meazahaymanot | Unsorted

Telegram-канал meazahaymanot - መዓዛ ሃይማኖት በጎ አድራጎትና ጉዞ ማህበር

3925

"ውድስት አንቲ በአፈ ነቢያት ወስብሕት በሐዋርያት አክሊለ በረከቱ ለያዕቆብ ወትምክህተ ቤቱ ለእስራኤል፡፡" "በነቢያት በሐዋርያት አንደበት የተመሰገንሽ የያዕቆብ የበረከቱ ዘውድ የእስራኤል ወገን መመኪያ አንቺ ነሽ"                  መጽሐፈ ሰዓታት የፌስቡክ ፔጃችን www.fb.me/meazhaimanot ይቀላቀሉን

Subscribe to a channel

መዓዛ ሃይማኖት በጎ አድራጎትና ጉዞ ማህበር

እንደ ቸርነትህ እንጅ
እንደ በደሌ አልሆነም
ምህረትህ የበዛልኝ
ይቅር ባይ ለዘላለም
ሲዝትብኝ ጠላቴ
አንተ ታጽናናኛለህ
በቃልህ እያበረታህ
ሁሌም ከእኔ ጋራ አለህ

ለውለታህ አመስግኘ
ለክብርህ እዘምራለሁ
ስምህ እየጣፈጠኝ
በፍቅር አመልክሃለሁ
ለመፍረድ አትቸኩልም
ሁሌም ትምረኛለህ
መልካሙ እረኛዬ ሆይ
እኔን ትጠብቃለህ

ምን አለ ያላረክልኝ
ያጎደልክብኝስ ከቶ
ውበት ጌጤ ሆነህልኝ
እኖራለሁ ሁሉ ተሟልቶ
ሰላም አለ ከቤትህ
አልመኝም ወደ ሌላ
ውብ ቃላት አፈለቀ
በአፌ ምስጋና ሞላ

ኃጢዓት በበዛበት ፀጋህ እየበዛልኝ
ወረት በሌለው ፍቅርህ
ጌታዬ እየወደድከኝ
በሰጠህኝ ዘመን ሁሉ
ለስምህ እዘምራለው
አባቴ ንገስ በልቤ
ክበርልኝ እልሃለው

በዛለው ትከሻዬ ላይ
ዓለም ጓዟን ጨምራብኝ
አቀርቅሬ አለቅሳለሁኝ
መከራው ተፈራርቆብኝ
አንተ ግን አይተህ ጠራኸኝ
ሸክሜንም ተሸከምከው
ከጠላት ነፃ አውጥኸኝ
በእጅህ አርፋለው


አቤቱ፥ ምሕረትህን እንዴት
አበዛህ! የሰው ልጆች
በክንፎችህ ጥላ ይታመናሉ።
❏  መዝሙር 36፥7

ዘማሪ ገብረአምላክ ደሳለኝ


/channel/meazahaymanot

Читать полностью…

መዓዛ ሃይማኖት በጎ አድራጎትና ጉዞ ማህበር

ማኅደረ ጥያቄ

፩.  ስግደት ስንት ዐይነት ነው?

፪.ለቅዱሳን መስገድን ያስተማረው ማን ነው

፫.እግዚአብሔር ቃል በቃል ለቅዱሳን ስግደት እንደሚገባ የተናገረበት የመጽሐፍ ቅዱስ ክፍል ጻፉ

፬.የሚሰገድባቸው ጊዜያት ጻፉ

፭. የማይሰገድባቸው ጊዜያት ጻፉ

መልሱን እስከ ማታ 3:00 ሰዓት በ
@Asitmeherobot አድርሱን

መልሱን ከላይ ባለው ሊንክ ብቻ ይላኩ

     ሁለተኛ ዙር ማኅደረ ጥያቄ

Читать полностью…

መዓዛ ሃይማኖት በጎ አድራጎትና ጉዞ ማህበር

ስንክሳር ዘወርሃ ታህሣሥ ስድስት(፮)

Читать полностью…

መዓዛ ሃይማኖት በጎ አድራጎትና ጉዞ ማህበር

የአምላክ ዐቃቤ ሕግ

ገባሬ መንክራት በገድሉ ያወቅነው
የእግሮቹ ትቢያ የአራዊት ስንቅ ነው
ገብረ መንፈስ ቅዱስ
የአምላክ ዐቃቤ ሕግ
የኢትዮጵያ ዋስ ነው ፈጥኖ የሚታደግ

🎤🎤🎤🎤🎤🎤🎤🎤🎤🎤🎤🎤🎤
እልልልልልል እልልልልልል 🕊️🕊️🕊️እልልል
🌹🌹🌹🕊🕊🕊🍂🍂🍂🍃🍃🥀🥀🥀☘☘🌿🌿🌿🌿👏👏👏👏👏🌾🌾🌾🌷🌷🍃🍂🌹🍂🌹🌹🌺🌺🌺🌺
እልልልልልልልልልልልልልልልልልልልልልልል

🕊🕊🎤🌹🌹🌹🌹🥀🌻🍃🍃🍃🍂🍂🍂👏👏🍀🍀🍀እልልልልል✝🌹🌹🥀🥀🎤🎤እልልልልልልልልል🍂🍂🍂🌹🥀🥀🥀

እልልልልልልልልልልል 🎤🌹🌹🌹🍀🍀👏👏🕊🕊🌻🌻🍃🥀🌹 🥀🌻🌻🌻🌹🌹🌹ዝማሬ መላእክት  ያሰማልን 🎤🎤🍂🍂🍂🍂🥀🥀🥀🥀🌻🌻🌻✝🌺🌺

Читать полностью…

መዓዛ ሃይማኖት በጎ አድራጎትና ጉዞ ማህበር

*ታኅሣሥ ፭ የዕለቱ ስንክሳር*
በመጋቤ ሐዲስ ቀሲስ አበበ
ለመምህራችን ቃለ ሕይወትያሰማልን
*
@meazahaymanot

Читать полностью…

መዓዛ ሃይማኖት በጎ አድራጎትና ጉዞ ማህበር

ማኅደረ ጥያቄ

1. ጸሎት በስንት ይከፈላል?

