meazahaymanot | Unsorted

Telegram-канал meazahaymanot - መዓዛ ሃይማኖት በጎ አድራጎትና ጉዞ ማህበር

3925

"ውድስት አንቲ በአፈ ነቢያት ወስብሕት በሐዋርያት አክሊለ በረከቱ ለያዕቆብ ወትምክህተ ቤቱ ለእስራኤል፡፡" "በነቢያት በሐዋርያት አንደበት የተመሰገንሽ የያዕቆብ የበረከቱ ዘውድ የእስራኤል ወገን መመኪያ አንቺ ነሽ"                  መጽሐፈ ሰዓታት የፌስቡክ ፔጃችን www.fb.me/meazhaimanot ይቀላቀሉን

Subscribe to a channel

መዓዛ ሃይማኖት በጎ አድራጎትና ጉዞ ማህበር

ማኅደረ ጥያቄ
1. በመጽሐፍ ቅዱስ ውስጥ ረጅም ዕድሜ የኖረው ሰው ማነው
ሀ. ማቱሳላ
ለ. ላሜሕ
ሐ. አብርሃም
መ. አዳም
2. የአብርሃም የስሙ ትርጉም ምን ማለት ነው
ሀ. ታጋሽ
ለ. የእምነት ሰው
ሐ. እግዚአብሔር ታማኝ
መ. የአሕዛብ አባት
3. የመጥምቁ ዮሐንስ እናት ማን ትባላለች
ሀ. ኤልዛቤል
ለ. ሃና
ሐ. ኤልሳቤጥ
መ. ርብቃ
4. ኤልሮኢ ማለት ምን ማለት ነው

ሀ. በውኑ የሚያየኝን አየሁት
ለ. ምርኮም ፈጠነ ብዝበዛም ቸኮለ
ሐ. እግዚአብሔር ታላቅ ነው
5. ይዲድያ የስሙ ትርጉም ምን ማለት ነው
ሀ. በእግዚአብሔር የተቀባ
ለ. በእግዚአብሔር የተወደደ
ሐ. የእግዚአብሔር ባርኮት
መ. የእግዚአብሔር ኃይል
መልሱን እስከ ማታ 3:00 ሰዓት በ @Asitmeherobot አድርሱን
#መልካም_እድል

Читать полностью…

መዓዛ ሃይማኖት በጎ አድራጎትና ጉዞ ማህበር

ስንክሳር ዘወርኃ ህዳር አሥር (፲)

