meazahaymanot | Unsorted

Telegram-канал meazahaymanot - መዓዛ ሃይማኖት በጎ አድራጎትና ጉዞ ማህበር

3925

"ውድስት አንቲ በአፈ ነቢያት ወስብሕት በሐዋርያት አክሊለ በረከቱ ለያዕቆብ ወትምክህተ ቤቱ ለእስራኤል፡፡" "በነቢያት በሐዋርያት አንደበት የተመሰገንሽ የያዕቆብ የበረከቱ ዘውድ የእስራኤል ወገን መመኪያ አንቺ ነሽ"                  መጽሐፈ ሰዓታት የፌስቡክ ፔጃችን www.fb.me/meazhaimanot ይቀላቀሉን

Subscribe to a channel

መዓዛ ሃይማኖት በጎ አድራጎትና ጉዞ ማህበር

የዕለቱ መልእክት

የእግዚአብሔር ስም ጽኑ ግንብ ነው፤
ጻድቅ ወደ እርሱ በመሮጥ ከፍ ከፍ ይላል።

መጽሐፈ ምሳሌ ፲፰÷፲

Читать полностью…

መዓዛ ሃይማኖት በጎ አድራጎትና ጉዞ ማህበር

ይህችን እድሜ

ይህችን እድሜ ለንስሐ የሠጠኸኝ
ተመስገን ተመስገንልኝ
መጨረሻዬን አሳምርልኝ
ተመስገን ተመስገንልኝ
       አዝ-----
የቅዱሳንን ፈለግ ተከትዬ
በዘመኔ ሁሉ አንተን አገልግዬ
ከጸኑት ጋር ልጽና አበርታኝ አምላኬ
ሳወድስህ ልኑር/2/ፊትህ ተንበርክኬ
       አዝ-----
ጳውሎስን የጠራ በደማስቆ
እንዳገለገለ የዐይኑ ቅርፊት ወልቆ
አድርገኝ ምርጥ እቃ መድኃኒቴ
ልኑር እንደቃልህ /2/በሕይወቴ
       አዝ-----
የቦሄዝን እርሻ መቃረሟን
ባለ ዕርስት ያረጋት ዘለዐለሟን
እንደ ሩት አድርገኝ ልበ ትሁት
ትዕዛዝህ ይሁነኝ/2/ ለእግሬ መብራት
       አዝ-----
በሠጠኸኝ ዕድሜ በአዲሱ ቀን
ካንተ ጋራ መኖር በመወሰን
ለዘለዓለም ሕይወት ልጅህ እንድበቃ
በጥበብ አኑረኝ በታመነው ቃልህ ነፍሴ ተጠብቃ


🙏🙏በዘማሪት ሲስተር ሕይወት ተፈሪ🙏🙏


@meazahaymanot
@meazahaymanot

Читать полностью…

መዓዛ ሃይማኖት በጎ አድራጎትና ጉዞ ማህበር

ስንክሳር ዘውርሃ መስከረም ሁለት(፪)
/channel/meazahaymanot

Читать полностью…

መዓዛ ሃይማኖት በጎ አድራጎትና ጉዞ ማህበር

ማኅደረ ጥያቄ

መንፈሳዊ ጥያቄ

1. የሊቀ ሰማዕታት የቅዱስ ጊዮርጊስ ትውልድ ቦታ የትነው

2. አምስቱ አዕማደ ምሥጢራትን በቅደም ተከተል ዘርዝሩ

3. ሰማዕቱ ቅዱስ ጊዮርጊስ ስንት ዓመት ተጋደለ?

4.ጌታ ሆይ መቅጃ የለህም ጕድጓዱም ጥልቅ ነው፤ እንግዲህ የሕይወት ውኃ ከወዴት ታገኛለህ? በማለት ጌታን ያነጋገረችው ሴት ማን ነች?

5.ከሠላሳ ስምንት ዓመት ጀምሮ ታምሞ የነበረው ሰው የተፈወሰው ቤተ ሳይዳ በመባል በምትታወቀው መጠመቂያ ተጠምቆ ነው። እውነት ወይስ ሐሰት?

6. ጳጉሜ ማለት ምን ማለት ነው

መልሱን እስከ ማታ 4:00 ⌚ በ  @Asitmeherobot አድርሱን

መልካም ዕድል

Читать полностью…

መዓዛ ሃይማኖት በጎ አድራጎትና ጉዞ ማህበር

ስንክሳር ዘወርሃ ጳጉሜን ሁለት(፪)
/channel/meazahaymanot

Читать полностью…

መዓዛ ሃይማኖት በጎ አድራጎትና ጉዞ ማህበር

✞ምስጋና እናቅርብ✞

በደስታ በሐሴት ዘለለ
መጥምቀ መለኮት በማህጸን ሳለ
በደስታ በሐሴት ዘለለ
    
የድንግል ሰላምታዋን በእናቱ ሆድ ሰምቶ
በደስታ ዘለለ ፍስሐን ተሞልቶ
ምን ያለ ድምጽ ነው እንዴት ቢያስደስተው
ዮሐንስ ማህፀን ውስጥ ደስታ ያዘለለው(፪)
አዝ= = = = =
በመንፈስቅዱስ ሙላት ኤልሳቤጥ ደስ አላት
ሰላምታ አቀረበች ሰግዳ ለአምላክ እናት
የስድስት ወር ፅንሷ ድንግልን ሲሰማ
በሆዷ አወደሰ በቅኔ በዜማ(፪)
አዝ= = = = =
ፅንሱ በማህጸን ሳለ የስድስት ወር
አንደበት ሆነችው እናቱ ስትዘምር
የወንጌል ሰባኪ የጌታ ምስክር
ደስታ አዘለለው ለአምላክ እናት ክብር(፪)

