የስካይ ስፖርቱ ኤክስፐርት ፖል ሜርሰን ስለ ሀሪ ኬን ክለባችንን መቀላቀል የሰጠው ሀሳብ...
🗣"እኔ አሁን ላይ የማንችስተር ዩናይትድ ማናጀሮች ብሆን ነገውኑ 100 ሚሊዮን ፓውንድ አውጥቼ ሀሪ ኬንን አስፈርመው ነበር።"
🗣"ለአንቶኒ 80 ሚልዮን ፓውንድ ያወጡት ዩናይትዶች ለኬን ይህንን ገንዘብ ቢያወጡ አንቶኒ በ10 አመት የሚያስቆጠራቸውን ጎሎች ኬን በአንድ ሲዝን ማስቆጠር ይችል ነበር።"
🗣"ሀሪ ኬን በቶተንሀም ቤት መጫወቱን ቀጥሎ ዋንጫ አያነሳም። በተመሳሳይም ማንችስተር ዩናይትድ እንደ ሀሪ ኬን አይነት አይምሬ አጥቂ የማይኖራቸው ከሆነ ለዋንጫ መወዳደር አይችሉም።"
@man_united_ethio_fans
@man_united_ethio_fans
ፎረስት በሊግ ካፕ ውድድር በሜዳ ባደረጋቸው ያለፉት አስር ጨዋታዎች ላይ የተሸነፈው በአንዱ ብቻ ነው በ7ቱ ድል አድርጎ በ2ቱ አቻ ተለያይቷል ።
@man_united_ethio_fans
@man_united_ethio_fans
ፎረስት በሁሉም ውድድር ከክለባችን ጋር ባደረገው ባለፉት 7 ጨዋታዎች ሽንፈት ገጥሞታል ።
ዛሬ የሚሸነፍ ከሆነ በተከታታይ ስምንት ጨዋታ ፎረስትን ያሸነፈው የመጀመሪያው ክለብ እንሆናል ።
@man_united_ethio_fans
@man_united_ethio_fans
ክለባችን በሊግ ካፕ ውድድር ከሜዳ ውጪ ባደረጋቸው ያለፉት 5 ጨዋታዎች በሙሉ አሸንፏል ።
በዚህም በተከታታይ ከሜዳ ውጪ ባደረጋቸው 5 ጨዋታዎች በማሸነፍ በውድድሩ ታሪክ ረጅሙ ሆኖ ተመዝግቧል የክለባችን 5 ድሎች ።
@man_united_ethio_fans
@man_united_ethio_fans
"ዩናይትድ የራሱ ክለብ እንደሆነ ይረዳል ብየ አስባለው!"
አሰልጣኝ ኤሪክ ቴንሃግ ድንቅ ብቃት ላይ ስለሚገኘው የክለባችን አጥቂ ማርከስ ራሽፎርድ ከክለቡ ጋር እያደረገ በሚገኘው አዲስ የውል ማራዘሚያ ንግግር ዙርያ ተከታዩን ብለዋል።
"አዎ እርግጥ ነው በክለቡ እና በተጨዋቹ መካከል የሚደረጉት ንግግሮች ሚስጥር ናቸው ። እንደማስበው እርሱ ማንችስተር ዩናይትድ የራሱ ክለብ እንደሆነ ይረዳል። ያ ቀዳሚው ነገር ነው በተጨማሪም እርሱ ባለው ከባቢ እና በዚህ ቡድን ምርጡን እግር ኳስ እየተጫወተ ይገኛል።"
@Man_united_ethio_fans
@Man_united_ethio_fans
ሌላኛው የእድል ፈጠራ ዘርፍ 'ወደ ሹትነት' የተቀየሩ ቁልፍ ኳሶችን ማቀበል ነው ።
በዚህ ረገድ ፍሬድ ፣ ጋርናቾ እና ጃደን ሳንቾ እስከ 6ኛ ያለውን ደረጃ ይዘው እናገኛቸዋለን ።
የብሩኖ ፈርናንዴዝ ፣ የክርስቲያን ኤሪክሰን እና የዲያጎ ዳሎት ግን የሚጠበቅ ነው ።
በዚህ ረገድ በምስሉ ላይ እንደምንመለከተው ማለሲያ ፣ ስኮት ማክቶሚናይ ፣ ማርሲያል እና አንቶኒ መሻሻል ያለባቸው ተጫዋቾች ናቸው ።
የሉክ ሻው ጥሩም መጥፎም ሊባል የማይችል ሲሆን መካከለኛ ነው። ቢሆንም ግን ከዚህ የበለጠ መሻሻል ይኖርበታል ።
@man_united_ethio_fans
@man_united_ethio_fans
💸ቢቲንግ ለምትመድቡ!
