meazahaymanot | Unsorted

Telegram-канал meazahaymanot - መዓዛ ሃይማኖት በጎ አድራጎትና ጉዞ ማህበር

3925

"ውድስት አንቲ በአፈ ነቢያት ወስብሕት በሐዋርያት አክሊለ በረከቱ ለያዕቆብ ወትምክህተ ቤቱ ለእስራኤል፡፡" "በነቢያት በሐዋርያት አንደበት የተመሰገንሽ የያዕቆብ የበረከቱ ዘውድ የእስራኤል ወገን መመኪያ አንቺ ነሽ"                  መጽሐፈ ሰዓታት የፌስቡክ ፔጃችን www.fb.me/meazhaimanot ይቀላቀሉን

Subscribe to a channel

መዓዛ ሃይማኖት በጎ አድራጎትና ጉዞ ማህበር

ወይራ ገነተ ሰማይ ቅድስት አርሴማ እና አቡነ እጨጌ ዮሐንስ ቤተክርስቲያን

ህዳር 29/2016 ዓ.ም

Читать полностью…

መዓዛ ሃይማኖት በጎ አድራጎትና ጉዞ ማህበር

ስንክሳር ዘወርሃ ህዳር ሃያ ዘጠኝ(፳፱)

@meazahaymanot

Читать полностью…

መዓዛ ሃይማኖት በጎ አድራጎትና ጉዞ ማህበር

✞የቃል ኪዳን አገር✞

የእግዚአብሔር ሕዝብ አገር
የቃልኪዳን ምድር /ኢትዮጵያ/(፪)
ምስጋናን ጀምሪ ብለሽ ሃሌ ሉያ

አይለውጥም ነብር ዥንጉርጉርነቱን
አይቀይርም ከቶ ኢትዮጵያዊ መልኩን
በሰርክ እና በንዋም እንዲሁም በነግሁ
ወደ እግዚአብሔር እጆችሽ ይዘርጉ

በብሉዩ በሓዲሱ በምኩራቡ በመቅደሱ
በአንድ አምላክ ጸንተሽ የኖርሽ
ቅድስት አገር ኢትዮጵያ ነሽ
አዝ= = = = =
በቅዱሱ መዝገብ ስምሽ የሰፈረ
ከቶ ማንም የለም እንደ አንቺ የከበረ
የአስራት አገሯ ለድንግል ማርያም
አንቺ እና ተዋሕዶ አትለያዩም

በብሉዩ በሓዲሱ በምኩራቡ በመቅደሱ
በአንድ አምላክ ጸንተሽ የኖርሽ
ቅድስት አገር ኢትዮጵያ ነሽ

አጊጠሽ የታየሽ በገዳም አድባራት
የምትጠበቂ በቅዱሳን ጸሎት
የክርስቶስ መስቀል ያረፈብሽ አገር
ትንሳኤሽን ያምጣው ቅዱስ እግዚአብሔር

በብሉዩ በሓዲሱ በምኩራቡ በመቅደሱ
በአንድ አምላክ ጸንተሽ የኖርሽ
ቅድስት አገር ኢትዮጵያ ነሽ

መዝሙር
ዲያቆን አቤል ተስፋዬ

"በውኑ ኢትዮጵያዊ መልኩን ወይስ ነብር ዝንጕርጕርነትን ይለውጥ ዘንድ ይችላልን?"

               ኤር ፲፫፥፳፫
╭══•|❀:✧๑♡๑✧❀|: ══╮
   @meazahaymanot
╰══•ೋ•✧๑♡๑✧•  ══╯

Читать полностью…

መዓዛ ሃይማኖት በጎ አድራጎትና ጉዞ ማህበር

ክቡራን የቻናላችን ተከታታዮች እግዚአብሔር ቢፈቅድና ብንደርስ  01/04/2016 ዓ.ም  9:00 ሰዓት ላይ ‟  ማኅደረ ጥያቄ ይጀምራል እንድትከታተሉ በልዑል እግዚአብሔር ስም እንጠይቃለን።

ሃሳብ አስተያየት @misiwani_Bot
አድርሱን



@meazahaymanot
@meazahaymanot
@meazahaymanot

Читать полностью…

መዓዛ ሃይማኖት በጎ አድራጎትና ጉዞ ማህበር

ክቡራን የተዋሕዶ ልጆች የዚህ መንፈሳዊ ቻናል ተከታታዮች እንዴት አደራችሁ አሜን የአባቶቻችን አምላክ የእኛም አምላክ ቅዱስ እግዚአብሔር የተመሰገነ ይሁን

አትለይምና የመመኪያችን ዘውድ የድኅነታችን መጀመሪያ የንጽሕናችን መሠረት እመአምላክ ቅድስት ድንግል ማርያም በተሰጣት ፀጋ የተመሰገነች ትሁን

