ሰላም ለጥምቀትከ በኍልቈ ክራማት ሠላሳ። እምዘወለደተከ ድንግል ዘኢተአምር አበሳ። አመ ቆምከ ዮም እግዚኦ ለዮርዳኖስ ማዕከለ ከርሣ። ለወድሶትከ ማዕበላቲሃ ተከውሳ። ወባረኩከ አናብርት ወዓሣ።
እንኳን ለብርሃነ ጥምቀቱ በሰላም አደረሳችሁ መልካም በዓል
በዕደ ዮሐንስ
በዕደ ዮሐንስ ተጠምቀ ኢየሱስ ናዝራዊ/2/
ሠማያዊ/4/ሠማያዊ ኢየሱስ ናዝራዊ/2/
አዳም ያጠፋውን ልጅነት ሊያስመልስ
በሠላሳ ዘመን ተጠመቀ ኢየሱስ
እርሱ አምላክ ሢሆን ፈጥሮ የሚገዛ
ወረደ ወደምድር እንዲሆነን ቤዛ
ኧኸ ሠማያዊ
ሊያጠፋው አቅልጦ እንደ አምላክነቱ
እረግጦ ሊሠርዝ እንደ ሠውነቱ
የፍጥረቱ ጌታ በዮርዳኖስ ቆሟል
የእዳውን ፅህፈት በስልጣኑ ሽሯል
የአንድነት ሶስትነት ተገልጧል ምስጢሩ
በዕደ ዮሐንስ ተጠምቆ መምህሩ
አብም በደመና ለልጁ መስክሯል
በአምሳለ ርግብ መንፈስ ቅዱስ ወርዷል
ሲነገር እንዲኖር የእርሱ ትህትና
ለዓለም እንዲገለጥ የባሪያው ልዕልና
ተጠማቂው ሄደ ወደ አጥማቂው
አምላክ የሠራልን ስርዓቱ ይህ ነው
በዕደ ዮሐንስ ተጠምቀ ኢየሱስ ናዝራዊ/2/
ሠማያዊ/4/ሠማያዊ ኢየሱስ ናዝራዊ/
ገሀድ ምንድን ነው?
ገሃድ የቃሉ ትርጉም መገለጥ መታየት ነው፡፡ በጥምቀት መገለጥ መባሉ ሰው የሆነው አምላክ በዓለም ሲኖር እስከ 30 ዓመት እድሜው ድረስ ሰዎችን ለማዳን የመጣ መሲህ ሰው የሆነበት፣ አምላክ ኢየሱስ ክርስቶስ እሱ መሆኑን ሳያውቁ ከኖሩ በኃላ በ 30 ዓመት እድሜው በባሕረ ዮርዳኖስ በእደ ዮሐንስ እጅ ሲጠመቅ አብ በደመና ሆኖ ‹‹የምወደው ልጄ ይህ ነው›› በማለቱ መንፈስ ቅዱስ በርግብ አምሳል በራሱ ላይ ሲያርፍ በመታየቱ ነቢያት ይወርዳል ይወለዳል ይሰቀላል ይሞታል ይነሳል ብለው የተናገሩለት መሲሕ እርሱ መሆኑ ተገልጦአልና እንዲሁም ሦስቱ አካላት በአንድ ጊዜ ታይተዋልና ምስጢረ ሥላሴ የተገለጠለት በመሆኑ ገሃድ ይባላል፡፡(ማቴ 3፡13-17)
ይህን በማሰብ ይምንጾመው ጾም “የገሃድ ጾም” ይባላል፡፡ ቀኑም ጥር 10 ቀን ለ 11 አጥቢያ ነው፡፡ስለዚህ ጥር 10 ቀን ከ ሰባቱ አጽዋማት አንዱ የሆነው የገሀድ ጾም ነው ማለት ነው!
ከተራ ምንድን ነው?