ብዙዎችን አሸናፉ እንዲሁም ትርፋማ እያደረገ የሚገኘው የ𝐀𝐌𝐔 𝐅𝐈𝐗𝐄𝐃 𝐁𝐄𝐓𝐓𝐈𝐍𝐆 𝐓𝐈𝐏𝐒 ቢቲንግ ቻናል እስካሁን አልተቀላቀሉም?ወይንስ አልሰሙም ይሆናል? ካልሰሙ እንጊዲያዎንስ እንንገሮ🗣
💸✅..በርካታ ጨዋታዎችን እየቀመረ ከተለያዩ Source በጥንቃቄ ትኬቶችን እየሰራ በየቀኑ የሚያቀርብላችሁ 𝐀𝐌𝐔 𝐅𝐈𝐗𝐄𝐃 𝐁𝐄𝐓𝐓𝐈𝐍𝐆 𝐓𝐈𝐏𝐒 በመቀላቀል ከኛ ጋር በአንድ ላይ በመሆን ያሸንፉ
👉ኑ አትርፉ! ቻናላችንን ይቀላቀሉ ስራችንን ይመልከቱ
ቴንሀግ አንቶኒ እያሳየው ስላለው አቋም ተከታዩን አስተያየት ሰጥቷል 🗣
"እሱ ሲጫወት ቡድኑም እያሸነፈ ነው። ያም ደግሞ እሱ ጥሩ በሆነ ሁኔታ እየተጫወተ እንዳለ መልእክት ይሰጥሀል።"
"ከዚህም በላይ ማረግ ይችላል። ለመሻሻል ብዙ ቦታ ይታየኛል። እናንተም እንደምታውቁት ተስፋ አረጋለሁ ይበልጥ በጨዋታ እንዲሳተፍ እና ቀጥተኛ እንዲሆን እንፈልጋለን።"
@man_united_ethio_fans
@man_united_ethio_fans
🗣| ውት ዌጎረስት
"በእግር ኳስ ህይወቴ ሁልጊዜም ቢሆን አንድ ነገርን አደርጋለሁ። ጎሎችን ማስቆጠር።"
"አሁን ሁለት ጨዋታ ሆኖኛል። ትልቅ የግብ እድሎችን እየሳትኩ ቢሆን ኖሮ እጨነቅ ነበር። ነገር ግን በእራሴ እተማመናለሁ። ማድረግ እችላለሁ። ከዛ በኋላ ደህና እሆናለሁ።
@man_united_ethio_fans
@man_united_ethio_fans
#የቀጠለ
🔴 የዕለቱ አልቢተሮች ⚪️
👉 የዛሬውን የኖቲንግሃምና ማንችስተር ዩናይትድ የካራባኦ ዋንጫ የመጀመሪያ ዙር ግማሽ ፍፃሜ ጨዋታ በዋና ዳኝነት የሚመራው እንግሊዛዊው አልቢትር ማይክል ኦሊቨር ሲሆን አልቢትሩ በዚህ የውድድር አመት ለመጀመሪያ ጊዜ በካራባኦ ዋንጫ ጨዋታ ላይ የሚዳኝ ይሆናል።
👉 ማይክል ኦሊቨር በዚህ የውድድር አመት ሁለት ጊዜ የዩናይትድን ጨዋታ የዳኘ ሲሆን አንደኛው ሊቨርፑልን በኦልድትራፎርድ ያሸነፍንበት ጨዋታ ሲሆን ሁለተኛው ደግሞበኢትሃድ በማንችስተር ሲቲ የተሸነፍንበት ጨዋታ ነው።
