meazahaymanot | Unsorted

Telegram-канал meazahaymanot - መዓዛ ሃይማኖት በጎ አድራጎትና ጉዞ ማህበር

4288

"ውድስት አንቲ በአፈ ነቢያት ወስብሕት በሐዋርያት አክሊለ በረከቱ ለያዕቆብ ወትምክህተ ቤቱ ለእስራኤል፡፡" "በነቢያት በሐዋርያት አንደበት የተመሰገንሽ የያዕቆብ የበረከቱ ዘውድ የእስራኤል ወገን መመኪያ አንቺ ነሽ"                  መጽሐፈ ሰዓታት የፌስቡክ ፔጃችን www.fb.me/meazhaimanot ይቀላቀሉን

Subscribe to a channel

መዓዛ ሃይማኖት በጎ አድራጎትና ጉዞ ማህበር

ሰው ብቻ አትሁን ድንቅ ስብከት ከመጋቤ ሐዲስ እሸቱ አለማዮ መከታተል ይፈልጋሉ ❓

Читать полностью…

መዓዛ ሃይማኖት በጎ አድራጎትና ጉዞ ማህበር

ስንክሳር ዘወርሃ ሐምሌ ሃያ ዘጠኝ(፳፱)
/channel/meazahaymanot

Читать полностью…

መዓዛ ሃይማኖት በጎ አድራጎትና ጉዞ ማህበር

" በስመ አብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ አሐዱ አምላክ አሜን "
      ●በመላው አለም ላይ የምትገኙ ውድ ኦርቶዶክሳውያን እህት ወንድሞቼ እንደ አላችሁበት ሰአት አቆጣጠሩ እንደምን አደምን አመሻችሁ እንደምን ዋላችሁ እንደምን ሰነበታችሁ 🙏

      የሀምሌ ወር በረከት ስራችንን ደብረ ብርሀን መጠለያ ካምፕ ለሚገኙት ወገኖቻችን አልባሳትን ጫማዎችን ንፅህና መጠበቂያዎችን አሰባስበን ሀምሌ 26/2015 እሮብ ቀን ሄደን ለወገኖቻችን አድለን ሰተናል ። በአሁን ነሀሴ ወር ደግሞ በወላይታ ሀገረ ስብከት ለሚገኙ ለ 40 ለገጠር ቤተ ክርስቲያኖች ማስቀደሻ እጥረት ላለባቸው ጧፍ፣ ዘቢብ ፣ እጣን ለማድረግ ዝግጅታችንን ዛሬ ጀምረናል ።

1, አንድ እስር ጧፍ = 800 ብር
2, አንድ ኪሎ እጣን = 500 ብር
3, አንድ ኪሎ ዘቢብ = 500 ብር

● ለአንድ ቤተ ክርስቲያን ለ1 ወር የሚያስፈልገው ወጪ 1,800 ብር ነው ።

ለ 40 ቤተ ክርስቲያኖች ከሆነ የሚያስፈልገው ገንዘብ መጠን 72,000 ብር ነው ። ሁላችንም በምንችለው አቅም የበኩላችንን እናድርግ

ኢትዮጵያ ንግድ ባንክ አካውንት ቁጥር
1000441182345
(ማህበረ ኤዶምያስ) ደረሰኙን በውስጥ መስመር  ወይም ግሩፕ ላይ ይላኩልን ።

➣ አስተባባሪ ማኅበረ ኤዶምያስ

Читать полностью…

መዓዛ ሃይማኖት በጎ አድራጎትና ጉዞ ማህበር

ምክረ አበው ዘቅዱስ ኤፍሬም

በወንድሙ ውድቀት የሚደሰት ሰው ተመሳሳይ ውድቀት ይጠብቀዋል፡፡


መልካም ቀን

Читать полностью…

መዓዛ ሃይማኖት በጎ አድራጎትና ጉዞ ማህበር

❤መድኃኔዓለም የለም የሚሳነው❤

መድኃኔዓለም የለም የሚሳነው
አማኑኤል የለም የሚሳነው
እርሱ ቃል ሲናገር ተራራው ሜዳ ነው
መድኃኔዓለም የለም የሚሳነው
+++++
አላስብም አልፈዋለሁ ብዬ
ጉንጭ አልፎ ትራሴን እያጠበ እንባዬን
እየተፈጸመ ኃይሉ በድካሜ
ማእበሉን አለፍኩኝ ቀለለልኝ ሸክሜ
++++++
የቤቴ እራስ ነው የእቅዴ መሪ
በክፉም በደጉም ነፍሴን አስተማሪ
ፈጥሮ የማይረሳኝ ቤዛዬ ደረሰ
ቤቴን ደስታ ሞላው እንባዬ ታበሰ
+++++
ትናንት ባዶ ነበር የለኝ የሚሰፈር
አንዳች አልነበረኝ የሚታይ የሚቆጠር
ከርሱ የተነሳ ዛሬ ግን ሙሉ ነኝ
ክብር ለእርሱ ይሁን አለ የማይተወኝ
+++++
እየከለከለ ለእኔ የማየጠቀመኝን
በጊዜ እየሰጠ ደግሞ የሚረባኝን
ሁሉ በእርሱ ሆኗል አልሆነም ያለ እርሱ
ውዳሴ ምስጋና ይድረስ ለንጉሱ
+++++
ውድ የተዋህዶ ልጆች እንኳን. ለቸሩ መድኃኒዓለም ወርኃዊ ክብረ በዓል በሰላም አደረሳችሁ አደረሰን ❤ #27

👉join *@meazahaymanot

Читать полностью…

መዓዛ ሃይማኖት በጎ አድራጎትና ጉዞ ማህበር

ስንክሳር ዘወርሃ ሐምሌ ሃያ ሰባት(፳፯)
/channel/meazahaymanot

Читать полностью…

መዓዛ ሃይማኖት በጎ አድራጎትና ጉዞ ማህበር

ምክረ አበው ወብፁዕ አቡነ እንድርያስ

እግዚአብሔር ለሴሰኝነትና ለአመጽ ዕድሜ አይሰጥም፣ ለንስሐ ግን ሁሌም እንደታገሠ ነው

መልካም ቀን

Читать полностью…

መዓዛ ሃይማኖት በጎ አድራጎትና ጉዞ ማህበር

💎በማርያም JOIN በማለት ይህን ቻናል ተቀላቀሉ 💎

Читать полностью…

መዓዛ ሃይማኖት በጎ አድራጎትና ጉዞ ማህበር

🛑መምህር እዮብ ይመኑ ..... የሚመጣው ዘመን የማን ነው ያስፈራል !!!

