#ገድልህ
ገድልህ በገድል ቤት ውስጥ ሲነበብ ስሰማ
ልቤ ተማረከብኝ በተክልዬ ግርማ
ደብረ ሊባኖስ ነው ያየሁት እርሱን
ሊባርክ ሲመጣ ሌት ቀን ገዳሙን
እየባረከ ይባርከናል እየቀደሰ ይቀድሰናል
ጸጋው በዝቶለት በአምላካችን
በክንፉ ይበራል ሊያማልደን
አቤት የተክለሃይማኖት ክብሩ
ሱራፌል ሆነ በሰማይ ሀገሩ
ጽና ይዞ እያጠነ ዙፋኑን
ያስታርቀናል ለሊትና ቀን
ያማልደናል ሌሊትና ቀን
#አዝ
እንግዶች ሆነን ዋሻው ስንሄድ
ያሳድረናል ትሁት ነው ውድ
የአምላክ ምስሌኒ ሆኖልናልና
ልጆቹ ሁሉ ወጡ ምነና
#አቤት የተክለሃይማኖት ክብሩ ......
........
#አዝ
በነፋስ አውታር ዘወትር ይሄዳል
በወንጌል መረብ ብዙውን ያጠምዳል
የታመመውን እየፈወሰ
ሙታን ያስነሳል እየቀደሰ
#አቤት የተክለሃይማኖት ክብሩ.....
................
#አዝ
ድካም የለበት ዘወትር ብርቱ
ግዳጅ ፈጻሚ ስውር ጸሎቱ
ተዘከረኒ በባሕር ወየብስ
ተክለሃይማኖት ስልህ ድረስ
@meazahaymanot
@meazahaymanot
ነሐሴ 24 ፳፬"የጻድቁ የአባታችን አቡነ ተክለሃይማኖት የእረፍት ክብረ በዓል ሥርዓተ ማኅሌት ከሊቃውንቱ ጋር አብረን እድናመሰግን እንደሚከተለው ተዘጋጅቷል #Share _ሼር_ይደረግ
የማንኛውም ወርኃ በዓልና ክብረ በዓል ሥርዓተ ማኅሌት መጀመሪያ (ሥርዓተ ነግሥ)
ስምዓኒ እግዚኦ ጸሎትየ፡ ሃሌ ሉያ ሃሌ ሉያ፡ ወይብጻሕ ቅድሜከ ገአርየ፡ ሃሌ ሉያ ሃሌ ሉያ፡ ወኢትሚጥ ገጸከ እምኔየ፡ በዕለተ ምንዳቤየ አጽምእ እዝነከ ኀቤየ፡ ሃሌ ሉያ ሃሌ ሉያ፡ አመ ዕለተ እጼውአከ ፍጡነ ስምዓኒ፡ ሃሌ ሉያ ሃሌ ሉያ፡ ለዓለም ወለዓለመ ዓለም፡ ሃሌ ሉያ ዘውእቱ ብሂል፡ ንወድሶ ለዘሃሎ እግዚአብሔር ልዑል፡ ስቡሕ ወውዱስ ዘሣረረ ኲሎ ዓለመ፡ በአሐቲ ቃል።
መልክዐ ሥላሴ
ሰላም ዕብል ለንዋየ ውስጥ ምሕረትክሙ: ትሩፋተ ገድል ኲኑኒ ሥላሴ አምጣነ ትሩፋት አንትሙ: ሶበ ሖርኩሰ ከመ እሳተፍ ገድሎሙ: ጊዮርጊስ ኢወሀበኒ መጠነ ነጥበ ጠል እምደሙ: ወተክለሃይማኖት ከልአኒ ስባረ እምዐጽሙ፡፡
ዚቅ
ቅዱስ ቅዱስ ቅዱስ እግዚአብሔር ዘኢይነውም ትጉህ: በውስተ ቅዱሳን ስቡሕ: ከመ ቀስተ ደመና የዓውዶ ሱራሄ: ሎቱ ለባሕቲቱ ይደሉ ስባሔ፡፡
ነግሥ
