††† በስመ አብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ አሐዱ አምላክ አሜን ! †††
#ጥር ፲፩
#ቅዱስ_በላትያኖስ
➤ ይህ ቅዱስ ሐዋርያዊ ጳጳስ የቀድሞዋ ሮም ሊቀ ጳጳሳት ሲሆን ቸር፣ ትጉህና በጐ እረኛ ነበር።
➤ መናፍቃንን ሲያርም፣ ምዕመናንን ሲመክር፣ ስለ መንጋው እንቅልፍ አጥቶ ኑሯል።
➤ በፍጻሜውም በዚህች ቀን ጥር ፲፩ የሮም ንጉሥ ለ፩ ዓመት አሰቃይቶ ገድሎታል።
➤ ዕሴተ ኖሎትን (የእረኝነት ዋጋንም) ከጌታችን ተቀብሏል።
✥••┈┈••●◉ ✞ ◉●••┈┈••✥
➤ የካቲት ፲፩ ቀን የሚከበሩ ዓመታዊ የቅዱሳን በዓላት
፩.አባ አውሎግ አንበሳዊ
፪.አባ አውሎጊን ጻድቅ (የአባ አውሎግ መምህር)
፫.አባ በላትያኖስ ሰማዕት (የሮም ሊቀ ጳጳሳት)
፬.አባ በትራ (የጻድቁ አባ ስልዋኖስ ደቀ መዝሙር)
፭.አባ አብርሃም ኤጲስ ቆጶስ
፮.አባ መቃቢስ
፯.አባ ኮንቲ
➤ ወርኀዊ በዓላት
፩.ቅዱስ ያሬድ ካህን
፪.ቅዱስ ገላውዴዎስ ሰማዕት
፫.ቅዱስ ፋሲለደስ ሰማዕት
፬.ብፁዐን ኢያቄም እና ሐና
፭.አቡነ ሐራ ድንግል ጻድቅ
✥••┈┈••●◉ ✞ ◉●••┈┈••✥
“ በቅዱሳንም ዘንድ ያለው የርስት ክብር ባለ ጠግነት ምን እንዲሆን ለምናምን ከሁሉ የሚበልጥ የኃይሉ ታላቅነት ምን እንዲሆን ታውቁ ዘንድ ነው፤”
— ኤፌሶን፩፥፲፱
✥••┈┈••●◉ ✞ ◉●••┈┈••✥
"✞✞✞ አምላከ አበው ቅዱሳን በመጽናታቸው ያጽናን። ከበረከታቸውም ያድለን።✞✞✞"
✞✞✞✞✞ አሜን ✞✞✞✞✞
✥••┈┈••●◉ ✞ ◉●••┈┈••✥
📖 ወስብሐት ለእግዚአብሔር 📖
📖 ወለወላዴቱ ድንግል 📖
📖 ወለመስቀሉ ክቡር 📖
📖✞✞✞✞✞📖
✞✞✞ ሃሳብ ➢
@gebrye_comment_bot
|❀:✧๑ ✞✞✞✞✞✞✞ ๑✧❀|:
✞✞✞ ይቀላቀሉ ➣
@mahteben_albetsm
††† በስመ አብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ አሐዱ አምላክ አሜን ! †††
#እንኳን_ለእመቤታችን_ለቅድስት_ድንግል_ማርያም_አመታዊ_በኃል_በሰላም_አደረሳቹ።
#ጥር ፳፩
#ዕረፍተ_ድንግል
➤ እመቤታችን ቅድስት ድንግል ማርያም ቅድመ ዓለም በአምላክ ልቡና ታስባ ትኖር ነበር። ከነገር ሁሉ በፊት እግዚአብሔር እናቱን ያውቃት ነበር።
➤ ዓለም ተፈጥሮ አዳምና ሔዋን ስተው መርገመ ሥጋና መርገመ ነፍስ አግኝቷቸው በኀዘን ንስሐ ቢገቡ "እትወለድ እም ወለተ ወለትከ - ከ፭ ቀን ተኩል (፭፼፭፻ ዘመናት) በኋላ ካንተ ባሕርይ ከምትገኝ ንጽሕት ዘር ተወልጄ አድንሃለሁ።" ብሎ ተስፋ ድኅነት ሰጠው።
➤ ከአዳም አንስቶ ለ፭፼፭፻ ዓመታት አበው፣ ነቢያትና ካህናት ስለ ድንግል ማርያም ብዙ ሐረገ ትንቢቶችን ተናገሩ። መዳኛቸውን ሱባኤ ቆጠሩላት፤ ምሳሌም መሰሉላት። ከሩቅ ዘመን ሁነውም ሊያገኟት እየተመኙ እጅ ነሷት።
"እምርሑቅሰ ርእይዋ ወተአምኅዋ" እንዲል።
#የድንግል_ማርያም_ሐረገ_ትውልድ
➢ #ከአዳም_በሴት
➢ #ከያሬድ_በሄኖክ
➢ #ከኖኅ_በሴም
➢ #ከአብርሃም_በይስሐቅ
➢ #ከያዕቆብ_በይሁዳና_በሌዊ
➢ #ከይሁዳ_በእሴይ፣ #በዳዊት፣ #በሰሎሞንና_በሕዝቅያስ ወርዳ
➢ #ከኢያቄም_ትደርሳለች።
➢ #ከሌዊ_ደግሞ_በአሮን፣ #አልዓዛር፣ #ፊንሐስ፣ #ቴክታና #በጥሪቃ #አድርጋ #ከሐና #ትደርሳለች።
➤ አባታችን አዳም ከገነት በወጣ በ፭፼፬፻፹፭ ዓመት ወላዲተ አምላክ ንጽሕና ሳይጐድልባት፣ ኃጢአት ሳያገኛት፣ ጥንተ አብሶ ሳይደርስባት ከደጋጉ ኢያቄም ወሐና ትወለዳለች።
“የሠራዊት ጌታ እግዚአብሔር ዘርን ባያስቀርልን ኖሮ፥ እንደ ሰዶም በሆንነ እንደ ገሞራም በመሰልነ ነበር።”
— ኢሳይያስ. ፩፥፱
“ወዳጄ ሆይ፥ ሁለንተናሽ ውብ ነው፥ ነውርም የለብሽም።”
— መኃልየ. ፬፥፯
"ወኢረኩሰት በምንትኒ እምዘፈጠራ" እንዳለ።
#ቅዱስ_ቴዎዶጦስ_ዘዕንቆራ
➤ ከዚያም ከእናት ከአባቷ ቤት ለሦስት ዓመታት ቆይታ ወደ ቤተ መቅደስ ትገባለች። በቤተ መቅደስም ለ፲፪ ዓመታት ፈጣሪዋን እግዚአብሔርን እያመሰገነችና እያገለገለች እርሷን ደግሞ መላእክተ ብርሃን እያገለገሏት ሕብስት ሰማያዊ ጽዋዕ ሰማያዊ እየመገቧት ኑራለች። ፲፭ ዓመት በሞላት ጊዜ አረጋዊ ዮሴፍ ያገለግላት ዘንድ ወደ ቤቱ ወሰዳት።
➤ በዚያም መልአከ ብሥራት ቅዱስ ገብርኤል ዜና ድኅነትን ነግሯት አካላዊ ቃልን በማኅጸንዋ ጸነሰችው። ነደ እሳትን ተሸከመችው፤ ቻለችው። "ጾርኪ ዘኢይትጸወር ወአግመርኪ ዘኢይትገመር" እንዳለ።
#ሊቁ_ቅዱስ_ኤፍሬም_ለብሐዊ
ወልደ እግዚአብሔርን ለ፱ ወር ከ፭ ቀን ጸንሳ እንበለ ተፈትሆ (በድንግልና) ወለደችው።
“ስለዚህ ጌታ ራሱ ምልክት ይሰጣችኋል፤ እነሆ፥ ድንግል ትፀንሳለች፥ ወንድ ልጅም ትወልዳለች፥ ስሙንም አማኑኤል ብላ ትጠራዋለች።”
— ኢሳይያስ. ፯፥፲፬
"ኢየሱስ" ብላ ስም አውጥታለት በገሊላ ለ፪ ዓመታት ቆዩ። አርዌ ሄሮድስ እገድላለሁ ብሎ በተነሳበት ወቅትም ልጇን አዝላ በረሃብ እና በጥም፣ በላበትና በድካም፣ በዕንባና በኀዘን ለ፫ ዓመት ከ፮ ወር ከገሊላ እስከ ኢትዮጵያ ተሰዳለች።
➤ ልጇ ጌታችን ፭ ዓመት ከ፮ ወር ሲሆነው ለድንግል ደግሞ ፳፩ ዓመት ከ፫ ወር ሲሆናት ወደ ናዝሬት ተመለሱ።
በናዝሬትም ለ፳፬ ዓመት ከ፮ ወር ልጇን ክርስቶስን እያሳደገች ነዳያንን እያሰበች ኑራለች። እርሷ ፵፭ ዓመት ልጇ ፴ ዓመት ሲሆናቸው ጌታችን ተጠመቀ
➤ በጉባኤ ትምህርት፣ ተአምራት ጀመረ። ለ፫ ዓመት ከ፫ ወርም ከዋለበት እየዋለች ካደረበትም እያደረች ትምህርቱን ሰማች።
የማዳን ቀኑ ደርሶ ልጇ ክርስቶስ ሲሰቀልም የመጨረሻውን ፍጹም ኀዘን አስተናገደች። አንጀቷ በኀዘን ተቃጠለ። በነፍሷም ሰይፍ አለፈ።
“ስምዖንም ባረካቸው እናቱን ማርያምንም፦ እነሆ፥ የብዙዎች ልብ አሳብ ይገለጥ ዘንድ፥ ይህ በእስራኤል ላሉት ለብዙዎቹ ለመውደቃቸውና ለመነሣታቸው ለሚቃወሙትም ምልክት ተሾሞአል፥ በአንቺም ደግሞ በነፍስሽ ሰይፍ ያልፋል አላት።”
— ሉቃስ. ፪፥፴፬-፴፭
➤ ጌታ በተነሳ ጊዜም ከፍጥረት ሁሉ ቀድማ ትንሣኤውን አየች። ለ፵ ቀናትም ሳትለይ ከልጇ ጋር ቆየች። ከልጇ ዕርገት በኋላ በጽርሐ ጽዮን ሐዋርያትን ሰብስባ ለጸጋ መንፈስ ቅዱስ አበቃች። በጽርሐ ጽዮንም ከአደራ ልጇ ከቅዱስ ዮሐንስ ጋር ለ፲፭ ዓመታት ኖረች።
➤ በእነዚህ ዓመታት ሥራ ሳትፈታ ስለ ኃጥአን ስትማልድ፣ ቃል ኪዳንን ከልጇ ስትቀበል፣ ሐዋርያትን ስታጽናና፣ ምሥጢርም ስትገልጽላቸው ኑራለች።
ዕድሜዋ ፷፬ በደረሰ ጊዜ ጥር ፳፩ ቀን መድኃኒታችን አእላፍ ቅዱሳንን አስከትሎ መጣ፤ ኢየሩሳሌምን ጨነቃት።
➤ አካባቢውም በፈውስ ተሞላ። በዓለም ላይም በጐ መዓዛ ወረደ። እመ ብርሃን ለፍጡር ከዚያ በፊት ባልተደረገ ለዘላለምም ለማንም በማይደረግ ሞገስ፣ ክብርና ተአምራት ዐረፈች። ሞቷ ብዙዎችን አስደንቋል።
"ሞትሰ ለመዋቲ ይደሉ
ሞታ ለማርያም የአጽብ ለኩሉ።" እንዲል።
➤ ከዚህ በኋላ መላእክት እየዘመሩ ሐዋርያቱም እያለቀሱ ወደ ጌቴሴማኒ በአጐበር ሥጋዋን ጋርደው ወሰዱ።
#ይህንን_ሊቃውንት፦
"ሐራ ሰማይ ብዙኃን እለ አልቦሙ ሐሳበ
እንዘ ይዜምሩ ቅድሜኪ ወመንገለ ድኅሬኪ ካዕበ ማርያም ሞትኪ ይመስል ከብካበ።" ሲሉ ይገልጡታል።
➤ በወቅቱ ግን አይሁድ በክፋት ሥጋዋን እናቃጥል ስላሉ ቅዱስ ገብርኤል (ጠባቂ መልአክ ነው።) እነርሱን ቀጥቶ እርሷን ከቅዱስ ዮሐንስ ጋር ወስዶ በዕጸ ሕይወት ሥር አኑሯታል። በዚያም መላእክት እያመሰገኗት ለ፪፻፭ ቀናት ቆይታለች።
➤ ቅዱስ ዮሐንስ መጥቶ ለሐዋርያቱ ክብረ ድንግልን ቢነግራቸው በጐ ቅንአት ቀንተው በነሐሴ ፩ ሱባኤ ጀመሩ።
➢ ሁለተኛው ሱባኤ ሲጠናቀቅም ጌታ የድንግል ማርያምን ንጹሕ ሥጋ ሰጣቸው። እየዘመሩም በጌቴሴማኒ ቀብረዋታል።
➢ በሦስተኛው ቀን (ነሐሴ ፲፮) እንደ ልጇ ባለ ትንሣኤ ተነስታ ዐርጋለች። ትንሣኤዋንና ዕርገቷንም ደጉ ሐዋርያ ቅዱስ ቶማስ አይቶ መግነዟን ተቀብሏል። ሐዋርያቱም መግነዟን ለበረከት ተካፍለው እንደ ገና በዓመቱ ነሐሴ ፩ ቀን ሱባኤ ገቡ።
➤ ለሁለት ሳምንታት ቆይተው ሁሉንም ወደ ሰማይ አወጣቸው። በፍጡር አንደበት ተከናውኖ የማይነገር ተድላ፣ ደስታና ምሥጢርንም አዩ።
➤ ጌታ ራሱ ቀድሶ ሁሉንም አቆረባቸው። የበዓሉን ቃል ኪዳን ሰምተው ከድንግል ተባርከው ወደ ደብረ ዘይት ተመልሰዋል።
✥••┈┈••●◉ ✞ ◉●••┈┈••✥
✞✞✞"ጽንዕት በድንግልና ሥርጉት በቅድስና እመቤታችን ጸጋውን ክብሩን እንዳይነሳን ለምኝልን። አእምሮውን፣ ለብዎውን፣ ጥበቡን በልቡናችን ሳይብን አሳድሪብን።"✞✞✞
✞✞✞✞✞ አሜን ✞✞✞✞✞
✥••┈┈••●◉ ✞ ◉●••┈┈••✥
📖 ወስብሐት ለእግዚአብሔር 📖
📖 ወለወላዴቱ ድንግል 📖
📖 ወለመስቀሉ ክቡር 📖
📖✞✞✞✞✞📖
✞✞✞ ሃሳብ ➢
@gebrye_comment_bot
|❀:✧๑ ✞✞✞✞✞✞✞ ๑✧❀|:
✞✞✞ ይቀላቀሉ ➣
@mahteben_albetsm
††† በስመ አብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ አሐዱ አምላክ አሜን ! †††
#ጥር ፯
#ሥሉስ_ቅዱስ
➤ ምሥጢራት በእምነት ለማይኖር በትሕትናም ለማይቀርብ የሚገለጡ አይደሉም።
➤ እግዚአብሔር አንድም ነው፤ ሦስትም ነው። ጊዜ ሣይሠፈር ዘመንም ሳይቆጠር እግዚአብሔር በስም፣ በአካል፣ በግብር ሦስትነቱ፤ በባሕርይ፣ በሕልውና፣ በመለኮትና በሥልጣን አንድነቱ የጸና አምላክ ነው።
➤ ከዓለም መፈጠር በፊት ስለ ነበረው ነገር የሚያውቅ ራሱ ሥላሴ ብቻ ነው። ዓለምን ከፈጠረ በኋላም ምሥጢረ ሥላሴ (መለኮት) ብለን የምንማረው ትምህርት እንድንና እንጠቀም ዘንድ እርሱ የገለጠልንን ያህል ብቻ ነው።
➤ ይኸውም በየጊዜው እርሱ ለወደዳቸውና ደስ ላሰኙት ቅዱሳኑ የገለጠው ምሥጢር ነው። ከዚህ አልፈን በሥጋዊ አዕምሯችን ጌታን "እንመርምርህ" ብንለው ግን ፍጻሜአችን ሞት ማደሪያችንም ገሃነመ እሳት መሆኑ አይቀርም።
➤ እግዚአብሔር በአንድነቱና ሦስትነቱ ሳለ ይህንን ዓለም ፈጠረ። እግዚአብሔር ዓለምን ለምን ፈጠረ ቢሉ ስሙን ቀድሰን ክብሩን እንድንወርስ ነው።
➤ ከዚህ የተረፈውን ምክንያት ግን ራሱ ያውቃል። በአንድነቱ ምንታዌ (ሁለትነት) በሦስትነቱ ርባዔ (አራትነት) የሌለበት የዘላለም አምላክ የፍጥረታት ሁሉ ፈጣሪ እግዚአብሔር ነው። አብ፣ ወልድ፣ መንፈስ ቅዱስ በስም፣ በአካል፣ በግብር ሦስትነት በባሕርይ፣ በሕልውናና በፈቃድ አንድነት የጸኑ ናቸው።
➤ በዚህ ጊዜ ተገኙ በዚህ ጊዜ ያልፋሉ አይባሉም። መጀመሪያም መጨረሻም እነርሱ ናቸውና። ርኅሩኀን ናቸውና በእናት ሥርዓት "ቅድስት ሥላሴ" እንላቸዋለን። የሚጠላቸው (የማያምንባቸውን) አይጠሉም።
➤ የሚወዳቸውን ግን እጽፍ ድርብ ይወዱታል። በቤቱም መጥተው ያድራሉ።
ከፍጥረታት ወገን ከእመቤታችን ቀጥሎ የአብርሃምን ያህል በሥላሴ ዘንድ የተወደደ ፍጡር የለም።
➤ አባታችን ቅዱስ አብርሃም የደግነት ሁሉ አባት ነውና በኬብሮን በመምሬ ዛፍ ሥር ሥላሴን ተቀብሎ አስተናግዷል።
አባታችን አብርሃም በ፺፱ ዓመቱ እናታችን ሣራ በ፹፱ ዓመቷ ሥላሴን በድንኳናቸው አስተናገዱ።
➤ አብርሃም እግራቸውን አጠበ። (ወይ መታደል!) በጀርባውም አዘላቸው። (ድንቅ አባት!) ምሳቸውንም አቀረበላቸው። እንደሚበሉ ሆኑለት። በዚያው ዕለትም የይስሐቅን መወለድ አበሠሩት።
➤ ሥላሴን ያስተናገደች ድንኳን (ሐይመት) የድንግል እመቤታችን ማርያም ምሳሌ ናት። በድንግል ላይ አብ ለአጽንኦ፣ መንፈስ ቅዱስ ለአንጽሖ፣ ወልድ በተለየ አካሉ ለሥጋዌ በእርሷ ላይ አርፈዋል (አድረዋልና)።
➤ በዓለ ሥላሴ በዚህ ቀን ጥር ፯ የሚከበረው ስለ ሁለት ምክንያቶች ነው።
➔ ቀዳሚው ሕንጻ ሰናዖርን ማፍረሳቸው ሲሆን
➔ ሁለተኛው ደግሞ ቅዳሴ ቤታቸው ነው።
➤ ሰናዖር ከሺህዎች ዓመታት በፊት በአሁኗ ኢራቅ አካባቢ እንደ ነበረ የሚነገርለት ግዛት ሲሆን ስሙ ለሃገሪቱም ለንጉሡም በተመሳሳይ ያገለግል ነበር።
➤ ከናምሩድ ክፋት በኋላ ሰናዖርና ወገኖቹ ከሰይጣን ተወዳጁ።
ከጥፋት ውኃ (ከኖኅ ዕረፍት) በኋላ በሥፍራው በአንድነት ይኖሩ ነበርና እርስ በርሳቸው "ኑ ሳንበተን ስማችን የሚጠራበትን ሕንጻ እንሥራ።
➤ በዚያውም አባቶቻችን በውኃ ያጠፋ እግዚአብሔርን እንውጋው።" ተባባሉ።
ቀጥለውም ሰማይ ጠቀስ ፎቅን ገነቡ። ከሕንጻው መርዘም የተነሳ በፀሐይ አብስለው በልተዋል ይባላል። ቀጥለውም ጦር እያነሱ ፈጣሪን ሊወጉ ወርውረዋል።
➤ መቼም የእነዚህን ሰዎች ክፋትና ቂልነት ስንሰማ ይገርመን ይሆናል። ግንኮ ዛሬ ሰለጠንኩ በሚለው ዓለም እየተሠራ ያለው ከዚህ የከፋ ነው። ቸርነቱ ቢጠብቀን እንጂ እንደ ክፋታችንስ ጠፊ ነበርን።
➤ ርኅሩኀን ሥላሴ ግን የሰናዖር ሰዎች የሠሩትን አይተው ማጥፋት ሲችሉ አላደረጉትም። የባሪያቸውን የኖኅን ቃል ኪዳን አስበዋልና። ይልቁኑ "ንዑ ንረድ ወንክአው ነገሮሙ ለከለዳውያን - ቋንቋቸውን እንደባልቀው።" አሉ እንጂ።
➤ ከለዳውያን ልሳናቸው ተደበላልቆ ፸፩ ቋንቋዎች ተፈጠሩ። እነርሱም ስምምነት አጥተው ተበተኑ። ሥላሴም ያን ሕንጻ በነፋስ ትቢያ እንዲሆን በተኑት። ስለዚህም እስከ ዛሬ ሥፍራው "ባቢሎን (ዝሩት)" ሲባል ይኖራል።
➤ ዳግመኛ በዚህች ዕለት አድያም ሰገድ ኢያሱ በኢትዮጵያ በነገሡ በአሥረኛው ዓመት (በ፲፮፻፹፬ ዓ/ም) በጐንደር ከተማ ንግሥተ አድባራት ቅድስት ሥላሴ ቤተ ክርስቲያን ተሰርታ ተጠናቃለች።
➤ ጥር ፯ ቀንም ሊቁ ክፍለ ዮሐንስን ጨምሮ በርካታ ምዕመናን፣ ሠራዊት፣ መሳፍንትና ሊቃውንት ባሉበት ቅዳሴ ቤታቸው ተከብሯል። በዕለቱም ታላቅ ሐሴት ተደርጓል። ኢያሱ አድያም ሰገድ ኃያል፣ ደግ፣ ጥበበኛ፣ አስተዋይ፣ መናኝ ንጉሥ ነውና።
➤ ቤተ ሥላሴን አስጊጿታልና ከዚህ ቀን ጀምሮ ጥር ሥላሴ በድምቀት የሚከበር ሆኗል። ነገር ግን በተሠራች በአሥራ ስድስት ዓመቷ ደጉ ኢያሱ ከተገደለ በኋላ ቤተ ክርስቲያኑ በአደጋ ፈርሷል።
➤ ዛሬ የምናየው በ፲፯፻፰ ዓ/ም በልጁ በአፄ ዳዊት ሣልሳዊ የታነጸውን ነው።
✥••┈┈••●◉ ✞ ◉●••┈┈••✥
✞✞✞"በበደላችን ሙታን በነበርን ግዜ ከልጁ ከእየሱስ ክርስቶስ ጋር ህይወትን የሰጠን አባታችን ቅዱስ እግዚያብሄር አብ በተገባን ሞት እርግማን ፋንታ ህይወትን የሸለመን አባታችን ቅዱስ እግዚያብሄር ወልድ አፅናኛችን ቅዱስ የእግዚያብሄር መንፈስ አባታችን እግዚያብሄር መንፈስ ቅዱስ ስም ይክበር ይመስገን ሰላሙን ፍቅሩን አድለን።"✞✞✞
✞✞✞✞✞ አሜን ✞✞✞✞✞
✥••┈┈••●◉ ✞ ◉●••┈┈••✥
📖 ወስብሐት ለእግዚአብሔር 📖
📖 ወለወላዴቱ ድንግል 📖
📖 ወለመስቀሉ ክቡር 📖
📖✞✞✞✞✞📖
✞✞✞ ሃሳብ ➢
@gebrye_comment_bot
✞✞✞ ይቀላቀሉ ➣
@mahteben_albetsm
††† በስመ አብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ አሐዱ አምላክ አሜን ! †††
#ጥር ፮
#በዓለ_ግዝረት
➤ "በዓል" ማለት በቁሙ "ክብር፣ መታሰቢያ" እንደ ማለት ነው። የበዓላት ባለቤት ደግሞ ራሱ እግዚአብሔር ነው። በመጻሕፍተ ኦሪት እንደ ተቀመጠው ጌታ ምርጦቹን (ሕዝቡን) ስለ በዓላት አዝዟል።
➤ ከሰንበት ጀምሮ የፋሲካ፣ የእሸት፣ የዳስ.....ወዘተ. በዓላት በብሉይ ኪዳን ይከበሩ ነበር።