2. በጸሎት ሕይወታችን ለማደግ ምን እናድርግ?

3. ዕሹ ታገኛላችሁ ለምኑ ይሰጣችኋል ደጁ ምቱ ይከፈትላችኋል”ይህ የመጽሐፍ ቅዱስ ቃል በየትኛ መጽሐፍ ክፍል ይገኛል ?

4. የጸሎት አቅጣጫ ምስራቅን የተመለከተ መሆን አለበት ለምን?

5.ምን አይነት ጸሎት በየትኛው ሰዓት ይጸለይ?

መልሱን እስከ ነገ 3:00 ሰዓት በ   @Asitmeherobot አድርሱን
    👆👆👆👆👆
መልሱን ከላይ ባለው ሊንክ ይላኩ

#መልካም_እድል



  ሁለተኛ ዙር ማኅደረ ጥያቄ

Читать полностью…

መዓዛ ሃይማኖት በጎ አድራጎትና ጉዞ ማህበር

ስንክሳር ዘወርሃ ታህሣሥ አራት(፬)

@meazahaymanot

Читать полностью…

መዓዛ ሃይማኖት በጎ አድራጎትና ጉዞ ማህበር

አቡነ ዜና ማርቆስ አባታቸው ዮሐንስ እናታቸው ማርያም ዘመዳ /ዲቦራ/ ይባላሉ፡፡ አባታቸው ዮሐንስ የአቡነ ተክለ ሃይማኖት አባት የአቡነ ጸጋ ዘአብ ወንድም ናቸው፡፡ እናታቸው ደግሞ የአቡነ ቀውስጦስ እኅት ናቸው፡፡ አቡነ ዜና ማርቆስ በወንጌላዊው ቅዱስ ማርቆስ ብሥራት የተጸነሱ አባት ናቸው፡፡ እኚህ አባት በተወለዱ በሦስተኛው ቀን ከእናታቸው እቅፍ ወርደው እሰግድ ለአብ እሰግድ ለወልድ እሰግድ ለመንፈስ ቅዱስ ብለው ሦስት ጊዜ ሰግደዋል፡፡
በ40 ቀናቸውም ሊጠመቁ ወደ ቤተክርስቲያን በወሰዷቸው ጊዜ ካህኑ በመጽሐፍ የሚያደርሱትን ሥርዓተ ጥምቀት እሳቸው በቃል አድርሰውታል፡፡ ሲያጠምቋቸውም ለአብ ለወልድ ለመንፈስ ቅዱስ እሰግዳለሁ ብለው ሦስት ጊዜ ሰግደዋል፡፡ በዚህ ጊዜ ውኃው ፈላ የ 72 ዓመት አጎታቸው እንድርያስ ይህን ተአምር ዐይተው ፈሩ ወደ ቤተ መቅደስ ሮጡ፡፡ መልአኩ ቅዱስ ሩፋኤል ምን አስፈራህ መላጣህን ተቀብተኸው ቢሆን ፀጉር ባበቀለ ነበር አላቸው እሳቸውም ተመልሰው ከውኃው ቢቀቡት ፀጉር አበቀለላቸው፡፡
አቡነ ዜና ማርቆስ 5 ዓመት በሆናቸው ጊዜ ወላጆቻቸው ወስደው ለመምህር ሰጣቸው በሦስት ዓመት ብሉይ ከሐዲስ አጥንተው በስምንት ዓመታቸው መዓረገ ዲቁና ለመቀበል ወደ አባ ቄርሎስ ሄዱ፡፡ ተቀብለው ሲመለሱ ሳይንት በምትባል ቦታ ላይ ሽፍቶች አግኝተዋቸው የእጃቸውን በትር ሳይቀር ነጠቋቸው አቡነ ዜና ማርቆስም አዘኑ ወደ እግዚአብሔር ቢያመለክቱ በትራቸው እባብ ሆኖ ሽፍቶቹን ነደፋቸው፡፡
30 ዓመት በሆናቸው ጊዜ ቤተሰባቸው ማርያም ክብራ የምትባል ደግ ሴት አጭተው አጋቧቸው ልማደ መርዓዊ ወመርዓት ያድርሱ ብለው መጋረጃ ጥለውባቸው ሄዱ፡፡ አቡነ ዜና ማርቆስም አንቺ እኅቴ ይህ ዓለም ኃላፊ ጠፊ ነው ምን ይረባናል ብለን እናደርገዋለን አሏት፡፡ እርሷም ብንተወው እወዳለሁ አለቻቸው፡፡ ኮብላይ ለልማዱ በሌሊት ይጓዛል እንዲሉ በሌሊት ወጥተው ሄዱ፡፡ ማርያም ክብራን መላእክት ጌተሴማኔ አድርሰዋት 7 ዓመት ኖራ ጥር 2 ቀን ዐርፋለች፡፡ በዛም አንበሦች ቀብረዋታል፡፡ ዋጋን የሚከፍል እግዚአብሔር አምላክም ስለተጋድሎዋ ሦስት አክሊላትን አቀዳጅቷታል፡፡
አቡነ ዜና ማርቆስንም መልአክ እየመራቸው ሀገረ ምሑር አድርሷቸዋል፡፡ በዛም ብዙ ተአምራትን እያሳዩ ሀገረ ገዢውንና ሕዝቡን አሳምነው በሀገረ ምሑር 5 ዓመት ከቆዩ በኋላ ወደ ጉራጌ ሀገር ሄደው አስተምረው ሕዝቡን ወደ እምነት መልሰዋል፡፡ አቡነ ተክለ ሃይማኖት ከዚየሩሳሌም ከተመለሱ በኋላ እኚህ ሁለቱ ቅዱሳን አባቶች ሲገናኙ ትሕትና ልማዳቸው የሆነ አቡነ ዜና ማርቆስ አቡነ ተክለ ሃይማኖትን አገልግለዋቸዋል በአንድነት ሆነውም አረማዊውን ሀገረ ገዢ ድል አሰግድን በተአምራት አሳምነው አጥምቀውታል፡፡ አቡነ ተክለ ሃይማኖት ሊሄዱ በተነሱ ጊዜ መዓረገ ምንኩስና ሰጥተዋቸዋል፡፡ መንገድ ሲሄዱም ዛፉ ድንጋዩ ሁሉ በግራ ቀኝ እየተከተላቸው በቃላቸው ተናግረው በቦታቸው አድንቀዋቸው ሄደዋል፡፡ እስከ ዛሬ ድረስ እነዚህ ዛፎች እንደዘመሙ ይታያሉ፡፡
አቡነ ዜና ማርቆስ መዓረገ ምንኩስና ከተቀበሉ በኋላ ደብረ ብሥራትን ገድመው እያስተማሩ ሲኖሩ ብዙ ተአምራት አድርገዋል፡፡ በ200 አንበሦች በ200 ነብሮች ታጅበው በደመና ተጭነው ደቅ ደርሰው ተመልሰዋል፡፡ በሌላ ጊዜም ቅዳሴ ገብተው ሲያቆርቡ ሰው በዘባቸውና መሸ፡፡ ፀሐይም ልትገባ ሆነ፡፡ ጸልየው ልክ እንደ ኢያሱ አቀብለው እስኪፈጽሙ ድረስ ፀሐይ ባለችበት አቆይተዋታል፡፡ አቡነ ዜና ማርቆስ በ8 እንጀራ 800 መነኮሳትን መግበው 103 መሶብ ተርፎ አንስተዋል፡፡ ከዚህ የበለጠ ብዙ ተአምራትን አድርገዋል፡፡
ከዚህ በኋላ በተስፋቸው ያመነ በቃልኪዳናቸው የተማጸነ ዋጋውን እንደማያጣ እግዚአብሔር አምላክ ነግሯቸው በተወለዱ በ140 ዘመናቸው ታኅሣሥ 3 ቀን ዐረፉ አምላካችን እግዚአብሔር ከአቡነ ዜና ማርቆስ ከበረከታቸው ከረድኤታቸው ያሳትፈን፡፡ የጻድቃን እመቤት ወላዲተ አምላክ ፍቅሯን ታሳድርብን፡፡
ወስብሐት ለእግዚአብሔር