👉#share እና #join ያድርጉ ያስደርጉ
👉@meazahaymanot

Читать полностью…

መዓዛ ሃይማኖት በጎ አድራጎትና ጉዞ ማህበር

ስንክሳር ዘወርሃ ሐምሌ ሃያ አምስት(፳፭)
/channel/meazahaymanot

Читать полностью…

መዓዛ ሃይማኖት በጎ አድራጎትና ጉዞ ማህበር

ዝክረ አባ ኖብ

ኖብ ማለት ጽሩይ ወርቅ ማለት ነው። ሀገራቸው ደቡብ ግብጽ ንሂሳ ነው። በዘመኑ ዲዮቅልጥያኖስ ዓለውያን አቢያተ ክርስቲያናትን  ሲያፈርሱ የምእመናን  ደማቸውን ሲያፈሱ በመንፈሳዊ ቅናት ተነሳስተው ለመመስከር  ወደ ገምኑዲ ሄዱ የጣዖትን ከንቱነት  የእግዚአብሔርን አምላክነት ሲመስክሩ መስፍነ ብሔሩ ሉክዮስ ፈጣሪህን ክደህ ለጣዖት አልሰግድም አሉ።በሰይፍ እቀጣሃለሁ አላቸው ከዚህ ሁሉ አምላክ  እንደሚያድነኝ አምናለሁ።አሉት ያገኛቸው መርከብ ቢሳፈር ነበርና በመርከብ ምሶሶ ቁልቁል አሰቅሎ ሥጋቸው እስኪተፈተፍ ድረስ ድረስ አስገረፋቸው።
   ከዚህ በኋላ ብላቴኖቹ ዓይናቸው ታውሯል። እሳቸው ግን የታዘዘ መልአክ ፈውሶ ከስቅላት አውርዷቸዋል።ምድረ አትሪክ ሲደርሱ ወደ ጌታ ሲያመለክቱ ብላቴናዎቹ ዓይኖቻቸው በርቶላቸዋል።በአምላካቸው አምነው አንገታቸውን ለሰይፍ ሰጥተው በሰማዕትነት አርፈዋል። አባ ኖብን ግን ሥቃዩ ይጽናበት ብሎ በብረት አልጋ በብረት ችንካር ቸንክሮ እሳት አስነደደባቸው መልአኩ መጥቶ ፈወሳቸው።የተቀበሉት መከራ ይህ ብቻ አይደለም ። ዓይን ከማየት ጆሮ ከማስማት እንዳያቋርጥ እሳቸውም ስመ እግዚአብሔር ጠርተው አምላክነቱን መስክረው ከመሠቃየት ያረፉበት ጊዜ የለም። ጊዜ ዕረፍታቸው ሲደርስ ጌታ ቃልኪዳናቸው የተማፀነውን ሁሉ እሳቸው ከገቡበት መካነ ዕረፍት  እንዲያገባላቸው ተስፋቸውን ነግሯቸው አንገታቸውን ለሰይፍ ሰጥተው በሰማዕትነት ዐርፈዋል።በዚህ የሚቆጠሩ አማንያንም አሠራቸውን ተከትለው አንገታቸውን ለሰይፍ ሰጥተው በሰማዕትነት ዐርፈዋል።

* የነበሩት በ4ኛው ም/ዓመት ድ/ል/ክ ሲሆን በሀገራችን ቡልጋ ውስጥ ኢቲሳ አካባቢ  በስማቸው የታነጸ ቤተክርስቲያን አለ።

@meazahaymanot

Читать полностью…

መዓዛ ሃይማኖት በጎ አድራጎትና ጉዞ ማህበር

ስንክሳር ዘወርሃ ሐምሌ ሃያ አራት(፳፬)
/channel/meazahaymanot

Читать полностью…

መዓዛ ሃይማኖት በጎ አድራጎትና ጉዞ ማህበር

ስንክሳር ዘወርሃ ሐምሌ ሃያ ሦስት(፳፫)
/channel/meazahaymanot

Читать полностью…

መዓዛ ሃይማኖት በጎ አድራጎትና ጉዞ ማህበር

•          ብጹዕ አቡነ ጎርጎርዮስ ካልዕ በሐምሌ 9)፸1 ዓ.ም. ዝዋይ ሲመጡ በመጀመሪያ ያገኙትና ብዙ የረዷቸው አቶ ተረፈ ነበሩ፡፡
•          ለልማት የተሰባሰቡ ባሕታውያን በሊቀ ጳጳሱ ቤት ባሉ መኖሪያ ክፍሎች ተቀምጠው ነበር፡፡ ወደ ዝዋይና አጎራባች ከተሞች በመሄድ የተለያዩ ነገሮችን ይፈጽሙ ነበር፡፡ የልማቱ ሥራ ፈጽሞ አልተሳካም ነበር፡፡ ብጹዕ አቡነ ጎርጎርዮስ ካልዕ በዝዋይ ካህናት ማሠልጠኛ የነበሩትን ባሕታውያን መስመር ለማስያዝ ባደረጉት ጥረት ከፍተኛ ተቃውሞ ገጠሟቸዋል፡፡
•          ብጹዕ አቡነ ጎርጎርዮስ ካልዕ ወደ ማሠልጠኛው ሲገቡ የተማሪዎች ማደሪያ የሌሊት ወፍ አያስገባም ነበር፡፡ ብጹዕነታቸው ያለምንም በጀት ከገዳማት፣ ከአድባራት፣ ከመንገድ የወደቁትን  እንዲሁም ከአካባቢው ሕጻናትን እያመጡ ማስተማር፣ ማሳደግ ጀመሩ፡፡ መምህራን በመቅጠር የአካባቢውን ሰዎችንም መሠረተ ትምህርት ያስተምሩ ነበር፡፡ በማሠልጠኛው ቤተ ክርስቲያን ባለመኖሩ ጸሎት የሚካሄደው በዛፍ ጥላ ሥር ነበር፡፡ ለቅዳሴ የሚሄዱት ከዝዋይ ከተማ ሰባት ኪ.ሜ. ወደ ምትርቀው አዳሚ ቱሉ ደብረ ጸሐይ ቅድስት ማርያም ነበር፡፡
•          በ9)፸፬ ዓ.ም. ቤተ ክርስቲያን፣ የእንግዶች ማረፊያ ቤት፣ ክርስትና ቤት፣ ወፍጮ ቤት በማሠራት በገዳም ሥርዓት እንዲተዳደር አድርገዋል፡፡
•          ለትምህርት ወደ ዝዋይ የሚመጣ በበጀት እጥረት አይመለስም ነበር፡፡ በክረምት መኝታ ቤት ሞልቶ በድንኳን እያደሩ የሚማሩ ተማሪዎች ነበሩ፡፡ ብዙዎች ከዝዋይ መለየት አቅቷቸው በዚያው ቀርተዋል፡፡ ዝዋይ ለሸዋ፣ ለአርሲና ለሐረር ካህናት ማሠልጠኛ ማዕከል ሆና ነበር፡፡ ዝዋይ በብጹዕ አቡነ ጎርጎርዮስ ጥረት ተለውጣ ነበር፡፡
•           ንቡረ ዕድ ክፍለ ዮሐንስ መኮንን ቤቴንና ትዳሬን ትቼ ለአራት ዓመት ከስድስት ወር የመነንኩት የብጹዕነታቸውን ትምህርት ፈልጌ ነው፡፡ ዘወትር በፍቅርና በስስት እከተላቸው ነበር፡፡ ገና ለገና ከንፈራቸው ሲንቀሳቀስ ልቤ በሐሴት ይሞላል፡፡ ----    ከዕለት ዕለት እየተደነቅኩ አብሬያቸው እኖር ነበር፡፡ በማለት ይናገራሉ፡፡
•          ብጹዕ አቡነ ጎርጎርዮስ ካልዕ የወንጌል አድማስ ዝዋይ አይደለም፡፡ ገና የምናዳርሰው ብዙ ሥፍራ አለ፡፡ በማለት በማሠልጠኛው ክፍለ ጊዜ ተመድቦላቸው በቀኝ እጃቸው በትረ ሙሴ፣ በግራ እጃቸው መስቀልና የሚያስተምሩበትን ጥራዝ ታቅፈው ማንንም ሳያስከትሉ ክፍል ገብተው ያስተምሩ ነበር፡፡ ለትምህርትና ለሥራ ከፍተኛ ትኩረት ስለነበራቸው ብዙ ጊዜ ለሰዎች ቀጠሮ አይሰጡም ነበር፡፡

