meazahaymanot | Unsorted

Telegram-канал meazahaymanot - መዓዛ ሃይማኖት በጎ አድራጎትና ጉዞ ማህበር

4288

"ውድስት አንቲ በአፈ ነቢያት ወስብሕት በሐዋርያት አክሊለ በረከቱ ለያዕቆብ ወትምክህተ ቤቱ ለእስራኤል፡፡" "በነቢያት በሐዋርያት አንደበት የተመሰገንሽ የያዕቆብ የበረከቱ ዘውድ የእስራኤል ወገን መመኪያ አንቺ ነሽ"                  መጽሐፈ ሰዓታት የፌስቡክ ፔጃችን www.fb.me/meazhaimanot ይቀላቀሉን

Subscribe to a channel

መዓዛ ሃይማኖት በጎ አድራጎትና ጉዞ ማህበር

ስንክሳር ዘወርሃ ሐምሌ ሃያ ሁለት(፳፪)
/channel/meazahaymanot

Читать полностью…

መዓዛ ሃይማኖት በጎ አድራጎትና ጉዞ ማህበር

ስንክሳር ዘወርሃ ሐምሌ ሃያ አንድ (፳፩)
/channel/SinkisarZekidusan2

Читать полностью…

መዓዛ ሃይማኖት በጎ አድራጎትና ጉዞ ማህበር

ስንክሳር ዘወርሃ ሐምሌ ሃያ(፳)
/channel/meazahaymanot

Читать полностью…

መዓዛ ሃይማኖት በጎ አድራጎትና ጉዞ ማህበር

እንኳን ለመጋቤ ሐዲስ ለሊቀ መላእክት ቅዱስ ገብርኤል ዓመታዊ በዓል በሰላም አደረሳችሁ

መልካም ቀን
መልካም በዓል

Читать полностью…

መዓዛ ሃይማኖት በጎ አድራጎትና ጉዞ ማህበር

ኢየሉጣ ወለደት ኢየሉጣ ወለደት ነቅዓ ጽጌረዳ ወለደት (፪)
ፀሐየ ጽድቅ የአውዳ ፀሐየ ጽድቅ (፪)

Читать полностью…

መዓዛ ሃይማኖት በጎ አድራጎትና ጉዞ ማህበር

https://youtu.be/5_BYH_8yrlc

Читать полностью…

መዓዛ ሃይማኖት በጎ አድራጎትና ጉዞ ማህበር

ስንክሳር ዘወርሃ ሐምሌ አሥራ ስድስት

Читать полностью…

መዓዛ ሃይማኖት በጎ አድራጎትና ጉዞ ማህበር

ስንክሳር ዘወርሃ ሐምሌ አሥራ አምስት
/channel/meazahaymanot

Читать полностью…

መዓዛ ሃይማኖት በጎ አድራጎትና ጉዞ ማህበር

ዝክረ ቅዱሳን

ዝክረ ቅዱስ አብሮኮሮንዮስ

Читать полностью…

መዓዛ ሃይማኖት በጎ አድራጎትና ጉዞ ማህበር

ስንክሳር ዘወርሃ ሐምሌ አሥራ አራት(፲፬)
/channel/meazahaymanot

Читать полностью…

መዓዛ ሃይማኖት በጎ አድራጎትና ጉዞ ማህበር

ዝክረ ቅዱሳን
ዝክረ አቡነ ብስንድዮስ እና ሰማዕቱ ቅዱስ አሞን

Читать полностью…

መዓዛ ሃይማኖት በጎ አድራጎትና ጉዞ ማህበር

ምክረ አበው

"የማታምንበትን ነገር ለሰው ስትል አትስራው ከሰራኸው እንደምትጠፋበት እወቅ።" (መጽሐፈ ምክር)

"አንደበቱን ከቧልት ያየውን ምስጢር ከመናገር የሚከለክል ሰው ልቦናውን ከኅልዮ ኃጢአት ያርቀዋል።" (አረጋዊ መንፈሳዊ)

"ጸጋ ቢሰጥህ  በተሰጠህ ጸጋ አመስግን ያልተሰጠህን እሻለሁ በማለት የተሰጠህን እዳታጣ።" (ማር ይስሃቅ)


መልካም ቀን
@meazahaymanot

Читать полностью…

መዓዛ ሃይማኖት በጎ አድራጎትና ጉዞ ማህበር

ምክረ አበው ዘቅዱስ ባስልዮስ ዘቂሳርያ

=> የጌታችን የኢየሱስ ክርስቶስ ፍቃድ የሰዎች ድኀነት ነው። ነገር ግን ሰው መዳንን ካልፈቀደ ራሱን  ወደ ፈቀደበት ይጨምራል። ስለዚህ ፍቃድህን ሁሉ ለፍቃደ እግዚአብሔር አስገዛ።

=>  ጭካኔ የተሞላ ጠላትነት በሰው ላይ የሚፈጽሙ ቁጣን የተሞሉ ሰዎች ከመርዛማዎች የዱር እንስሳት ጋር አንድ ናቸውና አማኒ ሆይ እባክህ በሰው አትጨክን

=> እግዚአብሔር እርስ በእርሳችን እንድንዋደድ ይፈልጋል። ነጻነት  ትርጉሙ  ይህ ነው። እግዚአብሔርና ወንድሞቻችንን መውደድ።

መልካም ቀን

@meazahaymanot

Читать полностью…

መዓዛ ሃይማኖት በጎ አድራጎትና ጉዞ ማህበር

✥•••••●◉ ✞ ◉●•••••✥
✍️"የሚሰማኝ ግን በእርጋታ ይቀመጣል ከመከራም ሥጋት ያርፋል"
📖ምሳ 1፥33
                       
#ስንክሳር          
             ዘሐምሌ
#አስራ አንድ (፲፩)     
              ✥•••••●◉ ✞ ◉●•••••✥

