ወወሃብኮሙ ትእምርት ለእለ ይፈርሁከ፣ለሚፈሩህ ምልክትን ሰጠሃቸው (መዝ 59፡4)...
ወወሃብኮሙ ትእምርት ለእለ ይፈርሁከ፣ለሚፈሩህ ምልክትን ሰጠሃቸው (መዝ 59፡4)
ይህንን የተናገረ ልበ አምላክ ቅዱስ ዳዊት ነው፡፡ ልበ አምላክ ቅዱስ ዳዊት ከተሰጡት 7ት ሃብታት አንዱ ሃብተ ትንቢት ነው። በዚተሰጠው ሃብተ ትንቢት የራቀው ቀርቦለታል፣ የቀረበው ተከናውኖለታል፣የረቀቀው ጐልቶለታል። ስለዚህም ከእርሱ በፊት የተደረገውን፣ በእርሱ ዘመን የሆነውን፣ ከእርሱም በኋላ እስከ እለተ ምፅአት የሚደረገውን ሁሉ ልዑል እግዚአብሔር ገልፆለት ብዙ ነገር ተንብይዋል። ከትንቢቶቹም መካከል አንዱ የመስቀሉ ነገር ነው፡፡
ቅዱስ መስቀል እንደ እንግዳ ደራሽ እንደ ውሃ ፈሳሽ ሳይሆን ትንቢት ሲነገርለት ምሳሌ ሲመሰልለት የኖረና በኃላም በከበረ በክርስቶስ ደም ተቀድሶ የመለኮት ዙፋን ሆኖ የተመረጠ ለክርስቲያኖች ኃይልና መመኪያ እንዲሁም አጋንንትን ድል መንሻ ነው፡፡
ስለ ቅዱስ መስቀሉ የተመሰለ ምሳሌ
በመጽሐፍ ቅዱስ የተመሰሉ ምሳሌዎች ምስጢራዊ ትርጉም አላቸው። ጌታችን አምላካችን መድኃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስም ቅዱስ ወንጌልን በብዙ ምሳሌ እየመሰለ ለህዝቡ በሚገባቸው መልኩ ያስተምራቸው ነበር፡፡ ከትምህርቱ በኃላም ቅዱሳን ሐዋርያት ለብቻቸው ሲሆኑ ምሳሌውን ተርጉምልን ይሉት ነበር፤ እርሱም ምሳሌውን ይተረጉምላቸው ነበር፡፡ ‹መስማት በሚችሉበት መጠን እነዚህን በሚመስል በብዙ ምሳሌ ቃሉን ነግራቸው፤ ያለምሳሌ ግን አልነገራቸውም። ለብቻቸውም ሲሆኑ ነገሩን ሁሉ ለገዛ ደቀመዛሙርቱ ይፈታላቸው /ይተረጉምላቸው/ ነበር› (ማር 4፡33 , 34) እንዲል;; ለመግቢያ ያህል ስለምሳሌ ይህንን ካልን ስለ ቅዱስ መስቀሉ የተመሰለ ምሳሌ ከብሉይ ኪዳን የሚከተለውን ምሳሌ እንመለከታለን።
ለህዝበ እስራኤል ድህነት የሆነው አርዌ ብርት
እስራኤል ዘሥጋ በግብፅ ምድር ለ430 ዓመት በባርነት ከኖሩ በኋላ በእግዚአብሔር ቸርነት በአባታቸው በእነ አብርሃም ቃል ኪዳን በሙሴ መሪነት በቅዱስ ሚካኤል ተራዳኢነት ባህር ተከፍሎላቸው፣ ጠላት ጠፍቶላቸው፣ መና ከደመና እየወረደላቸው፣ ውሃ ከአለት እየፈለቀላቸው፣ ቀን በአምደ ደመና ሌሊት በአምደ ብርሃን እየተጓዙ በምድረ በዳ 40 ዓመት ኑረዋል፡፡ በጉዟቸውም ላይ ሳሉ በልባቸው እግዚአብሔርን አሙት፤ እንዲህም አሉ ‹አሁን እግዚአብሔር መና አወረድኩላችሁ የሚለን ይህ ያለንበት አካባቢ ደጋ ስለሆነ ውርጭ /ጤዛ/ ያወጣውን ያንን እያረጋ መና አወረድኩላችሁ ይለናል ‹ይክልኑ እግዚአብሔር ስሪአ ማዕድ በገዳም› ‹እግዚአብሔር በምድረ በዳ /በቆላ/ መና ማውረድ ይችላልን? (መዝ 77፡20) አሉ። በዚህ ጊዜ እግዚአብሔር ሙሴን ህዝቡን ይዘህ ወደ ቆላ አውርዳቸው አለው በዚያም የፈለጉትን ሰጣቸው፤ ነገር ግን የሚበሉት በአፋቸው ሳለ ሁለት መንታ ምላስ ያለው እባብ እየነደፈ ህዝቡን አስጨነቃቸው። በዚህ ጊዜ ህዝቡ ሁሉ ወደ ሙሴ ቀርበው በእግዚአብሔር እና በአንተ ፊት በድለናል፣ እባቦችን ከእኛ ያርቅልን ዘንድ ወደ እግዚአብሔር ፀልይልን አሉት። ሙሴም ስለ ህዝቡ ወደ እግዚአብሔር ፀለየ። እግዚአብሔርም ፀሎቱን ተቀብሎ ለሙሴ እንዲህ አለው፤ ከጥሩ ናስ እባብን ሰርተህ በዓላማ ላይ ስቀል የተነደፈውም ሁሉ ሲያዩት