ማኅደረ ጥያቄ
ኢትዮጵያውያን ቅዱሳን ከሚባሉት ምረጡና ስለ ቅዱሱ ታሪክ በpdf አዘጋጁ የሚቆየው ለሁለት ሳምንት ነው ተሳተፉ
አዘጋጅታችሁ ከጨረሳችሁ በኋላ በ @Asitmeherobot ላኩልን
ወወለደት ወልደ ዘበኩራ
መንጦላዕተ ደመና ሠወራ/2x/
ትርጉም ፡ የበኩር ልጇን ወለደች የደመና መጋረጃም ጋረዳት
👇👇👇👇👇👇👇👇👇
👉 @meazahaymanot 👈
👉 @meazahaymanot 👈
👆👆👆👆👆👆👆👆👆
ማኅደረ ጥያቄ
ኢትዮጵያውያን ቅዱሳን ከሚባሉት ምረጡና ስለ ቅዱሱ ታሪክ በpdf አዘጋጁ የሚቆየው ለሁለት ሳምንት ነው ተሳተፉ
አዘጋጅታችሁ ከጨረሳችሁ በኋላ በ @Asitmeherobot ላኩልን
የልደት መዝሙር
ተወልደ ኢየሱስ
ተወልደ ኢየሱስ 'በቤተልሔም'(2) ዘይሁዳ በቤተልሔም:(2)
አዋልደ ጢሮስ 'አሜሃ ይሰግዳ'(2) በቤተልሔም:(2)
@meazahaymanot
እንዴት አመሻችሁ የመዓዛ ሃይማኖት ቤተሰቦች
የመዓዛ ሃይማኖት የፌስቡክ ገፅ ተከታዮችን ለመጨመርና የሚለቀቁ መረጃዎችን ለብዙዎች ተደራሽ እንዲሆን ሁላችንም ከስር የተጠቀሰውን በማድርግ ኃላፊነታችንን እንወጣ!
1. ይሄን የፌስቡክ ሊንክ ስንጫን 👉 fb.me/meazhaimanot ወደ መዓዛ ሃይማኖት የፌስቡክ ገፅ ይወስደናል (ወይም ሊንኩን ኮፒ በማድረግ ወደ ፌስቡክ አካውንታችን Search box ላይ Paste አድርገን Search ማድረግ እንችላለን)
⬇
2. ገፁን ላይክና ፎሎው ያላደረግን እናድርግ
⬇
3. በመቀጠል እዛው ገፅ ላይ 👇
#Invite_your_friend_to_like_this_page የሚለውን ስንጫን የፌስቡክ ጓደኞቻችን ስም ዝርዝር ይመጣልናል
⬇
3. የመጣልንን የስም ዝርዝር እያንዳንዱን መርጠን ስንጨርስ #Done የሚለውን በመጫን ጓደኞቻችን ገፁን ላይክ እንዲያደርጉ ጋበዝናቸው ማለት ነው። (ሁሉንም ጓደኞቻችንን invite አድርገን እስክንጨርስ የተጠቀሰውን ማድረግ አንርሳ)
facebook page: http://fb.me/meazhaimanot
ይቀላቀሉን ጓደኞቻችሁንም ወደ ገፃችን ይጋብዟቸው!
ማኅደረ ጥያቄ
፩. ቅዱሳን ሥዕላት በቤተክርስቲያን የተጀመረው መቼ ነው?
፪. ቅዱሳን ሥዕላት ለምን ያስፈልጋሉ?
