ታላቅ የንግስ መንፈሳዊ ጉዞ
ወደ
#ጅሩ_ቅድስት_አርሴማ_ገዳም
መነሻ 28/01/2016
መመለሻ 30/01/2016
የጉዞ ዋጋ ማረፊያ ቤት ጨምሮ 800 ብር
እና
#ዝቋላ_አቦ_ገዳም
መነሻ 04/02/2016
መመለሻ 05/02/2016
የጉዞ ዋጋ 500 ብር
0919811336
0910670054
0913003625
0919811101
አዘጋጅ
የየረር ጎሮ ደብረ ምሕረት ቅዱስ ገብርኤል
ፈለገ ሕይወት ሰንበት ትምህርት ቤት
††† በስመ አብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ አሐዱ አምላክ አሜን ! †††
ግንቦት
#እንኳን_ለደብረ_ምጥማቅ_ቅድስት_ድንግል_ማርያም_አመታዊ_በዓል_በሰላም_አደረሳቹ_አደረሰን።
#ደብረ ምጥማቅ
➤የአርያም ንግሥት የሰማይና የምድር እመቤት የሰውነታችንም መመኪያ ቅድስት ድንግል ማርያም በዚህች ዕለት በምድረ ግብጽ ለተከታታይ ቀናት ተገልጻለች።
#ጥንተ_ነገሩስ_እንደ_ምን_ነው_ቢሉ፦
➤ ለስም አጠራሩ ስግደት ይሁንና ጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ወደ ምድረ ግብጽና ኢትዮጵያ በተሰደደ ጊዜ ከድንግል እናቱ፣ ከዮሴፍና ሰሎሜ ጋር ዛሬ ደብረ ምጥማቅ በሚባለው ቦታ ላይ ዐርፎ ነበር።
➤ ቦታውን ባርኮ ለዘላለም ያንቺ መገለጫ ይሁን ብሎም ቃል ኪዳን ገብቶላት ነበር።
➤ ጊዜው በደረሰ ሰዓት ደብረ ምጥማቅ ተገድሞ የበርካታ መነኮሳት ቤት ሆነ። እመቤታችንም በልጇ ፈቃድ ግንቦት ፳፩ ቀን አእላፍ መላእክትን፣ ጻድቃን ሰማዕታትን አስከትላት መጣች።
➤ በዚያ ሕዝበ ክርስቲያንም አሕዛብም ተሰብስበው ለአምስት ቀናት ከእመ ብርሃን ጋር ይሰነብታሉ። እንግዲህ ልብ በሉት እንኳን የአርያም ንግሥት የአምላክ እናቱ እመቤታችንን ይቅርና በዚህ ዓለም ሰይጣን ቤቱ ያደረጋቸውን የመዝናኛው ኢንዳስትሪ ዝነኛ ሰዎችን ለማየት የዘመናችን ሰው እንዴት እንደሚቸኩል።
➤ እመቤታችንን በአካል መመልከት አይደለም ስሟን መጥራት ነፍስን ከሥጋ መለየት የሚችል ጣዕምና ደስታ አለው። ባይሆን ይሔ ለሚገባውና ላደለው ብቻ ነው።
➤ የደብረ ምጥማቅና የአካባቢዋ ሰዎች ከእመቤታችን ጋር የሚቆዩባቸው ቀናት የዘላለም የሕይወት ስንቅ የሚይዙባቸው ናቸው። ፈልገው የሚያጡት ጠይቀው የማይፈጸምላቸው ምንም ነገር አልነበረም። ነቢያት፣ ሐዋርያት፣ ጻድቃን፣ ሰማዕታት፣ ደናግል፣ መነኮሳት፣ መላእክትና ሊቃነ መላእክት ለድንግል ማርያም ሲሰግዱ ይታዩ ነበርና።
➤ እመ ብርሃንም እየመላለሰች ትባርካቸው ነበር። እነዚያ እርሷን ያዩ ዓይኖች፣ በፊቷ የቆሙ እግሮች ክብር ይገባቸዋል። አምስቱ ዕለታት ሲፈጸሙ ሕዝቡ እመቤታችንን በዕንባ ይሰናበቷታል። እመ ብርሃንም በብርሃን መስቀል ባርካቸው ከቅዱሳኑ ጋር ታርጋለች።
✥••┈┈••●◉ ✞ ◉●••┈┈••✥
#ለአባት_እናቶቻችን_የተገለጠች_እመቤታችን_ለእኛም_በረድኤት_ትገለጽልን_ጣዕመ_ስሟ_በአንደበታችን_ጣዕመ_ፍቅሯ_በልባችን_ይደርብን።
✞✞✞✞✞ አሜን ✞✞✞✞✞
📖 ወስብሐት ለእግዚአብሔር 📖
📖 ወለወላዴቱ ድንግል 📖
📖 ወለመስቀሉ ክቡር 📖
📖✞✞✞✞✞📖
✞✞✞ ሃሳብ ➢
@gebrye_comment_bot
|❀:✧๑ ✞✞✞✞✞✞✞ ๑✧❀|:
✞✞✞ ይቀላቀሉ ➣
@mahteben_albetsm
ዉድ እህት ወንድሞቼ እንኳን ለዓብይ ፆም(ፆመ ሁዱዴ)በሠላም አደረሣችሁ በማወቅና ባለማወቅ ካስቀየምኳችሁ በእግዚአብሔር ስም ይቅር በሉኝ ፆሙን በሠላም አስጀምሮ በሰላም ያሰፈጽመን
Читать полностью…††† በስመ አብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ አሐዱ አምላክ አሜን ! †††
#እስካሁን_ዘጠና_ዘጠኝ_ሰዎች_ገድያለሁ_አንተ_መቶኛው_ትሆናለህ
➢ አንድ ካህን በሞቃታማ ዕለት ብቻቸውን ጭር ባለ ጎዳና ላይ ሲሔዱ አንድ መሣሪያ ያነገተ የሚያስፈራ ሰው ድንገት ከዛፎች መሃል ዘልሎ ወጣና ከፊታቸው ቆመ።
➢ ቄሱ ላይ አፍጥጦ "እስካሁን ዘጠና ዘጠኝ ሰዎች ገድያለሁ አንተ መቶኛው ትሆናለህ!" አላቸው።
➢ ካህኑም መልሰው "ለመሞት ዝግጁ ነኝ ፣ ነገር ግን በጣም ስለጠማኝ ትንሽ ውኃ ሥጠኝና ትገድለኛለህ" አሉት። ነፍሰ ገዳዩ ለአፍታ ግራ ከተጋባ በኋላ በቄሱ ላይ መሣሪያውን እንደደገነ በዛፎቹ መካከል ካለው ምሽጉ ውስጥ በኩባያ ውኃ አምጥቶ እንዲጠጡ ሠጣቸው።
➢ ካህኑ ውኃውን እየጠጡ እያለ ግን ሽፍታው ድንገት በልብ ድካም ሕይወቱ አለፈች።
➢ የዚህን ሰው ነፍስ ወደ ገነት ለመውሰድ መላእክት በመጡ ጊዜ አጋንንት ነፍሱ የእኛ ፈንታ ናት ብለው ተከራከሯቸው። "ይህ ሰው ዘጠና ዘጠኝ ሰዎችን የገደለ ሲሆን እጅግ ብዙ ትንንሽ ኃጢአቶችንም ፈጽሟል። ነፍሱ የሚገባው ለእኛ ነው" አሉ።
➢ መላእክቱ ግን እንዲህ ብለው ለአጋንንቱ መለሱላቸው "ያደረገው እንዳለ ሆኖ ይህ ሰው ከሠራቸው ኃጢአቶች የበለጠ የሚመዝኑ በክርስቶስ ወንጌል የታዘዙ ሁለት ታላላቅ ተግባራትን ፈጽሟል። የመጀመሪያው ዘጠና ዘጠኝ ሰው እንደገደለ ለካህን መናዘዙ ሲሆን ሁለተኛው ለተጠማ ውኃ ማጠጣቱ ነው!" አሏቸው።
*➢ የትኛውንም ያህል ቢደጋገም እንኳን ከእግዚአብሔር ምሕረት ሊበልጥ የሚችል ኃጢአት የለም!_
➢ ቅዱስ ኒኮላይ ቬሊሚሮቪች (St. Nicholai Velimirovich)
ምንጭ: Anicent Christian Wisdom
ትርጉም: ዲያቆን ሄኖክ ኃይሌ
“በዚያም ወራት መጥምቁ ዮሐንስ፦ መንግሥተ ሰማያት ቀርባለችና ንስሐ ግቡ ብሎ በይሁዳ ምድረ በዳ እየሰበከ መጣ።”
— ማቴዎስ ፫÷*፪
✥••┈┈••●◉ ✞ ◉●••┈┈••✥
#እግዚያብሄር_አምላክ_ለንስሀ_ያብቃን
*✞✞✞✞✞ አሜን ✞✞✞✞✞_
✥••┈┈••●◉ ✞ ◉●••┈┈••✥
📖 ወስብሐት ለእግዚአብሔር 📖
📖 ወለወላዴቱ ድንግል 📖
📖 ወለመስቀሉ ክቡር �*�
📖✞✞✞✞✞📖
✞✞✞ ሃሳብ ➢
@gebrye_comment_bot
|❀:✧๑ ✞✞✞✞✞✞✞ ๑✧❀|:
✞✞✞ ይቀላቀሉ ➣
@mahteben_albetsm
††† በስመ አብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ አሐዱ አምላክ አሜን ! †††
#ግንቦት_፳፩
#ደብረ_ምጥማቅ
➢ የአርያም ንግሥት የሰማይና የምድር እመቤት የሰውነታችንም መመኪያ ቅድስት ድንግል ማርያም በዚህች ዕለት በምድረ ግብጽ ለተከታታይ ቀናት ተገልጻለች።
#ጥንተ_ነገሩስ_እንደ ምንነውቢሉ፦
➢ ለስም አጠራሩ ስግደት ይሁንና ጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ወደ ምድረ ግብጽና ኢትዮዽያ በተሰደደ ጊዜ ከድንግል እናቱ፣ ከዮሴፍና ሰሎሜ ጋር ዛሬ ደብረ ምጥማቅ በሚባለው ቦታ ላይ ዐርፎ ነበር።
➢ ቦታውን ባርኮ ለዘላለም ያንቺ መገለጫ ይሁን ብሎም ቃል ኪዳን ገብቶላት ነበር።
ጊዜው በደረሰ ሰዓት ደብረ ምጥማቅ ተገድሞ የበርካታ መነኮሳት ቤት ሆነ።
➢ እመቤታችንም በልጇ ፈቃድ ግንቦት ፳፩ ቀን አእላፍ መላእክትን፣ ጻድቃን ሰማዕታትን አስከትላት መጣች።
በዚያ ሕዝበ ክርስቲያንም አሕዛብም ተሰብስበው ለአምስት ቀናት ከእመ ብርሃን ጋር ይሰነብታሉ።
➢ እንግዲህ ልብ በሉት እንኳን የአርያም ንግሥት የአምላክ እናቱ እመቤታችንን ይቅርና በዚህ ዓለም ሰይጣን ቤቱ ያደረጋቸውን የመዝናኛው ኢንዳስትሪ ዝነኛ ሰዎችን ለማየት የዘመናችን ሰው እንዴት እንደሚቸኩል።
➢ እመቤታችንን በአካል መመልከት አይደለም ስሟን መጥራት ነፍስን ከሥጋ መለየት የሚችል ጣዕምና ደስታ አለው። ባይሆን ይሔ ለሚገባውና ላደለው ብቻ ነው።
➢ የደብረ ምጥማቅና የአካባቢዋ ሰዎች ከእመቤታችን ጋር የሚቆዩባቸው ቀናት የዘላለም የሕይወት ስንቅ የሚይዙባቸው ናቸው። ፈልገው የሚያጡት ጠይቀው የማይፈጸምላቸው ምንም ነገር አልነበረም። ነቢያት፣ ሐዋርያት፣ ጻድቃን፣ ሰማዕታት፣ ደናግል፣ መነኮሳት፣ መላእክትና ሊቃነ መላእክት ለድንግል ማርያም ሲሰግዱ ይታዩ ነበርና።
➢ እመ ብርሃንም እየመላለሰች ትባርካቸው ነበር። እነዚያ እርሷን ያዩ ዓይኖች፣ በፊቷ የቆሙ እግሮች ክብር ይገባቸዋል። አምስቱ ዕለታት ሲፈጸሙ ሕዝቡ እመቤታችንን በዕንባ ይሰናበቷታል። እመ ብርሃንም በብርሃን መስቀል ባርካቸው ከቅዱሳኑ ጋር ታርጋለች።
#ግንቦት\፳፩ቀንየሚከበሩዓመታዊየቅዱሳንበዓላት
፩.ቅድስት ደብረ ምጥማቅ (የእመቤታችን መገለጥ)
፪.አባ መርትያኖስ ጻድቅ (በዝሙት ላለመሰናከል እግራቸውን በእሳት ያቃጠሉ አባት)
፫.ቅዱስ አሮን ሶርያዊ
፬.ቅዱስ አሞጽ ነቢይ
#ወርኀዊ\በዓላት
፩.አበው ጎርጎርዮሳት
፪.አቡነ ምዕመነ ድንግል
፫.አቡነ አምደ ሥላሴ
#ለአባት_እናቶቻችን_የተገለጠች_እመቤታችን_ለእኛም_በረድኤት_ትገለጽልን_ጣዕመ_ስሟ_በአንደበታችን_ጣዕመ_ፍቅ_በልባችን_ይደርብን።
✞✞✞✞✞ አሜን ✞✞✞✞✞
✥••┈┈••●◉ ✞ ◉●••┈┈••✥
📖 ወስብሐት ለእግዚአብሔር 📖
📖 ወለወላዴቱ ድንግል 📖
📖 ወለመስቀሉ ክቡር 📖
📖✞✞✞✞✞📖
✞✞✞ ሃሳብ ➢
@gebrye_comment_bot
|❀:✧๑ ✞✞✞✞✞✞✞ ๑✧❀|:
✞✞✞ ይቀላቀሉ ➣
@mahteben_albetsm
ዘወረደ(ጾመ ሕርቃን)
«ዘወረደ» ማለት «የወረደ» ማለት ነው፡፡ አምላክ ሰው ሆነ፤ ሰው አምላክ ሆነ ማለት ነው። ይህም ጌታችን መድሃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ እኛን ለማዳንና ፍቅሩን ሊገልጽልን ከሰማያት መውረዱን ከድንግል ማርያም የእኛን ሥጋ መዋሐዱን የሚያዘክር፤ ከሰማየ ሰማያት ወርዶ ከቅድስት ድንግል ማርያም መወለዱን የሚያመላክት፣ የሚታወስበት፣ የሚነገርበት የዐቢይ ጾም አንደኛው ሳምንት ነው፡፡ዮሐ.3-13፡፡ እግዚአብሔር አምላክ ለአዳም በገባዉ ቃልኪዳን መሰረት “ የዘመኑ ፍጻሜ በደረሰ ጊዜ እግዚአብሔር ከሴት የተወለደውን ልጁን ላከ” እንዳለ ሐዋርያዉ ቅዱስ ጳዉሎስ የጠፋዉን አዳም ፍለጋ ከአባቱ እሪና ሳይጎድል ሳይለይ ከሰማይ መዉረዱን የምናዘክርበት በዓል ነዉ። ይህ ጾም የጾም መግቢያ የመጀመሪያ ሳምንት የምንጾመው ጾም ሲሆን ሕርቃል የሚል ስያሜ ተሰጥቶታል፡፡ እግዚአብሔር አምላክ ለአዳም “ከአምስት ቀን ተኩል በኋላ ከልጅ ልጅህ ተወልጄ በመልዕልተ መስቀል ተሰቅየ አድንኃለሁ” ብሎ ለአዳም ቃል ገባለት ፡፡ ዘፍ. ፫ ፥ ፲፭ ይህ ኪዳነ አዳም ይባላል ፡፡ የቃል ኪዳን ሁሉ መሠረት ነው ፡፡ ሁለቱን ኪዳናት (ብሉይ ወሐዲስ) በፅኑዕ ተስፋ ያስተሳሰረ የረጅም ዘመናት የድኅነት ሰንሰለት ነው ፡፡ ዘወረደ እርቀ አዳም ፤ ተስፋ አበው ፤ ትንቢተ ነቢያት ፤ ሱባኤ ካህናት መፈፀሙ ፤ ኪዳነ አዳም መሲህ መወለዱ የሚነገርበት የፍቅር አዋጅ ነው ፡፡
ዘወረደ ማለት?