መዝሙር
ትንቢት ቦጋለ

"ኤልሳቤጥም የማርያምን ሰላምታ በሰማች ጊዜ ፅንሱ በማኅፀንዋ ውስጥ ዘለለ፤"
ሉቃ፩፥፵፩
╭══•|❀:✧๑♡๑✧❀|: ══╮
    @meazahaymanot
╰══•ೋ•✧๑♡๑✧•  ══╯

Читать полностью…

መዓዛ ሃይማኖት በጎ አድራጎትና ጉዞ ማህበር

✞ምስጋና ለስምሽ✞

ምስጋና ለስምሽ ድንግል እመቤቴ
በአንቺ አማላጅነት ድኅነት በማግኘቴ
ቅዱሳን አባቶች ቀንም ከለሊት
ለአንቺ ይቀኛሉ እንዲህ በማለት

ከሀገረ ብህንሳ ፍቅርሽ አስገድዶት
የአንቺ ንጽህና ፍጹም አስደንቆት
አባ ሕርያቆስ ተሞልቶ በመንፈስ
ድንግል ሆይ አለ አንቺን ለማወደስ
አዝ= = = = =
ፋራን የተሰኘሽ የዕንባቆም ተራራ
በረከት የሞላሽ የገነት አዝመራ
እፀ ጳጦስ የተባልሽ የሙሴ ፅላት
የይስሐቅ መዓዛ የአብርሃም ደግነት
አዝ= = = = =
እንደተናገረው ዳዊት በትንቢቱ
በቀኝ ትቆማለች አምራ ንግሥቲቱ
ባለ ገንዘቦችም አሕዛብ በሙሉ
ለክብርሽ ዝቅ ብለው ለአንቺ ይሰግዳሉ
አዝ= = = = =
ዓለም የዳነብሽ አንቺ የኖህ መርከብ
ምስጋናሽ መብዛቱ እንደ ሰማይ ኮከብ
ዘወትር ሁል ጊዜ ቢሰላ ቢወራ
ድንግል ሆይ አያልቅም የአንቺ ድንቅ ሥራ

መዝሙር
በዓምደ ሃይማኖት ሰ/ት/ቤት

"ከእናንተ መከራን የሚቀበል ማንም
ቢኖር እርሱ ይጸልይ ደስ የሚለውም
ማንም ቢኖር እርሱ ይዘምር"


ያዕ ፭፥፲፫
╭══•|❀:✧๑♡๑✧❀|: ══╮
@meazahaymanot
╰══•ೋ•✧๑♡๑✧• ══╯

Читать полностью…

መዓዛ ሃይማኖት በጎ አድራጎትና ጉዞ ማህበር

ዓውደ ስብከት

🛑የኃጥያተኞች መንገድ ትጠፋለች || እጅግ ድንቅ ትምህርት በርእሰ ሊቃውንት አባ ገብረኪዳን ግርማ

Читать полностью…

መዓዛ ሃይማኖት በጎ አድራጎትና ጉዞ ማህበር

ከአሁን ጀምሮ እንደተለመደው ለቻናላችን ያላችሁን ሀሳብ አስተያየት ማቅረብ ትችላላችሁ። ቢኖሩ፣ ቢስተካከሉ የምትሏቸው ጉዳዮች ላይ አተኩራችሁ ስማችሁንና ከየት ሀገር እንደሆናችሁ እየገለጻችሁ በድምጽ ሆነ በጽሑፍ ላኩልን። ቤተሰቦቻችን የት የት እንዳሉም እንድናውቅና እንድንተዋወቅ ይረዳናል     ላይ @misiwani_Bot እንጠብቃችኋለን

ሐሳብ አስተያየታቸውን ጻፉልን

Читать полностью…

መዓዛ ሃይማኖት በጎ አድራጎትና ጉዞ ማህበር

ስንክሳር ዘወርሃ ነሐሴ ሃያ ስምንት ያዕቆብ(፳፰)
/channel/meazahaymanot

Читать полностью…

መዓዛ ሃይማኖት በጎ አድራጎትና ጉዞ ማህበር

ስንክሳር ዘወርሃ ነሐሴ ሃያ ሰባት(፳፯)
/channel/meazahaymanot

Читать полностью…

መዓዛ ሃይማኖት በጎ አድራጎትና ጉዞ ማህበር

✅ የቃልህ ፍቺ ያበራል፥ ሕፃናትንም አስተዋዮች ያደርጋል።”
— መዝሙር 118(119)፥130
🕎ስለ መጽሐፍ ቅዱስ ምንነት እንዲሁም በመጽሐፍ ቅዱስ ላሉት ምንባባት አንድምታቸው ትንታኔና ማብራርያ የሚያገኙበት ቻናል ይቀላቀሉ።

👉“መጽሐፍ” ለሚለው ምንጭ በግሪክ ቋንቋ ቢብሎስ (byblos) ከደንገል በተሠራ ወረቀት ወይም በብራና ከተጻፈ በኋላ በሁለት በትሮች...read more

👉መጽሐፍ ቅዱስ መቼ በአንድ ጥራዝ ተጠቀለለ? ከክ.ል.በ ይሁን በኋላ የተጻፉት ሁሉንም መጻሕፍቶች ለየብቻቸው ነበሩ፡፡ከ500ዎቹ ዓ.ዓ....read more

👉ኦሪት "ኦራይታ" ከሚል የሶርያ(አራማይክ) ቃል የተገኘ ሲሆን ትርጓሜውም "ሕግ" ወይም "ትምህርት" ማለት ነው።የመጠሪያ ምንጩም....read more