ከተራ ከበበ ካለው የግእዝ ግሥ የወጣ ነው፡፡ ፍችው ውኃ መከተር፣ መገደብ ማለት ነው፡፡ የጥምቀት ዋዜማ ታቦተ ሕጉ ከቤተ መቅደስ ወጥቶ ውኃ ባለበት አካባቢ ስለሚያድር የየአጥቢያው ሕዝብ እየተሰበሰበ በወንዝ ዳር ወይም በምንጭ አካባቢ ድንኳን ይተከላል፡፡ ድንኳንም ከሌለ ዳስ ሲጥል ይውላል፡፡ የምንጮች ውኃ ደካማ በመሆኑ እንዲጠራቀም ይከተራል ጉድጓድ እየተቆፈረ ውኃው እንዳይሄድ ይገደባል፡፡
• በበዓለ ጥምቀት የታቦታቱ ወደ ወንዝ መውረድ መድኃኔ ዓለም ክርስቶስ በእደ ዮሐንስ ለመጠመቅ ከገሊላ ወደ ዮርዳኖስ በዋዜማው የመኼዱ ምሳሌ ነው፡፡ ታቦቱ የጌታችን፣ምሳሌ ሲኾን ካህናቱ የመጥምቁ ዮሐንስ ምሳሌ ሲኾን መዘምራኑና ሕዝቡ ደግሞ ዮሐንስ ያጠመቃቸው ሕዝቦች ምሳሌዎች ናቸው፡፡
• በባሕረ ጥምቀቱ ላይ በሚንሳፈፍ ነገር መብራት መደረጉ በርግብ አምሳል ለወረደው መንፈስ ቅዱስ ምሳሌ ነው፡፡
"የአምላካችሁን የእግዚአብሔርን ቃል ኪዳን ታቦትና ሌዋውያን ካህናት ተሸክመውት ባያችሁ ጊዜ፥ ከሰፈራችሁ ተነስታችሁ ተከተሉት። " ኢያሱ 3:3
https://m.youtube.com/channel/UCKGh-U7U7pnvFUIEGXPOnNw
#ጥር_8/5/2016 #አቡነ_ኪሮስ
👉አንድ አምላክ በሆነ በአብ በወልድ በመንፈስ ቅዱስ ስም ቤተ ክርስቲያናችን በዚህ እለት በመታሠቢያ በዓላቸዉ ከምታስባቸዉ ቅዱሣን አንዱ ለሆኑት ፃድቁ አቡነ ኪሮስ ለወርሐዊ በአላቸው እንኳን አደረሰን
👉የጻድቁን ስም የሚጠራ አፍ ንዑድ ነው ክቡር ነው በእውነት የቅዱሱን አባት ክብር ለማግኘት መፋጠን ይበጃል አቡነ ኪሮስ የተወለዱት በ4ኛው መቶ ክ/ዘመን ሲሆን ወላጆቻቸው ነገሥታት ናቸው
👉ተወልደው ባደጉባት ሃገር ቁስጥንጥንያ ገና በልጅነት ምቾት ሳያሳሳቸው መጻሕፍትንና ትሕርምትን ተምረዋል ወንድማቸው (ታላቁ ቴዎዶስዮስ) በነገሠባቸው የመጀመሪያ ዓመታት በቤተ መንግስቱ ዙሪያ ግፍ በዝቶ ነበርና አቡነ ኪሮስ ከኃጢአት ለመራቅና ለጌታ ለመገዛት ከከተማው ጠፍተው አሕጉር አቁዋርጠው ወደ ግብፅ (ገዳመ አስቄጥስ) መጡ
👉እርሳቸውን ለመፈለግ የተደረገው ሙከራ አልተሳካም ይባስ ብሎ የንጉሡ ልጅ ገብረ ክርስቶስ ሙሽርነቱን ጥሎ ወደ ሌላ ሃገር መነነ "የቅኖች ትውልድ ይባረካል" እንዳለ ቅዱስ ዳዊት አቡነ ኪሮስ ለሙሽራው ገብረ ክርስቶስ አጎቱ ናቸው አቡነ ኪሮስ በገዳም ውስጥ የታላቁ አቡነ በብኑዳ ደቀ መዝሙር ሆነው ለዘመናት ቆይተዋል
👉ቅዱስ በብኑዳን አንበሳ በበላው ጊዜ በጣም አዝነው "ለምን ጌታ ሆይ?" በሚል መሬት ላይ ወድቀው አለቀሱ "ምክንያቱ ካልተነገረኝ አልነሳም" ብለው ከወደቁበት መሬት ላይ ሳይነሱ ለ40 ዓመታት አልቅሰዋል በዚህ ምክንያት ግማሹ አካላቸው አፈር ሆኖ ሣር በቅሎበታል ጌታችን ተገልጦ ምክንያቱን ነግሯቸዋል አካላቸውንም እንደነበረ መልሶላቸዋል::
👉አንድ ቀን ጻድቁ ለቅዱስ በብኑዳ ሞት ምክንያት የሆነው መነኮስ ታንቆ መሞቱን ሰምተው በጣም አዘኑ ሱባዔ ገብተው ፍጹም አልቅሰው ከጌታም አማልደው የዛን ኃጥእ ነፍስ ከሲዖል አውጥተዋል በሌላ ጊዜ ደግሞ ኃጥአን የሞሉበት አንድ ገዳም በግብፅ ነበርና መቅሰፍት ወርዶ ሁሉንም ባንድ ቀን ሲያጠፋቸው አዩ
