meazahaymanot | Unsorted

Telegram-канал meazahaymanot - መዓዛ ሃይማኖት በጎ አድራጎትና ጉዞ ማህበር

3925

"ውድስት አንቲ በአፈ ነቢያት ወስብሕት በሐዋርያት አክሊለ በረከቱ ለያዕቆብ ወትምክህተ ቤቱ ለእስራኤል፡፡" "በነቢያት በሐዋርያት አንደበት የተመሰገንሽ የያዕቆብ የበረከቱ ዘውድ የእስራኤል ወገን መመኪያ አንቺ ነሽ"                  መጽሐፈ ሰዓታት የፌስቡክ ፔጃችን www.fb.me/meazhaimanot ይቀላቀሉን

Subscribe to a channel

መዓዛ ሃይማኖት በጎ አድራጎትና ጉዞ ማህበር

ከአሁን ጀምሮ እንደተለመደው ለቻናላችን ያላችሁን ሀሳብ አስተያየት ማቅረብ ትችላላችሁ። ቢኖሩ፣ ቢስተካከሉ የምትሏቸው ጉዳዮች ላይ አተኩራችሁ ስማችሁንና ከየት ሀገር እንደሆናችሁ እየገለጻችሁ በድምጽ ሆነ በጽሑፍ ላኩልን። ቤተሰቦቻችን የት የት እንዳሉም እንድናውቅና እንድንተዋወቅ ይረዳናል     ላይ @misiwani_Bot እንጠብቃችኋለን

ሐሳብ አስተያየታቸውን ጻፉልን

Читать полностью…

መዓዛ ሃይማኖት በጎ አድራጎትና ጉዞ ማህበር

#ትኩረትለላሊበላ
ላሊበላ እጅግ አስደናቂ ኪነ-ህንፃ፣ የአባቶቻችን የታሪክ አሻራ፣ የቤተክርስቲያን ሰማያዊ ጥበብ መገለጫ፣ ብሎም የሀገር ቅርስ የሆነን የላሊበላ ውቅር አብያተ ክርስቲያናትን ከጥፋት መታደግ የሁላችንም ሀላፊነት ነው።

#ላሊበላንእንታደግ
#ትኩረትለላሊበላ
#SaveLalibela
#unescoworldheritage

Читать полностью…

መዓዛ ሃይማኖት በጎ አድራጎትና ጉዞ ማህበር

ስንክሳር ዘወርሃ ህዳር አንድ (፩)
@meazahaymanot

Читать полностью…

መዓዛ ሃይማኖት በጎ አድራጎትና ጉዞ ማህበር

   ማኅደረ ጥያቄ

1. የኢየሱስ ሥጋ ለምኖ የቀበረው ማነው

ሀ. አማሌቅ   ለ. አካዝያስ  ሐ.የአርማትያሱ ዮሴፍ  መ. ስምዖን ጴጥሮስ

2. በአስቆሮቱ ይሁዳ ቦታ የተተካው ሐዋርያ ማነው

ሀ. እስጢፋኖስ

ለ. ማቲያስ

ሐ. ማቴዎስ

መ በርስያን

3. ንጉሥ ዳዊት በእሥራኤል ለስንት አመት ነገሰ

ሀ. 15      ለ. 7       ሐ 38      መ. 40

4. አማኑኤል ማለት ምን ማለት ነው

ሀ. እግዚአብሔር ፈራጅ ነው

ለ. እግዚአብሔር ሁሉን ቻይ

ሐ. እግዚአብሔር ኃይላችን ነው

መ. እግዚአብሔር ከእኛ ጋር ሆነ ማለት ነው

5. በዛሬ ቀን የሚከበሩ የቅዱሳን በዓላትን ጻፉ

መልሱን እስከ ማታ 3:00 ሰዓት በ @Asitmeherobot አድርሱን


        #መልካም_እድል

Читать полностью…

መዓዛ ሃይማኖት በጎ አድራጎትና ጉዞ ማህበር

   ማኅደረ ጥያቄ

1. የኢየሱስ ሥጋ ለምኖ የቀበረው ማነው

ሀ. አማሌቅ   ለ. አካዝያስ  ሐ.የአርማትያሱ ዮሴፍ  መ. ስምዖን ጴጥሮስ

2. በአስቆሮቱ ይሁዳ ቦታ የተተካው ሐዋርያ ማነው

ሀ. እስጢፋኖስ

ለ. ማቲያስ

ሐ. ማቴዎስ

መ በርስያን

3. ንጉሥ ዳዊት በእሥራኤል ለስንት አመት ነገሰ

ሀ. 15      ለ. 7       ሐ 38      መ. 40

4. አማኑኤል ማለት ምን ማለት ነው

ሀ. እግዚአብሔር ፈራጅ ነው

ለ. እግዚአብሔር ሁሉን ቻይ

ሐ. እግዚአብሔር ኃይላችን ነው

መ. እግዚአብሔር ከእኛ ጋር ሆነ ማለት ነው

5. በዛሬ ቀን የሚከበሩ የቅዱሳን በዓላትን ጻፉ

መልሱን እስከ ነገ ማታ 3:00 ሰዓት በ @Asitmeherobot አድርሱን


        #መልካም_እድል

Читать полностью…

መዓዛ ሃይማኖት በጎ አድራጎትና ጉዞ ማህበር

ተዓምር ዘአቡነ እጨጌ ዘዮሐንስ ዘጸገሮ
@meazahaymanot

Читать полностью…

መዓዛ ሃይማኖት በጎ አድራጎትና ጉዞ ማህበር

ማኅደረ ጥያቄ

#መልስ

1. መ


ናትናኤልም፦ ከወዴት ታውቀኛለህ? አለው። ኢየሱስም መልሶ፦ ፊልጶስ ሳይጠራህ፥ ከበለስ በታች ሳለህ፥ አየሁህ አለው።

ዮሐንስ ወንጌል 1÷49

2. ሀ

አባትና እናትም አልነበራትምና የአጎቱ ልጅ ሀደሳ የተባለችውን አስቴርን አሳድጎ ነበር፤ ቆንጆይቱም የተዋበችና መልከ መልካም ነበረች፤ አባትዋና እናትዋም ከሞቱ በኋላ መርዶክዮስ እንደ ልጁ አድርጎ ወስዶአት ነበር።

