መተኛት በፊት የሚጸለይ ጸሎት
መዝሙር 142/143
አቤቱ፥ ጸሎቴን ስማ፤ በእውነትህ ልመናዬን አድምጥ፥ በጽድቅህም መልስልኝ።
ሕያው ሁሉ በፊትህ ጻድቅ አይደለምና ከባሪያህ ጋር ወደ ፍርድ አትግባ።
ጠላትህ ነፍሴን አሳድዶአታል፥ ሕይወቴንም በምድር ውስጥ አጐስቍሎአታል፤ ቀድሞ እንደ ሞተ ሰው በጨለማ አኑሮኛል።
ነፍሴ በውስጤ አለቀችብኝ፥ ልቤም በውስጤ ደነገጠብኝ።
የቀድሞውን ዘመን አሰብሁ፥ ሥራህንም ሁሉ አሰላሰልሁ፤ የእጅህንም ሥራ ተመለከትሁ።
እጆቼን ወደ አንተ ዘረጋሁ፤ ነፍሴም እንደ ምድረ በዳ አንተን ተጠማች።
አቤቱ፥ ፈጥነህ ስማኝ፤ ነፍሴ አልቃለች፤ ፊትህን ከኔ አትመልስ፥ ወደ ጕድጓድም እንደሚወርዱ አልሁን።
አንተን ታምኛለሁና በማለዳ ምሕረትህን አሰማኝ፤ አቤቱ፥ ነፍሴን ወደ አንተ አንሥቻለሁና የምሄድበትን መንገድ አስታውቀኝ።
አቤቱ፥ ወደ አንተ ተማፅኛለሁና ከጠላቶቼ አድነኝ።
አንተ አምላኬ ነህና ፈቃድህን ለማድረግ አስተምረኝ፤ ቅዱስ መንፈስህም በጽድቅ ምድር ይምራኝ።
አቤቱ፥ ስለ ስምህ ሕያው አድርገኝ፤ በጽድቅህም ነፍሴን ከመከራዋ አውጣት።
በምሕረትህ ጠላቶቼን ደምስሳቸው፥ እኔ ባሪያህ ነኝና ነፍሴን የሚያስጨንቁአትን ሁሉ አጥፋቸው።
ለአብ ለወልድ ወመንፈስ ቅዱስም ምስጋና ይሁን፤ መቼም መች ለዘላለሙ ይሁን።
• • •
ሃሌ ሉያ ምስጋና ለእግዚአብሔር፤ ሃሌ ሉያ በየጊዜው፣ በየሰዓቱ ምስጋና ለአምላካችን ይሁን።
እነሆ መዓልቱ አልፎ፤ ሌሊቱ ተተካ፤ ስለዚህ ቅዱስ ሆይ፤አመሰግንሃለሁ። ወደ አንተ እማልዳለሁ፤ የምትመጣውን ሌሊት ያለፍርሃት እንዳሳልፋት ጠብቀኝ።
አባቴ እግዚአብሔር የማይታዩትን ጠላቶቼን ምክር ታውቃለህ፤ የሥጋዬም ደካማነት በአንተ በፈጣሪዬ ዘንድ የታወቀ ነው፤ ስለዚህ በቸርነትህ በክንፍህ ጥላ ሸፍነህ እንድትጠብቅኝ፤ ነፍሴን በእጅህ አደራ እሰጣለሁ። ለመሞት እንዳልተኛ ዓይነ ልቦናዬን በመለኮታዊ ቃልህ አብራልኝ። ከጨለማው እንቅልፍ አንቅተህ፤ አንተን ለማመስገን አዘጋጀኝ። አንተ ሰውን የምትወድ ቸር ነህና።
ምንም ጊዜም ቅድስት ድንግል፤ ንጽሕት የሆንሽ የክርስቶስ እናቱ ድንግል ማርያም ሆይ፤ ነፍሴን ያጸናት ዘንድ፤ ጸሎትሽን ወደ ልጅሽ አቅርቢልኝ።
ጌታዬ እግዚአብሔር ሆይ፤ በመዓልት ከሚወረወር፤ በሌሊትም ከሚጣል ክፉ ሥራ ሁሉ ሠውረኝ። አቤቱ ጌታዬ፤ በዚች ዕለት በቃልም ቢሆን፤ በማሰብም ቢሆን፤ በሥራም ቢሁን፤ በግልጥና በሥውር የበደልሁትን ሁሉ ይቅር በለኝ፤ በምሕረትህም አስተሥርይልኝ። ስለ ቅዱስ ስምህ ብለህ ሕይወት ያለው እንቅልፍ ስጠኝ። ከክፉ ነገር የሚጠብቅኝን የሰላም መልአክ ላክልኝ፤ ጸጋህንና ምሕረትህን አብዛልኝ። ላንድ ልጅህ፤ ለጌታችን፤ ለአምላካችን፤ ለመድኃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ፤ ማሕያዊ (አዳኝ) ለሚሆን ለመንፈስ ቅዱስ ሁል ጊዜ ምስጋና አቀርባለሁ፤ አሜን።
ምን እጠይቅሎ መርሐግብር የተጠየቁ ጥያቄዎች
፩, አብ, ወልድ, መንፈስ ቅዱስ አንድ አምላክ ከሆኑ
ወልድ ጌታችን ኢየሱስ ከእመቤታችን ማርያም ሰው ከሆነና አምላክ ሰው ከሆነ
ከላይ ያየነው አንዱ አምላክ ሰው ሆነ ማለት አይሆንብንም ወይ? እንደዛ ከሆነ ደሞ አብም መንፈስ ቅዱስም ሰው ሁነዋል አያስብልብንም?
በስመአብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ አሜን 🙏🤲
፪የእኔ ጥያቄ ሙስሊሞች ህፃን ልጅ ሲሙት ለምን ነው ከቤተ ክርስቲያን ዉጪ የምቀብሩት ሙስሊም ሰለሆነነው ከምከኔቱም ከልተጠመቀ ተጠምቀችሁ ነው ክርስቲያን የምኩኑት እያሉ ይጠይቁኝል ?
መልሱን እነኾ
የማለዳ ጸሎት
መዝሙር 5
አቤቱ፥ ቃሌን አድምጥ፥ ጩኸቴንም አስተውል፤
የልመናዬን ቃል አድምጥ፥ ንጉሤና አምላኬ ሆይ፥ አቤቱ፥ ወደ አንተ እጸልያለሁና።
በማለዳ ድምፄን ትሰማለህ፥ በማለዳ በፊትህ እቆማለሁ፥ እጠብቃለሁም።
አንተ በደልን የማትወድድ አምላክ ነህና፤ ክፉ ከአንተ ጋር አያድርም።
በከንቱ የሚመኩ በዓይኖችህ ፊት አይኖሩም፤ ክፉ አድራጊዎችን ሁሉ ጠላህ።
ሐሰትን የሚናገሩትን ታጠፋቸዋለህ፤ ደም አፍሳሹንና ሸንጋዩን ሰው እግዚአብሔር ይጸየፋል።
እኔ ግን በምሕረትህ ብዛት ወደ ቤትህ እገባለሁ፤ አንተን በመፍራት ወደ ቅድስናህ መቅደስ እሰግዳለሁ።
አቤቱ፥ ስለ ጠላቶቼ በጽድቅህ ምራኝ፤ መንገዴን በፊትህ አቅና።
በአፋቸው እውነት የለምና፥ ልባቸውም ከንቱ ነው፤ ጕሮሮአቸው የተከፈተ መቃብር ነው፤ በምላሳቸው ይሸነግላሉ።
አቤቱ፥ ፍረድባቸው፥ በምክራቸውም ይውደቁ፤ ስለ ክፋታቸውም ብዛት አሳድዳቸው፥ እነርሱ ዐምፀውብሃልና።
በአንተ የሚታመኑት ሁሉ ግን ደስ ይላቸዋል፤ ለዘላለሙ ደስ ይላቸዋል፥ እነርሱንም ትጠብቃለህ፤ ስምህንም የሚወድዱ ሁሉ በአንተ ይመካሉ።
አንተ ጻድቁን ትባርከዋለህና፤ አቤቱ፥ እንደ ጋሻ በሞገስ ከለልኸን።
ምስጋና ለአብ ለወልድ ለመንፈስ ቅዱስ ይሁን፡ መቼም መች ለዘላለሙ አሜን።
• • •
ሃሌ ሉያ ምስጋና ለእግዚአብሔር፤ ሃሌ ሉያ በየጊዜው፣ በየሰአቱ ምስጋና ለአማኑኤል አምላካችን ይሁን።
አቤቱ ጌታዬ ኢየሱስ ክርስቶስ ሆይ፤ ምስጢር አውቅ ዘንድ ጸጋህን ለማግኘት አብቃኝ፤ ያጋንንትን ተንኮላቸውን ግለጥልኝ፣ በመንፈስ ቅዱስ አጋዥነት በጸሎት በምለምንህ ጊዜ፣ ከፊቴ አርቃቸው፣ አሳፍራቸው፣ ይህም በምሕረትህ ይሁንልኝ፣ ይደረግልኝ።
