ማኅደረ ጥያቄ
አእማደ ምሥጢር
1. አዕማደ ምስጢራት ምን ምን ናቸው?
2. የአዕማደ ምስጢራት መሠረት ምንድን ነው?
3. “ነአምን በአሃዱ አምላክ እግዚአብሔር" ሲል ምን ማለት ነው
4. አዕማደ ምስጢርን ማወቅ ለምን ይጠቅማል?
መልሱን እስከ ማታ 3:00 ሰዓት በ @Asitmeherobot አድርሱን
ከበጎ ነገር ጋር ተባበሩ
ማኅደረ ጥያቄ
አእማደ ምሥጢር
1. አዕማደ ምስጢራት ምን ምን ናቸው?
2. የአዕማደ ምስጢራት መሠረት ምንድን ነው?
3. “ነአምን በአሃዱ አምላክ እግዚአብሔር" ሲል ምን ማለት ነው
4. አዕማደ ምስጢርን ማወቅ ለምን ይጠቅማል?
መልሱን እስከ ማታ 3:00 ሰዓት በ @Asitmeherobot አድርሱን
ከበጎ ነገር ጋር ተባበሩ
Watch "MK TV || ቀጥታ ሥርጭት ከሚሊኒየም አዳራሽ || በጦርነት ለተጎዳው ለሰሜን ወሎ ሀገረ ስብከትን የገቢ ማሰባሰቢያ መርሐ ግብር - ሰኔ 25 /2015 ዓ.ም." on YouTube
https://www.youtube.com/live/pkjwwiKUf_k?feature=share
ማህበረ መዓዛ ሀይማኖት ሰኔ 21 በሚያደርገው ዝክር ላይ አንድ እናት 68 እሚጠጉ የአዕምሮ ህሙማን እና አረጋውያንን በሌላቸው አቅም እየረዱ ይገኛሉ ማህበረ መአዛ ሀይማኖት ሰኔ 21 በዕመቤታችን ስም በሚያደርገው ዝክር ላይ መሳተፍ ይቻላል እንጀራ ዳቦ ምስር ወይም በገንዘብ መርዳት ይቻላል
አቅመ ደካሞችን በእመቤታችን ስም በመዘከር የበረከቱ ተካፋዮች እንሁን ።
☎️0989680703
1000536032928
Filimon gebremichael
††† እንኳን ለጻድቅ ሊቀ ጳጳሳት አባ ድምያኖስ ዓመታዊ የዕረፍት በዓል በሰላም
. አደረሳችሁ፣ አደረሰን። †††
††† በስመ አብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ አሐዱ አምላክ አሜን! †††
😇 ††† አባ ድምያኖስ †††
😇 ††† አባ ድምያኖስ ተወልደው ያደጉት ግብጽ ውስጥ ነው:: ቤተሰቦቻቸው ክርስቲያኖች በመሆናቸው ገና በልጅነት ዕድሜአቸው ቅዱሳት መጻሕፍትንና በጐ ምግባራትን ተምረዋል:: ዕድሜአቸው ወደ ወጣትነቱ ሲጠጋ ሥርዓተ መነኮሳትን ለማጥናት ወደ ገዳመ አባ ዮሐንስ ሔዱ:: በዘመኑ ማንኛውም ሰው ተገቢውን ፈተና ሳያልፍ እንዲመነኩስ አይፈቀድለትም ነበር::
❤አንድ ሰው ሊመነኩስ ካሰበ በትክክል መናኝ መሆኑ ቢያንስ ለሦስት ቢበዛ ደግሞ ለአሥራ ሁለት ዓመታት እንዲፈተን ቅድስት ቤተ ክርስቲያን ታዝዛለች:: ይኸውም "ሥርዓተ አመክሮ" ይባላል:: ከአሥራ ሁለት ዓመታት በላይ መቆየት ከፈለገ ግን ይፈቀድለታል::