Читать полностью…

መዓዛ ሃይማኖት በጎ አድራጎትና ጉዞ ማህበር

ስንክሳር ዘወርሃ ሐምሌ አሥር (፲)
/channel/meazahaymanot

Читать полностью…

መዓዛ ሃይማኖት በጎ አድራጎትና ጉዞ ማህበር

ምክረ አበው ዘአባ እንጦንስ

"መንፈሳዊ ብቃት፥ የማይደረስበት እሩቅ፣ ወይም ከሰው ልጅ ችሎታ በላይ ነው፥ ብለን ማሰብ የለብንም። ሰዎች ባሕር አቋርጠው የሌላ ሀገር ፍልስፍና ሊማሩ ይሄዳሉ። የእግዚአብሔር ከተማ ግን በልባቸው ውስጥ ነው። እግዚአብሔር የሚጠብቅብን መልካም ምግባርም እዚያው ልባችን ላይ ነው ያለው። የሚጠበቅብን መሻታችንን ከእግዚአብሔር መሻት ጋር ማስማማት (አንድ ማድረግ) ብቻ ነው።"



መልካም ቀን

Читать полностью…

መዓዛ ሃይማኖት በጎ አድራጎትና ጉዞ ማህበር

ሁሉም ኦርቶዶክሳዊ ሰው ሊቀላቀልው የሚገባ ቻናል

Читать полностью…

መዓዛ ሃይማኖት በጎ አድራጎትና ጉዞ ማህበር

❤️አረጋጊው መልአክ❤️


አረጋጊው መልአክ የመላእክትን ዓለም
ገብርኤል አንተ ነህ አብሳሪ ለማርያም
(መተህ አረጋጋን ሰላምን ተናገር
እንጽና በእምነት እንኑር በፍቅር (2)

ባለንበት እንቁም እንፅና በእምነት
እስከምናውቅ ድረስ የፍጥረቱን አባት
ብለህ ስትናገር ገብርኤል በአርያም
በቃልህ ጸንተዋል እስከ ለዘለዓለም


የዱራውን ሜዳ ያንን የሞት መንደር
ከሰማያት ወርደህ ሞላኸው በመዝሙር
መጠፋፋት ይብቃ ይብዛ ሰላማችን
ገብርኤል አትለይ ቁም ከመኃላችን


በገሊላ መንደር ተልከህ ከእግዚአብሔር
ደስታ ይገባሻል ውዳሴ እና ክብር
ብለህ በትህትና የምስራች አልካት
ለድንግል ማርያም ደስታን አበሰርካት


ቂርቆስ ኢየሉጣ ለአምላክ ቢታመኑም
በሚፍለቀለቀው ቢጣሉ ከጋኑም
ገብርኤል ስትደርስ ውኃው ቀዘቀዘ
ሞትን ያሸንፋል ለአምላክ የታዘዘ

✥••┈┈••●◉ ✞ ◉●••┈┈••✥

/channel/meazhaymanot
/channel/meazahaymanot

Читать полностью…

መዓዛ ሃይማኖት በጎ አድራጎትና ጉዞ ማህበር

🌼🌼🌼🌼🌼🌼🌼🌼🌼🌼
ሥርዓተ ማህሌት ዘ ሐምሌ ገብርኤል
🍂🍂🍂🍂🍂🍂🍂🍂🍂🍂🍂
#ስቡህ_ከተባለ_በኃላ

መልክዐ ሥላሴ
ሰላም ለአቁያጺክሙ እለ ተኀብአ እምዐይን: አናምያኒሁ ሥላሴ ለሜላተ ሰማይ ብርሃን: ልብሰ ሰማዕትና ይኲነኒ ምሕረትክሙ ክዳን: ላዕሌየ እስመ ኢሀሎ ልብሰ እስጢፋኖስ እብን: ወሥርጋዌሁ እሳት ለቂርቆስ ሕጻን፡፡

ዚቅ
ሃሌ ሉያ ሃሌ ሉያ ሃሌ ሉያ: አንቃዕዲዎ ሰማየ: ጸለየ ወይቤ ቅዱስ ቂርቆስ እጼውዓከ እግዚእየ: ዘኢትሠዓር ንጉሠ ነገሥት መዋዒ: እጼውዓከ እግዚእየ: ዘሰቀልኮ ለሰማይ ከመ ቀመር: እጼውዓከ እግዚእየ: ዘበሥላሴከ ዓመድካ ለምድር: እጼውዓከ እግዚእየ: ኢየሱስ ክርስቶስ ጸግወኒ ስእለትየ።

ነግሥ
ሰላም ለልሳንከ መዝሙረ ቅዳሴ ዘነበልባል: ወለድምጸ ቃልከ ሐዋዝ ቀርነ መንግሥቱ ለቃል: ሞገሰ ክብሩ ሚካኤል ለተላፊኖስ ባዕል: አልቦ ዘይትማሰለከ በልማደ ምሕረት ወሣህል: እንበለ ባሕቲታ እኅትከ ማርያም ድንግል፡፡

ዚቅ
ተውህቦ ምሕረት ለሚካኤል: ወብሥራት ለገብርኤል: ወሀብተ ሰማያት ለማርያም ድንግል።

ዘጣዕሙ፦
ሰላም ለዝክረ ስምኪ ዘመንክር ጣእሙ: ለወልድኪ አምሳለ ደሙ: መሠረተ ሕይወት ማርያም ወጥንተ መድኃኒት ዘእምቀዲሙ:ኪያኪ ሠናይተ ዘፈጠረ ለቤዛ ዓለሙ:እግዚአብሔር ይትባረክ ወይትአኰት ስሙ፡፡

ዚቅ
ምንተ እንከ እብል በእንተ ማርያም
መሠረተ ጽድቅ ኀደረ ላዕሌሃ: ወአዘዘ ደመና በላዕሉ።

መልክአ ቂርቆስ
ሰላም ለዝክረ ስምከ ቂርቆስ ሕጻን: ዘፍካሬሁ ተብህለ ጽጌ ምዑዝ ዕፍራን: ለዝ ስምከ ነጋሢ ዘኢየዓርቆ ሥልጣን: ሶበ ይጼውዖ ልሳንየ ውስተ ገጸ ኲሉ መካን: ይደንገፅ ሞት ወይጒየይ ሰይጣን፡፡

ዚቅ
ኢየሉጣ ወለደት ነቅዓ ጽጌ ረዳ: ፀሐየ ጽድቅ የዓውዳ: መላእክት ይትዋነይዋ: ኢየሉጣ ምስለ ወልዳ እሳተ ገብሩ ሐመዳ: ሰአሉ ለነ አስተምሕሩ ለነ ጻድቃን: እስመ በጸሎተ ጻድቅ ትድኅን ወኢትማስን ሀገር።