ሰላም ለዝክረ ስምኪ ዘመንክር ጣዕሙ: ለወልድኪ አምሳለ ደሙ: መሠረተ ሕይወት ማርያም ወጥንተ መድኃኒት ዘእምቀዲሙ: ኪያኪ ሠናይተ ዘፈጠረ ለቤዛ ዓለሙ: እግዚአብሔር ይትባረክ ወይትአኮት ስሙ፡፡
ዚቅ
አመ ኖኅ ይእቲ መድኃኒት እንተ ኮነት አንቀጸ ሕይወት: ማርያም ቅድስት፡፡
ወረብ
ማርያም ቅድስት አንቀጸ ሕይወት አመ ኖኅ አንቀጸ ሕይወት ማርያም ቅድስት/፪/
ይእቲ መድኃኒት "እንተ ኮነት"/፪/አንቀጸ ሕይወት/፪/
መልክዐ ተክለሃይማኖት
ሰላም ለዝክረ ስምከ ዘጥንተ ፊደሉ መስቀል: ስም ክቡር ወስም ልዑል: ተክለሃይማኖት ማቴዎስ በዓለ ቀዳማይ ወንጌል: ከመ እወድሰከ መጠነ አውሥኦተ እክል: ማዕሠረ ልሳንየ ትፍታሕ ማርያም ድንግል።
ዚቅ
ወንጌለ መለኮት ሰበከ: ስምዓ ጽድቅ ኮንከ: ወበእንተዝ ተክለ ሃይማኖት ተሰመይከ፡፡
ወረብ
ወበእንተዝ "ተሰመይከ"/፪/ተክለሃይማኖት/፪/
"ስምዓ ጽድቅ ኮንከ"/፪/ተክለሃይማኖት/፪/
መልክዐ ተክለሃይማኖት
ሰላም ለአዕይንቲከ ዘአርያኣሆን ሐዋዝ: እለ ጽዱላት እማንቱ ከመ ሠርቀ ቤዝ: ተክለ ሃይማኖት ኅብአኒ እሞተ ኃጢአት አዚዝ: ለከሰ አኮ ከመዝ: ኢይረክበከ ሞት ዳግም እምዝ፡፡
አመላለስ
ዳግም እምዝ/፬/
ኢይረከቦ ሞት ለተክለ ሃይማኖት/፪/
ዓዲ
ወረብ
"ዳግም እምዝ"/፪/አይረከቦ ከመዝ ሞት ለተክለ ሃይማኖት/፪/
ኢይረከቦ እምዝ ሞት ለተክለሃይማኖት/፪/
መልክዐ ተክለሃይማኖት
ሰላም ለኲልያቲከ ዘፈተኖን በትዕግስት: ኢየሱስ ክርስቶስ አበ ብርሃናት: ተክለ ሃይማኖት ሰጋዲ ከመ መላእክት: ጸሎትከ ዘገበርካሃ እስከነ ኈልቊ ምዕት ዓመት: መድኃኒተ ትኩነኒ እምግሩም ቅሥት፡፡
ዚቅ
ተክለ ሃይማኖት ሰማዕት ሰባኬ መድኃኒት: ጸሎትከ ትኩነነ ፀወነ እመንሱት: ተክለ ሃይማኖት ሰማዕት ሰባኬ መድኃኒት፡፡
ወረብ
ሰማዕት ሰባኬ መድኃኒት ተክለ ሃይማኖት/፪/
ጸሎትከ ትኩነነ "ፀወነ እመንሱት"/፪//፪/
መልክዐ ተክለ ሃይማኖት
ሰላም ለፀዐተ ነፍስከ በስብሐተ አዕላፍ እንግልጋ: ለዓለም ዛቲ እምግብርናቲሃ ወጹጋ: ተክለ ሃይማኖት ቶማስ ለመርአስ ዐቃቤ ሕጋ: ለእለ ገብሩ ተዝካረከ እንዘ ሀለዉ በሥጋ: ሀቦሙ እግዚእየ ሞገሰ ወጸጋ፡፡
ዚቅ
ወወጽአት መንፈሱ ሶቤሃ: ወተቀበልዎ መላእክት በስብሐት ወበማኅሌት: እንዘ ይብሉ ሃሌ ሉያ: ወአብዕዎ ኢየሩሳሌም ሰማያዊተ፡፡
መልክዐ ተክለ ሃይማኖት