መጽሐፈ አስቴር 2÷7

3. ሐ


፤ እንዲህም ሆነ፤ ከዚህ ነገር በኋላ የእግዚአብሔር ባሪያ የነዌ ልጅ ኢያሱ ዕድሜው መቶ አሥር ዓመት ሲሆነው ሞተ።

መጽሐፈ ኢያሱ ወልደነዌ 24÷29

4. ለ

፤ ከጎፈር እንጨት መርከብን ለአንተ ሥራ፤ በመርከቢቱም ጉርጆችን አድርግ፥ በውስጥም በውጭም በቅጥራን ለቅልቃት።

ኦሪት ዘፍጥረት 6÷14

5. ጥቅምት 27 ቀን የሚከበሩ ዓመታዊ የቅዱሳን በዓላት

1.ጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ

2.ቅዱስ መቃርስ ብጹዓዊ

3.አቡነ መብዓ ጽዮን ጻድቅ

4.አባ ጽጌ ድንግል ዘወለቃ  


ወርኀዊ በዓላት

1.ቅዱስ መቃርስ (የመነኮሳት ሁሉ አለቃ)

2.ቅዱስ ያዕቆብ ዘግሙድ

3.ቅዱስ ገላውዴዎስ ሰማዕት (ንጉሠ ኢትዮዽያ)

4.ቅዱስ ቢፋሞን ጻድቅና ሰማዕት

5.ማር ቅዱስ ፊቅጦር ሰማዕት

ጥቅምት 28 ቀን የሚከበሩ ዓመታዊ የቅዱሳን በዓላት
1.አባ ይምዓታ ጻድቅ (ከተስዓቱ ቅዱሳን)

2.ቅዱሳን መርትያኖስ ወመርቆሬዎስ (ሰማዕታት)

3.አባታችን ያፌት (የኖኅ ልጅ)


📌 ወርኀዊ በዓላት
1.አማኑኤል ቸር አምላካችን

2.ቅዱሳን አበው (አብርሃም: ይስሐቅና ያዕቆብ)

3.ቅዱስ እንድራኒቆስና ሚስቱ ቅድስት አትናስያ

4.ቅድስት ዓመተ ክክርስቶስ

5.ቅዱስ ቴዎድሮስ ሮማዊ (ሰማዕት)

6.ቅዱስ አባዲርና ቅድስት ኢራኢ

የተሣተፉ

1. yodit 3/5

2. መቅደሰ ማርያም 5/5

3.እግዚአብሔር እረኛዬ ነው 3/5

4. ታሪክአየሁ 5/5

5. ያሬድ 4/5

6. kal 3/5

7. መላኩ 3/5

8. ሰምሀል 2/5

ለተሣተፉት ቃለ ሕይወትን ያሰማልን መንግሥተ ሰማያትን ያውርስልን

Читать полностью…

መዓዛ ሃይማኖት በጎ አድራጎትና ጉዞ ማህበር

ስንክሳር ዘወርሃ ጥቅምት ሃያ ስምንት(፳፰)
/channel/meazahaymanot

Читать полностью…

መዓዛ ሃይማኖት በጎ አድራጎትና ጉዞ ማህበር

🔴 #አዲስ_ዝማሬ "መድኃኔዓለም"

Читать полностью…

መዓዛ ሃይማኖት በጎ አድራጎትና ጉዞ ማህበር

እንኳን ለአባታችን አምላካችን መድኃኔዓለም እና ቅዱስ አባ መብዓ ጽዮን ዓመታዊ በዓል በሰላም አደረሰን

Читать полностью…

መዓዛ ሃይማኖት በጎ አድራጎትና ጉዞ ማህበር

እግዚአብሔርን ተስፋ የሚያደርጉ ግን እነርሱ ምድርን ይወርሳሉ››መዝ 37፡9

ልጄ ሆይ ሁል ጊዜም እግዚአብሔርን ተስፋ አድርገው እምነትህ ቢደክም ፍቅር ሲቀዘቅዝ ብታይስ እንኳ ተስፋ ቆርጠህ ወደ ኋላ አትመለስ፡፡ ነገ መለወጥን ተስፋ አድርግ እንጂ ክርስትና ከሥጋና ደም ጋር የምትታገልበት ሕይወት ሳይሆን ትግሉ ከጨለማ ገዥዎች ከክፋት መንፈሳውያን ሠራዊት ጋር መሆኑን አትዘንጋ፡፡ በሕይወትህ ውስጥ ጠላት ለማጥፋት የሚፈልገው ታላቅ የልብ ሻማ ተስፋ ነው፡፡ የልብህን ተስፋ አጥብቀህ ጠብቅ ተስፋ ካለ ሁሉን መልሰህ ማግኘት ትችላለህ፡፡ ተስፋ ከሌለህ ግን ልታምንም ልታፈቅርም ይከብዳል፡፡ ተስፋ የማታደርግ ከሆነ እንዴት ታምናለህ? ታፈቅራለህስ? ስለዚህ ልጄ ሆይ ዛሬን ብትወድቅ ተስፋ አትቁረጥ ተነስ እንጂ ዛሬ እንደ ቃሉ በፍቅር መኖር ቢያቅትህ መፍትሔው ተስፋ መቁረጥ አይደለም፡፡ በእግዚአብሔር ተስፋ ማድረግ እንጂ ዛሬ በአገልግሎትህ ብትደክም ተስፋ ቆርጠህ ከቤቱ ከቶ አትውጣ፡፡ ከሐዋርያት ጋር ሆነህ ጌታ ሆይ ወደ ማን እሄዳለሁ? አንተ የዘላለም ሕይወት ቃል አለህ በለው፡፡ ዮሐ 6፡68 ከዳዊት ጋርም ሆነህ አሁንስ ተስፋዬ ማነው አንተ እግዚአብሔር አይደለህምን በለው መዝ 38፡7 ፍሬ ለማፍራትም በእርሱ ተስፋ አድርግ፡፡ በተስፋ ለምትጠባበቀው ለምትሻውም ነፍስ ጌታ ቸር የሚራራም ነውና፡፡ ልጄ ሆይ አዳም ከገነት ቢሰደድ ይዞ የወጣው ሌላ አይደለም ተስፋን ነው፡፡ በጌታ ቀኝ የተሰቀለው ወንበዴ እድሜ ልኩን በክፉ ስራ ቢኖርም ተስፋን ግን አልጣለም በመጨረሻ ትንፋሽ ላይ ሳለ ወደ ሕይወት ያደረሰችው ይህች ተስፋ አለመቁረጥ ናት፡፡ በግራ ያለውማ ተስፋ በመቁረጡ የእምነትና የፍቅር ሻማዎቹ ሊበሩለት አልቻሉም፡፡ እንግዲህ ልጄ ሆይ በጊዜውም ያለጊዜውም እርሱን ተስፋ አድርገህ ኑር፡፡ በፍጹም ተስፋ አትቁረጥ፡፡