@meazahaymanot
@meazahaymanot
@meazahaymanot

Читать полностью…

መዓዛ ሃይማኖት በጎ አድራጎትና ጉዞ ማህበር

በዓታ ለማርያም



እንኳን አደረሰን

ቅድስት ድንግል ማርያም በ፶፻፬፻፹፭ ዓመተ ዓለም ከሐና እና ከኢያቄም በፈቃደ እግዚአብሔር ተወልዳ እስከ ሦስት ዓመት ድረስ የኖረችው በወላጆቿ ቤት ነበር፡፡ ከዚህ በኋላ ኢያቄምና ሐና የተሳሉትን ስእለታቸውን አስታውሰው ወስደው ለቤተ እግዚአብሔር ሰጧት፤ ካህኑ ዘካርያስም ስለምግቧ በመጨነቁ ሕዝቡን ሰብስቦ ሳለ መልአኩ ፋኑኤል ኅብስት ሰማያዊ ጽዋዕ ይዞ ከሰማይ ወረደ፤ ዘካርያስ ለእርሱ የመጣ ሀብት መስሎት ታጥቆ እጅ ነስቶ ቢቆም ወደ ላይ ራቀበት፡፡ ከስምዖን ጀምሮ በዚያ የተሰበሰቡት ሰዎችም በተራ ቢሞክሩ በተመሳሳይ ወደ ላይ ራቀባቸው፡፡ ምን አልባት ለእንግዶች የመጣ ሀብት እንደሆነ ብለው ሐና እና ኢያቄም እንዲቀርቡ አደረጓቸው፤ ለእነርሱም ራቀባቸው፤ ዘካርያስም ሐናን ‹‹እግዚአብሔር የሚያደርገውን የሚያውቅ የለምና ልጅቷን ትተሸ ወደዚህ ነይ›› ባላት ጊዜ ቅድስት ማርያም ድክ ድክ እያለች እናቷን ስትከተል መልአኩ ፋኑኤል ወደ እርሷ ቀርቦ አንድ ክንፉን አንጥፎ አንድ ክንፉን ጋርዶ መግቧት ዐረገ፤ ሊቀ ካህናቱም ሕዝቡም የምግቧ ነገር ከተያዘልን በቤት እግዚአብሔር ትኑር ብለው አስገቧት፤ይህም ታኅሣሥ ፫ ቀን ነበር፡፡

