▓▓▓▓▓▓ ግጥM ▓▓▓▓▓▓▓
ጠልተሽኝ ስትሸሺኝ ፣ ወድጄሽ ስከተል
ገፍተሽኝ የሄድሽው
የፍቅር ትርጉሙ ፣ ባይገባሽ ነው መሰል።
ይኸውልሽማ….
ፍቅር ማለት እኮ
ፈጣሪን ከዙፋን
ሰማያት አሻግሮ ፣ምድር ያወረደ
የመለኮት ኃይል ...
በስጋ እንዲገረፍ ፣ ጅራፍ የገመደ
ፍቅር ማለት ያ ነው …
ቃል ከስጋ ጋራ ፣ በአንድ ያዋሃደ ፡፡
።።።፣
ቃል ማለት ፍቅር ነው
ስጋን ተዋህዶ ፣ ልብን ያቆሰለ
ውህደት እንዲህ ነው …
በደም ስሩ ሰርጾ ፣ ጉልበቱ ለዛለ
ችሎ ነው ዝም የሚል …
ህመም እና ቁስሉን ፣አፍቃሪ ነኝ ያለ፡፡
።።።።
አፍቃሪ ነኝ ያለ ፣ ዙፍኑን ይረሳል
ክብሩን ዘንግቶ ፣ ፍቅሩን ያስታውሳል
እርቃኑን ተሰቅሎ ፣እርቃንን ያለብሳል
የእውነት ያፈቀረ...
ከሚጠሉት ፊት ላይ፣ ፍቅሩን ይጸንሳል::
።።
ጠልተሽ ለምትሸሺኝ፣ ወድጄ ስከተል፤
ገፍተሽኝ የሄድሽው …
የፍቅር ትርጉሙ፣ ባይገባሽ ነው መሰል
ይኸውልሽማ …..
ፍቅር ማለት እኮ ፣
ሌላውን ማዳን ነው ፣ራስን በማቁሰል
━━━━━━✦✗✦━━━━━━━
ምርጫዎ ስለሆነ እናመሰግናለን 😘
# ፍቅር_እዚህ_ቦታ_ፈገግ_ብሎ_ነበር
.
ያሳለፍነዉ ሁሉ
አሁን ትዝታ እንጂ
ዉስጡ ህይወት የለም እያልሽ ላገሩ
ታወሪያለሽ አሉ
.
.
(እኔ ግን ልንገርሽ)
የሁለታችን ፍቅር
ምን እንደሚመስል. . .
እንዴት እንደነበር
በሶስት ምስክር
1
አሁን በቀደም ለት
የሆነ ቦታ ላይ
ድምጻችን ከፍ አርገን የሳቅንበት ቦታ
ፒያሳ አደባባይ
ድንገት
በቀደም ለት
በዛ ቦታ ስሄድ
ከሰባት ወር በፊት
ስቀሽ የነበረዉ
ያንቺ ሳቅ ተሰማኝ
መራመድ አቃተኝ
የሚገርምሽ ነገር
ያለፈ ነዉ ያልሺዉ
ትዝታ ነዉ ያልሽዉ
ፍቅርሽና ሳቅሽ
ከሰባት ወር ኋላ እንደ ወንዝ ፍሳሽ
ይሰማል ልንገርሽ
.
(ታዲያ ለምንድን ነዉ)
የወንዝ ዉሀ ሳቅሽ
ያለፈ ትዝታ ምናምን ነዉ ብሎ
ማንም ተራ ዘፋኝ የሚሸነግልሽ
(ይልቅ እኔን ስሚኝ)
.
ወደየትም ሳይሆን
ወዴትም ተመለሽ
የትም ሳትደርሺ
ጊዜን እንዳቆምነዉ
እንኳን ጊዜ ቀርቶ ሰዓት እንዳልሄደ
ደቂቃ እንዳልሄደ
አስረጂ ሊሆንሽ
ምስክር ሊሆንሽ
ከምንም አቅጣጫ. . . የትም ሳትመለሽ
አደባባይ መሀል
ከቡና ጠረን ጋር
እንደወንዝ የሚፈስ
ሳቅሽን ትሰሚያለሽ
.
2
ትዝ ይልሽ እንደሆን
ካንቺ መኖሪያ ቤት
(የመጣሁኝ ጊዜ)
የመራራቅ ናፍቆት
አስክሮን ቸኩለን
ሰማያት ለመዝለቅ
ከመሬት ላይ ወድቀን
ፍቅር ስንሰራ
ፍቅር ስንሰራ
ፍቅር ስንሰራ
ከሴት ወዝሽ ጋራ
የጡትሽ ስር ሽቶ
ሸሚዜ ላይ ቀርቶ
ሸሚዜ ላይ ቀርቶ
ምወደዉን ሸሚዝ
ለመልበስ እርም አልኩኝ
ለብሼዉ እንዳልሄድ
ከበደኝ ጨነቀኝ
ያንቺን ጠረን ማጠብ. . .
ነፍስ የማጥፋት ያህል
ሀጥያት መስሎ ታየኝ
(የሚገርምሽ ነገር)
እስከ ዛሬ ድረስ
በመስኮቱ ዘልቆ. . .በበሬ
የሚወጣዉ የማለዳዉ ነፋስ
በሽቶሽ ጠረን ነዉ መንደሩን የሚብስ
.
3
ታስታዉሽ እንደሆን
የሆነ ቅዳሜ
የሆነ ዉብ ሆቴል
ደግሞም አትረሺዉም. . .ፍጻሜ ምሳ ነዉ
ይኼ እንኳን ትዝ ይላል
እና. . .
እኔና አንቺ ብቻ
የተቀመጥንበት ወንበር ጠረጴዛዉ
ከዘጠኝ ወር ኋላ. . .
እዛዉ ቤት ዳግመኛ ተመልሼ ባየዉ
የሚገርምሽ ነገር
ጻፊዉን ባላዉቅም
# ፍቅር_እዚህ_ቦታ_ፈገግ_ብሎ_ነበር
የሚል ጽሁፍ ሰቅለዉ
ከዘጠኝ ወር ኋላ
አንድ ለብቻዬ ካንድ አንቺ ናፍቆት ጋር
ነበር ለምትይዉ ለሁለታችን ፍቅር
(ምስክር ሊሆኑን)
ያኔ ሁለታችን የጠጣነዉ ወይን
ከወይንም. . . Two Ocean
እኔ የጨለጥኩት
አንቺ ያጋመስሽዉ
እኛ ያስተረፍነዉ
እስከዛሬ ድረስ
ያተረፍነዉ ማዕድ. . .
ጠርሙስና ጽዋዉ
በክብር ተቀምጧል
ማንም ሳያነሳዉ. . .ያኔ እንደነበረዉ
(ታዲያ ምን ማለት ነዉ)
.
.
.
ፒያሳ አደባባይ
የወንዝ ዉሃ ሳቅሽ
ከቡና ጠረን ጋ
ከኔ መኖሪያ ቤት. . .
የምወደዉ ሸሚዝ ላይ
የሽቶ መአዛሽ
ከሴት ላቦትሽ ጋር
ደግሞም
እዚያ ዉብ ሆቴል ስር
ያስተረፍነዉ . . .
ማዕድ ጠርሙስና ጽዋ
አንጀት ከሚበላ
ከቆንጆ ጥቅስ ጋር
‘’#ፍቅር_እዚህ_ቦታ_ፈገግ_ብሎ_ነበር::’’
.
ነበርን እስካሁን
በመሆን እያየሽ
ሳቅሽ ፈሶ ሳያልቅ
ከምወደዉ ሸሚዝ
የሽቶ መዓዛሽ ዉብ ጠረኑ ሳይለቅ
ማዕድ ሳይነሳ ጽዋዉ ሳይታጠብ
ሦሥቱን ምስክሮች በዓይንሽ ፊት እያየሽ
(ታዲያ ለምንድን ነዉ)
ያሳለፍነዉ ሁሉ
# አሁን_ትዝታ_እንጂ .....
# ዉስጡ_ህይወት_የለም
ብለሽ ለመንደሩ
ላገሩ ማዉራትሽ
እዉነት ለምንድን ነዉ?
.
.
.
.
.
©ኤፍሬም ስዩም
🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹ውድ የቻናላችን ተከታታዮች እንዴት ናችህ #ሴና የተሰኝው ተወዳጅነት ያተረፈው ልቦለድ ሊፈፀም ክፍል_37 ብቻ ቀርታል እንሆ ይህን የመጨረሻ ክፍል በቀጣይ ቀን ይዘን እንቀርባለን ይከታተሉን #ሸር ማድረጓን እንድይረሱ፨
🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹
ቻናላችንን ይቀላቀሉ
◦◦✧join 👇👇👇👇👇
@Mamusha23
@Mamusha23
@Mamusha23 🟢🟡🔴🟢🟡🔴🟢🟡🔴🟢🟡🔴🟢🟡🔴🟢🟡🔴
💞 #ሴና #ክፍል_ሠላሳ_አምስት 💞
. . . ዛሬም እንዳለፉት ቀናት የኪሩቤል ስልክ ነው የቀሰቀሰኝ፡፡ ቁርሳችንን ከበላን ብሀላ ትንሽ ተጨዋውተን ወደ ዶርሜ ተመለስኩ፡፡ ጉዋደኞቼ ይመጣሉ ፤ዶርሙን አስተካከልኩ፡፡ ዶርም እንደተቀመጥኩኝ ጉዋደኞቼ ደወሉልኝ፡፡ ሁሉም አንድ ቦታ ተገናኝተው ወደ ግቢ እየመጡ እንደሆነ ነገሩኝ፡፡ በጣም ደስ ቡሎኛል፡፡ ከዛሬ ቡሀላ ብቻዬን አላድርም ማለት ነው፡፡ በርግጥ ባለፉት ቀናት ሙሉ ሰአት አብሮኝ የነበረው ኪሩቤል ምንም ብቸኝነት እንዳይሰማኝ አድርጎኛል፡፡
ድንገት የዶርሜ በር ተንኳኳ፡፡ ከተቀመጥኩበት ተነስቼ ከፈትኩት፡፡ በሩን ከፈት ከማድረጌ ሚጣ ፈገግ ብላ እያየችኝ በሩ ላይ ቆማለች፡፡ በጣም ደስ አለኝ፡፡ ሁሉንም አንድ በአንድ አቅፌ ሰላም እያልኩኝ ወደ ውስጥ አስገባዋቸው፡፡ ገና እየመጣን ነው ያሉኝ ለካ ደርሰው ነው፡፡ እየተሳሳቅን እና እየተጨዋወትን ናፍቆታችንን እንገልፅ ጀመር፡፡ ሁሉም ስለደከማቸው ሻወር እንዲወስዱ ነግሬያቸው መጣው ብዬ ከዶርም ወጣው፡፡ ለኪሩቤል ደወልኩለት፡፡ የጠራሁት ቦታ መጣ፡፡ ጉዋደኞቼ ከመንገድ ስለመጡ ስለደከማቸው ከዶርም ከሚወጡ ምግብ እንድንገዛላቸው እኔ ቴካዌ አዝዤ ስለማላውቅ እንዲያጋዛኝ ነገርኩት፡፡ "አረ አንቺም ባትመጪ ብታዢኝ ይዤ መጣ ነበር ብር የለኝም እንጂ ፡፡ "አለኝ እየሳቀ፡፡ ገዛዝተን ከመጣን ቡሀላ ዶርም መግቢያ ድረስ ሸኝቶኝ ተመለሰ፡፡ ዶርም ስገባ ከ ሁለቱ በስተቀር ሌሎቹ ሻወር ሊወስዱ ወጥተዋል፡፡ ምግቡን ካቀራረብኩ ቡሀላ ሁሉም ሲመለሱ ተሰብስበን ምሳችንን በላን፡፡ ምናልባት ከደከማቸው ብዬ እንዳደረኩት ስለገባቸው በጣም አመሰገኑኝ፡፡
ጨዋታችን ቀጠለ፡፡ ስለገጠመኞቻችን እያወራን መሳሳቅ ጀመርን፡፡ በመሀል ስለ ፍሬ ጠየኩዋቸው፡፡ ሁሉም ዝም ዝም አሉ፡፡ "ምነው አግኝታቹት አታውቁም?" አልኩኝ ወደ ሚጣ እያየው፡፡ 'አረ ከዚ እንደሄድን እኮ በስንተኛው ቀን አጎቴጋር ምናምን ብሎ ወደ ባህርዳር ሄደ ከዛን ቡሀላ አንድ ቀን ነው እንዲሁ ለሰላምታ የተገናኘነው፡፡" አለችኝ፡፡ 'እና ለምንድነው ስልክ ማያነሳው?' አልኩኝ በድንገት ተናደድኩ፡፡ "የደወለልኝ ግዜ ስልኩን ሌላ ቦታ ረስቶት እንደሄደ እና ወደ ቤት ሲመለስ በዛው ተቀብሎ እንደሚመጣ ነው የነገረኝ፡፡ የዛን ቀንም የደወለልኝ በሰው ስልክ ነበር፡፡ "አለችኝ፡፡ እንደመንተባተብ እያለች፡፡ ሌሎቹ እንዳለ ዝም ብለው ያዪኛል፡፡ ምክንያቱ ምንም አልተዋጠልኝም፡፡ ግን ምንም ማለት አልፈልግም በይሁንታ ራሴን ነቅንቄ ወደ ሌላ ጨዋታ ገባን፡፡ በመሀል ስለ ኪሩቤል ማውራት ጀመርኩ፡፡ ከቀልዶቹ እያካፈልኩዋቸው ያደረግናቸውን ነገሮች እየነገርኳቸው ዶርሙን ሳቅ በሳቅ አደረግነው፡፡ እየተጫወትን ሳናስበው መሸ፡፡ መምሸቱንም ያወቅነው ኪሩቤል ሲደውል ነው፡፡
"ዛሬ ቀጣሽኝ አይደል? አይ ሰው ገና ለገና ጉዋደኞቼ መጡ ብለሽ ነዋ? እሺ እራት አንበላም ወይስ እሱንም ቴካዌ ላስመጣላቹ?" አለኝ ገና ስልክ ከማንሳቴ፡፡ ጉዋደኞቼ እራት ወጥተን እንድንበላ ስነግራቸው ተስማሙ፡፡ "እንደውም ጊቢውም ናፍቆናል እራት ብቻ ሳይሆን ጉብኝትም ጭምር ነው፡፡" እያሉ እየተሳሳቅን ልብሳችንን ቀያይረን ወጣን፡፡ ካፌ ስንደርስ ኪሩቤል በቁጥራችን ልክ ወንበር አስተካክሎ ጠበቀን፡፡ ከሁሉም ጋር ካስተዋወኩት ቡሀላ ሁላችንም ተቀመጥን፡፡ በኪሩቤል አቀባበል ሁሉም ተደስተዋል፡፡ ከግቢ ውጪ ሌላ ሆቴል ያለን ነው የመሰለን፡፡ እራት ከተመገብን ቡሀላ ጨዋታ ተጀመረ፡፡ ኪሩቤል አልተቻለም፡፡ ክብ ሰርተን ስንስቅ ካፌ ውስጥ ያሉት ተማሪዎች አይን በሙሉ እኛ ላይ ሆነ፡፡ በጣም ተጫወትን፡፡ ኪሩቤል ከጉዋደኞቼ ጋር በጣም ነው የተግባባው፡፡ ደስ የሚል ምሽትን አሳለፍን፡፡ ዶርም ከገባው ቡሀላ እንደለመድኩት ከኪሩቤል ጋር በስልክ አወራና እስቅ ጀመር፡፡ በድምፅ ካወራን ቡሀላ በፅሁፍ ማውራት ቀጠልን፡፡ አሁንም ግን የፍሬን ስልክ ሞክራለው፡፡ ይጠራል . . . አይነሳም፡፡ ጉዋደኞቼ ሁሉም ተኝተዋል፡፡ እኔ ግን በፍሬ ትዝታውስጥ ኪሩቤልን እያወራሁት ነው፡፡
ይ ቀ ጥ ላ ል . . .