ወረብ
"ኢየሉጣ ወለደት"/፪/ ነቅዓ ጽጌ ረዳ ወለደት/፪/
ፀሐየ ጽድቅ የዓውዳ ፀሐየ ጽድቅ/፪/

መልክዐ ቂርቆስ
ሰላም ለልሳንከ ለዐቃቤ ሥራይ በዕዱ: እንተ ተመትረ እምጒንዱ: ሕፃን ቂርቆስ ለጽሕርት ዘኢያፍርኀከ ነጐድጓዱ: ዮም ባርክ ማኅበረነ ለለ፩ዱ ፩ዱ: ከመ ባረኮ አብርሐም ለይስሐቅ ወልዱ።

ዚቅ
ሕፃን ወእሙ ክልኤሆሙ ፈጸሙ ገድሎሙ: ድምፃ ለጽሕርት ከመ ነጎድጓደ ክረምት: ኢፈርህዎ ለሞት ቅዱሳን ሰማዕት።

ወረብ
ሕፃን ወእሙ ክልኤሆሙ ፈጸሙ ገድሎሙ/፪/
ድምጻ "ለጽሕርት"/፪/ ከመ ነጎድጓደ ክረምት/፪/

መልክዐ ቂርቆስ
ሰላም ለእንግድዓከ ልቡና ዘከብዶ: ከመ እንግድዓሁ ለዕዝራ መጽሐፍ እንተ ይንዕዶ: ሕጻን ቂርቆስ ምስለ ወላዲትከ በተዋሕዶ: መኑ ከማከ ለእሳት አምሳለ አሣዕን ዘኬዶ: ወመኑ አምሳለ ማይ ዘአቊረረ ነዶ።

ዚቅ
ሃሌ ሃሌ ሉያ ይቤላ ሕጻን ለእሙ: ኢትፍርሂ እም ነበልባለ እሳት: ኢትፍርሂ እም ንፈጽም ገድለነ።

ወረብ
ይቤላ ሕፃን ለእሙ ኢትፍርሂ እም ነበልባለ እሳት/፪/
ንፈጽም ገድለነ ወስምዓነ ኢትፍርሂ እም/፪/

መልክዐ ቂርቆስ
ሰላም ለመልክዕከ በማየ ዮርዳኖስ ጥሙቅ: ወቅቡዕ በሜሮን ቅብዐ ሰላም ወእርቅ: በጸሎትከ ነጐድጓድ ወስዕለትከ መብረቅ: አቊረርከ ቂርቆስ ነበልባሎ ለእቶነ እሳት ምውቅ: ከመ ነደ እሳት አቊረሩ ሠለስቱ ደቂቅ።

ዚቅ
በጸሎቱ ለቅዱስ ቂርቆስ ወጽአ ማይ እምውስተ ጽሕርት: ወኮነ ጥምቀተ ለአግብርተ እግዚአብሔር: ጽዋዓ ሕይወት ወሀቦሙ: መገቦሙ ወመርሆሙ: እስመ ክርስቶስ ሀሎ ምስሌሆሙ፡፡

ወረብ
በጸሎቱ ለቅዱስ ቂርቆስ እምውስተ ጽሕርት ወጽአ ማይ እምውስተ ጽሕርት/፪/
ለአግብርተ እግዚአብሔር ኮነ ወኮነ ጥምቀተ/፪/

መልክዐ ቂርቆስ
ሰላም ለህላዌከ ማዕከለ ሰብአቱ ነገድ: እለ ሥዑላን በነድ: አስተምሕር ቂርቆስ ቅድመ መንበረ አብ ወወልድ: ኀበ ተሐንፀ መርጡልከ ወዘዚአከ ዐጸድ: ኢይምጻእ ለዓለም ዘይቀትል ብድብድ፡፡

ዚቅ
በዛቲ መካን ኢይምጻእ ሞተ ላሕም: ወኢብድብድ በሰብእ: ባርካ እግዚኦ ለዛቲ መካን: በዛቲ መካን ኢይኩን ሕፀተ ማይ: ወኢአባረ እክል: ባርካ እግዚኦ ለዛቲ መካን: ቂርቆስ ሕጻን አንጌቤናይ: ወልደ አንጌቤናይት፡፡

ወረብ
በዛቲ መካን ኢይኩን ኢይኩን  ሕፀተ /፪/
ባርካ ቂርቆስ ለዛቲ መካን ባርካ ለዛቲ መካን/፪/

መልክዐ ኢየሉጣ
ሰላም ለመልክአትኪ አርብዓ ወሠለስቱ: ዓዲ ሰላም ለጠብአያትኪ አርባዕቱ: ኢየሉጣ ቅድስት ለቂርቆስ ወላዲቱ: ሰአሊዮ በእንቲአየ ከመ አይጥፋዕ በከንቱ: ለእግዚአብሔር አምላከ ጽድቅ ዘብዙኅ ምሕረቱ።

ዚቅ
ሃሌ ሃሌ ሉያ ሃሌ ሉያ ሃሌ ሉያ ሰላማዊት: ሰላም ለኪ: ሰላመ ወልድኪ የሃሉ ላዕለ ኩልነ: ኢየሉጣ እምነ: ወእሙ ለቂርቆስ እግዚእነ: ሰአሊ ለነ አስተምሕሪ ለነ: ከመ ኢንቁም አንቀጸ፡፡

መልክዐ ገብርኤል
ሰላም ለልሳንከ ወለቃልከ ማኅተሙ: ለእስትንፋስከ ጠል ለእሳተ ባቢሎን አቊራሬ ፍሕሙ: ገብርኤል ዉኩል ለረድኤተ ጻድቃን ኲሎሙ: አንግፈኒ እምነበልባል ኢያንጥየኒ ሕማሙ: ከመ አንገፍኮሙ ቅድመ ለቂርቆስ ወእሙ።

