meazahaymanot | Unsorted

Telegram-канал meazahaymanot - መዓዛ ሃይማኖት በጎ አድራጎትና ጉዞ ማህበር

4288

"ውድስት አንቲ በአፈ ነቢያት ወስብሕት በሐዋርያት አክሊለ በረከቱ ለያዕቆብ ወትምክህተ ቤቱ ለእስራኤል፡፡" "በነቢያት በሐዋርያት አንደበት የተመሰገንሽ የያዕቆብ የበረከቱ ዘውድ የእስራኤል ወገን መመኪያ አንቺ ነሽ"                  መጽሐፈ ሰዓታት የፌስቡክ ፔጃችን www.fb.me/meazhaimanot ይቀላቀሉን

Subscribe to a channel

መዓዛ ሃይማኖት በጎ አድራጎትና ጉዞ ማህበር

✅ የቃልህ ፍቺ ያበራል፥ ሕፃናትንም አስተዋዮች ያደርጋል።”
— መዝሙር 118(119)፥130
🕎ስለ መጽሐፍ ቅዱስ ምንነት እንዲሁም በመጽሐፍ ቅዱስ ላሉት ምንባባት አንድምታቸው ትንታኔና ማብራርያ የሚያገኙበት ቻናል ይቀላቀሉ።

👉“መጽሐፍ” ለሚለው ምንጭ በግሪክ ቋንቋ ቢብሎስ (byblos) ከደንገል በተሠራ ወረቀት ወይም በብራና ከተጻፈ በኋላ በሁለት በትሮች...read more

👉መጽሐፍ ቅዱስ መቼ በአንድ ጥራዝ ተጠቀለለ? ከክ.ል.በ ይሁን በኋላ የተጻፉት ሁሉንም መጻሕፍቶች ለየብቻቸው ነበሩ፡፡ከ500ዎቹ ዓ.ዓ....read more

👉ኦሪት "ኦራይታ" ከሚል የሶርያ(አራማይክ) ቃል የተገኘ ሲሆን ትርጓሜውም "ሕግ" ወይም "ትምህርት" ማለት ነው።የመጠሪያ ምንጩም....read more



ወቅታዊ የቤተ ክርስቲያናችንን ጉዳይ እና መንፈሳዊ ጥንካሬያችንን እንድናበረታ የሚያግዙን መንፈሳዊ ቻናሎችን ይዘን ቀርበናል።እርስዎም ከእነዚህ መንፈሳዊ ቻናሎች የነፍስ ምግብ የሆነውን የእግዚአብሔርን ቃል እየተመገቡ መንፈሳዊ ሕይወትዎትን እንዲያጠናክሩ በእግዚአብሔር ስም ጥሪያችንን እናቀርባለን🙏
🙏ፈጣሪ ይባርከን🙏

ከነዚህ መፀሀፍት የተወጣጡበት
ትምህርትን መማር ይፈልጋሉ❔
እነሆ ብለናል :-
📚የባሕታውያን አባቶች ሕይወትና የመዝሙራት ተመስጦ
📖▓⇨ትምህርት በአባ ሺኖዳ ⇨ክፈት
📚የድያቢሎስ ውግያዎች
📖▓⇨ትምህርት ⇨ክፈት
📚አምደ ሀይማኖት
📖▓⇨በአባታችን ቅዱስ ሺኖዳ ⇨ክፈት
📚መንፈሳዊ ሕይወት
📖▓⇨በአቡነ ሺኖዳ ⇨ክፈት
📚መንፈሳዊ ሰው
📖▓⇨በአቡነ ሺኖዳ ⇨ክፈት
📚የአባቶች ሕይወት ንሮ እና ተመስጦ
📖▓⇨በአቡነ ሺኖዳ ⇨ክፈት
የመኖኮሳት ታሪክ እና ተመስጦ በብጽእ አቡነ ሺኖዳ ሳልሳዊ ይቀርብበታል።

Читать полностью…

መዓዛ ሃይማኖት በጎ አድራጎትና ጉዞ ማህበር

ስንክሳር ዘወርሃ ሐምሌ ስምንት-ክፍል አንድ(፰) /channel/meazahaymanot

Читать полностью…

መዓዛ ሃይማኖት በጎ አድራጎትና ጉዞ ማህበር

ደቀ መዛሙርቱም ራሱን ከአንገቱ ጋር ቢያደርጉት እንደ ቀድሞው ደኅና ኾኖላቸው በክብር ገንዘው ቀብረውታል፡፡ ሰያፊው ቅዱስ ጳውሎስን እንደ ገደለው ለመናገር ወደ ንጉሡ ሲመለስም ያቺ መጐናጸፊያዋን የሰጠችው ብላቴና ‹‹ጳውሎስ ወዴት አለ?›› አለችው፡፡ እርሱም ‹‹ራሱን ተቈርጦ በመጐናጸፊያሽ ተሸፍኖ ወድቋል›› ሲላት ‹‹ዋሽተሃል፤ እነሆ ጴጥሮስና ጳውሎስ በእኔ በኩል አልፈው ሔዱ፡፡ እነርሱም የመንግሥት ልብስ ለብሰዋል፡፡ በራሳቸውም በዕንቍ ያጌጡ አክሊላትን አድርገዋል፡፡ መጐናጸፊያዬንም ሰጡኝ፡፡ ይህችውም እነኋት፤ ተመልከታት›› ብላ ሰጠቸው፡፡ ከእርሱ ጋር ለነበሩትም አሳየቻቸው፡፡ አይተውም አደነቁ፤ ስለዚህም በጌታችን በኢየሱስ ክርስቶስ አመኑ፡፡

ቅዱሳን ጴጥሮስ እና ጳውሎስ በስብከተ ወንጌል አገልግሎታቸው ጨለማውን ዓለም በማድመቃቸው ‹ብርሃናተ ዓለም› ተብለው ይጠራሉ፡፡ የቅዱሳኑ አገልግሎት፣ ገድላቸው እና ተአምራቸው በመጽሐፈ ስንክሳር፣ በዜና ሐዋርያት እና በገድለ ሐዋርያት በሰፊው ተጽፎ ይገኛል፡፡ እኛም በዓለ ዕረፍታቸውን ለማስታወስ ያህል ታሪካቸውን በአጭሩ አቀረብን፡፡

ቅዱሳን ሐዋርያት ያቆዩልንን የቤተ ክርስቲያን አስተምህሮ ጠብቀን፣ በክርስቲያናዊ ምግባር ጸንተን እንድንኖር፤ በመጨረሻም የእግዚአብሔርን መንግሥት ለመውረስ እንድንበቃ የቅዱሳኑ ጸሎት ይርዳን፡፡

ወስብሐት ለእግዚአብሔር፡፡

በዲያቆን ኤፍሬም የኔሰው 

ምንጭ፡-

መጽሐፈ ስንክሳር፣ ሐምሌ ፭ ቀን፤

ዜና ሐዋርያት፤


https://m.youtube.com/channel/UCKGh-U7U7pnvFUIEGXPOnNw,

Читать полностью…

መዓዛ ሃይማኖት በጎ አድራጎትና ጉዞ ማህበር

ዝክረ ቅዱሳን መርሐግብር

ዝክረ ቅዱስ ጴጥሮስ ወጳውሎስ

Читать полностью…

መዓዛ ሃይማኖት በጎ አድራጎትና ጉዞ ማህበር

ስንክሳር ዘወርሃ ሐምሌ አምስት-ክፍል ሁለት
@meazahaymanot

Читать полностью…

መዓዛ ሃይማኖት በጎ አድራጎትና ጉዞ ማህበር

መዝሙር

ለሊቀ ጳጳሳት ቅዱስ ቄርሎስ
እስኪ በአንደበቴ ሰላምታ ላድርስ

በዘማሪት ሳምራዊት አበበ

@meazahaymanot

Читать полностью…

መዓዛ ሃይማኖት በጎ አድራጎትና ጉዞ ማህበር

ዝክረ ቅዱሳን

ዝክረ አቡነ ቄርሎስ

Читать полностью…

መዓዛ ሃይማኖት በጎ አድራጎትና ጉዞ ማህበር

እርስታችን ነሽ ❤️🌿

እርስታችን ነሽ እንወርስሻለን
ከምድርሽ ወይንን እንለቅማልን
ይትረፈረፋል ፅዋችን ሞልቶ
አንቺን ይዘናል አናፍርም ከቶ

የእንጀራ ምድር የፍቅር ሃገር
የለንም ወገን ካንች በስተቀር
በአክአብ መሬት የማንቀይርሽ
ደጅሽ ቆመናል ባርኪን በእጆችሽ
ዳዊት አባትሽ እንዳለው ብረሳሽ
ቀኜ ትርሳኝ በልቤ ላይ ነገሰሻል
ምልጃሽ እየጠበቀኝ