❤በዚህም መሠረት አባ ድምያኖስ ለአሥራ ሰባት ዓመታት በአጭር ታጥቀው ገዳሙን አገልግለዋል:: ገዳሙም ይገባሃል በሚል ዲቁና እንዲሾሙ አድርጓል:: ከዚህ በኋላ ከአባቶች ተባርከው: ገዳሙንም ተሰናብተው ወጡ:: ነገር ግን የወጡት ወደ ዓለም ሳይሆን ራቅ ወዳለ ገዳም ነው::
❤የረድዕነት ዘመናቸውን ጨርሰዋልና አዲስ በሔዱበት ገዳም ወደ መደበኛው ገድል ተሸጋገሩ:: ያም ማለት በጾም: በጸሎት: በስግደት: በትሕርምት: በትሕትናና በፍቅር ሙሉ ጊዜአቸውን ማሳለፍ ጀመሩ:: በእንዲሕ ያለ ግብርም ዘመናት አለፉ::
የወቅቱ የግብጽ ፓትርያርክ አባ ጴጥሮስ በእረኝነት ሥራ የሚያግዛቸው ሰው እንዲፈለግላቸው በጠየቁት መሠረት ትምሕርትም: ጽሕፈትም: በጐ ምግባራትም የተሟላለት ሰው እንደ አባ ድምያኖስ አልተገኘምና ያለፈቃዳቸው ወደ እስክንድርያ ተወስደው የፓትርያርኩ ረዳት ሆነው ተሾሙ:: በረዳትነት በቆዩበት ጊዜ በወንጌል አገልግሎትና በመንኖ ጥሪት ሕዝቡንና ሊቀ ጳጳሳቱን አስደስተዋል::
😇 ልክ አባ ጴጥሮስ ሲያርፉ ሕዝቡና ሊቃውንቱ በአንድ ድምጽ አባ ድምያኖስን
. ለፓትርያርክነት መርጧቸዋል::
😇 ጻድቁ ሊቀ ጳጳሳት በዘመነ ፕትርክናቸው ከግል የቅድስና ሕይወታቸው ባለፈ
. እነዚህን ፈተናዎች በመወጣታቸው ይመሰገናሉ::
❤1.ሕዝቡ ከሃይማኖታቸው እንዳይወጡና በምግባር እንዳይዝሉ ተግተው አስተምረዋል::
❤2.በአካል ያልደረሱባቸውን በጦማር (በመልዕክት) አስተምረዋል::
❤3.በዘመናቸው የተነሱትን መናፍቃን ተከራክረው : የተመለሰውን ተቀብለው : እንቢ ያሉትን አውግዘዋል::
❤4.ከአንጾኪያ ፓትርያርክ የመጣውን የኑፋቄ ጦማር (መልዕክት) በይፋ
. ተቃውመው አውግዘዋል::
❤ ለአርባ ሦስት ዓመታት የእስክንድርያ ሊቀ ጳጳሳት ሆነው ያገለገሉት አባ ድምያኖስ ከብዙ ትጋት በኋላ በመልካም ሽምግልና በዚህች ቀን ዐርፈዋል:: ከግብጽ አበው ሊቃነ ጳጳሳት ዝርዝር ውስጥም አርባ አምስተኛ ሆነው ተመዝግበዋል::
😇††† ልመናቸው : ክብራቸው : ጸጋ ረድኤታቸው አይለየን::
††† ሰኔ 18 ቀን የሚከበሩ ዓመታዊ የቅዱሳን በዓላት
1.አባ ድምያኖስ ጻድቅ ሊቀ ጳጳሳት
2.ቅዱስ ኤስድሮስ ሰማዕት
††† ወርኀዊ በዓላት
1.ቅዱስ ፊልጶስ ሐዋርያ
2.አቡነ ኤዎስጣቴዎስ ሰባኬ ሃይማኖት (ረባን)
3.አቡነ አኖሬዎስ ዘደብረ ጽጋጋ
4.ማር ያዕቆብ ግብጻዊ
††† "ስለዚህ በገዛ ደሙ የዋጃትን የእግዚአብሔርን ቤተ ክርስቲያንን ትጠብቁአት ዘንድ መንፈስ ቅዱስ እናንተን ጳጳሳት አድርጎ ለሾመባት : ለመንጋው ሁሉና ለራሳችሁ ተጠንቀቁ:: ከሄድሁ በኋላ ለመንጋው የማይራሩ ጨካኞች ተኩላዎች እንዲገቡባችሁ እኔ አውቃለሁ:: ስለዚህ ሦስት ዓመት ሌሊትና ቀን በእንባ እያንዳንዳችሁን ከመገሰጽ እንዳላቋረጥሁ እያሰባችሁ ትጉ::" †††
(ሐዋ. ፳፥፳፰)
††† ወስብሐት ለእግዚአብሔር †††
እንደምን አመሻችሁ?
