mamusha23 | Unsorted

Telegram-канал mamusha23 - ከ ገጣሚያን ብዕር ♣♠

224

በቻናላችን ★የተለያዩ ግጥሞችን ★አስተማሪና አዝናኝ ታሪኮችን ★አጫጭር ልቦለዶችን ★ጠቃሚ ምክሮችን እና አባባሎችን ያገኛሉ፡፡ ሀሳብ አስተያዬት ካለ @DesuT23 ያድርሱን፡፡ Join ☞ @Mamusha23 ☞ @Mamusha23 ☞ @Mamusha23

Subscribe to a channel

ከ ገጣሚያን ብዕር ♣♠

/channel/THartandliterature

Читать полностью…

ከ ገጣሚያን ብዕር ♣♠

. . . #እሷ . . .

ማግኘትም ማጣትም በኔ አልተጀመረ
ብዬ እፅናናለው አልሆን ሲለኝ ቀኔ
እሷን ያጣው እለት ግን
እራሴን አልሆንም እኔ

ሁሉን ነገሬ ተወስዶ ትቅርልኝ እሷ ብቻ
የህይወቴ ትርጉም የኑሮ ቅኔ መፍቻ

በጨለማ ከመኖር ያወጣችኝ ደርሳ
ለጎደለው ሀብቴ ሰላሜ ናት እሷ😢

እሷ ብቻ ትኑርልኝ ትታይ ከፍ ብላ
ህይወቴ ለርሷ ብቻ ነው አይደለም ለሌላ

ፍቅር ማለት ያ ነው እንዲ ያለ ስሜት
ልብ እስኪጠፋ መውደድ ነብስን እስከመስጠት

Читать полностью…

ከ ገጣሚያን ብዕር ♣♠

🇪🇹አንቺን የደፈረሽ ??❌
-------------------//-----------------------------
የሠዉ ዘር መገኛ የድንቅነሽ አገር
የነቢላል ሀበሽ የነፃነት ምድር
በቀኝ ያልተገዛሽ የጀግና ማደሪያ
የፈጣሪ ስራ የሆነች ማሳያ
ጢስ አባይ ፏፏቴ ሆኖ በረከተሽ
የራስሽ ብራና መጻፊያ የኖረሽ
44 ታቦታት ያለ ከመቅደስሽ
ነብዩ መ/ድ አንቺን የመረጡሸ
ዛሬ ማን መቶ ነዉ አንቺን የደፈረሸ

ወይ ታሪክ ረስቷል ስምሽን ካለወቀ
ሊደፍረሽ የመጣ
የሆነ ብቻ ነዉልቡ የተሠረቀ!!

🇪🇹🇪🇹
ያለወቀን መናቅ ጅልነት ያስብላል!!
👉ፅሁፍ:እርስትአብ -ተወልደ(ፍፄ)

Читать полностью…

ከ ገጣሚያን ብዕር ♣♠

አንቺ እፉዩ ገላ....
ይህ ላባሽ ገለባ..
ተከተይኝ አትበይ
ገደል እንዳልገባ..
እፍፍፍ....ሂጂ ብረሪ..
ከኔ ላያፀናሽ አትደናበሪ..
እፍፍፍ ሂጂልኝ በቃ
ራቂ ከነፍሴ..
ተስፋ ነው መናኖሬ
አንድ ሀቄን ታቅፌ...
ያዉቃል ባለነፍሴ
መኖርሺን አልሻም...
ሚዛን ላትደፊ
ሂጅ ከኔ አታመሽም...
ሂጂልኝ ከነፍሴ
ዘመናት እራቂኝ...
በነሽ እስክትጠፊ
ካቅምሽ አታቃይኝ! ሂ...ጂልኝ
☘️🥀🌹🍁🥀🌹
ገጣሚ #ህይወት

ከወደዱት ለወዳጅዎ ያጋሩት!

Читать полностью…

ከ ገጣሚያን ብዕር ♣♠

ኢላማህ
............



ቅድሚያ ኢላማው ፡ውስጥ ሰዶ
ቀስቱን ለማስገባት፤
ሊሰድ የቆመው ሰው፡ አይምሮና እጁ፡
መስማማት አለበት።


ቢሰድ ቢወረውር ፡ኢላማውን ባይመታ ፡
የተወረወረው ቀስት፤
ሁለት ነገር አለ፡ ግቡን እንዳይጨብጥ ፡
የጋረጠው አለት።



አንድ

በድል አጠናቆ ፡ከልቡ ተነስቶ፡
ኢላማውን ለመምታት፤
የወርዋሪው አይን ፡ኢላማው ላይ ብቻ፡
ማተኮር አለበት።

ሁለት

ያየውን ራዕይ፡ እውን ሆኖ እንዲያይ ፡
ግቡን እንዲመታው፤
መስደድ ብቻም ሳይሆን ፡እስከመጨረሻው፡
ቀስቱን ይለጥጠው።




ታዲያ ዋ

ድል ማድረግ ስትፈልግ ፡መንሳፈፍ እንድትችል
ከሰፊው ደመና፤
ለግብህ ትይዩ ፡የሚገኝ ስፋራ ላይ፡
መገኘትህን አጥና።።

ከዚን

ከወደዱት ለወዳጅዎ ያጋሩት

Читать полностью…

ከ ገጣሚያን ብዕር ♣♠

ኢትዮጲያዊ አልሆንም!😔😡😢


(እጩ ሎሬት በላይ በቀለ ወያ)


ከተቀበረበት አውጡት ቆፍራችሁ መልሱት እትብቴን
ኢትዮጲያዊ መሆን አልፈልግም እኔ እንኩ ዜግነቴን!


አንዳንዴ እንደዚህ.....
የራስን ማንነት መሸከም ይከብዳል
"ከመቻል" ተወልዶ
"አለመቻል" መሆን ሀገር ያዋርዳል
ሀገር ከሚዋረድ ...
ላገር ክብር ሲባል ሀገርም ይካዳል!!!

ኢትዮጲያዊ አልሆንም!!!
"የሳት ልጅ" ተብሎ
"አመድ" ሆኖ መኖር ክብሯን አይመጥንም
በኔ እየተጠራች ተዋርዳ ከምትኖር
በክደቴ ልጥፋ -በመጥፋቴ ትክበር

🙏🙏🙏Join🙏🙏🙏

በማለት ቤተሰባችንን እንጨምር
ቻናላችንን ይቀላቀሉ
◦◦✧join 👇👇👇👇👇
በቻናላችን ★የተለያዩ ግጥሞችን
★አስተማሪና አዝናኝ ታሪኮችን
★አጫጭር ልቦለዶችን
★ጠቃሚ ምክሮችን እና አባባሎችን
ያገኛሉ፡፡
ሀሳብ አስተያዬት ካለ @DesuT23 ያድርሱን፡፡
Join ☞ @Mamusha23
☞ @Mamusha23
☞ @Mamusha23

Читать полностью…

ከ ገጣሚያን ብዕር ♣♠

😂😂😂😂😂😂😂😂😂 ቀናቶች ሰው ቢሆኑ ስማቸው ሊሆን የሚችለው

ሰኞ → አስጨናቂ

ማክሰኞ → ቻላቸው

እሮብ → ይታገሱ

ሐሙስ → ተስፋዬ

አርብ → በረከት ቢሆነኝ

ቅዳሜ → ማን ጠግቦሽ

እሁድ → ማን ያዘዋል እንደሻው
መልካም ቅዳሚት.
ፈገግ ብላችሁ ዋሉ

በቻናላችን ★የተለያዩ ግጥሞችን
★አስተማሪና አዝናኝ ታሪኮችን
★አጫጭር ልቦለዶችን
★ጠቃሚ ምክሮችን እና አባባሎችን
ያገኛሉ፡፡
ሀሳብ አስተያዬት ካለ @DesuT23 ያድርሱን፡፡
Join ☞ @Mamusha23
☞ @Mamusha23
☞ @Mamusha23