ቻናላችንን ይቀላቀሉ
◦◦✧join 👇👇👇👇👇
@Mamusha23
@Mamusha23
@Mamusha23 🟢🟡🔴🟢🟡🔴🟢🟡🔴🟢🟡🔴🟢🟡🔴🟢🟡🔴
🇪🇹 #ኢትዮጵያ_ለዘለዓለም_ትኑር! 🇪🇹
❣ #ፍቅር_ያሸንፋል ❣
💞 #ሴና #ክፍል_ሠላሳ_አራት 💞
. . . በፍጥነት ከአልጋው ላይ ወርጄ የደወለውን ሳይ ኪሩቤል ነው፡፡ የፍሬን ስልክ እየጠበኩ ስለነበር ነው መሰለኝ አለመሆኑን ሳይ በጣም ቅር አለኝ፡፡ ኪሩቤልን ማውራት ጀመርኩ፡፡ በጣም ብዙ ሰአት ከኪሩቤል ጋር በስልክ አወራው፡፡ በጣም ተጫዋች ልጅ ነው፡፡ ቀልዶቹ ደሞ በእውቀት ላይ የተመሰረቱ ናቸው፡፡ አንዳንድ ሚያወራቸው ነገሮች እኔ ሚሰማኝን ስሜት በቀልድ አድርጉ ስለሆነ በጣም ተመችቶኛል፡፡ እንደዚ በአንድ ቀን መቀራረባችን በጣም ነው የገረመኝ፡፡ በመጨረሻም 'አረ ይቆጥርብካል በቃ ነገ ጥዋት ካቆምንበት እንቀጥላለን 'ስለው "አታስቢ ካርዱን በቁማሩ ብር ነው የሞላውት ከእራት በተረፈው "አለኝ፡፡ 'ይሄ ቁማር እውነትም አዋጪ ነው ነገም አስይዝ ከዛ ሙሉ ቀን እንንበሸበሽበታለን'አልኩት መልሼ፡፡ የሳቅ ብዛት ሆዴን አቁስሎታል፡፡ እኔም በአንድ ቀን ቀልደኛ ሆኛለው፡፡ ስልኩን ስዘጋው ጥዋት መልሼ እስካገኘው ቸኮልኩ፡፡ ልብሴን ቀያይሬ መብራት አጥፍቼ ተኛው፡፡
ጥዋት ከእንቅልፍ የቀሰቀሰኝ የኪሩቤል ስልክ ጥሪ ነበር፡፡ ገና አንድ ሰአት ነው፡፡ ገና ስልክ በማንሳቴ በተለመደው ጨዋታው ተቀበለኝ፡፡ አጣድፍ ከድርም እንድወጣ ካደረገኝ ብሀላ ካፌ ወሰደኝ፡፡ ካፌ ስንደርስ የመጀመሪያዎቹ ሳንሆን አንቀርም፡፡ ለምን በጥዋት እንደዚ እንደጠራኝ ስጠይቀው "ርቦኝ ነው "ሲል የመለሰልኝ መልስ በጣም አሳቀኝ፡፡ ትልቅ ቁምነገር እንደሚነግረኝ ሰው እንደዚ አሩዋሩጦ ያመጣኝ ለመብላት መሆኑን ሳስበው ሳቄን ማቁዋረጥ አልቻልኩም፡፡ ከጨዋታው በላይ ድፍረቱም ተመችቶኛል፡፡
ቁርስ ከጨረስን ቡሀላ ዛሬ ምሄድበት ከሌለ አብረን እንድንውል ጠየቀኝ፡፡ ምንም መሄጃ ስለሌለኝ አብሬው ለመዋል ተስማማው፡፡ ቀኑን ሙሉ ቦታ እየቀያየርን ስንስቅ እና ስንጫወት ጊቢውን ሳቅ በሳቅ አደረግነው፡፡ ኪሩቤል ለሳቅ የተፈጠረ ሰው እስኪመስለኝ ድረስ ባየው ነገር በሙሉ ሳቅ መፍጠር ይችላል፡፡ በደረስንበት ቦታ ሁሉ ጨዋታ ያመጣል፡፡ ያለፉትን አመታት በሙሉ ሳቅ በሳቅ ያደረጋቸው እስኪመስል ድረስ ነው ያዝናናኝ፡፡
ማታ ላይ እራት በልተን ተጨዋውተን ዶርም ከሸኘኝ ብሀላ "ዛሬ ግን አልደውልልሽም" አለኝ፡፡ 'ለምን 'ብዬ ስጠይቀው "እሱን ደውይና በስልክ ነግርሻለው" ብሎኝ አቅፎ ከሳመኝ ብሀላ ቻው ብሎኝ ሄደ፡፡ ዶርም ከገባው ቡሀላ ልብሴን ቀያይሬ አልጋዬ ላይ ከወጣው ቡሀላ ለኪሩቤል ደወልኩለት 'ለምንድነው ቆይ አልደውልም ያልከኝ? ' አልኩት ዝቅ ባለ ድምፅ፡፡ "እንዴ እኔ አልደውልም ያልኩት አንቺ እንድትደውይ ነዋ "አለኝ እየሳቀ፡፡ አይ ኪሩቤል በነዚ ቀናት ልቤን ሚነካ ደስታን የፈጠረ ሰው ነው፡፡ ጉዋደኞቼን ረሳዋቸው፡፡ የፍሬን ናፍቆት በትንሹም ቢሆን አስታገሰልኝ፡፡' ብቻዬን መሆኔን አይቶ ፈጣሪ ያመጣልኝ ጉዋደኛዬ ነክ 'ስል በጨዋታ መሀል ነገርኩት፡፡ ከዛም በመቀጠል ግቢ ከገባው ግዜ ጀምሮ ስላለው የግቢ ህይወቴ በአጠቃላይ ነገርኩት፡፡ ባገኘውት በሁለት ቀን ውስጥ እነዴት እንዲ አምኜ ስለራሴ እንደነገርኩት አላውቅም ግን በውስጤ ስለሱ የሆነ እምነት አደረብኝ፡፡ ስለኔ በነገርኩት ግዜ የነገረኝ ምክር አዘል ነገር ልክ እኔ ምፈልገውን እና ማስበውን አይነት ነገር ነበር፡፡ ውስጤን ሚያነበው ያህል ነው የተሰማኝ፡፡ ቀልዱንም ሆነ ቁምነገሩን ይችልበታል፡፡ በስልክ በጣም ብዙ ሰአት ካወራን ብሀላ ጥዋት እንገናኝ ተባብለን ተሰነባበትን፡፡ ኪሩቤል የመከረኝን ደግሜ ደጋግሜ ማሰላሰል ጀመርኩ፡፡ የነገረኝ ነገሮች በሙሉ በትክክል አስባቸው የነበሩትን ነው፡፡ እሱን እያሰላሰልኩ እንቅልፍ ወሰደኝ፡፡
ጥዋት እንደትናንቱ የኪሩቤል ስልክ ቀሰቀሰኝ፡፡ አብረን ቁርስ መብላት ፣መጫወት ፣መሳሳቅ ብቻ ጥሩ ጊዜን እያሳለፍን ነው፡፡ እመኛቸውው የነበሩ ቀናቶችን ማሳለፍ ጀመርኩኝ፡፡ ሀሳብ ጭንቀት የሌለባቸውን ቀናት ማሳለፍ ጀመርኩኝ፡፡ ኪሩቤል በነዚህ ሶስት ቀናት ብዙ ነገሮችን በሳቅ እያወዛ የሞራል ግንባታን ጨምሮ ብዙ ትምህርት ሰጠኝ፡፡ ነገ ጉዋደኞቼ ይመጣሉ፡፡ እሱንም ያወኩት ሚጣ በመደወሉዋ እንጂ ረስቼው ነበር፡፡ ከሁንም ለፍሬ ስልክ መደወሉን አላቆምኩም ፡፡ በሌላ ስልክም ብደውል አይነሳም፡፡ ዴቭን ስጠይቀው ሰላም ነው ይለኛል፡፡ ምን አድርጌው እንደዘጋኝ አላውቅም፡፡ ወይ ትምህርት ሲጀመር መምጣቱ ስለማይቀር የዛኔ አገኘዋለው ስል አሰብኩ፡፡ ከኪሩቤል ጋር ግቢ ውስጥ ያልረገጥነው ቦታ የለም ማለት ይቻላል፡፡ ሙሉ ቀን ሳቅ እና ጨዋታ፡፡ ጉዋደኞቼ ሲመጡ እንደማስተዋውቀው ቃል ገባውለት፡፡
ይ ቀ ጥ ላ ል . . .
ቻናላችንን ይቀላቀሉ
◦◦✧join 👇👇👇👇👇
@Mamusha23
@Mamusha23
@Mamusha23 🟢🟡🔴🟢🟡🔴🟢🟡🔴🟢🟡🔴🟢🟡🔴🟢🟡🔴
🇪🇹 #ኢትዮጵያ_ለዘለዓለም_ትኑር! 🇪🇹
❣ #ፍቅር_ያሸንፋል ❣
💞 #ሴና #ክፍል_ሠላሳ_ሁለት 💞
. . . ልክ ዶርም እንደደረስኩ በሩን ልከፍተው ስል ቁልፍ ነው፡፡ ማንም የለም ማለት ነው፡፡ የኔን ቁልፍ አውጥቼ በሩን ከፍቼ ገባው፡፡ ዶርሙ ያኔ ስንሄድ ትተነው እንደሄድነው ነው፡፡ ደነገጥኩኝ! ማንም አልመጣም ማለት ነው? ቦርሳዬን ካስቀመጥኩ ቡሀላ ስልኬን አውጥቼ ለሚጣ ደወልኩላት፡፡ ስለተነፋፈቅን ብዙ አወራን፡፡ ሰሞኑኑን ስልኬ ተበላሽቶ እንደተዘጋ እና አሁን ዶርም እንደሆንኩ ስነግራት ብዙ ቀን ደውለው እንዳጡኝ ነግራኝ" ምዝገባ ሀሙስ ስለሆነ እሮብ እንግባ ተባብለን ነው " አለችኝ፡፡ በጣም ተበሳጨው፡፡ ግን ወደቤት ከምመለስ ሁለት ቀን ዶርም ብቻዬን ባድር ይሻለኛል ብዬ ወሰንኩ፡፡
አልጋዬ ላይ ጋደም ብዬ ለፍሬ ደወልኩለት ፤አያነሳም፡፡ ደጋገምኩ መልስ የለም፡፡ ለ ዴቭ ደወልኩለት ገና ከማንሳቱ በወሬው ሳስቀኝ ጀመር፡፡ በመደወሌ በጣም ነው የተገረመው፡፡ ትንሽ ካወራውት ብሀላ ስለ ፍሬ ጠየኩት፡፡እሱ አዲስ አበባ እንዳለና ፍሬን በስልክ እንጂ በአካል እንዳላገኘው ነገረኝ፡፡ ለመጨረሻ ግዜ ከሰአታት በፊት መደዋወላቸውን ገልፆ ደህና እንደሆነ ሲነግረኝ ተረጋጋው፡፡ ጊቢ ከመጣ እንዲደውልልኝ ነግሬው ስልኩን ዘጋውት፡፡
ዶርም ውስጥ ብቻዬን መቀመጡ ሲጨንቀኝ ራሴን ዘና ለማድረግ ወደ ካፌ ሄጄ ሻይ እየጠጣው ቲቪ ማየት ጀመርኩ፡፡ ካፌው ውስጥ ብቻዬን የተቀመጥኩት እኔ ብቻ ነኝ፡፡ከአንድ ጥግ ተቀምጬ ቲቪ እያየው ሻይ ጠጣለው፡፡ በመሀል በመሀል ስልኬን እያነሳው ለፍሬ ደውላለው፡፡ አሁንም አያነሳም፡፡ምናልባት ስራ ላይ ይሆናል ስል አሰብኩ፡፡ስልኬን አስቀምጬ ቲቪውን መመልከቴን ቀጠልኩ፡፡ ብቻዬን ቁጭ በማለቴ ጨንቆኛል፡፡ ግን ዶርም ገብቼ ከምተኛ አዚህ ብቀመጥ ይሻለኛል ስል አሰብኩ፡፡
ቲቪውን እየተመለከትኩ ድንገት "ቲቪ ውስጥ ማንን እየፈለግሽ ነው? እንደዚ ያፈጠጥሽበት?" አለኝ አንድ ወንድ አጠገቤ ቆሞ፡፡ ቀና ብዬ አየውት፡፡ ምንም መልስ ሳልሰጠው አይኔን ወደ ቲቪው መለስኩኝ፡፡ " ከቅድም ጀምሮ እያየውሽ ነበር ብቻሽን ሆነሽ የቀጠርሽው ወይ የቀጠርሻት አሊያም የቀጠርሻቸው ቀሩ መሰለኝ፡፡ ቅር ካላለሽ ልቀመጥ? እኔም የቀጠርኳት ቀርታ ብቻዬን ቁጭ ብዬ ከምቆዝም ይሻላል" አለኝ አጠገቤ እንደቆመ፡፡ በእርግጥ ለኔም ብቻዬን ከመቀመጡ የተሻለ ነው፡፡ "እና ለምን ቆምክ አትቀመጥም?" አልኩት፡፡ "አረ ሳላስፈቅድ የመቀመጥ ልምዱም ስርአቱም ድፍረቱም ወጉም የለኝም፡፡ አስፈቅዶ በመቀመጥ አንቱታን ያተረፍኩ ተቀማጭ ነኝ፡፡ የቱጋ ልቀመጥ ታዲያ አንቺ የመረጥሽልኝ ወንበር ይመቸኛል?" አለኝ ፈገግ እያለ፡፡ ንግግሩ አዝናንቶኛል፡፡ የፈለከው አልኩት ፈገግታዬን ሳልደብቅ፡፡ ፈገግ ስል ይበልጥ ቀለል አለው መሰለኝ ከፊት ለፊቴ ያለውን ወንበር እየሳበ ወሬውን ካቆመበት ቀጠለ፡፡
"እናም እልሻለው ባትመጪም ቅጠሪኝ ብያት ላትመጣ ቀጥራኝ ይኸው ጠብቃታለው " አለኝ ወንበሩ ላይ ተስተካክሎ እየተቀመጠ፡፡ ታሪኩን ከመሀል ጀምሮ መሀል ላይ አቆመው፡፡ ምንም አላልኩትም ፈገግ ብዬ ተቀበልኩት፡፡ "ኪሩቤል እባላለው "አለኝ ቀኝ እጁን እየዘረጋልኝ፡፡ "ሴና እባላለው "አልኩት እየጨበጥኩት፡፡ ጠይም ረዘም ያለ ተጫዋች ቆንጅዬ ነገር ነው፡፡ ገና ከመምጣቱ ጀምሮ ፈገግታ ከፊቱ አልተለየውም፡፡
ከኪሩቤል ጋር ብዙ ተጨዋወትን፡፡ እሱ እየተናገረ እኔ እያዳመጥኩ አልፎ አልፎ እኔም እየተናገርኩ እየተሳሳቅን ሳናስበው ብዙ ቆየን፡፡ ምሳ ሰአት ሲደርስ ኪሩቤል የእጅ ሰአቱን ከተመለከተ ብሀላ "ካፌ ሳይዘጋ ልሂድ ምሳ ትሄጃለሽ ወይስ እዚ ነሽ?" አለኝ፡፡ አይ እኔ እዚሁ ነኝ አልኩት፡፡ "እንደዛ ከሆነ በቃ እዚሁ በላለው" አለኝ "እንዴ ታዲያ ለምን መጀመሪያ ልሂድ አልክ?" ስለው "አይ ምሳ እዚ ልብላ ምናምን ስል ጉራ እንዳይመስል ነው ለዛሬ እዚ ለመብላት ሚሆን አላጣም" ብሎ ከኪሱ ብዙ ዝርዝር ብር አወጣ፡፡ ነገረ ስራው አሳቀኝ፡፡ "አትሳቂ ይደርስብሻል እኔም ደርሶብኝ ነው" አለኝ ከሌላኛው ኪሱም ዝርዝር ሳንቲም እያወጣ፡፡ "ምንድነው የደረሰብክ?" አልኩት ሳቂን በግድ እያፈንኩ፡፡ "ብዙ ብር የያዝኩ እንዲመስለኝ ከቤት የተሰጠኝን 100ብሩ በሳንቲም እና በአንዳንድ ብር ዘርዝሬ ነው" አለኝ ጠረቤዛላይ የዘረገፈውን ሳንቲም እያስተካከለ፡፡ ከዚ በላይ ሳቄን መቆጣጠር አቃተኝ . . .ለቀኩት 'ይሄሁሉ 100ብር ነው? አልኩት፡፡ አዎ አለኝ በጭንቅላቱ አነቃንቆ፡፡ ሳንቲሙን አስተካክሎ ከጨረሰ ብሀላ ወደ ኪሱ እየመለሰ "በቃ አንዳንድ ምግብ አዘን በአንድ ላይ አድርገን እንብላ ?" አለኝ ፈገግታ በማይለየው ፊቱ፡፡ እኔ ሳቅ በሳቅ ሆኛለው . . .
ይ ቀ ጥ ላ ል . . .
ቻናላችንን ይቀላቀሉ
◦◦✧join 👇👇👇👇👇
@Mamusha23
@Mamusha23
@Mamusha23 🟢🟡🔴🟢🟡🔴🟢🟡🔴🟢🟡🔴🟢🟡🔴🟢🟡🔴
🇪🇹 #ኢትዮጵያ_ለዘለዓለም_ትኑር! 🇪🇹
❣ #ፍቅር_ያሸንፋል ❣
💞 #ሴና #ክፍል_ሠላሳ 💞
. . . ወንድሜ እኔን እየጠበቀ ነበር መሰለኝ ገና ሲያየኝ ከተቀመጠበት ብድግ ብሎ አይኑን እንዳፈጠጠ ወደኔ መራመድ ጀመረ፡፡ አጠገቤ ደርሱ ጥርሱን እንደነከሰ አንድ ግዜ በጥፊ መታኝ፡፡በጣም በሀይል ስለመታኝ ተገፍትሬ ከሳሎኑ በር ጋር በጭንቅላቴ ተጋጨው፡፡ ዞረብኝ ፣ጭልም አለብኝ ፣ወንዴሜ ከመታኝ ብሀላም ይጮሀል ፣ይቆጣል፡፡ እኔ ጩኸቱ እንጂ ምን እንደሚል አይሰማኝም፡፡ እንባዬ ለጉድ ይፈሳል ፣ጥርሴ ደምቶአል፡፡ ምንም አላልኩትም እያነባው ወደ ውጪ ወጣው፡፡
እናቴ ቤት አልነበረችም፡፡ ሰራተኛችን ስታየኝ ደነገጠች፤ሮጣ መጥታ እንባዬን እየጠረገች ምን እንዳጋጠመኝ ትጠይቀኝ ጀመር፡፡ መልስ አልሰጠዋትም ፡፡ ወደ መታጠቢያ ቦታ ወስዳኝ ፊቴን ታጠብኩ፡፡ የደማው ጥርሴ ተጉመጥምጬ ወጪ በረንዳላይ ተቀመጥኩ፡፡ እንባዬ አልቆመም ወንድሜ በተቀመጥኩበት መጥቶ ጩኸቱን ቀጠለ፡፡ መልስ አልሰጠውትም፡፡ ተቆጥቶ ፣ጭኾ ሲያበቃ መኪናው ውስጥ ገብቶ ከግቢው ወጣ፡፡ሰራተኛችን አስወጥታው የውጪ በር ከዘጋጋች ቡሀላ ወደኔ መጥታ ስለሆነው ነገር ትጠይቀኝ ጀመር፡፡
ላወራላት ስል እንባ ይተናነቀኛል ፣እልህ ያንቀጠቅጠኛል ፣እንተባተባለው፡፡ ጥርሴ አሁንም ይደማል፡፡ በድጋሜ እንባዬንም ደሜንም ታጥቤ ተመልሼ ቁጭ አልኩ፡፡አሁንም እያነባው ነው፡፡ በሩ ተንኳኳ፡፡ ሰራተኛዋ ሮጣ ከፈተች፡፡ እናቴ ነች፡፡ ገና ሳያት እንደ ህፃን ልጅ ስቅስቅ ብዬ አለቀስኩ፡፡ እየተንተባተብኩ የሆነውን ነገርኳት፡፡ እናቴ እንደህፃን ልጅ እቅፍ አድርጋ አባበለችኝ፡፡ ከተታጠብኩ ቡሀላ ቁርሴን በመጠኑ ቀማምሼ ክፍሌ ገባው፡፡
ዛሬ ቀኔ አጀማመሩ ጥሩ አይደለም በጣም ከፋኝ፡፡ ትንሽ ልጅ ሆኜ እንኳል ያልተገረፍኩ ልጅ ዛሬ በዚ እድሜዬ ሊያውም ምንም በማላውቀው ምክንያት መመታቴን ሳስበው አሁንም እንባዬ ይመጣል፡፡ ስልኬን ተነጥቄ ፣ተመትቼ ፣በጥዋቱ ቀኑ ከብዶኛል፡፡ አልጋዬ ላይ ጋደም እንዳልኩ አሁን ስላለውበት እና ስለ ወደፊት ምን ሊሆን እንደሚችል ፣ምን ማድረግ እንዳለብኝ ማሰብ ጀመርኩ፡፡ 'ወንድሞቼ ምን ሆነው ነው እንደዚህ ሚያደርጉኝ?' እያልኩ ራሴን ደጋግሜ ጠይቃለው፡፡
ስልኬ ተወስዶ ፍሬ ናፍቆኛል፡፡ ትምህርት ሊጀመር ቀናቶች ይቀራሉ፡፡ እኔ የዛሬው ቀን ራሱ አልመሽ ብሎኛል፡፡ ክፍሌ አልጋዬ ላይ ጋደም እንዳልኩ የግድግዳውን ሰአት ደጋግሜ እመለከታለው፡፡ ቀኑ ረዘመብኝ፡፡ እንኳን ሊመሽ የምሳ ሰአቱ ራሱ አልደርስ ብሎኛል፡፡ የተረገመ ቀን ሆነብኝ፡፡አልጋዬ ላይ እገላበጣለው፡፡ ምንም ምቀይረው ነገር የለም፡፡ አንዳንድ መፅሀፍት ለማንበብ እየገለጥኩ መልሼ አስቀምጣቸዋለው፡፡ማደርገው ግራ ገባኝ፡፡ ፍሬ ናፈቀኝ፡፡ 'ስልኬ ዝግ ሲሆንበት ይሄን ግዜ ምን እያሰበ ይሆን?' አስባለው፣ ምሽቱን ናፈኩት፡፡ ግን ደግሞ ሲመሽ ወንድሞቼ ይመጣሉ፡፡ ያ' ጭቅጭቃቸው ደሞ ይቀጥላል፡፡ እኔ በምን አይነት መንገድ ራሴን ከዚህ ማዳን እንዳለብኝ ማሰብ ጀመርኩ፡፡ ምንም ነገር ፤አንድም መላ ላገኝ አልቻልኩም፡፡ አሁንም ቀጠልኩ . . .
ይ ቀ ጥ ላ ል . . .
