኋትስአፕ መልእክቶችን የምቀበልበት የእጅ ስልኬ ነው።
#ማስታወሻ | ~ ከተቻለኝ ለመጀመሪያ ጊዜ ዛሬ ወደ ማታ በፌስቡክ Live ለመግባት እሞክራለሁ። የቀጠሮ ሰው ይበለን። አከተመ። ከኑመ ጋ ዱቢን።
•••
ሻሎም ! ሰላም !
ዘመድኩን በቀለ ነኝ።
ጥቅምት 5/2012 ዓም
ከራየን ወንዝ ማዶ።
YouTube - A call to refrain from double killing the victims
#Zemedkun_Vs_YouTube
Here is the fact that the YouTube company is unaware about. A massive massacre and displacement of The Ethiopian Orthodox Tewahdo believers and burning to ash of her Churches is being conducted.
The magnitude of such act is increasingly aggressive in the last three years. Upon a single phone call of an activist named Jawar, the precious lives of 86 Christians were slain away, just a year ago. The aftermath shown several displacements, burning down and demolition of more than 20 Churches.
Not limited to this, following a premeditated attack on 1st of July 2020, brutal genocide effected in the eastern and south eastern regions of Ethiopia. The corpse of the diseased were chopped. A child in its mother womb was brought to death, so that a Christian successor shouldn’t get born in “their land” as the aggressors proclaimed.
The right to life is at stake, especially when one is found to be Orthodox. There was an attempt to kill 5 Bishops as the charge of the attorney general shows. The houses and merchandises of the Orthodox believers were turned to ash devastatingly. All horrific things happen to the Christians.
The violent attacks were led by local and federal officials as the Ethiopian government itself witnessed. The Church condemned the act on her press release. And pronounced the attack as genocide.
Advocating to these people can’t in any way be considered hate speech. Zemedkun Bekele is one of many advocates to this regard. He has been doing his best to rehabilitate the displaced through a tireless effort. He uses YouTube as a social media platform, to facilitate and coordinate the purpose.
Recently we have learnt that YouTube has banned his channel as a result of hate speech report. Those people who reported against him should be the prime suspects who are in alliance with the same people instigating the death and the uncountable suffering the Church received.
Listening to this people is like double killing the victims. Hence we strongly disagree the decision of banning Zemedkun. Let YouTube show it stands with humanity by lifting the embargo.
#YouTube_lift_the_ban_against_Zemedkun_Bekele
ከብዙ ሕማም በኋላ የሠማያትና የምድር ጌታ በመስቀል ሆኖ “ተፈፀመ” አለ፡፡ በ9፡00 ሰዓት ላይ ሥጋውን ከነፍሱ ለየ ሰይጣንም እንደልማዱ ይህች ነፍስ የእኔ ናት ብሎ ቢጠጋ አምላካችን በነፋስ አውታር አሠረው በዚህ ጊዜ ዲያቢሎስ አንዲህ ሲል ጮኸ ‹መኑ ዝንቱ ዘምድረ ለብሰ ውእቱኬ ሰማያዊ ውእቱ› ‹እንደ ምድራዊ የለበሰ /ምድራዊ የመሠለ/ ነገር ግን ሠማያዊ የሆነ ይህ ማን ነው? በማለት ተናገረ፡፡
በዚህ ቅጽበት ጌታ ሲኦልን በረበረ አዳም እና ልጆቹን ከዲያቢሎስ ባርነት ነፃ አወጣ፡፡ ሊቃውንተ ቤተክርስቲያን ግን በዲሜጥሮስ ቀመር መሠረት አጽዋማትን በጠበቀ መልኩ ከትንሣኤ በዓል በፊት ያለውን አርብ “ስቅለት” ተብሎ እንዲከበር ሥርአት ሠርተዋል፡፡
የጌታችን የመድኃኒታችን የኢየሱስ ክርስቶስ የህማሙ ረድኤተ በረከት በሁላችን ላይ ይደርብን የድንግል ማርያም ፍቅሯን በልቡናችን ጣዕሟን በአንደበታችን ይሣልብን። መድኃኔዓለም ክርስቶስ ከዚህ ከሃላፊው ዓለም ያድነን።
አሜን
በኢትዮጵያ ቤተ ክርስቲያን ሥርዓት መሠረት በታቦታቱ ሁሉ ላይ የተጻፈው ‹‹አልፋና ኦሜጋ›› የሚለው የመድኃኔዓለም ክርስቶስ ስም ነው፡፡ ከስሙ ጋር ደግሞ በሁሉም ታቦታት ላይ የሚከተለው ጥቅስ በግእዝ ተጽፎአል፡፡ ‹‹ከመ ለስሙ ለኢየሱስ ክርስቶስ ይስግድ ኲሉ ብርክ ዘበሰማያት ወዘበምድር›› ‹‹ይህም በሰማይና በምድር ከምድርም በታች ያሉት ሁሉ በኢየሱስ ስም ይንበረከኩ ዘንድ›› የሚል ነው፡፡ (ፊልጵ. 2፡10) በታቦቱ ፊት የሚሰግድ ሰው ለምን እንደሚሰግድ በታቦቱ ላይ የሚጻፈው ይህ ጥቅስ ያስረዳናል፡፡ ምክንያቱ ‹‹ጉልበት ሁሉ ለኢየሱስ ስም ይሰግዱ ዘንድ›› ስለሚገባ ነው፡፡ የክርስቶስ ሥጋ እንደሚቆረስ ደሙ እንደሚፈስስ የሚያምን ሰው በዚህ መሠዊያ ፊት በፍርሃት ለክርስቶስ ይሰግዳል፡፡ ሥጋ ወደሙን ‹‹ተራ መታሰቢያ ብቻ ነው›› የሚል ሰው ግን በመሠዊያው ፊት እንዲሰግድና መሠዊያውን እንዲያከብር አንጠብቅም፡፡ የኢየሱስ ክርስቶስን ስም በታቦቷ ጽፋ ክብር የምትሠጥ የሐዲስ ኪዳን ቤተ ክርስቲያን ልጆች ስለሆንን እግዚአብሔርን እናመሰግናለን፡፡