#አዝ ======

ወደ ምድራችን መርቶን ስንገባ
አንቺን አገኘን ታላቁዋን መባ
የሕይወት ውሃ ፈልቁዋል ከሆድሽ
እንዳንጠማ ዳግም ልጆችሽ
ዳዊት አባትሽ እንዳለው ብረሳሽ
ቀኜ ትርሳኝ በልቤ ላይ ነገሰሻል
ምልጃሽ እየጠበቀኝ

#አዝ ======

ነዶው በዛልን የስንዴ ዛላ
ወይኑን ብንጨምቀው ፅዋችን ሞላ
መሆንሽ አውቀን የበረከት ምድር
አንጠፋም ድንግል ከመቅደስሽ ሥር
ዳዊት አባትሽ እንዳለው ብረሳሽ
ቀኜ ትርሳኝ በልቤ ላይ ነገሰሻል
ምልጃሽ እየጠበቀኝ

#አዝ ======

አሁን በደስታ ስፍራ ይዘናል
መስቀል ላይ ሆኖ ጌታ ሰጥቶናል
ከዚህች ርስት የሚነቅለን የለም
አትሞበታል የደሙን ማህተም
ዳዊት አባትሽ እንዳለው ብረሳሽ
ቀኜ ትርሳኝ በልቤ ላይ ነገሰሻል
ምልጃሽ እየጠበቀኝ

Читать полностью…

መዓዛ ሃይማኖት በጎ አድራጎትና ጉዞ ማህበር

ጌታ ሆይ ተመልከተን

ጵጵስና እንደ ቅጥር ሥራ

Читать полностью…

መዓዛ ሃይማኖት በጎ አድራጎትና ጉዞ ማህበር

ምክረ አበው ዘቅዱስ ማር ይስሐቅ

"አዋቂ ነኝ አትበል፡፡ አዋቂ ነኝ በማለት ሰይጣን በትዕቢት እንዳይዝህ፡፡ በምትናገረው ነገር ገራገር  ሁን፡፡ ሸካራ ነገር ተናግረህ ተዋርዶ እንዳያገኝህ የለዘበ የለዘበ ነገር ተናገር፡፡ ለሁሉ ወዳጅ ትሆናለህ፤ አዋቂ ነኝ፣ ጻድቅ ነኝ አትበል፡፡ አዋቂ ጻድቅ ሳትሆን ቀርተህ እንዳታፍር ፡፡"

መልካም ቀን
 

Читать полностью…

መዓዛ ሃይማኖት በጎ አድራጎትና ጉዞ ማህበር

ስንክሳር ዘወርሃ ሰኔ ሠላሳ(፴)
/channel/meazahaymanot

Читать полностью…

መዓዛ ሃይማኖት በጎ አድራጎትና ጉዞ ማህበር

የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተክርስቲያን ሥርዓት፣ ትውፊት እና አስተምህሮ  የጠበቁ ትምህርቶች እና መዝሙሮች እንዲሁም ወረቦችን እንዲሁም መንፈሳዊ ቦታዎችን መጎብኘት   የምትፈልጉ join በማለት ይቀላቀሉን ማኅበሩ ለሚያከናውናቸው አገልግሎቶች አጋዥ እንድትሆኑ በአክብሮት እንጋብዛለን።

/channel/meazahaymanot

Читать полностью…

መዓዛ ሃይማኖት በጎ አድራጎትና ጉዞ ማህበር

ስንክሳር ዘወርሃ ሰኔ ሃያ ዘጠኝ(፳፱)
/channel/meazahaymanot

Читать полностью…

መዓዛ ሃይማኖት በጎ አድራጎትና ጉዞ ማህበር

አንድ አምላክ በሚሆን በአብ በወልድ በመንፈስ ቅዱስ ስም አሜን
ሰኔ 28 ስመ እግዚአብሔር ከተጠራባቸው በፍርሀት ይታዘዙ የነበሩት ዳግመኛም ለነቢዩ ዕዝራ ታቦተ ጽዮን ባዘነች ሴት አምሳል እንደታየችው እንዲሁ ለአባታችንም አንዲት ያዘነች ሴት በራእይ መጥታ ዕጣን በማይታጠንበትና መሥዋዕተ ቍርባን በሌለበት ቦታ እንደ ሽኮኮ በጉድጓድ ውስጥ እንዳስቀመጧት የነገረቻቸው አቡነ ክፍለ ሥላሴ ዘዛውል ወዘባንብቆ ዕረፍታቸው ነው።

ኣቡነ ክፍለ ሥላሴ ከአባታቸው ከተክለ ማርያም ወልደ ዘኪዎስ እና ከእናታቸው ከርግበ ዳዊት ዛውል በሚባለው ቦታ ተወለዱ። በመጀመሪያ የወጣላቸው ስም ‹‹መሓርየ እግዚ» የሚባል ነው። አእምሮአቸው ንጹሕና ብሩሕ የሆኑት አቡነ ክፍለ ሥላሴ በልጅነታቸውም በጎችንና ፍየሎችን እያገዱ (እየጠበቁ) ወላጆቻቸውን ያገለግሉ ነበር።

አቡነ ክፍለ ሥላሴ በእናታቸው ማሕፀን ሳሉ የተመረጡ ስለነበሩ እግዚአብሔርን በመፍራት ይታወቁ ነበር፡ ስመ ሥላሴን በከንቱ አያነሡም ነበር። ስመ እግዚአብሔርም ከተጠራባቸው በፍርሃት ይታዘዛሉ። እረኞችም ከብቶቻቸውን እንዲመልሱላቸው የእግዚአብሔርን ስም ከጠሩባቸው ይታዘዟቸው ነበር። በዚኸም ነገር አቡነ ክፍለ ሥላሴ ታላቁን ጻድቅ አቡነ ዐቢየ እግዚእን መሰሉ። በትግራይና በጎንደር በእጅጉ የሚታወቀው ታላቁ ጻድቅ አቡነ ዐቢየ እግዚእ ገና ከልጅነቱ ጀምሮ የእግዚአብሔርን ስም ከጠሩበት ምንም ነገር ከማድረግ ወደኋላ አይልም ነበር። ከልጆችም ጋር ሲጫወቱ ልጆቹ ስለ እግዚአብሔር ብለህ ይህን አድርግልን " ሲሉት ያደርግላቸዋል። በእረኝነት ሳሉ ምሳውንም ሆነ እራቱን ለምስኪኖች ይሰጣል። ለእግዚአብሔር ስም እጅግ ቀናተኛ ስለነበረ ስሙን በመፍራት ስመ እግዚአብሔርን ጠርተው ‹‹ይህን ክፉ ነገር በራስህ ላይ. አድርግ›› ባሉት ጊዜ እንኳን በራሱ ላይ አንዳች ክፉ ነገር ወይም አደጋ ለማድረስ ወደኋላ አይልም ነበር። ይህንንም ሊፈትኑት ብለው አንድ ቀን ስለታም ጦር አምጥተው ስለ እግዚአብሔር ብለህ እስቲ ራስህን በዚህ ስለታም ጦር ትወጋ ዘንድ ና› ባሉት ጊዜ አብርሃም ልጁን ይስሐቅን ሊሠዋ በሕሊናው እንደወሰነ እርሱም በቁርጥ ሕሊና ሆኖ ራሱን በጦሩ ሊወጋ ሲል ዘለው ያዙት። በሌላም ጊዜ እንዲሁ ሊፈትኑት በጭነት ምክንያት ጀርባው የቆሰለ አህያ አምጥተው ዐቢየ እግዚእ ስለ እግዚአብሔር ብለህ የዚያችን አህያ ቁስሏን ላስ አሉት። እርሱም ያን ጊዜ ርኩስን ብስም ኃጢአት ይሆንብኛል፣ አይሆንም ካልኳቸው ደግሞ ስመ እግዚኣብሔርን ጠርተንበት እምቢ አለ ስለሚሉ የፈጣሪዬን ስም መዳፈር ይሆንብኛል ብሎ በልቡ አሰበና ያን ጊዜ ይስም ዘንድ ተመለሰ። ባልንጀሮቹም በቁርጥ ሕሊናው እንደወሰነ ባወቁ ጊዜ ሊያደርገውም ሲሔድ ተመልክተው ቶሎ ብለው ሮጠው ከኋላው ያዙት። እርሱም «እኔስ የፈጣሪዬን ስም እፈራለሁ ስሙን ተደፋፍሬ በምድር በሕይወት ከምኖር ሞት ይሻለኛል» አላቸው። አቡነ ክፍለ ሥላሴም እንዲሁ በፈሪሃ እግዚአብሔር ይታወቃሉ። ስመ ሥላሴን በከንቱ ፈጽመው ጠርተው አያውቁም፣ ስመ እግዚአብሔር ከተጠራባቸው ማንኛውንም ነገር ያደርጉ ነበር።