፫. በመጀመሪያ ጊዜ የጌታን ሥዕል የሳለው ቅዱስ አባት ማነው
፬. እኔና ቤቴ እግዚአብሔርን እናመልካለን ይኸ የመጽሐፍ ቅዱስ ጥቅስ በየትኛው የመጽሐፍ ክፍል ይገኛል
እውነት ወይም ሐሰት
፭. በመጀመሪያ የእመቤታችንን ሥዕል የሳለው አባ ሕርያቆስ ነው
መልሱን እስከ ማታ 3:00 ሰዓት በ @Asitmeherobot አድርሱን
መልሱን ከላይ ባለው ሊንክ ብቻ ይላኩ
#መልካም_እድል
ሁለተኛ ዙር ማኅደረ ጥያቄ
ራስን መግዛት (ክፍል -፩)
መንፈሳዊው ሰው ካሉት ብቃቶች መካከል አንዱና ዋነኛው ራስን መግዛት ነው፡፡ እርሱ ራሱን ለሥጋ ምኞትና ለፍላጎቶቹ አሳልፎ አይሰጥም፡፡ ሕሊናው የኃጢአትን ምኞት ሲናፍቅ ይህን አሳቡን በመቃወም መንፈሱ እንድትመራው በማድረግ ራሱን አጥብቆ ይገዛል:: መጽሐፍ ቅዱስ እንዲህ ይላል:- «በመንፈሱ ላይ የሚገዛ (መንፈሱን የሚገዛ) ከተማ ከሚወስድ ይበልጣል፡፡» ምሳ. 16፥32
እንደ መድኃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ትምህርት ራሱን የሚገዛ ወይም የሚመራ ማለት ሥጋው የጠየቀውን ሁሉ የማይሰጥ ይልቁኑ የሚቃወም ማለት ነው:: «ነፍሱን የሚወድ ያጠፋታል፤ነፍሱን በዚህ ዓለም የሚጠላ ለዘላለም ሕይወት ይጠብቃታል፡፡» ዮሐ. 12፥25።
ራስን መግዛት በውስጡ የተለያዩ ክፍሎች እንዳሉት እርግጥ ነው፡፡ እነርሱም፤-
1. #ምላስን_መግዛት፡፡
2. #አሳብን_መግዛት::
3. #ልብን_መግዛት፡፡ (ፍላጎትንና ምኞትን በመግዛት)
4. #ስሜትን_መግዛት::
5. #ሆድን_መግዛት (ምግብን በተመለከተ) ናቸው፡፡
ራሱን የሚመራ ሰው እርሱነቱን ለእሴትና ለዓላማ እንዲሁም ለሕግና ደንብ ያስገዛል፡፡ ራሱን መምራት የማይችል ሰው ግን በእርግጥ እርሱነቱን ለጥፋት ይጋብዛል፡፡ ራሱን የሚገዛ ሰው ነፍሱን በእውነተኛ ፍቅር ይወዳታል:: ራሱን የሚያቀናጣ ግን ነፍሱን ከማጣቱም በላይ ሌሎችም ከእርሱ ጋር አብረው እንዲጠፉ ያደርጋል፡፡ ራሱን አጥብቆ የሚጠብቀው በትጋቱ ነፍሱን ስለሚጠብቃትና በመልካም ሁኔታ ስለሚይዛት ያድናታል፡፡ አልፎ ተርፎም ሌሎችን ለማዳን ምክንያት ይሆናል፡፡ የራሱን አመለካከትና ግንኙነት በቅደም ተከተል ያደራጃል፡፡ በመጀመሪያ እግዚአብሔርን ያስቀድማል፤ በመቀጠል ሰዎችን ያስከትላል፤ በመጨረሻም ራሱን።
#ምላስን_መግዛት፡፡
መንፈሳዊው ሰው ቃላት ወይም አሳቦች ያቀበሉትን ወደ አእምሮው የመጡትን ሁሉ በአንደበቱ አይናገራቸውም፡፡ እያንዳንዱን ቃል ከአንደበቱ ከማውጣቱ በፊት ይመዝናል:: የእርሱ ሚዛን የሚለካው የቃሉን ፍሬ ነገር ብቻ ሳይሆን ትክክል መሆኑንና አለመሆኑንም ጭምር ነው፡፡ ከዚህ በተጨማሪ የእርሱ ዋና ዓላማው ቃሉ በሌሎች ሰዎች ላይ የሚያመጣውን ተጽዕኖ፣አፀፋና ውጤቱን ጭምር ነው::
የምላስ ወይም የአንደበት ስህተት ውጤት ሥጋን ማሳደፉንና የፍጥረትንም ሩጫ ማቃጠሉን የሚያውቅ ሰው ከመናገሩ በፊት ከፍተኛ ጥንቃቄ ያደርጋል:: ያዕ. 3፥5-6:: ከነቢዩ ከዳዊት ጋር ሆኖም:- «አቤቱ ለአፌ ጠባቂ አኑር፤ የከንፈሮቼንም መዝጊያ ጠብቅ፡፡» ይላል፡፡ እርሱ አንዴ ከአፉ የወጣው ቃል ተመልሶ ሊገባ እንደማይችል ያውቃል፡፡
ከዚህ በተጨማሪ ከአፉ የወጣው ቃል አድማጮቹ ጆሮ ከደረሰ በኋላ የተናገረውን መልሶ ሊውጠው፣ ወይም ይቅርታ ሊያገኝበት እንደማይችል አስቀድሞ ያውቃል:: ከዚህ በኋላ ስህተቱን ለማስተካከል ቢጥርም ጥፋቱ በእርሱ ላይ ዕዳ ሆኖ እንደሚቆጠር አጥብቆ ይረዳል፡፡ ከሁሉ በላይ ደግሞ ጌታ እንደተናገረው እንደሚኮነንበት ያውቃል፡ . . . ከቃልህ የተነሣ ትጸድቃለህና፤ ከቃልህም የተነሣ ትኮነናለህ፡፡» ማቴ. 12፥37::
#ይቀጥላል...