የታቦቱ ሌላ መጠሪያ የመሠዊያ ታቦት (ታቦተ ምሥዋዕ) የሚል ሲሆን ቅዱስ ጳውሎስ ስለዚህ መሠዊያ ‹‹መሠዊያ አለን በድንኳኒቱ የሚያገለግሉ ከእርሱ ሊበሉ መብት የላቸውም›› በማለት ስለ ሐዲስ ኪዳኑ መሠዊያ ይነግረናል፡፡ (ዕብ. 13፡10) ይህ መሠዊያ በኦሪት ድንኳን የሚያገለግሉ የአሮን ልጆች ከእርሱ ሊበሉ መብት የሌላቸው ለእኛ ክርስቲያኖች ብቻ በመሠዊያው ያለውን ሥጋና ደም እንድንበላ የተሠጠን ታቦተ ምሥዋዕ (Christian Alter) ነው፡፡ እነርሱ ቤተ እስራኤላውያን ነቢዩ እንደተናገረው "ከእንግዲህ አይሹትም የቃልኪዳኑ ታቦት ብለውም አይጠሩትም" ለእኛ ለአዲስ ኪዳን ልጆች ግን የተሠጠን የሥጋ ወደሙ ቃልኪዳን ነውና ዘላለማዊ ነው::
የታቦትን የሐዲስ ኪዳን አገልግሎት ስንናገር የሚቃወሙ ሰዎች ከሚያነሡት ተደጋጋሚ ትችት ‹‹አንዱ ታቦት ያላት የኢትዮጵያ ቤተ ክርስቲያን ብቻ ናት›› የሚል ነጥሎ የመምታት ጥረት ነው፡፡ በተለይም የግብፅ ቤተ ክርስቲያንን በመጥቀስ ‹‹ግብፆች ታቦት የላቸውም›› የሚል ንግግር ይዘወተራል፡፡ ለዚህ ጉዳይ እኛ መልስ ከምንሠጥ የራሳቸው የግብፃውያንን ምላሽ ብቻ ማስቀመጥ ይቀልለናል፡፡ ግብፃውያን ከኢትዮጵያ ቤተ ክርስቲያን ታቦት ጋር አቻ የሆኑ ሁለት ንዋያተ ቅድሳት አሏት፡፡ አንደኛው የመሠዊያው ጽላት (ሰሌዳ) /Alter Board/ ሲሆን ሁለተኛው ታቦት /Ark/ ነው፡፡
ቄስ ታድሮስ ማላቲ የተባሉት የቤተ ክርስቲያኒቱ እውቅ ጸሐፊ ‹‹Church The House of God›› በተሰኘው መጽሐፋቸው ላይ ስለ የመሠዊያው ሠሌዳ (Alter Board) አሠራር ሲናገሩ ‹‹ይህ የመሠዊያ ጽላት አንድ መስቀል ወይም ብዙ መስቀሎች ይሳሉበታል ፤ አልፋና ኦሜጋ ተብሎ ይጻፍበታል ፤ ከዚያም መዝ. 86፡1 ላይ ያለው መሠረቶቿ የተቀደሱ ተራሮች ናቸው የሚለው የመዝሙረ ዳዊት ቃል ይጻፍበታል፡፡›› ይሉና ስለ አሠራሩ ሲናገሩ ‹‹የግብፅ ቤተ ክርስቲያን መሠዊያው ስለሚሠራበት ቁስ የተደነገገ ሕግ የላትም ፤ እስከ አራተኛው ክፍለ ዘመን ድረስ ከእንጨት ብቻ ይሠራ ነበር፡፡ ከዕብነ በረድና ከድንጋይም ሊቀረጽ ይችላል፡፡›› ይህንን ካሉ በኋላም እግረ መንገዳቸውን ስለ ኢትዮጵያ ቤተ ክርስቲያን ታቦተ ምሥዋዕ ሲናገሩ ‹‹ከእንጨት የሚሠራ ታቦተ ምሥዋዕ እስካሁን ድረስ በኢትዮጵያ ቤተ ክርስቲያን አገልግሎት መሥጠቱን ቀጥሏል›› (Wooden Alters continue in use in the Ethiopian Church at the present time) ብለው ያጠቃልላሉ፡፡
ይህ ስለ መሠዊያ እንጂ ስለ ታቦት አይናገርም፡፡ ስለ ታቦት ደግሞ እኚሁ ጸሐፊና በቤተ ክርስቲያኒቱ ኦፊሴላዊ ድረ ገጾች ላይ የሚከተለው ተጽፎአል፡፡ ‹‹In the middle of the Alter, there is a wooden box, called in Coptic 'pi totc' which means 'a seat' or 'a throne', and is used as a Chalice-Stand. Usually it is cubicle in shape, about thirty centimetres high and twenty-five centimetres wide, the top is closed with high flaps. The beautiful carving is inlaid with ebony and ivory and is decorated with four small icons. It can be only the Lord in the last supper, St Mary, Archangel Michael, St. Mark and then the patron Saints.
It is called 'the Throne' for it represents the presence of the Crucified Lord. Its name also corresponds to the 'Ark of the Old Testament', for it contained the Tablets of Law written with the finger of God to declare God's covenant with man. The new Ark now contains the true Blood of Christ, as the New covenant, that fulfils the Law and the prophets.›› (‹‹ከመሠዊያው መካከል የሚቀመጥ የእንጨት ሳጥን ሲኖር ይህ በኮፕት ቲቶት ተብሎ የሚሠራ ሲሆን ትርጉሙም ‹መንበር› ወይም ዙፋን ማለት ነው፡፡ ጽዋው የሚቆመውም በዚህ ላይ ነው፡፡ ቅርጹ ክበባዊ ሲሆን 13/25 ሴንቲሜትር ነው፡፡ ከላይ በጨርቅ ይሸፈናል፡፡ በጥቁርና ነጭ ኽብረ ቀለማት ያጌጠ ሲሆን አራት ሥዕላት በዙሪያው ይደረጋሉ፡፡ ሥዕላቱ የጌታችን ጸሎተ ሐሙስ ሥዕል የእመቤታችን ፣ የቅዱስ ሚካኤልና የሚታሰበው ቅዱስ ሥዕላት ናቸው፡፡
‹ዙፋን› ተብሎ የሚጠራው የተሰቀለው ጌታ እንደሚያድርበት በማሰብ ነው፡፡ ይህ ስያሜም ‹ከብሉይ ኪዳኑ ታቦት› ጋር የሚመሳሰል ነው፡፡ ያ ታቦት እግዚአብሔር ከሕዝቡ ጋር ያደረገው ቃልኪዳን የተጻፈባቸው የሕግ ጽላት ያሉበት ነበር፡፡ አሁን ያለው አዲሱ ታቦት ግን እውነተኛውን የክርስቶስ ደም የያዘ ሲሆን ክርስቶስም ሕግንና ነቢያትን ፈጽሞ አዲሱን ኪዳን የሠጠን ነው፡፡››) ይህ ማብራሪያ ብፁዕ አቡነ ጎርጎርዮስ ስለ እኛ ቤተ ክርስቲያን ታቦት ከሠጡት ማብራሪያ ጋር ምንም አይለያይም፡፡ ይህን እንደ ማሳያ ጠቀስን እንጂ ታቦቱ ዑደት ባለማድረጉ እና በሥርዓቱ ይለያያል እንጂ በኢትዮጵያ ቤተ ክርስቲያን ለሥጋ ወደሙ መሠዊያ ነው ብላ ከምታከብረው ታቦት ጋር በክብርና በአገልግሎት አቻ የሆኑ በቅብዐ ሜሮን የሚከብሩና በመንበር የሚቀመጡ ንዋያተ ቅድሳት በሁሉም አብያተ ክርስቲያናት አሉ፡፡
ባለንበት ዘመን በሥጋ ወደሙ እውነተኛነት ከማያምኑ ሰዎች ጋር ስለ መሠዊያው አስፈላጊነት በመከራከር ብዙ ጊዜ ሲባክን ይታያል፡፡ የኢየሱስ ክርስቶስ ስም የተጻፈበትን ታቦት ‹ጣዖት› ነው የሚሉ ‹ክርስቲያኖች› እያየን እንደነቃለን፡፡ ‹‹ጉልበት ሁሉ ለኢየሱስ ክርስቶስ ስም ይንበርከክ›› ተብሎ የተጻፈበት ‹ጣዖት› እንዴት ይኖራል? ‹‹አልፋና ኦሜጋ›› የሚል ጣዖት አለ? ወንጌል በላዩ ላይ የተቀመጠበት ፣ በቅብዐ ሜሮን የከበረ ፣ ሥጋ ወደሙ የሚፈተትበት ታቦት እንዴት ጣዖት ተብሎ ይጠራል? አሐዱ አብ ቅዱስ አሐዱ ወልድ ቅዱስ አሐዱ ውእቱ መንፈስ ቅዱስ ተብሎ በሥላሴ ስም የሚቀደስበትን ታቦት ባዕድ አምልኮ ለማለት መድፈር እንዴት ያስደነግጣል፡፡
ከዛሬ ጀምሮ ትውልድ ሁሉ ብፅዕት ይሉኛል !
