meazahaymanot | Unsorted

Telegram-канал meazahaymanot - መዓዛ ሃይማኖት በጎ አድራጎትና ጉዞ ማህበር

4288

"ውድስት አንቲ በአፈ ነቢያት ወስብሕት በሐዋርያት አክሊለ በረከቱ ለያዕቆብ ወትምክህተ ቤቱ ለእስራኤል፡፡" "በነቢያት በሐዋርያት አንደበት የተመሰገንሽ የያዕቆብ የበረከቱ ዘውድ የእስራኤል ወገን መመኪያ አንቺ ነሽ"                  መጽሐፈ ሰዓታት የፌስቡክ ፔጃችን www.fb.me/meazhaimanot ይቀላቀሉን

Subscribe to a channel

መዓዛ ሃይማኖት በጎ አድራጎትና ጉዞ ማህበር

#ምክር_ለወዳጅ

ወዳጄ ሆይ !

"አገልጋይ ሆነህ ስትታዘዝ አትከፋ። ክርስቶስ የመጣው በባሪያ መልክ ነውና። እርሱ በጌትነት አርአያ ቢመጣ አይደንቅም ነበር። የዘላለም ጌታ በባሪያ መልክ መምጣቱ ግን ድንቅ ነው። አገልጋይነትን ክርስቶስ ሥጋ ለብሶ የባረከው ተግባር ነውና ደስ ይበልህ። አንተ የሰው አገር ተሰድደህ ተመችቶህ እንኳ ከፍቶህ ከሆነ ክርስቶስ ግን ወደማይመቸው ወደ ሲና በረሃ እንደ ተሰደደ አስታውስ። አንተ ለምነህ እንጀራ ስታገኝ በእንባ ትጎርሰዋለህ ፣ ክርስቶስ ግን በመስቀል ላይ ተጠማሁ ብሎ ሆምጣጤ እንደ ሰጡት አስብና ትሑት ሁን። አንተ በራስህ መቃብር ስትቀበር ክርስቶስ ግን በተውሶ መቃብር እንደ ተቀበረ እወቅ።"


መልካም ቀን

@meazahaymanot

Читать полностью…

መዓዛ ሃይማኖት በጎ አድራጎትና ጉዞ ማህበር

"ምክረ አበው ዘቅዱስ ዮሐንስአፈወርቅ"

ተወዳጆች ሆይ እስኪ ልጠይቃችሁ አንድ ሰው የተጣራ ወርቅ ልሰጣችሁ እመጣለሁና የሆነ ቦታ ላይ ጠብቁኝ ቢላችሁ ምን ታደርጋላችሁ? ወደዚያ ቦታ ለመሔድ አስፈላጊ ነው የምትሉትን ኹሉ አታደርጉምን? ቀኑን ሙሉም ቢሆን ቁጭ ብላችሁ አትጠብቁምን?

እግዚአብሔር እሰጣችኋለሁ ያላችሁ ግን አንዲት ወይም ዐሥር ወይም ሃያ ወይም መቶ ወይም አንድ ሺህ ቅንጣት ወርቅ አይደለም፤ ወይም ምድርን ኹሉ አይደለም፡፡ ከዚህ ኹሉ የምትበልጠው መንግሥተ ሰማያት እንጂ፡፡ ከዚህ የሚበልጥ ስጦታ ታዲያ ምን አለ? ይህንን ስጦታ ለማግኘት የማይደክሙ ሰዎችስ እንደምን ያሉ ምስኪናን ናቸው?


መልካም ቀን

Читать полностью…

መዓዛ ሃይማኖት በጎ አድራጎትና ጉዞ ማህበር

https://docs.google.com/forms/d/1LnRCOLLvC80rbdC-GjYgyEBVnYcUYJBcdFoBKu5ho7Q/edit

የማኅበሩ አባል መሆን የሚፈልግ ይኸን ፎርም ይሙላ

Читать полностью…

መዓዛ ሃይማኖት በጎ አድራጎትና ጉዞ ማህበር

እግዚኦ ሰላመከ ሃባ ለሃገር ጽድቀከኒ ለቤተክርስቲያን አግርር ጸራ ታህተ ለአገሪትነ ኢትዮጵያ

✞አምላክ ሆይ የኢትዮጵያን✞

አምላክ ሆይ የኢትዮጵያን ልመናዋን ስማ
እጆቿን ዘርግታ ስትማጸን ቆማ
በደም ስላስጌጧት በደም ስላጸኗት
ስለ ቅዱሳኗ በረከትን ስጣት

ረሃብ ጉስቁልና ፊቷን አጥቁሮታል
የልጇቿ እንግልት እረፍት ነስቷታል
ስለ ድንግል ብለህ ስለ አዛኝቱ
የአስራት ልጇቿ መልካም ይመልከቱ

እኔ እበለጥ እኔ እሻል እየተባባሉ
የአንድ አባት መሪዎች ጦር ይማዘዛሉ
ዙፋንህ በሆነች በታቦተ ጽዮን
ከእግሮቿ ስር ይጣል መለያየት ተንኮል