ከዚኸም በኋላ አቡነ ክፍለ ሥላሴ ወደ አቡነ ሳሙኤል ገዳም ደብረ ዓባይ ሔደው በሚያስደንቅ ትሕትና ለአባቶች እየታዘዙ መዝሙረ ዳዊትን ተማሩ፣ ቅዱሳት መጻሕፍትን አጠኑ። ከዚያም የአባቶችን ቡራኬ በመቀበል ወደ ደብረ ቢዘን በመሔድ የአቡነ ፊሊጶስንና የአቡነ ዮሐንስን ልጆች በማገልገል የቅዱሳኑን አሠረ ፍኖታቸውን ተከትለው በተጋድሎ ኖሩ። ሌሊትና ቀን በእያንዳንዱ ሥርዓተ ጸሎት ላይ አንድ አንድ ሺህ እየሰገዱ ይጸልዩ ስለነበር የእንቅልፍና የዕረፍት ጊዜ አልነበራቸውም። በእንደዚህም ዓይነት ተጋድሎ ከቆዩ በኋላ ከአቡነ ፊሊጶስ 6ኛ አበ ምኔት ከሆኑት ከአባ ገብረ ማርያም እጅ ምንኩስናን ተቀበሉ። ከመነኰሱም በኋላ መነኰሳቱ እህል እንዲፈጩ ሲያዟቸው አባታችን ክፍለ ሥላሴ በመታዘዝ ወደ እህል መፍጫው ቤት ገቡ፣ ነገር ግን አባታችን እህል መፍጨት አይችሉም ነበር። እርሳቸውም ወደ እግዚአብሔር ቢጸልዩ ሁሉም ሊፈጭ ተዘጋጅቶ የነበረው እሀል በተኣምራት ተፈጭቶ ተገኘ። መነኰሳቱ ግን ይህን አላወቁም ነበር።

አቡነ ክፍለ ሥላሴ ከዚኽ በኋላ ወደ ሀገረ ደምብያ ሔደው ከጳጳሱ እጅ ሥልጣነ ክህነትን ተቀበሉ። ከዚያም ሲመለሱ መረብ ወንዝ ሲደርሱ አብሯቸው የነበረውን የሥጋ ወንድማቸውን ‹‹ኦ ወንድሜ እነሆ በሥጋ የወለደን አባታችን ዛሬ ዐረፈ» በማለት የአባታቸውን መሞት በመንፈስ ቅዱስ ዐውቀው ነገሩት ወደ ሀገራቸውም ክገቡ በኋላ የሀገራቸው የውል ሰዎች ያላወቁ መስሏቸው የአባታቸውን መሞት ለኣቡነ ክፍለ ሥላሴ ነገሯቸው። አባታችንም አባቲ እንደሞተ አስቀድሜ ዐውቄያለሁ፤ እግዚአብሔር ወደ ገነት እንዲያስገባው በጸሎት አግዙኝ እንጂ አታልቅሱ›› አሏቸው። ሰዎቹም የተሰጣቸውን ጸጋ አድንቀው እግዚአብሔርን አመሰገኑ።

ጻድቁ ወደ ደብረ ቢዘን ተመልሰው ሔደው በክህነት እያገለገሉ ሳለ ወደ አቡነ እንድርያስ ሰፍኣ ደብረ ጽጌ ገዳም ለመሔድ እሰቡ፤ ነገር ግን ትልቅ ዋርካ ያለበትን ባምብቆ የተባለውን ተራራ በራእይ ከተመለከቱ በኋላ ወደዚያ እንዲሔዱ እምላካዊ መልእክት መጣላቸው። እርሳቸውም የመንፈስ ቅዱስን ፈቃድ በደስታ ተቀብለው ወደ ባምብቆ በመሔድ ቤተ ክርስቲያን አንጸው የቅድስት ስላሴን ታቦት አስገብተው በታላቅ ተጋድሎ መኖር ጀመሩ፤ በርካታ ደቀ መዛሙርትንም አፈሩ።

አቡነ ክፍለ ሥላሴ በባምብቆ ሳሉ ታቦተ ጽዮን ለነቢዩ ዕዝራ ባዘነች ሴት አምሳል እንደታየችው እንዲሁ ለአባታችንም አንዲት ያዘነች ሴት በራእይ መጥታ ዕጣን በማይታጠንበትና መሥዋዕተ ቍርባን በሌለበት ቦታ እንደ ሽኮኮ በጉድጓድ ውስጥ እንዳስቀመጧት ነገረቻቸው። በዚያም በበረሓ ውስጥ ደብቀው ያስቀመጧት ዮልዮስ የተባለ አንድ አመጸኛ መኰንን ቤተ ክርስቲያንን ሊያቃጥል በፈለገ ጊዜ ነው። አቡነ ክፍለ ሥላሴም ወደተነገራቸው ቦታ በመሔድ ካህናቱን በጉድጓድ ውስጥ ስላስቀመጡት ታቦት ሲጠይቋቸው እነርሱ ግን የደበቅነው ታቦት የለንም› አሏቸው። አባታችንም “ወንድሞቼ ሆይ! እውነቱን ተናገሩ›› በማለት በራእይ የተመለከቱትን ነገር ነገሯቸው። ካህናቱም ፈርተው አዎን አባታችን ይቅር በሉን፣ ዮልዮስን ፈርተን ታቦቱን ዋሻ ውስጥ ደብቀነዋል›› ብለው ቦታውን አሳዩአቸውና አውጥተው ወደ ቤተ ክርስቲያን መለሱት።

ከዚኽም በኋላ አቡነ ክፍለ ሥላሴ በገዳማቸው በጽኑ ተጋድሎ ላይ ሳሉ የጌታችን ጾም በደረሰ ጊዜ ልጆቻቸውን ጠሩና ሰባት ክንድ የሚሆን ጉድጓድ ቆፍራችሁ እኔ እዚያ ውስጥ ከገባሁ በኋላ ጉድጓዱን ሸፍኑት፣ ከላይ የዕንጨት ሰሌዳ አድርጋችሁ በድንጋይና በጠጠር አድርጋችሁ በመቃብር ምልክት ዝጉት” በማለት ነገሯቸው። ዳግመኛም ሰዎች የት ናቸው? ብለው ቢጠይቋችሁ የት እንዳለ አናውቅም, በሏቸው፤ አርባ ቀንና አርባ ሌሊት ሲሆን ግን ከፍታችሁ አረጋግጡ አሏቸው። አብርሃም የተባለው ደቀ መዝሙራቸውም ወደ ጉድጓዱ አብሯቸው በመግባት የአቡነ ክፍለ ሥላሴን እጆቻቸውንና እግሮቻቸውን በሰንሰለት ካሠራቸው በኋላ ወጣ፣ ጻድቁም እንዳዘዙት ጉድጓዱን ዘጉትና ሰው እንዳያውቀው አንድ ትልቅ መደብ ሠሩለት። ነገር ግን በማግሥቱ “ወዳጄ ክፍለ ሥላሴ ሆይ! ለምን እንደዚህ አደረግህ? አንተ ከዚህ ጉድጓድ ውስጥ ገብተህ ማነው ቅዱስ ሥጋውንና ክቡር ደሙን የሚያቀርብ? ማንስ ዕጣን ያጥናል? ስለዚህ አሁን ና ከዚህ ተነሥተህ ውጣ የሚል ራእይ ተመለከቱ፡ ወዲያውም የተዘጋው ጉድጓድ በተኣምር ተከፈተ ታስሮ የነበረው እጅና እግራቸውም ሰንሰለቱ በተኣምር ተፈታ። እርሳቸውም ወደ ቤተ

