መጽዓ ቃል
መጽዐ ቃል እም ደመና /ዘይብል/፪/
ዝንቱ ውእቱ ወልድየ ዘአፈቅር/፬/
መጣ ቃል ከደመና እንዲህ የሚል/፪/
የምወደው የማፈቅረው ልጄ ይህ ነው/፬/
✨✨✨በስመአብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ አሐዱ አምላክ አሜን።
👉ታላቅ መንፈሳዊ ጉዞ ወደ ደብረ ከርቤ ዳግማዊ ጎለጎታ ደብረ ማዕዶት ቅድስት አርሴማ አንድነት ገዳም።
👉ከአዲስ አበባ 150 ኪ.ሜ ርቀት ላይ የሚገኝ ቅዱስ ቦታ ነው።
ቀን:21/05/2016
መነሻ ሰአት: 12:00
የጉዞ ሁኔታ:ደርሶ መልስ
የጉዞ ዋጋ: 500 (ሙሉ መስተንግዶን ጨምሮ)
መነሻ ቦታ: ፒያሳ ገነተ ጽጌ ቅዱስ ጊዮርጊስ ቤተክርስቲያን - መገናኛ- ጣፎ
ለበለጠ መረጃ: 0989680703
0960029538
አዘጋጅ: መዓዛ ሃይማኖት በጎ አድራጎት ማኅበር
ማሳሰቢያ: ሁሉም ሰው መታወቂያ የመያዝ ግዴታ አለበት‼️
👉የረቡዕ የአርብ የቅዳሜ የመስቀል የመድኃኔዓለም የሚባል👇
መስቀል አብርሀ በከዋክብት አሠርገወ ሰማየ ።እምኵሉሰ ፀሐየ አርአየ ።
መስቀል አብርሀ በከዋክብት አሠርገወ ሰማየ።
ኅዲጎ ተስዓ
ኀዲጎ ተስዓ/፬/
ወተስዓተ/፫/ ነገደ
@meazahaymanot
@meazahaymanot
✧━━━━━━━━━━━━━━✧
❍ㅤ ⎙ㅤ ⌲ ᶜᵒᵐᵐᵉⁿᵗ ˢᵃᵛᵉ ˢʰᵃʳᵉ
ወተመሰሉ
ወተመሰሉ ሰብአ ዐይን አባግዓ ላባ ወማይ
ወጥምቀት ዐባይ/፬/ ዐባይ/፪/ ወጥምቀት ዐባይ/፪/
@meazahaymanot
@meazahaymanot
@meazahaymanot
✧━━━━━━━━━━━━━━━━✧
❍ㅤ ⎙ㅤ ⌲ ᶜᵒᵐᵐᵉⁿᵗ ˢᵃᵛᵉ ˢʰᵃʳᵉ
ኀዲጎ ተስዓ ፫
ኀዲጎ ተስዓ ወተስዓተ ነገደ/፪/
ማዕከለ ባሕር/፬/ ቆመ ማዕከለ ባሕር
@meazahaymanot
@meazahaymanot
@meazahaymanot
✧━━━━━━━━━━━━━━━━✧
❍ㅤ ⎙ㅤ ⌲ ᶜᵒᵐᵐᵉⁿᵗ ˢᵃᵛᵉ ˢʰᵃʳᵉ
በቅዳሴ ጸሎት በመሳተፋችን የኃጢአት ስርየት እናገኛለን፤ በረከተ ሥጋም በረከተ ነፍስም እንታደላለን፤ ከሁሉም በላይ የክርስቶስን ቅዱስ ሥጋውን በልተን ክቡር ደሙን ጠጥተን የዘለዓለም ሕይወትን እናገኛለን።
በቤተክርስቲያናችን የታወቁና እስከአሁንም በአገልግሎት ላይ ያሉ ቅዳሴያት በዓይነት 14 ሲሆኑ ቀደም ባሉት ዘመናት በተለይ በወርኀ ጽጌ ይቀደስ የነበረ ‹‹መዓዛ ቅዳሴ›› የሚባል 15ኛ ቅዳሴም በቤተ ክርስቲያናችን ይገኛል፡፡
የሚባል 15ኛ ቅዳሴም በቤተ ክርስቲያናችን ይገኛል፡፡ 14ቱ የቅዳሴ አይነቶች የሚከተሉት ናቸው፣
1. ቅዳሴ ዘሐዋርያት / Kidasse the Hawariat
2. ቅዳሴ ዘእግዚእ / Kidasse the Egzi
3. ቅዳሴ ዘዮሐንስ ወልደ ነጐድጓድ
4. ቅዳሴ ዘእግዝእትነ ማርያም / Kidasse the Anaphora of Our Lady
5. ቅዳሴ ዘሠለስቱ ምእት
6. ቅዳሴ ዘቅዱስ አትናቴዎስ / Kidasse the Anaphora of St Athnasious
7. ቅዳሴ ባስልዮስ
8. ቅዳሴ ዘቅዱስ ጎርጎርዮስ ኤጲስቆጳስ ዘኑሲስ (የሆሣዕና ቅዳሴ)
9. ቅዳሴ ዘቅዱስ ኤጲፋንዮስ / Kidasse the Anaphora of St Epiphaneous
10. ቅዳሴ ዘቅዱስ ዮሐንስ አፈወርቅ / Kidasse the Anaphora of St John Chrysostom
11. ቅዳሴ ዘቅዱስ ቄርሎስ
12. ቅዳሴ ያዕቆብ ዘሥሩግ
13. ቅዳሴ ዘቅዱስ ዲዮስቆሮስ / Kidasse the Dioscoros
14. ቅዳሴ ዘቅዱስ ጎርጎርዮስ
https://m.youtube.com/channel/UCKGh-U7U7pnvFUIEGXPOnNw