እምነት፣ ተስፋ እና ፍቅር የሞላበት ህይወት እግዚአብሔር ለሁላችንም ይስጠን። አሜን ።

Читать полностью…

መዓዛ ሃይማኖት በጎ አድራጎትና ጉዞ ማህበር

ምን እንጠይቅሎ መርሐግብር

" አስተውል፤ አባትህን ጠይቅ፥ ያስታውቅህማል፤ ሽማግሌዎችህን ጠይቅ፥ ይነግሩህማል። "
ኦ. ዘዳ 32÷ 7

እንኳን ደስ ያለን ምን እንጠይቅሎ ??? የተሰኘው ሳምንታዊ መርሐ ግብራችን  በእናንተ ጸሎት በእግዚአብሔር ቸርነት እነኾ ይቀጥላል

በመሆኑም ከዚህ በፊት በቴሌ ግራም ቻናላችን እንደምናደርገው በጥያቄዎቻችሁ ቅደም ተከተል መሠረት በየ ሳምንቱ ምላሽ የምንሰጥበት ሲሆን ግላዊ ጥያቄዎችንና ሰፊ ማብራሪያ የሚያስፈልጋቸውን ጥያቄዎች በኦዲዮ ቀድተን የምንልክላቹ መሆኑን ለማስታወስ እንወዳለን ::
ጥያቄዎቻችሁን ከታች ባለው የቴሌ ግራም አድራሻ    መላክ የምችሉ መሆኑን እንጠቁማለን "

@misiwani_Bot

@misiwani_Bot

 
    ይጠይቁ ይመለስልዎታል
    ይጠይቁ  ይመለስልዎታል

Читать полностью…

መዓዛ ሃይማኖት በጎ አድራጎትና ጉዞ ማህበር

ተኛት በፊት የሚጸለይ ጸሎት

መዝሙር 142/143

አቤቱ፥ ጸሎቴን ስማ፤ በእውነትህ ልመናዬን አድምጥ፥ በጽድቅህም መልስልኝ።
ሕያው ሁሉ በፊትህ ጻድቅ አይደለምና ከባሪያህ ጋር ወደ ፍርድ አትግባ።
ጠላትህ ነፍሴን አሳድዶአታል፥ ሕይወቴንም በምድር ውስጥ አጐስቍሎአታል፤ ቀድሞ እንደ ሞተ ሰው በጨለማ አኑሮኛል።
ነፍሴ በውስጤ አለቀችብኝ፥ ልቤም በውስጤ ደነገጠብኝ።
የቀድሞውን ዘመን አሰብሁ፥ ሥራህንም ሁሉ አሰላሰልሁ፤ የእጅህንም ሥራ ተመለከትሁ።
እጆቼን ወደ አንተ ዘረጋሁ፤ ነፍሴም እንደ ምድረ በዳ አንተን ተጠማች።
አቤቱ፥ ፈጥነህ ስማኝ፤ ነፍሴ አልቃለች፤ ፊትህን ከኔ አትመልስ፥ ወደ ጕድጓድም እንደሚወርዱ አልሁን።
አንተን ታምኛለሁና በማለዳ ምሕረትህን አሰማኝ፤ አቤቱ፥ ነፍሴን ወደ አንተ አንሥቻለሁና የምሄድበትን መንገድ አስታውቀኝ።
አቤቱ፥ ወደ አንተ ተማፅኛለሁና ከጠላቶቼ አድነኝ።
አንተ አምላኬ ነህና ፈቃድህን ለማድረግ አስተምረኝ፤ ቅዱስ መንፈስህም በጽድቅ ምድር ይምራኝ።
አቤቱ፥ ስለ ስምህ ሕያው አድርገኝ፤ በጽድቅህም ነፍሴን ከመከራዋ አውጣት።
በምሕረትህ ጠላቶቼን ደምስሳቸው፥ እኔ ባሪያህ ነኝና ነፍሴን የሚያስጨንቁአትን ሁሉ አጥፋቸው።

ለአብ ለወልድ ወመንፈስ ቅዱስም ምስጋና ይሁን፤ መቼም መች ለዘላለሙ ይሁን።
• • •
ሃሌ ሉያ ምስጋና ለእግዚአብሔር፤ ሃሌ ሉያ በየጊዜው፣ በየሰዓቱ ምስጋና ለአምላካችን ይሁን።
እነሆ መዓልቱ አልፎ፤ ሌሊቱ ተተካ፤ ስለዚህ ቅዱስ ሆይ፤አመሰግንሃለሁ። ወደ አንተ እማልዳለሁ፤ የምትመጣውን ሌሊት ያለፍርሃት እንዳሳልፋት ጠብቀኝ።

አባቴ እግዚአብሔር የማይታዩትን ጠላቶቼን ምክር ታውቃለህ፤ የሥጋዬም ደካማነት በአንተ በፈጣሪዬ ዘንድ የታወቀ ነው፤ ስለዚህ በቸርነትህ በክንፍህ ጥላ ሸፍነህ እንድትጠብቅኝ፤ ነፍሴን በእጅህ አደራ እሰጣለሁ። ለመሞት እንዳልተኛ ዓይነ ልቦናዬን በመለኮታዊ ቃልህ አብራልኝ። ከጨለማው እንቅልፍ አንቅተህ፤ አንተን ለማመስገን አዘጋጀኝ። አንተ ሰውን የምትወድ ቸር ነህና።
ምንም ጊዜም ቅድስት ድንግል፤ ንጽሕት የሆንሽ የክርስቶስ እናቱ ድንግል ማርያም ሆይ፤ ነፍሴን ያጸናት ዘንድ፤ ጸሎትሽን ወደ ልጅሽ አቅርቢልኝ።
ጌታዬ እግዚአብሔር ሆይ፤ በመዓልት ከሚወረወር፤ በሌሊትም ከሚጣል ክፉ ሥራ ሁሉ ሠውረኝ። አቤቱ ጌታዬ፤ በዚች ዕለት በቃልም ቢሆን፤ በማሰብም ቢሆን፤ በሥራም ቢሁን፤ በግልጥና በሥውር የበደልሁትን ሁሉ ይቅር በለኝ፤ በምሕረትህም አስተሥርይልኝ። ስለ ቅዱስ ስምህ ብለህ ሕይወት ያለው እንቅልፍ ስጠኝ። ከክፉ ነገር የሚጠብቅኝን የሰላም መልአክ ላክልኝ፤ ጸጋህንና ምሕረትህን አብዛልኝ። ላንድ ልጅህ፤ ለጌታችን፤ ለአምላካችን፤ ለመድኃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ፤ ማሕያዊ (አዳኝ) ለሚሆን ለመንፈስ ቅዱስ ሁል ጊዜ ምስጋና አቀርባለሁ፤ አሜን።