በህዝቦቿ ልብ ውስጥ ጠላት እሾህ ዘርቷል
ወንድም ወንድሙ ላይ እጆቹን አንስቷል
በግሸን ተራራ ስላለው መስቀልህ
ከጥፋት ታደጋት ጥልን አስወግደህ

በዙሪያዋ ከበው የሚጠሏት ሁሉ
መውደቋን መጥፋቷን ይጠባበቃሉ
ስለ ቅዱስ ጊዮርጊስ ስለ ጠባቂዋ
የተፈራ ይሁን ዙሪያ ዳር ድንበሯ

መሃረነ አብ ሃሌ ሉያ
ተሰሃለነ ወልድ ሃሌ ሉያ
መንፈስቅዱስ መሐሪ ተዘከረነ በሣህልከ

መዝሙር
የቦሌ ኆኅተ ብርሃን
ቅድስት ማርያም ሰ/ት/ቤት

"ኢትዮጵያ እጆቿን ወደ
እግዚአብሔር ትዘረጋለች።"
መዝ ፷፯፥፴፩
╭══•|❀:✧๑♡๑✧❀|: ══╮
@meazahaymanot
╰══•ೋ•✧๑♡๑✧• ══╯

Читать полностью…

መዓዛ ሃይማኖት በጎ አድራጎትና ጉዞ ማህበር

ስንክሳር ዘወርሃ ግንቦት ሃያ ስምንት(፳፰)
/channel/meazahaymanot

Читать полностью…

መዓዛ ሃይማኖት በጎ አድራጎትና ጉዞ ማህበር

#የሚጠብቀኝ_አይተኛም

የሚጠብቀኝ አይተኛም/2/
አያንቀላፋም

ቤት ባይኖረኝም እደጅ ባድርም
ቀን እና ለሊት ከኔ አይርቅም
ድምጸ አራዊት የለሊት ግርማ
ወደኔ አይቀርብም ድምጽህ ሲሰማ

አዝ____

መሰናክልን ለእግሮቼ አይሰጥም
ይሰውረኛል በቀኙ ሰላም
ፀሐይም በቀን አይተኩሰኝም
የአጋንንትም ሀይል አያስፈራኝም

አዝ____

ነፍሴን ጠበቃት ከጠላት ወጥመድ
ጌታዬ መራኝ በጽድቅ መንገድ
መውጣት መግባቴን እየጠበቀ
ለዚህ አበቃኝ እርሱ ባወቀ

አዝ____

የሰማዩን ጠል እታገሳለው
ሰው ከጨከነ ምን እሆናለው
ለሊት በድብቅ ለሚጎበኙኝ
ለጻድቃኑ ክብር አምላክ ይስጥልኝ

አዝ____

እንቅልፌን ባርኮ ለሰጠኝ የጌታ
በአለም ሀሳብ ሳልንገላታ
የእለት ምግቤንም ላልነሳኝ ፍጹም
ምስጋና ላቅርብ እስከ ዘለዓለም

መዝሙር
ሊቀ-መዘምራን ይልማ ኃይሉ

"እነሆ፥ እስራኤልን የሚጠብቅ
አይተኛም አያንቀላፋምም።"
👉 መዝሙረ ዳዊት 121:4

"ክርስቲያን ወገኖቼ እኛን የሚጠብቅ
አይተኛም እና አትፍሩ"

@meazahaymanot

Читать полностью…

መዓዛ ሃይማኖት በጎ አድራጎትና ጉዞ ማህበር

ፃድቁ ሐብተማርያም

ጻድቁ ሐብተማርያም
መጥተናል እኛ ልጆችህ
አድነን አውጣን ከፈተና
አልብሰን የብርሀንን ፋና

ፃድቁ - ሰባት አክሊላትን
ፃድቁ - በራሱ የደፋ
ፃድቁ - በጾም በፀሎት ነው
ፃድቁ - ሰይጣንን ያጠፋ
ፃድቁ - ፅድቅን የታጠቀው
ፃድቁ - የእግዚአብሔር አገልጋይ
ፃድቁ - ፃድቁ አባታችን
አቡነ - የኢትዮጵያ ሲሣይ

አዝ—-
ፃድቁ - የዮስቲናስ ጸጋ
ፃድቁ - የፍሬ ብሩክ
ፃድቁ - ለኛ ለልጆችህ
ፃድቁ - መመኪያ የሆንክ
ፃድቁ - በምልጃህ አድለን
ፃድቁ - ፍቅርና ሰላም
ፃድቁ - ፃድቁ አባታችን
አቡነ - ሐብተ ማርያም.