ድንግል ማርያምም ሰማያዊ ኅብስትና መጠጥ እየተመገበች ፲፪ ዓመት በቤተ መቅደስ ኖረች፡፡ ፲፭ ዓመት ሲሞላት ግን ለአቅመ ሔዋን በመድረሷ ከቤተ መቅደስ ትውጣልን በማለት አይሁድ በጠላትነት ተነሱባት፡፡ ካህኑ ዘካርያስም ይህን ሰምቶ እመቤታችንን ጠየቃት «ኦ ወለተ እስራኤል እፎ ትፈቅዲ ትንበሪ፤ ልጄ እንደምን ሆነሽ ልትኖሪ ትወጂያለሽ?» አላት፡፡ እርሷም «ከእግዚአብሐር በታች ያለኸኝ አባት አንተ ነህ፤ በዚያውም ላይ እናት አባቴ አደራ ያሉህ አንተን ነው፤ ወደ እግዚአብሔር አመልክትልኝ፤» አለችው፡፡ ዘካርያስም ጸለየ፤ እግዚአብሔርም ከነገደ ይሁዳ ሚስቶቻቸው የሞቱባቸውን በትራቸውን ሰብስበህ በቀዳማይ ሰዓተ ሌሊት ከቤተ መቅደስ አግብተህ ስትጸልይ አድረህ በቀዳማይ ሰዓተ መዓልት አውጣው ብሎ ምልክትም እሳይህአለው ብሎ ነገረው፡፡ እርሱም እንዳለው አድርጎ በማግሥቱ በትሮቹን አውጥተው ቢያዩ የዮሴፍ በትር አብባና አፍርታ ተገኘች፡፡ ከበትሩ ጫፍ ላይ «ኦ ዮሴፍ ወልደ ዳዊት ዕቀባ ለማርያም ፍኅርትከ፤ ዮሴፍ ሆይ እጮኛህ ማርያምን ጠብቃት፤» የሚል ጽሑፍ አገኙ፤ርግብም መጥታ በራሱ ላይ አርፋለች፤ ስለሆነም ዮሴፍ እንዲጠብቃት ተወሰነ፡፡

@meazahaymanot
@meazahaymanot
@meazahaymanot

Читать полностью…

መዓዛ ሃይማኖት በጎ አድራጎትና ጉዞ ማህበር

ማኅደረ ጥያቄ

#መልስ

1. ጸሎት፡- ቃሉ ግእዝ ነው፡፡ ጸለየ ለመነ ከሚለው ግሥ የወጣ ሲሆን ጸሎት፡- ማለት ልመና ነው፡፡ ጸሎት ምስጋናም ነው “ይትቀደስ ስምከ” /ስምህ ይቀደስ/ ስንል ምስጋና ነው፡፡ “ሲሳየነ ዘለለዕለትነ ሀበነ ዮም” /የዕለት ምግባችንን ዛሬ ስጠን/ ስንል ደግሞ ልመና ነው፡፡ እንዲሁም ጸሎት፡- ሰው ከልዑል እግዚአብሔር ጋር የሚነጋገርበት ነው፡፡ /ፍትሐ ነገሥት አንቀጽ 14/

2. በፍጹም እምነት መጸለይ ይገባል
በፍጹም እምነት የምንጸልየውን ጸሎት እግዚአብሔር ይቀበለዋል እየተጠራጠርን የምንጸልየውን ጸሎት ግን እግዚአብሔር አይቀበለውም፡፡ ጥርጥር ትልቅ የሰው ባለጋራ /ጠላት/ ነው፡፡ ጥርጥርን ማስወገድ ያስፈልጋል “አምናችሁ በጸሎት የምትለምኑትን ሁሉ ትቀበላላችሁ” /ማቴ. 21፡22/
በቅን ልቡና፣ በንጹሕ ልብ መጸለይ ይገባል
በቅን ልቡና፣ በንጹሕ ልብ የምንጸልየውን ጸሎት እግዚአብሔር ይቀበለዋል፡፡ ልባችንን የቂም በቀልና የክፋት ምሽግ አድርገን የምንጸልየውን ጸሎት ግን እግዚአብሔር አይቀበለውም፡፡ “ጸሎቱ ለመስተቀይም ከመዘርዕ ዘወድቀ ማእከለ አሥዋክ” /የቂመኛ ሰው ጸሎት በእሾህ መካል እንደ ወደቀ ዘርዕ ነው/ /መጽሐፈ መነኮሳት/፡፡
ሀሳባችንን ሰብስበን አንድ ልብ በመሆን መጸለይ ይገባል
ቅዱሳን አባቶቻችን ሐዋርያት የጰራቅሊጦስ ዕለት አንድ ልብ ሆነው ሲጸልዩ መንፈስ ቅዱስ ወርዶላቸዋል፡፡ /የሐ. ሥራ 2፡1-4/
በመፍራት ማለት ንስሐ በመግባት ከልብ በመጸጸት መጸለይ ይገባል /ፍትሐ ነገሥት አንቀጽ 14/
ነቢዩ ሕዝቅያስ በመፍራትና ከልብ በመጸጸት ሆኖ ስለጸለየ በዕድሜው ላይ አሥራ አምስት ዓመት ተጨምሮለታል፡፡ /2ኛ ነገሥት 20፡1-6/ /ኢሳ. 38፡1-5/
በጸሎት ጊዜ ቀጥ ብሎ መቆም እንደሚያስፈልግ ሥርዓት ተሠርቷል
“በጽባሕ እቀውም ቅድሜከ ወአስተርኢ ለከ”
/በማለዳ በፊትህ እቆማለሁ እታይሀለሁም/ /መዝ. 5፡3/
ፊትን ወደ ምሥራቅ መልሶ መጸለይ ይገባል