ከዚሁ ጋር በማያያዝ የሚዜመው ከላይ በርእሱ እንደገለጽነው የአዋጅ ቃል ነው። እንዲህ ይላል፦ “ሃሌ ሉያ እመቦ ብእሲ እምእመናን ዘቦአ ቤተ ክርስቲያን በጊዜ ቅዳሴ ወኢሰምኣ መጻሕፍተ ቅዱሳተ ወኢተአገሰ እስከ ኢፌጽሙ ጸሎተ ቅዳሴ ወኢተመጠወ እምቁርባን ይሰደድ እምቤተ ክርስቲያን እስመ አማሰነ ሕገ እግዚአብሔር ወአስተሐቀረ ቁመተ ቅድመ ንጉሥ ሰማያዊ ንጉሠ ሥጋ ወመንፈስ ከመዝ መሐሩነ ሐዋርያት በአብጥሊሶሙ - ሃሌ ሉያ በቅዳሴ ጊዜ ወደ ቤተ ክርስቲያን ገባ ሰው ቢኖር ቅዱሳት መጻሕፍትን ሰምቶ የቅዳሴውን ጸሎት እስኪጨርሱ ባይታገስ፣ ከቁርባን ባይቀበል፣ ከቤተ ክርስቲያን ይውጣ። የእግዚአብሔርን ሕግ አፍርስዋልና የነፍስና የሥጋ ንጉሥ በሚሆን በሰማያዊው ንጉሥ በክርስቶስ ፊት መቆምን አቃሏልና ሐዋርያት በሲኖዶሳቸው እንዲህ ሲሉ አስተማሩን” በማለት ይዜማል። እንግዲህ ይህ ሥርዓተ ቅዳሴው አሐዱ ተብሎ ከመጀመሩ በፊት በዜማ የሚተላለፍ መልዕክት ነው። ሥርዓተ ቅዳሴው ከመጀመሩ በፊት ቅዳሴውን ታግሰው ለማይፈጽሙ፣ ከጤና መታወክ ጋር በተያያዘ ምክንያት ካልሆነ በስተቀር በሰማያዊው ንጉሥ ፊት ቆመው የማያስቀድሱ ፣ከቅዱስ ቁርባን የማይቀበሉ ሰዎች ከቤተ ክርስቲያን መውጣት አለባቸው በማለት ሐዋርያት በሲኖዶስ ያወጁት አዋጅ ነው። እነዚህ የተዘረዘሩትን ነገሮች ማድረግ የማይችል ሰው ከሆነ በአፍአ ቆሞ ማስቀደስ ይችላል እንጂ እቤተ ክርስቲያን ውስት ቆሞ ማስቀደስ እንደሌለበት፣ ካደረገውም እግዚአብሔርን ማሳዘን እንደሆነ እንመለከታለን። ለዚህ ነው ቅዳሴ አስቀድሰን ከምስጢር ሳንሳተፍ ሥጋ ወደሙ ሳንቀበል መውጣት የለብን ተብሎ የሚነገረው።
በመጨረሻም “አንቲ ውእቱ መሶበ ወርቅ ንጹሕ እንተ ውስቴታ መና ኅቡዕ ኅብስት ዘወረደ እምሰማያት ወሃቤ ሕይወት ለኩሉ ዓለም - የተሰወረ መና በውስጧ ያለባት የወርቅ መሶብ አንቺ ነሽ። ከሰማያት የወረደ ኅብስት ለሰዎች ድኅነትን የሚሰ” የሚለው እንዲሁ በዜማ ይባል። መሶበ ወርቅ በብሉይ ኪዳን የመስዋዕት ማለትም ከስንዴ የሚሰራ ቂጣ ማስቀመጫ ነበር። በሐዲስ ኪዳንም ኅብስቱ ከቤተልሔም ወደ ቤተ መቅደስ የሚመጣበት ከንዋያተ ቅድሳት መካከል አንዱ ነው። ይህ መሶበ ወርቅ የእመቤታችን ምሳሌ ነው። ድኅነት የሚሰጠው ኅብስት በዚህ ውስት እንደተቀመጠ ሁሉ ድኅነተ ሥጋ ድህነተ ነፍስ የሰጠንን አምልክ በማህጸኗ የመሸከሟ ምሳሌ ነው። ይቆየን!
https://m.youtube.com/channel/UCKGh-U7U7pnvFUIEGXPOnNw
የቅዳሴ መግቢያ አዋጅ
ከገባሬ ሠናይ ካህኑ በስተቀር ሌሎቹ ልዑካን ወደ ቤተልሔም ወርደው ኅብስቱንና ወይኑን ይዘው ወደቤተ መቅደስ በሚመጡበት ሰዓት በዜማ የቅዳሴውን መግቢያ አዋጅ ያሰማሉ። ይህ ከቤተልሔም እስከ ቤተ መቅደስ ያለው ጉዞ የሚከናወነው ቃጭል እየተመታ ደወል እየተደወለ ነው። እዚህ ጋር ሁለቱን ነገሮች እንመልከት? ለምንድን ነው ከቤተልሔም እስከ ቤተ መቅደስ ጉዞ ሚደረገው? የደወሉስ መመታት ምክንት ምንድ ነው? ከቤተልሔም እስከ ቤተ መቅደስ የሚደረገው ጉዞ የሚያመለክተው ጌታችን መድኃኒታችን ኢሱስ ክርስቶስ በቤተልሄም ተወልዶ፣ ሰላሳ ሶስት ዓመት ከሶስት ወር አስተምሮ በመጨረሳም ከሊቶስጥራ እስከቀራንዮ ጨርቅ አልብሰው ግንድ አሸክመው እያዳፉ የወሰዱትን ጉዞ ለማስታወስ ነው። ደወሉም አምስት ጊዜ ይመታል። ይህም የክርስቶስን መምጣት አዋጅ ነጋሪ የነበረው፣ በተለይም አምላካችን ለቤዛ ዓለም መምጣቱን ድምጹን ከፍ አድርጎ “ነዋ በግዑ ለእግዚአብሔር ዘየሀትት ኃጢአተ ዓለም - እነሆ የዓለሙን ኃጢአት የሚያስወግድ የእግዚአብሔር በግ “ ዮሐ፤ 1፣36 እያለ የጮኸው የመጥምቁ ዮሐንስ ስብከት ምሳሌ ነው።
ወደ ቤተ መቅደስ ሲገቡም ከላይ እንደተገለጸው ዜማ በማዜም ነው። ይኸውም እንደየዕለቱና ዘመኑ ይለያያል። ዕለቱ ሰኞ፣ ማክሰኞና ረቡዕ ከሆነ፦ “እምነ በሐ ቅድስት ቤተ ክርስቲያን ስርጉት አረፋቲሃ ወስዕልት በእንቆጳዝዮን እምነ በሐ ቅድስት ቤተ ክርስቲያን - ቅድስት ቤተ ክርስቲያን ሆይ ሰላም ላንቺ ይሁን ግድግዳዎችሽ በጳዝዮን ዕንቁ የተጌጡ ናቸው፤ እናታችን ቤተ ክርስቲያን ሆይ ሰላም ላንቺ ይሁን።” በማለት በግዕዝ ዜማ በማዜም ወደ ቤተ መቅደስ ይገባሉ። ሕዝቡም አብሮ ያዜማል። ዕለቱ ረቡዕ፣ ዓርብና ቅዳሜ ከሆነ “መስቀል አብርሃ በከዋክብት አሰርገወ ሰማየ እምኩሉሰ ጸሐየ አርአየ - መስቀል አበራ በከዋክብት ሰማይን አስጌጠ ከሁሉም ጸሐይን አሳየ” ይባላል። በዕለተ ሰንበት ከሆነ ደግሞ “ኩሉ ዘገብራ ለጽድቅ ጻድቅ ውእቱ ወዘያከብር ሰንበተ ኢይበል ፈላሲ ዘገብአ ኀበ እግዚአብሔር ይፈልጠኒኑ እምሕዝቡ ኩሉ ዘገብራ ለጽድቅ ጻድቅ ውእቱ ወዘያከብር ሰንበተ - በጎን ሚያደርግ ሰንበትን የሚያከብር ሁሉ ጻድቅ ነው።