➤ በእርግጥ አሕዛብም ለጥፋታቸው በዓላትን ሲያከብሩ ኑረዋል። ዛሬም ቀጥለዋል። በዓላት በሐዲስ ኪዳንም ቀጥለዋል።
➤ የቅዱሳን ሐዋርያትና ሊቃውንትን ቀኖናዎች መሠረት አድርጋ ቤተ ክርስቲያን በዓላትን ታከብራለች።
እነዚህም ከጊዜ (ወቅት) አንጻር፦
#የሳምንት
#የወር_እና
#የዓመት በዓላት ተብለው ሲታወቁ ከተከባሪዎቹ አንጻር ደግሞ፦
#የጌታ
#የእመቤታችን_እና
#የቅዱሳን_ተብለው_ይከፈላሉ።
➤ ጌታ "በዓላትን አክብሩ።" ያለን ሥራ እንድንፈታ ሳይሆን ለአምልኮው እንድንተጋና የጽድቅ ተግባራትን እንድንከውን ነው።
➤ ስለዚህም በበዓላት መልካም ይሠራል እንጂ ተተኝቶ አይዋልም። የጌታችን በዓላቱ አሥራ ስምንት ሲሆኑ ፱ ዐበይት፣ ፱ ደግሞ ንዑሳን ተብለው ይታወቃሉ። ሁሉም ለእኛ የድኅንት ሥራ የተፈጸመባቸው ናቸው።
➤ የጌታ ዐበይት በዓላቱ፦
፩. #ጽንሰቱ (ትስብእቱ)
፪. #ልደቱ
፫. #ጥምቀቱ
፬. #ዑደተ_ሆሳዕናው
፭. #ስቅለቱ
፮. #ትንሣኤው
፯. #ዕርገቱ
፰. #በዓለ_ጰራቅሊጦስ_እና
፱. #በዓለ_ደብረ_ታቦር_ናቸው።
➤ ንዑሳን በዓላቱ ደግሞ፦
፩. #ስብከት
፪. #ብርሃን
፫. #ኖላዊ_ሔር
፬. #ጌና
፭. #ግዝረት
፮. #በዓቱ (በዓለ ስምዖን)
፯. #ቃና_ዘገሊላ
፰. #ደብረ_ዘይት_እና
፱. #በዓለ_መስቀል_ተብለው_ይታወቃሉ
➤ ከእነዚህም አንዱ በዓለ #ግዝረት ሁሌም በየዓመቱ ጥር ፮ ቀን ይከበራል። መድኃኒታችን ለእኛ ሲል በተዋሐደው ሥጋ ማርያም ሕግን ሁሉ ፈጽሟል። ራሱ 'ሠራዔ ሕግ' እንደ ሆነው ሁሉ 'ፈጻሜ ሕግ'ም ተብሏል።
➤ ለአብርሃም ባዘዘው
“እግዚአብሔርም አብርሃምን አለው፦ አንተ ደግሞ ቃል ኪዳኔን ትጠብቃለህ፥ አንተ ከአንተም በኋላ ዘርህ በትውልዳቸው።”
— ዘፍጥረት 17፥9
መሠረትም በተወለደ በ፰ ቀኑ ተገዝሯል። ስሙንም ኢየሱስ (መድኃኒት) ብለውታል።
“ሊገርዙት ስምንት ቀን በሞላ ጊዜ፥ በማኅፀን ሳይረገዝ በመልአኩ እንደ ተባለ፥ ስሙ ኢየሱስ ተብሎ ተጠራ።”
— ሉቃስ. ፪፥፳፩
➤ ነገር ግን የተገዘረው እንደ ፍጡር በምላጭ (በስለት) ሳይሆን በኪነ ጥበቡ ነው። "ማርያም ግዝር" እንዲሉ አበው። ልደቱ እንደማይመረመር ሁሉ ግዝረቱም አይመረመርም።
✥••┈┈••●◉ ✞ ◉●••┈┈••✥
✞✞✞"ለእኛ ሲል ሁሉን የሆነ መድኃኒታችን ክርስቶስ ለፍቅሩና ለክብሩ ያብቃን። ከበረከተ በዓለ ግዝረቱም አይለየን።"✞✞✞
✞✞✞✞✞ አሜን ✞✞✞✞✞
✥••┈┈••●◉ ✞ ◉●••┈┈••✥
📖 ወስብሐት ለእግዚአብሔር 📖
📖 ወለወላዴቱ ድንግል 📖
📖 ወለመስቀሉ ክቡር 📖
📖✞✞✞✞✞📖
✞✞✞ ሃሳብ ➢
@gebrye_comment_bot
✞✞✞ ይቀላቀሉ ➣
@mahteben_albetsm
††† በስመ አብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ አሐዱ አምላክ አሜን ! †††
#እንኳን_ለጌታችን_መድሀኒታችን_እየሱስ_ክርስቶስ_የልደት_በአል_በሰላም_አደረሳቹ
#ታህሳስ ፳፱
#ክፍል ፪
#ልደተ_ክርስቶስ
➢ ሄሮድስ ግን ዙፋኑን ሊወስድ ይችላል ብሎ በመፍራት ጌታ ኢየሱስን ለመግደል ፈለጎ እንጂ ሊያመልከው አልነበረም፡፡
➢ ሰብአ ሰገልም በኮከብ ተመርተው ቅድስት ማርያምን፣ ዮሴፍን እና ጌታ ኢየሱስን ወደ ነበሩበት በረት በደረሱ ጊዜ በጉልበታቸው ተንበረከኩ፤ አምላክነቱን በመረዳትም ለሕፃኑ ሰገዱለት፤ ዕጣን፣ ወርቅና ቀርቤንም የእጅ መንሻ አድርገው አቀረቡለት፡፡
➢ ሆኖም ግን ወደ ሄሮድስ አልተመለሱም፡፡ ሄሮድስ ኢየሱስን ሊጎዳ እንደሚፈልግ የሚያስጠነቅቅ ሕልም አስቀድመው በራእይ አይተው ነበርና፡፡ ይልቁንም በተለየ መንገድ ወደ ትውልድ ሀገራቸው ተመለሱ፡፡
➢ ከዚያን ጊዜ ጀምሮ የጌታችን መድኃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስን ልደት በመላው የኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ሃይማኖት ተከታዮች ዘንድ በድምቀት ይከበራል፤ እርሱ ለእኛ መድኅን ነውና፡፡
➢ የጌታችን መድኃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ልደት በሰውና በእግዚአብሔር መካከል እርቅ የወረደበት፣ ከኃጢአት ባርነት ነጻ የወጣንበት፣ ድንቅ የተዋሕዶ ምሥጢር የተፈጸመበት ነው፡፡
➢ ነቢያት ስለክርስቶስ የተናገሩት ሁሉ ተፈጽመ፤ ስለ ጌታችን መወለድ ቅዱስ ዳዊትም ‹‹ እነሆ በኤፍራታ ሰማነው በዱር ውስጥም አገኘነው›› ብሎ ተናግሯል፡፡
➔መዝ. ፴፩፥፮
➢ በጌታችን ኢየሱስ ልደት መላእክትና ሰዎች በአንድነት "ስብሐት ለእግዚአብሔር" እያሉ እግዚአብሔርን አመስግነዋል፡፡ በኃጢአታችን ሳቢያ አጥተነው የነበረውን አንድነት የመላእክትና የሰው ልጆች አንድነት ከብዙ ዘመን በኋላ በጌታችን ልደት እንደገና አገኘነው፡፡
➢ ሊቁ ቅዱስ ዮሐንስ አፈወርቅም እግዚአብሔር አምላክ የሰውን ዘር በሙሉ ያዳነበትን ድንቅ ሥራ ሲገልጽ እንዲህ ብሏል፤ "ምን እላለሁ? ምንስ እናገራለሁ? ከዘመን አስቀድሞ የነበረው እርሱ ሕፃን ሆኗልና፡፡ እኔ ፈጽሜ አደንቃለሁ፡፡ ከሰማየ ሰማያት በላይ የሚሆን፣ በዘለዓለማዊ ዙፋን የሚኖር እርሱ በበረት ተጣለ፡፡ ከሥጋዌ አስቀድሞ አይዳሰስ የነበረ አንዱ እርሱ በምድራውያን እጅ ተዳሰሰ፡፡ ኀጢአትን የሚያስተሰርይ እርሱን በጨርቅ ጠቀለሉት፤ ይህን ወዷልና፤"
➔ሃይማኖተ አበው ዘዮሐንስ አፈወርቅ፣ ፷፮፥፲፯
➢ እግዚአብሔር ወልድ ከእመቤታችን ቅድስት ድንግል ማርያም ከሥጋዋ ሥጋ፣ ከነፍሷ ነፍስ ነሥቶ ሰው ሆኖ ለእኛ የድኅነት መንገድ ሆነ፡፡ ጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ለአዳም የገባለትን ቃል ኪዳን ለመፈጸም ከሰማየ ሰማያት ወርዶ፣ ከቅድስት ድንግል ማርያም ተወልዶ፣ ሰው ሆኖ፣ በአጭር ቁመት በጠባብ ደረት ተወስኖ፣ በመስቀል ተሰቅሎ፣ ድኅነትን ለሰው ልጆች ሰጥቶ፣ በመስቀሉ ተጣልተው የነበሩ ሰባቱን መስተፃርራን (ሰውና እግዚአብሔርን መላእክትና ሰውን፣ ነፍስና ሥጋን፣ ሕዝብና አሕዛብን) አስታርቋል፡፡
➢ በጌታችን ልደት ምክንያት እኛም ዳግም ተወልደን ከሞት ወደ ሕይወት ተሸጋገርን፤ ከጨለማ ወጥተን ብርሃን አገኘን፤ የእርሱ መወለድ የእኛም የክርስቲያኖች ሁሉ ልደት ነውና በዓሉን በክርስቲያናዊ ምግባር ታንጸንና በሥርዓተ ቤተ ክርስቲያን ልናከብር ይገባል፡፡
✞✞✞"እግዚአብሔር አምላክ በዓሉን የሰላም፣ የፍቅር እና የአንድነት ያድርግል።"✞✞✞
✞✞✞✞✞ አሜን ✞✞✞✞✞
✥••┈┈••●◉ ✞ ◉●••┈┈••✥
📖 ወስብሐት ለእግዚአብሔር 📖
📖 ወለወላዴቱ ድንግል 📖
📖 ወለመስቀሉ ክቡር 📖
📖✞✞✞✞✞📖
✞✞✞ ሃሳብ ➢
@gebrye_comment_bot
|❀:✧๑ ✞✞✞✞✞✞✞ ๑✧❀|:
✞✞✞ ይቀላቀሉ ➣
@mahteben_albetsm
††† በስመ አብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ አሐዱ አምላክ አሜን ! †††
#ታህሳስ ፳፬
#ቅድስት_አስቴር
#ይህቺ_ቅድስት_እናት፦
➤ እስራኤል በባቢሎን ምርኮ ሳሉ የነበረች፣አባቷ አሚናዳብ ባለ መኖሩ በአጐቷ መርዶክዮስ እጅ ያደገች።
➤ እጅግ ውብ በመሆኗ የአርጤክስስ ሚስት (ንግሥት) ለመሆን የበቃች፣
ራሷን መስዋዕት አድርጋ ወገኖቿን አይሁድን ከሞት ያተረፈች።
➤ ለመርዶክዮስ ክብርን ለአማሌቃዊው ሐማ ደግሞ ስቅላትን ያስፈረደች እና እግዚአብሔር ሞገስ የሆናት እናት ናት።
ዛሬ ታህሳስ ፳፬ ዕረፍቷ ነው።
✥••┈┈••●◉ ✞ ◉●••┈┈••✥
➤ ታኅሣሥ ፳፬ ቀን የሚከበሩ ዓመታዊ የቅዱሳን በዓላት
፩.ቅዱስ አቡነ ተክለ ሃይማኖት
፪.ቅዱሳን ጸጋ ዘአብና እግዚእ ኃረያ
፫.ቅዱስ አግናጥዮስ ሐዋርያ
፬.ቅድስት አስቴር
፭.አባ ፊሎንጐስ ሊቀ ጳጳሳት
፮.አባ ጳውሊ ጻድቅ
፯.ጻድቃን ቅዱሳን ዘከዲህ
➤ ወርኀዊ በዓላት
፩.ቅዱስ ቶማስ ዘመርዐስ
፪.አቡነ ዘዮሐንስ ጻድቅ ዘክብራን
፫.ቅዱስ አጋቢጦስ (ጻድቅ ኤጲስቆጶስ)
፬.ቅዱስ አብላርዮስ ታላቁ
፭.ሃያ አራቱ ካህናተ ሰማይ (ሱራፌል)
፮.ቅዱስ አባ ሙሴ ጸሊም (ኢትዮጵያዊ)
፯.ቅድስት ክርስቶስ ሠምራ
✥••┈┈••●◉ ✞ ◉●••┈┈••✥
"ንግሥቲቱም አስቴር መልሳ፦ 'ንጉሥ ሆይ! በአንተ ዘንድ ሞገስን አግኝቼ እንደ ሆነ ንጉሡንም ደስ ቢያሰኘው ሕይወቴ በልመናዬ ሕዝቤም በመሻቴ ይሰጠኝ። እኔና ሕዝቤ ለመጥፋትና ለመገደል ለመደምሰስም ተሸጠናልና።' "
አስቴር ፯፥፫-፬
✥••┈┈••●◉ ✞ ◉●••┈┈••✥
✞✞✞"አምላከ ቅዱሳን ወዳጆቹን ባጸናበት ቅዱስ መንፈሱ እኛንም ያጽናን። ከበረከታቸውም ይክፈለን።"✞✞✞
✞✞✞✞✞ አሜን ✞✞✞✞✞
✥••┈┈••●◉ ✞ ◉●••┈┈••✥
📖 ወስብሐት ለእግዚአብሔር 📖
📖 ወለወላዴቱ ድንግል 📖
📖 ወለመስቀሉ ክቡር 📖
📖✞✞✞✞✞📖
✞✞✞ ሃሳብ ➢
@gebrye_comment_bot
|❀:✧๑ ✞✞✞✞✞✞✞ ๑✧❀|:
✞✞✞ ይቀላቀሉ ➣
@mahteben_albetsm
††† በስመ አብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ አሐዱ አምላክ አሜን ! †††
#ታህሳስ ፳፫
#ክፍል ፪
#ቅዱስ_ዳዊት_ልበ_አምላክ
➤ አያይዞም የምሥጢረ ሥጋዌን ነገር ቢገልጥለት "ናሁ ሰማዕናሁ በኤፍራታ - እነሆ በኤፍራታ ሰማነው።" ሲል ተናግሯል።
መዝ. ፻፴፩፥፮
➤ የኪዳኑ ጽላት (ጽዮን) ከአቢዳራ ቤት ስትመጣ ከዙፋኑ ወርዶ ከተራው ሕዝብ ጋርም ተቀላቅሎ በበገናና በመሰንቆ ተጫወተ።
➤ ስለ ፈጣሪው ክብሩን ተወ። ከዳን እስከ ቤርሳቤህ የሚገዛ ኃያል ንጉሥ ነበርና። በጽዮን ፊት እየወደቀ እየተነሳ፣ እየታጠቀ እየፈታ ሲዘምርም ሚስቱ ሜልኮል ናቀችው። እግዚአብሔር ግን ከፍ ከፍ አደረገው።
፪ሳሙ. ፮፥፲፮
➤ እግዚአብሔር ስለ ዳዊት ሲል ኢየሩሳሌምን ብዙ ጊዜ ታድጓል። ሰሎሞንና ሕዝቅያስን (ነገሥታቱን) ይቅር ያላቸው ስለ ባለሟሉ ስለ ዳዊት ነው።
የሐዲስ ኪዳን የመጀመሪያዋ ቃል "የዳዊት ልጅ....." የምትል ናት።
“የዳዊት ልጅ የአብርሃም ልጅ የኢየሱስ ክርስቶስ ትውልድ መጽሐፍ።”
— ማቴዎስ. ፩፥፩
➤ ጌታችን "ወልደ ዳዊት" መባልን ወዷልና። እንዲያውም ራሱ "እኔ የእሴይ ሥርና የዳዊት ዘር ነኝ።" ሲል ተናግሯል።
ራእይ ፳፪፥፲፮
➤ ነቢየ ጽድቅ ልበ አምላክ ቅዱስ ዳዊት እስራኤልን ለ፵ ዓመታት መርቶ አረጀ። "ምነው ያ ኃያል የእግዚአብሔር ሰው ቶሎ አረጀ?" ቢሉ ከገድሉ ጽናት ሰውነቱ ተቀጥቅጦ ነበርና።
➤ በዚያውም ላይ አንድ ቀን ስለ ሕዝበ እስራኤል ቤዛ ይሆናቸው ዘንድ በቀሳፊ መልአክ ፊት ቆሞ ነበርና (ዜና. ፳፩፥፲፮) ሰውነቱ ደከመ።
➤ በዚህ ጊዜም ልጁን ሰሎሞንን አንግሦ በ፸ ዓመቱ ከክርስቶስ ልደት ሺህ ዓመታት በፊት ዐርፏል።
➤ በራእየ ጐርጐርዮስ እንደ ተጻፈው ቅዱስ ዳዊትን በሰማይ ፺፱ ነገደ መላእክት ከበውት ያመሰግናል። ከእርሱ ዝማሬ ግርማ የተነሳ የሰማያት ግዘፋቸው ይናወጻል።
➤ በገድለ አቡነ ኪሮስ እንደ ተጻፈው ደግሞ ቅዱሳን ነፍሳቸው ከሥጋቸው የምትለየው በዳዊት በገና ጣዕመ ዝማሬ ነው።
➤ በነገረ ማርያም ትምህርት ደግሞ የቅዱስ ዳዊት ቤቱ ከልዑል አምላክ መንበር ሥር ነው። እንግዲህ ምን እላለሁ! ስለ ቅዱስ ዳዊት ከዚህም በላይ መጻሕፍት ብዙ ይላሉ። ክብሩ ታላቅ ነውና። በእውነት፣ በእውነት፣ በእውነት ያለ ሐሰት ለዳዊት ክብርና ምስጋና ይገባል!።
✥••┈┈••●◉ ✞ ◉●••┈┈••✥
➤ ታኅሣሥ ፳፫ ቀን የሚከበሩ ዓመታዊ የቅዱሳን በዓላት
፩.ቅዱስ ዳዊት ልበ አምላክ
፪.አባ ጢሞቴዎስ ገዳማዊ
፫.አባ ሳሙኤል ጻድቅ
፬.አባ ስምዖን ጻድቅ
፭.አባ ገብርኤል ጻድቅ
፮.አባ ይስሐቅ ጻድቅ
➤ ወርኀዊ በዓላት
፩.ቅዱስ ጊዮርጊስ ሊቀ ሰማዕታት
፪.ነቢየ ጽድቅ ቅዱስ ሰሎሞን (ንጉሠ እሥራኤል)
፫.ቅዱስ ዳንኤል ነቢይ
✥••┈┈••●◉ ✞ ◉●••┈┈••✥
"ከሕዝቤም የተመረጠውን ከፍ ከፍ አደረግሁ።ባሪያዬን ዳዊትን አገኘሁት። ቅዱስ ዘይትም ቀባሁት።እጄም ትረዳዋለች። ክንዴም ታጸናዋለች። ጠላት በእርሱ ላይ አይጠቀምም። የዓመጻ ልጅም መከራ አይጨምርበትም።
ጠላቶቹን ከፊቱ አጠፋለሁ የሚጠሉትንም አዋርዳቸዋለሁ።"
መዝሙር ፹፰፥፲፱-፳፫
✥••┈┈••●◉ ✞ ◉●••┈┈••✥
✞✞✞"አምላከ ዳዊት ስለ ከበረው ቃል ኪዳኑ ይማረን። ከንጹሕ አምልኮው ይክፈለን። በዝቶ ከተረፈ በረከቱም አይለየን።"✞✞✞
✞✞✞✞✞ አሜን ✞✞✞✞✞
✥••┈┈••●◉ ✞ ◉●••┈┈••✥
📖 ወስብሐት ለእግዚአብሔር 📖
📖 ወለወላዴቱ ድንግል 📖
📖 ወለመስቀሉ ክቡር 📖
📖✞✞✞✞✞📖
✞✞✞ ሃሳብ ➢
@gebrye_comment_bot
|❀:✧๑ ✞✞✞✞✞✞✞ ๑✧❀|:
✞✞✞ ይቀላቀሉ ➣
@mahteben_albetsm
††† በስመ አብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ አሐዱ አምላክ አሜን ! †††
#ታህሳስ ፳፪
#ቅዱስ_ደቅስዮስ
➤ ይህ ታላቅ የቤተ ክርስቲያን ሊቅ በዘመነ ጻድቃን አካባቢ እንደ ነበረ ይታመናል። ከምናኔ ሕይወቱ ባሻገር በመንፈስ ቅዱስ ምርጫ የጥልጥልያ ሃገር ጳጳስም ነበር። ይህ ቅዱስ ሰው በእውነቱ ያስቀናል።
➤ እመቤታችንን ሲወዳት መንጋትና መምሸቱ እንኳ አይታወቀውም ነበር። ፍቅሯ በደም ሥሮቹ ገብቶ በደስታ ያቃጥለው ነበርና ዘወትር እያመሰገናት አልጠግብ አለ። የሚያስደስትበትን ነገር ሲያስብ ደግሞ የተአምሯ ነገር ትዝ አለው።
➤ ከዚያ በፊት የእመቤታችን ተአምሯ በየቦታው ይነገራል፣ ይጻፋል፣ ይሰበካል። ግን በአንድ ጥራዝ አልተያዘም ነበርና በሱባኤ፣ በፈጣሪው እርዳታ፣ በፍጹም ድካም የእመ ብርሃንን ተአምራት ሰብስቦ በአንድ ጠረዘውና ለአገልግሎት ቀረበ።
➤ እርሷን ከመውደዱ የተነሳ ይህንን አድርጓልና እመ ብርሃን ወደ እርሱ ወረደች። "ወዳጄ ደቅስዮስ ደስ አሰኘኸኝ።" አለችው። መጽሐፉንም ተቀብላው ባረከችው። "አመሰግንሃለሁ" ብላውም ተሰወረችው።
➤ በዚህ ጊዜ ቅዱሱ ሐሴትን አደረገ። (እመቤታችን ማየት እንዴት ያለ ሞገስ ይሆን!)
➤ ቅዱስ ደቅስዮስ ግን ፍቅሯ እንደ እሳት ልቡን አቃጠለው። አሁንም ደስ ሊያሰኛት ምክንያትን ይሻ ነበር።
እመቤታችን ጌታን የጸነሰችበት በዓል (መጋቢት ፳፱) ሁሌም ዐቢይ ጾም ላይ እየዋለ ለማክበር አይመችም ነበርና ቅዱሱ ታኅሣሥ ፳፪ ቀን ሊያከብረው ወሰነ።
➤ በሃገሩ ያሉ ክርስቲያኖችን ጠርቶ ታላቅ በዓልን ለድንግል አከበረ።
ሕዝቡም ጸጋ በዝቶላቸው ስለ እመቤታችን ታላቅ ሐሴትን አደረጉ።
➤ በዚያች ሌሊትም እመ ብርሃን በሞገስ ወረደች። "ወዳጄ ደቅስዮስ! ዛሬም ፍጹም ደስ አሰኘኸኝ! እኔም ስለ ክብርህ ይህንን አመጣሁልህ።" ብላ ሰማያዊ ልብስና ዙፋን ሰጠችው።
➤ ማንም እንዳይቀመጥበት ነግራው ባርካው ዐረገች። ከዚህች ዕለት በኋላ ቅዱስ ደቅስዮስ ፈጣሪውንና ድንግል እናቱን ሲያገለግል፣ ተአምሯን ሲሰበስብ፣ ምዕመናንን ሲመራ ኑሮ በዚህች ዕለት ታህሳስ ፳፪ ዐርፏል።
➤ ከእርሱ በኋላ የተሾመው ጳጳስም በድፍረት በእርሱ ዙፋን ላይ በመቀመጡ መልአክ ቀስፎ ገሎታል። የእመቤታችንን ተአምር መስማትና ማንበብ ያለውን ዋጋ የሚያውቅ ጠላት ሰይጣን ግን ዛሬም ድረስ ባሳታቸው ሰዎች አድሮ ተአምሯን ይቃወማል።
➤ እኛ ግን ለእመቤታችን እንሰግዳለን! ተአምሯንም እንሰማለን! ጥቅማችንን እናውቃለንና!