እንዲሁም ቅዱሳን መላእክት ፣ቅዱሳን ነቢያት ፣ቅዱሳን ሐዋርያት ፣ቅዱሳን ጻድቃን ፣ቅዱሳን መካናት በተሰጣቸው ክብርና ፀጋ የተመሰገኑ ይሁኑ

ማኅደረ ጥያቄ (ጥያቄ መልስ ) መርሐግብር እስከሚጀምር  ምን እንጠይቅሎ የተሰኘው መርሐግብራችን ይቀጥላል

በመሆኑም ከዚህ በፊት በቴሌ ግራም ቻናላችን እንደምናደርገው በጥያቄዎቻችሁ ቅደም ተከተል መሠረት በየ ሳምንቱ ምላሽ የምንሰጥበት ሲሆን ግላዊ ጥያቄዎችንና ሰፊ ማብራሪያ የሚያስፈልጋቸውን ጥያቄዎች በኦዲዮ ቀድተን የምንልክላቹ መሆኑን ለማስታወስ እንወዳለን ::
ጥያቄዎቻችሁን ከታች ባለው የቴሌ ግራም ሊንክ መላክ የምችሉ መሆኑን እንጠቁማለን "

@misiwani_Bot

@misiwani_Bot

Читать полностью…

መዓዛ ሃይማኖት በጎ አድራጎትና ጉዞ ማህበር

ክቡራን የተዋሕዶ ልጆች የዚህ መንፈሳዊ ቻናል ተከታታዮች እንዴት አመሻችሁ አሜን የአባቶቻችን አምላክ የእኛም አምላክ ቅዱስ እግዚአብሔር የተመሰገነ ይሁን

አትለይምና የመመኪያችን ዘውድ የድኅነታችን መጀመሪያ የንጽሕናችን መሠረት እመአምላክ ቅድስት ድንግል ማርያም በተሰጣት ፀጋ የተመሰገነች ትሁን

እንዲሁም ቅዱሳን መላእክት ፣ቅዱሳን ነቢያት ፣ቅዱሳን ሐዋርያት ፣ቅዱሳን ጻድቃን ፣ቅዱሳን መካናት በተሰጣቸው ክብርና ፀጋ የተመሰገኑ ይሁኑ

ማኅደረ ጥያቄ (ጥያቄ መልስ ) መርሐግብር እስከሚጀምር  ምን እንጠይቅሎ የተሰኘው መርሐግብራችን ይቀጥላል

በመሆኑም ከዚህ በፊት በቴሌ ግራም ቻናላችን እንደምናደርገው በጥያቄዎቻችሁ ቅደም ተከተል መሠረት በየ ሳምንቱ ምላሽ የምንሰጥበት ሲሆን ግላዊ ጥያቄዎችንና ሰፊ ማብራሪያ የሚያስፈልጋቸውን ጥያቄዎች በኦዲዮ ቀድተን የምንልክላቹ መሆኑን ለማስታወስ እንወዳለን ::
ጥያቄዎቻችሁን ከታች ባለው የቴሌ ግራም ሊንክ መላክ የምችሉ መሆኑን እንጠቁማለን "

@misiwani_Bot

@misiwani_Bot

Читать полностью…

መዓዛ ሃይማኖት በጎ አድራጎትና ጉዞ ማህበር

ፃድቁ ሐብተማርያም

ጻድቁ ሐብተማርያም
መጥተናል እኛ ልጆችህ
አድነን አውጣን ከፈተና
አልብሰን የብርሀንን ፋና

ፃድቁ - ሰባት አክሊላትን
ፃድቁ - በራሱ የደፋ
ፃድቁ - በጾም በፀሎት ነው
ፃድቁ - ሰይጣንን ያጠፋ
ፃድቁ - ፅድቅን የታጠቀው
ፃድቁ - የእግዚአብሔር አገልጋይ
ፃድቁ - ፃድቁ አባታችን
አቡነ - የኢትዮጵያ ሲሣይ

አዝ—-
ፃድቁ - የዮስቲናስ ጸጋ
ፃድቁ - የፍሬ ብሩክ
ፃድቁ - ለኛ ለልጆችህ
ፃድቁ - መመኪያ የሆንክ
ፃድቁ - በምልጃህ አድለን
ፃድቁ - ፍቅርና ሰላም
ፃድቁ - ፃድቁ አባታችን
አቡነ - ሐብተ ማርያም.