ቻናላችንን ይቀላቀሉ
◦◦✧join 👇👇👇👇👇
@Mamusha23
@Mamusha23
@Mamusha23 🟢🟡🔴🟢🟡🔴🟢🟡🔴🟢🟡🔴🟢🟡🔴🟢🟡🔴
(ቀልቤን ባትሰርቂው)
ካፈቀርኩሽማ ዘመናት አለፈ
ወተቱም እረግቶ ፣ ለቅቤ ተረፈ
እሳቱም ባነደው ፣ አመድን ወለደ
ደግሼም ሳልጠራሽ፣ ኑሮተወደደ
ይኸው በትረካ፣ ስምሽን እያወጋሁ
ስንቱን አቀበት ፣ በሀሳቤ ወጣሁ
የሆዴ ማጀትም ፣ ቅኔውን ቢሰፋ
ወርቁን አላገኘ፣ ሚዛንም አልደፋ።
ሰውነቴም ቢሆን አቅሙን ተነጠቀ
ፍቅርሽን ተርቦ፣ በናፍቆት አለቀ።
ድሮም እኮ - - -
ያለባለቤቱ አይነድም እሣቱ
ማሩም ይቀርና ይበዛል እሬቱ
እህልም እኮ ካልዘሩት በወቅቱ
አረም ይከበዋል አያምርም ውጤቱ
ስለዚህ ውዴ - - -
በታሪክ ጀበና ፣ ስማችን ይቀዳ
ከራሳችን አልፎ፣ እንትረፍ ለባዳ
እንኳንስ የሰው ልጅ ፣ የተማረው ቀርቶ
እንስሳም ይኖራል ፣ በህብረት ተስማምቶ
እንደው ምን አለበት ፣ ቀልቤን ባትሰርቂው
አብረሽኝ ብትሆኝ ልቤን ባሳርፈው።
ቻናላችንን ይቀላቀሉ
◦◦✧join 👇👇👇👇👇
@Mamusha23
@Mamusha23
@Mamusha23 🟢🟡🔴🟢🟡🔴🟢🟡🔴🟢🟡🔴🟢🟡🔴🟢🟡🔴
💞 #ሴና #ክፍል_ሀያስምንት 💞
. . . ታክሲ ውስጥ እንደገባው ወደቤት መሄድ ስጀምር ቅር ቅር ይለኝ ጀመር፡፡ ከግቢ እየራኩ ስሄድ በመስኮት ዞሬ ተመለከትኩ፡፡ ሆዴን ባር ባር አለኝ፡፡ ሁለት ሳምንት ቤት ታስሬ ልቀመጥ ነው፡፡ የዶርሜ ልጆች ከ አሁኑ ናፈቁኝ፡፡ "ፍሬን ሁለት ሳምንት በ አካል አላገኘውም ማለት ነው?" ስልኬን አውጥቼ ማዳመጫዬን ጆሮዬ ላይ ካደረኩ ቡሀላ ለስለስ ያለ ሙዚቃ ከፍቼ የታክሲውን ጫጫታ ላለመስማት ድምፁን ከፍ አድርጌ እየሰማው ወደቤት ጉዞዬን ቀጠልኩ፡፡ የፍሬ ድምፅ እየተመላለሰ በሀሳቤ ይመጣብኛል "ሴና አፈቅርሻለው . . . " ታክሲው ጉዞውን ቀጥሎአል፡፡ እኔም ሙዚቃ እየሰማው በሀሳቤ ገስግሻለው . . . ዶርም ውስጥ ያለን ፍቅር ያሳለፍናቸው እያንዱ ቀናት የየራሳቸው የሆነ ገፅ አላቸው፡፡ ከፍሬ ጋር ያሳለፍናቸው ቀናት ፣የምሽት ቆይታችን . . . እኔ በትዝታ ወደ ሁዋላ ተመልሻለው ፤ታክሲው ወደፊት ይገሰግሳል፡፡
እቤት ስደርስ እናቴ ሁሌም እንደምታደርገው እንግዳ እንደሚመጣበት ሰው ሁሉን ነገር አዘጋጅታ ልብ በሚያቀልጠው ፈገግታዋ ተቀበለችኝ፡፡ እውነት እናቴ ባትኖር በወንድሞቼ ንዝንዝ እና በአባቴ ቁጣ ገና ድሮ ከቤት በጠፋው ነበር፡፡ እናቴንም ሳትፈልግ ተጨቃጫቂ እና ቁጡ እያደረጉዋት ቢሆንም ከነሱ ግን ትሻላለች፡፡ ገበታ ቀርቦ ቡና እየጠጣው ኸ እናቴ ጋር ስለ ግቢ ማውራት ጀመርኩ፡፡ እንደ ሁል ግዜው ስለ ትምህርቱ ብቻ ነው ማወራላት፡፡
ክፍሌ ገብቼ አልጋዬ ላይ ጋደም አልኩ፡፡ ከእንቅልፌ የተነሳውት ስልኬ ሲጮህ ነው፡፡ ወንድሜ ነው፡፡ አራት ግዜ ደውሎ አልሰማውትም ነበር አንስቼ አወራው ጀመር፡፡ የስልኩ መጮህ ሳያንስ እሱም ጮኸ፡፡ ቤት እንደገባው እና ስልኩን ያላነሳውት ተኝቼ እንደሆነ ነገርኩት፡፡ ብዙ ነገር ነው ያወራው ሁሉም ነገር ጩኸት እና ቁጣ ስለሆነ አልሰማውትም፡፡ ስልኩን ሲዘጋው ብቻ ኡፈይ አልኩ፡፡ ሰአቱ በጣም ሄዶአል፡፡ እናቴ በር ከፍታ እየገባች"አልቀሰቅስሽም ብዬ ነው እኮ ምሳ ብይ አስር ሰአት ሆነ እኮ" ብላኝ ሄደች፡፡ ጥዋት የለበስኩትን ልብስ እንኳን አልቀየርኩም ነበር፡፡
ልብሴን ቀይሬ ተታጥቤ ምሳ እየበላው ፍሬ ደወለ፡፡ አላነሳውለትም፡፡ ምሳዬን ከበላው ቡሀላ ክፍሌ ገብቼ ለፍሬ ደወልኩለት፡፡ ድምፄን ዝቅ አድርጌ ነው ማወራው፡፡ እሱ ሚለው ይሰማኛል የኔን ግን መስማት አልቻለም፡፡ በፅሁፍ ማውራት ጀመርን፡፡ ገና አንድ ቀን ሳናድር በጣም ተነፋፍቀናል፡፡ ቤት በሰላም እንደደረሰና ቤተሰቦቹን እንዳገኛቸው ነገረኝ፡፡ ከፍሬ ጋ' እያወራው ትልቁ ወንድሜ መጣ፡፡ ከመግባቱ ሰላምታ እንኳ ሳያቀርብ በጭቅጭቅ ጀመረኝ፡፡ ስልኬን አስቀምጬ ሰማው ጀመር፡፡ ምንም ሚያስቆጣ ነገር የለም፡፡ ዝም ብሎ ይጮህብኛል፡፡ ኡፍፍፍፍ. . . . . አሁንስ ሰለቸኝ! አሁን እንደበፊቱ ምታገስበት አቅም እያጣው ነው ፣ሰምቶ እንዳልሰማ ሚያደርግ ችሎታዬ ጠፍቶአል፡፡ የዶርም ጉዋደኞቼን እና ወንድሞቼን ማነፃፀር ጀመርኩ፡፡ ዶርም ውስጥ የተለያዩ ቤተሰብ ልጆች ሆነን ልክ እንደ አንድ እናት ልጆች ነው ያለን ፍቅር፡፡ ፍቅራችን ደስ ይላል፡፡ አንዳችን ሌላውን ላለማስከፋትስንሞክር ድንገት ብንስት እንኳ ይቅርታ እየተጠያየቅን፡፡ ቤት ግን ወንድሞቼ ፍፁም አንባገነን! ራሳቸውን ብቻ ሚሰሙ፡፡ ቤት ከኖርኩባቸው አመታት ዶርም ያሳለፍኩዋቸው ወራት እጅጉን የተለዩ ናቸው፡፡
የወንድሜ ንዝንዝ በአጭሩ ሚቋጭ አይደለም ጭራሽ ሌላኛውም ወንድሜ መጣ፡፡ ለሁለት አሰልቺ እና የማይመለከተኝን ጥያቄ ይጠይቁኝ ጀመር፡፡
ቤት ከመጣው ገና በመጀመሪያ ቀን ተሰላቸው፡፡ የቀሩኝ ቀናት ሳስባቸው አመታት የሆኑ ያክል ተሰማኝ፡፡ እንዴትም ብሎ ሠዓቱ ሄደ፡፡ምሽቱ መጥቶ ሁላችንም ለእራት ቀረብን፡፡ ከእራት ቡሀላ ሁሉም ወደ መኝታቸው ሄዱ፡፡እኔም ክፍሌ ገባው፡፡ ተመስገን አንድ ቀን አለፈ፡፡ ወዲያው ስልኬን ይዤ አልጋዬ ላይ ዘልዬ ወጣው፡፡ የፍሬን መልእክት ካነበብኩ ቡሀላ መልሼ ላኩለት፡፡ የዶርም ልጆች ሁሉንም በስልክ አወራዋቸው፡፡ ሁሉም በሰላም እንደገቡ ነገሩኝ፡፡ ሴቶችን ሳወራ ድምፄን ከፍ ባደርግ ችግር የለውም፡፡
እስኪነጋ ደሞ ነፃነት አለኝ፡፡ ክፍሌን ከዘጋው ማንም ሊረብሸኝ ቢሞክር ፣ ቢጠሩኝ ድምፄን አጥፍቼ ዝም እላለው፡፡ ነግቶ ቁርስ ካልተባለ ማንንም አልሰማም፡፡ አሁን አልጋዬ ላይ ጋደም ብዬ ከፍሬ ጋር በፅሁፍ ማውራቴን ቀጠልኩ . . .
ይ ቀ ጥ ላ ል . . .
💞 #ሴና #ክፍል_ሀያስድስት 💞
. . . ከዛ ግን ደስ ሚል ነገር እየተሰማኝ መጣ፡፡ ፍሬ አንገቴ ስር ሲስመኝ ሰውነቴ ይነዝአኝ ጀመር፡፡ ሳላስበው ከንፈሬን ሳመኝ፡፡ መጀመሪያ ደነገጥኩ ግን ማንገራገር አልቻልኩም፡፡ ደስ የሚል ነገር አለው፡፡ ስሜቱ አዲስ ሆነብኝ ግራ ሚያጋባ፡፡ ደስ ሚል እእእእእ...... እኔንጃ ብቻ ወስብስብ ፤ድብልቅልቅ ያለ ስሜት ተሰማኝ፡፡የመጀመሪያዬ ስለሆነም መሰለኝ እኔንጃ ማልገልፀው አይነት ስሜት ተሰማኝ፡፡ ፍሬ ከሳመኝ ቡሀላ ወደ ጆሮዬ "አፈቅርሻለው!" አለኝ ለሹክሹክታ፡፡ "ሴና አፈቅርሻለው! የኔ ብቻ እንድትሆኚ ፈልጋለው!" አለኝ ጆሮዬን እየሳመኝ፡፡ በጣም ደነገጥኩ ፣ፊቴን ሲያልበኝ ይሰማኛል! የፍሬ ትንፋሽ ሙቀት ጆሮዬን አልፎ ሙሉ ሰውነቴን እያሞቀኝ፡፡ እኔ ለማስቆም ምንም አላደረኩም ፣ሚያደርገውን ከመቀበል ውጪ "ሆዴ በጣም ነው ምወድሽ" አለኝ ፍሬ እቅፍ አድርጎ ደረቱ ላይ ድግፍ እያደረገኝ፡፡
በፍሬ እቅፍ ውስጥ ሆኜ ብዙ ነገር ማሰብ ጀመርኩ፡፡ 'አፈቅርሻለው' ሲለኝ የተሰማኝ ስሜት የደስታ ይሁን የድንጋጤ አላውቅም፡፡ ምንም መልስ አልሰጠውትም፡፡ በፍሬ እቅፍ ውስጥ እንዳለው ስልኬ ጠራ ወንድሜ ነበር፡፡
ከፍሬ ራቅ ብዬ ወንድሜን ካወራውት ቡሀላ ሰአቱም ስለመሸ ከፍሬ ጋር ተያይዘን ወደ ዶርም መሄድ ጀመርን፡፡ ወደ ዶርሜ ስደርስ ፍሬን እቅፍ አድርጌ ጉንጩን ሳምኩት፡፡ እሱ እጁን ኪሱ ከቶ እንደቆመ ነበር፡፡ ፍጥነቴ የገረመው ይመስላል፡፡ ቻው ከተባባልን ቡሀላ ወደ ዶርሜ ሄድኩ፡፡ ዶርሜ እንደገባው ሁሉንም ጉዋደኞቼን ደስታ በተሞላው ሁኔታ ሰላም ካልኳቸው ቡሀላ አልጋዬ ላይ ወጥቼ ጋደም አልኩ፡፡
"አፈቅርሻለው!" የፍሬ ድምፅ በውስጤ እየተመላለሰ ነው፡፡"አፈቅርሻለው!" አልፎ አልፎ የሳመኝ ከንፈሬን አጣቴ እየዳበስኩ ፈገግ እላለው፡፡ ምሽቷን እያሰበኩ በሀሳቡ ወደ ፍሬ ሄጃለው፡፡ ፍሬ በዚ ሰአት ምን እየሰራ ይሆን? እሱስ ምን እያሰበ ይሆን? ሀሳቤ እንዳለ ፍሬ ሆነ፡፡ አልጋዬ ላይ እየተገላበጥኩ ፍሬን ብቻ አስበዋለው፡፡ እነ ሚጣ ዝም ብለው ይታዘቡኛል፡፡ እኔ በሀሳብ ፍሬ ጋር ሄጃለው፡፡
"አንቺ ልጅ አረ ወደራስሽ ተመለሽ ፍንድቅድቅ አልሽ እኮ፡፡" አለችኝ እኑካ ወደ ቤት ምትወስዳቸውን እቃዎች እያስተካከለች፡፡ "አዎ ምን ተገኝቶ ነው እስኪ?" ሁሉም የተለመደ ጥያቄያቸውን አከታተሉብኝ፡፡ "አረ ረፍት ስለደረሰ ነው፡፡ ሌላ ምንም አይደለም"ብዬ ጉዳዩን ካደባበስኩ ቡሀላ ጨዋታ ለማስቀየር ሞከርኩ፡፡ስለ ሌላ ነገሮች ማውራት ስንጀምር ስልኬ መልእክት ገባ፡፡ ፍሬ ነው የላከልኝ መልእክት ግን በፊት ከሚልክልኝ የተለየ ነው፡፡ ጋደም ካልኩበት ቀና ብዬ ማንበብ ጀመርኩ፡፡ መልእክቱ እንዲህ ይላል"ሴና ገና የመጀመሪያ ቀን ካገኘውሽ ግዜ ጀምሮ ላንቺ ለየት ያለ ነገር ነበረኝ፡፡ በቀረብኩሽ ቁጥር ደግሞ ይበልጥ ነው የወደድኩሽ፡፡ ያኔ ትዝ ይልሻል . . . " ሚጣ ስልኬን ነጠከችኝ፡፡ አልጋዬ ላይ ቁጭ ብዬ እያነበብኩት ሲጠሩኝም አልሰማውም ሚጣ መጥታ ስልኬን እስክትቀማኝ ድረስ በ ፍሬ ፅሁፍ ላይ አተኩሬ ሚያደርጉትን አልሰማውም ነበር፡፡
የተነጠኩትን ስልኬን ለመቀበል ብሞክርም ማይቻል ሆነብኝ፡፡ ያለኝ አማራጭ መለመን ብቻ ነው፡፡ "እኛ ሰው አይደለንም? ስልክሽ ላይ ምን ቢኖረው ነው እንደዚ እስክትተሪ የማትሰሚን?" ሚጣ ስልኬን እንደያዘች በንዴት ስሜት ትተይቀኝ ጀመር፡፡ "አረ እኔ እንደዛ አይደለም . . . እኔኮ እ. . ." አላስጨረሰችኝም "ቆይ ምን ተልኮልሽ ነው ? ልየው እስኪ "ብላ ስልኬን መክፈት ጀመረች፡፡ "እንዴ እንደዛማ አይሆንም የውልሽ ሚጣ " መከራከር ጀመርኩ"ይከፈት አይደል?" ሁሉንም በአንድነት ጠየቀቻቸው፡፡" ሁሉም በአንድነት "ይከፈት ! ይከፈት! " በአንድ ድምፅ ዶርሙን ሌላ ድባብ ፈጠሩበት፡፡ ልመናው አልሳካ ቢለኝ ተስፋ ቆርጬ ቁጭ አልኩ፡፡ ሚጣ የተላከችልኝ መልእክት ከፈፈተች "ላንብበው"ላንብበው?" አለች ጮክ ብላ "አዎ ይነበብልን!" ሁሉም ተስማሙ ሚጣ ለማንበብ ጉሮሮዋን ስላ ከተዘጋጀች ቡሀላ . . .
ይ ቀ ጥ ላ ል . . .
❣
ሳቄን መልሽልኝ .☞(ሳሙኤል አዳነ)
ተግባር ላይ ያልታየ
ቃልሽን አምኜ ፤
እንችን ብቻ እያሰብኩ
ሰማይ ምድር ሁኜ ፤
ፊደል አሳምረሽ
የሰጠሽን ተስፋ፤
ድንገት ብትለይኝ
ሳቄን ይዞት ጠፋ።
ሳቄን መልሽልኝ
ልቤን ትቸዋለሁ፤
ልብ ማለት ቀርቶ
መስማት ጠልቻለሁ።
ቻናላችንን ይቀላቀሉ
◦◦✧join 👇👇👇👇👇
@Mamusha23
@Mamusha23
@Mamusha23 🟢🟡🔴🟢🟡🔴🟢🟡🔴🟢🟡🔴🟢🟡🔴🟢🟡🔴
💞 #ሴና #ክፍል_ሀያአራት 💞
. . . የተዘጋጀልኝ ነገር ምን እንደሆነ ለማየት ጓጓው፡፡ "ይሄንን ያደረኩት በብዙ መልኩ አመዛዝኜ ነው፡፡ በዶርማችን ውስጥ የሴና የሰሞኑ ጭንቀቱዋ ሁላችንንም ያስጨነቀን ነገር ነው፡፡ እናም ዛሬ . . ."
ቹቹ ስትናገር እኔ ይበልጥ ጉጉቴ ጨመረ፡፡ ምንድነው ያዘጋጀችልኝ? ጭንቀቴን ሚቀርፈው ነገር ምንድነው? የተጋረደው አይኔን ለመፍታት ከጫፍ ደረስኩ፡፡ 'አረ ማብራሪያው ቡሀላ ይደርሳል!' ብዬ ልጮህ ምንም አልቀረኝም፡፡ በመሀል ዝምታ ሰፈነ፡፡ ጨነቀኝ እየተጫወቱብኝ መሰለኝ፡፡በመቀጠል ቹቹ ከሁዋላዬ ቆማ ጨርቁን ከአይኔ ላይ ልታነሳልኝ ስትሞክር በጣም በመቸኮሌ እኔም አገዝኳት፡፡ በሁለት እጄ አይኔላይ የተሸፈነውን ጨርቅ ገለጥኩት፡፡ ደነገጥኩ! የሆነ ነገር ሰውነቴን ውርር አደረገኝ!