አዝ—-
ፃድቁ - ከሱራፌል ጋራ
ፃድቁ - ለማቅረብ ምስጋና
ፃድቁ - ፅድቅን ተጎናጽፎ
ፃድቁ - ሀብተ ንፅሕና
ፃድቁ - በደብረ ሊባኖስ
ፃድቁ - ይሰበይ ላይ ያለው
ፃድቁ - ፃድቁ አባታችን
አቡነ - ሐብተማርያም ነው

አዝ—-
ፃድቁ - ብርሃንን ለብሶ
ፃድቁ - የእሳት መስቀል ይዞ
ፃድቁ - በጾም ጸሎት ጸንቶ
ፃድቁ - ንግስናውን ትቶ
ፃድቁ - በደብረ ሊባኖስ
ፃድቁ - ይሰበይ ላይ ያለው
ፃድቁ - ፃድቁ አባታችን
አቡነ - ሐብተማርያም ነው

አዝ—-
ፃድቁ - ባለመቶ ፍሬ
ፃድቁ - ሀብተማርያም
ፃድቁ - ቤታችንን ሞላው
ፃድቁ - ፍቅርና ሰላም
ፃድቁ - ሚስጥርን ተካፈልክ
ፃድቁ - ከጽርሐአርያም
ፃድቁ - ፃድቁ አባታችን
አቡነ - ሐብተማርያም

@meazahaymanot

Читать полностью…

መዓዛ ሃይማኖት በጎ አድራጎትና ጉዞ ማህበር

ምልክቴ ነሽ
ዘማሪ ዲያቆን አቤል መክብብ ✧┈┈•◦●◈◎❖◎◈●◦•┈┈✧

ምልክቴ ነሽ ድንግል ለህይወቴ
በአንቺ ተፈታሁ ከእስራቴ
ቀና ብያለሁ አሁን ልጅሽ
ፀጋሽ ጎብኝቶኝ ቃልኪዳንሽ
አዝ
ተስፋ ያረኩት አልተበተነም
እንባዬ መሬት ከቶ አልወደቀም
ለበጎ ሆነ ማልቀስ ማንባቴ
ሰላም ሰፈነ በእልፍኝ በቤቴ

#ቅኔ ነጠኩኝ የአባ ጊዮርጊስን
ማህሌት ቆምኩኝ የሕርያቆስን
የያሬድ ዜማ ሞላ በልቤ
የለም ወጀቡ ቀርባኝ መርከቤ
አዝ
ወገቤን ታጠኩ ጭንቀቴን ጥየ
ዛሬስ በደስታ ይፍሰስ እንባየ
የሀዘን ልብሴን ድንግል ቀይራ
የደበዘዘው ህይወቴ በራ

#አራራይ ዜማ ዛሬ ተማርኩኝ
ፍቅሯ አሸነፈኝ እጄን ሰጠሁኝ
ቅኔ በልቤ ተመላለሰ
የድንግል ክብር ውስጤ ነገሰ
አዝ
የዘረጋሁት እጄ ተሞላ
ማርያም ሆናልኝ ጥላ ከለላ
የውስጤ ፀሎት ዛሬ ሌላ ነው
የድንግል ክብር ምልጃው ቀየረው

#ዛሬ ጎጆየ አንጸባረቀች
ያማረ ስንፔር ዕንቁ መሰለች
ቀንዴ ከፍ ከፍ አለልኝና
ሰዋሁ ለድንግል ይህን ምስጋና

ለኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ልጆች👇
•➢ ሼር // SHARE

Читать полностью…

መዓዛ ሃይማኖት በጎ አድራጎትና ጉዞ ማህበር

+++ክርስቶስ ተንሥአ እሙታን
በዓቢይ ኃይል ወሥልጣን
አሠሮ ለሰይጣን
አግዐዞ ለአዳም
ሰላም
እምይዕዜሰ
ኮነ
ፍስሐ ወሰላም+++++

ስንክሳር ዘወርሃ ግንቦት ሃያ አምስት(፳፭)
/channel/meazahaymanot

Читать полностью…

መዓዛ ሃይማኖት በጎ አድራጎትና ጉዞ ማህበር

#ሰላሜ_በአንተ_ነው

ሰላሜ ባንተ ነው የኔ ጌታ
እረፍቴ ባንተ ነው የኔ ጌታ
አልከለከል ምስጋና
አልከለከል ውዳሴ ለአንተ ውለታ

ጨለማዬ በአንተ በራልኝ
ከሰው ትከሻ ወረድኩኝ
የምመራበት ዱላዬ
በአንተ ተጥሏል ጌታዬ
አሁን በግላጭ አያለሁ
ሙሉ ሰው ባንተ ሆኛለሁ

አዝ= = = = =

የመውገሪያው ድንጋይ ቀረልኝ
ጠላቴ በፊቴ አፈረልኝ
በፊትህ አቆምከኝ በጸጋ
ገዝተኸኛልና በዋጋ
ለውለታህማ ምን እላለሁ
ተመስገን ብዬ አልፈዋለሁ

አዝ= = = = =

ሰላላውን እጄን አቅንተሃል
ሽባነቴንም ተርትረሃል
ደካማነቴ ተወገደ
ያክፉ መንፈስ ተሰደደ
ታውጆልኛል ነፃነቴ
አመልክሃለሁ በሕይወቴ

አዝ = = = = =

የአይኔ ላይ ቅርፊት ወለቀ
ሸክሜ ከላዬ ወደቀ
በደማሰቆ ብርሃን መራኸኝ
የራስህ ምርጥ ዕቃ አረግከኝ
ያከንቱ ድካሜ አለፈ
ልቤ ለፍቅርህ ተሸነፈ