Читать полностью…

መዓዛ ሃይማኖት በጎ አድራጎትና ጉዞ ማህበር

ማኅደረ ጥያቄ

#መልስ

1. ለ
ያዕቆብም ያንን ስፍራ ቤቴል ብሎ ጠራው፤ አስቀድሞ ግን የዚያች ከተማ ስም ሎዛ ነበረ።

ኦሪት ዘፍጥረት 28÷19

2. መ

በገሊላ ባሕር አጠገብ ሲመላለስም ሁለት ወንድማማች ጴጥሮስ የሚሉትን ስምዖንን ወንድሙንም እንድርያስን መረባቸውን ወደ ባሕር ሲጥሉ አየ፥ ዓሣ አጥማጆች ነበሩና።

ማቴዎስ ወንጌል 4÷18

3. ሀ

ይስሐቅም አርባ ዓመት ሲሆነው ርብቃን አገባ፤ እርስዋም በሁለት ወንዞች መካከል ያለ የሶርያዊው የባቱኤል ልጅና የሶርያዊው የላባ እኅት ናት።

ኦሪት ዘፍጥረት 25÷20

4. መ

የምድያም ነጋዶችም አለፉ፤ እነርሱም ዮሴፍን አንሥተው ከጕድጓድ አወጡት፤ ለእስማኤላውያንም ዮሴፍን በሀያ ብር ሸጡት፤ እነርሱም ዮሴፍን ወደ ግብፅ ወሰዱት።
ኦሪት ዘፍጥረት 37÷28

5. መልስ የለም (ቦነስ)

ዖፅ በሚባል አገር ስሙ ኢዮብ የተባለ አንድ ሰው ነበረ፤ ያም ሰው ፍጹምና ቅን፥ እግዚአብሔርንም የሚፈራ፥ ከክፋትም የራቀ ነበረ።

መጽሐፈ ኢዮብ 1÷1


የተሣተፉ

1. ፋንቱ 4/5

2. ዮሐንስ 4/5

3. መቅደሰ ማርያም 5/5

4. ኢየሩሳሌም 5/5

5. ናትናኤል 3/5

6. እግዚአብሔር እረኛዬ ነው 5/5

7. ያሬድ 5/5

8. yodit 4/5

9. Dagi 4/5

10 Meron 4/5

11. Tig  5/5

12. ሂሩት 4/5

13. ሰምሃል 4/5

14. sen  4/5

15. ታሪክአየሁ 4/5

16. ዘላለም 4/5
ለተሣተፋችሁ ሁሉ ቃለ ሕይወትን ያሰማልን መንግሥተ ሰማያትን ያውርስልን

#በርቱ

Читать полностью…

መዓዛ ሃይማኖት በጎ አድራጎትና ጉዞ ማህበር

ስንክሳር ዘወርሃ ጥቅምት ሃያ ሁለት (፳፪)
@meazahaymanot

Читать полностью…

መዓዛ ሃይማኖት በጎ አድራጎትና ጉዞ ማህበር

ስንክሳር ዘወርሃ ህዳር ሁለት(፪)

@meazahaymanot

Читать полностью…

መዓዛ ሃይማኖት በጎ አድራጎትና ጉዞ ማህበር

. የጥምቀት መዝሙራት

የማህበረ ኪዳነ ምህረት የመዝሙር
05

✞ማርያም ደስ ይበልሽ✞

ማርያም ማርያም ማርያም
ደስ ይበልሽ በገብርኤል ሰላምታ
በአንቺ ስላደረ የዓለም ሁሉ ጌታ (፪)

የአምላክ ቸርነቱ ፈቃዱ ሲሆን
ጨለማው ተገፎ ሲወጣ ብርሃን
መድኃኒት ሲመጣ ሰይጣን እንደ አፈረ
የዜናው አብሳሪ ገብርኤል ነበረ
አዝ= = = = =
ድንግል ተቀምጣ በቤተ መቅደስ
ሐርና ወርቁን አስማምታ ስትፈትል ንግሥት
ገብርኤል ገብርኤል ዜናዌ ሐዲስ
የአምላክን መወለድ ስጋ በመልበስ
አዝ= = = = =
ገብርኤል ሲያበስራት ድንግል ስትሰማ
አምላክ በርሷ አደረ የመለኮት ግርማ
እውነተኛ መልአክ መሆኑን ስላየች
ይሁንልኝ ብላ ቃሉን ተቀበለች

@meazahaymanot

Читать полностью…

መዓዛ ሃይማኖት በጎ አድራጎትና ጉዞ ማህበር

ማኅደረ ጥያቄ

1. ሐ

ከዚህም በኋላ አይሁድን ስለ ፈራ በስውር የኢየሱስ ደቀ መዝሙር የነበረ የአርማትያስ ዮሴፍ የኢየሱስን ሥጋ ሊወስድ ጲላጦስን ለመነ፤ ጲላጦስም ፈቀደለት። ስለዚህም መጥቶ የኢየሱስን ሥጋ ወሰደ።

    ዮሐንስ ወንጌል 19÷38

2. ለ

ዕጣም ተጣጣሉላቸው፥ ዕጣውም ለማትያስ ወደቀና ከአሥራ አንዱ ሐዋርያት ጋር ተቈጠረ።

  የሐዋርያት ሥራ 1÷26

3. መ

፤ ዳዊትም በእስራኤል ላይ የነገሠው ዘመን አርባ ዓመት ነበረ። በኬብሮን ሰባት ዓመት ነገሠ፤ በኢየሩሳሌምም ሠላሳ ሦስት ዓመት ነገሠ።

   መጽሐፈ ነገሥት ቀዳማዊ 2÷11

4. መ


እነሆ፥ ድንግል ትፀንሳለች ልጅም ትወልዳለች፥ ስሙንም አማኑኤል ይሉታል የተባለው ይፈጸም ዘንድ ይህ ሁሉ ሆኖአል፥ ትርጓሜውም። እግዚአብሔር ከእኛ ጋር የሚል ነው።