እናቴ፣ መመኪያዬ፣ እመቤቴ ድንግል ማርያም ሆይ ተስፋዬ አንቺ ነሽና የተቀደሰውን ጸጋሽን በመተማመን፣ ወደ ልጅሽ ወደ ኢየሱስ ክርስቶስ እንድታማልጂኝ እለምንሻለሁ። የመለኮታዊ ልጅሽ ቸርነት እንዳይለየኝ ሁል ጊዜ ጸልዪልኝ። ያንቺም ረድኤት እንዲጎበኘኝ ፍቅርሽ እንዲበዛልኝ አድርጊልኝ። የተወደድሽ ርኅርኅት ድንግል ማርያም ሆይ ተስፋዬን በአማላጅነትሽ ላይ አደርጋለሁ፤ በየጊዜውም ሁሉ ጥበቃሽ እንዳይለየኝ የጸጋሽ ብርሃን ይብራልኝ።
አቤቱ የኃያላን አምላክ ዓለም ሳይፈጠር የነበርክ፣ ዓለሙን ሁሉ አሳልፈህ ለዘላለሙ የምትኖር የፍጥረት ሁሉ ጌታ፤ ፀሐይን ለቀን ብርሃን፣ ሌሊትን ለሰው ልጅ ዕረፍት የፈጠርክ፤ አቤቱ አንተን አመሰግናለሁ፤ አንተ ሌሊቱን በሰላም አሳልፈህ ወደቀኑ መጀመርያ ጠዋት ስለአደረስከኝ አመሰግንሃለሁ፤ የዓለሙ ሁሉ ንጉሥ ወደሆንክ ወደ አንተ ልመናዬን አቀርባለሁ። እውነት የሆነውን የእውቀትን ብርሃን ግለጥልኝ፤ የልቦናዬን ፀዳል አብራልኝ፤ መለኮታዊ ብርሃንህን በልቦናዬ ይበራልኝ ዘንድ የጀመርኩትንም መዓልት በጽድቅና በንጽሕና እንዲሁም በመልካም ሥርዓት ፈጽሜ ያለ እንቅፋት በሕይወት እንዳሳልፈው አድርገኝ። አንተ ብሩክ ነህና ክብር፣ ምስጋና፣ ስግደት ለአብ ለወልድ ለመንፈስ ቅዱስ አቀርባለሁ፤ ዛሬም ዘወትርም በየጊዜያቱ ሁሉ እስከዘላለም ፤ አሜን።
አባቴ እግዚአብሔር የማይታዩትን ጠላቶቼን ምክር ታውቃለህ፤ የሥጋዬም ደካማነት በአንተ በፈጣሪዬ ዘንድ የታወቀ ነው፤ ስለዚህ በቸርነትህ በክንፍህ ጥላ ሸፍነህ እንድትጠብቅኝ፤ ነፍሴን በእጅህ አደራ እሰጣለሁ። ለመሞት እንዳልተኛ ዓይነ ልቦናዬን በመለኮታዊ ቃልህ አብራልኝ። ከጨለማው እንቅልፍ አንቅተህ፤ አንተን ለማመስገን አዘጋጀኝ። አንተ ሰውን የምትወድ ቸር ነህና።
ምንም ጊዜም ቅድስት ድንግል፤ ንጽሕት የሆንሽ የክርስቶስ እናቱ ድንግል ማርያም ሆይ፤ ነፍሴን ያጸናት ዘንድ፤ ጸሎትሽን ወደ ልጅሽ አቅርቢልኝ።
ጌታዬ እግዚአብሔር ሆይ፤ በመዓልት ከሚወረወር፤ በሌሊትም ከሚጣል ክፉ ሥራ ሁሉ ሠውረኝ። አቤቱ ጌታዬ፤ በዚች ዕለት በቃልም ቢሆን፤ በማሰብም ቢሆን፤ በሥራም ቢሁን፤ በግልጥና በሥውር የበደልሁትን ሁሉ ይቅር በለኝ፤ በምሕረትህም አስተሥርይልኝ። ስለ ቅዱስ ስምህ ብለህ ሕይወት ያለው እንቅልፍ ስጠኝ። ከክፉ ነገር የሚጠብቅኝን የሰላም መልአክ ላክልኝ፤ ጸጋህንና ምሕረትህን አብዛልኝ። ላንድ ልጅህ፤ ለጌታችን፤ ለአምላካችን፤ ለመድኃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ፤ ማሕያዊ (አዳኝ) ለሚሆን ለመንፈስ ቅዱስ ሁል ጊዜ ምስጋና አቀርባለሁ፤ አሜን።
✞አዝላው ወረደች✞
አዝላው ወረደች ወደ ግብፅ(፪)
ስደተኛዋ የአምላክ እናት
ይህ ዓለም ለእርሷ መች ተገባት
ዓለም በምኗ ታስተናግዳት
የፍቅር ምንጯ ተሟጦባት
እነ ኮቲባን እየላከች
የአምላክን እናት ተሳደበች
እነ ሄሮድስን እየላከች
ህፃኑን ልትገድል አሳደደች
አዝ= = = = =
የክብርን ጌታ ተሸክማ
ውርደት ለበሰች እንደ ሸማ
የሀብቱን ጌታ በጀርባ አዝላ
ሰው ተዘከራት ተቸግራ
አዝ= = = = =
በቃሉ ትዕዛዝ ምድርን ሠርቶ
ተንከራተተ ማደሪያ እጥቶ
ጌታ ሲወለድ የምሥራች
በረት ሰጠችው ዓለም ታካች
አዝ= = = = =
ግና መላእክት በሰማያት
ሃሌ ሉያ አሉ በፍርሃት
ወልድን በአብ ቀኝ ከላይ አይተው
ደግሞም በምድር ከድንግል ክንድ
ከላይም ሳይጎድል ተመልክተው{፪}
አዝ= = = = =
ዓለም በምኗ ታስተናግዳት
የፍቅር ምንጯ ተሟጦባት
እነ ኮቲባን እየላከች
የአምላክን እናት ተሳደበች
እነ ሄሮድስን እየላከች
አዝ= = = = =
ህፃኑን ልትገድል አሳደደች
በቃሉ ትዕዛዝ ምድርን ሠርቶ
ተንከራተተ ማደሪያ እጥቶ
ጌታ ሲወለድ የምሥራች
በረት ሰጠችው ዓለም ታካች
መዝሙር
ይልማ ኃይሉ
"… በእግዚአብሔር ተዘጋጅቶላት ወደ ነበረው ስፍራ ወደ በረሀ ሸሸች። …"
ራእ፲፪፥፮
╭══•|❀:✧๑♡๑✧❀|: ══╮
@meazahaymanot
╰══•ೋ•✧๑♡๑✧• ══╯
✞በብርሃን ፀዳል✞
በብርሃን ፀዳል ተከባ እመቤቴ
በደመና ዙፋን ተቀምጣ ከፊቴ
የጽጌውን ዜማ ስንዘምር በደስታ
በምስጋናሽ መጠጥ/ሲሰማኝ እርካታ/(፪)
እንባዬ ሲቀዳ ናፍቆትሽ መስጦኝ
ከደስታ በላይ አንቺን ስላየሁኝ
ምኞቴ ተሳክቶ ፊትሽን አይቼው
የሌሊቱ ህልሜ /የቀን ምኞቴ ነው/(፪)
አዝ= = = = =
ሩኅሩኅ ነሽና ይህ ህልሜ ተሳክቶ
አመስግኜሽ ድንግል ህልናዬ ረክቶ
ልጅሽ ልሁን ድንግል ከስርሽ አልጥፋ
አንቺን በማመስገን/ህሊናዬ ይትጋ/(፪)
አዝ= = = = =
ልጅሽ ልሁን ድንግል ከስርሽ አልጥፋ
አንቺን በማመስገን ህሊናዬ ይርካ
የምስጋናሽ ብዕር ብራናሽ ልሁን
ስምሽ ይፃፍብኝ /በልዩ ህብር/(፪)
መዝሙር
ይልማ ኃይሉ
"እግዚአብሔርን አመስግኑ፥ መዝሙር መልካም ነውና።"
መዝ፻፵፯፥፩
╭══•|❀:✧๑♡๑✧❀|: ══╮
@meazahaymanot
╰══•ೋ•✧๑♡๑✧• ══╯
እንኳን ለአባታችን ለመጥምቀ መለኮት ቅዱስ ዮሐንስ ወርሀዊ መታሰቢያ በሰላም አደረሳችሁ።
ቅዱስ ዮሐንስ ከሀጢአት በቀር ያሰባችሁትን ሁሉ ይሙላላችሁ።
"ሰላም ለአስናኒከ
ሳቅ ሥላቅን ላለመዱ ጥርሶችህንና የመዘበት ከንቱ የዋዛ ቃልን ላልተናገር አንደበትህ ሰላምታ ይገባል። ኃላፊ ወርቅን የናቅህ ቅዱስ ዮሐንስ ሆይ የክቡር በዓልህ የምስጋና እምቢልታ በተነፋ ጊዜ ነጎድጓድን ያመጣል። መብረቅንም ያስከትላል። ቅዱስ ዮሐንስ ሆይ በየወሩ በሁለተኛው ወይንም በሠላሳኛው የበዓልህ ዕለት ብቻ ሳይኾን ዘወትር “ቅዱስ ዮሐንስ ቅዱስ ዮሐንስ” እንድልህ በእኔ በአገልጋይህ ላይ ፍቅርህን አሳድርብኝ።"
