meazahaymanot | Unsorted

Telegram-канал meazahaymanot - መዓዛ ሃይማኖት በጎ አድራጎትና ጉዞ ማህበር

3925

"ውድስት አንቲ በአፈ ነቢያት ወስብሕት በሐዋርያት አክሊለ በረከቱ ለያዕቆብ ወትምክህተ ቤቱ ለእስራኤል፡፡" "በነቢያት በሐዋርያት አንደበት የተመሰገንሽ የያዕቆብ የበረከቱ ዘውድ የእስራኤል ወገን መመኪያ አንቺ ነሽ"                  መጽሐፈ ሰዓታት የፌስቡክ ፔጃችን www.fb.me/meazhaimanot ይቀላቀሉን

Subscribe to a channel

መዓዛ ሃይማኖት በጎ አድራጎትና ጉዞ ማህበር

ስንክሳር ዘወርሃ መስከረም ሃያ አምስት (፳፭) /channel/meazahaymanot

Читать полностью…

መዓዛ ሃይማኖት በጎ አድራጎትና ጉዞ ማህበር

♦️ተክለ ሃይማኖት ጻድቅ📍አዲስ ዝማሬ በቪዲዮ📍Zemari D/Besufekad Andargachew በተወዳጁ ዘማሪ ዲ/በሱፍቃድ አንዳርጋቸው📍

Читать полностью…

መዓዛ ሃይማኖት በጎ አድራጎትና ጉዞ ማህበር

ስንክሳር ዘወርሃ መስከረም ሃያ አራት(፳፬) /channel/meazahaymanot

Читать полностью…

መዓዛ ሃይማኖት በጎ አድራጎትና ጉዞ ማህበር

መልሱ: መ ልበ አምላክ ቅዱስ ዳዊት


ዳዊትም እጁን ወደ ኮረጆው አግብቶ አንድ ድንጋይ ወሰደ፥ ወነጨፈውም፥ ፍልስጥኤማዊውንም ግምባሩን መታ፤ ድንጋዩም በግምባሩ ተቀረቀረ፥ እርሱም በምድር ላይ በፊቱ ተደፋ።


መጽሐፈ ሳሙኤል ቀዳማዊ ፲፯÷፶፩


ለተሣተፋችሁ ሁሉ ቃለ ሕይወትን ያሰማልን መንግሥተ ሰማያትን ያውርስልን

Читать полностью…

መዓዛ ሃይማኖት በጎ አድራጎትና ጉዞ ማህበር

ሊቀ መላእክት ቅዱስ ዑራኤል

ዑራኤል የሚለው ስም “ዑር” እና “ኤል” ከሚሉ ሁለት ቃላት የተመሠረተ ነው። ዑራኤል ማለት ትርጉሙ “የብርሃን ጌታ”፣ ”የአምላክ ብርሃን” ማለት ነው። ቅዱስ ዑራኤል ከ7ቱ ሊቃነ መላእክት አንዱ ሲሆን ከፍጥረተ ዓለም ጀምሮ በመብረቅና በነጎድጓድ ላይ የተሾመ መልአክ ነው። በመሆኑም መባርቅት ለጥጋብና ለበረከት እንዲበርቁ ነጎድጓድም ለሰላም እንዲሆን
ያሰማራል። መ.ሄኖክ 6፥2 ምስጢረ ሰማይና እውቀትንም ሁሉ ለሄኖክ የገለጸለት የፀሐይን
የጨረቃን የከዋክብትንና የሰማይ ሰራዊትን ብርሃንን የሚመራ እርሱ መሆኑን ለሄኖክ ነግሮታል።