በአንዳንድ ነገሮች አለመመቻቸት ምክንያት ከይቅርታ ጋር እሑድ ጉዞ አይኖረንም።
እግዚአብሔር ቢፈቅድ እና ብንደርስ በሚቀጥለው ሳምንት ጉዞ ይኖረናል፣በተሳትፎ አትለዩን።
ማኅደረ ጥያቄ
መልስ
1.እግዚአብሔር የግዕዝ ቋንቋ ቃል ሲሆን ትርጓሜውም እግዚእ ማለት ገዢ ወይም ጌታ ሲሆን፤ ብሔር ማለት ደግሞ ስብሰባ /ብሄር ወይም አገር ማለት ነው። የተሟላ ትርጉም የብሔር ገዢ ከሁሉ በላይ የሆነ ዓለምን የፈጠረ ብቸኛ አለቃ ማለት ነው።
2. እምነትና ሃይማኖት: እምነት የሚለው ቃል መሠረታዊ ቃሉ ግዕዝ ሲሆን ትርጓሜውም ማመን ወይም መታመን ማለት ነው፡፡ ማመን ማለት ስለእግዚአብሔር የሰሙትንና የተረዱትን እንዲሁም የተቀበሉትን ትምህርት እውነት ነው ብሎ በልብ መቀበል ነው (ሮሜ 10፡17)፡፡ መታመን ደግሞ ያመኑትንና የተቀበሉትን እምነት በሰው ፊት ሳይፈሩና ሳያፍሩ መመስከር ነው::
ሃይማኖት ማለት ለዓለም ፈጣሪ አለው ብለው የሚያምኑት እምነት ነው፡፡ ለዓለም ፈጣሪ አለው ብለው የሚመሰክሩት ቃል ነው፡፡ ሃይማኖት ሰው ፈጣሪውን የሚያመልክበት፣ የእግዚአብሔር ልጅ የሚሆንበት፣ ጽድቅንም የሚሠራበት፣ የዘላለም ሕይወትን የሚያገኝበት መንገድ ነው፡፡ ሃይማኖትም አንዲት ናት፡፡ ኤፌ 4፡5
3. ዶግማና ቀኖና
ዶግማ ቃሉ የግሪክ ሲሆን ፍችውም የእምነት መሠረት ማለት ነው፡፡
ቀኖና የሚለው ቃልም የግሪክ ሲሆን ሥርዓት ማለት ነው::
4. ቤተክርስቲያን፡ እንደ ሊቃውንተ ቤተ ክርስቲያን አመሥጥሮ ቤተ ክርስቲያን ማለት እግዚአብሔር ግዕዛን ካላቸው ፍጥረታት ጋር ያለው ግንኙነት ነው፡፡ ይህም ሦስት አይነት ትርጉም አለው፡፡ ቤተክርስቲያን ማለት የክርስቲያኖች ኅብረት፡ የክርስቲያኖች አንድነት ነው (1ኛ ቆሮ 11፡28)፡፡ ቤተክርስቲያን ማለት የክርስቲያኖች መኖሪያ፡ የእግዚአብሔር ቤት ነው
5. ቅድስት ቤተክርስቲያን አምስቱን አዕማድ “የምስጢር ትምህርቶች” ትላቸዋለች፡፡ “ምሥጢር” የሚለው ቃል “አመሠጠረ” ከሚለው ግስ የተገኘ ቃል ሲሆን ስውር ፣ ድብቅ ፣ ሽሽግ ማለት ነው፡፡ ምሥጢር በሁለት ይከፈላል፡፡ እነርሱም የፈጣሪ ምሥጢር (ሊገለጥ የማይችል፤ ከ እስከ የሌለው ምሥጢር) እና የፍጡራን ምሥጢር (በጊዜ የሚገለጥ /የሚታወቅ/፤ የሰውና የመላእክት ምሥጢር) ናቸው፡፡ ሊቃውንቱም አምስቱ አዕማደ ምስጢራት ስለምን ምሥጢር እንደተባሉ ሲያብራሩ በዓይኔ ካላሣያችሁኝ በእጄ ካላሲዛችሁኝ ብሎ አላምንም አልማርም ይሉ ዘንድ አይገባም በቃል ተምሮ በልቡና ተመራምሮ አዎን ብሎ የሚማሯቸው ስለሆኑ ምሥጢር ተባሉ በማለት ገልጸዋል፡፡(ሃይ. አበው ዘአትናትዮስ 14÷ 39 ሃይ. አበው ዘኤራቅሊስ
የተሣተፉ
1. ቤተልሔም 5/5
2. መዓዛ 4/5
3. አምላክየ ነፅረኒ 4/5
4. 25613 4/5
ለተሳተፉት ቃለ ሕይወትን ያሰማልን
ምክረ አበው ዘቅዱስ ዮሐንስ አፈወርቅ
✍..."ችግር ለራሳችን እንድንጸልይ ያነቃቃናል፤ ፍቅር ደግሞ ለሌሎች ሰዎች እንድንጸልይ ያስገድደናል"....✍
ጾመ ድኅነት ያድርግልን
መልካም ቀን
ማኅደረ ጥያቄ
አእማደ ምሥጢር
1. አዕማደ ምስጢራት ምን ምን ናቸው?