——————————————————-
ማርያምም እንዲህ አለች፡—
ነፍሴ ጌታን ታከብረዋለች፥ መንፈሴም በአምላኬ በመድኃኒቴ ሐሴት ታደርጋለች፤የባሪያይቱን ውርደት ተመልክቶአልና።
እነሆም፥ ከዛሬ ጀምሮ ትውልድ ሁሉ ብፅዕት ይሉኛል፤ብርቱ የሆነ እርሱ በእኔ ታላቅ ሥራ አድርጎአልና፤ ስሙም ቅዱስ ነው።
ምሕረቱም ለሚፈሩት እስከ ትውልድና ትውልድ ይኖራል።
በክንዱ ኃይል አድርጎአል፤ ትዕቢተኞችን በልባቸው አሳብ በትኖአል፤ ገዥዎችን ከዙፋናቸው አዋርዶአል፤ ትሑታንንም ከፍ አድርጎአል፤የተራቡትን በበጎ ነገር አጥግቦአል፤ ባለ ጠጎችንም ባዶአቸውን ሰዶአቸዋል።
ለአባቶቻችን እንደ ተናገረ፥ ለአብርሃምና ለዘሩ ለዘላለም ምሕረቱ ትዝ እያለው እስራኤልን ብላቴናውን ረድቶአል።
የሉቃስ ወንጌል 1፤46-55
እንኳን ለእመቤታችን ቅድስት ድንግል ማርያም ዓመታዊ በዓል በሰላም አደረሰን አደረሳችሁ !
ለመጀመሪያዋ ቋንቋችን፣ ለመጨረሻዋ እናታችን ምስጋናን እናቅርብ!! #ዕግትዋ_ለጽዮን ፤ #ጽዮንን_ክበቡአት!!
ዕድሜያችን ባከነ እየተሳቀቀ፣
ልጅ ሆነን አጓጉቶን ፥ ልጅ ሆነን አለቀ ።
እንደገና መወለድ ቢቻል እንኳ አልፈልግም እንጂ ፤ እንደገና ብወለድ ኖሮ ብዙ የማስተካክላቸው የቤት ሥራዎችና የማካክሳቸው የባከኑ ጊዜያት ነበሩኝ። እጅግ በጣም ብዙ!!
አሁን ግን በተሰጠኝ ዕድሜ እንድሠራበትና ዕድሜ ለንስሐ ፥ ዘመን ለፍስሐ እንዲሆነኝ አምላኬን እለምናለሁ፡፡ እናቴን እመ ብርሃንን እማልላለሁ።
የመልከአ ማርያም ደራሲ ይህን እንዳለ፡-
#ሕይወትዬ_በንዝህላል_እመ_ተሰልጠ_ወኀልቀ፤
#ወስክኒ_ክራማተ_እስከ_እገብር_ጽድቀ፡፡
"እናቴ ማርያም ሆይ ዘመኔ ህይወቴ በዋዛ ፈዛዛ በንዝላልነት አልቋልና መልካም [እስክሠራ] የምሠራበትን፣ ጽድቅ [እስክፈጽም] የምፈጽምበትን ጊዜ፣ ዘመን፣ ዓመት፣ ዕድሜ ጨምሪልኝ" እያልኩ እማጸንሻለሁ።
ጣዕምሽን በአንደበቴ፣ ፍቅርሽን በልቦናዬ፣ ንፅሕናሽን በህሊናዬ፣ ቅድስናሽን በሰውነቴ እንዲስልብኝ፤ እንዲያሳድርብኝ!! አዎ ይሳልብኝ፤ ያሳድርብኝ!! ይበልጡኑ ለውዳሴሽ እንድተጋ ….. ወስክኒ ክራማተ እስከ እገብር ጽድቀ፡፡
ስብሐተ እግዚአብሔር ሌትና ቀን በሚፈስበት በዓል፣ ንግሥተ ሰማይ ወምድር እመ ብርሃን ክብሯ በሚነገርበት፣ ቅዳሴዋ ውዳሴዋ በሚደርስበት በድንግል እናታችን መታሰቢያ ዕለት መወለዴ እጅግ ሲበዛ ያስደስተኛል፡፡
ለእመ ብርሃን የሚገባትን ክብር የሚሰጣትና በምልጃዋ ተማምኖ በእናትነት የሚቀበላት ኦርቶዶክሳዊ ክርስቲያን ሁሉ ይህን ቀን መመኘቱ ግን አይቀርም፡፡ እኔም በዓለ ጽዮንን ክብሩን ሳስብ ልደቴ በዚሁ ቀን የመሆኑ ደስታዬ ወደር የለውም፡፡ የማከብረው ልደቴን ሳይሆን፤ የእመቤቴን በዓለ ክብር ነውና!!
በዓሉ የሁላችንም ኦርቶዶክሳዊያን ስለሆነ መልካም በዓል እንዲሆንልን እየተመኘሁ፤ ልበ አምላክ ቅዱስ ዳዊት እንደተናገረ፤ ክርስቲያኖች ሁላችን ፦
#ጽዮንን_ክበቡአት_በዙሪያዋም_ተመላለሱ፥
#ግንቦችዋንም_ቍጠሩ_በብርታትዋ_ልባችሁን_አኑሩ፤
#አዳራሽዋን_አስቡ_ለሚመጣው_ትውልድ_ትነግሩ_ዘንድ
#ለዓለምና_ለዘላለም_ይህ_አምላካችን_ነው፥
#እርሱም_ለዘላለም_ይመራናል።
(መዝ.48፥12-14) እያልን ዘር ቀለም ሳንለይ በእናታችን ጽዮን ማርያም ፍቅር አንድ ሆነን እንዘምር። በሃይማኖት አንድነት ቤተሰቦች እንሁን (ገላ.6፥10)።
ዘማሪ ዲ/ን ቴዎድሮስ ዮሴፍም "ማርያም ማርያም" በሚል መዝሙሩ ፦
#በተወለድኩበት_በመጀመሪያው_ቀን፣
#ስምሽን_እየጠራሁ_ወጣሁ_ከማኅፀን፡፡
ሲል እንደተቀኘ፤ ለመጀመሪያዋ ቋንቋችን፣ ለመጨረሻዋ እናታችን ምስጋናን እናቅርብ!!