Читать полностью…

ከ ገጣሚያን ብዕር ♣♠

አደራ ጠርጥሪኝ

ስምሽን ስሰማ እንባ አይኔን ካሞቀኝ
ስላንቺ ሳወራ ሳግ ደርሶ ካነቀኝ
ፀሀይ ከበረደኝ ሳቅ ከኔ ከራቀ
መከፋት ደስታየን ከእኔ ከሰረቀ

አደራ ጠርጥሪኝ
ናፍቀሽኝ ይሆናል ሰው ልከሽ አስጠሪኝ

በእብዶች መካከል ደህና ከተሰኘሁ
በዝናብ ሲርሱ ደርቄ ከታየሁ
በትልቅ ሰው ለቅሶ ሳቄ ካመለጠኝ
ሀገር ባሳቀ ቀልድ እንባ ካጠመቀኝ

አደራ ጠርጥሪኝ
ናፍቀሽኝ ይሆናል ሰው ልከሽ አስጠሪኝ

ከጨረቃ ጋራ ሳወጋ ካመሸሁ
ከሚያውቁሽ ከሚያውቁኝ ከራሴ ከሸሸሁ
አለም ከደበተኝ ከከረፋኝ ሀገር
በሆነ ባልሆነው ካለኝ ነገር ነገር

አደራ ጠርጥሪኝ
ናፍቀሽኝ ይሆናል ሰው ልከሽ አስጠሪኝ

ይሄው አሁን እንኳ
ስላንቺ እየፃፍኩኝ ላብ ሞልቷል ግንባሬ
ቁጭ ብየ ራሱ ልሩጥ ይላል እግሬ

እኔ እወድሻለሁ ማለቱን ትቻለሁ
በስምሽ መማሉን ረስቼዋለሁ
ለምን ለምን ለምን
ለምን አንቺን ብቻ ለምን ከሰው መርጦ
የሚያርበተብተኝ
የሚያብሰከስከኝ ከሌላው አብልጦ
....ማለቱን ካበዛሁ

አደራ ጠርጥሪኝ
ናፍቀሽኝ ይሆናል ሰው ልከሽ አስጠሪኝ

አወ ናፍቀሽኛል አልክድም ወድቄ
ዝም ብለሽ ነይልኝ አታብዢ ጥያቄ
መልሴ ሁኝኝና
ከወደቅኩበት ጥግ ነይ ፈልገሽ አንሺኝ
መራቅሽ አሞኛል በመቅረብ ፈውሺኝ


አደራ....


በቻናላችን ★የተለያዩ ግጥሞችን
★አስተማሪና አዝናኝ ታሪኮችን
★አጫጭር ልቦለዶችን
★ጠቃሚ ምክሮችን እና አባባሎችን
ያገኛሉ፡፡
ሀሳብ አስተያዬት ካለ @DesuT23 ያድርሱን፡፡
Join ☞ @Mamusha23
☞ @Mamusha23
☞ @Mamusha23

Читать полностью…

ከ ገጣሚያን ብዕር ♣♠

ማን ይሆን ያጠፋው?🥱

በእርቃን ቀረሽ ፋሽን ልብሷ ተቀዳዶ
በግድ እዩኝ ብትል አያት አይኑን ሰዶ
ከተገላለጠ ከፍም ጭኗ አፍጦ
ከሷነቷ በላይ ለገላዋ ቋምጦ
በጆቹ ሊያስገባት ቃላቶችን መረጦ
ስጦታ ደርድሮ
እንዳለችው አድሮ
ምኞቱ እስኪሳካ ያለ ልኳ አክብሮ
ሊያቀርባት ሊያለምዳት
❤️ እቅድ አወጣላትእ❤️
በስተመጨረሻም የኋላ የኋላ
የልቡ ሞላለት አቀፈ ያን ገላ
ክር እና መርፌ ቸይነት
ከኋላው ተጣበቀ
ቅስፈት መደብ ልፊያ
በላብ ተጠመቀ
❤️ሁሉም ያኔ አለቀ❤️
በአፍታ ጥብብቆሽ.........
በደቂቆች እልፊት...........
በሰከንዶች ንዝረት..........
እርካታ ማእበል
ወጀቡ በርዶለት
ቀዝቅዞ ግለቱ *የስሜቱ ንዝረት
ተጠቅማት ጨርሶ ጥሏት እንደ አሮጌ
ቢያያት ትክ ብሎ ከመደቡ ግርጌ
ያ የጎመጀለት ሰውነት አካሏ
ወዘናው ተዛንፎ የውበት አክሊሏ
ቀሎ ታየው ላይኑ የሴትነት ምስሏ
💔💔😔

🙏🙏🙏
ቻናላችንን ይቀላቀሉ
◦◦✧join 👇👇👇👇👇
በቻናላችን ★የተለያዩ ግጥሞችን
★አስተማሪና አዝናኝ ታሪኮችን
★አጫጭር ልቦለዶችን
★ጠቃሚ ምክሮችን እና አባባሎችን
ያገኛሉ፡፡
ሀሳብ አስተያዬት ካለ @DesuT23 ያድርሱን፡፡
Join ☞ @Mamusha23
☞ @Mamusha23
☞ @Mamusha23

Читать полностью…

ከ ገጣሚያን ብዕር ♣♠

♠️♠️♠️ነግሬሽ ነበረ♠️♠️♠️♠️

ሴት ክብሯን ረስታ ፣ ጭኗን እንዳታምነው
ሁሉን ያጣል ብዬ ፣ የሁሉም የሆነው!!!

ነግሬሽ ነበረ
ውበት ደም ግባትሽ ፣ ሁሉን እንደሚስብ
የወንድ ልጅን ዐይን..
ከተበተነበት ፣ እንደሚሰበስብ
ነግሬሽ ነበረ...
ትንሽ ስትዘነጊኝ ፣ ብዙ እንደማስብ!!!

ነግሬሽ ነበረ... ባትሰሚኝም እንኳ
ሳሙና ነው ብዬ ፣ የቆንጆ ሴት መልኳ
እድፋም ስሜቶችን...
አሽታ ስታነፃ ፣ ያበቃል ታሪኳ!!!

ነግሬሽ ነበረ
ሴት ልጅ ስታማርጥ ፣ ለራሷ ምራጭ ናት
በክብር ነው እንጂ...
በመውለድ አይደለም ፣ የሚኮነው እናት፡፡
ክብረ ቢስ ህይወቶች ፣ ጣፍጠው አይቀጥሉም
የወለዱ ሁሉ እናቶች አይደሉም
ነግሬሽ ነበረ
እናትነት ስሟ
ከክብሯ ነው እንጂ ፣ ከልጇ እንዳልመጣ
ወልዳም ምንም ነች ፣ ሴት ክብሯን ስታጣ።

ነግሬሽ ነበረ...
ሴት ክብሯን ስትጥል ፣ እድሜዋ ይሔዳል
የወንድ ልጅ ቤቱ...
የሴትልጅ ውበት ነው ፣ ካየበት ይለምዳል፡፡

ነግሬሽ ነበረ...
ጭንሽ ሴትነትን ፣ ከቶ እንደማይበልጠው
ቁንጅናም ይረክሳል!
ብቻውን እንዲቀር ፣ ሁሉም ከመረጠው!
ብነግርሽ ብነግርሽ ፣ ባትሰሚኝም ቅሉ
"ሰደበኝ" በማለት ፣ ታወሪያለሽ አሉ
ልክ ነሽ አንዳንዴ
እውነቶች ውሸት ፊት ፣ ስድብ ይመሥላሉ።

ሞኝ ሰው ሲመክሩት
ሞኝ ሰው ሲነግሩት
የቀኑበት መስሎት ፣ በከንቱ ቢታበይ
ግን እነግርሻለሁ!
ነግሪያት ነበር ስል
ቀንቶ ተናገረኝ ፣ ወይም ሰደበኝ በይ።

ግን እነግርሻለሁ
ግን እመክርሻለሁ
ሴት ልጅ ክብሯ ሲጎድል ፣ ውበቷ አይመችም
ሁሉም ይመኟታል ፣ ከአንዱም ልብ የለችም!!!