ወቅታዊ የቤተ ክርስቲያናችንን ጉዳይ እና መንፈሳዊ ጥንካሬያችንን እንድናበረታ የሚያግዙን መንፈሳዊ ቻናሎችን ይዘን ቀርበናል።እርስዎም ከእነዚህ መንፈሳዊ ቻናሎች የነፍስ ምግብ የሆነውን የእግዚአብሔርን ቃል እየተመገቡ መንፈሳዊ ሕይወትዎትን እንዲያጠናክሩ በእግዚአብሔር ስም ጥሪያችንን እናቀርባለን🙏
🙏ፈጣሪ ይባርከን🙏

ከነዚህ መፀሀፍት የተወጣጡበት
ትምህርትን መማር ይፈልጋሉ❔
እነሆ ብለናል :-
📚የባሕታውያን አባቶች ሕይወትና የመዝሙራት ተመስጦ
📖▓⇨ትምህርት በአባ ሺኖዳ ⇨ክፈት
📚የድያቢሎስ ውግያዎች
📖▓⇨ትምህርት ⇨ክፈት
📚አምደ ሀይማኖት
📖▓⇨በአባታችን ቅዱስ ሺኖዳ ⇨ክፈት
📚መንፈሳዊ ሕይወት
📖▓⇨በአቡነ ሺኖዳ ⇨ክፈት
📚መንፈሳዊ ሰው
📖▓⇨በአቡነ ሺኖዳ ⇨ክፈት
📚የአባቶች ሕይወት ንሮ እና ተመስጦ
📖▓⇨በአቡነ ሺኖዳ ⇨ክፈት
የመኖኮሳት ታሪክ እና ተመስጦ በብጽእ አቡነ ሺኖዳ ሳልሳዊ ይቀርብበታል።

Читать полностью…

መዓዛ ሃይማኖት በጎ አድራጎትና ጉዞ ማህበር

#ዓለም የተጣላቸው እነሱም የናቁ፣
#አይሆነንም ብለው ዞር ብለው ያላዩ።
#በተግባር የሚታይ ለጽድቅ መኖራቸው፣
#እውነተኛ አገልጋይ ቅዱሳኑ ናቸው።

#እነሱን ቢያረገኝ ተመኘሁ፣
#እነሱን ቢያረገኝ ተመኘሁ፣

#ለስማቸው ቅኔን ተቀኘሁ፣
#ለክብራቸው ቅኔን ተቀኘሁ።

#Join:/channel/meazahaymanot

Читать полностью…

መዓዛ ሃይማኖት በጎ አድራጎትና ጉዞ ማህበር

🔴 አዲስ ዝማሬ " አባ ተክለ ሃይማኖት " ዘማሪ ዲያቆን እንዳለ ደረጄ @-mahtot

👉
#share እና #join ያድርጉ ያስደርጉ
👉
@enatachinmaryam
👉
@enatachinmaryam
👉
@enatachinmaryam

Читать полностью…

መዓዛ ሃይማኖት በጎ አድራጎትና ጉዞ ማህበር

ማኅደረ ጥያቄ



1. ሊቃነ መላእክት የምንላቸው ስንት ናቸው?

2.ሐዋርያው ቅዱስ ጴጥሮስ ከሞት ያስነሳት ብላቴና ማን ትባላለች ?


3. የእመቤታችን የቅርብ ዘመዶች ተብለው በመጽሐፍ ላይ ከተቀመጡት ውስጥ ሦስቱን ጻፉ

4. ቅዳሴ ማርያምን የደረሰው ቅዱስ አባት ማን ይባላል ?

5. በዚህ ቀን የሚከበሩ ቅዱሳንን ጻፉ

መልሱን እስከ ማታ 3:00 ሰዓት @Asitmeherobot  አድርሱን

Читать полностью…

መዓዛ ሃይማኖት በጎ አድራጎትና ጉዞ ማህበር

ስንክሳር ዘውርሃ መስከረም ሦስት(፫)
/channel/meazahaymanot

Читать полностью…

መዓዛ ሃይማኖት በጎ አድራጎትና ጉዞ ማህበር

የዕለቱ መልእክት

ልጄ ሆይ፥ ሕጌን አትርሳ፥ ልብህም ትእዛዛቴን ይጠብቅ።
 ብዙ ዘመናትና ረጅም ዕድሜ ሰላምም ይጨምሩልሃልና።
 ምሕረትና እውነት ከአንተ አይራቁ፤ በአንገትህ እሰራቸው፤ በልብህ ጽላት ጻፋቸው።
 በእግዚአብሔርና በሰው ፊትም ሞገስንና መልካም ዝናን ታገኛለህ።
 በፍጹም ልብህ በእግዚአብሔር ታመን፥ በራስህም ማስተዋል አትደገፍ፤
በመንገድህ ሁሉ እርሱን እወቅ፥ እርሱም ጎዳናህን ያቀናልሃል።
መጽሐፈ ምሳሌ ፫÷፭-፮

Читать полностью…

መዓዛ ሃይማኖት በጎ አድራጎትና ጉዞ ማህበር

✅ የቃልህ ፍቺ ያበራል፥ ሕፃናትንም አስተዋዮች ያደርጋል።”
— መዝሙር 118(119)፥130
🕎ስለ መጽሐፍ ቅዱስ ምንነት እንዲሁም በመጽሐፍ ቅዱስ ላሉት ምንባባት አንድምታቸው ትንታኔና ማብራርያ የሚያገኙበት ቻናል ይቀላቀሉ።

👉“መጽሐፍ” ለሚለው ምንጭ በግሪክ ቋንቋ ቢብሎስ (byblos) ከደንገል በተሠራ ወረቀት ወይም በብራና ከተጻፈ በኋላ በሁለት በትሮች...read more

👉መጽሐፍ ቅዱስ መቼ በአንድ ጥራዝ ተጠቀለለ? ከክ.ል.በ ይሁን በኋላ የተጻፉት ሁሉንም መጻሕፍቶች ለየብቻቸው ነበሩ፡፡ከ500ዎቹ ዓ.ዓ....read more