  ማቴዎስ ወንጌል 1÷23

5. ጥቅምት 29 ቀን የሚከበሩ ዓመታዊ የቅዱሳን በዓላት
1.አቡነ ሳሙኤል ጻድቅ (ዘደብረ ወገግ)
2.አባ ጸቃውዐ ድንግል (ዘደብረ ዘኸኝ)
3.ቅዱስ ድሜጥሮስ ሰማዕት
4.ቅዱስ ስቅጣር ሰማዕት

ወርኀዊ በዓላት
1.የፈጣሪያችን ኢየሱስ ክርስቶስ ልደት
2.ቅዱስ ዼጥሮስ ተፍጻሜተ ሰማዕት
3.ቅዱስ ማርቆስ ዘቶርማቅ
4.ቅድስት ፍቅርተ ክርስቶስ ኢትዮዽያዊት
5.ቅዱስ ዘርዐ ክርስቶስ
6.ቅድስት አርሴማ ድንግል

ጥቅምት 30 ቀን የሚከበሩ ዓመታዊ የቅዱሳን በዓላት
1.ቅዱስ ማርቆስ ሐዋርያ
2.ቅዱስ አርስጥቦሎስ (አባቱ)
3.ቅድስት ማርያም (እናቱ)
4.ቅዱስ ዮሐንስ መጥምቀ መለኮት
5.አባ አብርሃም ገዳማዊ
6 ቅዱስ ይስሐቅ ንጉሥ

ወርኀዊ በዓላት
1.ቅዱስ ጐርጐርዮስ ነባቤ መለኮት
2.ቅድስት ሶፍያ ሰማዕት
3.አባ ሣሉሲ ክቡር ጻድቅ

የተሣተፉ

1. ሜሮን 4/5

2. yalemsew 3/5

3. Hirut 4/5

4. Selam 5/5

5. ታምሩ 5/5

6.ታሪክአየሁ 4/5

7. sinte 5/5

8. eliyab 5/5

9. G.M.A 5/5

10. መቅደሰ ማርያም 5/5

11.ዮሐንስ  5/5

12.ፍሬው 5/5

13.ዮዲት 5/5

14. አንፋሮ 3/5

15.ያሬድ 5/5

ለተሣተፋችሁ ቃለ ሕይወትን ያሰማልን መንግሥተ ሰማያትን ያውርስልን

Читать полностью…

መዓዛ ሃይማኖት በጎ አድራጎትና ጉዞ ማህበር

✞ እግዚአብሔር የወደቁትን ያነሳል

እግዚአብሔር የወደቁትን
ያነሳል የተረሱት ያስታውሳል
የተናቁት ያከብራል

አንተ በክብር ላይ ክብር ስጨምር
እረኛው ይሻማል በንጉስ ወንበር
ጌታ ትውዳለ የተናቁትን አንተ
ልብን እንጂ አታይም ፊትን
#አዝ
ሳሙኤል ልከ ጠርተ ትቀባለክ
ያንበሶቹን አፍ አንተ ትዘጋለክ
በጌርጌሲኖር በመቃብር ስፍራ
አየሁ አምላኬ ለሰው ልጅ ስትራራ
#አዝ
ጠላታችን ደርሳ ቢያስጨንቀንም
ትሞታለ ብሎ ቢዝትብንም
በሃሰት ቢጥለን ከመከራ ቤት
በእግዚአብሔር ቸርነት ወጣን ከስራት
#አዝ
ይደግፋል ክንድህ የተጋቁትን
ከሰው በታች ሆኑ የሚኖሩትን
ደስታ ትሰጣል ሃዘን አርቀህ
አይቀርም አልቅሶ አንተን ያመነህ
#አዝ
ጠላታችን ደርሳ ቢያስጨንቀንም
ትሞታለ ብሎ ቢዝትብንም
በሃሰት ቢጥለን ከመከራ ቤት
በእግዚአብሔር ቸርነት ወጣን ከስራት

💚 @meazahaymanot❤️

Читать полностью…

መዓዛ ሃይማኖት በጎ አድራጎትና ጉዞ ማህበር

ከውለታ በላይ ነው ያንተ ውለታ
ከስጦታ በላይ ነው ያንተ ስጦታ
ስራህ አስገረመኝ ከፍ በል ጌታ
እጄን በእጄን በአፌ ጫንኩኝ ከፍ በል ጌታ

እንዳላጠፋ ሰው ከቶ እንዳልበደለ
በሚያስደንቅ ፍቅር ሁሌ ታልፈኛለህ
ጸጋህ ተትረፍርፎ በዛና ሰላሜ
እጄን በአፌ ጫንኩኝ ዙፋንህ ስር ቆሜ

እግሮቼ ሲሮጡ ወደ ሞት ሸለቆ
ይቅርታህ መለሰኝ ከነበልባል ነጥቆ
በጥበብ በትግስት ታሰድገኛለህ
ወይንህን ስትጠብቅ መች ትሰለቻለህ

ቀና ብየ ሳየው ሰማይ ማደሪያህን
እጅግ አደንቃለሁ ግርማ ጌትነትክን
ዝቅ ስል ከቤቴ ስትሰራ አይሀለሁ
ከመገረም በቀር ሌላ ምን እላለሁ

ያልታሰበ ነገር አድርገህልኛል
በጠላቶቼ ፊት አሞግሰህኛል
መስዋእትን ብሰዋ የከንፈሬን ፍሬ
ለስጦታህማ አልጠግብም ዘምሬ

Читать полностью…

መዓዛ ሃይማኖት በጎ አድራጎትና ጉዞ ማህበር

ስንክሳር ዘወርሃ ጥቅምት ሃያ ዘጠኝ(፳፱)
@meazahaymanot

Читать полностью…

መዓዛ ሃይማኖት በጎ አድራጎትና ጉዞ ማህበር

ማኅደረ ጥያቄ

፩. ጌታችን አምላካችን ኢየሱስ ክርስቶስ ናትናኤልን ያየው የት ነው

ሀ. በያዕቆብ ቤት   ለ. በምኩራብ  

ሐ.በቤተመቅደስ     መ. ከበለሱ በታች

፪. የአስቴር አጎት ማን ይባላል ?