መልክአ ዮሐንስ
@meazahaymanot
#አርሴማ
አርሴማ አርሴማ ቅድስት ሰማዕት(2)
ሞገስ አግኝተሻል በክርስቶስ ፊት
አርሴማ------ታምርሽ ልዩ ነው
አርሴማ------ገድልሽ አስደናቂ
አርሴማ------ስምሽ ብርሃን ነው
አርሴማ------ማለዳ ፈንጣቂ
አዝ___
አርሴማ------ስምሽን እየጠራ
አርሴማ------ጠግቧል የተራበው
አርሴማ------ምስኪኑም ዘመረ
አርሴማ------ባንቺ አልፎ መከራው
አዝ___
አርሴማ------ፅኑ ነው ኪዳንሽ
አርሴማ------የተሰጠሽ ከአምላክ
አርሴማ------በአይኔ አይቻለው
አርሴማ------ጠላት ሲንበረከክ
አዝ___
አርሴማ------ዓለም ይስማው ዛሬ
አርሴማ------ዜና ተጋድሎሽን
አርሴማ------ይገረም ይደነቅ
አርሴማ------ይመስክር ዝናሽን
🕊
[ † እንኳን ለድንግልና ሰማዕት አርሴማ ቅድስት ወዮሐንስ ወንጌላዊ ዓመታዊ በዓል በሰላም አደረሳችሁ። † ]
† በስመ አብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ አሐዱ አምላክ አሜን! †
🕊 † ቅድስት አርሴማ ድንግል † 🕊
† እናታችን ቅድስት አርሴማን በምን እንመስላታለን? እርሷ በአድማስ ላይ ተቀምጦ እንደሚያበራ እንቁ ናትና ክብሯ ብዙ ነው:: መድኃኒታችን ክርስቶስ በወንጌል እንዳለው "በተራራ ላይ ያለች ከተማ ልትሠወር አይቻላትምና" የሰማዕቷ ሕይወት በፊታችን እንደ ብርሃን ተገልጦ ይታያል::
¤ ቅድስት አርሴማ እንደ ልጅ ወላጆቿን በመታዘዝ ደስ ያሰኘች ቡርክት ናት::
¤ ቅድስት አርሴማ ይሕ ቀረሽ የማይሏት ውብ ናት::
¤ ቅድስት አርሴማ ድንግል ናት::
¤ ቅድስት አርሴማ ባሕታዊት ጻድቅ ናት::
¤ ቅድስት አርሴማ ኃያል ሰማዕት ናት::
ይሕስ እንደ ምን ነው ቢሉ :-
አበው በትውፊት እንደ ነገሩን ከሆነ ቅዱሱ ጐርጐርዮስ የታላቋ ሰማዕት ቅድስት አርሴማ ትልቅ ወንድም ነው:: በዜና ሰማዕታት ተጽፎ እንደሚገኘው በዚያ የመከራ ዘመን ቅዱስ ጐርጐርዮስ ሦስት ኃላፊነቶች ነበሩበት :-
፩. ቅድስት አርሴማን ጨምሮ ደናግሉን ማጽናት::
፪. ትምሕርተ ቤተ ክርስቲያንን በሚገባ ማጥናት::
፫. የሚመጣውን መከራ ለመቀበል ራሱን ማዘጋጀት::
ቅዱሱ ሦስቱንም ኃላፊነቶች በሚገባ በመወጣቱ ከራሱ አልፎ ለሌሎቹ አርአያ መሆን ቻለ:: ያቺን ንጽሕት አርበኛ ቅድስት አርሴማንም አጽንቶ የደናግሉ መሪ አደረጋት:: መከራው በጣም ገፍቶ እስከ መጣበት ጊዜ ድረስ በአንድ የደናግል ገዳም ውስጥ ሆነው ይጸልዩ: ይጾሙ: ገዳማዊ ሥራንም ይሠሩ ነበር::
ለዚህም ነው ቅድስት አርሴማና ቅዱስ ጐርጐርዮስ ጻድቃን የምንላቸው:: በኋላ ግን ማሕደረ ሰይጣን ዲዮቅልጢያኖስ በመልኳ ተማርኮ ቅድስት አርሴማን ካላገባሁ በማለቱ ቅዱስ ጐርጐርዮስ ድንግሏን አርሴማን ጨምሮ ፲፳፯ ክርስቲያኖችን ይዞ ወደ አርማንያ ተሰደደ::
በአርማንያም በአንድ ገዳም ውስጥ ተደብቀው በጾምና በጸሎት ለጥቂት ጊዜ ቆዩ: ነገር ግን ረሃብ ፈጃቸው:: የሚላስ የሚቀመስ ነገር በአካባቢው ባለ መኖሩ ቅዱስ ጐርጐርዮስ ወደ ከተማ ለመውጣት ተገደደ::
በዚያም በድርጣድስ ቤተ መንግስት ውስጥ ባርነት ተቀጠረ:: በሚያገኛት ገንዘብም ወገኖቹን ይረዳ ነበር:: መከራው ግን አለቀቃቸውም:: ርጉም ዲዮቅልጢያኖስ ቅዱሳኑ ወደ አርማንያ መሔዳቸውን ስለ ሰማ ይዞ እንዲልክለት ድርጣድስን ላከው::
ድርጣድስ ግን ቅድስት አርሴማን ባያት ጊዜ ከውበቷ የተነሳ መታገስ ባለመቻሉ "ካላገባሁሽ" አላት:: ድንግሊቱ ግን "እኔ የክርስቶስ ሙሽራ ነኝ: አይሆንም" አለችው:: ሊያስፈራራት ሞከረ:: ዐይኗ እያየ ደናግሉን ጨፈጨፋቸው::
አልሳካልህ ቢለው በአደባባይ በግድ ሊያገባት ቢሞክር እጁን ጠምዝዛ በሰው ሁሉ ፊት መሬት ላይ ጣለችው:: እጅግ ስላፈረ አስገረፋት: አሰቃያት: ዐይኗንም አወጣ:: በመጨረሻም አንገቷን አስቆርጦ ከሰማዕታቱ ጋር ተራራ ላይ ጣላት::
ከነገር ሁሉ በኋላ ድርጣድስና ባለሟሎቹ ለአደን በሔዱበት ርኩስ መንፈስ ወደ አውሬነት [እሪያነት] ቀየራቸው::
የንጉሡ እንስሳ [አውሬ] መሆን በአርማንያ ታላቅ ድንጋጤን ፈጠረ:: የንጉሡ እህት ስታለቅስ በራዕይ "ለእመ ኢያዕረግምዎ ለጐርጐርዮስ አልብክሙ ድኂን - ጐርጐርዮስን ከተቀበረበት ካላወጣችሁት አትድኑም" አላቸው:: ወዲያውም ቆፍረው አወጡት::
ቅዱሱ እንደ ወጣ ዕረፍትን አልፈለገም:: ለ፲፭ ዓመታት ቀባሪ አጥቶ የተበተነውን የቅድስት አርሴማንና የሰማዕታቱን አጽም ሰብስቦ በክብር አኖረው:: ድርጣድስና ባለሟሎቹንም ወደ በርሃ ሒዶ ፈወሳቸው::
የሰማዕቷ ቅድስት አርሴማ አጽም በ፲፬ኛው መቶ ክ/ዘመን ከሌሎች ሰማዕታት አጽም ጋር ወደ ሃገራችን እንደ መጣ አባቶቻችን በትውፊት ነግረውናል:: ለዚህም ይመስላል ቡርክቷ እናታችን ከሌሎች ሃገራት ለይታ ለኢትዮዽያውያን ልዩ ፍቅር ያላት:: በዋናው ገዳሟ [ወሎ / ኩላማሶ / ስባ / ውስጥ የሚገኝ ነው] ጨምሮ ስሟ በተጠራበት ሁሉ ኃይልን ታደርጋለችና::
ነገር ግን ወንድሞቼና እሕቶቼ በቅድስቷ እናታችን ስም የሚነግዱ ሥጋውያን ሰዎች በዝተዋልና እንጠንቀቅ:: የሰማዕቷ ክብር ብዙ ነውና በሕልም ላይ ብቻ አንታመን:: አባ እንጦንስ እንዳሉት "በሕልሙ የሚታመን ሰው ከንቱ ነውና::"
በዚህ ዕለት ከሰማዕቷ ጋር የመንፈስ እናቷን ቅድስት አጋታን ልናስባት ይገባናል:: ይህች እናት እመ-ምኔት ስትሆን ቅድስት አርሴማን ታስተምራት: ታጸናት: ከጐኗም ትቆምላት ነበር:: ረሃቧን: ጥሟን: ስደቷን: መከራዋንም ሁሉ አብራት ተሳትፋለች:: በፍጻሜውም አብራት ተሰይፋለች::
