meazahaymanot | Unsorted

Telegram-канал meazahaymanot - መዓዛ ሃይማኖት በጎ አድራጎትና ጉዞ ማህበር

3925

"ውድስት አንቲ በአፈ ነቢያት ወስብሕት በሐዋርያት አክሊለ በረከቱ ለያዕቆብ ወትምክህተ ቤቱ ለእስራኤል፡፡" "በነቢያት በሐዋርያት አንደበት የተመሰገንሽ የያዕቆብ የበረከቱ ዘውድ የእስራኤል ወገን መመኪያ አንቺ ነሽ"                  መጽሐፈ ሰዓታት የፌስቡክ ፔጃችን www.fb.me/meazhaimanot ይቀላቀሉን

Subscribe to a channel

መዓዛ ሃይማኖት በጎ አድራጎትና ጉዞ ማህበር

✞ሕዝቦቿን ባርክላት✞

ሃሌ ሃሌ ሉያ ሃሌ ሃሌ ሉያ (፪)
ሕዝቦቿን ባርክላት ለኢትዮጵያ (፪)

በዘር በሃይማኖት እንዳይለያዩ
አንድነት ስጣቸው/በፍቅር እንዲቆዩ/(፪)
ምድሯን እንድትለመልም እንድትሆን ሰላም
ልጆችዋን ባርክላት/መድኃኔዓለም/(፪)
አዝ= = = = =
እጆቿን ዘርግታ ቆማ ስትጸልይ
በረከት ላክላት/ሆነህ በሰማይ/(፪)
ትሰግድልሃለች ወገቧን አጥብቃ
ቆይታለች እስካሁን/ማተቧን ጠብቃ/(፪)
አዝ= = = = =
አትርሳት ጠዋት ማታ እርሷ እንዳትከፋ
ጥላቻ ይወገድ /ጦርንትን አጥፋ/(፪)
በረድኤትህ ጎብኛት ረሃብ ይወገድ
በሽታና ችግር /ይገታ መሰደድ/(፪)

መዝሙር
ኪነጥበብ ወልደቂርቆስ

"ኢትዮጵያ እጆቿን ወደ
እግዚአብሔር ትዘረጋለች።"
መዝ ፷፯፥፴፩

Читать полностью…

መዓዛ ሃይማኖት በጎ አድራጎትና ጉዞ ማህበር

♥ መድኃኔዓለም ♥

💠«መድኃኔዓለም ማለት ዓለምን ያዳነ የዓለም መድኃኒት  ማለት ነው።ሰው በመበደሉ ምክንያት ከክብር ተዋርዶ ይኖር ነበር።ኢየሱስ ክርስቶስ ግን የተዋረደውን ሰው እርሱ በመስቀል ተሰቅሎ ወደ ቀደመ ክብሩ መለሰው።ምን ዓይነት ፍቅር ነው????? ወንድሜ/እህቴ አስባችሁታል ግን ስለእኛ ብሎ እኛን ለማዳን ብሎኮ ነው የተሰቀለው።ራቁትን መሰቀል ምን ያህል አሳፋሪ ነገር እንደሆነ እናውቀዋለን።ጌታ ግን እኛን ለማዳን ብሎ ራቁትን መሰቀልን ናቀው። በፈጠራቸው ፍጥረታት ተተፋበት።እኛን ትእግስት ሊያስተምረን እነርሱን ማጥፋት እየቻለ እርሱ ግን በፍቅር እያየ የማያውቁትን አያውቁምና አባት ሆይ ይቅር በላቸው ይል ነበር። ክርስቶስ እኛን ለማዳን ሲሰድቡት አልተሳደበም ሲንቁት አልናቃቸውም ሲታበዩበት ሁሉ እርሱ ግን በትሕትና ያያቸው ነበር።ታድያ እኛ ደግሞ ራሳችንን ለማዳን ሰዎች ሲንቁን ሲሰድቡን ሲታበዩብን በፍቅር በዝምታ ማለፍ ይጠበቅብናል።ይህን ካደረግን የክርስቶስ ደቀመዝሙር እንባላለን። በ5 ችንካር ነበር የቸነከሩት።በመስቀል የተገኙ ድንግል ማርያምና ሐዋርያው ዮሐንስ ነበሩ።አንተም በመስቀሉ ስር ለመገኘት ከፈለግህ ትዕግስትን ፍቅርን ትሕትናን ገንዘብ አድርግ።