ዝዋይ በሦስቱ ሕግጋት
ብጹዕ አቡነ ጎርጎርዮስ ካልዕ በዝዋይ ካህናት ማሠልጠኛ ሦስት ሕግጋት አውጥተው ነበር፡፡
ሀ. በሥራ  ሰዓት
•   ፈረንጆች ገንዘብ የሚሰጡን ራሳችንን እንድንችል ሊያስተምሩን እንጂ ሊጦሩን ፈልገው አይደለም፡፡  በማለት የማሰልጠኛው አገልግሎት ዘላቂነት እንዲኖረው ለደቀ መዛሙርቱ የአትክልት ኩትኳቶና ሌሎች ተግባራትን ያስተምሩ ነበር፡፡  በማሠልጠኛው የተለያየ አትክልት፣ አዝርእትና ፍራፍሬ አልምተዋል፡፡
ለ. በትምህርት ሰዓት
•          ለካህናት ማሠልጠኛው ሥርዓተ ትምህርት ቀርጸው፣ የመማሪያና ማስተማሪያ ጥራዝ አዘጋጅተው ያስተምሩ ነበር፡፡
•          በ1980 ዓ.ም. 12 የዩኒቨርስቲ ተማሪዎችን ተቀብለው በክረምት መርሐ ግብር ማስተማር ጀመሩ፡፡

ሐ. በጸሎት ሰዓት
•   በዚህ በረሃ የወድቅኩት የማንንም ዶክተር ተስፋ አድርጌ ሳይሆን እመቤቴን ተስፋ አድርጌ ነው፡፡ ወባ መራቢያ ሥፍራ የሙት ልጆች ሰብስቤ የገባሁት ወላዲተ አምላክን ተስፋ አድርጌ ነው፡፡ ጸሎታ ለማርያም ከተባለ በኋላ የሚገባ ሰው ሰይጣን መስሎ ስለሚታየኝ ሰውነቴ ይለዋወጣልና አትፈታተኑኝ፡፡
ደቂቃ ሳይዛነፉ መገኘት ግዴታ ነው፡፡ በሦስቱም ቦታዎች ብጹዕነታቸው ከሰዓቱ ቀድመው ይገኛሉ፡፡  ዘወትር በመኝታ ቤትና በመማሪያ ክፍል በመሄድ ይቆጣጠራሉ፣ ያረፈደ፣ ያልተገኘ ተማሪ ይቀጣል፡፡
የምሞተው በልጆቼ መሐል ነው፡፡ ለወባ ብዬ ክርስቶስ ያሸከመኝን መስቀል ጥዬ ልጆቼን በትኜ አዲስ አበባ አልቀመጥም፡፡
•          ብጹዕ አቡነ ጎርጎርዮስ ካልዕ  በወባ ተይዘው ክፉኛ ታመው ሕክምና አግኝተው ሲሻላቸው  አዲስ አበባ እንዲቀመጡ  ሲመክሯቸው ለብጹዕ ወቅዱስ አቡነ ተክለ ሃይማኖት  የሰጡት ምላሽ ነበር፡፡
•          ከተማሪዎች ጋር በየጢሻው እየገቡ ሰሠሩ ጋሬጣ ልብሳቸውን ሲይዝባቸው እንኳን መለስ ብለው አያዩትም፡፡ ሲሠሩ ለልብሳቸው አይጨነቁም ነበር፡፡
•          በትረ ሙሴያቸውን  በቀኝ ክርናቸው ተደግፈ ው፣ በግራ እጃቸው በትረ ሙሴውን ጫፍ ይዘው፣ መስቀላቸውን በቀኝ እጃቸው ይዘው ጫፉን  ጉንጫቸው ላይ አሳርፈው ይቆማሉ፡፡
•          ሲቀመጡም በፍጹም እግራቸውን አዛንፈው ወይንም አነባብረው አይቀመጡም፡፡
•          ከመንገድ ሲመጡ ልጆቻቸውን ሳያዩ አያድሩም፣ የት፣ ለምን እንደሄዱና ምን እንደተደረገ ይነግሩአቸዋል፡፡
•          የሚመገቡትም ከተማሪዎች ጋር ነበር፡፡ ከተማሪዎቹ የሚለዩት በጠረጴዛ ነበር፡፡ መነኮሳት በአንድ ክፍል መጽሐፈ መነኮሳት እየተነበበላቸው ሥርዓተ አበውን እየተማሩ  ይመገቡ ነበር፡፡ በምግብ ቤቱ ድምጽ ማሰማት ፈጽሞ ክልክል ነበር፡፡ 
      ዘወትር ለደቀ መዛሙርቱ እዚህ በረሃ የወደቅኩት ሰው አፈራለሁ በማለት እንጂ አልጫ ፍትፍት ብፈልግ ከመሐል ከተማ አልወጣም ነበር፡፡ ለትምህርት ጊዜ አትስጡ፡፡ የምንኖረው በዓለም ነው፡፡ ገማቾች ጥያቄ ያቀርቡልናል፡፡ ስለዚህ በመማር ብቁ እንሁን፡፡ በማለት በዓላማ መጽናት እንዳለባቸው ያስተምሩ ነበር፡፡  ብጹእነታቸው ዘወትር ምንም ነገር ሸፋፍኖ ማለፍ አይወዱም፡፡ ቁርጥ ያለና ግልጽ ውሳኔ ይወስናሉ፡፡
•          ብጹእነታቸው በዓለም መድረክ የቤተ ክርስቲያን መልእክተኛ ነበሩ፡፡ ተመራማሪና ጸሐፊ ነበሩ፡፡
•          ሦስት ጃማይካውያንን በዝዋይ አስተማረው ለማዕርገ ቅስና አብቅተዋል፡፡
የብጹእነታቸው ፍሬዎች
•    ብጹዕ አቡነ ጎርጎርዮስ ራብዕ
•    ብጹዕ አቡነ መልከ ጸዴቅ ካልእ
•    ብጹዕ አቡነ ኤልያስ ሣልስ
•    ብጹዕ አቡነ ያዕቆብ
•    ብጹዕ አቡነ ማርቆስ
•    ብጹዕ አቡነ ድሜጥሮስ
የታተሙ የብጹእነታቸው መጻሕፍቶች
•  መሠረተ እምነት- ለሕጻናት ትምህርተ ሃይማኖትን ለማስተማር የተዘጋጀ
•  የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን ታሪክ
•  የቤተ ክርስቲያን ታሪክ በዓለም መድረክ
•  ምሥጢራተ ቤተ ክርስቲያን
ያልታተሙ የብጹእነታቸው መጻሕፍቶች
•  ሥርዓተ ኖሎት
•  ነገረ ሃይማኖት
•  ኦርቶዶክሳዊ የስብከት ዘዴ
•  ቤተ ክርስቲያንህን እወቅ
•  ሰላም ተዋሕዶ የተሰኘው የመዝሙር ግጥም ደራሲም ናቸው፡፡
የብጹእነታቸው ድንቅ አባባሎች
•  ስለ እመቤታችን መናገር የምንችለው ስለሰውና ስለ እግዚአብሔር ስናውቅ ብቻ ነው፡፡
•  የቤተ ክርስቲያን ሕይወት በመስቀል ላይ ነው፡፡ ፈተና ይበዛበታል፡፡ ስለዚህ ከግል ሕይወታችሁ ይልቅ የቤተ ክርስቲያናችሁን አቋም አጠናክሩ፡፡