👉ፃድቁ በዚህም ምክንያት ለ30 ዓመታት አልቅሰው ሙታኑን አስነስተው ንስሃ ሰጥተው ገዳሙን የጻድቃን ሕይወታቸውንም የፍቅር አድርገውታል ፃድቁ እመቤታችንን ከመውደዳቸው የተነሳ በስዕሏ ፊት አብዝተው ይሰግዱና ያለቅሱ ነበር እመ አምላክም ተገልጣ ትባርካቸው ነበር
👉ከዚህ በሁዋላ ወደ ምዕራብ አቅጣጫ ሒደው ለ57 ዓመታት ማንንም ሳያዩ ተጋደሉጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ (ለስም አጠራሩ ስግደት ይሁንና) በየቀኑ ይጐበኛቸው ቁጭ ብሎም ያወራቸው ነበር
👉በመጨረሻም ጌታ አእላፍ መላእክትን ፃድቃን ሰማዕታትን ድንግል እመቤታችንና ቅዱስ ዳዊትን አስከትሎ ወረደ
👉ቅዱስ ዳዊት ቀርቦ እያጫወታቸው በበገናው እየደረደረላቸው ከዝማሬው ጣዕም የተነሳ ነፍሳቸው ከሥጋቸው በፍቅር ተለየች ጌታችንም ታቅፎ ስሞ ይዟቸው አረገ
👉ሥጋቸውን አባ ባውማ ቀበሩት የአቡነ ኪሮስ ቁመታቸው ቀጥ ያለ ፅሕማቸውም የተንዠረገገ ነበር እድሜአቸውን ግን መገመት የሚቻል አይመስለኝም
👉የፃድቁ አባታችን ምልጃና ፀሎት ይጠብቀን ረድኤት በረከታቸዉ አይለየን "አሜን"
ታላቅ መንፈሳዊ ጉባኤ በቡራዩ ክ/ከተማ የጠሮ መካነ ቅዱሳን አቡነ ገብረ መንፈስ ቅዱስ ወቅድስት አርሴማ ቤተክርስቲያን የገቢ ማሳሰቢያ
ጉባኤው የሚከናወንበት ቦታ: መንበረ ጸባኦት ቅድስት ሥላሴ ቤተክርስቲያን አዳራሽ (አራት ኪሎ)
የጉባኤ ቀን : መጋቢት 15/2016 ዓ.ም
መግቢያ ዋጋ : 100 ብር ብቻ
የመንፈሳዊ ጉባኤውን ትኬት የሚፈልጉ ከሆነ ይደውሉ፡፡ 0960029538
ባሉበት ትኬቱ እንዲደርሶ እናደርጋለን፡፡ ሰብሰብ አድርገው ቢገዙ ይበረታታል! እናመሰግናለን
የመንፈሳዊ ጉባኤውን ትኬት የሚፈልጉ ከሆነ ይደውሉ፡፡ 0960029538
ባሉበት ትኬቱ እንዲደርሶ እናደርጋለን፡፡ ሰብሰብ አድርገው ቢገዙ ይበረታታል! እናመሰግናለን
ወይከውን ፡ ቡሩከ ፡ ስሙ ፡ ለዓለም ፡
እምቅድመ ፡ ፀሐይ ፡ ሀሎ ፡ ስሙ ፤
ወይትባረኩ ፡ ቦቱ ፡ ኵሎሙ ፡ አሕዛበ ፡ ምድር
መዝሙረ ዳዊት 71÷17-18
✨✨✨በስመአብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ አሐዱ አምላክ አሜን።
👉ታላቅ መንፈሳዊ ጉዞ ወደ ደብረ ከርቤ ዳግማዊ ጎለጎታ ደብረ ማዕዶት ቅድስት አርሴማ አንድነት ገዳም።
👉ከአዲስ አበባ 150 ኪ.ሜ ርቀት ላይ የሚገኝ ቅዱስ ቦታ ነው።
ቀን:21/05/2016
መነሻ ሰአት: 12:00
የጉዞ ሁኔታ:ደርሶ መልስ
የጉዞ ዋጋ: 500 (ሙሉ መስተንግዶን ጨምሮ)
መነሻ ቦታ: ፒያሳ ገነተ ጽጌ ቅዱስ ጊዮርጊስ ቤተክርስቲያን - መገናኛ- ጣፎ
ለበለጠ መረጃ: 0989680703
0960029538
አዘጋጅ: መዓዛ ሃይማኖት በጎ አድራጎት ማኅበር
ማሳሰቢያ: ሁሉም ሰው መታወቂያ የመያዝ ግዴታ አለበት‼️
የበረከት ሥራ መሥራት የምትፈልጉ
ለተቸገሩ የገጠር አቢያተ ክርስቲያናት ለፍልሰታ ጾም ማስቀደሻ የሚሆን እጣን ፣ ዘቢብ ፣ ጧፍ ፣ ሻማ እንርዳ
+25160029538 እና +251935468111 ይደውሉ ወይም @wengelyohannes አነጋግሩን
ወይን ጠጅ እኮ የላቸዉም (ዮሐ.፪፡፫)
. . .