👏🌾💐👀ሁላችንም በሥላሴ ስልጣን አምነን በአንድነት እንዘምር እስትንፋስ ያለው ሁሉ እግዚአብሔርን ያመስግን መዝ 150:6📚

Читать полностью…

መዓዛ ሃይማኖት በጎ አድራጎትና ጉዞ ማህበር

https://docs.google.com/forms/d/1LnRCOLLvC80rbdC-GjYgyEBVnYcUYJBcdFoBKu5ho7Q/edit

የማኅበሩ አባል መሆን የሚፈልግ ይኸን ፎርም ይሙላ

Читать полностью…

መዓዛ ሃይማኖት በጎ አድራጎትና ጉዞ ማህበር

ምክረ አበው ዘቅዱስ ሳዊሮስ ዘአንጾኪያ

የምወዳችሁ ወንድሞቼ ሆይ ስለ አእምሮአችን ሕጸጽ ጸልዩልን፤ጌታ በፍጹም ቸርነቱ እስከ መጨረሻ እስትንፋስ ፍጻሜ ድረስ በቀናች ሃይማኖት ያጽናን ዘንድ ተስፋችን ይህ ብቻ ነው፤ለአብ ለወልድ ለመንፈስ ቅዱስ ለዘለዓለሙ በእውነት ክብር ምስጋና ይገባቸዋል  አሜን
    
መልካም ቀን

Читать полностью…

መዓዛ ሃይማኖት በጎ አድራጎትና ጉዞ ማህበር

እንኳን ለእናታችንና ለእመቤታችን ለቅድስት ድንግል ማርያም በዓል በሰላምና በጤና አደረሰን አደረሰን 🙏

ግንቦት ፳፩ ቀን- ደብረ ምጥማቅ

Читать полностью…

መዓዛ ሃይማኖት በጎ አድራጎትና ጉዞ ማህበር

🔔ታላቅ የንግስ ጉዞ #ግንቦት 21 ወደ🔔

                   #ጻድቃኔ_ማርያም

ግንቦት 21ቀን በታላቅ ድምቀት የሚከበረውን የእመቤታችን የቅድስት ድንግል ማርያምን በደብረ ምጥማቅ የተገለጠችበትን በዓለ ንግስ ለማክበር እና ከረጅም አመታት የግንባታ ቆይታ በኋላ በምትመረቀው

       ✝የምዕመናን ተስፋ
       ✝የድውያን ፈውስ
       ✝ለተቸገሩ ሁሉ ረዳት
       ✝የዘርዓያዕቆብ እመቤት ወደሆነች እናታችን
ጻድቃኔ ማርያም የበዓለ ንግሱ እና የሕንጻ ምርቃቱ በዓል ተካፋይ እንሁን።

    በእለቱም ቅዱስ ፓትሪያርኩን ጨምሮ በርካታ አበው ብጹአን ሊቃነ ጳጳሳት  ጥሪ የተደረገላቸው እንዶች ይገኛሉ እና ሁላችሁም ተጋብዛችኋል።

🎪 መዓዛ ሃይማኖት መንፈሳዊ ጉዞ ማኅበር  በ21 የደርሶ መልስ ጉዞ አዘጋጅቷል
              

                💵 ደርሶ መልስ 700ብር

    ➛ ከአዲስ አበባ 👉 ፒያሳ ጊዮርጊስ
                             👉 መገናኛ
                          
                         
   ☎️ # 0989680703 ደውለው ይመዝገቡ

   💒 መዓዛ ሃይማኖትመንፈሳዊ ጉዞ ማኅበር ⛪️

Читать полностью…

መዓዛ ሃይማኖት በጎ አድራጎትና ጉዞ ማህበር

🔔ታላቅ የንግስ ጉዞ #ግንቦት 21 ወደ🔔

                   #ጻድቃኔ_ማርያም

ግንቦት 21ቀን በታላቅ ድምቀት የሚከበረውን የእመቤታችን የቅድስት ድንግል ማርያምን በደብረ ምጥማቅ የተገለጠችበትን በዓለ ንግስ ለማክበር እና ከረጅም አመታት የግንባታ ቆይታ በኋላ በምትመረቀው

       ✝የምዕመናን ተስፋ
       ✝የድውያን ፈውስ
       ✝ለተቸገሩ ሁሉ ረዳት
       ✝የዘርዓያዕቆብ እመቤት ወደሆነች እናታችን
ጻድቃኔ ማርያም የበዓለ ንግሱ እና የሕንጻ ምርቃቱ በዓል ተካፋይ እንሁን።

    በእለቱም ቅዱስ ፓትሪያርኩን ጨምሮ በርካታ አበው ብጹአን ሊቃነ ጳጳሳት  ጥሪ የተደረገላቸው እንዶች ይገኛሉ እና ሁላችሁም ተጋብዛችኋል።