Читать полностью…

መዓዛ ሃይማኖት በጎ አድራጎትና ጉዞ ማህበር

✞ዑራኤል✞

አባቴ ጠባቂዬ ሞገሴ ታዳጊዬ
ዑራኤል ለኔ ልዪ ነህ
የምትረዳኝ ከአምላክ ተልከህ

በደመ ክርስቶስ ዑራኤል መልአክ
ልትቀድስ ዓለምን >> >>
በክብር አስጊጦ >> >>
አምላክ መረጠህ >> >>
ለኔስ ልዩ ነው ያንተ ፍቅር
ቁምልኝ ቅዱስ ዑራኤል በቅድመ እግዚአብሔር
አዝ= = = = =
የእውቀትን ጽዋ ዑራኤል መልአክ
ለዕዝራ እንዳጠጣህ >> >>
እኔንም ከኃጢአት >> >>
ከሞት አፍ አውጣኝ >> >>
ለኔስ ልዩ ነው ያንተ ፍቅር
ቁምልኝ ቅዱስ ዑራኤል በቅድመ እግዚአብሔር
አዝ= = = = =
የመንገዴ እንቅፋት ዑራኤል መልአክ
ተነሳ ከፊቴ >> >>
የአምላክ ባለመዋዕል >> >>
ሆነኸኝ ብርታቴ >> >>
ለኔስ ልዩ ነው ያንተ ፍቅር
ቁምልኝ ቅዱስ ዑራኤል በቅድመ እግዚአብሔር
አዝ= = = = =
በእምነት አበረታኝ ዑራኤል መልአክ
ለነፍሴ እየራራ >> >>
አገዘኝ ዑራኤል >> >>
ፍሬን እንዳፈራ >> >>
ለኔስ ልዩ ነው ያንተ ፍቅር
ቁምልኝ ቅዱስ ዑራኤል በቅድመ እግዚአብሔር

እንኳን አደረሳችሁ አደረሰን🥰
🙏 መልካም በአል 🙏

ለኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ልጆች👇🏽
•➢ ሼር // SHARE


መዝሙር
ሊቀ መዘምራን ቴዎድሮስ ዮሴፍ

@meazahaymanot

Читать полностью…

መዓዛ ሃይማኖት በጎ አድራጎትና ጉዞ ማህበር

ምክረ አበው ዘቅዱስ ሄሬኔዎስ

“ባለመታዘዝ የእንጨት ፍሬን በመብላት ምክንያት የመጣውን ሞት፣ መድኃኔ ዓለም ኢየሱስ ክርስቶስ በመታዘዝ በእንጨት መስቀል ላይ ተሰቅሎ ሞትን አስወግዶ ሕይወትን ሰጠን”

መልካም ቀን

Читать полностью…

መዓዛ ሃይማኖት በጎ አድራጎትና ጉዞ ማህበር

✅ የቃልህ ፍቺ ያበራል፥ ሕፃናትንም አስተዋዮች ያደርጋል።”
— መዝሙር 118(119)፥130
🕎ስለ መጽሐፍ ቅዱስ ምንነት እንዲሁም በመጽሐፍ ቅዱስ ላሉት ምንባባት አንድምታቸው ትንታኔና ማብራርያ የሚያገኙበት ቻናል ይቀላቀሉ።

👉“መጽሐፍ” ለሚለው ምንጭ በግሪክ ቋንቋ ቢብሎስ (byblos) ከደንገል በተሠራ ወረቀት ወይም በብራና ከተጻፈ በኋላ በሁለት በትሮች...read more

👉መጽሐፍ ቅዱስ መቼ በአንድ ጥራዝ ተጠቀለለ? ከክ.ል.በ ይሁን በኋላ የተጻፉት ሁሉንም መጻሕፍቶች ለየብቻቸው ነበሩ፡፡ከ500ዎቹ ዓ.ዓ....read more

👉ኦሪት "ኦራይታ" ከሚል የሶርያ(አራማይክ) ቃል የተገኘ ሲሆን ትርጓሜውም "ሕግ" ወይም "ትምህርት" ማለት ነው።የመጠሪያ ምንጩም....read more



ወቅታዊ የቤተ ክርስቲያናችንን ጉዳይ እና መንፈሳዊ ጥንካሬያችንን እንድናበረታ የሚያግዙን መንፈሳዊ ቻናሎችን ይዘን ቀርበናል።እርስዎም ከእነዚህ መንፈሳዊ ቻናሎች የነፍስ ምግብ የሆነውን የእግዚአብሔርን ቃል እየተመገቡ መንፈሳዊ ሕይወትዎትን እንዲያጠናክሩ በእግዚአብሔር ስም ጥሪያችንን እናቀርባለን🙏
🙏ፈጣሪ ይባርከን🙏

ከነዚህ መፀሀፍት የተወጣጡበት
ትምህርትን መማር ይፈልጋሉ❔
እነሆ ብለናል :-
📚የባሕታውያን አባቶች ሕይወትና የመዝሙራት ተመስጦ
📖▓⇨ትምህርት በአባ ሺኖዳ ⇨ክፈት
📚የድያቢሎስ ውግያዎች
📖▓⇨ትምህርት ⇨ክፈት
📚አምደ ሀይማኖት
📖▓⇨በአባታችን ቅዱስ ሺኖዳ ⇨ክፈት
📚መንፈሳዊ ሕይወት
📖▓⇨በአቡነ ሺኖዳ ⇨ክፈት
📚መንፈሳዊ ሰው
📖▓⇨በአቡነ ሺኖዳ ⇨ክፈት
📚የአባቶች ሕይወት ንሮ እና ተመስጦ
📖▓⇨በአቡነ ሺኖዳ ⇨ክፈት
የመኖኮሳት ታሪክ እና ተመስጦ በብጽእ አቡነ ሺኖዳ ሳልሳዊ ይቀርብበታል።