መድኃኔዓለም በቸርነቱ ይቅር ይበለን።

ቴሌግራም ይቀላቀሉ /channel/meazahaymanot

Читать полностью…

መዓዛ ሃይማኖት በጎ አድራጎትና ጉዞ ማህበር

ሥርዓተ ቅዳሴ
ክፍል ፪
የሥርዓተ ቅዳሴ ክፍሎች
ባለፈው ጊዜ ሥርዓት ምን ማለት እንደሆነና የሥርዓተ ቤተ ክርስቲያን ምንጮችን ተመልክተናል። ለዛሬው ደግሞ የሥርዓተ ቅዳሴን ክፍሎች የምንመለከት ሲሆን በቅድሚያ የቅዳሴን ትርጉም እናያለን። ቅዳሴ የሚለው ቀደሰ ከሚለው የግእዝ ቃል የተገኘ ሲሆን አመሰገነ፣ ምስጋና አቀረበ ማለት ነው። ቅዳሴ ደግሞ ምስጋና ማለት ነው። በቤተ ክርስቲያን በርካታ የምስጋና ዓይነቶች ያሉ ሲሆን ዋና ዋናዎቹ ማኅሌት፣ ሰዓታት፣ ኪዳን (ስብሐተ ነግሕ) እና ቅዳሴ ናቸው። ማንኛውም አገልግሎት ከተሰጠ በኋላ በመጨረሻ የሚቀርበው የጸሎት፣ የምስጋና ክፍል ቅዳሴ ነው። የማኅሌቱ፣ የሰዓታቱ፣ የስብሐተ ነግሑ አገልግሎት ከተሰጠ በኋላ መቋጫው፣ መደምደሚያው ቅዳሴ ነው። ምክንያቱም የጌታችን የመድኃኒታችን የኢየሱስ ክርስቶስ ሥጋና ደሙ የሚፈተትበት፣ በካህናት የሚቀርበው መስዋዕተ እግዚአብሔር የሚያርግበት፣ ኅብስትና ወይኑ ወደ ፍጹም አማናዊ ሥጋ ወልደ እግዚአብሔርና ደመ ወልደ እግዚአብሔር የሚቀየርበት የምስጋና ክፍል ስለሆነ ነው። ማኅሌት ቢቆም ሰዓታት ቢደርስ ያለ ቅዳሴ ሊሆን አይችልም። ማኅሌትና ሰዓታት በሌለበት ግን ቅዳሴ ተቀድሶ ሥጋ ወደሙ ይፈተታል። ስለዚህ በቤተ ክርስቲያናችን ለቅዳሴ ሚሰጠው ትኩረት ልዩ የሆነው ለዚህ ነው።
አንድ የቅዳሴ ጸሎት ሶስት ክፍሎችን የያዘ ሲሆን እነዚህም፦
1ኛ. የመዘጋጃ ቅዳሴ
2ኛ. የንባብ ቅዳሴ
3ኛ. ፍሬ ቅዳሴ ናቸው።
1ኛ. የመዘጋጃ ቅዳሴ (ግባዓተ መንጦላዕት)
ይህ የቅዳሴ ክፍል ለዋናው ቅዳሴ አስፈላጊ የሆኑ ነገሮች የሚዘጋጁበት፣ በንዋያተ ቅድሳቱ ላይ ጸሎት የሚደረግበት ክፍል ሲሆን ጸሎቱ የሚደረገው መጋረጃው ሳይገለጥ በመቅደሱ ውስጥ የሚፈጸም ስለሆነ ግብዓተ መንጦላዕት (በመጋረጃ ውስጥ) የሚደረግ ጸሎት ተብሏል። በጥንታውያን አብያተ ክርስቲያናት በተለይም ቤተ ንጉስ ወይም በክብ ቅርጽ በተሰሩ አብያተ ክርስቲያናት በመቅደሱ መግቢያ በር ላይ ካለው መጋረጃ በተጨማሪ በመቅደሱ ውስጥ ከመንበሩ ፊት ለፊት የሚዘረጋ ትልቅ መጋረጃ አለ። ይህም መንጦላዕት ይባላል። በዚህ ዘመን በኖህ መርከብ ወይም በመስቀል ቅርጽ በሚሰሩ ዘመናዊ አብያተ ክርስቲያናት ውስጥ ብዙ ጊዜ የለም። እንዲሁም አባቶች ይህንን የቅዳሴ ክፍል ሥርዓተ ግብጽ ይሉታል። በአጠቃላይ ይህ የቅዳሴ ክፍል ካሕኑ ወደቤተ መቅደስ ገብቶ “ሚ መጠን ግርምት ዛቲ ዕለት - ይቺ ቀን ምን ያህል የምታስፈራ ናት ይቺ ሰዓትስ ምን ያህል የምታስጨንቅ ናት መንፈስ ቅዱስ ከላይ የሚወርድባት …” በማለት ድምጹን ከፍ አድርጎ እስከሚያሰማበት ድረስ ያለው ክፍል ነው። ካህኑ ወደቤተ መቅደስ ሲገባ እመቅደሱ መግቢያ ላይ አንድ ጊዜ፣ ቀጥሎም በመንበሩ ስር ሶስት ጊዜ ይሰግዳል። ይኸውም በመጀመሪያ ወደ መቅደሱ ከመግባቱ በፊት ቅድመ ግብዓተ መንጦላዕት የተሰኘውን የቅዱስ ጎርጎርዮስን “እግዚአብሔር አምላክነ ዘተአምር ኩሎ ሕሊና ሰብእ ወትፈትን ልበ ወኵልያተ - እግዚአብሐር አምላክችን ሁሉን የምታውቅ፣ የሰውን ሕሊና የምትመረምር፣ ልብና ኩላሊትን የምታውቅ …” የሚለውን ጸሎት ይጸልያል። በመቀጠል ወደቤተ መቅደስ ውስጥ ገብቶ ነገር ግን ወደ መንበሩ ከመግባቱ በፊት ቀደም ሲል ባልነው በመቅደሱ መግቢያ ባለው መጋረጃና ከመናበሩ ፊት ከተዘረጋው መጋረጃ (መንጦላዕት) መካከል ሁኖ አንድ ጊዜ ይሰግድና “እግዚአብሔር አምላክነ ወፈጠረነ ዘገበርከ ኵሎ በቃልከ ወአባዕከነ ውስተ ዝንቱ ምስጢር - ሁሉን በቃልህ የፈጠርክ እግዚአብሔር አምላካችን ሆይ ወደዚህ ድንቅ ጥብብ ያገባኸን” በማለት የቅዱስ ባስልዮስን ጸሎት ይጸልያል። በመቀጠልም መንጦላዕቱን ከፍቶ በመግባት ሶስት ጊዜ ከመንበሩ ስር ሰግዶ “እግዚአብሔር አምላክነ ዘይነብር መልዕልተ መላእክት ወሊቃነ መላእክት አጋእዝት ወሥልጣናት ኪሩቤል ወሱራፌል - እግዚአብሔር አምላካችን ሆይ ከመላእክትና ከመላእክት አለቆች፣ ከገዢዎች እና ከስልጣናት፣ ከኪሩቤልና ከሱራፌል በላይ የምትቀመጥ …” የሚለውን የቅዱስ ዮሐንስን ጸሎት ይጸልያል።