Читать полностью…

መዓዛ ሃይማኖት በጎ አድራጎትና ጉዞ ማህበር

ስንክሳር ዘወርሃ ሰኔ ሃያ ስምንት(፳፰)
/channel/meazahaymanot

Читать полностью…

መዓዛ ሃይማኖት በጎ አድራጎትና ጉዞ ማህበር

ስንክሳር ዘወርሃ ሐምሌ ስምንት-ክፍል ሁለት(፰) /channel/meazahaymanot

Читать полностью…

መዓዛ ሃይማኖት በጎ አድራጎትና ጉዞ ማህበር

#አጋዕዝተ_ዓለም_ቅድስት_ሥላሴ
ሐምሌ ሰባት በዚህች ቀን ሥሉስ ቅዱስ በአብርሃም ቤት የተገለጡበት ነው፡፡አብ ወልድ መንፈስ ቅዱስ በስም በአካል በግብር ሦስትነት በባሕርይ በሕልውናና በፈቃድ አንድነት የጸኑ ናቸው፡፡ በዚህ ጊዜ ተገኙ፣ በዚህ ጊዜ ያልፋሉ አይባሉም መጀመሪያም መጨረሻም እነርሱ ናቸውና፡፡ ርሕሩሐን ናቸውና በእናት ሥርዓት ‹‹ቅድስት ሥላሴ›› እንላቸዋለን፡፡ የሚጠላቸው (የማያምንባቸውን) አይጠሉም፡፡ የሚወዳቸውን ግን እጽፍ ድርብ ይወዱታል፣ በቤቱም መጥተው ያድራሉ፡፡ ከፍጥረታት ወገን ከእመቤታችን ቀጥሎ የአብርሃምን ያህል በሥላሴ ዘንድ የተወደደ ፍጡር የለም፡፡ አባታችን ቅዱስ አብርሃም የደግነት ሁሉ አባት ነውና በኬብሮን በመምሬ ዛፍ ሥር ሥላሴን ተቀብሎ አስተናግዷል፡፡አባታችን አብርሃም በዘጠና ዘጠኝ ዓመቱ እናታችን ሣራ በሰማንያ ዘጠኝ ዓመቷ ሥላሴን በድንኳናቸው አስተናገዱ፡፡አብርሃም እግራቸውን አጠበ፡፡ በጀርባውም አዘላቸው፡፡ምሳቸውንም አቀረበላቸው፡፡እነርሱም እንደሚበሉ ሆኑለት፡፡ በዚያው ዕለትም የይስሃቅን መወለድ አበሠሩት፡፡ አብርሃም ከደግነቱና እንግዳ ከመውደዱ የተነሣ በተመሳቀለ ጎዳና ላይ ድንኳን ሠርቶ የወጣ የመረደውን፣ የመጣ የሄደውን ሁሉ እየተቀበለ እግዚአብሔርን እያገለገለ የሚኖር ጻድቅ ነበር፡፡ ለዚህም ነው አብርሃም በወይራ ግራር (በመምሬ) ዛፍ ሥር ተቀምጦ ሳለ እግዚአብሔር አንድነቱን ሦስትነቱን የገለጠለት፡፡ዘፍ 18÷1-25፣ሮሜ 4÷3፡፡ ቀትር ሰዓት ላይ በድንኳኑ ደጅ ተቀምጦ እንግዳ ሲጠብቅ እግዚአብሔር ታየው ተነጋገረው፡፡ አንገቱን ቀና አድርጎ ዐይኑን አራምዶ በተመለከተ ጊዜ እነሆ ሦስት ሰዎች ከበላዩ ባለ ተራራ ላይ ቆመው አያቸው፣ ወደ እርሱም ሲወርዱ አይቶ ፈጥኖ ሄዶ ከሰግደላቸው በኋላ ‹‹አቤቱ በፊትህስ ሞገስ አግኝቼ እንደሆነ ባሪያህን አትለፈኝ ብዬ እለምናለሁ፤ ጥቂት ውኃ ይምጣላችሁ እግራችሁን ታጠቡ…›› እያለ በትሕትና በመጋበዝ ወደ ድንኳኑ አስገብቶ በሚገባ ጋበዛቸው፡፡ ‹‹በፊትህስ ሞገስ አግኝቼ›› ብሎ አንድነታቸውን፣ ‹‹ጥቂት ውኃ ይምጣላችሁ እግራችሁን ታጠቡ›› ብሎ የሦስትነታቸውን ምስጢር ገልጾአል፡፡ያች ሥላሴ የገቡባት የአብርሃም ድንኳን የእመቤታችን ምሳሌ ናት፡፡ ሥላሴ ወደ አብርሃም ድንኳን እንደገቡ ሁሉ በእመቤታችን በቅድስት ድንግል ማርያምም አብ ለአጽንዖ፣ መንፈስ ቅዱስ ለአንጽሖ፣ ወልድ በተለየ አካሉ ሥጋዋን ለመዋሐድ የማደራቸው ምሳሌ በመሆኑ አማናዊቷ የሥላሴ ማደሪያ የአብርሃም ድንኳን እመቤታችን ናት፡፡ሉቃ 1÷35 እግዚአብሔርም አብርሃምን የዛሬ ዓመት ልጅ እንደሚወልድ ነግሮት በዓመቱ ይስሐቅን ወልዷል፡፡ሁለቱ ሰዎች ከአብርሃም ድንኳን ወጥተው ወደ ሰዶም ወደ ገሞራ ሄዱ፣ አብርሃምም ይሸኛቸው ዘንድ አብሯቸው ሄደ፡፡ የሄዱትም ሁለቱ ሰዎች አብና መንፈስ ቅዱስ ናቸው፡፡ ነገር ግን አንዱ ወልድ በአብርሃም ቤት ቀርቷል ይኸውም ከቤተ አብርሃም ሰው እንደሚሆን ለማጠየቅ ነው፡፡አብርሃምም ተመልሶ በእግዚአብሔር ፊት ቆመ፡፡እግዚአብሔርም የሚሠራውን ሁሉ ከአብርሃም አይሠውርም ነበርና የሰዶምን የገሞራን ጥፋት ነገረው፡፡አብርሃምም ይቅር እንዲላቸው አብዝቶ ለመነላቸው፡፡
#ምስጋና_ይሁን_ለአብ_ለወልድ_ለመንፈስ_ቅዱስዛሬም ዘውትርም እስከ ዘለዓለም!የአብርሃሙ ሥላሴ ሥሉስ ቅዱስን በምግባር በሃይማኖት ሆነን እናገለግል ዘንድ የቅዱሳኑ ጸሎት ይርዳን!

Читать полностью…

መዓዛ ሃይማኖት በጎ አድራጎትና ጉዞ ማህበር

መዓዛ ሃይማኖት ጉዞ ማህበር:
ብርሃናተ ዓለም ቅዱስ ጴጥሮስ ወጳውሎስ

በየዓመቱ ሐምሌ ፭ ቀን በአንድ በኩል የጾመ ሐዋርያት ፋሲካ የሚከበርበት ዕለት ሲኾን፣ በሌላ በኩል ደግሞ የብርሃናተ ዓለም ቅዱሳን ጴጥሮስ እና ጳውሎስ በዓለ ዕረፍትም በዚሁ ዕለት ይዘከራል፡፡ በዛሬው ዝግጅታችን የእነዚህን ቅዱሳን ታሪክ በቅደም ተከተል በአጭሩ ይዘንላችሁ ቀርበናል፤

ቅዱስ ጴጥሮስ

ቅዱስ ጴጥሮስ በአባቱ የሮቤል፣ በእናቱ የስምዖን ነገድ ሲኾን፣ የተወለደውም በገሊላ አውራጃ በቤተ ሳይዳ ነው፡፡ ወላጆቹ ያወጡለት ስም ‹ስምዖን› ነበር፡፡ ጌታችን አምላካችንና መድኀኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ‹ጴጥሮስ› ብሎ ጠርቶታል፡፡ ትርጕሙም በግሪክ ቋንቋ ዓለት (መሠረት) ማለት ነው፡፡ ቅዱስ ጴጥሮስ የሚተዳደረው በዓሣ አጥማጅነት የነበረ ሲኾን፣ ሰዎችን በወንጌል መረብ እያጠመደ ወደ ክርስትና ሕይወት ይመልስ ዘንድ ጌታችን ለሐዋርያነት ጠርቶታል (ሉቃ. ፭፥፲፤ ማር. ፩፥፲፮)፡፡