Читать полностью…

መዓዛ ሃይማኖት በጎ አድራጎትና ጉዞ ማህበር

ሐምሌ ፳፰ (28)
#እጨጌ_አቡነ_ፊልጶስ_ዘደብረ_ሊባኖስ፥ #፫ኛው #እጨጌ_በዓለ_ዕረፍቱ፡፡

እጨጌ አቡነ ፊልጶስ ዘደብረ ሊባኖስ፥ ፫ኛው እጨጌ፡፡
በዚህች በሐምሌ 28 ቀን ከጻድቁ አቡነ ተክለ ሃይማኖት በኋላ ለ3ኛ ጊዜ በወንበራቸው ላይ ለ፳፭ ዓመታት (ከጥቅምት 24 ቀን 1306 ዓ.ም. እስከ ሐምሌ 28 ቀን 1331 ዓ.ም.) በእጨጌነት የተቀመጠው እጨጌ አቡነ ፊልጶስ ሥጋው በደብረ ሐቃሊት(ደቡብ ጎንደር) በክብር ያረፈበት ነው፡፡

እጨጌ አቡነ ፊልጶስ፤
፠ በአቡነ ተክለ ሃይማኖት እጅ የመነኰሰ፤
፠ ደብረ ሊባኖስን በ12ት ንቡራነ እድ ያስጌጠና ከእነርሱም አንዱ የሆነ፥
፠ 12ቱ ንቡራነ እድ ሃገረ ስብከት ዕጣ ሲጣጣሉ ፍቼና ደብረ ሊባኖስ ሀገረ ስብከት የደረሰው፤
፠ የአቡነ ተክለ ሃይማኖትን መቃብር 12ቱ ንቡራነ ዕድ በዓመት አንድ ወር ተራ ገብተው እንዲያጥኑ ግንቦት 12ና ነሐሴ 24 ደግሞ ሁሉም ንቡራነ እድና የአቡነ ተክለ ሃይማኖት ደቀ መዛሙርት እንዲሰበሰቡ ሥርዐትን የሠራ፤ በግንቦት 12 ቀን ሲያጥንም 12ት መላእክት አብረው መንበሩን ከበው ቅዱስ ቅዱስ ቅዱስ ይሉ ነበር፤ እርሱም 13ኛ ሁኖ ያይና ይመለከት የነበር፤
፠ የኢትዮጵያ ሊቀ ካህን የነበረ፥
፠ በመቋሚያው 41 ጸበሎችን ያፈለቀ፥
፠ አብዛኛውን ሕይወቱን በሰማዕትነት ያሳለፈ፥ ያረፈውም ከሚያስተዳድረው ገዳም ርቆ በሰማዕትነት ሕይወት ሳለ በደቡብ ጎንደር ደብረ ሐቃሊት ነው፤
እጨጌ ፊልጶስ በዘመኑ የነበሩት ነገሥታት ብዙ ሚስቶች በማግባታቸው ነገሥታቱን ሳይፈራና ሳይፍር በመገሰጹ ፭ ጊዜ (በትግራይ፣ በደራ፣ በዝዋይ ባሕረ ደሴት፣ በዳሞት ገማስቄና በወለቃ) በስደት ቆይቶ፡፡ ጌርጌሳ በሚባል አካባቢ ሳለ ጳጳሱን አባ ሰላማን በሐቃሊት ቅበረኝ አለው፤ ጳጳሱም በቃሬዛ አድርጎ ከጌርጌሳ ወደ ደብረ ሐቃሊት(ደቡብ ጎንደር) ወሰደው፤ ጌታችንም ፯ት አክሊላትን አቀዳጀው በደብረ ሐቃሊትም በ74ት ዓመቱ በሐምሌ 28 ቀን በ1267 ዓ.ም. በሰላም ዐረፈ፡፡ ከ140 ዓመታት በኋላ በመጋቢት 23 ቀን በ1481 ዓ.ም. ወደ ደብረ ሊባኖስ አጽሙ በክብር ፈለሰ፡፡

የአቡነ ተክለ ሃይማኖት ደቀ መዛሙርት ከአንተ በኋላ በወንበርህ የሚቀመጠው ማነው ብለው በጠየቁት ጊዜ፤ የሞተውን ዲያቆን አስነሥቶ በመላክ ‹‹ኤልሳዕ ወደኔ ይምጣ፥ ፊሊጶስ ስለ እኔ ተሹሞ በወንበሬ ይቀመጥ ‹እርሱ ለብዙዎች አሕዛብ አባት ይሆናልና የክርስቶስንም መንጋ በጽድቅና በቅን ይጠብቃል› ብሎኛል› ብሎ በወንበሩ ላይ እንደሚቀመጥ የመሰከረለት ነው፡፡

ሰላም ለከ ፊልጶስ ግፉዕ እም እለ ቆሙ ብዙኃን ላዕሌከ፤
አሜኃ እስከነ ፈጸምከ፤
መዊተ በስደትከ፡፡

ለእግዚአብሔር ክብር ይሁን፤ እኛንም በጻድቁ አቡነ ፊልጶስ ጸሎትና አማላጅነት ይማረን፤ አሜን፡፡

Читать полностью…

መዓዛ ሃይማኖት በጎ አድራጎትና ጉዞ ማህበር

🌿🍁🌿🍁🌿🍁🌿🍁🌿🍁🌿🍁🌿🍁

እንኳን ክርስቶስን ለሚወዱ #ለቅዱስ_እንድራኒቆስና #ሚስቱ_ቅድስት_አትናስያ_ለመታሰቢያ_በዐላቸው በሰላም አደረሰን። በተጨማሪም በዚህች ቀን ከሚታሰቡ፦ ከከቅዱሳን አባቶቻችን #ከአብርሃም_ከይስሐቅና_ከያዕቆብ ከመታሰቢያቸው እግዚአብሔር አምላክ ረድኤትና በረከትን ያሳትፈን።

🌿🍁🌿🍁🌿🍁🌿🍁🌿🍁🌿🍁🌿🍁

Читать полностью…

መዓዛ ሃይማኖት በጎ አድራጎትና ጉዞ ማህበር

ምክረ አበው ዘማር ይስሐቅ

"ንስሐ ለተጠመቁ ሠዎች ከጥምቀት በኃላ የተሰጠች ሀብት ናት"