በህይወት ይኖራል አለው። ሙሴም የናሱን እባብ ሰርቶ በዓላማ ላይ ሰቀለ፣ እባብም የነደፋቸው ሰው ሁሉ የናሱን እባብ ባየ ጊዜ ዳነ፡፡ (ዘኁ 21፡7-9) ይላል፡፡ ይህ እንግዲህ ስለ ቅዱስ መስቀሉ መድኅኒትነት ህይወትነት አስቀድሞ የነበረ ምሳሌ ነው። አባቶቻችን ሊተረጉሙት ሕዝበ እስራኤል የእስራኤል ዘነፍስ የክርስቲያኖች ምሳሌ ናቸው። በምድረ በዳ ያስጨነቃቸው /የነደፋቸው/ መርዘኛዋ እባብ የጥንት ጠላታችን የዲያብሎስ ምሳሌ ነው። እርሱም 5500 ዘመን የሰው ልጆችን በሲኦል እያስጨነቀ ለመኖሩ ምሳሌ ነው። የህዝቡ ሁሉ ጩኽት የአበው ቀደምትን፣ የነቢያትንና የካህናትን ሱባኤ መስዋዕትነት ያመለክታል። እነርሱም በመስዋዕታቸው በሱባኤያቸው እግዚአብሔር እንዲያድናቸው አጥብቀው ለመለመናቸው ምሳሌ ነው፡፡ (ኢሳ 64፡1) ‹ሰማዮችን ቀድደህ ምነው ብትወርድ› እንዲል።እግዚአብሔርም ልመናቸውን ሰምቶ ከእመቤታችን ከቅድስት ድንግል ማርያም በህቱም ድንግልና ተፀንሶ, በህቱም ድንግልና ተወልዶ፣ በ30 ዘመኑ ተጠምቆ፣ ዞሮ አስተምሮ፣ በኋላም ስለ ድህነተ ዓለም በመልዕልተ መስቀል ተሰቅሎ ለማዳኑ ምሳሌ ነው። የናሱ እባብ የክርስቶስ ምሳሌ ነው፤ በዚያ መርዝ እንደሌለበት ለእርሱም ክብር ይግባውና ኃጢአት የለበትም። ዓላማውም የመስቀሉ ምሳሌ ነው። ለሙሴ ህዝቡ ሁሉ ሲያየው ይዳን ብሎ ለህዝቡ የሚድኑበትን ምልክት እንደሰጠው ሁሉ በወልድ ውሉደ እግዚአብሔር በክርስቶስ ክርስቲያን የተባሉ ምዕመናንም የክርስቶስን መስቀል ተሳልመው እንዲሚባረኩ ፣ ተማጽነው እንደሚድኑ የእግዚአብሔር ፈቃዱ እንደሆነ የሚያሳይ ምሳሌ ነው። ይህ ምሳሌም እውነተኛ እንደሆነ ጌታችን አምላካችን መድኅኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ በቅዱስ ወንጌል ሲገልፅ እንዲህ ብሏል ‹ሙሴም በምድረ በዳ እባብን እንደሰቀለ እንዲሁ በእርሱ የማያምን ሁሉ የዘለዓለም ሕይወት እንዲኖረው እንጂ እንዳይጠፋ የሰው ልጅ ክርስቶስ ይሰቀል ዘንድ ይገባዋል፡፡› (ዮሐ 3፡14, 15) ብሏል፡፡ እንግዲህ ስለቅዱስ መስቀሉ ከተመሰሉ ብዙ ምሳሌዎች መካከል አንዱን ይህንን ብቻ ወስደን ለትምህርታችን ተመለከትን እንጂ ብዙ ተነግሮለታል፡፡ በመቀጠልም መስቀሉ ለክርስቲያኖች የተሰጠበትን ምክንያት እንመለከታለን፡፡
ሀ. መስቀሉ ለክርስቲያኖች ምልክት ነው
ምልክት መለያ መታወቂያ ነው፡፡ መስቀልም ክርስቲያኖች ከኢ-አማንያን /ከአህዛብ/ የሚለዩበት ከእግዚአብሔር ዘንድ የተሰጠ ምልክት ነው፤ ‹ለሚፈሩህ ምልክትን ሰጠሃቸው› (መዝ59፡4) እንዲል። እስራኤል ዘሥጋ በግብፅ ሳሉ ከቀሳፊ መልአክ እንዲድኑ የበጉን ደም ምልክት በቤታቸው በመቃኑና በመድረኩ እንዲረጩ በእግዚአብሔር ታዘው ነበር፡፡ በዚህም የደም ምልክት ከቀሳፊ መላእክ ተጠብቀዋል፡፡ (ዘፀ 12፡13) ክርስቲያኖችም በክርስቶስ ደም መዳናቸውን የሚያበስር የመስቀሉ ምልክትነት ነው፡፡
ለ. መስቀሉ ለክርስቲያኖች ሃይል ነው