🕊 † ቅዱስ ዮሐንስ ወንጌላዊ † 🕊
- የቤተ ክርስቲያን ምሰሶ
- ምድራዊው መልአክ
- የጌታ ወዳጅ
- የድንግል ማርያም የአደራ ልጅ
- የንጽሕና አባት
- ቁጹረ ገጽ
- የፍቅር ሐዋርያ
- የምሥጢር አዳራሽ
- የሐዋርያት ሞገሳቸው
- ነባቤ መለኮት ቅዱስ ዮሐንስ ወልደ ነጐድጓድ ዛሬ ይከብራል::
ምክንያቱም "ቀዳሚሁ ቃል" [ዮሐ.፩፥፩] ብሎ እንደ ንስር መጥቆ ወንጌሉን በዚህች ቀን ጽፏልና::
✞ አምላከ ቅዱሳን ለኛ ለባሮቹ የቅድስቷን ጽናት: የወንጌላዊውንም ፍቅር ያድለን:: በረከታቸውን ከማይጐድል እጁ አብዝቶ ይስጠን::
🕊
[ ✞ መስከረም ፳፱ [ 29 ] ቀን የሚከበሩ ዓመታዊ የቅዱሳን በዓላት ]
፩. ቅድስት አርሴማ ድንግል [ሰማዕት]
፪. ቅድስት አጋታ [እመ ምኔት]
፫. "፻፲፱" ሰማዕታት [የቅድስት አርሴማ ማሕበር]
፬. ቅዱስ ዮሐንስ ወንጌላዊ [ነባቤ መለኮት]
፭. ቅድስት ክርስቶስ ክብራ ኢትዮዽያዊት [በዚህ ቀን ነፍሳትን ከሲዖል ታወጣለች]
[ ✞ ወርኀዊ በዓላት ]
፩. የፈጣሪያችንና ጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ በዓለ ልደት
፪. ቅዱስ ዼጥሮስ ተፍጻሜተ ሰማዕት
፫. ቅዱስ ማርቆስ ዘቶርማቅ
፬. ቅድስት ፍቅርተ ክርስቶስ ኢትዮዽያዊት
፭. ቅዱስ ዘርዐ ክርስቶስ [ጻድቅና ሰማዕት]
✞ " በመጀመሪያ ቃል ነበረ:: ቃልም በእግዚአብሔር ዘንድ ነበረ:: ቃልም እግዚአብሔር ነበረ :: ይህ በመጀመሪያው በእግዚአብሔር ዘንድ ነበረ:: ሁሉ በእርሱ ሆነ:: ከሆነውም አንዳች ስንኳ ያለ እርሱ አልሆነም:: በእርሱ ሕይወት ነበረች:: ሕይወትም የሰው ብርሃን ነበረች:: ብርሃንም በጨለማ ይበራል:: ጨለማም አላሸነፈውም::" ✞ [ዮሐ. ፩፥፩]
† ወስብሐት ለእግዚአብሔር †
† ወለወላዲቱ ድንግል †
† ወለመስቀሉ ክቡር †
[ ዲ/ን ዮርዳኖስ አበበ ]
† † †
▬▬▬▬▬ ▬▬▬ ▬▬▬▬▬
💖 🕊 💖
🕊
† በስመ አብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ አሐዱ አምላክ አሜን! †
[ † መስከረም ፳፰ [ 28 ] † ]
🕊 † ቅዱሳን አባዲርና እህቱ ኢራኢ † 🕊
† በ፫ ኛው መቶ ክ/ዘመን የሮም መንግስት ዓለምን የሚያስተዳድረው በሁለት ከተሞች: ማለትም በራሷ በሮምና በአንጾኪያ ነበር:: የወቅቱ ንጉሥ ኑማርያኖስ ሲሆን የቤተ መንግስቱ ልዑላንና የጦር አለቆች ቅዱሳኑ :- ፋሲለደስ: ገላውዴዎስ: ፊቅጦር: መቃርስ: አባዲር: ቴዎድሮስ [ሦስቱም] አውሳብዮስ: ዮስጦስ: አቦሊ: ሌሎቹም ነበሩ::
ሴቶቹ ደግሞ ቅዱሳቱ:- ማርታ: ሶፍያ: ኢራኢ: ታኡክልያ: ሌሎቹም ነበሩ:: ለእነዚህ ሁሉ የበላይ ደግሞ ቅዱስ ፋሲለደስ ነበር:: ወቅቱ ከፋርስ: ከቁዝና ከበርበር ጦርነት የሚበዛበት ነበርና ባጋጣሚ ንጉሡ ኑማርያኖስ በሰልፍ መካከል ተመትቶ ወደቀ/ሞተ::
የሮም መንግስትም ባዶ ሆነች:: ዙፋኑን መያዝ ለቅዱስ ፋሲለደስም ሆነ ለሌሎቹ ቅዱሳን ቀላል ነበር:: ግን እነሱ ዝም ብለው ጠላትን ለመዋጋት ወጡ::
በዘመኑ ደግሞ በግብጽ የፍየል እረኛ የነበረና ከልጅነቱ ሰይጣን የሚያናግረው አንድ አግሪዻዳ የሚሉት ጉልበተኛ ሰው ነበር:: ንጉሡ ከወለዳቸው ልጆች ሁለቱ ሴቶች ክፉዎች ነበሩና ትንሿ አግሪዻዳን ማንም በሌለበት አንግሣ ጠበቀቻቸው:: ስሙንም ዲዮቅልጢያኖስ አለችው::
በቤተ ክርስቲያን ታሪክ ከሰይጣን ቀጥሎ እንደዚህ የከፋ ስም የለም:: የዓለም ክርስቲያኖችን የጨፈጨፈ ሰው ነው:: ትልቋ ደግሞ የትንሿን አይታ መክስምያኖስ የሚባል አውሬ አግብታ አነገሠችው:: ዓለምም በእነዚህ ጨካኝ ሰዎች እጅ ወደቀች::
ሠራዊቱ ሁሉ በሚሊየን ይቆጠራሉ:: የተደረገውን ሲያዩ ተበሳጩ:: ይህንን የተመለከተው ቅዱሱ ፋሲለደስ ግን ልዑላኑንና አለቆችን ሰብስቦ:- "ይህ ዓለም ከነ ክብሩ ጠፊ ነው:: ስለዚህ የተሻለውን የክርስቶስን መንግስት እንምረጥ" አላቸው:: ሁሉም እንደ አንድ ልብ መካሪ ደስ ተሰኝተው ምድራዊ ክብራቸውን ሊተው ወሰኑ::
ቀጥለውም በአንድ ቤት ተሰብስበው ይጾሙ: ይጸልዩ ገቡ:: ወደ ውጪ የሚወጡት ለምጽዋት ብቻ ነበር:: ቅዱሳኑ አባዲርና ኢራኢም ከእነዚህ መካከል በመሆናቸው ተጋድሏቸውን ቀጠሉ:: በተለይ ቅዱስ አባዲር በሌሊት በመካነ ጸሎቱ ሲጸልይ ያድርና በቀን ነዳያንን ይጐበኛል::
አመሻሽ ላይ ደግሞ ልብሱን ለውጦ ወደ እሥር ቤት ይሔዳል:: እሱ የአንጾኪያ ሠራዊት አለቃ: ኃያል የጦር መሪ ነውና ሁሉ ይወደውና ያከብረው ነበር:: በዚህም ምክንያት የእሥር ቤት ዘበኞች ምንም ከዲዮቅልጢያኖስ ከባድ ትዕዛዝ ቢኖርባቸውም ለቅዱሱ ግን ይከፍቱለት ነበር::
እርሱም ወደ እሥር ቤት ገብቶ ቁስላቸውን ጠርጐ: እግራቸውን አጥቦ: ለረሃባቸው መደገፊያ የሚሆን ማዕድም አጉርሷቸው ይወጣ ነበር:: በእንዲህ ያለ ግብር ሳለ ስለ ክርስቶስ የሚሰዋበት ጊዜ ደረሰ::
አንድ ቀን በመካነ ጸሎቱ ለምስጋና ሲተጋ ክብር ይግባውና መድኃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ተገለጠለት:: "ስምህን ለዘለዓለም አከብረዋለሁ:: በሰማያዊት ርስቴም አነግሥሃለሁና ከእህትህ ኢራኢ ጋር ወደ ምድረ ግብጽ ወርዳችሁ መስክሩ" ብሎት: ለእሷም በተመሳሳይ "ወንድምሽ የሚያዝሽን ሥሪ" ብሏት መድኃኒታችን ዐረገ::