ይቀጥላል

https://m.youtube.com/channel/UCKGh-U7U7pnvFUIEGXPOnNw

Читать полностью…

መዓዛ ሃይማኖት በጎ አድራጎትና ጉዞ ማህበር

ወወለደት ወልድ ዘበኩራ

@meazahaymanot

Читать полностью…

መዓዛ ሃይማኖት በጎ አድራጎትና ጉዞ ማህበር

ስንክሳር ዘወርሃ ታህሣሥ ሃያ ስድስት(፳፮)
/channel/meazahaymanot

Читать полностью…

መዓዛ ሃይማኖት በጎ አድራጎትና ጉዞ ማህበር

በቤተልሔም ተወልደ/2x/ አማኑኤል
እምዘርአ ዳዊት/4x/ ተወልደ አማኑኤል
ትርጉም ፡ አማኑኤል ከዳዊት ዘር በቤተልሔም ተወለደ
👇👇👇👇👇👇👇👇👇
👉 @meazahaymanot 👈
👆👆👆👆👆👆👆👆👆

Читать полностью…

መዓዛ ሃይማኖት በጎ አድራጎትና ጉዞ ማህበር

በኮከብ መጹኡ ሰብአ ሰገል (፪)
ይስግዱ ለአማኑኤል ይስግዱ (፪)

Читать полностью…

መዓዛ ሃይማኖት በጎ አድራጎትና ጉዞ ማህበር

ስንክሳር ዘወርሃ ታህሣሥ ሃያ አምስት(፳፭)
/channel/meazahaymanot

Читать полностью…

መዓዛ ሃይማኖት በጎ አድራጎትና ጉዞ ማህበር

ቀበና ምዕራፈ ጻድቃን አቡነ ተክለሃይማኖት ቅዱስ ገብርኤል ወአቡነ ሀብተ ማርያም ቤተክርስቲያን

የጻዲቁ አቡነ ተክለሃይማኖት የልደት በዓል ብፁዕ አቡነ እንድርያስ በተገኙበቶ እንዲህ እየተከበረ ይገኛል

ታኅሣሥ 24/2016 ዓ.ም

Читать полностью…

መዓዛ ሃይማኖት በጎ አድራጎትና ጉዞ ማህበር

​​​​ታህሳስ 24

በዚህች ቀን ታላቁ ጻድቅ አቡነ ተክልሃይማኖት የተወለዱበት ቀን ነው። የትውልድ ቦታቸው ሸዋ ጽላልሽ አወራጃ ዞረሬ ነው፤ የአባታቸው ስም ጸጋ ዘአብ የእናታቸው ስም እግዚ ሐርያ ይባላል መካን ነበሩ ልጅ እንዲሰጣቸው ወደ እግዚያብሔር ዘወትር ይጸልዩ ነበር፤ መጋቢት 12 ቀን እንዲህ ሆነ።

ሞተሎሜ የተባለ ጣኦት አምላኪ ንጉስ አገራቸውን ወረረ መንደሩንም አጠፋ ጸጋ ዘአብ ወንዝ ውስጥ ገብቶ አመለጠ እግዚ ሐርያ ግን ተማርካ ሄደች፤ በጣም መልከ መልካም ስለነበረች ሞቶሎሜ ሊያገባት አሰበ ታላቅ ድግስም ደገሰ አገር ምድሩ ተሰብስቦ ሲዘፍን ሲጨፍር ሳለ ቅዱስ ሚካኤል ታላቅ መብረቅ ነጎድጓድ አሰማ ብዙዎች ሞቱ እግዚሐርያን በክንፎ ተሸክሞ ዞረሬ ከቤተክርስቲያን ውስጥ አስቀመጣት ከባለቤቷ ጸጋ ዘአብ ጋር ተገናኙ ተቃቅፈው ተላቀሱ፤ከሁለት ቀን በኃላ መጋቢት 24 ቀን ተክለሃይማኖት ተጸነሱ።