ቅዱስ ጴጥሮስ በመንፈሳዊ ቅንዓቱና ለጌታችን በነበረው ፍቅር የሐዋርያት አለቃ ኾኖ ተሹሟል፡፡ ለአገልግሎት ከተጠራበት ጊዜ ጀምሮም በእስያ፣ በሮም፣ በሰማርያ፣ በልዳ፣ በኢዮጴ፣ በአንጾኪያ፣ በገላትያና በሌሎችም አገሮች እየተዘዋወረ ወንጌልን ሰብኳል፡፡ በስብከቱ ምክንያትም ልዩ ልዩ መከራን ተቀብሏል፡፡ በክርስቶስ ኀይል አጋዥነት ብዙ ድንቆችንና ተአምራትን አድርጓል፡፡ ከተሰጠው ጸጋ ብዛት የተነሣ በጥላው ሕሙማን ይፈወሱ ነበር (ሐዋ. ፭፥፲፭)፡፡ ሐዋርያው በቃል ካስተማረው ትምህርት በተጨማሪ በመጽሐፍ ቅዱስ በስሙ የተመዘገቡ ሁለት መልእክታትን ጽፏል (፩ኛ እና ፪ኛ ጴጥሮስ)፡፡

የቅዱስ ጴጥሮስ ምድራዊ የአገልግሎት ዘመኑ ሊፈጸም ሲቃረብም እንዲህ ኾነ፤ በዘመኑ የክርስቲያኖች ጠላት የነበረው የሮም ንጉሥ ወደ አካይያ ዘምቶ ድል አድርጎ በደስታ ወደ ሮሜ ሲመለስ መኳንንቱን ለማስደሰት፤ ጣዖታቱንም ለማክበር ሲል በቅዱስ ጴጥሮስና በሌሎችም ክርስቲያኖች ላይ የሞት ፍርድ ዐወጀ፡፡ ቅዱስ ጴጥሮስም በሮም ሲያስተምር ቆይቶ የሮም መኳንንት እንዳይገድሉት ትጥቁን ለውጦ ከሮም ሲወጣ ጌታችን መስቀል ተሸክሞ ተገለጸለት፡፡

በዚህጊዜ ‹‹አቤቱ ጌታ ሆይ ወዴት ትሔዳለህ?›› ሲል ቢጠይቀው ጌታችንም ‹‹ልሰቀል ወደ ሮም እሔዳለሁ›› አለው፡፡ ‹‹ዳግመኛ ትሰቀላለህን?›› ባለው ጊዜም ‹‹አንተ ስትፈራ ጊዜ ነው እንጂ›› ሲል መለሰለት፡፡ ያን ጊዜም ‹‹ጐልማሳ ሳለህ ወገብህን ታጥቀህ ወደ ወደድኸው ትሔድ ነበር፡፡ ስትሸመግል ግን እጅህን ታነሣና ሌላ ሰው ያስታጥቅሃል፤ ወደማትወደውም ይወስድሃል፤›› (ዮሐ. ፳፩፥፲፰) በማለት ጌታችን የነገረው ቃል አሟሟቱን የሚያመለክት መኾኑን አስታውሶ ወደ ሮም ተመልሶ ስብከቱን ቀጠለ፡፡

በሮማውያን ሕግ ቅጣት የተፈረደበት ወንጀለኛ የሮም አገር ተወላጅ ከኾነ የወንጀሉ ክብደትና ቅለት እየታየ ግርፋት ወይም ሞት ይፈረድበታል እንጂ በአንድ ወንጀል ሁለት ቅጣት አይቀጣም ነበር፡፡ ወንጀለኛው የውጪ አገር ዜጋ (ከሮም ውጪ) ከኾነ ግን ለምሳሌ ቅጣቱ ግርፋት ከኾነ ከተገረፈ በኋላ እስራት ይጨመርበታል፤ ቅጣቱ ሞት ከኾነም ከገረፉት በኋላ በመስቀል ወይም በሌላ መሣርያ ይገድሉት ነበር፡፡ ቅዱስ ጴጥሮስ ዜግነቱ ሮማዊ አልነበረምና በግርፋትም፣ በእስራትም በሞትም እንዲቀጣ ተፈረደበት፡፡

እንደ ሥርዓታቸውም ቅዱስ ጴጥሮስን ከገረፉት በኋላ ሊሰቅሉት ሲሉ ወታደሮቹን ‹‹እንደ ክብር ንጉሥ እንደ ጌታዬ ኢየሱስ ክርስቶስ አቁማችሁ ሳይኾን፣ ዘቅዝቃችሁ ስቀሉኝ›› አላቸው፡፡ እነርሱም እንዳላቸው አድርገው ሐምሌ ፭ ቀን ዘቅዝቀው ሰቅለውታል፡፡ በመስቀል ላይ ሳለም ተከታዮቹን በሃይማኖታቸው እንዲጸኑ ካዘዛቸው በኋላ ነፍሱን ለእግዚአብሔር ሰጠ፡፡ ሥጋውንም መርቄሎስ የሚባለው ደቀ መዝሙሩ ሽቱ ቀብቶ፣ በነጭ ሐር ገንዞ ዛሬ ቫቲካን በምትባለዋ ስፍራ በክብር ቀብሮታል፡፡

ቅዱስ ጳውሎስ

ቅዱስ ጳውሎስ ለአገልግሎት ከመጠራቱ በፊት ‹ሳውል› ይባል ነበር፡፡ ከኦሪቱ ምሁር ከገማልያል ሕገ ኦሪትንና መጻሕፍተ ነቢያትን ተምሯል፡፡ ለሕገ ኦሪት ቀናኢ ከመኾኑ የተነሣም የክርስቶስ ተከታዮችን ዅሉ ያሳድድ ነበር፡፡ ቅዱስ እስጢፋኖስ በድንጋይ ተደብድቦ በሰማዕትነት በሞተ ጊዜ ቅዱስ ጳውሎስ የገዳዮቹ ልብስ ጠባቂ ነበር (ሐዋ. ፯፥፶፰፤ ፳፪፥፳)፡፡ ክርስቲያኖችን ለማሳደድ ወደ ደማስቆ ሲሔድ ከመንገድ ላይ ለሐዋርያነት ተጠርቷል (ሐዋ. ፱፥፩-፴፩፤ ፳፪፥፩-፳፩)፡፡

ለሐዋርያነት ከተጠራበት ጊዜ ጀምሮም በመላው ዓለም እየተዘዋወረ ወንጌልን በመስበክ ብዙዎችን በኢየሱስ ክርስቶስ ስም አሳምኗል፡፡ ሲሰብክም ጣዖት አምላኪ፣ ሕመምተኛ፣ ችግረኛ፣ አረማዊና አይሁዳዊ እየመሰለ ብዙዎችን አስተምሮ ለእግዚአብሔር መንግሥት አዘጋጅቷል (፩ኛ ቆሮ. ፱፥፲፱-፳፫)፡፡ ዐረብ፣ አንጾኪያ፣ እልዋሪቆን፣ ሊቃኦንያ፣ ሦርያ፣ ግሪክና ልስጥራን ካስተማረባቸው አገሮች ጥቂቶቹ ናቸው፡፡

ወንጌልን በመስበኩ ምክንያትም ከአይሁድና ከአረማውያን ዘንድ ብዙ መከራና ስቃይ ደርሶበታል፡፡ ቅዱስ ጳውሎስ ከእግዚአብሔር በተሰጠው ጸጋ ብዙ ድንቆችንና ተአምራትን አድርጓል፡፡ በልብሱ ቅዳጅም ሕሙማን ይፈወሱ ነበር (ሐዋ. ፲፱፥፲፩)፡፡ ሐዋርያው በቃል ካስተማረው ሌላ በመጽሐፍ ቅዱስ በስሙ የተመዘገቡ ፲፬ መልእክታት አሉት፡፡

አገልግሎቱን ሊፈጽም ሲልም የሮም ንጉሥ ኔሮን ቄሣር የክርስቲያኖች ቍጥር እየጨመረ የመጣው በቅዱስ ጳውሎስ ትምህርት በመማረካቸው ምክንያት መኾኑን ተረድቶ፤ ይልቁንም የቤተ መንግሥቱ ሰዎች ሳይቀር በቅዱስ ጳውሎስ በመማረካቸው ተቈጥቶ ቅዱስ ጳውሎስን ወደ ፍርድ ሸንጎው አስቀረበው፡፡ ቅዱስ ጳውሎስም በቀኝ እጁ ከሰንሰለቱ ጋር መስቀሉን ይዞ ንጉሡንና ወታደሮችን ሳይፈራ የኢየሱስ ክርስቶስን የእግዚአብሔር ልጅነትና አምላካዊ ሥልጣን ይመሰክር ነበር፡፡