ሃይል መንፈሳዊ ሃይል ሰማያዊ የምናገኝበት ከእግዚአብሔር የተሰጠን ይህ ቅዱስ መስቀሉ ነው። ሐዋርያው ቅዱስ ጳውሎስ ይህንን ሲገልፅ ‹የመስቀሉ ቃል ለሚጠፉት ሞኝነት ለእኛ ለምንድን ግን የእግዚአብሔር ኃይል ነው› (1ቆሮ 1፡18) ብሏል፡፡ ‹ለሚጠፉት› ብሎ በመስቀሉ ለሚቀጠቀጡ ለአጋንነት አንድም አጋንንት አድሮባቸው በክህደት ለፀኑ ኢ-አማንያን /መናፍቃን/ የመስቀሉ ነገር ሞኝነት ይመስላል፤ ሐይማኖት አፅንተው ምግባር አቅንተው መስቀሉን መጠጊያ ላደረጉ ምዕመናን ግን ኃይል ነው ማለቱ ነው፡፡ ከዚህ ኃይለ ቃል ጋር ቅዱስ ዳዊትም ይተባበራል። (መዝ 43፡5) ‹በአንተ ጠላቶቻችንን እንወጋቸዋለን በስምህም በላያችን የቆሙትን እናዋርዳቸዋልን› ብሏል። እኛም ክርስቶስ በሰጠን በመስቀሉ ኃይል ስመ ሥላሴን በመጥራት ማለትም በስመ አብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ አሐዱ አምላክ በማለት በትምህርተ መስቀል በማማተብ በላያችን የቆሙ ማለትም ኃጢአት በማሳሰብና በማሰራት የሚታወቁ አጋንንትን ድል የምንነሳበት በቅዱስ መስቀሉ ኃይል እንደሆነ እንረዳለን፡፡
ሐ. መስቀሉ ለክርስቲያኖች መመኪያ ነው
መስቀል በጥንተ ታሪኩ የእርግማንና የኃጢአት አርማ ሆኖ መቆየቱ ቢታወቅም ዛሬ ግን የክርስቲያኖች መመኪያና አለኝታ መከታና የድል አርማ ነው፡፡
✞ መስቀል ክብሬ ነው ✞
ምልክቴ ነው ከገጽ ማምለጫዬ
መስቀል ክብሬ ነው ከክፉ መውጫዬ
የእባቡ እራስ ሚቀጠቀጥበት
በመስቀል ቤዛነት መርገም ተሻረበት
ሰው በዕፀ መስቀል ከእግዚአብሔር ታረቀ
የምሕረት ቀን ወጣ መከራው ራቀ
ኦ በመስቀል ጠላት ተቸገረ
" " " " ጨለማው ተሻረ
" " " " ደሙን አፈሰሰ
" " " " ስጋውን ቆረሰ
/አዝ=====
ፊቴን ሰውነቴን በእርሱ አማትባለው
በልቤ አትሜ በአንገቴ አስረዋለው
አይሁድ በሚክዱት እኔ ግን አምኜ
እግሩ ለቆመበት እሰግዳለሁ ድኜ
ኦ በመስቀል እስረኛ ተፈታ
" " " " ከሳሹ ተረታ
" " " " ሞትን ገደለልን
" " " " በሩን ከፈተልን
/አዝ=====
የቤዛ ክርስቶስ የክብሩ ዙፋን ነው
በዕምነት የሚያጸና በስሙ ላመነው
የቅድስና የሕይወት ማሕተም
መስቀል ትምክህት ነው እስከ ዘለዓለም
ኦ በመስቀል ፍቅሩን ገለጸልን
" " " " ነብሱን ለኛ ሰጠን
" " " " እንባችን ታበሰ
" " " " ጸጋ ተለበሰ
/አዝ=====
ፊቴን ሰውነቴን በእርሱ አማትባለው
በልቤ አትሜ በአንገቴ አስረዋለው
አይሁድ በሚክዱት እኔ ግን አምኜ
እግሩ ለቆመበት እሰግዳለሁ ድኜ
ኦ በመስቀል እስረኛ ተፈታ
" " " " ከሳሹ ተረታ
" " " " ሞትን ገደለልን
" " " " በሩን ከፈተልን
👉ዘማሪ ዲያቆን አቤል መክብብ
ይቤሎሙ ኢየሱስ ለአይሁድ እመኑ ብየ
ወእመኑ በአቡየ አበርህ (፪)በመስቀልየ
ትርጉም፡ ኢየሱስ ለአይሁድ በእኔ እመኑ አላቸው በአባቴም እመኑ በመስቀሌ አበራለሁ
አየኸው ደመራ መስቀል ሲያበራ
መስቀል አለወይ ቆሟል ወይ
አለ እንጂ ለምፅ ያነጻል እንጂ
ያዉ ቆሟል ድዉይ ይፈዉሳል
አምነዋለሁ የት አገኘዋለሁ
አለልህ እሠረው በአንገትህ
ከልብህ ተሳለመው አምነህ
እኮራለሁ በዕፀ መስቀሉ
ይፈዉሳል ሙታንን ያስነሣል
ድል ያደርጋል ሰይጣንን ይመታል (፫)
@meazahaymanot
የዕለቱ መልእክት
በፍጹም ልብኽ በእግዚአብሔር ታመን፥በራስኽም ማስተዋል አትደገፍ፤ በመንገድኽ ዅሉ ርሱን ዕወቅ፥ርሱም ጐዳናኽን ያቀናልኻል።
መጽሐፈ ምሳሌ ፫÷፭-፮
Trust in the LORD with all your heart and lean not on your own understanding; in all your ways acknowledge him, and he will make your paths straight.