በዛሬዋ ቀን 1167 ዓ/ም ተወለዱ ቀኑ አርብ ነበር፤ በተወለዱ በ3ኛ ቀናቸው እሁድ በ 3 ሰዓት “አሐዱ አብ ቅዱስ አሐዱ ወልድ ቅዱስ አሐዱ ውእቱ መንፈስ ቅዱስ” ብለው ሥላሴን አመሰገኑ፤ ሁለተኛ ተአምር ከዚህ በታች ያለው ስዕል ተክልዬ የአንድ ዓመት ከመንፈቅ ህጻን እያሉ ነው፤ በድፍን ሸዋ ርሃብ ተከስቶ ነበር በተለይም በዞረሬ እግዚሐርያ አዘነች አለቀሰች ምነው እርቧት ነው ጠምቷት ነው ቢሉ የለም እርቧትስ ጠምቷትስ አይደለም የቅዱስ ሚካኤል ዝክሩ ታጎለቢኝ ብላ እንጂ።

ህጻኑ ተክለሃይማኖት ከእናቱ ጭን ወርዶ እየዳኸ ወደ ጓዳ ሄደ አንስታ አቀፈችው እርሱ ግን አለቀሰ ዱቄት የተቀመጠበትን እንቅብ እንድትሰጠው በእጁ ጠቆማት ሊጫወትበት መስሏት ሰጠችው በትንንሽ እጆቹ እንቅቡ ላይ አማተበ ዱቄቱ ሞልቱ ፈሰሰ ዳግመኛ የቅቤ የዘይት ማስቀመጫ ማድጋዎች ላይ በተመሳሳይ አማተበ ሞልቶ ፈሰሰ ቤቱ በበረከት ተትረፈረፈ፤ የቅዱስ ሚካኤልን ዝክሩን አዘከረች አገሬውን ጠርታ መገበች፤ ለተቸገሩትም አብዝታ ሰጠች፤ ይህ በረከት ሁለቱም እስኪሞቱ ድረስ አላለቀም ይላል ገድላቸው።

ተክለ ሃይማኖት በ 99 ዓመት ከ8 ወር ከ5 ቀን በዚህ ምድር ኖረው ነሐሴ 24 ቀን አርፈዋል። በደብረሊባኖስ ገዳማቸው የንፍሮ ውኃ አይነስውር ያበራል ድውይ ይፈውሳል ገድላቸው ሊነበብ ሲወጣ አጋንንት ተቃጠልን ይላሉ ሲገርም ምን ያህል ባለጸጎች ነን። ከበዓሉ በረከት ያሳትፈን።

#ሼር
💚 @meazahaymanot💚
💛 @meazahaymanot💛
❤️ @meazahaymanot ❤️

Читать полностью…

መዓዛ ሃይማኖት በጎ አድራጎትና ጉዞ ማህበር

ስንክሳር ዘወርሃ ታህሣሥ ሃያ አራት(፳፬)
@meazahaymanot

Читать полностью…

መዓዛ ሃይማኖት በጎ አድራጎትና ጉዞ ማህበር

ክቡራን የቻናላችን ተከታታዮች እግዚአብሔር ቢፈቅድና ብንደርስ  25/04/2016 ዓ.ም  9:00 ሰዓት ላይ ‟  መንፈሳዊ ተከታታይ ትምህርት ይጀምራል እንድትከታተሉ በልዑል እግዚአብሔር ስም እንጠይቃለን።

ሃሳብ አስተያየት @misiwani_Bot
አድርሱን

ዛሬ ይጀመራል


@meazahaymanot
@meazahaymanot
@meazahaymanot

Читать полностью…

መዓዛ ሃይማኖት በጎ አድራጎትና ጉዞ ማህበር

ስንክሳር ዘወርሃ ታህሣሥ ሃያ ሦስት(፳፫)
/channel/meazahaymanot

Читать полностью…

መዓዛ ሃይማኖት በጎ አድራጎትና ጉዞ ማህበር

ስንክሳር ዘወርሃ ታህሣሥ ሃያ ሁለት(፳፪)
/channel/meazahaymanot

Читать полностью…

መዓዛ ሃይማኖት በጎ አድራጎትና ጉዞ ማህበር

ከአሁን ጀምሮ እንደተለመደው ለቻናላችን ያላችሁን ሀሳብ አስተያየት ማቅረብ ትችላላችሁ። ቢኖሩ፣ ቢስተካከሉ የምትሏቸው ጉዳዮች ላይ አተኩራችሁ ስማችሁንና ከየት ሀገር እንደሆናችሁ እየገለጻችሁ በድምጽ ሆነ በጽሑፍ ላኩልን። ቤተሰቦቻችን የት የት እንዳሉም እንድናውቅና እንድንተዋወቅ ይረዳናል     ላይ @misiwani_Bot እንጠብቃችኋለን

ሐሳብ አስተያየታቸውን ጻፉልን

Читать полностью…

መዓዛ ሃይማኖት በጎ አድራጎትና ጉዞ ማህበር

Take a look at this post… '‹‹ለጠቢብ ሰው ትምህርትን ስጠው፤ ጥበብንም ያበዛል›› (ምሳ. ፱፥፱)'.
http://meazahaymanot.blogspot.com/2022/01/blog-post.html