(#በብፁዕ_አቡነ_ሺኖዳ_ሣልሳዊ
#መንፈሳዊ_ሰው_መጽሐፍ ገጽ 122-128
#በአያሌው_ዘኢየሱስ_የተተረጎመ)
የምስራች
የምስራች ደስ ይበለን/2x/
የዓለም መድኃኒት ተወለደልን
ምስራች ደስ ይበለን
የምስራች ደስ ይበለን/2x/
ጌታችን ተወልዶ አይተነው መጣን/2x/
ንጉስ ሄሮድስ ይህን ሲሰማ/2x/
ፈልጋችሁ አምጡት በቀን በጨለማ/2x/
ሰብአ ሰገል እንደታዘዙት/2x/
በኮከብ ተመርተው ህፃኑን አገኙት/2x/
ሰገዱለት ከመሬት ወድቀው/2x/
ወርቅና ዕጣኑን ከርቤውንም ሰጥተው/2x/
👇👇👇👇👇👇👇👇👇
👉 @meazahaymanot 👈
👆👆👆👆👆👆👆👆👆
ማኅደረ ጥያቄ
፩.መልአኩ ዮሐንስን ለምን እንዳይሰግድለት ጠየቀው?
፪.መልአኩ ከሌሎች ለይቶ ዮሐንስን ለምን እንዳይሰግድ ጠየቀው?
፫. ምን ብለን ወይም እያልን እንስገድ
፬. በልተን መስገድ እንችላለን?
፭.ስግደትን እንዴት እንለማመድ
መልሱን እስከ ማታ 3:00 ሰዓት @Asitmeherobot አድርሱን
መልሱን በሊንኩ ብቻ ይላኩ
#መልካም_እድል
ሁለተኛ ዙር ማኅደረ ጥያቄ
እንኳን ለሰማዕቷ እናታችን ለቅድስት በርብራ ዓመታዊ በዓል በሰላም አደረሳችሁ የሰማዕቷ እናታችን ታሪክ ማግኘት የምትፈልጉ በፌስቡክ ፔጃችን ላይ በመግባት ያገኙታል
በመጀመሪያ ፔጃችንን ፎሎ ላይክ ሼር በማድረግ አዳርሱ
መታሰቢያ በዓሏ ታኅሣሥ ፰
እንኳን ለሰማዕቷ እናታችን ለቅድስት በርብራ ዓመታዊ በዓል በሰላም አደረሳችሁ የሰማዕቷ እናታችን ታሪክ ማግኘት የምትፈልጉ በፌስቡክ ፔጃችን ላይ በመግባት ያገኙታል
በመጀመሪያ ፔጃችንን ፎሎ ላይክ ሼር በማድረግ አዳርሱ
መታሰቢያ በዓሏ ታኅሣሥ ፰
#በጎል_ሰከበ
በጎል ሰከበ በአጽርቅት ተጠብለለ /2/
ቤዛ ኩሉ ዓለም/2/ ዮም ተወለደ /4/
#ትርጉም፡-
በበረት ተኛ በጨርቅ ተጠቀለለ
የዓለም መድኃኒት/2/ ዛሬ ተወለደ/2/
💚 @meazahaymanot💚
💛 @meazahaymanot 💛
❤️ @meazahaymanot❤️
*ወደ እግዚአብሔር በጮኽን ጊዜ ድምፃችንን ሰማ መልአክንም ሰድዶ ከግብፅ አወጣን*
*(ኦሪት ዘኁልቁ ፳ ፥ ፲፮)*
በላእከ ወንጌል ቀሲስ ተክለ ወልድ ደምሴ
ለመምህራችን ቃለ ሕይወት ያሰማልን
//ደቂቃው *45:33*//
መልካም ቆይታ🌾
ማኅደረ ጥያቄ
፩. ቅዱሳን ሥዕላት በቤተክርስቲያን የተጀመረው መቼ ነው?