ወደ እግዚአብሄር አምልኮ የገባ መጻተኛ ከሕዝቡ ሁሉ ይለየኝ? ይሆን አይበል በጎ ያደረገ ሰንበትን የሚያከብር ሁሉ ጻድቅ ነው።” የሚለው እንዲሁ በግዕዝ ዜማ ይባላል። እነዚህ በሶስቱ ጊዜያት ለምን ተለያዩ? ስንል ይህ ቀለም በቤተ ክርስቲያናችን እስመ ለዓለም ተብሎ ይጠራል። እስመ ለዓለም ደግሞ የዘወትር፣ ቅንዋትና የሰንበት ተብሎ ለሶስት ይከፈላል። ቅንዋትና የሰንበት ከዘወትሩ ቀለም የተለያየበት ምክንያት ቅንዋት ማለት መቸንከር ማለት ሲሆን ጌታችን መድኃኒታችን ኢሱስ ክርስቶስን በመስቀል ላይ ስለደረሰበት መከራ የሚያወሳ፤ ችንካሩን፣ ግርፋቱን፣ ሞቱን፣ በማንሳትና በማውሳት የተደረሰ ነው። በዚህ ቀለም ውስጥ የግዴታ መስቀልን የሚጠቅስ ነገር መኖር አለበት። ለዚህ ነው መስቀል አብርሃ የተባለው። ረቡዕና ዐርብ ቅዳሜ ቅንዋት የተባለበት ምክንያት ደግሞ ረቡዕ አይሁድ ክርስቶስን በስቅላት ለመግደል የተስማሙበት፣ ዓርብ በመስቀል ቸንክረው የሰቀሉት፣ ቅዳሜ የቸነከሩትና የገደሉት አምላክ በከርሰ መቃብር ውስጥ እንዳደረ በማውሳት የሚነገር ቃለ እግዚአብሔር ነው። በእርግጥ በማኅሌቱ ቅንዋት የሚቆመው ቅዳሜ ብቻ ነው። በቅዳሴው ግን በሶስቱም ቀናት ይባላል። የዕለተ ሰንበት እስመ ለዓለም ደግሞ ሰንበት የሚል ቃል ያለበት መሆን አለበት። ከላይ እንዳየነው ሰንበትን የሚያከብር ሰው የሚያገኘውን ዋጋ ይነግረናል። ምክንያቱም የሰንበት ጌታዋ ኢሱስ ክርስቶስ ነው። ሰንበትን ማክበር እርሱን ማክበር ነው። በማኅሌቱ እስመ ለዓለም ካየን ደግሞ “እግዚአ ለሰንበት” የሚለው ቃል አይቀርም። ትርጉሙም የሰንበት ጌታ ማለት ሲሆን ጌታችን ኢሱስ ክርስቶስ ሙስና መቃብርን ድል አድርጎ የተነሳባትና ለሰው ልጆች የደስታ ቀን አድርጎ የሰጣለት ዕለት መሆኗ ሁልጊዜም በሰንበቱ ይዘከራል።
ከላይ ያየነው በየዕለቱ ተከፍሎ የሚባል ሲሆን ዘመኑ ደግሞ በበዓለ ሃምሳ ወይንም ትንሳኤ ከዋለ በኋላ ባሉት ሃምሳ ቀናት ደግሞ የሚባለው የተለየ ቀለም ነው። ይኸውም፦ “ሃሌ ሉያ ዮሴፍ ወኒቆዲሞስ ገነዝዎ ለኢየሱስ በሰንዱናት ለዘተንስአ እሙታን በመንክር ኪን - ዮሴፍና ኒቆዲምን ኢየሱስን በሰንዱናት ገነዙት እርሱም በታላቅ ተአምር ከሙታን ተለይቶ ተነሳ” የሚለውን በአራራይ ዜማ ይባላል። እንደሚታወቀው በዚህን ወቅት ጌታችን ሞትን ድል ነስቶ መቃብር ክፈቱልኝ፣ መግነዝ ፍቱልኝ ሳይል ኅትምት ከምትሆን ከድንግል ማርያም የተወለደው እርሱ ኅቱም ከሆነ መቃብር መነሳቱን የምንዘክርበት ነው።
ይቀጥላል
https://m.youtube.com/channel/UCKGh-U7U7pnvFUIEGXPOnNw
አዲስ የልደት መዝሙር
#ጽድቅና_ሰላም
👳♂ሊቀ መዘምራን ቴዎድሮስና ቀሲስ ወንድወሰን
ለኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ልጆች👇
•➢ ሼር // SHARE
☑️ሼር ይደረግ
💾4.6 MB Mp3
#share & join
🔻 𝒔𝒖𝒃𝒔𝒄𝒓𝒊𝒃𝒆 🔻
@meazahaymanot
@meazahaymanot
🔻 𝒔𝒖𝒃𝒔𝒄𝒓𝒊𝒃𝒆 🔻
✞ ብርሃን ዘበአማን ✞
"ብርሃን ዘበአማን ዘያበርህ ለኲሉ ሰብእ፣ ለእለ ይነብሩ ውስተ ዓለም፣ በእንተ ፍቅረ ሰብእ መጻእከ ውስተ ዓለም፤ ወኲሉ ፍጥር ተፈሥሃ በምጽአትከ"
"በዚህ ዓለም ለሚኖሩት ሰዎች ሁሉ የምታበራ እውነተኛ ብርሃን ስለ ሰው ፍቅር ወደ ዓለም የመጣህ ፍጥረት ሁሉ በመምጣትህ ደስ አለው"/ውዳሴ ማርያም ዘሰኑይ/
በውጭም በሀገር ውስጥም ላላቹ ለመላው የክርስትና እምነት ተከታዮች በሙሉ
✞ እንኳን ለጌታችን ለመድኃኒታችን ለኢየሱስ ክርስቶስ የልደት በዓል በሰላም አደረሰን፤ የሰላም በዓል ያድርግልን!