ሰላም ለበድነ ሥጋከ ኤልሳዕ መምህር ዘገነዛ: በሠናይ ፄና መዓዛ: ተክለ ሃይማኖት ሰባኪ ፊልጶስ ዘብሔረ ጋዛ: ለሥጋየ መሬታዊት እመ የኀልቅ እዘዛ: ስብረተ ዐፅምከ ይኩነኒ ቤዛ፡፡
ዚቅ
ሖረ ኀቤሁ ለተክለ ሃይማኖት ቀዲሙ ሌሊተ: ኤልሳዕ ስሙ መልአኮሙ ለአርድዕት: ውእቱኒ አምጽአ ከርቤ አፈዋት: ገነዝዎ በሰንዱናት ለተክለሃይማኖት።
መልክዐ ተክለሃይማኖት
ሰላም ለግንዘተ ሥጋከ በዘቦቱ ይትመኀፀኑ: ነገሥተ እስራኤል ኄራን ዘአስተሣነይዎ በበዘመኑ: ተክለ ሃይማኖት ሠዋዒ ለእግዚአብሔር ካህኑ: አድኀነኒ እምጸብአ ከይሲ ዘዐሥር ቀርኑ: ወእምብእሲ ዘክልኤ ልሳኑ፡፡
ዚቅ
መላእክት አእመሩ ሃይማኖተከ: ነገሥት ሐነፁ መካነከ: አባ ተክለሃይማኖት ክርስቶስ ዘአፍቀርከ፡፡
መልክዐ ተክለሃይማኖት
ሰላም ለመቃብሪከ እምቅድመ ትኑም ውስቴታ: ታቦተ ማርያም ድንግል ዘአንበርከ በውሳጢታ: ተክለሃይማኖት አቡየ ለወልድከ ዕጓለ ማውታ: ለበረከትከ ይከልለኒ ረድኤታ: ወይዑደኒ ዘጽድቅከ ወልታ።
ዚቅ
ጸለየ ተክለ ሃይማኖት እንዘ ይብል ኀበ ተቀብረ ሥጋየ ወተክዕወ ደምየ ህየ ይኩን በረከት፡፡
ወረብ
ጸለየ ተክለ ሃይማኖት እንዘ ይብል ኀበ ተክዕወ ደምየ/፪/
"ህየ ይኩን"/፪/በረከት/፪/
አንገርጋሪ
ሞቶሙሰ ለጻድቃን ሕይወቶሙ ውእቱ እስመ ለጻድቅ ይትሌዓል ቀርኑ በክብር ጻድቃን እለ አስመርዎ ለእግዚኦሙ ምድረ ብርህተ ወጽዱተ ይወርሱ፡፡
እስመ ለዓለም
ደሪዖሙ ተአጊሦሙ: መጠዉ ነፍሶሙ ለሞት: እለ ሎቱ ተቀንዩ በሕወቶሙ: እምፀሐይ ይበርህ ገጾሙ: እለ አጥረይዋ ለትዕግስት: እለ...: እፎ አምሰጥዎ ለመድብብ ከመ ይባዕዎ ለመርኀብ: እለ...: ዕፎ አመሠጥዎ ለሞት: ዓደዉ እሞት ውስተ ሕይወት: እለ...: እለ ጸውዖሙ ወይቤሎሙ: ንዑ ለአቡየ ቡሩካኑ: እለ...: አመ ያቀውም አባግዐ በየማኑ: ወአጣሌ በጸጋሙ: እለ...: አሜሃ ይቤሎሙ ለእለ በየማኑ: ንዑ ለአቡየ ቡሩካኑ: እለ...:ወያወርሶሙ ምድረ ሐዳሰ: እንተ ታውኀዝ ሀሊበ ወመዓረ: እለ...:ገነት ትፍሥሕት ኪያሃ አውረሶሙ ወዓቀቦሙ ከመ ብንተ ዓይን ለጻድቃን: እለ ሎቱ ተቀንዩ በሕይወቶሙ፡፡
👇👇👇👇👇👇👇👇👇👇👇👇.👉አስተማሪ ጹሑፎችና ያሬዳዊ ዝማሬ ለማግኝት ከስር ያለውን ሊንክ በመጫን ላይክ 👍 ሼር በማድረግ /channel/meazahaymanot👆👆👆👆ለሌሎች ያስተላልፉ መልካሙን ያካፍሉ!!!