ከዚያች ቀን ጀምሮ ቅዱስ አባዲርና እህቱ ኢራኢ ወደ ግብጽ የሚወርዱበትን መንገድ ይፈልጉ ነበር:: እናታቸው ግን (የቅዱስ ፋሲለደስ እህት ናት) ነገሩን ስትሰማ አለቀሰችባቸው:: "ልጆቼ አትሙቱብኝ: ዲዮቅልጢያኖስንም አትናገሩት" ስትል አማለቻቸው::
ከጥቂት ቀናት በኋላም ቅዱሱ ከእህቱ ጋር ከሶርያ ጠፍቶ ግብጽ ገቡ:: በዚያ ግን ፈተና ገጠመው:: በየመንገዱ የሚያየው ሕዝቡና ሠራዊት ሁሉ "ጌታችን አባዲር" እያለ ይሰግድለት ገባ:: ቀደም ሲል እንዳልነው እርሱ ኃያል የጦር መሪ: የሠራዊቱም አለቃ ነውና::
ቅዱሱ ግን ወደ ክርስቶስ ሊሔድ ናፍቋልና ሠራዊቱን እና ሕዝቡን:- "የሚገርማችሁ ሁሉም ሰው እንዲህ ይለኛል:: ግን'ኮ እኔ አንድ ተራ ምስኪን ክርስቲያን እንጂ የምትሉት ሰው አይደለሁም" ብሎ አታለላቸው::
ቀጥሎ በክርስትናው ተከሶ ከእህቱ ጋር ለፍርድ ቀረበና ስቃይ ታዘዘባቸው:: ለሰው ዐይን የሚከብዱ ብዙ ስቃዮችን ካሳለፉ በኋላም ሞት ተፈረደባቸው:: ነገር ግን አንገታቸው ከመሰየፉ በፊት መኮንኑ አርያኖስ ትክ ብሎ ሲያየው ተጠራጥሮ "ማንነትህን እንድትነግረኝ በአምላክህ አምየሃለሁ" አለው::
ቅዱስ አባዲርም መልሶ "አንተም ማንነቴን ካወቅክ በኋላ እኔን መግደል እንዳትተው ማልልኝ" አለው:: ማለለትም "እኔ አባዲር ነኝ" አለው:: በዚያች ቅጽበት አርያኖስ ከመደንገጡ የተነሳ መሬት ጠበበችው:: በፊቱ ተደፍቶ "ወዮልኝ! ጌታየን አባዲርን ያሰቃየሁ" እያለ አለቀሰ:: ነገር ግን ምሏልና በ300 ዓ/ም አካባቢ እያዘነ በዚህች ቀን ቅዱስ አባዲርንና እህቱን ኢራኢን አሰይፏቸዋል::
🕊 † ቅድስት ሶስና † 🕊
† ይህች እናት የነበረችው ቅ.ል.ክርስቶስ በ፭፻ [500] ዓመት አካባቢ ነው:: እሥራኤላውያን በናቡከደነጾር ተማርከው ፋርስ ባቢሎን ወርደው ሳሉ: የኬልቅዩስ ልጅ: የደጉ ኢዮአቄም ሚስት የሆነች እናት ናት::
ቅድስት ሶስና በስደት ሃገር እግዚአብሔርን የምታመልክ: ለባሏ የምትታመን: ለቤተሰቦቿም ኩራት የሆነች ወጣት: በዚያውም ላይ እጅግ የምታምር ነበረች:: በዘመኑ ሕግን እናውቃለን የሚሉ ፪ ረበናት ግን ከቅድስናዋ ሊያጐድሏት ይሹ ነበርና: አልሳካላችሁ ቢላቸው በሃሰት ከሰው በወገኖቿ ፊት ሞትን አስፈረዱባት::
በፍርድ ፊት ቁማ ሳለ እርሷ በፍጹም እንባ ወደ ፈጣሪዋ ትጸልይ ነበርና እግዚአብሔር ፍርዱን ላከ:: ሊገድሏት ሲወስዷት የኋላው ነቢዩ ቅዱስ ዳንኤል ያን ጊዜ ብላቴና ነበርና "እኔ ከዚህች የተባረከች ሴት ደም ንጹሕ ነኝ" ሲል ጮኸ::
ይህንን የሰሙ ዳኞችም የፍርድ ዙፋኑን ለቀቁለት:: ሁለቱን ረበናት ለየብቻቸው አድርጐ ዝሙትን ስትሠራ በየት ቦታ ላይ እንዳዩዋት ጠየቃቸው:: ጌታ ሲፈርድባቸው አንዱ በኮክ: ሌላኛው በሮማን ዛፍ ሥር አለ:: በዚህ ጊዜ ሕዝቡ እነዚህን ሃሰተኛ ረበናት [መምሕራን] ስለ እርሷ ፈንታ ወግረው ገደሏቸው:: ቅድስት ሶስና ግን ባለ ዘመኗ ሁሉ ፈጣሪዋን አገልግላ በዚህች ቀን ዐርፋለች::
† አምላከ ቅዱሳን ከክፉ ሰዎች ምክር: ከአጋንንትም ሴራ በቸርነቱ ይጠብቀን:: የወዳጆቹንም ጸጋ ክብራቸውን ያድለን::
🕊
[ † መስከረም ፳፰ [ 28 ] ቀን የሚከበሩ ዓመታዊ የቅዱሳን በዓላት ]
፩. ቅዱስ አባዲር ሰማዕት
፪. ቅድስት ኢራኢ እህቱ
፫. ቅድስት ሶስና እናታችን
፬. ቅዱስ ሉቃስ መነኮስ
፭. ቅዱስ ዻውፍርና
[ † ወርሐዊ በዓላት ]
፩. አምላካችን አማኑኤል
፪. አበው ቅዱሳን አብረሃም, ይስሐቅ, ያዕቆብ
፫. ቅዱስ እንድራኒቆስ ሚስቱ ቅድስት አትናስያ
፬. ቅድስት ዓመተ ክርስቶስ
፭. ቅዱስ ቴዎድሮስ ዘሮሜ ሰማዕት
† " ሶስናም ቃሏን አሰምታ ጮኸች:- 'ዘላለም ጸንተህ የምትኖር: የተሠወረውን የምታውቅ: የሚደረገውን ሁሉ ሳይደረግ የምታውቅ ፈጣሪ ሆይ! በሐሰት እንደ ጣሉኝ አንተታውቃለህ:: እነዚህ መመሕራንም ክፉ ነገርን ባደረጉብኝ ገንዘብ: የሠራሁት ኃጢአት ሳይኖር እነሆ እሞታለሁ' አለች:: እግዚአብሔርም ቃሏን ሰማት::" † [ሶስና.፩፥፵፩]
† ወስብሐት ለእግዚአብሔር †
† ወለወላዲቱ ድንግል †
† ወለመስቀሉ ክቡር †
[ ዲ/ን ዮርዳኖስ አበበ ]
† † †
▬▬▬▬▬ ▬▬▬ ▬▬▬▬▬
💖 🕊 💖
ምን እንጠይቅሎ መርሐግብር
" አስተውል፤ አባትህን ጠይቅ፥ ያስታውቅህማል፤ ሽማግሌዎችህን ጠይቅ፥ ይነግሩህማል። "
ኦ. ዘዳ 32÷ 7
እንኳን ደስ ያለን ምን እንጠይቅሎ ??? የተሰኘው ሳምንታዊ መርሐ ግብራችን በእናንተ ጸሎት በእግዚአብሔር ቸርነት እነኾ ዛሬይጀምራል
በመሆኑም ከዚህ በፊት በቴሌ ግራም ቻናላችን እንደምናደርገው በጥያቄዎቻችሁ ቅደም ተከተል መሠረት በየ ሳምንቱ ምላሽ የምንሰጥበት ሲሆን ግላዊ ጥያቄዎችንና ሰፊ ማብራሪያ የሚያስፈልጋቸውን ጥያቄዎች በኦዲዮ ቀድተን የምንልክላቹ መሆኑን ለማስታወስ እንወዳለን ::
ጥያቄዎቻችሁን ከታች ባለው የቴሌ ግራም አድራሻ መላክ የምችሉ መሆኑን እንጠቁማለን "
@misiwani_Bot
@misiwani_Bot
ይጠይቁ ይመለስልዎታል
🔒
ውድ የመዓዛ ሃይማኖት ቻናል ቤተሰቦች ቻናላችን መርዳት የምትፈልጉ ከታች ያለዉን ሊንክ ለጓደኞቻችሁ Copy አድርጋቹ በመላክ ወይም ይህንን መልዕክት በቀጥታ forward በማድረግ አበረታቱን።
🔒
ለምትወዷቸዉ ሰዎች የምትወዱትን ቻናላችንን ላኩላቸዉ።
🔏
ዉድ ወንድሞቼና እህቶች አንድ ቅን ሰዉ ቢያንስ ለ5 ሰዎች ሼር ቢያደርግ በ30 ደቂቃ ዉስጥ በ1,000 ቅን ሰዎች 5,000 አዳዲስ ቤተሰቦችን ማግኘት እንችላለን!!