ዚቅ
ዘረዳእኮሙ ለሰማዕት: ወበላሕኮሙ እምእሳት: አድኅነነ እግዚኦ ሃሌ ሉያ: እምዕለት እኪት።

ወረብ
ዘረዳእኮሙ ለሰማዕት ወባላሕኮሙ እምእሳት ሊቀ መላእክት/፪/
እግዚኦ አድኅነነ "ሃሌ ሉያ"/፪/ እም ዕለት እኪት/፪/

ምልጣን፦
ይቤላ ሕፃን ለእሙ: ኢትፍርሂ እም ነበልባለ እሳት: ዘአድኃኖሙ ለአናንያ ወአዛርያ ወሚሳኤል ውእቱ ያድኅነነ
አመላለስ:
ለአናንያ ወአዛርያ ወሚሳኤል/፪/
ውእቱ ያድኅነነ ወሚሳኤል ውእቱ ያድኅነነ/፪/

ወረብ
ይቤላ ሕፃን ለእሙ "ኢትፍርሂ እም"/፪/ ነበልባለ እሳት/፪/
ዘአድኃኖሙ "ለአናንያ"/፪/ ወአዛርያ ወሚሳኤል/፪/

እስመ ለዓለም
ይትባረክ እግዚአብሔር አምላከ አበዊነ: አምላኮሙ ለቂርቆስ ወእሙ: በብዝኃ ኃይሉ ወበጽንዓ ትዕግሥቱ: አርአየ ጸጋሁ ላዕለ ሕፃን: ሕፃን ዘኮና መርሐ ለእሙ ዘሠለስቱ ዓም: ኢፈርሐ ነበልባለ እሳት ዘይወጽእ እምአፈ ዕቶን: አርአየ ጸጋሁ ላዕለ ሕፃን: አኃዘ ለእሙ ዕዳ ዘየማን ወሰሀባ ቅድመ መኮንን: አርአየ ጸጋሁ ላዕለ ሕፃን: ወይቤላ ሕፃን ለእሙ ጥብዒኬ እም ወኢትናፍቂ: እምዝ ዳግመ አልቦቱ ኲነኔ: አርአየ ጸጋሁ ላዕለ ሕፃን ማ- አእኰትዎ ወሰብሕዎ: ወባረክዎ ለአብ፡፡

አመላለስ
አእኮትዎ ወሰብሕዎ/፪/
አእኮትዎ ወሰብሕዎ/፬/

ወረብ
ወይቤላ ሕፃን ለእሙ ጥብዒኬ እም ወኢትናፍቂ/፪/
እምዝ ዳግመ አልቦቱ ኲነኔ እምዝ ዳግመ/፪/

@meazahaymanot

Читать полностью…

መዓዛ ሃይማኖት በጎ አድራጎትና ጉዞ ማህበር

ከኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን
ቅዱስ ሲኖዶስ ጽ/ቤት የተሰጠ መግለጫ፤
*******

ሐምሌ ፲፯ ቀን ፳፻፲፭ ዓ/ም አዲስ አበባ
"""""""""""""""""""""""""""""""""""""""

  1. በክልል ትግራይ በተከሰተው ጦርነት ምክንያት በክልሉ ከሚገኙት አህጉረ ስብከት ጋር ተቋርጦ የነበረውን መዋቅራዊ ግንኙነት ችግር በውይይት እንዲፈታ ቅዱስ ሲኖዶስ ተደጋጋሚ የሰላም ጥሪና ልዑካኑን በአካል ልኮ ከፍተኛ ጥረት እያደረገ ባለበት ወቅት በክልሉ የሚገኙ ብፁዓን አባቶች ሕገ ቤተ ክርስቲያንንና ቀኖና ቤተ ክርስቲያንን በመጣስ ቅዱስ ፓትርያርኩ ሊቀ ጳጳስ ዘአክሱም ተብለው በሚጠሩበት በማዕከላዊ ትግራይ ዞን አክሱም ሀገረ ስብከት በርእሰ አድባራት ወገዳማት አክሱም ጽዮን ቤተ ክርስቲያን ሐምሌ 15 እና 16 ቀን 2015 ዓ.ም. በተከናወነ ሕገ ወጥ ሢመተ ኤጲስ ቆጶሳት መፈጸሙን በመገናኛ ብዙኃን ለማወቅ ችለናል፡፡ በመሆኑም በዚህ የዶግማና የቀኖና ጥሰት ተግባር የቅዱስ ሲኖዶስ ጽ/ቤት በእጅጉ አዝኗል፡፡ 

2. በመሆኑም የተከሰተው የዶግማ፣ የቀኖና እና አስተዳደራዊ ጥሰት አስመልክቶ ተወያይቶ ተገቢውን ለመወሰን ለሐምሌ 25 ቀን 2015 ዓ.ም. አስቸኳይ የቅዱስ ሲኖዶስ ምልዓተ ጉባኤ ጥሪ ተላልፏል፡፡

3. የስብሰባው ቀን ሊራዘም የቻለው በውጭው ክፍለ ዓለማት ያሉት ሊቃነ ጳጳሳት መገኘት ስላለባቸው የጉዞ ቀኑ እንዳያጥር እና በሀገር ውስጥ የሚገኙትም ሊቃነ ጳጳሳት ለቅዱስ ገብርኤል ዓመታዊ ክብረ በዓል ምክንያት ለአገልግሎት ወደ አህጉረ ስብከታቸው የሄዱ በመሆኑ ለመመለሻ የሚያስፈልገውን ጊዜ ታሳቢ በማድረግ ነው፡፡

4. በየደረጃ ያሉ የቅድስት ቤተ ክርስቲያናችን የሥራ ኃላፊዎች እና ሊቃውንተ ቤተ ክርስቲያን እንዲሁም ምዕመናን ከአሁን ቀደም በቤተ ክርስቲያናችን ላይ በደረሰው ፈተና በሐዘንና በጸሎት ከቤተ ክርስቲያናችን ጎን በመቆም ላሳያችሁት ጽናት እያመሰገንን አሁንም በደረሰው ፈተና እንዳሁን ቀደሙ ሁሉ በሐዘንና በጸሎት ከቤተ ክርስቲያናችን ጎን ጸንታችሁ እንድትቆሙ ጥሪያችንን እናስተላልፋለን፡፡