proverbs 3÷5-6
መልካም ቀን
#በስመ_አብ_ወወልድ_ወመንፈስ_ቅዱስ_አሐዱ_አምላክ_አሜን
🌹🌹🌹🌹🌹🌹🌹🌹🌹
#እንኳን_አደረሳችሁ_አደረሰን
🧚♀🧚♀🧚♀🧚♀🧚♀🧚♀🧚♀🧚♀🧚♀
🌾🌿👉#ወርኃ ዘጽጌ
🌾🌾🌾🌾🌾🌾🌾🌾🌾🌾🌾🌾🌾
🍀🌹#መግቢያ
👉#ጽጌ ማለት #ጸገየ አበበ ከሚለው ከግዕዝ የተገኘ ሲሆን አበባ ማለት ነው። በቤ/ክ ናችን አስተምህሮና በቅዱስ ያሬድ የዜማ ይትበሃል #ከመስከረም ፳፮ እስከ #ኅዳር ፭ ያለው ወቅት ሲሆን ይኸውም አንድ ወር ከዐሥር ቀን ወይም አርባ ቀን ይሆናል።
ይህ ወቅት ወርኃ ጽጌ ዘመነ ጽጌ ተብሎ ይጠራል፤በእነዚህ ሰሞናት በቤ/ክ የሚነበቡ ምንባባት የሚዘመሩት መዝሙራት የሚሰበኩት ስብከቶች የሚቆመው ማኅሌት ሁሉ ምድርን በጽጌያት ማሸብረቁን የሚገልጽ ይሆናል።
አበባና ፍሬ የሃይማኖትና የምግባር ምሳሌዎች ናቸው፤ፍሬ ያለ አበባ አበባም ያለፍሬ መገኘት እንደማይችል ሃይማኖትም ያለ ምግባር፣ምግባርም ያለ ሃይማኖት ዋጋ የማያስጥ መሆኑን ያመለክታል።
፦የማኅሌተ ጽጌና የጾመ ጽጌ አጀማመር
የእመቤታችን የስደቷ መታስቢያ ወር በቤተ ክርስቲያናችን የሚከበረው በማኅሌት፣በቅዳሴና በዝክር ነው።በወርኃ ጽጌ ባሉት ሳምንታት ከቅዳሜ ማታ እሰከ እሑድ ጠዋት አበው ካህናት የሚያቀርቡት ዝማሬ ከቅዱስ ያሬድ ድጓ፣ከማኅሌተ ጽጌና ከሰቆቃወ ድንግል የተውጣጣና ሦስት ወገን ያለው ነው። ዝክሩም፣በአሁኑ ወቅት በከተሞች አካባቢ እየተረሳና ሌላ መልክ እየያዘ ቢመጣም፤
ሥራቱ ግን ዘወትር እሑድ የአንድ አካባቢ ሰዎች ማዕከላዊ በሆነ ቦታ ተሰባሰበው በእመቤታችን ስም የሚዘክሩት ነው።ዐቅመ ደካሞች፣ድኾችና መንገደኞች ተጠርተው በእመቤታች ስም እንዲበሉና እንዲጠጡ ይደረጋል።ይህም ትውፊት እመቤታችን ወደ ኢትዮጵያ በመጣች ጊዜ ኢትዮጵያውያን አባቶችና እናቶች ያደረጉላትን መስተንግዶ ለማሰብ ነው።
የጻድቁ አቡነ ዜና ማርቆስ ዜና ገድል የጽጌን ጾም አስመልክቶ የሚከተለውን ይተርካል
፦(አቡነ ዜና ማርቆስ የምሁርን ሕዝብ አስተምረውና አሳምነው ካጠመቁ በኋላ እንደገና ለማስተማር ወደ ይፋት ሂዱ። በዚያም ክርስቶስ ሥጋ ለብሶ ከድንግል ማርያም ተወልዶ ስለኛ ኃጢአት ተሰቅሎ ሞተ፤በሦስተኛ ቀን ከሙታን ተነሣ እያሉ ሲያስተምሩ አንድ አይሁዳዊ እንድት እንዲህ እያለ ያስተምራል ሲል ተቃውሞ አቀረበባቸው።እርሳቸውም የብሉይና ሐዲስ ዐዋቂና ብልህ ስለነበሩ የሚከተለውን ጥቅስ እየጠቀሱ ያስረዱት ጀመር።