#ለመረጃ_ያህልም፦
➤ የእመቤታችንን ተአምር የሰበሰበ (ቅዱስ ደቅስዮስ)
➢ የተአምሯን ሥርዓት ያዘጋጁ (ቅዱሳን አበው ማቴዎስ፣ ማርቆስና አብርሃም ሶርያዊ)
➢ እሰግድ ለኪን የደረሰው (ቅዱስ ዮሐንስ አፈ ወርቅ)
➢ የተአምሯን ሃሌታ (ቅዱስ ያሬድ)
➢የዘወትሩን መቅድም (ቅዱሳን ሊቃውንት) ናቸው።
✥••┈┈••●◉ ✞ ◉●••┈┈••✥
✞✞✞_"የታላቁ አባታችን ቅዱስ ደቅስዮስ ረድኤት በረከት ለዘላለም ይደርብን የእመቤታችን ቅድስት ድንግል ማርያም ልመናዋ ክብሯ በእውነት ለዘላለሙ ይደርብን_!።"✞✞✞
✞✞✞✞✞ አሜን ✞✞✞✞✞
✥••┈┈••●◉ ✞ ◉●••┈┈••✥
📖 ወስብሐት ለእግዚአብሔር 📖
📖 ወለወላዴቱ ድንግል 📖
📖 ወለመስቀሉ ክቡር 📖
📖✞✞✞✞✞📖
✞✞✞ ሃሳብ ➢
@gebrye\_comment\_bot
|❀:✧๑ ✞✞✞✞✞✞✞ ๑✧❀|:
✞✞✞ ይቀላቀሉ ➣
@mahteben\_albetsm
††† በስመ አብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ አሐዱ አምላክ አሜን ! †††
#ታህሳስ ፳፩
#አባ_ይስሐቅ_ጻድቅ
➤ ይህ ቅዱስ በመካከለኛው ዘመን በምድረ ግብጽ የነበረ ገዳማዊ ነው። መንኖ ለብዙ ዘመናት በገዳም ሲኖር ምኞቱ አንዲት ብቻ ነበረች።
➤ እመቤታችንን በአካል መመልከትን ይፈልግ ነበር። የገዳሙ ጠባቂ በመሆኑ መነኮሳት ሲተኙ መቅደሱን ከፍቶ በድንግል ማርያም ሥዕል ፊት ይጸልይ፣ ይሰግድ፣ ያነባ ነበር።
➤ እንዲህ ለ፯ ዓመታት ስለ ተጋ ድንግል እመ ብርሃን ልመናውን ሰማች።
በዚህ ዕለትም ከፀሐይ ፯ እጅ ደምቃ ወደ እርሱ መጣች። ደንግጦ ሲወድቅ አነሳችው።
➤ "ከ፫ ቀናት በኋላ እመለሳለሁ።" ብላም ተሠወረችው። በ፳፫ ቀንም ዐረፈ።
"በዛቲ ዕለት ሶበ ጸለየ ጥቡዐ
ለይስሐቅ አስተርዓየቶ እም አይቆናሃ ወጺአ እምጸዳለ መብረቅ ጥቀ እንዘ ትጸድል ስብአ።" እንዳለ ደራሲ።
✥••┈┈••●◉ ✞ ◉●••┈┈••✥
➤ ታኅሣሥ ፳፩ ቀን የሚከበሩ ዓመታዊ የቅዱሳን በዓላት
፩.ኖላዊ ሔር
፪.ቅዱስ በርናባስ ሐዋርያ
፫.አባ ይስሐቅ ጻድቅ
➤ ወርኀዊ በዓላት
፩.ቅድስት ድንግል እግዝእትነ ማርያም
፪.አበው ጎርጎርዮሳት
፫.አቡነ ምዕመነ ድንግል
፬.አቡነ አምደ ሥላሴ
፭.አባ አሮን ሶርያዊ
፮.አባ መርትያኖስ ጻድቅ
✥••┈┈••●◉ ✞ ◉●••┈┈••✥
✞✞✞"አምላከ ቅዱሳን ከጻድቁ አባ ይስሐቅ ረድኤት በረከት ይደርብን።"✞✞✞
✞✞✞✞✞ አሜን ✞✞✞✞✞
✥••┈┈••●◉ ✞ ◉●••┈┈••✥
📖 ወስብሐት ለእግዚአብሔር 📖
📖 ወለወላዴቱ ድንግል 📖
📖 ወለመስቀሉ ክቡር 📖
📖✞✞✞✞✞📖
✞✞✞ ሃሳብ ➢
@gebrye_comment_bot
|❀:✧๑ ✞✞✞✞✞✞✞ ๑✧❀|:
✞✞✞ ይቀላቀሉ ➣
@mahteben_albetsm
✞✞#መንበረ_መንግስት_ግቢ_ቅዱስ_ገብርኤል_ገዳም✞✞
✥••┈┈••●◉ ✞ ◉●••┈┈••✥
#እንኳን_ለመላኩ_ቅዱስ_ገብርኤል_አመታዊ_በዓል_በሰላም_አደረሳችሁ_አደረሰን።
✥••┈┈••●◉ ✞ ◉●••┈┈••✥
✞✞✞ "የመልዓኩ ቅዱስ ገብርኤል ጸጋ እና ምልጃ እንዲሁም ጥበቃ አይለየን ለሀገራችን ሰላምን ምህረትን ያውርድልን በሰላም ያውለን።"✞✞✞
✞✞✞✞✞ አሜን ✞✞✞✞✞
✞✞✞ ሃሳብ 👇
@gebrye_comment_bot
✞✞✞ ይቀላቀሉ 👇
@mahteben_albetsm
††† በስመ አብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ አሐዱ አምላክ አሜን ! †††
#ታህሳስ ፲፰
#አቡነ_ሰላማ_ከሣቴ_ብርሃን
➤ ቅዱሱ በትውልዳቸው ግሪካዊ ቢሆኑም ሶርያ አካባቢ እንዳደጉ ይታመናል። በቀደመ ስማቸው ፍሬምናጦስ የሚባሉት አቡነ ሰላማ ወደ ኢትዮጵያ የመጡት በአደጋ ምክንያት ቢመስልም ውስጡ ግን ፈቃደ እግዚአብሔር ነበረበት።
➤ በድንበር ጠባቂዎች ከባልንጀራቸው ኤዴስዮስ ጋር ተይዘው ወደ አክሱም የመጡት በንጉሥ ታዜር (አይዛና) እና በሚስቱ ሶፍያ (አሕየዋ) ዘመን ነው። ጊዜው በውል ባይታወቅም በአራተኛው መቶ ክፍለ ዘመን ነው።
➤ ፍሬምናጦስ ምንም የመጡበት ዓላማ ስብከተ ወንጌል ባይሆንም በአክሱም ቤተ መንግሥት አካባቢ ይሰብኩ ነበር። ያን ጊዜ በጃንደረባው ቅዱስ ባኮስ የተቀጣጠለው የክርስትና ችቦ ውስጥ ውስጡን በሃገሪቱ ነበረና ፍሬምናጦስ አልተቸገሩም። በተለይ ኢዛናና ሳይዛናን ከልጅነት ስላስተማሯቸው ነገሮች የተሳኩ ሆኑ።
➤ ንጉሥ ታዜር እንደ ሞተ ሁለቱ ሕፃናት በመንበሩ ተቀመጡ። ፍሬምናጦስንም ወደ ግብጽ ጳጳስና ጥምቀት ከመጻሕፍት ጋር እንዲያመጣላቸው ላኩ።
➤ ሐዋርያዊ ቅዱስ አትናቴዎስም ፍሬምናጦስን "ሰላማ" ብሎ ሰይሞ በጵጵስና፣ በንዋየ ቅድሳትና በመጻሕፍት ሸልሞ መለሳቸው።
➤ አቡነ ሰላማ ወደ ኢትዮጵያ እንደተመለሱ ከነገሥታቱ ጀምረው ለሕዝቡ ጥምቀትን አደሉ። ኢዛናና ሳይዛናም አብርሃ እና አጽብሃ ተብለው ስማቸው ተደነገለ።
➤ ከዚያ በኋላ ድንቅ በሚሆን አገልግሎት ነገሥታቱ፣ ጳጳሱ ሰላማና ሊቀ ካህናቱ እንበረም ለክርስትና መስፋፋት በጋራ ሠርተዋል።
#የአቡነ_ሰላማ_ትሩፋቶች፦
፩.ጵጵስናና ክህነትን ከእውነተኛ ምንጭ አምጥተዋል።
፪.ክርስትናና ጥምቀትን በሃገራችን አስፋፍተዋል።
፫.ቅዱሳት መጻሕፍትን ከውጭ ልሳኖች ተርጉመዋል።
፬.ገዳማዊ ሕይወትን ጀምረዋል።
፭.አብያተ ክርስቲያናትን አንጸዋል።
፮.ግዕዝ ቋንቋን አሻሽለዋል።
ሀ.ከግራ ወደ ቀኝ እንዲፃፍ
ለ.እርባታ እንዲኖረው
ሐ.ከ"አቦጊዳ" ወደ "ሀለሐመ" ቀይረዋል።
➤ ባላቸው ንጹሕ የቅድስና ሕይወት ለሕዝቡ ምሳሌ ሆነዋ። "ወበእንተዝ ተሰይመ ከሳቴ ብርሃን" እንዲል በነዚህ ምክንያቶች "ከሣቴ ብርሃን" (ብርሃንን የገለጠ) ሲባሉ ይኖራሉ።
➤ በመጨረሻም ከመልካሙ ገድል በኋላ በ፫፻፶፪ ዓ/ም ዐርፈው ተቀብረዋል። ቅዱሱ ለሃገራችን ጳጳስ ሆነው የተሾሙት በዚህች ዕለት ትህሳስ ፲፰ ነው።
✥••┈┈••●◉ ✞ ◉●••┈┈••✥
➤ ታኅሣሥ ፲፰ ቀን የሚከበሩ ዓመታዊ የቅዱሳን በዓላት
፩.ቅዱስ ቶማስ ሐዋርያ (ፍልሠቱ)
፪.ቅዱስ ቲቶ ሐዋርያ (ፍልሠቱ)
፫.አቡነ ሰላማ ከሣቴ ብርሃን
፬.ቅዱስ ፊልሞና ባሕታዊ
፭.ቅዱስ ኢርቅላ
➤ ወርኀዊ በዓላት
፩.አቡነ ኤዎስጣቴዎስ ረባን
፪.አቡነ አኖሬዎስ ዓቢይ
፫.ማር ያዕቆብ ግብጻዊ
፬.ቅዱስ ያዕቆብ ሐዋርያ (ከሰባ ሁለቱ)
፭.ቅዱስ ፊልጶስ ሐዋርያ (ከአሥራ ሁለቱ)
✥••┈┈••●◉ ✞ ◉●••┈┈••✥
✞✞✞"አምላከ አበው ከአባታችን አቡነ ሰላማ ከሣቴ ብርሃን ረድኤት በረከት ያሳትፈን መልካም እለተ ሰንበት።"✞✞✞
✞✞✞✞✞ አሜን ✞✞✞✞✞
✥••┈┈••●◉ ✞ ◉●••┈┈••✥
📖 ወስብሐት ለእግዚአብሔር 📖
📖 ወለወላዴቱ ድንግል 📖
📖 ወለመስቀሉ ክቡር 📖
📖✞✞✞✞✞📖
✞✞✞ ሃሳብ ➢
@gebrye_comment_bot
|❀:✧๑ ✞✞✞✞✞✞✞ ๑✧❀|:
✞✞✞ ይቀላቀሉ ➣
@mahteben_albetsm
††† በስመ አብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ አሐዱ አምላክ አሜን ! †††
#ታህሳስ ፲፯
#አባ_መቃርስ_ገዳማዊ
➤ "መቃርስ" የሚለው ቃል በዮናኒ ልሳን "ብፁዕ" እንደ ማለት ሲሆን የመነኮሳት አለቃ ቅዱስ መቃርስን ጨምሮ በርካታ ቅዱሳን በስሙ ተጠርተውበታል። በነገረ ቅዱሳን ታዋቂ ከሆኑት አንዱና ተጠቃሹ ዛሬ የምናከብረው አባት ሲሆን ብዙ ጊዜ "ዘይሴሰይ ቆቅሃ - ቆቅን የሚበላው" እየተባለ ይጠራል።
➤ የዚህንም ምክንያቱን እንመለከታለን። ቅዱስ መቃርስ በአምስተኛው መቶ ክፍለ ዘመን በምድረ ግብጽ የነበረ የዘመነ ጻድቃን ፍሬ ነው። ከእርሱ በፊት ታላቁ መቃርስ፣ መቃርስ ቀሲስና መቃርስ ዘቃው የተባሉ አባቶች ስለ ነበሩ እርሱን አራተኛው መቃርስ እያሉ መጥራት የተለመደ ነው።
➤ በወጣትነቱ ከዓለም ወጥቶ ገዳም ገባ። ቀጥሎም መነኮሰ። ግን ወሬን፣ ሐሜትንና ትዕቢትን ፈጽሞ ይጠላ ነበርና ከገዳሙ ወጥቶ ሰው ወደማይኖርበት በርሃ ሔደ።
➤ ግን በአካባቢው የሚበላ ነገር ከዛፍ ፍሬ ከሣር ዘርም እንኳ ምንም ነገርን ማግኘት አልቻለም። ጾሞ በራበው ጊዜም "ፍጥረትን የምትመግብ ጌታ ሆይ! ራቴን አብላኝ?" ሲል ጸለየ።
➤ እግዚአብሔርም አንዲት ቆቅን አምጥቶለት በላ። ከዚህ በኋላም ምግቡ ቆቅ ብቻ ሆነ። ማታ ማታ አንድ ቆቅ ይያዝለታል። እርሱም አመስግኖ እየበላ ዘመናት አለፉ።
➤ እግዚአብሔር የዚህ ገዳማዊ ዜና እንዲገለጥ ስለ ፈለገ አንድ የቁስጥንጥንያ መነኮስ ከሃገሩ ተነስቶ ወደ በርሃ ወረደ። መጠለያ በዓት ሲፈልግም አንድ አረጋዊ ባሕታዊ ቆቅ ሲያጠምድ ተመልክቶ ደነገጠ።
➤ "መነኮስ ሆኖ እንዴት ሥጋ ይበላል።" ሲልም ተናደደ። ነገሩን ለሊቀ ጳጳሳቱ ይነግር ዘንድም በመጣበት መንገድ እየቸኮለ ተመለሰ። የሃገሩን ፓትርያርክም "አባታችን አንድ ባሕታዊ እምነታችንን ሊያሰድብ እንዲህ አደረገኮ።" ቢለው ነገሩ እርግጥ ይሆን ዘንድ ፓትርያርኩ አንድ ሰው ጨምሮ ሁለቱን ላካቸው።
➤ በዚያች ቀንም ቅዱስ መቃርስ ለመጀመሪያ ጊዜ ሦስት ቆቆች ገቡለት:: "ጌታዬ! ሁለቱን ምን ላድርጋቸው?" ሲል መነኮሳቱ ወደ እርሱ ደረሱ። ደስ ብሎት ፈጣሪን እያመሰገነ ሠርቶ አቀረበላቸው።
➤ እነርሱ ግን ቅዱሱን ናቁት። "አንበላም" አሉት። አባ መቃርስም የተጠበሱትን ቆቆች እፍ እፍ እያለ ነፍስ ዘራባቸውና እንዲበሩ አደረገ። በዚህ የደነገጡት መነኮሳቱ ሰግደውለት እየተሯሯጡ ወደ ሃገራቸው ተመለሱ።
➤ ባሙበት አፋቸው "ታላቅ ሰው ተገኝቷል፤ በረከቱ አይለፋችሁ።" ሲሉ ሰበኩ። ይህ ሲሰማም ፓትርያርኩ ከነ ሕዝቡ፣ ንጉሡ ከነ ሠራዊቱ ሊባረኩ ወደ በርሃው ወረዱ። ግን ቅዱስ መልአክ ተሸክሞት ወደ ብሔረ ሕያዋን ሲያርግ ደረሱ።
➤ እየጮሁ "አባ በረከትህን? የድህነት ቃልህን?" አሉት። እርሱም "ይጹም አፉክሙ እምነገረ ውዴት ወሐሜት - አፋችሁ ከሐሜት ከነገር ሥራት ይጹም። ካህናት ትምህርት፣ መነኮሳት ትሕርምትን አታብዙ። ልቡናችሁ አይታበይ። ሰላም ለእናንተ ይሁን!" ብሏቸው ከዓይናቸው ተሰወረ። ወደ ብሔረ ሕያዋንም ገባ።
✥••┈┈••●◉ ✞ ◉●••┈┈••✥
✞✞✞"የአባታችን አባ መቃርስ ረድኤት በረከት ይደርብን"✞✞✞
✞✞✞✞✞ አሜን ✞✞✞✞✞
✥••┈┈••●◉ ✞ ◉●••┈┈••✥
📖 ወስብሐት ለእግዚአብሔር 📖
📖 ወለወላዴቱ ድንግል 📖
📖 ወለመስቀሉ ክቡር 📖
📖✞✞✞✞✞📖
✞✞✞ ሃሳብ ➢
@gebrye_comment_bot
|❀:✧๑ ✞✞✞✞✞✞✞ ๑✧❀|:
✞✞✞ ይቀላቀሉ ➣
@mahteben_albetsm
††† በስመ አብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ አሐዱ አምላክ አሜን ! †††
#ታህሳስ ፲፯
#ክፍል ፩
#ቅዱስ_ሉቃስ_ዘዓምድ
"ዘዓምድ" በሚል ስም ከሚታወቁ የቤተ ክርስቲያን አበው መካከል አራቱ ቅድሚያውን ይይዛሉ።
#እነዚህም፦
#ቅዱስ_ስምዖን_ዘዓምድ፣
#ቅዱስ_አጋቶን_ዘዓምድ፣
#ቅዱስ_ዳንኤል_ዘዓምድ_እና
#ቅዱስ_ሉቃስ_ዘዓምድ_ናቸው።
"ዘዓምድ" የሚለውን ቃል ምሥራቃውያን በልሳናቸው "THE STYLITE" ይሉታል። የእኛው ቃል ደግሞ ከግዕዝ የተወረሰ ነውና በቁሙ ቢተረጐም "የምሰሶው" የሚል ትርጉምን ይይዛል። ይህም በሁለት ምክንያቶች ነው።
➤ አንደኛው ቅዱሳኑ ተጋድሏቸውን የፈጸሙት ከረዥም ምሰሶ ላይ ወጥተው በመጸለይ ስለሆነ ነው። ሌላኛው ምክንያት ደግሞ እነዚህ አባቶች በዘመኑ ለነበሩ ምዕመናንና መነኮሳት አጽናኝ፣ አስተማሪ፣ መሪና ፈዋሽ በመሆናቸውና እንደ ምሰሶ ተተክለው ሳይነቃነቁ በመጸለያቸው ነው።
➤ ልክ ከዓለም ሃገራት ብዙ ስውራንን እና ቅዱሳን ነገሥታትን በመያዝ ሃገራችን ቀዳሚ እንደ ሆነችው ሁሉ ምሰሶ ላይ ወጥተው የሚጋደሉ ቅዱሳንም ሶርያውያንና ምሥራቃውያን ናቸው። በዚህ ዕለትም ቅድስት ቤተ ክርስቲያን የታላቁን ቅዱስ ሉቃስ ዘዓምድን በዓል ታከብራለችና ከዜና ሕይወቱ ለበረከት ጥቂት እንካፈል።
➤ ቅዱስ ሉቃስ ተወልዶ ያደገው በፋርስ (በአሁኗ ኢራን) ሲሆን ዘመኑም ዘመነ ጻድቃን (ከሦስተኛው እስከ ስድስተኛው መቶ ክፍለ ዘመን ድረስ) እንደ ሆነ ይታመናል። ዛሬን አያድርገውና በጊዜው በጣም ብዙ በዚያም ላይ ጽኑዕ የሆኑ ክርስቲያኖች በሃገሪቱ ነበሩ።
➤ በወቅቱ በየሥፍራው ዜና ቅዱሳን ሰፍቶ ነበርና ብዙዎቹ ወደ ምናኔ እየሔዱ ገዳማትን አጨናንቀው ነበር። መንፈሳዊ ቅንዓት የሚያቃጥላቸው ክርስቲያኖችም ብዙ ነበሩ።
➤ ቅዱስ ሉቃስ ከልጅነቱ መሠረቱ ክርስትና ነው። ልጅ ሳለም ሃይማኖቱን በሚገባ አውቋል። ወጣት በሆነ ጊዜ ሠርቶ መብላት ሃይማኖታዊ ግዴታም ነውና ሥራ ፍለጋ ወጣ።
➤ በጊዜው ደግሞ በቀላሉ የሚገኝ ሥራ የሠራዊት አባል ወይም በዘመኑ ልሳን "ወታደር" መሆን ነበርና ሒዶ ገባ። ውትድርና የኃጢአት ሥራ አይደለም። ሃገርን፣ ዳርን፣ ድንበርን እየጠበቁ ራስን መስዋእት ማድረግ ነውና።
➤ ነገር ግን አንዳንዶቻችን የማይገባ ሥራ ስንሠራበት ለእኛም ለወገንም የማይበጅ ድርጊት ስንፈጽም ይታያል። ለዚህ ደግሞ እግዚአብሔር በምድርም ሆነ በሰማይ ይፈርዳልና ሁላችንም በተሠማራንበት ሙያ ሁሉ እንደሚገባ ልንኖር ግድ ይለናል። የአባቶች ሕይወት እንዲህ ነበርና።
➤ ቅዱስ ሉቃስም ወታደር (ጭፍራ) ነው። ግን ደግሞ ክርስቲያን ነው። በሁለቱም ማንነቶቹ የሚጠበቁበትን እየተወጣ የወጣትነት ስሜቱን በፈጣሪው ኃይል እየገታ ራሱን ለእግዚአብሔር እያስገዛ ቀጠለ።
➤ እንደሚታወቀው ሰው በሥራው መጠን ክፍያው (ደሞዙ) እና ማዕረጉ (ሥልጣኑ) ከፍ እያለ መሔዱ አይቀርም። ምንም እንኳ ብዙ እንዲህ ዓይነት ተግባራት በዘመናችን ቀዝቃዞች ቢሆኑም። የሠራውን ትቶ ላልሠራው መሸለም በክርስትናው ዓለም ትልቅ ስህተት ነው።
➤ ምናልባትም ይሔው ገርሞት ይመስለኛል፦
"ሃገሬ ኢትዮጵያ ሞኝ ነሽ ተላላ፣
የሞተልሽ ቀርቶ የገደለሽ በላ።" ሲል የሃገራችን ሕዝብ የተቀኘው።
➤ ቅዱስ ሉቃስም እንደ ሥራው መጠን ከፍ እያለ ሒዶ የፋርስ ሠራዊት ሃቤ ምዕት (የመቶ አለቃ) ለመሆን በቃ።
➤ ቅዱስ ሉቃስ የጦር መሪነት ሥራውን እያከናወነ ጐን ለጐን ለፈጣሪው ይገዛ መጻሕፍትን ያነብ ነበር። በተለይ ዜና ቅዱሳን ዕለት ዕለት ይስበው ነበርና ልቡናው ወደ ፍቅረ ክርስቶስ ተመሰጠ። ይህችን ዓለም ትቷት ሊሔድም ተመኘ።
➤ በጐ ምኞትን የሚፈጽም ጌታም ልቡን አበርትቶለት ከዓለማዊ ንብረቱ አንድም ነገርን ሳያስከትል ሹመቱንም ትቶ በርሃ ገባ። በዚያም በረድዕ ሥርዓት የአባቶች ደቀ መዝሙር ሆነ። አዛዥነትን ትቶ ታዛዥ ተገልጋይነትን ትቶ አገልጋይ ሆነ።
➤ ትሕትናውንና ትጋቱን የተመለከቱ አበውም ወደ ምንኩስና ማዕረግ ከፍ አደረጉት። አሁንም ታጥቆ አገልግሎቱን ቀጠለ። እውቀቱን፣ ማስተዋሉንና ቅድስናውን ያዩ አባቶች በጐ እረኛ እንደሚሆን ስላወቁም ቅስናን ሾሙት።
➤ ከዚህ በኋላ ግን ቅዱስ ሉቃስ የተጋድሎውን ደረጃ ከፍ አደረገ። በመጀመሪያ ጾሙን ከአንድ ቀን ወደ ሦስት ቀን አሸጋገረ። ትንሽ ቆይቶ ግን ጾሙ ሰባት ቀን ሆነ። ምን ጊዜም እህልን የሚቀምሰው በዕለተ ሰንበት (እሑድ) ብቻ ሆነ።
➤ ሁልጊዜም በዕለተ ሰንበት ቅዳሴን ይቀድሳል። ለእርሱ ሥጋ ወደሙን ተቀብሎ ለሌሎቹ ያቀብላል። ከዚያም ወደ በዓቱ ሒዶ አንዲት ጳኩሲማን ይመገባል። "ጳኩሲማን" አባቶች በቀደመ ልሳን "የዳቦ ለከት" ይሉታል። በዘመኑ ልሳን "ትንሽ የዳቦ ቁራጭ" እንደ ማለት ነው።
➤ ከዚህ ጐንም ወገቡን በሰንሰለት ታጥቆ በፍጹም መንፈሱ ይጸልይና ይሰግድ ነበር። በዚህ ተጋድሎ ላይ ሳለም በታላቁ አባ አጋቶን ሕይወት መቅናትን ቀና። በአንደበት ከሚወጣ ኃጢአት ይጠበቅ ዘንድም ሙልሙል ድንጋይ አዘጋጅቶ ጐረሰው።
#ይቀጥላል......