@meazahaymanot

Читать полностью…

መዓዛ ሃይማኖት በጎ አድራጎትና ጉዞ ማህበር

መዝገበ ሥላሴ ያለም ብርሃን ናቸው

በዘማሪት ሲ/ር ሕይወት

Читать полностью…

መዓዛ ሃይማኖት በጎ አድራጎትና ጉዞ ማህበር

#ዝክረ_አቡነ_መዝገበ_ሥላሴ

አቡነ መዝገበ ሥላሴ፡- አቡነ መዝገበ ሥላሴ በታሪካዊነቱና በያዛቸው ድንቅ ድንቅ ቅርሶች ከሚታወቀውና ኢትዮጵያዊውን ሀሳበ ዘመን በመቀመር ከሚታወቀው ከእውነተኛው የብህትውና ቦታ ከደብረ ገሪዛን ቅድስት ማርያም ጉንዳጉንዶ ገዳም የተገኙ ታላቅ አባት ናቸው፡፡ እነ አቡነ አበከረዙንን ጨምሮ የባሕረ ሐሳብ ፍልስፍናና የሥነ ጽሑፍ ማዕከል ከሆነው ከዚህ ገዳም የወጡ ገድል ተጽፎላቸው፣ ታቦት በስማቸው የተቀረጸላቸው ከ17 በላይ ታላላቅ ቅዱሳን አሉ፡፡ አቡነ መዝገበ ሥላሴም ከእነዚህ የበቁ ቅዱሳን ውስጥ አንዱ ናቸው፡፡ አባታቸው ሀብተ ጽዮን እናታቸው ማርያም ሞገሳ ሲባሉ እነርሱም በእግዚአብሔር ፊት ቅኖች ነበሩ፡፡ ማርያም ሞገሳ ዕለት ዕለት አምሃ(ስጦታ) እየያዘች ወደ ቤተ ክርስቲያን እየሄደች ስትጸልይ በአንደኛው ዕለት የታዘዘ መልአክ መጥቶ ‹‹በእግዚአብሔር ፊት ሞገስ ያገኘና የተባረከ ልጅ ትወልጃለሽ›› ብሎ አበሰራት፡፡እርሷም ‹‹ከማኅፀኔ እንደፀሐይ የሚያበራ ልጅ ሲወጣ አየሁ›› አለች፡፡ በዚህም መሠረት አቡነ መዝገበ ሥላሴ በምሥራቃዊ ትግራይ ዞን በገላውዴዎስ ዘመነ መንግሥት በ1532 ዓ.ም ተወለዱ፡፡ በ40ኛ ቀናቸውም ሲጠመቁ ሰጊድለአብ ተባሉ፡፡ ሰጊድለአብ ከዕለታት በአንደኛው ቀን የእግዚአብሔር መልአክ ከእናታቸው እቅፍ ውስጥ ነጥቆ ወስዶ ደብረ ከስዋ (ደብረ ገሪዛን) ጉንዳጉንዶ ቅድስት ማርያም ገዳም አደረሳቸው፡፡ ወደ ቅድስተ ቅዱሳኑም ካስገባቸው በኋላ በውስጥ የነበሩትን ንዋያት ሁሉ እያሳየ ‹‹አንተ ሕፃን ሆይ! ዕወቅ ይህ የምታየው ሁሉ የአንተ ነው፣ ትጠብቀውም ዘንድ እግዚአብሔር ሰጥቶሃል፡፡ ደግሞም የክርስቶስን በጎች ትጠብቅ ዘንድ ተሰጥቶሃልና ፈጽሞ ደስ ይበልህ›› አላቸውና ፈጥኖ ወደ እናታቸው እቅፍ መለሳቸው፡፡ ዕድሜአቸውም ለትምህርት ሲደርስ ወደ ጉንዳጉንዶ ተመልሰው የሁሉንም መጻሕፍትን ምሥጢር ጠንቅቀው ተማሩ፡፡ በገዳሙም የምንኩስናን ሥራ እየሠሩ በተጋድሎ ኖሩ፡፡ ክብርት እመቤታችንም ተገልጻላቸው ‹‹ልጄ በተፈቀደልህ ተጋድሎ አሰልጥኖሃልና ጨክን፣ በርታ እኔም ከአንተ አልለይም›› አለቻው፡፡ ከመነኮሱም በኋላ ስማቸው ‹‹አቡነ መዝገበ ሥላሴ›› ተባሉ፡፡
አቡነ መዝገበ ሥላሴ ስብከተ ወንጌልን በመላ ሀገራችን በማስፋፋት ብዙ የደከሙ ታላቅ አባት ናቸው፡፡ በዚህም ምክንያት ‹‹የሐዋርያት አምሳል›› ተብለዋል፡፡ የገዳሙ አበምኔት ሲያርፉ መነኮሳቱ በፈቃደ እግዚአብሔር አቡነ መዝገበ ሥላሴን ይዘው በግድ አበምኔትነት ሾሟቸው፡፡ እሳቸውም ከተሾሙ በኋላ በመላ ሀገራችን ተዘዋውረው ወንጌልን ሰብከዋል፡፡ ብዙ ድውያንን ፈውሰዋል፣ ሙታንን አንሥተዋል፡፡ በዓታቸውንም በማጽናት በጸሎት ተወስነው የዐይኖቻቸው ቅንድቦች እስኪላጡ ድረስ ጉንጮቻቸውም እስኪቀሉ ድረስ በጸሎት ይተጉ ነበር፡፡ 40 ቀንና 40 ሌሊትም ይጾማሉ፡፡ ስግደታቸውም በቀንና በሌሊት ያለ እረፍት እንደመንኮራኩር ፈጣን ሆነ፡፡ ወዛቸውና ዕንባቸው አንድ ላይ ተቀላቅሎ እንደጅረት እስኪፈስ ድረስ በጭንቅ ተጋድሎ እንደኖሩ ገድላቸው ይናገራል፡፡ እመቤታችንም ብዙ ጊዜ እየተገለጠችላቸው ከህመማቸው እየፈወሰች ታበረታቸው ነበር፡፡ ከዕለታትም በአንደኛው ቀን አቡነ መዝገበ ሥላሴ ራእይ ተመለከቱ፡፡ እነሆም ውበታቸው የሚያስገርም፣ መልካቸውም የሚያስደንቅ፣ የምስጋና ነፀብራቅ የከበባቸው፣ የራሳቸው ፀጉር ነጭ የሆነ ሦስት ወፎችን ተመለከቱ፡፡ አባታችንም አንድ ጊዜ ሦስት ሌላ ጊዜ ደግሞ አንድ ሲሆኑ ተመልክተው ፈጽሞ አደነቁ፡፡ እንዲህ እያደነቁ ሳለ እግዚአብሔር በቃሉ ጠርቶ ካነጋገራቸው በኋላ ብዙ ምሥጢራትን ነገራቸው፡፡ ለመረጣቸው ቅዱሳን እንዲህ መገለጥ ለእግዚአብሔር ልማዱ ነውና ለአባታችን ለአዳም፣ ለሄኖክ፣ ለኖኅ፣ ለአብርሃም በልዩ ልዩ ህብር ተገልጧል፡፡ ኦ.ዘፍ 3፡10፣ 5፡24፣ 6፡13፣ 18፡1 ፡፡ ለሕዝቅኤልም በኮበር ወንዝ፣ ለዳንኤል በሱሳ ግንብ፣ ለኢሳይያስ ሱራፌል እያመሰገኑት ተገልጦላቸዋል፡፡ ሕዝ 1፡1፣ ዳን 8፡1-3፣ ኢሳ 6፡1-3፡፡ አቡነ መዝገበ ሥላሴ በዘመን ደረጃ በኋለኛው ዘመን የተነሡ አባት ይሁኑ እንጂ በሰጡት ሐዋርያዊ አገልግሎትና ገንዘብ ባደረጉት የተጋድሎ ጽናት የከበሩ ቅዱሳን ሐዋርያትን መስለዋቸዋል፡፡ የታዘዘ መልአክ ወደ መንግሥተ ሰማያት ነጥቆ ወስዶ ማደሪያቸውን አሳይቷቸው መልሶ ወደ ምድር ካመጣቸው በኋላ የዕረፍታቸው ጊዜ እንደደረሰ ነገራቸው፡፡ ‹‹በሰኔ ወር ታርፋለህ›› ቢላቸው ‹‹በሰኔማ ልጆቼ ተዝካሬን ማድረግ አይችሉም›› አሉት፡፡ መልአኩም መልሶ ‹‹ዕረፍትህ በሐምሌ ይሁን›› ቢላቸው ጻድቁ አሁንም ‹‹አይሆንም›› ብለው ተከራከሩ፡፡ በነሐሴም እንደዚያው ሆነ፡፡ መልአኩም መስከረምን አሳልፎ በጥቅምት እንደሚያርፉ ነግሯቸው ዐረገ፡፡ ከዚህም በኋላ ለስም አጠራሩ ምስጋና ይግባውና ጌታችን ቅድስት እናቱን፣ መላእክትን፣ ቅዱሳን ጻድቃን ሰማዕታትን ሁሉ አስከትሎ መጥቶ ‹‹አንተ የዓሥራ አንደኛው ሰዓት ቅጥረኛ ወዳጄ ሆይ! (ከቅዱሳን ሁሉ በኋላ የተነሣህ-ማቴ 20፡1-5) የምስራች እነግርህ ዘንድ የድካምህም ዋጋ እሰጥህ ዘንድ መጥቻለሁ፡፡ እነሆ ከጠዋት ጀምሮ ከደከሙት ጋር አንድ አድርጌሃለሁ፡፡ ከአንተም ጋር ቃልኪዳን ገብቻለሁ፣ ስምህን በእምነት የጠራ፣ መታሰቢያህን ያደረገ፣ በጸሎትህም የታመነ እስከ ሰማንያ ሺህ ስድስት መቶ (80,600) ነፍሳት ዓሥራት ይሁኑህ…›› በማለት ቃልኪዳን ከገባላቸው በኋላ ወደ ሰማያት ዐረገ፡፡ በዚያን ጊዜም አቡነ መዝገበ ሥላሴ ፊታቸው እንደፀሐይ አበራና ጥቅምት 9 ቀን ከሌሊቱ በ6 ሰዓት እንደመልካም እንቅልፍ ዐረፉ፡፡ መላ ዘመናቸው 115 ሲሆን የደብረ ገሪዛን ጉንዳጉንዶ ቅድስት ማርያም ገዳም አበምኔት ሆነው ከመሾማቸው በፊት 62 ዓመት፣ ከተሾሙበት ጊዜ እስከ ዕለተ ዕረፍታቸው ድረስ 53 ዓመት ነው፡፡ መካነ መቃብራቸው እዚያው የደብረ ገሪዛን ጉንዳጉንዶ ቅድስት ማርያም ገዳም ይገኛል፡፡ በጉንዳጉንዶና አዲግራት በሚገኘው ገዳማቸው ውስጥ በስማቸው የፈለቁ ብዙ ፈዋሽ ጠበሎች አሉ፡፡ አዲግራት የሚገኘው ገዳማቸው ውስጥ ያለው ጠበል የትኛውንም በሽታ በአስቸኳይ ፈውስ በመስጠት ይታወቃል፡፡ ተጠማቂው ሰው የማይድንም ከሆነ ቶሎ ይሞታል እንጂ ከ7 ቀን በላይ አይቆይም፡፡ ጻድቁ ብዙ የተጋደሉበት ይህ ገዳም በግራኝ አህመድ ዘመን 44 ጽላቶች ተሰውረውበታል፡፡ ዮዲት ጉዲትም ልታገኘው ያልቻለችው ታላቅ ገዳም ነው፡፡ በአንድ ወቅት ከሃዲያን አሕዛብ ጦረኞች ወደ ገዳሙ ሲወጡ በተአምራት ወደ ፅድ ዛፍነት ተለውጠዋል፡፡ ፅዶቹ አሁንም ድረስ በገዳሙ ክልል ውስጥ የሚገኙ ሲሆን ፅዶቹን በእሳት አቃጥለው ከሰል ቢያደርጓቸው ደም ሆነው ይፈሳሉ እንጂ ፈጽሞ ከሰል መሆን አይችሉም፡ ፡ (ገድለ አቡነ መዝገበ ሥላሴ)
የአቡነ መዝገበ ሥላሴ ረድኤት በረከታቸው ይደርብን፣ በጸሎታቸው ይማረን!