ዛሬ ያለንበት ዓለም ያላለቀበት ምን አለ? ዛሬ ያለንበት ዓለም ያልጎደለበት ምን አለ? ብዙ አልቆበታል፣ብዙ ጎድሎበታል፡፡ ዓለም ምን ጊዜም ቢሆን ሞልቶለት አያውቅም፣በአንድ በኩል ሲሞላ በሌላ በኩል የጎድላል፣ማለዳ ደስታ ቢሆን ማታ ሐዘን ነው ፣ዛሬ ቢሾሙ ነገ መሻር ነው፣ዛሬ ቢጠግቡ ነገ መራብ ነው፣ዛሬ ሌላውን መስቀል ላይ ቢያወጡ ነገ መስቀል ላይ መውጣት ነው፡፡ የዓለም ህልውና ፣ደስታና ሐዘን የሚፈራረቁበት እጅግ በጣም የተወሳሰበ ነው፡፡በዚህ ወንጌል የተጠቀሱት ሙሽሮች ሠርግ ላይ ‹‹ወሀለወት ህየ እሙ ለእግዚእ ኢየሱስ›› (የጌታችን የመድኃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ እናቱም ከዚያ ነበረች) ጌታችንም ከደቀ መዛሙርቱ ጋር በዚያ እንደ ነበሩ ወንጌሉ ነግሮናል፡፡ ስለሆነም የጎደለው ሞልቶላቸዋል፣ተአምራት ተሠርቶላቸው ውሃው ወይነ ቃና ሆኖላቸዋል፣ በሕይወታችን፣በፕሮግራማችን እግዚእብሔር አምላካችን እንዲኖርበት ፣እንዲገኝበት እናድርግ፡፡
በፕሮግራማችን፣በበዓላችን ላይ የእግዚአብሔር እንደራሴዎች፣የእግዚአብሔር ሰዎች ይኑሩበት፣ ይጠሩበት፣ይጋበዙበት፣ዋና ዂነው ይገለጡበት፣ይህ ከሆነ ይህን ካደረግን እመቤታችን በዚያ አለች፤፡ ጌታችን መድኃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ከደቀመዛሙርቱ ጋር በዚያ ነበሩ ማለት እንችላለን፡፡ ያን ጊዜ የጎደለው ይሞላልናል፣ያጣነውን እናገኛለን፣የተመኘነው ይፈጸምልናል፣ተአምራት ይደረግልናል፣ የምንጠጣው ውሃው ወይን ቃና ይሆንልናል፡፡
ዛሬ ያጣነው ወይም ያለቀብን የወይን ጠጅ አይደለም፣ከወይን ጠጅ ይልቅ እጅግ የሚጣፍጠው ፍቅር ነው፡፡ ከዓለማት ሁሉ የጎደለው፣ያለቀው የተሟጠጠው ፍቅር ነው፡፡ በዘንድሮው በዓለ ጥምቀትና ቃና ዘገሊላ ለዓለም ሁሉ እመቤታችን ቅድስት ድንግል ማርያም ፊት በማያስመልስ ፣አንገት በማያስቀልስ ልመናዋ ‹‹ወይንኬ አልቦሙ›› (ወይን ጠጅ እኮ የላቸዉም) ሳይሆን ‹‹ፍቅርኬ አልቦሙ›› ፍቅርኮ የላቸውም ብላ ትማጸንልን ዘንድ እንማጸናት፡፡በእውነት በሰው ሁሉ ዘንድ በዓለም ሁሉ መተማመን፣ታማኝነት፣መታዘዝ፣መከባበር ፣ርኅራኄ ጎድሏል፡፡ ጭካኔ፣ራስ ወዳድነት፣ቸልተኝነት፣ ጥላቻ ነግሷል፣ሞልቷል፡፡ ይህ ደግሞ የትም ሊያደርሰን አይችልም፡፡በሥጋም፣በነፍስም የሚያመጣው ውድቀትን፣ክስረትን፣ኲነኔን ነው፤ አሁን ካለው የበለጠ ድህነትንም የሚጋብዝ ይሆናል፡፡
ከመጠላላት ፣ከመለያየት፣በጎሪጥ ከመተያየት አልፎ የሰላም መታጣት፣ የጦርነት መቀስቀስ፣የሞት፣ የእልቂት፣የኅልፈት መንገሥ በእጅጉ ይበዛል፤ዛሬ በመላዉ ዓለማችን የሚታየው ይኸው ነው፡፡ ሰላም፣መረጋጋት፣ፍቅር ያጡት ድሆቹ አህጉር ብቻ አይደሉም፣እንዲያውም በበለጸጉት ዓለማት ይበልጥ ችግሩ፣ውጥረቱ፣ሽብሩ በእጅጉ ተባብሶ ይታያል፡፡ በአሁኑ ሰዓት የመላው ዓለም ህልውና ጥያቄ ውስጥ ነው ያለው፡፡ ሥጋቱ በየቀኑ እየጨመረ ከመሔድ በስተቀር ሲቀንስ አይታይም፤ድሆቹ አህጉር ቢሆኑም