ፍሬ ነው፡፡ አዎ አጠገቤ የቆመው ፍሬ ነው፡፡' አ . . .እ . . . 'ተንተባተብኩ ፡፡ማውራትም አልቻልኩም፡፡ 'ፍ . . . ፍ . . . ፍሬ . . .አን . . ተ' ተንቀጠቀጥኩ ፡፡ምን እንደተሰማኝ እንኳ በቅጡ አላውቀዉም፡፡ ፍሬ ወደኔ ተጠጋ . . . አይኖቼ እንባ አቀረሩ፡፡ እቅፍ አደረገኝእኔም እቅፍ አደረኩት፡፡ ጭምቅ . . .አድርጌ አቀፎኩት፡፡ እንባዬ መውረድ ጀመረ፡፡ አላመንኩም ፍሬን ነው ያቀፍኩት? ቀና ብዬ አይኑን አየውት መልሼ አቀፍኩት፡፡ "እንዴት ግን ይሄንን ሁሉ ቀን ?" አላስጨረሰኝም አንድ ጣቱን ከንፈሬ ላይ አድርጎ "ሁሉንም እርሺው በቃ"አለኝ፡፡ 'እሺ 'አልኩት መልሼ እያቀፍኩት አንገቱ ስር ሽጉጥ ብዬ፡፡ እንባዬ በጉንጬ ላይ ይወርዳል፡፡ "አታልቅሺያ አሁን እኮ አለሁ" አለኝ ፍሬ ጉንጬን በሁለት እጆቹ እየጠረገ፡፡
እኔ የተሰማኝን ደስታ መግለፅ እንኳ አልቻልኩም፡፡ ውስጤ ሰላም አገኘ ፡፡ትልቅ መረጋጋት ነው የተሰማኝ፡፡ ሁሉም ቆመው በደስታ እየተመለከቱን ነበር፡፡ ፍሬ ጉንጬን ከጠረገ ቡሀላ እጄን ይዞኝ ከአንደኛው መቀመጫላይ አብረን ቁጭ አልን፡፡ ሁሉም ተቀመጡ፡፡ የሁሉም ፊት ላይ ደስታ ይነበባል፡፡ እኔም በጣም ነው ደስ ያለኝ፡፡ ያ' ሁሉ ጭንቀቴ ወዴት እንደገባ፡፡ ቅልል ነው ያለኝ፡፡ በተቀመጥንበት መቀመጫ ላይ የፍሬን ትከሻ ድግፍ ብዬ በእጆቼ ወገቡን እና ሆዱን እቅፍ እንዳደረኩ እሱም አንገቴን አቅፎኝ እስሩ ሹግጥ ብዬ ሁሉንም ተራ በተራ እመለከታቸው ጀመር፡፡ የሁሉም ፊት ላይ ደስታ ይነበባል፡፡
ይህ ሁሉ ሲሆን ቆማ ትመለከት የነበረችው ቹቹ አሁንም እንደቆመች ናት፡፡ ሁላችንም ቦታ ቦታ ይዘን ክብ ሰርተን ከተቀመጥን ቡሀላ ንግግሩዋን ቀጠለች፡፡"ያው እንግዲ እህታችን ሴና ሰሞኑን ይረብሻት እና ሰላም ይነሳት የነበረው ነገር አሁን ላይ የተፈታ ይመስለኛል፡፡ ይሄንን ደሞ እንድናደርግ ሀሳብ ያመጣችው ሚጣ ስትሆን ሁላችንም በመተባበር አንድ ነገር እናድርግ ባልነው መሰረት ይኸው እንዲህ ሆነ፡፡ ሁላቹም ፈጣሪ ያክብራቹ፡፡ በጣም ደስ ሚል ምሽት ነበር፡፡ እና በቃ አሁን መሽቶአል ወደ ዶርም" አለች ፡፡ በንግግሩዋ መጨረሻ ላይ ሁሉም አጨበጨቡ፡፡ እየተሳሳቅን እና እየተጨዋወትን ትንሽ ከቆየን ቡሀላ ወደ ዶርም መሄድ ጀመርን፡፡
ወደ ዶርም መግቢያ ስንደርስ ፍሬ ሁሉንም ከተሰናበተ ቡሀላ በመጨረሻ ሁለታችን ቀረን፡፡ እንደከዚ ቀደሙ 'ደና ደር ፣ደና ደሪ' ብቻ ተባብለን መለያየት አልቻልንም፡፡ ሊሄድ ሲል ጠራዋለው ፣ልሄድ ስል ይጠራኛል፡፡ በመጨረሻም "በቃ ግቢ በስልክ እናወራለን ብዙ ካመሸው ዶርም ይቅጡኛል" ካለኝ ቡሀላ አቅፎኝ ተሰናብቶኝ ሄደ፡፡ መንገድ እንደሚሄድ ሰው ትንሽ ቆሜ አየሁት፡፡
ዶርም ስገባ በ ላፕቶፕ ዘፈን ከፍተው እየጨፈሩ ዶርሙን አድምቀውታል፡፡ እንኳን ደስ አለሽ እያሉ ሁሉም በተራ አቀፉኝ፡፡ የዶርማችን ፍቅር እውነት ደስ አለኝ፡፡ "ግን እንዴት እንደዚ ልታደርጉ ቻላቹ?"አልኩኝ ከወደበሩ ከሚገኘው አልጋ ላይ እየተቀመጥኩ፡፡ ጭፈራቸውን አቁመው ዘፈኑን ከዘጉ ቡሀላ ሁሉም ቦታ ቦታ ይዘው መቀመጥ ጀመሩ፡፡ ጥያቄዬን ደገምኩት "ግን እንዴት መጣላቹ ይሄ ሀሳብ?" አልኩኝ በፈገግታ የተሞላ ፊታቸውን መልሼ በፈገግታ እየተመለከትኩ፡፡ "የውልሽ ሴና" አለች ሚጣ ተመቻችታ እየተቀመጠች፡፡ "የውልሽ ሴና . . . ."
ይ ቀ ጥ ላ ል . . .
@Mamusha23
@Mamusha23
@Mamusha23
💞 #ሴና #ክፍል_ሀያሶስት 💞
. . . ራስ ምታቴ ጨመረ በጣም ጭንቅንቅ ሚያደርግ ስሜት ይሰማኛል፡፡እንደምንም ራሴን ለማረጋጋት እየሞከርኩ ነው፡፡ሚጣ በተደጋጋሚ ብትጠይቀኝም ምክንያቴን እኔ ራሱ እንደማላውቀው ነገርኳት፡፡
ቀናት ተቆጠሩ የሆዴን በሆዴ ይዤ ቀጠልኩ፡፡ቅዳሜና እሁድ ቤት ስሄድ ከበፊቱ ይበልጥ ይጨንቀኝ ጀመር፡፡ ትምህርቱም እየቀጠለ ፣እኔም ተማሪዎችን እየተግባባው ግቢውንም በደንብ እየለመድኩት ፣ዶርም ውስጥም ሁላችንም እየተግባባን መጣን፡፡ የኛ ዶርም ውስጥ የተመደብነው 8ብንሆንም አንደኛዋ ግን መጥታም አታውቅም የቀረነው ግን ከቀን ወደቀን የዶርም አንድነታችን እየጠነከረ መጣ፡፡ እነ ቹቹ ሚያመሹ ቀን እንጠብቃቸው ጀመርን፡፡ ዶርማችንን እየወደድኩት መጣው፡፡ወር አለፈ ቀናት ተቆጠሩ፡፡ይሄንን ሁሉ ግዜ ግን በውስጤ ያለውን ነገር ለማንም አልተናገርኩም፡፡ ዛሬም ድረስ ስልኬ ላይ የፍሬን መልእክቶች አነባቸዋለው፡፡ እነዛ ወክ ያደረግንባቸው ምሽቶች የመጀመሪያዎቼም ስለሆኑ መሰለኝ ዛሬም ድረስ ውስጤ አሉ፡፡
በዚህ ሁሉ ግዜ ፍሬን በአካል አግኝቼው አላውቅም፡፡ አንድ ግቢውስጥ ሁነን አለመገናኘታችን አስገርሞኛል፡፡እኔ ከነሚጣጋር ስሆን ፍሬ አይመጣም፤እንዳጋጣሚ እኔ የሌለው ቀን ፍሬ እንደመጣ ይነግሩኛል፡፡አለመገጣጠም ይሁን ፍሬ ከኔ እየራቀ አልገባኝም፡፡ስለሱ ወሬ ሲነሳ ደስ ይለኛል ፣ናፍቀዋለው ለሱ የሆነ ስሜት ይሰማኛል፡፡"ምን እየሆንኩ ነው ግን?"ስል ራሴን ጠይቃለው፡፡ ዴቭን ሳገኘው ስለፍሬ ልጠይቅ እያልኩ ተወዋለው፡፡ ሽንፈት መስሎ ይታየኛል፡፡ "ግን ምኑን ነው ምሸነፈው?" የተደበላለቀ ነገር ውስጥ ነኝ፡፡ አሁንም ድረስ ውስጤ አልተረጋጋም ፣የሆነ ነገር የጎደለ ያህል ቅር ቅር ይለኛል፡፡
ዛሬ የዶርም ልጆች ተሰብስበን እራት አንድ ላይ ልንበላ ተቀጣጥረናል፡፡ ሀሳቡን ያመጣችው ቹቹ ነች፡፡ ሁላችንም ምሽት ላይ ግቢውስጥ በአንዱ ካፌ ተሰብስበን እራት ከበላን ብሀላ ቹቹ አንድ ልታሳየን ምትፈልገው ነገር እንዳለ ነግራን ሁላችንም ተያይዘን ወደ ምትወስደን ቦታ እንከተላት ጀመር፡፡
ከአንድ ተማሪዎች ከማይበዙበት ቦታ እንደደረስን እዚ እንድንቀመጥ ነገረችን፡፡ እኔ ውስጤ ተጨነቀ፡፡ ይሄ ቦታ ከፍሬጋር ማታ መታ እንቀመጥበት ነበር፡፡ ሁላችንም ቦታ ቦታ ይዘን ተቀመጥን፡፡ ቹቹ ከመሀከላችን ቆማ ንግግር ታደርግ ጀመር "እህቶቼ እንደምን አመሻቹ፡፡ ያው እንግዲ ዛሬ እንዲ እንድንሰባሰብ ያደረኩዋቹ እኛ አንድ ክፍል ውስጥ ምንኖር ልጆች ነን፡፡ ያ' ማለት ደሞ ልክ እንደ አንድ ወላጅ ልጆች ነን ማለት ነው፡፡ እዚ ሆነን የሆነ ነገር ቢደርስብን ከወላጆቻችንም ሆነ ከማንም ቀድመን አንዳኝን ነን ለአንዳችን ምንደርሰው፡፡ በዶርም ውስጥ ስንኖኖር አንዳች የሌላውን ደስታም ሆነ ሀዘን እንጋራለን፡፡ አብረን ስንሆን በጋራ ምናሳልፋቸው ነገሮች ደሞ ብዙ ናቸው፡፡ዛሬ እንደመጀመሪያ በዶርማችን የተፈጠረ አንድ ነገር አለ እሱን እናስተካክላለን፡፡እና ብዙ እንዳለፈልፍባቹ ሴና ተነሺ "አለች፡፡
እኔን እንድነሳ ካደረገችን ቡሀላ በአንድ ጨርቅ አይኔን ልታስረኝ እንደሆነ ነገረችኝ፡፡ፈራው ምን ሊፈጠር እንደሚችል ልገምትም አልቻልኩም፡፡"እንግዲ ሴና ዛሬ ላንቺ አንድ ደስ ሚል ነገር አለ" አለች ቹቹ አይኔን አስራ ስታበቃ፡፡'ምን ይሆን?' አልኩኝ ፤አይኔ እስኪፈታ ቸኮልኩ ፤የተዘጋጀልኝ ነገር ምን እንደሆነ ለማየት በጣም ጓጓው . . .
ይ ቀ ጥ ላ ል . . .
እስቲ ልጠይቅሽ
💔💔💔💔
አስቲ ልጠይቅሽ እውነቱን ንገሪኝ
ልብሽን ጠይቄው ሀሳብሽ አይጣለኝ
እውነት ከወደድሽኝ አውነት ካፈቀርሺኝ
ያኔ በክፉ ጊዚዬ ለምን ሄድሽ ጥለሽኝ?
ልቤን ለምን ፋቅሽው ፤ ፍቅሬን ለምን ናቅሽው?
ውዴ ምን ባረግ ነው አይኔን ያስነባሽው?
ቃል ካንደበቴ ርቆ እስኪጠፋኝ ምለው
ውዴ ለምን ነበር ቃላቴን ያሰርሽው?
አስቲ ልጠይቅሽ ቃል ካለሽ መልሽው
💔💔💔
ቻናላችንን ይቀላቀሉ
◦◦✧join 👇👇👇👇👇
@Mamusha23
@Mamusha23
@Mamusha23 🟢🟡🔴🟢🟡🔴🟢🟡🔴🟢🟡🔴🟢🟡🔴🟢🟡🔴
💞 #ሴና #ክፍል_ሀያአንድ 💞
. . . ከቀጠሮዬ ቦታ ደስደርስ ስልክ ደውዬ ተገናኘን፡፡ እንደጠበኳት ግን አይደለችም፡፡ዝንጥ ያለች ቆንጅዬ ልጅ ነች፡፡ ሰላምታ ከተለዋወጥን ቡሀላ ተዋውቀን ተቀመጥኩ፡፡ ፌቨን ነው ስሟ፡፡ ትንሽ እንዳወራን ተግባባን ፡፡ ፌቨን ቀለል ያለች ተጫዋች ልጅ ነች፡፡ ቡዙ ተጨዋወትን በዚህ መሀል ስልኬ ሶስት ግዜ ተደውሎአል፡፡ ፍሬ ነው አላነሳውትም፡፡ ቀኔን ከፌቨን ጋር አሳለፍኩ፡፡
ወደ አመሻሽ ላይ እና ሚጣ ደውለው እራት አብሬያቸው እንድበላ ጠየቁኝ፡፡ አብሬያቸው መሆንን ፈልጌያለው፡፡ ግን ፍሬ ሊኖር ይችላል ብዬ ስላሰብኩ ሰበብ ፈጥሬ መቅረትን መረጥኩ፡፡"ትንሽ አመም አድርጎኝ ወደ ዶርም እየሄድኩ ነው፡፡ ባይሆን ስትመጡ እራት ይዛቹልኝ ኑ" ብያቸው ወደ ዶርሜ አቀናው፡፡
ዶርሜ ስገባ ያቺን ባለ መነፅር አልጋዋላይ ተኝታ ኮምፒውተሯን እየጎረጎረች አገኘዋት፡፡ ሰላም ተባብለን ለምን ብቻዬን እንደመጣው ስትጠይቀኝ ትንሽ ራሴን አመም አድርጎኝ እንደሆነ ነግሬያት ልብሴን ቀይሬ ተጣጥቤ አልጋዬላይ ወጥቼ ተኛው፡፡ ከእንቅልፌ የባነንኩት በሚጣ ጥሪ ነው፡፡ "ምን ሆነሽ ነው? በጣም አመመሽ እንዴ?" አለችኝ ግንባሬን በእጇ እየዳበሰች፡፡ "የት ውለሽ ነው? ምን ሆነሽ ነው? የጥያቄ መአት እያከታተሉ ይጠይቁኝ ጀመር፡፡ ብዙም አላወራውም ያመጡልኝን እራት ከበላሁ ቡሀላ ተመልሼ አልጋዬላይ ወጣሁ፡፡ ስለውሎዋቸው ያጫውቱኝ ጀመር፡፡ እያወራን ስልኬ መልእክት ገባ ፡፡ ፍሬ ነው አነብቤው ተውኩት፡፡ ጨዋታችን ቀጠለ፡፡
እንዲ እንዲያ እያልኩ ቀናት ተቆጠሩ ፣ሳምንቱም አለቀ ፣ቤት ደርሼ ተመለስኩ፡፡ ለቹቹ ቃል እንደገባውላት ፍሬን አንድ ሳምንት ሳላገኘው፡፡ በቀጠሮዋችን ቀን ከቹቹ ጋር የተለመደው ቦታ ተቀምጠን ስላለፈው ነገር ማውራት ጀመርን፡፡ "ይኸው ፍቅር እንዳልያዘኝ እወቂ፡፡ አንድ ሳምንት አላገኘውትም ግን ምንም አልተሰማኝም ፣ምንም አልሆንኩም" አልኳት ግዳጁን እንደተወጣ መልእክተኛ ፡፡ "ስለዚህ በዚሁ ትቀጥያለሽ ማለት ነው" አለችኝ ቹቹ፡፡ አልገባኝም ፤ደነገጥኩ "ማለት ከዚህ ቡሀላ ፍሬን ላላገኘው?" አልኳት፡፡ "እንደዛ ማለቴ አይደለም ከዚህ ቡሀላም ስለፍሬ አታስቢም ፣ብዙ ግዜሽን ከፍሬ ጋር አታሳልፊም፡፡ በቃ እንደማንኛውም ተራ ጉዋደኛ ብቻ ይሆናል ምትቀራረቢው" አለችኝ፡፡
" 'ለምንድነው?' ብለሽ እንደምታስቢ አውቃለው፡፡ አንቺ በዚህ ግዜ ስለ ፍቅር ምንም ማሰብም ፣ፍቅረኛ እንዲኖርሽ አትፈልጊም፡፡ ፍሬ ደሞ በአጭር ቀን ውስጥ በጣም የቀረብሽው ወንድ ነው፡፡ በዚህ ከቀጠልሽ ደሞ ወደ ፍቅር ማይቀየርበት ምክንያት አይኖርም፡፡ስለዚህ ግንኙነታቹን ትቀንሻለሽ፡፡ ይሄንን ደሞ ምመክርሽ ላንቺው ብዬ ነው፡፡" አለችኝ ቹቹ፡፡ ዝም ብዬ ማሰብ ጀመርኩ፡፡ ምንም ሳልናገር ከ አስር ደቂቃ በላይ አሳለፍኩ፡፡ ብዙ አወጣው አወረድኩ፡፡ "እውነቷን ነው? አይ ምንም ችግር የለውም . . . "ቹቹም ዝም ብላ ታየኝ ጀመር፡፡ እንደመጀመሪያው ቀን ዛሬ ወዲያው ልስማማ አልቻልኩም፡፡ "እሺ" የማለት ድፍረት አጣው፡፡ "ይሄንን ግዜ ወስደሽ በደንብ አስቢበት፡፡ የምርጫ ጉዳይ አይደለም፡፡ እሺ ወይ እንቢ እንድትይኝ አይደለም፡፡ ራስሽ እንድታስቢው ፤ራስሽን በራስሽ እንድትመረምሪበት ነው የነገርኩሽ" አለችኝ ቹቹ አይኔን እያየች፡፡ እንማስብበት ነግሬያት በተለመደው ሰአት ተለያየን፡፡
ወደሚጣ ስልክ ስደውል ፍሬ አነሳው፡፡ "ሴና ግን ምን አድርጌሽ ነው? እንደዚ ሚያስከፋ ነገር አደረኩሽ ግን? . . ."ገና እያወራኝ ስልኩን ዘጋውት፡፡ ደነገጥኩኝ፡፡ 'እውነት ምን አድርጎኝ ነው ግን?' ብዬ አሰብኩ፡፡ 'እንዴት ግን የሚጣን ስልክ አነሳው?ምናልባት አብረው ሆነው ይሆናል፡፡' እነሚጣ የት እንዳሉ ለማወቅ ነበር የደወልኩት፡፡
ትንሽ ቆይቶ ፍሬ በራሱ ስልክ መልእክት ላከልኝ፡፡ በቆምኩበት ከፍቼ ማንበብ ጀመርኩ፡፡ እያነበብኩ ወደመሀል ስደርስ ሳላስበው እንባዬ መጣ፡፡ ማንበቤን ቀጠልኩ፡፡ እንባዬ አይኔን ሸፎኖኝ ስልኬላይ መንጠባጠብ ጀመረ፡፡ የላከልኝ መልእክት እንዲህ የሚል ነው . . .
ይ ቀ ጥ ላ ል . .
አ.........ለ..........
እንቅልፍ ጨከነ ህልም ሆነ ቀረ
አይን ተጎልጉሎ አፍጦ አደረ
ቀናት ለሳምንታት ሳምንታት ለወራት
እየተዋዋሱ ወገባችን ድካም እየቀጨቀጫት
ማን ማንን አምኖ በሰላም ይተኛል
እምነት እንደሁ በጉም ደምቀቱን ተነፍጓል
እንቅልፍም እንቢ አለ
ሰላምን እንቢ አለ
እየሞተ እያየ ሞትን እየረሳ
ኧረ መቼ ይሆን ሰው መሆን ሚወሳ ?