አዝ—-
ፃድቁ - ከሱራፌል ጋራ
ፃድቁ - ለማቅረብ ምስጋና
ፃድቁ - ፅድቅን ተጎናጽፎ
ፃድቁ - ሀብተ ንፅሕና
ፃድቁ - በደብረ ሊባኖስ
ፃድቁ - ይሰበይ ላይ ያለው
ፃድቁ - ፃድቁ አባታችን
አቡነ - ሐብተማርያም ነው

አዝ—-
ፃድቁ - ብርሃንን ለብሶ
ፃድቁ - የእሳት መስቀል ይዞ
ፃድቁ - በጾም ጸሎት ጸንቶ
ፃድቁ - ንግስናውን ትቶ
ፃድቁ - በደብረ ሊባኖስ
ፃድቁ - ይሰበይ ላይ ያለው
ፃድቁ - ፃድቁ አባታችን
አቡነ - ሐብተማርያም ነው

አዝ—-
ፃድቁ - ባለመቶ ፍሬ
ፃድቁ - ሀብተማርያም
ፃድቁ - ቤታችንን ሞላው
ፃድቁ - ፍቅርና ሰላም
ፃድቁ - ሚስጥርን ተካፈልክ
ፃድቁ - ከጽርሐአርያም
ፃድቁ - ፃድቁ አባታችን
አቡነ - ሐብተማርያም

@meazahaymanot

Читать полностью…

መዓዛ ሃይማኖት በጎ አድራጎትና ጉዞ ማህበር

ስንክሳር ዘወርሃ ህዳር ሃያ ስድስት(፳፮)

@meazahaymanot

Читать полностью…

መዓዛ ሃይማኖት በጎ አድራጎትና ጉዞ ማህበር

መርቆሬዎስ /2/
የችግሬ ደራሽ ና በፈረስ
እንባዬን ልታብስ ፈጥነህ ድረስ

ባስልዮስ ጎርጎሪወቀስ ሰምሯል ልመናቸው
ስዕሉ ዘለለ ታምራት አያችሁ
እናንተን የረዳ መጥቶ በፈረስ
ዛሬም ለኛ ይድረስ ይምጣ መርቆሬዎስ

አዝ_

ዑልያኖስ ተገድሏል ሃይማኖት ይስፋፋል
ብሎ መሰከረ መርቆርዮስ ሃያል
ገፀ ከላባቱ ባህርይ ቀየሩ
እርሱን ለማገልገል ከእግሩ ስር አደሩ

አዝ_

ትካዜ ሀዘኔ ይርቃል ጭንቀቴ
መርቆርዮስ ሲመጣ ሲገባ ከቤቴ
በፀሊም ፈረሱ እየገሰገሰ
መርቆሬዎስ ወዳጄ ስጠራው ደረሰ

አዝ_

ስቃዩን ሊያረዝም ዳኪዎስ ወደደ
ከጨለማ እስር ቤት ታስሮ ተወሰደ
በጋለ ሹል ብረት መርቆሬዎስ ተወጋ
ስሙ ተሰየመ ከሰማዕት ጋ

አዝ_

አልፈራም መከራ አልፈራም ችግር
መፍቅሬ አብ ካለ ያኘሎፓዴር
ቂሳርያ እስር ቤት መርቆሬዎስ ታሰረ
ወህኒ ቤቱ በራ እግዚአብሔር ከበረ

ለኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ልጆች👇
                •➢ ሼር // SHARE

Читать полностью…

መዓዛ ሃይማኖት በጎ አድራጎትና ጉዞ ማህበር

ስንክሳር ዘወርሃ ህዳር ሃያ አምስት(፳፭)
@meazahaymanot

Читать полностью…

መዓዛ ሃይማኖት በጎ አድራጎትና ጉዞ ማህበር

እንኳን ለጻዲቁ አባታችን ለአቡነ ተክለሃይማኖት ዓመታዊ በዓል በሰላም አደረሳችሁ
   
       መልካም ቀን

Читать полностью…

መዓዛ ሃይማኖት በጎ አድራጎትና ጉዞ ማህበር

ከአሁን ጀምሮ እንደተለመደው ለቻናላችን ያላችሁን ሀሳብ አስተያየት ማቅረብ ትችላላችሁ። ቢኖሩ፣ ቢስተካከሉ የምትሏቸው ጉዳዮች ላይ አተኩራችሁ ስማችሁንና ከየት ሀገር እንደሆናችሁ እየገለጻችሁ በድምጽ ሆነ በጽሑፍ ላኩልን። ቤተሰቦቻችን የት የት እንዳሉም እንድናውቅና እንድንተዋወቅ ይረዳናል     ላይ @misiwani_Bot እንጠብቃችኋለን

ሐሳብ አስተያየታቸውን ጻፉልን

Читать полностью…

መዓዛ ሃይማኖት በጎ አድራጎትና ጉዞ ማህበር

ክቡራን የቻናላችን ተከታታዮች የእምዬ ኦርቶዶክስ ልጆች  የመጀመሪያ ዙር  ጥያቄ እና መልስ (ማኅደረ ጥያቄ ) ዛሬ ተጠናቋል ሁለተኛ ዙር ማኅደረ ጥያቄ መቼ እንደሚጀመር የምናሳውቃችሁ ይሆናል

የእግዚአብሔር ቃል ለሁሉም ይዳረስ ዘንድ ጸልዩ

Читать полностью…

መዓዛ ሃይማኖት በጎ አድራጎትና ጉዞ ማህበር

ማኅደረ ጥያቄ

፩. ከሐዋርያት መካከል  አስቀድሞ "አንተ የእግዚአብሔር ልጅ ነህ" ብሎ የተናገረው ማን ነው?