መ.ሄኖክ 28፥13 “ቅድስት ድንግል ማርያምን፣ ከልጇ ከአምላካችን ከኢየሱስ ክርስቶስ ጋር ወደ ግብጽ ስትሰደድ መንገድ የመራ፤ ክርስቶስ ለዓለም ቤዛ በተሰቀለ ጊዜ፣ ክቡር ደሙን በብርሃን ጽዋ ተቀብሎ፣ በብርሃነ መነሳንስ በዓለም ላይ የረጨ፤ እውቀት ለተሰዎረባቸው ለነቢዩ ዕዝራ ሱቱኤል ጽዋ ጥበብን ያጠጣ፤ ኢትዮጵያዊውን ሊቅ አባ ጊዮርጊስ ዘጋስጫ መርካታ ቅዱሳት መጻሕፍትን አንዲደርሱ ያገዘ፣ የረዳና የዕውቀት ጽዋን ያጠጣ መልአኩ ቅዱስ ዑራኤል ነው፡፡

የመልአኩ ዓመታዊ ክብረ በዓላት

የቅዱስ ዑራኤል ዓመታዊ ክብረ በዓላቱ የሚከበርባቸው ቀናት የሚከተሉት ናቸው፡፡

ጥር 22 በዓለ ሲመቱ፣
መጋቢት 27 የጌታ ደሙን ለዓለም የረጨበት፣
ሐምሌ 21 እና 22 ቅዳሴ ቤቱ የሚከበርበት።


በአምላኩ አማላጅነቱን ኑና ተማጸኑት። በጸሎቱ ለተማጸነ ከአምላኩ በረከትን ምህረትን የሚያሰጥ አዛኝ እርሩህ መልአክ ነው። አሁንም ይህ ዓለም በአማላጅነቱ አምኖ ጸበሉን ቢጠጣ ከክፉ በሽታ እንደ
ሚፈወሱ ቃለ ኪዳን ተሰጥቶታል፣

የቅዱስ ዑራኤል በረከት በሁላችንም ላይ ይደር!! አሜን


https://m.youtube.com/channel/UCKGh-U7U7pnvFUIEGXPOnNw

Читать полностью…

መዓዛ ሃይማኖት በጎ አድራጎትና ጉዞ ማህበር

ስንክሳር ዘወርሃ መስከረም ሃያ ሁለት(፳፪) /channel/meazahaymanot

Читать полностью…

መዓዛ ሃይማኖት በጎ አድራጎትና ጉዞ ማህበር

✞  ምልክቴ ነሽ  ✞

ምልክቴ ነሽ ድንግል ለህይወቴ
ባ'ንቺ ተፈታሁ ከእስራቴ
ቀና ብያለሁ አሁን ልጅሽ
ፀጋሽ ጎብኝቶኝ ቃል-ኪዳንሽ


ተስፋ ያ'ረኩት አልተበተነም
እንባየ መሬት ከቶ አልወደቀም
ለበጎ ሆነ ማልቀስ ማንባቴ
ሰላም ሰፈነ በልፍኝ በቤቴ

      ቅኔ ነጠኩኝ ያ'ባ ጊዮርጊስን
      ቆምኩኝ ቅዳሴ የህርያቆስን
      የያሬድ ዜማ ሞላ በልቤ
      የለም ወጀቡ ቀርባኝ መርከቤ
    
          አዝ.............

ወገቤን ታ'ጠኩ ጭንቀቴን ጥየ
ዛሬስ በደስታ ይፍሰስ እንባየ
የሀዘን ልብሴን ድንግል ቀይራ
የደበዘዘው ህይወቴ በራ

     አራራይ ዜማ ዛሬ ተማርኩኝ
     ፍቅሯ አሸነፈኝ እጄን ሰጠሁኝ
     ቅኔ በልቤ ተመላለሰ
     የድንግል ክብር ውስጤ ነገሰ

              አዝ...........

የዘረጋሁት እጄ ተሞላ
ማርያም ሆናልኝ ጥላ ከለላ
የውስጤ ፀሎት ዛሬ ሌላ ነው
የድንግል ክብር ምልጃው ቀየረው

      ዛሬ ጎጆየ አንፀባረቀች
     ያማረ ሰንፔር እንቁ መሰለች
     ቀንዴ ከፍ ከፍ አለልኝና
     ሰዋሁ ለድንግል ይህን ምስጋና