በጸሎት ጊዜ መስገድ ይገባል
ይኸውም ጸሎቱን ስንጀምርና ስንጨርስ እንዲሁም በጸሎት ጊዜ ስግደትን ከሚያነሳ አንቀጽ ስንደርስ መስገድ ይገባል፡፡ /ፍትሐ ነገሥት አንቀጽ 14/
ጸሎት ስንጀምር በትእምርተ መስቀል /በመስቀል ምልክት/ ማማተብ ይገባል
ስናማትብም ከላይ ወደታች ከግራ ወደ ቀኝ ነው፡፡ ይህም ምሳሌ አለው፡፡ ከላይ ወደታች የምናማትብበት ምክንያት የሰላም አምላክ መድኃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ እኛን ለማዳን ከሰማየ ሰማያት የመውረዱ ምሳሌ ነው፡፡ ከግራ ወደቀኝ የምናማትብበት ምክንያት ደግሞ መድኃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ በመስቀል ላይ ተሰቅሎ፣ ስለእኛ ሞቶ ከሞት ወደ ሕይወት ከኀሣር ወደ ክብር፣ ከሲኦል ወደገነት የመመለሱ ምሳሌ ነው፡፡ በቀኝ ገነት፣ በግራ ሲኦል ይመሰላልና፡፡ /ፍትሐ ነገሥት አንቀጽ 14/

3. ሰው ከእንቅልፍ ነቅቶ ከመኝታው ተነስቶ ገና ሥራ ሳይጀምር የሚጸልየው ጸሎት ነው፡፡ /በነግህ/
በ3 ሰዓት
በ6 ሰዓት
በ9 ሰዓት
በ11 ሰዓት /በሠርክ/
በመኝታ ጊዜ
በመንፈቀ ሌሊት /ከሌሊቱ በ6 ሰዓት/

4.ይህ ዓይነት ግን ከጸሎትና ከጦም በቀር አይወጣም አላቸው።

ማቴዎስ ወንጌል 17÷21

አምናችሁም በጸሎት የምትለምኑትን ሁሉ ትቀበላላችሁ አላቸው።

ማቴዎስ ወንጌል 21÷22


እናንተ ግብዞች ጻፎችና ፈሪሳውያን፥ በጸሎት ርዝመት እያመካኛችሁ የመበለቶችን ቤት ስለምትበሉ፥ ወዮላችሁ፤ ስለዚህ የባሰ ፍርድ ትቀበላላችሁ።

ማቴዎስ ወንጌል 23÷17

የተሣተፉ

1. እግዚአብሔር እረኛዬ ነው4/4

2. መቅደሰ ማርያም 4/4

3. Liya 4/4

4. Ruth 4/4

5. ሰሎሞን 4/4

6. ኤልያብ 4/4

7. Yises4/4

8. ልጅ ቢኒ 4/4

9. tomi 4/4

ለተሣተፉት ቃለ ሕይወትን ያሰማልን መንግሥተ ሰማያትን ያውርስልን

#ሁለተኛ_ዙር_ማኅደረ_ጥያቄ

Читать полностью…

መዓዛ ሃይማኖት በጎ አድራጎትና ጉዞ ማህበር

ልቁም ለምስጋና

@meazahaymanot

Читать полностью…

መዓዛ ሃይማኖት በጎ አድራጎትና ጉዞ ማህበር

እግዚአብሔር ወዶና ፈቅዶ ለዚህች ቀን ደርሰና እግዚአብሔር ይመስገን

ማኅደረ ጥያቄ

፩. ጸሎት ማለት ምን ማለት ነው

፪.በምን አይነት መንገድ መጸለይ አለብን

፫. የጸሎት ጊዜያት ስንት ናቸው

፬. መጽሐፍ ቅዱስ ስለ ጸሎት ምን ይላል

መልሱን እስከ ነገ 6:00 ሰዓት @Asitmeherobot አድርሱን


መልሱን ከላይ ባለው ሊንክ ብቻ ይላኩ

#መልካም_እድል

Читать полностью…

መዓዛ ሃይማኖት በጎ አድራጎትና ጉዞ ማህበር

ስንክሳር ዘወርሃ ታህሣሥ አንድ(፩)

@meazhaymanot

Читать полностью…

መዓዛ ሃይማኖት በጎ አድራጎትና ጉዞ ማህበር

ክቡራን የቻናላችን ተከታታዮች እግዚአብሔር ቢፈቅድና ብንደርስ  01/04/2016 ዓ.ም  9:00 ሰዓት ላይ ‟  ማኅደረ ጥያቄ ይጀምራል እንድትከታተሉ በልዑል እግዚአብሔር ስም እንጠይቃለን።

ሃሳብ አስተያየት @misiwani_Bot
አድርሱን

አንድ ቀን ቀረ


@meazahaymanot
@meazahaymanot
@meazahaymanot

Читать полностью…

መዓዛ ሃይማኖት በጎ አድራጎትና ጉዞ ማህበር

ድንግል ማርያም ሆይ
ድንግል ሆይ ስለ ኢትዮጵያ አሳስቢ
ድንግል ሆይ ስለ ኦርቶዶክስ አሳስቢ
ድንግል ሆይ ስለ ቤተክርስትያናችን አሳስቢ
ድንግል ሆይ ስለ ጳጳሳት አሳስቢ
ድንግል ሆይ አባቶች ካህናት አሳስቢ
ድንግል ሆይ ስለ ዲያቆናት አሳስቢ
ድንግል ሆይ ስለ ሰባክያን ዘማርያን አሳስቢ
ድንግል ሆይ ስለ ምዕመናን አሳስቢ
ድንግል ሆይ ስለ ሞቱት አሳስቢ
ድንግል ሆይ ስለተሰደዱት አሳስቢ
ድንግል ሆይ ስለ ታመሙ አሳስቢ
ድንግል ሆይ ስለታሰሩት አሳስቢ
ድንግል ሆይ ስለ ተራቡ አሳስቢ
ድንግል ሆይ በኃጥያት ስላለነው አሳስቢ
ድንግል ሆይ ስለመከራችን አሳስቢ
ድንግል ሆይ ስለ በደላችን አሳስቢ
ድንግል ሆይ ልጅሽ ይቅርታውን ያድለን ዘንድ ለምኝልን

የያዕቆብ ሌሊት ይሁንልን

Читать полностью…

መዓዛ ሃይማኖት በጎ አድራጎትና ጉዞ ማህበር

ማኅደረ ጥያቄ

፩.  ስግደት ስንት ዐይነት ነው?