✍️በላይ በቀለ ወያ እንደፃፈው✍️
በቻናላችን ★የተለያዩ ግጥሞችን
★አስተማሪና አዝናኝ ታሪኮችን
★አጫጭር ልቦለዶችን
★ጠቃሚ ምክሮችን እና አባባሎችን
ያገኛሉ፡፡
ሀሳብ አስተያዬት ካለ @DesuT23 ያድርሱን፡፡
Join ☞ @Mamusha23
☞ @Mamusha23
☞ @Mamusha23

Читать полностью…

ከ ገጣሚያን ብዕር ♣♠

"ወንዝ ድንጋይ ቦርቡሮ የሚገባው ሀይለኛ ስለሆነ ሳይሆን ያለማቋረጥ ስለሚፈስ ነው ፡፡"
#ጂም_ዋትኪንስ
〰〰〰〰〰
''ህይወት በራሷ፣ ምንም ያልተሳለባት ባዶ የሰዕል ሸራ ነች። ስንፈልግ መከራን፣ ስንፈልግ ሐሴትን የምንስልባት .... ባዶ ሸራ።"
#ኦሾ
〰〰〰〰〰
"ጥንካሬ እና እድገት የሚመጡት (persistence) በተከታታይ ጥረት እና ትግል ብቻ ነው።"
#ናፖሊዮን_ሂል
〰〰〰〰〰
"የሰው ልጅ ውድቀት አንደኛው መንስኤ የውሳኔ ማጣት ነው። አንድ ሰው ምንም ያህል እምቅ እውቀት ቢኖረው ፤ ምንም ያህል የሚያሰደንቅ ሃሳቦችን ማመንጨት ቢችልም ውሳኔ መወሰን ካልቻለ ግን አቅሙ ሁሉ ከውስጡ አይወጣም።"
#ናፖሊዮን_ሂል
〰〰〰〰〰
በቻናላችን ★የተለያዩ ግጥሞችን
★አስተማሪና አዝናኝ ታሪኮችን
★አጫጭር ልቦለዶችን
ያገኛሉ፡፡
ሀሳብ አስተያዬት ካለ @DesuT23 ያድርሱን፡፡
Join ☞ @Mamusha23
☞ @Mamusha23
☞ @Mamusha23

Читать полностью…

ከ ገጣሚያን ብዕር ♣♠

🗯 #መልካም ነገሮች የሚገኙት #በእንቅስቃሴ ውስጥ ነው። #መጥፎ ነገሮች ግን ካለንበት ድረስ ይመጣሉ።

〰〰〰〰〰〰
🪙 በገንዘብህ #የጥቅም ጓደኞችን ልታፈራ ትችላለህ በውበትህ #የስሜት ጓደኞችን ልታፈራ ትችላለህ በእምነትህና በስነ—ምግባርህ ግን··· #የህይወት #ጓደኞችን ታፈራለህ።

#ከወደዱት #ሼር #ያድርጉ
••●◉Join us & share◉●••

Читать полностью…

ከ ገጣሚያን ብዕር ♣♠

🇪🇹🇪🇹ግራ ገባኝሳ🇪🇹🇪🇹

(ከ ደሳለኝ ፀጋው)
Mamusha negni

ሰላም አውለኝ ብዬ በቀኘ ብነሳ
የሀገሬ ነገር ግራ ገባኝሳ፡፡

ለውድቷ እናቴ ሰላም ለሀገሬ
ትውልዷ ለሞተው ባሉባልታ ወሬ፡፡
አንች ድንቅ ምድር የእግዜር እጅ ስራ
ለዓለም ተምሳሌቷ ስምሽ የሚያበራ
የእምነት የቃል-ኪዳን የሐይማኖት ስፍራ፡፡
ፀሎትሽ የት ሔደ እምነትሽ የት ገባ
አባቶች የት ገቡ የፅናትሽ ካባ፡፡

አልገባኝም እኔ የገባው ይናገር
በተራ አሉባልታ መች ይቆማል ሀገር፡፡
ሀገር ማለት ምን ነው?
ወገን ማለት ምን ነው?
ህዝብስ ማለት ምን ነው?

ጎበዝ ግራገባኝ ሳ

ሽዎች ተሰልፈው ሽዎች ከተገፉ
ሀገር የማዳኑ የቱጋ ነው ትርፉ፡፡
ሰበርነው ቆረጥነው ለሚል ተራ ወሬ
ስለምን ይላካል የወገኔ በሬ
ስለምንስ ይሙት ሚሲኪኑ ገበሬ
ይህ አይደለም ቃልሽ አስተውይ ሀገሬ፡፡

አንች ድንቅ ምድር
አንች ሚሲኪን ሀገር
ጠበቃሽ ማን ይሆን የእውነት ምስክር
ድሮ ያኔ እንደነበርን ሀገር
ሸንሽነው ሳይሸጡን በቋንቋና በዘር
እንበልጥግ የሚሉ ሳይመጡ በሚስጥር
ለዛች ለሀገሬ ለታላቋ ምድር
ዓለም የሚያስፈራ ጠላት የሚያሽብር
ከስጋ ከደሙ ወስዶ የሚገብር
ለማተቡ ሚሞት ቃሉን የሚያከብር
የጀርባ ደጀኗ ነበራት ወታደር፡፡

አሁን ግን የት አለ???
ወገን እያለቀ ሀገር ሲሆን ወና
የት አል ወታደሯ???
የት አል ጠበቃዋ???
ሚሲኪን እዬሞተ ተቆጥሮ እንደዝና
ድንቄም ብልፅግና!::

እንትና ጀነራል እንትና ሚኒስትር
ሻለቃና ሻንበል እንትና ወታደር
በበዛበት ሀገር፡፡
የገበሬው መዝመት ይዋጥልናልወይ
የወጣቱስ መሞት ግፍ አይሆነንም ወይ፡፡

"ለዚክ ለዚክማ ከናቴጋ ባደርኩ" ሆነና ተረቱ
ሀገር ያምሳሉ እነ ብልጥግና እነ ስራ ፈቱ፡፡

ሰከን በል ወገኔ አስብ ተጠራጠር
በሆታ በልልታ አትድንም ሀገር፡፡
ያዝ በለው እያለ ከፊት ለፊት ብቻ
ከሗላ ጠላትህ እንዳይወጋህ ብቻ፡፡

ሰላም ለኢትዮጵያ
ሰላም ለሀገሬ

🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹


28/11/2013 ዓም

Читать полностью…

ከ ገጣሚያን ብዕር ♣♠

###ሰበር አትበሉን###

ዓይኗ ለታወረ መሪ ላጣች ሀገር
ምሁራኖች አልቀው በሴራ ባሻጠር
ደንቆሮዎች ቁመው ውስጧን ለመመዝበር
ግራ ለተጋባት ለዚች ሚስኪን ምድር
ምን ሊጠቅመን ሰበር?

አትበሉን በጌታ ቃሉ ያስፈራናል
ሰበር ስትነግሩን እኛ ተሰብረናል፡፡

ምንድነው ሰበሩ የታል አድስ ዜና
ተስፋን አለምላሚ ብስራት ለህሌና
የታል? የታል? አድስ ዜና?