https://m.youtube.com/channel/UCKGh-U7U7pnvFUIEGXPOnNw

Читать полностью…

መዓዛ ሃይማኖት በጎ አድራጎትና ጉዞ ማህበር

የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተክርስቲያን ሥርዓት፣ ትውፊት እና አስተምህሮ  የጠበቁ ትምህርቶች እና መዝሙሮች እንዲሁም ወረቦችን እንዲሁም መንፈሳዊ ቦታዎችን መጎብኘት    የምትፈልጉ join በማለት ይቀላቀሉን ማኅበሩ ለሚያከናውናቸው አገልግሎቶች አጋዥ እንድትሆኑ በአክብሮት እንጋብዛለን።

/channel/meazahaymanot


Share

Читать полностью…

መዓዛ ሃይማኖት በጎ አድራጎትና ጉዞ ማህበር

ማኅደረ ጥያቄ

፩. በመጽሐፍ ቅዱስ  ውስጥ ሰው ያደረገው የመጀመሪያ ኃጢአት ምንድነው

ሀ. ዝሙት


ለ. ስርቆት

ሐ. የተከለከለውን ፍሬ መብላት

መ. ነፍስን ማጥፋት

፪. ጌታችን መድኃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ የተሰቀለበት ቦታ ምን ይባላል

ሀ. ደማስቆ

ለ. ጎልጎታ

ሐ. ቤተልሔም

መ. አኬልዳማ

፫. የአጋር ልጅ ማን ይባላል

ሀ. ይስሐቅ

ለ.  ሮቤል

ሐ. ያዕቆብ

መ. እስማኤል

፬.  የሙሴ ወንድም ማን ይባላል

ሀ. አሮን

ለ. ዮቶር

ሐ. ጌዲዎን

መ. ሶምሶን

፭. በዛሬ ዕለት የሚከብሩ ቅዱሳን በዓላትን ጻፉ

መልሱን እስከ ዛሬ 10:00 በ @Asitmeherobot አድርሱን

Читать полностью…

መዓዛ ሃይማኖት በጎ አድራጎትና ጉዞ ማህበር

ማኅደረ ጥያቄ

፩. በመጽሐፍ ቅዱስ ውስጥ ሰው ያደረገው የመጀመሪያ ኃጢአት ምንድነው

ሀ. ዝሙት


ለ. ስርቆት

ሐ. የተከለከለውን ፍሬ መብላት

መ. ነፍስን ማጥፋት

፪. ጌታችን መድኃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ የተሰቀለበት ቦታ ምን ይባላል

ሀ. ደማስቆ

ለ. ጎልጎታ

ሐ. ቤተልሔም

መ. አኬልዳማ

፫. የአጋር ልጅ ማን ይባላል

ሀ. ይስሐቅ

ለ. ሮቤል

ሐ. ያዕቆብ

መ. እስማኤል

፬. የሙሴ ወንድም ማን ይባላል

ሀ. አሮን

ለ. ዮቶር

ሐ. ጌዲዎን

መ. ሶምሶን

፭. በዛሬ ዕለት የሚከብሩ ቅዱሳን በዓላትን ጻፉ

መልሱን እስከ ነገ 6:00 በ @Asitmeherobot አድርሱን

Читать полностью…

መዓዛ ሃይማኖት በጎ አድራጎትና ጉዞ ማህበር

ስንክሳር ዘወርሃ ህዳር ሰባት(፯)
@meazahaymanot

Читать полностью…

መዓዛ ሃይማኖት በጎ አድራጎትና ጉዞ ማህበር

ማኅደረ ጥያቄ

1.በቤተክርስቲያን ሻማ ምሳሌነቱ ምንድን ነው?