Читать полностью…

መዓዛ ሃይማኖት በጎ አድራጎትና ጉዞ ማህበር

ስንክሳር ዘወርሃ ታህሣሥ ሃያ ሰባት-(፳፯) /channel/meazahaymanot

Читать полностью…

መዓዛ ሃይማኖት በጎ አድራጎትና ጉዞ ማህበር

ዮም ፍስሐ ኮነ በእንተ ልደቱ ለክርስቶስ
እም ቅድስት ድንግል ድንግል ውእቱ ኢየሲስ ክርስቶስ

👇👇👇👇👇👇👇👇👇👇👇👇👇
👉👉👉@meazahaymanot 👈👈👈
👉👉 👉@meazahaymanot 👈👈👈
👉 👉 👉@meazahaymanot 👈👈👈
👆👆👆👆👆👆👆👆👆👆👆👆👆

Читать полностью…

መዓዛ ሃይማኖት በጎ አድራጎትና ጉዞ ማህበር

ወወለደት ወልደ ዘበኩራ
መንጦላዕተ ደመና ሠወራ/2x/
ትርጉም ፡ የበኩር ልጇን ወለደች የደመና መጋረጃም ጋረዳት


👇👇👇👇👇👇👇👇👇
👉 @meazahaymanot 👈
👉 @meazahaymanot 👈
👆👆👆👆👆👆👆👆👆

Читать полностью…

መዓዛ ሃይማኖት በጎ አድራጎትና ጉዞ ማህበር

ሥርዓተ ቅዳሴ
ሥርዓተ ቅዳሴ የሚለውን ቃል ስንመለከት "ሥርዓት" ማለት አሠራር፣ አፈፃጸም ተብሎ የሚተረጎም ሲሆን "ቅዳሴ" ደግሞ ምሥጋና ማለት ነው፤ ይኸውም ለፈጣሬ ሰማያት ወምድር ለእግዚአብሔር የሚቀርብምሥጋና ማለታችን ነው። እንግዲህ ቅዳሴ በሐዲስ ኪዳን የተጀመረው በቤተ ልሔም ሲሆን የጀመሩትም ሰማያውያን መላእክት ናቸው፤ ጌታችንና አምላካችን መድኃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ለአባታችን ለአዳም በ፭ሺ ፭መቶ ዘመን ከልጅ ልጅህ ተወልጄ አድንሃለሁ ያለው አምላካዊ የተስፋ ቃል ሲፈጸም ቤተ ልሔም በምትባል የዳዊት ከተማ "ስብሐት ለእግዚአብሔር በሰማያት ወሰላም በምድር ስምረቱ ለሰብእ" ክብር ለእግዚአብሔር በአርያም ይሁን፤ ሰላምም በምድር ለሰውም በጎ ፈቃድ እያሉ ሰማያውያን መላእክት እንዳመሰገኑ በሉቃስ ወንጌል ምዕ. ፪ ቁ፥፲፬ ተጽፎ እናገኛለን።


  ይቀጥላል

@meazahaymanot
@meazahaymanot

Читать полностью…

መዓዛ ሃይማኖት በጎ አድራጎትና ጉዞ ማህበር

ዮሐንስ አጥመቆ ለኢየሱስ
በፈለገ ዮርዳኖስ በፈለገ ፈለገ ዮርዳኖስ

ትርጉም፡ ዮሐንስ ኢየሱስን በዮርዳኖስ ወንዝ አጠመቀው
👇👇👇👇👇👇👇👇👇
👉 @meazahaymanot 👈
👆👆👆👆👆👆👆👆👆

Читать полностью…

መዓዛ ሃይማኖት በጎ አድራጎትና ጉዞ ማህበር

ይትፌስሃ አድባረ ፅዮን ወይትኃስያ አዋልደ ኢትዮጵያ
እስመ ተወልደ ብኁተ ልደት መድኃኔዓለም በኢየሩሳሌም መድኃኔዓለም

ትርጉም ፡ የፅዮን ተራሮች ይደሰታሉ የኢትዮጵያም ቆነጃጅትም ይደሰታሉ በልደት የሰለጠነ መድኃኔዓለም በኢየሩሳሌም ተወልዷልና
👇👇👇👇👇👇👇👇👇
👉 @meazahaymanot 👈
👆👆👆👆👆👆👆👆👆

Читать полностью…

መዓዛ ሃይማኖት በጎ አድራጎትና ጉዞ ማህበር

የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተክርስቲያን ሥርዓት፣ ትውፊት እና አስተምህሮ  የጠበቁ ትምህርቶች እና መዝሙሮች እንዲሁም ወረቦችን እንዲሁም መንፈሳዊ ቦታዎችን መጎብኘት    የምትፈልጉ join በማለት ይቀላቀሉን ማኅበሩ ለሚያከናውናቸው አገልግሎቶች አጋዥ እንድትሆኑ በአክብሮት እንጋብዛለን።

/channel/meazahaymanot


Share

Читать полностью…

መዓዛ ሃይማኖት በጎ አድራጎትና ጉዞ ማህበር


ዓምደ ብርሃን ዘኢትዮጵያ
አባተክለሃይማኖት ሐዲስ ሐዋርያ
እኔ ምስክር ነኝ ያሳደገኝ ቤቱ
ያላስማረው የለም አባ በጸሎቱ

ዘማሪት ፀዳለ ጎበዜ

Читать полностью…

መዓዛ ሃይማኖት በጎ አድራጎትና ጉዞ ማህበር

ሰላም ለልደትከ ድኅረ ነበረት መካነ ። ለእምከ ልባ ከመ ቃለ መልአክ አምነ ። ተክለ ሃይማኖት በርትዕ እንተ ቀነይከ አዝማነ ። መልአ ምድረ ትምህርትከ እምወሰን ወሰነ ወሰማያተ ጽድቅከ ከደነ ።