መልካም በዓል ለሁላችንም 🌸🥀💐
#ዕግትዋ_ለጽዮን ፤ #ጽዮንን_ክበቡአት
ለመጀመሪያዋ ቋንቋችን፣ ለመጨረሻዋ እናታችን ምስጋናን እናቅርብ!!
(በሕዳር ጽዮን ቀን 2013 ዓ.ም)
@lijredeat07
ልጅ ረድኤት አባተ ዘጂንካ ሥላሴ
~ ማስታወቂያ እና
አጭር የዜና ጦማር
*~★★~*
• ቻናሌ 200 ሺ ሰው ብቻ ነው መቀበል የሚችለው፣ የሚፈቀድለትም። ቶሎ ቦታ ያዙ። ባለማዕተብ ጓደኞቻችሁንም ጋብዙ። ፍጠኑ።
#ETHIOPIA | ~ አዲስ የመወያያ ቻናል መከፈቱን ስለማሳወቅ። Comment መስጠትም ይቻላል። ጓደኞቻችሁንም ጋብዙ።
/channel/zemede_Discussion
•••
የፌስቡክ ፔጄ ቢዘጋብኝ ወደ ዩቲዩብ መንደር ሄድኩኝ። በዚያም መንደር ብዙ ሳልቆይ የዩቲዩብ ቻናሌንም ዘግተው፣ አዳፍተውና ገፍትረው ተረባርበው ወደታች ወረወሩኝ። እነሱ በአፍጢሙ ይደፋል ብለው ሲጠብቁኝ እግዚአብሔር ጭራሽ ላያወርዱኝ፣ ላይደርሱብኝም ከፍ አድርጎ ወደ ላይ በአየር ላይ አስቀመጠኝ። ያለ ዋይፋይ፣ ያለ ኢንተርኔት በየቤቱ በቴሌቭጅን እንድገለጥ አደረገኝ። ክብር ለመድኃኔዓለም። ለወለደችው ለእናቱም ይድረስልኝ አሜን።
•••
ፌስቡክና ዩቲዩብ በተጣሉኝ ጊዜ እስከአሁን ፊቱን ያላጠቆረብኝ የራሺያ ኦርቶዶክሱ የቴሌግራም ካምፓኒ ነው። ቴሌግራም ሆደሰፊ፣ ታጋሽም ነው። ደግሞም ከእነዚያ መንደር ባለቤቶችም ይለያል። ቢያንስ የእመቤታችንን ስም ይጠራል። እናም እኔም የአዛኚቱ ወዳጅ አሽከር የሥላሴ ባርያም መሆኔን አይቶ ነው መሰል እስከአሁን አንዳችም የመግፋት ምልክት አላሳየኝም። ቴሌግራምም ቴሌግራሜም እስከአሁን ሰላም ነን።
•••
በቴሌግራም መንደር አንድ የነበረው ቅሬታ በቻናሉ ውይይት፣ ኃሳብ መለዋወጥ ያለመቻል ብቻ ነበር። እሱን ነገር በዛሬው ዕለት፣ ህዳር 3/2013 ዓም መፍትሄ አግኝቷል። በተመረጠ ርዕስ፣ በተመረጠው ሰዓት፣ የመወያያ፣ ሃሳብ የመለዋወጫ ቻናልም ይኸው ከፍቻለሁ። ከዛሬ ጀምሮ በምጽፈው ጦማር ላይ አስተያየት መስጠትም ይቻላል። ታዲያ በጨዋ ደንብ ነው። በቴሌግራም ደግነቱ ሁሉም ሰው በራሱ የግል ስልክ ቁጥሩ ነው የሚገባው። የብዕር ስም እንጂ የሚኖረው የብዕር ስልክ ቁጥር የለውም። እንደ ፌስቡክ ለመሳደብም፣ ባለጌ ለመሆንም አይመችም። በቴሌግራም ጨዋ መሆን ግድ ነው። ከቴሌግራም ቻናሌ አንድ ጊዜ ከተወገዱ አከተመ። እናም ጨዋ መሆን ለራስ ነው።
•••
የቴሌግራም ቻናል የሚፈልገው የሰው ብዛት ሁለት መቶሺህ ሰው ብቻ ነው። ሁለት መቶ ሺ ሰው። ከዚህ በላይ አይይዝም። አይፈቅድምም። እናም ነፍስ ያላቸው ባለ ማዕተብ ጓደኞቻችሁን ጭምር በመጋበዝ ወደ ዘመዴ የውይይት መድረክ አምጧቸው። ጋብዟቸው።
/channel/zemede_Discussion አዲሱ ቻናሌ ነው። የሚገርመው ነገር ገና የመወያያ ቻናሉን ሳላስተዋውቀው ከአሁኑ ወደ 154 ጓደኞቼ ቤት ለእምቦሳ ብለው ተከስተዋል። እንኳን ደህና መጣችሁ።
… በመጨረሻም !!
ዛሬ ከወደ ራያ ቆቦ አንድ ጆሮ ጭው የሚያደርግ መረጃ ደርሶኛል። ህወሓት በራያ ግንባር ከሰሞኑ ልክ እንደማይካድራው አይነት ዘግናኝ መርዶ ሳታሰማን አትቀርም እየተባለ ነው። በራያ ንፁህ ዐማሮች ናቸው የተባሉትን በሙሉ ህወሓት ለቃቅማ ወደ መታረጃ ከምፖች መውሰዷን ከሥፍራው አምልጠው የመጡ ዐማሮች ተናግረዋል ተብሏል። ውጊያው ሊጀመር ከጫፍ ደርሷል። እናም ህወሓት መሸነፌ ካልቀረ በማለት በራያ ላይ ከፍተኛ የዘር ማጥፋት ለመፈጸም መዘጋጀቷ ነው የሚነገረው። የሚገርመው ነገር ፦
• በሶማሊያም የታረደው ዐማራ
• በደቡብም የታረደው ዐማራ
• በቤኒሻንጉልም የታረደው ዐማራ
• በኦሮሚያም የታረደው ዐማራ
• ትናንት በማይካድራም የታረደው ዐማራ
• ዛሬም ሊታረድ ወደ መታረጃ ቄራው የገባው ዐማራ።
… በቃ ዐማራ ማለት የኢትዮጵያ ኃጢአት የማስተሰረያ በግ ሆነ ማለት ነው? ህወሓቶች ይሄን ነገር ባይሞክሩት ይሻላቸዋል። ለራሳቸውና ለዘራቸው ሲሉ ባይሞክሩት ይሻላቸዋል። ምክሬ ነው።
•••
በተረፈ እንደተለመደው ዛሬም እንደ ትናንቱ በተለመደው ሰዓት በመረጃ ቲቪ እንገናኛለን። ሰብሰብ ብላችሁ ጠብቁኝ።
ሰምታችኋል ! ኣ
እውነት - “እናም እውነቱን ታውቃላችሁ እውነትም አርነት ያወጣችኋል።” ዮሐ 8
46. ድል አድራጊ - “ድል አድራጊ ለሆንኩ ፣ እኔ ድል እንደሆንኩ እና ከአባቴ ጋር በዙፋኑ ላይ እንደተቀመጥኩ ከእኔ ጋር በዙፋኔ ላይ የመቀመጥ መብትን እሰጣለሁ” ራእይ 3:21
47. - ድንቅ መካር፣
48- ኃያል አምላክ ፣
49--_ የዘላለም አባት ፣
50- የሰላም ልዑል - “ለእኛ አንድ ሕፃን ተወልዶልናልና ለእኛ ወንድ ልጅ ተሰጥቶናልና መንግሥቱም በጫንቃው ላይ ይሆናል። እርሱም ድንቅ መካር ፣ ኃያል አምላክ ፣ የዘላለም አባት ፣ የሰላም ልዑል ይባላል። ” ነው ኢሳ 9 6
ለዛሬ ይብቃኝ እቀጥላለሁ
አማኑኤል አምላክ ችርነቱ ምህረቱ አይለየን ፍቅርና ሰላሙን ያድለን አሜን
ጥቅምት28 2013 ,
መጋቤ ምስጢር ቡሩክ አሳመረ
ጎዶኞቼ ሆይ በሉ ዳይ ፈጠን በሉ በመረጃ ቴቪ የዩቲዩብ መንደራችን እንገናኝ
https://www.youtube.com/channel/UCuwWDftx2gxmC2D50So0gag
ሻሎም ! ሰላም !