🎪 መዓዛ ሃይማኖት መንፈሳዊ ጉዞ ማኅበር  በ21 የደርሶ መልስ ጉዞ አዘጋጅቷል
              

                💵 ደርሶ መልስ 700ብር

    ➛ ከአዲስ አበባ 👉 ፒያሳ ጊዮርጊስ
                             👉 መገናኛ
                          
                         
   ☎️ # 0989680703 ደውለው ይመዝገቡ

   💒 መዓዛ ሃይማኖትመንፈሳዊ ጉዞ ማኅበር ⛪️

Читать полностью…

መዓዛ ሃይማኖት በጎ አድራጎትና ጉዞ ማህበር

ስንክሳር ዘወርሃ ሰኔ ሁለት(፪)
@meazahaymanot

Читать полностью…

መዓዛ ሃይማኖት በጎ አድራጎትና ጉዞ ማህበር

ስንክሳር ዘወርሃ ሰኔ አንድ(፩)
/channel/meazahaymanot

Читать полностью…

መዓዛ ሃይማኖት በጎ አድራጎትና ጉዞ ማህበር

ስንክሳር ዘወርሃ ግንቦት ሠላሳ(፴)
/channel/meazahaymanot

Читать полностью…

መዓዛ ሃይማኖት በጎ አድራጎትና ጉዞ ማህበር

ስንክሳር ዘወርሃ ግንቦት ሃያ ዘጠኝ(፳፱)
/channel/meazahaymanot

Читать полностью…

መዓዛ ሃይማኖት በጎ አድራጎትና ጉዞ ማህበር

ከአሁን ጀምሮ እንደተለመደው ለቻናላችን ያላችሁን ሀሳብ አስተያየት ማቅረብ ትችላላችሁ። ቢኖሩ፣ ቢስተካከሉ የምትሏቸው ጉዳዮች ላይ አተኩራችሁ ስማችሁንና ከየት ሀገር እንደሆናችሁ እየገለጻችሁ በድምጽ ሆነ በጽሑፍ ላኩልን። ቤተሰቦቻችን የት የት እንዳሉም እንድናውቅና እንድንተዋወቅ ይረዳናል     ላይ @misiwani_Bot እንጠብቃችኋለን

ሐሳብ አስተያየታቸውን ጻፉልን

Читать полностью…

መዓዛ ሃይማኖት በጎ አድራጎትና ጉዞ ማህበር

+++ክርስቶስ ተንሥአ እሙታን
በዓቢይ ኃይል ወሥልጣን
አሠሮ ለሰይጣን
አግዐዞ ለአዳም
ሰላም
እምይዕዜሰ
ኮነ
ፍስሐ ወሰላም+++++

ስንክሳር ዘወርሃ ግንቦት ሃያ ሰባት(፳፯)
/channel/meazahaymanot

Читать полностью…

መዓዛ ሃይማኖት በጎ አድራጎትና ጉዞ ማህበር

+++ክርስቶስ ተንሥአ እሙታን
በዓቢይ ኃይል ወሥልጣን
አሠሮ ለሰይጣን
አግዐዞ ለአዳም
ሰላም
እምይዕዜሰ
ኮነ
ፍስሐ ወሰላም+++++

ስንክሳር ዘወርሃ ግንቦት ሃያ ስድስት(፳፮)
/channel/meazahaymanot

Читать полностью…

መዓዛ ሃይማኖት በጎ አድራጎትና ጉዞ ማህበር

ምክረ አበው ዘብፁዕ አቡነ ጎርጎርዮስ

"ልጆቻችሁን ይዛችሁ ወደ ቤተክርስቲያን ኑ! ብቻችሁን አትምጡ፡፡ ብቻችሁን ከመጣችሁ ወደ ሌላ ይሔዳሉ እናንተ እዚህ መጥታችሁ የምትሰሩትን አያውቅም ፡፡ ወዴት እንደሔዳችሁ አያውቅም፡፡ ወራሾቻችሁ አይሆንም ፡፡ ስለዚህም ወደ ቤተክርስቲያን ስትመጡ ልጆቻችሁን ይዛችሁ ኑ፡፡ አሳዩአቸው ሥዕሉን ይሳሙ ቅዳሴ ጠበል ይጠጡ በእምነት አሻሹአቸው መስቀል እንድስሙ አስተማሯቸው ዕጣኑን ያሽትቱ ሥጋ ወደሙን ይቀበሉ ቃጭሉን ይስሙ ደውል ሲደውል ይስሙ ቄሳቸው ማን እንደሆነ ቤተክርስቲያናቸው ምን እንደሆነች በውስጧ ምን ምን እንደሚሰራ ያጥኑ ይማሩ ወደ ሰንበቴው እጃችሁን ይዘው ይከተሉ ወደ ማህበር ስትሔዱም  ይዛችኋቸው ሂዱ ቆሎውን ዳቦውን ተሸክመው ወደ ሰንበቴው ይምጡ ይማሩ እነርሱም ነገ ይሄን እንዲወርሱ የነገ ባለአደራዎች መሆናቸውን እንዲያውቁ ።"