እስራኤላውያን ቀደም ሲል ሰዎች ድንጋይን በማዘጋጀት፣ እንጨትን በመጥረብ፣ ቆዳን በመፋቅ፣ ኅብር ባላቸው ቀለማት በመሳል ለትውልድ እንዲተላለፉ ያደርጉ ነበር፡፡ የቅዱሳት ሥዕላት አጀማመር ዘመነ ኦሪትን መነሻ ያደረገ ነው፤ አስቀድሞ ልዑል እግዚአብሔር ለነቢዩ ሙሴ በታቦተ ሕጉ ላይ ሥዕለ ኪሩብን እንዲሥል አዘዘው፡፡(ዘጸ. ፳፭፥፲፱-፳)
ስለ ቅዱሳትሥዕላት አጀማመር በመጽሐፍ ቅዱስ እንዲህ ተብሎ ተጽፏል፡፡ ‹‹በቅድስተ ቅዱሳኑም ውስጥ ቁመታቸው አሥር ክንድ የሆነ ከወይራ እንጨት ሁለት ኪሩቤልን ሠራ፡፡ የኪሩብም አንደኛው ክንፍ አምስት ክንድ÷ የኪሩብም ሁለተኛው ክንፍ አምስት ክንድ ነበረ፤ ከአንደኛው ክንፍ ጫፍ ጀምሮ እስከ ሁለተኛው ክንፍ ጫፍ ድረስ አሥር ክንድ ነበረ፡፡ ሁለቱም ኪሩቤል አንድ ልክና አንድ መልክ ነበረ፡፡ የአንዱ ኪሩብ ቁመት አሥር ክንድ ነበረ÷ የሁለተኛውም ኪሩብ እንዲሁ ነበረ፡፡ ኪሩቤልንም በውስጠኛው ቤት አኖራቸው፤ የኪሩቤልም ክንፎቻቸው ተዘርግተው ነበር፡፡ የአንዱም ኪሩብ ክንፍ አንደኛውን ግንብ ይነካ ነበር÷ የሁለተኛውም ኪሩብ ክንፍ ሁለተኛውን ግንብ ይነካ ነበር፤ የሁለቱም ክንፎች በቤቱ መካከል እርስ በርሳቸው ይነካኩ ነበር፡፡ ኪሩቤልንም በወርቅ ለበጣቸው፡፡ በቤቱም ግንብ ሁሉ ዙሪያ በውስጥና በውጭ የኪሩቤልና የዘንባባ ዛፍ የፈነዳም አበባ ምስል ቀረጸ››፡፡(፩ኛ ነገሥት ፮፥፳፫-፳፱) በትንቢተ ሕዝቅኤልም ‹‹አንተም÷ የሰው ልጅ ሆይ÷ ጡቡን ወስደህ በፊት አኑራት፤ የኢየሩሳሌምንም ከተማ ሥዕል ሣልባት፤ ክበባት›› ይላል ሕዝ.፬፥፩)፡፡
በጥንት ዘመን ሰዎች የመጽሐፍ ቅዱስን ታሪክ በዋሻ ውስጥ በሥዕል እያስደገፉ ያስተምሩ ነበር፡፡ ከዚህም ባሻገር ለእምነታቸው ሲሉ ለተጋደሉ እና መሥዕዋትነትን ለከፈሉ ቅዱሳን መታሰቢያ ይሆን ዘንድ ሥዕል በመሣል ታሪካቸውን አስቀምጠዋል፡፡ ክርስቲያኖች ይህንን እያደረጉ ለዘመናት ከቆዩ በኋላ በስምንተኛው መቶ ክፍለ ዘመን መጀመሪያ አካባቢ በሮማውያን ክርስቲያኖች እና በቢዛንታይን ክርስቲያኖች ዘንድ አለመግባባት ተፈጠረ፡፡ በዚህም ዘመን ይኖሩ የነበሩ ክርስቲያኖች ቅዱሳት ሥዕላትን ምክንያት በማድረግ በሁለት ጽንፍ ተከፈሉ፡፡ የመጀመሪያዎቹ ኢኮኖላትሪያ ሲባሉ እነዚህም ክርስቲያኖች ቅዱሳት ሥዕላትን ከመጠን በላይ አብዝተው ከመውደዳቸው የተነሳ እንደ አማልክት የሚቆጥሩ ናቸው፡፡ ሁለተኛዎቹ ደግሞ ኢኮኖማኺያ ሲባሉ እነዚህም ክርስቲያኖች ቅዱሳት ሥዕላት ከነጭራሹ አያስፈልጉም በማለት ከአምልኮት ሥፍራ መወገድ አለባቸው የሚል አመለካከት የያዙ ነበሩ፡፡ ይህም አለመግባባት ለረጅም ዘመናት ከቀጠለ በኋላ በ፯፻፹፯ እ.ኤ.አ ሁለተኛው የኒቅያ ጉባኤ ተደርጎ ለቅዱሳት ሥዕላት አክብሮት እና ስግደት እንደሚገባ ተወሰነ፡፡ በዚህም ጉባኤ መሠረት ቅዱሳት ሥዕላት በቤተክርስቲያን ውስጥ የእግዚአብሔር ክብሩ መገለጫ ሁነው የሚያገለግሉ የቅድስት ሥላሴ፤ የጌታችን የመድኃኒታችን የኢየሱስ ክርስቶስ፤ የእመቤታችን ቅድስት ድንግል ማርያም፤ የቅዱሳን መላእክት፤ የነቢያትና ሐዋርያት የጻድቃንና ሰማዕታት ሥዕላት ናቸው፡፡
፪. ቅዱሳን ሥዕላት ለምን ያስፈልጋሉ?