ደዌያት ሠልጥነውባቸዋል፤ ከደዌያቱ መብዛት የተነሣም ከረኀቡ ሌላ በየዕለቱም የሚሰማው የሞት መርዶ ኹኗል፡፡ ዓለም እንደዚህ ካለ የችግር አዘቅት ይወጣ ዘንድ የእመቤታችን ቅድስት ድንግል ማርያም ጸሎትና ልመና፤ምልጃ ያስፈልገዋል፡፡ እርስዋ እመቤታችን ቅድስት ድንግል ማርያም ከጸለየችልን፣ካሳሰበችልን ችግራችን ወዲያውኑ መፍትሔ ያገኛል፤ሞቱ ወደ ሕይወት፤ ድንጋጤው ወደ ደስታ ፤ ውሃው ወደ ወይንነት፤ ሽብሩ፣ረብሻው፣ ጫጫተው ወደ ሰላም ፣ ወደ መረጋጋት ይለወጣል፡፡ይህ ሁሉ እንዲሆንልን እርስዋን ቅድስት ማርያምን በሕይወታችን ልዩ ሥፍራ እንዲኖራት ማድረግ አለብን ፤ ‹‹ወሀለወት ህየ እሙ ለእግዚእ ኢየሱስ
ብፁዕ አቡነ መልከጼዴቅ ካልዕ በቃና ዘገሊላ አሥራ ስድስት ዓመት በፊት ያስተማሩት ትምህርት
በቃና ዘገሊላ ከብካብ ኮነ፣ ወሰማይኒ ረስዮ ወይነ፤»
(በገሊላ አውራጃ በቃና መንደር ሰርግ ሆነ፤ ውኃውንም ወደ ወይንነት ለወጠው።) ዮሐ ፪፥፩-፲፩
ጌታችን መድኃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ በገሊላ አውራጃ በዳዊት ከተማ በቤተልሔም ምድረ ኤፍራታ ተወልዶ በሠላሣ ዘመኑ በሠላሣ ዓመተ ምሕረት በፈለገ ዮርዳኖስ በእደ ዮሐንስ ተጠምቆ ሳይውል ሳያድር ወደ ገዳመ ቆሮንቶስ ገብቶ አርባ መዓልት አርባ ሌሊት ጾመ ጸለየ፤ በጠላት ዲያብሎስ ተፈተነ። ፈተናውን ድል አድርጎ ሱባኤውን ፈጽሞ በወጣ በሦስተኛው ቀን ከእናቱ ከቅድስተ ቅዱሳን ድንግል ማርያም እና ከቅዱሳን ሐዋርያቱ ጋር በመሆን በገሊላ አውራጃ በቃና መንደር በሰርግ ቤት ተገኝቶ ቤተ ከብካቡን በትምህርቱ በተአምራቱ ባረከ።
ኢየሱስ ክርስቶስ ይኽን ድንቅ ተአምር በቃና ዘገሊላ ያደረገው በገዳመ ቆሮንቶስ ሱባኤውን ፈጽሞ በወጣ በሦስተኛው ቀን የካቲት ፳፫ ቀን ነው። ይሁንና አባቶቻችን ሊቃውንት «የውኃ በዓል ከውኃ በዓል ጋር መቀናጀት አለበት» በማለት በጥምቀት በዓል ማግስት ጥር ፲፪ ቀን እንዲከበር አድርገውታል። እኛም ይኽንኑ ቀን ጠብቀን በዓሉን በማክበር ላይ እንገኛለን።
በቃና ዘገሊላ የተደረገው ይኽ ተአምር በዮሐንስ ወንጌል በምእራፍ ፪ ከቁጥር ፩-፲፩ ድረስ ተጽፎ ይገኛል። በዓሉ ቃና ዘገሊላ የሚል ስያሜ ያገኘውና በዚህ ስም ሊጠራ የቻለው አምላካችን፣ ጌታችንና መድኃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ የገሊላ ሀገር ክፍል በምትሆን ቃና በተባለችው ቦታ በፈጸመው ተአምር ምክንያት መነሻነት ነው። ከቅዱስ መጽሐፍ ላይ ተጽፎ የሚገኘው ሙሉ ቃል እንዲህ ይላል፦