ሀ. መርዶክዮስ

ለ. ካም

ሐ. ሄሮድስ

መ. ሃማ

፫. ኢያሱ በምድር ላይ ስንት አመት ኖረ

ሀ. 58     ለ. 100     ሐ. 110    መ. 120

፬. የኖህ መርከብ ከምን ተሰራ

ሀ. ከዝግባ እንጨት

ለ. ከጎፈር እንጨት

ሐ. ከወይራ እንጨት

መ. ከባህር ዛፍ እንጨት

፭. በዛሬ ዕለት የሚከበሩ ቅዱሳን በዓላት ጻፉ

መልሱን እስከ ማታ3:00 ሰዓት በ @Asitmeherobot አድርሱን

         #መልካም_እድል

Читать полностью…

መዓዛ ሃይማኖት በጎ አድራጎትና ጉዞ ማህበር

ማኅደረ ጥያቄ

፩. ጌታችን አምላካችን ኢየሱስ ክርስቶስ ናትናኤልን ያየው የት ነው

ሀ. በያዕቆብ ቤት ለ. በምኩራብ

ሐ.በቤተመቅደስ መ. ከበለሱ በታች

፪. የአስቴር አጎት ማን ይባላል ?

ሀ. መርዶክዮስ

ለ. ካም

ሐ. ሄሮድስ

መ. ሃማ

፫. ኢያሱ በምድር ላይ ስንት አመት ኖረ

ሀ. 58 ለ. 100 ሐ. 110 መ. 120

፬. የኖህ መርከብ ከምን ተሰራ

ሀ. ከዝግባ እንጨት

ለ. ከጎፈር እንጨት

ሐ. ከወይራ እንጨት

መ. ከባህር ዛፍ እንጨት

፭. በዛሬ ዕለት የሚከበሩ ቅዱሳን በዓላት ጻፉ

መልሱን እስከ ነገ 7:00 ሰዓት በ @Asitmeherobot አድርሱን

#መልካም_እድል

Читать полностью…

መዓዛ ሃይማኖት በጎ አድራጎትና ጉዞ ማህበር

በኩረ ፍሥሐ ቀሲስ ኃይለኢየሱስ ተመስገን

ጥቅምት ፳፯ ተዝካረ ስቅለቱ ለእግዚእነ

በስመ አብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ አሐዱ አምላክ አሜን

እንኳን ለመድኃኔዓለም ዓመታዊ ክብረ በዓል ዝክረ ጥንተ ስቅለት አደረሳችሁ አደረሰን
ከሁሉ አስቀድሞ ሃይማኖትን መመስከር እንዲገባ “ ከመዝ ነአምን ዘአልቦቱ እም በሰማያት፤ ወአብ በዲበ ምድር ” በሰማይ ያለእናት ከአብ መወለዱን፣ በምድርም ያለ አባት ከድንግል ማርያም መወለዱን እናምናለን። ይህንንም አባቶቻችን ሊቃውንተ ቤተክርስቲያን ቅድመ ዓለም ከእግዚአብሔር አብ ያለ እናት፣ አካል ዘእምአካል ባሕርይ ዘእምባሕርይ የተወለደ ተቀዳሚ ተከታይ የሌለው አካላዊ ቃል ፤ ድኀረ ዓለም ከእመቤታችን ቅድስት ድንግል ማርያም ያለ አባት፣ መለወጥ ሳያገኛት ዘር ምክንያት ሳይሆን ከሥጋዋ ሥጋ ከነፍሷ ነፍስ ነስቶ የተወለደ፤ ወልደ እግዚአብሔር በመለኮቱ ወልደ ማርያም በትስብእቱ ብለው አምልተው እንዲያስተምሩን  “ከመ አሐዱ ውእቱ ባሕቲቱ ውእቱ አምላክ ወሰብእ ኅቡረ” ትርጉሙም  እርሱ በተዋሕዶ ሰው የሆነ አምላክ ነው ማለት ነው።  ሃይማኖተ አበው ዘጎርጎርዮስ ፴፭፥፳፩

መጋቢት ፳፯  በቃል መነገሩ በልብ መታሰቡ ከፍ ከፍ ይበልና ጌታችን መድኃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ  የተሠቀለበት ጥንተ ስቅለቱ የሚታሰብበት ቀን ነው ፡፡  ይሁን እንጂ ሊቃውንተ ቤተክርስቲያን በዲሜጥሮስ ቀመር መሠረት አጽዋማትን በጠበቀ መልኩ ከትንሣኤ በዓል በፊት ያለውን አርብ “ስቅለት” ተብሎ እንዲከበር ሥርአት ሠርተዋል፡፡መጋቢት ፳፯ ቀን በዓቢይ ጾም ስለሚውል በዓቢይ ጾም ሀዘን እንጂ ደስታ ስለሌለ በዓል ማክበርም ስለማይፈቀድ፤ ወደ ጥቅምት ፳፯ ተዛውሮ ደስ ብሎን እንድናከብረው ቤተክርስቲያን ሥርዓት ሰርታለች ።

ጥቅምት ፳፯ ዝክረ ጥንተ ስቅለቱን ቤተክርስቲያናችን ጌታችን በመስቀሉ ስለፈጸመልን የማዳን ስራ “ በመስቀሉ ወበቃሉ አዕበዮሙ ለአበዊነ ” ። በመስቀሉና በቃሉ አባቶቻችንን ከፍ ከፍ አደረጋቸው እያለች እየዘመረች ታስበዋለች። ከዚህም በተጨማሪ ጥቅምት ፳፯  በወርኀ ጽጌ ውስጥ ያለ በመሆኑ “  …እስመ ውእቱ ክብሮሙ ለቅዱሳን መድኃኒቶሙ ለጻድቃን  አሠርገዋ ለምድር በጽጌ ሮማን ስብሐተ ዋህድ ዘምስለ ምህረት በመስቀሉ ወበቃሉ አዕበዮሙ ለአበዊነ ” እያለች የቅዱሳን ክብራቸው የጻድቃን መድኃኒት የሆነው ጌታ ምድርን በአበባ የሚያስጌጣት እንደሆነ በመመስከር ትዘምራለች ።

“እስመ አንተ ትክል አንጽሖትየ እግዚኦ  ወበቃልከ እለ ለምፅ አንጻሕከ  ወበጽጌያት ምድረ አሠርጐከ  ወበመስቀልከ ለጻድቃን አብራህከ ”  ልታነጻኝ ይቻልሃል አቤቱ ለምጻሞቹን በቃልህ እንጽተሃልና እያሉ አባቶቻችን በመስቀሉ ለጻድቃን ማብራቱን እያሰቡ በዓሉን በመዝሙር በደስታ ያከብሩታል