ሀ. ቅዱስ ጴጥሮስ
ለ. ቅዱስ ቶማስ
ሐ.ቅዱስ ናትናኤል
መ. ቅዱስ ፊልጶስ

፪. የጌታችን ዐበይት በዓላት ስንት ናቸው?

ሀ/ 7
ለ/8
ሐ/9
መ/10

፫. የቤተክርስቲያንናችን ትምህርት የሆነው የትኛው ነው?

ሀ/እግዚአብሔር አንድም ሦስትም ነው
ለ/መንፈስ ቅዱስ የሰረጸ ከአብ ብቻ ነው
ሐ/እመቤታችን ቅድስት ድንግል ማርያም የአምላክ እናት ናት
መ/ሁሉም መልስ ይሆናል

፬. የመንግስተ ሰማያት ምሳሌ የሆነው የትኛው ነው ❓
ሀ// በእርሻው መካከል ዘር የዘራው ሰው
ለ// እመቤታችን ቅድስት ድንግል ማርያም
ሐ// መልካምን ዕንቁ የሚሻ ነጋዴ
መ// ሁሉም መልስ ይሆናሉ

፭. ስግደት በምን አይነት ይከፋፈላል❓
ሀ// የአምልኮ እና የጸጋ
ለ// የጸጋ እና የአክብሮት
ሐ// የአክብሮት የጸጋና የአምልኮ
መ// መልሱ አልተሰጠም

መልሱን እስከ ማታ 3:00 ሰዓት በ @Asitmeherobot አድርሱን
     ☝️☝️☝️☝️☝️
    መልሱን በዚህ ሊንክ ብቻ  ላኩ

    #መልካም_እድል

Читать полностью…

መዓዛ ሃይማኖት በጎ አድራጎትና ጉዞ ማህበር

ስንክሳር ዘወርሃ ህዳር ሃያ ሁለት(፳፪)
@meazahaymanot

Читать полностью…

መዓዛ ሃይማኖት በጎ አድራጎትና ጉዞ ማህበር

ህዳር 29/2016 #ፃድቁ_ዮሐንስ_ዘጠገሮ

👉በስመ #አብ_ወወልድ_ወመንፈስ_ቅዱስ አሐዱ አምላክ አሜን አምላካችን መድኃኒታችን #ኢየሱስ_ክርስቶስን በፃድቁ ስም ለምናመሰግንበት ፃድቁ #እጨጌ_ዮሐንስ_ዘጠገሮ በምልጃ ፀሎታቸዉ እንዲያስቡን ለምንማፀንበት አመታዊ የልደት በአል መታሠቢያ ክብረ በአላቸውእንኳን አደረሰን

👉ኅዳር ሃያ ዘጠኝ በዚህች ቀን #አቡነ_እጨጌ_ዮሐንስ ዘጠገሮ ልደታቸው ነው ፃድቁ አባታችን የተወለዱት በኢየሩሳሌም አውራጃ ልዩ ስሙ ሳሬራ በሚባል ቦታ ነው የካቲት 28 ቀን ተፀንሰው ህዳር 29 ተወለዱ

👉አባታቸው #ድላሶር እናታቸው #እምነ_ፅዮን ይባላሉ ሲወለዱ በወላጆቻቸው ቤት ውስጥ ብርሃን ወርዷል ወላጆቻቸውም #እግዚአብሔርን የሚፈሩ ደጋግ ክርስቲያኖች ናቸው አባታችን ገና በተወለዱ በ5 ዓመታቸው ወላጆቻቸው ወደ እግዚአብሔር ቤት ይዘዋቸው የእመቤታችንን ሥዕል ተመልክተው በደስታ ተመልተው ሳቁ   

👉አምላክን የወለደች የብርሃን እናቱ #እመቤታችንም ከምሥሉ ወጥታ በምን አውቀኸኝ ነው ብላ አቅፋ ሳመችውና ከእንግዲ ወዲህ የልጄ አገልጋይ ትሆናለህ ኑሮህም እንደ #መላእክት ይሆናል በአንተ ምክንያት ብዙ ሰዎች ይድናሉ በምድር ላይም 500 አመት ትኖራለህ ብላ ባርካው ተሰወረች