            መልካም ቀን

Читать полностью…

መዓዛ ሃይማኖት በጎ አድራጎትና ጉዞ ማህበር

✥•••••●◉ ✞ ◉●•••••✥
✍️"የሚሰማኝ ግን በእርጋታ ይቀመጣል ከመከራም ሥጋት ያርፋል"📖ምሳ 1፥33☦📚
        
✥•••••●◉ ✞ ◉●•••••✥
📗ስንክሳር ዘወርኃ ግንቦት ፳፬/24/

Читать полностью…

መዓዛ ሃይማኖት በጎ አድራጎትና ጉዞ ማህበር

ስንክሳር ዘወርሃ ግንቦት ሃያ ሦስት(፳፫)
+++ክርስቶስ ተንሥአ እሙታን
በዓቢይ ኃይል ወሥልጣን
አሠሮ ለሰይጣን
አግዐዞ ለአዳም
ሰላም
እምይዕዜሰ
ኮነ
ፍስሐ ወሰላም+++++
/channel/meazahaymanot

Читать полностью…

መዓዛ ሃይማኖት በጎ አድራጎትና ጉዞ ማህበር

🔴"ዑራኤል" ዘማሪት ሲስተር ሕይወት ተፈሪ [ቸር ሆይ ቁጥር ፭ ]urael

Читать полностью…

መዓዛ ሃይማኖት በጎ አድራጎትና ጉዞ ማህበር

ስንክሳር ዘወርሃ ግንቦት ሃያ ሁለት(፳፪)
+++ክርስቶስ ተንሥአ እሙታን
በዓቢይ ኃይል ወሥልጣን
አሠሮ ለሰይጣን
አግዐዞ ለአዳም
ሰላም
እምይዕዜሰ
ኮነ
ፍስሐ ወሰላም+++++
/channel/meazahaymanot

Читать полностью…

መዓዛ ሃይማኖት በጎ አድራጎትና ጉዞ ማህበር

🍀🍀🍀🍀🍀🍀🍀🍀🍀🍀🍀🍀🍀🍀
ሥርዓተ ማኅሌት ዘግንቦት ማርያም (ደብረ ምጥማቅ)
🌼🌼🌼🌼🌼🌼🌼🌼🌼🌼🌼🌼🌼🌼☘
የማንኛውም ወርኃ በዓልና ክብረ በዓል ሥርዓተ ማኅሌት መጀመሪያ "ሥርዓተ ነግሥ"
ስምዓኒ እግዚኦ ጸሎትየ፡ ሃሌ ሉያ ሃሌ ሉያ፡ ወይብጻሕ ቅድሜከ ገዓርየ፡ ሃሌ ሉያ ሃሌ ሉያ፡ ወኢትሚጥ ገፀከ እምኔየ፡ በዕለተ ምንዳቤየ አጽምእ ዕዝነከ ኃቤየ፡ ሃሌ ሉያ ሃሌ ሉያ፡ አመ ዕለተ እጼውአከ ፍጡነ ስምዓኒ፡ ሃሌ ሉያ ሃሌ ሉያ፡ ለዓለም ወለዓለመ ዓለም፡ ሃሌ ሉያ ዘውእቱ ብሂል፡ ንወድሶ ለዘሃሎ እግዚአብሔር ልዑል፡ ስቡሕ ወውዱስ ዘሣረረ ኲሎ ዓለመ፡ በአሐቲ ቃል።

መልክዐ ሥላሴ
ሰላም ለኲልያቲክሙ እለ ዕሩያን በአካል: ዓለመክሙ ሥላሴ አመ ሐወጸ በሣሕል: እምኔክሙ አሐዱ እግዚአብሔር ቃል: ተፈጸመ ተስፋ አበው በማርያም ድንግል: ወበቀራንዮ ተተክለ መድኃኒት መስቀል።

ዚቅ
ወሀለወት አሐቲ ድንግል ብርህት ከመ ፀሐይ: እንተ ታስተርኢ እምአርዕስተ አድባር: ወትትመረጎዝ በትእምርተ መስቀል።

ነግሥ
ሰላም ለልሣንከ መዝሙረ ቅዳሴ ዘነበልባል: ወለድምፀ ቃልከ ሐዋዝ ቀርነ መንግሥቱ ለቃል: ሞገሰ ክብሩ ሚካኤል ለተላፊኖስ ባዕል: አልቦ ዘይትማሰለከ በልማደ ምሕረት ወሣሕል: እንበለ ባሕቲታ እኅትከ ማርያም_ድንግል።

ዚቅ
መላእክት በልሳነ እሳት ይሴብሑኪ: መላእክት በአክናፈ ብርሃን ይኬልሉኪ: ማርያም እምነ ወእሙ ለእግዚእነ: መላእክት በቀለመ ወርቅ ይጽሕፉ ውዳሴኪ: እስከ ዳግም ምጽአቱ ለበኲርኪ።