ወስብሐት ለእግዚአብሔር
🔺✞በሰው ዘንድ ቢሟጠጥ✞🔺
በሰው ዘንድ ቢሟጠጥ ተስፋና ደስታ
እኛስ ፈጣሪ አለን ሁሉን የሚረታ
ተስፋ እንደሌላቸው አንሆንም ከቶ
ክርስቶስ አለልን የሚያሳይ አብርቶ(፪)
ያለቀሱ ሁሉ ይስቃሉ አይቀርም
ይለዋውጠዋል ጌታ መድኃኔዓለም
ማንም ያላሰበው ያልጠበቀውን ድል
ለኛ ለምስኪኖች ጌታ ይሰጠናል
ማንም ያልጠበቀውን ያልገመተውን ድል
ለኛ ለምስኪኖች ጌታ ይሰጠናል
አዝ = = = = =
ሰዎች ቢጠበቡ ገንዘብ ለመሰብሰብ
ይጠላለፋሉ ባልጠበቁት መረብ
እግዚአብሔርን ይዘው በቅን ካልተጓዙ
ክፋትና ተንኮል ብዙ ነው መዘዙ
አዝ = = = = =
ድሆች አስለቅሶ ግፍ የሚሰበስብ
ምን ይመልስ ይሆን ጌታ ፊት ሲቀርብ
ለዚህች አጭር ዘመን የሚስገበገቡ
አይረኩም አይጠግቡም ድሆች እያስራቡ
አዝ= = = = =
የእህል ሽታ ጠፍቶ መሶቡም ቢራቆት
ተስፋችን ሙሉ ነው እኛስ በጌታ ፊት
ይህን ክፉ ዘመን ያሻግራል ጌታ
ከሠራን በኋላ በጸሎት እንበርታ
✞ መአዛህ ያዉዳል ✞
ደብረ ሊባኖስ ገዳም
መአዛህ ያዉዳል ለአለም /2/
ደብረ ሊባኖስ ላይ
ክብርህን አይተናል /2/
በጻዲቁ ፀሎት
እረፍት አግኝተናል
ቅዱስ ላሊበላ ገዳም
መአዛህ ያዉዳል ለአለም /2/
ቅዱስ ላሊባላ
የሰራህው ስራ /2/
ለእኛ መዳን ሆኖአል
ፅድቅን እንድንሰራ
ዝቋላዉ አቦ ገዳም
መአዛህ ያዉዳል ለአለም /2/
በረከትህን ናፍቀን
አምነን በምልጃህ /2/
ገብረ መንፈስ ቅዱስ
መጣን ከደጅህ
ሸንኮራዉ ዮሐንስ ገዳም
መአዛህ ያውዳል ለአለም /2/
ሽንኮራዉ ዮሐንስ
ስመ ገናና ነህ /2/
በአራቱም ማእዘን
ትመሰገናለህ
👉ዘማሪት ውዴ ታችበሌ
#Share and #join ያድርጉ፤ ያስደርጉ።
@meazahaymanot
ለሁሉ የምትሰጥ
የእውቀት አይኖችን ለሁሉ የምትሰጥ
እንዳንል አግዘን እኔ አበልጥ እኔ እበልጥ
እንዳንል አግዘን እኔ አበልጥ እኔ እበልጥ
አዝ-----
በትምክህት ሆነን በአንዳች እንዳንፈርድ
በሰው ያለው ድካም አለ በእኛም ዘንድ
በምሕረቱ ብዛት ተሸፍኖ እንጂ
እጅግ ብዙ ድካም አለ በኛ እጅ/2/
አዝ-----
ተገልጦ ነው እንጂ ኃይሉ በኛ ድካም
ኃጢአት የሌለበት አንድስ እንኳን የለም
እኔ እሻላለሁ አንበል በልባችን
አግናጥዮስ አለ በመካከላችን/2/
አዝ-----
አንዱ የአንዱን ድካም እያገዘ ይኑር
የኃጢአትን ብዛት ይሸፍናል ፍቅር
መቅደም ስለሌለ ለብቻው ሮጦ
ያጸድቀናል እንጂ እግዚአብሔር መርጦ/2/
አዝ-----
እራሱን ከፍ አድርጎ ሌላውን የሚንቅ
በአመነው አይጸናም ቅርብ ነው ለመውደቅ
የትሕትናን ሕይወት ይነግረናል ቃሉ
እኛ የማንጠቅም ባሪያዎች ነን በሉ/2/
አዝ-----
በክርስቶስ ፍቅር እንውደድ ሁሉን
ነፍሰ ገዳይ ሆነን እንዳናጣ ክብሩን
እየተባባልን የአጵሎስ የኬፋ
ካላመኑት ይልቅ ብሰን እንዳንከፋ/2/
🙏🙏አዲስ ዝማሬ በዘማሪ ዲያቆን አቤል መክብብ🙏🙏
ማኅደረ ጥያቄ
1. ያዕቆብ በሕልሙ ከምድር እስከ ሰማይ የተዘረጋች የወርቅ መሰላል ያየበት ቦታ የት ነው
2. ስለ እመቤታችን ኅቱም ድንግልና የተናገረው ነቢይ____ነው.?
3. ከሐዋርያት መካከል አስቀድሞ "አንተ የእግዚአብሔር ልጅ ነህ" ብሎ የተናገረው ማን ነው?
4. የአዳም ሰባተኛ ትውልድ ማን ነው?
5. ሊቀ-ሐዋርያት ተብሎ ሚታወቀው ማን ነበር?