@meazahaymanot
💠💠💠💠💠💠💠
ሥርዓተ ማኅሌት ዘልደት
🍀🍀🍀🍀🍀🍀🍀🍀🍀🍀🍀🍀
የማንኛውም ወርኃ በዓልና ክብረ በዓል ሥርዓተ ማኅሌት መጀመሪያ "ሥርዓተ ነግሥ"
ስምዓኒ እግዚኦ ጸሎትየ ሃሌ ሉያ፤ ሃሌ ሉያ ወይብጻሕ ቅድሜከ ገዓርየ ሃሌ ሉያ፤ ሃሌ ሉያ ወኢትሚጥ ገፀከ እምኔየ፤ በዕለተ ምንዳቤየ አጽምእ ዕዝነከ ኀቤየ ሃሌ ሉያ፤ ሃሌ ሉያ አመ ዕለተ እጼውአከ ፍጡነ ስምዓኒ ሃሌ ሉያ፤ ሃሌ ሉያ ለዓለም ወለዓለመ ዓለም፤ ሃሌ ሉያ ዘውእቱ ብሂል፤ ንወድሶ ለዘሃሎ እግዚአብሔር ልዑል፤ ስቡሕ ወውዱስ ዘሣረረ ኲሎ ዓለመ፤ በአሐቲ ቃል።
@meazahaymanot
መልክአ ሥላሴ
ሰላም ለአጻብኢክሙ እለ እምአጽፋር ኢይትሌለዩ፤ ለቤትክሙ ሥላሴ ዘኢየኃልቅ ንዋዩ፤ አመ አብዓልክሙ ሰብአ ድኅረ አንደዩ ጌጋዩ፤ ዘኢርእዩ እምቅድመ ዮም መላእክተ ሰማይ ርእዩ፤ ወአግብርተ ሰብእ መላእክት ተሰምዩ።
ዚቅ
ርእይዎ ኖሎት አእኮትዎ መላእክት፤ ለዘተወልደ እማርያም እምቅድስት ድንግል፤ ዮም ሰማያዊ በጎል ሰከበ።
ወረብ
'ርእይዎ ኖሎት'/፪/ አእኮትዎ መላእክት/፪/
ዮም ሰማያዊ በጎል ሰከበ ለዘተወልደ እምቅድስት ድንግል/፪/
ዘጣእሙ፦
ሰላም ለዝክረ ስምኪ ዘመንክር ጣዕሙ፤ ለወልድኪ አምሳለ ደሙ፤ መሠረተ ህይወት ማርያም ወጥንተ መድኃኒት ዘእምቀዲሙ፤ ኪያኪ ሠናይተ ዘፈጠረ ለቤዛ ዓለሙ፤ እግዚአብሔር ይትባረክ ወይትአኮት ስሙ።
ዚቅ
መሠረታቲሃ ውስተ አድባር ቅዱሳን፤ ወብእሲ ተወልደ በውስቴታ።
ነግሥ
ሰላም ለልደትከ ኦ አማኑኤል፤ ዘቀዳሚ ወዘደኃሪ ብሉየ መዋዕል፤ ኢየሱስ ክርስቶስ ዘአብ ቃል፤ እፎ እፎ አግመረተከ ድንግል፤ ወእፎ እንዘ አምላክ ሰከብከ በጎል።
@meazahaymanot
ዚቅ
በጎል ሰከበ በአጽርቅት ተጠብለለ፤ ውስተ ማኅጸነ ድንግል ኃደረ፤ እፎ ተሴሰየ ሀሊበ ከመ ሕፃናት።
@meazahaymanot
ወረብ
በጎል ሰከበ በአጽርቅት ተጠብለለ ኃደረ ማኅጸነ ድንግል/፪/
እፎ 'ተሴሰየ'/፪/ ሀሊበ ከመ ሕፃናት ተሴሰየ/፪/
@meazahaymanot
መልክአ ኢየሱስ
ሰላም ለዝክረ ስምከ ስመ መሐላ ዘኢይሔሱ፤ ዘአንበረ ቅድመ እግዚአብሔር በአትሮንሱ፤ ኢየሱስ ክርስቶስ ለዳዊት ባሕርየ ከርሱ፤ አክሊለ ስምከ እንዘ ይትቄጸል በርእሱ፤ አህጉረ ፀር ወረሰ ኢያሱ።
@meazahaymanot
ዚቅ
ሃሌ ሃሌ ሉያ ንሰብከ ወልደ እምዘርዓ ዳዊት ዘመጽአ፤ ወተወልደ በሥጋ ሰብእ፤ እንዘ ኢየዓርቅ እመንበረ ስብሐቲሁ፣ ውስተ ማኅፀነ ድንግል ኀደረ ሥጋ ኮነ ወተወልደ፤ ትጉኃን የአምኑ ልደቶ፤ ወሱራፌል ይቀውሙ ዓውዶ፤ መጽአ ይቤዝወነ ውስተ ዓለም የሀበነ ሰላመ፤ ጋዳ ያበውዑ ቁርባነ።
ወረብ
'ውስተ ማኅጸነ ድንግል ኃደረ'/፪/ ሥጋ ኮነ/፪/
ወተወልደ በሥጋ ሰብእ ሥጋ ሰብእ በሥጋ ሰብእ/፪/
ዘበአታ፦
ወልድ ተወልደ መድኃኒነ ፤ጥዩቀ እምዘርዓ ዳዊት፤ በቤተልሔም ዘይሁዳ
ወረብ፦
ወልድ ተወልደ መድኃኒነ ጥዩቀ ወልድ ተወልደ
እምዘርዓ ዳዊት ቤተልሔም በቤተልሔም
መልክአ ኢየሱስ
ሰላም ለአጽፋረ እዴከ ዘኅበሪሆን ፀዓዳ፤ በምገባር ወግእዝ እለ ይትዋሐዳ፤ ኢየሱስ ክርስቶስ ምስፍና አባሉ ለይሁዳ፤ ለመንግሥትከ ሰፋኒት እንዘ ይትመሐለሉ ዓውዳ፤ ሰብአ ሰገል አወፈዩ ጋዳ።
ዚቅ
አንፈርዓጹ ሰብአ ሰገል፤ አምኃሆሙ አምጽኡ መድምመ፤ ረኪቦሙ ሕፃነ ዘተወልደ ለነ።
@meazahaymanot
ወረብ
አንፈርዓጹ ሰብአ ሰገል/፬/
አምኃሁ አምጽኡ መድምመ/፪/
@meazahaymanot
መልክአ ኢየሱስ
እምኲሉ ይኄይስ በሥላሴከ ተአምኖ፤ ወበወላዲትከ ተማኅፅኖ፤ ኢየሱስ ክርስቶስ እምቤተ መንግሥት ወተክህኖ፤ ተሰብኦትከ እመቦ ዘያስተሐቅር መኒኖ፤ ያንኮርኲር ታሕት ደይን ግዱፈ ከዊኖ።
@meazahaymanot
ዚቅ