✥••┈┈••●◉ ✞ ◉●••┈┈••✥
📖 ወስብሐት ለእግዚአብሔር 📖
📖 ወለወላዴቱ ድንግል 📖
📖 ወለመስቀሉ ክቡር 📖
📖✞✞✞✞✞📖
✞✞✞ ሃሳብ ➢
@gebrye_comment_bot
|❀:✧๑ ✞✞✞✞✞✞✞ ๑✧❀|:
✞✞✞ ይቀላቀሉ ➣
@mahteben_albetsm
††† በስመ አብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ አሐዱ አምላክ አሜን ! †††
"በላይ ያለውን አስቡ እንጂ በምድር ያለውን አይደለም!"
ቆላ.፫÷፪
➢ በላይ በሰማይ ያለውን እያሰቡ የሚኖሩ ሰዎች ዘወትር ነፍሳቸው በተስፋ ትለመልማለች።
➢ በምድር መከራ ቢበዛባቸው እንኳ በሰማይ የተዘጋጀላቸውን ደስታ እያሰቡ ይጽናናሉ።
➢ እዚህ ላይ የእስጢፋኖስን ታሪክ ማንሳቱ ለምንነጋገርበት ርዕሰ ጉዳይ ሳይጠቅመን አይቀርም። ቀዳሜ ሰማዕት እስጢፋኖስ ትንሽ ትልቁ ተነስቶ በድንጋይ ሲወግረው ምንም እንኳ መከራው ቢበዛበትም እርሱ ግን በላይ በሰማይ ያለውን ሰማያዊ ዋጋ እያሰበ ራሱን በእጅጉ ያጽናና ነበር።
“እነሆ፥ ሰማያት ተከፍተው የሰው ልጅም በእግዚአብሔር ቀኝ ቆሞ አያለሁ አለ።”
— ሐዋርያት ፯÷፶፮
➢ እኛም ልክ እንደ እስጢፋኖስ ሰማያዊ አስተሳሰብ ሲኖርህ ምድራውያን የሆኑ ሰዎች ያለ ምክንያት እየተነሱ ያሳድዱሀል። ነገር ግን በዚያን ጊዜ ተስፋህን ሁሉ አሳዳጆችህ ወደ ላይ ተንጠራርተው በማይደርሱበት በሰማይ ከፍታ ላይ ስለሰቀልከው እስከ ጥልቁ ድረስ ቢያሳድዱህም እንኳ በፍጹም ተስፋህን ማጨለም አይችሉም።
➢ ስለዚህ ሰማያዊው ንጉሥ ክርስቶስ ነፍስህን ከአሳዳጆችህ ነጥቆ በእቅፉ እንደሚቀበላት ስለምታምን የሚወግሩህን ሁሉ ከቁምነገር ሳትቆጥራቸው ከሰማዩ አባትህ ጋር በሰማያዊ ቋንቋ ትነጋገራለህ።
“እስጢፋኖስም፦ ጌታ ኢየሱስ ሆይ፥ ነፍሴን ተቀበል ብሎ ሲጠራ ይወግሩት ነበር።”
— ሐዋርያት ፯÷፶፱
➢ ሲጀመር በላይ በሰማይ ያለውን ሰማያዊ ሕይወት እንጂ በምድር ያለውን ምድራዊ ነገር ማሰብ የመንፈሳዊ ሰው ጠባይ አይደለም።
➢ ስለዚህ አንተ መንፈሳዊ ነኝ ካልክ አስተሳሰብህ ሁሉ ሰማያዊ መሆን አለበት።
➢ ሰማያዊ አስተሳሰብ ያለው ሰው ደግሞ በክርስቶስ አንድ የሆኑትን ሁሉ አቅፎ ይቀበላል እንጅ ዘረኝነትን አያስብም። ምክንያቱም ዘረኝነት በሰማይ የለምና።
➢ ሰማያዊ አስተሳሰብ ያለው ሰው የባልንጀራውን ስም በሀሜት ቢላ እየዘለዘለ ቦጭቆ አይበላም።
ምክንያቱም ሀሜት በሰማይ የለምና።
ያለመታደል ሆኖ ብዙዎቻችን ሰማያውያን ነን እያል ራሳችንን እያታለልን ከንቱ ሆኖ በምድር ላይ የሚቀረውን ምድራዊ ሥራ እንሠራለን።
➢ ሰማያዊ አስተሳሰብ ያለው ሰው ግን በምድር እየኖረ ፳፬ ሰዓት ሰማያዊ ሥራን ይሠራል።
ሐዋርያው ቅ/ጳውሎስም፦
"...ሌሊትና ቀን በባሕር ውስጥ ኖርሁ።"
በማለት በምድር ላይ ሆኖ 24ሰዓት ሰማያዊ ሥራን እንዴት አድርጎ ይሠራ እንደነበረ ያሳየናል።
“ሦስት ጊዜ በበትር ተመታሁ፤ አንድ ጊዜ በድንጋይ ተወገርሁ፤ መርከቤ ሦስት ጊዜ ተሰበረ፤ ሌሊትና ቀን በባሕር ውስጥ ኖርሁ።”
— ፪ኛ ቆሮ ፲፩፥፳፭
➢ መንፈሳዊ ሰው አስተሳሰቡ ሁሉ ሰማያዊ ስለሆነ ለምድራዊ ፈተና በቀላሉ የሚበገር አይደለም። ምክንያቱም የቀበሮ መንጫጫት ለአንበሳ ስጋት አይሆንምና።
➢ ደግሞም ጉርጦች ከውኃ ውስጥ እየተንጫጩ አንበሳ መሀል ድረስ ገብቶ ጠጥቶ እንደሚወጣው ሁሉ ሰማያዊ አስተሳሰብ ያለው ሰውም ያለምንም ፍርሀት በምድራውያን ፈታኞች መካከል ገብቶ ሰማያዊ ሥራን ሠርቶ ይወጣል።
የተወደዳችሁ የልዑል እግዚአብሔር ቤተሰቦች!
#አሁንም_ደግሜ_እላለሁ፦
“በላይ ያለውን አስቡ እንጂ በምድር ያለውን አይደለም።”
— ቆላስይስ ፫÷፪
#ደግሞም፦
#አባታችን_በሰማይ_ነው።
“እንግዲህ እናንተስ እንዲህ ጸልዩ፦ በሰማያት የምትኖር አባታችን ሆይ፥”
— ማቴዎስ ፮÷፱
#ሀገራችን_በሰማይ_ነው።
“እኛ አገራችን በሰማይ ነውና፥ ከዚያም ደግሞ የሚመጣ መድኃኒትን እርሱንም ጌታን ኢየሱስ ክርስቶስን እንጠባበቃለን፤”
— ፊልጵስዩስ ፫÷፳
#መኖርያችን_በሰማይ_ነው።
“በአባቴ ቤት ብዙ መኖሪያ አለ፤ እንዲህስ ባይሆን ባልኋችሁ ነበር፤ ስፍራ አዘጋጅላችሁ ዘንድ እሄዳለሁና፤”
— ዮሐንስ ፲፬÷፪
#መዝገባችን_በሰማይ_ነው።
“ነገር ግን ብልም ዝገትም በማያጠፉት ሌቦችም ቆፍረው በማይሠርቁት ዘንድ ለእናንተ በሰማይ መዝገብ ሰብስቡ፤”
— ማቴዎስ ፮÷፳
#ስለዚህ፦
➢ በላይ በሰማይ ያለውን አስቡ እንጂ በምድር ያለውን አታስቡ!
#ምክንያቱም፦
“ስለ ሥጋ ማሰብ ሞት ነውና፥ ስለ መንፈስ ማሰብ ግን ሕይወትና ሰላም ነው።”
— ሮሜ ፰÷፮
➢ ሐዋርያውም የአስተሳሰቡን ፍጹም ሰማያዊነት ሲገልጥ፦
“በእነዚህም በሁለቱ እጨነቃለሁ፤ ልሄድ ከክርስቶስም ጋር ልኖር እናፍቃለሁ፥ ከሁሉ ይልቅ እጅግ የሚሻል ነውና፤”
— ፊልጵስዩስ ፩÷፳፫
#ተመልከቱ!
➢በምድር እየኖረ አስተሳሰቡ ሁሉ ሰማያዊ ነው። ምናለ ግን ሁላችንም እንደዚህ ያለ ኅሊና ቢኖረን???
ብዙዎቻችን እኮ በሰማይ የተዘጋጀልንን ዋጋ ስላልተረዳን ነው።
#ዘወትር_ቁልቁል_የምናስበው።
#ጥላቻን_የሚዘሩት፣
#ደም_የሚያፈስሱት፣
➢ ሀገር የሚያናውጡት ሁሉ ሰማያዊ አስተሳሰብ የሌላቸው ናቸው። እኛ ግን ሀገራችን በሰማይ ነውና፥ ከላይ ከሰማይ የሆነውን ዋጋ በተስፋ እንጠባበቃለን።
“እኛ አገራችን በሰማይ ነውና፥ ከዚያም ደግሞ የሚመጣ መድኃኒትን እርሱንም ጌታን ኢየሱስ ክርስቶስን እንጠባበቃለን፤”
— ፊልጵስዩስ ፫÷፳
➢ በዚህም ደግሞ ዋጋችን በሰማይ ታላቅ እንደሚሆን እምነታችን ሙሉ ነው።
“ዋጋችሁ በሰማያት ታላቅ ነውና ደስ ይበላችሁ፥ ሐሴትም አድርጉ፤ ከእናንተ በፊት የነበሩትን ነቢያትን እንዲሁ አሳድደዋቸዋልና።”
— ማቴዎስ ፭÷፲፪
ስለዚህ የተወደዳችሁ የልዑል እግዚአብሔር ቤተሰቦች! እባካችሁ ምድራዊውን ነገር በማሰብ ውድ ጊዜአችሁን በከንቱ አታባክኑ!
✥••┈┈••●◉ ✞ ◉●••┈┈••✥
📖 ወስብሐት ለእግዚአብሔር 📖
📖 ወለወላዴቱ ድንግል 📖
📖 ወለመስቀሉ ክቡር 📖
📖✞✞✞✞✞📖
✞✞✞ ሃሳብ ➢
@gebrye_comment_bot
|❀:✧๑ ✞✞✞✞✞✞✞ ๑✧❀|:
✞✞✞ ይቀላቀሉ ➣
@mahteben_albetsm
††† በስመ አብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ አሐዱ አምላክ አሜን ! †††
#ታህሳስ ፲፫
#አባ_አብራኮስ_ገዳማዊ
➤ አባቶቻችን ይህንን ቅዱስ "ኃያል መነኮስ" ይሉታል። በ፳ቱ ወደ በርሃ ገብቶ ለ፸ ዓመታት በበርሃ ሲጋደል ፺ ዓመት ሞልቶታል። ሰይጣንን መፈናፈኛ አሳጥቶ ከአካባቢው አርቆታል።
➤ ሰይጣንም እርሱን መጣል ስላልቻለ ቢያንስ ከጾሙ፣ ጸሎቱና ስግደቱ ትንሽ ቢቀንስልኝ ብሎ አዲስ የፈተና ስልትን ፈጠረ። በገሃድ ቀርቦም "አብራኮስ አንተ ደክመሃል። ግንኮ ገና ፶ ዓመት እድሜ አለህ።" አለው።
➤ ቅዱሱ ግን ሰይጣንን "አሳዘንከኝ! እኔኮ ገና ፻ ዓመት ያለኝ መስሎኝ ነው በጥቂቱ የምጋደለው። እንዲያ ከሆነማ ከነበረኝ ጾም፣ ጸሎትና ስግደት በእጥፉ እጨምራለሁ።" ቢለው ሰይጣን አፍሮ ተመልሷል። ቅዱስ አብራኮስ ግን በዚያው ዘመን በ፺ ዓመቱ ዐርፏል።
✥••┈┈••●◉ ✞ ◉●••┈┈••✥
➤ ታኅሣሥ ፲፫ ቀን የሚከበሩ ዓመታዊ የቅዱሳን በዓላት
፩.አቡነ ዘርዓ ቡሩክ ጻድቅ
፪.ቅዱስ መቃርስ ገዳማዊ
፫.አባ አብራኮስ ገዳማዊ
፬.ብጽዕት ሐና (የእመቤታችን እናት)
፭.አባ በጽንፍርዮስ ሰማዕት
፮.አባ ሚካኤል ዘቀልሞን
➤ ወርኀዊ በዓላት
፩.እግዚአብሔር አብ
፪.ቅዱስ ሩፋኤል ሊቀ መላእክት
፫.ቅዱስ አርሳንዮስ ጠቢብ ገዳማዊ
፬.ዘጠና ዘጠኙ ነገደ መላእክት
፭.ቅዱስ አስከናፍር ሮማዊ
፮.አሥራ ሦስቱ ግኁሳን አበው
✥••┈┈••●◉ ✞ ◉●••┈┈••✥
"ነቢይን በነቢይ ስም የሚቀበል የነቢይን ዋጋ ይወስዳል። ጻድቅን በጻድቅ ስም የሚቀበል የጻድቁን ዋጋ ይወስዳል። ማንም ከእነዚህ ከታናናሾቹ ለአንዱ ቀዝቃዛ ውኃ ብቻ በደቀ መዝሙር ስም የሚያጠጣ እውነት እላችኋለሁ ዋጋው አይጠፋበትም።"
-----ማቴዎስ ፲፥፵፩-፵፪
✥••┈┈••●◉ ✞ ◉●••┈┈••✥
✞✞✞"አምላከ አበው ቅዱሳን በመጽናታቸው ያጽናን ከበረከታቸውም ያድለን።"✞✞✞
✞✞✞✞✞ አሜን ✞✞✞✞✞
✥••┈┈••●◉ ✞ ◉●••┈┈••✥
📖 ወስብሐት ለእግዚአብሔር 📖
📖 ወለወላዴቱ ድንግል 📖
📖 ወለመስቀሉ ክቡር 📖
📖✞✞✞✞✞📖
✞✞✞ ሃሳብ ➢
@gebrye_comment_bot
|❀:✧๑ ✞✞✞✞✞✞✞ ๑✧❀|:
✞✞✞ ይቀላቀሉ ➣
@mahteben_albetsm
††† በስመ አብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ አሐዱ አምላክ አሜን ! †††
#ጥር ፲
#አባ_ኤስድሮስ_ገዳማዊ
➤ አባ ኤስድሮስ ግብጻዊ ሲሆኑ ሹመትን ጠልተው ፈርማ በሚባል ገዳም ለ፷ ዓመታት በበርሃ ውስጥ ከ፲፰፼ በላይ ድርሳናትን ጽፈዋል።
➤ ይህም በዓለም ታሪክ ብዙ መጻሕፍትን በመጻፍ ቀዳሚው ያደርጋቸዋል። ከድርሳናቱ መካከል ፪፼ ያህሉ ዛሬም ድረስ በግብጽ በርሃ ውስጥ ይገኛሉ።
✥••┈┈••●◉ ✞ ◉●••┈┈••✥
➤ የካቲት ፲ ቀን የሚከበሩ ዓመታዊ የቅዱሳን በዓላት
፩.ቅዱስ ያዕቆብ ሐዋርያ (ወልደ እልፍዮስ)
፪.ቅዱስ ዮስጦስ ሰማዕት
፫.አባ ኤስድሮስ ጻድቅ (ዘሃገረ ፈርማ)
፬.አባ ፌሎ ሰማዕት
፭.ቅዱስ ስምዖን
፮.ቅዱስ ኒቆላዎስ
➤ ወርኀዊ በዓላት
፩.ቅዱስ ዕፀ መስቀል
፪.ቅዱስ ናትናኤል ሐዋርያ
፫.ቅዱስ ኒቆላዎስ ዘሃገረ ሜራ
፬.ቅዱስ ቆስጠንጢኖስ ጻድቅ ንጉሥ
፭.ቅድስት ዕሌኒ ንግሥት
፮.አቡነ መልክዐ ክርስቶስ
✥••┈┈••●◉ ✞ ◉●••┈┈••✥
"ራሳቸውም ስለ እናንተ ሲያማልዱ፥ በእናንተ ላይ ከሚሆነው ከሚበልጠው ከእግዚአብሔር ጸጋ የተነሣ ይናፍቁአችኋል።ስለማይነገር ስጦታው እግዚአብሔር ይመስገን።"
— ፪ቆሮ ፱፥፲፬-፲፭
“ለቅዱሳን እንደሚገባ ግን ዝሙትና ርኵሰት ሁሉ ወይም መመኘት በእናንተ ዘንድ ከቶ አይሰማ፤”
— ኤፌሶን ፭፥፫
✥••┈┈••●◉ ✞ ◉●••┈┈••✥
"✞✞✞ አምላከ ቅዱሳን ቸርነቱን ምሕረቱን ያብዛልን። በምልጃቸው ሃገራችንን ከክፉ ጠብቆ ከበረከታቸው ይክፈለን።✞✞✞"
✞✞✞✞✞ አሜን ✞✞✞✞✞
✥••┈┈••●◉ ✞ ◉●••┈┈••✥
📖 ወስብሐት ለእግዚአብሔር 📖
📖 ወለወላዴቱ ድንግል 📖
📖 ወለመስቀሉ ክቡር 📖
📖✞✞✞✞✞📖
✞✞✞ ሃሳብ ➢
@gebrye_comment_bot
|❀:✧๑ ✞✞✞✞✞✞✞ ๑✧❀|:
✞✞✞ ይቀላቀሉ ➣
@mahteben_albetsm
††† በስመ አብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ አሐዱ አምላክ አሜን ! †††
#ጥር ፲፫
#ቃና_ዘገሊላ
➢ "ቃና" የሚለው ቃል በሃገራችን ልሳን (በአማርኛ) የምግብን፣ የመጠጥን ጥፍጥና ወይም በጐ መዓዛን የሚያመለክት ነው። ምናልባትም ከዚህ በዓል ምሥጢር የተወሰደ ሳይሆን አይቀርም።
➢ በቤተ ክርስቲያን ታሪክ ግን ቃና ከገሊላ አውራጃዎች አንዷ ናት። ለስም አጠራሩ ስግደት ይሁንና የክብር ባለቤት መድኃኒታችን ክርስቶስ በዚህች ሥፍራ ተገኝቶ በድንግል እናቱ ምልጃ ታላቅ ተአምርን በዚህች ዕለት ጥር ፲፪ ሠርቷል።
➢ "ተአምር" የሚለውን ቃል በቁሙ "ምልክት" ብሎ መተርጐም ይቻላል። መሠረታዊ መልዕክቱ ግን ነጮቹ በልሳናቸው (Miracle) የሚሉት ዓይነት ነው።
➢ ከተፈጥሮ ሕግ ውጪ (በላይ) ከፍጡራንም ችሎታ የላቀ ነገር ሲሠራ (ሲፈጸም) ተአምር ይባላል። ተአምር የእግዚአብሔር የባሕርይ ገንዘቡ ነው።
➢ እርሱ ዓለምን ከመፍጠሩ ጀምሮ እያንዳንዷ ተግባሩ ለእኛ ተአምራት ናቸው። ስለዚህም ነው "#ኤልሻዳይ #ከሐሌ_ኩሉ #ሁሉን_ቻይ" እያልን የምንጠራው።
➢ እግዚአብሔር ፍጡራኑን ይወዳልና እርሱ ለወደዳቸውና ደስ ላሰኙት ተአምራት ማድረግን ሰጥቷል። በብሉይ ኪዳን እነ ሙሴ ባሕር ሲከፍሉ፣ መና ሲያዘንሙ፣ ውኃ ሲያፈልቁ (ኦሪትን ተመልከት።) እነ ኤልያስ ሰማይን ሲለጉሙ፣ እሳትን ሲያዘንሙ፣ ሙታንን ሲያስነሱ (፩ነገሥትን ተመልከት።) እንደ ነበር ይታወቃል።
➢ እንዲያውም በሙሉ መጽሐፍ ቅዱስ የተአምር መጽሐፍ ነው ብሎ ለመናገርም ያስደፍራል። በሐዲስ ኪዳንም መድኃኒታችን ብዙ ተአምራትን ሠርቶ ለሐዋርያቱ የተአምራት ጸጋውን ሰጥቷቸዋል።
➔ ማቴዎስ. ፲፥፰ ፤ ፲፯፥፳
➔ ማርቆስ . ፲፮፥፲፯
➔ ሉቃስ . ፲፥፲፯
➔ ዮሐንስ. ፲፬፥፲፪
➢ እነርሱም በተሰጣቸው ሥልጣን ብዙ ተአምራትን ሠርተዋል።
➔ የሐዋርያት . ፫፥፮ ፤ ፭፥፩ ፤ ፭፥፲፪ ፤ ፰፥፮ ፤ ፱፥፴፫-፵፫ ፤ ፲፬፥፰ ፤ ፲፱፥፲፩
➢ ቅዱስ ዮሐንስ ሐዋርያ በወንጌሉ ምዕራፍ ፪ ላይ እንዳስቀመጠው የቃና ዘገሊላው ተአምር የመጀመሪያው ነው። "ወዝንቱ ቀዳሜ ተአምር....." እንዲል።
“ኢየሱስ ይህን የምልክቶች መጀመሪያ በገሊላ ቃና አደረገ፤ ክብሩንም ገለጠ፥ ደቀ መዛሙርቱም በእርሱ አመኑ።”
— ዮሐንስ. ፪፥፲፩
➢ ያ ማለት ግን ጌታ ከዚያ በፊት ተአምራትን አልሠራም ማለት አይደለም።
➢ ይልቁኑ ራሱን ከገለጠና ከተጠመቀ በኋላ የሠራው የመጀመሪያው ተአምር ነው ሲል ነው እንጂ። ምክንያቱም መድኃኒታችን እንደ ተጠመቀ ዕለቱኑ ገዳመ ቆረንቶስ ገብቷልና።
“ከዚያ ወዲያ ኢየሱስ ከዲያብሎስ ይፈተን ዘንድ መንፈስ ወደ ምድረ በዳ ወሰደው፥”
— ማቴዎስ. ፬፥፩
➢ አንድም በቃና ሌሎች ተአምራትን የሚሠራ ነውና ይህ ተአምር በቃና የመጀመሪያው ሆነ። ትክክለኛው የቃና ዘገሊላ ቀን የካቲት ፳፫ ነው። ጥር ፲፩ ተጠምቆ የካቲት ፳፩ ቀን ከጾም ተመልሷል። ከዚያም የካቲት ፳፫ ቀን ደቀ መዛሙርቱን ሰብስቦ ሒዷል።
➢ ነገር ግን አበው መንፈስ ቅዱስ እንደ መራቸው የውኃ በዓል ከውኃ በዓል ጋር ይስማማል ብለው ጥር ፲፪ አድርገውታል።
➢ በቃና ዘገሊላ ሙሽራው ዶኪማስ ሲሆን ባለ ሠርጉ ደግሞ አባቱ ዮአኪን ነው። ይህም ለሐዋርያው ቅዱስ ናትናኤል አጐቱ ነው። የልጁ ጋብቻ የተቀደሰ ይሆን ዘንድም ጌታ ክርስቶስን፣ ድንግል እናቱንና ባለሟሎቹ ሐዋርያትን ወደ ሠርጉ ጠራ።
➢ ምንም እንኳ መድኃኒታችንና እመቤታችን ከድግሱ የማይበሉ ቢሆኑም (በትሕርምት ኗሪዎች ነበሩና።) ጠሪውን ደስ ለማሰኘት ሠርጉን ለመቀደስና የጋብቻን ክቡርነት ለማሳየት አብረው ታደሙ።
➢ የሠርጉ ሥነ ሥርዓት ሲጀመር በድንኳኑ ውስጥ ጌታ ከመካከል ተቀመጠ። ድንግል በቀኙ፣ ዮሐንስ በግራው ሲቀመጡ፣ ሌሎች ሐዋርያት ግራና ቀኝ ከበው ተቀመጡ። ሲበላና ሲጠጣ ድንገት የተደገሰው ምግብና መጠጥ አለቀ።
➢ ደጋሾቹ በጭንቅ ላይ ሳሉም አይጠና ሆዷ ድንግል እመ ብርሃን የሆነውን አወቀች።
#እንዴት_አወቀች_ቢሉ፦
➢ በጸጋ፣ አንድም "ከልጅሽ አማልጂን።" ብለው ቢለምኗት ነው ይሏል። እመቤታችን በዚያ ጊዜ ወደ ልጇ ቀርባ ቸር ልጇን "ወይንኬ አልቦሙ - ወይኑኮ አልቆባቸዋል።" አለችው። ለጊዜው ወይኑም፣ ምግቡም ስላለቀባቸው እንዲህ አለች።
➢ በምሥጢሩ ግን ወይን ያለችው ፍቅርን፣ ቅዱስ ቃሉንና ክቡር ደሙን ነው። ጌታም ይመልሳል፦
"ምንት ብየ ምስሌኪ ኦ ብእሲቶ ዓዲ ኢበጽሐ ጊዜየ - አንቺ ሆይ! (እናቴ ሆይ!) ያልሽኝን አላደርግ ዘንድ ካንቺ ጋር ምን ጠብ አለኝ? ነገር ግን ጊዜው ገና አልደረሰም ብየ ነው እንጂ።" አላት።
#ምክንያቱም_ጌታ
የወይን ጋኖቹ እስኪያልቁ ይጠብቅ ነበር። (አበረከተ ይሉታልና።)
አንድም ይሁዳ ወጥቶ ነበርና እርሱ እስኪመለስ ነው። (እኔ ስወጣ ጠብቆ ተአምር ሠራ ብሎ ለክፋቱ ምክንያት እንዳያቀርብ።)
➢ አንድም "ወይን (ቅዱስ ደሜን) የምሰጠው በቀራንዮ አንባ ነው።" ሲል "ጊዜዬ ገና ነው።" ብሏታል። አንዳንድ ልቡናቸው የጠፋ ወገኖቻችን ጌታ እመቤታችንን እንዳቃለላት (ሎቱ ስብሐት! ወላቲ ስብሐት!) አስመስለው ይናገራሉ።
➢ ይህንን እንኳን ጌታ ባለጌዎቹ እነርሱም አያደርጉት።
"አባትህንና እናትህን አክብር።"
ዘጸ. ፳፥፲፪ ያለ ጌታ እንዴት ለእናቱ ክብርን ይነፍጋል?