👉 ኦሊቨር ባለፈው የውድድር አመትም የካራባኦ ዋንጫ ግማሽ ፍፃሜን የዳኘ ሲሆን በወቅቱ ጨዋታው በአርሰናልና በሊቨርፑል መሃከል ነበር። ጨዋታውም 0 ለ 0 ሲጠናቀቅ አልቢትሩ በመጀመሪያው አጋማሽ ቀይ ካርድ ማሳየት ችለው ነበር።
✅ || ዋና አልቢትር
👉 ማይክል ኦሊቨር
✅ || ረዳት አልቢተሮች
👉 ስትዋርት በርት
👉 ሲሞን ቤኔት
✅ || አራተኛ ዳኛ
👉 ሲሞን ሁፐር
✅ || የቫር ዋና ዳኛ
👉 ፒተር ባንክስ
✅ || ረዳቱ
👉 ቲም ውድ
#ይቀጥላል
@Man_United_Ethio_Fans
@Man_United_Ethio_Fans
#የቀጠለ
⚪️የአሰልጣኞች አስተያየት⚪️
🗣 ኤሪክ ቴንሃግ 🎙
"ክለባችን ወደ ፎረስት አቅንቶ ከኖቲንግሃሞች ጋር ከተጨወተ ረጅም ጊዜ ተቆጥሯል። እናም እኔ እንደማስበው በዛ ያለውን ነገር እንወደዋለን ጥሩ ድባብም ይኖራል። ሁልጊዜም ጥሩ ድባብ ያለባቸው ጨዋታዎች ደስ ይላሉ ጥሩ ፉክክር ይኖራል።"
"አዎ ሁሉም ነገር መጨረሻው ዋንጫዎችን ማሸነፍ ነው። አዎ ጥሩ እድል አለን ነገር ግን ጨዋታ በጨዋታ ነው መሄድ ያለብን። አሁን ላይ ፎረስቶችን በሁለት ዙር እንገጥማለን። ስለዚህ ትኩረታችን በአሁኑ ጨዋታ ላይ ነው። ስለቀጣዩ አናስብም ምክንያቱም ያዘናጋናል ስለዚህ ሃሳባችን ሁሉ ነገ ላይ ነው።"
"ግልፅ ነው በጥሩ መንገድ እየሄድን ነው። ለጊዜው የተሳካ አይደለም ምክንያቱም ጥር ላይ ዋንጫዎችን አታሸንፍም ግን የካቲት ላይ ቢያንስ አንድ ማሸነፍ ትችላለህ። እናም እሱን አላማ አድርገን መጓዝ አለብን። ሁልጊዜም ዋንጫዎችን ለማግኘት የተሻለ ቦታ ላይ ሆኖ መገኘት ትልቅ ነገር ነው።"
#ይቀጥላል
@Man_United_Ethio_Fans
@Man_United_Ethio_Fans
#የቀጠለ
⚪️ የቡድን ዜና ማንችስተር ዩናይትድ