Читать полностью…

መዓዛ ሃይማኖት በጎ አድራጎትና ጉዞ ማህበር

ሥርዓተ ቀብሩ ተፈጽሟል።
በረከታቸው ይደርብን

Читать полностью…

መዓዛ ሃይማኖት በጎ አድራጎትና ጉዞ ማህበር

ስንክሳር ዘወርሃ መስከረም ሃያ(፳) /channel/meazahaymanot

Читать полностью…

መዓዛ ሃይማኖት በጎ አድራጎትና ጉዞ ማህበር

ስንክሳር ዘወርሃ መስከረም አሥራ ዘጠኝ(፲፱)
@meazahaymanot

Читать полностью…

መዓዛ ሃይማኖት በጎ አድራጎትና ጉዞ ማህበር

ብፁዕ አቡነ ሰላማ የታዕካ ነገሥት በዓታ ለማርያምና የመንበረ መንግሥት ቅዱስ ገብርኤል ቤተክርስቲያን የበላይ ጠባቂ ሊቀ ጳጳስ ሥርዓተ ቀብርን አስመልክቶ የቅዱስ ሲኖዶስ ጽ/ቤት መግለጫ ሰጠ።

+++++++++++++++++++++++++++++++++++++++!
ብፁዕ አቡነ ሰላማ የታዕካ ነገሥት በዓታ ለማርያምና የመንበረ መንግሥት ቅዱስ ገብርኤል ቤተክርስቲያን የበላይ ጠባቂ ሊቀ ጳጳስ ሥርዓተ ቀብር እሑድ መስከረም 20 ቀን 2016 ዓ.ም በመንበረ ጸባኦት ቅድስት ሥላሴ ካቴድራል ከቀኑ 6 ሰዓት ይፈጸማል ሲሉ የቅዱስ ሲኖዶስ ዋና ጸሐፊ ለለኢኦተቤ ቴቪ (EOTC TV) ገለጹ።
የቅዱስ ሲኖዶስ ዋና ጸሐፊ እና የኒውዮርክ እና አካባቢው ሀገረ ስብከት ሊቀ ጳጳስ ብፁዕ አቡነ ጴጥሮስ (ዶ/ር) እንደገለጹት የብፁዕ አቡነ ሰላማ የታዕካ ነገሥት በዓታ ለማርያምና የመንበረ መንግሥት ቅዱስ ገብርኤል ቤተክርስቲያን የበላይ ጠባቂ ሊቀ ጳጳስ ክቡር አስክሬን ነገ ቅዳሜ መስከረም 19 ቀን 2016 ዓ.ም ከቀኑ በ 9 ሰዓት ከሀሌሉያ ሆስፒታል ወደ መንበረ ፓትርያርክ ቅድስት ማርያም ገዳም የሚመጣ ሲሆን ለሊቀ ጳጳስ በሚመጥን ሥርዓተ ጸሎተ ፍትሐት ሲፈታ አድሮ በማኅሌትና በቅዳሴ ሥርዓተ ጸሎቱ የሚከናወን ይሆናል።
እሑድ መስከረም 20 ቀን 2016 ዓ.ም ከቅዳሴ በኃላ የብፁዕነታቸው ክቡር አስክሬን ወደ በመንበረ ጸባኦት ቅድስት ሥላሴ ካቴድራል የሚሄድ ሲሆን በዚያ አስፈላጊው መንፈሳዊ ሥርዓት ተከናውኖ ግብአተ መሬት እንደሚፈጸም የቅዱስ ሲኖዶስ ዋና ጸሐፊ ለለኢኦተቤ ቴቪ (EOTC TV) በሰጡት መግለጫ ገልጸዋል ዘመድ ወዳጆቻቸውና የመንፈስ ቅዱስ ልጆቻቸው በመርሐ ግብሩ መሠረት ተገኝተው አባታችንን እንዲሸኙ ጥሪ ቀርቧል።

ዘጋቢ መ/ር አቤል አሰፋ
ምንጭ፦ EOTC TV ኢኦተቤ ቴቪ
መስከረም 18 ቀን 2016 ዓ.ም

Читать полностью…

መዓዛ ሃይማኖት በጎ አድራጎትና ጉዞ ማህበር

ትካዜህን በእግዚአብሔር ላይ ጣል፥ እርሱም ይደግፍሃል፤ ለጻድቁም ለዘላለም ሁከትን አይሰጠውም።

መዝሙረ ዳዊት ፶፭÷፳፪

Cast thy burden upon the LORD, and he shall sustain thee: he shall never suffer the righteous to be moved.