የምስጢረ ሥጋዌ(የአምላክ ሰው መሆን) ትምህርት ነው፡፡ ዘወረደ ስንል አምላክ ወረደ ከቅድስት ድንግል ማርያም ተወለደ ፤ በፍጹም ተዋሕዶ ሰው ሆነ ማለታችን ነው ፡፡ አምላካችን ኢየሱስ ክርስቶስ ሕያው ሲሆን ሞቶ በመብል ምክንያት የሞተው አዳምን ሕያው አደረገው ፡፡ አምላክ ወልደ አምላክ በመስቀል ላይ በፈቃዱ ሞቶ ለአዳም ያለውን ታላቅ ፍቅር ገለጸ ፡፡
ጠላቶቹ ሳለን ከእግዚአብሔር ጋር በልጁ ሞት ከታረቅን ፥ ይልቁንም ከታረቅን በኃላ በሕይወቱ እንድናለን ፡፡ ሮሜ. 5 ፥ ፲ ፡፡ በዚህም ትህትናን ፍቅርን አስተማረን ፡፡
የመጀመሪያ የዐብይ ጾም መግቢያ እሁድ ዘወረደ ይባላል ደግሞም ጾመ ሕርቃል ይባላል፡፡ ስያሜውም፤ በ614 ዓ.ም ኪርዮስ የተባለ የፋርስ ንጉሥ ኢየሩሳሌምን በመውረር ጥቃት አደረሰ፡፡ በዚህ ወቅት በኢየሩሳሌም ንግሥት ዕሌኒ በሠራችው ቤተመቅደስ ውስጥ ሲገባ ንግሥቷ በክብር አስቀምጣው የነበረው የጌታችን የመድኃኒታችን የኢየሱስ ክርስቶስ መስቀል እንደ ፀሐይ ሲያበራ አገኘው፡፡ ቢነካው አቃጠለው ዲያቆናቱን አሸክሞ ሌላውን ንዋየ ቅድሳት ዘርፎ 60ሺ የሚደርሱትን አቁስሎ ገድሎ 3ሺ የሚሆኑትን ማርኮ ከተማዋንም አቃጥሎ ወደ ፋርስ ባቢሎን ይመለሳል፡፡ በዚህ ጊዜ ከጦርነቱ ያመለጡ በየዋሻው በየጉራንጉሩ ገብተው የተሸሸጉ ተሰብስበው ከ14 ዓመት በኋላ በ628 ጩኸታቸውንና የደረሰባቸውን በደል ለክርስቲየኑ የሮም ንጉሥ ሕርቃል ይነግሩታል፡፡ እርሱም ሐዋርያት ሰውን የገደለ እድሜውን በሙሉ ይጹም ስላሉ እንዴት ላድርገው አላቸው እኛ የአንተን እድሜ ተከፋፍለን እንጾማለን ብለው አንድ አንድ ሳምንት ደርሷቸው ጾሙን በሚገባ ጾመውታል፡፡ የጌታችን የኢየሱስ ክርስቶስ መስቀልና የተማረኩ ክርስቲያኖችን ለመመለስ ሕርቃል ጦር መዝዞ በኪርዮስ ላይ ተነሳበት ድል ለሕርቃል ሆነና መስቀሉን ያለበትን አጥቶ ሲቸገር መስቀሉን ሲቀብርና ዲያቆናቱን ሲያስገድል በመስኮት ሆና ያየችው ከኢየሩሳሌም የተማረከች አንዲት ብላቴና አሳይታው አውጥቶ በልብሰ መንግሥቱ ጠቅልሎ ወደ ቁስጥንጥንያ ተመለሰ፡፡ የተማረኩት በሙሉ ነጻ ወጡ ይህን ለማሰብ ለማስታወስ በተጨማሪ በኃጢአት ላይ ድል እንድናገኝ መንፈሳዊ ጦር በውስጣችን እንዲበዛልን መስቀልህ ከምርኮ እንደተመለሰ እኛንም ከኃጢአት ምርኮ መልሰን ለሕርቃል ድል መንሳትንና በጠላቶቹ ላይ ኃይልን እንደሰጠኸው ለእኛም በኃጢአት ላይ ድል መንሳት መንፈሳዊ ኃይልን ስጠን እያልን እንጾመዋለን፡፡ በጌታ ጾም ላይ እንዲጾም የሆነበት ምክንያት ጾሙ የጌታ ጾም በሚጾምበት ወቅት ላይ ስለተጾመ ቤተክርስቲያናችን አብራ ደንግጋዋለች፡፡እዚህ ላይ በዚያን ጊዜ ለሕርቃል ሕዝቡ ሱባኤ ይዞለታል፡፡ ዛሬም እኛ ለቤተክርስቲያን ያደረግነውን በማሰብ እግዚአብሔር አምላክ ለሕርቃል የሰጠውን በጠላቶቹ ላይ ድል መንሳትን ለእኛም እንዲሰጠን የምንጠይቅበት ስለሆነ የመጀመሪያውን ሳምንት በሕርቃል ሰይመን ጾሙን እንጾማለን፡፡የእኛ ጠላት የጨለማ ገዥ የሆነው ዲያቢሎስ ነውና እሱን ደግሞ በጾም እንደምናሸንፈው ጌታችን መድኃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ አስተምሮናል፡፡ ጾም ስጋችንን ለነፍሳችን የምናስገዛበት ከፈጣሪ ጋር የምንገናኝበት የጽድቅ መንገድ ለስጋ ጤንነትም ቢሆን አስፈላጊያችን የሆነ አንዱና ዋነኛዉ የጽድቅ እቃ ጦራችን ነዉ፡፡ሆኖም የጾም ወቅት ሲመጣ አቀበት የሚወጡ ይመስል የሚፈሩትና የሚያማርሩት ሳይሆን እንኳን መጣልን ተብሎ በጉጉት የሚናፈቅ መሆን አለበት፡፡ስለሆነም ማንኛዉም ሰዉ ጾሙን ሲጀምር የሚከተሉትን ጉዳዮች በደንብ ሊያጤናቸዉ ይገባል፡፡
የዲያብሎስን ሥራ ሊያፈርስየተገለጠው የእግዚአብሔር ልጅም በፆም ድል ማድረግን ለእኛ አስተምሮናል። እኛምበዚህ በአብይ ፆም የለመነውና የጠየቅነው ነገር ሁሉ ከኃጢአት በስተቀርእንዲከናወንልን ፆምን ገንዘባችን እናድርግ። በፆም የተጠቀሙ ቅዱሳን አባቶችና ቅዱሳንእናቶች እንዳሉን እናስተውል። በተለይ አሁን በቤተ ክርስቲያን ላይ እየደረሰበሚታየው አስቸጋሪ ፈተና እያንዳንዳችን ልባዊ ፆም በመፆም ልዑል
እግዚአብሔር የፀሎታችንን ምላሽ እንዲሰጠን እንማፀን።
ጾም ጸሎታችን የቅዱሳን አምላክ እግዚአብሔር ይቀበልልን አሜን።
ወስብሐት ለእግዚአብሔር
#ዝቋላ_ገዳም
የዝቋላ አቡነ ገብረ መንፈስ ቅዱስ ገዳም በ1168 ዓ.ም. ታላቁ ጻድቅ አቡነ ገብረ መንፈስ ቅዱስ በዚህ ዓለም በሕይወተ ሥጋ በነበሩበት ጊዜ ከግብጽ ወደ ኢትዮጵያ መጥተው ቅዱሳት በሆኑ እግሮቻቸው በመርገጥና በመባረክ በተራራው አናት ላይ በሚገኘው ውብና ማራኪ በሆነው ባሕር ውስጥ ለ1)///1ዐዐ ዓመታት በመጸለይ ከዘለዓለማዊው አምላካችን ኢየሱስ ክርስቶስ የማይታበል ሕያው ቃል ኪዳን የተቀበሉበት በ04//14ኛው መቶ ክፍለ ዘመን ከዚህ ዓለም በሞት ከተለዩ በኋላ ጽላታቸው የተቀረጸበት ቤተክርስቲያናቸው የታነጸበት በክቡር ስማቸው ገዳም የተመሠረተበት አምላከ ገብረ መንፈስ ቅዱስ ብርሃነ ረድኤቱን በየጊዜው የሚገልጥበት በሀገራችን ኢትዮጵያ አሉ ከሚባሉት ጥንታዊና ታሪካዊ ገዳማት አንዱ ነው፡፡
የዚህን ታላቅ ገዳም አመሠራረትና ታሪክ እንዲሁም መልክአ ምድር አቀማመጡን በመጠኑ ከዚህ እንደሚከተለው እናቀርባለን፡፡
የደብረ ዝቋላ ገዳም ከተመሠረተ ከላይ ለመግለጽ እንደሞከርነው የ835 ዓመት እድሜን ያስቆጠረ ታላቅ ገዳም ነው፡፡ የመጀመሪያው መሥራች በውስጡ ልዩ ልዩ ጸዋትወ መከራዎችን በመቀበል ገድላቸውን የፈጸሙበት ታላቁ ጻድቅ አቡነ ገብረ መንፈስ ቅዱስ ሲሆኑ እርሣቸው በ1ሺ4)//14ዐዐ ዓመት ውስጥ በነበረውና በኢትዮጵያው ንጉሥ በአጼ ዳዊት ልጅ በሕዝበናኝ (እንድርያስ) ዘመነ መንግሥት ካረፉ በኋላ ንጉሡ ሕዝበናኝ (ሁለተኛ ስሙ እንድርያስ) በዚህ አምሳለ ደብረ ታቦር በተሰኘ፣ አቡነ ገብረ መንፈስ ቅዱስ ለእኛ ለኢትዮጵያውያን የማይታበል ሕያው ቃል ኪዳን ከልዑል እግዚአብሔር በተቀበሉበት ተራራ ላይ በስማቸው ጽላት በማስቀረፅ ቤተክርስቲያን በማነጽ ገዳም እንዲመሠረት ካደረጉ በኋላ በሺህ የሚቆጠሩ መናንያን መነኮሳት በውስጡ ለዓለም ሰላም ለሕዝበ ክርስቲያን ይቅርታና ምሕረትን ከእግዚአብሔር እየለመኑ ትሩፋን እየሠሩ መንፈሳዊ አገልግሎትን እያገለገሉ እስከ ግራኝ ወረራ ድረስ ገዳሙን በማስፋፋት ቆይተዋል፡፡
ኋላም ግራኝ መሐመድ የኢትዮጵያን ገዳማትና አድባራት ባቃጠለና ባጠፋ ጊዜ ይህም ገዳም በግራኝ ወረራ መነኮሳቱ ተጨፍጭፈው አልቀዋል፣ ቤተክርስቲያኑም ተቃጥሏል፣ ገዳሙም ፈርሷል፡፡ ይሁን እንጂ ገዳሙ ዘወትር መንፈስ ቅዱስ የማይለየው እውነተኛ የቅዱሳን ቦታ በመሆኑ ሥራውን ባህታውያን ሳይለዩት እስከ ንጉሥ ማህለ ሥላሴ ዘመነ መንግሥት ድረስ ለብዙ ዓመታት ያህል ጠፍ (ባዶ መሬት) ሆኖ ቆይቷል፡፡
በኋላም የንጉሥ ወሰን ሰገድ ልጅ የሆኑት ንጉሥ ሣህለ ሥላሴ የታላቁ ጻድቅ የአቡነ ገብረ መንፈስ ቅዱስ መካነ ገድል የሆነውን የዝቋላን ገዳም እንደገና አሳድሰው እንደ ቀድሞው የመንፈሳውያንና የመናንያን መነኮሳት መሰብሰቢያ አድርገው አቋቁመውታል፡፡
ከዚያም በኋላ አጼ ምኒልክ ለገዳሙ መናንያን መነኮሳት መተዳደሪያ ሰፊ ርስት ጉልት ከመስጠታቸውም በላይ የመንፈሳዊ መተዳደሪያ ሕግና ሥርዓቱንም በወቅቱ ከነበሩት መንፈሳውያን አባቶች ጋር ሆነው በመወሰን ያወጡት ሕግ የሚሻሻለው በቅዱስ ሲኖዶስ ተሻሽሎ እነሆ እስከ አሁን ያለው የአቡነ ገብረ መንፈስ ቅዱስ ቤተክርስቲያንም አጼ ምኒልክ ያሠሩት ነው፡፡ ይህ ብቻም ሳይሆን አጼ ምኒልክ ለደብረ ዝቋላ ገዳም ብዙ መጻሕፍትና ንዋየ ቅድሳትን የሰጡ ሲሆን አስከ አሁንም በቅርስነት ተጠብቀው ይገኛሉ፡፡
የደብረ ዝቋላ ገዳምን መልክአ ምድር አቀማመጡን ስንመለከት
የዝቋላ አቡ ገብረ መንፈስ ቅዱስ ገዳም በታላቅ ተራራ ላይ የተመሠረተ ውብና ማራኪ የሆነ ምን ጊዜም ጸጋ እግዚአብሔር የማይለየውና ንጹህ ጤናማ አየር ያለው በአጠቃላይ ተፈጥሮ ያደለው እውነተኛ መካነ ቅዱሳን ነው፡፡
ወደዚህ ታላቅ ገዳም ለመድረስ ከአዲስ አበባ እስከ ዝቋላ ተራራ ‘2/82 ኪ.ሜ. ርዝመት ያለው ሲሆን የተራራው ርዝመት በመኪና መንገድ 9/9 ኪ.ሜ. ነው፡፡ በእግር ተራራው ብቻ ከ2 ሰዓት ተኩል እስከ 3 ሰዓት ያስኬዳል፡፡ ይሁን እንጂ የዝቋላ ተራራ ዙሪያውን በደን የተሸፈነ በመሆኑ ተራራውን ለመውጣት ጉዞ ሲጀምሩ ውብና ማራኪ የሆነው የደን መዓዛ፣ የመንፈስ ቅዱስ ጸጋ፣ የቅዱሳን ረድኤት ልብን እየመሰጠ ያለምንም ድካም ከተራራው አናት ላይ ያደርሳል፡፡
ከዚያም ታላቁ ጻድቅ አቡነ ገብረ መንፈስ ቅዱስ ለዓለም ሰላም ለኢትዮጵያ ምሕረትን በመለመን 1ዐዐ ዓመት ሙሉ በውስጡ የጸለዩበትን ባህር ዙሪያውን ጥቅጥቅ ባለ የተፈጥሮ ደንና የባሕር ዛፍ አጣና በሚያካክል ቀጤማ ተከቦ ሲታይ ሰማያዊ ገነትን የሚያስታውስ ምድራዊ ገነት እውነተኛ የጽድቅ ቦታ ለመንፈሳውያን መኖሪያ የተፈጠረ መሆኑንና ታላቅነቱን ያስመሰክራል፡፡ በዚህም የሐይቅ ጸበል ብዙ ሕሙማን ከልዩ ልዩ ደዌያቸው ይፈወሱበታል፡፡
የዚህ ሐይቅ አቀማመጥ ከተራራው አናት ላይ እንደ ገበታ ወይም ሣህን በጎድጓዳ ቦታ ላይ ያለ ሆኖ ዙሪያው በደንና በቀጤማ የተከበበ ነው፡፡ እጅግ በጣም የሚያስደንቀው ይህ ባህር ባልታሰበ ጊዜ እንደ አምፖል ያለ ብርሃን በግምት ርዝመቱ ከ2 እስከ 3 ሜትር የሚደርስ በባህሩ መካከል ሲበራ ማየት በዝቋላ አቡነ ገብረ መንፈስ ቅዱስ ገዳም ለሚኖሩ መነኮሳት የተለመደ ነው፡፡
የብርሃኑም ዓይነት ነጭ ሲሆን ይህ ከላይ የጠቀስነው ዓይነት ብርሃን በመካከሉ የሚቆም ሲሆን በቀጤማው ዙሪያ ደግሞ እንደ አምፖል ዓይነት ብርሃን ባህሩን ከቦት ለብዙ ሰዓት ይቆያል አንዳንድ ቀንም ሙሉ ሌሊቱን ሲያበራ የሚያድርበት ጊዜ አለ፤ ይህን ስንል ለአንባብያን ማመን ያስቸግር ይሆናል፡፡ ነገር ግን የሚጠራጠር ሁሉ በዝቋላ ገዳም ለጥቂት ቀን ከተቀመጠና እግዚአብሔር ከፈቀደለት አይቶ ማመን ይችላል፡፡
ከዚህ በላይ የአቡነ ገብረ መንፈስ ቅዱስን አስደናቂ ተአምርና የገዳሙን ይዘት በመጠኑ አቅርበናል፡፡ በዝቋላ አቡነ ገብረ መንፈስ ቅዱስ ገደም በየዋሻውና በየጫካው ወድቀው ለዓለም ሰላምን ለሕዝበ ክርስቲያን ይቅርታና ምሕረትን ከልዑል እግዚአብሔር እየለመኑ የሚኖሩ ባህታውያን ያሉበት በብዙ የሚቆጠሩ አረጋውያን አባቶችና እናቶች እንዲሁም አቅመ ደካሞች የሚጦሩበት አምላከ ገብረ መንፈስ ቅዱስ ብርሃነ ረድኤቱን ሁል ጊዜ የሚገልጥበት ታላቅ ገዳም ስለሆነ ምዕመናን በዚህ ቅዱስ ቦታ በመገኘት የቅዱሳንን በረከት በመቀበል የታላቁ ጻድቅ የአቡነ ገብረ መንፈስ ቅዱስ የቃል ኪዳናቸው ተካፋይ ትሆኑ ዘንድ እያመላከትን ጽሁፋችንን በዚሁ እናጠቃልላለን፡፡
የጻድቁ በረከት ከሁላችን ጋር ይሁን አሜን፡፡
ምንጭ፡- “ልሳነ ተዋሕዶ ዘኦርቶዶክስ” መጽሔት 1986 ዓ.ም.