ዘጣዕሙ
ሰላም ለዝክረ ስምኪ ዘመንክር ጣዕሙ: ለወልድኪ አምሳለ ደሙ: መሠረተ ህይወት ማርያም ወጥንተ መድኃኒት ዘእምቀዲሙ: ኪያኪ ሠናይተ ዘፈጠረ ለቤዛ ዓለሙ: እግዚአብሔር ይትባረክ ወይትአኮት ስሙ።

ዚቅ
እግዚአብሔር ውእቱ ብርሃንኪ ለዓለም: ወመሠረትኪ ለትውልደ ትውልድ: ኢየኀልቅ ብዝኃ ሰላምኪ: ወነገሥት ይትቀነዩ ለኪ: ያመጽኡ አምኃኪ እምርኁቅ ብሔር።
@meazahaymanot
@meazahaymanot
መልክአ ማርያም
ሰላም ሰላም ለዝክረ ስምኪ ሐዋዝ: እምነ ከልበኔ ወቊስጥ ወእምነ ሰንበልት ምዑዝ: ማርያም ድንግል ለባሲተ ዓቢይ ትዕዛዝ: ይስቅየኒ ለለጽባሑ ወይነ ፍቅርኪ አዚዝ: ከመ ይሰቅዮ ውኂዝ ለሠናይ አርዝ።

ዚቅ
በአልባሰ ወርቅ ዑጽፍት ወኁብርት: እኅትየ መርዓት ርግብየ ሠናይት: ርቱዕ አፍቅሮትኪ እምወይን: መዓዛ ዕፍረትኪ እምኲሉ አፈው: እትፌሣሕ ወእትኃሠይ ብኪ: ናፍቅር አጥባትኪ እምወይን: ኲለንታኪ ሠናይት እንተ እምኀቤየ: አልብኪ ነውር ወኢምንትኒ ላዕሌኪ: ፃዒ እምሊባኖስ እኅትየ መርዓት።

ወረብ
"በአልባሰ ወርቅ"/፪/ ዑጽፍት ወኁብርት/፪/
እኅትየ መርዓት ርግብየ ሠናይት እኅትየ/፪/

መልክዐ ማርያም
ሰላም ለገጽኪ ዘጥቀ ይልሂ: እምሥነ ከዋክብት ወወርኅ ወእምሥነ ፀሐይ መብርሒ: ማርያም ድንግል ፍንዋትየ ሠርሂ: በመዓልት ወበሌሊት ኢይርከበኒ ጸናሂ: መሥገርተ አበሳ ዘይጠፍር ወግብ ይድሂ።

ዚቅ
ከበበ ገፃ ከመ ወርኅ: ወአዕይንቲሃ ከመ ኮከበ ጽባሕ: ወቆማ ከመ በቀልት ለማርያም ድንግል: ወላህያ ከመ ጽጌረዳ: ከመ ፍህም ቀይሕ ከናፍሪሃ: እስመ ወለደት ለነ መና ኅቡዓ: ዘውእቱ ህብስተ ህይወት: መፍትሔ ሕማማት።

ወረብ
ከበበ ገፃ ከመ ወርኅ ወአዕይንቲሃ ከመ ኮከበ ጽባሕ/፪/
ወቆማ ከመ በቀልት ለማርያም ድንግል/፪/

መልክዐ ማርያም
ሰላም ለጒርኤኪ ሠናይ እምወይን: በከመ ይቤ ሰሎሞን: ማርያም_ድንግል ለባሲተ ዓቢይ ብርሃን: ክድንኒ ገርዜነ ጸጋ ኢያዕጽበኒ ዕርቃን: ዘኢአነምዎ ጠቢባን በኪን።

ዚቅ
በከመ ይቤ ሰሎሞን በእንተ ማርያም: ንዑ ንትፈጋዕ ወኢይኅልፈነ ጽጌ ደመና መስቀል ዘዮም አብርሃ በስነ ማርያም: ጴጥሮስኒ ሰመያ እመ ብርሃን: ጳውሎስኒ ይቤላ ደብተራ ግዕዛን: አጽገዩ ሕዝበ ወመሐይምናን: በቤተ መርዓ ተመልዑ ክርስቲያን።

ወረብ
በከመ ይቤ "ሰሎሞን"/፪/ በእንተ ማርያም/፪/
ንዑ ንትፈጋዕ ወኢይኅልፈነ "ጽጌ"/፪/ ደመና አብርሃ በስነ ማርያም/፪/

መልክዐ ማርያም
ሰላም ለመልክዕኪ ዘተሠርገወ አሚረ: ዘያበርህ ወትረ: ፍቅርትየ አንቲ እንተ ታበድሪ ፍቅረ: አርእይኒ ገፀ ዚአኪ ማርያም ምዕረ: ዘኢይሰምዖ ካልዕ እንግርኪ ነገረ።

ዚቅ
ትበርህ እምኮከበ ጽባሕ: ወታስተርኢ እምአርእስተ አድባር: አዳም ወሠናይት ጽዕዱት: ወብርህት ከመ ፀሐይ።
@meazahaymanot
@meazahaymanot
ወረብ
ትበርህ እምኮከበ ጽባሕ ወታስተርኢ እምአርዕስተ አድባር/፪/
አዳም ወሠናይት ጽዕዱት ወብርህት ከመ ፀሐይ ብርህት/፪/