(ትወፅ ዕ በትር እምሥርወ እሴይ፤ወየዓርግ ጽጌ እምጒንዱ)፤ትርጓሜውም (ከእሴይ ሥር በትር ትወጣለች ከግንዱም አበባ ይወጣል ያቆጠቁጣል)ማለት ነው።በትር አመቤታችን ድንግል ማርያም ስትሆን ጽጌ ደግሞ ከእርስዋ የተወለደው ጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ነው ሲሉ አቡነ ዜና ማርቆስ በትንቢተ ኢሳይያስ ም ዕ.፲፩፥፩ ያለውን ትርጓሜውንና ምስጢሩን ዘርዝረው ባስረዱት ጊዜ አይሁዳዊው አምኖ ትምህርታቸውን ተቀበለ።
🌳🌳🌳🌳🌳🌳🌳🌳🌳🌳🌳🌳🌳
አቡነ ዜና ማርቆስ ሐዲስ ኪዳን አስተምረው አሳምነው ካጠመቁት በኋላ አመነኲሱት፤ስሙንም ጽጌ ብርሃን ብለው ሰየሙት፤አባ ጽጌ ብርሃን ምሁረ ኦሪት ስለነበር መጻሕፍተ ሐዲሳትን ለማጥናት ምቹ ሆነለት፤ቀጥሎም ከርሳቸው ጋር እየተዘዋወረ ወንጌልን ያስተምር ጀመር።
🌷🌷🌷🌷🌷🌷🌷🌷🌷🌷🌷🌷🌷
ይህንንም ከፈጸመ በኋላ እንደ መዝሙረ ዳዊት መቶ ኅምሳ አድርጎ ማኅሌተ ጽጌን ደረሰ ።አባ ጽጌ ብርሃን ይህንን በደረሰበት ጊዜ የወረኢሉ ተወላጅና የደብረ ሐንታው አባ ገብረ ማርያም አማካሪው ነበር።ድርሰቱንም ሲደርስ ቤት እየመታና በአምስት ስንኝ እየከፋፈለ ነው።.....አባ ጽጌ ብርሃንና አባ ገብረ ማርያም #ከመስከረም ፳፮ቀን እ ስከ # ኅዳር ፭ ቀን ድረስ ማኅሌተ ጽጌ ለመቆምና የጽጌን ጾም ለመጾም በየዓመቱ በደብረ ብሥራት እየመጡ ይሰነብቱና ቊስቋምን ውለው ወደየበአታቸው ይመለሱ ነበር።
ይህም የማኅሌተ ጽጌ ድርሰት በሰምና ወርቅ የተደረሰ ኾኖ አበባን ሰም፤ጌታንና እመቤታችንን ወርቅ እያደረገ ስለሚናገር ለሚያነበውና ለሚጸልየው እጅግ ያስደስታል
እንግዲህ ከላይ ከቀረበው የአባታችን የገድል ክፍል ለመረዳት እንደሚቻለው አባ ጽጌ ብርሃንና አባ ገብረ ማርያም የጽጌን ማኅሌት መቆም ወቅቱንም በፈቃዳቸው መጾም ጀምረዋል።ዘመኑም በ፲፬ኛው ክፍለ ዘመን መጀመሪያ ላይ ነው።
🌷🌷🌷🌷🌷🌷🌿🌿
ከዚያ ወዲህ ግን ጥቂት በጥቂት እያሉ አብያተ ክርስቲያናት በወርኃ ጽጌ የጽጌን ማኅሌት መቆም ጀመሩ፤ጥቂት መነኮሳትና አንዳንድ ምእመናንም በገዛ ፈቃዳቸው ወቅቱን መጾም ያዙ።በዘመናችን በወርኃ ጽጌ የጽጌን ማኅሌት መቆም ስለ ተለመደ ከማታው በሦስት ሰዓት ይደወላል።ሴቱ ወንዱ፤ትንሹም ትልቁም ይሰበሰባል፤ማኅሌተ ጽጌው እየተዜመ ፤አስፈላጊ የሆነው በጸናጽል በከበሮ እየተመረ ገደና እየተወረበ እየተሸበሸበ እስከ ጠዋቱ ፲፪ ሰዓት ድረስ ተቁሞ ይታደራል። #የጽጌ ጾም
🌹🌹🌹🌹🌹🌹🌹🌹🌹
#የውዴታ(የፈቃድ)እንጂ የግዴታ አይደለም!!