ማወቅ በጄ ነበር አቧራን ማራገፍ
ፈሩን ለቀቅንና እያየነው እልፍ
ለካ እናቴ ትሙት አትበል ተው ብሎ
የመከረኝ ለታ አፌን ተቀብሎ
ሊገልብኝ ኑሯል ቢላውን አስሎ
የልቡን ሊሰራ እያዘነ መስሎ
አንድነት ውበት ነው ብሎ ሲያሳምነኝ
አንድ ላይ ሊገለን እኔ መቼ መስሎኝ
አትገረምም ወይ በአንተ አምሮ እሱ እያሰበ
ሀሳብህን ሰርቆ ወደፈለገበት ሽምጥ ጋለበ
ዘመናዊነት ነው የዘመኑ ብሎ
ሳትወለድ ቀብሮህ በቃላት ሸንግሎ
እናማ ሞተናል ከአንዴም ሁለቴ
ከሁለቴ ሶስቴ ከሶስቴም አራቴ
ሁሌ እንሞታለን በቶሎ ካልባነን
መጠቀም አለብን አዕምሯችንን
መለየት አለብን ማሰብ እና ስሜት
ከዛማ መቃብር ፈንቅሎ መነሳት
💞 #ሴና #ክፍል_ሠላሳ_ሰባት 💞
. . . አይኔን ስገልጥ ነጭ ኮርኒስ ነው የታየኝ፡፡ አልጋ ላይ እንደተኛው ይሰማኛል፡፡ አንገቴን ወደ ጎን ዞር ሳደርግ አጠገቤ አንድ ነጭ ጋወን የለበሰ ሰው ቆሞ የአይዞሽ አሁን ደና ነሽ" አለኝ ግንባሬን በመዳፉ እየዳበሰ፡፡ የተኛውት የሀኪም ቤት ክፍል ውስጥ እንደሆነ ገባኝ፡፡ ወዲያው የክፍሉ በር ተከፍቶ እነ ሚጣ ተከታትለው ገቡ፡፡ "አሁን እንዴት ነሽ?" እያሉ ጥያቄ ያከታትሉብኝ ጀመር፡፡ "አሁን ደና ስለሆነች ይዛቹሀት መሄድ ትችላላቹ ፡፡ትንሽ ድንጋጤው እንጂ ሌላ ምንም ችግር የለባትም" አለ ባለ ነጭ ጋወኑ ሀኪም፡፡ እነ ሚጣ ደግፈው ከአልጋ ካወረዱኝ ብሀላ ጫማዬን አድርገውልኝ ከተኛውበት ክፍል ይዘውኝ ወጡ፡፡
ከክፍሉ ስወጣ ከግቢ ውጪ ያለ ሀኪም ቤት እንደነበርኩ ገባኝ፡፡ አይኔ ያነባል፡፡ እነ ሚጣ አይዞሽ ይሉኛል ፣ ጥያቄ ይጠይቁኛል ፣ማብራሪያ ይሰጡኛል ፣ሊያረጋጉኝ ይሞክራሉ፡፡ እኔ ግን ማልቀሴን አላቆምኩም፡፡ ከሀኪም ቤቱ በር ላይ ስደርስ ያየውት ግራ ገባኝ ፡፡ የወንድሜ መኪና ቆሞአል፡፡ እንዴት እንደሰማ ግራ ገባኝ፡፡ "ቆይ ውስጥ ነው ይመጣል"አለችኝ ሚጣ በቀኝ በኩል ደግፋኝ እንደቆመች፡፡ እንዴት መጣ? ማን ነገረው? ቆይ እኔ እንዴት እዚ መጣው?' ጠየኳት ሚጣን እንባዬ አሁንም እንደወረደ ነው፡፡ ድምፄ ጉንፋን እንደያዘው ሰው ተዘግቶአል፡፡ "ቆይ ሁሉንም እናውራለን፡፡ አሁን ተረጋጊ"አለችኝ ሚጣ ጉንጬ ላይ የወረደውን እንባዬን በሹራቧ ጫፍ እየጠረገች፡፡ በዚ መሀል ወንድሜ መጣ "አይዞሽ ምንም አልሆንሽም"ብሎ አቀፈኝ፡፡ ጥያቄ ሆነብኝ፡፡ ወዲያው የመኪናውን ሁዋላ በር ከከፈተልኝ ብሀላ ወደ ውስጥ ገባው፡፡ ሚጣ ተከትላኝ ገባች፡፡ ሌሎቹ ከተሰናበቱኝ ቡሀላ ሄዱ፡፡
ወንድሜ ወኪናውን አስነስቶ መሄድ ሲጀምር 'ቆይ ምንድነው ነገሩ ግራ አጋባቹኝ እኮ 'አልኩኝ በደከመ ድምፅ፡፡ ማንም መልስ አልሰጠኝም፡፡ ወንድሜ መኪናውን እየነዳ ከከተማ ወጣ ወዳለ ቦታ ከወሰደን ብሀላ መኪናውን ከአንድ ሜዳማ ስፍራ አቁሞ ሞተሩን ካጠፋ ብሀላ ከመኪናው ወረደ፡፡ሚጣም ተከትላው ወረደች፡፡ ግራ ገባኝ እኔም ተከትያቸው ወረድኩኝ፡፡ ወንድሜ መኪናውን ተደግፎ ቆመ፡፡ ገና ከመኪና ከመውረዴ ሚጣ ማውራትጀመረች፡፡ "የውልሽ ሴና ያኔ ለ እረፍት ወደ ቤት የሄድን ሰአት ነበር ፍሬ በድንገተኛ አደጋ ያረፈው፡፡ እና የዛን እለት ላንቺ ይሄንን ልነግርሽ አስቤ ነገር ግን እንደዚ አይነት ነገር በስልክ ብነግርሽ ያለሽበት ሁኔታ ደሞ ጥሩ ባይሆን ይሄንን ስትሰሚ የሆነ ነገር ቢፈጠር ወይም የሆነ ነገር በራስሽ ላይ ብታደርሺ ብዬ ስለፈራው ለወንድምሽ ደወልኩለት፡፡ የሱን ስልክ ከየት አገኘሽው ካልሽኝ እኛ ግቢ ምትማረው የባልደረባችን ልጅ ያልሽኝ ከሷ ነው የተቀበልኩት፡፡ የሷን ስልክ ደሞ ያገኘውት እነሱ ዶርም የምትኖር ልጅ ጉዋደኛ እሱን ጠይቄ በሱ በኩል አድርጌ አፈላልጌ ነው፡፡ ያ አማራጭ ባይኖረኝ የዛኔ ቀጥታ አዲስ አበባ ቤታቹ መጣ ነበር፡፡ ይሄንን አድርጌ ለወንድምሽ ደውዬ ሁሉንም ነገር ነገርኩት፡፡ የዛን እለት ወንድምሽ ሰበብ ፈልጎ ስልክሽን ተቀበለሽ፡፡ ያንን ያደረግነው ደሞ ከሌላ ሰው እንዳትገናኚ እና ከሌላ ሰው እንዳትሰሚው አስበን ነው፡፡"
ሚጣ ይሄንን ስትነግረኝ ወንድሜን እየተመለከትኩት ማንባቴን ቀጠልኩ፡፡ ሚጣ ቀጠለች፡፡ " . . .ለ ዴቭ ስትደውይለት አጠገቤ ነበር፡፡ ፍሬን እንዳላየው እና አዲስ አበባ እንሆነ እንዲነግርሽ የነገርኩት እኔ ነበርኩኝ፡፡ ሰኞ ለምዝገባ መጥተሽ ምዝገባ አርብ ነው ሀሙስ እንመጣለን ያልኩሽ ግዜ እኔ ግቢ ነበርኩኝ፡፡ ሌሎቹም የዶርም ልጆች መጥተው ከተመዘገብን ብሀላ ወንድምሽ ንቺን ግቢ እንዳደረሰሽ በሌላ በር ገብቶ አንቺ መምጣት እንደማትችይ ነግሮ ግቢ ውስጥ በሚያውቀው ሰው አማካይነት እንድትመዘገቢ አደረግን፡፡ ከዛ እኔና የዶርም ልጆች እናንተ ቤት ነበርን፡፡ ምክንያቱም ሀሙስ ነው ምንመጣው ያልንሽ ብቻሽን እንድትሆኚ ነበር፡፡ ብቻሽን እንድትሆኚ ካደረግን ብሀላ ወንድምሽ ኪሩቤልን ላከው፡፡ ኪሩቤል በአጋጣሚ ካፌ ውስጥ የተዋወቅሽው ተማሪ ሳይሆን የስነልቦና ባለሙያ የሆነ የወንድምሽ ጉዋደኛ ነው፡፡ የፍሬ ስልክ ሲሙ የወጣው በዴቭ ስም ነው፡፡ስለዚ ፍሬ ሲያርፍ ዴቭ ሲሙን አውጥቶ ስለነበር በዛ ስልክ ሚደወሉ ጥሪዎችን በሙሉ ለፍሬ የተደወሉ ይሆናሉ ስለሚል አያነሳውም፡፡
እኔና ወንድምሽ ይሄንን ስናደርግ ሀሳቡ የኪሩቤል ነበር፡፡ እኛ ያሰብነው ፍሬን ቀስ በቀስ እንድትረሺው ነበር፡፡ ለዛ ነው ኪሩቤል ቢዚ ያደረገሽ፡፡ ያው ባልጠበቅነው መንገድ እውነቱን አወቅሽ እነጂ" ፡፡ ሚጣ ይሄንን ሁሉ ስታወራ እኔ እያነባው በግርምት አዳምጣት ነበር፡፡ ወንድሜ መኪናውን እንደተደገፈ ቆሞ ያዳምጣት ነበር፡፡ ወደወንድሜ እየተመለከትኩ ላወራ ስል "ሴና ከህፃንነችሽ ጀምሮ ሳደርግ የነበረው ነገር አንቺ እህቴን በጣም ሰለምወድሽ ነበር፡፡ ታላቅ እንደመሆኔ ደሞ አንቺን ከብዙ ነገር ጠብቄ ትልቅ ሰው ማድረግ ነበር እቅዴ ፡፡ እኔ ይህን ሳደርግ ደሙ ሙሉ ቤተሰባችን ስለሚቀበለኝ አንቺ ይሄንን ከጥላቻ ትቆጥሪያለሽ፡፡ በርግጥ እኔም አበዛውት ግን ላንቺው አስቤ የማደርገው ነገር ስለ. . . " አላስጨረስኩትም ወንድሜ ላይ ጥምጥም አልኩበት፡፡ ይሄንን ሁሉ ነገር ያደርግ የነበረው ለኔው ሲል መሆኑን ሳስብ ስቅስቅ ብዬ አለቀስኩ፡፡ ወንድሜን ለቅቄ ሚጣን አቀፍኳት፡፡ ተቃቅፈን አለቀስን፡፡
ወደ ከተማ እየተመለስን በጭንቅላቴ ብዙ ሀሳቦች ተመላለሱ፡፡ ዠእውነት ለካ ቤተሰቦቼ ለኔ ፍቅር አላቸው፡፡ የተከተሉት መንገድ የጎዳኝ ቢመስለኝም ሁሉን ሚያደርጉት ለኔ ብለው ነው፡፡ የዶርሜ ልጆች እውነትም ለካ ከልባቸው ነው ጉዋደኝነታቸው፡፡ ለኔ ሰሜት ምን ያህል እንደሚጨነቁ አሰብኩኝ፡፡ እውነት እኛ ሰዎች ባሰቡልን ልክ እያሰብናቸው ነው?' ብዬ ራሴን ጠየኩት፡፡ ዶርም ስገባ ስለሁሉም ነገር ጉዋደኞቼን አመሰገንኳቸው፡፡ ከኪሩቤል ጋርም ጉወደኝነታችን ቀጠለ፡፡ ወንድሜና ጉዋደኞቼ ባደረጉት ነገር በጣም ብዙ ተማርኩኝ፡፡ ጉዋደኝነት ፣ቤተሰብ እውነተኛ ፍቅርን ከነሱ አገኘው፡፡ የፍሬ ህልፈት እጅጉን የከፋ ሀዘን ቢያደርስብኝም ቤተሰቦቼ እና ጉዋደኞቼ ከጎኔ በመሆናቸው ብርታት ሰጡኝ፡፡
ይሄ ታሪክ ከተፈጠረ አመት አለፈው፡፡ አሁን እኔ የሁለተኛ አመት ተማሪ ሆኛለው፡፡ ዶርም ስሄድ ቤቴ ቤት ስሄድ ዶርሜ ይናፍቀኝ ጀመር፡፡ በትምህርቴ ውጤታማ እየሆንኩኝ ነው፡፡እስካሁን የፍቀር ጉዋደኛ አልያዝኩም፡፡ ፍሬ ዛሬም በልቤ አለ፡፡ ነገር ግን ቤተሰቦቼና ጉዋደኞቼ አብረውኝ ስላሉ ደስተኛ ነኝ፡፡ ለሁሉም ነገር ደሞ ፈጣሪን አመሰግናለው፡፡ አምላክ የፍቅርን ጉልበት በቤተሰቦቼና በጉዋደኞቼ በኩል አስተምሮኛል፡፡
ይህንን ታሪክ ያነበባቹ በሙሉ ከዚህ እንደምትማሩ ተስፋ አደርጋለው፡፡
. . . ህይወት ይቀጥላል . . .
ተፈፀመ
ቻናላችንን ይቀላቀሉ
◦◦✧join 👇👇👇👇👇
@Mamusha23
@Mamusha23
@Mamusha23
💞 #ሴና #ክፍል_ሠላሳ_ስድስት 💞
. . . ዛሬ በጥዋቱ ነው የተነሳውት፡፡ ኪሩቤል ልክ በሰአቱ ሲደውል እኔ ቀድሜው መነሳቴን ነግሬው ጉዋደኞቼን ጨምሮ አብረን ቁርስ በላን፡፡ ዛሬ ምንመዘገብበት ቀን ነው፡፡ ኪሩቤል ሲቀር ሁላችንም ተያይዘን ሄድን፡፡ምዝገባ ቦታ ስንደርስ ማንም ተማሪ የለም፡፡ "ተማሪው ምን ነካው ? ቀኑ አልፍ ነው ወይስ እኛ ቀድመን ነው?" ስንባባል ሚጣ "መታወቂያ ነው አስቀምጠው ሚሄዱት መታወቂያቹን አምጡ እና እዚ ጠብቁኝ "ብላ መታወቂያችንን ሰብስባ ወደውስጥ ገባች፡፡ ትንሽ ቆይታ "በቃ መታወቂያ ነገ ነው ምንቀበለው" ብላን ተያይዘን ቡዙ ግዜ ተሰብስበን ምኅቀመጥበት ቦታ ሄድን፡፡ እስከ ምሳ ሰአት ከዛ ቦታ አልተነሳንም፡፡ ያለፋት ሳምንታት ምን ይመስሉ እንደነበር ተራ በተራ መጨዋወት ጀመርን፡፡ የኔ ተራ ሲደርስ 'ብዙም ደስ አይልም ይልቅ ተነሱ ወደ ምሳ ርቦኛል 'አልኩዋቸው ተጨማሪ ጥያቄ እንዳይጠይቁኝ ስል ከተቀመጥኩበት እየተነሳው፡፡ ሁሉም ተከትለውኝ ተነሱ ፡፡ ማንም ምንም አልተናገረኝም፡፡ በፊትም ቤት ውስጥ ያለውን ነገር የተወሰነ ያህል ስለሚያውቁ ይረዱኛል፡፡
ምሳ ልንበላ ወደ ካፌ እየሄድን ኪሩቤል ደወለ "እስኪ አምስት ብር ሙይልኝ የምሳ " አለኝ በአሳዛኝ ድምፅ፡፡ በጣም ነው ያሳቀኝ፡፡ ከጉዋደኞቼ ጋር እየመጣው እንደሆነ እና እዛው ካፌ እንዲጠብቀኝ ነግሬው ስልኩን ዘጋውት፡፡ በስልክ ያለኝን ለጉዋደኞቼ ስነግራቸው ሁሉም ሳቁ፡፡ ኪሩቤል ከሁሉም ጋር ተግባብቶአል፡፡ ገና በመጀመሪያ ቀን እንደዛ ሲጫወት ሳየው ጉዋደኞቼን ከድሮ ጀምሮ ሚያውቃቸው ነው ሚመስለው፡፡ካፌ ስንደርስ ኪሩቤል ዝርዝር ብር ይዞ ካፌው በር ላይ ተቀምጦአል፡፡ ገና አንዳየነው ሁላችንም ሳቅን፡፡ ተሰብስበን ምሳ አብረን በላን፡፡
ከምሳ ብሀላ ሌሎቹ ጉዋደኞቼን ከ ኪሩቤል ጋር ትተን እኔ እና ሚጣ ወደ ዶርም እየሄድን ሳለ አንድ ልጅ መጥታ ሚጣን ተጠምጥማባት ካቀፈቻት ቡሀላ እኔን ጨበጠችኝ፡፡ ወዴት እየሄድን እንደሆነ ጠይቃን ሚጣን "እንዴት ነው በረታቹ ? እኔም እኮ ወደ ግቢ መጣው ተመልሼም ሳልጠይቃቹ፡፡ ወይዘሮ አዲስ እንዴት ናቸው? በረቱ ? " አለች፡፡ ሚጣ በጣም ደነገጠች ምትመልሰው መልስ አጣች፡፡ "ሴና እኔ መጣለው እየሄድሽ ጠብቂኝ" አለችኝ፡፡ ግራ ገባኝ የሆነ ነገር ውርር ሲያደርገኝ ይሰማኛል፡፡ እሺ ብዬ መንገዴን ቀጠልኩ፡፡ ትንሽ ከሄድኩኝ ብሀላ አንድ ጥግ ቆሜ ማጣን መጠበቅ ጀመርኩ፡፡ ሚጣና ልጅቱዋ ሚያወሩትን ባልሰማም ግን በደንብ ይታዩኛል፡፡ ሚጣ እያለቀሰች ነው፡፡ ከእጅ ቦርሳዋ ውስጥ ሶፍት አውጥታ እንባዋን ትጠራርጋለች፡፡ ቡዙ ቆመው ካወሩ ቡሀላ ሚጣ ወደኔ መጣች፡፡ በጣም ደንግጫለው ሚጣ አይኗ ቀልቶአል፡፡ ምን እንደሆነች ብጠይቃትም ምንም መልስ አትሰጠኝም አይኗን በሶፍት እየጠረገች ዶርም ደረስን፡፡
ምን ተፈጥሮ እንደሆነ ስጠይቃት "ጎረቤት ለቅሶ ነበር አብሮ አደጋችን አርፎ ለቅሶ ላይ ነበር የቆየውት ስለሱ ነው ያነሳችብኝ፡፡ "አለችኝ ሚጣ እንባዋን እያፈሰሰች፡፡ ደነገጥኩኝ! . . . እግሬ ተንቀጠቀጠ . . . ቅድም ልጅቷ "ወይዘሮ አዲስ በረቱ?" ያለችው ትዝ አለኝ፡፡ የሆነ ግዜ ፍሬ ስለቤተሰቦቹ ሲነግረኝ የእናቱ ስም አዲስ እንደሚባል ነግሮኝ ነበር፡፡ መናገር አቃተኝ የሙት የሙቴን "ፍሬስ?" አልኳት ሚጣን፡፡ "ፍሬ ምንም አልሆነም አለ" አለችኝ እያነባች፡፡ "ሚጣ አትዋሺኝ! ፍሬ የታለ? ስልኩን አያነሳ ! ግቢ አልመጣ ! ፍሬ ምን ሆኖ ነው! ሚጣ በፈጠረሽ አትዋሺኝ ፍሬ ምን ሆነ!?" የሚጣን ትከሻ ይዤ በጩኸት ጠየኩዋት፡፡" ፍሬ ምንም አልሆነም ተረጋጊ "አለችኝ ሚጣ ራሱዋን ለማረጋጋት እየሞከረች፡፡ "ሚጣ አትዋሺኝ የቅድሙዋን ልጅ ጠይቃታለው ፍሬ ምን ሆነ!? ሚጣ በምትወጂው ይሁንብሽ ! በፈጠረሽ ፍሬ ምን ሆኖአል?" እንባዬ መውረድ ጀመረ፡፡ መጠየቁ አልሆን ሲለኝ መለመን ጀመርኩ "ሚጣ ፍሬ የት ነው ያለው? ፍሬ ምን ሆኖ ነው የጠፋው?"