Читать полностью…

መዓዛ ሃይማኖት በጎ አድራጎትና ጉዞ ማህበር

✔ሥርዓተ ማኅሌት ታኅሣሥ ዘአቡነ ተክለ ሃይማኖት

የማንኛውም ወርኃ በዓልና ክብረ በዓል ሥርዓተ ማኅሌት መጀመሪያ
ስምዓኒ እግዚኦ ጸሎትየ፡ ሃሌ ሉያ ሃሌ ሉያ፡ ወይብጻሕ ቅድሜከ ገዓርየ፡ ሃሌ ሉያ ሃሌ ሉያ፡ ወኢትሚጥ ገፀከ እምኔየ፡ በዕለተ ምንዳቤየ አጽምእ ዕዝነከ ኃቤየ፡ ሃሌ ሉያ ሃሌ ሉያ፡ አመ ዕለተ እጼውአከ ፍጡነ ስምዓኒ፡ ሃሌ ሉያ ሃሌ ሉያ፡ ለዓለም ወለዓለመ ዓለም፡ ሃሌ ሉያ ዘውእቱ ብሂል፡ ንወድሶ ለዘሃሎ እግዚአብሔር ልዑል፡ ስቡሕ ወውዱስ ዘሣረረ ኲሎ ዓለመ፡ በአሐቲ ቃል።

መልክአ ሥላሴ
ሰላም ዕብል ለንዋየ ውስጥ ምሕረትክሙ፤ ትሩፋተ ገድል ኩኑኒ ሥላሴ አምጣነ ትሩፋት አንትሙ፤ ሶበ ሖርኩሰ ከመ እሳተፍ ገድሎሙ፤ ጊዮርጊስ ኢወሀበኒ መጠነ ነጥበ ጠል እምደሙ፤ ወተክለ ሃይማኖት ከልአኒ ስባረ እምዐፅሙ።

ዚቅ
ሃሌ ሉያ ለአብ ሃሌ ሉያ ለወልድ፤ ሃሌ ሉያ ወለመንፈስ ቅዱስ፤ አክሊለ ሰማዕት ሠያሜ ካህናት፤ ወረደ እምሰማይ ዲበ ምድር፤ በመስፈርተ ጥበቡ ለአቡሁ።

መልክአ ሚካኤል
ሰላም ለሕፅንከ እንተ በዲቤሁ ሕቁፍ፤ ጸሎተ ቅዱሳን ውኩፍ፤ ሚካኤል ክቡር መስፍነ ትጉሃን አእላፍ፤ ለረዲኦትየ ከመ ዘይሠርር ዖፍ፤ እንዘ ትሠርር ነዓ በ፪ኤ አክናፍ።

ዚቅ
እስመ ፩ዱ ውእቱ፤ ሚካኤል ዘይረድኦሙ፤ ለኲሎሙ ቅዱሳን።

ነግሥ
ሰላም ለዝክረ ስምኪ ዘመንክር ጣዕሙ፤ ለወልድኪ አምሳለ ደሙ፤ መሠረተ ህይወት ማርያም ወጥንተ መድኃኒት ዘእምቀዲሙ፤ ኪያኪ ሠናይተ ዘፈጠረ ለቤዛ ዓለሙ፤ እግዚአብሔር ይትባረክ ወይትአኮት ስሙ።

ዚቅ
ቅንዑ ለእንተ ተዓቢ ጸጋ መድኃኒት ለነፍስ ወሥጋ፤ እስመ ርቱዓት ፍናዊሃ ጻድቃን የሐውርዎን፤ ወኃጥአን ይስዕንዎን ዘእንበለ ትብጻሕ ግብተ አሠንዩ ፍኖተ፤ ይፌነ ለክሙ እመቅደሱ ረድኤተ፤ መድኃኒተ መቤዛዊተ እሞ ቅድስተ።

ነግሥ
ሰላም ለልደትከ ተክለ ሃይማኖት ሐዋርያ፤ ለሰብአ ግብፅ ወኢትዮጵያ፤ ሞገሰ ልደትከ አባ በአዕይንቲሃ ርእያ፤ ነፍስየ ትባርኮሙ ወታስተበጽኦሙ ነያ፤ ለጸጋ ዘአብ ወለእግዚእ ኃረያ።

ዚቅ
ኮከብ ብሩህ ዘሠረቀ እምአቅሌስያ፤ ቤተ ክርስቲያን ዘንሰምያ፤ ኮኖሙ አበ ለሰብአ ግብፅ ወኢትዮጵያ፤ አማን ተክለ ሃይማኖት ሐዋርያ።

መልክአ ተክለ ሃይማኖት
ሰላም ለጽንሰትከ ወለልደትከ እምከርሥ፤ አመ ዕሥራ ወረቡዑ ለወርኃ ታኅሣሥ፤ ተክለ ሃይማኖት በኲሉ ወበውስተ ኲሉ ውዱስ፤ ናሁ ወጠንኩ ወእቤ ለስብሐቲከ ሐዲስ፤ በስመ አብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ።