#ልቡና_ይስጠን!
➢ ወደ ጉዳያችን ስንመለስ መድኃኒታችን እንዲህ ሲል መለሰላት። ተግባብተዋልና እመ ብርሃን አሳላፊዎቹን "ኩሎ ዘይቤለክሙ ግበሩ - የሚላችሁን ሁሉ አድርጉ።" አለቻቸው።
“እናቱም ለአገልጋዮቹ፦ የሚላችሁን ሁሉ አድርጉ አለቻቸው።”
— ዮሐንስ. ፪፥፭
➢ ጌታም በስድስቱ ጋኖች ውኃ አስሞልቶ በተአምራት ወይን አደረጋቸው።
እንጀራውን ወጡን በየሥፍራው ሞላው። ታላቅ ደስታም ሆነ።
➢ የአሳላፊዎቹ አለቃም (ለአባታችን አብርሃም ምሳሌ ነው።) ከወይኑ ጥፍጥና የተነሳ አደነቀ። በዚህም የድንግል ማርያም አማላጅነት፣ የመድኃኒታችን ከሃሊነት ታወቀ፤ ተገለጠ።
✥••┈┈••●◉ ✞ ◉●••┈┈••✥
✞✞✞"_አምላከ ቅዱሳን ወይነ ቃና ፍቅሩን ያሳድርብን። ከድንግል እናቱ ምልጃና ከቅዱሳኑ በረከትም አይለየን_።"✞✞✞
✞✞✞✞✞ አሜን ✞✞✞✞✞
✥••┈┈••●◉ ✞ ◉●••┈┈••✥
📖 ወስብሐት ለእግዚአብሔር 📖
📖 ወለወላዴቱ ድንግል 📖
📖 ወለመስቀሉ ክቡር 📖
📖✞✞✞✞✞📖
✞✞✞ ሃሳብ ➢
@gebrye_comment_bot
|❀:✧๑ ✞✞✞✞✞✞✞ ๑✧❀|:
✞✞✞ ይቀላቀሉ ➣
@mahteben_albetsm
††† በስመ አብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ አሐዱ አምላክ አሜን ! †††
#ጥር ፮
#ጻድቅ_ኖኅ
➤ የዚህን ታላቅ ቅዱስ ሰው ክብር የሚያውቅና የሚያከብረው ሁሉ ንዑድ ነው። አባታችን ኖኅ ዛሬ በዓለም የሚመላለሰው ሰው ሁሉ አባት ነው። ደግ ጻድቅና ነቢይ ሰው ነው።
➤ ከአባታችን አዳም ፲ኛው ጻድቅ ሲሆን ከ፲፭ አበው ነቢያትም አንዱ ነው። ከአባቱ ከላሜሕ ተወልዶ፣ በደብር ቅዱስ አድጐ፣ ንጽሐ መላእክትን ገንዘብ አድርጐ፣ ለ፭፻ ዓመታት በድንግልና ኑሯል።
➤ በእነዚህ ጊዜያትም አጽመ አዳምን እየጠበቀና መስዋዕትን ለልዑል አምላክ እየሰዋ ያመልክ ነበር። የሴት ልጆች ከቃየን ልጆች ጋር ተባብረው ዓለም በረከሰች ጊዜም በእግዚአብሔር ፊት ጻድቅ ሆኖ ተገኝቷል።
➤ ከሚስቱ (እናታችን) ሐይከል (አምዛራ) ጋር ፫ ጊዜ አብሮ አድሮ ሴም፣ ካምና ያፌትን ወልዷል።
➤ የጥፋት ውኃ በመጣ ጊዜም የእመቤታችን ምሳሌ በሆነች መርከብ ድኗል። ከመርከብ ወጥቶም ከጌታ ጋር በቀስተ ደመና ምስክርነት ቃል ኪዳን ተጋብቷል።
➤ ከዚያም ዓለምን ለ፫ ልጆቹ አካፍሎ ለ፫፻፶ ዓመታት በበጐ አምልኮ ኑሯል። በዚህች ቀንም ጥር ፮ ዕድሜን ጠግቦ በ፱፻፶ ዐርፏል።
✥••┈┈••●◉ ✞ ◉●••┈┈••✥
➤ ጥር ፮ ቀን የሚከበሩ ዓመታዊ በዓላት።
፩.በዓለ ግዝረቱ ለክርስቶስ
፪.ቅዱስ ኤልያስ ነቢይ
፫.ቅዱስ ኖኅ ጻድቅ
፬.ታላቁ ቅዱስ ባስልዮስ ዘቂሣርያ
፭.አባ ሙሴ ገዳማዊ
፮.አባ ወርክያኖስ
➤ ወርኀዊ በዓላት
፩.ቅድስት ደብረ ቁስቋም
፪.አባታችን አዳምና እናታችን ሔዋን
፫.ቅዱስ ዮሴፍ አረጋዊ
፬.ቅድስት ሰሎሜ
፭.አባ አርከ ሥሉስ
፮.አባ ጽጌ ድንግል
፯.ቅድስት አርሴማ ድንግል
✥••┈┈••●◉ ✞ ◉●••┈┈••✥
✞✞✞"የፃድቁ አባታችን የጻድቅ ኖኅ ረድኤት በረከት ይደርብን።"✞✞✞
✞✞✞✞✞ አሜን ✞✞✞✞✞
✥••┈┈••●◉ ✞ ◉●••┈┈••✥
📖 ወስብሐት ለእግዚአብሔር 📖
📖 ወለወላዴቱ ድንግል 📖
📖 ወለመስቀሉ ክቡር 📖
📖✞✞✞✞✞📖
✞✞✞ ሃሳብ ➢
@gebrye_comment_bot
|❀:✧๑ ✞✞✞✞✞✞✞ ๑✧❀|:
✞✞✞ ይቀላቀሉ ➣
@mahteben_albetsm
††† በስመ አብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ አሐዱ አምላክ አሜን ! †††
#ጥር ፭
#ቅዱስ_አውስግንዮስ_አረጋዊ
➤ ይህ ቅዱስ አባት በሃይማኖቱ ጽናት፣ በምግባሩ ብዛት ለወጣቶች አብነት መሆን የቻለ አባት ነው።
➤ በብዛት የሚታወቀው በሰማዕትነቱ ቢሆንም በቅዱስ ሰውነቱ በርካታ መልካም ነገሮችን ሠርቷል።
➤ በአራተኛው መቶ ክፍለ ዘመን መነሻ አካባቢ (ዘመነ ሰማዕታት ሊጠናቀቅ ሲል ማለት ነው።) የቅዱስ ቆስጠንጢኖስ (የንጉሡ) ወታደር ሁኖ ተቀጠረ።
➤ ንጉሡ ወደ መክስምያኖስ ለጦርነት ሲሔድ በሰማይ ላይ መስቀልና "ኒኮስጣጣን" የሚል ጽሑፍን ተመልክቷል።
➤ ሁሉም ሰው ለመተርጐም ሲፈራ ወጣቱ አውስግንዮስ ግን በድፍረት ለንጉሡ ክብረ መስቀልንና ትርጉሙን አስረዳ።
➤ በቅዱሱ ንጉሥ ሥርም በወታደርነት ለሃያ ዓመታት አገለገለ። ከዚያም ሥጋዊ ተግባሩን ትቶ በጾምና በጸሎት፣ ሰዎችንም በማስታረቅ፣ በማስተማርም ተወሰነ።
➤ ፈጣሪ ጸጋውን አብዝቶለትም ዕድሜው ፻፲ ዓመት ደረሰ። በጊዜውም የነበረው ከሃዲው ዑልያኖስ "ሰዎችን አስታርቀሃልና ክርስቶስን አምልከሃል።" በሚል በዚህች ቀን ጥር ፭ አንገቱን አሰይፎታል። ዑልያኖስን ደግሞ ቅዱስ መርቆሬዎስ ተበቅሎታል።
✥••┈┈••●◉ ✞ ◉●••┈┈••✥
➤ ጥር ፭ ቀን የሚከበሩ ዓመታዊ የቅዱሳን በዓላት
፩.ቅዱስ አባ ማቴዎስ
፪.ቅዱስ አውስግንዮስ አረጋዊ (ሰማዕት)
፫.ቅድስት እስክንድርያ
፬.ቅድስት አውስያ ሰማዕት
➤ ወርኀዊ በዓላት
፩.ቅዱስ ጴጥሮስ ሊቀ ሐዋርያት
፪.ቅዱስ ጳውሎስ ብርሃነ ዓለም
፫.አቡነ ገብረ መንፈስ ቅዱስ
፬.ቅዱስ ዮሐኒ ኢትዮጵያዊ
፭.ቅዱስ አሞኒ ዘናሒሶ
፮.ቅድስት አውጋንያ (ሰማዕትና ጻድቅ)
✥••┈┈••●◉ ✞ ◉●••┈┈••✥
"አባቶች ሆይ! ከመጀመሪያ የነበረውን አውቃችኋልና እጽፍላችኋለሁ። ጐበዞች ሆይ! ክፉውን አሸንፋችኋልና እጽፍላችኋለሁ። ልጆች ሆይ! አብን አውቃችኋልና እጽፍላችኋለሁ። አባቶች ሆይ! ከመጀመሪያ የነበረውን አውቃችኋልና እጽፍላችኋለሁ። ጐበዞች ሆይ! ብርቱ ስለ ሆናችሁ፣ የእግዚአብሔርም ቃል በእናንተ ስለሚኖር፣ ክፉውንም ስላሸነፋችሁ እጽፍላችኋለሁ።"
➔ ፩ዮሐ ፪፥፲፫-፲፬
✥••┈┈••●◉ ✞ ◉●••┈┈••✥
✞✞✞"አምላከ ቅዱሳን ስለ አባቶቻችን ሲል ይማረን። ከበረከታቸውም ይክፈለን።"✞✞✞
✞✞✞✞✞ አሜን ✞✞✞✞✞
✥••┈┈••●◉ ✞ ◉●••┈┈••✥
📖 ወስብሐት ለእግዚአብሔር 📖
📖 ወለወላዴቱ ድንግል 📖
📖 ወለመስቀሉ ክቡር 📖
📖✞✞✞✞✞📖
✞✞✞ ሃሳብ ➢
@gebrye_comment_bot
|❀:✧๑ ✞✞✞✞✞✞✞ ๑✧❀|:
✞✞✞ ይቀላቀሉ ➣
@mahteben_albetsm
††† በስመ አብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ አሐዱ አምላክ አሜን ! †††
#እንኳን_ለጌታችን_መድሀኒታችን_እየሱስ_ክርስቶስ_የልደት_በአል_በሰላም_አደረሳቹ
#ታህሳስ ፳፱
#ክፍል ፩
#ልደተ_ክርስቶስ
➢ ቅድስት ድንግል ማርያም ለአረጋዊው ዮሴፍ ከታጨች በኋላ ናዝሬት ገሊላ ከምትባል ከተማ ትኖር በነበረበት ከዕለታት በአንዱ ቀን ውኃ ቀድታ ስትመለስ መንገድ ላይ በመሄድ ሳለች የእግዚአብሔር መልአክ ወደ እርሷ ቀርቦ እንዲህ አላት።
➢ "ትፀንሲ!" እርሷም ድምጽን ሰምታ መለስ ብላ ብታይም ከአጠገቧ ማንንም ማየት ባለመቻሏ"አዳም አባቴን እና ሔዋን እናቴን ያሳተ ጠላት ይሆናል እንጂ ሌላ አይደለም" ብላ አሰበች፡፡
➢ ዳግመኛም "ትፀንሲ" የሚል ድምጽ ሰማች፡፡ "ይህ ነገር ደጋገመኝ፤ እንዲህ ያለውን ነገር ከቤተ መቅደስ ሆነው ሊረዱት ይገባል" ብላ ከቤተ መቅደስ ገብታ ወርቅና ሐር እያስማማች መፍተል ጀመረች፡፡ (ነገረ ማርያም)
➢ መልአኩ ቅዱስ ገብርኤልም በአምሳለ አረጋዊ እንዲህ አላት "ደስ ይበልሽ÷ ጸጋን የተመላሽ ሆይ÷ እግዚአብሔር ከአንቺ ጋር ነው፤ ከሴቶች መካከል አንቺ የተባረክሽ ነሽ፡፡"
➢ ድንግል ማርያምም "እንዲህ ያለ የምስጋና እጅ መንሻ እንዴት ይደረግልኛል?" ብላ ጠየቀችው፡፡ መልአኩም መልሶ "ማርያም ሆይ አትፍሪ፤ ከእግዚአብሔር ዘንድ ባለሟልነትን አግኝተሻልና፤ እነሆ ትፀንሺያለሽ፤ ወንድ ትወልጃለሽ፤ ስሙንም ኢየሱስ ትይዋለሽ፤ ይህ የሚወለደው ከሦስቱ ቅዱስ አንዱ ቅዱስ ነው፤ እርሱም የእግዚአብሔር ልጅ ይባላል" አላት፡፡
➢ እርሷም "ይህ ነገር እንደምን ይሆንልኛል፤ ወንድ ሳላውቅ? " አለችው፡፡ መልአኩ ገብርኤልም "መንፈስ ቅዱስ ይጠብቅሻል፤ የልዑል ኃይልም ያድርብሻል" አላት፡፡
➢ እርሷም የመልአኩን ቃል ተቀብላ "እንደ ቃልህ ይደረግልኝ" አለችው፤ በዚህ ጊዜ አካላዊ ቃል በግብረ መንፈስ ቅዱስ ተፀነሰ፡፡
➔ ሉቃ. ፩፥፳፰-፳፱
➔ ኢሳ. ፯÷፲፬
➤ ከዚህ በኋላም ንጉሥ አውግስጦስ ቄሳር ሕዝቡን ቀረጥ ለማስከፈል እንዲያመቸው በእስራኤል ሀገር ውስጥ ይኖሩ የነበሩ ሰዎችን ለማወቅ ቆጠራ እንዲደርግ አዘዘ፡፡
➢ ሕዝቡም ለመቆጠር ወደ ትውልድ ስፋራው መጓዝ ጀመረ፡፡ እመቤታችን ድንግል ማርያምም የንጉሥ ዳዊት ዘር ሀረግ ስለነበራት ግዛቱ ወደ ነበረው ቤተ ልሔም ከአረጋዊው ዮሱፍ ጋር ሄደች፡፡
➢ በዚያም ሳሉ እመቤታችን መውለጇ ቀን ደረሰ፡፡ ሆኖም ግን ከተማዋ ትንሽ ስለነበረችና ለመመዝገብ የመጣው ሰው ብዙ ስለነበረ ማረፊያ ቦታ ሊያገኙ አልቻሉም፡፡ አረጋዊው ዮሴፍም ከብዙ ድካም በኋላ ከብተቾች የሚያርፉበት በረት አግኝቶ እመቤታችንን በዚያ አስቀመጣት፡፡
➢ በከብቶች በረት ውስጥ ሳሉ እመቤታችን የመውለጃዋ ጊዜ በመድረሱ ጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስን ወለደችው፤ በጨርቅ ጠቅልላ በበረት ውስጥ አስተኛችው፡፡
➢ በዚያን ሌሊት በቤተ ልሔም ይኖሩ የነበሩ እረኞችም ከብቶቻቸውን ሲጠብቁ የእግዚአብሔር መልአክ በእረኞቹ አጠገብ ቆመ፤ የእግዚአብሔርም ብርሃን በዙሪያቸው በራ፤ በጣምም ፈሩ፡፡ መልአኩም እንዲህ አላቸው "እነሆ ለእናንተና ለሕዝቡ ሁሉ ደስታ የሚሆን ታላቅ የምሥራች እነግራችኋለሁና አትፍሩ፤ እነሆ፥ ዛሬ በዳዊት ከተማ መድኅሀኒት ተወልዶላችኋል፡፡ ይኸውም ጌታ እና እግዚአብሔር የሆነ መድኃኒታችን ኢያሱስ ክርስቶስ ነው፡፡ እናንተም ባገኛችሁት ጊዜ ምልክቱ እንዲህ ነው፡፡ ሕፃን በጨርቅ ተጠቅልሎ በበረት ውስጥ ተኝቶ ታገኙታላችሁ፤ ድንገትም ከዚያ መልአክ ጋር ብዙ የሰማይ መላእክት እግዚአብሔርን እያመሰገኑ መጡ፡፡"
➔ ሉቃ.፪፥፲-፲፫
➢ እረኞቹም እርስ በርሳቸው "እስከ ቤተ ልሔም እንሂድ፤ እግዚአብሔርም የገለጠልንን ይህን ነገር እንወቅ" ተባባሉ፤ ፈጥነውም ሄዱ፡፡ ድንግል ማርያምንና ዮሴፍንም በከብቶቹ በረት አገኙአቸው፡፡
➢ ሕፃኑንም በአዩት ጊዜ የነገሩአቸው እውን መሆኑን ስላዩ በጣም ተደነቁ፡፡ እረኞቹም እንደነገሩአቸው ባዩትና በሰሙት ሁሉ እግዚአብሔርን እያመሰገኑ "በሰማይ ለእግዚአብሔር ክብር ይሁን፤ በምድርም ለሰው ልጆች በጎፈቃድ ሆነ ብለው እያመሰገኑና እያከበሩ ወደመጡበት ተመለሱ፡፡
➔ ሉቃ.፪፥፲፭-፲፰
➢ ሰብአ ሰገልም የእግዚአብሔር ልጅ የተወለደበትን ዋሻ የሚያመለክት ኮከብ እየመራቸው ከምሥራቅ ወደ እርሱ መጡ፤ ስለ አምላክ መወለድ አስቀድመው ያውቁ ነበርና፡፡ ስለሆነም ኮከቡን ተከትለው ልጁን ይፈልጉ ነበር፡፡
➢ የይሁዳም ንጉሥ ሄሮድስ ሕፃኑን ስለሚሹት ጠቢባን ሰዎች ሲሰማ ቀደም ብሎ ወደ ቤተ መንግሥቱ ጋበዛቸው፡፡ እንደ እነርሱም ጌታችን ኢየሱስን ለማምለክ እንደሚፈልግ በመግለጽ ልጁን ሲያገኙት ወደ እርሱ ይዘውት እንደሚመጡ ጥበበኞቹን ጠየቃቸው፡፡
#ይቀጥላል.........