።
፩ ለሥርዓተ አምልኮ ያስፈልጋሉ
ቅዱሳት ሥዕላት ሰውንና እግዚአብሔርን የሚያገናኙ መንፈሳዊ ሀብቶች ናቸው። በሥዕል ፊት ቆሞ መጸለይ፡ ወይንም መስገድ ሥዕሉን አምላክ ማድረግ አይደለም። ነገር ግን የሥዕሉን ባለቤት በሥዕሉ ፊት ሆኖ በመማጸን በረከቱን ለማግኘት የሚፈጸም ሥርዓት ነው። ሥዕሉ ለባለቤቱ መታሰቢያ ነው። “የጻድቅ መታሰቢያ ለበረከት ነው ተብሎ እንደተጻፈ” ምሳ. ፲፡፯ የሥዕሉን ባለቤት አቅርቦ ያሳየናል። ገድሉን፣ ተአምራቱንና ቃል ኪዳኑን ያስታውሰናል። በመንፈስም ድልድይ ሆኖ ከሥዕሉ ባለቤት ያገናኘናል።
ሙሴና አሮን ወደ ደብተራ ኦሪት ገብተው በታቦቱና ሥዕለ ኪሩብ ፊት እየሰገዱ ከእግዚአብሔር ትዕዛዝ ይቀበሉ ነበር ዘኁ. ፲፮፡፵፭
፪ ለትምህርት ያስፈልጋሉ
ቅዱሳት ሥዕላት ሲሣሉ የሥዕሉን ባለቤት ዐቢይ ገድልና ተአምራት በሚያጎላ መልኩ ነው። ስለሆነም ማንኛውም ምእመን የሥዕሉን ባለቤት መንፈሳዊ ተጋድሎ በቀላሉ እንዲረዳ ያደርገዋል። ለምሳሌ የጻድቁ አባታችን የአቡነ ተክለ ሃይማኖት ሥዕል ሲሣል ለ22 ዓመታት 8 ጦሮችን ከግራ ከቀኝ ከፊት ከኋላ አስተክለው ሲጸልዩ አንድ እግራቸው በቁመት ብዛት መቆረጡን እንዲሁም ስለ ቅድስናቸው ከተሰጣቸው ስድስት የብርሃን ክንፎች ጋር ተደርጎ ይሣላል። ክህነታቸውን ለመግለጽም የእርፍ መስቀልና ጽና ይዘው ይሣላል። የሥዕሉ ባለቤት እንዲታወቅም በሥዕሉ ላይ አጭር የጽሑፍ መግለጫ ይቀመጣል። ”ዘከመ ጸለየ አቡነ ተክለሃይማኖት” እንዲል። በዚህ ሥዕል ምእመናን የጻድቁን ተጋድሎ ይማሩበታል፤ አርአያም ያደርጉታል።
እንግዲህ ቅዱሳት ሥዕላት ይህን መንፈሳዊ አገልግሎት የሚሰጡን ከሆነ በጥንቃቄ በመያዝ መገልገል እንደሚገባና ዘወትር በጸሎት ሰዓት ከፊት ለፊታችን በማስቀመጥ ልንጸልይ እንደሚገባ ቅድስት ቤተ ክርስቲያን መልዕክቷን ታስተላልፋለች
፫. በመጀመሪያ ጊዜ የጌታን ሥዕል የሳለው ቅዱስ አባት ማነው?