ዚቅ
በእንተ ልደቱ ለተክለ ሃይማኖት አድባር ኮኑ ኅብስተ ሕይወት፤ ወዕፀወ ገዳምኒ ፈረዩ አስካለ በረከት፤ ማየ ባሕርኒ ኮነት ሀሊበ ወመዓረ፤ ወመላእክት ተጋቢዖሙ፤ ሰፍሑ ክነፊሆሙ፤ ወጸለሉ ላዕለ ተክለ ሃይማኖት፤ ወበህየ ገብሩ በዓለ።

ዓዲ (ወይም)
ዚቅ
ተጸንሰ በከርሥ ሥጋ ኮነ፤ ወልደቱ ተአውቀ እመንፈስ ቅዱስ።

ወረብ
በእንተ ልደቱ ለተክለ ሃይማኖት 'አድባር ኮኑ'/፪/ ኅብስተ ሕይወት/፪/
ወዕፀወ ገዳምኒ ፈረዩ አስካለ በረከት/፪/

መልክአ ተክለ ሃይማኖት
ሰላም ለልሳንከ በሠሉስ ዕለት ዘተውህባ፤ አኮቴተ ታቅርብ ለወልደ ማርያም ንጉሠ ሕዝባ፤ ተክለ ሃይማኖት ጸዋሚ ዮሐንስ ዘቤተ ራባ፤ ታሠምረከ ልሳንየ በአምጣነ ኲሉ ንባባ፤ ከመ አሥመሮሙ ያዕቆብ ለላባ።

ዚቅ
ከሠተ አፉሁ ወልሳኑ ነበበ፤ አእኮቶ ወባረኮ ለእግዚአብሔር፤ መልዓ መንፈስ ቅዱስ ላዕለ ተክለ ሃይማኖት፤ ተነበየ ወይቤ፤ አንሥአ ለነ ቀርነ መድኃኒትነ።

ወረብ
ከሠተ አፉሁ ወልሳኑ ነበበ ወባረኮ ለእግዚአብሔር/፪/
መልዓ መንፈስ ቅዱስ ላዕለ ተክለ ሃይማኖት/፪/

መልክአ ተክለ ሃይማኖት
ሰላም ለሕንብርትከ ማዕከለ ከርሥ ሀላዊ፤ ዘተቶስሐ በደሙ ለወልደ ማርያም ናዝራዊ፤ ተክለ ሃይማኖት ጽጌ ዘሠረጽከ እምአረጋዊ፤ ተበሀሉ በእንቲአከ ካህናተ ይሁዳ ወሌዊ፤ መልአከኑ ሰማያዊ ወብእሲ ምድራዊ።

ዚቅ
በከመ ዜነዎ መንፈሳዊ ለጸጋ ዘአብ አረጋዊ፤ ተክለ ሃይማኖት ተወልደ ዓርኩ ለመርዓዊ ሰማያዊ።

ወረብ
'በከመ ዜነዎ'/፪/ መንፈሳዊ ለጸጋ ዘአብ/፪/
ተወልደ ተክለ ሃይማኖት ዓርኩ ለመርዓዊ/፪/

መልክአ ተክለ ሃይማኖት
ሰላም ለቆምከ ዘጶደሬ ሰማይ ልብሱ፤ ልሳናት ቦቱ እለ ይቄድሱ፤ ተክለ ሃይማኖት በለዝ ለእግዚአብሔር ዓምደ መቅደሱ፤ ጸውዐኒ እትሉ እግዚኦ ኀበ እግርከ አንሶሱ፤ ከመ ተለዎ ለሙሴ ኢያሱ።

ዚቅ
ሃሌ ሉያ ሃሌ ሉያ ሃሌ ሉያ ዘለዓለም ፍሡሕ፤ ገጹ ብሩህ እምነቢያት፤ ልሳኑ በሊህ፤ ዘለዓለም ፍሡሕ ቆሙ ነዊህ፤ ዲበ ዕንግድዓሁ ጽሕሙ ስፉሕ፤ ዘለዓለም ፍሡሕ፤ ዕንባቆምኒ ይቤ ድምፆ ሰማዕኩ ግብሮ አንከርኩ፤ ፍኖቶ ዘእምዓለም ርኢኩ።

ወረብ
ሃሌ ሃሌ ሉያ ዘለዓለም ፍሡሕ/፪/
ገጹ ብሩህ እምነቢያት ልሳኑ በሊህ ለተክለ ሃይማኖት/፪/

መልክአ ተክለ ሃይማኖት
እንዘ አኃሥሥ በረከተከ አእዳወ ልብየ በአንሥኦ፤ እለ መርሐ ክርስቶስ ወጴጥሮስ ከመ ኀሠሡከ በተማልዖ፤ ተክለ ሃይማኖት ውኁድ ሰአልኩከ በአስተብቊዖ፤ ለጻድቅሰ ኅዳጥ ቃል ይብቊዖ፤ ተሰጥወኒ እግዚኦ እግዚኦ።