ጎዶኞቼ ሆይ በሉ ዳይ ፈጠን በሉ በመረጃ ቴቪ የዩቲዩብ መንደራችን እንገናኝ
https://www.youtube.com/channel/UCuwWDftx2gxmC2D50So0gag
ሻሎም ! ሰላም !
ይድረስ ለወዳጆቻችን በሙሉ በያላችሁበት፦
ዛሬ ደግሞ ከጥቂት ደቂቃዎች በኋላ በወዳጃችን በሊቀ መዘምራን ጸሐፌ ትእዛዝ ታዴዮስ ግርማ
https://www.youtube.com/channel/UCKo5yiOO1_RmqKvlUwzh1YA
የዩቲዩብ ቻናል እንቀርብና የዕለተ ሰንበት ወጎችን እናወጋለን። በሉ ወደ ታዲዮስ ቤት እንሂድ። በዚያም እንገናኝ። ጠብቁኝማ።
ነጭነጯንማ እናወራለን።
ሻሎም ! ሰላም !
‹‹ወልድኪ መድኃኔዓለም ዲበ ዕፅ ተቀነወ ዘፄወወ ሕዝበ በደሙ ቤዘወ››
‹‹ልጅሽ መድኃኔዓለም በመስቀል ላይ ተቸነከረ በባርነት የነበረውን ሕዝብ በደሙ ተቤዠ››
አባታችን አዳም በበሊዓ ዕጸ በለስ (ዕጸ በለስ በመብላት) ከአምላኩ ተጣልቶ ከገነት ወጥቶ ጸጋውን አጥቶ ለድካም ለመከራ ከምድረ ፋይድ ገብቶ ባለበት ጊዜ ራሱን ጎድቶ ያነባውን ያለቀሰውን የዕንባ ለቅሶ በደሙ ያቀረበውን የይቅርታ መስዋዕት ፈጣሪው ተመልክቶለት የመጀመሪያውን ከሰው ልጅ ጋር ያደረገውን ቃል ኪዳን ለእርሱ ሰጠው፡፡ ቃል ኪዳኑም ይህ ነበር ‹ዓለም (አንተና ዘርህ) በአንተ ደም አትድንም ከአምስት ቀን ተኩል በኋላ (ከ5500 ዘመን) ከልጅ ልጅህ ተወልጄ በደሜ አድንሃለሁ›፡፡
በመሆኑም አዳም የተሰጠውን የተስፋ ቃል በማሰብ በተስፋ ይኖር ጀመር፡፡ ይህ የተገባለት ተስፋ ከአምላኩ ይቅርታን አግኝቶ ‹በእንተ ሔዋን ተአጽወ ኆኅተ ገነት› ‹በሔዋን ምክንያት የገነት ደጅ ተዘጋ› እንዲል በበደላቸው ተዘግታ የነበረችው ገነት መከፈትን የምታበስር ታላቅ ተስፋ ነበረች፡፡ከአዳም በኋላ የተነሳው በህገ ልቡና ቀናውን ቢከተል በረከት እየበዛለት እድሜው እየተጨመረለት ጥፋትን ቢከተል እድሜው እያጠረበት ሞቱ እየቀረበበት ያለ ሕግ በልቡና መሪነት ይኖሩ ነበር፡፡ ሆኖም ግን መልካም የሠራው በጽድቅ ሥራው ገነትን ሊከፍት አልቻለም ነበር፡፡ ምግባሩ ሰናይ ካልሆነው ጋር በሲኦል ይደመር ነበር እንጂ! ምንም ቅሉ ይህ ቢሆንም መልካም ሥራ ሠርተው ያረፉትን ቅዱሳን ጻድቃን ነቢያትን በቸርነቱ በረድኤቱ ይጠብቃቸው ነበር፡፡ ጥላ የፀሐይን ሙቀት እንዲከላከል እንዲሁ ረድኤተ እግዚአብሔር መልካም ስራ የሰሩትን በሲኦል ካለው ስቃይ እና መከራ ይጠብቃቸው ነበር፡፡
እግዚአብሔር ለአዳም የገባውን ቃል በየዘመኑ በተነሱ ነቢያት ተፈፃሚ እንደሚሆን አፍ ከፍቶ ቃል አሣክቶ ንግግር አቅንቶ ሕዝቡን ያፅናና ነበር፡፡ ሕዝቅኤል ነቢይ በዘመኑ “ርኢኩ ኆኅተ በምሥራቅ ኀቱም በዓቢይ መንክር ማኀተም አልቦ ዘቦአ ዘእንበለ እግዚአ ኃያላን” “በታላቅ ቁልፍ የተዘጋች ደጅ በመሥራቅ አየሁ ከኃያላን ጌታ በቀር ወደ እርስዋ ገብቶ የወጣ የለም” /ህዝ 4፡4/ ሲል፣ ነቢዩ ኢሳያስም “ህፃን ተወልደ ለነ ወልድ ተውህበ ለነ” “ህፃን ተወልዶልናል ወንድ ልጅም ተሠጥቶናል” /ኢሳ 9፡6/ “ናሁ ድንግል ትፀንስ ወትወልድ ወልደ ወትስምዮ ስሙ አማኑኤል” “እነሆ ድንግል በድንግልና ትፀንሳለች ወንድ ልጅም ትወልዳለች ስሙንም አማኑኤል ትለዋለች “ /ኢሳ 7፡14/ ፣ እና ሌሎችም ነቢያት ከደቂቀ ነቢያት እንደሚክያስ ያሉ ከአበይት ነቢያት ከላይ ከተጠቀሱት ውጪ እንደ ነቢዩ ዳንኤል ያሉ ነቢያቶች አባታችን መዝሙረኛው ቅዱስ ዳዊትም “ናሁ ሰማዕናሁ በኤፍራታ ወረከብናሁ ውስተ ዖመ ገዳም” “እነሆ በኤፍራታ ሰማነው በዱር ውስጥም አገኘነው” በማለት ስለ ወልደ እግዚአብሔር ሰው መሆን ትንቢት ተናግረዋል፡፡ አምላካችን ቅዱስ እግዚአብሔር ይታየው ምሣሌ የተነገረው ትንቢት ይፈፅም ዘንድ ጊዜው ሲደርስ ንጽሐ ሥጋ፣ ንስሐ ኀሊና፣ ንጽሐ ነፍስን አስተባብራ በያዘችው አስቀድሞ በሥላሴ ኀሊና በታሰበችው በድንግል ማኀፀን በብሥራተ ገብርኤል አደረ፡፡ ጠባቧ የድንግል ማኀፀን ስፍሕት (ሰፊ) ሆና የሠማይ ስርዓት ተከናወነባት ኋላም እንደ ሠው ስርዓት ፈጣሬ ዓለማት ወልድ ኢየሱስ ክርስቶስ በበረሃ ውስጥ በቤተልሔም ተወለደ /ሉቃ 2/ “ፈቂዶ ይፌውስ ትዝምደ ሰብእ ተገረም በማኀፀነ ድንግል “የሠውን ወገን ያድን ዘንድ ወዶ ፈቅዶ በድንግል ማኀፀን አደረ” እንዲል ትምህርተ ኀብአት በተጨማሪ “ሥጋ ለብሰ ዘይማስን ወዘኢይማስን ለሥጋ መዋቲ ረሰዮ ዘኢይማስን” “የማይፈርሰው የሚፈርሰው ሥጋ ለበስ የሚሞተው ሥጋ እንዳይሞት /እንዳይፈርስ/ አደረገው” ተብሎ እንደተፃፈ (በትምህርት