እዚህ ጋ ማረክነው
እዚህ ጋ ገደልነው
ይሔን ያህል ሞተ ያን ያክል ወደመ
ለሚል የመረዶ ዶፍ ያሉባልታ ወሬ
ሰበር አትበሉን ለማይኖረው ፎሬ፡፡

ቃሉ ተቀይሮ ሰበርን ሁኗል አሉ
ወገኑን በማረድ ከተፈታ ውሉ
ሯንዳ ባደገች ከአለም ሀገር ሁሉ፡፡

አትገሩን ለኛ አትበሉን ሰበር
በጊዜያችን ታርደን እስክገባ ካፈር
ይቅርብን ብስራቱ መርዶውን መናገር፡፡

አድምጠኝ ወገኔ ስማኝ በጥሞና
በዚች በታመመች በደከመች ሀገር
አትደነቅ ጎበዝ ብርቅ አይደለም ሰበር
ወድህ ነው ወዳጄ የሞታችን ሚስጥር፡፡

ከላይ ነው ችግሩ ከስልጣኑ ማማ
በምሁራን ቦታ ተሰብስቦ ዶማ.....
ሀገር በቁፋሮ ይመራ መስሏቸው
ሀገር በገጀራ ይመራ መስሏቸው
ጨፍጭፈው ጨረሱን ደን መስለናቸው፡፡

እናማ ወገኔ
ሰው ያለ መክሊቱ መች ይሆናልና
እውቀቱን አሳዬው መስክ ጥመድና፡፡
ይወቅ ደረጃውን ሀገር ከሚያሸብር
ከብትና የሰው ልጅ መቼም አብሮ አያድር፡፡

መታሰቢያነቱ
በየሜዳው ለሚሞተው የሰው ልጅ በሙሉ ይሁን፡፡

ከደሳለኝ 18/08/2013

Читать полностью…

ከ ገጣሚያን ብዕር ♣♠

ከላይ
የእግዜር ፀሐይ



ቻይና ጫማ ፣ መሐል ኦነግ ሸኔ
ከፊት ብልጥግና ፣ ከኋላ ወያኔ
የቱ ጋር ሆኜ ነው ፣ ምቃጠለው እኔ?!

✍በላይ በቀለ ወያ

Читать полностью…

ከ ገጣሚያን ብዕር ♣♠

የወንዶች ሳሎን ..!
(በእውቀቱ ስዩም)

በቀደም ዳጎስ ያለ ደመወዝ ተቀብየ ፥ ነጠር ነጠር እያልሁ በሰፈራችን ሳልፍ፥ “ በውቄ ግባና ጸጉርህን ትንሽ ላሰማምርልህ " የሚል ድምጽ ሰማሁ፤ የብዙ ዘመን ጸጉር አስተካካየ ሳሚ ነው ፤ ሚካያ በሐይሉ ፤ ጸጉሬንም ቆጥረሀል “ ብላ የዘፈነችው ለሳሚ ይመስለኛል፤ ሳሚ ፈጣን ነው ፤ | ወሬ አያበዛም፤ በርግጥ ቶንዶሱ እንደ ጊንጥ ይቆነጥጣል፤ መቅሱንም በትርፍ ጊዜው የዳቦ ቆሎ እሚቆርጥበት ይመስለኛል ፤ ያም ሆኖ በሀያ ደቂቃ ውስጥ አሰማምሮ ይልከኛል፤ ሰባ ብር እከፍለዋለሁ፤ ሳሚ ብዙ አያወራም፤ደንበኞቹን አይሸነግልም፤

አንድ ቀን የሆነ ሰውየ ከመስተካከያው ወንበር ላይ ጉብ እንዳለ፥ “ እንዴት ነው? ጸጉሬ ላይ ሽበት ጣል ጣል እያለበት ነው አይደል?” ሲል ሳሚን ጠየቀው፥ ምላሽ ሳይሆን ማጽናኛ ነበር የሚጠብቀው። ሳሚ ፥ ከቦረንቅ ድንጋይ ተጠርቦ የወጣ የመሰለውን የሰውየውን ራስ በትካዜ እየተመለከተ፥ እንዲህ አለ፥ “ በሽበቱ ላይ ጥቁር ጣል ጣል ብሎበታል ማለት ይሻላል “ ሰውየው በጣም ተናደደ እና እዚያው ወንበሩ ላይ ተጨማሪ ሽበቶችን አቆጠቆጠ፤

የዚያን ቀን ሳሚ “ ግባና ላሰማምርልህ “ ሲለኝ ፥ በልቤ ለእድሌም አላሳየው” አልሁና በአፌ ። ለዛሬ አያስፈልገኝም” ብየው አለፍሁ፤ ከጥቂት ደቂቆች በሁዋላ ፤በከተማው ውስጥ የታወቀ የከፍተኛው ማህበረሰብ መዋቢያ የሆነ የወንዶች ሳሎን ውስጥ ራሴን አገኘሁት:: ሰራተኞች በሙሉ ሴቶች መሆናቸውን ሳይ ፥ ለምን “ የወንዶች ሳሎን” እንደተባለ ሊገባኝ አልቻለም፤ የሌላቸው ማሽን የለም፤ ኤክስሬይና ሲቲ ስካን ሁሉ አላቸው፤ አንዲቱ አስተካካይ ዙፋን እሚመስል ወንበር ላይ አስቀመጠችኝና ግምጃ የመሰለ መጎናጸፍያ አለበሰችኝ ፤ ከዝያ ወናፍ መሳይ አንስታ አየር ስትለቅብኝ ጠጉሮቼ እንደማለዳ አንሶላ ቀጥ ብለው ቆሙ! ለመጀመርያ ጊዜ መሀል ራሴን በመስታውት ማየት ቻልኩ፤ መሀል ራሴ ላይ ከቀሩት ጸጉሮች ይልቅ አፍንጫየ ውስጥ የተሰገሰጉ ጸጉሮች በቁጥር እንደሚልቁ ስመለከት አልቅስ አልቅስ አለኝ፤ ወደ ሀብት እና ወደ መላጣነት በተመሳሳይ ሰአት መቃረቤን ስገነዘብ፥ የዚህ አለም ከንቱነት ጎልቶ ታየኝ፤ ስመለጥ ምን እንደምመስል ራሴን አሰብኩት፤ አጤ ምኒልክ ያለ ሻሽ ! እንደ ፓስተር ዮኒ አስተክላለሁ ወይስ እንደ ሰይፉ ፋንታ ሁን በመላጣየ ጸንቸ እኖራለሁ? እያልሁ ሳስብ፥

“ ቀጣዩ ክፍል ሂድና ኤሚ ታጥብሀለች” አለችኝ ፤ የማስዋብ ሙከራ የምካሂድበኝ ልጅ:: ቀጣዩ ክፍል እንደገባሁ፥ አማረች የተባለች ሴትዮ ተቀብላ መከዳ ያለው መክተፍያ እሚመስል ጣውላ ላይ አንጋለለችኝ ፤ ፊቴ ላይ አንድ እፍኝ ዝልግልግ ነገር ደፈደፈችበት! ከዛ ፊቴን ለፒዛ እንደታጨ ሊጥ ደጋግማ ዳመጠችው:: በማስቀጠል፥ የውሀ እሩምታ ዘለግ አድርጋ ለቀቀችብኝ ! ግልጡን ለመናገር ያክል Waterboarding የተባለው የጓንታናሞ ቅጣት አካሄደችብኝ ! በመጨረሻ በመስታወት ፊት ቆምኩ፤ ተድበስብሶ የቆየው የግንባሬ መስመር አሁን በደንብ ፍጥጥ ብሎ ፥ የጉንዳን የቀለበት መንገድ ይመስላል ፤ ጸጉሬ ተቀባበለ የጃርት ወስፌ መስሎ ትኩረት ብቻ ሳይሆን እንደ ዲሸ ቻናል ይስባል! በመጨረሻ አንድ ሺህ ብር ቆጥረው ሲቀበሉኝ - ዊልስሚዝን መሰልህ “ ያሉኝን አልረሳውም:: ከሳሎንየው እንደወጣሁ ስልኬን አንስቸ ደወልኩ፤
ሄሎ ሳሚ! “ አቤት” “ ብዙ ወረፋ ከሌለበህ ብቅ ልበል?”