††† በስመ አብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ አሐዱ
አምላክ አሜን! †††
መስከረም ፳፮
●◎◦◦◎● ተአምረ ማርያም ●◎◦◦◎●
➤ተአምር ማለት "ድንቅ፣ ምልክት፣ ከተፈጥሮ ሥርዓት ውጪ የሆነ ክዋኔ፣ በሰብአዊ አቅም ሊሠራ የማይችል ተግባር (ድርጊት)" ነው።
➤ተአምራት ከባለቤቱ ከጌታችን ሲሆኑ የባሕርዩ ናቸው። ከቅዱሳኑ ሲሆኑ ደግሞ የጸጋ እንላቸዋለን። ቅዱስ መጽሐፍ ላይ በእግዚአብሔር ወዳጆች የተሠሩ ተአምራት እጅግ ብዙ ናቸው።
●◎◦ ነገር ግን
➤ተአምራት ከአጋንንትም ሊሆኑ እንደሚችሉ መረዳት።
ሁሌ ምልክትን (ተአምርን) አለመፈለግ። መመርመርና ማስተዋል ከአንድ ክርስቲያን ይጠበቃል።
➤ቅዱስ ዮሐንስ አፈ ወርቅ በድርሳኑ እንደ ነገረን ተአምር መሥራት ከሲዖል እሳት አያድንም። ጌታም በዚህ ነገር ተባብሮበታል።
“በዚያ ቀን ብዙዎች፦ ጌታ ሆይ፥ ጌታ ሆይ፥ በስምህ ትንቢት አልተናገርንምን፥ በስምህስ አጋንንትን አላወጣንምን፥ በስምህስ ብዙ ተአምራትን አላደረግንምን? ይሉኛል።”
— ማቴዎስ ፯፥፳፪
“እርሱ ግን መልሶ እንዲህ አላቸው፦ ክፉና አመንዝራ ትውልድ ምልክት ይሻል፥ ከነቢዩም ከዮናስ ምልክት በቀር ምልክት አይሰጠውም።”
— ማቴዎስ ፲፪÷፴፱
➤ከጌታችን እግዚአብሔር ቀጥሎ የድንግል ማርያምን ያህል ተአምራትን የሠራ አይገኝም። እንዲያው ሌላውን ትተን በእያንዳንዳችን ሕይወት ላይ እንኳ ብዙ ድንቅ ነገሮችን አድርጋለችና ምስክሮቹ እኛው ራሳችን ነን።
➤የእመቤታችን ተአምር የተጀመረው ገና ከፍጥረተ ዓለም ነው። በእርግጥ ይህንን ለመረዳት ሠፊ አዕምሮና አስተዋይ ልቡናን ይጠይቃል።
➤ድንግል ማርያም ማለት የእግዚአብሔር የቸርነቱ ግምጃ ቤት የጸጋው ደጅ ናት። እርሱ ይህንን መርጦ ወዷልና።
➤እመ ብርሃን ተጸንሳ ከተወለደች በኋላ ደግሞ እጅግ ብዙ ኃይልን ታደርግ ነበር። በዚህ ዕለት መስከረም ፳፮ እመቤታችን ያደረገችው ተአምር ደግሞ ድንቅ ነው።
➤አጐቷ /ጠባቂዋ/ አገልጋዩዋ አረጋዊ ቅዱስ ዮሴፍ ከቤተ መቅደስ ተቀብሎ ካመጣት በኋላ እርሱ እንጨትን ይጠርብ ነበር። ዘመኑ ዘመነ ዐጸባ (የችግር ዘመን) በመሆኑ ለሥራ ጉዳይ ወደ ሩቅ ሃገር ሒዶ የተመለሰው ከወራት በኋላ ነው።
➤ዮሐንስ የሚሉት ፈላስፋ ባልንጀራ ነበረውና ሽማግሌው ዮሴፍ ልብ ያላለውን ነገር ነገረው። "ይህች ብላቴና ጸንሳለችና መርምራት።" ብሎ ሔደ።
➤ቅዱስ ዮሴፍ ግን ደነገጠ። "እኔ እንዲህ ያለ ነገር እንኳን በገቢር (በሥራ) በሃሳብም አላውቅባት።" ብሎት ወደ ቤት ገባ።
➤ቀጥሎም እመቤታችንን "ልጄ ሆይ! ከማን ጸነስሽ?" አላት። "እመንፈስ ቅዱስ" አለችው። ግራ ገባው፤ ምሥጢርም ተሠወረበት። "እንዴት አንዲት ሴት ያለ ወንድ ዘር ልትጸንስ ትችላለች?" ብሎ ያወጣ ያወርድ፤ ይጨነቅም ገባ።
➤ የእኛ እመቤት ግን እንደ ጨነቀው ባወቀች ጊዜ ጠርታ ወደ ውጪ ይዛው ወጣች። ከረዥም ጊዜ በፊት ጠርቦ የጣለውን እንጨት አንስታ ተከለችውና ጸለየችበት። በደቂቃም የአረጋዊው ዓይን እያየ ያ ደረቅ እንጨት ለምልሞ አብቦ አፈራ።
➤ቅዱስ ዮሴፍ በጣም ደነገጠ። "አባቴ ተመልከት እስኪ! ይህንን ማን አደረገ?" አለችው። "ልጄና እመቤቴ! እግዚአብሔር ነው።" አላት። እርሷም "በማኅጸኔ ያለውም ኢሳይያስ ትንቢትን የተናገረለት አምላክ ነውና ሁሉን ይችላል።" አለችው።
➤አረጋዊውም ቅዱስ ኤራቅሊስ በሃይማኖተ አበው እንደ ነገረን "ሰገደ ላቲ" ወደ ምድር ወድቆ በፊቷ ሰገደ።
✥••┈┈••●◉ ✞ ◉●••┈┈••✥
●◎◦◦◎● ቅዱስ ዮሐንስ መጥምቅ ●◎◦◦◎●
➤ቅዱስ ወንጌል ላይ ከእመቤታችን ቀጥሎ የዘካርያስን ቤተሰብ ያህል ክብሩ የተገለጠለት ፍጡር ይኖራል ብሎ መናገሩ ይከብዳል።
➤ቅዱስ ሉቃስ ወንጌሉን የጀመረው በዚህ ቅዱስ ቤተሰብ ነውና መንፈስ ቅዱስ እንዲህ ሲል አጽፎታል:: "ዘካርያስ ካህኑና ቅድስት ኤልሳቤጥ በሰውና በእግዚአብሔር ፊት ያለ ነቀፋ የሚኖሩ ጻድቃን ነበሩ።" ይላቸዋል።
“ሁለቱም በጌታ ትእዛዝና ሕግጋት ሁሉ ያለ ነቀፋ እየሄዱ በእግዚአብሔር ፊት ጻድቃን ነበሩ።”
— ሉቃስ ፩÷፮
➤የሰውን እንተወውና በእግዚአብሔር ፊት ያለ ነቀፋ መኖር ምን ይረቅ? ለዚህ አንክሮ (አድናቆት) ይገባል! እሊህ ቅዱሳን ባልና ሚስት ግን መካኖች በመሆናቸው ልጅ ሳይወልዱ ዘመናቸው አልፎ ነበር።
➤እንደ ቤተ ክርስቲያን ትውፊት ዕድሜአቸው የኤልሳቤጥ ዘጠና የዘካርያስ ደግሞ መቶ ደርሶ ነበር። ፍጹም መታገሳቸውን የተመለከተ ጌታ ግን በስተ እርጅናቸው ከሰው ሁሉ በላይ የሆነ ትንቢት ለብቻው የተነገረለት ታላቅ ነቢይን ይሰጣቸው ዘንድ መልአከ ብሥራት ቅዱስ ገብርኤልን ላከላቸው።
“የአዋጅ ነጋሪ ቃል፦ የእግዚአብሔርን መንገድ በምድረ በዳ ጥረጉ፥ ለአምላካችንም ጐዳና በበረሀ አስተካከሉ።”
— ኢሳይያስ ፵÷፫
“እነሆ፥ መልእክተኛዬን እልካለሁ፥ መንገድንም በፊቴ ያስተካክላል፤ እናንተም የምትፈልጉት ጌታ በድንገት ወደ መቅደሱ ይመጣል፤ የምትወዱትም የቃል ኪዳን መልእክተኛ፥ እነሆ፥ ይመጣል፥ ይላል የሠራዊት ጌታ እግዚአብሔር።”
— ሚልክያስ ፫÷፩
➤ቅዱስ ዘካርያስ ሰው ነውና ከደስታ ብዛት በመከራከሩ ድዳ ሆነ:: ቅድስቲቷ ግን መስከረም ፳፮ ቀን ታላቁን ሰው ጸንሳ ለስድስት ወራት ራሷን ሠወረች።
➤በስድስተኛው ወር የፍጥረት ሁሉ ጌታ በተጸነሰ ጊዜ የአርያም ንግሥት ድንግል እመቤታችን ደጋ ደጋውን ወደ ኤልሳቤጥ መጣች። ሁለቱ ቅዱሳት የእኅትማማች ልጆች ናቸው።
➤የአምላክ እናቱ ስትደርስና "ሰላም" ስትላቸው መንፈስ ቅዱስ በእናትና ልጅ ወርዶ ኤልሳቤጥ በምስጋና፣ ዮሐንስ ደግሞ ገና በማኅጸን ሳለ በደስታ ዘለለ (ሰገደ)።
➤ከዚህ በኋላ ሰኔ ፴ ቀን ተወልዶ አባቱ ዘካርያስ "ዮሐንስ" ሲለው አንደበቱ ተፈትቶለታል።
➤መስከረም ፳፮ ቀን የሚከበሩ ዓመታዊ የቅዱሳን በዓላት
፩. ቅድስት ድንግል ማርያም
፪. ቅዱስ ዮሴፍ አረጋዊ
፫. ቅዱስ ዮሐንስ መጥምቅ (ጽንሰቱ)
፬. ቅዱሳን ዘካርያስና ኤልሳቤጥ
፭. ቅዱስ አቦሊ ሰማዕት (ፍልሠቱ)
➤ወርኀዊ በዓላት
፩. ቅዱስ ቶማስ ሐዋርያ
፪. አቡነ ሃብተ ማርያም ጻድቅ
፫. አቡነ ኢየሱስ ሞዐ ዘሐይቅ
፬. ቅዱሳን ሰማዕታተ ናግራን
፭. ቅዱስ አቡነ ሰላማ ከሣቴ ብርሃን
"ኤልሳቤጥም የማርያምን ሰላምታ በሰማች ጊዜ ፅንሱ በማኅፀንዋ ውስጥ ዘለለ፤ በኤልሳቤጥም መንፈስ ቅዱስ ሞላባት፥ በታላቅ ድምፅም ጮኻ እንዲህ አለች፦ አንቺ ከሴቶች መካከል የተባረክሽ ነሽ፥ የማኅፀንሽም ፍሬ የተባረከ ነው። የጌታዬ እናት ወደ እኔ ትመጣ ዘንድ እንዴት ይሆንልኛል? እነሆ፥ የሰላምታሽ ድምጽ በጆሮዬ በመጣ ጊዜ ፅንሱ በማኅፀኔ በደስታ ዘሎአልና።ከጌታ፤ የተነገረላት ቃል ይፈጸማልና ያመነች ብፅዕት ናት።"
-------ሉቃስ ፩÷፵፩-፵፭
✞✞✞ የእመቤታችን ልመናዋ፣ ክብሯ፣ የልጇ የወዳጇም ቸርነት በእውነት ከሁላችን ጋር ይሁን። የመጥምቁንም በረከት ያብዛልን። ✞✞✞
✞ሉቃስ✞✞✞ አሜን ✞✞✞✞✞
✥••┈┈••●◉ ✞ ◉●••┈┈••✥
📖📖ወስብሐት ለ እግዚአብሔር📖📖
📖✞✞✞✞✞📖
✞✞✞ ሃሳብ ➢ @gebrye_comment_bot
|❀:✧๑ ✞✞✞✞✞✞✞ ๑✧❀|:
✞✞✞ ይቀላቀሉ ➣ @mahteben_albetsm
❀✿ የዐፄ ዘርዐ ያዕቆብ ደብዳቤ ✿❀
❍●◦─━•⊰❀✿❀⊱•━─◦●❍
በስመ አብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ ፩ አምላክ...አሜን፡፡ ተፈነወት ዛቲ ክርታስ እም ኀበ ንጉሥነ ዘርዓ ያዕቆብ ዘተሰምየ ቈስጠንጢኖስ ኅበ ኵሎም ማኅበረ እስራኤል ወሀበ ኵሎሙ ካህናተ ደብተራ ዘመርጡል ለእለ ትነብሩ ኀበ ደብረ እግዚአብሔር ኣብ ወውእቱ አቡነ ወውእቱ እምነ ወውእቱ ዓቃቤ ነፍሳቲነ። ወይእዜኒ ይዕቀብክሙ...አሜን።...
ወናሁ ፈኖነ ለክሙ ዓቢያተ ባሕርያተ ዘኢይትረከብ ኢበወርቅ ወኢበዕንቁ’ ወኢበምንትኒ ንዋያተ ዓለም ዘኢይትረከብዎን ፈኖነ ለክሙ መስቀሉ ለወልደ እግዚአብሔር ዘተሰቅላ ቦቱ እግዚኣ ሰማያት ወምድር ወከለሜዳሂ ዘአልበስዎ በዕለተ ስቅለት ወሰፍነግሂ ዘአስተይዎ ቦቱ ብሒአ ዘምስለ ሐሞት ወከርቤ ቱሱሕ ዘወፀአ በመዋዕሊነ እምብሔረ አፍርንግ፡፡ ወለመስቀለ ወልደ እግዚአብሔርሰ ሶበ ረከበቶ እሌኒ እቴጌበኢየሩሳሌም ወወሰደቶ እስከ ብሔረ አፍርንግ፡፡ ወተካፈልዎ ሰብዓቱ ነገሥተ አፍርንግ። ወለአቡየሂ ዳዊት ፈነው እምውእቱ መስቀል ዘብዓቱ መስቀል ወይእዜኒ ፈነው ለነ እም ውእቱ መስቀል ዘምስለ ከለሜዳ ወስፍነግ ከለሜዳሰ ወሰፍነግ፡፡ ኢመጽአ እምቅድመዝ ዘእንበለ ይእዜ በመዋዕሊነ።...
በስመ አብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ ፩ አምላክ፡፡... አሜን።
ይህቺ ደብዳቤ ቈስጠንጢኖስ ከተባለው ንጉሣችን ከዘርዐ ያዕቆብ ለእስራኤል ማኅበር ሁሉ (የነገሥታቱ ዘሮች እስራኤል ነበረ የሚባሉት) እንዲሁም በደብረ እግዚአብሔር አብ (ግሼን) መቅደስ ለምትኖሩ ካህናት ሁሉ ተላከች፡፡ እሱ (እግዚአብሔር) አባታችንም እናታችንም ነው:: የነፍሳችን ጠባቂ ነው። አሁንም ይጠብቃችሁ፡፡...አሜን።....
እነሆ በወርቅ፥በዕንቍ እንዲያውም በማንኛውም የዚህ ዓለም ገንዘብ የማይገኙ ታላላቅ ጥሪቶችን ልከንላችኋል። የሰማያትና የምድር ጌታ የተሰቀለበትን የእግዚአብሔር ልጅን መስቀል የተሰቀለ ዕለት ያለበሱትን የለምድ ልብስ መጻጻ ሐሞት ከርቤ በጥብጠው ያጠጡበትን ሰፍነግ ልከንላችኋል። (እነዚህ ሁሉ) በኛ ዘመን ከፈረንጅ ሀገር የመጡ ናቸው። የእግዚአብሔርን ልጅ መስቀል ዕሌኒ ባገኘችው ጊዜ ወደ ፈረንጆች ሀገር ወሰደችው፡፡ ሰባቱም የፈረንጅ ሀገር ንጉሦች ተካፈሉት፡፡ ለአባቴ ለዳዊት ከዚህ መስቀል ላይ (ቈርጠው) ልከውለት ነበር። አሁን ደግሞ ለኛ ከዚሁ መስቀል ላይ (ቈርጠው) ከከለሜዳውና ከሰፍነጉ ጋር ላኩልን። ከለሜዳውና ሰፍነጉ አሁን በኛ ዘመን እንጂ ከዚህ በፊት (ወደኛ ሀገር) አልመጣም ነበረ:: ...
ዐፄ ዘርዐ ያዕቆብ በደብዳቤው ላይ መስቀሉ እንዴት ሆኖ እንደመጣ ይተርካል።
ወለ መስቀለ ወልደ እግዚአብሔርሰ ፈነዉ ለነ ወዲዮሙ በመስቀል ዘወርቅ ውስተ ውሳጤ መስቀል ዘወርቅ ዘመንክር ግብረቱ፡፡ ቀፊሎሙ በቀማጥር ዘወርቅ፡፡ ወሶበ ያቀውምዎ ይቀውም በመከየደ ወርቅ እንተ ገብሩ ሎቱ ጠቢባነ አፍርንጅ -
የወልደ እግዚአብሔርን መስቀል የላኩልን በወርቅ መስቀል ወስጥ በሚገኝ፣ አሠራሩ በሚያስደንቅ፣ የወርቅ መስቀል ውስጥ ከትተው ነው፡፡ ያንንም የወርቅ መስቀል በወርቅ በተለበጠ ሳጥን አኑረውታል፡፡ ለማቆምም ሲያስፈልግ የፈረንጅ ጠቢባን በሠሩለት የወርቅ መቆሚያ ይቆማል፡፡»
<ወለመስቀለ ክርስቶስሰ ዘምስለ ሙዳዩ መስቀል ዘወርቅ ወደይኖ ውስጠ ሣጹን ዘወርቅ - የክርስቶስንም መስቀል ከሙዳዩ ከወርቅ መስቀሉ ጋር በወርቅ ሳጥን አኖርነው፡፡» ይላል፡፡ በዚህ ሳጥን ከለሜዳውንና ለፍነጉን ከነወርቅ መያዛቸው ጨመርናቸው | በሳጥኑ ውስጥም የወርቅ መስቀል ሠርተንበት ነበር፡፡ ደግሞ አራት የወርቅ ሰንሰለቶች ነበሩ። የወርቅ መያዣዎቻቸውም ብዙ ነበሩ፡፡ የሳጥነም መክደኛ የወርቅ ነበር፡፡ ሳጥኑም የሚቆለፈው በወርቅ መቆለፊያ ነው፡፡ የወርቅ ሳጥኑን ያሠራንበት ዋጋ 3750 ዲናር ነው፡፡ በወርቅ በተለበጠው በዕንጨት ሳጥን ውስጥ ያስገባነው የወርቅ ሳጥን፣ ለዕንጨቱ ማስጌጫ ወርቅ ያወጣነው 1987(ዲናር ነው፡፡ ይሄንንም ሁሉ ለእግዚአብሔር አብ፣ ለልጁና ለመንፈስ ቅዱስ ሰጠን>፡፡
ዐፄ ዘርዐ ያዕቆብ የመስቀሉ በዓል ግማደ መስቀሉን፣ ከለሜዳውንና ሰፍነጉን ባገኘንበት በመስከረም 21 ቀን በእመቤታችን በማርያም በዓል እናክብር ይላል። ዳግመኛም የመስቀሉን በዓል በመጋቢት 10 ቀን፣ ደግሞም በነሐሴ 14 ቀን እናክብር ይላል፡፡ በዚህ ዕለት ከሐዲ ክርስቲያናዊ በወጋው ጊዜ መስቀሉ ደምና ውኃ በአንድነት አፍስሷልና፡፡ አንድ አይሁዳዊም ከመስቀሉ ከወጣው ከውኃውና ከደሙ ወስዶ ዕውር የነበረ ልጁን ቢቀባው አየ። በመስከረም 17 ቀንም የመስቀልን በዓል አክብሩ፡፡ በአባቴ በዳዊት ዘመን መስቀሉ የወጣበት ነውና፡፡ ደግሞም ከቀድሞ ጀምሮ እንደተሠራው በመስከረም 17 ቀን የመስቀልን በዓል አክብሩ፡፡
═────━━━━⊱✿⊰━━━━────═
ሃሳብ👉🏽 @hadis_comment_bot
▬▬▬▬▬❀✿❀▬▬▬▬▬
👇👇👇ይቀጥላል 👇👇👇
◉◉◉◦◦◦▬▬▬▬▬▬▬▬▬▬◦◦◦◉◉◉
ይቀላቀሉ👉🏽 @yemaryammekenet
━━━━━━━━━━━━━━━━━━━━━━━
 ̄ ̄ ̄ ̄ ̄🙏 ̄ ̄ ̄ ̄ ̄
 ̄ ̄ ̄─━━━━⊱✿⊰━━━━─ ̄
💬 - http://t.me/hadis_comment_bot | join - http://t.me/yemaryammekenet
††† በስመ አብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ አሐዱ አምላክ አሜን ! †††
ነሀሴ ፲፫
#ደብረ\_ታቦር
➢ ደብረ ታቦር በቁሙ እሥራኤል ውስጥ ከሚገኙ ተራሮች አንዱ ነው:: ተራራው ብዙ ታሪካዊ ዳራዎች ቢኖሩትም ክብሩ ከፍ ከፍ ያለው ግን ጌታችን ብርሃነ መለኮቱን ስለ ገለጸበት ነው::
#ይሕስ\_እንደ\_ምን\_ነው\_ቢሉ:-
➢ አካላዊ ቃል ኢየሱስ ክርስቶስ ሥጋችንን በተዋሐደባት በዚያች በተወደደች ጊዜ ደቀ መዛሙርቱ ስለ እግዚአብሔር መንግስት ምሥጢርን ይማሩ ነበር:: በጊዜው ግን አበው ሐዋርያት ምሥጢር ባይገባቸው አንድም ገና መንፈስ ቅዱስ በእነርሱ ላይ አልወረደም ነበርና እምነታቸው ሙሉ አልነበረም::
➢ ጌታም አምላክነቱን በየጊዜው በቃልም በተግባርም ይገልጥላቸው ነበር:: በእርግጥ ያንን ነደ እሳት: ሰማያት የማይችሉትን ግሩማዊ አምላክ በትሑት ሰብዕና መመልከቱ ሊከብድ እንደሚችል መገመት አያዳግትም::
➢ ጌታችን ብዙ ተአምራትን በአምላካዊ ጥበቡ ሠርቷል:: እጅግ ድንቅ ከሆኑት መካከል ደግሞ ቅድሚያውን ደብረ ታቦር ይይዛል:: ጌታ ስለ ምን መለኮታዊ ክብሩን በደብረ ታቦር ገለጸ ቢሉ:-
፩~ትንቢቱ ሊፈጸም
“ተአምራትህ በጨለማ፥ ጽድቅህንም በመርሳት ምድር ትታወቃለችን?”