የእመቤታችንን ስደት በማሰብ ከትሩፋት ወገን የሚጾም ስለሆን ምእመናን ሁሉ እንዲጾሙት አይገደዱም፤የሚጾመው የማይጾመውን ለምን አልጾምክም ብሎ ሊፈር ድበት ስለራሱም እየጾምኩ ነው ብሎ መናገር አይገባውም።
የፈቃድ መሆኑንም የሚያሳየው ይኸው ነው። #የማይጾመውም በልቡ ያመሰግናል፣ስደቷ ን እያሰበ ማኅሌቷን እየዘመረ ያሳልፋል ማለት ነው።ከእመቤታችን እረድኤት በረከት ያሳትፈን!!!
🌷🌾🌹🌿🌹🌾🍀🌷🌿🌹🌾🌷🌿
@meazahaymanot
https://docs.google.com/forms/d/1LnRCOLLvC80rbdC-GjYgyEBVnYcUYJBcdFoBKu5ho7Q/edit#responses
በማህበሩ የበጎ አድራጎት ተግባር ላይ መሳተፍ የሚፈልጉ አባላትን በመመዝገብ ለይ ይገኛል። እርሶም የዚህ መልካም አገልግሎት ተሳታፊ ይሆኑ ዘንድ መንፈሳዊ ጥሪያችንን እያስተላለፍን፤ መልካም ፈቃድዎ ከሆነ አና ስለማህበራችን የበለጠ ለመረዳት (Join) የሚለውን በመጫን የድህረ ገጻችን አባል ይሁኑ፡፡ ከድህረ ገጻችንም የሚገኘውን የአባልነት መመዝገብያ ቅጽ በመሙላት የማህበሩ አባል በመሆን አብረውን ይሰሩ ዘንድ መንፈሳዊ ጥሪያችንን በልዑል እግዚአብሔር ስም እና በእናታችን በቅድስት ድንግል ማርያም ስም እናቀርባለን።
እፀ መስቀል
እፀ መስቀል የክብር መውረሻ
ሞትን ድል መንሻ
የክብር ባለቤት - - - እፀ መስቀል
የተሰዋበት - - - እፀ መስቀል
እፀመስቀሉ ነው - - - እፀ መስቀል
የአለም መድኃኒት - - - እፀ መስቀል
#አዝ
እንደእሌኒ ንግስት - - - እፀ መስቀል
ፍፁም አክብራችሁ - - - እፀ መስቀል
ሁላችሁ ገስግሱ - - - እፀ መስቀል
መስቀሉን ይዛችሁ - - - እፀ መስቀል
#አዝ
ያለኃይለ መስቀል - - - እፀ መስቀል
የሰላም አርማችን - - - እፀ መስቀል
ሊጠፋ አይችልም - - - እፀ መስቀል
ሰይጣን ጠላታችን - - - እፀ መስቀል
#አዝ
እሳተ መለኮት - - - እፀ መስቀል
ዙፋኑ የሆነው - - - እፀ መስቀል
ሰይጣንን የሚያነድ - - - እፀ መስቀል
እፀ መስቀሉ ነው - - - እፀ መስቀል
#አዝ
እንደተባረከ - - - እፀ መስቀል
ቆስጠንጢኖስ ንጉሥ - - - እፀ መስቀል
በመስቀል ብርሃን - - -እፀ መስቀል
ወደ ሕይወት እንገስግስ - እፀ መስቀል
#አዝ
የተዋህዶ ልጆች - - - እፀ መስቀል
ገስግሱ በተስፋ - - - እፀ መስቀል
እፀ መስቀል ያዙ - - - እፀ መስ
ከክርስቶስ መስቀል በቀር ሌላ ትምክህት ከእኔ ይራቅ (ገላ 6፡14) አይሁድ በመገረዝና ሕግን በመፈፀም ይመካሉ ጳውሎስ ግን በክርስቶስ የመሥዋዕትነት ሥራ ይመካል በእግዚአብሔር ክብር ተስፋ እንመካለን (ሮሜ 5፡2) መከራ ትዕግሥትን እንደሚያደርግ ትዕግሥትም ፈተናን ፈተናም ተስፋን እንደሚያደርግ እያወቅን በመከራቸውን እንመካለን (ሮሜ 5፡3) በማለት ሐዋርያው ቅዱስ ጳውሎስ እንደተናገረው ዲያብሎስ ድል የተነሣበት እኛም የቀደመ ክብራችንን ያገኘንበት በመሆኑ መስቀል ትምክህታችን ነው፡፡
ባጠቃላይም እናታችን ቤተ ክርስቲያን በዘወትር ጸሎቷ መስቀል ኃይላችን ነው፣ መስቀል ጽንአ ነፍሳችን ነው፣ መስቀል ቤዛችን ነው፣ መስቀል የነፍሳችን መድኃኒት ነው፣ አይሁድ ክደውታል፣ እኛ ግን አመንን፣ ያመንን እኛም በመስቀሉ ኃይል ዳንን ብላ ታስተምረናለች። ይህም የክርስቶስ መስቀል ዘወትር በልብ የሚታሰብ፣ በድርጊት የሚገለጽ በመሆኑ በመስቀሉ ኃይል መድኃኒትን አደረገ ብላ ቤተ ክርስቲያን በዝማሬ ትገልጻለች። ምክንያቱም መስቀል ጥል የተገደለበት ፣ ዲያብሎስ ከመንገድ የተወገደበት ነው;; (ኤፌ 2፡16,ቆላ 2፡14)። ስለዚህ ሰይጣን ይፈራዋል ተሸንፎበታል። ጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ በደሙ የዋጀው መስቀል ኃይል ነው። ስለዚህ ነው ሐዋርያው ቅዱስ ጳውሎስ የመስቀሉ ቃል ለሚጠፉት ሞኝነት ለእኛ ለምንድን ግን የእግዚአብሔር ኃይል ነው ያለው (1 ቆሮ 1፡18)፡፡
የሥላሴ ቸርነት፣የእመቤታችን አማላጅነት፣የመስቀሉ በረከት ይደርብን፡፡
አሜን!!!