Читать полностью…

ከ ገጣሚያን ብዕር ♣♠

ግጥም ከገጣሚያን, [6/30/2022 11:16 AM]

አንቺ ጋር ስጣላ...
መንግስትን ተሳደብ ፣ ተሳደብ ይለኛል
ከሰደብኩት ደሞ ፣ አስሮ ይገርፈኛል
ከገረፈኝ ደሞ...
ለጊዜውም ቢሆን ፣ አንቺን ያስረሳኛል!
ከረሳሁሽ ደሞ...
አጣኋትኝ ብዬ ፣ አላስብም ቅንጣት
ተሳድቦ መገረፍ....
ሳይሻል አይቀርም፣ አፍቅሮ ከማጣት፡፡
Belay Bekele Weya
••••◉••••

Читать полностью…

ከ ገጣሚያን ብዕር ♣♠

""🤍ፍቅሬ ብለህ ጥራኝ🤍""

አወ አብርን አድገናል አፍርም ፍጭተናል
በአንድ ስሀን ብልተን ባንድ አልጋ አድርናል
የልጅነት ነገር ሆኖብን ነገሩ ባሌ ሚስቴ
ተባብለን ነበር እንዲት ደስ ይል ነበር አወይ ልጅነቴ

የስውነት ግዝፍት የእድሜም መርዘም
የአእምሮ መብስል ማስብ ማገናዘብም
ተጅምሮ ዛሬ አይናፍርነትም መጣ ተከትሎ
እንዱ ሲያለቅስ አንዱን ላያስቅ አባብሎ

ልክ እንደ ልጅነት እንደጥንቱ ግዜ
ድንገት ሳላስበው ነይ እህት አለም በምትለኝ ግዜ
ውስጤን ይከፍዋል ከእህትነት ይልቅ ፍቅርህ ከብዶታል
እንዳልተነፍስው እንዳልናገርው ልቤ ፍራተባ ይላል

እስኪ በል ንገርኝ ልክ እንደልኝነት
እንደ መልካሙ ጊዜ እንዲያ እንዳለፍንበት
ፍቅሬ ብለህ ጥራኝ ካልሆነልህ ሚስቴ ተንፍስልኝና እኔም እፎይ ልበል ይፍታ ምኞቴ

ፍቅሬ ብለህ ጥራኝ እንደ ልጅነቴ
ባሌ ብዬ ልጥራህ ይሳካ ምኞቴ

//ሂሩት//ሂራ✍️

Читать полностью…

ከ ገጣሚያን ብዕር ♣♠

ማን ቀባሽ ለሆዴ?

እቴ...
ምነው አንድ ልቤን ሳልፈቅድ ነጠቅሽኝ
መንፈሴን ምርኮ አርገሽ ቀልቤን አሳጣሽኝ!
ለምንድነው ነፍሴ አንቺን የተጠማች
ከጉያሽ መጠለል ማረፍ የናፈቀች?

እቴ...
በአባቶቻችን ወግ ባገራችን ባህል
ሰልፈኛን ነው እንጂ ምርኮን ማን ይወጋል?
ይልቅ...
ያንቺም ፈቃድ ይሁን ደስታየን አትንሽኝ
ልረፍ ከደረትሽ ትንፋሽሽ ያርሰኝ
ጣቶችሽ ይዳብሱኝ
ባይተዋር ከንፈሬን ከንፈርሽ ይላሰኝ
የጭንሽ ስር አለም ሴትነትሽ ይግዛኝ!!!

እቴ...
አንቺ ነሽ አለሜ ሌላ አለም የለኝም
ተቀበይኝ ልረፍ ፍቅር አያስጨክንም!!!

Читать полностью…

ከ ገጣሚያን ብዕር ♣♠

#ጅብ #የፃፈው #ግጥም

እንጦጦ ጫካ ውስጥ
የሰከረ ሰይጣን ፣ በልቶ የሰከረ
ብሶቱን ቁጭቱን
በሰው ልጆች ቋንቋ ፣ እያንጎራጎረ
አንድ ሰካራም ጅብ ፣ እንዲህ ሲል ነበረ።
።።
" ስማኝ የኢትዮጵያ ህዝብ ፣ ፍረድ ያገሬ ሰው
እኔ የሀገርህ ጅብ ፣ ከሰው የማልደርሰው
ጫካዬን መንጥረህ
ህንፃ ስትገነባ
ወደሌላ ጫካ ፣ ለመኖር ምፈልሰው
ስሜን ከሰው ተራ
ዝቅ አርገህ አትየው ፣ ክብሬን አትቀንሰው።
የቀን ጅቦች ብለህ
የቀን ሰዎችህን ፣ በኔ ስም አትጥራ
አዎን የቀን ጅብ ነኝ ፣
ብቻ መብላት ማላውቅ ፣ ላካፍል ምጣራ
ማየት የሚቻለኝ ፣ በብርሐንና በጨለማ ስፍራ
አዎን የቀን ጅብ ነኝ
የቀን ሰው ስላልሆንኩ ፣ ኖራለሁ ስኮራ
ክብሬን ዝቅ አድርገህ
ክብረ ቢስ ሰዎችን ፣ በኔ ስም አትጥራ ።
።።።።
ስማኝ የሀገሬ ሰው ፣ እራስህ ፍረደኝ
እንደውሻ ባልለምድ ፣ እንደበግ ባታርደኝ
በሬ ባልሆንልህ ፣ አስረህ ባትጠምደኝ
አፈንግጬ ብኖር ፣
ላንተ ባልገዛ ፣ ሰው በስሜ አትጥራ
ዝቅ አርገህ አትየኝ ፣ ከቀን ሰዎች ስፍራ
አዎ የቀን ጅብ ነኝ
በቀን ጅብነቴ ፣ ቀንበቀን ምኮራ።
።።።።
ስማኝ የሀገሬ ሰው ፣ ፍረድ የኢትዮጵያ ህዝብ
እኔ የሀገርህ ጅብ
እንደ ሰው ጨክኜ ፣ ጅቦችን አልበላም
በዘር ከፋፍዬ ፣ ጅቦች አላጣላም
የጅብ መሰቃያ ፣ እስርቤት አልከፍትም
ትውልዴን እንደ ሰው ፣ አላንኮታኩትም
ከጅቦች ቀምቼ
ለነገ ምበላው ፣ ሀብት አላካብትም
ልክ እንደ ቀን ሰዎች ፣ ሲያገኝ አይሰስትም
ጅብ መሆን ያኮራል
በጋራ ይበላል ፣ ምግብ አያሻግትም
ጮኾ አገኘሁ ይላል ፣ ጠርቶ ያካፍላል
እንዴት ከኔ እኩል
ክብረ ቢስ የቀን ሰው ፣ የቀን ጅብ ይባላል?
ሌላው ሌላው ቀርቶ
ይሞታታል እንጂ ፣ ጅብ ስኳር ይበላል?
ያውም ከነ ስኳር ፣ ፋብሪካ ቆርጥሞ
ደግሞ
ደግሞ
ደግሞ
ጅብ ጅብን ይገድላል ፣ በጅቦች ተሹሞ?
ጅብ ህንፃ ይሰራል
ጅብ ጅቦችን ያስራል?
እንዴት ለቀኑ ሰው ፣ ጅብ ስሜ ይጠራል?
።።።።
አዎ የቀን ጅብ ነኝ ፣
በቀን ጅብነቴ ፣ ቀን በቀን ምመካ
ሰው እንዳይበላኝ ነው
ከቀን ሰው ሸሽቼ ፣ የምኖረው ጫካ!!!

፨፨በላይ በቀለወያ፨፨

በቻናላችን ★የተለያዩ ግጥሞችን
★አስተማሪና አዝናኝ ታሪኮችን
★አጫጭር ልቦለዶችን
★ጠቃሚ ምክሮችን እና አባባሎችን
ያገኛሉ፡፡
ሀሳብ አስተያዬት ካለ @DesuT23 ያድርሱን፡፡
Join ☞ @Mamusha23
☞ @Mamusha23
☞ @Mamusha23

Читать полностью…

ከ ገጣሚያን ብዕር ♣♠

ለውጥ የለም አትበሉ!

(በወጣትና አንጋፋ ተወዳጇ ገጣሚ ህሌና ደሳለኝ!)

ለውጥ የለም አትበሉ...
ሆደ ጩቤ ይሉት~አፈ ቅቤ ነግሶ
በየቀኑ ሰበር~በየቀኑ ለቅሶ
መልካም ዜና ናፍቆት~ጆሮ ግንባር ላይ ነው
'ምንሰማው ይቀድማል~ባ'ይናችን ካየነው


ለ.ው.ጥ.ማ አ.ለ!
መገዳደል አለ
መፈናቀል አለ
ሴራ ማሴር አለ
መንገድ መዝጋት አለ
ዘረኝነት አለ
አድሎአዊነት አለ
ይህ ሁሉ ተደርጎም ማስተባበል አለ
ለዚህ ስራ ስኬት ~ለትግላችን ሲባል
አለም አጨብጭቦ~አክብሮ ሾመልን
ስለዚህ....
እንለወጣለን~ገና ከመሀሉ
ይሄ ሁሉ እያለ~ለውጥ አታጣጥሉ
ከዚህ በላይ የለም~ለውጥ የለም አትበሉ
የኋሊትም ቢሆን~ብዙ ለውጦች አሉ!!!