👉 በማንችስተር ዩናይትድ በኩል በዛሬው ጨዋታ ላይ አንቶኒ ማርሻልና ዲዮጎ ዳሎት የማይገኙ ሲሆን ሁለቱም ባለፉት ጨዋታዎች ጉዳት እንዳጋጠማቸውና በማገገም ላይ እንዳሉ ይታወቃል። በረጅም ጊዜ ጉዳት ከስብስቡ ውጪ የሆነው ዶኒ ቫንዴቢክም ለዛሬውም ጨዋታ አይደርስም።
👉 በተጨማሪም በግል ጉዳይ ምክንያት ለረጅም ጊዜ ከቡድኑ ርቆ የነበረው እንግሊዛዊው አጥቂ ጄደን ሳንቾ ምንም እንኳን ከቡድኑ ጋር ልምምድ ቢጀምርም በዛሬው ጨዋታም እንደማይገኝ አሰልጣኝ ኤሪክ ቴንሃግ በመግለጫቸው ተናግረዋል።
👉 በባለፈው ጨዋታ በሁለት ቢጫ ምክንያት ከጨዋታው ውጪ የነበረው ብራዚላዊው የተከላካይ አማካይ ካሴሚሮ ወደ ቋሚ አሰላለፍ እንደሚመለስ ሲጠበቅ በቻርልተኑ ጨዋታ ላይም በቅጣት ምክንያት ያልተሰለፈው ብሩኖ ፈርናንዴዝ ለዛሬው ጨዋታ የሚደርስ ይሆናል።
⚪️ በጨዋታው በዩናይትድ በኩል የማይሰለፉ ተጫዋቾች ⚪️
👉 አንቶኒ ማርሻል - በጉዳት❌
👉 ዲዮጎ ዳሎት - በጉዳት ❌
👉 ዶኒ ቫንዴቢክ - በጉዳት ❌
👉 ጄደን ሳንቾ - በግል ምክንያት ❌
#ይቀጥላል
@Man_United_Ethio_Fans
@Man_United_Ethio_Fans
ዋልያዎቹ ከቻን ውድድር በጊዜ ተሰናብተዋል!
የኢትዮጵያ ብሄራዊ ቡድን በአልጄሪያ እየተካሄደ በሚገኘው የቻን አፍሪካ ዋንጫ ከምድቡ ሳያልፍ ቀርቷል።ምሽቱን የመጨረሻ የምድብ ጨዋታውን ከሊብያ አቻው ጋር ያደረገው
ዋሊያው በጋቶች ፓኖም የፍፁም ቅጣት ምት ግብ ቀዳሚ መሆን ቢችሉም ሊብያዎች አከታትለው ባስቆጠሯቸው 3 ግቦች ሶስት ለ አንድ በሆነ ውጤት ተሸንፏል።
በሌላ የምድቡ ጨዋታ አልጀሪያ የሞዛምቢክ ብሄራዊ ቡድንን አንድ ለዜሮ በሆነው ውጤት ማሸነፍ ችላለች። በዚህም አልጀሪያ እና ሞዛምቢክ ከምድባቸው ማለፋቸውን ሲያረጋግጡ ሃገራችን ኢትዮጵያ እና ሊቢያ ደግሞ ወደ መጡበት ወደየ ሃገራቸው በቶሎ ተሸኝተዋል።
መልካም አዳር ዩናይትዳውያን!
የነገ ሰው ይበለን!