2. የአዕማደ ምስጢራት መሠረት ምንድን ነው?
3. “ነአምን በአሃዱ አምላክ እግዚአብሔር" ሲል ምን ማለት ነው
4. አዕማደ ምስጢርን ማወቅ ለምን ይጠቅማል?
መልሱን እስከ ማታ 3:00 ሰዓት በ @Asitmeherobot አድርሱን
ከበጎ ነገር ጋር ተባበሩ
ማኅደረ ጥያቄ
አእማደ ምሥጢር
1. አዕማደ ምስጢራት ምን ምን ናቸው?
2. የአዕማደ ምስጢራት መሠረት ምንድን ነው?
3. “ነአምን በአሃዱ አምላክ እግዚአብሔር" ሲል ምን ማለት ነው
4. አዕማደ ምስጢርን ማወቅ ለምን ይጠቅማል?
መልሱን እስከ ማታ 3:00 ሰዓት በ @Asitmeherobot አድርሱን
ከበጎ ነገር ጋር ተባበሩ
ማኅደረ ጥያቄ
አእማደ ምሥጢር
1. አዕማደ ምስጢራት ምን ምን ናቸው?
2. የአዕማደ ምስጢራት መሠረት ምንድን ነው?
3. “ነአምን በአሃዱ አምላክ እግዚአብሔር" ሲል ምን ማለት ነው
4. አዕማደ ምስጢርን ማወቅ ለምን ይጠቅማል?
መልሱን እስከ ነገ ማታ 3:00 ሰዓት በ @Asitmeherobot አድርሱን
ከበጎ ነገር ጋር ተባበሩ
ምክረ አበው ዘቅዱስ ጎርጎርዮስ ዘእንዚናዙ
=> በሃይማኖት ጥንቃቄ እንጂ ምናለበት አይሰራም ።ጥንቃቄ ፍጻሜው ሕይወት ምናለበት መድረሻው ሞት ነው።
=> በእግዚአብሔር ሕያው ሆነህ እንድትኖር በእግዚአብሔር ፍቃድ ኑር።
=> የምላስ ቀስት የራቀውን አቅርበው ፣ የረቀቀውን አግዝፎ የማይመታው ነገር የለምና ለአንደበቴ ጠባቂ አኑር ብለህ ጸልይ።
መልካም ቀን
✝ በስመ አብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ አሐዱ አምላክ አሜን ✝
"ቤተክርስቲያን ሀኪም ቤት ናት "
ሊቁ አፈ በረከት ቅዱስ ዮሐንስ አፈወርቅ
🙏 እንኳን ለእመቤታችን ለቅድስት ድንግል ማርያም ዓመታዊ ቅዳሴ ቤት መታሰቢያ በዓል አደረሳችሁ አደረስን 🙏
👉 ሰኔ ፳፩(21) በዓለ እግዝእትነ ማርያም ወጢሞቴዎስ ወተዝካር ተአምር ዘቶማስ 👉
👉 ዘነግህ ምስባክ 👉
ወንሰግድ ውስተ መካን ኀበ ቆመ እግረ እግዚእነ
ተንሥአ እግዚኦ ውስተ ዕረፍትከ
አንተ ወታቦተ መቅደስከ
👉 ትርጉም 👉
እግሮቼ በሚቆሙበት ሥፍራ እንሰግዳለን
አቤቱ ወደ ዕረፍትህ ተነሥ
አንተና የመቅደስህ ታቦት
መዝ ፻፴፩-፯
131 7
👉 ወንጌል 👉
ሉቃ ም ፩ ቁ ፴፱-፶፯
1 39 57
✝ የቅዳሴ ምንባባት ✝
ኤፌ ም ፪ ቁ ፲፫-ፍ.ም
፩ ጴጥ ም ፪ ቁ ፬-፲፩
ግብ.ሐዋ ም ፩ ቁ ፲፪-፲፭