መልሱን እስከ ነገ ማታ 3:00 በ @Asitmeherobot አድርሱን
🔴 አዲስ ዝማሬ " የቃል ኪዳኑ መዝገብ " ዘማሪት መስከረም ንጉሴ @-mahtot
👉#share እና #join ያድርጉ ያስደርጉ
@meazahaymanot
🌿🍁🌿🍁🌿🍁🌿🍁🌿🍁🌿🍁🌿🍁
እንኳን
#የኢትዮጽያ_ብርሃን_ለተባሉት ለታላቁ አባት ለከበረ ሐዲስ ሐዋርያ ለትሩፋትም መምህር ለሆነ #ለአቡነ_ተክለ_ሃይማኖት_በዓለ_ለዕረፍት
#የኢትዮጽያዊቷ_ጻድቅ_ቅድስት_ክርስቶስ_ሠምራ_በዓለ_ዕረፍት እና ለታላቁ አባት ለክርስቶስ ምስክር ለሐዋርያው ለመርዓስ አገር ኤጲስ ቆጶስ ለተጋዳይ #ለቅዱስ_አባት_ቶማስ በዓለ ዕረፍት በዓል በሰላም አደረሰን። በተጨማሪ በዚች ቀን ከሚታሰቡ፦ #ከአብርሃም_ከይስሐቅና_ከያዕቆብ ከመታሰቢያቸው እግዚአብሔር አምላክ ረድኤትና በረከትን ያሳትፈን።
🌿🍁🌿🍁🌿🍁🌿🍁🌿🍁🌿🍁🌿🍁
ማኅደረ ጥያቄ
1. ሊቃነ መላእክት የምንላቸው ስንት ናቸው?
2.ሐዋርያው ቅዱስ ጴጥሮስ ከሞት ያስነሳት ብላቴና ማን ትባላለች ?
3. የእመቤታችን የቅርብ ዘመዶች ተብለው በመጽሐፍ ላይ ከተቀመጡት ውስጥ ሦስቱን ጻፉ
4. ቅዳሴ ማርያምን የደረሰው ቅዱስ አባት ማን ይባላል ?
5. በዚህ ቀን የሚከበሩ ቅዱሳንን ጻፉ
መልሱን እስከ ነገ ማታ 3:00 ሰዓት @Asitmeherobot አድርሱን
#ዑራኤል_ደረሰ🌿
🥀🥀🥀🥀🥀🥀🥀🥀🥀
።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።
"ከቅዱሳን መላእክት አንዱ ኡራኤል በመብረቅና በነጎድጏድ ላይ የተሾመ ነዉ" ሄኖክ 6:3
አቤቱ የመላእክት ሁሉ አለቃ የሚሆን የቅዱስ ዑራኤል አምላክ ጌታ ኢየሱስ ክርስቶስ ሆይ በክርስቶስ ክርስቶሳውያን የተሰኘን የጥምቀት ልጆች ከመከራ ሥጋ ፤ከመከራ ነፍስ ጠብቀን ለዘለዓለሙ አሜን።🤲💐💐💐💐💐💐
✅ የቃልህ ፍቺ ያበራል፥ ሕፃናትንም አስተዋዮች ያደርጋል።”
— መዝሙር 118(119)፥130
🕎ስለ መጽሐፍ ቅዱስ ምንነት እንዲሁም በመጽሐፍ ቅዱስ ላሉት ምንባባት አንድምታቸው ትንታኔና ማብራርያ የሚያገኙበት ቻናል ይቀላቀሉ።
👉“መጽሐፍ” ለሚለው ምንጭ በግሪክ ቋንቋ ቢብሎስ (byblos) ከደንገል በተሠራ ወረቀት ወይም በብራና ከተጻፈ በኋላ በሁለት በትሮች...read more
👉መጽሐፍ ቅዱስ መቼ በአንድ ጥራዝ ተጠቀለለ? ከክ.ል.በ ይሁን በኋላ የተጻፉት ሁሉንም መጻሕፍቶች ለየብቻቸው ነበሩ፡፡ከ500ዎቹ ዓ.ዓ....read more
👉ኦሪት "ኦራይታ" ከሚል የሶርያ(አራማይክ) ቃል የተገኘ ሲሆን ትርጓሜውም "ሕግ" ወይም "ትምህርት" ማለት ነው።የመጠሪያ ምንጩም....read more