2. ወንጌል የሚለው ቃል ሲተረጎም

3. ዕጣን በቤተክርስቲያን ያለው ምሳሌነቱ ምንድነው

4. ርዕሰ መነኮሳት በመባል የሚታወቀው አባት ማን ነው?

5. ስለስንበተ-ክርስቲያንና ስለ ዕለተ ምጽአት የሚናገረው ቅዳሴ የማን ቅዳሴ ነው?

መልሱን እስከ ማታ3:00 ሰዓት በ @Asitmeherobot  አድርሱን

Читать полностью…

መዓዛ ሃይማኖት በጎ አድራጎትና ጉዞ ማህበር

ማኅደረ ጥያቄ

1.በቤተክርስቲያን ሻማ ምሳሌነቱ ምንድን ነው?

2. ወንጌል የሚለው ቃል ሲተረጎም

3. ዕጣን በቤተክርስቲያን ያለው ምሳሌነቱ ምንድነው

4. ርዕሰ መነኮሳት በመባል የሚታወቀው አባት ማን ነው?

5. ስለስንበተ-ክርስቲያንና ስለ ዕለተ ምጽአት የሚናገረው ቅዳሴ የማን ቅዳሴ ነው?

መልሱን እስከ ዛሬ 6:00 ሰዓት በ @Asitmeherobot  አድርሱን

Читать полностью…

መዓዛ ሃይማኖት በጎ አድራጎትና ጉዞ ማህበር

ስንክሳር ዘወርሃ ህዳር ስድስት(፮)
@meazahaymanot

Читать полностью…

መዓዛ ሃይማኖት በጎ አድራጎትና ጉዞ ማህበር

ስንክሳር ዘወርሃ ህዳር አምስት(፭)
@meazahaymanot

Читать полностью…

መዓዛ ሃይማኖት በጎ አድራጎትና ጉዞ ማህበር

ማኅደረ ጥያቄ

1. ሀ. ኦሪት ዘፍጥረት

እግዚአብሔርም ኖኅን አለው። የሥጋ ሁሉ ፍጻሜ በፊቴ ደርሶአል፤ ከእነርሱ የተነሣ ምድር በግፍ ተሞልታለችና፤ እኔም እነሆ ከምድር ጋር አጠፋቸዋለሁ።

ኦሪት ዘፍጥረት 6÷13

2. ሐ.

ከእኔ በቀር ሌሎች አማልክት አይሁኑልህ።

ኦሪት ዘጸአት 20÷3

3. ሐ


የኢየሱስ ክርስቶስም ልደት እንዲህ ነበረ። እናቱ ማርያም ለዮሴፍ በታጨች ጊዜ ሳይገናኙ ከመንፈስ ቅዱስ ፀንሳ ተገኘች።

ማቴዎስ ወንጌል 1÷18

4. ለ. ነቢዩ ኤርምያስ

ከእግዚአብሔር ዘንድ ወደ ኤርምያስ የመጣ ቃል፥ እንዲህም አለው። ተነሥተህ ወደ ሸክላ ሠሪው ቤት ውረድ፥ በዚያም ቃሌን አሰማሃለሁ።

ትንቢተ ኤርምያስ 18÷2

5. አቡነ ተክለሃይማኖት
አቡነ ዜና ማርቆስ
አቡነ ሐብተ ማርያም
እናታችን ቅድስት ክርስቶስ ሰምራ
ቅዱስ ያሬድ
ቅድስት ወለተ ጴጥሮስ
አቡነ መድኃኒነ እግዚእ
ቅድስት ወለተ ጳውሎስ
አቡነ ሳሙኤል ዘዋልድባ
ቅድስት ሐይመተ ሥላሴ
አቡነ ሚናስ ዘዋልድባ

የተሣተፉ

1. tomi 5/5

2. Sine T 4/5

3.ናትናኤል 3/5

4. መቅደሰ ማርያም 5/5

5. ታሪክአየሁ 4/5

6. tig 4/5

7. እግዚአብሔር እረኛዬ ነው 5/5

8. ኢየሩሳሌም 4/5


ለተሣተፉት ቃለ ሕይወትን ያሰማልን መንግሥተ ሰማያትን ያውርስልን

Читать полностью…

መዓዛ ሃይማኖት በጎ አድራጎትና ጉዞ ማህበር

ስንክሳር ዘወርሃ ህዳር አራት (፬)
@meazahaymanot

Читать полностью…

መዓዛ ሃይማኖት በጎ አድራጎትና ጉዞ ማህበር

​​♦✟✞✟ኖላዊነ ሔር መድሐኔዓለም✟✞✟♦

ኖላዊነ ሔር መድሐኔዓለም
ለነፍስ ወለሥጋ ወለኵሉ ዓለም
ዕቀበነ ዕቀበነ ዕቀበነ ለዓለም ዓለም/፪/

/አዝማች/

ድምጼን ይለዩታል በጎቼ በሙሉ
አያሥታቸውም መንገደኛ ሁሉ
በራሡ በአምላክ የተባለላችሁ
በጎች ተሠብሰቡ ወደ በረታችሁ

/አዝማች/

ነብይ ነኝ የሚል የሠፈር ዜናዊ
አድርጎ የሾመ ራሡን ወንጌላዊ
ነጣቂ ተኩላው ተበራክቷልና
መንጋኽን ጠብቀው በዕምነት እንዲጸና

/አዝማች/

ከአምላክ የተላከ እውነተኛ እረኛ
ለመንጋው የሚያስብ ያይደለ ምንደኛ
ፊት የተማረ ነው ኋላም የተሾመ
በሐዋርያዊ ክኅነት በእውነት የታተመ