👉ከዚያችም ቀን ጀምሮ  አባ ዮሐንስ #ለክርስቶስ ተላልፎ ተሰጠ 50 ዓመትም በበረሃ ሲጋደል ኖሮ ከ50 ዓመት በኋላ በደመና ተጭኖ በመልአኩ #በቅዱስ_ገብርኤል መሪነት ወደ ቅድስት ሀገር ኢትዮጵያ መጡ ጻድቁ አባታችን በአቡነ #ተክለሃይማኖት ዘመን መጨረሻ የመጡ ሲሆን ምንኩስና ከደብረ ሊባኖስ ገዳም #ከአቡነ_ተክለ_ሃይማኖት ተቀብለው በዚያው በደብረ ሊባኖስ ገዳም ለ50 ዓመት በፆምና በጸሎት በተጋድሎ ኖረዋል 

👉ከዚኽም በኋላ #አባ_ዮሐንስ ወደ ተዘጋቸላቸው ምድር #በቅዱስ_ገብርኤል አሳሳቢነት ወደ ጠገሮ መጡ ይኽም ጠገሮ ያለው ገዳማቸው በሰሜን ሸዋ በመንዝና ይፋት ክልል መዘዞ በሚባል ቦታ ሲደርሱ በእግር አንድ ሰዓት ከተጓዙ በኋላ ይገኛል

👉ሕዝቡ በተለምዶ #እጨ_ዮሐንስ እያለ ይጠራቸዋል እንጂ ስማቸው #እጨጌ_ዮሐንስ ነው #አቡነ_እጨጌ_ዮሐንስ መስቀል ከሰማይ የወረደላቸው ታላቅ አባት ናቸው መስቀሉም ሁልጊዜ ተአምር ይሠራል በልደታቸው ቀን ኅዳር 29 ቀን መስቀሉ ከመቅደሱ ወጥቶ በካህናቱ ታጅቦ ወደ ፀበሉ ሲወርድ ከየት እንደመጣ ሳይታሰብ ደመና መጥቶ ከመስቀሉ ላይ ብቻ እረቦና እንደ ጃንጥላ ተዘርግቶ አብሮ ወደ ፀበሉ ይወርዳል

👉እዛው ቆይቶ #መስቀሉ ሲመለስም አብሮ አጅቦ ይመለስና መስቀሉ ቤተ መቅደስ ውስጥ ሲገባ ደመናው ወዴት እንደተበተነ ሳይታወቅ ይጠፋል ይህ በዘመናችንም ጭምር እየታየ ያለ ታላቅ ተአምር ነው

👉የፃድቁ አባታችን ታሪክ ከብዙ በጥቂቱ ይህን ይመስላል

👉የአባታችን ፀሎትና ልመና ሀገራችንን ህዝባችንን ከክፉ መከራ ሁሉ ይሠዉርልን የከበረዉ ቃል ኪዳናቸው ሁላችንንም ይጠብቀን "አሜን" 💒 💚 💛 ❤️ 💒

Читать полностью…

መዓዛ ሃይማኖት በጎ አድራጎትና ጉዞ ማህበር

ክቡራን የቻናላችን ተከታታዮች እግዚአብሔር ቢፈቅድና ብንደርስ  01/04/2016 ዓ.ም  9:00 ሰዓት ላይ ‟  ማኅደረ ጥያቄ ይጀምራል እንድትከታተሉ በልዑል እግዚአብሔር ስም እንጠይቃለን።

ሃሳብ አስተያየት @misiwani_Bot
አድርሱን

ሦስት ቀን ቀረ


@meazahaymanot
@meazahaymanot
@meazahaymanot

Читать полностью…

መዓዛ ሃይማኖት በጎ አድራጎትና ጉዞ ማህበር

ስንክሳር ዘወርሃ ህዳር ሃያ ስምንት(፳፰)

@meazahaymanot

Читать полностью…

መዓዛ ሃይማኖት በጎ አድራጎትና ጉዞ ማህበር

አቤቱ ባንተ ታምኛለሁና አትጣለኝ✝ 
                                                  
Size:- 36.3MB
Length:-1:44:20
       
     በርዕሰ ሊቃውንት አባ ገብረ ኪዳን ግርማ
http://t.me/meazahaymanot
http://t.me/meazahaymanot

Читать полностью…

መዓዛ ሃይማኖት በጎ አድራጎትና ጉዞ ማህበር

ስንክሳር ዘወርኃ ህዳር ሃያ ሰባት

@meazahaymanot

Читать полностью…

መዓዛ ሃይማኖት በጎ አድራጎትና ጉዞ ማህበር

በስመአብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ አሐዱ አምላክ አሜን !!!

እንዴት ከረማችሁ እንዴት አደራችሁ አሜን ለዚህ ቀን ያደረስን  እግዚአብሔር  ይመስገን

      እንሆ እግዚአብሔር ደስ የሚያሰኘው
    ነፍሳችንንም  የምናድንበት
አቅምየሌላቸው አረጋውያን፣እናቶች፣አባቶች፣አሳዳጊ የሌላቸው ሕፃናት የምንመለከትበት ቀን ደረሰ
እግዚአብሔር ወልድ  ለኛ ብሎ ምንም ሳይጎድልበት  እኛ ከሱ ትሕትናን መደጋገፍን ገንዘብ እናደርግ ዘንድ ሲል  በከብቶች በረት ተወለደ  የሚለብሰውም አጥቶ እንሰሳት ትንፋሻቸውን ገበሩለት?