ወቅታዊ የቤተ ክርስቲያናችንን ጉዳይ እና መንፈሳዊ ጥንካሬያችንን እንድናበረታ የሚያግዙን መንፈሳዊ ቻናሎችን ይዘን ቀርበናል።እርስዎም ከእነዚህ መንፈሳዊ ቻናሎች የነፍስ ምግብ የሆነውን የእግዚአብሔርን ቃል እየተመገቡ መንፈሳዊ ሕይወትዎትን እንዲያጠናክሩ በእግዚአብሔር ስም ጥሪያችንን እናቀርባለን🙏
🙏ፈጣሪ ይባርከን🙏
ከነዚህ መፀሀፍት የተወጣጡበት
ትምህርትን መማር ይፈልጋሉ❔
እነሆ ብለናል :-
📚የባሕታውያን አባቶች ሕይወትና የመዝሙራት ተመስጦ
📖▓⇨ትምህርት በአባ ሺኖዳ ⇨ክፈት
📚የድያቢሎስ ውግያዎች
📖▓⇨ትምህርት ⇨ክፈት
📚አምደ ሀይማኖት
📖▓⇨በአባታችን ቅዱስ ሺኖዳ ⇨ክፈት
📚መንፈሳዊ ሕይወት
📖▓⇨በአቡነ ሺኖዳ ⇨ክፈት
📚መንፈሳዊ ሰው
📖▓⇨በአቡነ ሺኖዳ ⇨ክፈት
📚የአባቶች ሕይወት ንሮ እና ተመስጦ
📖▓⇨በአቡነ ሺኖዳ ⇨ክፈት
የመኖኮሳት ታሪክ እና ተመስጦ በብጽእ አቡነ ሺኖዳ ሳልሳዊ ይቀርብበታል።
ማኅደረ ጥያቄ
1. ፍኖተ ሎዛ
ይኸውም ያዕቆብ ከአባቱ ከይሥሐቅ በረከትን ተቀብሎ ወደ አጐቱ ወደ ላባ ሲኼድ መሸበትና መንገድ እልፍ ብሎ ደንጊያ ተንተርሶ ቢተኛ በሕልሙ የወርቅ መሰላል ከምድር እስከ ሰማይ ተተክላ፤ መላእክት በእርከኗ ሲወጡባት ሲወርዱባት፤ በላይዋ ላይ ዙፋን ተነጽፎባት፤ በዚያ ላይ ልዑል እግዚአብሔር ተቀምጦባት አይቷል፡፡
ኦሪት ዘፍጥረት 28÷10-22
2. ርኢኩ ኆኅተ በምሥራቅ ኀቱም በዓቢይ መንክር ማኀተም አልቦ ዘቦአ ዘእንበለ እግዚአ ኃያላን” “በታላቅ ቁልፍ የተዘጋች ደጅ በመሥራቅ አየሁ ከኃያላን ጌታ በቀር ወደ እርስዋ ገብቶ የወጣ የለም” /ህዝ 4፡4/
3. ጴጥሮስ “አንተ ክርስቶስ የህያው እግዚአብሔር ልጅ ነህ”(ማቴ.16፥16)
4. ሔኖክ ኦሪት ዘፍጥረት ምዕራፍ ፭÷፲፰ ይሁዳ ፩÷፲፬
መጽሐፈ ዜና መዋዕል ቀዳማዊ ምዕራፍ ፩÷፫
5. ሊቀ ሐዋርያት ቅዱስ_ጴጥሮስ
የተሣተፉ
1. ፀጋ 4/5
2. ወለተ ኢየሱስ 3/5
3. ኪዳነ ምህረት እናቴ 4/5
4. ታምሩ 5/5
5. መስኪ 5/5
6. ቅድስት 4/5
7. Tig 5/5
8. እያየሁ እንዳላየሁ 5/5
9. ሳራ 4/5
10. Ephrem B 4/5
11. Dagi 5/5
12.Tomi 5/5
13. ቤተልሔም። 3/5
14. Grumita 5/5
15. Tigist F 5/5
16. ዲ/ን ፍሬው 5/5
ለተሣተፉት ቃለ ሕይወትን ያሰማልን
ማኅደረ ጥያቄ
1. ያዕቆብ በሕልሙ ከምድር እስከ ሰማይ የተዘረጋች የወርቅ መሰላል ያየበት ቦታ የት ነው
2. ስለ እመቤታችን ኅቱም ድንግልና የተናገረው ነቢይ____ነው.?
3. ከሐዋርያት መካከል አስቀድሞ "አንተ የእግዚአብሔር ልጅ ነህ" ብሎ የተናገረው ማን ነው?
4. የአዳም ሰባተኛ ትውልድ ማን ነው?
5. ሊቀ-ሐዋርያት ተብሎ ሚታወቀው ማን ነበር?