ስግደት ሦስት ዓይነት ነው
ሀ/ የአምልኮ ስግደት
ለ/ የጸጋ ስግደት
ሐ/ የአክብሮት ስግደት


፪.ለቅዱሳን መስገድን ያስተማረው ማን ነው።

-  ለቅዱሳን መስገድን ያስተማረው እግዚአብሔር ነው!

ዘፍ. 27፡29፣ ዘፍ.37-41 ፣ዘፍ.37፡7

፫.እግዚአብሔር ቃል በቃል ለቅዱሳን ስግደት እንደሚገባ የተናገረበት የመጽሐፍ ቅዱስ ክፍል ጻፉ

" አሕዛብ ይገዙልህ ሕዝብም ይስገዱልህ፤ ለወንድሞችህ ጌታ ሁን፥ የእናትህም ልጆች ይስገዱልህ፤ የሚረግምህ እርሱ ርጉም ይሁን የሚባርክህም ቡሩክ ይሁን። "
(ኦሪት ዘፍጥረት 27:29)


፬.የሚሰገድባቸው ጊዜያት ጻፉ

- በጸሎት ጊዜ ስግደትን የሚያነሳበት አንቀጽ (ቦታ) ሲደርስ።
- በፆም ወራት
- በሰሞነ ሕማማት
- በቅዳሴ ጊዜ
- በንስሐ ጊዜ
- ስንሳለም


፭. የማይሰገድባቸው ጊዜያት ጻፉ

- በሁለቱ ሰንበታት (ቅዳሜ እና እሁድ)
- በበዓለ ሃምሳ
- በቅዱስ ሚካኤል፣ በእመቤታችን ቅድስት ድንግል ማርያም እና በበዓለወልድ እለታት
- ስጋ ወደሙን ስንቀበል።


የተሣተፉ

1. መቅደሰ ማርያም 5/5

2. ሰሎሞን 5/5

3. Tig 5/5

4. የድንግል ልጅ 5/5

5. liya 3/5

6. Tomi 3/5

ለተሣተፉት ቃለ ሕይወትን ያሰማልን መንግሥተ ሰማያትን ያውርስልን

Читать полностью…

መዓዛ ሃይማኖት በጎ አድራጎትና ጉዞ ማህበር

✞ የዕምነትሽ ጽናት ✞

ታላቅ በሆነው እምነትሽ ታመንኩኝ
ካለሽበት ገስግሼ መጣሁኝ
እናቴ ክብርሽን አንግሼ
ሆንኩኝ እንደ ህፃን ታድሼ
እናቴ ቅድስት አርሴማ
ዝናሽ በአለም ተሰማ

ስመጣ ባ'ልጋ ነበረ
ተስፋዬም የተሰበረ
በእምነትሽ በፀበልሽ
ሰው ሁኜ ቆምኩኝ ደጅሽ
ልናገር ዝናሽን ላውራ
ይደነቅ ያ'ምላክሽ ስራ
ተጋድሎሽ የእምነትሽ ፅናት
ሆኖኛል የእምነቴ መብራት

አዝ.......

ደምግባት ከንቱ ብለሽ
ለሰማይ ክብር የታጨሽ
የእምነቴ ሀሰረ ፍኖት
በምልጃሽ አለሁኝ በህይወት
የልቡን ለነገረሽ
ፈጥኖ ይደርሳል መልስሽ
ዘንባባሽ ህይወት ይዘራል
የጠራሽ ማን አፍሮ ያውቃል

አዝ.......

እርዳታሽ የደረሰለት
ያመጣል የልቡን ስለት
ላመኑሽ ፈውስሽ ቅርብ ነው
ባ'ንች አፍሮ የሄደ ማን ነው
የልቡን ለነገረሽ
ፈጥኖ ይደርሳል መልስሽ
ዘንባባሽ ህይወት ይዘራል
የጠራሽ ማን አፍሮ ያውቃል

አዝ.......

ስመጣ ባ'ልጋ ነበረ
ተስፋዬም የተሰበረ
በእምነትሽ በፀበልሽ
ሰው ሁኜ ቆምኩኝ ደጅሽ
ልናገር ዝናሽን ላውራ
ይደነቅ ያ'ምላክሽ ስራ
ተጋድሎሽ የእምነትሽ ፅናት
ሆኖኛል የእምነቴ መብራት

💚
💛

╭══•|❀:✧๑♡๑✧❀|: ══╮
  @
meazahaymanot
╰══•ೋ•✧๑♡๑✧•  ══╯

Читать полностью…

መዓዛ ሃይማኖት በጎ አድራጎትና ጉዞ ማህበር

ማኅደረ ጥያቄ

፩. ስግደት ስንት ዐይነት ነው?

፪.ለቅዱሳን መስገድን ያስተማረው ማን ነው

፫.እግዚአብሔር ቃል በቃል ለቅዱሳን ስግደት እንደሚገባ የተናገረበት የመጽሐፍ ቅዱስ ክፍል ጻፉ

፬.የሚሰገድባቸው ጊዜያት ጻፉ

፭. የማይሰገድባቸው ጊዜያት ጻፉ

መልሱን እስከ ነገ 6:00 ሰዓት በ
@Asitmeherobot አድርሱን

መልሱን ከላይ ባለው ሊንክ ብቻ ይላኩ

ሁለተኛ ዙር ማኅደረ ጥያቄ

Читать полностью…

መዓዛ ሃይማኖት በጎ አድራጎትና ጉዞ ማህበር

ማኅደረ ጥያቄ

1. ጸሎት በስንት ይከፈላል?