5. በመላው ዓለም የምትገኙ የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን እምነት ተከታዮች የቅዱስ ሲኖዶስ ምልዓተ ጉባኤ በጉዳዩ ላይ ተወያይቶ ተገቢውን ውሳኔ እስከሚሰጥ ድረስ በትግዕስት እንድትጠብቁ እናሳስባለን፡፡

6. ምንም እንኳን ለቅዱስ ሲኖዶስ አባላት በሙሉ ጥሪው በደብዳቤ የተላለፈ ቢሆንም የመልእክቱ በፍጥነት መድረስ ካለው ስጋት አንጻር የችግሩን ተደጋጋሚነትና አሳሳቢነት ከግምት ውስጥ በማስገባት በሀገር ውስጥም ሆነ በውጭው ክፍለ ዓለማት የምትገኙ ብፁዓን ሊቃነ ጳጳሳት የቅዱስ ሲኖዶስ አባላት በሙሉ እስከ ሐምሌ 24 ቀን 2015 ዓ.ም. ድረስ ተጠቃላችሁ ወደ ጽርሐ መንበረ ፓትርያርክ እንድትመጡ በጥብቅ እናሳስባለን፡፡


7. ሁሉም የቤተ ክርስቲያናችን ሚዲያዎችና ሌሎች መገናኛ ብዙኃን ይህን መልዕክት ለሁሉም ተደራሽ እንዲሆን መልእክቱን በማስተላለፍ ኃላፊነታችሁን እንድትወጡ በቤተ ክርስቲያናችን ስም እንጠይቃለን፡፡

ወስብሐት ለእግዚአብሔር
ሐምሌ 17 ቀን 2015 ዓ.ም.


ምንጭ : ሕዝብ ግንኙነት መምሪያ

Читать полностью…

መዓዛ ሃይማኖት በጎ አድራጎትና ጉዞ ማህበር

ምክረ አበው ዘቅዱስ ሳዊሮስ ዘአንጾኪያ

የምወዳችሁ ወንድሞቼ ሆይ ስለ አእምሮአችን ሕጸጽ ጸልዩልን፤ጌታ በፍጹም ቸርነቱ እስከ መጨረሻ እስትንፋስ ፍጻሜ ድረስ በቀናች ሃይማኖት ያጽናን ዘንድ ተስፋችን ይህ ብቻ ነው፤ለአብ ለወልድ ለመንፈስ ቅዱስ ለዘለዓለሙ በእውነት ክብር ምስጋና ይገባቸዋል  አሜን
    
መልካም ዕለተ ሰንበት

Читать полностью…

መዓዛ ሃይማኖት በጎ አድራጎትና ጉዞ ማህበር

"እናንተን  ንጹሐን  ቅዱስ ሲኖዶስን ተወቃሽ የሚያደርገው አንዳችም ነገር የለም"

"በትግራይና  በፌደራል  መንግሥት፣  በትግራይና  በአማራ  ክልል  ባለው  አለመግባባት   ችግሮችን  ለመፍታት  በምልዓተ  ጉባኤ   ቅዱስ  ሲኖዶስ  ፊት  እናንተም  ባላችሁበት ይህ  ችግር  በዚህ  ሊቀጥል  አይገባውም  ችግር  ከመፈጠሩ  በፊት  የሰላም  ኮሚቴ  ይቋቋም  ብሎ  ቅዱስ  ሲኖዶስ  ጮሗል?  አልጮህም?  እናንተስ  በዚያን  ጊዜ  ምን  ትሉ  ነበር? 

በመጨረሻም   ቅዱስ  ሲኖዶስ   ጉዳዩን  ተመልክቶ  ችግሩን  ለመፍታት በፌደራል  መንግሥት፣  በትግራይና  በአማራ   ክልል ያለው  ችግር  እንዲፈታ  እንደ  ጥንቱ    ታቦት  ይዘን፣  መስቀል  ይዘን፣ ሕዝባችንን  እናገናኝ ዝም  ብለን  ማየት  የለብንም  ብሎ  ቅዱስ  ሲኖዶስ  ሲጮህ  ምን  ነበር  ያላችሁት አባቶች?

ደም በሚፈስበት ቦታ ላይ ሄዳችሁ አስታርቁ ትግራይ ለምን ሰላም ሆነ ነው ወይ ይህንን የምትሉ አላላችሁንም?

ቤተክርስቲያን ዝም አለች አላችሁ፤ ምነው  ቤተክርስቲያን  ምንም  እንዳልተናገረች  ደግማችሁ  ደጋግማችሁ  ተናገራችሁ፡፡  ያውም  ከብፁዓን  አበው  ሊቃነ  ጳጳሳት ስሕተትን  ለማረም   ስሕተት  መደገም  የለበትም፡፡  ቅዱስ  ሲኖዶስ  ዛሬም  ጉዳዩን  አይቶ ችግሩን  ለመፍታት ይቅርታ  የሚለውን  ጥያቄም  አቅርቧል፡፡  ነገም  ያቀርባል  በሚገባው  በመልኩ  በአንጻሩ  ደግሞ  የሠራው  ያደረገው  ነገር ሊቀበር  አይገባውም ሊነገርለት  ይገባል፡፡ ስለዚህ  በዚህ ጥፋት ከሆነ እናንተም እኛም የጋራ ተወቃሾች እንሆናለን እንጂ እናንተን  ንጹሐን  ቅዱስ ሲኖዶስን ተወቃሽ የሚያደርገው አንዳችም ነገር የለም፡፡"