ኀቡአት)፡፡አባታችን ቅዱስ ያሬድም በአንቀጸ ብርሃን “እንዘ አልቦቱ እም በሰማያት ወአብ በዲበ ምድር “በሠማይ እናት በምድር ደግሞ አባት የለውም” በማለት ሁለተኛ ልደቱ ያለ አባት መሆኑን ይገልፃል ጌታችን ከወላዲተ አምላክ ከድንግል ሥጋን ከነሣ በኋላ /ከተወለደ በኋላ/ እንደ ህፃናት እየተጫወተ እየተማረ ከኃጢአት በስተቀር የሠውን ስርአት ሁሉ ፈፅሟል፡፡ ‹ወኮነ ሰብአ ከማነ ዘእንበለ ኃጢአት በህቲታ› “ከኃጢአት በቀር እንደ እኛ ሰው ሆነ› እንዳለ ቅዱስ ኤፍሬም /ውዳሴ ማርያም ዘሐሙስ/ ጌታችን መድኃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ የዕብራውያንን ህግ ተምሮ በ30 ዘመኑ በዮሐንስ እጅ በዮርዳኖስ ከተጠመቀ በኋላ አርባ ቀንና ሌሊት ፆሞ ብዙ ተአምራትን ፈፅሟል፡፡ ይህንን ሲገልፅ ሊቁ ቅዱስ ሕርያቆስ እንዲህ አለ ‹ፍጹመ ኮነ ሰብአ ወኩሎ ሕገ ሰብአ ፈጸመ ዘእንበለ ኃጢአት› ‹ከኃጢአት በስተቀር የሰውን ሕግ ፈፀመ ‹እምኀበ ዮሐንስ ተጠምቀ ውስተ ገዳም ተመከረ ርኀበ ወጸምአ ወተአምራት ገብረ› ‹ፍፁም ሰው ሆነ ከኃጢአት በስተቀር የሠውን ህግ ፈፀመ የዕብራውያንን ሕግ ተማረ ከዮሐንስ ዘንድ ተጠመቀ በበረሀ ተፈተነ ››/ቅዳሴ ማርያም/
ጌታችን መድኃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ አዳምን ነፃ የሚያወጣበት ራሱን አሣልፎ የሚሠጥበት ጊዜ ከመድረሱ አሰቀድሞ በዕለተ ሐሙስ ምሽት መድኃኒት የሚሆን ሥጋውና ደሙን ለዓለም ሠጥቷል፡፡ ስርዓተ ቁርባንን ሠርቷል፡፡ /ማቴ 26፡26/ ይህንን ሥርዓት ከሠራ በኋላም አይሁድ ተሰብስበው ሊይዙት ገመድ ይዘው ወደ ጌቴሴማኒ መጡ፡፡ ‹‹ዘይሰሰይ አክልየ አንስአ ሰኰናሁ በላዕሌየ› ‹እንጀራዬን የበላ በእኔ ላይ ተረከዙን አነሣ /መዝ 40፡9/ እንዳለ ቅዱስ ዳዊት፣ ያስተምረው የነበረው የአስቆሮቱ ይሁዳ በ30 ብር አሳልፎ ሠጠው አይሁደም፣ < አምላክ ነኝ ይላል>፣ ፣ ፣ የሰንበትን ቀን ሽሯል በሚሉ የሐሰት ሀሳቦች ተነሥተው ከተያዘበት ሠዓት ጀምረው ያሰቃዩት ነበር፡፡ ሲነጋም በሐሰት ክስ አስፈርደውበት ሊቀጡት በጲላጦስ ፊት አቆሙት፡፡ ‹ሰላም ለአዕጋሪከ እለ ጠብዓ ለቀዊም ቅድመ ጲላጦስ መስፍነ ይሁዳ ወሮም› ‹በሮም እና በይሁዳ መስፍን በጲላጦስ ፊት ያለ ፍርሃት በድፍረት ለቆሙ እግሮችህ ሠላም እላለሁ> እንዲል /መልክዓ ኢየሱስ/›፡፡ የይሁዳ እና የሮም መስፍን የሆነው ጲላጦስ በደል ባያገኝበት የሕዝቡን ዓመፅ ፈርቶ አንደ ፈቃዳቸው ፈረደላቸው አይሁድም እየገፉ፣ እያዳፉ መስቀል አሸክመው ወደ ቀራንዮ አወጡት፡፡ በዕለተ አርብ 6፡00 ሰዓት በሆነም ጊዜ እጆቹን እግሮቹን ቸነከሩት በመስቀል ላይ ሰቀሉት ከገረፉት ግርፋትም የተነሳ ሥጋው አልቆ አጥንቶቹ ይታዩ ነበር (ድርሳነ ማኅየዊ)፡፡ በመዝ 21 ላይ ‹‹ዐገቱኒ ከለባት ብዙኃን ማኀበረ ለእኩያን ቀነውኒ እደውየ ወእገርየ፣ ወኆለቁ ኩሎ አዕፅምትየ›› ‹‹ብዙ ውሾች ከብበውኛልና የክፋተኞች ጉባኤም ያዘኝ እጆቼን እግሮቼን ቸነከሩኝ አጠንቶቼ ሁሉ ተቆጠሩ›› ተብሎ በቅዱስ ዳዊት እንደተነገረ ጌታችን አዳም እፀ በለስን ስለመብላቱ ጌታ በአፍ ሀሞት ተጐነጨ፣ ይህንን ሁሉ መከራ ስለ አዳም ተቀበለ በጠቅላላው 13 ሕማማትን ስለ ሠው ልጆች ተሸከመ፡፡ በቅዳሴ እግዚእ ላይ “ሰፍሐ እደዊሁ ለሕማም ሐመ ከመ ሕሙማን ያድኀን እለ ተወከሉ በላዕሌሁ” ‹‹እጆቹን ለሕማም ዘረጋ በእርሱ የታመኑትን ያድን ዘንድ አንደ ሕሙማን ታመመ›› ተብሎ እንደተፃፈ፡፡
አንዳንዶች ‹ታቦት ተሰርቆ ተሸጠ› የሚሉ ዜናዎችን በማራገብ ታቦቱ ኃይል የለውም ሊሉን ይሞክራሉ፡፡ እንኳን የክርስቶስ ስም የተጻፈበት ታቦት ቀርቶ ራሱ ክርስቶስ በሠላሳ ብር ተሸጦ ከሊቶስጥራ እስከ ቀራንዮ እየተተፋበት ፣ እየተደበደበ ተጎትቶ ተሰቅሎ የለምን? ክብር ይግባውና ኃይል የለውም ሊባል ይችላል? ‹‹ታቦቱን ገልጠን እናሳያለን›› ብለው እየፎከሩ ቤተ ክርስቲያንን ያዋረዱ የሚመስላቸው ፣ በታቦቱ እግዚአብሔርን የምታመልከውን ቤተ ክርስቲያን ታቦት ታመልካለች ብለው ያላለችውን በግድ ብላለች ብለው ድርቅ የሚሉ ሰዎች ስናይ ከማዘን ውጪ ምን እንላለን? ቤተ ክርስቲያን ታቦትን የምትሸፍነው ስለሚሠዋበት የጌታችን ሥጋና ደም ክብር እንጂ ቢገለጥ የምታፍርበት ነገር ኖሮ አይደለም፡፡ ቢገለጥ የሚታየው የመድኃኔዓለም ክርስቶስና የቅዱሳኑ ስም ነው፡፡ ጌታዋ ዕርቃኑን በመሰቀሉ ያላፈረች ቤተ ክርስቲያን ስሙ በተጻፈበት ታቦት አታፍርም!