"ሴና ፍሬ አርፎአል" አለችኝ ሚጣ ስቅስቅ ብላ እያለቀሰች፡፡ አላመንኩም በሁለት አጄ ጭምድድ አድርጌ የያዝኩትን የሚጣን ትከሻ ለቀኩት፡፡ ከዚሁ ብሀላ ማስታውሰው የሆነ ነገር ኩሀላ ጭንቅላቴን ሲመታው ነው . . .
©
ይ ቀ ጥ ላ ል . . .
❣
ቻናላችንን ይቀላቀሉ
◦◦✧join 👇👇👇👇👇
@Mamusha23
@Mamusha23
@Mamusha23 🟢🟡🔴🟢🟡🔴🟢🟡🔴🟢🟡🔴🟢🟡🔴🟢🟡🔴
🇪🇹 #ኢትዮጵያ_ለዘለዓለም_ትኑር! 🇪🇹
❣ #ፍቅር_ያሸንፋል ❣
"ሲና" የተሰኝው ተወዳጅ እና ተናፍቂው ልቦለዳችን በብዙሃኑ ዘንድ መናፈቁን👩👩👧👧👩👩👧👧👩👩👧👧 እንደቀጠለ ነው እንሆ አጓጊነቱን እያስደመመን ይቀጥላል በሚለው ስሜት ውስጥ እንደከተተን አሁን ሊያልቅብን 🙆🙆🙆♂🙆♂የመጨረሻ ክፍሎች እየታዳረስነን ነው እርሶም የእንድማሩበት እንዲዝናኑ ለሚፈልጉ ለወዳጅ ለዘመዶቻቸው #ሽር_ማድረጓን👈 እንዳይረሱ ፨ ስለተከታተሉ እና ተመራጮች ስላደረጉን👏👏👏 ከልባችን እናመሰግናለን🙏🙏🙏 ኑ አብረውን ይስሩ ፨
ቻናላችንን ይቀላቀሉ
◦◦✧join 👇👇👇👇👇
@Mamusha23
@Mamusha23
@Mamusha23 🟢🟡🔴🟢🟡🔴🟢🟡🔴🟢🟡🔴🟢🟡🔴🟢🟡🔴
💞 #ሴና #ክፍል_ሠላሳ_ሶስት 💞
. . . እኔ ሳቅ በሳቅ ሆኛለው፡፡ ኪሩቤል በጣም ነው ያዝናናኝ፡፡ ብዙ ከሳኩኝ ብሀላ " አንዴ ላቁዋርጥሽ እና ምን እንዘዝ?" አለኝ ሳቄ አላልቅ ሲለው፡፡ እሱ የተመቸውን እንዲያዝ ከፈቀድኩለት ቡሀላ ምግብ ቀርቦ መመገብ ጀመርን፡፡ ምግቡን እስክንጨርስ እንኳ ሳቅ አልተለየኝም ነበር፡፡
ምሳችንን ከጨረስን ብሀላ አንድ ቦታ ላሳይሽ ብሎኝ ይዞኝ ከካፌው ወጣ፡፡ በመንገዳችን ላይ በሚያወራው ወሬ እና በሚያደርገው ድርጊት በጣም ነበር ሚያዝናናኝ፡፡ ብዙ ከሄድን ብሀላ የግቢው ዋና መውጫ በር ጋ ደረስን፡፡ "እንዴ ምታሳየኝ ቦታ የት ነው?" አልኩት ወደ መውጫ በር ጋ ቆሜ፡፡ "እዚሁ ቅርብ ነው በእግር የ3ደቂቃ መንገድ "አለኝ፡፡ ከግቢ ውጪ የትም እንደማልሄድ ከታላቅ ይቅርታ ጋር ገለፅኩለት፡፡ ትንሽ ቢወተውተኝም እሺ ልለው አልቻልኩም፡፡ "በቃ አንቺ ካልሄድሽ እኔ ደርሼ መጣለው እና ቡሀላ እራት ላይ ይመችሻል?" አለኝ፡፡ "እኔንጃ ከተመቸኝ ደውልልካለው"ብዬው ከተሰነባበትን ቡሀላ እሱ ከግቢው ወጥቶ ሄደ፡፡ እኔም ወደ ሁዋላ ተመልሼ ወደዶርም ማቅናት ጀመርኩ፡፡ ደስ ሚል ግዜ ነበር ያሳለፍኩት፡፡
ዶርም እንደገባው አልጋዬላይ በጀርባዬ ተጋድሜ ለፍሬ ስልክ መደወል ጀመርኩ ፡፡ ይጠራል ግን አያነሳም፡፡ ሁለት ግዜ ሞክሬ ተውኩ፡፡ ስልኬን አሰቀምጬ ጋደም ባልኩበት የኪሩቤልን ጨዋታና ቀልዶች እያስታወስኩ ደግሜ እንዳዲስ እስቅ ጀመር፡፡ ትንሽ እንደቆየ ጋደም ባልኩበት እንቅልፍ ወሰደኝ፡፡ ከእንቅልፌ ስነቃ አስራሁለት ሰአት አልፎአል፡፡ ከአልጋዬ ወርጄ በመስኮት ወደውጪ ሳይ እየጨለመ ነው፡፡ ወዲያው ስልኬን አንስቼ ለ ኪሩቤል ደወልኩለት፡፡ ገና ከመጥራቱ ኪሩቤል ስልኩን አንስቶ መጮህ ጀመረ" በፈጣሪ ስም ሀያ ደቂቃ ብታረፍጂ ኖሮ መቶ ብር አስበልተሽኝ ነበር፡፡ ለትንሽ አተረፍሽኝ፡፡ በቃ የእራት ብር ሸቅያለው በሱ እንበላለን መጣው "ብሎ ስልኩን ዘጋው፡፡ ለማለት የፈለገው አልገባኝም ግን ልብሴን እና ፀጉሬን አስተካክዬ ልወጣ ስል ለካ የት እንደምንገናኝ አልነገረኝም ፡፡ መልሼ ደወልኩ አሁንም እንደቅድሙ በፍጥነት አንስቶት "የት እንደምንገናኝ ነዋ ልትጠይቂኝ የፈለግሽው የቅድሙ ካፌ በር ላይ ነይ፡፡ መልሰሽ በመደወልሽ ቦነስ አግኝተናል በዚ ደሞ ሻይ እንጠጣለን" ብሎ ስልኩን መልሶ ዘጋው፡፡ በጣም ግራ አጋባኝ ምን እንዳገኘን ምን እንዳወራ ምንም አልገባኝም፡፡ ቢሆንም ተስተካክዬ ስጨርስ ከዶርም ወጥቼ ወደ ካፌው አቀናው፡፡
ከካፌው ስደርስ ኪሩቤል ቀድሞኝ ወደ በሩ ጋር ቆሞ እየጠበቀኝ ነበር፡፡ እንደተገናኘን ሰላምታ ከተለዋወጥን ብሀላ ምንም ሳያወራኝ ወደውስጥ ገባን፡፡ውስጥ ቦታ ይዘን ከተቀመጥን ብሀላ "ቆይ ቅድም ምንድነው በስልክ ያልከኝ? ምንድነው ማስበላክ? ምንድነው የሻይ ተጨመረልን ያልከኝ?" ስል ጥያቄ አከታተልኩበት፡፡ "ነግርሻለው ቆይ እራት አዝዤ ልምጣና የአሁኑ የኔ ግብዣ ስለሆነ አንቺ እንድትመርጪ አልፈቅድልሽም" ብሎ በተቀመጥኩበት ትቶኝ ሄደ፡፡ ትንሽ ቆይቶ እንደተመለሰ ስለሁኔታው ያስረዳኝ ጀመር፡፡" የውልሽ ቅድም እራት እንብላ ብለሽ እስከ 1 ሰአት እንደምትደውይ ከጉዋደኞቼ ጋር ተወራርጄ ነበር፡፡ ለአንድ ሀያ ጉዳይ በመደወልሽ ይኸው መቶ ብር ሸቀልን፡፡ እንደገና ደግሞ ወዲያው ስልኩን እንደዘጋውት የት እንደምንገናኝ ልትጠይቂኝ መልሰሽ እንደምትደውይ ወዲያው በሀያ ብር አስያዝኩ፡፡ እንደፈራውትም መልሰሽ ደወልሽ፡፡ ይኸው ተጨማሪ ሀያ ብር ሸቀልን ማለት ነው፡፡" አለኝ ዝርዝር ብሮች እያሳየኝ፡፡ ነገረ ስራው በሙሉ አስቂኝ ነው፡፡ ለምን እንዴት ሚሉ ሌሎች ጠሸያቄዎችን ላነሳበት አልፈለኩም፡፡ ያዘዝነው እራት መጥቶ እየተመገብን መጨዋወት ጀመርን፡፡በመሀል በመሀል ማውቃቸው ልጆችን ሰላም ስል አይቶ "የዲን ልጅ ነሽ እንዴ?" አለኝ፡፡ ንግግሩ እና መልሱ እንዳለ የተጠና ነው ሚመስለው፡፡
ምሽት ላይ አሪፍ ግዜ ካሳለፍን ቡሀላ በጣም ስለመሸ እንሂድ ተባብለን ከካፌ ወጣን፡፡ ኪሩበል በተለመደው ጨዋታው እያዝናናኝ ዶርም ድረስ ሸኝቶኝ ሊሄድ ሲል 'አትገባም?' ስል ጠየኩት፡፡ "እሺ "ብሎ ተከተለኝ፡፡ ሳቄን መቆጣጠር አልቻልኩም፡፡ እንደምንም ሳቄን አቁሜ 'ሆሆሆ ወንድሜ አንተ አታደርገውም አይባልም 'አልኩትና መልሼው እኔ ወደዶርሜ ገባው፡፡ዶርም እንደደረስኩ የመጀመሪያው ስራዬ ለፍሬ ስልክ መደወል ነበር፡፡ ነገር ግን አሁንም ስልኩ አይጠራም፡፡ በጣም ተናደድኩኝ ስልኬን ጠረቤዛው ላይ ወርውሬ ልብሴን እንኳ ሳልቀይር አልጋዬላይ ወጥቼ በጀርባዬ ጋደም አልኩ፡፡ 'ፍሬ ምን ሆኖ ነው? የኔን ስልክ ብቻ ነው ማያነሳው ወይስ? ነገ በሌላ ስልክ እደውልለታለው ቆይ 'ብዬ ከራሴ ጋር እያወራው ስልኬ ጠራ ፡፡ በፍጥነት ከአልጋው ወርጄ የደወለውን ሳይ . . .
ይ ቀ ጥ ላ ል . . .
❣
ቻናላችንን ይቀላቀሉ
◦◦✧join 👇👇👇👇👇
@Mamusha23
@Mamusha23
@Mamusha23 🟢🟡🔴🟢🟡🔴🟢🟡🔴🟢🟡🔴🟢🟡🔴🟢🟡🔴
🇪🇹 #ኢትዮጵያ_ለዘለዓለም_ትኑር! 🇪🇹
❣ #ፍቅር_ያሸንፋል ❣
💞 #ሴና #ክፍል_ሠላሳ_አንድ 💞
. . . እነዛ አስጨነቂ እና አሰልቺ ቀናት አለፉ፡፡ ቤት ውስጥ ከወንድሞቼ ጋር መነጋገር ካቆምኩ ቆየሁ፡፡ እነሱ ሲመጡ እኔ ክፍሌ ገባለሁ፡፡ እንዲ እንዲያ እያልኩ የረፍት ቀናቶች ላይቀርላቸው የግዳቸውን አለፉ፡፡ ድር ትምህርትቤት ረፍት ሲባል ለተማሪዎች ደስታ ነው፡፡ለኔ ግን በተቃራኒው ሀዘን ፣ጭንቀት፡፡ አሁን ደሞ ባሰብኝ፡፡ ያም ሆነ ይህ ነገ ወደ ትምህረትቤት ሄዳለው፡፡
ማታ ወንድሞቼ ሲመጡ እኔ ክፍሌ አልጋዬላይ ጋደም ብዬ መፅሀፍ እያነበብኩ ነው፡፡ "ሳሎን ትፈለጊያለሽ" ብላ ጠራችኝ የቤት ሰራተኛችን፡፡ ኡፍፍፍፍ . . . ዛሬ ደሞ ስለምን ሊጨቀጭቁኝ ነው እያልኩ የግዴን ተነስቼ ሄድኩኝ፡፡ ከኔ በስተቀር ሙሉ ቤተሰብ ተሰብስቦ ቲቪ እያዩ እያወሩ ነበር፡፡ እኔን ሲያዩ ሁሉም ወሬያቸውን አቁዋርጠው የቲቪውን ድምፅ አጥፍተው ወደኔ መመልከት ጀመሩ፡፡ ቁጭ እንድል ካዘዙኝ ቡሀላ ተራ በተራ የምክር መአት ያወርዱብኝ ጀመር፡፡ እኔ የነሱ ምክር ምኑም አይታየኝም፡፡ ብቻ እስኪጨርሱ ጓጓው፡፡ ልክ አውርተው ሲጨርሱ ተነስቼ ልሄድ ስል አባቴ "በይ ከነገ ጀምሮ ወደ ትምህርት ስለምትሄጂ ያዢው " ሲል ስልኬን ሰጠኝ፡፡ በጣም ደስ አልኝ፡፡ ሳላስበው ሳቄ መጣ፡፡ የደስታ ሳቅ . . . ስልኬን እንደተቀበልኩ ሮጬ ክፍሌ ገባው፡፡ በሬን ከመዝጋቴ ስልኬን ለመክፈት ሞከርኩ፡፡ ቻርጅ ዘግቶአል፡፡ ቻርጀር ሰክቼ ትንሽ እስኪሞላ አጠገብ ቀጭ አልኩ፡፡ በጣም ቸኮልኩ ፡፡ስልኬ እጄ ሲገባ ይበልጥ ፍሬ ናፈቀኝ፡፡
ስልኬ እንደከፈተ መጀመሪያ ለፍሬ መልእክት ላኩለት፡፡ ስልኬን እንደታቀፍኩኝ አልጋዬ ላይ ጋደም ብዬ ፍሬን ማሰብ ጀመርኩ፡፡ ስልኬን ሳገኝ ፍሬን በአካል ያገኘው ያክል ነበር የተሰማኝ፡፡ ጋደም እንዳልኩ ብዙ ጠበኩ ፍሬ መልእክት አልመለሰም፡፡ ደግሜ ልልክ አስቤ ተውኩት፡፡ ስልኬን አስቀምጬ ለነገ ያዘጋጀዋቸው እቃዎች እና ልብሶች አለመጉደላቸውን አረጋግጬ መልሼ አልጋዬ ላይ ጋደም አልኩ፡፡ አሁንም ስልኬን ተመለከትኩ ምንም የለም፡፡ እንቅልፍ አልወስድ አለኝ፡፡ ለሊቱ ረዘመብኝ፡፡ ነግቶ ግቢ እስከምሄድ ቸኮልኩ፡፡
እንዲሁ ስገላበጥ እንቅልፍ በአይኔ ሳይዞር ነጋ፡፡ ልብሴን ቀያይሬ ቁርሴን እንደበላው ቦርሳዬን አዝዬ ልወጣ ስል ወንድሜ "አብረን እንሄዳለን እሸኝሻለው "አለኝ፡፡ ከታክሲ ሰልፍ ገላግሎኛል ፡፡ግን ደሞ ከወንድሜ ንዝንዝ ሰልፉ ይሻለኛል፡፡ ግቢ በር ላይ እንዳደረሰኝ ተሰናብቶኝ ወደጉዳዩ ሄደ፡፡ እኔም ቦርሳዬን እንዳዘልኩ ወደ ዶርሜ አቀናው፡፡
"መጣውላቹ ጉዋደኞቼ
ወራቶች ተኝቼ"
ልጅ እያለው መስከረም ላይ ስንገናኝ ምንላት ግጥም ትዝ አለችኝ፡፡ ወደ ዶርሜ ስሄድ አንዳንድ ማውቃቸውን ልጆች ሰላም እያልኩ ነበር፡፡ ለጉዋደኞቼ አልደወልኩም፡፡ ምክንያቱም ድምፄን አጥፍቼ ድንገት ላገኛቸው ነው የፈለኩት፡፡
ልክ ዶርም እንደደረስኩ በሩን ልከፍተው ስል ቁልፍ ነው፡፡ ማንም የለም ማለት ነው፡፡ የኔን ቁልፍ አውጥቼ በሩን ከፍቼ ገባው፡፡ ዶርሙ ያኔ ስንሄድ ትተነው እንደሄድነው ነው፡፡ ደነገጥኩኝ! ማንም አልመጣም ማለት ነው? ቦርሳዬን ካስቀመጥኩ ቡሀላ ስልኬን አውጥቼ ለሚጣ ደወልኩላት . . .
ይ ቀ ጥ ላ ል . . .