/አዝማች/

ከጌታ የመጣ ከአልሆነ ክኅነቱ
ከአበው የተለየ ከሆነ ትምሕርቱ
በበሩ የአልገባ ሌባ ነው ሥለ አለ
ምዕሠናን አትስሙት አሣቹ ሥለ አለ

/አዝማች/

ጩኸታችን ሠምተኽ ጭንቃችን አይተኽ
በየዘመናችን የሚታደግ ልከኽ
እውነተኛ መምሕር የበጎች እረኛ
አንተው አሠማራን ተመልከት ወደ እኛ።

ለኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ልጆች👇
•➢ ሼር // SHARE

@meazahaymanot
@meazahaymanot

Читать полностью…

መዓዛ ሃይማኖት በጎ አድራጎትና ጉዞ ማህበር

ማኅደረ ጥያቄ

1. በመጽሐፍ ቅዱስ ውስጥ ረጅም ዕድሜ የኖረው ሰው ማነው

ሀ. ማቱሳላ

ለ. ላሜሕ

ሐ. አብርሃም

መ. አዳም

2. የአብርሃም የስሙ ትርጉም ምን ማለት ነው

ሀ. ታጋሽ

ለ. የእምነት ሰው

ሐ. እግዚአብሔር ታማኝ

መ. የአሕዛብ አባት

3. የመጥምቁ ዮሐንስ እናት ማን ትባላለች

ሀ. ኤልዛቤል

ለ. ሃና

ሐ. ኤልሳቤጥ

መ. ርብቃ

4. ኤልሮኢ ማለት ምን ማለት ነው

ሀ. በውኑ የሚያየኝን አየሁት

ለ. ምርኮም ፈጠነ ብዝበዛም ቸኮለ

ሐ. እግዚአብሔር ታላቅ ነው

5. ይዲድያ የስሙ ትርጉም ምን ማለት ነው

ሀ. በእግዚአብሔር የተቀባ

ለ. በእግዚአብሔር የተወደደ

ሐ. የእግዚአብሔር ባርኮት

መ. የእግዚአብሔር ኃይል

መልሱን እስከ ነገ 6:00 ሰዓት በ @Asitmeherobot አድርሱን

#መልካም_እድል

Читать полностью…

መዓዛ ሃይማኖት በጎ አድራጎትና ጉዞ ማህበር

ከአሁን ጀምሮ እንደተለመደው ለቻናላችን ያላችሁን ሀሳብ አስተያየት ማቅረብ ትችላላችሁ። ቢኖሩ፣ ቢስተካከሉ የምትሏቸው ጉዳዮች ላይ አተኩራችሁ ስማችሁንና ከየት ሀገር እንደሆናችሁ እየገለጻችሁ በድምጽ ሆነ በጽሑፍ ላኩልን። ቤተሰቦቻችን የት የት እንዳሉም እንድናውቅና እንድንተዋወቅ ይረዳናል     ላይ @misiwani_Bot እንጠብቃችኋለን

ሐሳብ አስተያየታቸውን ጻፉልን

Читать полностью…

መዓዛ ሃይማኖት በጎ አድራጎትና ጉዞ ማህበር

መዝገበ ሥላሴ ያለም ብርሃን ናቸው

መዝገበ ሥላሴ የዓለም ብርሃን ናቸው
ይኸው ለዘላለም ያበራል ሥራቸው(×2)

👇👇👇👇👇👇👇👇👇👇
👉 @meazahaymanot 👈
👉 @meazahaymanot 👈
👉👆👆👆👆👆👆👆👆👆

Читать полностью…

መዓዛ ሃይማኖት በጎ አድራጎትና ጉዞ ማህበር

ስንክሳር ዘህዳር ዘጠኝ

@meazahaymanot

Читать полностью…

መዓዛ ሃይማኖት በጎ አድራጎትና ጉዞ ማህበር

ማኅደረ ጥያቄ

#መልስ

በስመ ሥላሴ ጥያቄ ለበረከት ልሞክር

፩//ሐ

፪//ለ

፫//መ

፬//ሀ

፭// ኅዳር 7 ቀን የሚከበሩ ዓመታዊ የቅዱሳን በዓላት
1.ቅዱስ ጊዮርጊስ ሊቀ ሰማዕታት (ቅዳሴ ቤቱ)
2.ቅዱስ ጊዮርጊስ እስክንድርያዊ
3.ቅዱሳን ዘኖቢስና ዘኖብያ (ሰማዕታት)
4.ቅዱስ ሚናስ ዘተመይ
5.ቅዱሳን መርቆሬዎስና ዮሐንስ (ጻድቃን ወሰማዕት)
6.አባ ናሕርው ሰማዕት

ወርሐዊ በዓላት

1.ሥሉስ ቅዱስ (አብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ)
2.አባ ጊዮርጊስ ዘጋስጫ
3.አባ ሲኖዳ (የባሕታውያን አለቃ)
4.አባ ዳንኤል ዘገዳመ ሲሐት
5.አባ ባውላ ገዳማዊ
6.ቅዱስ አትናቴዎስ ሐዋርያዊ
7.ቅዱስ አግናጥዮስ (ለአንበሳ የተሰጠ)


ኅዳር 8 ቀን የሚከበሩ ዓመታዊ የቅዱሳን በዓላት
1.ቅዱሳን 4ቱ እንስሳ (ኪሩቤል)
2.ቅዱስ አፍኒን ሊቀ መላእክት
3.አባ ቅፍሮንያ ጻድቅ
4.ቅዱስ ቆስጠንጢኖስ ንጉሥ (ዘምስለ ቅዱስ መስቀል)
5.ቅድስት እግዚእ ክብራ

ወርሐዊ በዓላት

1.ቅዱስ ሙሴ ሊቀ ነቢያት
2.አባ ብሶይ (ቢሾይ)
3.አቡነ ኪሮስ
4.አባ ሳሙኤል ዘደብረ ቀልሞን
5.ቅዱስ ማትያስ ሐዋርያ (ከ12ቱ ሐዋርያት)