ወካዕበ ተማኅፀነ በማርያም እምከ፤ እንተ ይእቲ እግዝእትነ፤ ወትምክሕተ ዘመድነ በወሊዶተ ዚአከ።
@meazahaymanot
ወረብ
'ትምክሕተ ዘመድነ'/፪/ በወሊዶተ ዚአከ/፪/
ይእቲ 'እግዝእትነ'/፪/ ማርያም ድንግል/፪/
ማኅሌተ ጽጌ
ኦ ዝ መንክር በዘዚአኪ አምሳል፤ ኮከበ ትንቢት ዘቦቱ መልክአ ሕፃን ሥዑል፤ ሠረቀ ያርኢ ተአምረኪ ድንግል፤ ወመርሖሙ ለሰብአ ሰገል እምርሑቅ ደወል፤ ጽጌኪ ኀበ ሀሎ ይሰክብ በጎል።
ዚቅ
ወኖሎት በቤተ ልሔም፤ አንከሩ እምዘርእዩ ወሰምዑ፤ ሰብአ ሰገል ርእዮሙ ኮከበ፤ መጽኡ እምርኁቅ ብሔር፤ ከመ ይስግዱ ለወልድኪ ወይግነዩ ለኪ።
@meazahaymanot
ወረብ
በኮከብ መጽኡ ሰብአ ሰገል/፪/
ይስግዱ ለአማኑኤል ይስግዱ/፪/
@meazahaymanot
አንገርጋሪ
ዮም ፍሥሐ ኮነ በእንተ ልደቱ ለክርስቶስ፤ እምቅድስት ድንግል፤ ውእቱ ኢየሱስ ክርስቶስ፤ ዘሎቱ ሰብአ ሰገል ሰገዱ ሎቱ፤ አማን፤ መንክር ስብሐተ ልደቱ።
@meazahaymanot
አመላለስ
'አማን በአማን'/፪/ መንክር 'አማን በአማን'/፪//፩/
መንክር ስብሐተ ልደቱ/፬/
@meazahaymanot
ወረብ
ዮም ፍሥሐ ኮነ በእንተ ልደቱ ለክርስቶስ/፪/
እምቅድስት 'ድንግል'/፪/ ውእቱ ኢየሱስ ክርስቶስ/፪/
@meazahaymanot
እስመ ለዓለም
ተወልደ ኢየሱስ በቤተ ልሔም ዘይሁዳ፤ አዋልደ ጢሮስ አሜሃ ይሰግዳ፤ ሰብአ ሰገል አምጽኡ ሎቱ ጋዳ፤ ወይትኃሠያ አዋልደ ይሁዳ።
አመላለስ፦
ሰብአ ሰገል አምጽኡ ሎቱ ጋዳ፤[፪]
ወይትኃሠያ አዋልደ ይሁዳ።[፬]
@meazahaymanot
ወረብ
ተወልደ ኢየሱስ 'በቤተ ልሔም'/፪/ ዘይሁዳ በቤተ ልሔም/፪/
አዋልደ ጢሮስ 'አሜሃ ይሰግዳ'/፪/ በቤተ ልሔም/፪/
@meazahaymanot
ዕዝል
በጎል ሰከበ በአጽርቅት ተጠብለለ፤ ውስተ ማኅጸነ ድንግል ኃደረ፤ ዮም ተወልደ፤ እግዚእ ወመድኅን፤ ቤዛ ኲሉ ዓለም።
@meazahaymanot
@meazahaymanot
አመላለስ
ቤዛ ኲሉ ዓለም ዮም ተወልደ/፪/
'ቤዛ ኲሉ ዓለም'/፪/ ዮም ተወልደ/፬/
@meazahaymanot
ሰላም
ተሣሐልከ እግዚኦ ምድረከ ሃሌ ሉያ፤ ንሰብክ ወልደ እምዘርዓ ዳዊት ዘመጽአ፤ ወተወልደ በሥጋ ሰብእ፤ እንዘ ኢየዓርቅ እመንበረ ስብሐቲሁ፤ ውስተ ማኅጸነ ድንግል ኃደረ ሥጋ ኮነ ወተወልደ፤ ትጉሃን የአምኑ ልደቶ፤ ወሱራፌል ይቀውሙ ዓውዶ፤ መጽአ ይቤዝወነ ውስተ ዓለም የሀበነ ሰላመ፤ ጋዳ ያበውዑ ቁርባነ።
@meazahaymanot
@meazahaymanot
#Join & share
ኀዲጎ ተስዓ ወተስዓተ ነገደ/፪/
ማዕከለ ባሕር/፬/ ቆመ ማዕከለ ባሕር
@meazahaymanot
@meazahaymanot
@meazahaymanot
✧━━━━━━━━━━━━━━━✧
❍ㅤ ⎙ㅤ ⌲ ᶜᵒᵐᵐᵉⁿᵗ ˢᵃᵛᵉ ˢʰᵃʳᵉ
ሶበ መጽአ ቃል
ሶበ መጽአ ቃል እም ሰማይ ለተናብቦ
ከበቦ/፫/ ለማየ ባሕር መጽአ ነድ ለማይ ከበቦ/፪/
@meazahaymanot
@meazahaymanot
✧━━━━━━━━━━━━━━✧
❍ㅤ ⎙ㅤ ⌲ ᶜᵒᵐᵐᵉⁿᵗ ˢᵃᵛᵉ ˢʰᵃʳᵉ
በስመ አብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ አሐዱ አምላክ ንዌጥን
በረድኤተ እግዚአብሔር ሕያው ወላዲተ
አምላክ ጸሎታ ወበረከታ የሃሉ ምስሌነ ለዓለመ ዓለም
አሜን።
ረድኤተ እግዚአብሔርን አጋዥ በማድረግ ሥርዓተ ቅዳሴ ትምህርታችንን እንጀምራለን
እምነ በሀ
እምነ በሀ፥ ቅድስት ቤተ ክርስቲያን ፥ ስርጉት አረፋቲሃ ወሥዕልት በእንቁ ጳዝዮን
@meazahaymanot
ሃሌ/፫/ሉያ ሃሌ/፪/ሉያ ሃሌሉያ ተጠምቀ ሰማያዊ በእደ መሬታዊ/፪/
@meazahaymanot
@meazahaymanot
✧━━━━━━━━━━━━━━━✧
❍ㅤ ⎙ㅤ ⌲ ᶜᵒᵐᵐᵉⁿᵗ ˢᵃᵛᵉ ˢʰᵃʳᵉ
ልደታ ማርያም ሆይ እናቴ.....