#ለትብብራቹ_ከልብ_እናመሰግናለን
🔒
〰〰〰〰〰〰〰〰〰〰〰〰〰
Share share
@meazahaymanot
@meazahaymanot
@meazahaymanot
ማንኛውንም ሀሳብ አስተያየት
👉 @misiwani_Bot ላይ አድርሱን። ይህ የናንተው ቻናል ነው።√
🙏 እናመሰግናለን 🙏
መልሱ : መ ነነዌ
የነነዌ ሕዝቦች መዠመሪያ ባቢሎናውያን ሲኾኑ /ዘፍ.፲፡፲፩/ አስታሮት (“የባሕር አምላክ”)የሚባል ጣዖትን ያመልኩ ነበር፡፡ ከተማይቱ በሃብቷና በውበቷ ትታወቅ ነበር፡፡ የአሦር ነገሥታትም በጦርነት የማረኳቸውን ሰዎች ያጉሩባት ስለ ነበረች “ባርያ” ተብለው የሚታሰቡ ሰዎች የሚበዙባት ነበረች፡፡ ነገሥታቱ በጨካኝነታቸው፣ የብዙ ንጹሐን ዜጐችን ደም በከንቱ በማፍሰስ፣ በምርኮኞች ሞትና ስቃይ ደስ በመሰኘት እንደ መዝናኛም በመቊጠር ይታወቃሉ፡፡ ነቢዩ ናሆም “የደም ከተማ” ብሎ የጠራትም ከዚኹ የተነሣ ነው /ናሆ.፫፡፩/፡፡ ነቢዩ ዮናስ ይኽችን ከተማ ነበር ወደ ንስሐ እንዲጠራ በልዑል እግዚአብሔር የተላከው፡፡
ለተሣተፉ ሁሉ ቃለ ሕይወትን ያሰማልን መንግሥተ ሰማያትን ያውርስልን
ልጅህ ስለሆንኩኝ
ልጅህ ስለሆንኩኝ የሥላሴ ፍጥረት
ተክለሃይማኖት ስጠኝ የእጅህን በረከት
ጥቂት ይበቃኛል ባዶዬን ልሙላበት
ቤተ ሰሊሆም ነች የስምህ መጠሪያ
ፈለቀች ትምርትህ ከወንጌል ገበያ
ምንጭ ሆኖ ፈሰሰ እኛም እረካን
የአምላክን መና በገርድህ አየን
አዝ = = = = = =
እልፍ አእላፍ ሆነው በዝተው ቢሰለፉ
የጥፋትን ጉድጓድ አጋንንት ቢያሰፉ
ቅዱስ መስቀልህን ይዘህ ትነሣለህ
ለነፍሴ ዋስ ሆነህ ትቆምላታለህ
አዝ = = = = = =
ተክለሃይማኖት እኔን በምልጃህ አስበኝ
ረድኤት በረከትህ ከኔ እንዳይለኝ
ታሪኬን ቀይረው ጎዶሎዬን ሞልተህ
መራራ ሕይወቴን በወንጌል አጣፍጠህ
አዝ = = = = = =
ዛሬም ተአምራትህ በዓለም ይሰማል
ቁስለኛው አካሌ በጸበልህ ድኗል
ጸሎትህ ፈውስ ሆኖኝ ከሞት ተርፌአለሁ
በሄድኩበት ሁሉ ተክልዬ እልሃለሁ
መዝሙር
ዘማሪ ፍቃዱ አማረ
<< ቅዱሳን በዓለም ላይ እንዲፈርዱ አታውቁምን >>
፩ ቆሮ ፮፥፪
╭══•|❀:✧๑♡๑✧❀|: ══╮
@meazahaymanot
╰══•ೋ•✧๑♡๑✧• ══╯
፩. አምላክ ለምን ሰው ሆነ?
* ፍጹም ካሳ ለመክፈል
በአዳም ምክንያት ወደ ዓለም ኀጢያት ወደ ዓለም ገብቶ ትውልዱን ሁሉ ተቆጣጥሮ ስለነበር የሚጸለየው ጸሎት የሚሠዋው መሥዋዕት የሚያድን አልነበረም፡፡ (ኢሳ 64፥6) ብዙዎች የብሉይ ኪዳን አበው ደማቸውን አፍሰዋል፡፡ መራራ ሞትን ታግሰዋል ነገርግን የበደል ካሳ መሆን ግን አልቻሉም ምክንያቱም የበደሉ ዘር ስለነበረባቸውና የእግዚአብሔር ክብር ስለጎደላቸው፡፡ ስለዚህም ፍፁም አምላክ የሆነ አምላካዊ ቃል በምድር ላይ ፍፁም አምላክ ፍፁም ሰው ሆኖ ተገለጠ፡፡
የዓለምን ኀጢያት ተሸከመ (ኢሳ 53፥4) ቅድስት ሕይወቱንም መሥዋዕት አድርጎ ካሳ ከፈለልን (ኢሳ 53፥5) ቅዱስ ጳውሎስ “በዓለም ፍፃሜ ራሱን በመሠዋት ኀጢአትን ሊሽር አንድ ጊዜ ተገልጧልና” ብሎ እንደተናገረው (ዕብ 9፥26) በተጨማሪም (ዮሐ 10፥15-18) ተመልከት
* አርአያ ለመሆን
የሰው ልጅ የሰይጣን ቃል በመስማት ሥነ ምግባር ብልሹነትን ወደ ዓለም አስገባ፡፡ በዚህም ምክንያት ስለሌላው ራሱን አሳልፎ መስጠት ሲገባው ራሱን ከተጠያቂነት ለማውጣት ሌላውን አሳልፎ መስጠት ጀመረ (ዘፍ 3፥12) ምቀኝነት ክፋት መግደል ወደ ሰው ልብ ገቡ (ዘፍ 4፥8፤13፥3፣ መዝ 61፥4) በመሆኑም ወልደ እግዚአብሔር ከምድር የጠፋውን የበጎ ምግባር ሕይወት አርአያ ሆኖ ለመመለስ ሰው ሆነ፡፡ ለአርአያነት መምጣቱንም “ከእኔ ተማሩ” በማለት ገለጸ፡፡ (ማቴ 1129) “እኔ እንደወደድኳችሁ እርስ በእርሳችሁ ተዋደዱ” በማለት የፍቅርን ትዕዛዝ አስተላልፏል፡፡ (ዮሐ 15፥17) ቅዱስ ጴጥሮስም “ክርስቶስም ደግሞ ፍለጋውን እንድትከተሉ ምሳሌ ትቶላችሁ መከራን ተቀብሎአል” ሲል እንደተናገረ ጌታችን አርአያ ለመሆን ሰው ሆነ፡፡ (2ኛ ጴጥ 2፥21)
* ፍቅሩን ለመግለጥ
እግዚአብሔር አምላክ ሰውን በአርአያውና በምሳሌው የፈጠረው ያለምክንያት ስለወደደን ነው፡፡ (ሆሴ 14፥4) ይህም ከሁሉ ፍጥረት ሰውን አልቆና አክብሮ በመፍጠሩ ታውቋል፡፡ የሰው ልጅ በዲያብሎስ ፈተና ተጠልፎ የራሱን ፈቃድ ተጠቅሞ ሞት ቢፈረድበትም እራሱ ወርዶ እንደሚያድን ቃል ገባ ፈጸመውም፡፡ “እርሱ አስቀድሞ ወዶናልና” እያለ ሐዋርያው ቅዱስ ዮሐንስ እኛ አምላካችንን እንድንወደው በፍቅር ሕግ ከመታወጁ በፊት እርሱ እንደወደደን ይገልፃል፡፡ (ዮሐ 3፥16) “እግዚአብሔር አንድያ ልጁ እስኪሰጥ ድረስ አለምን ሁሉ እንዲሁ ወዱዋልና” ብሎ ጽፎልናል፡፡ በተጨማሪም (1ኛ ዮሐ 4፥19፣ ሮሜ 5፥8፣ ኤፌ 2፥4) ተመልከት
ከላይ ከጠቀስናቸው ምክንያቶችም በተጨማሪ
* ለአዳም የገባለትን ቃል ኪዳን ለመፈጸም
* የሰይጣንን ጥበብ ለመሻር
* ምድር ለመልካም ተፈጥራ ሳለ በኀጢያት ረክሳ ነበርና በቅዱሳን እግሮቹ ተመላልሶ ሊባርካት (ኢሳ 45፥18፣ 3፥17)
* ከእኛ በላይ ማንም የለም ለሚሉ ከሁሉ በላይ የሆነ አምላክ መኖሩን ለመግለጽ
* አምላክ አካላዊ አይደለም ይሉ ነበርና አካላዊነቱን ለመግለጽ
* እውነተኛ ሰላምና ዕርቅን ለመስጠት
ወደ ዓለም የመጣው ማነው?