Psalms 55÷22

መልካም ቀን

Читать полностью…

መዓዛ ሃይማኖት በጎ አድራጎትና ጉዞ ማህበር

የመስቀል ደመራ በዓል አከባበር በጥቂቱ ይኸን ይመስላል የዓመት ሰው ይበለን

Читать полностью…

መዓዛ ሃይማኖት በጎ አድራጎትና ጉዞ ማህበር

በምሥራቅ ወለጋ ሀገረ ስብከት ነቀምት ከተማ የ2016 ዓ.ም መስቀል ደመራ በዓል አከባበር በፎቶ።

Читать полностью…

መዓዛ ሃይማኖት በጎ አድራጎትና ጉዞ ማህበር

መስቀል ደመራ በዓል በመስቀል አደባባይ መስከረም 16

Читать полностью…

መዓዛ ሃይማኖት በጎ አድራጎትና ጉዞ ማህበር

🔴 አዲስ ዝማሬ " ደስ ብሰኝ " ዘማሪት ሲስተር ኩሪባቸው ተስፋዬ @-mahtot
https://youtube.com/watch?v=o3m45Pn5Clg&si=JcegqtyPfcYlB_E3

Читать полностью…

መዓዛ ሃይማኖት በጎ አድራጎትና ጉዞ ማህበር

መልስ: ሐ. ፍጥሞ

እኔ ወንድማችሁ የሆንሁ ከእናንተም ጋር አብሬ መከራውንና መንግሥቱን የኢየሱስ ክርስቶስንም ትዕግሥት የምካፈል ዮሐንስ ስለ እግዚአብሔር ቃልና ስለ ኢየሱስ ምስክር ፍጥሞ በምትባል ደሴት ነበርሁ።” የዮሐንስ ራእይ ፩፤፱


የተሣተፋችሁ ሁሉ ቃለ ሕይወትን ያሰማልን መንግሥተ ሰማያትን ያውርስልን

Читать полностью…

መዓዛ ሃይማኖት በጎ አድራጎትና ጉዞ ማህበር

#ገድልከ_ግሩም

ገድልከ ግሩም ነገርከ ጥዑም 
ጊዮርጊስ ኃያል እንቍ ስም /ቅረበነ/(፫)በሠላም

#ትርጉም
ገድልህ ግሩም አስደናቂ ኃያሉ ጊዮርጊስ ስምህ
እንቁ የከበረ ነው በሰላም ቅረበን

╭══•|❀:✧๑♡๑✧❀|: ══╮
@meazahaymanot
╰══•ೋ•✧๑♡๑✧• ══╯

Читать полностью…

መዓዛ ሃይማኖት በጎ አድራጎትና ጉዞ ማህበር

ስንክሳር ዘወርሃ መስከረም ሃያ ሦስት(፳፫) /channel/meazahaymanot

Читать полностью…

መዓዛ ሃይማኖት በጎ አድራጎትና ጉዞ ማህበር

እንኳን ለሊቀ መላእክት ቅዱስ ዑራኤል ወርኃዊ በዓል በሠላም አደረሳችሁ

ለተፈጥሮትከ፡-
ዑራኤል ሆይ፡- ያለ መናገር በጥንት አርምሞ ከነፋስና ከእሳት ለተፈጠረ ተፈጥሮህ ሰላም እላለሁ፡፡ ዑራኤል ሆይ የተፈጥሮና የይቅርታና የቸርነት ክቡር መልአክ ነህና ስለኛ ስለሰው ልጆች ወደ ልዑል እግዚአብሔር ማልድ አማላጅነትህ ዘወትር ከጥፋት ያድናልና፡፡