«በሦስተኛውም ቀን በገሊላ ቃና ሰርግ ነበረ፥ የኢየሱስም እናት በዚያ ነበረች፤ ኢየሱስም ደግሞ ደቀ መዛሙርቱም ወደ ሰርጉ ታደሙ። የወይን ጠጅም ባለቀ ጊዜ የኢየሱስ እናት። የወይን ጠጅ እኮ የላቸውም አለችው። ኢየሱስም። አንቺ ሴት፥ ከአንቺ ጋር ምን አለኝ? ጊዜዬ ገና አልደረሰም አላት። እናቱም ለአገልጋዮቹ። የሚላችሁን ሁሉ አድርጉ አለቻቸው። አይሁድም እንደሚያደርጉት የማንጻት ልማድ ስድስት የድንጋይ ጋኖች በዚያ ተቀምጠው ነበር፥ እያንዳንዳቸውም ሁለት ወይም ሦስት እንስራ ይይዙ ነበር። ኢየሱስም። ጋኖቹን ውኃ ሙሉአቸው አላቸው። እስከ አፋቸውም ሙሉአቸው አላቸው። እስከ አፋቸውም ሞሉአቸው። አሁን ቀድታችሁ ለአሳዳሪው ስጡት አላቸው፤ ሰጡትም። አሳዳሪውም የወይን ጠጅ የሆነውን ውሃ በቀመሰ ጊዜ ከወዴት እንደ መጣ አላወቀም፤ ውኃውን የቀዱት አገልጋዮች ግን ያውቁ ነበር፤ አሳዳሪው ሙሽራውን ጠርቶ። ሰው ሁሉ አስቀድሞ መልካሙን የወይን ጠጅ ያቀርባል፥ ከሰከሩም በኋላ መናኛውን፤ አንተስ መልካሙን የወይን ጠጅ እስከ አሁን አቆይተሃል አለው። ኢየሱስ ይህን የምልክቶች መጀመሪያ በገሊላ ቃና አደረገ፤ ክብሩንም ገለጠ፥ ደቀ መዛሙርቱም በእርሱ አመኑ።»
በቃና ዘገሊላ የተፈጸመው ይኽ ሰርግ ሙሽራ የሆነውን ኢየሱስ ክርስቶስን እንድናስብና እንድናስታውስ ያደርገናል። ሚዜው የሙሽራው አገልጋይ ነውና መጥምቁ ዮሐንስ ሙሽራ በሆነው በኢየሱስ ክርስቶስ መደሰቱንና ሊያገለግለው የተዘጋጀ መሆኑን ሲያስረዳ ፦ «ሙሽራይቱ ያለችው እርሱ ሙሽራ ነው፤ ቆሞ የሚሰማው ሚዜው ግን በሙሽራው ድምጽ እጅግ ደስ ይለዋል። እንግዲህ ይህ ደስታዬ ተፈጸመ። እርሱ ሊልቅ እኔ ግን ላንስ ያስፈልጋል።» ዮሐ ፫፥፳፱-፴ ይለናል። በቃና ዘገሊላ በሰርጉ ቤት ተገኝቶ ተአምሩን የጀመረው ኢየሱስ ክርስቶስ ከእናቱ እና ከሐዋርያት ጋር አብሮ ነበርና አማላጅ እና ተማላጅ ማን እንደሆነ በልዩ ምሥጢር ተስተውሎበታል። ወንጌላዊው ቅዱስ ሉቃስ በተከታታይ ልዩ የሆነውን ብሥራት ሲያሰማ እንዲህ በማለት ጽፎልናል፦ በስድስተኛው ወር ማለትም መልአኩ ገብርኤል ካህኑ ዘካርያስን
«ጸሎትህ ተሰምቶልሃልና አትፍራ ሚስትህ ኤልሳቤጥም ወንድ ልጅ ትወልድልሃለች፥ ስሙንም ዮሐንስ ትለዋለህ። ደስታና ተድላም ይሆንልሃል፥ በመወለዱም ብዙዎች ደስ ይላቸዋል።» ካለው በኋላ ለእመቤታችን ለቅድስት ድንግል ማርያም በክብር ተገልጦ «ደስ ይበልሽ፥ ጸጋ የሞላብሽ ሆይ፥ ጌታ ከአንቺ ጋር ነው፤ አንቺ ከሴቶች መካከል የተባረክሽ ነሽ።» ብሏታል።
እመቤታችን ቅድስት ድንግል ማርያምም በአብሣሪው መልአክ በቅዱስ ገብርኤል እንደተነገራት በእውነት ጸጋን የተሞላች ናትና በሰርግ ቤት የጎደለውን የጓዳውን ምሥጢር ተረድታ የሠርጉ ሥነ-ሥርዓት በሠመረና በተዋጣለት ሁኔታ እየተከናወነ ድንገት የወይን ጠጅ በማለቁ ተጨንቀውና ግራ ተጋብተው አስተናባሪዎቹ በታወኩበት ሰዓት የጭንቅ አማላጅ ናትና ወደ ልጅዋ ወደ ወዳጅዋ ወደ ኢየሱስ ክርስቶስ ዘወር ብላ «ወይን እኮ የላቸውም» በማለት አሳስባ ባዶ የሆኑት የድንጋይ ጋኖች ውኃ ተሞልተው ጣፋጭ ወይን ጠጅ ተገኝቶባቸዋል።
ሐዋርያው ቅዱስ ጳውሎስ በመልእክቱ «እግዚአብሔርንም የመምሰል ምሥጢር ያለ ጥርጥር ታላቅ ነው፤ በሥጋ የተገለጠ፥ በመንፈስ የጸደቀ፥ ለመላእክት የታየ፥ በአሕዛብ የተሰበከ፥ በዓለም የታመነ፥ በክብር ያረገ። ፩ጢሞ ፫፥፲፮ በማለት እንደጻፈልን ከድንቅ በላይ ድንቅ በሆነ ተዋሕዶ በሥጋ መገለጡ ከእመቤታችን ተወልዶ ነውና በልደቱ ጊዜ አብራ እንደነበረችው እንዲሁ ደግሞ በሞቱ ጊዜ ከእርሱ እንዳልተለየች እንረዳለን።