ብፁዕ አቡነ አብርሃም የጠቅላይ ቤተ ክህነት
ዋና ሥራ አስኪያጅና የባህር ዳር ሀገረ ስብከት ሊቀ ጳጳስ

Читать полностью…

መዓዛ ሃይማኖት በጎ አድራጎትና ጉዞ ማህበር

ቅዱስ አብሮኮሮንዮስ ሰማዕት✝ ††† ቅዱሱ ተወልዶ ያደገው በአንጾኪያ (ሶርያ) በ3ኛው መቶ ክ/ዘመን አካባቢ ነው:: አባቱ ደግ ክርስቲያን የነበረ ሲሆን ስሙ #ክርስቶፎሮስ ይባላል:: "ለባሴ ክርስቶስ" እንደ ማለት ነው:: እናቱ ግን #ቴዎዳስያ የምትባል አረማዊት ነበረች:: ምንም እንኩዋ አባቱ ክርስቲያን ቢሆን እናቱ ኃይለኛ የቤተ መንግስት ሰው ስለነበረች በልጅነቱ አብሮኮሮንዮስ ክርስትናን ሊማር አልቻለም:: የልጁን አረማዊ መሆን ያልወደደ አባት አማራጩ አንድ ብቻ ነበር:: እሱም ወደ ጌታ መለመን ነበር:: በእንዲሕ ያለ ግብር ዘመናት ጐርፈው አብሮኮሮንዮስ ክርስቶስን ሳያውቅ 20 ዓመት ሆነው:: እናቱ ወስዳ: አሰልጥና ለጣዖት አምላኪ ንጉሥ ሰጠችው:: ንጉሡም የጦር አለቃ አድርጐ ሾመውና አንድ ትዕዛዝ ሰጠው:: "ክርስቲያኖችን ሁሉ ባገኘህበት ቦታ ጨፍጭፍ:: ቤታቸውንም አቃጥል::" #አብሮኮሮንዮስ ሊፈጽም ሠራዊት አስከትሎ ሲወጣ ግን የአባቱ የ20 ዘመናት ለቅሶና ጸሎት ፍሬ አፈራ:: ገና መንገድ ላይ ሳለ ለስም አጠራሩ ጌትነት ይሁንና መድኃኒታችን የሱስ_ክርስቶስ ድምጹን ከሰማይ ላከለት:: "ወደ እውነተኛ መንገድ ተመለስ:: ካልሆነ ግን ሾተሉን ብትረግጥ ላንተ ይብስብሃል" አለው:: አብሮኮሮንዮስም እየተንቀጠቀጠ "አቤቱ አንተ ማነህ?" አለው:: ጌታም "ኢየሱስ ክርስቶስ ነኝ" ሲል መለሰለት:: ዳግመኛም "ምልክት ስጠኝ" ቢለው የብርሃን መስቀል በሰማይ ላይ ገለጠለት:: ቅዱስ አብሮኮሮንዮስ ጊዜ አላጠፋም:: ሠራዊቱን ይዞ ወደ ንጉሡ ከተማ ተመልሶ ንጉሡን በድፍረት አለው:- "እኔ ክርስቲያን ነኝ:: ክርስቶስንም አመልካለሁ::" ካነጋገሩ የተነሳ አባቱን ደስ ሲለው ንጉሡና እናቱ ግን ደነገጡ:: ንጉሡ ሊያስፈራራው ሞከረ:: ግን አልተሳካለትም:: ከዚያማ ያሰቃየው ገባ:: አንድ ቀን አካሉ እስኪቆራረጥ ገረፉት:: በእሳትም አቃጠሉት:: ሞተ ብለው አስበው ነበር:: ወደ እርሱ ሲመለሱ ግን ጌታችን አድኖታልና የሰንበር ምልክት እንኩዋ በአካሉ ላይ አልተገኘም:: እናቱ ቴዎዳስያ ከዚህ በላይ ምልክትን አልፈለገችም:: በደቂቃዎች ልዩነት እርሷም ወደ ክርስትና ተመለሰች:: ልጇንም ቀድማ ሐምሌ 6 ቀን ሰማዕት ሆነች:: ቅዱስ አብሮኮርዮስን ግን ለበርካታ ጊዜያት አሰቃይተው ከክርስቶስ ፍቅር ሊለዩት ባለመቻላቸው በዚህች ቀን ገድለውታል:: አባት: እናትና ልጅ (ክርስቶፎሮስ: ቴዎዳስያና አብሮኮሮንዮስ) ለሰማያዊ ርስት በቅተዋል:: አባት ይሏቹሃል እንዲህ ነው!

Читать полностью…

መዓዛ ሃይማኖት በጎ አድራጎትና ጉዞ ማህበር

ምክረ አበው ዘቅዱስ ጎርጎርዮስ ዘኑሲስ

=>  ሰው በመንፈሳዊ ሕይወቱ የራሱን ፍቃድ እየተወ በመጣ መጠን ወደ ስኬት ይወጣል። ነገር ግን የራሱን ፍቃድ እየፈፀመ በሔደ ቁጥር በራሱ ላይ ጉዳት ያመጣል።

=>  ንጹሕ ልብ የእግዚአብሔር እውነተኛ መልክ የታተመበት ነው።

=> እግዚአብሔር ማየት ማለት እንደማይታይ /በባሕርይ መለኮቱ/ ማወቅ ማለት ነው። እግዚአብሔርን ማወቅ ማለት ባሕርይው  በሙላ እንደማይታወቅ ማወቅ ማለት ነው።