ዲያቆን ሄኖክ ኃይሌ
+++ ታቦትና ኢየሱስ ክርስቶስ +++
የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን ታቦታት ላይ የተጻፈው ምንድር ነው? ተብለው ቢጠየቁ መልስዎ ምን ይሆን? ‹ዐሥርቱ ትእዛዛት ተጽፈዋል› ካሉ መልስዎ ትክክል አይደለም፡፡ ትክክለኛውን መልስ ከመመልከታችን በፊት ጥቂት ነገሮች ስለ ታቦት እንመልከት፡፡ ብዙ ጊዜ ስለ ታቦት አስፈላጊነት በሚሠጡ ማብራሪያዎች ላይ ሰፊውን ቦታ የሚይዘው ስለ ብሉይ ኪዳን ታቦት የሚናገሩ ጥቅሶችን በመጥቀስ በመሆኑ ምክንያት ስለ ታቦት የሚነሡ ጥያቄዎች እንዳያቋርጡ ያደረገ ይመስላል፡፡ ስለዚህ በዚህች አጭር ጽሑፍ ‹ነገርን ከሥሩ› የሚለውን አካሔድ ሳንከተል በቀጥታ ስለ ሐዲስ ኪዳን ታቦት ብቻ እንመለከታለን፡፡
ታቦት በሐዲስ ኪዳን ለምን ያስፈልጋል? የሚለውን ጥያቄ ለመመለስ ጌታችን በመጨረሻዋ ምሽት ሐሙስ ምሥጢረ ቁርባንን ባስተማረ ጊዜ ያደረገውን እናስታውስ፡፡ ጌታችን ሐዋርያቱ በተሰበሰቡበት ‹‹እንጀራውን አንሥቶ ባረከ ቆርሶም ሠጣቸው እንካችሁ ብሉ ይህ ሥጋዬ ነው አለ፡፡ ጽዋውንም አንሥቶ አመሰገነ እንካችሁ ጠጡ ይህ ስለብዙዎች የኃጢአት ይቅርታ የሚፈስሰው የሐዲስ ኪዳን ደሜ ነው አለ›› (ማቴ. 26፡26) ጌታችን አስቀድሞ ‹‹ሥጋዬን የሚበላ ደሜን የሚጠጣ የዘላለም ሕይወት አለው›› ብሎ በትምህርት የመሠረተውን ምሥጢረ ቁርባን በተግባር ለሐዋርያቱ በዚህ መልኩ አስተማራቸው፡፡ (ዮሐ. 6፡56) ሐዋርያቱም ከጌታችን ዕርገት በኋላ ወንጌልን እየሰበኩ ‹‹እንጀራውን በመቁረስ ይተጉ ነበር›› (ሐዋ.2፡42) ቅዱስ ጳውሎስም ‹‹ከጌታ የተቀበልሁትን ለእናንተ ደግሞ አሳልፌ ሠጥቻችኋለሁ›› በማለት ሥጋ ወደሙን እንዴት መቀበል እንደሚገባና ‹ሳይገባው የሚቀበል የጌታ ሥጋና ደም ዕዳ›› እንዳለበት በማስተማር የቁርባንን ሥርዓት ደነገገ፡፡ (1ቆሮ. 11፡23-30)
ልብ እንበል የክርስቶስ ሥጋና ደም መሠጠቱን የሚያምን አንድ ክርስቲያን ይህ የከበረ ሥጋና ደም እንደ ተራ ማዕድ በየቦታው ፣ በየጠረጴዛው ሊቀርብ ይችላል ብሎ ለማሰብ እጅግ ይከብደዋል፡፡ ስለዚህም ቤተ ክርስቲያን ዘመነ ሰማዕታት አልፎ ስደትዋ እስካበቃበት ዘመን ድረስ በሒደት እየተሻሻለ በመጣ የቤተ መቅደስ ሥርዓት የሐዲስ ኪዳኑን መሥዋዕት በክብር ለመሠዋትና ለምእመናን ለማቀበል በቅታለች፡፡ የበግና የፍየል ደም ይሠዋ በነበረበት የኦሪት ዘመን እንኳን ለብቻው ትልቅ መሠዊያ ተዘጋጅቶ ፣ መሠዊያው ተቀድሶ ሰው በማይገባበት በመገናኛው ድንኳን ውስጥ በክብር ተቀምጦ ነበር፡፡ በድንኳኒቱ ውስጥ የሚያገለግሉት አሮንና ልጆቹም የተለየ ልብስ ለብሰው የበጉን ደም በመሠዊያው ዙሪያ ባለው ቀርነ ምሥዋዕ (የመሠዊያ ቀንድ) ላይ እየቀቡ ሥርዓቱን ይፈጽሙ ነበር፡፡ ለበግና ለፍየል መሥዋዕት ይህ ሁሉ ክብር ከተሠጠ እንደ በግ ስለ ሁላችን ኃጢአት ራሱን መሥዋዕት አድርጎ ያቀረበው የእግዚአብሔር በግ ፣ እንደ ሊቀ ካህናትነቱ እጁን በመስቀል ላይ ዘርግቶ የተሠዋውና ሥጋና ደሙን እንካችሁ ብሉ ብሎ የሠጠን የኢየሱስ ክርስቶስ ሥጋና ደም መሥዋዕት ሆኖ የሚቀርብበት መሠዊያ ምንኛ የከበረ ይሆን?
የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን የሥጋ ወደሙ ‹መሠዊያ› የምትለው ታቦት በቅርጽም ፣ በአገልግሎትም ፣ በክብርም በኦሪት እግዚአብሔር ለሙሴ ከሠጠው ታቦት ጋር አንድ አይደለም፡፡ የቀደመው ታቦት በአራት ካህናት የሚያዝ በውስጡ ጽላት የሚቀመጥበት ሲሆን የአሁኑ ታቦት ግን የጽላት ቅርጽ ያለው ጽሌ (ሰሌዳ) ነው፡፡ ቤተ ክርስቲያኒቱ የሐዲስ ኪዳኑን ታቦት በሦስት ስያሜ ትጠራዋለች - የቃልኪዳኑ ታቦት ፣ ጽላት እና መሠዊያ ብላ፡፡ የቃልኪዳኑ ታቦት የሚባለው እግዚአብሔር ከእስራኤል ጋር ስላደረገው ስለ ቀድሞ ቃልኪዳን ሳይሆን ‹‹ሥጋዬን የሚበላ ደሜን የሚጠጣ የዘላለም ሕይወት አለው›› ተብሎ ስለተሠጠው እና ‹‹ስለብዙዎች የኃጢአት ይቅርታ የሚፈስሰው የሐዲስ ኪዳን ደሜ ነው›› ብሎ ጌታችን ስለ ሠጠን አዲሱ ኪዳን ነው፡፡ (ማቴ. 26፡26-30) የቃልኪዳኑ ታቦት የሚባለው በሥጋ ወደሙ ስለተሠጠን ሐዲስ ኪዳን ነው፡፡ ታቦት መባሉ ደግሞ እግዚአብሔር በረድኤት የሚያድርበት ፣ በሥጋ ወደሙ ደግሞ በአካል የሚገለጥበት ዙፋን ስለሆነ ነው፡፡
ጽላት (ሰሌዳ) የሚባለው ዐሠርቱ ትእዛዛት ተጽፈውበት አይደለም፡፡ የሕግ ሁሉ ፈጻሚ የሆነው የመድኃኔዓለም ክርስቶስ ‹‹አልፋና ኦሜጋ›› የሚለው የከበረ ስሙ በታቦቱ ላይ ስለተጻፈ ነው፡፡ (ሥርዓተ ቤተ ክርስቲያን /ሊቀ ካህናት ክንፈ ገብርኤል አልታዬ/ ፣ የኢትዮጵያ ቤተ ክርስቲያን ታሪክ /ብፁዕ አቡነ ጎርጎርዮስ/)
አንዳንድ ሰዎች ‹‹የኢትዮጵያ ቤተ ክርስቲያን ታቦት ከኦሪቱ ጋር አይመሳሰልም!›› ብለው እንደ ትልቅ መከራከሪያ ሲያውጁ ማየት እጅግ ያስገርማል፡፡ አንዴ ‹ኦሪታዊት ነሽ› አንድ ጊዜ ደግሞ ‹‹ለምን እንደ ኦሪቱ አልሆንሽም›› ብሎ ንትርክ ግራ ያጋባል፡፡
ሌሎች ደግሞ "በበዛችሁም ጊዜ በምድርም ላይ በረባችሁ ጊዜ፥ ይላል እግዚአብሔር፥ በዚያ ዘመን፦ የእግዚአብሔር የቃል ኪዳኑ ታቦት፡ ብለው ከእንግዲህ ወዲህ አይጠሩም፤ ልብ አያደርጉትም፥ አያስቡትምም፥ አይሹትምም፥ ከእንግዲህ ወዲህም አይደረግም:" የሚለውን ጥቅስ ለአሁኑ ታቦት አለማስፈለግ ሊጠቅሱ ይሞክራሉ:: (ኤር 3:16) ይህ ቃል ግን እስራኤል የቃል ኪዳኑ ታቦት ብለው የሚጠሩት የኦሪቱ ታቦት ለእነርሱ አገልግሎት መሥጠት እንዳቆመና እግዚአብሔርም ከሕዝቡ ጋር አዲስ ቃል ኪዳን እንደሚገባ የሚያስረዳ ነው:: አሁን የምገለገልበት ታቦት የቀደመው ቃልኪዳን ታቦት ሳይሆን "ይህ የሐዲስ ኪዳን ደሜ ነው" ብሎ በደሙ አዲስ ኪዳን የሠጠበትን ሥጋውንና ደሙን የምንቀበልበት የአዲስ ኪዳን ታቦት ነው:: አዎ እስራኤል የቀደመውን ታቦት አይሹትም ዐሠርቱ ትእዛዛት ያለበት የቃልኪዳን ታቦትም ከእንግዲህ ወዲህ አይደረግም:: እኛ ያለን አዲስ ኪዳን በስሙ የተጠራበት የክርስቶስ ቃልኪዳን ነው::
የኦሪቱን ያልመሰለው አሁን ያለነው ሐዲስ ኪዳን ላይ ስለሆነና የታቦቱ አገልግሎት የተለየ ስለሆነ ነው፡፡ የሐዲስ ኪዳኑ ታቦ ት ከቀድሞው አንድ ታቦት ተለይቶ በቁጥር የበዛውም ለብዙዎች መድረስ ያለበት የክርስቶስ ሥጋና ደም የሚፈተትበት መሠዊያ ስለሆነ ነው፡፡ መድኃኒት ቤት የሚበዛው መድኃኒት የሚያስፈልጋቸው ሰዎች ሲበዙም አይደል? ታቦት የበዛው በታቦቱ የሚሠዋው መሥዋዕት ለብዙዎች ስለ ኃጢአት ይቅርታ የሚፈስሰውና ከኃጢአት ሁሉ የሚያነጻው ያለሱ ሕይወት የላችሁም የተባልነው ሥጋና ደሙ ለኃጢአት በሽተኞች ስለሚያስፈልገን ነው::
ብፁዕ አቡነ ጎርጎርዮስ እንዲህ ሲሉ ያብራራሉ ‹‹የኦሪት ጽላት እግዚአብሔር በደመና ተከናንቦ ሙሴንና አሮንን የሚያነጋግርበት ለእስራኤል ብቻ በረድኤት የሚገለጥበት ዙፋን ነበር፡፡ ይህ ግን (የሐዲስ ኪዳኑ ታቦት) የአምላክ ሥጋና ደም የሚፈተትበት (ጌታችን) ሥጋዬን የበላ ደሜን የጠጣ የዘላለም ሕይወት አለው ሥጋዬን ብሉ ደሜን ጠጡ እያለ ያመኑትን የሚጠራበት የምሕረት ምሥዋዕ (መሠዊያ) ነው፡፡ ክብርና ስግደትም የሚደረግለት ለዚህ ነው፡፡›› (የኢትዮጵያ ቤተ ክርስቲያን ታሪክ ገጽ 109) ሌላው አስገራሚ ነገር አቡነ ጎርጎርዮስ በታቦት ሥርዓት ከግሪኮች አንዲሚስዮን ጋር እንደምንመሳሰል ጠቅሰው ሲጽፉ ግሪኮቹ ደግሞ ስለ አንዲሚስዮን ሲያብራሩ ከኢትዮጵያ ታቦት ጋር የሚመሳሰል ብለው መጻፋቸው ነው።