Читать полностью…

መዓዛ ሃይማኖት በጎ አድራጎትና ጉዞ ማህበር

ብዙኃን ማርያም

በቤተ ክርስቲያናችን ከሚዘከሩ የእመቤታችን ቅድስት ድንግል ማርያም ክብረ በዓላት መካከል መስከረም ፳፩ ቀን የሚውለው በዓል ‹‹ብዙኃን ማርያም›› በመባል ይታወቃል፡፡ በዓሉ በሁለት ዐበይት ምክንያቶች ይከበራል፤ የመጀመሪያው ሊቃውንተ ቤተ ክርስቲያን ሃይማኖታዊ ውሳኔ ለማዘጋጀት ከሩቅም ከቅርብም የተሰባበሰቡት ቀን፤ ሁለተኛው ደግሞ ጌታችን መድኀኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ የተሰቀለበት ዕፀ መስቀል በግሸን ደብረ ከርቤ የተቀመጠበት ዕለት መኾኑ ነው፡፡ ሁለቱንም ታሪኮች ከዚህ ቀጥለን እንመለከታቸዋለን፤

በ፫፻፳፭ ዓ.ም አርዮስ የሚባል መናፍቅ የእግዚአብሔር ወልድን የባሕርይ አምላክነት አልቀበልም በሚል ክህደት እርሱ ተሰናክሎ ለሌሎችም መሰናክል ኾነ፡፡ ኦርቶዶክሳውያን ሊቃውንት አርዮስ ክህደቱን እንዲተው ቢመክሩትም ሊመለስ አልቻለም፡፡ ይህ የአርዮስ ክህደትም በሊቃውንቱ መካከል መለያየትን ፈጥሯል፡፡ ጊዜው ታላቁ ንጉሥ ቈስጠንጢኖስ ‹‹አብያተ ጣዖታት ይትአጸዋ አብያተ ክርስቲያናት ይትረኀዋ፤ የጣዖታት ቤቶች ይዘጉ! አብያተ ክርስቲያናት ይከፈቱ!›› የሚል ዐዋጅ የነገረበት ወቅት ነበርና ንጉሥ ቈስጠንጢኖስ በአርዮስ ክህደት ምክንያት በኒቅያ የሃይማኖት ጉባኤ እንዲካሔድ በየአገሩ ላሉ ሊቃውንት መልእክት አስተላለፈ፡፡

በዚህም መሠረት ከሚያዝያ ፳፩ ቀን ጀምሮ እስከ መስከረም ፳፩ ቀን ድረስ ፳፫፻፵፰ (ሁለት ሺሕ ሦስት መቶ ዐርባ ስምንት) ሊቃውንት በኒቅያ ተሰበሰቡ፡፡ ኒቅያ ለዚህ ጉባኤ የተመረጠችበት ምክንያትም ጳጳሱን ከማኅበረ ካህናቱ፤ ንጉሡን ከሠራዊቱ ጋር አጠቃላ ለመያዝ የምትችል ሰፊና ምቹ ቦታ ከመኾኗ ባሻገር ለኹሉም አማካይ ሥፍራ ስለ ነበረች ነው፡፡ በጉባኤው ከተሰበሰቡ ሊቃውንት መካከልም እንደ ቅዱሳን ሐዋርያት ሙታንን ያስነሡ፣ ለምጽ ያነጹ፣ አንካሳ ያረቱ፣ የዕውራንን ዓይን ያበሩ ድውያንን የፈወሱ፣ ሌላም ልዩ ልዩ ተአምር ያደረጉ፤ እንደዚሁም ስለ ርትዕት ሃይማኖታቸው በመጋደል ዓይናቸው የፈረጠ፣ እጃቸው የተቈረጠ ይገኙበታል፡፡