@Man_united_ethio_fans
@Man_united_ethio_fans
ራሺ በሊግ ካፕ ውድድር ባደረጋቸው ያለፉት 10 ጨዋታዎች ላይ ዘጠኝ ጎሎች አስቆጥሯል በዚህ ሲዝን ደሞ በሶስት ጨዋታዎች 4 ጎሎችን አስቆጥሯል ።
@man_united_ethio_fans
@man_united_ethio_fans
ክለባችን ከፎረስት ጋር ባደረጋቸው 3 የሊግ ካፕ ጨዋታዎችን በሙሉ ማሸነፍ ችሏል ።
በ1982/83 በሩብ ፍፃሜ 4ለ0 አሸንፈናል
በ1991/92 በፍፃሜ 1ለ0 አሸንፈናል
በ1998/99 በ4ተኛ ዙር 2ለ1 አሸንፈናል
@man_united_ethio_fans
@man_united_ethio_fans
ክለባችን 17 ጊዜ በሊግ ካፕ የግማሽ ፍፃሜ ጨዋታ ተጫውቷል ከክለባችን በላይ ብዙ ጊዜ ለግማሽ ፍፃሜ የደረሰው ሊቨርፑል 18 ጊዜ ነው ።
@man_united_ethio_fans
@man_united_ethio_fans
ቴንሃግ አክለው ፒኤስጂ በማርከስ ላይ ስላለው ፍላጎት 🗣
"ሁሉም የክለባችን ተጨዋቾች በሌሎች ክለቦች ፍላጎት እንዲጣልባቸው እመኛለው ምክንያቱም ይህ ማለት እኛ ጥሩ ስራን እየሰራን እንደሆነ የሚያሳይ ነው።"
@Man_united_ethio_fans
@Man_united_ethio_fans
መልካም ዜና እቃዎች በተወደዱበት በዚህ ወቅት
✅እናት ፋሽን ብራንድ የወንድች አልባሳት በፍሬ እንደዚሁም በጅምላ በማይታመን ዋጋ አቅርባለች!
♦️ሱሪዎች
♦️ቲቸርቶች
♦️ጃኬቶች
♦️ሸሚዞች
♦️old scohol ጃኬቶች
📩በ inbox @absebest አዋሩኝ
☎️ ደውሎ ለማገኘት 0932095047 📞 0932095047
የቴሌግራም👇👇👇 ቻናላችንን: @enateyewendochalbasat
👉 @enateyewendochalbasat
👉 @enateyewendochalbasat
ይቀላቀሉ! @enateyewendochalbasat
👉 @enateyewendochalbasat
👉 @enateyewendochalbasat
✅ አድራሻ ድሬዳዋ ፣ ቁ1 ደርዘን ተራ
ቁ2 አሽዋ የገበያ ማዕከል የቤት ቁጥር 331 በመላው ሀገሪቷም ባላቹበት እንልክላቹሀለን።
👉 @enateyewendochalbasat
👉 @enateyewendochalbasat ይቀላቀሉ @enateyewendochalbasat
#status
ማርከስ ራሽፎርድ ከአለም ዋንጫው መልስ በካራባኦ ካፕ ውድድር:
2 ጨዋታዎችን አደረገ
3 ግቦችን አስቆጠረ
@Man_united_ethio_fans
@Man_united_ethio_fans
የክለባችን ዋና የግብ እድል ፈጣሪዎች !
በዚህ የውድድር አመት ላይ የክለባችን ጥሩ የግብ እድሎችን መፍጠር የቻሉ አራት ተጫዋቾች በምስሉ ላይ የምትመለከቷቸው ናቸው ።
አንደኛ ላይ ያለው ብሩኖ ፈርናንዴዝ ሲሆን 64 ቁልፍ ኳሶች አቀብሎ 5 አሲስት አለው ።
ሁለተኛ ላይ ያለው ደግሞ ክርስቲያን ኤሪክሰን ሲሆን 41 ቁልፍ ኳሶች አቀብሎ 9 አሲስት አለው ።
ሶስተኛ ላይ ያለው ዲያጎ ዳሎት እንደዚሁ 30 ቁልፍ ኳሶችን አቀብሎ 1 አሲስት አድርጓል ።
አራተኛ ላይ የተቀመጠው ደግሞ ማርከስ ራሽፎርድ ነው 26 ቁልፍ ኳስ አቀብሎ 5 አሲስት አለው ።
ቁጥሩ ተጫዋቾቹ በሁሉም የውድድር መድረኮች ላይ ያስመዘገቧቸው ናቸው ።
@man_united_ethio_fans
@man_united_ethio_fans
ቫር ጥቅም ላይ ይውላል!