መልክዐ ማርያም
በዝንቱ ቃለ ማኅሌት ወበዝንቱ ይባቤ: ለዘይስዕለኪ ብእሲ ጊዜ ረከቦ ምንዳቤ: ብጽሒ ፍጡነ ትሰጠዊዮ ዘይቤ: ማርያም ዕንቊየ ክርስቲሎቤ ወምዕዝተ ምግባር እምከርቤ: ዘጸገየ ማሕጸንኪ አፈወ ነባቤ።
@meazahaymanot
@meazahaymanot
ዚቅ
ኢይትአጸው አናቅጽኪ: ክቡራት ዕንቊ መሠረትኪ ሠናይት ሰላማዊት እንተ ናፈቅራ በጽድቅ: መዓዛ አፉሃ ከመ ኮል።
@meazahaymanot
@meazahaymanot
ወረብ
ኢይትአጸው አናቅጽኪ ክቡራት ዕንቊ መሠረትኪ/፪/
ሠናይት ሰላማዊት "እንተ ናፈቅራ"/፪/ በጽድቅ/፪/

ማኅሌተ ጽጌ
ኦ ሰላመ ሰጣዊት እንተ ትሔውጺ እምርኁቅ: ወትትረአዪ ለኲሉ በደብረ ምጥማቅ: ተፈሥሒ ድንግል ዘገዳመ ጽጌ ማዕነቅ: እስመ ተሰምዓ በምድርነ ቃለ ተአምርኪ ጽድቅ: ለአድኅኖ ኃጥዕ ዘይበቊዕ እምብሩር ወወርቅ።
@meazahaymanot
@meazahaymanot
ዚቅ
እንተ ታስተርኢ እምአርእስተ አድባር ርኁቅ: ጻድቃን ኪያሃ አብደሩ እምወርቅ: ሀገረ ክርስቶስ ሐዳስ ንድቅ: ወበውስቴታ የሐጽር ጽድቅ።
@meazahaymanot
@meazahaymanot
ምልጣን
ዓይ ይእቲ ዛቲ እንተ ታስተርኢ እምርኁቅ ከመ ማኅቶት: ብርህት ከመ ፀሐይ: ሙሴኒ ርእያ ሀገር ቅድስት: ዕዝራኒ ተናገራ: ዳዊት ዘመራ።
@meazahaymanot
@meazahaymanot
አመላለስ
ዕዝራኒ ተናገራ/፪/
ተናገራ ዳዊት ዘመራ ተናገራ ዘመራ ዳዊት/፪/
@meazahaymanot
@meazahaymanot
እስመ ለዓለም
ዓይ ይእቲ ዛቲ እንተ ትሔውጽ ከመ ጎህ: አዳም ከመ ወርኅ: ሠናይት ከመ ሥርዓት: ብርህት ከመ ፀሐይ: እምሊባኖስ ትወጽእ መርዓት: እምነ ጽዮን አግዓዚት: ታቦተ ፍሥሃ ምስሌሃ: ወአሕዛብኒ ቅድመ ገፃ: ወትረ ተሃሉ ምስሌነ።



      @meazahaymanot
    # Join & share #

Читать полностью…

መዓዛ ሃይማኖት በጎ አድራጎትና ጉዞ ማህበር

ምክረ አበው ዘአባ እንጦንስ

"መንፈሳዊ ብቃት፥ የማይደረስበት እሩቅ፣ ወይም ከሰው ልጅ ችሎታ በላይ ነው፥ ብለን ማሰብ የለብንም። ሰዎች ባሕር አቋርጠው የሌላ ሀገር ፍልስፍና ሊማሩ ይሄዳሉ። የእግዚአብሔር ከተማ ግን በልባቸው ውስጥ ነው። እግዚአብሔር የሚጠብቅብን መልካም ምግባርም እዚያው ልባችን ላይ ነው ያለው። የሚጠበቅብን መሻታችንን ከእግዚአብሔር መሻት ጋር ማስማማት (አንድ ማድረግ) ብቻ ነው።"



መልካም ቀን

Читать полностью…

መዓዛ ሃይማኖት በጎ አድራጎትና ጉዞ ማህበር

ምክረ አበው ዘአባ እንጦንስ

"መንፈሳዊ ብቃት፥ የማይደረስበት እሩቅ፣ ወይም ከሰው ልጅ ችሎታ በላይ ነው፥ ብለን ማሰብ የለብንም። ሰዎች ባሕር አቋርጠው የሌላ ሀገር ፍልስፍና ሊማሩ ይሄዳሉ። የእግዚአብሔር ከተማ ግን በልባቸው ውስጥ ነው። እግዚአብሔር የሚጠብቅብን መልካም ምግባርም እዚያው ልባችን ላይ ነው ያለው። የሚጠበቅብን መሻታችንን ከእግዚአብሔር መሻት ጋር ማስማማት (አንድ ማድረግ) ብቻ ነው።"



መልካም ቀን

Читать полностью…
Subscribe to a channel