ሊቃውንቱ ሱባዔ ይዘው በጸሎት ከቆዩ በኋላ ኅዳር ፱ ቀን በንጉሥ ቈስጠንጢኖስ ሊቀ መንበርነት፣ በእለእስክንድሮስ አፈ ጉባኤነት ጉባኤው ተጀመረ፡፡ ንጉሡ ሊቃውንቱን ‹‹ስማችሁን፣ አገራችሁንና ሃይማኖታችሁን ጽፋችሁ ስጡኝ›› ባላቸው ጊዜም ከ፳፫፻፵፰ቱ መካከል ፫፻፲፰ (ሦስት መቶ ዐሥራ ስምንቱ) ሊቃውንት ሃይማኖታቸውን ሲገልጹ እንደ አንድ ልብ መካሪ፣ እንደ አንድ ቃል ተናጋሪ ኾነው ‹‹ዘዕሩይ ምስለ አብ በመለኮቱ፤ ወልድ ከአብና ከመንፈስ ቅዱስ ጋር በመለኮት፣ በሥልጣን፣ በፈቃድ፣ በህልውና አንድ ነው›› ብለው ጽፈው ሰጡት፡፡ ንጉሡም ‹‹ሃይማኖት እንደ ፫፻፲፰ቱ ሊቃውንት ይኹን›› ብሎ ዐዋጅ አስነግሯል፡፡ እነዚህ ሊቃውንት በኦሪት ዘፍጥረት የተጠቀሱት ፫፻፲፰ቱ የአብርሃም ብላቴኖች ምሳሌዎች ናቸው /ዘፍ.፲፬፥፲፬/፡፡

፫፻፲፰ቱ ሊቃውንት በጉባኤው አርዮስን አውግዘው በመለየት ‹‹ነአምን በአሐዱ አምላክ፤ በአንድ አምላክ እናምናለን›› የሚለውን የሃይማኖት ጸሎት (የሃይማኖት መሠረት) እና ሌሎችንም የሃይማኖት ውሳኔዎችን ደንግገዋል፡፡ ሊቃውንቱ ጉባኤውን ያካሔዱት ኅዳር ፱ ቀን ይኹን እንጂ በአንድነት የተሰባሰቡት መስከረም ፳፩ ቀን ስለ ነበረ ይህ ዕለት ‹‹ብዙኃን ማርያም›› እየተባለ ይጠራል፡፡ ብዙ የቤተ ክርስቲያን አባቶች ለሃይማኖታዊ ጉባኤ የተሳባሰቡበት ዕለት ነውና፡፡

በሌላ በኩል መስከረም ፳፩ ቀን የጌታችን መድኀኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ መስቀል በአምባሰል ተራራ በግሸን ደብረ ከርቤ የገባበትና በዓሉ የከበረበት ዕለት ነው፡፡ ታሪኩም በአጭሩ የሚከተለው ነው፤

ዐፄ ዳዊት መንፈሳዊና ደግ ንጉሥ ነበሩ፡፡ በዘመናቸው በኢትዮጵያ ቸነፈር ተከሥቶ ሕዝቡ ስለ ተሰቃየባቸው እጅግ አዘኑ፤ በጸሎት ወደ እግዚአብሔር ቢያመለክቱም ከእግዚአብሔር ዘንድ የተላኩ ባሕታዊ መጥተው ‹‹የጌታችን መድኀኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስን መስቀል አስመጥተህ በአገርህ በኢትዮጵያ ቤተ ክርስቲያን አሠርተህ ብታስቀምጥ ረሃቡ፣ ቸነፈሩ ኹሉ ይታገሥልሃል›› አሏቸው፡፡ ዐፄ ዳዊትም ከብዙ ገጸ በረከት (ስጦታ) ጋር ‹‹የጌታችንን መስቀል ላኩልኝ›› የሚል መልእክት አስይዘው መልእክተኞችን ወደ ኢየሩሳሌም ሰደዱ፡፡ መልእክተኞቹም በታዘዙት መሠረት መስቀሉን ይዘው መምጣታቸውን ዐፄ ዳዊት ሲሰሙ ‹‹ክተት ሠራዊት ምታ ነጋሪት›› ብለው መስቀሉን ለመቀበል ጉዞ ጀመሩ፡፡