ይኽንንም ወንጌላዊው ዮሐንስ «ነገር ግን በኢየሱስ መስቀል አጠገብ እናቱ፥ የእናቱም እኅት፥ የቀለዮጳም ሚስት ማርያም፥ መግደላዊትም ማርያም ቆመው ነበር።» ዮሐ ፲፱፥፳፭ በማለት በጻፈልን መልእክት ለማወቅ ችለናል።
በመጀመርያ በልደቱ በኋላም በሞቱ ጊዜ አብራው የነበረች ቅድስት ድንግል ማርያም ዘመኗን በሙሉ በፍጹም እንዳልተለየችው ተአምሩን በጀመረበት በቃና ዘገሊላም አብራው ነበረችና ዛሬ ትውልዱ ሁሉ የሚኮራበትን የአማላጅነት ሥራ በቃና ዘገሊላ ፈጽማለች።
«አንቺ ሴት ከአንቺ ጋር ምን አለኝ» በሚለው ቃል ብዙዎች ተሰናክለውበት ቢገኙም ሊቃውንተ ቤተ ክርስቲያን አምልተውና አስፍተው ምሥጢራትን የነገሯቸው የተዋሕዶ ልጆች ግን በእናትና በልጅ መካከል ያለውን የንግግር ዘይቤ ተረድተው እውነቱን ሲመሰክሩ ይኖራሉ። እመቤታችን ቅድስት ድንግል ማርያም በእግዚአብሔር ፊት የሚቆመው ከእግዚአብሔር ተልኮ የመጣውን አብሳሪ መልአክ «እንደ ቃልህ ይደረግልኝ» እንዳለችው ኢየሱስ ክርስቶስም እመቤታችንን «ከአንቺ ጋር ምን አለኝ» (እንደ ቃልሽ ይሁን) በማለት ጥያቄዋን መልሷል፤ ምልጃዋን ተቀብሏል።
«ጊዚዬ አልደረሰም» በማለት ቢናገርም ስለ እናቱ ስለ ቅድስት ድንግል ማርያም ሲል የእናቱን ልመና ተቀብሎ ተአምራቱን ፈጽሟል። እናታችን ቅድስት ድንግል ማርያም ሳይነግሯት በልባቸው ያለውን የምታውቅ እናት ናትና የሰርጉ አስተናባሪዎችን ኃዘን ተመልክታ ከልጇ ከወዳጇ አማልዳ የጎደላቸውን እንደሞላች ለእኛም ትውልድ ሁሉ ብፅዕት ይሉኛል ብላ በተፈጸመላት ቃል ጎዶሏችንን ትሙላልን። የሰዎችን ጭንቅ አውቃ ሳይነግሯት ያማለደች እናት ስሟን ጠርተው ለሚለምኗትማ የበለጠ ታደርጋለችና ሁላችንንም በተሰጣት ጸጋ ታማልደን።
ከእናታችን ከቅድስት ድንግል ማርያም ረድኤቷን በረከቷን ያሳድርብን አሜን!!
ባለማዕተቦችን ወደዚህ ቻናል ይጋብዙ
✞ በወንጌሉ_ያመናችሁ ✞
በወንጌሉ ያመናችሁ/2/
እንኳን ለብርሃነ ጥምቀቱ አደረሳችሁ/2/
የጠፋዉ ስማችን ከ ክብራችን ጋራ
ይኸዉ ተመለሰ ባምላካችን ስራ
ባርነት ፈታልን ልጆቹ ልንባል
የድንግል ማርያም ልጅ በ ዩርዳኖስ ቆሞል
/አዝ * * * * *
ጨለማዉ ተገፎ ሠይጣን ተሸንፎ
በጌታ መገለጥ ዓለም ሁሉ አርፎ
ሲጠመቅ በ ዉሀ በእደ ዩሀንስ
የእዳችን ታየ ሲደመሰስ
/አዝ * * * * *
ከክብሩ የተነሳ ተራሮች ዘለሉ
ደመና ጥላ ቆጥሮ ሲታዘዙ ዋሉ
የሚወደዉ ልጄ ደስም ሚለኝ በርሱ
የሚል ድምፅም ሰማን ሲናገር ቅዱሱ
/አዝ * * * * *
ይፈር ዛሬ እንግዲ ተዋርዳል ጠላት
ክሳችን ላይ ቆማል ያለም መዳኒት
እረቂቁ በዝቶ ሲመጣ ወደ ምድር
ሸክማችን ተጣለ የተጫነን ቀንበር
@meazahaymanot
@meazahaymanot
በስመ አብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ አሐዱ አምላክ አሜን!