ዚቅ
አባ ተክለ ሃይማኖት ጸሊ በእንቲአነ፤ እንዘ ብዙኅ ውዳሴከ ውኁደ ነገርኩ፤ ይኩነኒ ምዝጋና።

ወረብ
በእንቲአነ ጸሊ አባ ተክለ ሃይማኖት/፪/
እንዘ ብዙኅ ውዳሴከ ውኁደ ነገርኩ ይኩነኒ ምዝጋና ይኩነኒ/፪/

አንገርጋሪ
አባ አቡነ አቡነ መምህርነ፤ እምአዕላፍ ኅሩይ ሐውጽ እምሰማይ፤ ብርሃንከ ከመ ንርአይ፤ አማን ተክለ ሃይማኖት ፀሐይ።

አመላለስ
አማን በአማን/፬/
ተክለ ሃይማኖት ፀሐይ/፪/

ወረብ
አባ አቡነ አባ 'መምህርነ'/፪/ አባ ተክለ ሃይማኖት/፪/
'እምአዕላፍ ኅሩይ'/፪/ ኅሩይ ተክለ ሃይማኖት/፪/


እስመ ለዓለም
ንጹሕ ከመ ዕጣን ብሩህ ከመ ፀሐይ፤ ብርሃኖሙ ለጻድቃን ውእቱ ኢየሱስ ክርስቶስ፤ ኦሆ ብሂሎ ተዓዛዜ ከዊኖ፤ መጽአ ውስተ ዓለም፤ ርሡይ ወሥርግው ይትፌኖ ወልድ።

ወረብ
ንጹሕ ከመ ዕጣን ብሩህ ከመ 'ፀሐይ'/፪/ ተክለ ሃይማኖት/፪/
ብርሃኖሙ ለጻድቃን ውእቱ ኢየሱስ ክርስቶስ/፪/

https://www.youtube.com/channel/UCKGh-U7U7pnvFUIEGXPOnNw

መልካም በዓል

Читать полностью…

መዓዛ ሃይማኖት በጎ አድራጎትና ጉዞ ማህበር

#ገድልከ_ግሩም

ገድልከ ግሩም ነገርከ ጥዑም 
ጊዮርጊስ ኃያል እንቍ ስም /ቅረበነ/(፫)በሠላም

#ትርጉም
ገድልህ ግሩም አስደናቂ ኃያሉ ጊዮርጊስ ስምህ
እንቁ የከበረ ነው በሰላም ቅረበን

╭══•|❀:✧๑♡๑✧❀|: ══╮
@meazahaymanot
╰══•ೋ•✧๑♡๑✧• ══╯

Читать полностью…

መዓዛ ሃይማኖት በጎ አድራጎትና ጉዞ ማህበር

✞ዑራኤል✞

አባቴ ጠባቂዬ ሞገሴ ታዳጊዬ
ዑራኤል ለኔ ልዪ ነህ
የምትረዳኝ ከአምላክ ተልከህ

በደመ ክርስቶስ ዑራኤል መልአክ
ልትቀድስ ዓለምን >> >>
በክብር አስጊጦ >> >>
አምላክ መረጠህ >> >>
ለኔስ ልዩ ነው ያንተ ፍቅር
ቁምልኝ ቅዱስ ዑራኤል በቅድመ እግዚአብሔር
አዝ= = = = =
የእውቀትን ጽዋ ዑራኤል መልአክ
ለዕዝራ እንዳጠጣህ >> >>
እኔንም ከኃጢአት >> >>
ከሞት አፍ አውጣኝ >> >>
ለኔስ ልዩ ነው ያንተ ፍቅር
ቁምልኝ ቅዱስ ዑራኤል በቅድመ እግዚአብሔር
አዝ= = = = =
የመንገዴ እንቅፋት ዑራኤል መልአክ
ተነሳ ከፊቴ >> >>
የአምላክ ባለመዋዕል >> >>
ሆነኸኝ ብርታቴ >> >>
ለኔስ ልዩ ነው ያንተ ፍቅር
ቁምልኝ ቅዱስ ዑራኤል በቅድመ እግዚአብሔር
አዝ= = = = =
በእምነት አበረታኝ ዑራኤል መልአክ
ለነፍሴ እየራራ >> >>
አገዘኝ ዑራኤል >> >>
ፍሬን እንዳፈራ >> >>
ለኔስ ልዩ ነው ያንተ ፍቅር
ቁምልኝ ቅዱስ ዑራኤል በቅድመ እግዚአብሔር

እንኳን አደረሳችሁ አደረሰን🥰
🙏 መልካም በአል 🙏

ለኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ልጆች👇🏽
•➢ ሼር // SHARE





@meazahaymanot

Читать полностью…

መዓዛ ሃይማኖት በጎ አድራጎትና ጉዞ ማህበር

በአባታችን በተክለሃይማኖት ጸሎትና በአባታችን በሀብተ ማርያም ጸሎት በአባ ሳሙኤል  ጸሎት በአባታችን ሙሴ ጸሊም ጸሎት በእናታችን በቅድስት ክርስቶስ ሠምራ ጸሎት በእናታችን በቅድስት ፍቅርተ ክርስቶስ ጸሎት በረከታቸው ይደርብን በጸሎታቸው ይማረን። ከመከራ ሥጋ ከመከራ ነፍስ ይጠብቀን አሜን ።

በቅዱሳኑ ታሪክ ላይ ለተሣተፉት ሁሉ ቃለ ሕይወትን ያሰማልን

Читать полностью…

መዓዛ ሃይማኖት በጎ አድራጎትና ጉዞ ማህበር

ስንክሳር ዘወርሃ ታህሣሥ ሃያ አንድ (፳፩)
/channel/meazahaymanot

Читать полностью…
Subscribe to a channel