👉ኦሪት "ኦራይታ" ከሚል የሶርያ(አራማይክ) ቃል የተገኘ ሲሆን ትርጓሜውም "ሕግ" ወይም "ትምህርት" ማለት ነው።የመጠሪያ ምንጩም....read more



ወቅታዊ የቤተ ክርስቲያናችንን ጉዳይ እና መንፈሳዊ ጥንካሬያችንን እንድናበረታ የሚያግዙን መንፈሳዊ ቻናሎችን ይዘን ቀርበናል።እርስዎም ከእነዚህ መንፈሳዊ ቻናሎች የነፍስ ምግብ የሆነውን የእግዚአብሔርን ቃል እየተመገቡ መንፈሳዊ ሕይወትዎትን እንዲያጠናክሩ በእግዚአብሔር ስም ጥሪያችንን እናቀርባለን🙏
🙏ፈጣሪ ይባርከን🙏

ከነዚህ መፀሀፍት የተወጣጡበት
ትምህርትን መማር ይፈልጋሉ❔
እነሆ ብለናል :-
📚የባሕታውያን አባቶች ሕይወትና የመዝሙራት ተመስጦ
📖▓⇨ትምህርት በአባ ሺኖዳ ⇨ክፈት
📚የድያቢሎስ ውግያዎች
📖▓⇨ትምህርት ⇨ክፈት
📚አምደ ሀይማኖት
📖▓⇨በአባታችን ቅዱስ ሺኖዳ ⇨ክፈት
📚መንፈሳዊ ሕይወት
📖▓⇨በአቡነ ሺኖዳ ⇨ክፈት
📚መንፈሳዊ ሰው
📖▓⇨በአቡነ ሺኖዳ ⇨ክፈት
📚የአባቶች ሕይወት ንሮ እና ተመስጦ
📖▓⇨በአቡነ ሺኖዳ ⇨ክፈት
የመኖኮሳት ታሪክ እና ተመስጦ በብጽእ አቡነ ሺኖዳ ሳልሳዊ ይቀርብበታል።

Читать полностью…

መዓዛ ሃይማኖት በጎ አድራጎትና ጉዞ ማህበር

✞ አባ አቡነ ✞

አባ አቡነ አባ መምህርነ
ተክለሃይማኖት ባርከነ(፪)
አባ መምህርነ

ስም አጠራርህ የከበረ ነው
ተክለሃይማኖት ስራህ ድንቅ ነው
በቤትህ ሆነን ሁሉን አገኘን
በጸሎትህ ኃይል እንመካለን(፪)
  አዝ= = = = =
ከገድልህ ፅናት ወደቁ አጋንንት
ክብርህ ብዙ ነው ተክለሃይማኖት
መንጋውን ጠብቅ ዛሬም እንደጥንቱ
ጠላት የሚያርቅ ስምህ ነው ብርቱ(፪)
  አዝ= = = = =
በእጅህ በረከት በቃልህ ትምህርት
ሆነሀል ለእኛ የእምነት አብነት
የወንጌል መምህር ታማኝ እረኛ
ቀድመህ ምትገኝ ዛሬም ስለኛ(፪)
  አዝ= = = = =
በደብረ አስቦ የቆምከው ቁመት
ደብረሊባኖስ የጸለይክበት
ድውያን ሁሉ ይፈወሳሉ
መድኃኒት ሆኗል እምነት ጠበሉ(፪)

መዝሙር
ዘማሪት መቅደስ ማሪዬ

" ቅዱሳን በዓለም ላይ እንዲፈርዱ አታውቁምን?"

፩ቆሮ ፮ ፥ ፪
╭══•|❀:✧๑♡๑✧❀|: ══╮
@meazahaymanot
╰══•ೋ•✧๑♡๑✧• ══╯

Читать полностью…

መዓዛ ሃይማኖት በጎ አድራጎትና ጉዞ ማህበር

ማኅደረ ጥያቄ

መንፈሳዊ ጥያቄ

1. የሊቀ ሰማዕታት የቅዱስ ጊዮርጊስ ትውልድ ቦታ የትነው

2. አምስቱ አዕማደ ምሥጢራትን በቅደም ተከተል ዘርዝሩ

3. ሰማዕቱ ቅዱስ ጊዮርጊስ ስንት ዓመት ተጋደለ?

4.ጌታ ሆይ መቅጃ የለህም ጕድጓዱም ጥልቅ ነው፤ እንግዲህ የሕይወት ውኃ ከወዴት ታገኛለህ? በማለት ጌታን ያነጋገረችው ሴት ማን ነች?

5.ከሠላሳ ስምንት ዓመት ጀምሮ ታምሞ የነበረው ሰው የተፈወሰው ቤተ ሳይዳ በመባል በምትታወቀው መጠመቂያ ተጠምቆ ነው። እውነት ወይስ ሐሰት?

6. ጳጉሜ ማለት ምን ማለት ነው

መልሱን እስከ ማታ 4:00 ⌚ በ @Asitmeherobot አድርሱን

መልካም ዕድል

Читать полностью…

መዓዛ ሃይማኖት በጎ አድራጎትና ጉዞ ማህበር

ስንክሳር ዘወርሃ ጳጉሜን አንድ (፩)
/channel/meazahaymanot

Читать полностью…

መዓዛ ሃይማኖት በጎ አድራጎትና ጉዞ ማህበር

ስንክሳር ዘወርሃ ነሐሴ ሠላሳ (፴)
/channel/meazahaymanot

Читать полностью…

መዓዛ ሃይማኖት በጎ አድራጎትና ጉዞ ማህበር

ስንክሳር ዘወርሃ ነሐሴ ሃያ ዘጠኝ(፳፱)
/channel/meazahaymanot

Читать полностью…

መዓዛ ሃይማኖት በጎ አድራጎትና ጉዞ ማህበር

     እግዚአብሔር ያፅናናሽ

እግዚአብሔር ያፅናናሽ እንባሽን ያብሰው
ቤተክርስቲያን ሆይ እስከመጨረሻው
ካህንሽ በመቅደስ ከበጎቹ ጋራ ስለታረደብሽ
እንደ ራሔል እንባ እግዚአብሔር ያስብሽ