ንጉሡም በቍጣ ይሙት በቃ ፈረደበት፡፡ ከላይ እንደ ተገለጸው ሮማውያን የሞት ፍርድ ሲፈርዱ የሚቀጣው ሰው የሌላ አገር ዜጋ ከኾነ ከፍርዱ ውጪ ተጨማሪ ቅጣት ይቀጡትና ይገድሉት ነበር፡፡ ቅዱስ ጳውሎስ ግን የሮም ዜግነት ስለ ነበረው ሳይገርፉ በአንድ ቅጣት ብቻ በሰይፍ እንዲገደል ወስነውበታል፡፡ ወደሚገደልበት ስፍራ ሲወስዱትም በንግግሩና በአስተያየቱ ዅሉ ምንም ፍርኀት አይታይበትም ነበር፡፡ እንዳውም በጦርነት ድል አድርጎና ማርኮ እንደ ተመለሰ ወታደር ይደሰት ነበር እንጂ፡፡ ለሚገድሉትም ይቅርታን ይለምን ነበር፡፡

በገዳዮቹና በተከታዮቹ ፊትም የክርስትና ሽልማቱ የእግዚአብሔር መንግሥት መኾኑን የሚያስገነዝብ ቃል እያስተማረ እግዚአብሔር የሚሰጠውን የጽድቅ አክሊል ለመቀበል ይቻኮል ነበር (፪ኛ ቆሮ. ፬፥፮-፲፰)፡፡ ወታደሮች ሊገድሉት ሲወስዱትም ከንጉሥ ኔሮን ወገን የኾነችውን የአንዲት ብላቴና መጐናጸፊያ ‹‹ዛሬ እመልስልሻለሁ›› ብሎ ከተቀበላት በኋላ ‹‹መልካሙን ገድል ተጋድያለሁ፤ ሩጫዬን ጨርሻለሁ፡፡ ሃይማኖቴን ጠብቄአለሁ፤ ወደፊትም የጽድቅ አክሊል ተዘጋጅቶልኛል፤›› በማለት ራሱ በመልእክቱ እንደ ተናገረው (፪ኛ ጢሞ. ፬፥፯-፰)፣ ፊቱን በብላቴናዋ መጐናጸፊያ ተሸፍኖ አንገቱን በሰይፍ ተቀልቶ አገልግሎቱን በሰማዕትነት ፈጽሟል፡፡

Читать полностью…

መዓዛ ሃይማኖት በጎ አድራጎትና ጉዞ ማህበር

✅ የቃልህ ፍቺ ያበራል፥ ሕፃናትንም አስተዋዮች ያደርጋል።”
— መዝሙር 118(119)፥130
🕎ስለ መጽሐፍ ቅዱስ ምንነት እንዲሁም በመጽሐፍ ቅዱስ ላሉት ምንባባት አንድምታቸው ትንታኔና ማብራርያ የሚያገኙበት ቻናል ይቀላቀሉ።

👉“መጽሐፍ” ለሚለው ምንጭ በግሪክ ቋንቋ ቢብሎስ (byblos) ከደንገል በተሠራ ወረቀት ወይም በብራና ከተጻፈ በኋላ በሁለት በትሮች...read more

👉መጽሐፍ ቅዱስ መቼ በአንድ ጥራዝ ተጠቀለለ? ከክ.ል.በ ይሁን በኋላ የተጻፉት ሁሉንም መጻሕፍቶች ለየብቻቸው ነበሩ፡፡ከ500ዎቹ ዓ.ዓ....read more

👉ኦሪት "ኦራይታ" ከሚል የሶርያ(አራማይክ) ቃል የተገኘ ሲሆን ትርጓሜውም "ሕግ" ወይም "ትምህርት" ማለት ነው።የመጠሪያ ምንጩም....read more



ወቅታዊ የቤተ ክርስቲያናችንን ጉዳይ እና መንፈሳዊ ጥንካሬያችንን እንድናበረታ የሚያግዙን መንፈሳዊ ቻናሎችን ይዘን ቀርበናል።እርስዎም ከእነዚህ መንፈሳዊ ቻናሎች የነፍስ ምግብ የሆነውን የእግዚአብሔርን ቃል እየተመገቡ መንፈሳዊ ሕይወትዎትን እንዲያጠናክሩ በእግዚአብሔር ስም ጥሪያችንን እናቀርባለን🙏
🙏ፈጣሪ ይባርከን🙏

ከነዚህ መፀሀፍት የተወጣጡበት
ትምህርትን መማር ይፈልጋሉ❔
እነሆ ብለናል :-
📚የባሕታውያን አባቶች ሕይወትና የመዝሙራት ተመስጦ
📖▓⇨ትምህርት በአባ ሺኖዳ ⇨ክፈት
📚የድያቢሎስ ውግያዎች
📖▓⇨ትምህርት ⇨ክፈት
📚አምደ ሀይማኖት
📖▓⇨በአባታችን ቅዱስ ሺኖዳ ⇨ክፈት
📚መንፈሳዊ ሕይወት
📖▓⇨በአቡነ ሺኖዳ ⇨ክፈት
📚መንፈሳዊ ሰው
📖▓⇨በአቡነ ሺኖዳ ⇨ክፈት
📚የአባቶች ሕይወት ንሮ እና ተመስጦ
📖▓⇨በአቡነ ሺኖዳ ⇨ክፈት
የመኖኮሳት ታሪክ እና ተመስጦ በብጽእ አቡነ ሺኖዳ ሳልሳዊ ይቀርብበታል።

Читать полностью…

መዓዛ ሃይማኖት በጎ አድራጎትና ጉዞ ማህበር

ስንክሳር ዘወርሃ ሐምሌ አምስት-ክፍል አንድ

@meazahaymanot

Читать полностью…

መዓዛ ሃይማኖት በጎ አድራጎትና ጉዞ ማህበር

ዝክረ  ቅዱሳን  መርሐ  ግብር
   በስመ አብ ወወልድ  ወመንፈስ  ቅዱስ አሐዱ  አምላክ  አሜን

ሐምሌ ፫ ቀን ቅዱስ  ቄርሎስ ሊቀ ጳጳሳት ዘእስክንድርያ

   ቄርሎስ ማለት ኀያል አንበሳ ብፁዕ  ገብረ አምላክ ኅሩይ ዘርዕ ሰናይ ጽጌ ፍሬ መስተገብረ ምድር ኵሉ ለአምላክ  ይትከሀሎ ማለት ነው።
ቅዱስ  ቄርሎስ በ፫፻፸፭  አ ም  በእስክንድርያ  ተወለደ።
የአባ ቴዎፍሎስ የእህቱ ልጅ ነው። በተወለደ በ፯  ዓመቱ ወደ ገዳመ አስቄጥስ ኺዶ ከአባ መቃርስ ዘንድ ብሉይና ሐዲስን በፍጥነት  በ፲፪  አመቱ ተማረ። « ወሶበ ይሰምዖ ለቀለም ያጸንኦ አሐደ ጊዜ ወይመስል ከመ ቀዳሚ ተምህረ” እንዲል ትርጉም « ቀለም ሲነገር አስቀድሞ የተማረው ይመስላል አንድ ጊዜ ያጠናውም ነበር።
ከዚህ በኋላም  ከአባ ሰራብዮን ስርአተ ምንኩስናን ተምሯል ።በትምህርቱም  እጅግ ተወዳጅ ና ጣፋጭ አንደበት  ነበረው። ቴዎፍሎስም ካረፈ በኋላ  ሊቀ ጵጵስና ሾሙትና በዘመኑ ቤተክርስቲያን  በራች።
የንስጥሮስን ክህደትም የሻረነው ንስጥሮስም ክህደቱ እመቤታችንን  የክርስቶስ  እናት አይደለችም በማለት ነበር። ንስጥሮስንም  መስከረም ፲፪ ቀን በጉባኤው  አውግዞ  ለየው። ይህንስ ክህደት  ከምን አገኘው ቢሉ ሳምሳጢ የተባለ አንድ ባሕታዊ ነበር። በገዳም ውስጥም ለረጅም ጊዜ የቆየ ነበር እናም ቤልሆር በመልአክ ተመስሎ መጥቶ ጾምህ ጸሎትህ ከእግዚአብሔር  ዘንድ ተሰምቷል  አምላክ  በድንግልና  የተወለደ  አይምሰልህ  ፣በሩካቤ  ተወለደ እንጂ ይህም ሰው ደግ ኾነ ፤ በ፴ አመቱ በዮርዳኖስ  በዮሐንስ  እጅ ሲጠመቅ ለስላሴ የጸጋ ልጅ ሆነ በማለት  አስካደው።እርሱም እውነት መስሎት  ለትያሮስ ትያሮስም ፣ለድያድሮስ፣ድያድሮስም ለንስጥሮስን ፣እርሱም ለልዮንና ለመርቅያን አስተማረ። መርቅያን ንጉሥ ልዮን ሊቀ ጳጳሳት በነበሩበት  ጊዜ ይህን ክህደት ማስተማር  ጀመሩ።ቅዱስ ቄርሎስም አፈ ጉባኤ ኹኖ ንስጥሮስን  ፈቶታል። በጉባኤውም ፰ ቀኖናዎች ተደንግገዋል። በዚህም ንስጥሮስ ተወግዞ ወደ ላዕላይ ግብፅ ተሰደደ ።ቄርሎስም ካለበት ድረስ በመሄድ መማለድ ይገባል  ብሎ እርሱን የባሕርይ  አምላክ እሷንም  ወላዲተ አምላክ በላት ከክህደትክ ተመለስ አለው። እርሱም  አይ ይች ሃይማኖት ተስማምታኛለች አለው። ለእኔ እንዳልታዘዝከኝ አንደበትህም ለአንተ  አይታዘዝልህ አለው እርሱም ዐንደበቱ ተጎልጉሎ ውጥቶ ከልቡ ላይ ወድቆ ደምና መግል እየተፋ እንደውሻ እየጮኸ  ሙቷል። እሱንም ባወገዘበት ወቅት ፲፪ አንቀጽ ደረሰ። በውስጦም የቀናች ሃይማኖትን ገለጠ። ክርስቶስ  ከተወለደ በኋላ  ፩ አካል  ፩ ባሕርይ  እንደሆነ አስረዳ ። ከ፫፻ ሃይማኖት  ወጥተው ክርስቶስን  ፪ አካል  ፪ ባሕርይ  የሚሉ መናፍቃንን አውግዞ  ለይቷቸዋል።
በተሾመበት ወቅት  ብዙ ድርሳናትን  ተግሳጻትንና ቅዳሴን ጽፏል።ይህንንም  በማድረጉ ታላቅ የቅድስት  ቤተክርስቲያን  ጠበቃ ተጋዳይም ይሉት ነበር። ምድራውያን መላእክት  ከተባሉት ከ ፳፬  ደራሲያን አንዱ ነው። በወንጌላዊው ማርቆስ መንበር ለ፴፪ አመት ተቀምጦል።
እርሱም  እንድህ ባለ ግብር ኖሮ ለሊቀ ጳጳስነት በተመረጠ በ፵፫  አመቱ  በዚህች  ቀን ሐምሌ  ፫  ዐርፏል።
በረከቱ አይለየን።