በባለፉት የካራባኦ ዋንጫ የሩብ ፍፃሜ ጨዋታዎች ጥቅም ያልዋለው ቫር በዛሬው ጨዋታ ግን ወደ አገልግሎቱ እንደሚመለስ ይፋ ሆኗል ።
@Man_united_ethio_fans
@Man_united_ethio_fans
🗣| ውት ዌጎረስት
"እዚህ መሆን አስደናቂ ነው። ድባቡ ፣ የደጋፊዎችም ሁኔታ። የጨዋታዎቹ ሁኔታ። በጣም የሚገርም ነው። እዚህ ከአንድ ሳምንት በላይ ቆይቻለሁ። እናም በጥሩ ሁኔታ እየሄደልኝ ነው።"
@man_united_ethio_fans
@man_united_ethio_fans
#የቀጠለ
🔴 የውጤት ግምቶች ⚪️
🎯 አብዛኛዎቹ አቋማሪ ድርጅቶች እንዲሁም ሚዲያዎች ጨዋታው በ ዩናይትድ አሸናፊነት ይጠናቀቃል በማለት የገመቱ ሲሆን ፤ እኔም የዩናይትድን ጥንካሬና የማሸነፍ ስነልቦና ከግምት በማስገባት ጨዋታው 2 ለ 1 በዩናይትድ አሸናፊነት ይጠናቀቃል ስል የግል ግምቴን አስቀምጫለሁ።
🔴 የግል የአሰላለፍ ግምት ⚪️
➛ዩናይትድ (4-2-3-1)= ዴህያ ፣ ቢሳካ ፣ ቫራን፣ ሊቻ ፣ ሾው ፣ ካሴሚሮ፣ ኤሪክሰን ፣ ብሩኖ ፣ ራሽፎርድ ፣ ዌግሆርስት፣ አንቶኒ
➛ ኖቲንግሃም (4-3-3)= ሄኔሲይ፣ ዊሊያምስ ፣ ዎራል፣ ቦሊ ፣ ቶፎሎ ፣ ያቴስ ፣ ማንጋላ ፣ ኮልባክ፣ ጆንሰን፣ ጊብስ ዋይት፣ ሊንጋርድ
🔴 የቀጥታ ስርጭት ⚪️
🎯 ጨዋታውን በልዩ ሁኔታ ልክ ከምሽቱ 5:00 ሲል ጀምሮ በቀጥታ ስርጭት በፅሁፍ ወደናንተ የምናደርስ ይሆናል። ከዚህ በተጨማሪም በስልክ እና በኮምፕዩተር ጨዋታውን ልትመለከቱ የምትችሉባቸውን አማራጮች ጨዋታ ከመጀመሩ አስቀድመን ወደ እናንተ የምናደርስ መሆኑን ከወዲሁ እንገልፃለን።
ድል ለታላቁ ክለባችን ለማንችስተር ዩናይትድ ይሁን ⚪️
@Man_United_Ethio_Fans
@Man_United_Ethio_Fans
#የቀጠለ
🔴የአሰልጣኞች አስተያየት🔴
🗣 ስቲቭ ኩፐር 🎙
" ተጨዋቾቼን በሙሉ የማጥቃት ሃይል ወደ ጨዋታው እንዲገቡ ነግሬአቸዋለሁ። ወደ ግማሽ ፍፃሜ መድረስ እውነት ለመናገር ቀላል አይደለም። ይህንን ውድድር እንደሌሎች ውድድሮች ተመልክተን ነው እየገፋንበት ነው። ማሸነፍ የምንፈልገው ትልቅ ውድድር ነው።"
"ለዚህ ጨዋታ ማገገሚያና መዘጋጃ በቂ ጊዜ ነበረን ግልፅ ነው። ሁለቱም ጨዋታዎች ጥሩ ጊዜ ላይ ሆነውናል። ግማሽ ፍፃሜ ነው። ያለንን ሁሉ መስጠት እንፈልጋለን። በሙሉ ሃይል ልናጠቃ እንፈልጋለን። ግልፅ ነው ዩናይትድ ነው። ደርሶ መልስ ጨዋታም ነው። እናም ጠንካራ ጨዋታ ይጠብቀናል ግን ሁሉ ነገራችንን እንሰጥበታለን።"