— መዝሙር "፹፰÷፲፪
፪~ምሳሌው ሊፈጸም (ባርቅና ዲቦራ በሢሣራ ላይ ድልን ተቀዳጅተዋልና::
፫~ሊቀ ነቢያት ሙሴ "ልይህ" ብሎ ከአንድ ሺ አምስት ዓመታት በፊት ጠይቆ ነበርና እርሱን ለመፈጸም
፬ አንድነቱን: ሦስትነቱን ለመግለጽ
፮ ቤተ ክርስቲያንን በምሳሌ ለማሳየት
፮ ተራራውን ለመቀደስ
፯ የሐዋርያቱን ልብ ለማጽናት . . . ወዘተ ነው::
➢ ነሐሴ 7 ቀን ጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ደቀ መዛሙርቱን ወደ ቂሣርያ ፊልጶስ ወስዶ "የሰውን ልጅ ማን ይሉታል?" ብሎ ጠይቋቸው ነበር:: እነርሱም የራሳቸውን ሐሳብ የሌላ እያስመሰሉ "አንዳንዶቹ ኤልያስ: አንዳንዶቹም ሙሴ: ሌሎቹም ከነቢያት አንዱ ነው ይሉሃል::" አሉት::
➢ ኩላሊትን የሚመረምር ፈጣሪ ነውና "እናንተስ ማን ትሉኛላችሁ?" ቢላቸው ደንግጠው ዝም አሉ:: የሃይማኖት አባት: ባለ በጐ ሽምግልና ቅዱስ ጴጥሮስ ግን በመካከላቸው ቆሞ "አንተ ውዕቱ ክርስቶስ ወልደ እግዚአብሔር ሕያው - የሕያው እግዚአብሔር አንድያ የባሕርይ ልጁ ክርስቶስ አንተ ነህ::" አለው:: በዚያን ጊዜ ቃለ ብጽዓን እና የመንግስተ ሰማያት መክፈቻ ተሰጠው::
-----ማቴ. ፲፮÷፲፫
➢ መጽሐፍ እንደሚል ደግሞ እንዲህ ከሆነ ከስድስተኛው ቀን በኋላ ጌታችን አሥራ ሁለቱን ደቀ መዛሙርቱን ወደ ደብረ ታቦር ወሰዳቸው:: ዘጠኙን በእግረ ደብር (ከተራራው ሥር) ትቶ ሦስቱን (ጴጥሮስን: ዮሐንስንና ያዕቆብን) ይዟቸው ወጣ:: እኒሕ ሐዋርያት "አዕማድ: አርዕስት: ሐዋርያተ ምሥጢርም" ይባላሉ::
➢ በተራራው ላይ ሳሉም ድንገት የጌታችን መልኩ ከፀሐይ ሰባት እጅ አበራ፤ ከመብረቅም ሰባት እጅ አበረቀ:: "ወኮነ ልብሱ ጸዐዳ ከመ በረድ" እንዲል ከታቦር የተነሳው ብርሃነ ገጹ አርሞንኤም ደርሷል:: ያንን ተመልክተው መቆም ያልቻሉት ሐዋርያቱ ፈጥነው መሬት ላይ እንደ ሻሽ ተነጠፉ::
➢ በዚያች ሰዓት ሙሴ ከመቃብር: ኤልያስም ከብሔረ ሕያዋን መጡ:: አንዳንዶቹ ጌታን "ነቢይ" (ሎቱ ስብሐት) ብለውታልና ሙሴና ኤልያስ ተናገሩ:- "ስለ ምን አንተን ነቢይ ይሉሃል፤ እግዚአ ነቢያት-የነቢያት ፈጣሪ ነህ እንጂ" እያሉ ተገዙለት: አመሰገኑት::
➢ ነገር ግን በቦታው ጸንተው መቆየት አልቻሉም:: መለኮታዊ ብርሃኑ ቢበዘብዛቸው ቅዱስ ሙሴም ወደ መቃብሩ: ቅዱስ ኤልያስም ወደ ማደሪያው በድንጋጤ ሩጠዋል::
➢ በዚያች ሰዓት ሊቀ ሐዋርያት ጌታን "ሠናይ ለነ ኀልዎ ዝየ:: ንግበር ሠለስተ ማኅደረ: አሐደ ለከ: ወአሐደ ለሙሴ: ወአሐደ ለኤልያስ - ጌታ ሆይ! በዚህ መኖር ለኛ መልካም ነው:: በዚህም ሦስት ዳስ እንሥራ:: አንዱን ለአንተ: አንዱንም ለሙሴ: አንዱን ለኤልያስ" ብሎታል::
➢ ቅዱስ ጴጥሮስ ለራሱ ሳያስብ ለጌታና ለቅዱሳን ነቢያቱ "ቤት እንሥራ" በማለቱ ሲመሰገን ጌታን የመጣበትን የማዳን ሥራ የሚያስተው ጥያቄ በማቅረቡ ከድካም ተቆጥሮበታል:: ለሁሉም ግን ሐሳቡ ድንቅና መንፈሳዊ ነው::
➢ እርሱ ይሕንን ሲናገር መንፈስ ቅዱስ በደመና አምሳል ወረደና ከበባቸው:: አብ ከሰማይ ሆኖ "ዝንቱ ውዕቱ ወልድየ ዘአፈቅር: ወሎቱ ስምዕዎ - የምወደው: የምወልደው: ሕልው ሆኘ የምመለክበት የባሕርይ ልጄ እርሱ ነውና ስሙት::" ሲል ተናገረ::
➢ ደቀ መዛሙርቱም ከፍርሃት የተነሳ በዚያች ሰዓት እንደ በድን ሁነው ነበርና ጌታችን ቀርቦ ቀሰቀሳቸው:: በተነሱ ጊዜ ግን ሁሉም ነገር ወደ ነበረበት ተመልሶ ነበር::
ማቴዎስ . ፲፯ ማርቆስ. ፱,
➢ በደብረ ታቦር የጌታችንን ብርሃነ መለኮት ያዩ ሦስቱ ሐዋርያት ብቻ አይደሉም:: እመ ብርሃን ካለችበት ሆና ስትመለከት ፰ ሐዋርያት ደግሞ በተራራው ሥር ሆነው በተደሞ ተመልክተዋል::
➢ ይሕንን ድንቅ ብርሃነ መለኮት ያላየ ይሁዳ ብቻ ሲሆን እርሱም ስለ ክፋቱ የኢሳይያስ ትንቢት ተፈጽሞበታል:: ኃጢአተኛው የእግዚአብሔርን ክብር እንደማያይ ተነግሮበታልና:: "ያአትትዎ ለኃጥእ ከመ ኢይርዐይ ስብሐተ እግዚአብሔር" እንዲል::
---ኢሳያስ ፳፭÷፲
#ሊቁም\_የደብረ\_ታቦርን\_ምሥጢር\_ሲያደንቅ\_እንዲህ\_ብሏል:-
"ጸርሐ አብ ኪያከ በውዳሴ
ወበርእስከ ጸለለ መንፈሰ ቅዳሴ:
አመ ገበርከ እግዚኦ በታቦር ምስለ ሐዋርያት ክናሴ:
መንገለ ሀሎ ኤልያስ ወኀበ ሐለወ ሙሴ:
ዘመለኮትከ ወልድ ከሠትከ ሥላሴ::"
➢ ነሐሴ ፲፫ ቀን የሚከበሩ ዓመታዊ የቅዱሳን በዓላት
፩ ደብረ ታቦር /ደብረ ምሥጢር/ ደብረ በረከት
፪ ቅዱስ ሙሴ ሊቀ ነቢያት (ልደቱ)
፫ ቅዱስ ኤልያስ ነቢይ
፬ ቅዱሳን አበው ሐዋርያት
፭ አባ ጋልዮን መስተጋድል
፮ አቡነ ዓቢየ እግዚእ ጻድቅ (ልደታቸው)
፯ ቅድስት ኦፍራ ሰማዕት
➢ ወርኀዊ በዓላት
፩ እግዚአብሔር አብ
፪ ቅዱስ ሩፋኤል ሊቀ መላእክት
፫ ዘጠና ዘጠኙ ነገደ መላእክት
፬ ቅዱስ አስከናፍር
፭ አሥራ ሦስቱ ግኁሳን አባቶች
፮ ቅዱስ አርሳንዮስ ጠቢብ ገዳማዊ
፯ አቡነ ዘርዐ ቡሩክ
✥••┈┈••●◉ ✞ ◉●••┈┈••✥
✞✞✞ ለወዳጆቹ ብርሃነ መለኮቱን የገለጠ ጌታ የእኛንም ዓይነ ልቡናችንን ያብራልን:: ከበዓሉ በረከትም ያሳትፈን::✞✞✞
✞✞✞✞✞ አሜን ✞✞✞✞✞
✥••┈┈••●◉ ✞ ◉●••┈┈••✥
📖 ወስብሐት ለእግዚአብሔር 📖
📖 ወለወላዴቱ ድንግል 📖
📖 ወለመስቀሉ ክቡር 📖
📖✞✞✞✞✞📖
✞✞✞ ሃሳብ ➢
@gebrye\_comment\_bot
|❀:✧๑ ✞✞✞✞✞✞✞ ๑✧❀|:
✞✞✞ ይቀላቀሉ ➣
@mahteben\_albetsm
††† በስመ አብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ አሐዱ አምላክ አሜን ! †††
#ሰኔ_፴
#ቅዱስ_ዮሐንስ_መጥምቅ
➢ቅዱስ ወንጌል ላይ ከእመቤታችን ቀጥሎ የነ ዘካርያስን ቤተሰብ ያህል ክብሩ የተገለጠለት ፍጡር ይኖራል ብሎ መናገሩ ይከብዳል።
➢ ቅዱስ ሉቃስ ወንጌሉን የጀመረው በዚህ ቅዱስ ቤተሰብ ነውና መንፈስ ቅዱስ እንዲህ ሲል አጽፎታል።
➢ "ዘካርያስ ካህኑና ቅድስት ኤልሳቤጥ በሰውና በእግዚአብሔር ፊት ያለ ነቀፋ የሚኖሩ ጻድቃን ነበሩ።" ይላቸዋል።
“ሁለቱም በጌታ ትእዛዝና ሕግጋት ሁሉ ያለ ነቀፋ እየሄዱ በእግዚአብሔር ፊት ጻድቃን ነበሩ።”
— ሉቃስ . ፩፥፮
➢ የሰውን እንተወውና በእግዚአብሔር ፊት ያለ ነቀፋ መኖር ምን ይረቅ? ለዚህ አንክሮ (አድናቆት) ይገባል!
➢ እኒህን ቅዱሳን ባልና ሚስት ግን መካኖች በመሆናቸው ልጅ ሳይወልዱ ዘመናቸው አልፎ ነበር።
➢ እንደ ቤተ ክርስቲያን ትውፊት ዕድሜአቸው የኤልሳቤጥ ፹ የዘካርያስ ደግሞ ፻ ደርሶ ነበር። ፍጹም መታገሳቸውን የተመለከተ ጌታ ግን በስተእርጅናቸው ከሰው ሁሉ በላይ የሆነ፣ ትንቢት ለብቻው የተነገረለት
“የአዋጅ ነጋሪ ቃል፦ የእግዚአብሔርን መንገድ በምድረ በዳ ጥረጉ፥ ለአምላካችንም ጐዳና በበረሀ አስተካከሉ።”
— ኢሳይያስ. ፵፥፫
ታላቅ ነቢይን ይሰጣቸው ዘንድ መልአከ ብሥራት ቅዱስ ገብርኤልን ላከላቸው።
➢ ቅዱስ ዘካርያስ ሰው ነውና ከደስታ ብዛት በመከራከሩ ድዳ ሆነ። ቅድስቲቷ ግን መስከረም ፳፮ ቀን ታላቁን ሰው ጸንሳ ለ፮ ወራት ራሷን ሠወረች።
➢ በስድስተኛው ወር የፍጥረት ሁሉ ጌታ በተጸነሰ ጊዜ የአርያም ንግሥት ድንግል እመቤታችን ደጋ ደጋውን ወደ ኤልሳቤጥ መጣች። ሁለቱ ቅዱሳት የእኅትማማች ልጆች ናቸው።
➢ የአምላክ እናቱ ስትደርስና "ሰላም" ስትላቸው መንፈስ ቅዱስ በእናትና ልጅ ወርዶ ኤልሳቤጥ በምስጋና ዮሐንስ ደግሞ ገና በማኅጸን ሳለ በደስታ ዘለለ (ሰገደ)። ከዚህ በኋላ በዚህች ቀን (ሰኔ ፴) ተወልዶ አባቱ ዘካርያስ "ዮሐንስ" ሲለው አንደበቱ ተፈትቶለታል።
➢ #መጥምቀ_መለኮት_ቅዱስ_ዮሐንስ፦
➔የቅዱሳኑ ዘካርያስና ኤልሳቤጥ ልጅ፣
➔በማኅጸን ሳለ መንፈስ ቅዱስ የሞላበት፣
➔በበርሃ ያደገና በገዳማዊ ቅድስና ያጌጠ፣
➔እስራኤልን ለንስሐ ያጠመቀ፣
➔የጌታችንን መንገድ የጠረገ፣
➔ጌታውን ያጠመቀና
➔ስለ እውነት አንገቱን የተቆረጠ ታላቅ ሰው ነው።
➢ #ስለዚህም_ቤተ_ክርስቲያን፦
ነቢይ፣ ሐዋርያ፣ ሰማዕት፣ ጻድቅ፣ ገዳማዊ፣ መጥምቀ መለኮት፣ ጸያሔ ፍኖት፣ ቃለ ዐዋዲ ብላ ታከብረዋለች።
✥••┈┈••●◉ ✞ ◉●••┈┈••✥
#የመጥምቀ_መለኮት_ቅዱስ_ዮሀንስ_ረድኤት_በረከት_ከሁላችን_ጋር_ይሁን።
✞✞✞✞✞ አሜን ✞✞✞✞✞
✥••┈┈••●◉ ✞ ◉●••┈┈••✥
📖 ወስብሐት ለእግዚአብሔር 📖
📖 ወለወላዴቱ ድንግል 📖
📖 ወለመስቀሉ ክቡር 📖
📖✞✞✞✞✞📖
✞✞✞ ሃሳብ ➢
@gebrye_comment_bot
|❀:✧๑ ✞✞✞✞✞✞✞ ๑✧❀|:
✞✞✞ ይቀላቀሉ ➣
@mahteben_albetsm
††† በስመ አብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ አሐዱ አምላክ አሜን ! †††
#እንኳን_ለዐቢይ_ጾም_በሰላም_አደረሰን!!