✝ ምስባክ ✝
ቀደስ ማኀደሮ ልዑል
እግዚአብሔር ውስተ ማዕከለ ኢትትሐወክ
ወይረድአ እግዚአብሔር ፍጽመ
🙏 ትርጉም 🙏
ልዑል ማደሪያው ቀደስ
እግዚአብሔር በመካከልዋ ነው አትናወጥም
እግዚብሔርም ፈጥኖ ይረዳታል
መዝ ፵፭-፬
45 4
✝ ወንጌል ✝
ማቴ ም ፲፮ ቁ ፲፫-፳
16 13 20
✝ ቅዳሴ ✝
ዘእግዚእነ
❖ አቤቱ ለአዕይንተ ልቡና ውስጣዊ ብርሃንን ስጥ እያስቡህና ላንተ እየተገዙ አንተን ለይተው ያመስግኑህ ዘንድ ዕድላቸው አንተ ብቻ ነህና ❖
ቅዳሴ እግዚእነ
ም ፩ ቁ ፶፬
1 54
✝ በዓለ ምህረት በዓለ ፀጋ በዓለ ሐሴት ያድርግል ፆሙ ለማበርከት ያብቃ ከቸሩ መድኃኔዓለም በቸርነቱ ይማረን ከእናታችን ከቅድስት ድንግል ማርያም ምልጃዋ ቃል ኪዳኗዋ ይጠብቅን ውዳሴ ማርያም ቅዳሴ ማርያም የሰኔ ጎልጎታ መዓዛ ቅዳሴ የተቀበለ የኛንም ፆም ፀሎት ስግደት በብሩህ ገጽ ይቀበልልን ✝
@meazahaymanot
ምክረ አበው ዘቅዱስ ኤፍሬም
ሕሊናህ ኃጢአትን ከማሰብ ይጡም፡ አእምሮህም ኃጢአትን ከማስታወስ ይከልከል፡፡ ክፉን ከመመኘት ሁሉ ጡም፡፡ ዐይኖችህ ከንቱ የሆኑ ነገሮችን ከመመልከት፣ ጆሮህም ከንቱ ከሆኑ ዘፈኖችና ከሐሜተኞች ሹክሹክታዎች ጠብቅ፡፡ አንደበትህ ከሐሜት፣ በሌላው ላይ ከመፍረድ ፣ከስድብ፣ ከውሸት፣ ከማታለል፣ ከሽንገላ ንግግሮች እንዲሁም ከማይጠቅሙና አጸያፊ ከሆኑ ቃላት ይጡሙ፡፡ እጆችህም ሰውን ከመግደልና የሌላውን ንብረት ከመዝረፍ ይጡሙ፡፡ እግሮችህም ኃጢአትን ለመፈጸም ከመሄድ ይጡሙ፡፡ ከክፉ ተመለስ መልካምንም ፈጽም፡፡
መልካም ቀን
ምክረ አበው ዘቅዱስ ሚናስ
‹‹ወርቅ በእሳት እንደሚፈተን ሁሉ የክርስቶስንም ፀጋና ክብር ሳይፈተኑ ማግኘት አይቻልም የዚህ ዓለም ፈተናና እሳት ቶሎ ያልፋል ይጠፋል ኃጢያተኞች የሚገቡበት የገሀነም እሳት ግን ለዘላለም እንደ ነደደ ይኖራል››
መልካም ቀን
የ፳፻ ፲ወ፭ ዓ/ም የስብከተ ወንጌል እና የሰበካ ጉባኤ ማደራጃ የጋራ የአገልግሎት ሥምሪት ሥልጠና ተከናወነ።
********
ሰኔ፲፬ቀን ፳፻ ፲ወ፭ዓ.ም
""""""""""""""""""""""""
አዲስአበባ -ኢትዮጵያ
******
የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተክርስቲያን መንበረ ፖትርያርክ ጠቅላይ ጽ/ቤት ስብከተ ወንጌልና ሐዋርያዊ ተልዕኮ መምሪያና የሰበካ ጉባኤ ማደራጃ መምሪያ በጋራ የሚያስተባብሩት በስብከተ ወንጌል ማስፋፋትና በሰበካ መንፈሳዊ ጉባኤ አደረጃጀት ዙሪያ በ፵፰ አህጉረ ስብከት ሥልጠና ለመሥጠት ዝግጅት መጠናቀቂ ተገለጸ።