Читать полностью…

መዓዛ ሃይማኖት በጎ አድራጎትና ጉዞ ማህበር

✅ የቃልህ ፍቺ ያበራል፥ ሕፃናትንም አስተዋዮች ያደርጋል።”
— መዝሙር 118(119)፥130
🕎ስለ መጽሐፍ ቅዱስ ምንነት እንዲሁም በመጽሐፍ ቅዱስ ላሉት ምንባባት አንድምታቸው ትንታኔና ማብራርያ የሚያገኙበት ቻናል ይቀላቀሉ።

👉“መጽሐፍ” ለሚለው ምንጭ በግሪክ ቋንቋ ቢብሎስ (byblos) ከደንገል በተሠራ ወረቀት ወይም በብራና ከተጻፈ በኋላ በሁለት በትሮች...read more

👉መጽሐፍ ቅዱስ መቼ በአንድ ጥራዝ ተጠቀለለ? ከክ.ል.በ ይሁን በኋላ የተጻፉት ሁሉንም መጻሕፍቶች ለየብቻቸው ነበሩ፡፡ከ500ዎቹ ዓ.ዓ....read more

👉ኦሪት "ኦራይታ" ከሚል የሶርያ(አራማይክ) ቃል የተገኘ ሲሆን ትርጓሜውም "ሕግ" ወይም "ትምህርት" ማለት ነው።የመጠሪያ ምንጩም....read more



ወቅታዊ የቤተ ክርስቲያናችንን ጉዳይ እና መንፈሳዊ ጥንካሬያችንን እንድናበረታ የሚያግዙን መንፈሳዊ ቻናሎችን ይዘን ቀርበናል።እርስዎም ከእነዚህ መንፈሳዊ ቻናሎች የነፍስ ምግብ የሆነውን የእግዚአብሔርን ቃል እየተመገቡ መንፈሳዊ ሕይወትዎትን እንዲያጠናክሩ በእግዚአብሔር ስም ጥሪያችንን እናቀርባለን🙏
🙏ፈጣሪ ይባርከን🙏

ከነዚህ መፀሀፍት የተወጣጡበት
ትምህርትን መማር ይፈልጋሉ❔
እነሆ ብለናል :-
📚የባሕታውያን አባቶች ሕይወትና የመዝሙራት ተመስጦ
📖▓⇨ትምህርት በአባ ሺኖዳ ⇨ክፈት
📚የድያቢሎስ ውግያዎች
📖▓⇨ትምህርት ⇨ክፈት
📚አምደ ሀይማኖት
📖▓⇨በአባታችን ቅዱስ ሺኖዳ ⇨ክፈት
📚መንፈሳዊ ሕይወት
📖▓⇨በአቡነ ሺኖዳ ⇨ክፈት
📚መንፈሳዊ ሰው
📖▓⇨በአቡነ ሺኖዳ ⇨ክፈት
📚የአባቶች ሕይወት ንሮ እና ተመስጦ
📖▓⇨በአቡነ ሺኖዳ ⇨ክፈት
የመኖኮሳት ታሪክ እና ተመስጦ በብጽእ አቡነ ሺኖዳ ሳልሳዊ ይቀርብበታል።

Читать полностью…

መዓዛ ሃይማኖት በጎ አድራጎትና ጉዞ ማህበር

ከአሁን ጀምሮ እንደተለመደው ለቻናላችን ያላችሁን ሀሳብ አስተያየት ማቅረብ ትችላላችሁ። ቢኖሩ፣ ቢስተካከሉ የምትሏቸው ጉዳዮች ላይ አተኩራችሁ ስማችሁንና ከየት ሀገር እንደሆናችሁ እየገለጻችሁ በድምጽ ሆነ በጽሑፍ ላኩልን። ቤተሰቦቻችን የት የት እንዳሉም እንድናውቅና እንድንተዋወቅ ይረዳናል     ላይ @misiwani_Bot እንጠብቃችኋለን

ሐሳብ አስተያየታቸውን ጻፉልን

Читать полностью…

መዓዛ ሃይማኖት በጎ አድራጎትና ጉዞ ማህበር

✅ የቃልህ ፍቺ ያበራል፥ ሕፃናትንም አስተዋዮች ያደርጋል።”
— መዝሙር 118(119)፥130
🕎ስለ መጽሐፍ ቅዱስ ምንነት እንዲሁም በመጽሐፍ ቅዱስ ላሉት ምንባባት አንድምታቸው ትንታኔና ማብራርያ የሚያገኙበት ቻናል ይቀላቀሉ።

👉“መጽሐፍ” ለሚለው ምንጭ በግሪክ ቋንቋ ቢብሎስ (byblos) ከደንገል በተሠራ ወረቀት ወይም በብራና ከተጻፈ በኋላ በሁለት በትሮች...read more

👉መጽሐፍ ቅዱስ መቼ በአንድ ጥራዝ ተጠቀለለ? ከክ.ል.በ ይሁን በኋላ የተጻፉት ሁሉንም መጻሕፍቶች ለየብቻቸው ነበሩ፡፡ከ500ዎቹ ዓ.ዓ....read more

👉ኦሪት "ኦራይታ" ከሚል የሶርያ(አራማይክ) ቃል የተገኘ ሲሆን ትርጓሜውም "ሕግ" ወይም "ትምህርት" ማለት ነው።የመጠሪያ ምንጩም....read more



ወቅታዊ የቤተ ክርስቲያናችንን ጉዳይ እና መንፈሳዊ ጥንካሬያችንን እንድናበረታ የሚያግዙን መንፈሳዊ ቻናሎችን ይዘን ቀርበናል።እርስዎም ከእነዚህ መንፈሳዊ ቻናሎች የነፍስ ምግብ የሆነውን የእግዚአብሔርን ቃል እየተመገቡ መንፈሳዊ ሕይወትዎትን እንዲያጠናክሩ በእግዚአብሔር ስም ጥሪያችንን እናቀርባለን🙏
🙏ፈጣሪ ይባርከን🙏