መልካም ቀን

Читать полностью…

መዓዛ ሃይማኖት በጎ አድራጎትና ጉዞ ማህበር

አንድ አምላክ በሚሆን በአብ በወልድ በመንፈስ ቅዱስ ስም አሜን
ሐምሌ 13-ነቢያት እየተገለጡለት ትንቢታቸውን የተረጎሙለትና የእጆቹም ጣቶች እንደፋና የሚያበሩለት የከበረ አባ ብስንድዮስ ዕረፍቱ ነው፡፡
+ ዳግመኛም በዚኽች ዕለት ሰማዕቱ ቅዱስ አሞን ምስክር ሆኖ ዐረፈ፡፡
አባ ብስንድዮስ፡- ቅዱሳት መጻሕፍትን በሙሉ ጠንቅቆ ያጠና በተጋድሎውም እጅግ የታወቀ መነኩሴ ነው፡፡ የነቢያትን መጻሕፍት ለጸሎት አንብቦ እስኪጨርስ ድረስ ትንቢቱን የሚያነብለት ነቢይ ይገለጥለትና የተሰወረውን ምሥጢር ይገልጥለት ነበር፡፡ የአባ ብስንድዮስ የእጆቹም ጣቶች እንደፋና ያበሩ ነበር፡፡ እግዚአብሔር በአባ ብስንድዮስ እጆች ድንቅ ድንቅ የሆኑ ተአምራትን አደረገ፡፡
አባ ብስንድዮስ በዕድሜው ዘመን ሁሉ የሴት ፊት አላየም፡፡ ከዕለታትም በአንደኛው ቀን በሆዷ ውስጥ ታላቅ ደዌ የነበረባት አንዲት ሴት ነበረች፡፡ እርሷም ከአባ ብስንድዮስ በዓት በር ላይ ጠብቃ በድንገት አገኘችው፡፡ አባ ብስንድዮስም ባያት ጊዜ ትቷት ሮጠ፡፡ ሴቲቱ ብትከተለውም እንዳልደረሰችበት ባየች ጊዜ እግሩ የረገጣትን አንዲት አፍኝ አፈር ዘግና በእምነት ብትበላ ከደዌዋ ፈጥና ዳነች፡፡
በአንዲት ዕለትም ለአባ ብስንድዮስ ሦስት ሰዎች ተገለጡለትና ‹‹የእግዚአብሔርን ቤተ ክርስቲያን ትመግባት አለህ›› ብለው መክፈቻ ቁልፍን ሰጡት፡፡ ከዚህም በኋላ አባ ብስንድዮስ ቅፍፅ በሚባል አገር ላይ ኤጲስቆጶስነት ተሾመ፡፡ የቁርባን ቅዳሴ በሚቀድስ ጊዜ ጌታችንን እጆቹ በመሠዊያው ላይ ሆነው ይመለከተው ነበር፡፡ መላእክቶቹም በዙሪያው ቆመው ያያቸው ነበር፡፡ በሌላ ጊዜም አንድ ላይ ቄስ እየቀደሰ ሳለ በመሠዊያው ፊት ምራቁን ተፋ፡፡ ቅዳሴውም በተፈጸመ ጊዜ አባ ብስንድዮስ ያንን ቄስ ‹‹… የተፋኸው ምራቅ በመሠዊያው ዙሪያ በቆሙ በኪሩቤል ክንፎች ላይ እንደወደቀ አታውቅምን/›› ብሎ ገሠጸው፡፡ ያን ጊዜ ያንን ቄስ መንቀጥቀጥ ያዘው ተሸክመው ወደ ቤቱ ወሰዱትና ታሞ ሞተ።ከዚህም በኋላ አባ ብስንድዮስ የዕረፍቱን ጊዜ ዐውቆ ሕዝቡን ጠርቶ በቀናች ሃይማኖት እስከመጨረሻ እንዲጸኑ ከመከራቸው በኋላ ነፍሱን ለእግዚአብሔር ሰጠ፡፡ የአባ ብስንድዮስ ረድኤት በረከቱ ይደርብን በጸሎቱ ይማረን!
+ + +
ሰማዕቱ ቅዱስ አሞን፡- ይኸውም ቅዱስ ከደቡባዊ ግብጽ ከቡና አውራጃ የተገኘ ሰማዕት ነው፡፡ ሊቀ መላእክት ቅዱስ ሚካኤል ተገለጠለትና በጌታችን ስም ሰማዕት ይሆን ዘንድ እንዳለው አስረዳው፡፡ ቅዱስ አሞንም ወደ እንዴናው ገዥ በመሄድ በከሃዲው መኮንን በአውግስጦስ ፊት ቀርቦ በጌታችን ታመነ፡፡ መኮንኑም በመንኮራኩር ውስጥ ከቶ አሠቃየው፡፡ በእሳት ላይ በመጣል በእሳት በጋለ ብረት አስደበደበው፡፡ በውሽባ ቤት እሳት ማንደጃ ውስጥ በመክተት በእሳት አቃጠሉት፡፡ የእራሱንም ቆዳ ገፈው በራሱ ላይ የእሳት ፍሕም በማኖር በእጅጉ አሠቃዩት፡፡ እግዚአብሔርም ከመከራው ሁሉ አስታግሶት ያለ ምንም ጉዳት ጤነኛ አድርጎ አስነሣው፡፡ ጌታችንም በጎልማሳ አምሳል በብርሃን ሠረገላ ሆኖ ተገለጠለትና ‹‹ወዳጄ አሞን ሆይ እኔ ሁልጊዜ ከአንተ ጋር እኖራለሁ፣ ስምህን የሚጠራውን መታሰቢያህን የሚያደርገውን ገድልህን የሚጽፈውን ሁሉ እኔ በመንግሥቴ ውስጥ አስበዋለሁ›› ብሎ ሰላምታ ሰጥቶት በክብር ዐረገ፡፡
ቅዱስ አሞንም በሥጋው ሳለ ብዙ ታላላቅ ተአምራትን አደረገ፡፡ ብዙዎችንም ጌታችንን ወደማመን መለሳቸው፡፡ መኮንኑንም እርሱን ማሠቃየት በሰለቸው ጊዜ የቅዱስ አሞንን ራስ በሰይፍ ይቆርጡት ዘንድ አዘዘ፡፡ ቅዱሱም ሰማዕትነቱን በድል ፈጽሞ የክብርን አክሊል ተቀዳጀ፡፡ ቅዱስ ዮልዮስም በዚያ ነበረና የቅዱስ አሞንን ሥጋ ወስዶ በመልካም ልብስ ገንዞ ከሁለት አገልጋዮቹ ጋር ወደ አገሩ ላከው፡፡ የቅዱሱም ሥጋ በላይኛው ግብጽ አሁንም ድረስ ብዙ አስደናቂ ተአምራትን እየሠራ አለ፡፡ የሰማዕቱ የቅዱስ አሞን ረድኤት በረከቱ ይደርብን በጸሎቱ ይማረን!
ምንጭ፦ ከገድላት አንደበትና ስንክሳር ዘወርኀ ሐምሌ
✞ ✞ ✞

Читать полностью…

መዓዛ ሃይማኖት በጎ አድራጎትና ጉዞ ማህበር

ስብሐት ለአብ ለአኃዜ ኲሉ ዓለም ስብሐት ለወልድ ለገባሬ ኩሉ ዓለም (፪)
ስብሐት ለመንፈስ ቅዱስ ለዘያርኁ ክረምተ በበዓመት (፪)