ስለ ጌታ ፍቅር ማህተሟን ይዛ አክሊል ተቀዳጀች
በደሙ ከዋጃት ከክርስቶስ ጋራ እኖራለሁ አለች
የእምነት ሰማዕትነት ሲመጣ በገሃድ
ይሻሙ ነበረ ከእሳቱ ለመንደድ
         አዝ
በዚህ በእኛ ዘነን ቅዱሳን ተሻሙ
አክሊልን ለመውሰድ ከሁሉ ሊቀድሙ
የተክለ ሃይማኖት የክርስቶስ ሰምራ ህፃናት ተነሱ
በመሞት ህይወትን ከእግዚአብሔር ሊወርሱ
        አዝ
አህዛብ አትድከም በመግደል አትፀድቅም
ነፍሰ ገዳይነት አሸንፎ አያውቅም
በበቀል ጭካኔ የሰው ልጅን ማረድ
እጅግ የወጣ ነው ከሃይማኖት መንገድ
         አዝ
እቺ ቤተክርስቲያን የተገነባችው በደም ስለሆነ
በሞት ህይወት ሊያገኝ ክርስትያን ታመነ
ምድሪቱ ለእግዚአብሔር የተቀደሰች ናት
ህዝቧም ሊወድቅ ቀርቧል እንደበግ መስዋዕት

          ሊቀ መዘምራን ይልማ ሃይሉ

Читать полностью…

መዓዛ ሃይማኖት በጎ አድራጎትና ጉዞ ማህበር

ቸሩ ሆይ

ቸሩ ሆይ ቸሩ ሆይ ናና
ቸሩ ሆይ አማኑኤል ናና
የእስራኤል መና ቸሩ ሆይ ናና
ቸሩ ሆይ መድኃኔዓለም ናና

        አዝ....
ቸሩ ሆይ… ለዓይነ ስውር መሪ
ቸሩ ሆይ..ምርኩዝ መመኪያ ነህ
ቸሩ ሆይ… አንተን የሚመስል
ቸሩ ሆይ… ምንም ነገር የለም
ቸሩ ሆይ …ምሕረትና ፍቅርህ
ቸሩ ሆይ… ወሰን ወደር የለው
ቸሩ ሆይ …ሳንወድህ ወደኸን
ቸሩ ሆይ… ፈልገህ ጠራኸን

      አዝ....
ቸሩ ሆይ ሰምተህ እንዳልሰማህ
ቸሩ ሆይ አይተህ እንዳላየህ
ቸሩ ሆይ ሁሉን ታልፈዋለህ
ቸሩ ሆይ ፍቅራዊ አባት ነህ
ቸሩ ሆይ አማኑኤል ጌታ
ቸሩ ሆይ ቸሩ ፈጣሪያችን
ቸሩ ሆይ ውለታህ ብዙ ነው
ቸሩ ሆይ ለኛ የዋልክልን

       አዝ....
ቸሩ ሆይ በከብቶች ማደሪያ
ቸሩ ሆይ በዚያች ትንሽ ግርግም
ቸሩ ሆይ ተወልዶ አዳነን
ቸሩ ሆይ ጌታ መድኃኒዓለም
ቸሩ ሆይ እልል በሉ ሰዎች
ቸሩ ሆይ በአንድ ላይ ዘምሩ
ቸሩ ሆይ ስብሃት ለእግዚአብሔር
ቸሩ ሆይ በአርያም በሉ

╭══•|❀:✧๑♡๑✧❀|: ══╮
  @meazahaymanot
╰══•ೋ•✧๑♡๑✧•  ══╯

Читать полностью…

መዓዛ ሃይማኖት በጎ አድራጎትና ጉዞ ማህበር

✅ የቃልህ ፍቺ ያበራል፥ ሕፃናትንም አስተዋዮች ያደርጋል።”
— መዝሙር 118(119)፥130
🕎ስለ መጽሐፍ ቅዱስ ምንነት እንዲሁም በመጽሐፍ ቅዱስ ላሉት ምንባባት አንድምታቸው ትንታኔና ማብራርያ የሚያገኙበት ቻናል ይቀላቀሉ።

👉“መጽሐፍ” ለሚለው ምንጭ በግሪክ ቋንቋ ቢብሎስ (byblos) ከደንገል በተሠራ ወረቀት ወይም በብራና ከተጻፈ በኋላ በሁለት በትሮች...read more

👉መጽሐፍ ቅዱስ መቼ በአንድ ጥራዝ ተጠቀለለ? ከክ.ል.በ ይሁን በኋላ የተጻፉት ሁሉንም መጻሕፍቶች ለየብቻቸው ነበሩ፡፡ከ500ዎቹ ዓ.ዓ....read more

👉ኦሪት "ኦራይታ" ከሚል የሶርያ(አራማይክ) ቃል የተገኘ ሲሆን ትርጓሜውም "ሕግ" ወይም "ትምህርት" ማለት ነው።የመጠሪያ ምንጩም....read more



ወቅታዊ የቤተ ክርስቲያናችንን ጉዳይ እና መንፈሳዊ ጥንካሬያችንን እንድናበረታ የሚያግዙን መንፈሳዊ ቻናሎችን ይዘን ቀርበናል።እርስዎም ከእነዚህ መንፈሳዊ ቻናሎች የነፍስ ምግብ የሆነውን የእግዚአብሔርን ቃል እየተመገቡ መንፈሳዊ ሕይወትዎትን እንዲያጠናክሩ በእግዚአብሔር ስም ጥሪያችንን እናቀርባለን🙏
🙏ፈጣሪ ይባርከን🙏