" ወሳኝ ውድድርና ዋንጫ ነው። ይሄንን እድል ዳግም እንደማናገኘው አስበን መታገል አለብን። የመጨረሻ የሆነ ያህል መታገል አለብን። እኔ ሁሌም በሲቲ ግራውንድ ላይ ጥሩ ስሜት አለኝ ልዩ ድባብ ይኖራል።ሲቲ ግራውንድ ሁሌም ልዩ ነው ይሄ አይቀየርም። እናም ያንን መጠቀም አለብን።"
#ይቀጥላል
@Man_United_Ethio_Fans
@Man_United_Ethio_Fans
#የቀጠለ
🔴 የቡድን ዜና ኖቲንግሃም
👉 በኖቲንግሃም በኩል በጉዳትና በሊጉ ህግ ምክንያት በውሰት ከማንችስተር ዩናይትድ ያስፈረሙትን የቋሚ በረኛቸውን ዲን ሄንደርሰንን ግልጋሎት የማያገኙ ሲሆን ምንም እንኳን ተጨዋቹ ጉዳት ቢያጋጥመውም ማንችስተር ዩናይትዶች ተጨዋቹ እንዲጫወት ፈቃድ አልሰጡም ነበር ።
👉 በተጨማሪም ኖቲንግሃሞች የታይዎ አዎንዪ እና የቼኩ ኩያቴን ግልጋሎት በጉዳት ምክንያት የማያገኙ ሲሆን በረጅም ጊዜ ጉዳት በቡድኑ የማይገኙት ኦማር ሪቻርድስ፣ ጁሊያን ባያንኮን፣ ኦማር ሪቻርድስ እና ሙሳ ኒያካቴን ግልጋሎት አያገኙም።
👉 በተጨማሪም እንግሊዛዊው ቁመተ መለሎ የተከላካይ አማካይ ሪያን ያቴስ በጉዳት ምክንያት በጨዋታው ላይ የመሰለፉ ነገር አጠራጣሪ ነው። ከዚህ የተለየ የጉዳት ዜና በኖቲንግሃም በኩል ያልተሰማ ሲሆን አሰልጣኙ ቋሚ አሰላለፋቸውን ይዘው እንደሚገቡ ይጠበቃል።
🔴 በጨዋታው ኖቲንግሃም በኩል የማይሰለፉ ተጫዋቾች 🔴
👉 ዲን ሄንደርሰን - በጉዳትና በሊጉ ህግ❌
👉 ታይዎ አዎንዪ - በጉዳት ❌
👉 ጁሊያን ባያንኮን - በጉዳት ❌
👉 ቼኩ ኩያቴ - በጉዳት ❌
👉 ኦማር ሪቻርድስ - በጉዳት ❌
👉ሪያን ያቴስ - አጠራጣሪ ⁉️
#ይቀጥላል
@Man_United_Ethio_Fans
@Man_United_Ethio_Fans
አሸናፊው በአሰልጣኞች Master mind በፊትም አሁንም የሚወሰንበት ሀያሉ ፍልሚያ ነገ ይጠብቀናል እስከ እዛው ደህና እደሩልን ዩናይትዳዊያን።
@man_united_ethio_fans
@man_united_ethio_fans
የማንችስተር ዩናይትድ የአካዳሚ አጥቂ አሚር ኢብራጊሞቭ ከማን ሲቲ አቻው ጋር አድርጎት በነበረው ጨዋታ ያስቆጠራትን ድንቅ ቅጣት ምት በቪደዮ ቻናላችን ተጋበዙ 🔥
👉@man_united_ethio_fans_video
👉@man_united_ethio_fans_video