ወደ ዓለም የመጣው ከሦስቱ አካላት አንዱ ወለድ ነው፡፡
ከመላእክት ወገን ቢልክስ ወይም ሌላ አዲስ ፍጥረት ፈጥሮ መላክ ሲችል አንደኛ ልጁን ወልድ ለምን ላከው ቢሉ አስቀድሞ የገባለትን ቃል ሊፈጽም ነው አስቀድሞ የገባለት ቃል ምንድር ነው ቢሉ ከልጅ ልጅህ ተወልጄ አድንሃለሁ የሚለው ነው በዘፍጥረት መጽሐፍም አዳም ከእኛ እንደ አንዱ ሆነ ሆነ (ዘፍ3÷23) ብሎ መለኮታዊ ባሕርዩን እንደሚካፍል ተገልጦል፡፡ቅዱስ ኤፍሬም ሶርያዊ ይህንን በተመለከተ ሲናገር‹‹ አሐዱ ዘእምቅድስት ሥላሴ ርእዮ ትሕትናነ አጽነነ ሰማየ ሰማያት መጽዐ ወኀደረ ውስተ ከርሠ ድንግል ወኮነ ሰብእ ከማነ ዘእንበለ ኃጢአት ባሕቲታ ወተወልደ›› ብሏል(ውዳሴ ማር ዘሐሙስ)
አብና መንፈስ ቅዱስ ሰው ያልሆኑት ለምንድን ነው
አንደኛ ወልድ ከአብ ከመንፈስ ቅዱስ ተለይቶ ጥንተ ግብሩ መወለድ ስለሆነ
ቤተክርስቲያን ለወለድ ሁለት ልደታት እንዳሉት ታምናለች፡፡ ይህንንም በተመለከተ አበው ‹‹ ነአምን ክልኤተ ልደታተ››(ሃይ አበው 34÷6 84÷25) ይኸውም ቀዳማዊ ልደት እና ደኀራዊ ልደት ናቸው፡፡ “ለእግዚአብሔር ልጅ ሁለት ልደታት እንዳሉት ልናምን ይገባል፡፡ መጀመሪያ ከዘመን ሁሉ በፊት ከእግዚአብሔር አብ መወለዱ ነው፡፡ ዳግመኛም በኋላ ዘመን ከእመቤታችን ቅድስት ድንግል ማርያም የተወለደው መወለዱ ነው” ሲል ሊቁ ባስሊዮስ ዘቂሳርያ አስረድቷል፡፡ አንዱ በመንፈስ አንዱ በሥጋ የተከወነ ሲሆን ቀዳማዊ ልደቱ በድኀራዊ ልደቱ እንደተገለጠ አበው ያስተምራሉ፡፡ አባ ጊዮርጊስ ዘጋስጫ በአርጋኖን ድርሰቱ ‹‹ልደት ቀዳማዊ ተዐውቀ በድኀራዊ ልደት›› እንዳለ፡፡
✞አዲሱን ቀን በምስጋና✞
እጀምራለሁ አዲሱን ቀን በምስጋና
ቸርነትህ ለዚህ አድርሶኛልና
ምህረትህ ዘመኔን ያድስ ጌታ ክርስቶስ
ምህረትህ ዘመኔን ያድስ አምላክ ክርስቶስ
ትናንትን አለፍኩት ቸርከኝ ይህን ዓመት
ተባርኳል ሕይወቴ አንተ ኖረህበት
ቃሉ የሚጠግን ሐዘን እየሻረ
ማን አለ እንደ አንተ(፪)እኔን ያከበረ
/ሁሌ አዲስ ነው የአንተ ፍቅር
ክበር እላለሁ ክበር/(፪)
አዝ= = = = =
አይተህ ቸል ያላልከኝ ጩኸቴን ሰምተህ
ቁስሌን የፈወስከው ሐኪሜ አንተ ነህ
በሚደነቅ ምህረት በደሌን የማርከው
ሥራኝ በዚህ ዓመት(፪)አድርገኝ አዲስ ሰው
/ሁሌ አዲስ ነው የአንተ ፍቅር
ክበር እላለሁ ክበር/(፪)
አዝ= = = = =
አእዋፍ በማለዳ ምስጋና ያቀርባሉ
ለሊቱ እንዳለፈ ብርሃን ያበስራሉ
ወራት እና ዓመታት ታድሰው ይመጣሉ
ኃያሉ እግዚአብሔር (፪)ክብርን ይገልጣሉ
እጹብ እጹብ የአንተ ሥራ
እንዲህ በቀላል አይወራ
ግሩም ግሩም የአንተ ሥራ
እንዲህ በቀላል አይወራ
አዝ= = = = =
አላማዬ አንተ ነህ ሕይወቴን የምትመራ
ማንነቴ ይመስክር ማዳንህን ያውራ
ይህን አመት ደግሞ ለንስሐ ተውከኝ
ፍቅር ነህ ጌታዬ(፪)እንዲሁ የወደድከኝ
እጹብ እጹብ የአንተ ሥራ
እንዲህ በቀላል አይወራ
ግሩም ግሩም የአንተ ሥራ
እንዲህ በቀላል አይወራ
መዝሙር
ዲያቆን ዘለዓለም ታከለ (ዘጎላ)
፩ጴጥ፬፥፫
╭══•|❀:✧๑♡๑✧❀|: ══╮
@meazahaymanot
╰══•ೋ•✧๑♡๑✧• ══╯
ከመተኛት በፊት የሚጸለይ ጸሎት
መዝሙር 142/143
አቤቱ፥ ጸሎቴን ስማ፤ በእውነትህ ልመናዬን አድምጥ፥ በጽድቅህም መልስልኝ።
ሕያው ሁሉ በፊትህ ጻድቅ አይደለምና ከባሪያህ ጋር ወደ ፍርድ አትግባ።
ጠላትህ ነፍሴን አሳድዶአታል፥ ሕይወቴንም በምድር ውስጥ አጐስቍሎአታል፤ ቀድሞ እንደ ሞተ ሰው በጨለማ አኑሮኛል።
ነፍሴ በውስጤ አለቀችብኝ፥ ልቤም በውስጤ ደነገጠብኝ።
የቀድሞውን ዘመን አሰብሁ፥ ሥራህንም ሁሉ አሰላሰልሁ፤ የእጅህንም ሥራ ተመለከትሁ።
እጆቼን ወደ አንተ ዘረጋሁ፤ ነፍሴም እንደ ምድረ በዳ አንተን ተጠማች።
አቤቱ፥ ፈጥነህ ስማኝ፤ ነፍሴ አልቃለች፤ ፊትህን ከኔ አትመልስ፥ ወደ ጕድጓድም እንደሚወርዱ አልሁን።
አንተን ታምኛለሁና በማለዳ ምሕረትህን አሰማኝ፤ አቤቱ፥ ነፍሴን ወደ አንተ አንሥቻለሁና የምሄድበትን መንገድ አስታውቀኝ።
አቤቱ፥ ወደ አንተ ተማፅኛለሁና ከጠላቶቼ አድነኝ።
አንተ አምላኬ ነህና ፈቃድህን ለማድረግ አስተምረኝ፤ ቅዱስ መንፈስህም በጽድቅ ምድር ይምራኝ።
አቤቱ፥ ስለ ስምህ ሕያው አድርገኝ፤ በጽድቅህም ነፍሴን ከመከራዋ አውጣት።
በምሕረትህ ጠላቶቼን ደምስሳቸው፥ እኔ ባሪያህ ነኝና ነፍሴን የሚያስጨንቁአትን ሁሉ አጥፋቸው።
ለአብ ለወልድ ወመንፈስ ቅዱስም ምስጋና ይሁን፤ መቼም መች ለዘላለሙ ይሁን።
• • •
ሃሌ ሉያ ምስጋና ለእግዚአብሔር፤ ሃሌ ሉያ በየጊዜው፣ በየሰዓቱ ምስጋና ለአምላካችን ይሁን።
እነሆ መዓልቱ አልፎ፤ ሌሊቱ ተተካ፤ ስለዚህ ቅዱስ ሆይ፤አመሰግንሃለሁ። ወደ አንተ እማልዳለሁ፤ የምትመጣውን ሌሊት ያለፍርሃት እንዳሳልፋት ጠብቀኝ።
መልሱ መ በኤደን ገነት
አራተኛውም ወንዝ ኤፍራጥስ ነው። እግዚአብሔር አምላክም ሰውን ወስዶ ያበጃትም ይጠብቃትም ዘንድ በዔድን ገነት አኖረው።
ኦሪት ዘፍጥረት ፪÷፲፭-፳፭
ለተሣተፋችሁ ሁሉ ቃለ ሕይወትን ያሰማልን መንግሥተ ሰማያትን ያውርስልን
ከቤቱ አይለይልን
#በርቱ
#ዮሐንስ_ክቡር
ዮሐንስ ክቡር ነቢየ ልዑል
ብእሴ ሰላም /4/ ዘንብረቱ ንብረቱ ገዳም /2/
#ትርጉም፡- የከበረ የልዑል ነቢይ ዮሐንስ ሆይ መኖሪያው በገዳም የሆነ የሰላም ሰው ነው ፡፡
♡#በፍጥነት_ይቀላቀሉ_አብረን_እንዘምር♡
╭═•|❀:✧๑✝♡๑✧❀|: ═╮
@meazahaymanot
@meazahaymanot
@meazahaymanot
╰═•ೋ•✧✝๑♡๑✧• ═╯
🌸 ታላቅ በሆነው እምነትሽ 🌸
ታላቅ በሆነው እምነትሽ ታመንኩኝ
ካለሽበት ገስግሼ መጣሁኝ
እናቴ ክብርሽን አንግሼ
ሆንኩኝ እንደ ህፃን ታድሼ
እናቴ ቅድስት አርሴማ
ዝናሽ ለዓለም ተሰማ
ስመጣ ባልጋ ነበረ
ተስፋዬም የተሰበረ
በእምነትሽ በፀበልሽ
ሰው ሆኜ ቆምኩኝ ደጅሽ
ልናገር ዝናሽን ላውራ
ይደነቅ የአምላክሽ ሥራ
ተጋድሎሽ የእምነትሽ ፅናት
ሆኖኛል የእምነቴ መብራት
ደምግባት ከንቱ ብለሽ
ለሰማይ ክብር ታጭተሽ
የእምነቴ አሰረ ፍኖት
በምልጃሽ አለሁ በህይወት
የልቡን ለነገረሽ
ፈጥኖ ይደርሳል መልስሽ
ዘንባባሽ ህይወት ይዘራል
የጠራሽ ማን አፍሮ ያውቃል
እርዳታሽ የደረሰለት
ያመጣል የልቡን ስለት
ላመኑሽ ፈውስሽ ቅርብ ነው
ባንቺ አፍሮ የሄደው ማነው
የልቡን ለነገረሽ
ፈጥኖ ይደርሳል መልስሽ
ዘንባባሽ ህይወት ይዘራል
የጠራሽ ማን አፍሮ ያውቃል
✞ አማኑኤል ስምከ ልዑል ✞
● መዝሙር ●
♡ ዲያቆን ልዑልሰገድ ጌታቸው ♡
╭══•|❀:✧๑♡๑✧❀|: ══╮
@meazahaymanot
╰══•ೋ•✧๑♡๑✧• ══╯
ጾመ ጽጌ እንኳን አደረሳችሁ !