ወበከመ ሙሴ ሰቀሎ ለአርዌ ምድር በገዳም ከማሁ ሀለዎ ለወልደ ዕጓለ እመሕያው ይሰቀል” ዮሐ ፫፥፲፬ ሙሴ እባብ በምድረ በዳ እንደሰቀለ የሰው ልጅ ክርስቶስ ይሰቀል ዘንድ አለው  ብሎ እንደተናገረ  የክብር ባለቤት ጌታችን መድኃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ስለ ዓለም ድኅነት የተሰቀለው መጋቢት ፳፯ ቀን ነው ።
ክርስቶስ ስለስቅለቱ ሲናገር ምሳሌ የሚሆነውን፣ ሙሴ በምድረ ባዳ የሰቀለውን፣ የነሐሱን እባብ “ሙሴ እባብ በምድረ በዳ እንደሰቀለ የሰው ልጅ ክርስቶስ ይሰቀል ዘንድ አለው” ብሎ ምሳሌውን ተናግሯል።

የሠራዊት ጌታ እግዚአብሔር እስራኤልን ከደመና መና አውርዶ፣ከጭንጫ ውሀ አፍልቆ ቢመግባቸው ከዚህ ምድሩ ብቅ፣ሰማዩ ዝቅ ቢልለት፣ ከደጋ ላይ ቢሆንለት የውርጭ ሰደቃ እያበጀ፣ ውሀውን እያረጋ፣ መና መገብኳችሁ ይላል እንጅ ይክልኑ እግዚአብሔር ሠሪዓ ማዕድ በገዳም። ቆላ በሆነማ ባልተቻለውም ነበር ብለዋል ።ጌታም ሊያስተምራቸው ፣  የርሱን ከሃሊነት ሊያሳያቸው፣  የእነርሱንም ሀሰት ሊገልጥባቸው ፣  ሙሴን ነቅዓ ማይ የሌለበት በርሐ ይዘሀቸው ውረድ ብሎት ቢሄዱ መናው ወርዶላቸዋል፣ ውሀውም ፈልቆላቸዋል ።ነገር ግን ነዘር የሚባል እባብ እየነከሰ ይፈጃቸው ጀመር።ከዚህ በኋላ እስራኤል ሙሴ ዘንድ ሂደው ከጌታ ምህረት ቸርነት ከሰው ስሕተት ኃጢአት አይታጣም በእግዚአብሔርና በአንተ ላይ ተናግረን በድለናል  እባቦችን ከኛ ያርቅልን ዘንድ ወደ እግዚአብሔር አመልክትልን አማልደን አሉት።ሙሴም ስለሕዝቡ  ወደ እግዚአብሔር ቢጸልይ  ጽሩዩን ብርት አርዌ አስመስለህ ሠርተህ ከሚገናኙበት አደባባይ ከእንጨት ላይ ስቀልላቸው አለው። ሙሴም እባብን ሠርቶ በዓላማ ላይ ሰቀለ እባብም የነደፈችው ሰው ሁሉ የነሐሱን እባብ ባየ ጊዜ ዳነ። (ኦሪ ዘኁ ፳፩ ፥፩፡፱)

ይህንም ምሳሌ አባቶቻችን በትርጓሜ ወንጌል ቅዱስ እንዳስቀመጡልን አርዌ ምድር የዲያብሎስ፤አርዌ ብርት የጌታ ምሳሌ ነው ። በአርዌ ምድር(እባብ) መርዝ እንዳለበት በዲያብሎስም ፍዳ ኃጢአት አለበት።በአርዌ ብርት መርዝ እንደሌለበት በጌታም ፍዳ ኃጢአት የለበትም ።አርዌ ብርት በአርዌ ምድር አምሳል መሰቀሉ ጌታ በአምሳለ እኩያን እንደወንጀለኛ ተቆጥሮ ለመሰቀሉ ምሳሌ ነው። ዳግመኛም  “ተኈለቈ ምስለ ጊጉያን” ከዐመፀኞችም ጋር ተቈጥሯልና  ኢሳ  ፶፫፥፲፪  የሚለውን ትንቢት ፈጽሟል። ምሳሌውን አውቆ አስመስሏል ትንቢቱንም አውቆ አናግሯል ።

ጲላጦስ አይሁድን ከሁለቱ ማናቸውን ላድንላችሁ ትወዳላችሁ ቢላቸው በርባንን ፍታልን ክርስቶስ የተባለ ኢየሱስን ግን ስቀለው አሉ ።ጲላጦስም  በዚህ ሰው ደም ከመጣ ፍዳ ሁሉ ንጹሕ ነኝ ብሎ ባደባባይ እጁን ታጠበ። አይሁድ ደሙ በኛም በልጅ ልጆቻችንም ይሁን አሉ። እርሱም በርባንን ፈታላቸው ጌታንም አሳልፎ ሰጣቸው። ማቴ ፳፯ ፥፳፭

ቅዳሴ ዮሐንስ አፈወርቅ “ሊቃነ መላእክት በመፍራትና በመንቀጥቀጥ ከፊቱ የሚቆሙለትን በአደባባይ አቆሙት፤ ኃጢያትን ይቅር የሚለውን ኃጥእ አሉት፤ በመኳንንት በሚፈርደው በርሱ ፈረዱበት” ፡፡  እንዲል ክርስቶስን አይሁድ ስቀለው ብለው ፈረዱበት

አክሊልን የሚያቀናጀውን የነገሥታት ንጉሥ ኢየሱስ ክርስቶስን አነገስንህ ብለውታልና ጭፍሮች በፍና ተሣልቆ የእሾህ አክሊል ታተው ደፉለት “ወጸፈሩ ሐራ አክሊለ ዘሦክ ወአስተቀጸልዎ ዲበ ርእሱ” ዮሐ ፲፱፥፪ ። ኢየሱስ ክርስቶስ  የእሾኽ አክሊል በመቀዳጀቱ ዕፀ በለስን በልቶ  “ምድር እሾኽንና አሜከላን ታበቅልብኻለች” ዘፍ  ፫፥፲፰  ብሎ የፈረደበትን አዳም  ስለርሱ ክሶ መርገሙን ደምስሶለታል ።