ስላንቺ ውዳሴ ልፃፍ ብል ምን ያህል ቃል ይበቃል ፣
ሚስጥር ነሽ የማትገለጭ ፍቅርሽ ከሁሉ ይልቃል፣
ዜማሽ እንደ ማዕበል ነፍስን ከስጋ ይነጥቃል ፣
ትህትናሽ ክንፉን ዘርግቶ ወደ አርያም ያመጥቃል ፤
የእንቁ ብርሃን ከቦሻል ፊትሽ ያንፀባርቃል ፣
አለም ብፅይት እያለ ከእግርሽ ጫማ ስር ይወድቃል።
ቅኔሽ የማይፈታ መዓዛሽ ያማረ ውብ ፀአዳ ፣
ሱላማጢስ የሠላም እናት ሙሽራዬ ነይ የእኔ እንግዳ
ጳጦስ ዘደብረ ሲና እንቆጳዝዮን ማዕፍዳ ፣
ዘላለም ነው እናቴ ሰላም ካንቺ የሚቀዳ ።
ማርያም ማርያም ልበልሽ ምርኩዝ ሆነሽኝ ድጋፌ ፣
መሶበ ወርቅ ንፁህ አንቺ ነሽ ህይወት መፃፌ ፣
ከማር ሊጣፍጥ ውዳሴሽ ሞልቶ ይፈሳል በአፌ
ልደታ ለማርያም ምልጃዋ አይለየን🙏
#መልካም__ቀን 🙏
በሐዋርያት ሥራ ምዕራፍ ፩ ቁጥር ፰ ጌታችን መድኃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ለደቀ መዛሙርቱ የተናገራቸው ቃል «በኢየሩሳሌምና በይሁዳ ሁሉ፤ በሰማርያ እስከ ምድር ዳርቻ ድረስም ምስክሮቼ ትሆኑኛላችሁ»
ምስክርነት ካላችሁ በዚህ ቻናል መመስከር እግዚአብሔርን ማመስገን ትችላላችሁ
@misiwani_Bot አድርሱን
ውድ የዚህ ቻናል ተከታታይ የኦርቶዶክሳዊት ተዋሕዶ ልጆች እንኳን ለብርሃነ ልደቱ በሠላም አደረሳችሁ
ይኸን pdf በማንበብ መንፈሳዊ ሕይወታችሁን አበርቱ
ልደተ ክርስቶስ
ቅድስት ድንግል ማርያም ለአረጋዊው ዮሴፍ ከታጨች በኋላ ናዝሬት ገሊላ ከምትባል ከተማ ትኖር በነበረበት ከዕለታት በአንዱ ቀን ውኃ ቀድታ ስትመለስ መንገድ ላይ በመሄድ ሳለች የእግዚአብሔር መልአክ ወደ እርሷ ቀርቦ እንዲህ አላት፤ ‹‹ትፀንሲ!›› እርሷም ድምጽን ሰምታ መለስ ብላ ብታይም ከአጠገቧ ማንንም ማየት ባለመቻሏ ‹‹አዳም አባቴን እና ሔዋን እናቴን ያሳተ ጠላት ይሆናል እንጂ ሌላ አይደለም›› ብላ አሰበች፡፡ ዳግመኛም ‹‹ትፀንሲ›› የሚል ድምጽ ሰማች፡፡ ‹‹ይህ ነገር ደጋገመኝ፤ እንዲህ ያለውን ነገር ከቤተ መቅደስ ሆነው ሊረዱት ይገባል›› ብላ ከቤተ መቅደስ ገብታ ወርቅና ሐር እያስማማች መፍተል ጀመረች፡፡ (ነገረ ማርያም)
መልአኩ ቅዱስ ገብርኤልም በአምሳለ አረጋዊ እንዲህ አላት ‹‹ደስ ይበልሽ÷ ጸጋን የተመላሽ ሆይ÷ እግዚአብሔር ከአንቺ ጋር ነው፤ ከሴቶች መካከል አንቺ የተባረክሽ ነሽ፡፡›› ድንግል ማርያምም ‹‹እንዲህ ያለ የምስጋና እጅ መንሻ እንዴት ይደረግልኛል?›› ብላ ጠየቀችው፡፡ መልአኩም መልሶ ‹‹ማርያም ሆይ አትፍሪ፤ ከእግዚአብሔር ዘንድ ባለሟልነትን አግኝተሻልና፤ እነሆ ትፀንሺያለሽ፤ ወንድ ትወልጃለሽ፤ ስሙንም ኢየሱስ ትይዋለሽ፤ ይህ የሚወለደው ከሦስቱ ቅዱስ አንዱ ቅዱስ ነው፤ እርሱም የእግዚአብሔር ልጅ ይባላል›› አላት፡፡ እርሷም ‹‹ይህ ነገር እንደምን ይሆንልኛል፤ ወንድ ሳላውቅ?›› አለችው፡፡ መልአኩ ገብርኤልም ‹‹መንፈስ ቅዱስ ይጠብቅሻል፤ የልዑል ኃይልም ያድርብሻል›› አላት፡፡ እርሷም የመልአኩን ቃል ተቀብላ ‹‹እንደ ቃልህ ይደረግልኝ›› አለችው፤ በዚህ ጊዜ አካላዊ ቃል በግብረ መንፈስ ቅዱስ ተፀነሰ፡፡ (ሉቃ. ፩፥፳፰-፳፱፣ ኢሳ. ፯÷፲፬)
ከዚህ በኋላም ንጉሥ አውግስጦስ ቄሳር ሕዝቡን ቀረጥ ለማስከፈል እንዲያመቸው በእስራኤል ሀገር ውስጥ ይኖሩ የነበሩ ሰዎችን ለማወቅ ቆጠራ እንዲደርግ አዘዘ፡፡ ሕዝቡም ለመቆጠር ወደ ትውልድ ስፋራው መጓዝ ጀመረ፡፡ እመቤታችን ድንግል ማርያምም የንጉሥ ዳዊት ዘር ሀረግ ስለነበራት ግዛቱ ወደ ነበረው ቤተ ልሔም ከአረጋዊው ዮሱፍ ጋር ሄደች፡፡ በዚያም ሳሉ እመቤታችን መውለጇ ቀን ደረሰ፡፡ ሆኖም ግን ከተማዋ ትንሽ ስለነበረችና ለመመዝገብ የመጣው ሰው ብዙ ስለነበረ ማረፊያ ቦታ ሊያገኙ አልቻሉም፡፡ አረጋዊው ዮሴፍም ከብዙ ድካም በኋላ ከብተቾች የሚያርፉበት በረት አግኝቶ እመቤታችንን በዚያ አስቀመጣት፡፡
በከብቶች በረት ውስጥ ሳሉ እመቤታችን የመውለጃዋ ጊዜ በመድረሱ ጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስን ወለደችው፤ በጨርቅ ጠቅልላ በበረት ውስጥ አስተኛችው፡፡