#የካቲት ፳፱
#ዐቢይ_ጾም
➢ ዐቢይ ለምን ተባለ ቢሉ ‹‹ዐበየ›› ማለት ከፍ አለ ማለት ሲሆን ከዚህም ግስ አቢይ የሚለው ቅጽል ይገኛል፡፡ዐቢይ ማለት ከፍ ያለ ትልቅ ማለት ነው፡፡
#ዐቢይ_ጾም_የተባለበት_ምክንያት፡-
፩. ጌታችን መድኃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ የጾመው ጾም ስለሆነ
፪. በቀኑ ቁጥር ከሌሎች አጽዋማት የሚበልጥ ስለሆነ
፫. ሦስቱ ታላላቅ የሰይጣን ፈተናዎች ማለትም 'ትዕቢት' 'ስስት' 'ፍቅረ ነዋይ' ድል የተመቱበት ስለሆነ ነው፡፡
➢ በቤተክርስቲያን ስያሜ መሰረት በዐቢይ ጾም ውስጥ የሚውሉ ሰንበታት እያንዳንዳቸው መጠሪያ ስም ሲኖራቸው የመጀመሪያው ሰንበትም ዘወረደ ይባላል፡፡
#ዘወረደ
➢ የዐቢይ ጾም የመጀመሪያው ሰንበት ሲሆን ይህም ቅድመ ዓለም የነበረ ዓለምን ፈጥሮ የሚኖር አልፋና ኦሜጋ ከሰማየ ሰማያት መውረዱንና ከእመቤታችን ከቅድስተ ቅዱሳን ከንጽሕተ ንጹሐን ከድንግል ማርያም መወለዱን የሚያመለክት ሥያሜ ነው፡፡
✥••┈┈••●◉ ✞ ◉●••┈┈••✥
✞✞✞" ዘወረደ ብለን የጀመርነውን ጾም ሆሳህና ብለን ለመጨረስ ያብቃን "✞✞✞
✞✞✞✞✞ አሜን ✞✞✞✞✞
✥••┈┈••●◉ ✞ ◉●••┈┈••✥
📖 ወስብሐት ለእግዚአብሔር 📖
📖 ወለወላዴቱ ድንግል 📖
📖 ወለመስቀሉ ክቡር 📖
📖✞✞✞✞✞📖
✞✞✞ ሃሳብ ➢
@gebrye_comment_bot
|❀:✧๑ ✞✞✞✞✞✞✞ ๑✧❀|:
✞✞✞ ይቀላቀሉ ➣
@mahteben_albetsm
††† በስመ አብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ አሐዱ አምላክ አሜን ! †††
#ጥር ፲፭
#ፆመ_ነነዌ
➢ የነነዌ ሰዎች ለሰሩት ሐጢያት የእግዚአብሔርን ምህረትና ይቅርታ ለመጠየቅ የፆሙትን ለማስታወስ ነው።
➢ እኛ የምንፆመው የበፊቱን ለማስታወስ ብቻ ሳይሆን ዋናው በአንድ ላይ የህብረት ንስሃ ለመግባት እና አምላክን ይቅርታ ለመጠየቅ ነው። በክርስቲያን ህይወት ውስጥ ንስሐ ትልቅ የእምነት አካል ነው።
➢ የነነዌ ሰዎች እንዳጠፉ ሁሉ እኛም እናጠፍለን፤ የነነዌ ሰዎች ንስሐ እንደገቡ እኛም ንስሐ እንገባለን፤ እግዚአብሔርም ይቅር ይለናል።
#የነነዌ_ፆም_ታሪክ
1. ➢ ዮናስ ወደ ነነዌ ከተማ እንዲሄድ ታዘዘ እግዚአብሔር ነብዩ ዮናስን ወደ ነነዌ ከተማ እንዲሄድ አዘዘው፡፡ ዮናስ ግን ወደ ነነዌ ሂድና ስበክ ሲባል እምቢ ብሎ ወደ ተርሴስ ለመኰብለል በመርከብ ተሳፈረ፡፡
➔ ማዕበል በመነሳቱም ወደ ባህር ተወረወረ፡፡ እግዚአብሔር ግን ዮናስን ሊያርመው፤ አስተምሮ ሊልከው ባህር ውስጥ አሳ አንበሪ አዘጋጀለት፡፡
➔ ዮናስም ወደባህር ሲጣል ከአሳ አንበሪ ሆድ ለ፫ ቀን በመቆየት የጌታ ምሳሌ ሆነ፡፡
"" እግዚአብሔርም ዮናስን የሚውጥ ታላቅ ዓሣ አሰናዳ፤ ዮናስም ሦስት ቀንና ሦስት ሌሊት በዓሣው ሆድ ውስጥ ነበረ። ዮናስም በዓሣው ሆድ ውስጥ ሆኖ ወደ አምላኩ ወደ እግዚአብሔር ጸለየ፥ እንዲህም አለ፦በመከራዬ ሳለሁ ወደ አምላኬ ወደ እግዚአብሔር ጮኽሁ፥ እርሱም ሰማኝ፤ በሲኦልም ሆድ ውስጥ ሆኜ ጮኽሁ፥ ቃሌንም አዳመጥህ።""
— ትንቢተ ዮናስ ፪÷፩-፫
2. ➢ ዮናስ ነነዌ ገብቶ አጭር የሆነ ስብከት ሰበከ ከአሳ አንበሪ ሆድ ከ፫ ቀን በኋላ የተተፋው ዮናስ ወደ ነነዌ ከተማ በቀጥታ ሄደ፡፡ እሱም ወደ ነነዌ ከተማ ከገባ በኋላ አጭር ቃል ብቻ ተናገረ…
‹‹በ፫ ቀን ውስጥ ነነዌ ትገለበጣለች አለ።››
“ዮናስም የአንድ ቀን መንገድ ያህል ወደ ከተማይቱ ውስጥ ሊገባ ጀመረ፤ ጮኾም፦ በሦስት ቀን ውስጥ ነነዌ ትገለበጣለች አለ።”
— ትንቢተ ዮናስ ፫÷፬
3. ➢ በነነዌ የ ፫ ቀን ፆም ታወጀ
ንጉሱ ታላቅ አዋጅ አወጣ እኛ በበደልነው በደል ሕጻናት ሆኑ እንሰሳት መቀጣታቸው አይቀርምና ሁሉም ይጹሙ በእጃቸው ካለው ግፍ ይመለሱ፤ ንጉሱም ከዙፋኑ ተነሥቶ መጐናጸፊያውን አወለቀ ማቅም ለበሰ፥ በአመድም ላይ ተቀመጠ፡፡
"" የነነዌም ሰዎች እግዚአብሔርን አመኑ፤ ለጾም አዋጅ ነገሩ፥ ከታላቁም ጀምሮ እስከ ታናሹ ድረስ ማቅ ለበሱ። ወሬውም ወደ ነነዌ ንጉሥ ደረሰ፤ እርሱም ከዙፋኑ ተነሥቶ መጐናጸፊያውን አወለቀ ማቅም ለበሰ፥ በአመድም ላይ ተቀመጠ።
— ትንቢተ ዮናስ ፫÷፭-፮
4. ➢ እግዚአብሔርም ለነነዌ ምህረት አደረገ፤ ዮናስ ግን ተበሳጨ
‹‹እግዚአብሔርም ከክፉ መንገዳቸው እንደተመለሱ ሥራቸውን አየ እግዚአብሔርም ያደርግባቸው ዘንድ በተናገረው ክፉ ነገር ተጸጽቶ አላደረገውም።››
“እግዚአብሔርም ከክፉ መንገዳቸው እንደተመለሱ ሥራቸውን አየ፤ እግዚአብሔርም ያደርግባቸው ዘንድ በተናገረው ክፉ ነገር ተጸጽቶ አላደረገውም።”
—ትንቢተ ዮናስ ፫÷፲
➔ #ዮናስ_ግን_ተበሳጨ
‹‹ አቤቱ፥ እለምንሃለሁ በአገሬ ሳለሁ የተናገርሁት ይህ አልነበረምን? አንተ ቸርና ይቅር ባይ፥ ታጋሽም፥ ምሕረትህም የበዛ፥ ከክፉው ነገርም የተነሣ የምትጸጸት አምላክ እንደ ሆንህ አውቄ ነበርና ስለዚህ ወደ ተርሴስ ለመኰብለል ፈጥኜ ነበር።››
“ወደ እግዚአብሔርም ጸለየና፦ አቤቱ፥ እለምንሃለሁ፤ በአገሬ ሳለሁ የተናገርሁት ይህ አልነበረምን? አንተ ቸርና ይቅር ባይ፥ ታጋሽም፥ ምሕረትህም የበዛ፥ ከክፉው ነገርም የተነሣ የምትጸጸት አምላክ እንደ ሆንህ አውቄ ነበርና ስለዚህ ወደ ተርሴስ ለመኰብለል ፈጥኜ ነበር።”
— ትንቢተ ዮናስ ፬÷፪
5. ➔ እግዚአብሔርም ዮናስን አስተማረው ፈጣሪም የከተማውን መቃጠል ለማየት ተራራ ላይ የተቀመጠውን ዮናስን በዕለት በቅላ ከጸሀይ ሙቀት ኣሳርፋው በዕለት በደረቀችው ቅል ሲበሳጭ እንዲህ ብሎ አስተማረው፡፡
‹‹ አንተ ትበቅል ዘንድ ላልደከምህባት ላላሳደግሃትም፥ በአንድ ሌሊት ለበቀለች፥ በአንድ ሌሊትም ለደረቀችው ቅል አዝነሃል። እኔስ ቀኛቸውንና ግራቸውን የማይለዩ ከመቶ ሀያ ሺህ የሚበልጡ ሰዎችና ብዙ እንስሶች ላሉባት ለታላቂቱ ከተማ ለነነዌ አላዝንምን? አለው።››
"እግዚአብሔርም፦ አንተ ትበቅል ዘንድ ላልደከምህባት ላላሳደግሃትም፥ በአንድ ሌሊት ለበቀለች፥ በአንድ ሌሊትም ለደረቀችው ቅል አዝነሃል። እኔስ ቀኛቸውንና ግራቸውን የማይለዩ ከመቶ ሀያ ሺህ የሚበልጡ ሰዎችና ብዙ እንስሶች ላሉባት ለታላቂቱ ከተማ ለነነዌ አላዝንምን? አለው።"
— ትንቢተ ዮናስ ፬÷፲-፲፩
✥••┈┈••●◉ ✞ ◉●••┈┈••✥
"✞✞✞ _ለነነዌ ህዝብ ምህረትን የላከ አምላክ ለእኛ ለኢትዮጵያውያን ምህረቱን ይልክልን ፆሙ ከኃጥያት መመለሻ የመንግስቱን መውረሻ ይድርግልን ምህረትን ያድለን_። ✞✞✞"
✞✞✞✞✞ አሜን ✞✞✞✞✞
✥••┈┈••●◉ ✞ ◉●••┈┈••✥
📖 ወስብሐት ለእግዚአብሔር 📖
📖 ወለወላዴቱ ድንግል 📖
📖 ወለመስቀሉ ክቡር 📖
📖✞✞✞✞✞📖
✞✞✞ ሃሳብ ➢
@gebrye_comment_bot
|❀:✧๑ ✞✞✞✞✞✞✞ ๑✧❀|:
✞✞✞ ይቀላቀሉ ➣
@mahteben_albetsm
▬▱፲፪ ▱▬ ፲፪ ▬▱፲፪▱▬
🌷ግእዝን በርቀት ፲፪ኛ ዙር 🌷
እንኳን ለቅዱስ ሚካኤል ዓመታዊ
ክብረ በዓል በሰላም አደረሳችኹ!
እንደሚታወቀው ግእዝን በርቀት በተሰኘ መርሐ ግብር በእግዚአብሔር መልካም ፈቃድ እስካኹን በ፲፩ ዙሮች በብዙ ሺሕ የሚቈጠሩ ተማሪዎችን ከግእዝ ቋንቋ ጋራ ለማስተዋወቅ ተሞክሯል።
አኹን ደግሞ በ ፲፪ኛ ዙር በርካታ ተማሪዎችን
በክረምቱ ለማስተማር ዝግጅት ተደርጓል። በመኾኑም እስካኹን ከ፩ኛ እስከ ፲፩ኛ ዙር ላልተማሩ ብቻ ፣ የግእዝ ዕውቀት ለሌላቸው፣ ለጀማሪዎች የሚኾን ትምህርት ለመስጠት ስለታሰበ የግእዝ ቋንቋን መማር ለሚፈልግ ማንኛውም ሰው ኹሉ መልእክቱን በማስተላለፍ ከታች የተቀመጠውን ሊንኩን እንድትሰጡ አደራ እያልኹ የምዝገባ ጊዜው ዐጭር በመኾኑ የሚጠናቀቅበትንና ትምህርቱ የሚጀመርበትን
ጊዜ በቅርቡ አሳውቃለኹ።
ትምህርቱ የተዘጋጀው ለጀማሪዎች ሲኾን
በቴሌግራም፣ ለኹለት ወራት፣ በነጻ (ያለምንም ክፍያ) ይሰጣል። ወደ ቻናሉ ለመግባት የሚከተለውን ሊንክ መጫን እና 'JOIN' ማለት
ብቻ ሲኾን ዕድሜአቸው ፲፪ ዓመትና ከዚያ በላይ የኾኑ መማር ለሚፈልጉ ኹሉ መልእክቱን እንድታስተላልፉ በታላቅ ትሕትና እጠይቃለኹ።
@geezdistance12
ግዛቸው ደጀኑ (የትምህርቱ አስተባባሪ)
ሠኔ ፲፪, ፳፻፲፭ ዓ.ም
▬▱፲፪ ▱▬ ፲፪ ▬▱፲፪▱▬
አባቱ 🍂የቁስጥንጥያ ገዢ የነበረው #ቴዎድሲዮስ
እናቱ 👏የቁስጥንጥንያ እመቤት #መርኬዛ
#ቅዱስ_ገብረ_ክርስቶስ
በግንቦት 14 ቀን ከጫጉላ ቤት የመነነበት
በስሙ በታነጸ ቤ/ክ በድምቀት ይከብራል።
🍂 ደጋግ የሆኑት በሀይማኖት በምግባር ጸንተው እግዚአብሔርን በመፍራት የሚኖሩት ቤተሰቦቹ ልጅ አልነበረቻውምና ኢየሩሳሌም ድረስ ሄደው በስለት ያገኙት ልጃቸው ነው።
በስለት ያገኙትም ስለሆነ ፦
👉 በግዕዙ ( ገብረ ክርስቶስ )
👉 በአማረኛ ( የአምላክ አገልጋይ)
በማለት ስሙን አውጥተውለታል።
🍂የንጉስ ልጅ እንደ መሆኑ በጥበብ በዕውቀት አግዚአብሔር በመፍራት አሳድገውታል።
🍂ለአካለ መጠን በደረሰም ሥልጣኑን የሚረከብ ነውና ለሮሜው ንጉስ ልጅ ከሆነችው ጋር አጭተው በስርዐታቸው አጋብተዋቸዋል።
🍂 በምድራዊ ሕይወት ሰማያውያን መላእክትን በሚያስመስለው በድንግልና ሕይወት ይኖር ዘንድ ውሳኔው ነውና፤ ይህንን ነገር 🍂ለሙሽሪት አስረድቷት እግዚአብሔር ከአንቻ ጋር ይሁን ብሏት የክርስቶስ ሙሽራ ሆኖ በሌሊት ከጫጉላው ወጥቶ በመርከብ ተሳፍሮ ርቆ ሄዷል።
🍂አባቱም በወታደረቹ ቢያስፈልገው ሊያገኘው አልቻለም። እርሱ ግን በእንዲት ቤተክርስቲያን አጸድ ስር ከነዳያን ጋር ተቀምቶ አራሱን ሰውሮ 👉 15 ዓመት ያህል ኖሯል። በኋላም ለአንድ መነኩሴ የእርሱ ነገር ተገልጾለት ለህዝቡ ቢናገርበት ታወቀብኝ ብሎ ርቆ ሄዷል።
🍂በእግዚአብሔረም ፍቃድ ወደ አባት እናቴ ቤት ሄጄ በዚያ እየተመጸወትኩ እኖራለው ብሎ ሂዷል። በዚያም ትራፊ አየተደፋበት ውሾች እንዲበሉት አጥንች ቢደፉበትም ፤ውሾቹ ግን የእግሩን ቁስል ይልሱለት ነበር።በዚህም ሕይወት 👉 15 ዓመት ያህል ኑሯል።
🍂ቅዱሱም የ30 ዓመት የሕይወቱን ዜና በክርታስ ይጽፍ ነበር እና በጥር 14 ቀን በንጽሕና በቅድስና ሕይወት የክርስቶስ ሙሽራ እንደሆነ ነፍሱ ከስጋው ተለይታለች።
🍂የጻፈውም ተነበበ በቤተ መንግስቱም ታላቅ ሀዘን ተደረገ በዚዪኑም ቀን በክብር ገንዘው ቀብረውታል።
በዚያም ጊዜ ብዙ ድውያነ ሰጋ ተፈውሰዋል። ህዝቡም ከሚገባው በላይ በዝቶ ነበረና ንጉሡ የወርቅ ገንዘብን እየበተነ 🍂ህዝቡ ገንዘቡን ሲለቅም በዚያኑ ባረፈበት ቀን ጥር 14 ቀን ሊቀ ጳጳሱ በተገኙበት ስረዓተ ቀብሩ ተፈጽሟል።
🍂 በግንቦት 14 ቀን ከጫጉላ ቤት የመነነበት
በስሙ በታነጸ ቤ/ክ በድምቀት ይከብራል።
ወረኃዊ መታሰቢያውም በ14 ነው።
👏 የቅዱስ አባታችን የገብረ ክርስቶስ ረድኤት በረከቱ ከሁላችን ጋር ይሁን 👏
🍂 ሀገራችንን በቃልኪዳኑ ይጠብቅልን 🍂
🙏 🙏 🙏
የኢኦተቤ መገናኛ ብዙኀን አገልግሎት ሥርጭት ድርጅት/ EOTC Broadcasting Service Agency/
➽ የዩቲዮብ ገጻችን
http://www.youtube.com/c/eotctv
➽ የፌስ ቡክ ገጻችንን
https://www.facebook.com/eotctvchannel
††† በስመ አብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ አሐዱ አምላክ አሜን ! †††
#እንኳን_ለቸሪ_መድኃኔዓለም_አመታዊ_በአል_በሰላም_አደረሳቹ_አደረሰን
#መድኃኔዓለም_ክርስቶስ
➢ ጌታችን መድኃኔ ዓለም ክርስቶስ ለእኛ ሲል በፈጸመው የማዳን ሥራ ክፉዎች አይሁድ ከምሽቱ ሦስት ሰዓት ጌቴሴማኒ ውስጥ ያዙት።
➢ ሙሉውን ሌሊት ከቀያፋ ወደ ሐና፣ ከሐና ወደ ቀያፋ ሲያመላልሱት አስረው ሲደበድቡት አድረዋል።
➢ ዝም ቢላቸው ዓይኑን ሸፍነው በጥፊ መቱት።
➢ ምራቃቸውን ተፉበት፤ ዘበቱበት።
➢ ራሱንም በዘንግ መቱት።
#እርሱ_ግን_ሁሉን_ታገሰ።
➢ በጧት ከገዢው ዘንድ ሞት እንዲፈረድበት አቀረቡት። በሠለስት (ሦስት ሰዓት ላይ) አካሉ እስኪያልቅ እየተዘባበቱ ስድስት ሺህ ስድስት መቶ ስልሳ ስድስት (፷፮፻፷፮) ገረፉት።