ከነዚህ መፀሀፍት የተወጣጡበት
ትምህርትን መማር ይፈልጋሉ❔
እነሆ ብለናል :-
📚የባሕታውያን አባቶች ሕይወትና የመዝሙራት ተመስጦ
📖▓⇨ትምህርት በአባ ሺኖዳ ⇨ክፈት
📚የድያቢሎስ ውግያዎች
📖▓⇨ትምህርት ⇨ክፈት
📚አምደ ሀይማኖት
📖▓⇨በአባታችን ቅዱስ ሺኖዳ ⇨ክፈት
📚መንፈሳዊ ሕይወት
📖▓⇨በአቡነ ሺኖዳ ⇨ክፈት
📚መንፈሳዊ ሰው
📖▓⇨በአቡነ ሺኖዳ ⇨ክፈት
📚የአባቶች ሕይወት ንሮ እና ተመስጦ
📖▓⇨በአቡነ ሺኖዳ ⇨ክፈት
የመኖኮሳት ታሪክ እና ተመስጦ በብጽእ አቡነ ሺኖዳ ሳልሳዊ ይቀርብበታል።

Читать полностью…

መዓዛ ሃይማኖት በጎ አድራጎትና ጉዞ ማህበር

ማኅደረ ጥያቄ

1. ሰባቱ ሊቃነ መላእክት
1. ቅዱስ ሚካኤል
2. ቅዱስ ገብርኤል
3. ቅዱስ ሩፋኤል
4. ቅዱስ ራጉኤል
5. ቅዱስ ዑራኤል
6. ቅዱስ ፋኑኤል
7. ቅዱስ ሳቁኤል

2. የሚሉአት አንዲት ደቀ መዝሙር ነበረች፥ ትርጓሜውም ዶርቃ ማለት ነው፤ እርስዋም መልካም ነገር የሞላባት ምጽዋትም የምታደርግ ነበረች። በዚያም ወራት ታመመችና ሞተች፤ ጴጥሮስም ሁሉን ወደ ውጭ አስወጥቶ ተንበርክኮም ጸለየ፥ ወደ ሬሳውም ዘወር ብሎ። ጣቢታ ሆይ፥ ተነሺ አላት። እርስዋም ዓይኖችዋን ከፈተች ጴጥሮስንም ባየች ጊዜ ተቀመጠች። እጁንም ለእርስዋ ሰጥቶ አስነሣት፤ ቅዱሳንንና መበለቶችንም ጠራ ሕያውም ሆና በፊታቸው አቆማት። (ሐዋ. ፱፡፴፮-፵፩) 

3. ኢያቄም/ሐና 

4. አባሕርያቆስ ኤጲስ ቆጶስ ዘሃገረ ብህንሳ 

5.   ነሐሴ 24
አቡነ ተክለ ሃይማኖት ወቶማስ ወ ፱፼ሰማዕታት አብርሃም ይስሐቅ ያዕቆብ

            ነሐሴ 26
በዓለ ፅንሰቱ ለወላዴ አእላፍ አቡነ ኢየሱስ ሞአ ዘ ሃይቅ እስጢፋኖስ ወ አቡነ ሀብተ ማርያም ጻድቅ

የተሣተፉ

1. tamiru  3/5

2. ዘላለም  5/5

3. tig 5/5

4. Mahi 4/5

5.  sen  5/5

6. Tomi 5/5

7. ቤተልሔም 5/5


ለተሣተፉት ቃለ ሕይወትን ያሰማልን

Читать полностью…

መዓዛ ሃይማኖት በጎ አድራጎትና ጉዞ ማህበር

ስንክሳር ዘወርሃ ነሐሴ ሃያ ስድስት(፳፮)
/channel/meazahaymanot

Читать полностью…

መዓዛ ሃይማኖት በጎ አድራጎትና ጉዞ ማህበር

ስንክሳር ዘወርሃ ነሐሴ ሃያ አምስት(፳፭)
/channel/meazahaymanot

Читать полностью…

መዓዛ ሃይማኖት በጎ አድራጎትና ጉዞ ማህበር

ዕረፍት በዓል

ቅዱሳን ጻድቃን በሕይወተ ሥጋ እያሉ፣ ከሞቱም በኋላ (በዐጸደ ነፍስ ኾነው) በጸሎታቸው ለሚታመኑ፤ በቃል ኪዳናቸው ለሚማጸኑ ምእመናን የድኅነተ ሥጋ፣ የድኅነት ነፍስ ምክንያቶች ናቸው፡፡ ቅዱሳን ጻድቃን በመንፈሳዊ አርአያነታቸው፣ በጸሎታቸውና በትምህርታቸው ከከበቡን የነፍስ ጠላቶች፤ ከርኲሳን መናፍስትና ከጨለማው ልጆች፤ ከክፉ ሰዎች ሽንገላና ተንኰል ለመጠበቅ ከእግዚአብሔር የተቀበሉት ሥልጣን ምን ጊዜም ይሠራል፡፡ በጻድቃን መኖር አገር ከጥፋት ትድናለች፡፡ የጻድቃንን ስም ጠርቶ እግዚአብሔርን በመለመን በረከትና ረድኤት ይገኛል፡፡ ስለ ጻድቃን ብሎ እግዚአብሔር ምሕረቱን ያድላል፡፡ ጻድቃንን ማሰብ፣ ሥራቸውንም መዘከር ክርስቲያናዊ ሕይወታችንን ያጐለምስልናል፡፡ በነፍስ በሥጋም ይጠብቀናል፤ ይረባናል፤ ይጠቅመናል፡፡ ስለዚህም ነው ቤተ ክርስቲያናችን ጻድቃንን እንድናስባቸው፤ በስማቸውም ለድሆችና ለጦም አዳሮች እንድንመጸውት፤ መታሰቢያቸውንም እንድናደርግ የምትመክረን፣ የምታስተምረን፡፡ ከእነዚህ ቅዱሳን መካከል መካከል ጻድቁ አቡነ ተክለ ሃይማኖት አንዱ ናቸው፡፡