መልካም ቀን

Читать полностью…

መዓዛ ሃይማኖት በጎ አድራጎትና ጉዞ ማህበር

ቅዱስ ላልይበላ

ቅዱስ ላልይበላ ላልይበላ
ቅዱስ ላልይበላ ላልይበላ
ዕፁብ ነው ድንቅ ነው የሠራው
ምሳሌም የለው
       አዝ-----
ዘውትር ብመላለስ     ላልይበላ  
ዐይኔም አይጠግበው   " " " "
የሠው ስራ አይደለም    " " " "
የሥላሴ ነው                " " " "
       አዝ-----
በማህጸን ሳለ       ላልይበላ
ስለተመረጠ          " " " "
ቤተ-መቅደስ ሠራ  " " " "
ድንጋዩ ያጌጠ       " " " "
       አዝ-----
የአሰራሩ ዘይቤ      ላልይበላ
ከላይ ወደ ታች        " " " "
ስነ ሕንጻው ሲታይ    " " " "
የማይሰለች             " " " "
ላዩ አረንጓዴ ነው      " " " "
ውስጠኛው ባሕር    " " " "
ጸበሉ የፈለቀው       " " " "
ከቋጥኙ ስር           " " " "
       አዝ-----
በዕምነት የመጡ        ላልይበላ
ከቤተ ጊዮርጊስ           " " " "
አንቀላፉ ከዚያው         " " " "
ምፅአት እስኪደርስ      " " " "
ማርኳቸዋልና              " " " "
የእግዚአብሔር ቅዱስ  " " " "

🙏🙏በመልዐከ ሰላም ዘማሪ ቀሲስ እንግዳወርቅ በቀለ🙏🙏

              @meazahaymanot

Читать полностью…

መዓዛ ሃይማኖት በጎ አድራጎትና ጉዞ ማህበር

ስንክሳር ዘወርሃ ሐምሌ ሃያ ስድስት(፳፮)
/channel/meazahaymanot

Читать полностью…

መዓዛ ሃይማኖት በጎ አድራጎትና ጉዞ ማህበር

የቅዱስ ሲኖዶስ አስቸኳይ ምልአተ
ጉባኤ ስብሰባ በጸሎት ተከፈተ።
*******

ሐምሌ ፳፭ ቀን ፳፻፲፭ ዓ/ም አዲስ አበባ

የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተክርስቲያን ቅዱስ ሲኖዶስ በክልል ትግራይ ባሉ አህጉረ ስብከት ለመንፈሳዊ አገልግሎት ተመድበው የነበሩ አራት ብፁዓን አበው ሊቃነ ጳጳሳት ሐምሌ ፲፮ እና ፳፫ ቀን ፳፻፲፭ ዓ/ም በፈጸሟቸው የቀኖና ቤተክርስቲያን እና የሕግጋተ ቤተክርስቲያን ጥሰቶች ዙሪያ ለመወያየትና ሕግጋተ ቤተክርስቲያንን መሠረት ያደረጉ ውሳኔዎችን ለማሳለፍ ጉባኤውን በጸሎት ጀመረ።

ሕገወጥ ድርጊቱ መፈጸሙን ተከትሎ በቅዱስ ሲኖዶስ ጽ/ቤት በኩል የተጠራውን  አስቸኳይ የቅዱስ ሲኖዶስ ምልአተ ጉባኤ ስብሰባ ለመጀመር ዛሬ ሐምሌ ፳፭ ቀን ፳፻፲፭ ዓ/ም በመንበረ ፓትርያርክ ቅድስተ ቅዱሳን ማርያም ገዳም ቀኖና ቤተክርስቲያንና ሕገ ቤተክርስቲያን በሚያዘው ሥርዓት መሠረት የመክፈቻ ጸሎቱ ደርሷል።

የመክፈቻ ጸሎቱ በብፁዕ ወቅዱስ አቡነ ማትያስ ፓትርያርክ ርእሰ ሊቃነ ጳጳሳት ዘኢትዮጵያ ሊቀ ጳጳስ ዘአክሱም ወእጨጌ ዘመንበረ ተክለሃይማኖት የተመራ ሲሆን በመርሐ ግብሩ ላይ ብፁዕ አቡነ አብርሃም የመንበረ ፓትርያርክ ጠቅላይ ቤተክህነት ዋና ሥራ አስኪያጅ እና የባሕር ዳር ሀገረ ስብከት ሊቀ ጳጳስ፣ ብፁዕ አቡነ ጴጥሮስ የቅዱስ ሲኖዶስ ዋና ጸሐፊና በሀገር ውስጥና በውጭ ሀገራት ባሉ አህጉረ ስብከቶች ተመድበው የቤተክርስቲያንን አገልግሎት የሚመሩ ብፁዓን አበው ሊቃነ ጳጳሳት ተገኝተዋል።

የቅዱስ ሲኖዶስ ጽ/ቤት ባወጣው የድርጊት መርሐ ግብር መሠረት ዛሬ በጸሎት የተጀመረው የቅዱስ ሲኖዶስ አስቸኳይ ምልአተ ጉባኤ ነገ ሐምሌ ፳፮ ቀን ፳፻፲፭ ዓ/ም ጠዋት 2:30 ሰዓት በተያዙት አጀንዳዎች ላይ በመወያየት የቤተክርስቲያናችንን ቀኖናትና ሕግጋት የሚያስከብሩ ውሳኔዎችን እንደሚያሳልፍ ይጠበቃል

Читать полностью…

መዓዛ ሃይማኖት በጎ አድራጎትና ጉዞ ማህበር

ምክረ አበው ዘብፁዕ ወቅዱስ አቡነ ሺኖዳ

አንተ ሌሎችን የምትምር ከሆነ እግዚአብሔርም አንተን ይምርሃል። ነገር ግን አንተ እቁጡና ጨካኝ ሆነህ ሳለህ የእጅህን ዋጋ ብታገኝ እንዳታማርር።

መልካም ቀን

Читать полностью…

መዓዛ ሃይማኖት በጎ አድራጎትና ጉዞ ማህበር

ሰላም ላንተ አባ ኖብ

ሰላም ላንተ አባ ኖብ ቅዱስ (2)
በእሾኽ መካከል የበቀልክ በለስ(2)

@meazahaymanot

Читать полностью…

መዓዛ ሃይማኖት በጎ አድራጎትና ጉዞ ማህበር

ምክረ አበው ዘአባ እንጦንስ

"መንፈሳዊ ብቃት፥ የማይደረስበት እሩቅ፣ ወይም ከሰው ልጅ ችሎታ በላይ ነው፥ ብለን ማሰብ የለብንም። ሰዎች ባሕር አቋርጠው የሌላ ሀገር ፍልስፍና ሊማሩ ይሄዳሉ። የእግዚአብሔር ከተማ ግን በልባቸው ውስጥ ነው። እግዚአብሔር የሚጠብቅብን መልካም ምግባርም እዚያው ልባችን ላይ ነው ያለው። የሚጠበቅብን መሻታችንን ከእግዚአብሔር መሻት ጋር ማስማማት (አንድ ማድረግ) ብቻ ነው።"



መልካም ቀን

Читать полностью…

መዓዛ ሃይማኖት በጎ አድራጎትና ጉዞ ማህበር

ሰማዕተ ኢየሱስ የእውነትን ምስክር
ሕያውነው በስማይ ብጹህ ነው በምድር
ደራጎነን በጦር ወግቶ ገደለና/2/
ከሞት አፍ አዳነኝ ጊዮርጊስ ደረሰና/2/