እናቶቼ አባቶቼ ወንድሞቼ እህቶቼ አሁንም
በእኛ ዘመን እግዚአብሔር በነዳያን ላይ አድሮ
አልብሱኝ፣ አጠጡኝ ፣አብሉኝ እያለ ነው።

እናሰተውል  ብዙ ገቢረ ተአምር ከሚሰራ ይልቅ  በስሙ ለነደያን እጁን የዘረጋ በእግዚአብሔር  ፊት እጅግ የከበረ ነው።

ስለዚህ ሁላችንንም ያለችንን ለነዳያን እንስጥ
ምንም ባይኖረን ቢያንስ የአንድ ቀን ካርድ ለአንድ ነዳያን ዳቦ መግዣ ይሆናል ስለዚህ
ወገኖች በኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ቁጥር✟✟✟ 1000-13-24-85-929 GERBA K.GIORGIS ENA KT.K/MIHRET S/T👈👈👈👈

ከላይ በተቀመጠው አካውንት እያስገባችሁ
ደረሰኙን እስክሪን ሹት እያረጋችሁ ላኩልን

እግዚአብሔር  ሀገራችንን ይጠብቅልን
የተሰደዱትን ወደ ሀገራቸው ይመልስልን
እኛም ከበዓለ ልደቱ በረከት እንሳተፍ ዘንድ
ልቦናችንን ያቅናልን።

Читать полностью…

መዓዛ ሃይማኖት በጎ አድራጎትና ጉዞ ማህበር

እንኳን ለጻድቁ አቡነ ኢየሱስ ሞዓ እና የጻድቁ አቡነ ሐብተ ማርያም የዕረፍት በዓል በሰላም አደረሳችሁ

የአባታችን የአቡነ ኢየሱስ ሞዓ እና የአቡነ ሐብተ ማርያም ረድኤታቸው ጸሎታቸውና አማላጅነታቸው ከሁላችንም ጋር ይሁን አሜን

መልካም ቀን

Читать полностью…

መዓዛ ሃይማኖት በጎ አድራጎትና ጉዞ ማህበር

ክቡራን የተዋሕዶ ልጆች የዚህ መንፈሳዊ ቻናል ተከታታዮች እንዴት አመሻችሁ አሜን የአባቶቻችን አምላክ የእኛም አምላክ ቅዱስ እግዚአብሔር የተመሰገነ ይሁን

አትለይምና የመመኪያችን ዘውድ የድኅነታችን መጀመሪያ የንጽሕናችን መሠረት እመአምላክ ቅድስት ድንግል ማርያም በተሰጣት ፀጋ የተመሰገነች ትሁን

እንዲሁም ቅዱሳን መላእክት ፣ቅዱሳን ነቢያት ፣ቅዱሳን ሐዋርያት ፣ቅዱሳን ጻድቃን ፣ቅዱሳን መካናት በተሰጣቸው ክብርና ፀጋ የተመሰገኑ ይሁኑ

ማኅደረ ጥያቄ (ጥያቄ መልስ ) መርሐግብር እስከሚጀምር ምን እንጠይቅሎ የተሰኘው መርሐግብራችን ይቀጥላል

በመሆኑም ከዚህ በፊት በቴሌ ግራም ቻናላችን እንደምናደርገው በጥያቄዎቻችሁ ቅደም ተከተል መሠረት በየ ሳምንቱ ምላሽ የምንሰጥበት ሲሆን ግላዊ ጥያቄዎችንና ሰፊ ማብራሪያ የሚያስፈልጋቸውን ጥያቄዎች በኦዲዮ ቀድተን የምንልክላቹ መሆኑን ለማስታወስ እንወዳለን ::
ጥያቄዎቻችሁን ከታች ባለው የቴሌ ግራም ሊንክ መላክ የምችሉ መሆኑን እንጠቁማለን "

@misiwani_Bot

@misiwani_Bot

Читать полностью…

መዓዛ ሃይማኖት በጎ አድራጎትና ጉዞ ማህበር

እንኳን ለቅዱስ መርቆሪዎስ አመታዊ ክብረ በዓል በሰላም አደረሳችሁ አደረሰን!!!