✥••┈┈••●◉ ✞ ◉●••┈┈••✥
✞✞✞"እግዚአብሔር አምላክ በዓሉን የሰላም፣ የፍቅር እና የአንድነት ያድርግልን።"✞✞✞
✞✞✞✞✞ አሜን ✞✞✞✞✞
✥••┈┈••●◉ ✞ ◉●••┈┈••✥
📖 ወስብሐት ለእግዚአብሔር 📖
📖 ወለወላዴቱ ድንግል 📖
📖 ወለመስቀሉ ክቡር 📖
📖✞✞✞✞✞📖
✞✞✞ ሃሳብ ➢
@gebrye_comment_bot
|❀:✧๑ ✞✞✞✞✞✞✞ ๑✧❀|:
✞✞✞ ይቀላቀሉ ➣
@mahteben_albetsm
††† በስመ አብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ አሐዱ አምላክ አሜን ! †††
#ታህሳስ ፳፬
#ቅዱስ ተክለ ሃይማኖት ሐዋርያዊ
#ልደት
➤ መልካም ዛፍ መልካም ፍሬን ያፈራልና ተክለ ሃይማኖትን የወለዱት ደጋጉ ጸጋ ዘአብ ካህኑና እግዚእ ኃረያ ናቸው። እርሱ በክህነቱ እርሷ በደግነቷ፣ በምጽዋቷ ጸንተው ቢኖሩ እግዚአብሔር ጣፋጭ ፍሬን ሰጥቷቸዋል።
➤ በዳሞቱ ገዢ በሞተለሚ አደጋ ቢደርስባቸው ቅዱስ ሚካኤል ጸጋ ዘአብን ከሞት እግዚእ ኃረያን ከትድምርተ አረሚ (ከአረማዊ ጋብቻ) አድኗቸዋል። በኋላም የቅዱሱን መወለድ አብስሯቸዋል።
➤ ጻድቁ አቡነ ተክለ ሃይማኖት የተጸነሱት መጋቢት ፳፬ ቀን በ፲፪፻፮ ዓ/ም ሲሆን የተወለዱት ደግሞ ታኅሣሥ ፳፬ ቀን በ፲፪፻፯ ዓ/ም ነው። በተወለዱበት ቀንም ብዙ ተአምራት ተገልጸዋል። ቤታቸውም በበረከት ሞልቷል።
#ዕድገት
➤ የጻድቁ የመጀመሪያ ስማቸው "ፍሥሃ ጽዮን" ይሰኛል። ይህንን ስም ይዘው አባታቸው ጸጋ ዘአብን ተከትለው አድገዋል። በተለይ ቅዱሳት መጻሕፍትን (ብሉያት፣ ሐዲሳትን) ተምረዋል። በሥጋዊው ጐዳናም ብርቱ አዳኝ እንደ ነበሩ ይነገራል። ዲቁናም ከወቅቱ ጳጳስ አባ ጌርሎስ ተቀብለዋል።
#መጠራት
➤ አንድ ቀን ፍሥሃ ጽዮን ለአደን ወጥቶ ሲያነጣጥር ድንገት ከሰማይ አስደንጋጭ ድምጽ ተሰማ። የክብር ባለቤት ጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ አእላፍ መላእክት እያመሰገኑት በሚካኤል ክንፍ ተቀምጦ ወረደ።
➤ የወጣቱን አዳኝ ፍርሃቱን አርቆ ጌታችን ተናገረ። "ከዛሬ ጀምሮ ስምህ ተክለ ሃይማኖት (ተክለ ሥላሴ) ይሁን።
➤ ከዚህ በኋላ አራዊትን ሳይሆን ነፍሳትን ታድናለህ። ዘወትር ካንተ ጋር ነኝ።" ብሎ በግርማ ዐረገ። ቅዱስ ተክለ ሃይማኖት ከዚህ በኋላ ሰዓትን አላጠፉም። ንብረታቸውን ለነዳያን በትነው በትር ብቻ ይዘው ቤታቸው እንደ ተከፈተ ወደ ምናኔ ወጡ።
#አገልግሎት
➤ ቅዱስ ተክለ ሃይማኖት ከጳጳሱ ቅስና ተቀብለው የወንጌል አገልግሎትን ጀመሩ። በመጀመሪያ ስብከታቸው እዚያው ሽዋ (ጽላልሽ) አካባቢ ብቻ በአሥር ሺህ የሚቆጠሩ ሰዎችን አሳምነው አጠመቁ። ያን ጊዜ ኢትዮጵያ ሁለት መልክ ነበራት።
➔ ፩ኛ.ዮዲት (ጉዲት) በፈጠረችው ጣጣና በእስላሞች ተጽዕኖ ወደ ደቡብ አካባቢ ያለው ነዋሪ አንድም ሃይማኖቱን ክዷል ወይም በባዕድ አምልኮ ተጠምዷል።
➔ ፪ኛው. ደግሞ በዛግዌ ነገሥታት ጥረት ክርስትናና ምናኔ ተነቃቅቶ ነበር።
ግማሹ ሃገር በጨለመበት ወቅት የደረሱት ሐዲስ ሐዋርያ አባ ተክለ ሃይማኖት በወጣት ጉልበታቸውና በኃይለ መንፈስ ቅዱስ ብዙ ቦታዎችን አደረሱ።
ሕዝቡንና መሳፍንቱን ወደ ሃይማኖት መልሰው ማርያኖችን (ጠንቋዮችን) አጥፍተዋል።
#ገዳማዊ\_ሕይወት
➤ ቅዱስ ተክለ ሃይማኖት በወንጌል ብርሃን ኢትዮጵያን ከማብራታቸው ባለፈ ገዳማዊ ሕይወትንም አስፋፍተዋል። እርሳቸው ከሁሉ የተሻሉ ሳሉም በሦስት ገዳማት በረድዕነት አገልግለዋል።
➤ እነዚህም በአቡነ በጸሎተ ሚካኤል ገዳም ለ፲፪ ዓመታት፣ በአቡነ ኢየሱስ ሞዐ ዘሐይቅ ገዳም ለ፯ ዓመታት፣ በደብረ ዳሞ ከአቡነ ዮሐኒ ጋር ለ፯ ዓመታት በአጠቃላይ ለ፳፮ ዓመታት አገልግለዋል።
➤ በአቡነ ኢየሱስ ሞዐ ከመነኮሱ በኋላም ወደ ምድረ ሽዋ (ዞረሬ) ተመልሰው በአንዲት በዓት ውስጥ ለ፳፪ ዓመታት ቆመው ጸልየዋል።
➤ በተሰበረ እግራቸውም ፮ ጦሮችን በግራና በቀኝ ተክለው ለ፯ዓመታት ጸልየዋል።
#ስድስት\_ክንፍ
➤ ኢትዮጵያዊው ጻድቅና ሐዋርያ ቅዱስ ተክለ ሃይማኖት ከኢትዮጵያ ወደ ኢየሩሳሌም ተጉዘው ከቅዱሳት መካናት ተባርከዋል። ጻድቁ ምድረ እስራኤል የገቡት በየመንገዱ መንፈሳዊ ዘርን እየዘሩ፣ እያስተማሩና እያሳመኑ ነበር።
➤ የወቅቱ ሊቀ ጳጳሳት አባ ሚካኤል ጋርም ተገናኝተው ቡራኬን ተሰጣጥተዋል። ዋናው ጉዳይ ግን ከዚህ በኋላ ነው።
➤ ጻድቁ እመቤታችንና ጌታችን ከጽንሰታቸው እስከ ዕርገታቸው የረገጧቸውን ቦታዎች ሲመለከቱ በፍጹም ተደሞ እንባቸው ይፈስ ነበር።
ምክንያቱም እግዚአብሔር ስላበቃቸው ተክለ ሃይማኖት የሚያዩት ቦታውን አልነበረም። በገሃድ፦
በቤተ መቅደስ ብስራቱን፣
በቤተ ልሔም ልደቱን፣
በቤተ ዮሴፍ ግዝረቱን፣
በፈለገ ዮርዳኖስ ጥምቀቱን፣
በቤተ አልዓዛር ተአምራቱን ይመለከቱ ነበር።
➤ የጉብኝታቸው የመጨረሻ ክፍል ወደ ሆነው ቀራንዮ ደርሰው ጌታቸውን እንደ ተሰቀለ ሆኖ ቢመለከቱት ከዓይናቸው ይፈስ የነበረው ቁጡ እንባ መልኩን ቀየረና ዓይናቸው ጠፋ።
➤ በዚያች ቅጽበት ስም አጠራሯ የከበረ እመቤታችን ድንግል ማርያም ፈጥና ደርሳ አባታችንን ወደ ሰማይ አሳረገቻቸው።
#በዚያም፦
የብርሃን ዓይን ተቀብለው፣
፮ ክንፍ አብቅለው፣
የወርቅ ካባ ላንቃ ለብሰው፣
ማዕጠንተ ወርቁን ይዘው፣
ከ፳፬ ካህናተ ሰማይም ተደምረው፣
ሥላሴን በአንድነቱና ሦስትነቱ ተመልክተው "ስብሐት ወክብር ለሥሉስ ቅዱስ ይደሉ" ብለው መንበረ ጸባኦትን አጥነው ወደ መሬት ተመልሰዋል።
#ተአምራት
➤ የአቡነ ተክለ ሃይማኖት ተአምራት እንደ ሰማይ ከዋክብት የበዛ ነው።
➢ሙት አንስተዋል፣
➢ድውያንን ፈውሰዋል፣
➢አጋንንትን አሳደዋል፣
➢እሳትን ጨብጠዋል፣
➢በክንፍ በረዋል፣
➢ደመናን ዙፋን አድርገዋል።
➢ብዙ ደቀ መዛሙርትን አፍርተው ደብረ ሊባኖስን መሥርተዋል። በዚያም ሴትና ወንድ መነኮሳት እንደ ሕፃናት አብረው ኑረዋል። በዘመናቸው ሰይጣን ታሥሯልና።
#ዕረፍት
➤ ጻድቅ፣ ሰማዕትና ሐዋርያ አቡነ ተክለ ሃይማኖት ብርሃን ሆነው፣ መከራን በብዙ ተቀብለው፣ እልፍ አእላፍ ፍሬን አፍርተው በተወለዱ በ፺፱ ዓመት ከ፰ ወር ከ፩ ቀናቸው ነሐሴ ፳፬ ቀን በ፲፫፻፮ ዓ/ም ዐርፈዋል። ጌታ፣ ድንግል ማርያምና ቅዱሳን ከሰማይ ወርደው ተቀብለዋቸዋል። አሥር ትውልድ የሚያስምር ቃል ኪዳንም ተቀብለዋል።
✥••┈┈••●◉ ✞ ◉●••┈┈••✥
✞✞✞"የፃድቁ አባታችን አቡነ ተክለ ሀይማኖት ረድኤት በረከት ይደርብን ከቃል ኪዳናቸው ያሳትፈን መልካም እለተ ሰንበት።"✞✞✞
✞✞✞✞✞ አሜን ✞✞✞✞✞
✥••┈┈••●◉ ✞ ◉●••┈┈••✥
📖 ወስብሐት ለእግዚአብሔር 📖
📖 ወለወላዴቱ ድንግል 📖
📖 ወለመስቀሉ ክቡር 📖
📖✞✞✞✞✞📖
✞✞✞ ሃሳብ ➢
@gebrye\_comment\_bot
|❀:✧๑ ✞✞✞✞✞✞✞ ๑✧❀|:
✞✞✞ ይቀላቀሉ ➣
@mahteben\_albetsm
††† በስመ አብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ አሐዱ አምላክ አሜን ! †††
#ታህሳስ ፳፫
#ክፍል ፩
#ቅዱስ_ዳዊት_ልበ_አምላክ
#ቅዱስ_መጽሐፍ_እንዲህ_ይላል፦
"እግዚአብሔር ለዳዊት በእውነት ማለ፤ አይጸጸትም።"
መዝሙር . ፻፴፩፥፲፩
➤ አሁን በእግዚአብሔር መጸጸት ኑሮበት አይደለም። ቅዱስ ዳዊት የማያጸጽት ፍጹም ወዳጅ መሆኑን ሲገልጥ ነው እንጂ።
➤ ጌታ ቅዱስ ዳዊትን "እንደ ልቤ የሆነ፣ ፈቃዴን የሚፈጽም፣ ባሪያዬን ዳዊትን አገኘሁት።"
መዝሙር . ፹፰፥፳
ብሎ ሲናገር ሰምተን እጅግ አደነቅን።
እንደ አምላክ ልብ ሆኖ መገኘት ምን ይረቅ?! ምንስ ይደንቅ?! ለዚህ አንክሮ ይገባል!
➤ ጌታ ይቀጥልና ደግሞ "ዳዊትን እንዳልዋሸው አንድ ጊዜ በቅዱስነቴ ማልሁ።" መዝሙር . ፹፰፥፴፭ ይላል።
➤ አቤት አባታችን ዳዊት ክብር፣ የክብር ክብር፣ ውዳሴና ስግደትም ላንተ በጸጋ ይገባል እንላለን። ነቢየ ጽድቅ ቅዱስ ዳዊት ፯ ሃብታት ሲኖሩት፦
፩. #ሃብተ_ትንቢት
፪. #ሃብተ_መንግሥት
፫. #ሃብተ_ክህነት
፬. #ሃብተ_በገና (መዝሙር)
፭. #ሃብተ_ፈውስ
፮. #ሃብተ_መዊዕ (ድል መንሳት) እና
፯. #ሃብተ_ኃይል_ተብለው_ይታወቃሉ።
#በሰባቱ_ስሞቹም፦
፩. #ጻድቅ
፪. #የዋህ
፫. #ንጹሕ
፬. #ብእሴ_እግዚአብሔር
፭. #ነቢየ_ጽድቅ
፮. #መዘምር
፯. #ልበ_አምላክ_ተብሎ_ይጠራል።
➤ ልበ አምላክ ቅዱስ ዳዊት ስለ ልደቱ ሲናገር "እስመ ናሁ በኃጢአት ተጸነስኩ - በኃጢአት ተጸነስኩ።" ይላል።
መዝሙር . ፶፥፭
➤ አበው እንደ ነገሩን የቅዱስ ዳዊት አባት ደጉ እሴይ ከነገደ ይሁዳ የኢዮቤድ ልጅ ነው።
➤ ሚስቱን ሁብሊን አንድ ጐልማሳ በዝሙት ዓይን ሲፈልጋት ተመልክቶ ነበር። አንድ ቀንም መንገድ ሔድኩ ብሎ ግን ያንን ጐልማሳ መስሎ ተመልሶ አብሯት አድሯል። በዚያች ሌሊትም ቅዱስ ዳዊት ተጸንሷልና እንዲህ ብሏል።
➤ ቅዱስ ዳዊት ከሕፃንነቱ ጀምሮ ጸጋ መንፈስ ቅዱስ ያደረበት ነበር። ሕፃን ሳለ በእረኝነት በጐቹን አያስነካም ነበር። አንበሳውን በጡጫ፣ ድቡን በእርግጫ፣ ነብሩን በሩጫ የያዙትን ያስጥላቸው ነበር። በጥቂቱ በበግ እረኝነት ስለ ታመነ ለእስራኤል እረኛ ሊሆን ተመርጧል።
➤ እግዚአብሔር ሳዖልን ከናቀው በኋላ ከእሴይ ልጆች መካከል "እንደ ልቤ የሆነውን ቀብተህ አንግስልኝ።" ቢለው ነቢዩ ሳሙኤል ቤተልሔም ገብቷል።
➤ በዚያም ከኤልያብ እስከ አሚናዳብ ሰባቱን የእሴይን ልጆች ቢፈትን አልሆነም። በቅዱስ ሚካኤል ጠቋሚነት ግን ከእረኝነቱ ዳዊት ተጠራ።
➤ ገና ከርቀት ሲመጣ የዘይት ቀርኑ ቦግ ብሎ ተከፈተ። በቅዱስ ዳዊት ራስ ላይም እንደ እሳት ፈላ። በአምላክ ምርጫም በ፲፪ ዓመቱ ንጉሥ ተባለ።
➤ ኢሎፍላውያን በጠላትነት በተነሱባቸው ጊዜም ጐልያድ የሚሉት የጌት ሰው እስራኤልን ሲያስጨንቅ ለ፵ ቀናት ቆይቶ ነበር።
➤ ለአምላኩ ስምና ክብር የሚቀና ቅዱስ ዳዊት ግን በድፍረት ገጥሞ በፈጣሪው ኃይል በጠጠር ጥሎታል። ከእስራኤልም ሽሙጥን አርቋል። ግን ቅዱሱ ብላቴና፣ ጐልያድ ደግሞ ስድስት ክንድ (ሦስት ሜትር) የሚረዝም ሰው ነበር።
➤ ቅዱስ ዳዊት ንጉሥ እንዲሆን ተቀብቶ ዙፋን አልጠበቀውም። ጠላታቸውን ጥሎ ስላዳናቸው ፈንታ ሳዖልን በገና እየደረደረ ስለ ፈወሰው ፈንታም ሊገደል ተፈለገ።
➤ ፈጣሪው ከእርሱ ጋር ባይሆንም ይገድሉት ነበር። እርሱ ግን ለ፲፰ ዓመታት በትእግስት ተሰደደ። ከአንዴም ሁለት ሦስቴ ጠላቱን ሳዖልን አሳቻ ሥፍራ ላይ አግኝቶ በምሕረት ተወው። በዚህ የዋሕነቱም በብሉይ ሆኖ "ጠላቶቻችሁን ውደዱ።" የምትለውን ሕግ ፈጸማት።
ማቴ . ፯፥፵፭
መዝ. ፲፮፥፬
➤ ቅዱስ ዳዊት የስደት ዘመኑ ሲፈጸም ሳዖል ሞተ። ምን ጠላቱ ቢሆን "የሳዖል ገዳይ ነኝ።" ያለውን ተበቀለ። ስለ ጠላቱም አለቀሰ።
➤ ፴ ዓመት ሲሆነው ነግሦ ለ፯ ዓመታት በኬብሮን ለ፴፫ ዓመታት በኢየሩሳሌም (ጽዮን) ሕዝበ እግዚአብሔርን ጠብቋል።
➤ በዘመኑም ጠላቶቹን ሁሉ ድል አድርጓል። በልጁ አቤሴሎም እጅ መሰደድን በሳሚ ወልደ ጌራ መሰደብንም ታግሷል።
➤ ቅዱሱ ንጉሥ ሁሉ ነገር የተሰጠው አባት ነው። ሁሉ ሕይወቱም ለእኛ ትምህርት ቤት ነው። ሰው ነውና የኦርዮን ሚስት ቀምቶ ኦርዮን አስገድሎ ነበር። ጉዳዩን ነቢዩ ናታን በምሳሌ ሲነግረው ፍጹም ተጸጸተ።
➤ ማቅ ለብሶ አመድ ነስንሶ አለቀሰ። መሬትንም በእንባው ክንድ አራሳት። ሐረግ እስከ ማብቀልም ደረሰ። እግዚአብሔርም ንስሐውን ተቀብሎ ከፍ ከፍ አደረገው። በንስሐ ለምትገኝ ጸጋም ምሳሌ ሆነ።
➤ በቤተ ክርስቲያን ትምህርት ቅዱስ ዳዊትን የሚያህል ነቢይ (ምሥጢር የበዛለት) አልተገኘም። "ከዓለም በፊት እንዲህ ነበረ።" ብሎ ከዚያ ከስነ ፍጥረት እስከ ዳግም ምጽዓት የተናገረ እርሱ ነው።
➤ ስለ መላእክት፣ ነቢያት፣ ሐዋርያት፣ ጻድቃን፣ ሰማዕታት፣ ደናግልና መነኮሳት ሁሉ መናገሩ ይደነቃል። ስለ ድንግል ማርያምና ስለ መድኃኒታችን ክርስቶስም አምልቶ አስፍቶ ተናግሯል።
➤ ፻፶ ምዕራፎች ባሉት መጽሐፈ ትንቢቱ ኃላፍያትንና መጻዕያትን ተመልክቷል።
#ስለዚህ_አበው፦
"አልቦ ምሥጢር ወአልቦ ትንቢት
ዘኢተናገረ አቡነ ዳዊት።" ይላሉ።
➤ ቅዱሱ ነቢይና ንጉሥ በጣም የሚታወቀው በዝማሬው ነው። ለራሱ ባለ ፲ አውታር ለመዘምራኑ ደግሞ ባለ ፰ አውታር በገናን አዘጋጅቶ ፈጣሪውን ያመሰግን ነበር።
➤ ፳፬ ሰዓት ሙሉ ስብሐተ እግዚአብሔር እንዳይቋረጥ ፴፻፹፰ መዘምራንን በአሳፍ መሪነት መድቦ ነበር።
ራሱም በፍጹም ተመስጦ ማር ማር እያለው እግዚአብሔርን ያመሰግነው ነበር። "ቃልህ ለጉሮሮዬ ጣፋጭ ነው።" እንዲል።
መዝ. ፻፲፰፥፻፫
➤ የዳዊት መዝሙሩ ለአጋንንት ትልቅ ጠላት ነው። ቅዱሳን መላእክትም በዳዊት መዝሙር ይዘምራሉ።
"በዘቦቱ ይሴብሑ ሰማያውያን ወምድራውያን" እንዲል።
➤ ቅዱስ ዳዊት ጽዮንን አንጾ ጽላተ ኪዳኑን አመጣ። ለአምላከ ያዕቆብ ማደሪያን ሊፈልግም ዓይኑ ከእንቅልፍ ተከለከለ።
መዝ. ፻፴፩፥፪
➤ የፈጣሪውን ፈቃድ ሊጠይቅ ሱባኤ ቢገባ "አኮ አንተ ዘትነድቅ ሊተ ቤተ - አንተ ሳትሆን የሚሠራልኝ ልጅህ ነው።" አለው።
#ይቀጥላል.....
✥••┈┈••●◉ ✞ ◉●••┈┈••✥
✞✞✞"አምላከ ዳዊት ስለ ከበረው ቃል ኪዳኑ ይማረን። ከንጹሕ አምልኮው ይክፈለን። በዝቶ ከተረፈ በረከቱም አይለየን።"✞✞✞
✞✞✞✞✞ አሜን ✞✞✞✞✞
✥••┈┈••●◉ ✞ ◉●••┈┈••✥
📖 ወስብሐት ለእግዚአብሔር 📖
📖 ወለወላዴቱ ድንግል 📖
📖 ወለመስቀሉ ክቡር 📖
📖✞✞✞✞✞📖
✞✞✞ ሃሳብ ➢
@gebrye_comment_bot
|❀:✧๑ ✞✞✞✞✞✞✞ ๑✧❀|:
✞✞✞ ይቀላቀሉ ➣
@mahteben_albetsm
††† በስመ አብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ አሐዱ አምላክ አሜን ! †††
#ብሥራተ_ገብርኤል
➤ በቤተክርስቲያን አስተምህሮ ታህሳስ ፳፪ ብሥራተ ገብርኤል ይባላል፤ ይህም ቅዱስ ገብርኤል ለእመቤታችን ጌታን እንደምትወልድ ብሥራቱን የነገረበት ቀን ነው።
➤ እንዴት ብሥራቱንማ የነገራት መጋቢት ፳፱ ቀን ነው ካሉ ትክክል ነው፤ ብሥራቱን የነገራት መጋቢት ፳፱ ቀን በዕለተ እሁድ ከቀኑ ፫ ሰዓት ላይ ነው።
#ታዲያ_ዛሬ_ለምን_እናከብረዋለን?