@meazahaymanot

Читать полностью…

መዓዛ ሃይማኖት በጎ አድራጎትና ጉዞ ማህበር

• ሰው ፍላጎቱን ካላሸነፈ የእግዚአብሔር ሊሆን አይችልም፡፡
•  ሥጋዊ ፍላጎቶችን ማሸነፍ ለአክሊለ ሕይወት የሚያበቃ ሰማዕትነት ነው፡፡
•  ኢትዮጵያ ለእግዚአብሔር የምሥጢር ሀገር ናት፡፡
•          ሐምሌ 15 ቀን 1982 ዓ.ም. በሕጻናት አምባ ( በዛሬው አላጌ ግብርና ኮሌጅ) የደብረ መዊዕ ቅዱስ ሚካኤል  ቤተ ክርስቲያን መሠረት አስቀምጠው ሰው  የሚፈልገውን  ከፈጸመ የሚጠብቀው ሞቱን ነው፡፡ በማለት ብዙዎችን የሚያስገርም ነገር ተናግረው ነበር፡፡
•          ሐምሌ 22 ቀን 1982 ዓ.ም. ከጠዋቱ አንድ ሰዓት ተኩል ወደ መቂ ቅዱስ ሚካኤል ቤተ ክርስቲያን ለአገልግሎት ሲሄዱ በድንገተኛ የመኪና አደጋ በተወለዱ በሃምሳ ዓመታቸው አርፈዋል፡፡
•           በዕለቱ አብረዋቸው የነበሩት ዲያቆን ጳውሎስ በቀለና የመኪናው አሽከርካሪ ዲያቆን ኤፍሬም ዘውዴም በለጋ ዕድሜያቸው አርፈዋል፡፡

ለብጹእነታቸው የተደረጉ መታሰቢያዎች
•    ትምህርት ቤቶች
•    አዳራሾች
•    ቤተ መጻሕፍት
•    ሐውልት በስማቸው ተሰይሞላቸዋል፡፡

@meazahaymanot
@meazahaymanot

Читать полностью…

መዓዛ ሃይማኖት በጎ አድራጎትና ጉዞ ማህበር

ዜና ሕይወቱ ለብጹዕ አቡነ ጎርጎርዮስ ካልዕ(፲፱፻፴፪ — ፲፱፻፹፪)
ዜና ሕይወቱ ለብጹዕ  አቡነ ጎርጎርዮስ ካልዕ 
           (፲፱፻፴፪ — ፲፱፻፹፪)
            
በጸሎተ ቅዳሴ አስቀድመው ስላረፉ ወገኖች እንለምናለን፡፡  የቅዱሳንን ሕይወት እናስታውሳለን፡፡ ዜና አበውን መጻፍ መጽሐፍ ቅዱሳዊ ትውፊት አለው፡፡ የቅድስት፣ አሐቲ፣ ሐዋርያዊትና እንተ ላዕለ ኲሉ ቤተ ክርስቲያን አበው በዘመነ ብሉይ በዜና መዋዕል፣ በዘመነ ሐዲስ በግብረ ሐዋርያትና  በዘመነ ሊቃውንት -  በስንክሳርና በገድላት የተጻፉትን አበው የተጋድሎ ሕይወት በማንሣት ምእመናንን ለማስተማር ይጠቀሙበታል፡፡ ይህ ትውፊት በዘመናችንም የተለያዩ አባቶችን ዜና ሕይወት አንሥተን እንድንነጋገር አስችሎናል፡፡
የአባቶችን ታሪክ ምን እናጠናለን?
•       ፈጣሪያችንን እንዴትና ለምን እንደምናመልክ ለመማር
•       በፈተና ለመጽናትና ለተጋድሎ ለመዘጋጀት
•       ከአበው በረከትና ረድኤት ለመሳተፍ
•       ሕይወታችንን ለማየት
•       ምግባር ትሩፋት ለመማር
•       የቤተ ክርስቲያንን ፈተናና ጉዞ ለማየትና ከታሪክ ለመማር ይጠቅመናል፡፡

የወረቀቱ ዐበይት ዓላማዎች
•          የብጹዕ አቡነ ጎርጎርዮስ ካልዕ አጭር የሕይወት ታሪክን ማስቃኘት
•          ብጹዕ አቡነ ጎርጎርዮስ ካልዕ በሕይወተ ሥጋ በነበሩበት ዘመን በቤተ ክርስቲያን የነበረውን አጠቃላይ ሁኔታ በወፍ በረር  ማሳየት ነው፡፡