መጋቢት ፳፯ ቀን ክርስቶስ ኢየሱስ በመስቀል በተሰቀለ ጊዜ፤ የተሰቀለው የክብር ባለቤት ሰማይን የፈጠረ ነውና  ፀሐይ ጨልማለች፣ ጨረቃ ደም ሆኗል፣ ከዋክብት ረግፈዋል። የተሰቀለው የክብር ባለቤት ምድርንም የፈጠረ ነውና በምድር የቤተ መቅደሱ መጋረጃ ከላይ እስከ ታች ለኹለት ተቀዷል፤ ምድር ተናውጣ ዐለቶች ተሠንጥቀዋል፤ መቃብራት ተከፍተዋል፤ ከ፭፻ በላይ ሙታን ተነሥተዋል (ማቴ ፳፯ )፡፡

ኦ አእዳው እለ ለሐኳሁ ለአዳም ተቀነዋ በቅንዋተ መስቀል ፤ ኦ አእጋር እለ አንሶሰዋ ውስተ ገነት ተቀነዋ በቅንዋተ መስቀል

አዳምን የፈጠሩ እጆች በመስቀል ቀኖት ተቸነከሩ ወዮ፤በገነት የተመላለሱ እግሮች በመስቀል ቀኖት ተቸነከሩ ወዮ፡፡ እንዲል  ቅዳሴ ዮሐንስ አፈወርቅ ስቅለቱን በዲሜጥሮስ ቀመር አውጥተን የጌታን መከራውን አስበን በስግደት ህማማቱን እናስባለን በዝክረ ጥንተ ስቅለቱ በጥቅምት ፳፯ ደግሞ በመስቀል የተደረገልንን አስበን እናመሰግነዋለን፡፡

Читать полностью…

መዓዛ ሃይማኖት በጎ አድራጎትና ጉዞ ማህበር

ስንክሳር ዘወርሃ መስከረም ሃያ ሰባት(፳፯) /channel/meazahaymanot

Читать полностью…

መዓዛ ሃይማኖት በጎ አድራጎትና ጉዞ ማህበር

ስንክሳር ዘወርሃ ጥቅምት ሃያ ስድስት(፳፮) /channel/meazahaymanot

Читать полностью…

መዓዛ ሃይማኖት በጎ አድራጎትና ጉዞ ማህበር

ስንክሳር ዘወርሃ ጥቅምት ሃያ አምስት (፳፭)
/channel/meazahaymanot

Читать полностью…

መዓዛ ሃይማኖት በጎ አድራጎትና ጉዞ ማህበር

🔒
ውድ የመዓዛ ሃይማኖት ቻናል ቤተሰቦች ቻናላችን መርዳት የምትፈልጉ ከታች ያለዉን ሊንክ ለጓደኞቻችሁ Copy አድርጋቹ በመላክ ወይም ይህንን መልዕክት በቀጥታ forward በማድረግ አበረታቱን።
🔒
ለምትወዷቸዉ ሰዎች የምትወዱትን ቻናላችንን ላኩላቸዉ።
🔏
ዉድ ወንድሞቼና እህቶች አንድ ቅን ሰዉ ቢያንስ ለ5 ሰዎች ሼር ቢያደርግ በ30 ደቂቃ ዉስጥ በ1,000 ቅን ሰዎች 5,000 አዳዲስ ቤተሰቦችን ማግኘት እንችላለን!!
#ለትብብራቹ_ከልብ_እናመሰግናለን
🔒
〰〰〰〰〰〰〰〰〰〰〰〰〰
Share share
@meazahaymanot
@meazahaymanot
@meazahaymanot
ማንኛውንም ሀሳብ አስተያየት
👉   @misiwani_Bot ላይ አድርሱን። ይህ የናንተው ቻናል ነው።√
🙏 እናመሰግናለን 🙏

Читать полностью…

መዓዛ ሃይማኖት በጎ አድራጎትና ጉዞ ማህበር

ማኅደረ ጥያቄ
፩. ያዕቆብ ድንጋይ ተንተርሶ ህልም ያለመበትን ቦታ ምን ብሎ ጠራው
ሀ. ከነዓን ለ. ቤቴል ሐ. ጲንኤል
መ. ሎዛ
፪. አባታችን ሊቀ ሐዋርያት ቅዱስ ጴጥሮስ የጌታ ደቀመዝሙር ከመሆኑ በፊት ምን ነበር
ሀ. እረኛ ለ. ሐኪም ሐ. ቀራጭ
መ. አሳ አጥማጅ
፫. የይስሐቅ ሚስት ስሟ ማን ነበር
ሀ. ርብቃ
ለ. ሀና
ሐ. ሊድያ
መ. ሳራ
፬. ወንድሞቹ በሀያ ዲናር የሸጡት ማነው

ሀ. ይሁዳ ለ. ሕንደኬ ሐ. ዳንኤል
መ. ዮሴፍ
፭. አባታችን ኢዮብ ይኖርበት የነበረ ሀገር ምን ይባላል
ሀ. ኤዶምያስ
ለ ሞሪያም
ሐ. ኦድ
መ. ምድያም
መልሱን እስከ ማታ 3:00 ሰዓት በ @Asitmeherobot አድርሱን

#መልካም_እድል

Читать полностью…

መዓዛ ሃይማኖት በጎ አድራጎትና ጉዞ ማህበር

ማኅደረ ጥያቄ

፩. ያዕቆብ ድንጋይ ተንተርሶ ህልም ያለመበትን ቦታ ምን ብሎ ጠራው

ሀ. ከነዓን ለ. ቤቴል ሐ. ጲንኤል

መ. ሎዛ

፪. አባታችን ሊቀ ሐዋርያት ቅዱስ ጴጥሮስ የጌታ ደቀመዝሙር ከመሆኑ በፊት ምን ነበር

ሀ. እረኛ ለ. ሐኪም ሐ. ቀራጭ

መ. አሳ አጥማጅ

፫. የይስሐቅ ሚስት ስሟ ማን ነበር

ሀ. ርብቃ

ለ. ሀና

ሐ. ሊድያ

መ. ሳራ

፬. ወንድሞቹ በሀያ ዲናር የሸጡት ማነው

ሀ. ይሁዳ ለ. ሕንደኬ ሐ. ዳንኤል

መ. ዮሴፍ

፭. አባታችን ኢዮብ ይኖርበት የነበረ ሀገር ምን ይባላል

ሀ. ኤዶምያስ

ለ ሞሪያም

ሐ. ኦድ


መ. ምድያም

መልሱን እስከ ነገ 6:00 ሰዓት በ @Asitmeherobot አድርሱን

#መልካም_እድል

Читать полностью…
Subscribe to a channel