Читать полностью…

መዓዛ ሃይማኖት በጎ አድራጎትና ጉዞ ማህበር

በሲኤምሲ መካነ ጻድቃን አቡነ ተክለሃይማኖት እና ቅድስት ልደታ ለማርያም ቤተክርስቲያን በዓል አከባበር

Читать полностью…

መዓዛ ሃይማኖት በጎ አድራጎትና ጉዞ ማህበር

ስንክሳር ዘወርሃ ህዳር ሃያ አራት(፳፬)

@meazahaymanot

Читать полностью…

መዓዛ ሃይማኖት በጎ አድራጎትና ጉዞ ማህበር

ስንክሳር ዘወርሃ ህዳር ሃያ ሦስት(፳፫)

@meazahaymanot

Читать полностью…

መዓዛ ሃይማኖት በጎ አድራጎትና ጉዞ ማህበር

ማኅደረ ጥያቄ

#መልስ

1. ሀ

‹‹አንተ ውእቱ ክርስቶስ ወልደ እግዚአብሔር ሕያው፤ አንተ የሕያው እግዚአብሔር ልጅ ክርስቶስ ነህ››
ማቴዎስ ወንጌል 16÷13

2. ሐ

ብስራት
ልደት
ጥምቀት
ደብረታቦር
ሆሳዕና
ስቅለት
ትንሳኤ
እርገት
ጵራቅሊጦስ

3. መ

ምሥጢረ ሥላሴ
ነገረ ማርያም

4. መ

ማቴ 13፤24 ሌላ ምሳሌ አቀረበላቸው እንዲህም አለ፦ መንግሥተ ሰማያት በእርሻው መልካም ዘርን የዘራን ሰው ትመስላለች።


” መንግሥተ ሰማያት ክቡር ዕንቁን የሚሻ ነጋዴን ትመስላለች።” ማቴ.13፡45


5.ሐ

የስግደት አፈጻጸም ሥርዐት መሬት ላይ በመውደቅ ወይም ሙሉ በሙሉ ተደፍተው የሚሰግዱት ስግደት ሲሆን በልዩ ስሙ  ወዲቅ በመባል ይታወቃል።

* ሁለተኛው የስግደት ዐይነት  ‎አስተብርኮ /Kneeling/ በመባል ይታወቃል፡፡ ይህም ስያሜው እንደሚጠቁመው ጉልበትን ሸብረክ በማድረግ፣ በጉልበት በመቆም ወይም በመንበርከክ የሚፈጸም ነው፡፡

* ሦስተኛው የስግደት አፈጻጸም ዐይነት  አድንኖ /Bowing/ ይባላል፡፡አድንኖ ራሥን፣ ግንባርን፣ አንገትን ዝቅ በማድረግ የሚሰገድ ነው - “አድንኑ አርእስቲክሙ ቅድመ እግዚአብሔር አምላክነ…” እንዲባል በቅዳሴ፡፡

የአምልኮ ስግደት: ለእግዚአብሔር የምንሰግደው የስግደት ዐይነት ሲሆን የአምልኮ /የባሕርይ/ ስግደት ይባላል፡፡ 
የጸጋ ስግደት: ጸጋ እግዚአብሔርን ላገኙ ቅዱሳን ሁሉ የሚሰገድ የጸጋ ስግደት ነው፡፡ ቅድስት ድንግል ማርያም ፣ ቅዱስ መስቀል ፣ ቅዱሳን መላእክት ፣ ሰማዕታት ፣ ፃድቃን ፣ ቅዱሳን ፣ ቅድስት ቤተ ክርስቲያን ፣ ቅዱሳን ቦታዎች ፣ ታቦት ፣ ቅዱሳት ንዋያት እዚህ ውስጥ የሚካተቱ ናቸው፡፡


የአክብሮት ሰላምታ ስግደት (Latria)

🕹 መጽሐፍ ቅዱስ በቀደመው ዘመን ሰዎች ሰላምታ ለመለዋወጥና አክብሮታቸውን ለመገላለጥ ሲሉ ለሚያውቁም ሆነ ለማያውቁት ሰው ይሰግዱ እንደነበር ያሳያል፤ የሚዋደዱት ጓደኛሞች የዳዊትና የዮናታንን ስንብት እናስቀድም

✍‹‹ዳዊትም ከሥፍራው በደቡብ አጠገብ ተነሣ፤ በምድርም ላይ በግንባሩ ተደፋ፤ ሦስት ጊዜም ለሰላምታ ሰገደ፤ እየተላቀሱም እርስ በእርሳቸው ተሳሳሙ ይልቁንም ዳዊት እጅግ አለቀሰ››
📖1ኛ ሳሙ 20፥41