ዐፄ ዳዊት ስናር (ሱዳን) ደርሰው ከመልእክተኞቹ ጋር ተገናኝተው መስቀሉን በክብር አጅበው ወደ መካከል ኢትዮጵያ ለማስገባት ሲነሡም ከበቅሏቸው ወድቀው ጥቅምት ፱ ቀን ከዚህ ዓለም በሞት ተለዩ፤ በዚህም ሠራዊታቸው ተደናግጠው የጌታችንን መስቀል እዚያው ትተው የዐፄ ዳዊትን አስከሬን ይዘው ተመለሱ፡፡ መስቀሉ በስናር ከቆየ በኋላ የዐፄ ዳዊት ልጅ ዘርዐ ያዕቆብ ሲነግሡ ወደ መሃል ኢትዮጵያ አምጥተው ቤተ ክርስቲያን አሠርተው ለማስቀመጥ ቢያስቡም ምቹ ቦታ ግን ሊያገኙ አልቻሉም ነበር፡፡ ንጉሡና ሠራዊታቸው ምቹ ቦታ ሲፈልጉ መስቀሉን በኤረር ተራራ፣ በደብረ ብርሃን፣ በመናገሻ ማርያም ዓምባ፣ በእንጦጦ ጋራ ብዙ ጊዜ አስቀምጠውት ቆይተዋል፡፡

መስቀሉ በእንጦጦ ጋራ ሳለ እግዚአብሔር አምላክ ‹‹አንብር መስቀልየ በዲበ መስቀል፤ መስቀሌን በመስቀለኛ ተራራ ላይ አስቀምጥ›› የሚል ቃል ለንጉሡ በራእይ ነገራቸው፡፡ መስቀሉን ወደ ወሎ ሀገረ ስብከት እንዲወስዱትም አዘዛቸው፡፡ ንጉሡና ሠራዊታቸው በእግዚአብሔር መሪነት መስቀሉን ይዘው ወሎ ሲደርሱም ጌታችን ወደ አምባሰል እያመለከተ ‹‹አንብር መስቀልየ በዲበ መስቀል፤ መስቀሌን በመስቀለኛ ተራራ ላይ አስቀምጥ›› ይላቸው ነበር፤ ንጉሡ መስቀሉን ይዘው ወደ ቦታው ሲያመሩ መስቀለኛው የግሸን ተራራን አገኙ፤ በዚያም ቤተ ክርስቲያን አሠርተው በ፲፬፻፵፮ (1446) ዓ.ም የጌታችንን መስቀል በክብር አስቀምጠውታል፡፡

ከዚህ በኋላ ንጉሡ ‹‹መካከሏ ገነት፤ ዳሯ እሳት ይኹን! የበረረ ወፍ፣ የሠገረ ቆቅ አይታደንባት! በድንገት ሰው የገደለ፣ ቋንጃ የቈረጠ ወንጀለኛ አይያዝባት!›› ብለው ዐዋጅ ነግረዋል፡፡ የእመቤታችን ጽላትም አብሮ በግሸን ደብረ ከርቤ እንዲቀመጥ አድርገዋል፡፡ ስለዚህም መስከረም ፳፩ ቀን በየዓመቱ በቤተ ክርስቲያናችን በድምቀት ይከበራል፡፡ ኀጢአታቸውን ለካህን ተናዘው፣ ንስሐ ገብተው በዚህ ዕለት ወደ ግሸን ደብረ ከርቤ በመሔድ የሚጸልዩና የሚማጸኑ ምእመናን ኹሉ እስከ ሰባት ትውልድ ድረስ የምሕረት ቃል ኪዳን እንደሚያገኙም ጤፉት በተባለችው መጽሐፍ ተጠቅሷል፡፡