የተሣተፉ

1. መቅደሰ ማርያም 5/5

2. እግዚአብሔር እረኛዬ ነው 4/5

3. ዮሐንስ 5/5

4. ታሪክአየሁ 4/5

5. Tomi 5/5

6. መንበረ መንግሥት 3/5

7. fanta 3/5

8. yodit 5/5

9.Tamiru 5/5

10. Meron 5/5

11. ወለተኢየሱስ 4/5

12. hirut 5/5

13. ሪች 3/5

14. ስኒ 4/5

15. አሌክሳንደር 4/5

16. የኔነህ 5/5

ለተሣተፉ ቃለ ሕይወትን ያሰማልን መንግሥተ ሰማያትን ያውርስልን

Читать полностью…

መዓዛ ሃይማኖት በጎ አድራጎትና ጉዞ ማህበር

ስንክሳር ዘወርሃ ኅዳር ስምንት (፰)
@meazahaymanot

Читать полностью…

መዓዛ ሃይማኖት በጎ አድራጎትና ጉዞ ማህበር

🔴 #አዲስ_ዝማሬ ዘማሪ ዲያቆን ቃለአብ ክብሮም

Читать полностью…

መዓዛ ሃይማኖት በጎ አድራጎትና ጉዞ ማህበር

 ፩//በቤተክርስቲያን ሻማ ምሳሌነቱ ምንድን ነው?

  ለመንግስተ-ሰማያት ብርሃን
  ለእግዚአብሔር ብርሃን መሆን
   ለቅዱሳን ሕይወት

፪//ወንጌል የሚለው ቃል ሲተረጎም
   ቃለ እግዚአብሔር ማለት ነው
  የክርስቶስ ሕይወት ማለት ነው
  ግብረ ሐዋርያት ማለት ነው
   የምሥራች/መልካም ዜና ማለት ነው
፫// ዕጣን በቤተክርስቲያን ያለው ምሳሌነት
  የቅዱሳን ጸሎት መዓዛ ነው
  የእመቤታችን ምሳሌ ነው
   የተስፋ መንግሥተ ሰማያት ምሳሌ ነው

 ፬//አባ እንጦንስ

፭//ቅዳሴ አትናቴዎስ

የተሣተፉ

1. መቅደሰ ማርያም 5/5

2. Ισαακ μαθεου 4/5

3. ልጅ ቢኒ 5/5

4. tig 5/5

5. Tomi 5/5

6. ታሪክአየሁ 5/5

ለተሣተፉት ቃለ ሕይወትን ያሰማልን መንግሥተ ሰማያትን ያውርስልን

Читать полностью…

መዓዛ ሃይማኖት በጎ አድራጎትና ጉዞ ማህበር

#ኅዳር_6
#ደብረ_ቁስቋም


ኅዳር ስድስት በዚህች ዕለት ክብርት እመቤታችን ከተወደደ ልጇ ጋር ከስደት በሚመለሱበት ጊዜ ደብረ ቁስቋም ገብተው ካገኛቸው ድካም ዐረፉ፡፡

አምላክን የወለደች በድንጋሌ ሥጋ በድንጋሌ ነፍስ የጸናች ክብርት እመቤታችን ከስደት በተመለሰች ጊዜ እንዲህ ሆነ፡- የብርሃን እናቱ ክብርት እመቤታችን ልጇን ይዛ ከእነ ዮሴፍ ጋር ወደ ምድረ ግብፅ ስትሰደድ ግብፅ ደርሰው በዚያ ቢቀመጡም ነገርን ግብፅ አልተመቸቻውም፡፡ ሕዝቡም በሰላም አልተቀበላቸውም፡፡ እንዲያውም በምድረ ግብፅ ብዙ ተሠቃይተዋል፡፡ ከግብፅም ተነሥተው ወደ ኢትዮጵያ በመጡ ጊዜ ግን ኢትዮጵያ ሕዝብ ሁሉ በሰላምና በፍቅር ተቀበላቸው፡፡ ከመንገዱና ከርሃብ ጥሙ ጽናት የተነሣ እጅግ ደክማለችና የኢትዮጵያ ሰዎች እመቤታችንን አይተው እጅግ አዘኑላት፡፡ ‹‹ይህችስ የነገሥታት ዘር ትመሥላለች ነገር ግን አንዳች ችግር አጋጥሟት ተሰዳ ወደ ሀገራችን መጥታለች..›› ብለው እንክብካቤን አደረጉላት፡፡ እግራቸውን አጥበው በክብር ማረፊያዎች ላይ አሳረፏቸው፡፡ መልካም መስተንግዶም አደረጉላቸው፡፡ እመቤታችንም ከድካሟ ካረፈች በኋላ ሀገሪቱን በእጅጉ ወደደቻትና የተወደደ ልጇን ‹‹ይህን ሀገርና ሕዝቧን በመላ ወድጃቸዋልሁና በዚህ እስከ መጨረሻው እንኑር›› አለችው፡፡ ጌታችንም ክብርት እናቱን ‹‹ይህች ቅድስት ሀገር ናት፣ በኋለኛው ዘመን የቅዱሳን መነኮሳት ቦታ ትሆናለች፡፡ በውስጧም እስከ ዓለም ፍጻሜ ድረስ እመሰገንባታለሁ፤ የአንቺም ስም ሳይጠራ አይውልባትም›› አላት፡፡

ከዚህም በኋላ ጌታችን ደመና ጠቅሶ በእርሷ ላይ ተቀመጡ፡፡ መልአኩ ቅዱስ ዑራኤልም መጣና እየመራቸው መላ ኢትዮጵያን ጎበኟት፡፡ እመቤታችንም ሀገሪቱንና ሕዝቦቿን ወዳቸዋለች ደስም ተሰኝታባቸዋለችና ጌታችን ለክብርት እናቱ ‹‹ይህችን ቅድስት ሀገር አሥራት አድርጌ ሰጠሁሽ›› አላት፡፡ እመቤታችንም እጅግ ተደስታ ‹‹ልጄ አምላኬ›› ብላ አመሰገነችው፡፡ ከዚህም በኋላ ከአንዱ ቦታ ወደ አንዱ ቦታ እየተዘዋወሩ መላዋ ኢትዮጵያን በኪደተ እግራቸው ባረኳት፡፡ ጌታችንም ‹‹በዚህ ቦታ እንዲህ ዓይነት ቤተ ክርስቲያን ይታነጻል፤ እከሌ የሚባል እንዲህ ዓይነት ቅዱስ ይነሣል…›› እያለ ብዙ ምሥጢራትን ለክብርት እናቱ ነገራት፡፡ ከዚህም በኋላ የስደቱ ዘመን ሲያልፍ ሄሮድስም በመጨረሻ ክፉ አሟሟትን ሲሞት መልአኩ ወደ ገሊላ አውራጃ እንዲመለሱ ነገራቸው፡፡ እመቤታችንም ‹‹ከዚህች ሀገርስ ባንሄድ እመርጣለሁ›› ስትለው የተወደደ ልጇ ግን ‹‹እናቴ ሆይ ጽድቅንና ፈቃድን ሁሉ ልንፈጽም ይገባናል›› ብሎ አጽናናትና ወደ ሀገራቸው ተመልሰው ሄዱ፡፡