🕯 #ቅድስት_ሥላሴ (ጥር 7)
ሥላሴ የሚለው ቃል ‹‹ሠለሰ›› ሦስት አደረገ ከሚለው የግእዝ ግሥ የተገኘ ነው፡፡ ይህም በምሥጢረ ሥላሴ ስለ ነገረ ሃይማኖት የሚያስረዳ ሲሆን አንድም ሦስትም ተብሎ ይተረጎማል፡፡ ስለዚህ እግዚአብሔርን አንድም ሦስትም ብለን ማመናችንን የምንገልፅበት የሃይማኖት ዶግማ ነው፡፡ የሥላሴ አንድነታቸው በመለኮት፣ በፈቃድ፣ በስልጣን፤ (ኢሳ 66፥1) ሲሆን በስም፣ በአካል፣ በግብር ሦስት ቢባሉም አንድ አምላክ እንጂ ሦስት አማልክት አይባሉም፤ (2ቆሮ 13፥14 ፣ ኤፌ 4፥5)።
በመጽሐፍ ቅዱስ እንደተመዘገበው ከጥፋት ውኃ በኋላ የኖኅ ልጆች ወልደው ተዋልደው ብዙዎች ሆኑ፤ (ዘፍ 9፥1 ፣ ዘፍ 10፥1)፡፡ በባቢሎን የነበሩት በሰናዖር ሰፊ ሜዳ አግኝተው ‹‹በምድር ላይ ሳንበተን ስም ማስጠሪያ ግንብ እንገንባ›› ብለው መክረው ታላቅ ግንብ ገነቡ፡፡ የኩሽ ልጅ ናምሩድ በምድር ላይ ኃያል መሆንን በጀመረ ጊዜ ግዛቱም በሰናዖር ባቢሎን ነበር፡፡ በናምሩድ ኃያልነት እና መሪነት ከዚያ ሆነው ጦር እየሰበቁ ይወረውሩ ጀመር፤ ሰይጣንም ከደመና በምትሀት ደም እየቀባ ይልክላቸዋል፤ እነርሱም ደሙን እያዩ ‹‹አሁን አብን ወጋነው፣ አሁን ወልድን ወጋነው፣ አሁን መንፈስ ቅዱስን ወጋነው›› ይሉ ጀመር፡፡ በሕዝቡ ላይ ዲያብሎስ ስለ ሰለጠነባቸው እና ለሌሎች ከሀድያን ትምህርት ይሆን ዘንድ ‹‹ንዑ ንረድ ወንክዐው ነገሮሙ›› በማለት እግዚአብሔር ቋንቋቸውን ለያየባቸው፤ እነርሱም የማይግባቡ የማይደማመጡ ሆነው በምድር ላይ ሁሉ ተበታትነዋል፡፡ከተማይቱም ስምዋ ባቢሎን ተባለ፡፡ ባለማስተዋል የሠሩትንም ሕንፃ ዓመጻ ነፋስ ጠራርጎ አጥፍቶታል፡፡ ይህን ያደረጉበት የቅድስት ሥላሴ በዓል ጥር 7 ቀን ይከበራል፡፡
ይህም ቅድስት ሥላሴ በኃጢአት የተገነባውን የሰናዖር ግንብ ያፈረሱበት አንድነታቸውንና ሦስትነታቸውን በግልጽ ያሳዩበት ቀን ነው፤ (ዘፍ 11÷1-9)፡፡ እግዚአብሔርም አለ ‹‹ኑ እንውረድ፤ አንዱ የአንዱን ነገር እንዳይሰማው ቋንቋቸውን በዚያ እንደባልቀው››)፡፡ ‹‹እግዚአብሔርም አለ›› አንድነታቸውን ሲያጠይቅ ‹‹ኑ እንውረድ›› ሦስትነታቸውን ያጠይቃል፡፡ ከበዓሉ በረከት ያሳትፈን አሜን!
ወስብሐት ለእግዚአብሔር!
ምንጭ፦ መጽሐፍ ቅዱስ
━━━━━✦📖 ❖ 📖✦━━━━━
🔵 telegram channel:
➺ /channel/meazahaymanot
⚪️ facebook page: fb.me/meazhaimanot
🔵 YouTube Channel: መዓዛ ሃይማኖት : https//YouTube.com/meazahaymanot
ኵሉ ዘገብራ ለጽድቅ ጻድቅ ውእቱ ወዘያከብር ሰንበተ። ኢይበል ፈላሲ ዘገብአ ኀበ እግዚአብሔር ይፈልጠኒኑ እምሕዝቡ።(ኵሉ ዘገብራ ለጽድቅ፣ ጻድቅ ውእቱ ወዘያከብር ሰንበተ።
@meazahaymanot
*© ኢየሱስ ሖረ*
ኢየሱስ ሖረ ሀገረ እሴይ/፪/
ዮሐንስ አጥመቆ በማይ /፪/
ትርጉም፡- ኢየሱስ ወደ እሴይ ሀገረ ሄዶ
ዮሐንስም በውኃ አጠመቀው።