የእመቤታችን ስደት በጾም በጸሎት የምታስቡ ወይም የምታሳልፉ የእመቤታችን የቅድስት ድንግል ማርያም የቃልኪዳን ልጆች እንኳን አደረሳችሁ
ጾመ ጽጌ ከመስከረም 26 እስከ ኅዳር 5 ያለው አንድ ወር ከዐሥር ቀን ወይም 40 ቀን ወርኃ ጽጌ፣ ዘመነ ጸጌ፣ ተብሎ ይጠራል፡፡ በነዚህም ቀናት በየቤተክርስቲያኑ የሚነበቡ ምንባቦች፣ የሚዘመሩት መዝሙሮች፣ የሚሰበከው ስብከት፣ የሚቆመው ማኅሌት በጠቅላላው የሚነገረው ስብሐት እግዚአብሔር ሁሉ ሰማይ በከዋክብት ምድር በጽጌያት አሸብርቀው የሚታዩ መሆናቸውን የሚገልጽ ነው፡፡
ወርኃ ጽጌ ለሚከናወነው መንፈሰዊ አገልግሎት መነሻው “መልአኩ ሕፃኑንና እናቱን ወደ ግብፅ ይዘሃቸው ሽሽ፣ የሕፃኑን ነፍስ ሊገድሉት ይፈልጋሉና” ሲል ለዮሴፍ በሕልሙ በነገረው መሠረተ ዮሴፍም ሕፃኑንና እናቱን ድንግል ማርያምን ይዞ ወደ ግብፅ መሰደዱና እመቤታችንና ሕፃኑ ሦስት ዓመት ከመንፈቅ በስደት ከኖሩ በኋላ /ራእይ.12፣6/ ወደ አገራቸው ወደ ናዝሬት የመመለሳቸው መታሰቢያ ነው፡፡ /ማቴ. 2፣13-23፣ ት.ኢሳ.19፣1፣ እንባቆም 3፣6-7፣ መዝ.83፣3/፡፡
ይህንንም በ14ኛው መቶ ክፍለ ዘመን የተነሡ አባ ጽጌ ብርሃን ፍሬ ከአበባ አበባም ከፍሬ እንደሚገኝ ሁሉ እመቤታችን ቅድስት ድንግል ማርያምንና ልጇን ኢየሱስ ክርስቶስን በአበባና በፍሬ እየመለሰ በሚያስረዳው ድርሰታቸው እንዲህ በማለት ገልጸውለታል፡፡ “ አፈወ ሮማን ማርያም ጽጌ ቀናንሞ ወአበሜ፣ እስከ ተጸምሐየየ በጾም ዘመልክዕኪ ጊዜ ድክታሜ፣ እምተመነይኩ ተሳትፎ ከመ አኅትኪ ሰሎሜ፣ ወፍሥሓኪ ዘአልቦ ፍጻሜ”፡፡ ሲተረጎምም የሮማን ሽቱ የቀናንሞ አበባ የምትሆኚ ማርያም ሆይ፣ በርሃብ በጾም አበባ የመሰለ የመልክሽ ደም ግባት እስኪጠወልግ ድረስ በስደትና በልቅሶ የደረሰብሽን ችግርና ድካም መከራሽንም ሁሉ እንደ እኅትሽ እንደ ሰሎሜ አብሬሽ ብቀበል ምኞቴ ነበር፤ በዚህ ፍጻሜ የሌለውን ደስታሽን እሳተፍ ነበር፡፡ እንዲሁም አባ አርክ ሥሉስ በስደቷ የደረሰባትን ኀዘን ፣ ልቅሶና ሰቆቃ አስመልክተው በደረሱት ‘ሰቆቃወ ድንግል” በሚለው ድርሰታቸው እንዲህ አሉ፣ ፀሐይን የምትለብሽ የብርሃን ልጅ ቅድስት ድንግል ማርያም ከክፉ ከሄሮድስ ዘንድ ልጅሽን ባሸሸሽ ጊዜ የደረሰብሽን ችግሮች ጨረቃን የሚጫሙ እግሮችሽ በመንገድ ብዛትና በአሸዋ ግለት እንደ ጎበጎቡ ሲሰማ ሰው ይቅርና ድንጋዩም ባለቀሰ ነበር”፡ የእመቤታችን የስደቷ መታሰቢያ ወር በቤተ ክርስቲያናችን የሚከበረው በማኅሌት፣ በቅዳሴና በዝክር ነው፡፡ በወርኃ ጽጌ ባሉት ሳምንታት ከቅዳሜ ማታ እስከ እሑድ ጠዋት አበው ካህናት የሚያቀርቡት ዝማሬ ከቅዱስ ያሬድ ድጓ፣ ከማኅሌት ጽጌና ከሰቆቃው ድንግል የተውጣጣና ሦስት ወገን ያለው ነው፡፡ ዝክሩም፣ በአሁኑ ወቅት በከተሞች አካባቢ እየተረሳ ቢመጣም፣ ዘወትር እሑድ የአንድ አካባቢ ሰዎች ማዕከላዊ በሆነ ቦታ ተሰባስበው በእመቤታችን ስም የሚዘክሩት ነው፡፡ ዐቅመ ደካሞች፣ ድሆችና መንገደኞች ተጠርተው በእመቤታችን ስም እንዲበሉና እንዲጠጡ ይደረጋል፡፡
ይህም ትውፊት እመቤታችን ወደ ኢትዮጵያ በመጣች ጊዜ ኢትዮጵያውያን አባቶችና እናቶች ያደረጉላትን መስተንግዶ ለማሰብ ነው፡፡
የእናታችን እመቤታችን የቅድስት ድንግል ማርያም እረድኤቷበረከቷ ፆሎት ልመናዋ ፍቅሯ ጣዕሟ እናትነቷ አማላጅነቷ አይለየን አሜን።
https://m.youtube.com/channel/UCKGh-U7U7pnvFUIEGXPOnNw
መልሱ : ሐ. 12
ኦሪት ዘፍጥረት ፳፭÷፴፮
ሀ. የልያ ልጆች፡- ሮቤል፥ ስምዖን፥ ሌዊ፥ ይሁዳ፥ ይሳኮር፥ ዛብሉን
ለ. የራሔል አገልጋይ የሆነችው የባላ ልጆች፡- ዳን፥ ንፍታሌም
ሐ. የልያ አገልጋይ የሆነችው የዘለፋ ልጆች፡- ጋድ፥ አሴር
መ. የራሔል ልጆች፡- ዮሴፍ፥ ብንያም ናቸው።
ለተሣተፈ ሁሉ ቃለሕይወትን ያሰማልን መንግሥተ ሰማያትን ያውርስልን