አቡነ ተክለ ሃይማኖት በእግዚአብሔር መልካም ፈቃድ፤ በሊቀ መላእክት ቅዱስ ሚካኤል ብሥራት ከአባታቸው ከካህኑ ጸጋ ዘአብ እና ከእናታቸው ከቅድስት እግዚእ ኃረያ ታኅሣሥ ፳፬ ቀን ፲፪፻፲፪ (1212) ዓ.ም በቡልጋ አውራጃ ኢቲሳ በሚባል ቦታ ተወለዱ፡፡ (ቦታው በአሁኑ ሰዓት ደብረ ጽላልሽ ኢቲሳ ተክለ ሃይማኖት ተብሎ ይጠራል)፡፡ በተወለዱ በሦስተኛው ቀን እሑድ ከጠዋቱ በሦስት ሰዓት ከእናታቸው ዕቅፍ ወርደው ‹‹አሐዱ አብ ቅዱስአሐዱ ወልድ ቅዱስ አሐዱ ውእቱ መንፈስ ቅዱስ፤ አንዱ አብ ቅዱስ ነው፤ አንዱ ወልድ ቅዱስ ነው፤አንዱ መንፈስ ቅዱስ ቅዱስ ነው›› በማለት ሥላሴን አመስግነዋል፡፡ በተወለዱ በ፲፭ ዓመታቸው መዓርገ ዲቊናን፤ በ፳፪ ዓመታቸው ደግሞ መዓርገ ቅስናን ከግብጻዊው ጳጳስ አባ ጌርሎስ (ቄርሎስ) ተቀብለዋል፡፡

ወላጆቻቸው ያወጡላቸው ስም ‹ፍሥሐ ጽዮን› ነው፡፡ በአንድ ወቅት ሕፃኑ ፍሥሐ ጽዮን ወደ ጫካ ለአደን ሔዱ፡፡ በዚያች ዕለት ጌታችን አምላካችንና መድኀኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ተገልጦ ጸጋ መንፈስ ቅዱን አሳደረባቸው፡፡ ለሐዋርያዊ አገልግሎት ወንጌል ወዳልተዳረሰበት ቦታ እንደሚልካቸውም አስረዳቸው፡፡ ቅዱስ ሚካኤልም ከአውሬ አዳኝነት ሰውን ወደ እግዚአብሔር መንግሥት ለመመለስ እንደ ተመረጡ፤ አጋንንትን የማውጣት፣ ተአምራትን የማድረግ ሥልጣን እንደ ተሰጣቸው፤ ስማቸውም‹ተክለ ሃይማኖት› እንደሚባል፤ ትርጓሜውም ተክለ አብ፣ ተክለ ወልድ፣ ተክለ መንፈስ ቅዱስ ማለት እንደ ኾነ አበሠራቸው፡፡ ከዚህ በኋላ ያላቸውን ንብረት ዅሉ ለቤተ ክርስቲያንና ለነዳያን ሰጥተው ‹‹አቤቱጌታዬ ኢየሱስ ክርስቶስ ሆይ! የመንግሥተ ሰማያትንበር ትከፍትልኝ ዘንድ እነሆ ቤቴን እንደ ተከፈተተውኹልህ›› በማለት ቤታቸውን ትተው ወንጌልን ለማስተማር ፈጥነው ወጡ፡፡ ከዚያ ጊዜ ጀምረው በመላው ኢትዮጵያ እየተዘዋወሩ ወንጌልን በመስበክና ተአምራትን በማድረግ ብዙ አሕዛብን ከአምልኮተ ጣዖት ወደ አምልኮተ እግዚአብሔር፤ ከገቢረ ኀጢአት ወደ ገቢረ ጽድቅ መልሰዋል፡፡ አብያተ ክርስቲያናትንም አሳንጸዋል፡፡

ከዚህ በኋላ በደብረ ሊባኖስ ገዳም (ገዳመ አስቦ) ዋሻ በመግባትም ሁለቱን በፊት፣ ሁለቱን በኋላ ሁለቱን በቀኝ፣ ሁለቱን በግራ ስምንት ጦሮችን ተክለው እጆቻቸውን በትእምርተ መስቀል በመዘርጋት የክርስቶስን ሕማም፣ ሞትና ነገረ መስቀል በማሰብ በተመስጦ ሌሊትና ቀን ያለ ማቋረጥ በጾም፣ በጸሎት ተወስነው ሲጋደሉ፤ ከቊመት ብዛት የተነሣ በ፺፪ኛ ዓመታቸው ጥር ፬ ቀን ፲፪፻፹፱ (1289) ዓ.ም አንዲቱ የእግራቸው አገዳ ተሰብራለች፡፡ ደቀ መዛሙርቱም የመንፈሳዊ አባታቸውን ስባረ ዐፅም (የዐፅም ስባሪ) አክብረው በሥርዓት አኑረዋታል፡፡ እግራቸው እስኪሰበር የቆዩባቸው ዓመታትም ፳፪ ናቸው፡፡ ለሰባት ዓመታት በአንድ እግራቸው ቆመው ያለ ምግብና ያለ ውኃ በትኅርምት ሌሊትና ቀን እንደ ምሰሶ ጸንተው በትጋት ለሰው ዘር ዅሉ ድኅነትን ሲለምኑ ኖረዋል፡፡ ከሰባቱ ዓመታት ውስጥ ጥቂት ውኃ የቀመሱት በአራተኛው ዓመት ብቻ እንደ ነበረ መጽሐፈ ገድላቸው ይናገራል፡፡