በቻናላችን ★የተለያዩ ግጥሞችን
★አስተማሪና አዝናኝ ታሪኮችን
★አጫጭር ልቦለዶችን
★ጠቃሚ ምክሮችን እና አባባሎችን
ያገኛሉ፡፡
ሀሳብ አስተያዬት ካለ @DesuT23 ያድርሱን፡፡
Join ☞ @Mamusha23
☞ @Mamusha23
☞ @Mamusha23

Читать полностью…

ከ ገጣሚያን ብዕር ♣♠

ፈገግ ብላችሁ ዋሉ

(በላይ በቀለ ወያ)

ዛሬ ቅዳሜ ነው!
.
.
ልባቸውን አይቶ
እግር የነሳቸው ፣ ቀርፋፋ ቀናቶች
ዘልዛላ ለሊቶች
እንደ ማቱ ሳላ ፣ እድሜ የሚያዘግሙ
ከሰኞ ተነስተው ፣ አርብ እስከሚያከትሙ
በስራ በትምህርት
በስብሰባ ብዛት
በሰበብ ባስባቡ ፣ ሲያቀጥኑኝ አክርረው
እንደ ጠቦት ቆዳ ፣ ሲሰቅሉኝ ወጥረው
በአማራሪ ቀኖች ፣ የማልማረረው
እራሴን ለማጥፋት
ብዙ ጊዜ አስቤ ፣ ሀሳብ ምቀይረው
ለቅዳሜ ስል ነው።
።።።
ዛሬ ቅዳሜ ነው
ይገለባል ቀሚስ ፣ ይወልቃል ሺህ ሱሪ
መኖሩን ያመልካል ፣ ኑሮን አማራሪ
ሁሉም አርበኛ ነው
ትንሽ ሞቅ ሲለው ፣ ይሆናል ፎካሪ
ጀግናን ልግደል ብሎ ፣ ይሸልላል ፈሪ
ነይና ላሳይሽ
ቅዳሜ ካልመጣሽ ፣ ለዘልዓለም ቅሪ።
።።።
ዛሬ ቅዳሜ ነው
በየ ፋርማሲ ቤት
የመፈንቅለ ፅንስ ፣ ኪኒን ይሸመታል
መንገድ ትራንስፖርት ፣ መንገዱን ይስታል
"መብራት ኀይል" ያለው
ዋና ሥራ አስኪያሃጅ ፣ አምፖል ይሸምታል
"ለሀገሩ ሟች ነው!"
ብለን ያሞገስነው ፣ ለአንዲት ሴት ይሞታል
ከሰባኪ አንደበት ፣ ስድብ ይመረታል።
።።።።
ነይና ላሳይሽ
ፌስቡክ ላይ ምታውቂው ፣ "ትዳሩን አክባሪ"
ታማኝ ባለንጀራ ፣ ለልጆቹ ኗሪ"
ብለን ምንቀናበት
ዋጋ ሲደራደር ፣ ከሴተኛ አዳሪ።
።።።
ነይና ላሳይሽ
ፌስቡክ ከምንለው ፣ ከአስመሳዮች መንደር
ፃድቅ ነኝ እያለ
ሌላን ለመተቸት ፣ የማይግደረደር
በብርሃን ፍጥነት ፣ ለሃጥያት ሲንደረደር
ነይና ላሳይሽ
የሚታዘቡንን ፣ ታዝበን እንደር።
።።።
ዛሬ ቅዳሜ ነው!
ነይና ላሳይሽ
ከበረዶ ሲጫር ፣ የማይጠፋ እሳት
ስንቱ ራሱን ፃድቅ
አድርጎ እንደኖረ ፣ በሌሎች መሳሳት
ቅዳሜ ብቻውን
የዓመት ደስታ ነው ፣ ሀዘንን ለመርሳት
ቅዳሜ ብቻውን
የተስፋ አቅም ነው ፣ ወድቆ ለመነሳት።
።።።።
ዛሬ ቅዳሜ ነው
ወይ ዘላለም ቅሪ ፣ ወይ ነይ ብለሽ እሺ
ስትመጪ ደግሞ
ቦርሳሽ ውስጥ ነጠላ ፣ መያዝ እንዳትረሺ።
ምክንያቱም ሲነጋ
እሁድ ነው ሰንበት ነው ፣ የቀኖች ዘልዛላ
ብቻውን ቢቆጥሩት ፣ አመት የሚሞላ
ቤተስኪያን እየሳምን ፣
ፎቶ እንድንነሳ ፣ አትርሺ ነጠላ።
።።።
ዛሬ ቅዳሜ ነው
ሲጋብዘው ያድራል ፣ ዳኛውን ተከሳሽ
ምስጢሩን ይዘራል ፣ የሰው ምስጢር አሳሽ
ሀጥያቱን ያሰጣል ፣ የሰው ሀጥያት ጠንሳሽ
ጌታ ፅድቄን ይንሳኝ! ፣ ፈጣሪ እኔን ይኝሳሽ
ከእርግማኔ አታልፊም! ፣
ቅዳሜ ከቀረሽ ፣ ወይም ደግሞ መጥተሽ ፣ ነጠላ ከረሳሽ
#ሼርርርርርርርርር

በቻናላችን ★የተለያዩ ግጥሞችን
★አስተማሪና አዝናኝ ታሪኮችን
★አጫጭር ልቦለዶችን
★ጠቃሚ ምክሮችን እና አባባሎችን
ያገኛሉ፡፡
ሀሳብ አስተያዬት ካለ @DesuT23 ያድርሱን፡፡
Join ☞ @Mamusha23
☞ @Mamusha23
☞ @Mamusha23

Читать полностью…

ከ ገጣሚያን ብዕር ♣♠

የኔና ያንቺ ህይወት
#############

ውዴ የኔ ፍቅር የኔ ሁለንተና
የልቤ ተሟጋች አርበኛ ሳተና
ፍቅር ብቻ ሳትሆኝ አንቺኮ እናት ነሽ
ከመውደድም በላይ ፍቅር የሞላብሽ

የኔ ሠላማዊ
የኔ ሁለንተና
የኔ ልዪ'ኮ ነሽ
የኔ......የኔ
የኔ......የኔ

በሚል ተራ ቃላት ሁሉም በሚገልፀው
የኔና ያንቺ ህይወት ደራሲም አይፅፈው
ገጣሚም አይገጥመው ሰዐሊም አይደፍረው

የኔና ያንቺ ህይወት...
ከመዋደድ በላይ ከመፋቀር በላይ
በፀብ የተሞላች ደስ የምትል ስቃይ

መጣላት መታረቅ
መታረቅ መጣላት
ደሞ ትንሽ ኩርፍ
ደሞ መዘጋጋት...
አሁንም መታረቅ
አሁንም መጣላት
ደሞ ሌላ ማኩረፍ
ሌላ መዘጋጋት....

እውነት እውነት ስልሽ...
የኔና ያንቺ ህይወት ሙሉ ፊልም ቢሆን
ከዚ ትእይንት ውጪ ሌላ ምንም አይኖር።
በቻናላችን ★የተለያዩ ግጥሞችን
★አስተማሪና አዝናኝ ታሪኮችን
★አጫጭር ልቦለዶችን
★ጠቃሚ ምክሮችን እና አባባሎችን
ያገኛሉ፡፡
ሀሳብ አስተያዬት ካለ @DesuT23 ያድርሱን፡፡
Join ☞ @Mamusha23
☞ @Mamusha23
☞ @Mamusha23

Читать полностью…

ከ ገጣሚያን ብዕር ♣♠

ንጋት ከወደድክ ምሽትን አትጥላ ሳይመሽ አይነጋምና..መድረስም ከፈለክ መራመድ አይረሳህ ...የህይወትን ፅጌሬዳነት ወደህ እሾኳን አትጥላ ውበቷ ነውና...መኖር ካሰኝህ ተስፍ ማረግ አይዘንጋህ ተስፍህ የህይወት ድልድይ ነውና...ማመንህን አትጥላት መታመንን ማግኛህ ናትና....ልግስናህን አጥብቀህ ውደዳት የፍርድህ ቀን ዋስህ ናትና....በምላሽ ውስጥ ያልሆነ መውደድን ማፍቀርን አርግ ፍፁም ሠው ያረግሃልና !!