Читать полностью…

መዓዛ ሃይማኖት በጎ አድራጎትና ጉዞ ማህበር

ስንክሳር ዘወርሃ ሐምሌ አሥራ ሦስት(፲፫)
/channel/meazahaymanot

Читать полностью…

መዓዛ ሃይማኖት በጎ አድራጎትና ጉዞ ማህበር

ስንክሳር ዘወርሃ ሐምሌ አሥራ ሁለት (፲፪)
/channel/meazahaymanot

Читать полностью…

መዓዛ ሃይማኖት በጎ አድራጎትና ጉዞ ማህበር

ምክረ አበው ዘብፁዕ አቡነ ጎርጎርዮስ

"ልጆቻችሁን ይዛችሁ ወደ ቤተክርስቲያን ኑ! ብቻችሁን አትምጡ፡፡ ብቻችሁን ከመጣችሁ ወደ ሌላ ይሔዳሉ እናንተ እዚህ መጥታችሁ የምትሰሩትን አያውቅም ፡፡ ወዴት እንደሔዳችሁ አያውቅም፡፡ ወራሾቻችሁ አይሆንም ፡፡ ስለዚህም ወደ ቤተክርስቲያን ስትመጡ ልጆቻችሁን ይዛችሁ ኑ፡፡ አሳዩአቸው ሥዕሉን ይሳሙ ቅዳሴ ጠበል ይጠጡ በእምነት አሻሹአቸው መስቀል እንድስሙ አስተማሯቸው ዕጣኑን ያሽትቱ ሥጋ ወደሙን ይቀበሉ ቃጭሉን ይስሙ ደውል ሲደውል ይስሙ ቄሳቸው ማን እንደሆነ ቤተክርስቲያናቸው ምን እንደሆነች በውስጧ ምን ምን እንደሚሰራ ያጥኑ ይማሩ ወደ ሰንበቴው እጃችሁን ይዘው ይከተሉ ወደ ማህበር ስትሔዱም  ይዛችኋቸው ሂዱ ቆሎውን ዳቦውን ተሸክመው ወደ ሰንበቴው ይምጡ ይማሩ እነርሱም ነገ ይሄን እንዲወርሱ የነገ ባለአደራዎች መሆናቸውን እንዲያውቁ ።"

            መልካም ቀን

Читать полностью…

መዓዛ ሃይማኖት በጎ አድራጎትና ጉዞ ማህበር

የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ
ቤተክርስቲያን ፱ ኤጲስ ቆጶሳትን ሾመች።
**

ምሌ ፱ ቀን ፳፻፲፭ ዓ/ም አዲስ አበባ
""""""""""""""""""""""""""""""""""""

ሐምሌ ፳፱ ቀን ፳፻፲፭ ዓ/ም በኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተክርስቲያን ቅዱስ ሲኖዶስ ምልዓተ ጉባኤ ለዘጠኝ አህጉረ ስብከት የተመረጡት ፱ ቆሞሳት ዛሬ ሐምሌ ፱ ቀን ፳፻፲፭ ዓ/ም በመንበረ ፓትርያርክ ቅድስተ ቅዱሳን ማርያም ገዳም በተፈጸመ ሥርዓት በብፁዕ ወቅዱስ አቡነ ማትያስ ፓትርያርክ ርእሰ ሊቃነ ጳጳሳት ዘኢትዮጵያ ሊቀ ጳጳስ ዘአክሱም ወእጨጌ ዘመንበረ ተክለሃይማኖት እና በብፁዓን አበው ሊቃነ ጳጳሳት አንብሮተ እድ በኤጲስ ቆጶስነት ተሹመዋል።

ከሌሊቱ ፱ ስዓት ጀምሮ በተከናወነው ሥርዓተ ሢመት ላይ የተለያዩ የሃይማኖት መሪዎች።፣ ግብዣ የተደረገላቸው የክብር እንግዶች፣ ከየአህጉረ ስብከቱ የመጡ ሊቃውንት፣ የሥራ ኃላፊዎች እና ምእመናን ተገኝተዋል።

በዚህም መሠረት የሚከተሉት አባቶች በቅድስት ቤተክርስቲያን የተሰጣቸውን ሥያሜ ይዘው ለተጠቀሱት አህጉረ ስብከት ተመድበዋል።

፩- ቆሞስ አባ ክንፈገብርኤል ተክለማርያም ብፁዕ አቡነ ገሪማ ተብለው ተሠይመው ጌዴኦ አማሮና ቡርጂ ሀገረ ስብከት

፪- ቆሞስ አባ ሣህለማርያም ቶላ ብፁዕ አቡነ ገብርኤል ተብለው ተሠይመው ለምዕራብ ሸዋ ሀገረ ስብከት

፫- ቆሞስ አባ ስብሐትለአብ ኃይለማርያም ብፁዕ አቡነ ጢሞቴዎስ ተብለው ተሠይመው ዳውሮና ኮንታ ሀገረ ስብከት

፬- ቆሞስ አባ አምደሚካኤል ኃይሌ ብፁዕ አቡነ ኤልሳዕ ተብለው ተሠይመው ምሥራቅ ወለጋ ሀገረ ስብከት

፭- ቆሞስ አባ ኃይለማርያም ጌታቸው ብፁዕ አቡነ በርተሎሜዎስም ተብለው ተሠይመው በድሬዳዋ ሀገረ ስብከት

፮- ቆሞስ አባ ጥላሁን ወርቁ ብፁዕ አቡነ ኤፍሬም ተብለው ተሠይመው በቡኖ በደሌ ሀገረ ስብከት

፯- ቆሞስ አባ ዘተክለሃይማኖት ገብሬ ብፁዕ አቡነ ኤጲፋንዮስ ተብለው ተሠይመው በሆሮ ጉድሩ ሀገረ ስብከት

፰- ቆሞስ አባ እስጢፋኖስ ገብሬ ብፁዕ አቡነ ዳንኤል ተብለው ተሠይመው በምዕራብ ወለጋ ሀገረ ስብከት

፱- ቆሞስ አባ ወልደገብርኤል አበበ ብፁዕ አቡነ ኒቆዲሞስ ተብለው ተሠይመው በምሥራቅ ሐረርጌ ሀገረ ስብከት ተመድበዋል።

ምንጭ: ኢቲ አርት ሚዲያ

Читать полностью…
Subscribe to a channel