በዚያን ሌሊት በቤተ ልሔም ይኖሩ የነበሩ እረኞችም ከብቶቻቸውን ሲጠብቁ የእግዚአብሔር መልአክ በእረኞቹ አጠገብ ቆመ፤ የእግዚአብሔርም ብርሃን በዙሪያቸው በራ፤ በጣምም ፈሩ፡፡ መልአኩም እንዲህ አላቸው ‹‹እነሆ ለእናንተና ለሕዝቡ ሁሉ ደስታ የሚሆን ታላቅ የምሥራች እነግራችኋለሁና አትፍሩ፤ እነሆ፥ ዛሬ በዳዊት ከተማ መድኅን ተወልዶላችኋል፡፡ ይኸውም ጌታ እና እግዚአብሔር የሆነ መድኃኒታችን ኢያሱስ ክርስቶስ ነው፡፡ እናንተም ባገኛችሁት ጊዜ ምልክቱ እንዲህ ነው፡፡ ሕፃን በጨርቅ ተጠቅልሎ በበረት ውስጥ ተኝቶ ታገኙታላችሁ፤ ድንገትም ከዚያ መልአክ ጋር ብዙ የሰማይ መላእክት እግዚአብሔርን እያመሰገኑ መጡ፡፡›› (ሉቃ.፪፥፲-፲፫)
እረኞቹም እርስ በርሳቸው ‹‹እስከ ቤተ ልሔም እንሂድ፤ እግዚአብሔርም የገለጠልንን ይህን ነገር እንወቅ›› ተባባሉ፤ ፈጥነውም ሄዱ፡፡ ድንግል ማርያምንና ዮሴፍንም በከብቶቹ በረት አገኙአቸው፡፡ ሕፃኑንም በአዩት ጊዜ የነገሩአቸው እውን መሆኑን ስላዩ በጣም ተደነቁ፡፡ እረኞቹም እንደነገሩአቸው ባዩትና በሰሙት ሁሉ እግዚአብሔርን እያመሰገኑ ‹‹በሰማይ ለእግዚአብሔር ክብር ይሁን፤ በምድርም ለሰው ልጆች በጎፈቃድ ሆነ›› ብለው እያመሰገኑና እያከበሩ ወደመጡበት ተመለሱ፡፡ (ሉቃ.፪፥፲፭-፲፰)
ሰብአ ሰገልም የእግዚአብሔር ልጅ የተወለደበትን ዋሻ የሚያመለክት ኮከብ እየመራቸው ከምሥራቅ ወደ እርሱ መጡ፤ ስለ አምላክ መወለድ አስቀድመው ያውቁ ነበርና፡፡ ስለሆነም ኮከቡን ተከትለው ልጁን ይፈልጉ ነበር፡፡ የይሁዳም ንጉሥ ሄሮድስ ሕፃኑን ስለሚሹት ጠቢባን ሰዎች ሲሰማ ቀደም ብሎ ወደ ቤተ መንግሥቱ ጋበዛቸው፡፡ እንደ እነርሱም ጌታችን ኢየሱስን ለማምለክ እንደሚፈልግ በመግለጽ ልጁን ሲያገኙት ወደ እርሱ ይዘውት እንደሚመጡ ጥበበኞቹን ጠየቃቸው፡፡ ሄሮድስ ግን ዙፋኑን ሊወስድ ይችላል ብሎ በመፍራት ጌታ ኢየሱስን ለመግደል ፈለጎ እንጂ ሊያመልከው አልነበረም፡፡
ሰብአ ሰገልም በኮከብ ተመርተው ቅድስት ማርያምን፣ ዮሴፍን እና ጌታ ኢየሱስን ወደ ነበሩበት በረት በደረሱ ጊዜ በጉልበታቸው ተንበረከኩ፤ አምላክነቱን በመረዳትም ለሕፃኑ ሰገዱለት፤ ዕጣን፣ ወርቅና ቀርቤንም የእጅ መንሻ አድርገው አቀረቡለት፡፡
ሆኖም ግን ወደ ሄሮድስ አልተመለሱም፡፡ ሄሮድስ ኢየሱስን ሊጎዳ እንደሚፈልግ የሚያስጠነቅቅ ሕልም አስቀድመው በራእይ አይተው ነበርና፡፡ ይልቁንም በተለየ መንገድ ወደ ትውልድ ሀገራቸው ተመለሱ፡፡
ከዚያን ጊዜ ጀምሮ የጌታችን መድኃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስን ልደት በመላው የኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ሃይማኖት ተከታዮች ዘንድ በድምቀት ይከበራል፤ እርሱ ለእኛ መድኅን ነውና፡፡
የጌታችን መድኃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ልደት በሰውና በእግዚአብሔር መካከል እርቅ የወረደበት፣ ከኃጢአት ባርነት ነጻ የወጣንበት፣ ድንቅ የተዋሕዶ ምሥጢር የተፈጸመበት ነው፡፡ ነቢያት ስለክርስቶስ የተናገሩት ሁሉ ተፈጽመ፤ ስለ ጌታችን መወለድ ቅዱስ ዳዊትም ‹‹እነሆ በኤፍራታ ሰማነው በዱር ውስጥም አገኘነው›› ብሎ ተናግሯል፡፡ (መዝ. ፴፩፥፮)
በጌታችን ኢየሱስ ልደት መላእክትና ሰዎች በአንድነት ‹‹ስብሐት ለእግዚአብሔር›› እያሉ እግዚአብሔርን አመስግነዋል፡፡ በኃጢአታችን ሳቢያ አጥተነው የነበረውን አንድነት የመላእክትና የሰው ልጆች አንድነት ከብዙ ዘመን በኋላ በጌታችን ልደት እንደገና አገኘነው፡፡
ሊቁ ቅዱስ ዮሐንስ አፈወርቅም እግዚአብሔር አምላክ የሰውን ዘር በሙሉ ያዳነበትን ድንቅ ሥራ ሲገልጽ እንዲህ ብሏል፤ ‹‹ምን እላለሁ? ምንስ እናገራለሁ? ከዘመን አስቀድሞ የነበረው እርሱ ሕፃን ሆኗልና፡፡ እኔ ፈጽሜ አደንቃለሁ፡፡ ከሰማየ ሰማያት በላይ የሚሆን፣ በዘለዓለማዊ ዙፋን የሚኖር እርሱ በበረት ተጣለ፡፡ ከሥጋዌ አስቀድሞ አይዳሰስ የነበረ አንዱ እርሱ በምድራውያን እጅ ተዳሰሰ፡፡ ኀጢአትን የሚያስተሰርይ እርሱን በጨርቅ ጠቀለሉት፤ ይህን ወዷልና፤›› (ሃይማኖተ አበው ዘዮሐንስ አፈወርቅ፣ ፷፮፥፲፯)