ዛሬ ሰኔ ፲፬ቀን ፳፻ ፲ወ፭ ዓ/ም በመንበረ ፖትርያርክ ጠቅላይ ቤተክህነት ጽርሐ ተዋሕዶ የመሰብሰቢያ አዳራሽ በሥምሪቱ ተሳታፊ ለሆኑ ሊቃውንተ ቤተክርስቲያን በሁለቱም መምሪያዎች ስለተዘጋጀው የሥልጠና ሠነድ እና ዕቅበተ እምነትን አስመልክቶ የተዘጋጀው መርሐ ግብር በብፁዕ አቡነ ጴጥሮስ (ዶ/ር) የቅዱስ ሲኖዶስ ዋና ጸሐፊና የኒው ዮርክና አካባቢው ሀገረ ስብከት ሊቀጳጳስ እና በብፁዕ አቡነ ማርቆስ የስብከተ ወንጌልና ሐዋርያዊ ተልእኮ መምሪያ የበላይ ኃላፊ ሊቀ ጳጳስ ጸሎትና አባታዊ የመግቢያ መልእክት ተጀምሯል።
በየመምሪያዎቹ የተዘጋጁትን መርሐ ግብሮች አስመልክቶ ክቡር መልአከ ሰላም ቆሞስ አባ ቃለጽድቅ ሙሉጌታ (ዶ/ር) የስብከተ ወንጌልና ሐዋርያዊ ተልዕኮ መምሪያ ዋና ኃላፊ እና በክቡር ሊቀ ኅሩያን መሐሪ አስረስ የሰበካ ጉባኤ ማደራጃ መምሪያ ዋና ኃላፊ ገለጻ ተደርጓል።
ከዚህ ቀደም የሁለቱ መምሪያዎች የአገልግሎት ሥምሪቶቹን በተናጠል ሲያደርጉ የቆዩ ቢሆንም በዚህ ዓመት የተሻለ ውጤት ለማምጣት ሲባል በጋራ ለመሥራት ባደረጉት ስምምነት መነሻነት የጋራ ስምሪቱ ዕቅድ ተዘጋጅቷል ።
ሥምሪቱ የሚደረገው ከሰኔ ፲፭ -፳፭ ቀን ፳፻ ፲ ወ፭ ዓ.ም ሲሆን በእቅድ በተያዙ ፴፰ አህጉረ ስብከት ትምህርትና ሥልጠናውን የሚሰጡ ፸፯ አገልጋዮች በሁለቱም መምሪያዎች በጋራ ተመድበዋል።
ለተጨማሪ መረጃ
+ + +
1. ድረገጽ:- https://eotceth.org
2. ፌስ ቡክ ገጽ:- የ/ኢ/ኦ/ተ/ቤተክርስቲያን ሕዝብ ግንኙነት መምሪያ/Department of Public Relati፦
+251111262652 +251111262818
4.eotcprdepartment@gmail.com
5. ፖስታ፦ 1283 አዲስ አበባ
ፎቶግራፍ መ/ሰ አባ ኪሮስ ወልደአብ
ማኅደረ ጥያቄ
አእማደ ምሥጢር
1. እግዚአብሔር ማለት ምን ማለት ነው?
2. እምነትና ሃይማኖት ልዩነታቸውን አስረዱ
3. ትምህርት ሃይማኖት (የሃይማኖት ትምህርት) በስንት ይከፈላል?
4. ቤተክርስቲያን ማለት ምን ማለት ነው?
5. ለምን ምስጢራት ተባሉ?
መልሱን እስከ ማታ 3:00 ሰዓት በ @Astimeherobot አድርሱን
ከበጎ ነገር ጋር ተባበሩ