ቻናላችንን ይቀላቀሉ
◦◦✧join 👇👇👇👇👇
@Mamusha23
@Mamusha23
@Mamusha23 🟢🟡🔴🟢🟡🔴🟢🟡🔴🟢🟡🔴🟢🟡🔴🟢🟡🔴
💞 #ሴና #ክፍል_ሀያዘጠኝ 💞
. . . እቤት ውስጥ ማደርጋቸው ነገሮች ቀን በቀን ተደጋጋሚ እና አሰልቺ ናቸው፡፡ ጥዋት መነሳት. . . ክፍሌን ማፅዳት. . . ቁርስ መብላት . . . ከዛ መፅሀፍ ማንበብ ወይም ቲቪ ማየት . . . ከዛን ምሳ . . . ቡና . . . ማንበብ. . . አመሻሽ ላይ ወንድሞቼ ሲመጡ አሰልቺ ንዝንዝ . . . እንደገና እራት ኡፍፍ በጣም ስልችት ያለኝ የቀን ከቀን ድግግሞሽ፡፡ ፍሬ ቀን ቀን ስራ ስለሚሰራ አላገኘውም ፡፡ ማታ ከእራት ሰአት ቡሀላ ግን ሁሉም ወደመኝታ ሲሄዱ በደስታ እየቦረኩ ሮጬ ወደ ክፍሌ ገባለው፡፡ የናፈቀኝን ፍሬን አገኘዋለው ፣አወራዋለው ስልችት ያለነኝን ቀን ማታ ፍሬን ሳወራ ራሴን አድሳለው፡፡
አስረኛ ቀን ላይ ደርሻለው፡፡ አስር አሰልቺ ቀናት አለፉ፡፡ ቤት ከመጣው ወደ ውጪ ወጥቼ አላውቅም፡፡ ዛሬ በአስረኛ ቀኔ ከእኔቴ ጋር ከቤት ልወጣ ነው፡፡ በጣም ነው ደስ ያለኝ፡፡ ውጪ ወጥቼ የማላውቅ ያህል ነው የጉዋጓውት፡፡ እንሂድ ብላ የጠራችኝ እናቴ ቶሎ እንድንሄዱድ ማጣድፋት እኔ፡፡ ልብሴን ለመቀያየር ሰከንድ አልፈጀብኝም፡፡ ወዲያው ለባብሼ ተነሳው፡፡ የውጪውን በር አልፌ ስወጣ ለአመታት በቤት የታሰርኩ ያህል ነበር የተሰማኝ፡፡ ውጪ ያለውን አየር እንደነፃነት አየር ነው የሳብኩት፡፡
እንደወጣን እናቴ ምትወስደኝ ቦታ ሁሉ በደስታ እየተከተልኳት መሄድ ጀመርኩ፡፡ እኔ ከቤት መውጣቴን ብቻ ነው ምፈልገው፡፡ ከእኔቴ ጋር የተለያዩ ቦታዎችን ካዳረስን ቡሀላ ወደቤት መመለስ ስንጀምር እንደገና ቅር ይለኝ ጀመር፡፡' ደሞ አሁንም ወደ እስር ቤት? ' አልኩኝ ለራሴ፡፡ ቤት እነደገባው ቀኑ እንዲመሽልኝ ምንም ሳላደርግ ማንንም ሳላወራ ቀጥታ ክፍሌ ገብቼ ተኛው፡፡
የተነሳውት ለእራት ሰአት ነው፡፡ እራት እየበላው "ለምን በቀን ተኛሽ?" የሚል መሰረተቢስ ጭቅጭቅ ከወንድሜ ተጀመረ፡፡ አሁንስ አስጠላኝ፡፡ ጭራሽ ከደርም ልጆች ጋር እያገናኘ "ከእንቅልፋሞች ጋር ገጥመሽ ነዋ ቀኑን ሙሉ ስትተኚ ምትውይው?" ሲል በጣም ተናደድኩ፡፡ እየተቀባበሉ ማውራት ጀመሩ፡፡ በመሀል ስልኬ ጠራ፡፡ ማን እንደደወለ ላይ ስልኬን ሳነሳው ወንድሜ ስልኬን ነጠቀኝ፡፡ "ቤት ውስጥ ከሆንሽ እንደውም ስልክ ምንም አያደርግልሽም ስራ ነው ሚያስፈታሽ !" ቡሎ ስልኬን አጥፍቶት አጠገቡ አስቀመጠ፡፡ እጅግ በጣም ተናደድኩ፡፡ እንባዬ መጣ፡፡ እራቱን ትቼ ክፍሌ ወደክፍሌ ሄድኩ፡፡ በሩን ከውስጥ ቆልፌ አልጋዬላይ ቁጭ አልኩ፡፡ እንባዬ መፍሰስ ጀመረ፡፡ በጣም ነው የመረረኝ፡፡ ቁጭ ብዬ እያለቀስኩ የክፍሌ በር ተንኳኳ፡፡ ዝም አልኩ፡፡ "ክፈቺ እኔ ነኝ ቢያንስ እራትሽን ጨርሺ" አለችኝ እናቴ፡፡ ምንም አላልኳትም የክፍሌን መብራት አጥፍቼ አልጋዬላይ ወጥቼ ጋደም አልኩ፡፡ እልኽ ያስለቅሰኛል፡፡ እራሴን በጣም አመመኝ፡፡ እንባዬ አልቆም አለ፡፡
በሩ በሀይል መንኳኳት ጀመረ፡፡ "አንቺ ምን ሆንኩ ነው ምትይው!?ጭራሽ ለዚህም በቃሽ! . . . " ወንድሜ ከበሩ ቆሞ መጮህ ጀመረ፡፡ ጆርዬን ያዝኩት፡፡ አሁንም ከበር ቆሞ ይጮሀል፡፡ መልስ አልሰጠውትም፡፡ በመጨረሻ ሲደክመው ሄደ፡፡እኔም ማንባቴን ቀጠልኩ፡፡ 'ቀይ ግን ወንድሞቼ ለምንድነው አንደዚህ ሚሆኑት? ቆይ ግን እኔ ይሄንን ያህል ጠላት ነኝ? ለምንድነው ከሌሎች ማገኘውን ፍቅር ፣እንክብካቤ ፣ሰላም ከቤተሰቦቼ ማላገኘው? ለምንድነው!?' አልጋዬላይ ጋደም እንዳልኩ ማልቀሴን ቀጠልኩ፡፡
ምን ግዜ እንቅልፍ እንደወሰደኝ አላውቅም፡፡ ጥዋት ከእንቅልፌ ባነንኩ፡፡ ቀና ብዬ የግድግዳ ሰአቴን ተመለከትኩ ሶስት ሰአት አልፎአል፡፡ የቆለፍኩት በሬን ከፍቼ ወጣው፡፡ እንባ የደረቀበትን ፊቴን ታጥቤ ወደሳሎን አመራው ሳሎን እንደደረስኩ ደነገጥኩ፡፡ ትልቁ ወንድሜ ቁጭ ብሎአል፡፡ ለወትሮ እሁድ ካልሆነ በቀር በዚህ ሰአት ቤት አይገኝም ነበር፡፡ ወንድሜ እኔን እየጠበቀ ነበር መሰለኝ ገና ሲያየኝ ከተቀመጠበት ብድግ ብሎ አይኑን እንዳፈጠጠ ወደኔ መራመድ ጀመረ . . .
ይ ቀ ጥ ላ ል . . .
❣
ቻናላችንን ይቀላቀሉ
◦◦✧join 👇👇👇👇👇
@Mamusha23
@Mamusha23
@Mamusha23 🟢🟡🔴🟢🟡🔴🟢🟡🔴🟢🟡🔴🟢🟡🔴🟢🟡🔴
በልብህ ውስጥ በርካታ ጦርነቶች ይኖራሉ። ልብህ እጅግ የሚጣረሱ ሀሳቦችን የያዙ ወታደሮች የመስዋትነት አውድማ እንደሆነም አትዘንጋ። ያመንክበት ወታደር ግን ከትግል ሜዳው እንዲያፈገፍግና ከመሀል መንገድ እንዲመለስ አትፍቀድ። ያኔ ነው የመርህ ሰው የምትሆነው።
┄┉┉✽̶»ቻናላችንን ይቀላቀሉ
◦◦✧join 👇👇👇👇👇
@Mamusha23
@Mamusha23
@Mamusha23 🟢🟡🔴🟢🟡🔴🟢🟡🔴🟢🟡🔴🟢🟡🔴🟢🟡🔴
💞 #ሴና #ክፍል_ሀያሰባት 💞
. . .ሚጣ ለማንበብ ጉሮሮዋን ካዘጋጀች ቡሀላ ሁሉም ተመስጦ እየተባበቃት መሆኑን በአይኑዋ ቃኘት አድርጋ ስታበቃ "አይ እናንተ ግን ለወሬ ያላቹ ፍቅር፤ እውነት ማነበው መስሎዋቹ ነው እንደዚ የጓጓቹት?" እያለች መሳቅ ጀመረች፡፡ ሁሉም ማጉረምረም ጀመሩ፡፡ ሚጣ እየሳቀች "እንቺ ስልክሽን የግል ሚስጥርሽን መንካትማ ወንጀል ነው፡፡" ስትል ስልኬን ሰጠችኝ፡፡ እኔ ደስ አለኝ ሌሎቹ ግን እየተጉረመረሙ ወደጀመሩት ነገር ተመለሱ፡፡
አኔ የፍሬን መልእክት ካቆምኩበት ቀጠልኩ ". . . ያኔ ትዝ ይልሻል ከነ ዴቭ ተለይተን ለብቻችን ወክ ስናደርግ ሁለታችን ብቻ ስንሆን በዛ በምሽት ምናሳልፋቸው ግዜያት ፤ ማታ ማታ ምንላላካቸው መልእክቶች ብቻ አንቺን ለመውደድ ብዙ ግዜ አልፈጀብኝም፡፡ ከዛን ብሀላ ግን ድንገት ባላሰብኩት ምክንያት ዘጋሽኝ፡፡ የዛን ግዜ እንዴት እንደሆንኩ አትጠይቂኝ፡፡ በማላውቀው ምክንያት በመሆኑ በጣም ነበር የጨነቀኝ፡፡ አሁን አልፎአል ምክነያትሽን ግን የሆነ ቀን ትነግሪኛለሽ ብዬ አስባለው፡፡ ሴና የኔ ብቻ እንድትሆኚ ነው ምፈልገው በቃ አንድን ሰው ለማፍቀር አመታት መቆጠር የለባቸውም ፍቃድሽ ከሆነ ሁሌም ልንከባከብሽ ዝግጁ ነኝ፡፡ ሁሌም ከጎንሽ ሆናለው፡፡ ሴናዬ አፈቅርሻለው! ልድገምልሽ አፈቅርሻለው!" የላከልኝን መልእክት ሁለት ግዜ ነው ያነበብኩት፡፡ ምን ብዬ እንደምልክለት ግን ግራ ገባኝ፡፡ አፈቅርሻለው ስላለኝ በጣም ደስ የሚል ስሜት ነው የተሰማኝ፡፡ ግን አፈቅርሀለው ማለት ፈራው፡፡ ስለ ፍቅር አውርቼም ሆነ አስቤ አላውቅም፡፡ በቃ ምን ማለት እንዳለብኝ እንኳ ማወቅ አቃተኝ፡፡ ስልኬን እነደያዝኩ ምለውን እያሰብኩ ብዙ ቆየው፡፡
እነ ሚጣ ዶርም ውስጥ ይተራመሳሉ፡፡ ነገ ሁሉም ለእረፍት ወደየ ቤታቸው ለመሄድ ጉዋጉተው እቃቸውን እያስተካከሉ ናቸው፡፡ እኔ ደሞ በተቃራኒው ነኝ፡፡ ወደ ቤት መሄዴን ሳስበው እብረከረካለው፡፡ በዛ ላይ ከ አስራ አምስት ቀን በላይ ቤት ልቀመጥ መሆኑን ሳስበው ከ አሁኑ ከበደኝ፡፡ ፍሬንም ለ አስራ አምስት ቀን በአካል አላገኘውም ማለት ነው፡፡ ስልኬን እንደያዝኩኝ በሌላ ሀሳብ ተውጬ ለፍሬ መልእክቱን ሳልመልስለት ቆየው፡፡ ብዙ ስለቆየው ፍሬ ሌላ መልእክት ላከልኝ፡፡"ማር ተኛሽ እንዴ?" ይላል፡፡ ከፍሬጋ ባለኝ ነገር ደስተኛ ነኝ ግን በመልእክት አፈቅርሀለው ለማለትም ሆነ ሌላ ነገር ስለ ፍቅር ማውራት አልቻልኩም፡፡ መልእክቱን ሳልመልስ ተኛው፡፡
ጠዋት ሁሉም እቃቸውን አዘገጃጅተው ጨርሰው ለመሄድ ሲዘገጃጁ እኔም የግዴን ሻንጣዬን ሸክፌ ተነሳው፡፡ከመውጣቴ በፊት ፍሬን አገኘውት፡፡"ማታ ደከመሽ አይደል? በግዜ ተኛሽ መሰለኝ የኔ እንቅልፋም" አለኝ በሚያምር ፈገግታው ወደኔ እየቀረበኝ፡፡ ጉንጬን ከሳመኝ ቡሀላ ተመልሶ እንደማይገናኝ ሰው ለረጅም ሰአት ተቃቅፈን ቆየን፡፡ "አረ በቃ ተላቀቁ የማትገናኙ ነው ሚመስለው እኮ" አለች ቹቹ ተቃቅፈን አንላቀቅ ስንል፡፡ ሁሉንም እያቀፍኩ ከተሰናበትኩ ቡሀላ ፍሬ ደግሞ ጉንጬን ስሞኝ ተሰናብቼው ሳበቃ የኔ መንገድ ከሁሉም ስለሚለይ እኔ ብቻዬን ከግቢ መውጣት ጀመርኩ፡፡ ብዙ ተማሪዎች ቦርሳቸውን እንደተሸከሙ ወደየቤታቸው ለመሄድ እያኮበኮቡ ይገኛሉ፡፡ እየሄዱም ያሉ አሉ፡፡ ግማሾቹ ይሰነባበታሉ ፣ይተቃቀፋሉ ፤ሩቅ የሆኑ ወደ ቤት የማይሄዱ ደሞ ጉዋደኞቻቸውን ይሸኛሉ፡፡ አነዚህን ሁሉ እየታዘብኩ በመሀላቸው አቁዋርጬ ከ ግቢ ወጣው፡፡
ታክሲ ውስጥ እንደገባው ወደቤት መሄድ ስጀምር ቅር ቅር ይለኝ ጀመር፡፡ ከግቢ እየራኩ ስሄድ በመስኮት ዞሬ ተመለከትኩ፡፡ ሆዴን ባር ባር አለኝ፡፡ ሁለት ሳምንት ቤት ታስሬ ልቀመጥ ነው፡፡ የዶርሜ ልጆች ከ አሁኑ ናፈቁኝ፡፡ "ፍሬን ሁለት ሳምንት በ አካል አላገኘውም ማለት ነው?" ስልኬን አውጥቼ ማዳመጫዬን ጆሮዬ ላይ ካደረኩ ቡሀላ ለስለስ ያለ ሙዚቃ ከፍቼ የታክሲውን ጫጫታ ላለመስማት ድምፁን ከፍ አድርጌ እየሰማው ወደቤት ጉዞዬን ቀጠልኩ፡፡ የፍሬ ድምፅ እየተመላለሰ በሀሳቤ ይመጣብኛል "ሴና አፈቅርሻለው . . . " ታክሲው ጉዞውን ቀጥሎአል፡፡ እኔም ሙዚቃ እየሰማው በሀሳቤ ገስግሻለው . . .
ይ ቀ ጥ ላ ል . . .
💞 #ሴና #ክፍል_ሀያአምስት 💞
. . . "የውልሽ ሴና እኛ አንድ ዶርም ምንኖር ልጆች እንደ አንድ ቤተሰብ ነን፡፡ አብረን እንማራለን ፣አብረን እንበላለን እንጠጣለን ፣ውሎዋችን አንድ ላይ ነው ፣አዳራችንም አንድ ላይ ነው፡፡ ይሄ አንድ ቤት ውስጥ ማኖሩ እህታማቾች እንኳን ብዙ ግዜያቸውን እንደኛ አያሳልፉም፡፡ እኛ በዚህ ሁሉ ቀናት አብረን እንደ አንድ እናት ልጆች ነበር ስንውል ስናድር የነበረው፡፡ በነዚህ ቀናቶች ደግሞ አንዳችን የሌኛችንን ሁኔታ ለመረዳት ብዙም አይከብደንም፡፡
ሴና ያንቺም ነገር አሁን እንዳልኩሽ ነው፡፡ ተጫዋች ፣ሳቂታ ፣ደስተኛ ፣ንቁ የነበርሽ ልጅ በአንድ ግዜ ያ' ሳቅሽ ሲጠፋ ፣ጭንቅንቅ ስትይ ስታዝኚ ስናይ 'ምን ሆና ነው?' የሚል ጥያቄ ውስጣችን ይፈጠራል፡፡ አብረን እስከኖርን ድረስ ደሞ ያንቺን ደስታና ሀዘን መጋራት ግድ ይለናል፡፡ እናም በቹቹ አነሳሽነት በሁላችንም ተሳታፊነት ችግርሽ ምን እንደሆነ አጣርተን ከደረስንበት ቡሃላ መፍትሄ አግኝተን ይኸው ለዚ ደረስን እልሻለው፡፡" አለች የደስ ደስ ያለው ሳቋን እየሳቀች፡፡
ሚጣ ስታወራ ሁሉም በተመስጦ አተኩሮ ያዳምጡዋት ነበር፡፡ ተናግራ ስትጨርስ ሳናስበው ሁላችንም አጨበጨብን፡፡ ሁሉንም ተራ በተራ ተነስቼ አቀፍኳቸው፡፡ አብሮ መኖር ይኼው ነው፡፡ አንዱ ሌላውን መረዳት ፣አንዱ ስለሌላው ማሰብ፡፡ እውነት ያደረጉት ነገር በጣም ውስጤን ነካው፡፡ሳላስበው የደስታ እንባ አነባው፡፡የዛን ምሽት እየተጫወትን እየተሳሳቅን በእህታማችነት መንፈስ አደርን፡፡
ጥዋት ስነሳ ደስተኛዋ ሴና ሆኛለው፡፡ ነቃ ያልኩ ፣ቀኔን በፈገግታ ምጀምር ፡፡ተጣጥበን ቀርሳችንን በልተን ክፍል ስንገባ ሙሉ ትኩረቴን ትምህርቴ ላይ አድርጌ እከታተል ጀመርኩ፡፡ ወደቀድሞዋ ሴና ተመለስኩ፡፡ ከክፍል ስወጣ ፍሬን አገኘዋለው፡፡ አብረን ምሳ እንበላለን፡፡ ግቢውስጥ ያለኝ ነገር በሙሉ የሚያስደስት ሆነ፡፡
እንዲ እንዲያ እያልን ቀናት ተቆጠሩ ፣ሳምንታትም አለፉ፡፡ የዶርማችን ፍቅር ፣አንድነት ፣ህብር ቀን ከ ቀን እየጨመረ መጣ፡፡ እነ ቹቹ ማምሸታቸውን ሆነ መስከራቸውን አላቆሙም ነገር ግን መጠናቸውን በጣም ቀንሰዋል፡፡ ከበዛ በሳምንት ሶስት ቀን ብቻ ቢያመሹ ነው፡፡ ብዙውን ግዜ የዶርም ልጆች አብረን ማሳለፍ ጀመርን፡፡
ከፍሬ ጋር ያለኝ ቅርርብ በጣም ጥልቅ እየሆነ መጣ፡፡ ቀን በቀን እንገናኛለን ፣ምሽት በስልክ መልእክት እናወራለን ይባስ ብሎ ቫይበር ፣ፌስቡክ እንድጠቀም አድርጎኝ ቅዳሜና እሁድ ቤት ሆኜም እንኳን አብሮኝ ያለ ያህል እንዲሰማኝ ያደርግ ጀመር፡፡ በግቢ ውስጥ ሆነ በውጪ ብዙ ወንዶች ያወሩኛል፡፡ እኔ ለአንዳቸውም ቦታ አልሰጥም፡፡ግቢ ውስጥ ከፍሬ ውጪ ምቀርበው ወንድ ዴቭ ብቻ ነው፡፡ የክፍሌን ወንዶች ክንኳን ከሰላምታ በዘለለ አልፎ አልፎ ለትምህርት ነክ ጉዳዮች ካልሆነ ስለሌላ ነገር አላወራቸውም፡፡ ፍሬ ብዙ ነገሬ እየሆነ መጣ፡፡
ከወራት ቡሀላ የመጀመሪያ መንፈቅ ትምህርት ማለቂያ ፈተና ተፈትነን ከጨረስን ቡሀላ በመሀል ባለን እረፍት ሁላችንም ወደየቤታችን ስለምንሄድ ፈተና ከጨረስን በነጋታው ያለውን ሙሉ ቀን አብረን እንድናሳልፍ ተስማምተን ቀኑን አብረን አሳለፍን፡፡ ምሽት ላይ እኔና ፍሬ ብቻችንን ሆነን ወደ አንድ ተማሪ ወደማይበዛበት ቦታ ሄድን፡፡ ቅዳሜና እሁድ ለሁለት ቀን ቤት ስሄድ ሚናፍቀኝ ልጅ አሁን ደሞ ከሁለት ሳምንት በላይ እንደማላገኘው ሳውቅ ልቤ ይረበሽ ጀመር፡፡
ከቦታው ስንደርስ ከዛፍ ስር የሚገኝ አንድ መቀመጫ ላይ ጎን ለ ጎን ቁጭ ብለን ማውራት ጀመርን፡፡"ሆዴ ለሁለት ሳምንት ልትናፍቂኝ ነው እኮ. . ." አለኝ አንገቴን አቅፎ ወደ ራሱ እያስጠጋኝ፡፡ "እኔም እኮ ትናፍቀኛለክ . . ." አልኩት አንገቱ ስር ሽጉጥ እያልኩኝ፡፡ትንሽ ካወራን ቡሃላ እንዴት እንደሆነ ባላውቅም አንድ ያልጠበኩት ነገር ተፈጠረ፡፡ በመጀመሪያ ደነገጥኩ ሰውነቴ በሙሉ ነዘረኝ፡፡ ከዛ ግን . . .