➢ ሊቶስጥሮስ አደባባይ ላይ እርጥብ መስቀል አሸክመው ወደ ቀራንዮ ወሰዱት። ስድስት ሰዓት ላይ በረዣዥም ብረቶች አምስት ቦታ ላይ ቸንክረው ሰቀሉት። ሰባት ታላላቅ ተአምራት በምድርና በሰማይ ታዩ።
ዓለም በጨለማ ሳለች ጌታ በመስቀል ላይ ሰባት ቃላትን ተናገረ። ከቀኑ ዘጠኝ ሰዓት አካባቢ በባሕርይ ሥልጣኑ ቅድስት ነፍሱን ከቅዱስ ሥጋው ለየ።
➢ በዚያች ሰዓትም ወደ ሲዖል ወርዶ የታሠሩትን ሁሉ ፈታ። አሥራ አንድ ሰዓት ላይ ደጋጉ ዮሴፍና ኒቆዲሞስ ከታላቅ ክብርና ሐዘን ጋር በአዲስ መቃብር ቀበሩት።
➢ በዚያች ቀን ድንግል ማርያም ልቧ በሐዘን ተቃጠለ። ወዳጁ ቅዱስ ዮሐንስም ፍፁም ልቅሶን አለቀሰ። ቅዱሳት አንስት በዋይታ ዋሉ።
➢ ፈጣሪያችን ኢየሱስ ክርስቶስ የተሰቀለው መጋቢት ፳፯ ቀን ቢሆንም በዓሉ ወደ ጥቅምት እንዲመጣ ያደረጉት አበው ሊቃውንት ናቸው። ምክንያቱም ብዙ ጊዜ መጋቢት ፳፯ የሚውለው ዓቢይ ጾም ውስጥ በመሆኑና የንግሥ በዓላት በዓቢይ ጾም ስለማይፈቀዱ ነው።
➢ ምንም እንኳ በቅርብ ጊዜ በዓቢይ ጾም የሚያነግሡ አንዳንድ አብያተ ክርስቲያናት ቢኖሩም አባቶቻችን ግን እንዲህ ያለውን ሥርዓት አላቆዩልንም። ከበሮና የቸብቸቦ ዝማሬም በወቅቱ የተፈቀደ አይደለም። በዚህም ምክንያት የበዓለ ስቅለት ንግሡ ወደ ጥቅምት ፳፯ ሲመጣ፣ የመጋቢት ፭ የአቡነ ገብረ መንፈስ ቅዱስ ንግሥ ወደ ጥቅምት ፭፣ የመጋቢት ፲ መስቀል ወደ መስከረም ፲፯ መጥቶ እንዲከበር ሆኗል።
#ጥቅምት_፳፯ቀንየሚከበሩዓመታየቅዱሳንበዓላት
፩. መድኃኔዓለም ክርስቶስ
፪.ቅዱስ መቃርስ ብጹዓዊ
፫.አቡነ መብዓ ጽዮን ጻድቅ
፬.አባ ጽጌ ድንግል ዘወለቃ
#ወርኀዊ\በዓላት
፩.ቅዱስ መቃርስ (የመነኮሳት ሁሉ አለቃ)
፪.ቅዱስ ያዕቆብ ዘግሙድ
፫.ቅዱስ ገላውዴዎስ ሰማዕት (ንጉሠ ኢትዮጵያ)
፬.ቅዱስ ቢፋሞን ጻድቅና ሰማዕት
፭.ማር ቅዱስ ፊቅጦር ሰማዕት
በእውነት ደዌያችንን ተቀበለ ሕመማችንንም ተሸክሞአል፤ እኛ ግን እንደ ተመታ በእግዚአብሔርም እንደ ተቀሠፈ እንደ ተቸገረም ቈጠርነው። እርሱ ግን ስለ መተላለፋችን ቈሰለ፥ ስለ በደላችንም ደቀቀ፤ የደኅንነታችንም ተግሣጽ በእርሱ ላይ ነበረ፥ በእርሱም ቍስል እኛ ተፈወስን።
ኢሳይያስ ፶፫÷፬-፭
✥••┈┈••●◉ ✞ ◉●••┈┈••✥
#ከቸሩ_መድኃኔዓለም_ፍቅሩ_ረድኤት_በረከቱ_ይደርብን_መልካም_እለተ_ሰንበት
✞✞✞✞✞ አሜን ✞✞✞✞✞
📖 ወስብሐት ለእግዚአብሔር 📖
📖 ወለወላዴቱ ድንግል 📖
📖 ወለመስቀሉ ክቡር 📖
📖✞✞✞✞✞📖
✞✞✞ ሃሳብ ➢
@gebrye_comment_bot
|❀:✧๑ ✞✞✞✞✞✞✞ ๑✧❀|:
✞✞✞ ይቀላቀሉ ➣
@mahteben_albetsm
††† በስመ አብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ አሐዱ አምላክ አሜን ! †††
ሰኔ ፯
ቅዱስ ያዕቆብ ዘሥሩግ
➢ በቤተ ክርስቲያን ታሪክ በደራሲነታቸው፣ በወንጌል አገልግሎታቸውና በቅድስናቸው ከተመሠከረላቸው ዐበይት ሊቃውንት አንዱ ቅዱስ ያዕቆብ ዘሥሩግ ነው።
➢ ሊቁ የተወለደው መጋቢት ፳፯ ቀን በ፬፻፴፫ ዓ.ም ሲሆን ሃገሩ ሶርያ ነው። ወላጆቹ ክርስቲያኖች ለዚያውም አባቱ ሊቀ ካህናት ነበር። ቅዱስ ያዕቆብ ገና በልጅነቱ ጀምሮ ጸጋ እግዚአብሔር የጠራው ነውና በብዙ ነገሩ የተለየ ነበር።
➢ አንድ ቀን በዕለተ ሰንበት ገና በሦስት ዓመቱ እናቱ አቅፋ ወደ ቤተ መቅደስ ወሰደችው። ምዕመናን ቅዱስ ሥጋውንና ክቡር ደሙን ሲቀበሉ ሕፃኑ ያዕቆብም ይቆርብ ዘንድ ቀረበ። ሊቀ ጳጳሱ ደሙን በዕርፈ መስቀል ሊያቀብለው ሲል መልአኩ መጥቶ "በጽዋው ጋተው" አለው። የጌታን ደም በጽዋ ቢጠጣ ምሥጢር ተገለጸለትና "አንሰ እፈርሕ ሠለስተ ግብራተ - እኔስ ሦስት ነገሮች ያስፈሩኛል።" ሲል አሰምቶ ተናገረ።
ጳጳሱና ሕዝቡ ወደ ሕፃኑ ያዕቆብ ቀርበው "ምን ምን?" አሉት።
#እርሱም፦
፩.ነፍሴ ከሥጋየ ስትለይ
፪.ቅድመ እግዚአብሔር ለፍርድ ስቀርብ
፫.ከፈጣሪዬ የፍርድ ቃል ሲወጣ አላቸው።
ያን ጊዜ ሕዝቡና ሊቀ ጳጳሳቱ "እግዚአብሔር በዚህ ሕፃን አድሮ ዘለፈን።" እያሉ ለንስሐ በቅተዋል።
➢ ቅዱስ ያዕቆብ ሰባት ዓመት ሲሞላው ይማር ብለው ወደ ጉባዔ አስገቡት። በአምስት ዓመታት ብሉይ ከሐዲስ ጠንቅቆ በአሥራ ሁለት ዓመቱ ሊቅ ሆኗል። በዚህ ወቅት የነበሩ ታላላቅ ሊቃነ ጳጳሳት ወደ እርሱ ተሰብስበው "እንግዳ ድርሰት ድረስልን። አዲስ ምሥጢር ንገረን?" አሉት። እርሱ ግን ሲቻለው ስለ ትሕትና "አልችልም" አላቸው።
➢ "እንግዲያውስ ትንቢተ ሕዝቅኤልን ተርጉምልን?" ቢሉት ባጭር ታጥቆ አመሥጥሮላቸው ተደስተዋል። ፈጣሪንም አመስግነዋል።
# ቅዱስ ያዕቆብ ከዚህ በኋላ ወደ ገዳም ገብቶ ትሕርምተ አበውን፣ ዕጸበ ገዳምን፣ ሕይወተ ቅዱሳንን በተግባር ተምሯል። በድንግልናው ጸንቶ ጾምና ጸሎትን እያዘወተረ ኑሯል። በፈቃደ እግዚአብሔር የሥሩግ (በኤፍራጥስና ጤግሮስ ወንዞች መካከል የምትገኝ የሶርያ ግዛት ናት።) ኤጲስ ቆጶስ ሆኖ ተሹሟል።
#በዘመኑም፦
፩.የ፬፻፶፩ን የኬልቄዶን ጉባኤ አውግዟል።
፪.ብዙ መናፍቃንን ተከራክሮ ምላሽ አሳጥቷል።
፫.በወንጌል አገልግሎት መልካም እረኝነቱን አሳይቷል።
፬.ዛሬ የምንገለገልበትን መጽሐፈ ቅዳሴውን ጨምሮ በርካታ መንፈሳዊ ድርሰቶችን ደርሷል።
➢ በመጨረሻም ከብዙ የተጋድሎና የቅድስና ዓመታት በኋላ በተወለደ በሰባ ሁለት ዓመቱ በ፭፻፭ ዓ.ም በዚህች ቀን ዐርፏል። አንዳንድ ምንጮች ደግሞ ሰኔ ፳፯ ቀን እንዳረፈ ይናገራሉ። ቅዱስ ያዕቆብ ዘሥሩግ ለቤተ ክርስቲያን የቁርጥ ቀን ተወዳጅ ልጇ ነውና በእጅጉ ታከብረዋለች።
➢ ሰኔ ፯ ቀን የሚከበሩ ዓመታዊ የቅዱሳን በዓላት
፩.ቅዱስ ያዕቆብ ዘሥሩግ
፪.ቅዱስ፣ ቡሩክና አሸናፊ አባ አበስኪሮን (ታላቅ ሰማዕትና ባለ ብዙ ተአምራት)
፫.አሥራ ስድስት ሺህ ሰማዕታት (በአንድ ቀን የተገደሉ)
፬.የእመቤታችን ቤተ ክርስቲያን የተከፈተበት በዓል (ከአንድ ሺ ዓመታት በፊት ምስር (CAIRO) ውስጥ)
➢ ወርኀዊ በዓላት
፩.ሥሉስ ቅዱስ (አብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ)
፪.አባ ጊዮርጊስ ዘጋስጫ
፫.አባ ሲኖዳ (የባሕታውያን አለቃ)
፬.አባ ዳንኤል ዘገዳመ ሲሐት
፭.አባ ባውላ ገዳማዊ
፮.ቅዱስ አትናቴዎስ ሐዋርያዊ
፯.ቅዱስ አግናጥዮስ (ለአንበሳ የተሰጠ)
"ይህንን እዘዝና አስተምር። በቃልና በኑሮ በፍቅርም በእምነትም በንጽህናም ለሚያምኑቱ ምሳሌ ሁን እንጂ ማንም ታናሽነትህን አይናቀው። እስክመጣ ድረስ ለማንበብና ለመምከር ለማስተማርም ተጠንቀቅ።"
፩ጢሞ ፬፥፲፩-፲፫
✥••┈┈••●◉ ✞ ◉●••┈┈••✥
አምላከ ቅዱሳን ከታላቁ ሊቅ በረከት ይክፈለን።
✞✞✞✞✞ አሜን ✞ች✞✞✞✞
✥••┈┈••●◉ ✞ ◉●••┈┈••✥
📖 ወስብሐት ለእግዚአብሔር 📖
📖 ወለወላዴቱ ድንግል 📖
📖 ወለመስቀሉ ክቡር 📖
📖✞✞✞✞✞📖
✞✞✞ ሃሳብ ➢
@gebrye_comment_bot
|❀:✧๑ ✞✞✞✞✞✞✞ ๑✧❀|:
✞✞✞ ይቀላቀሉ ➣
@mahteben_albetsm
††† በስመ አብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ አሐዱ አምላክ አሜን ! †††
#የካቲት ፳፭-፮-፳፺፲፬
#ፓትርያርክ_ብፁዕ_ወቅዱስ_አቡነ_መርቆሬዎስ
➤ #ብፁዕ_ወቅዱስ_አቡነ_መርቆሬዎስ በፊት ስማቸው አባ ዘሊባኖስ ፈንታ የሚባሉት ብፁዕ ወቅዱስ ፓትርያርክ አቡነ መርቆሬዎስ፣ በጎንደር ክፍለ ሀገር በደብረ ታቦር አውራጃ በአለታ ወረዳ አረጊት ኪዳነ ምሕረት በተባለችው ገዳም ሰበካ፣ ልዩ ስሙ ማር ምድር በ1930 ዓ.ም.፣ ከብላታ ፈንታ ተሰማና ከወ/ሮ ለምለም ገሰሰ ተወለዱ፡፡
➤ ማዕርገ ምንኵስናን በጣና ገዳም ዳጋ እስጢፋኖስ በመግባትከመምህር ኃይለ ማርያም(በኋላ የባሕር ዳር ቅዱስ ጊዮርጊስ መልአከ ገነት) በ1961 ዓ.ም. የተቀበሉ ሲሆን፣ በዚሁ ዓመት ማዕርገ ቅስናን፣ ከጎጃም ሀገረ ስብከት ሊቀ ጳጳስ ከብፁዕ አቡነ ማርቆስ ተቀብለዋል፡፡
➤ ባላቸው በቂ የቤተ ክርስቲያን ዕውቀትና ባሳዩትም የመንፈሳዊ አገልግሎትና የሥራ ወዳድነት፣ ቤተ ክርስቲያኗ ጥር 13 ቀን 1971 ዓ.ም. ባደረገችው የ13 ኤጲስ ቆጶሳት ምርጫ፣ በቅዱስ ሲኖዶስ፣ በካህናትና በምእመናን በከፍተኛ ድምፅ ተመርጠው የኦጋዴን አውራጃ ኤጲስ ቆጶስ ኾነው ተሾመዋል፡፡
➤ ብፁዕ አቡነ መርቆሬዎስ፣ በ1971 ዓ.ም. ወደ ጎንደር ሀገረ ስብከት ተዛውረዋል፡፡
➤ ብፁዕ ወቅዱስ አቡነ መርቆሬዎስ፣ 4ኛ ፓትርያርክ ኾነው የተሾሙት፣ ነሐሴ 29 ቀን 1980 ዓ.ም. ሲኾን፣ በፖሊቲካዊ ግፊትና ጫና መንበራቸውን ለቀው ከሀገር ከመውጣታቸው በፊት እስከ ነሐሴ 28 ቀን 1983 ዓ.ም. ድረስ ለቤተ ክርስቲያን አጠቃላይ አመራር ሲሰጡ ቆይተዋል፡፡
➤ ከ26 ዓመታት ስደት በኋላ፣ ሐምሌ 25 ቀን 2010 ዓ.ም.፣ በስሙ በተሠየሙበት በሰማዕቱ ቅዱስ መርቆሬዎስ ክብረ በዓል ወደ ቅድስት ሀገራቸው ኢትዮጵያ መመለሳቸውን፣ ይታወቃል፡፡
➤ አራተኛው የኢትዮጵያ ፓትርያርክ ብፁዕ ወቅዱስ አቡነ መርቆሬዎስ ከቀናት በፊት ህመም አጋጥሟቸው በሀሌሉያ ሆስፒታል በህክምና ላይ የነበሩ ሲሆን ዛሬ ከዚህ ዓለም ድካም ማረፋቸው ተነግሯል።
#የብፁዕ_ወቅዱስ_አቡነ_መርቆሬዎስ_በረከታቸው_ይደርብን።
#አሜን_አሜን_አሜን
✍"ሰው ነኝ" የሚል ኹሉ ይህንን የሞዐ ተዋሕዶ ጥሪ ይፈጽም!
በዚህ ሊንክ በመግባት sign በማድረግ ለተዋህዶ ድምፅ እንሁን ጥያቄዎቻችን ይመለሱልን አላፊነታችን እንወጣ ሼር በማድረግ ለተዋህዶ ልጆች ያጋሩ።
(እዚህ በመጫንም ድምጹን ያሰማ፤ ይፈርም https://chng.it/TzzhV2Wr5C )
የሞዐ ተዋሕዶ ጥሪ ለኦርቶዶክሳዊያንና በማንኛውም የእምነት መሥመር ውስጥ ለሚገኙ እና ለሰው ልጅ እኩልነት፣ በነፍስ የመኖር መብት፣ የዜግነት ክብር የማግኘት እና አምልኮተ እግዚአብሔርን በነፃነት የመፈጸም መብት ለምታምኑ ሁሉ፡-
ጉዳዩ፡- የኦርቶዶክስ ተዋህዶ ክርስትናን ማንነት (Cultural and religious identity) እና የኦርቶዶክስ ክርስቲያንን ዘር ማጥፋትን (Orthodox Christian Genocide ) ስለ መከላከል ፡-
የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤተ ክርስቲያንን እንደ አንድ የሃይማኖት ሥርዓታዊ ተቋም ለማዳከምና ተከታዮቿ ክርስቲያኖችን ለማጥፋት ግልጽ ርእዮተ ዓለማዊ፣ ሥርዓታዊና መዋቅራዊ ጥቃት ከተጀመረበት ከ1966 ዓ.ም. እስከ ዛሬ ድረስ ጥቃቱ ቀጥሏል። በአብዮት፣ በብሔር እኩልነት፣ በመንግሥት ለውጥ እና በጎሣ ግጭት ስም ተሸፍኖ ሲካሄድ ቆይቶ በአሁኑ ጊዜ ወደ ግልጽ ጥቃት ተሸጋግሯል።
በተለም ባለፉት 4 ዓመታት በቤኒሻንጉል ጉምዝ፣ በደቡብ ክልል፣ በኦሮሚያ ክልል፣ በአዲስ አባባ ከተማ፣ በአማራ ክልል ልዩ ዞኖች፣ በሶማሌ ክልል፣ በትግራይ ክልል አክሱም ዳንግላት ማርያም ወዘተ ኦርቶዶክሳዊያን በሃይማኖታቸው ምክንያት ከፍተኛ ፍጅትና ጥቃት ተፈጽሞባቸዋል፣ አቢያተ ክርስቲያናት ተቃጥለዋል፣ ክርስቲያኖች ተፈናቅለው ተሰዳዋል። ኦርቶዶክሳዊንን ማግለል፣ መግደልና ሁለገብ ጥቃት ሥር ማዋል በግልጽ ቢካሄድም አጥፊዎች ሲቀጡ፣ የዜጎችን ደኅንነት መጠበቅ የሚገባው የመንግሥት መዋቅር ግዴታውን ከመወጣት ይልቅ ሲሸፋፍን ማየት የተለመደ ሆኗል።
ኦርቶዶክሳዊያንን በገዛ አገራቸው በዘር በቋንቋ እየከፋፈሉ፣ ድብቅ የዘር ፖለቲካ አጀንዳን ወደ ፖለቲካዊ ርእዮት በማሳደግ፣ በመደራጀት፣ በመዋቀርና አመራር በመሥጠት ኦርቶዶክሳውያንን የማጥፋት ሂደቱን ዝም ሊባል ከማይገባው ደረጃ ላይ ደርሷል።
በመሆኑም የፌዴራል መንግሥት እና የክልል መንግሥታት እና መዋቅሮቻቸው የዜጎችን ሰላምና ደኅንነት የኃላፊነታቸውን እንዲወጡ ግፊት ለማደርግ የተባበረ ድምጽ ማሰማት ጊዜ የሚሰጠው አይደለም።
እናም “እዚህ ላይ ይበቃል” ማለት ይገባል የምትሉ ሁላችሁ ኦርቶዶክስ ክርስቲያኖች እና በሰው ልጅ እኩልነትና ክብር የምታምኑ የሌላ እምነት ተከታዮች ሁሉ ይህን ፔትሽን በመፈረም ለእውነት፣ ለፍትሕ፣ ለሰብአዊነት እንድትቆሙ ጥሪያችንን እናቀርባለን። እውነትና ፍትሕ ለዘላለም ያሸንፋሉ!!!