ጻድቁ አባታችን ምድራዊ ሕይወታቸውን በተጋድሎና በሐዋርያዊ አገልግሎት ከፈጸሙ በኋላ ከዚህ ዓለም ውጣ ውረድ የሚያልፉበት ቀን ተቃረበ፡፡ በዚህ ጊዜ መድኀኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ከእናቱ ከቅድስት ድንግል ማርያም፣ ከቅዱሳን መላእክት፣ ከቅዱሳን ነቢያትና ከቅዱሳን ሐዋርያት ጋር ወደ እርሳቸው በመምጣት የሚያርፉበት ዕለት መድረሱን ነገራቸው፡፡ የተጋድሏቸውን ጽናት አድንቆ በስማቸው መታሰቢያ ለሚያደርጉ፣ ለነዳያን ለሚመጸዉቱ ቤተ ክርስቲያን ለሚያሠሩ የምሕረት ቃል ኪዳን ሰጥቷቸው በክብር በምስጋና ወደ ሰማይ ዐረገ፡፡ ስለ ተጋድሏቸው ጽናትም ‹‹በሰው እጅ የማይለካውንይህንን የመንግሥት አዳራሽ ውሰድ›› በማለት የመለኮትን ነገር የሚናገር የእሳት አንደበት ያለው የጸጋ ልብስ አልብሷቸዋል፤ በመስቀል ምልክት ያጌጡ ሰባት የሕይወት አክሊላትንም አቀዳጅቷቸዋል፡፡

አቡነ ተክለ ሃይማኖት የዕረፍታቸው ጊዜ መቃረቡን ባወቁ ጊዜ የመንፈስ ልጆቻቸውን ጠርተው ጌታችን የነገራቸውን ዅሉ አስረድተው አባታዊ ምክርና ተግሣፅ ከሰጧቸው በኋላ ነሐሴ ፳፬ ቀን ከዚህ ዓለም ድካም ዐርፈዋል፡፡ የመንፈስ ልጆቻቸውም ለአንድ ቅዱስ አባትና ካህን በሚገባ ሥርዓት በማኅሌት፣ በዝማሬና በምስጋና ቀብረዋቸዋል፡፡ ጌታችንም ከእመቤታችንና ከቅዱሳን መላእክት ጋር ተገልጾላቸዋል፤ ነፍሳቸውንም ‹‹የጠራሽ፣ ንጽሕትነፍስ ሆይ ወደ እኔ ነዪ›› ብሎ በክብር ተቀብሏታል፡፡ በመጽሐፈ ገድላቸው እንደ ተጠቀሰው አቡነ ተክለ ሃይማኖት በዚህ ዓለም የኖሩበት ዕድሜ ዘጠና ዘጠኝ ዓመት ከዐሥር ወር ከዐሥር ቀን ነው፡፡ በእናት አባታቸው ቤት ፳፪ ዓመት፤ በከተታ ፫ ዓመት፤ በይፋት ፱ ወር፤ በዳሞት ፲፪ ዓመት፤ በአማራ ፲ ዓመት፤ በሐይቅ ፲ ዓመት፤ በደብረ ዳሞ ፲፪ ዓመት፤ በትግራይና በኢየሩሳሌም ገዳማት ፩ ዓመት፤ ዳዳ በሚባል አገር ፩ ወር፤ በደብረ አስቦ ገዳም ፳፱ ዓመት ከ፲ ቀን መቆየታቸውን መጽሐፈ ገድላቸው ይናገራል (ገ.ተ.ሃ ፶፱፥፲፬-፲፭)፡፡

በአጠቃላይ ጻድቁ አቡነ ተክለ ሃይማኖት ሕይወታቸዉን ሙሉ ለእግዚአብሔር በመስጠት፣ እንደ በሬ ተጠምደው፣ እንደ ገበሬ ታጥቀው ይህንን ዓለም ንቀው፣ በጾም በጸሎት ተወስነው በብሕትውና ከመኖራቸው ባሻገር እንደ ቅዱሳን ሐዋርያት ወንጌልን በመላው ኢትዮጵያ እየተዘዋወሩ የሰበኩ፤ በጌታችን አምላካችንና መድኀኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ስም ድውያነ ሥጋን በተአምራት፣ ድውያነ ነፍስን በትምህርት የፈወሱ ሐዋርያ ናቸው፡፡ ቅድስት ቤተ ክርስቲያችንም ‹‹እናንተን የሚቀበል እኔንይቀበላል፤ እኔንም የሚቀበል የላከኝን ይቀበላል፡፡ነቢይን በነቢይ ስም የሚቀበል የነቢይን ዋጋያገኛል፡፡ ጻድቅንም በጻድቅ ስም የሚቀበል የጻድቁንዋጋ ያገኛል፡፡ ማንም ከእነዚህ ከታናናሾቹ ለአንዱቀዝቃዛ ጽዋ ብቻ በደቀ መዝሙር ስም የሚያጠጣእውነት እላችኋለሁ፤ ዋጋው አይጠፋበትም›› (ማቴ. ፲፥፵-፵፪) በማለት ጌታችን የተናገረውን መለኮታዊ ቃል ኪዳን መሠረት አድርጋ መጋቢት ፳፬ ቀን የፅንሰታቸውን፤ ታኅሣሥ ፳፬ ቀን የልደታቸውን፤ ጥር ፬ ቀን የስባረ ዐፅማቸውን (እግራቸው የተሰበረበትን)፤ ግንቦት ፲፪ ቀን የፍልሰተ ዐፅማቸውን፤ ነሐሴ ፳፬ ቀን የዕረፍታቸውን በዓል በትላቅ ደስታ ታከብራለች፡፡ የጻድቁ በረከት አይለየን፡፡

ወስብሐት ለእግዚአብሔር

Читать полностью…
Subscribe to a channel