መስቀል ቤዛችን ነው
መስቀል ቤዛችን ነው ድል መንሻ ኃይላችን/2/
ከኃጢአት በሽታ የሚፈውሰን/2/
በኃጢአት ጨለማ ተውጠን ሳለን/2/
የክርስቶስ መስቀል ብርሃን ሆነልን/2/
እንድንመስለው ጌታችንን
እንሸከመው ዕፀ መስቀሉን/2/
እንድንሸከም ዕፀ መስቀሉን/2/
ሰውነታችንን ማንፃት አለብን/2/
@meazahaymanot
✞አለው ሞገስ✞
አለው አለው ሞገስ ኧኸ አለው ሞገስ
የመስቀል በዓል ሲደርስ ኧኸ አለው ሞገስ
አለው አለው አበባ ኧኸ አለው አበባ
የመስቀል በዓል ሲገባ ኧኸ አለው አበባ
አለው አለው ደስታ ኧኸ አለው ደስታ
መስቀል ሲከብር በእልልታ ኧኸ አለው ደስታ
አለው አለው ሰላም ኧኸ አለዉ ሰላም
መስቀል ሲታይ በአለም ኧኸ አለው ሰላም
አለን አለን አለኝታ ኧኸ አለን አለኝታ
እፀመስቀል መከታ ኧኧ አለን አለኝታ
እዩት እዩት ሲያበራ ኧኸ እዩት ሲያበራ
የመስቀል በዓል ደመራ ኧኸ እዩት ሲያበራ
እዩት እዩት ሲያምር ኧኸ እዩት ሲያምር
መስቀል በዓለም ሲከብር ኧኸ እዩት ሲያምር
👇
•➢ ሼር // SHARE
https://docs.google.com/forms/d/1LnRCOLLvC80rbdC-GjYgyEBVnYcUYJBcdFoBKu5ho7Q/edit#responses
በማህበሩ የበጎ አድራጎት ተግባር ላይ መሳተፍ የሚፈልጉ አባላትን በመመዝገብ ለይ ይገኛል። እርሶም የዚህ መልካም አገልግሎት ተሳታፊ ይሆኑ ዘንድ መንፈሳዊ ጥሪያችንን እያስተላለፍን፤ መልካም ፈቃድዎ ከሆነ አና ስለማህበራችን የበለጠ ለመረዳት (Join) የሚለውን በመጫን የድህረ ገጻችን አባል ይሁኑ፡፡ ከድህረ ገጻችንም የሚገኘውን የአባልነት መመዝገብያ ቅጽ በመሙላት የማህበሩ አባል በመሆን አብረውን ይሰሩ ዘንድ መንፈሳዊ ጥሪያችንን በልዑል እግዚአብሔር ስም እና በእናታችን በቅድስት ድንግል ማርያም ስም እናቀርባለን።
#ሰንበተ ክርስትያን
እሑድ ማለት"አሐደ" ከሚለው የግዕዝ ቃል የወጣ ሲኾን ትርጉሙ የመጀመሪያ እንደማለት ነው። ይኽች ዕለት በመጽሐፍ ቅዱስ "ከሳምንቱ በፊተኛው ቀን " በመባል ትታወቃለች።
ዮሐንስም በራዕዩ "የጌታ ቀን" ያላት ናት
(ራዕይ 1፥10)
ቅዱስ ያሬድም በድጓው ላይ "ዕለተ እግዚአብሔር" የሚላት ዕለተ እሑድ ናት።
👉 እግዚአብሔር ሥራውን የጀመረባት ለሥነ ፍጥረት የመጀመሪያ ጥንተ ዕለት።
👉ጌታችን የተጸነሰባትና ዕርቅ የተወጠነባት የፍስሐ ቀን።
👉ዕለተ ትንሣኤ።
👉የቤተክርስቲያን የልደት ቀን።
👉መንፈስ ቅዱስ ለሐዋርያት የወረደባት - ኃይልና ጽናትን ያገኙባት ዕለት።
👉ጌታ በክበበ ትስብዕት በግርማ መለኮት ዳግም በቅዱሳን መላዕክቱ ታጅቦ በጌትነቱ ለፍርድ የሚመጣባት ታላቅ የፍርድ ቀን።
👉የተለያዩ መንፈሳዊ አገልግሎቶች የሚካኼዱባት ዕለት ናት።
#መልካም ዕለተ ሰንበት
#ባለ ማዕተቦችን ወደዚህ ግሩፕ ይጋብዙ
ለመቀላቀል @meazahaymanot
ኀበሩ ቃለ ነቢያተ
ወይቤሉ መስቀል ብርሃን ለኵሉዓለም
ትርጉም፡ ነቢያት በቃል ተባበሩ መስቀል ለዓለም ብርሃን ነው አሉ
@meazahaymanot
#ኀበ_ቀራንዮ