ወንጌላዊው ዮሐንስ ነው።
ጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ በተሰቀለበት ዘመን የነበረው የሮማ ቄሣር ጢባርዮስ ቄሣር ይባላል፡፡ የቄሣሩ ልጅም ታማሚ ነበር፡፡ ቄሣሩም የጌታን የማዳን ሥራ እየሰማና እነ ጲላጦስንም የጻፉለትን ደብዳቤ እየተመለከተ “ከዚያ ደግ ሰው መቃብር ወስዶ ልጄን ማን ባሳለመልኝ?” እያለ ይመኝ ነበር፡፡ በመጨረሻም ልጁን ወስደው በጌታ መቃብር ላይ ሲያኖሩት ከሕመሙ ስለተፈወሰለት ፍቅሩን ለመግለጥ የጌታን ሥዕል የሚሥልለት ሰው ያፈላልግ ጀመር፡፡ከዚያ በኋላም ዮሐንስ ወልደ ነጐድጓድ ተገኘና ልክ በዕለተ ዓርብ እንዳየው አድርጐ ሥሎ ሰጠው፡፡
፬. እኔና ቤቴ እግዚአብሔርን እናመልካለን ይኸ የመጽሐፍ ቅዱስ ጥቅስ በየትኛው የመጽሐፍ ክፍል ይገኛል?" እግዚአብሔርንም ማምለክ ክፉ መስሎ ቢታያችሁ፥ አባቶቻችሁ በወንዝ ማዶ ሳሉ ያመለኩአቸውን አማልክት ወይም በምድራቸው ያላችሁባቸውን የአሞራውያንን አማልክት ታመልኩ እንደ ሆነ፥ የምታመልኩትን ዛሬ ምረጡ። እኔና ቤቴ ግን እግዚአብሔርን እናመልካለን። "
(መጽሐፈ ኢያሱ ወልደ ነዌ 24:15)
እውነት ወይም ሐሰት
፭. በመጀመሪያ የእመቤታችንን ሥዕል የሳለው አባ ሕርያቆስ ነው።መልሱ ሐሰት ነው ምክንያቱም አባ ሕርያቆስ የእመቤታችንን ቅዳሴ ሲደርስ የእመቤታችን ቅድስት ድንግል ማርያም ሥዕል የሣለው ደግሞ ከ ሰባ ሁለቱ አርድዕት ውስጥ የሆነው ቅዱስ ሉቃስ ነው
።
የተሣተፉ
1. መቅደሰ ማርያም 4/5
2. Ruth 4/5
3. G eysus 4/5
4. መልካሙ 5/5
5. ልብ ያለህ አስተውል 4/5
6. liya 5/5
7. ሰሎሞን 5/5
8. ልጅ ቢኒ 5/5
9. የድንግል ልጅ 4/5
10. Tig 4/5
ለተሣተፉት ቃለ ሕይወትን ያሰማልን መንግሥተ ሰማያትን ያውርስልን
ለእስትንፋስከ
ጸጋ መንፈስ ቅዱስ ለተመላ እስትንፋስህ ሰላምታ የሚገባህ ንዑድ ክቡር ሊቅ ምሉዐ ሞገስ ቅዱስ ያሬድ ሆይ በመቅደሰ ጽዮን በጣዕመ ቃልህ በዘመርህ ጊዜ ለፍጡራን ኹሉ መድኃኒት የሚኾን ጣዕመ ማኅሌትን አስገኘህ።
✍ መልክዓ ቅዱስ ያሬድ
መልካም ቀን
ማኅደረ ጥያቄ
፩. ቅዱሳን ሥዕላት በቤተክርስቲያን የተጀመረው መቼ ነው?
፪. ቅዱሳን ሥዕላት ለምን ያስፈልጋሉ?
፫. በመጀመሪያ ጊዜ የጌታን ሥዕል የሳለው ቅዱስ አባት ማነው
፬. እኔና ቤቴ እግዚአብሔርን እናመልካለን ይኸ የመጽሐፍ ቅዱስ ጥቅስ በየትኛው የመጽሐፍ ክፍል ይገኛል
እውነት ወይም ሐሰት
፭. በመጀመሪያ የእመቤታችንን ሥዕል የሳለው አባ ሕርያቆስ ነው
መልሱን እስከ ነገ 6:00 ሰዓት በ @Asitmeherobot አድርሱን
መልሱን ከላይ ባለው ሊንክ ብቻ ይላኩ
#መልካም_እድል
ሁለተኛ ዙር ማኅደረ ጥያቄ
በኤፍራታ ምድር
በኤፍራታ ምድር በቤተልሄም/2/
ጌታ ተወለደ ከድንግል ማርያም/2/
ብራናዊው ኮከብ ከሰማይ ዝቅ አለ/2/
ፍጥረትም ዘመረ ሀሌ ሉያ እያለ/2/
አዝ............