ይ ቀ ጥ ላ ል . . .
ቻናላችንን ይቀላቀሉ
◦◦✧join 👇👇👇👇👇
@Mamusha23
@Mamusha23
@Mamusha23 🟢🟡🔴🟢🟡🔴🟢🟡🔴🟢🟡🔴🟢🟡🔴🟢🟡🔴
••●•• #በቃ_ፎንቅቃለች 🤣 ••●••
• • ● • •
ሳቁን እያደነቀች፣አይን አይኑን እያያች
የሱን ዱካ ይዛ ከተመላለሰች
ስለሱ እያሰበች፣ሳተኛ ካደረች
ስታየው ከፈራች፣ከተደናበረች
ያላየችው ጊዜ፣ልቧ እሷን ጥሎ
ፍለጋ ከወጣ
ከዚህ በላይ ፍቅር ከወዴት ሊመጣ
ይሄን ሁሉ አይታ፣አላፈቀርኩትም
ብላ ከገገመች፣በቃ ፎንቅቃለች።😘😍
••●••
ቻናላችንን ይቀላቀሉ
◦◦✧join 👇👇👇👇👇
@Mamusha23
@Mamusha23
@Mamusha23 🟢🟡🔴🟢🟡🔴🟢🟡🔴🟢🟡🔴🟢🟡🔴🟢🟡🔴
ሚዛኑ ጠፋብኝ
ፍቅር መመዘኛ ምንድነው መስፈርቱ🤔
ውስጤ ያለው ፍቅር ማስቀመጫ ቋቱ😍
ቆይ ፍቅር በሚዛን እንዴት ይመዘናል😏
ሚዛኑ ቢከብደው በምን የቀነሳል🙄
ፍቅር እቃ አደለም ሚዛን እሚኖረው😡
የሄኛውን ኪሎ ያኛውን ቀንሰው👀
አይባል እንግዲ ፍቅር ሚዛን የለው🤷♂️
ቻናላችንን ይቀላቀሉ
◦◦✧join 👇👇👇👇👇
@Mamusha23
@Mamusha23
@Mamusha23 🟢🟡🔴🟢🟡🔴🟢🟡🔴🟢🟡🔴🟢🟡🔴🟢🟡🔴
💞 #ሴና #ክፍል_ሀያሁለት 💞
. . . የላከልኝ መልእክት እንዲህ የሚል ነው"ሴና ይሄንን መልእክት ማታ ነበር ልልክልሽ የነበረው፡፡ ግን ምናልባት ሳይመቻት ይሆናል ስልም መልሼ አሰብኩ፡፡ አሁን ገን ጥርጣሬዬ እውነት መሆኑን አሳየሽኝ፡፡
ሴና በዚች አንድ ሳምንት ያሳለፍነው ግዜ ለብዙ ግዜያት አብሬያቸው የቆየው ሌሎች ሴቶች ጋር ያሳለፍኩትን ግዜ በእጥፍ የሚበልጥ ነው፡፡ ምን እንዳስቀየምኩሽ ፣ምን እንዳጠፋው ወይ ያልተመቸሽ ነገር ምን እንደሆነ ራሱ ሳትናገሪ በድንገት ጠፋሽ፡፡ 'አንድ ሳምንት ለምታውቃት ልጅ ምንድነው እንደዚ ሙጭጭ ማለት፡፡' እስኪሉኝ የዶርም ልጆች ስላንቺ ሳስብ ስጨነቅ ነበር፡፡አንቺ ግን ትክክል አልሰራሽም፡፡ በእውነት እልሻለው ትክክል አልሰራሽም፡፡ አንቺ ምክንያት ሊኖርሽ ይችላል፡፡ ግን ምንም ሆነ ምን ከኔጋር ሚገናኝ ምክንያት የሚኖርሽ አይመስለኝም፡፡ መጀመሪያ ያገኘውሽ ቀን የሆነ ነገር ነበር የተሰማኝ፡፡ያለፈውን መጥፎ ግዜ አስታወሽኝ አሁን ፡፡ ምን እንደሆነ ልነግርሽ አልችልም፡፡ እና ሴናዬ በቃ አንቺ ያመንሽበት ነገር ከሆነ ችግር የለውም አልደውልም ፣ መልእክትም አልክም፡፡ እኔ ሴት ምናምን ወዲያ ወዲ ማደርግ መስሎሽም ከሆነ ተሳስተሻል፡፡ እንደዛ ቢሆን አንድ ሳምንት ላወኩሽ ይሄንን ሁሉ ባለፈለፍኩ በሁለተኛው ቀን ነበር ምረሳሽ፡፡ እና በቃ እኔን ሽሽት ከ ጉዋደኞችሽ አትራቂ፡፡ እኔ አልደርስብሽም፡፡ መንገድ ላስ ስንገናኝ 'ሰላም' በይኝ ግን እሺ፡፡ ደና ሁኚ፡፡"
አንብቤው እንደጨረስኩ ባለሁበት አካባቢ መቀመጫ ፈልጌ ቁጭ አልኩ፡፡ ሳላስበው በጉንጬ ላይ የወረደውን እንባዬን አብሼ መልሼ መልእክቱን ማየት ጀመርኩ፡፡ አላውቅም ብቻ የሆነ ነገር ረበሸኝ፡፡ ልቤ ድንግጥ ድንግጥ ይላል፡፡ የማላውቀው የጭንቀት ስሜት ተሰማኝ፡፡ እንደምንም ራሴን አረጋግቼ ወደ ዶርም ሄድኩኝ፡፡
ዶርሜ አልጋዬላይ ጋደም እንዳልኩ ፊቴ ላይ ሚመጣው ፍሬ ነው፡፡ ብገላበጥም ፣ጥቅልል ብዬ ብተኛም ፍሬን ብቻ ማሰብ ሆነ ስራዬ፡፡ ስልኬን አውጥቼ ከመጀመሪያ ቀን ጀምሮ ከፍሬ ጋር የተላላክናቸውን መልእክቶች ማንበብ ጀመርኩኝ፡፡ እነዛን ቀናት በውስጤ እያሰብኳቸው ብቻዬን ፈገግ እላለው፡፡ ዛሬ የላከልኝን መልእክት ደግሜ ሳነበው እንባዬ ይመጣል፡፡
እውነቱን ነው እኮ ግን ምን አደረገኝ ቆይ? ከኔጋር ግዜውን ስላጠፋ ነው? አብሮኝ ስለሆነ ነው? ስለቀረበኝ ነው? የራሴን ስሜት ብቻ ለምን ተከተልኩ? ሳላስበው እንባዬ ይፈሳል፡፡ የሆነ ቅር ቅር ሚል ነገር ይሰማኛል፡፡ አልጋዬላይ ጋደም በዬ በትዝታ ከፍሬ ጋር እየተጫወትኩ እንቅልፍ ወሰደኝ፡፡
ከእንቅልፌ ስነሳ እኩለ ለሊት አልፎአል፡፡ ራሴን በጣም አሞኛል፡፡ አልጋዬ ላይ እንዳለው ቀና ብዬ ዶርሙን በአይኔ ቃኘው፡፡ ሁሉም ተኝተዋል፡፡ ጠረቤዛ ላይ የፕላስቲክ ምሪንዳ እና ብስኩት ተቀምጦአል፡፡ ምናልባት ለኔ ይሆናል ብዬ አሰብኩ፡፡ ስልኬን ስመለከት 16 ግዜ ተደውሎአል፡፡ደነገጥኩ ወንድሜ እና አባቴ ናቸው፡፡ አሁን እንዳልደውል ወረበሽ ይሆናል፡፡ የፍሬን መልእክት ስላጣው ቅር አለኝ፡፡ተመልሼ ተኛሁ ግን እንቅልፍ አልወስድ አለኝ፡፡ እንዲሁ ስገላበጥ አነጋው፡፡
ጥዋት የዶርሜ ልጆች ሲነሱ ሁሉም በየተራ "ሴና ማታ ምን ሆነሽ ነው?" ይሉኝ ጀመር፡፡መልሼ ጠየኳቸው"ምን ሆንኩኝ?" ስል፡፡ "እንዴ ማታ ብንጠራሽ አትሰሚ ደሙ አልቅሰሽ ነበር? ስልክሽም ያንን ሁሉ ግዜ እንደዛ እየጠራ መጨረሻ እንዳይጨነቁ ብዬ 'ትንሽ ራሱዋን አመም አድርጎዋት ተኝታ ነው'አልኩልሽ፡፡ ቆይ ግን ምን ሆነሽ ነው?" አለችኝ እኑካ፡፡'አይ ተመስገን ስልኬን ካነሳቹ ሌላው ቀላል ነው' አልኩኝ በሆዴ፡፡
"ሜምናልባት እራት ካልበላሽ ብለን ነው ያመጣንልሽ እኮ ፆምሽን ነዋ ያደርሽው?" አለችኝ ሚጣ እንደመቆጣት ብላ፡፡ "እሺ አሁን ቁርስ በላዋለው "ብያቸው ልተጣጠብ ወጣው፡፡ ተጣጥቤ ስመለስ ራስምታቴ ባሰብኝ፡፡ አልጋዬ ላይ ተመልሼ ተኛው፡፡ ቢጠይቁኝም መልስ የለኝም፡፡ "የክፍል ሰአት እየደረሰ ስለሆነ እናንተ ሂዱ በቃ እኔ እዚ አለው" አለች ቹቹ፡፡ አሁን ድምፁዋን ስሰማ ነው መኖሩዋን ያወኩት፡፡ "አይ እኔ አለው እናንተ ሂዱ" አለች ሚጣ፡፡ ከቹቹ ጋር ተቃራኒ እንደሆኑ አውቃለው፡፡ "ካልሽ እንዳልሽ ይሁን "ስትል ቹቹና ጉዋደኞቹዋ ተያይዘው ወጡ፡፡ እነ እኑካም ተከታትለው ወጡ፡፡ በመጨረሻም ባለ መነፅሯ ወጣች፡፡ እኔና ሚጣ ብቻ ቀረን፡፡ አልጋዬላይ ተጠቅልዬ ጋደም እንዳልኩ ነኝ፡፡
"ምን ሆነሽ ነው ግን? ሰሞኑን እኮ ልክ አይደለሽም" አለችኝ ሚጣ፡፡ "ምንም አልሆንኩም" አልኳት እንባ እየተናነቀኝ፡፡"የሆነ ነገርማ ሆነሻል ፤ግድ የለሽም ንገሪኝ" ስትል በጥያቄ አስጨነቀችኝ፡፡" እኔም ግራ ገብቶኛል ሚጣ ፡፡ እኔ ራሴ አላውቅም! እንዲነው ምልሽ ! ተረድቼ ማስረዳሽ ! የሆንኩትን ማውቀው ነገር የለኝም! እኔም ግራ ገብቶኛል እኮ! ምን ሆንኩ ልበልሽ!? እንዴት ላስረዳሽ!? " እንባዬ እየወረደ ሀይለቃል የተቀላቀለበት መልስ መለስኩላት፡፡ ራስምታቴ ጨመረ . . .
ይ ቀ ጥ ላ ል . . .
.......✍
በህይወት ዘመን ከሚያጋጥሙህ ፍልሚያዎች
እጅግ በጣም ፈታኙ እውነታውን ጠንቅቆ በሚያውቀው አእምሮህና
እውነታውን መቀበል ባቃተው ልብህ መካከል የሚደረግ ፍልሚያ ነው።
ቻናላችንን ይቀላቀሉ
◦◦✧join 👇👇👇👇👇
@Mamusha23
@Mamusha23
@Mamusha23 🟢🟡🔴🟢🟡🔴🟢🟡🔴🟢🟡🔴🟢🟡🔴🟢🟡🔴
💞 #ሴና #ክፍል_ሀያ 💞
. . . "ሴና ምን ሆነሻል?" ከወሰደኝ ሀሳብ የቹቹ ጥሪ መለሰኝ፡፡ እንዲሁ ነው ብያት ከቹቹ ጋር ከተስማማን ብሀላ ጨዋታ ቀይረን ስለሌላ ነገር ማውራት ጀመርን፡፡በዚህ መሀል ስልኬ ጠራ ፡፡ፍሬ ነውስልኬን አይቼ ቀና ብዬ ቹቹን እየተመለከትኳት "ፍሬ ደወለ" አልኩ እንደመደንገጥ ብዬ፡፡"እና ይደውላ ምነው ልታነሽው ባልሆነ፡፡"ስትለኝ ምንም መልስ ሳልሰጣት ስልኬን አስቀምጬ ጨዋታችንን ቀጠልን፡፡ ብዙ ከተጨዋወትን ቡሀላ ቹቹ ምትሄድበት እንዳለ ነግራኝ ካፌ ትታኝ ወጣች፡፡
ትንሽ ብቻዬን እንደተቀመጥኩ ለነ ሚጣ ልደውል አስቤ ደግሞ ፍሬ ቢኖርስ ብዬ ተዉኩት፡፡ ወንድሜ አግኛት ላለኝ ልጅ ልደውል አልደውል ስል ብዙ አመነታው፡፡በመጨረሻም ደወልኩላት፡፡ ረጋ ያለች ልጅ ትመስላለች ትንሽ አናግሬያት ከተዋወቅን ብሃላ ከቻለች እንድንገናኝ ስጠይቃት "ዛሬ ክላስ የለኝም ቤት ነኝ ጥዋት ነው ምመጣው"አለችኝ፡፡ 'ጎሽ ከኔም የባሰ አለ ማለት ነው' አልኩ በሆዴ፡፡ነገ ላገኛት ተቀጣጥረን ስልኩን ዘግቼ ቁጭ ብዬ ቲቪ ላይ ማፍጠጥ ጀመርኩ፡፡ ብቻዬን ነው የተቀመጥኩት፡፡ አይኔ ቲቪ ያያል እንጂ ሀሳቤ ሌላ ቦታ ነው፡፡
"አረ ቆንጆ ብቻሽን ምነው? ከገባው ጀምሮ ሳይሽ ብቻሽን ነሽ የማን ፋራ ነው አስደግፎሽ የቀረው?" እያለ ከፊትለፊቴ ያለ ወንበር ስቦ ተቀመጠ አንድ ፀጉረ ጨበሬ ወንድ፡፡ምንም መልስ አልሰጠውትም፡፡ ከተቀመጠ ቡሃላ "ወንበሩ ግን ሰው አለው?" አለኝ መልስ አልሰጠውትም ወደ ወንበሬ መደገፊያ ደገፍ ብዬ እጄን በደረቴ አድርጌ ተቀመጥኩ፡፡ "ፆም ገባ እንዴ?" አለኝ ፡፡ 'የምን ፆም?' ስለው "ተመስገን አልገባም ማለት ነው፡፡ምነው ብቻሽን እዚ ማንን እየጠበቅሽ ነው?" አለ፡፡ከመጣ ሰአት ጀም ሌላም ያላስታወስኮቸው ብዙ ነገሮች አወራ ፣ሊቀልድ ማከረ ፣ሊያስገርመኝ ሞከረ፡፡ እኔ በራሴ ሀሳብ ውስጥ ነኝ፡፡ ወሬው ቢያቅተኝ ለሚጣ ደውዬ ቀጥሮ እንደሚጠብቅ ሰው'የት ናቹ ቆየው እኮ ከመጣው የት ልምጣ' አልኩኝ እንደመቆጣት ብዬ፡፡ሚጣ ያልኳት ግራ ቢገባትም ያሉበትን ነገረችኝ፡፡ እዛው ጠብቁኝ ብዬ ተነሳው፡፡ ልጁ አብሮኝ ተነሳ"እኔም ወደዛው ስለሆንኩ ልሸኝሽ?" አለኝ፡፡ 'ምሄድበትን እንዴት አወክ?' ብዬ ስጠይቀው "እሱን ስትደርሺ ነዋ ማውቀው"አለኝ፡፡ 'ውይ በናትክ ወንድሜ ተወኝ'ብዬ ወደነሚጣ ገሰገስኩ፡፡
ከነሚጣ ጋር ስገናኝ ረጅም ቀን ያጣዋቸው ያህል ነበር የናፈቁኝ፡፡ ሁሉንም ሰላም ብዬ "ምነው ቅድም ፍሬ እየደወለልሽ አታነሺም አብረን ነበርን" አሉኝ፡፡ ከሰው ጋር እንደነበርኩ ነግሬያቸው ካፌ ውስጥ ያጋጠመኝን ልጅ ነግሬያቸው መሳሳቅ ጀመርን፡፡
ማታ ዶርም ገብቼ ልብሴን ከቀያየርኩ ቡሀላ ክፍል ገብተው ከፃፉት ማስታወሻ ላይ መገልበጥ ስጀምር የፍሬ መልእክት በስልኬ ገባ"ምነው ጠፋሽ በሰላም ነው?" ሚል ነበር፡፡ አንበቤ ብቻ ስልኬን መልሼ አስቀምጬ መፃፌን ቀጠልኩ፡፡ ዶርም ውስጥ እያወራን እየተሳሳቅን ስለነበር ለፍሬ መልእክት አለመመለሴ ብዙም ቅር አላለኝም፡፡
ጥዋት ወደ ክፍል ስንሄድ ፍሬን ባላገኘው ብዬ በውስጤ ተመኘው፡፡ ጠልቼው አይደለም ግን ደሞ . . . በቃ ብቻ ላገኘው አልፈለኩም፡፡ ብዙ ቀን ወደክፍል ስንሄድ ፍሬና ዴቭን እናገኛቸዋለን፡፡ ዛሬ አላገኘናቸውም የሆዴን ሰማኝ መሰለኝ፡፡
ቀን ከክፍል ስንወጣ ምሳ ካፌ እንግባ ወይስ ውጪ እንብላ ብዬ ጠየኩዋቸው፡፡ "አረ ዴቭ ዛሬ ምሳ በኔ ነው ብሎአል ልደውልለት እንደውም ብላ ስልኳን መነካካት ጀመረች፡፡ ደነገጥኩ 'ወይኔ ጉዴ ፍሬም ይመጣል ማለት ነው እኮ' አልኩኝ ለራሴ፡፡ በዚህ መሀል የወንድሜ ባልደረባ ልጅ ደወለች፡፡ ከተመቸኝ አሁን እንዳገኛት ጠየቀችኝ፡፡ እንደሚመቸኝ ነግሬያት ለነሚጣ 'በጣም ይቅርታ ረስቼው ነው ወንድሜ እንዳገኛት የነገረኝ ልጅ አለች አሁን ነበር ቀጠሮዋችን፡፡ረስቼው ነው በጣም ይቅርታ ጉዋደኞቼ ቡሀላ አገኛቹሀለው ብዬ ጉንጫቸውን ስሜያቸው ተሰናበትከበቸው፡፡በመሄዴ ደስ ባይላቸውም በእሺታ ራሳቸውን እየነቀነቁ ተቀበሉኝ፡፡ ትቻቸው ሄድኩ፡፡
ግን እስከመቼ? ለአንድ ሳምንት ወይስ እስከመጨረሻው? ቆይ ዛሬን እንዲ አለፍኩ ነገስ? ምን እያደረኩ ነው? ምን እየሆንኩ ነው? ውስጤ ብዙ ጥያቄ ይመላለሳል፡፡ እየተወዛገብኩ እርምጃዬ ወደ ቀጠሮዬ እያመራኝ ነው . . .
ይ ቀ ጥ ላ ል . . .
❣