ኀበ ቀራንዮ ደብረ መድኃኒት
ቀራኒዮ /2/ ኀበ ቀራኒዮ
አዝ===========
የመስቀሉ ቃል ለእኛ የእግዚአብሔር ኃይል ነው /2/
ለማያምኑት ሞኝነት ነው ለእኛ ግን ሕይወት ነው
አዝ===========
እንመሰክራለን ፈጣሪያችን አለ
እንመሰክራለን ፈጣሪያችን አለ
እንመነው አንካደው ፈጣሪያችን ቸር ነው
አዝ===========
እንመሰክራለን ድንግል አማላጅ ናት
እንመሰክራለን ድንግል አማላጅ ናት
እንመናት አንካዳት የአማኑኤል እናት ናት
አዝ===========
ኀበ ጥበባት ኀበ ልሣናት /2/
ዮሐንስ /2/ ወንጌለ ስብከት
♡#በፍጥነት_ይቀላቀሉ_አብረን_እንዘምር♡
╭═•|❀:✧๑✝♡๑✧❀|: ═╮
@meazahaymanot
@meazahaymanot
@meazahaymanot
╰═•ೋ•✧✝๑♡๑✧• ═╯
የዕለቱ መልእክት
እኔ ከአንተ ጋራ ነኝና አትፍራ፤እኔ አምላክኽ ነኝና አትደንግጥ፤አበረታኻለኹ፥እረዳኽማለኹ፥በጽድቄም ቀኝ ደግፌ እይዝኻለኹ።
ኢሳይያስ ፵፩÷፲
So do not fear, for I am with you; do not be dismayed, for I am your God. I will strengthen you and help you; I will uphold you with my righteous right hand
Isaiah 41:10
መልካም ቀን
https://docs.google.com/forms/d/1LnRCOLLvC80rbdC-GjYgyEBVnYcUYJBcdFoBKu5ho7Q/edit#responses
በማህበሩ የበጎ አድራጎት ተግባር ላይ መሳተፍ የሚፈልጉ አባላትን በመመዝገብ ለይ ይገኛል። እርሶም የዚህ መልካም አገልግሎት ተሳታፊ ይሆኑ ዘንድ መንፈሳዊ ጥሪያችንን እያስተላለፍን፤ መልካም ፈቃድዎ ከሆነ አና ስለማህበራችን የበለጠ ለመረዳት (Join) የሚለውን በመጫን የድህረ ገጻችን አባል ይሁኑ፡፡ ከድህረ ገጻችንም የሚገኘውን የአባልነት መመዝገብያ ቅጽ በመሙላት የማህበሩ አባል በመሆን አብረውን ይሰሩ ዘንድ መንፈሳዊ ጥሪያችንን በልዑል እግዚአብሔር ስም እና በእናታችን በቅድስት ድንግል ማርያም ስም እናቀርባለን።
#የመስቀሉ ፍቅር
የመስቀሉ ፍቅር (ነገር) ሲገባን (4)
እመቤታችንን እናያታለን
የመስቀሉ ፍቅር የገባቸው (4)
እመቤታችን አለች ከጎናችው
አዝ--------------------------
አባ ሕርያቆስ አባታችን
የመስቀሉ ነገር ሲገባው
ልቤ አፈለቀ አለ መልካም ነገር
ከእመቤታችን ጋር ስነጋገር
ከድንግል ማርያም ጋረ ስነጋገር
አዝ--------------------------
ለመናኔው ጸሎት ልዩ ዕጣን
የዋሻው ሻማ ነሽ እመብርሃን
መዓዛሽ ሸተተኝ ከግሸን
ትናፍቂኛለሽ ምን ልሁን (2)
አዝ--------------------------
ዳዊት በመዝሙሩ ያነሳሳሻል
ያዕቆብ ድንኳን ነሽ ይልሻል
የእግዚአበሔር ሀገር የሚሉሽ
እመቤቴ ማርያም አንቺ ነሽ (2)
አዝ--------------------------
ቤተ ልሔም ስሄድ አይሻለሁ
ቀራንዮ ስሄድ አይሻለሁ
ፍጹም አትለዪም ከልጅሽ
ያንችስ ልዩ ነው ፍቅርሽ (2)
ሊቀ. መ ይልማ