መንጋውን በሌሊት ሲጠብቁ እረኞች
ከሰማይም ሰሙ ታላቅ የምስራች
በመላእክት ግርማ ምድር ስታበራ
የሚያስጨንቅ ነበር እጅግ የሚያስፈራ
አዝ..........
ድንገትም የሰማይ ሰራዊት ተገልጠው
ባንድነት ዘመሩ ከኖሎት ጋር ሆነው
ክብር ለእግዚአብሔር በአርያም ብለው
ሰላምን በምድር በጎ ፍቃድ ለሰው
አዝ..........
ቤተልሄም ሄደው ጌታን ተሳለሙ
ከእናቱ ጋራ ሆነው በግርግም አገኙት
የመላእክትን ዜማ እረኞች አወሩ
በልዩ ምስጋና አምላክን ሲያከብሩ
አዝ.........
በመዝሙር ቢሆን ፍስሐ ደስታ
በዳዊት ከተማ ተወለደ ጌታ
ህፃን ከእናቱ ጋር በግርግም ፈለጉት
እርሱ ነው ለሰዎች የድነት ምልክት
መዝሙር (ጥናት)
👇👇👇👇👇
@meazahaymanot
ማኅደረ ጥያቄ
፩.መልአኩ ዮሐንስን ለምን እንዳይሰግድለት ጠየቀው?
ራእይ ፲፱ ÷ ፲ “ልሰግድለትም በእግሩ ፊት ተደፋሁ እርሱም እንዳታደርገው ተጠንቀቅ ከአንተ ጋር የኢየሱስም ምስክር ካላቸው ከወንድሞችህ ጋር አብሬ ባሪያ ነኝ ለእግዚአብሔር ስገድ፤ የኢየሱስ ምስክር የትንቢት መንፈስ ነውና አለኝ”።
ራእይ ፳፪ ÷ ፰ - ፱ “ይህንም ያየሁትና የሰማሁት እኔ ዮሐንስ ነኝ፡፡ በሰማሁትና ባየሁትም ጊዜ ይህን ባሳየኝ በመልአኩ እግር ፊት እሰግድ ዘንድ ተደፋሁ፡፡ እርሱም እንዳታደርገው ተጠንቀቅ ከአንተ ጋር ከወንድሞችህም ከነቢያት ጋር የዚህንም መጽሐፍ ቃል ከሚጠብቁ ጋር አብሬ ባሪያ ነኝ፤ ለእግዚአብሔር ስገድ አለኝ፡፡”
፪.መልአኩ ከሌሎች ለይቶ ዮሐንስን ለምን እንዳይሰግድ ጠየቀው?ሌሎች ቅዱሳን ለመላእክት ሲሰግዱ ያልተከለከሉት ዮሐንስ ግን እንዳይሰግድ የተጠየቀው ስለ
ክብሩ
ነው፡፡
ከክብሮቹም መካከል
1. ዮሐንስ አልሞተም።
2. አላገባም።
3. እንደ መላእክት ዓለመ መላእክትን ዐይቷል፡፡
4. ክህነት ያለው በመሆኑ።
ዮሐንስ ከሌሎቹ ለመላእክት ከሰገዱት ቅዱሳን ይልቅ የከበረና ከመላእክት ጋር የተካከለ እንዲያውም የበለጠ ነው፡፡ ስለዚህ የምትተካከለኝ ወይም የምትበልጠኝ ሆነህ ለኔ መስገድ አይገባህም ሲል ስለትሕትና
መልአኩ ዮሐንስን እንዳታደርገው ተጠንቀቅ አለው፡፡
፫. ምን ብለን ወይም እያልን እንስገድ?