#ከወደዱት #ሼር #ያድርጉ
••●◉Join us & share◉●••👇

➟➟➟➟➟➛➟➟➟➟➟➟
በቻናላችን ★የተለያዩ ግጥሞችን
★አስተማሪና አዝናኝ ታሪኮችን
★አጫጭር ልቦለዶችን
★ጠቃሚ ምክሮችን እና አባባሎችን
ያገኛሉ፡፡
ሀሳብ አስተያዬት ካለ @DesuT23 ያድርሱን፡፡
Join ☞ @Mamusha23
☞ @Mamusha23
☞ @Mamusha23

Читать полностью…

ከ ገጣሚያን ብዕር ♣♠

"ለመጀመር ትልቅ መሆን አይጠበቅብህም ነገር ግን ትልቅ ለመሆን መጀመር አለብህ ፡፡"
#ዚግ_ዚግላር
〰〰〰〰
"አንተ ጠንክረህ በዝምታ ስትሰራ ፣ ስኬትህ ጮኾ ይናገራል፡፡ "
#ፍራንክ_ኦሽን
〰〰〰〰
‹‹ እምነት ማለት ምንም እንኳን ሙሉው የሕይወት መሰላል ባይታይህም የመሠላሉን የመጀመሪያውን እርካብ መርገጥ ነው፡፡ ››
#ማርቲን_ሉተር
〰〰〰〰
"ሕይወት ልክ እንደ ካሜራ ነች ፡፡ የምትፈልገውና ጠቃሚ ነገር ላይ ስታተኩር ሌሎቹ የማያስፈልጉት እየደበዘዙ ይሄዳሉ ፡፡"
#ያልታወቀ
〰〰〰〰
" አንድ የደስታ በር ሲዘጋ፣ ሌላ የደስታ በር ይከፈታል። እኛ ግን አብዛኛውን ጊዜ ወደ ተዘጋው በር እንጂ ወደተከፈተልን አናይም፡፡"
#ሔለን_ኬለር

በቻናላችን ★የተለያዩ ግጥሞችን
★አስተማሪና አዝናኝ ታሪኮችን
★አጫጭር ልቦለዶችን
ያገኛሉ፡፡
ሀሳብ አስተያዬት ካለ @DesuT23 ያድርሱን፡፡
Join ☞ @Mamusha23
☞ @Mamusha23
☞ @Mamusha23

Читать полностью…

ከ ገጣሚያን ብዕር ♣♠

"ከዓለማችን ሕዝቦች መካከል አንድ ከመቶ የሚሆኑት ብቻ ያስባሉ፤
ሶስት ከመቶ የሚሆኑት የሚያስቡ ይመስላቸዋል፤ ዘጠና ስድስት ከመቶ የሚሆኑት ግን ከማሰብ ሞት ይቀላቸዋል!"
🗣 #ቦብ_ኘሮክተር

〰️〰️〰️〰️〰️

☑️ #ታዲያ #እኛ #የትኛው #ውስጥ #ነን?

የዚህን ጥያቄ መልስ ለማግኘት ውጤትህን ብቻ ማየት በቂ ነው።
ዛሬ እያገኘህ ያለኸው ውጤት የማትፈልገውና ከትላንትናው ከአምናውና ከካቻምናው ውጤትህ የማይሻል ከሆነ የማሰብ ችግር እንዳለብህ መጠርጠር ይኖርብሀል።
የማያስብ ሰው 70አመት ቢኖር እውነታው 70አመት አይኖርም ፤
አንዷን ዓመት ለሰባ ተደጋጋሚ ዓመታት ይኖራታል እንጂ!
ታዲያ ከሚያስቡት የአለማችን አንድ ፐርሰንት ውስጥ መግባት ሲችል(ሲያስብ) 70 የተለያዩ አመታትን መኖር ይችላል።

በርግጥ ሕይወት ምርጫ ስለሆነች "#ማሰብም ሆነ #ማሳበብ" የራሳችን ምርጫ ነው።
ስናስብ የድንቅ ሰው ህይወት እንኖራለን ስናሳብብ ደግሞ የተራ ሰው ህይወት እንኖራለን።

〰️〰️〰️
"የሰው ልጅ በአዕምሮው አስቦ በልቡ ካመነ ፣ በእጁ ይጨብጠዋል!"
🗣 ናፖልዮን ሂል
⁣ ⁣ ⁣ ⁣



#ከወደዱት #ሼር #ያድርጉ

Читать полностью…

ከ ገጣሚያን ብዕር ♣♠

.......♦️አሳና አሞራ♦️........

ከጊዜያት ብዛት ምንም ብንላመድ
ከትውውቅ ጥልቀተ ወዳጅነታችን
ምን እንኳ ቢገመድ በጠንካራ ገመድ
መላመዱ አይሎ ቢሆንም መዋደድ
በእኔና አንቺ መሀል
ትልቅ ገደል አለ የሚያስቀር ከመንገድ
ምክንያቱን በተረት ላስረዳሽ የኔ ውድ
ከእለታት አንድ ቀን
በሰማይ ሚኖረው በራሪው አሞራ
ምግብ ለመፈለግ ሲወርድ ከተራራ
ክንፉን እያማታ በተራ በተራ
ድንገት ሳያስበው በፍቅር ተያዘ
በውሃ ውስጥ ካለች ካንዷ አሳ ጋራ
ከዚያም በየቀኑ አሳዋን ለማየት
ቀዬውን ቀይሮ ወረደ ከመሬት
አሳዋም በፍቅሩ ተልክፋ ኖራለች
ድምፁን እንደሰማች
ከባህር ወደ የብስ ቶሎ ትዘላለች
ብሎም ከውሃ ውስጥ ለመውጣት ትሻለች
ግና ምን ያረጋል ተፈጥሮ ሆነና
ምንም ቢዋደዱ በመፋቀር ዳና
አንድ ሆነው አይኖሩም አይቻልምና
አሞራው ውሃ ውስጥ ለመግባት ቢሞክር
አሳዋም መሬት ላይ ለመኖር ብትጥር
ሁለቱም አንድ ላይ መሞታቸው አይቀር
በዚህ የተነሳም አልሆንልህ ሲለው
ማየት እንጂ መንካት እንደማይችል ሲያውቀው
ፍቅሩን በልቡ አርጎ በረረ አሞራው .......
አሳዋም ሰረገች ከጥልቅ ከባህሩ
እንደማይሆን ስታውቅ
ከአሞራ ጋራ አንድ ላይ መኖሩ
የእኔና ያንቺም ነገር እንዲሁ ነው በቃ
በእጄ ሚያስገባሽ የለኝም ጠበቃ
ኑሮሽ ከኑሮዬ ሀሳብሽ ካሳቤ
ለየቅል ሆነና ልብሽና ልቤ
እጅጉን አራቀሽ ከቅርብ ካጠገቤ
የኔን አለም ጥዬ ወዳንቺ እንዳልመጣ
ቀሊል እኮ አይደለም የኛማ ጋሬጣ
እንግዲያው እኔማ አንቺን ባልጠላሽም
ብዙ አትድከሚ እኔ አልሆንሽም
ምንም ብንላመድ ብንቀራረብም
አሳና አምራ ነን አንድ ላይ አኖርም !!!
🙏🙏🙏
ቻናላችንን ይቀላቀሉ

Читать полностью…

ከ ገጣሚያን ብዕር ♣♠

ሀይ እንዴት ናችሁ ውዶች?