የወረቀቱ ውሱንነት

•          ብጹዕ አቡነ ጎርጎርዮስ ካልዕ ካንቀላፉ ከአሥር ዓመታት በኋላ በመዘጋጀቱ ብዙ ታሪክ ተዘንግቷል፡፡
የብጹዕ አቡነ ጎርጎርዮስ ካልዕ ልደትና አስተዳደግ
•          ብጹዕ አቡነ ጎርጎርዮስ ካልዕ በ፲፱፻፴፪ ዓ.ም. ከአቶ ገበየሁ እሰየና ከወ/ሮ አሰለፈች ካሣ በስዕለት በደሴ ከተማ ተወለዱ፡፡ ወላጆቻቸው ልጆች እየወለዱ እየጠፉባቸው ስለተቸገሩ ለሕጻኑ የሰጡት  ስም ተስፋዬ የሚል ነበር፡፡    
•          የብጹዕ አቡነ ጎርጎርዮስ ካልዕ አጎት የነበሩት አለቃ ድንቁ- አንድ ቀን ሕጻኑ ተስፋዬ ገበየሁ የእንጨት መስቀል ሠርቶ ጓደኞቻቸውን ለማሳለም ሲሞክር፣ በሌላ ቀን ደግሞ  መጽሐፈ ድጓቸውን ገልጠው ሲመለከት በማየታቸው ዕድሜ ሰጥቶኝ የዚህን ሕጻን መጨረሻ ባሳየኝ በማለት ተናግረው እንደነበር ቤተሰቦቻቸው ይገልጻሉ፡፡
•          ፊደል የቆጠሩት በደሴ መድኃኔ ዓለም ነበር፡፡
•          ከየኔታ ክፍሌ ( አባ ክፍለ ማርያም) ጋር መገናኘታቸው የሕይወት መስመራቸውን ለውጦታል፡፡
•          ብጹዕ አቡነ ጎርጎርዮስ ካልዕ በሕጻንነታቸው የኔታ ክፍሌን ተከትለው  ከደሴ መድኃኔ ዓለም ወደ ገነተ ማርያም፣ ከዚያም ወደ ነአኲቶ ለአብና ወደ አባ ቡሩክ ገዳም ትምህርት ፍለጋ ሄደዋል፡፡
•           ከየኔታ ክፍሌ የውዳሴና የቅዳሴ ማርያም ትርጓሜያትን፣ አዕማደ ምሥጢራትን ባሕረ ሐሳብን ቀጽለዋል፡፡ በተማሪ ቤት ሳሉ ጥያቄና ክርክር ይወዱ እንዲሁም የተነገራቸውን ቀለም ይይዙ ስለነበር በየኔታ ክፍሌ ስማቸው መዝገበ ሥላሴ ክፍሌ ተባለ፡፡
•          መዝገበ ሥላሴ ክፍሌ ከብጹእ አቡነ ይስሐቅ ማዕርገ ዲቁና ተቀብለዋል፡፡ በ፲፱፻፶፮ ዓ.ም. ወደ ደብረ ሊባኖስ ገዳም በመምጣት ማዕርገ ምንኵስና ተቀብለዋል፡፡
•          በአዲስ ዓለም ደብረ ጽዮን ማርያም ከነበሩት  ከታላቁ የቅኔ መምህር አፈወርቅ መንገሻ ቅኔ ከአገባቡ፣ በደብረ ሊባኖስ ገዳም ከመምህር ፍሥሐና ከመምህር ገብረ ሕይወት የመጻሕፍተ ሐዲሳት ትርጓሜና ትምህርተ ሃይማኖት ከመምህር ቢረሳው ደግሞ መጻሕፍተ ሊቃውንትን አኺደዋል፡፡
•          በደብረ ጽጌ ቅድስት ማርያም ከመሪ ጌታ አብተው ላሊታግዳን ምዕራፍ፣ ጾመ ድጓን፣ ከመምህር ልዑል መዝገበ ቅዳሴን ተምረዋል፡፡ በደብረ ሊባኖስ ዳቤ እየጋገሩ አባቶችን አገልግለዋል፡፡ በገዳማዊ ሕይወታቸው የሰገዱበት የእጃቸው ፈለግ ሞፈር የሄደበት የበሬ ጫንቃ ይመስል እንደነበር በገዳም በቅርብ የሚያውቋቸው አበው ይናገራሉ፡፡
•          በ፲፱፻፶፯ ዓ.ም. ከብጹእ ወቅዱስ አቡነ ባስልዮስ ማዕርገ ቅስና ተቀብለዋል፡፡
•          ከመምህር ፍሥሐ ወደ ብጹእ አቡነ ቴዎፍሎስ ተልከው ወደ ሐረርጌ በመሄድ ከመንፈሳዊ አገልግሎቱ ጎን ለጎን የአንደኛና የሁለተኛ ደረጃ ትምህርታቸውን ተከታትለዋል፡፡
•          በ፲፱፻፷፫ ዓ.ም. ለከፍተኛ ትምህርት በብጹእ አቡነ ቴዎፍሎስ ወደ ግሪክ ተልከዋል፡፡
•          በደሴተ ፍጥሞ ለሁለት ዓመት መንፈሳዊ ትምህርት ተምረው - ዲፕሎማ ፣ከአቴንስ የኒቨርስቲ - በሥነ መለኮት የማስትሬት ዲግሪ ፣ ከስዊዘርላንድ ፍሪበሪን ዩኒቨርስቲ - በፈረንሳይኛ ቋንቋ የምስክር ወረቀት እንዲሁም በኢየሩሳሌም ደብረ ጽዮን የግሪክ መንፈሳዊ ኮሌጅ- በአረብኛ ቋንቋ የምስክር ወረቀት አግኝተዋል፡፡
•          በኢየሩሳሌም በደብረ ገነት ኪዳነ ምሕረት - የኢትዮጵያውያንን ልጆች በማሰባሰብ ባሕላቸውንና ቋንቋቸውን በማስተማርና የዕጣንና ከርቤ ቅመማ በማካሄድ ለገዳሙ ገቢ ያስገኙ ነበር፡፡
•          ብጹዕ አቡነ ጎርጎርዮስ ካልዕ ቤተ ክርስቲያን  በተቸገረችበት ወቅት የተገኙ አባት ነበሩ፡፡
•          ብጹዕነታቸው በኢየሩሳሌም አንድ ቀን ሌሊት ከተኙበት ክፍል አንድ ቀላ ያለ ረጅም ሰው ቀስቅሷቸው  አሁን በዚህ የምትቀመጥበት ጊዜ አይደለም፡፡ ወንጌል ለማስተማር  ወደ ኢትዮጵያ እንሂድ ይላቸዋል፡፡ በትእዛዙ ግራ በመጋባት ማንነቱን ሲጠይቁት ኤፍሬም ሶርያዊ ነኝ፡፡ ይላቸዋል፡፡
•          ጠዋት ከብጹዕ ወቅዱስ አቡነ ተክለ ሃይማኖት ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት ዘኢትዮጵያ  ወደ ኢትዮጵያ እንዲመጡ ጥሪ ደረሳቸው፡፡ በተደረገላቸው ጥሪ መሠረት ወደ ኢትዮጵያ በመምጣት ጥር ፲፫ ቀን ፲፱፻፸፩ ዓ.ም. ብጹዕ አቡነ ጎርጎርዮስ ኤጲስ ቆጶስ ዘሸዋ ተብለው ተሹመዋል፡፡
•          ለቅዱስ ሲኖዶስ የመተዳደሪያ ደንብ አዘጋጅተው እንዲጸድቅ በማድረጋቸው የተነሣ ልዩ ልዩ ውንጀላዎች( መንበረ ፓትረያርክ ለመገልበጥ ይፈልጋሉ፣ በርዳታ የተሠጠ ዶላር ወስደዋል፡፡) ቀረበባቸው፡፡ ይህ ሁኔታ ሥራ ሊያሠራቸው ባለመቻሉ ለቤተ ክርስቲያን ተልእኮ ለመፋጠን ወደ ዝዋይ ወረዱ፡፡
•  የዝዋይ ካህናት ማሠልጠኛ በ1960 ዓ.ም. ከዓለም አብያተ ክርስቲያናት በተገኘ ርዳታ ግንባታው ተጀምሮ በ1960 ዓ.ም. ተመርቋል፡፡ ከስድስት ዓመታት በኋላ በሀገራችን በተፈጠረው የመንግሥት ለውጥ የተነሣ ተማሪዎቹ ተበትነውና ማሠልጠኛው ተዘግቶ ነበር፡፡ ደርግ ማሠልጠኛውን ለዕድገት በኅብረት ዘመቻ ጣቢያነት አውሎት ነበር፡፡ በ1970 ዓ.ም. ባሕታውያን በከተማ ውስጥ እየተዘዋወሩ በሚያስተምሩት ትምህርት ደርግ ደስተኛ ባለመሆኑ ተሰብስበው ወደ ማሠልጠኛው እንዲገቡ ተድርጎ ነበር፡፡
•          በዝዋይ ካህናት ማሠልጠኛ ከነበሩት አራት የጥበቃ ሠራተኞች አንዱ አቶ ተረፈ አስፋው ነበሩ፡፡
•          አቶ ተረፈ አስፋው ማሠልጠኛውን ለሁለት ዓመታት ያለ ደመወዝ ሲጠብቁ በጦር እስከመወጋት ደርሰው ነበር፡፡ ታመውም ከማሰልጠኛው ባለመለየት ለቤተ ክርስቲያን ጠብቀው ያቆዩ ታላቅ ባለውለታ ናቸው፡፡

Читать полностью…

መዓዛ ሃይማኖት በጎ አድራጎትና ጉዞ ማህበር

ኦርቶዶክሳውያን እንኳን ለሊቀ መላእክት ቅዱ ዑራኤል ቅዳሴ ቤት ክብረ በዓል በሰላም አደረሳችሁ

Читать полностью…
Subscribe to a channel