ከነዚህ መፀሀፍት የተወጣጡበት
ትምህርትን መማር ይፈልጋሉ❔
እነሆ ብለናል :-
📚የባሕታውያን አባቶች ሕይወትና የመዝሙራት ተመስጦ
📖▓⇨ትምህርት በአባ ሺኖዳ ⇨ክፈት
📚የድያቢሎስ ውግያዎች
📖▓⇨ትምህርት ⇨ክፈት
📚አምደ ሀይማኖት
📖▓⇨በአባታችን ቅዱስ ሺኖዳ ⇨ክፈት
📚መንፈሳዊ ሕይወት
📖▓⇨በአቡነ ሺኖዳ ⇨ክፈት
📚መንፈሳዊ ሰው
📖▓⇨በአቡነ ሺኖዳ ⇨ክፈት
📚የአባቶች ሕይወት ንሮ እና ተመስጦ
📖▓⇨በአቡነ ሺኖዳ ⇨ክፈት
የመኖኮሳት ታሪክ እና ተመስጦ በብጽእ አቡነ ሺኖዳ ሳልሳዊ ይቀርብበታል።

Читать полностью…

መዓዛ ሃይማኖት በጎ አድራጎትና ጉዞ ማህበር

ስንክሳር ዘወርሃ ሐምሌ አንድ(፩)
/channel/meazahaymanot

Читать полностью…

መዓዛ ሃይማኖት በጎ አድራጎትና ጉዞ ማህበር

ብፁዕ  ወቅዱስ አቡነ ማትያስ ቀዳማዊ ፓትርያርክ ርእሰ ሊቃነ ጳጳሳት ዘኢትዮጵያ ሊቀ ጳጳስ ዘአክሱም ወእጨጌ ዘመንበረ ተክለ ሃይማኖት
የእጩ ኤጲስ ቆጶሳት ምርጫ በተመለከተ  ሰኔ 29ቀን 2015 ዓ.ም መግለጫ ሰጡ ።

በተጨማሪም በክልል ትግራይ በተካሄደው ጦርነት ወቅት ቅድስት ቤተክርስቲያን ሐዋርያዊትና ታሪካዊት ቤተክርስቲያን እንደመሆኗ መጠን ጦርነቱ እንዲቆም በወቅቱ መግለጫ ባለመስጠቷ ፣ በጦርነቱ መካከል ወደ ትግራይ ክልል መግባትና መውጣት በሚቻልበት ወቅትም በክልሉ የሚገኙ ብፁዓን አበው ሊቃነ ጳጳሳትን ፣ ሊቃውንተ ቤተ ክርስቲያንንና መላው ሕዝበ ትግራይን በአካል በቦታው ተገኝታ ባለመጠየቋና ባለማጽናናቷ ፣ ጦርነቱ ቆሞ በሀገር አቀፍ ደረጃ እርቀ ሰላም ከወረደበት ጀምሮ ለደረሰው ጉዳት በቅዱስ ሲኖዶስ የተወሰነውን ሰብአዊ ድጋፍ በውሳኔው መሠረት በወቅቱ ማድረስ ባለመቻሏ ፣ በዚሁም የተነሣ በቤተ ክርስቲያኗና በመላው ሕዝበ ትግራይ መካከል ለተፈጠረው ቅሬታና አለመግባባት ቅዱስ ሲኖዶስ ይቅርታ ጠይቋል።

          ምንጭ:- eotc tv

@meazahaymanot

Читать полностью…

መዓዛ ሃይማኖት በጎ አድራጎትና ጉዞ ማህበር

ምክረ አበው

ሥጋችን ምግብ ሲያጣ እንደሚደክም ሁሉ ነፍስም ምግቧን የእግዚአብሔርን ቃል ስታጣ ትደክማለች።

                    አቡነ ሺኖዳ ሳልሳዊ

መልካም ቀን

Читать полностью…

መዓዛ ሃይማኖት በጎ አድራጎትና ጉዞ ማህበር

ክርስቲያን ገብተው በእጃቸው ሲያጨበጭቡ አስሯቸው የነበረው ልጃቸው ድምፅ ሰምቶ ሲመጣ አባታችንን ሲመለከት ደነገጠና አባቴ ሆይ! ማን አወጣህ?›› ማንስ እጅህንና እግርህን ፈታህ አላቸው። እርሳቸውም ለልጆቻቸው የሆነውን ሁሉ ነገሯቸው።

አቡነ ክፍለ ሥላሴ ደብረ መድኀኒት ብለው በሰየሟት ገዳማቸው ባምብቆ አካባቢ የከብት በሽታ (ጉልሓይ) ተከስቶ ነበር ነገር ግን ያንን በሽታ ያመጣውን ክፉ ሰይጣን ጻድቁ በጸሎታቸው ኀይል እያስጮኹ አባረው ጣሉት፤ ድምፁንም ሰምተው የአካባቢው ሰዎች ጠላታቸው እንደወደቀ ዐውቀው ከብቶቻቸውም ጤነኞች ስለሆኑላቸው የአቡነ ክፍለ ሥላሴን አምላክ አመሰገኑ።

ጻድቁ የተሰወረውን ሁሉ ያውቁ ነበር፤ አንድ ቀን ወደ ቤተ ክርስቲያን መሔድ የማያስችል ሕማም አጋጠማቸውና በእርሳቸው ፋንታ አንድ እግሩን የሚያመው ወዳጃቸውን ሔዶ ዕጣን እንዲያጥን ነገሩት። እርሱም ሔዶ ግድግዳውን ተጠግቶ በሰሜንና በደቡብ አጥኖ በምዕራንና በምሥራቅ ሳያጥን ተመልሶ ሊጠይቃቸው ሲመጣ አባታችንም ‹‹አንተ ወንድሜ ስለምን እንደዚህ ታደርጋለህ? ለምን እንደአባቶቻችን አድርገህ በምዕራብና በምሥራቅ አላጠንክም?›› አሉት ይህንንም ሲሰማ ያ ካህን ደንግጦ በሠራው ስሕተት ንስሓ ገባና እግዚአብሔርን አመሰገነ።

በመጨረሻም የአቡነ ክፍለ ሥላሴ ጊዜ ዕረፍታቸው ሲደርስ ለአንድ ወዳጃቸው ለሆነ ካህን “ወንድሜ ሆይ! እኔ ማክሰኞ ቀን በአባታችን በአብርሃም በዓል ዕለት እሞታለሁ›› በማለት የሚያርፉበትን ቀን ነገሩት። በተናገሩትም መሠረት ከምንኵስናቸው በፊት 20 ዓመት ከምንኩስናቸው በኋላ 8 ዓመት ኖረው በ28 ዓመታቸው ሰኔ 28 ቀን በዕለተ ማክሰኞ ዐረፉ። ጻድቁ ራሳቸው በተከሏትና በጸለዩባት በደብረ መድኀኒት ቅድስት ሥላሴ ባምብቆ ከተቀበሩ በኋላም ብዙ ተኣምራት አድርገዋል። ዝክራቸውን ያደረገ በጸሎታቸው የተማጸነ በዚህ ዓለም ከመከራ ሥጋ፣ በሚመጣውም ዓለም ከመከራ ነፍስ እንደሚድን ጌታችን በአምላካዊ ቅዱስ ቃሉ ቃልኪዳን ስለገባላቸው የባምብቆ ሕዝብና የዛውል ሕዝብ ሰኔ 28 ቀን በዓላቸውን በታላቅ ክብር ያከብራሉ።

የአቡነ ክፍለ ሥላሴ ዘዛውል ወዘባንብቆ ረድኤት በረከታቸው ይደርብን በጸሎታቸው ይማረን!
(ምንጭ በእንተ ቅዱሳን ኅሩያን መጽሐፍ)

Читать полностью…

መዓዛ ሃይማኖት በጎ አድራጎትና ጉዞ ማህበር

ዝክረ ቅዱሳን

ዝክረ አቡነ ክፍለ ሥላሴ

Читать полностью…

መዓዛ ሃይማኖት በጎ አድራጎትና ጉዞ ማህበር

ማነው የሰማዕቱ ቅዱስ ጊዮርጊስ ወዳጅ
መስታወት፣ምንጣፍ ፣መስኮት፣በር የሚችል

   ቤተክርስቲያኑን መርዳት የምትፈልጉ በኢትዮጵያ ንግድ ባንክ  አድቻ ቅዱስ ጊዮርጊስ ህንፃ አሰሪ ኮሚቴ 1000518773047 በማስገባት የአባታችንን የሰማዕቱ ቅዱስ ጊዮርጊስ ቤት እንስራ።በረከቱ በሁላችንም ላይ ይደርብን አሜን

ካስገቡ በኋላ ፎቶ አንስተው/ screenshot አድርገው ይላኩልን

0989680703
0960029538

Читать полностью…
Subscribe to a channel