ሠላምና ጤና ክብርና ምስጋና በያላችሁበት እንድደርስ ተመኘሁ፡፡
ኧረ... አሜን በሉ ከአሜንታ ብዙ ነገር ይቀራል ይባላል፡፡
እ.....የልጅ ምርቃት አይደርስም! ማነው ያለው ይሔ አሉባልታ ነው እንዳትሰሙ፡፡

እና ውሎ እንዴት ነበር? እርግጠኛ ነኝ አሪፍ ነበር ፡፡
ምን አገባክ እንዳትሉኝ ...... ለነገሩ ብትሉኝስ ባሁኑ ሰዓት ማን አለ በማያገባው የማይገባ እ.... እነንትናስ ባልተጠሩበት ገብተው አይደል የሚፈተፍቱት ምን ይደንቃል እ.... !

እኛ ሰፈር ውሎ ሀሪፍ ነበር፡፡ "ነይ በክረምት ...." የሚለውን ሙዚቃ ዘግተን "ፀሀዬ ደመቀች ..." በሚለው ሙዚቃ ፈታ እያልን ነበር፡፡ ደመቅ ሸብረቅ ያለ ውሎ ነው፡፡ ብቻ ደስ ይላል!

በአጋጣሚ የወጣችውን ፀሀይ እዬሞቅን ራዴወናችንን ከፈት ከማረጋችን ምን ብንሰማ ጥሩ ነው፡፡ ኧረ ለወሬም አይመች ጁንታውን ለመደምሰስ የሚል የሴት ድምፅ አንሰማም ይሔ ነገር ሱስ ሆነባቼው እንዴ? ነው አፋቼው ላይ ተነቀሱት ግራ ገባንኮ!

የጧት ወሬ የጠማውን ጆሯችንን አቁመን የተናጋሪዋን ማንነት ለማወቅ ስንሾካሾክ ከመሀላችን አንዱ የመዲናዋ ከንቲባ ነች አለ፡፡

ኦ...! እና ምን እያለች ነው አለ አዱ ደግሞ እስኪ ዝም ብለክ አዳምጥ አለ ፈጠር ብሎ የተቀመጠው ነገሩን ስንረዳው ዛሬ በመድናዋ ሰልፍ ነበር ፡፡

"አልሰሜን ግባ በለው አለ ያገሬ ሰው" እኛ መች ሰማን አለ የመጄመሪያው ልጅ ውሏችን በዚክ ነበር የተጀመረው፡፡

አይ አንች ሀገሬ መሠለፍ የማይታክተው ህዝብ ያለብሽ ድንቅ ምድር አንዳንዴ ግን ዝም ብዬ ሳስብ የመሠለፍ ባህላችንን ለምን በዩኔስኮ አናስመዘግበውም እ.... ፀሀዩ መንግስታችን ግን ቢያስብበት መልካም ነው ለሱም አንድ ስኬት ነው፡፡

ይሔን ከመወለዳችን በፊት እናቶቻችን ማህፀን እያለን ለምርመራ መሠለፍ የጀመርነውን ባህላችንን ከዛም ለወሊድ፣ለክትባት ፣ከኬጅ እስከ ስራ ፍለጋ እያልን አሁን ሰዎች ለራሳቸው አለማ ጠርተው እሚያሰለፉንን እና ሸማቾች የምንሰለፈውን ጨምሮ ባህልን የማስተላለፍ ሂደት ትኩረት ሰጥተን ብንሰራበት ለመንግስታችን ብልጥግና የሚያሰጥ ኩራት ነው፡


ድንቄም መሰለፍ !
እኔ ምለው ህዝባችን ግን እንዴ ዓይነ በሲር አይኑን ጨፍኖ በመሪ ከሚሰለፍ ለምን ዓይኑን ገልጦ ስላስመረረው የኑሮ ውድነት አይሰለፍም???

ግርም ይለኛል! "የራሷ አሮባት የሰው ታማስል" አሉ፡፡ ዘላለም አለም የሆዳሞች አድማቂ ሆኖ እስከመቼ? እ......
ሲወጡ መሰለፍ ሲወርዱ መሰለፍ ግራ ገባንኮ ጎበዝ ! ይሔ ነገር ደመወዛቼው ሰልፍ ነው እንዴ?

ኤጭ !
ግራ አታጋቡና ለሰላም ተሰለፉ
ለጠብም
ለሞትም ተሰለፉ አልበዛም እንዴ!

እስኪ ነገሩን ተወያዩበት እንዴኔ ግራ የገባው እንዳለ እርግጠኛ ነኝ ፡፡
እኔ ጥያቄዬ መልስ ባያገኝም ከታች ባሉት ስንኞች ተሰናበትኩ፡፡

ሰላማችን ይብዛ፡፡

አንተ የእግዜር አፈር አንተ የእግዜር መሬት
ልብህ ደንዳና ነው ተሸክሟል መአት፡፡
ሰልፈኛ ሲረግጥህ እሪ አትልም ወይ
ይህ ሁሉ መከራ ሲሆን ባንተ ለይ፡፡
ፍጥረቱ ታውሮ ሁኗል ሞገደኛ
አልቅስ ለፈጣሪ ለሰማዩ ዳኛ፡፡
የሰራህን ጌታ ለምነው አጥብቀህ
ለሰልፈኞቹ ሲል እሳት እንዳደርግህ፡፡

🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹


ከደሳለኝ 15/11/2013 ዓም

Читать полностью…

ከ ገጣሚያን ብዕር ♣♠

ዘር ሲቆጠር

ልጅ
አባት
አያት
ቅድመ አያት
ቅም አያት
ቅማንት
ሽማት
ምንዥላት
እንጅላት
ፍናጅ
ቅናጅ
እሰልጥ
አመልጥ
ማንትቤ
ደርባቴ
እያለ ይቀጥላል
😁😁😁🍁🍁

Читать полностью…

ከ ገጣሚያን ብዕር ♣♠

➲ አንተ ስትናፍቀኝ....


እንዲህ ያደርገኛል እንዲህ ይሰማኛል
ሳቅና ጫወታ ደስታ ........ይርቀኛል
ሞቋል ያልኩት ቤቴ ወና ይሆንብኛል
ውበቱ ጠፍቶብኝ ጭንቀት ይወረኛል
እውነቴን ነው ምልክ ትናፍቀኛለህ....
እንደ ዳግመ ትንሣኤ ያውም እንደ ምፃት
ነፍሴ አንተን ስትራብ ሰትጠብቅ በፅናት
ስለ ፍቅርህ የፆምኩ ......ትመጣለህ እያልኩ
አለሁኝ በተስፋ እስከ ዛሬ ድረስ አንተን እየጠበኩ
ለፍቅርህ ሞነኮስኩ ....... አለምን ተፀየፍኩ
አይታየኝ ሌላ አንተን......... ብቻ እያሰብኩ
በልቤ ገዳም ውስጥ ሰለ አንተ ፀለይኩ
አንዲያገናኘን ብዬ አምላክን ተማፀንኩ

እናልህ አለሜ.....

ከሰው ጋር ለመኖር ስስቅ ያዬ ሁሉ
ጎሎባት የማያውቅ ደስተኛ ናት አሉ
ምስጢር ያልተረዱ ያልገባቸው ውሉ
ማሽላም ሚስቀው ሲያር ነው መሀሉ

በናፍቆትህ ቅጣት በትዝታ ጅራፍ
በሃሳብ ጀልባ ላይ መአበሉን ሲቀዝፍ
አድማስ ተሻግሬ በምናቤ ሲከንፍ
በተስፋ ደከምኩኝ በናፍቆት ስንሳፈፍ።

ይሁን ግድ የለኝም ይሄንን ችላለው
ሁሉን ተቋቁሜ አንተን ጠብቃለዉ
ምን አማራጭ አለኝ እስረኛህ ሆኛለሁ
ፈርዶብኛል ፍቅርህ ሌላ ምን እላለሁ!!

™ መልካሙ ✍

━━━━━━✦✗✦━━━━━━━
ምርጫዎ ስለሆነ እናመሰግናለን 😘

Читать полностью…
Subscribe to a channel