ተመልሰውም ሊሄዱ ሲነሡ የኢትዮጵያ ሰዎች ልዩ ልዩ አምሐ እጅ መንሻ ሰጧቸው፡፡ ልዩ ልዩ ልብሶች፣ ወርቅ፣ ዕጣን፣ ከርቤ፣ ሽቱ እና ሥንቀቸውን በግመሎች ላይ ጭነው እመቤታችንንና የተወደደ ልጇንም በበቅሎ ላይ አስቀምጠው በክብር ሸኟቸው፡፡ እመቤታችንም ልጇን ታቅፋ በበቅሎ ተቀምጣ በበረሃው በመጓዝ ወደ መጣችበት አገር ሄደች፡፡ ኢትዮጵያንም የሰጧትን ብዙ እጅ መንሻዎች በግመሎች ጭና ይዛ ወደ አገሯ በተመለሰች ጊዜ ከአንድ ባሕር ዳር ደረሰች፡፡ ከዚያም የጀልባውን ባለቤት ‹‹እግዚአብሔርን ስለመውደድ አሻግረኝ›› ብላ ለመነችው፡፡ ባለጀልባውም ‹‹እነሆ ዕቃ የተጫኑ አምስት ግመሎችና ከአንቺ ጋር ከዚህም ሕፃን ጭምር አምስት ሰዎች እመለከታለሁ፣ አንቺ የተቀመጥሽባት በቅሎም አለች፡፡ ጀልባዋም ታናሽ ናት፣ የመቀመጫ ክፍሏም በውስጧ የተሳፈሩት ሰዎችም ተጨናንቀው ነው ያሉት፡፡ ስለዚህ እንዴት ላሻግርሽ እችላለሁ? ነገር ግን እመቤቴ ሆይ! ይቅርታ አድርጊልኝ ይህን በክፋት አላደረግሁትምና›› አላት፡፡

ክብርት እመቤታችንም የጀልባው ባለቤት ሊያሻግራት እንዳልቻለ በተረዳች ጊዜ ‹‹ልጄ ሆይ የእግዚአብሔር ልጅ እንደመሆንህ ይህን ትልቅ ወንዝ ለመሻገር የአምላክነትህን ሥራ ትሠራ ዘንድ እለምንሃለሁ›› ስትል ማለደችው፡፡ ያንጊዜም ጌታችን ክብርት እናቱን ‹‹የወለደሽኝ እናቴ ሆይ! አትዘኝ›› ብሎ አረጋጋት፡፡ ዳግመኛም ‹‹በእኔ ፈቃድ በአባቴ ፈቃድ በመንፈስ ቅዱስ ፈቃድ ካንቺ ሰው ሆኛለሁና ሰው መሆኔንም ከአባቴ በቀር መስተፍሥሒ ከሚሆን ከመንፈስ ቅዱስም በቀር ያወቀ የለም፡፡ ዳግመኛም በሕያዋንና በሙታን ለመፍረድ ለሁሉም እንደየሥራው እከፍለው ዘንድ እመጣለሁ፡፡ ያችንም ሰዓት የሰማይ መላእክትም ቢሆኑ የአዳም ልጆችም ቢሆኑም ከእኔና ከአባቴ ከመንፈስ ቅዱስም በቀር የሚያውቃት የለም፡፡ ያንጊዜ ‹ዐመፅን የሚናገር አንደበት ሁሉ ይዘጋል› ብሎ አባትሽ ዳዊት እንደተናገረ እከራከራለሁ የሚል አንደበት እንደድዳ ምላሽ ያጣል›› አላት፡፡

ክብርት እመቤታችን ማርያምም ይህንን ሁሉ ምሥጢር የተወደደ ልጇ የነገራትን ታስተውለው በልቧም ትጠብቀው ነበር፡፡ ጌታችንም አምላካችን መድኃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስም ለክብርት እናቱ ይህንን ከነገራት በኋላ ቀኝ እጁን ዘርግቶ ከወንዙ ማዶ ጢር በሚባል ተራራ ያሉትን ድንጋዮች ጠቀሳቸው፡፡ ያንጊዜም እነዚህ ድንጋዮች እየተገለባበጡ መጥተው እንደ ጀልባ ሆነው በወራጁ ወንዝ ላይ ተንሳፈፉ፡፡ ከዚያም እመቤታችንን ከሕፃኑ ጋር ከነቤተሰቧና ከነጓዟ አሻገረሯት፡፡

እነዚህንም ድንጋዮች ያዩ ሰዎች ሁሉ እጅግ አድንቀው ‹‹ብቻውን ድንቅ ተአምራት ያደረገ፣ እስራኤልን የፈጠረ እግዚአብሔር ይክበር ይመስገን የጌትነቱም ስም የተመሰገነ ነው›› እያሉ አመሰገኑ፡፡ እነዚህም የተባረኩ ሰዎች ወንዙን ከተሻገሩ በኋላ በዚህች አገር ለስምንት ቀን ተቀመጡ፡፡ ከዚህም በኋላ አምላክን የወለደች በድንጋሌ ሥጋ በድንጋሌ ነፍስ የጸናች ክብርት እመቤታችን ስለደረገላት መልካም ሥራ ሁሉ እግዚአብሔርን ፈጽማ እያመሰገነች ወደ አባቷ ወደ ዳዊት አገር ተመለሰች፡፡