፩ የምስጋና ጸሎት(ጸሎተ አኰቴት)
፪ የምህላ ጸሎት
፫ ጸሎተ አስተብቁዖት

2. በጸሎት ሕይወታችን ለማደግ ምን እናድርግ?

- በማለዳ በመነሳት የዕለቱን ጸሎት ማድረስ።
- በየሰዓቱ መጸለይን መልመድ።
- በማንኛውም ቦታ መጸለይን መልመድ።
- በችግር ውስጥ ላሉ ሰዎች እና በችግር ውስጥ ስንሆን መጸለይ መልመድ።
- ኃጢያታችንን በማመን መጸለይን መልመድ።

3. ዕሹ ታገኛላችሁ ለምኑ ይሰጣችኋል ደጁ ምቱ ይከፈትላችኋል”ይህ የመጽሐፍ ቅዱስ ቃል በየትኛ መጽሐፍ ክፍል ይገኛል ?

" ለምኑ፥ ይሰጣችሁማል፤ ፈልጉ፥ ታገኙማላችሁ፤ መዝጊያን አንኳኩ፥ ይከፈትላችሁማል።"
(የማቴዎስ ወንጌል ፯:፯)

4. የጸሎት አቅጣጫ ምስራቅን የተመለከተ መሆን አለበት ለምን?

ክብር ምስጋና ይግባውና ክርስቶስ በዳግም ምጽአቱ ጊዜ በእርሱ ይገለጽ ዘንድ ነውና። ትንቢተኛው ቅዱስ ዳዊት። ወደ ሰማይ ላረገው እግዚአብሔር ምስጋና አቅርቡ በምሥራቅ በኩል ባለው ሰማይ  የኃይል ቃሉን አሰማ።
በዚህችውም ቦታ (ምስራቅ) ቃሉ የተሰማባት ምጽአቱ የሚደረግባት ናት። የሚጸልይ ፊቱን ወደእርሷ ይመልስ ዘንድ መጽሐፍ አዘዘች።
(ፍትሐ ነገስት አንቀጽ ፲፬)
- አንድም ምሥራቅ የቤተክርስቲያን ምሳሌ ስለሆነች።
- አንድም ምሥራቅ የመንግስተ ሰማያት ምሳሌ ስለሆነች። ርስት መንግስተ ሰማይን እያሰብን እንጸልያለን።

5.ምን አይነት ጸሎት በየትኛው ሰዓት ይጸለይ?

የማለዳ ጸሎት እግዚአብሔር አበርትቶናልና የሌሊቱንም ጨለማ አሳልፎናልና ምስጋና ይገባሀል ብለን የምንጸልይበት ሰዓት ነው።
የ፫ ሰዓት ጸሎት መጸለይም ጲላጦስ በጌታችን ላይ ስለፈረደበት ነው። ይህ ሰዓት የተገረፈበት ነው። ይህንንም እያሰብን የምንጸልይበት ሰዓት ነው።
የ፮ ሰዓት ጸሎት ስነ ስቅለቱን እያሰብን የሚጸለይ ጸሎት ነው።
የ፱ ሰዓት ጸሎት ነፍሱን ከስጋው የለየበት ሰዓት ነው ይህንንም እያሰብን የምንጸልይበት ሰዓት ነው።
የ፲፩ ሰዓት ጸሎት ዮሴፍ እና ኒቆዲሞስ ገንዘው የቀበሩበት ሰዓት ነው።ይህንንም እያሰብን የምንጸልይበት ሰዓት ነው።
የንዋም ጸሎት  ከቀኑ ድካም አሳርፎ እረፍተ ስጋ ስለሰጠን እግዚአብሔር ሆይ ተመስገን የምንልበት ሰዓት ነው።
የሌሊት ጸሎት በቤተልሔም ዋሻ የተወለደበት፣ ሞትን ድል አድርጎ የተነሳበት ነው ይህንንም እያሰብን እንጸልያለን።

የተሣተፉ

1. ዘላለም  4/5

2. Tomi 4/5

3.liya 4/5

4.መቅደሰ ማርያም 5/5

5. ሰሎሞን 5/5

6. ገብረ ማርያም 5/5

7. lij bini 5/5

ለተሣተፉት ቃለ ሕይወትን ያሰማልን መንግሥተ ሰማያትን ያውርስልን

ሁለተኛው ዙር ማኅደረ ጥያቄ

Читать полностью…

መዓዛ ሃይማኖት በጎ አድራጎትና ጉዞ ማህበር

https://vm.tiktok.com/ZM66FyV94/

Читать полностью…

መዓዛ ሃይማኖት በጎ አድራጎትና ጉዞ ማህበር

✞ሕዝቦቿን ባርክላት✞

ሃሌ ሃሌ ሉያ ሃሌ ሃሌ ሉያ (፪)
ሕዝቦቿን ባርክላት ለኢትዮጵያ (፪)

በዘር በሃይማኖት እንዳይለያዩ
አንድነት ስጣቸው/በፍቅር እንዲቆዩ/(፪)
ምድሯን እንድትለመልም እንድትሆን ሰላም
ልጆችዋን ባርክላት/መድኃኔዓለም/(፪)
አዝ= = = = =
እጆቿን ዘርግታ ቆማ ስትጸልይ
በረከት ላክላት/ሆነህ በሰማይ/(፪)
ትሰግድልሃለች ወገቧን አጥብቃ
ቆይታለች እስካሁን/ማተቧን ጠብቃ/(፪)
አዝ= = = = =
አትርሳት ጠዋት ማታ እርሷ እንዳትከፋ
ጥላቻ ይወገድ /ጦርንትን አጥፋ/(፪)
በረድኤትህ ጎብኛት ረሃብ ይወገድ
በሽታና ችግር /ይገታ መሰደድ/(፪)

መዝሙር
ኪነጥበብ ወልደቂርቆስ

"ኢትዮጵያ እጆቿን ወደ
እግዚአብሔር ትዘረጋለች።"
መዝ ፷፯፥፴፩

Читать полностью…

መዓዛ ሃይማኖት በጎ አድራጎትና ጉዞ ማህበር

ማኅደረ ጥያቄ

1. ጸሎት በስንት ይከፈላል?