አስቸኳይ የመንግሥት ምላሽ የሚፈልጉ የኦርቶዶክሳዊያን ጥያቄዎች
1. በሕገመንግሥት፣ በፖለቲካ ማኒፌስቶ፣ በመደበኛ ትምህርት፣ በሚዲያና መሰል መንገዶች ኦርቶዶክሳዊ አስተምህሮንና ኦርቶዶክሳዊያንን ለጥቃት የሚያጋልጡ መልዕክቶች በአስቸኳይ በሕግ እንዲታገዱ::
2. ኦርቶዶክሳዊያንን ለይቶ ከሥራ፣ ከመንግሥት ኃላፊነት፣ ከሀብት ማፍራት እድሎች የሚያገል ከቀበሌ እስከ ፌደራል የተዘረጋው ሃይማኖታዊ መንግሥትና መዋቅር በአስቸኳይ እንዲቆምና ሃይማኖታዊ ሳይሆን ሕዝባዊ መሆኑን በተግባር እንዲያረጋግጥ::
3. ኦርቶዶክሳዊት ቤተ ክርስቲያንን በቋንቋና በተለያዩ ዘውጎች ለመከፋፈል የሚደረገው ፖለቲካዊ ጥረት በጥናትና በምርምር ስም የሚደረጉ የመከፋፈል ዘመቻዎች እና ተግባራት እንዲታደጉ::
4. በኦርቶዶክሳዊያን ላይ ያነጣጠሩ የአካል፣ የሥነልቦና፣ የኢኮኖሚ፣ የማኀበራዊ፣ የፖለቲካ፣ የማፈናቀል፣ ከአገራዊ ተሳትፎ የመገለልና የፍጅት ጥቃቶች በአስቸኳይ እንዲቆሙ::
5. እስከ አሁን የተፈጸሙ ጥቃቶች በዝርዝር ተገልጾ አጥፊዎች ለሕግ እንዲቀርቡ እና የተጎዱት እንዲካሱ::
6. በመላው አገሪቱ የተፈናቀሉ ኦርቶዶክሳዊያን ወደ ቀደመ ቦታቸው እንዲመለሱ::
7. “አዲሲቷ ኢትዮጵያ” በሚል ሽፋን ኦርቶዶክሳዊ አሻራዎችን የማጥፋት ፖለቲካዊ ሂደት በአስቸኳይ እንዲገታ እና በግልጽ ይቅርታ ተጠይቆ እርምት እንዲወሰድ::
በኢ/ኦ/ተ/ቤ/ክ የየርር ጎሮ ደ/ምህረት ቅ/ገብርኤል ቤ/ክ በደብሩ የሚደረጉ አገልግሎቶችን በsocial media በዓለም አቀፍ ደረጃ ተደራሽ ለማድረግ የተለያዩ ሚዲያዎችን እየተጠቀመ ይገኛል፡፡ እረርሶም ከዚህ በታች በተቀመጡ ማስፈንጠርያዎች (Links) በመጠቀም በየሳምንቱ ሀሙስ እና እሁድ የቀጥታ ስርጭት ሽፋን ባሉበት ሆነው ይከታተሉ፡፡ ወዳጅዎንም ይጋብዙ፡፡
Gmail Account
- yerar.goro.st.gabriel.church@gmail.com
YouTube channel
- https://www.youtube.com/channel/UCiuO3IjWWEw4Ss6M-c3dODA
Telegram Account link
- /channel/Yerar_Goro_St_Gabriel_Church
ከየረር ጎሮ ደብረ ምሕረት ቅዱስ ገብርኤል ቤተ ክርስቲያን በአዲሱ ዓመት በቀጥታ የሚተላለፈውን ትምህርተ ወንጌል፣ ዝማሬና መንፈሳዊ አገልግሎት እንዲሁም የጽሁፍ መልእክቶችን ለመከታተል ቴሌክራሙን join ጉግሉን ፎሎው you tubuን ሰብሰክራይብ ያድርጉ።
የትኛውንም ሃይማኖታዊ ጥያቄዎች መልስ ያገኙበታል።
❀✿ የዐፄ ዘርዐ ያዕቆብ ደብዳቤ ✿❀
❍●◦─━•⊰❀👆👆👆❀⊱•━─◦●❍
የቀጠለ
ከዕንጨት ተሠርቶ በወርቅ በተለበጠው ሳጥን ውስጥ የሐና እመ ማርያም፣ የሐዋርያው በርተሎሜዎስ፣ የልዳው የቅዱስ ጊዮርጊስ የአንጾኪያው ሰማዕት የቅዱስ ገላውዴዎስ' የሊቃነ ጳጳሳቱ የሳዊሮስና የዲዮስቆሮስ፤ የቤተ ልሔም ሕፃናት ዕፅሞች አሉ፤ ይላል ዐፄ ዘርዐ ያዕቆብ፡፡ እንዲቀደስበት የእመቤታችንን ታቦት መላኩን፤ በመካከል ባለው በብርሃን በር የጌታ ወንድም የያዕቆብ ዐፅም፣ የቀዳሜ ሰማዕት የቅዱስ እስጢፋኖስ ዐፅም፣ የበርናባስና የአርሴማ ዐፅሞች መኖራቸውን ይጠቅስና እነዚህን ሁሉ ለእግዚአብሔር አብ ቤተ ክርስቲያን
መስጠቱን ይገልጣል፡፡ ንዋያቱንና ዐፅሞቹን ለያዙት ሳጥኖች ወርቅ መለበጫ በድምሩ 17 ሺሕ 91 ዲናር (ወይም ወቄት ወርቅ) መውጣቱን ይገልጣል። እነዚህ ሁሉ ወደ ግሼን ሲገቡ ካህናቱ እያጠኑና እየዘመሩ፤ ሕዝቡ ልብሳቸውን እያነጠፉ እንዲቀበሉ ጥሪ ያቀርባል፡፡
በዚህ የዐፄ ዘርዐ ያዕቆብ ደብዳቤ መሠረት ግማደ መስቀሉ ሁለት ጊዜ መጥቷል ማለት ነው፡፡ የመጀመሪያው በዐፄ ዘርዐ ዳዊት ዘመን በ1396 ዓ.ም. መጥቶ መስከረም 17 ቀን የደረሰውና በኋላ ደግሞ በዐፄ ዘርዐ ያዕቆብ ዘመን መጥቶ መስከረም 21 ቀን የደረሰው ማለት ነው፡፡ በዐፄ ዘርዐ ያዕቆብ ዘመን የመጣው ግማደ መስቀል ብቻውን አልነበረም፡፡ ከእርሱ ጋር በርካታ ንዋያተ ቅድሳት እና ዐፅመ ቅዱሳን አብረው መጥተዋል። ዋና ዋናዎቹ፦
1 ግማደ መስቀሉ
2 ሰፍነጉ
3 ከለሜዳው
4. ዐፅመ ቅዱሳን
ዐፄ ዘርዐ ያዕቆብ ወደ ግሼን ወስዶ ያስቀመጠው በእርሱ ዘመን የመጣውን መሆን አለበት። ዐፄ ዘርዐ ያዕቆብም ወደ አውሮፓ ልኡካንን ልኮ ነበር፡፡ በእርሱ ዘመን አባ ሚካኤልና አባ ገብርኤል የሚባሉ ሁለት ሊቃነ ጳጳሳትም ከእስክንድርያ መጥተዋል፡፡ ከዚህም በተጨማሪ መስቀሉ የመጣበትን ቦታ ሲነግረን! እቴጌ ዕሌኒ መስቀሉን በኢየሩሳሌም ካወጣችው በኋላ ወደ ፈረንጅ ሀገር መውሰዷን፣ በዚያም ሰባቱ የፈረንጅ ነገሥታት እንደተካፈሉት ይገልጣል። የመጣዉ ከእስክንድርያ መሆኑን አያመለክትም፡፡ እንዲያውም የመስቀሉን መቆሚያ የአፍርንጅ ጥበብ ብሎ ይገልጠዋል፡፡ ነገሩን ያያያዘው ከፈረንጅ ጋር
እንጂ ከግብጽ ጋር አይደለም፡፡ ይሄም ግማደ መስቀሉ መነሻው ቬነስ ነው ከሚለው ጋር ይስማማል፡፡ የግብጽ አባቶች ግማደ መስቀሉን ከቬነስ አምጥተው ወይም ለእነርሱ ያስመጡትን ከሌሎች ንዋያት ጋር ጨምረው ልከውለታል ማለት ነው፡፡
ታሪከ ነገሥቶቻችን ይሄንን በዐፄ ዳዊት ዘመን የመጣውን ግማደ መስቀል ያነሡታል። «በመዋዕሊሁ (ለንጉሥ ዳዊት) መጽአ ዕጸ መስቀሉ ለክርስቶስ - በንጉሥ ዳዊት ዘመን የክርስቶስ መስቀል ግማዱ መጣ ይላሉ ዜና መዋዕሎቹ5:: መጽሐፈ ጤፉት ብነገሠ በ15ዓመት፣ በተወለደ በ50 ዓመት፣ «አንብር መስቀልየ በዲበ መስቀል የሚለውን ራእይ ማየቱን ይናገራል፡፡ ይሄም በ1441 ዓ.ም. መሆኑ ነው::
═────━━━━⊱✿⊰━━━━────═
ሃሳብ👉🏽 @hadis_comment_bot
▬▬▬▬▬❀✿❀▬▬▬▬▬
ዲ/ዳንኤል ክብረት፣ ከእቴጌ ዕሌኒ እስከ ቅድስት ወለተ ጴጥሮስ፣ 2013
◉◉◉◦◦◦▬▬▬▬▬▬▬▬▬▬◦◦◦◉◉◉
ይቀላቀሉ👉🏽 @yemaryammekenet
━━━━━━━━━━━━━━━━━━━━━━━
 ̄ ̄ ̄ ̄ ̄🙏 ̄ ̄ ̄ ̄ ̄
 ̄ ̄ ̄─━━━━⊱✿⊰━━━━─ ̄
💬 - http://t.me/hadis_comment_bot | join - http://t.me/yemaryammekenet
❀✿፠መልካም አዲስ አመት!፠✿❀
❍●◦─━•⊰❀✿❀⊱•━─◦●❍
꧁༻❀✿❀༺꧂
አዲስዓመት
መልካምአዲስዓመት
መልካም አዲስዓመት
መልካም አዲስዓመት
መልካም አዲስዓመት
መልካም አዲስዓመት
አዲስዓመት
አዲስዓመት
አዲስዓመት
አዲስዓመት
አዲስዓመት
አዲስዓመት
አዲስዓመት
አዲስዓመት
አዲስዓመት
አዲስዓመት አዲስዓመት
አዲስዓመትአዲስዓመትአዲስዓመት
አዲስዓመትአዲስዓመትአዲስዓመት
አዲስዓመት
መልካምአዲስዓመት
መልካምአዲስዓመትአዲስዓመት
አዲስዓመት አዲስዓመት
አዲስዓመት አዲስዓመት
አዲስዓመት አዲስዓመት
አዲስዓመት አዲስዓመት
አዲስዓመት አዲስዓመት
አዲስዓመት አዲስዓመት
አዲስዓመት አዲስዓመት
አዲስዓመት አዲስዓመት
አዲስዓመት አዲስዓመት
መልካም አዲስዓመትአዲስዓመት
መልካምአዲስዓመት
አዲስዓመት
ዓመት
አዲስዓመት
መልካምአዲስዓመት
አዲስዓመት
አዲስዓመት
አዲስዓመት
አዲስዓመት
አዲስዓመት
አዲስዓመት
አዲስዓመት
አዲስዓመት
አዲስዓመት
አዲስዓመት
አዲስዓመት
አዲስዓመት አዲስ
አዲስዓመት አዲስዓመት
መልካምአዲስዓመትመልካም
መልካም
መልካም
መልካም
መልካም አዲስ አመት
መልካም አዲስ አመት
መልካም አዲስ አመት
መልካም አዲስ አመት
መልካም አዲስ አመት ይሁንልን ቢኒባ
መልካም አዲስ አመት ይሁንልን ቢኒባ
መልካም አዲስ አመት ይሁንልን ቢኒባ
አዲስ አመት
አዲስ አመት
አዲስ አመት
አዲስ አመት
አዲስ አመት
አዲስ አመት
አዲስ አመት
═────━━━━⊱✿⊰━━━━────═
“በቸርነትህ ዓመትን ታቀዳጃለህ።”
— መዝሙር ፷፭፥፲፩
꧁༻❀✿❀༺꧂
❀✿❀ አዲሱ አመት ❀✿❀
❀✿❀ ግጭት ጠፍቶ ፍቅር ❀✿❀
❀✿❀ ሀዘን ተፍቶ ደስታ ❀✿❀
❀✿❀ እንባ ተጠርጎ ሳቅ ❀✿❀
❀✿❀ ረሀብ ጠፍቶ ጥጋብ ❀✿❀
❀✿❀ ጥማት ጠፍቶ እርካታ ❀✿❀
❀✿❀ ፃድቅ የሚፀናበት ❀✿❀
❀✿❀ሀጥ ንስሀ የሚገባበት❀✿❀
❀✿❀ አመት ያርግልን።❀✿❀
❀✿❀መልካም አዲስ አመት❀✿❀
✿ይሁንላቹ ከነ መላው ቤተሰቦቻቹ ✿
አሜን አሜን አሜን
༻❀✿❀༺
ሃሳብ👉🏽 @gebrye\_comment\_bot
▬▬▬▬▬❀✿❀▬▬▬▬▬
❀✿፠መልካም አዲስ አመት!፠✿❀
❀✿፠መልካም አዲስ አመት!፠✿❀
❀✿፠መልካም አዲስ አመት!፠✿❀
◉◉◉◦◦◦▬▬▬▬▬▬▬▬▬▬◦◦◦◉◉◉
ይቀላቀሉ👉 @mahteben\_albetsm
━━━━━━━━━━━━━━━━━━━━━━━
 ̄ ̄ ̄ ̄ ̄🙏 ̄ ̄ ̄ ̄ ̄
 ̄ ̄ ̄─━━━━⊱✿⊰━━━━─ ̄
††† በስመ አብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ አሐዱ አምላክ አሜን ! †††
# ሱባኤማለትምንማለትነው ?
➢ሱባኤ ቃሉ የግዕዝ ቃል ሲሆን ትርጉሙ ሰባት 7 ማለት ነው ሱባኤ ፍጹም ዕለታትንና ቦታን ወስኖ ለተወሰኑ ቀናት መቆየት ማለት ነው። አንድ ሱባኤ 7፤ ሁለት ሱባኤ 14 እያለ ይቀጥላል።