መልሱን እስከ ማታ 3:00 በ @Asitmeherobot አድርሱን
✅ የቃልህ ፍቺ ያበራል፥ ሕፃናትንም አስተዋዮች ያደርጋል።”
— መዝሙር 118(119)፥130
🕎ስለ መጽሐፍ ቅዱስ ምንነት እንዲሁም በመጽሐፍ ቅዱስ ላሉት ምንባባት አንድምታቸው ትንታኔና ማብራርያ የሚያገኙበት ቻናል ይቀላቀሉ።
👉“መጽሐፍ” ለሚለው ምንጭ በግሪክ ቋንቋ ቢብሎስ (byblos) ከደንገል በተሠራ ወረቀት ወይም በብራና ከተጻፈ በኋላ በሁለት በትሮች...read more
👉መጽሐፍ ቅዱስ መቼ በአንድ ጥራዝ ተጠቀለለ? ከክ.ል.በ ይሁን በኋላ የተጻፉት ሁሉንም መጻሕፍቶች ለየብቻቸው ነበሩ፡፡ከ500ዎቹ ዓ.ዓ....read more
👉ኦሪት "ኦራይታ" ከሚል የሶርያ(አራማይክ) ቃል የተገኘ ሲሆን ትርጓሜውም "ሕግ" ወይም "ትምህርት" ማለት ነው።የመጠሪያ ምንጩም....read more
ወቅታዊ የቤተ ክርስቲያናችንን ጉዳይ እና መንፈሳዊ ጥንካሬያችንን እንድናበረታ የሚያግዙን መንፈሳዊ ቻናሎችን ይዘን ቀርበናል።እርስዎም ከእነዚህ መንፈሳዊ ቻናሎች የነፍስ ምግብ የሆነውን የእግዚአብሔርን ቃል እየተመገቡ መንፈሳዊ ሕይወትዎትን እንዲያጠናክሩ በእግዚአብሔር ስም ጥሪያችንን እናቀርባለን🙏
🙏ፈጣሪ ይባርከን🙏
ከነዚህ መፀሀፍት የተወጣጡበት
ትምህርትን መማር ይፈልጋሉ❔
እነሆ ብለናል :-
📚የባሕታውያን አባቶች ሕይወትና የመዝሙራት ተመስጦ
📖▓⇨ትምህርት በአባ ሺኖዳ ⇨ክፈት
📚የድያቢሎስ ውግያዎች
📖▓⇨ትምህርት ⇨ክፈት
📚አምደ ሀይማኖት
📖▓⇨በአባታችን ቅዱስ ሺኖዳ ⇨ክፈት
📚መንፈሳዊ ሕይወት
📖▓⇨በአቡነ ሺኖዳ ⇨ክፈት
📚መንፈሳዊ ሰው
📖▓⇨በአቡነ ሺኖዳ ⇨ክፈት
📚የአባቶች ሕይወት ንሮ እና ተመስጦ
📖▓⇨በአቡነ ሺኖዳ ⇨ክፈት
የመኖኮሳት ታሪክ እና ተመስጦ በብጽእ አቡነ ሺኖዳ ሳልሳዊ ይቀርብበታል።
ማኅደረ ጥያቄ
1.ነገር የሚለው ቃል ሲተረጎም ፡- ወግ፣ ታሪክ፣ መልዕክት፣ ሥርዓት ተብሎ ሊተረጎም ይችላል
2. ቤተ ክርስቲያን የሚለው ቃል ሦስት ዓይነት ሰዋስዋዊና ዘይቤአዊ ትርጕም አለው (አባ ጎርጎርዮስ ፲፱፻፸፰፣ ገጽ ፲፪-፲፯)፡፡
• የመጀመሪያው ሕንፃ ቤተ ክርስቲያንን ያመለክታል፡፡ ይኸውም ሐዋርያው ቅዱስ ጳውሎስ፡- “ወደ ማኅበር ስትሰበሰቡ በመካከላችሁ መለያየት እንዳለ እሰማለሁ” (፩ኛ ቆሮ. ፲፩፡፲፰) እንዳለው የክርስቲያኖች ቤት፣ የክርስቲያኖች መኖሪያ ማለት ነው፡፡ መንፈስ ቅዱስ ባወቀ የክርስቶስ ደም በነጠበበት የምትተከል፣ በብፁዓን ሊቃነ ጳጳሳት በቅዱስ ሜሮን የከበረች፣ ሥላሴ በአንድነት በሦስትነት የሚመሰገኑባት፣ የክርስቶስ ሥጋዌ የሚነገርባት፣ ሥጋውና ደሙ የሚፈተትባት ቅድስት መካን ቤተ ክርስቲያን ተብላ እንደተጠራች ቅዱሳት መጻሕፍት በስፋት ይገልጻሉ፡፡