➤ ወርሃ መጋቢት ታላቁ ዓቢይ ጾም የሚውልበት ወር በመሆኑ ቅዱሳን አባቶቻችን እንደዚህ ዓይነት ሥርዓት ሰሩ፦
➢ የመጋቢት ፳፯ ስቅለቱን ጥቅምት ፳፯ ቀን እንዲሁም
➢ የመጋቢት ፭ አቡነ ገብረመንፈስ ቅዱስ እረፍት ቀን ወደ ጥቅምት ፭ ቀን ዞሮ እንዲከበር አደረጉ፡፡
➢ የመጋቢት ፳፱ ብሥራቱን ደግሞ ታሕሳስ ፳፪ ቀን ዞሮ እንዲከበር ያደረገው ታላቁ አባት የጥልጥልያ ኤጲስ ቆጶስ #ደቅስዮስ ይባላል።
➢ በእመቤታች ፍቅር ልቡ የነደደ ታላቅ ጻድቅ ነው የእመቤታችንን ታአምራቷን የሚናገር መጽሐፍ የሰበሰበ አባት ነው፡፡
➢ የጌታን ልደት ከመከበሩ አንድ ሳምንት ቀደም ብሎ ብሥራቱ መከበር አለበት ብሎ ሥርዓት ሰራ። አገሬውንም ሰብስቦ ታላቅ የደስታ በዓል አደረገ።
የዚህ ታላቅ አባት እረፍቱም ታህሳስ ፳፪ በዛሬዋ ቀን ነው።
➢ ደቅስዮስ ሰርቶልን ያለፈውን ስርዓት ቤተክርስቲያን ተቀብላ ይኸው ዛሬም ድረስ ታከብረዋለች።
➢ በተለይም በአዲስ አበባ ብስራተ ገብርኤል ቤተክርስቲያን ታቦተ ህጉ ወጥቶ በደማቁ ተከብሮ ይውላል፡፡
✞
"አብሳሪው መልክ ቅዱስ ገብርኤል ለሁላችህን ብስራቱን ያሰማን ከበዓሉ በረከት ያሳትፈን፡፡"
✞ አሜን ✞
➢ ሀሳብ
✞ @gebrye_comment_bot
➢ ይቀላቀሉ
✞ @mahteben_albetsm
††† በስመ አብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ አሐዱ አምላክ አሜን ! †††
#ታህሳስ ፳፩
#ቅዱስ_በርናባስ_ሐዋርያ
➤ ቅዱሱ ሐዋርያ ስሙ ሲጠራ ሞገስ አለው። የቅዱሱ ሰው የመጀመሪያ ስሙ ዮሴፍ ሲሆን በርናባስ ያለው መድኃኒታችን ክርስቶስ ነው። ትርጉሙም "ወልደ ኑዛዜ - የመጽናናት ልጅ" እንደ ማለት ነው።
➤ በምሥጢሩ ግን "ማሕደረ መንፈስ ቅዱስ - የመንፈስ ቅዱስ ማደሪያ" እንደ ማለት ያስተረጉማል። ቅዱስ በርናባስ ምንም በትውልዱ እስራኤላዊ ቢሆን ተወልዶ ያደገው በቆጵሮስ ነው። እስከ ወጣትነት ጊዜውም የቆየው እዚያው ነው።
➤ የመድኃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስን ሰው የመሆኑ ዜና ሲሰማ ግን ወደ ኢየሩሳሌም መጥቶ መድኅን ክርስቶስን ተመለከተ። ጌታውንም ሊከተል በልቡ ቆረጠ።
➤ የፈጠረን ክርስቶስም እንዲረባ (እንዲጠቅም) አውቆ ስሙን ቀይሮ አስከተለው። ከ፸፪ አርድእትም ደመረው።
ቅዱስ በርናባስ እንደ ወንድሞቹ ሐዋርያት ለ፫ ዓመት ከ፫ ወር ከጌታ እግር ቁጭ ብሎ ተማረ።
➤ ተአምራቱንም ሁሉ ተመለከተ። ከጌታ ዕርገት በኋላ ፻፳ ቤተሰብ በጽርሐ ጽዮን ሲጸልዩም አብሮ ይተጋ ነበር። በጊዜውም አበው ሐዋርያት በይሁዳ ፈንታ ከ፲፩ የሚቆጠረውን ሰው ለመምረጥ ፪ ሰዎችን አቅርበው ነበርና አንዱ ይኸው ቅዱስ ነው። እዚያውም ላይ ጌታችንን ከመጀመሪያው ጀምሮ ማገልገሉ ተመስክሮለታል።
— ሐዋርያት. ፩፥፳፪
➤ ስሙንም ኢዮስጦስ ብለውታል። ባለ ፫ ስም ነበርና። በወቅቱም ዕጣ በቅዱስ ማትያስ ላይ ስለ ወደቀ በርናባስ ከ፸፪ አርድእት ማትያስ ከ፲፪ ሐዋርያት ሆነው ቀጠሉ።
➤ ከዚህ በኋላ ቅዱስ በርናባስ መንፈስ ቅዱስን ተቀብሎ በኃይል ያገለግል ጀመር። የሐዋርያትን ዜና በሚናገር መጽሐፍ ላይ የተጻፉና ስለ ቅዱሱ ማንነት የሚናገሩ ክፍሎችን እንመልከት።
፩. ቅዱሳን ሐዋርያት የእኔ የሚሉት ንብረት ሳይኖራቸው ያላቸውን በጋራ እየተጠቀሙ በፍቅር ይኖሩ ዘንድ የመንፈስ ቅዱስ ትዕዛዝ ነበር። ያለውን ሁሉ ሸጦ በሐዋርያት እግር ላይ በማኖር ደግሞ ቀዳሚውን ሥፍራ ቅዱስ በርናባስ ይይዛል።
— ሐዋርያት. ፬፥፴፮
በዚህም የዘመነ ሐዋርያት የመጀመሪያው መናኝ ተብሏል።
፪. ልሳነ እፍረት (ብርሃነ ዓለም) ቅዱስ ጳውሎስ ባመነ ጊዜ ሐዋርያት ለማመን ተቸግረው ነበር። የሆነውን ሁሉ አስረድቶ ቅዱስ ጳውሎስን ከሐዋርያት ጋር የቀላቀለው ይህ ቅዱስ ነው።
— ሐዋርያት. ፱፥፳፮
፫. አንድ ቀን መንፈስ ቅዱስ "ፍልጥዎሙ ሊተ ለሳውል ወለበርናባስ - በርናባስና ሳውልን (ጳውሎስን) ለዩልኝ።" በማለቱ ሐዋርያት ጾመው ጸልየው እጃቸው ከጫኑባቸው በኋላ ላኳቸው።
— ሐዋርያት. ፲፫፥፩
➤ እነርሱም ወንጌልን እየሰበኩ በየሃገሩ ዞሩ። በሃገረ ልስጥራን መጻጉዕን ስለ ፈወሱ ሕዝቡ "እናምልካችሁ" ብለው የአማልክትን ስም አወጡላቸው። ሁለቱ ቅዱሳን ግን ይህንን ሲሰሙ ልብሳቸውን ቀደው በጭንቅ አስተዋቸው። መመለክ የብቻው የፈጣሪ ገንዘብ ነውና።
— ሐዋርያት. ፲፬፥፰-፲፰
— ዘጸአት . ፳፥፩
፬. በአንጾኪያ የነበሩ አሕዛብ ክርስትናን በተቀበሉ ጊዜ ከሐዋርያት ተልኮ ሒዶ በጐ ጐዳናን መራቸው።
ሐዋ. “ወሬውም በኢየሩሳሌም ባለችው ቤተ ክርስቲያን ስለ እነርሱ ተሰማ፥ በርናባስንም ወደ አንጾኪያ ላኩት፤”
— ሐዋርያት ፲፩፥፳፪
➤ ቅዱስነታቸውን በርናባስ በአገልግሎት ዘመኑ መጀመሪያ ከቅዱስ ጳውሎስ ጋር ቀጥሎ ደግሞ ቅዱስ ማርቆስን አስከትሎ ብዙ አሕጉራትን አስተምሯል። ቆጵሮስም ሃገረ ስብከቱ ናት።
➤ ቅዱሱ ከብዙ ትጋት በኋላ በዚህች ቀን አረማውያንና አይሁድ ገድለውታል። ቅዱስ ማርቆስም ገንዞ ቀብሮታል።
➤ ስለርሱ መጽሐፍ "ደግ መንፈስ ቅዱስ የሞላበት ነው።" ይላልና ክብር ይገባዋል!
“ደግ ሰውና መንፈስ ቅዱስ እምነትም የሞላበት ነበረና። ብዙ ሕዝብም ወደ ጌታ ተጨመሩ።”
— ሐዋርያት. ፲፩፥፳፬
✥••┈┈••●◉ ✞ ◉●••┈┈••✥
✞✞✞"የእስራኤል እረኛ ሥጋችንን ከመቅሰፍት ነፍሳችንን ከገሃነመ እሳት ይጠብቅልን። ከበረከተ ቅዱሳንም ይክፈለን።"✞✞✞
✞✞✞✞✞ አሜን ✞✞✞✞✞
✥••┈┈••●◉ ✞ ◉●••┈┈••✥
📖 ወስብሐት ለእግዚአብሔር 📖
📖 ወለወላዴቱ ድንግል 📖
📖 ወለመስቀሉ ክቡር 📖
📖✞✞✞✞✞📖
✞✞✞ ሃሳብ ➢
@gebrye_comment_bot
|❀:✧๑ ✞✞✞✞✞✞✞ ๑✧❀|:
✞✞✞ ይቀላቀሉ ➣
@mahteben_albetsm
††† በስመ አብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ አሐዱ አምላክ አሜን ! †††
#ታህሳስ ፲፱
#መልአኩ_ቅዱስ_ገብርኤል
➤ ገብርኤል ማለት የእግዚአብሔርን ልጅ የሚመስል ጌታና አገልጋይ ማለት ነው፡፡ ብርሃናዊ መልዓክ ቅዱስ ገብርኤል ፤ ቅዱሳን ሰማዕታት ገድላቸውን እንዲፈፅሙ እሳቱን እና ስለቱን ፈርተው ወደኋላ እንዳይመለሱ ይረዳቸዋል፡፡
➤ከ፯ ሊቃነመላዕክት በተራዳዒነቱና በአማላጅነቱ ያዘኑትን ለማፅናናት ፤ ምስራች ለመናገር ከእግዚአብሄር የሚላከው አንዱና ዋነኛው በእግዚአብሔር ፊት የሚቆመው መልዓክ ቅዱስ ገብርኤል ነው፡፡
➤ ታህሳስ ፲፱ ብርሃናዊው መልዓክ ቅዱስ ገብርኤል ሰለስቱ ደቂቅን ከዕቶን እሳት ያዳነበት ዕለት በመሆኑ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤተክርስቲያን ዓመታዊ በዓል በመባል በፀሎትና በምስጋና በደማቅ ሁኔታ ታከብራለች፡፡
#የታሪኩ_መነሻ . . .
➤ ባቢሎንን ይመራ የነበረው ናቡክደነፆር በእግዚአብሔር የማያምን ጣዖትን የሚያመልክ ንጉስ ነበር፡፡ በወቅቱም ቁመቱ ፷ ወርዱ ፮ ክንድ የሆነውን የወርቅ ምስል በማሰራት ሕዝቡ እንዲሰሩ በማዘዝ ሁሉም ሰው ላሰራው ጣዖት መስገድ እንዳለባቸው ይህን በማይፈፅሙት ላይ ቅጣቱ ከባድ እንደሆነ አዋጅ አሳወጀ፡፡
➤ የንጉሱ አስተሳሰብ ለእግዚአብሔር ወዳጆች ከባድ ፈተና ቢሆንም እውነተኛዎቹን አማኞች ግን በእግዚአብሔር ላይ ያላቸው እምነት ሊቀይረው አልቻለም፡፡ ቅጣቱንም በማሰብ እና በመፍራት ሁሉም እግዚአብሔርን በመካድ ለጣዖቱ ሰገዱ፡፡
➤ በዚህ ፈታኝ ዘመን ነበር አናንያ ፣ አዛርያን እና ሚሳኤል የተባሉ ሶስት ወጣቶች ግን ለእግዚአብሔር ያላቸውን መታመን አሳዩ፡፡
➤ ለጣዖቱ ያልሰገደ ወደ እቶን እሳት ተጥሎ እንደሚሞት ቁርጥ ያለ ወሳኔ እንደሆነ ቢያውቁም ያለምንም ፍርሃት በአንሰግድም አቋማቸው በመፅናት "ንጉስ ሆይ የፈጠረንን አምላካችንን ክደን አንተ ላቆምከው ጣኦት አንሰግድም !" አሉት፡፡
➤ በ፫ ወጣቶች ድርጊትና ድፍረት በጣም የተቆጣው ንጉስ ናቡክደነፆር አገልጋዮቹን ጠርቶ እሳቱ ፯ እጥፍ እንዲነድ ትዕዛዝ ሰጠ፡፡
➤ ወደ እሳቱም እንዲከቷቸው አዘዘ፡፡ የንጉሱ አገልጋዮች ሶስቱን ወጣቶች #አናንያን ፣ #አዛርያን ፣ #ሚሳኤልን እያንከበከቡ ወደ እቶን እሳቱ ወረወሯቸው፡፡
➤ እሳቱ ከነበረው ኃይል የተነሳ ወላፈኑ አገልጋዮቹን እዛው እንደ ማገዶ አነደዳቸው፡፡ ሠለስቱ ደቂቅ ግን ከየት እንደመጣ ካልታወቀ እንግዳ ጋር በመሆን በዕቶን እሳቱ ውስጥ እግዚአብሔርን እያመሰገኑ በደስታ ይመላለሱ ጀመር፡፡
➤ ይህም ተዓምር ንጉሱን እና መኳንንቶቹን እንዴት ሊሆን ቻለ ብለው ተገረሙ፡፡ ንጉሱም በዚህ ወቅት በመደነቅ
" እነሆ እኔ በእሳቱ መካከል የሚመላለሱ አራት ሰዎች ይታዩኛል፡፡ እሳቱ ምንም አልጎዳቸውም ፡፡ አራተኛው ግን የአማልክትን(የእግዚአብሔርን) ልጅ ይመስላል፡፡ " አለ፡፡
➤ ንጉስ ናቡክደነጾር በግልፅ ተመልክቶ እንደመሰከረው የነደደውን እሳት በማብረድ ለሠለስቱ ደቂቅ ቤዛ የሆናቸው ሊቀ መላዕክት ቅዱስ ገብርኤል ነው፡፡
➤ ስለ ሃይማኖታቸው መከራ የተቀበሉን የአግዚአብሔር ወዳጆችን በእምነት የሚያፀና ታላቅ መላዕክት ነው፡፡ ከነደደ እሳት ባልተናነሰ መከራና ችግር ውስጥ ገብተው በቅዱስ ገብርኤል አማላጅነት ከሞት ስጋ ነፍስ ድነው በመልዓኩ ስም በፈለቀ ጸበል ተጠምቀው ደዌ በሽታ ጭንቀትና ሀዘን የራቀላቸው እጅግ ብዙዎች ናቸው፡፡
✥••┈┈••●◉ ✞ ◉●••┈┈••✥
➤ ታኅሣሥ ፲፱ ቀን የሚከበሩ ዓመታዊ የቅዱሳን በዓላት
፩.ቅዱስ ገብርኤል ሊቀ መላእክት
፪.ቅዱስ ዮሐንስ ዘቡርልስ
፫.አቡነ ስነ ኢየሱስ ጻድቅ
††† ወርኀዊ በዓላት
፩.ቅዱስ ኤስድሮስ ሰማዕት
፪.አቡነ ዓቢየ እግዚእ ጻድቅ
፫.አቡነ ዮሴፍ ብርሃነ ዓለም
፬.ቅዱስ ይምርሐነ ክርስቶስ
✥••┈┈••●◉ ✞ ◉●••┈┈••✥
✞✞✞"የመልዓኩ ቅዱስ ገብርኤል ጸጋ እና ምልጃ እንዲሁም ጥበቃ አይለየን። የአናንያን ፣ አዛርያን ፣ ሚሳኤልን ረድኤት በረከት ይደርብን።"✞✞✞
✞✞✞✞✞ አሜን ✞✞✞✞✞
✥••┈┈••●◉ ✞ ◉●••┈┈••✥
📖 ወስብሐት ለእግዚአብሔር 📖
📖 ወለወላዴቱ ድንግል 📖
📖 ወለመስቀሉ ክቡር 📖
📖✞✞✞✞✞📖
✞✞✞ ሃሳብ ➢
@gebrye_comment_bot
|❀:✧๑ ✞✞✞✞✞✞✞ ๑✧❀|:
✞✞✞ ይቀላቀሉ ➣
@mahteben_albetsm
††† በስመ አብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ አሐዱ አምላክ አሜን ! †††
#ታህሳስ ፲፰
#ቅዱስ_ቲቶ_ሐዋርያ
➤ የጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ደቀ መዝሙር ቅዱስ ቲቶ ከ፸፪ አርድእት አንዱ ሲሆን በተወሰነ መንገድም ቢሆን የተዘነጋ ሐዋርያ አይደለም።
➤ በተለይ ደግሞ ቅዱስ ጳውሎስ ከጻፋቸው ፲፬ መልእክታት መካከል አንዷ የተላከችው ለዚህ ቅዱስ በመሆኗ ታሪኩ ባይነገር እንኳ ስሙ አይረሳም። ቅዱስ ጳውሎስም በመልእክታቱ በጐ ስሙን እየደጋገመ ያነሳዋል።
➤ ቅዱስ ቲቶ የተወለደው በአንደኛው መቶ ክፍለ ዘመን እስያ ውስጥ ቀርጤስ በምትባል ከተማ ነው። መዳን በእውቀት ይመስላቸው ስለ ነበር የአካባቢው ሰዎች የግሪክን ፍልስፍና ጠንክረው ይማሩ ነበር።
➤ ቅዱስ ቲቶም በወጣትነቱ ወደ ትምህርት ቤት ገብቶ የግሪክን ፍልሥፍናና የዮናናውያንን ጥበበ ሥጋ ተማረ። በጥቂት ጊዜም የሁሉ የበላይ ሆነ።
➤ ቅዱሱ ምክንያቱን ሳያውቀው ለእኔ ቢጤዎች ያበላ፣ ያጠጣ፣ ይንከባከባቸውም ነበር። እግዚአብሔር ግን የዚህ ቅን ሰው በጐነቱ እንዲሁ እንዲቀር አልወደደምና አንድ ቀን በራእይ ተገለጠለት።
➤ በራእይም አንድ ምንነቱን ያልተረዳው ነገር "ቲቶ ሆይ! ስለ ነፍስህ ድኅነት ተጋደል። ይህ ዓለም ኃላፊ ነው።" ሲለው ሰማ። ከእንቅልፉ ነቅቶ በእጅጉ ደነገጠ። የሚያደርገውንም አጣ። ያናገራቸው ሁሉ ምንም ሊገባቸው አልቻለም።
➤ ድንገት ግን በዚያ ሰሞን ከወደ ኢየሩሳሌም አዲስ ዜና ተሰማ። "ክርስቶስ የሚሉት ኢየሱስ እርሱም የባሕርይ አምላክ የሆነ ወደ ምድር ወርዶ ስለ እግዚአብሔር መንግሥትም እየሰበከ ነው።" ሲሉ ለቲቶ ነገሩት።
➤ "ሌላስ ምን አያችሁ?" አላቸው። "በእጆቹ ድውያን ይፈወሳሉ፣ ሙታን ይነሳሉ፣ እውራን ያያሉ፣ ለምጻሞች ይነጻሉ፣ ሌሎች ብዙ ተአምራትም እየተደረጉ ነው።" አሉት።
➤ የወቅቱ የሃገረ አክራጥስ መኮንን ፈላስፋ ነበርና ስለ ክርስቶስ ሲሰማ ሊመራመር ወደደ።
"ብልህ ጥበበኛ ሰው ፈልጉልኝ።" ብሎ ተከታዮችን ቢልካቸው ከቲቶ የተሻለ በአካባቢው አልነበረምና እርሱኑ አመጡት። መኮንኑ ቲቶን "ነገሩ ትክክል ወይም ስሕተት መሆኑን በጥልቅ መርምረህ ምላሽ አምጣልኝ።" ብሎ ላከው።
➤ ቅዱስ ቲቶም ፈጥኖ ተነስቶ ወደ ኢየሩሳሌም ገሰገሰ። ወደ ከተማዋ እንደገባም ጌታችንን አፈላልጐ አገኘው።
፩. ጌታችን ክርስቶስ በሥልጣነ ቃሉ ደዌያትን ሲያርቅ አጋንንትን ሲያሳድዳቸው ተመልክቶ ይህ ሥራ የፍጡር እንዳልሆነ ተረዳ።
፪. ጌታችን የሚያስተምረው ትምህርት ከግሪክ ፍልሥፍና እጅግ ርቆና መጥቆ አገኘው። ጌታ በጣዕመ ቃሉ የሚያስተምረው ሰማያዊ በዚያ ላይ ዘላለማዊ የሆነ ትምህርት ነው። በራእይ "ስለ ነፍስህ ተጋደል።" ያለው ምሥጢር አሁን ተተረጐመለት።
➤ በዚህ ምክንያትም ጊዜ አላጠፋም። ወዲያውኑ አምኖ ተከታዩ ሆነ። ጌታም ከ፸፪ አርድእት ደመረው። የአክራጥስ መኮንን "ምነው ዘገየህ?" ቢለው ያየውን ሁሉ ጽፎ እንደማይመለስም አክሎ ደብዳቤ ላከለት።
➤ ከዚህ በኋላ ቅዱስ ቲቶ ከጌታችን እግር ለ፫ ዓመታት ተምሮ በበዓለ ፶ መንፈስ ቅዱስን ተቀብሎ በመላው እስያ ወንጌልን ሰብኳል። ቅዱስ ጳውሎስ ባመነ ጊዜ ደግሞ የእርሱ ደቀ መዝሙር ሆኖ ለ፳፭ ዓመታት አስተምሯል።
➤ ቅዱስ ጳውሎስ ሰማዕት ከሆነ በኋላ ደግሞ ወደ አክራጥስ ተመልሶ ሕዝቡን አሳምኖና አጥምቆ ቤተ ክርስቲያንን አንጿል። ዕድሜው በደረሰ ጊዜም መምህራንን፣ ካህናትን ሹሞላቸው ባርኳቸውም ዐርፏል።
➤ ዛሬ ታህሳስ ፲፰ የቅዱሱ ሐዋርያ በዓለ ፍልሠቱ ነው።
✥••┈┈••●◉ ✞ ◉●••┈┈••✥
"የእግዚአብሔር ባሪያና የኢየሱስ ክርስቶስ ሐዋርያ የሆነ ጳውሎስ፥ በእግዚአብሔር ለተመረጡት እምነት እንዲሆንላቸው በዘላለምም ሕይወት ተስፋ እንደ አምልኮት ያለውን እውነት እንዲያውቁ የተላከ፤ ስለዚህም ሕይወት የማይዋሽ እግዚአብሔር ከዘላለም ዘመናት በፊት ተስፋ ሰጠ፥ በዘመኑም ጊዜ፥ መድኃኒታችን እግዚአብሔር እንዳዘዘ፥ ለእኔ አደራ በተሰጠኝ ስብከት ቃሉን ገለጠ፤ በሃይማኖት ኅብረት እውነተኛ ልጄ ለሚሆን ለቲቶ፤ ከእግዚአብሔር አብ ከመድኃኒታችንም ከጌታ ከኢየሱስ ክርስቶስ ጸጋና ምሕረት ሰላምም ይሁን።
----- ቲቶ.፩÷፩-፬
✥••┈┈••●◉ ✞ ◉●••┈┈••✥
✞✞✞"አምላከ አበው ቅዱሳን በመጽናታቸው ያጽናን። ከበረከታቸውም ያድለን መልካም እለተ ሰንበት።"✞✞✞
✞✞✞✞✞ አሜን ✞✞✞✞✞
✥••┈┈••●◉ ✞ ◉●••┈┈••✥
📖 ወስብሐት ለእግዚአብሔር 📖
📖 ወለወላዴቱ ድንግል 📖
📖 ወለመስቀሉ ክቡር 📖
📖✞✞✞✞✞📖
✞✞✞ ሃሳብ ➢
@gebrye_comment_bot
|❀:✧๑ ✞✞✞✞✞✞✞ ๑✧❀|:
✞✞✞ ይቀላቀሉ ➣
@mahteben_albetsm
††† በስመ አብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ አሐዱ አምላክ አሜን ! †††
#ታህሳስ ፲፯
#ክፍል ፪
#ቅዱስ_ሉቃስ_ዘዓምድ
➤ ያ ድንጋይ የሚወጣው በሳምንት አንዴ ለሥጋ ወደሙና ለቁርባን ብቻ ነበር። ማንም ምንም ቢያደርገውም ሆነ ቢናገረው ምንም አይመልስም። ይህም ተጋድሎ "አርምሞና ትዕግስት" ይባላል።
➤ አርምሞ (ዝምታ) አንደበትን መቀደስ ሲሆን ትዕግስት ደግሞ ልብን ጸጥ አድርጐ መቀደስ ነው። ሁለቱ ጸጥ ካሉ ሰውነትም ከኃጢአት ማዕበል ጸጥ ይላልና። የክብር ባለቤት መድኃኒታችን ክርስቶስም በመዋዕለ ስብከቱ ማርያምን "ኃርየት መክፈልተ ሠናየ - በጐ እድልን መረጠች።" ያላት ስለዚህ ሃብቷ እንደ ሆነ መተርጉማን አትተዋል።
(ሉቃ. ፲ ፣ ቅዳሴ ማርያም)
➤ ቅዱስ ሉቃስ በዚህ ሕይወቱ ለሦስት ዓመታት ቆየ። በኋላ አምላክ ቅዱስ መልአኩን ልኮ ወደ ቁስጥንጥንያ መራው። የብርሃን መስቀል እየመራውም ወደ ምሥራቅ ተጓዘ።
➤ በዚያም እስከ ዛሬ ድረስ የሚታወቅበትን ተጋድሎ ጀመረ። ከቁስጥንጥንያ ከተማ አቅራቢያ አንድ ምሰሶ አግኝቶ በላዩ ላይ ወጣ። በዚያም ከእርሱ በፊት የነበሩ ቅዱሳን አባ ስምዖንና አባ አጋቶን ዘዓምድ እንዳደረጉት ያደርግ ጀመር።
➤ በምሰሶው ላይ መቀመጥ ስለ ማይቻል ትልቁና የመጀመሪያው ገድል ያለ ዕረፍት መቆም ነው። በተረፈ ግን ለአካባቢው ምዕመናን መሪ አስተማሪ ነበር። ዝናውን እየሰሙ ሰዎች ከተለያየ አሕጉር ይመጡ ነበር።
➤ ያላመኑትን በስብከቱ ማሳመን ያመኑትንም በምክሩ ማጽናትን ቀጠለ። እርሱ አስተምሮት የማይለወጥ አልነበረም። ምክንያቱም ምሉዓ መንፈስ ቅዱስ (መንፈስ ቅዱስ የመላበት) ነውና አጋንንት በሥፍራው አይቆሙምና።
➤ በጊዜውም ጳጳሳቱም፣ ካህናቱም፣ ሕዝቡም፣ መሳፍንቱም ይወዱት ነበር። ቢያዝኑ አጽናኝ፣ ቢታመሙ ፈዋሽ፣ ከፈጣሪ ቢጣሉ አስታራቂ ነበርና። እንዲህ ባለ ተጋድሎ ቅዱስ ሉቃስ ለአርባ አምስት ዓመታት በምሰሶው ላይ ቆየ። ስለዚህ እስከ ዛሬም ድረስ "ዘዓምድ" እየተባለ ይጠራል።
➤ እግዚአብሔር ሊያሳርፈው በፈለገ ጊዜም ደቀ መዝሙሩን ጠርቶ ወደ ከተማ ላከው። መልእክቱን የሰሙት የቁስጥንጥንያ ከተማ መሳፍንት፣ ጳጳሳት፣ ሕዝቡና ካህናቱ እየተሯሯጡ ቢመጡ ታኅሣሥ ፲፭ ቀን በፍቅር ዐርፎ አገኙት።
➤ እያዘኑ በታላቅ ለቅሶና ዝማሬ ወደ ቁስጥንጥንያ አደረሱት። በዚያም በክብር በዚህች ቀን ከአበው መቃብር ቀበሩት።
ዛሬም ድረስ በአካባቢው ክቡር አባት ነው!