ስንሰግድ ‹‹ኪሪያላይሶን ወይም አቤቱ ይቅር በለኝ፣›› እያልን ነው የምንሰግደው፡፡
እንዲህ እያልን በመስገዳችን ኃጢአታችንን እያስታወስን ምህረት ከፈጣሪ
እየጠየቅን ነው የምንሰግደው፡፡ ጀማሪዎች እና ደካሞች የምንሰግደው 41
ወይም 64 እና 105 ነው፡፡ 41 የምሰግደው ምሳሌነቱ 12ቱን እግዚኦ መሃረነ
ክርስቶ፣12ቱን በእንተ ማርያም መሃረነ ክርስቶስ፣12ቱን ኪሪያላይሶን፣ 5ቱ
ደግሞ የጌታ የአምስቱ ችንካሮች ምሳሌ ናቸው፡፡ አንድ ላይ ስንደምራው 41
ይመጣሉ፡፡ 64 የመስገዳችን ምሳሌ የእናቱን የድንግል ማርያምን መላ ዘመንዋን
ለእኛ ብላ የደረሰባትን ረሃብ፣ጥም እና እንግልት፣ስደት በማሰብ የምንሰግደው
ነው፡፡ 105 የምንሰግደው የጌታን 41 የእመቤታችንን 64 በማድረግ አንድ ላይ
የምንሰግደው ምሳሌ ነው፡፡ ግን ጠቅለል አድርገን ‹‹ኪሪያላይሶን ወይም አቤቱ
ይቅር በለኝ›› እያልን መስገድ፡፡
፬. በልተን መስገድ እንችላለን?
የንስሐ ስግደት ሲሆን ነው ሳንበላ እንደጾምን የምንሰግደው፡፡ ምክንያቱም የንስሐ ስግደት የቅጣት ስግደት ስለሆነ በልተን፣አቅም አጠራቅመን፣ኃይል ሰብስበን ሳይሆን በጾም ደክመን መስገዱ ይመረጣል፡፡ ከአጋንንት ጋር ለመዋጋት በምናደርገው ስግደት ውስጥ ለምሳሌ ማታ ያስለመድነውን ጸሎት ካደረስን በኃላ መስገድ እንችላለን፡፡
፭.ስግደትን እንዴት እንለማመድመጀመሪያ ልምድን ስንመለከት ልምድ የምንለው በእለት ተእለት ተግባራችን ውስጥ የምናገኘው እድገት ነው፡፡ ስለዚህ ዕለት ተዕለት ቀስ እያልን የምንለምደው ወይም የምንሰግደው ለቅድስና ደረጃ ያደርሰናል። በቀን ፵፩ ስለ ጌታችን መከራ ስንል እያደግንም ስንመጣ ፷፬ ደግሞ ሰለ ድንግል ማርያም እያልን ፻፭ እያልን.....፼እንደ አቡነ ገብረመንፈስ ቅዱስ በመንፈሳዊ ቀስ በቀስ እናድጋለን።
የተሣተፉ
1 መቅደሰ ማርያም 5/5
2. ሰሎሞን 5/5
3. Tig 5/5
4. ልብ ያለህ አስተውል 4/5
5. liya 5/5
6. Lij beni 5/5
7. Selam 5/5
ለተሣተፉት ቃለ ሕይወትን ያሰማልን መንግሥተ ሰማያት ያውርሰልን
ሰላም ለዝክረ ስምከ አምሳለ ፀቃውዕ ጣዕመ ወሞገስ ጥቀ ለገብረ መንፈስ ቅዱስ በከመ ስሙ እስትንፋሰ ክርስቶስ መምህረ አበ ቅዱሳን ኩሎሙ ስብሐታተ ዘመልክእከ ወበመሌሊቱ ወዓቅሙ ሰሌዳ ረሲ ጠቢባን ይቅልሙ
መልክዓ እስትንፋሰ ክርስቶስ
እንኳን ለጻዲቁ አባታችን ለአቡነ እስትንፋሰ ክርስቶስ የልደት በዓል በሰላም አደረሳችሁ
ማኅደረ ጥያቄ
፩.መልአኩ ዮሐንስን ለምን እንዳይሰግድለት ጠየቀው?
፪.መልአኩ ከሌሎች ለይቶ ዮሐንስን ለምን እንዳይሰግድ ጠየቀው?
፫. ምን ብለን ወይም እያልን እንስገድ
፬. በልተን መስገድ እንችላለን?
፭.ስግደትን እንዴት እንለማመድ
መልሱን እስከ ነገ 6:00 ሰዓት @Asitmeherobot አድርሱን
መልሱን በሊንኩ ብቻ ይላኩ
#መልካም_እድል
ሁለተኛ ዙር ማኅደረ ጥያቄ