እግዚአብሔር ወልድ ከእመቤታችን ቅድስት ድንግል ማርያም ከሥጋዋ ሥጋ፣ ከነፍሷ ነፍስ ነሥቶ ሰው ሆኖ ለእኛ የድኅነት መንገድ ሆነ፡፡ ጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ለአዳም የገባለትን ቃል ኪዳን ለመፈጸም ከሰማየ ሰማያት ወርዶ፣ ከቅድስት ድንግል ማርያም ተወልዶ፣ ሰው ሆኖ፣ በአጭር ቁመት በጠባብ ደረት ተወስኖ፣ በመስቀል ተሰቅሎ፣ ድኅነትን ለሰው ልጆች ሰጥቶ፣ በመስቀሉ ተጣልተው የነበሩ ሰባቱን መስተፃርራን (ሰውና እግዚአብሔርን መላእክትና ሰውን፣ ነፍስና ሥጋን፣ ሕዝብና አሕዛብን) አስታርቋል፡፡
በጌታችን ልደት ምክንያት እኛም ዳግም ተወልደን ከሞት ወደ ሕይወት ተሸጋገርን፤ ከጨለማ ወጥተን ብርሃን አገኘን፤ የእርሱ መወለድ የእኛም የክርስቲያኖች ሁሉ ልደት ነውና በዓሉን በክርስቲያናዊ ምግባር ታንጸንና በሥርዓተ ቤተ ክርስቲያን ልናከብር ይገባል፡፡
ሥርዓተ ቅዳሴ
ክፍል ፫
2ኛ. ጸሎተ አኮቴት (የንዑሰ ክርስቲያን ቅዳሴ)
ሁለተኛው የቅዳሴ ክፍል ጸሎተ አኮቴት ሲሆን አኮቴት ማለት አዕኮተ አመሰገነ ካለው የግስ ቃል የተገኘ ነው። ትርጉሙም ምስጋና ማለት ነው። ይህ ክፍል የንዑሰ ክርስቲያን ቅዳሴ ወይም የንባብ ቅዳሴ ተብሎም ይጠራል። በዚህ የቅዳሴ ክፍል ሁሉም ምእመናን ማለትም ንዑሰ ክርስቲያንን ጨምሮ የሚሳተፉበት ቅዳሴ ነው። በዚህም የተነሳ የንዑሰ ክርስቲያን ቅዳሴ ተብሎ ይጠራል። ንዑሰ ክርስቲያን ማለት በጥምቀት ሀብተ ወልድና ስመ ክርስትና ያላገኙ ነገር ግን ይህንን የእግዚአብሔርን ልጅነት በጥምቀት ከማግኘታቸው በፊት ትምህርተ ክርስትናን በመማር ላይ የሚገኙ ናቸው። በዚህ የትምህርት ጊዜ ውስጥ እያሉ ቤተ ክርስቲያን መሄዳቸውን አያቀርጡም፤ በቅዳሴም ይሳተፋሉ። ነገር ግን ሁሉንም የቅዳሴ ክፍል አይካፈሉም። ምክንያቱም ለምስጢር ያልበቁ በመሆናቸው ምስጢረ ስጋወ ደሙ በሚፈጸምበት ሶስተኛው የቅዳሴ ክፍል (ፍሬ ቅዳሴ) ላይ መሳተፍ ስለሌለባቸው “ጻዑ ንዑሰ ክርስቲያን - ታናናሽ የክርስቲያን ወገኖች (ክርስትናን ያልተቀበላችሁ) ውጡ” ተብሎ በዲያቆኑ እስከሚታወጅበት ድረስ ብቻ ቆመው ያስቀድሳሉ። እነዚህ ንዑሰ ክርስቲያን በሥርዓተ ቤተ ክርስቲያን ቆመው የሚያስቀድሱበት ቦታ ሁሉ ተወስኖላቸዋል። ይኸውም በመስዕ በኩል ቆመው በማስቀደስ ጻዑ እስከሚባል ይቆያሉ። መስዕ ማለት ከቤተ ክርስቲያን አቅጣጫዎች አንዱ ነው። በቤተ ክርስቲያን ስምንት አቅጣጫዎች ያሉ ሲሆን ሁሉም የቤተ ክርስቲያን ሥርዓት ይፈጸምባቸዋል። እነዚህም ሰሜን፣ ደቡብ፣ ምስራቅ፣ ምዕራብ፣ መስዕ (በሰሜንና በምስራቅ መካከል ወይም ሰሜናዊ ምሰራቅ)፣ ባሕር (በሰሜን በምዕራብ)፣ ሌብ (በደቡብ እና በምስራቅ) እና አዜብ (በደቡብና በምዕራብ መካከል ያለ) ስፍራ ነው። ስለዚህ ንዑሰ ክርስቲያን በመስዕ ወይም በቤተ ክርስቲያን ሰሜናዊ ምስራቅ በኩል ቆመው እስከ ጻዑ ድረስ እንዲያስቀድሱ ተወስኗል።
ይህ ክፍል የንባብ ቅዳሴ የተባለበት ምክንያት አራቱም የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት የሚነበቡበት ክፍል ስለሆነ ነው። ገባሬ ሠናዩ ዲያቆን (ዋናው ዲያቆን) ከቅዱስ ጳውሎስን መልዕክታት፣ ንፍቁ ዲያቆን (ሁለተኛው ዲያቆን) ከሐዋርያት መልዕክታት፣ ንፍቁ ቄስ የሐዋርያት ሥራን እና ገባሬ ሠናዩ ቄስ ደግሞ ወንጌል ያነባል። ሁሉም የሐዲስ ኪዳን ንባባት ተነበው የሚያበቁት እዚህ ክፍል ውስጥ ስለሆነ የንባብ ቅዳሴም ተብሎ ይጠራል።
ይህ ክፍል የሚጀምረው “ሚ መጠን ግርምት ዛቲ ዕለት - ይህቺ ዕለት ምንኛ የምታስፈራ ናት” ከሚለው ጀምሮ ጻዑ ንዑሰ ክርስቲያን እስከሚባል ድረስ ያለው ነው። በውስጡ በርካታ ነገሮችን የያዘ ስለሆነ ቀጥለን በአጭር በአጭሩ እነዚህን እንመለከታለን።
https://m.youtube.com/channel/UCKGh-U7U7pnvFUIEGXPOnNw