➤ ታኅሣሥ ፲፯ ቀን የሚከበሩ ዓመታዊ የቅዱሳን በዓላት
፩.ቅዱስ ሉቃስ ዘዓምድ
፪.ቅዱስ ናትናኤል ጻማዊ
፫.ቅዱስ ማርቆስ
➤ ወርኀዊ በዓላት
፩.ቅዱስ እስጢፋኖስ ሊቀ ዲያቆናት (ወቀዳሜ ሰማዕት)
፪.ቅዱስ ያዕቆብ ሐዋርያ (ወልደ ዘብዴዎስ)
፫.ቅዱሳን አበው መክሲሞስና ዱማቴዎስ
፬.አባ ገሪማ ዘመደራ
፭.አባ ጰላሞን ፈላሢ
፮.አባ ለትጹን የዋህ
፯.ቅዱስ ኤጲፋንዮስ ሊቅ
፰.ቅድስት ወለተ ጴጥሮስ
✥••┈┈••●◉ ✞ ◉●••┈┈••✥
"ጻድቅ እንደ ዘንባባ ያፈራል። እንደ ሊባኖስ ዝግባም ያድጋል።
በእግዚአብሔር ቤት ውስጥ ተተክለዋል።
በአምላካችንም አደባባይ ውስጥ ይበቅላሉ። ያን ጊዜ በለመለመ ሽምግልና ያፈራሉ። ደስተኞችም ሆነው ይኖራሉ።"
-----መዝሙር ፺፩፥፲፪-፲፬
✥••┈┈••●◉ ✞ ◉●••┈┈••✥
✞✞✞"አምላከ ቅዱስ ሉቃስ መካሪ ዘካሪ አባቶችን አያሳጣን። ከቅዱሱ በረከትም ያሳትፈን።"✞✞✞
✞✞✞✞✞ አሜን ✞✞✞✞✞
✥••┈┈••●◉ ✞ ◉●••┈┈••✥
📖 ወስብሐት ለእግዚአብሔር 📖
📖 ወለወላዴቱ ድንግል 📖
📖 ወለመስቀሉ ክቡር 📖
📖✞✞✞✞✞📖
✞✞✞ ሃሳብ ➢
@gebrye_comment_bot
|❀:✧๑ ✞✞✞✞✞✞✞ ๑✧❀|:
✞✞✞ ይቀላቀሉ ➣
@mahteben_albetsm
††† በስመ አብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ አሐዱ አምላክ አሜን ! †††
#ታህሳስ ፲፮
#አቡነ_ዘርዓ_ቡሩክ
➤ ሃገራችን ኢትዮጵያ ብሉይ ከሐዲስ ያልጐደለባት፣ በክርስቶስና በድንግል እናቱ ኪደተ እግር የተቀደሰች፣ የቅዱሳን መጠጊያ እና ብዙ ቅዱሳንን ከእቅፏ ያፈራች ስለ ሆነች የተባረከች ሃገር ትባላለች።
➤ ሁሉም የሃገራችን ክፍሎች ቅዱሳንን አፍርተዋል። በምሥራቅም፣ በምዕራብም፣ በሰሜንም፣ በደቡብም ያሉ አካባቢዎች ሁሉ የቅዱሳን ቤቶች ናቸው። ቅዱሳንን በብዛት ካፈሩ አካባቢዎች አንዱ ደግሞ ምድረ ጐጃም ነው።
➤ በጐጃም አካባቢ ከተነሱ ቅዱሳን ደግሞ አንዱና ስመ ጥሩ ጻድቅ አቡነ ዘርዓ ቡሩክ ናቸው። አቡነ ዘርዓ ቡሩክ በብዙ ጐዳና የተለዩ አባት ናቸው።
#ለመጥቀስ_ያህል_እንኳን፦
፩. በታሪክ ዓለምን ከበው የያዙ ሁለቱ ግሩማን አራዊት (ብሔሞትና ሌዋታንን) ጥርስ ቆጥረው ብዙ ምሥጢራትንም ተመልክተው ተመልሰዋል። (በነገራችሁ ላይ ይህ ጉዳይ ዛሬም ድረስ ሳይንሱ በብዙ ድካም ያልደረሰበት ነው።)
፪. ጻድቁ በልደታቸው ጊዜ ዓይነ ስውራንን አብርተዋል። ለራሳቸው ግን ይህን የግፍ ዓለም ላለማየት ጸልየው ዓይናቸው እንዲጠፋ አድርገዋል።
፫. መጽሐፍ ቅዱስ እንደሚል ቅዱስ ኢያሱ በገባኦን ፀሐይን አቁሟል። ዘርዓ ቡሩክ ግን በጥበበ እግዚአብሔር ፀሐይን ለ፭ አመታት አቁመዋል።
፬. ጻድቁ ከንጽሕናቸው ብዛት ፲፪ ክንፍ (መንፈሳዊ ክንፍ) ተሰጥቷቸው ነበር። ከዚህ በተረፈም በጾም፣ በጸሎት፣ በትሕርምትና በስብከተ ወንጌል ፍጹም ጽሙድ ነበሩ።
➤ ጻድቁ የተወለዱት በአሥራ ስድስተኛው መቶ ክፍለ ዘመን እዚያው ጐጃም ውስጥ ሲሆን አባታቸው ደመ ክርስቶስ እናታቸው ደግሞ ማርያም ሞገሳ ይባላሉ።
➤ ወላጆቻቸው በልጅ እጦት ተማለው እኒህን የተቀደሱ ፍሬ አገኙ። "ጸጋ ኢየሱስ" ብለዋቸዋል። ከኢየሱስ ክርስቶስ ተሰጥተዋቸዋልና::
➤ ቀጥሎ የወለዱትንም "ተስፋ ኢየሱስ" ብለውታል። ይህም የጻድቁ ታናሽ ወንድም ነው። በሒደት ግን የጸጋ ኢየሱስ ስም በፈቃደ እግዚአብሔር ወደ ዘርዓ ቡሩክነት ተቀይሯል።
➤ ጻድቁን ስመ ጥር ካደረጓቸው ሥራዎቻቸው መካከል በአፄ ሱስንዮስ ዘመን የሠሩት ቅድሚያውን ይወስዳል።
#ነገሩ_እንዲህ_ነው፦
➤ በ፲፭፻፺፰ ዓ/ም በኢትዮጵያ ላይ የነገሡት አፄ ሱስንዮስ ጴጥሮስ (ፔድሮ) ፓኤዝ ከሚባል ፈረንጅ መናፍቅ ጋር በፈጠሩት ወዳጅነት ሃይማኖታቸውን ለወጡ። ካቶሊክ (ሮማዊም) ሆኑ።
➤ በኋላም አልፎንሱ ሜንዴዝ የሚሉት እሾህ መጥቶ ሁሉም የኢትዮጵያ ሕዝብ መናፍቅ እንዲሆን ከንጉሡ ጋር መከረ። ለጊዜው በቤተ መንግሥቱ አካባቢ የነበሩ መሣፍንት ተቀላቀሉ። እየቆየ ግን ዜናው በመላ ሃገሪቱ ተሰማ።
➤ በተለይ በ፲፮፻፲፩ ዓ/ም በተዋሕዶ አማኞችና በመናፍቁ ንጉሥ መካከል ነገሩ ተካሮ ጳጳሱ አቡነ ስምዖን ጠዳ ላይ መገደላቸው ተሰማ። በዚህ ጊዜ ገበሬው ከእርሻው፣ ሴቷ ከማዕድ ቤት፣ ካህኑ ከመቅደሱ፣ ነጋዴው ከገበያው እየወጡ ስለ ቀናችው ሃይማኖት ደማቸውን አፈሰሱ።
➤ በበዓት የተወሰኑ በሺህ የሚቆጠሩ ቅዱሳንም ወጥተው ተሰየፉ። በዚህ ጊዜም የግሺው አቡነ ዘርዓ ቡሩክ ዳዊታቸውን አንግበው ለሰማዕትነት ሔዱ። ዓባይ ወንዝ ላይ ሲደርሱ ዳዊታቸውን ወደ ወንዙ ውስጥ ጣሉት።
➤ ተሻግረውም ከንጉሡ አደባባይ ደንቀዝ ደረሱ። በጊዜውም ልክ እንደነ ፍቅርተ ክርስቶስና ወለተ ጴጥሮስ እርሳቸውም መከራ ደረሰባቸው።
➤ ንጉሡም ሳይገደሉ እንዲታሠሩ አደረገ። በጨለማ እስር ቤትም ፭ ዓመታትን ሲያሳልፉ ትኩስ ምግብን ያመጡላቸው ነበር።
➤ እርሳቸው ግን ምግባቸው ሰማያዊ ነበርና አልነኩትም። ከ፭ ዓመታት በኋላም ያ ሁሉ ምግብ በተአምራት በትኩስነቱ እየጨሰ ተገኝቷል። ዘርዓ ቡሩክም ከእሥር ተፈትተዋል።
➤ እግዚአብሔርም በከሐዲው ንጉሥ ላይ ፈርዶ ፋሲል ነግሷል፤ ሃይማኖት ተመልሷል። ጻድቁም በዓባይ ወንዝ ላይ የጣሉት ዳዊታቸውን ሳይርስ አግኝተውታል።
➤ ጐጃም ሲደርሱም ሰይጣን እርሳቸውን መስሎ ሲያስት ስላገኙት ወደ ጥልቁ አስጥመውታል። በተረፈ ዘመናቸው አቡነ ዘርዓ ቡሩክ ብዙ ተጋድለው ጥር ፲፫ ቀን ዐርፈዋል።
➤ ታኅሣሥ ፲፫ ቀን ልደታቸው ነው።
ድንቅ ሠሪ አባት ናቸውና ዛሬም በግሺ ብዙ ተአምራት ይደረጋሉ!
✞✞✞"የአባታችን አቡነ ዘርዓ ቡሩክ ረድኤት በረከት ይደርብን።"✞✞✞
✞✞✞✞✞ አሜን ✞✞✞✞✞
✥••┈┈••●◉ ✞ ◉●••┈┈••✥
📖 ወስብሐት ለእግዚአብሔር 📖
📖 ወለወላዴቱ ድንግል 📖
📖 ወለመስቀሉ ክቡር 📖
📖✞✞✞✞✞📖
✞✞✞ ሃሳብ ➢
@gebrye_comment_bot
|❀:✧๑ ✞✞✞✞✞✞✞ ๑✧❀|:
✞✞✞ ይቀላቀሉ ➣
@mahteben_albetsm
††† በስመ አብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ አሐዱ አምላክ አሜን ! †††
#ኃጥያትን_ስትሠራ፦ መዝሙረ ዳዊት ፶፩ አንብብ፣
መዝሙር ፶፩÷፩-፲፱
"አቤቱ፥ እንደ ቸርነትህ መጠን ማረኝ፤ እንደ ምሕረትህም ብዛት መተላለፌን ደምስስ። ከበደሌ ፈጽሞ እጠበኝ፥ ከኃጢአቴም አንጻኝ፤ እኔ መተላለፌን አውቃለሁና፥ ኃጢአቴም ሁልጊዜ በፊቴ ነውና። አንተን ብቻ በደልሁ፥ በፊትህም ክፋትን አደረግሁ፥ በነገርህም ትጸድቅ ዘንድ በፍርድህም ንጹሕ ትሆን ዘንድ። እነሆ፥ በዓመፃ ተፀነስሁ፥ እናቴም በኃጢአት ወለደችኝ። እነሆ፥ እውነትን ወደድህ፤ የማይታይ ስውር ጥበብን አስታወቅኸኝ። በሂሶጵ እርጨኝ፥ እነጻማለሁ፤ እጠበኝ፥ ከበረዶም ይልቅ ነጭ እሆናለሁ። ሐሤትንና ደስታን አሰማኝ፥ የሰበርሃቸውም አጥንቶቼ ደስ ይላቸዋል። ከኃጢአቴ ፊትህን መልስ፥ በደሌንም ሁሉ ደምስስልኝ። አቤቱ፥ ንጹሕ ልብን ፍጠርልኝ፥ የቀናውንም መንፈስ በውስጤ አድስ። ከፊትህ አትጣለኝ፥ ቅዱስ መንፈስህንም ከእኔ ላይ አትውሰድብኝ። የማዳንህን ደስታ ስጠኝ፥ በእሽታ መንፈስም ደግፈኝ። ለሕግ ተላላፎች መንገድህን አስተምራለሁ፥ ኃጢአተኞችም ወደ አንተ ይመለሳሉ። የመድኃኒቴ አምላክ እግዚአብሔር ሆይ፥ ከደም አድነኝ፥ አንደበቴም በአንተ ጽድቅ ትደሰታለች። አቤቱ፥ ከንፈሮቼን ክፈት፥ አፌም ምስጋናህን ያወራል። መሥዋዕትን ብትወድድስ በሰጠሁህ ነበር የሚቃጠለውም መሥዋዕት ደስ አያሰኝህም። የእግዚአብሔር መሥዋዕት የተሰበረ መንፈስ ነው፥ የተሰበርውንና የተዋረደውን ልብ እግዚአብሔር አይንቅም። አቤቱ፥ በውዴታህ ጽዮንን አሰማምራት፤ የኢየሩሳሌምንም ቅጽሮች ሥራ። የጽድቁን መሥዋዕት መባውንም የሚቃጠለውንም መሥዋዕት በወደድህ ጊዜ፥ ያን ጊዜ በመሠዊያህ ላይ ፍሪዳዎችን ይሠዋሉ።"
#አደጋ_ሲያጋጥምህ፦ መዝሙረ ዳዊት ፺፩ አንብብ፣
መዝሙር ፺፩÷፩-፲፮
"በልዑል መጠጊያ የሚኖር ሁሉን በሚችል አምላክ ጥላ ውስጥ ያድራል። እግዚአብሔርን፦ አንተ መታመኛዬ ነህ እለዋለሁ፤ አምላኬና መሸሸጊያዬ ነው፥ በእርሱም እታመናለሁ። እርሱ ከአዳኝ ወጥመድ ከሚያስደነግጥም ነገር ያድንሃልና። በላባዎቹ ይጋርድሃል፥ በክንፎቹም በታች ትተማመናለህ፤ እውነት እንደ ጋሻ ይከብብሃል። ከሌሊት ግርማ፥ በቀን ከሚበርር ፍላጻ፥ በጨለማ ከሚሄድ ክፉ ነገር፥ ከአደጋና ከቀትር ጋኔን አትፈራም። በአጠገብህ ሺህ በቀኝህም አሥር ሺህ ይወድቃሉ፤ ወደ አንተ ግን አይቀርብም። በዓይኖችህ ብቻ ትመለከታለህ፥ የኃጥኣንንም ብድራት ታያለህ። አቤቱ፥ አንተ ተስፋዬ ነህና፤ ልዑልን መጠጊያህ አደረግህ። ክፉ ነገር ወደ አንተ አይቀርብም፥ መቅሠፍትም ወደ ቤትህ አይገባም። በመንገድህ ሁሉ ይጠብቁህ ዘንድ መላእክቱን ስለ አንተ ያዝዛቸዋልና፤ እግርህም በድንጋይ እንዳትሰናከል በእጆቻቸው ያነሡሃል። በተኵላና በእባብ ላይ ትጫማለህ፤ አንበሳውንና ዘንዶውን ትረግጣለህ። በእኔ ተማምኖአልና አስጥለዋለሁ፤ ስሜንም አውቆአልና እጋርደዋለሁ። ይጠራኛል እመልስለትማለሁ፥ በመከራውም ጊዜ ከእርሱ ጋራ እሆናለሁ፤ አድነዋለሁ አከብረውማለሁ። ረጅምን ዕድሜ አጠግበዋለሁ፥ ማዳኔንም አሳየዋለሁ።
#ሰዎች_ቢያሳዝኑህ፦ መዝሙረ ዳዊት ፳፯ አንብብ
መዝሙር ፳፯÷፩-፲፬
"እግዚአብሔር ብርሃኔና መድኃኒቴ ነው፤ የሚያስፈራኝ ማን ነው? እግዚአብሔር የሕይወቴ መታመኛዋ ነው፤ የሚያስደነግጠኝ ማን ነው? ክፉዎች፥ አስጨናቂዎቼ ጠላቶቼም፥ ሥጋዬን ይበሉ ዘንድ በቀረቡ ጊዜ፥ እነርሱ ተሰናከሉና ወደቁ። ሠራዊትም ቢሰፍርብኝ ልቤ አይፈራም፤ ሰልፍም ቢነሣብኝ በዚህ እተማመናለሁ። እግዚአብሔርን አንዲት ነገር ለመንሁት እርስዋንም እሻለሁ፤ በሕይወቴ ዘመን ሁሉ በእግዚአብሔር ቤት እኖር ዘንድ፥ እግዚአብሔርን ደስ የሚያሰኘውንም አይ ዘንድ፥ መቅደሱንም እመለከት ዘንድ። በመከራዬ ቀን በድንኳኑ ሰውሮኛልና፥ በድንኳኑም መሸሸጊያ ሸሽጎኛልና፥ በዓለት ላይ ከፍ ከፍ አድርጎኛልና። እነሆ፥ አሁን በዙሪያ ባሉ በጠላቶቼ ላይ ራሴን ከፍ ከፍ አደረገ፤ በድንኳኑም የእልልታ መሥዋዕትን ሠዋሁ፥ ለእግዚአብሔር እቀኛለሁ እዘምርለትማለሁ። አቤቱ፥ ወደ አንተ የጮኽሁትን ቃሌን ስማኝ፤ ማረኝና አድምጠኝ። አንተ ፊቴን እሹት ባልህ ጊዜ፦ አቤቱ፥ ፊትህን እሻለሁ ልቤ አንተን አለ። ፊትህን ከእኔ አትሰውር፥ ተቈጥተህ ከባሪያህ ፈቀቅ አትበል፤ ረዳት ሁነኝ፥ አትጣለኝም፥ የመድኃኒቴም አምላክ ሆይ፥ አትተውኝ። አባቴና እናቴ ትተውኛልና፥ እግዚአብሔር ግን ተቀበለኝ። አቤቱ፥ መንገድህን አስተምረኝ፥ ስለ ጠላቶቼም በቀና መንገድ ምራኝ። የሐሰት ምስክሮችና ዓመፀኞች ተነሥተውብኛልና ለጠላቶቼ ፈቃድ አትስጠኝ። የእግዚአብሔርን ቸርነት በሕያዋን ምድር አይ ዘንድ አምናለሁ። እግዚአብሔርን ተስፋ አድርግ፤ በርታ፥ ልብህም ይጽና፤ እግዚአብሔርን ተስፋ አድርግ።"
✥••┈┈••●◉ ✞ ◉●••┈┈••✥
📖 ወስብሐት ለእግዚአብሔር 📖
📖 ወለወላዴቱ ድንግል 📖
📖 ወለመስቀሉ ክቡር 📖
📖✞✞✞✞✞📖
✞✞✞ ሃሳብ ➢
@gebrye_comment_bot
|❀:✧๑ ✞✞✞✞✞✞✞ ๑✧❀|:
✞✞✞ ይቀላቀሉ ➣
@mahteben_albetsm
††† በስመ አብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ አሐዱ አምላክ አሜን ! †††
#ታህሳስ ፲፪
#ቅዱሳን_አንቂጦስ_ወፎጢኖስ
➤ እነዚህ ቅዱሳን በሥጋ ወንድማማቾች ሲሆኑ የዘመነ ሰማዕታት ፍሬዎች ናቸው። ዜና ሕይወታቸውን ሳስበው ይገርመኛል። በእሳት የወጣትነት ዘመናቸው በሃይማኖት ጸንተው ፍቅረ ክርስቶስ እንደ እሳት በላያቸው ላይ ይነድ ነበር።
➤ በእውነት ክርስቶስን በከንፈር ያይደለ በፍጹም ልቡና መውደድ እንዴት ያለ መታደል ነው! ክርስቶስን የወደደ የድንግል እናቱና የቅዱሳን ወዳጆቹ ፍቅር ይበዛለታል እንጂ አይቀንስበትም።
➤ ቅዱሳኑ አንቂጦስና ፎጢኖስ ወጣትነት የዓለም ኑሮ ሳያታልላቸው ለሰማዕትነት ራሳቸውን አዘጋጁ። እንኳን ሰውን አራዊትን የሚያስበረግግ የስቃይ ዓይነት ተሰልፎ ሳለ በፍጹም አልደነገጡም።
➤ መጀመሪያ አንቂጦስን አቀረቡት። ገረፉት፤ ምንም አልሆነም። በእሳት አቃጠሉት፤ ምንም አልነካውም። ለአንበሳ ሰጡት፤ እነርሱ ግን ሰገዱለት። ከዳር ሆኖ ይህንን ሁሉ ሲመለከት የነበረው ወንድሙ ፎጢኖስ ዘሎ ወደ መከራ አደባባይ ገባ።
➤ "ወንድሜ የክርስቶስ ነውና መቼም አታሸንፈውም።" ሲል ጮኸ። በዚህ ጊዜም በሥፍራው የነበሩ ብዙ አሕዛብ "የእነዚህ ወጣቶች አምላክ አምላካችን ነው።" አሉ። መኮንኑም ሁለቱን ቅዱሳን ከብዙ ሕዝብ ጋር አሰይፏቸዋል።
➤ እንደ እኔ ያለ ኃጢአተኛም በስማቸው እንዲህ ሊጸልይ ይገባል፦
"ሰላም ዕብል ለአንቂጦስ ማኅበሮ
እለ በእሳት ፈጸሙ ረዊጸ ወተባድሮ
ያብጽሑኒ እሉ ምስለ መላእክት ድርገተ ዘምሮ
ህየ አኀሉ ወሬዛ ነዳየ ኩሉ አዕምሮ
ኀበ ይዘብጣ ደናግል ከበሮ።"
(አርኬ)
✥••┈┈••●◉ ✞ ◉●••┈┈••✥
➤ ታኅሣሥ ፲፪ ቀን የሚከበሩ ዓመታዊ የቅዱሳን በዓላት
፩.አቡነ ሳሙኤል ዘዋልድባ
፪.ቅዱሳን አንቂጦስ ወፎጢኖስ (ሰማዕታት)
፫.አባ ነድራ
፬.ቅዱስ ዮሐንስ ተአማኒ
፭.ጉቡዓን ኤጲስ ቆጶሳት
➤ ወርኀዊ በዓላት
፩.ቅዱስ ሚካኤል ሊቀ መላእክት
፪.ቅዱስ ላሊበላ ጻድቅ (ንጉሠ ኢትዮጵያ)
፫.ቅዱስ ዮሐንስ አፈ ወርቅ
፬.ቅዱስ ቴዎድሮስ ምሥራቃዊ (ሰማዕት)
፭.ቅድስት ክርስቶስ ሠምራ
፮.ቅዱስ ማቴዎስ ሐዋርያ
፯.ቅዱስ ድሜጥሮስ ሊቅ
✥••┈┈••●◉ ✞ ◉●••┈┈••✥
✞✞✞"የቅዱሳን አንቂጦስ ወፎጢኖስ ረድኤት በረከታቸው ይደርብን።"✞✞✞
✞✞✞✞✞ አሜን ✞✞✞✞✞
✥••┈┈••●◉ ✞ ◉●••┈┈••✥
📖 ወስብሐት ለእግዚአብሔር 📖
📖 ወለወላዴቱ ድንግል 📖
📖 ወለመስቀሉ ክቡር 📖
📖✞✞✞✞✞📖
✞✞✞ ሃሳብ ➢
@gebrye_comment_bot
|❀:✧๑ ✞✞✞✞✞✞✞ ๑✧❀|:
✞✞✞ ይቀላቀሉ ➣
@mahteben_albetsm