# ሰውለምንሱባዔይገባል ?
1, #ለመለመን
➢ ስንለምን ግን ይሚጠቅመንን ለይተን መሆን አለበት። አንዳንድ ጊዜ ልመናችንን አናውቅም የዘብዴዎስ ልጆች ያዕቆብና ዮሐንስ የለመኑት አለ ማር 10 ጌታም ምን
ልፈጽምላችሁ ትወዳላችሁ አላቸው እነሱም አምላክን ምድራዊ ንጉስ አደረጉትና በዙፋንህ ግራና ቀኝ አድርገን
አሉት? እርሱም የምትለምኑትን አታውቁም አላቸው። የምንለምነው ብዙ ነው እግዚአብሔር የሚመልስልን
ግን የሚጠቅመንን ነው
➢ #ሱባኤ\ስንገባ_የገባንበት_ አላማ ካለንበሱባኤውመጨረሻመልስእናገኛለን
2. ከእግዚአብሔር ጋር ለመነጋገር ነው
ሙሴ አርባ ቀንና አርባ ለሊት ከፆመና ከፀለየ በኋላ ከአምላኩ ጋር ተነጋግሯል
3. ከቅዱሳን በረከትን ለመሳተፍ
የእመቤታችን ፆም ሱባኤ ስንገባ ከእመቤታችን በረከትን ለማግኘት
4. ምስጢር እንዲገለጽልን ብዙ ጊዜ ለሰው የማንናገረው ድፍን ያለ ነገር
ይገጥመናል በዚህን ጊዜ ሱባዔ እንገባለን። እመቤታችን ቅድስት ድንግል ማርያም በ3ኛው ነው ለቅዱስ ገብርኤል መልስ የመለሰችለት። እመቤታችን
ውሃውን አስቀምጣ ወደ ቤተመቅደስ ነው የገባችው ዘግታ ሱባኤዋን ጀመረች ።ቅዱስ ገብርኤል እዛም አልቀረም
ቤተመቅደስ ገባ አናገረችውም
ሐዋርያትም የእመቤታችንን እርገት ለማየት ነው 16 ቀን ሱባኤ የገቡት እሱም ድጋሚ ገለጸላቸው እኔ ዳንኤል ሶስት ሳምንት እንጀራ አልበላሁም ማለፊያ
ውሃም አልጠጣሁም።
“በዚያም ወራት እኔ ዳንኤል ሦስት ሳምንት ሙሉ ሳዝን ነበርሁ።”
— ዳንኤል ፲÷፪
5. መንፈሳዊ ስራን ለመስራት
ክህነት ምልኩስና ጋብቻ ወዘት የመሳሰሉትን ለመፈጸም ሱባኤ ያስፈልጋል። ሐዋርያት ዓለምን ዞረው ለማስተማር ሱባዔ ገብተዋል
#የሱባኤ\አይነቶች
የሱባኤ አይነቶች ሦስት ናቸው::
፩. #የግል_ሱባኤ
፪. #የማህበር_ሱባኤ
፫. #የአዋጅ_ሱባኤ
፩ #የግል_ሱባኤ_በሁለት_ይከፈላል ::
1. ዝግ ሱባኤ
2. የንስሀ ሱባኤ
➢ ንስሀ ከገባን በኋላ ንስሀ አባቴ ቀጣኝ እንላለን ንስሀ ቅጣት ሳይሆን ህክምና መዳህኒት ነው። እነዚህን ሁለት ሱባኤዎችን ስንፈጽም የክህነት
አባቶች ያስፈልጋሉ።
፪. #የማህበር_ሱባኤ
➢በማህበር ስለማህበር ስለ ሀገር የሚጸለይበት ሱባኤ ነው
፫. #የአዋጅ_ሱባኤ
➢ ማንም በሀገር ደረጃ አያውጀውም በሲኖዶስ የሚታወጅ ነው።
#የሱባኤ_ቅድመ_ዝግጅቶች
1. መጠናቀቅ በመጀመሪያ አንድ ሰው ሱባኤ ከመጀመሩበፊት መጠናቀቅ አለበት።በቅዳሴ ሰዓት ስልክ ይዘን እየረበሽን እግዚአብሔር ከእኛ ጋር በሚነጋገርበት ጊዜ እኛ ለብቻችን እናወራለን ይሄ ተገቢ አይደለም።
ቅዳሴ ከሁሉ በላይ የከበረ ነው ከቅዳሴ በላይ ምን አለ? የክርስቶስ ስጋና ደም የሚፈተትበት መልአክት እንደ ሻሽ የሚነጠፍበት::
2. ምክረ ካህን ከአባቶቻችን ምክር ማግኘት አለብን ከሱባኤ በፊት
ስትጸልዩ እንደ ግብዞች አትሁኑ
“ስትጸልዩም እንደ ግብዞች አትሁኑ፤ ለሰው ይታዩ ዘንድ በምኩራብና በመንገድ ማዕዘን ቆመው መጸለይን ይወዳሉና፤ እውነት እላችኋለሁ፥ ዋጋቸውን ተቀብለዋል።”
— ማቴዎስ ፮÷፭
3. የሚፈለገውን ነገር ማሟላት
4. አቅምን ማወቅ ይህ በጣም ከባድ ነው ያለ አቅም ብንጀምረው አንፈጽመውም::
ፆመን ፆመን ሲያቅተን እግዚአብሔር ን እናማርራለን ይሄ ተገቢ አይደለም።
5. ቦታ መምረጥ ቦታ መምረጥ ማለት ለፈተና የማያጋልጡ መሆን አለበት::
#በሱባኤ_ወቅት_የምንጠብቃቸው_ስርዓቶች
1. #አንደበትን_መጠበቅ
አንደበት እሳት ነው ከአንድ ምላስ መርገምና ምርቃት ይወጣሉ
አንደበትም እሳት ነው። አንደበት በብልቶቻችን መካከል ዓመፀኛ ዓለም ሆኖአል፤ ሥጋን ሁሉ ያሳድፋልና፥ የፍጥረትንም ሩጫ ያቃጥላል፥ በገሃነምም ይቃጠላል። የአራዊትና የወፎች የተንቀሳቃሾችና በባሕር ያለ የፍጥረት ወገን ሁሉ በሰው ይገራል፥ ደግሞ ተገርቶአል፤ ነገር ግን አንደበትን ሊገራ ማንም ሰው አይችልም፤ የሚገድል መርዝ የሞላበት ወላዋይ ክፋት ነው። በእርሱ ጌታንና አብን እንባርካለን፤ በእርሱም እንደ እግዚአብሔር ምሳሌ የተፈጠሩትን ሰዎች እንረግማለን፤ ከአንድ አፍ በረከትና መርገም ይወጣሉ። ወንድሞቼ ሆይ፥ ይህ እንዲህ ሊሆን አይገባም።
ያዕቆብ ፫÷፮-፲
ለአፌ ጠባቂን አኑር
“ምላሳቸውን እንደ እባብ ሳሉ፤ ከከንፈራቸው በታች የእፉኝት መርዝ ነው።”
— መዝሙር ፻፵፫÷፫
2. በሱባኤ ወቅት አብዝቶ መጸለይ
በፊት ከምናደርገው ጸሎት የበለጠ መፀለይ አለብን።
3. በመጠን መመገብ በሱባኤ ወቅት አብዝተን ከመመገብ መቆጠብ አለብን::
ጉልበቶቼ በፆም ደከሙ
4. በሱባኤ ወቅት አብዝተን መማር አለብን:: ዝግ ሱባኤ ካልሆነ ደጋግመን መማር አለብን
5. በሱባኤ ወቅት አለባበስን ማስተካከል
ማቅ ባንለብስ አመድ ባንነሰንስም ቢቻለን ገላን የሚያሳዩ ልብሶችን መልበስ የለብንም ያለበለዛ ሱባዔው ከንቱ ነው በሱባኤያችን ምንም አናገኝም::
መልካም ሱባኤ ይሁንላችሁ
#ፆሙን_የድህነት_የምህረት_የሰላም_የፍቅር_ፆም_ያርግልን።
✞✞✞✞✞ አሜን ✞✞✞✞✞
✥••┈┈••●◉ ✞ ◉●••┈┈••✥
📖 ወስብሐት ለእግዚአብሔር 📖
📖 ወለወላዴቱ ድንግል 📖
📖 ወለመስቀሉ ክቡር 📖
📖✞✞✞✞✞📖
✞✞✞ ሃሳብ ➢
@gebrye_comment_bot
|❀:✧๑ ✞✞✞✞✞✞✞ ๑✧❀|:
✞✞✞ ይቀላቀሉ ➣
@mahteben_albetsm
††† በስመ አብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ አሐዱ አምላክ አሜን ! †††
ይድረስ ለኦርቶዶክሳውያን
ሁላችንም ጎግል ማፕ እየገባን "suggest an edit" የሚለው ጋር እየገባን "ወይም ኢድ" ብለው የጻፉትን እያጠፋን፡፡ መስቀል አደባባይ ብቻ የሚል እንላክ፡፡ ጎግል አጠንቶ ይወስናል፡፡ ማልቀስ ምን ይሰራል፡፡ መስራት እንጂ፡፡ እኛም እኮ እጅ አለን
Edit ለማድረግ ስቴፕ
1 Google መግባት
2 Google map ብሎ ሰርች ማድረግ
3 Google map የሚለውን በመንካት መግባት
6 ሰርች ላይ meskel square ሰርች
7 "suggest an edit" በመግባት change or edit የሚለውን በመንካት
8 መስቀል አደባባይ ወይም ኢድ አደባባይ የሚለውን ወይም ኢድ አደባባይ የሚለውን በማጥፋት መስቀል አደባባይ የሚለውን በማስቀረት
9 በመጨረሻም ከላይ ያለችውን sand ምልክቱዋን በመንካት ሀላፊነታችን እንወጣ።
መስቀል አደባባይ የማፀደቅ በአንድ ሰው ብቻ ስለማይሆን ለመላው ኦርቶዶክሳውያን ሼር በማድረግ ሀላፊነታችን እንወጣ።
✥••┈┈••●◉ ✞ ◉●••┈┈••✥
📖✞✞✞✞✞📖
✞✞✞ ሃሳብ ➢
@gebrye_comment_bot
|❀:✧๑ ✞✞✞✞✞✞✞ ๑✧❀|:
✞✞✞ ይቀላቀሉ ➣
@mahteben_albetsm
††† በስመ አብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ አሐዱ አምላክ አሜን ! †††
አዋጅ አዋጅ አዋጅ
ለ 1 ሳምንት ግዴታ ሁሉም ኦርቶዶክስ ነኝ የሚል ካለ ከላይ የላክነው የቅዱስ አባታችን ብፁዕ ወቅዱስ አቡነ ማትያስ ቀዳማዊ ፓትርያርክ ርዕሰ ሊቀነ ጳጳሳት ዘኢትዮጵያ ሊቀ ጳጳስ ዘአክሱም ወእጨጌ ዘመንበረ ተክለሃይማኖት ፕሮፋይል ፒክቸር በማድረግ በአባታችን ላይ እየደረሰ ያለው ጫና እና ተቃውሞ በመንቀፍ ከአባታችን ጎን መሆናችንን ለአባታችን ያለንን ክብርና በኦርቶዶክስ ተዋህዶ እየደረሰ ያለውን ጫና እንቃወም
"በመልክታቸው ላትስማማ ትችላለህ... ክብረ ፕትርክናቸውን ማክበር ውዴታ ሳይሆን መንፈሳዊ ግዴታችን ነው!!
ሁሉም ኦርቶዶክስ እንዲያደርግና አሕዛብና ከሀዲዎችን ማስገረም አለብን። የሚያስገርመው ነገር ምንድን ነው ካላቹ ሁላችን በተመሳሳይ ሰዓትና ቀን profile picture ማረጋችን ነው። ኦርቶዶክሶች ሲነኩን እንደ ምድር አሸዋ እንደምንበዛ ማሳያም ነው። ነገ ሳይሆን ዛሬ ዛሬ ሳይሆን አሁን ሁሉም ኦርቶዶክስ profile picture በማድረግ ግዴታውን ይወጣ መልዕክቱን በማስተላለፍ የበኩሉዎን ይወጡ። ለ30 የኦርቶዶክስ ቤተሰብ ፎርዋርድ እናድርግ
ብፁዕ ወቅዱስ አቡነ ማትያስ ቀዳማዊ ፓትርያርክ ርእሰ ሊቃነ ጳጳሳት ዘኢትዮጵያ ሊቀ ጳጳስ ዘአክሱም ወእጨጌ ዘመንበረ ተክለሃይማኖት ቡራኬው ትድረሰን አሜን።
✥••┈┈••●◉ ✞ ◉●••┈┈••✥
📖✞✞✞✞✞📖
✞✞✞ ሃሳብ ➢
@gebrye_comment_bot
|❀:✧๑ ✞✞✞✞✞✞✞ ๑✧❀|:
✞✞✞ ይቀላቀሉ ➣
@mahteben_albetsm
††† በስመ አብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ አሐዱ አምላክ አሜን ! †††
#ጥር ፲፮
#ሰባቱ_ኪዳናት
፩. ኪዳነ አዳም
፪. ኪዳነ ኖኅ
፫. ኪዳነ መልከ ጼዴቅ
፬. ኪዳነ አብርሃም
፭. ኪዳነ ሙሴ
፮. ኪዳነ ዳዊት
፯. ኪዳነ ምሕረት
#ኪዳነ_ምሕረት
➢ በብሉይ ኪዳን የነበሩ ስድስቱ ኪዳናት በዘመናቸው ክቡርና ሕዝቡን ከመቅሰፍት ይታደጉ የነበሩ ቢሆንም ከሲኦል ማዳን ግን አልቻሉም።
➢ ስለዚህም አንድ ፍጹም ኪዳን ያስፈልግ ነበር። ይህን ፍጹም ኪዳን ይፈጽም ዘንድም ከቅድስት ሥላሴ አንዱ ወልድ ከሰማያት ወርዶ በድንግል ማርያም ማኅጸን አደረ።
➢ በፍጹም ተዋሕዶም በሕቱም ድንግልና ተወልዶ፣ አድጎ፣ ተጠምቆ፣ አስተምሮ፣ ሙቶ፣ ተነስቶና ዐርጐ ሥጋ ማርያምን በዘባነ ኪሩብ አስቀመጠው።
#ኪዳነ_ምሕረት
#የምሕረት_ኪዳን
➢ የምንለው አንዱ ታዲያ ይሔው ነው።
➢ የጌታችን መጸነሱ፣ መወለዱ፣ መሰደዱ፣ መጠመቁ፣ ማስተማሩ፣ ሥጋውንና ደሙን መስጠቱ፣ መሰቀሉ፣ መሞቱና መነሳቱ፣ ማረጉና መንፈስ ቅዱስን መላኩ በአንድ ላይ ኪዳነ ምሕረት ይባላል።
➢ ታዲያ ይህ ሁሉ የተደረገው በሥጋ ማርያም ነውና የኪዳኑ ባለቤት እመቤታችን ቅድስት ድንግል ማርያም ናት።
➢ የእርሷ ኪዳን የስድስቱን አበው ኪዳናት ፍጹም በማድረጉ "የኪዳናት ማሕተም" ይባላል። የድንግል ማርያም ኪዳኗ ከሲኦልና ከገሃነም ሊታደገን አቅሙ አለውና።
➢ መድኃኒታችን ክርስቶስ ለድንግል እናቱ ቃል ኪዳኑን ያጸናላት ደግሞ ካረገ ከዓመታት በኋላ ጐልጐታ ላይ ነው።
እመ ብርሃን በዚያ ቁማ ስለ ኃጥአን ስታለቅስ "እናቴ ሆይ! በስምሽ ያመነውን በቃል ኪዳንሽ የተማጸነውን እምርልሻለሁ።" ብሎ ደስ አሰኝቷታልና።
➢ ይሔው በእመ ብርሃን ምልጃና ቃል ኪዳን ምዕመናን ከመቅሰፍትና ከገሃነመ እሳት ማምለጥ ከጀመሩ ፪፼ ዓመታት ሆኑ።
➢ ዛሬም እኛ ኃጥአን ልጆቿ ከእሳት እንደምታድነን አምነን በጥላዋ ሥር እንኖራለን።
"ኢትዝክሪ ብነ አበሳነ ኃጢአተነ ወጌጋየነ ማርያም እሙ ለእግዚእነ
በኪዳንኪ ወበስደትኪ ድንግል ተማሕጸነ።"
"ድንግል፣ ሆይ! ኃጢአታችን፣ አበሳችንና በደላችንን አታስቢብን ዘንድ በስደትሽና በኪዳንሽ ተማጽነናል።"
➢ የአርያም ንግሥት፣ የሰማያውያንና ምድራውያን ሁሉ እመቤት፣ የአምላክ እናት፣ ቅድስት፣ ስብሕት፣ ክብርት፣ ልዕልት፣ ቡርክት፣ ፍስሕትና ጥዕምት የሆነች ድንግል ማርያም የድኅነታችን መሠረት ላመኑባት አንገት የማታስደፋ እውነተኛ አማላጅ ናት።
➢ በዚህች ዕለት የካቲት ፲፮ ስለ ወገኖቿ የሰው ልጆች ፍቅር በእንባ ያቀረበችውን ልመና የባሕርይ አምላክ የሆነ ልጇ ተቀብሎ በማይዋሽ ንጹሕ አንደበቱ ቃል ኪዳን ገብቶላታል። በስምሽ ያመነ በቃል ኪዳንሽ የተማመነ እሳትን አያይም ብሏታል።
✥••┈┈••●◉ ✞ ◉●••┈┈••✥
"✞✞✞ ቸሩ መድኃኔ ዓለም ከእመቤታችን በረከተ ኪዳን አይለየን። በዓሉንም የሰላም፣ የፍቅርና የበረከት ያድርግልን።✞✞✞"
✞✞✞✞✞ አሜን ✞✞✞✞✞
✥••┈┈••●◉ ✞ ◉●••┈┈••✥
📖 ወስብሐት ለእግዚአብሔር 📖
📖 ወለወላዴቱ ድንግል 📖
📖 ወለመስቀሉ ክቡር 📖
📖✞✞✞✞✞📖
✞✞✞ ሃሳብ ➢
@gebrye_comment_bot
|❀:✧๑ ✞✞✞✞✞✞✞ ๑✧❀|:
✞✞✞ ይቀላቀሉ ➣
@mahteben_albetsm
††† በስመ አብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ አሐዱ አምላክ አሜን ! †††
#ጥር ፲፩
#አባ_አውሎግ_አንበሳዊ
➤ አባ አውሎግ ማለት ከቀደመው ዘመን ጻድቃን አንዱ፣ እንደ ገዳማውያን ፍፁም ባሕታዊ፣ እንደ ሐዋርያት ብዙ ሃገራትን በስብከተ ወንጌል ያሳመኑ፣
➤ በግብጽና በሶርያ በርሃዎች ለ፺ ዓመታት የተጋደሉ ጻድቅና ሐዋርያ ሲሆኑ የሚጓዙበትና የሚታዘዛቸው ግሩም አንበሳ ነበር።
በዚህም አባ አውሎግ "አንበሳዊ" ስትል ቅድስት ቤተ ክርስቲያን ትጠራቸዋለች።
አባ አውሎግ ከሚታወቁበት አገልግሎት አንዱ ስብከተ ወንጌል ነው።
➤ ምንም እንኳን ገዳማዊ ቅዱስ ቢሆኑም ያላመኑትን ለማሳመን ያመኑትንም ለማጽናት ተጋድለዋል።
➤ እግዚአብሔር በሰጣቸው አናብስት
በአንዱ ላይ ተጭነው
“አቤቱ፥ ተመለስ፥ እስከ መቼስ ነው? ስለ ባሪያዎችህም ተምዋገት።”
— መዝሙር. ፺፥፲፫
➤ በሌላኛው ላይ እቃቸውን አስቀምጠው በየአኅጉራቱ ከመምህራቸው ቅዱስ አውሎጊን ጋር ይዘዋወሩም ነበር። የጌታ ቸርነት ሆኖም አናብስቱ የቅዱሳኑን ፈቃድ ሳይነገራቸው ያውቁ ነበር።
➤ ሲርባቸውም ተግተው ይመግቧቸው ነበር። እንዲያውም አንዴ ቅዱሳኑ እንደራባቸው አንዱ አንበሳ ሲያውቅ ከበርሃ ወደ ገበያ መንገድ ወጥቶ ተመለከተ።
➤ በአህያ ላይ ልጁንና ስንቁን (ዳቦ) ጭኖ የሚሔድ ሽማግሌ ነበርና ዳቦውን አንስቶ ወስዶ ለእነ አባ አውሎግ ሰጣቸው።
➤ ከድንጋጤ የተነሳም ሕፃኑ ሙቶ ነበርና ሽማግሌ አባቱ አዘነ። አንበሳው ግን ሕፃኑንም ወደ ቅዱሳኑ ወስዶ አስረከበ።
➤ ቅዱሳኑም ከሕብስቱ በመጠናቸው በልተው ቢባርኩት እንዳልተበላ ሆነ። ሕፃኑንም ከሞት በጸሎታቸው አስነስተው ለአንበሳው ሰጥተውታል።
➤ አንበሳውም ስንቁንና ልጁን ለአረጋዊው ሰጥቶት በደስታ ወደ ሃገሩ ተመልሷል። ቅዱስ አባ አውሎግና መምህሩ አውሎጊን ከ፺ ዓመታት በላይ በዘለቀ ተጋድሏቸው አጋንንትን ያሳፍሩ ዘንድ ለጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ንጹሕ መስዋዕት ይሆኑለት ዘንድ በትጋት ኑረዋል።
#ብዙ_ተአምራትን_ተሠርተዋል
➢እንደ ሊቀ ነቢያት ቅዱስ ሙሴ ባሕር ከፍለዋል።
➢ እንደ ቅዱሳን ሐዋርያት ሙት አንስተዋል፤ ድውያንን ፈውሰዋል።
➢ እንደ ቅዱስ ዳንኤል አናብስትን ገዝተዋል።
#ይህች_ዕለተ_ዕረፍታቸው_ናት።
✥••┈┈••●◉ ✞ ◉●••┈┈••✥
"✞✞✞ ከአባታችን አባ አውሎግ አንበሳዊ ረደኤት በረከት ይደርብን በእምነታችን ያፅናን።✞✞✞"
✞✞✞✞✞ አሜን ✞✞✞✞✞
✥••┈┈••●◉ ✞ ◉●••┈┈••✥
📖 ወስብሐት ለእግዚአብሔር 📖
📖 ወለወላዴቱ ድንግል 📖
📖 ወለመስቀሉ ክቡር 📖
📖✞✞✞✞✞📖
✞✞✞ ሃሳብ ➢
@gebrye_comment_bot
|❀:✧๑ ✞✞✞✞✞✞✞ ๑✧❀|:
✞✞✞ ይቀላቀሉ ➣
@mahteben_albetsm