ምንጭ፡- መጽሐፈ ታሪክ ወግስ፣ መ/ር አፈወርቅ ተክሌ፤ ፳፻፭ ዓ.ም፣ አዲስ አበባ፤ ገጽ ፫፶፬-፫፶፮፡፡


https://m.youtube.com/channel/UCKGh-U7U7pnvFUIEGXPOnNw

Читать полностью…

መዓዛ ሃይማኖት በጎ አድራጎትና ጉዞ ማህበር

ስንክሳር ዘወርሃ መስከረም ሃያ አንድ(፳፩) /channel/meazahaymanot

Читать полностью…

መዓዛ ሃይማኖት በጎ አድራጎትና ጉዞ ማህበር

መልሱ ሐ. ምናሴ


፤ እርሱም። ጌታ ሆይ፥ እስራኤልን በምን አድናለሁ? ወገኔ ከምናሴ ነገድ ከሁሉ ይልቅ የተጠቃ ነው፤ እኔም በአባቴ ቤት የሁሉ ታናሽ ነኝ አለው።

መጽሐፈ መሣፍንት ፮÷፲፭-፵

ለተሣተፉችሁ ሁሉ ቃለ ሕይወትን ያሰማልን መንግሥተ ሰማያትን ያውርስልን

Читать полностью…

መዓዛ ሃይማኖት በጎ አድራጎትና ጉዞ ማህበር

ገብርኤል - ሩኅሩኅ መልዐክ ነህ
በዘማሪት ፋንቱ ወልዴ


@meazahaymanot
@meazahaymanot

Читать полностью…

መዓዛ ሃይማኖት በጎ አድራጎትና ጉዞ ማህበር

ክቡራን የቻናላችን ተከታታዮች እግዚአብሔር ቢፈቅድና ብንደርስ 19/01/2016 ዓ.ም  9:00 ሰዓት ላይ ‟  ማኅደረ ጥያቄ ይጀምራል እንድትከታተሉ በልዑል እግዚአብሔር ስም እንጠይቃለን።

ሃሳብ አስተያየት @misiwani_Bot
አድርሱን

ነገ ይጀመራል

@meazahaymanot
@meazahaymanot
@meazahaymanot

Читать полностью…

መዓዛ ሃይማኖት በጎ አድራጎትና ጉዞ ማህበር

ዜና እረፍት

መስከረም ፲፰ቀን፳፻ ፲ወ፮ዓ.ም
*********************
ብፁዕ አቡነ ሰማ ከዚህ ዓለም ድካም አረፉ።
*****************************

ጸሎተኛው፣ደጉ፣ርህሩሁና ታጋሹ አረጋዊው አባት ብፁዕ አቡነ ሰላማ ዛሬ መስከረም ፲፰ቀን ፳፻ ፲ወ፮ዓ.ም ከዚህ ዓለም ድካም አርፈዋል።ብፁዕ አባታችን ባደረባቸው ህመም ምክንያት በአዲስ አበባ ሀሌሉያ ሆስፒታል በህክምና ላይ እንዳሉ ነው ከዚህ ዓለም ድካም ያረፉት።የብፁዕነታቸውን ሽኝት መርሐ ግብር በተመለከተ በቋሚ ሲኖዶስ እንደተወሰነ ዝርዝሩን የምናሳውቅ ይሆናል።

የብፁዕነታቸው በረከት ይደርብን

Читать полностью…

መዓዛ ሃይማኖት በጎ አድራጎትና ጉዞ ማህበር

ስንክሳር ዘወርሃ መስከረም አሥራ ስምንት
/channel/meazahaymanot

Читать полностью…

መዓዛ ሃይማኖት በጎ አድራጎትና ጉዞ ማህበር

ምዕራብ ሐረርጌ ሀገረስብከት ጭሮ ከተማ

Читать полностью…

መዓዛ ሃይማኖት በጎ አድራጎትና ጉዞ ማህበር

መስቀል ደመራ አከባበር በጅማ
መስከረም 16/2016 ዓ.ም

Читать полностью…

መዓዛ ሃይማኖት በጎ አድራጎትና ጉዞ ማህበር

የባቱ ዝዋይ ደብረ ገነት ቅዱስ ጊዮርጊስ ካቴድራል አበው ፡ የሰንበት ት/ቤት ዘማሪያን ፡ መንፈሳዊ ማኅበራት ጉዞ ወደ ዝዋይ መስቀል አደባባይ ፡- መልካም በዓል
__________________________

Читать полностью…
Subscribe to a channel