“ቤተ ክርስቲያን እንሒድ ባሉኝ ጊዜ ደስ አለኝ” (መዝ. ፻፳፩፡፩)፤ “በቤተ ክርስቲያንም አንድ ዓመት ሙሉ ተሰበሰቡ” (ሐዋ. ፲፩፡፳፮) የሚሉት ንባቦች የቤተ ክርስቲያን አንደኛው ዘይቤአዊ ትርጕም ሕንፃ ቤተ ክርስቲያን መሆኑን ያስረዳሉ፡፡
• ሁለተኛው ደግሞ እያንዳንዱ ምእመን (ክርስቲያን) ቤተ ክርስቲያን የሚባል መሆኑን የሚያስገነዝብ ትርጕም አለው፡፡ ብርሃነ ዓለም ቅዱስ ጳውሎስ “የእግዚአብሔር ቤተ መቅደስእንደሆናችሁ የእግዚአብሔርም መንፈስ እንዲኖርባችሁ አታውቁምን? ማንም የእግዚአብሔርን ቤተ መቅደስ ቢያፈርስ እግዚአብሔር እርሱን ያፈርሰዋል፤ የእግዚአብሔር ቤተመቅደስ ቅዱስ ነውና፥ ያውም እናንተ ናችሁ” (፩ኛ ቆሮ. ፫፡፲፮)፣ “… ወይስ ሥጋችሁ ከእግዚአብሔር የተቀበላችሁት በእናንተ የሚኖረው የመንፈስ ቅዱስ ቤተ መቅደስ እንደ ሆነአታውቁምን? በዋጋ ተገዝታችኋልና ለራሳችሁ አይደላችሁም፤ ስለዚህ በሥጋችሁ እግዚአብሔርን አክብሩ” (፩ኛ ቆሮ. ፮፡፲፱) በማለት የገለጸው ይህን ነው፡፡ ይኸውም በመንፈሳዊና በምሥጢራዊ ልደት ከክርስቶስ የተወለዱ፥ እርሱ አድሮባቸው የሚኖሩ፥ በቅዱስ ሜሮን የታተሙ (፩ኛ ዮሐ. ፪፡፳) እና ሥጋውንና ደሙን የተቀበሉ ምእመናንን ለማመልከት ነው፡፡
• ሦስተኛው ትርጕም ደግሞ “በባቢሎን ያለች ቤተ ክርስቲያን ልጄም ማርቆስ ሰላምታ ያቀርቡላችኋል” (፩ኛ ጴጥ. ፭፡፲፫) እንዲል የክርስቲያኖችን ኅብረት ወይም አንድነት (ማኅበረ ምእመናንን) የሚያመለክት ነው፡፡
3. ግሪኮች “ኤክሌሲያ” የሚለውን ቃል መጀመሪያ አንድን ፖለቲካዊ፣ ማኅበራዊ ወይም አስተዳደራዊ ችግር ለመፍታት ለተሰበሰቡ ሽማግሌዎች መጠሪያ ይጠቀሙበት ነበር፡፡ በ፪፻፹፬ ከክርስቶስ ልደት በፊት ብሉይ ኪዳንን ከዕብራይስጥ ወደ ጽርዕ የተረጐሙት ሰብዓ ሊቃናት ግን “ቀሃል” የሚለውን የዕብራይስጥ ቃል “ኤክሌሲያ” ብለው ተርጕመውታል፡፡
የተሣተፉ
1. ያለም ሰው 3/3
2. እኔም ትውልድ ነኝ 3/3
3. Tig. 3/3
4. ዘላለም 3/3
5. ወለተ ሰማዕት 2.5/3
6. ቤተልሔም 3/3
7. G/eysus 3/3
8. Grumita 3/3
ለተሳተፉት ቃለ ሕይወትን ያሰማልን መንግሥተ ሰማያትን ያውርስልን በቤቱ ያጽናልን
ማኅደረ ጥያቄ
1. ነገር ማለት ምን ማለት ነው
2. ቤተ ክርስቲያን የሚለውንም ቃል ስንተረጉመው ስንት ትርጓሜ ይሰጠናል
3. ኤክሌሲያ ማለት ምን ማለት ነው.
መልሱን እስከ ማታ 3:00 ሰዓት በ @Asitmeherobot ያድርሱን
ማኅደረ ጥያቄ
1. ነገር ማለት ምን ማለት ነው
2. ቤተ ክርስቲያን የሚለውንም ቃል ስንተረጉመው ስንት ትርጓሜ ይሰጠናል
3. ኤክሌሲያ ማለት ምን ማለት ነው.
መልሱን እስከ ማታ 3:00 ሰዓት በ @Asitmeherobot ያድርሱን