2. በጸሎት ሕይወታችን ለማደግ ምን እናድርግ?

3. ዕሹ ታገኛላችሁ ለምኑ ይሰጣችኋል ደጁ ምቱ ይከፈትላችኋል”ይህ የመጽሐፍ ቅዱስ ቃል በየትኛ መጽሐፍ ክፍል ይገኛል ?

4. የጸሎት አቅጣጫ ምስራቅን የተመለከተ መሆን አለበት ለምን?

5.ምን አይነት ጸሎት በየትኛው ሰዓት ይጸለይ?

መልሱን እስከ ነገ 6:00 ሰዓት በ @Asitmeherobot አድርሱን
👆👆👆👆👆
መልሱን ከላይ ባለው ሊንክ ይላኩ

#መልካም_እድል



ሁለተኛ ዙር ማኅደረ ጥያቄ

Читать полностью…

መዓዛ ሃይማኖት በጎ አድራጎትና ጉዞ ማህበር

ጻዲቁ አቡነ ዜና ማርቆስ በረከታቸው ይደርብን እንኳን አደረሳችሁ

Читать полностью…

መዓዛ ሃይማኖት በጎ አድራጎትና ጉዞ ማህበር

ስንክሳር ዘወርሃ ታህሣሥ ሦስት(፫)

@meazahaymanot

Читать полностью…

መዓዛ ሃይማኖት በጎ አድራጎትና ጉዞ ማህበር

ማኅደረ ጥያቄ

፩. ጸሎት ማለት ምን ማለት ነው

፪.በምን አይነት መንገድ መጸለይ አለብን

፫. የጸሎት ጊዜያት ስንት ናቸው

፬. መጽሐፍ ቅዱስ ስለ ጸሎት ምን ይላል

መልሱን እስከ ማታ 3:00 ሰዓት @Asitmeherobot አድርሱን


መልሱን ከላይ ባለው ሊንክ ብቻ ይላኩ

#መልካም_እድል

Читать полностью…

መዓዛ ሃይማኖት በጎ አድራጎትና ጉዞ ማህበር

ስንክሳር ዘወርሃ ታህሣሥ ሁለት(፪)

@meazhaymanot

Читать полностью…

መዓዛ ሃይማኖት በጎ አድራጎትና ጉዞ ማህበር

ክቡራን የቻናላችን ተከታታዮች እግዚአብሔር ቢፈቅድና ብንደርስ  01/04/2016 ዓ.ም  9:00 ሰዓት ላይ ‟  ማኅደረ ጥያቄ ይጀምራል እንድትከታተሉ በልዑል እግዚአብሔር ስም እንጠይቃለን።

ሃሳብ አስተያየት @misiwani_Bot
አድርሱን

ዛሬ ይጀመራል


@meazahaymanot
@meazahaymanot
@meazahaymanot

Читать полностью…

መዓዛ ሃይማኖት በጎ አድራጎትና ጉዞ ማህበር

ድንግል ማርያም ሆይ
ድንግል ሆይ ስለ ኢትዮጵያ አሳስቢ
ድንግል ሆይ ስለ ኦርቶዶክስ አሳስቢ
ድንግል ሆይ ስለ ቤተክርስትያናችን አሳስቢ
ድንግል ሆይ ስለ ጳጳሳት አሳስቢ
ድንግል ሆይ አባቶች ካህናት አሳስቢ
ድንግል ሆይ ስለ ዲያቆናት አሳስቢ
ድንግል ሆይ ስለ ሰባክያን ዘማርያን አሳስቢ
ድንግል ሆይ ስለ ምዕመናን አሳስቢ
ድንግል ሆይ ስለ ሞቱት አሳስቢ
ድንግል ሆይ ስለተሰደዱት አሳስቢ
ድንግል ሆይ ስለ ታመሙ አሳስቢ
ድንግል ሆይ ስለታሰሩት አሳስቢ
ድንግል ሆይ ስለ ተራቡ አሳስቢ
ድንግል ሆይ በኃጥያት ስላለነው አሳስቢ
ድንግል ሆይ ስለመከራችን አሳስቢ
ድንግል ሆይ ስለ በደላችን አሳስቢ
ድንግል ሆይ ልጅሽ ይቅርታውን ያድለን ዘንድ ለምኝልን

የያዕቆብ ሌሊት ይሁንልን

Читать полностью…

መዓዛ ሃይማኖት በጎ አድራጎትና ጉዞ ማህበር

ስንክሳር ዘወርሃ ህዳር ሠላሳ---
@meazahaymanot

Читать полностью…

መዓዛ ሃይማኖት በጎ አድራጎትና ጉዞ ማህበር

ክቡራን የቻናላችን ተከታታዮች እግዚአብሔር ቢፈቅድና ብንደርስ  01/04/2016 ዓ.ም  9:00 ሰዓት ላይ ‟  ማኅደረ ጥያቄ ይጀምራል እንድትከታተሉ በልዑል እግዚአብሔር ስም እንጠይቃለን።

ሃሳብ አስተያየት @misiwani_Bot
አድርሱን

ሁለት ቀን ቀረ


@meazahaymanot
@meazahaymanot
@meazahaymanot

Читать полностью…
Subscribe to a channel