ዳግመኛም በኋለኛው ዘመን ጌታችን በዚህ በደብረ ቍስቋም ቅዱሳን ሐዋርያቶቹን ሰበሰባቸውና ታቦትንና ቤተ ክርስቲያንን አክብሮ የቍርባን መሥዋዕትንም ሠርቶ ቅዱስ ሥጋውንና ክቡር ደሙን ለወገኖቹ ሰጣቸው፡፡ ለዚህም ነገር የእስክንድርያ አገር ሊቃነ ጳጳሳት ቅዱሳን አባቶቻችን ቄርሎስና ቴዎፍሎስ ምስክሮቹ ሆኑ፡፡

( ስንክሳር ዘተዋሕዶ እና #ገድላት_አንደበት)

Читать полностью…

መዓዛ ሃይማኖት በጎ አድራጎትና ጉዞ ማህበር

ተመየጢ ተመየጢ እግዝእትየ ማርያም ሀገረኪ (፪)
ወኢትጐንድዪ በግብፅ በግብፅ ከመ ዘአልብኪ ቤተ (፪)

Читать полностью…

መዓዛ ሃይማኖት በጎ አድራጎትና ጉዞ ማህበር

ማኅደረ ጥያቄ

1.በቤተክርስቲያን ሻማ ምሳሌነቱ ምንድን ነው?

2. ወንጌል የሚለው ቃል ሲተረጎም

3. ዕጣን በቤተክርስቲያን ያለው ምሳሌነቱ ምንድነው

4. ርዕሰ መነኮሳት በመባል የሚታወቀው አባት ማን ነው?

5. ስለስንበተ-ክርስቲያንና ስለ ዕለተ ምጽአት የሚናገረው ቅዳሴ የማን ቅዳሴ ነው?

መልሱን እስከ ነገ 6:00 ሰዓት በ @Asitmeherobot  አድርሱን

Читать полностью…

መዓዛ ሃይማኖት በጎ አድራጎትና ጉዞ ማህበር

ብጹዕ አቡነ ጴጥሮስ የቅዱስ ሲኖዶስ ዋና ጸሐፊ እና ብጹዕ አቡነ ሄኖክ የአዲስ አበባ ሀገረ ስብከት ሊቀ ጳጳስ በተለያየ ሰዓታት በጥይት ተመትተው ሕከምና ላይ ያሉት መልአከ መንክራት አባ ኤርምያስን ጠይቀው አጽናንተው ተመልሰዋል።

Читать полностью…

መዓዛ ሃይማኖት በጎ አድራጎትና ጉዞ ማህበር

ማኅደረ ጥያቄ

፩. የኖህ ታሪክ የተጻፈው በየትኛው የመጽሐፍ ቅዱስ ክፍል ውስጥ ነው

ሀ. ኦሪት ዘፍጥረት

ለ. ኦሪት ዘዳግም

ሐ.ኦሪት ዘሌዋውያን

መ. ኦሪት ዘጸአት

፪. ከአሥርቱ ትእዛዛት ውስጥ የመጀመሪያው ትእዛዝ ምንድነው

ሀ. አትስረቅ

ለ. በሐሰት አትመስክር

ሐ.ከእኔ በቀር ሌሎች አማልክት አታምልክ

መ. አታመንዝር

፫. የጌታችን የመድኃኒታችን የኢየሱስ ክርስቶስ እናት ማን ትባላለች

ሀ. ቅድስት ሐና

ለ.ቅድስት ኤልሳቤጥ

ሐ. ቅድስት ማርያም

መ. ቅድስት ማርታ

፬. እግዚአብሔር ወደ ሸክላ ሰሪው የላከው ነቢይ ማነው

ሀ. ነቢዩ አሞጽ

ለ. ነቢዩ ኤርሚያስ

ሐ. ነቢዩ ኢሳይያስ

መ. ነቢዩ ሐጌ

፭. ኢትዮጵያውያን ቅዱሳን የሚባሉትን ጻፉ

መልሱን እስከ  ማታ 3:00 ሰዓት በ @Asitmeherobot አድርሱን


        #መልካም_እድል

Читать полностью…

መዓዛ ሃይማኖት በጎ አድራጎትና ጉዞ ማህበር

ማኅደረ ጥያቄ

፩. የኖህ ታሪክ የተጻፈው በየትኛው የመጽሐፍ ቅዱስ ክፍል ውስጥ ነው

ሀ. ኦሪት ዘፍጥረት

ለ. ኦሪት ዘዳግም

ሐ.ኦሪት ዘሌዋውያን

መ. ኦሪት ዘጸአት

፪. ከአሥርቱ ትእዛዛት ውስጥ የመጀመሪያው ትእዛዝ ምንድነው

ሀ. አትስረቅ

ለ. በሐሰት አትመስክር

ሐ.ከእኔ በቀር ሌሎች አማልክት አታምልክ

መ. አታመንዝር

፫. የጌታችን የመድኃኒታችን የኢየሱስ ክርስቶስ እናት ማን ትባላለች

ሀ. ቅድስት ሐና

ለ.ቅድስት ኤልሳቤጥ

ሐ. ቅድስት ማርያም

መ. ቅድስት ማርታ

፬. እግዚአብሔር ወደ ሸክላ ሰሪው የላከው ነቢይ ማነው

ሀ. ነቢዩ አሞጽ

ለ. ነቢዩ ኤርሚያስ

ሐ. ነቢዩ ኢሳይያስ

መ. ነቢዩ ሐጌ

፭. ኢትዮጵያውያን ቅዱሳን የሚባሉትን ጻፉ

መልሱን እስከ  ነገ 7:00 ሰዓት በ @Asitmeherobot አድርሱን


        #መልካም_እድል

Читать полностью…

መዓዛ ሃይማኖት በጎ አድራጎትና ጉዞ ማህበር

ስንክሳር ዘወርሃ ህዳር ሦስት (፫)
@meazahaymanot

Читать полностью…
Subscribe to a channel