ለቅዱሳን መስገድን ያስተማረው እግዚአብሔር ነው
በዘፍ. 27፡29፣ ዘፍ.37-41፣ዘፍ.37፡7 ፣በራእየ ዮሐንስ 3÷1


የተሣተፉ

1. ፍቅር ያሸንፋል 5/5

2. ሰላም 5/5

3. Begize 3/5

4. Fanta 3/5

5. Tamiru 5/5

6. ሰኒ 5/5

7. መላኩ 5/5

8. hirut 5/5

9. Sol 3/5

10. ኤልያብ 4/5

11. መቅደሰማርያም 5/5

12. ብሌን 5/5

13. Tomi 5/5

14. ሜሮን 5/5

15. Liya 5/5

16. Radiet 5/5

17. Tig 5/5

18. ቤተልሔም 5/5

19. አሰፋ 5/5

20. kal 5/5

21.tirngo 4/5

22. Semhal 4/5

23. Buze 5/5

24. ታሪክአየሁ 5/5

25. selam 5/5

26. Natneal 4/5

27. Yodit 5/5

28. ገብረ ማርያም 5/5

29. ቅዱስ 5/5

30. ይታገሱ 5/5

31. እግዚአብሔር እረኛዬ ነው 4/5

ለተሣተፉት ቃለ ሕይወትን ያሰማልን መንግሥተ ሰማያትን ያውርስልን

Читать полностью…

መዓዛ ሃይማኖት በጎ አድራጎትና ጉዞ ማህበር

✞ዑራኤል✞

አባቴ ጠባቂዬ ሞገሴ ታዳጊዬ
ዑራኤል ለኔ ልዪ ነህ
የምትረዳኝ ከአምላክ ተልከህ

በደመ ክርስቶስ ዑራኤል መልአክ
ልትቀድስ ዓለምን >> >>
በክብር አስጊጦ >> >>
አምላክ መረጠህ >> >>
ለኔስ ልዩ ነው ያንተ ፍቅር
ቁምልኝ ቅዱስ ዑራኤል በቅድመ እግዚአብሔር
አዝ= = = = =
የእውቀትን ጽዋ ዑራኤል መልአክ
ለዕዝራ እንዳጠጣህ >> >>
እኔንም ከኃጢአት >> >>
ከሞት አፍ አውጣኝ >> >>
ለኔስ ልዩ ነው ያንተ ፍቅር
ቁምልኝ ቅዱስ ዑራኤል በቅድመ እግዚአብሔር
አዝ= = = = =
የመንገዴ እንቅፋት ዑራኤል መልአክ
ተነሳ ከፊቴ >> >>
የአምላክ ባለመዋዕል >> >>
ሆነኸኝ ብርታቴ >> >>
ለኔስ ልዩ ነው ያንተ ፍቅር
ቁምልኝ ቅዱስ ዑራኤል በቅድመ እግዚአብሔር
አዝ= = = = =
በእምነት አበረታኝ ዑራኤል መልአክ
ለነፍሴ እየራራ >> >>
አገዘኝ ዑራኤል >> >>
ፍሬን እንዳፈራ >> >>
ለኔስ ልዩ ነው ያንተ ፍቅር
ቁምልኝ ቅዱስ ዑራኤል በቅድመ እግዚአብሔር

እንኳን አደረሳችሁ አደረሰን🥰
🙏 መልካም በአል 🙏

ለኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ልጆች👇🏽
•➢ ሼር // SHARE





@meazahaymanot

Читать полностью…

መዓዛ ሃይማኖት በጎ አድራጎትና ጉዞ ማህበር

ማኅደረ ጥያቄ

፩. ከሐዋርያት መካከል  አስቀድሞ "አንተ የእግዚአብሔር ልጅ ነህ" ብሎ የተናገረው ማን ነው?

ሀ. ቅዱስ ጴጥሮስ
ለ. ቅዱስ ቶማስ
ሐ.ቅዱስ ናትናኤል
መ. ቅዱስ ፊልጶስ

፪. የጌታችን ዐበይት በዓላት ስንት ናቸው?

ሀ/ 7
ለ/8
ሐ/9
መ/10

፫. የቤተክርስቲያንናችን ትምህርት የሆነው የትኛው ነው?

ሀ/እግዚአብሔር አንድም ሦስትም ነው
ለ/መንፈስ ቅዱስ የሰረጸ ከአብ ብቻ ነው
ሐ/እመቤታችን ቅድስት ድንግል ማርያም የአምላክ እናት ናት
መ/ሁሉም መልስ ይሆናል

፬. የመንግስተ ሰማያት ምሳሌ የሆነው የትኛው ነው ❓
ሀ// በእርሻው መካከል ዘር የዘራው ሰው
ለ// እመቤታችን ቅድስት ድንግል ማርያም
ሐ// መልካምን ዕንቁ የሚሻ ነጋዴ
መ// ሁሉም መልስ ይሆናሉ

፭. ስግደት በምን አይነት ይከፋፈላል❓
ሀ// የአምልኮ እና የጸጋ
ለ// የጸጋ እና የአክብሮት
ሐ// የአክብሮት የጸጋና የአምልኮ
መ// መልሱ አልተሰጠም

መልሱን እስከ ነገ 6:00 ሰዓት በ @Asitmeherobot አድርሱን
☝️☝️☝️☝️☝️
መልሱን በዚህ ሊንክ ብቻ ላኩ

#መልካም_እድል

Читать полностью…
Subscribe to a channel