meazahaymanot | Unsorted

Telegram-канал meazahaymanot - መዓዛ ሃይማኖት በጎ አድራጎትና ጉዞ ማህበር

3925

"ውድስት አንቲ በአፈ ነቢያት ወስብሕት በሐዋርያት አክሊለ በረከቱ ለያዕቆብ ወትምክህተ ቤቱ ለእስራኤል፡፡" "በነቢያት በሐዋርያት አንደበት የተመሰገንሽ የያዕቆብ የበረከቱ ዘውድ የእስራኤል ወገን መመኪያ አንቺ ነሽ"                  መጽሐፈ ሰዓታት የፌስቡክ ፔጃችን www.fb.me/meazhaimanot ይቀላቀሉን

Subscribe to a channel

መዓዛ ሃይማኖት በጎ አድራጎትና ጉዞ ማህበር

ሰብስክራይብ በማድረግ ቤተሰብ ይሁኑ እኔ ተቀላቅያለሁ

#እ_ና_ን_ተ_ስ

Читать полностью…

መዓዛ ሃይማኖት በጎ አድራጎትና ጉዞ ማህበር

ደብረ ጽጌ ቅዱስ ኡራኤል ቤተክርስቲያን የሊቀመላእክት ቅዱስ ዑራኤል ዓመታዊ በዓል እየተከበረ ይገኛል

Читать полностью…

መዓዛ ሃይማኖት በጎ አድራጎትና ጉዞ ማህበር

አስተርእዮ ማርያም በዓል በደብረ ምጥማቅ ሰዓሊተ ምሕረት ቅድስት ድንግል ማርያም ቤተክርስቲያን  እንዲህ እየተከበረ ይገኛል

ጥር 21/2016 ዓ.ም

Читать полностью…

መዓዛ ሃይማኖት በጎ አድራጎትና ጉዞ ማህበር

እንኳን ለእመቤታችን ለቅድስት ድንግል ማርያም በዓለ እረፍት(ጥር21) ፤አስተርዮ ማርያም በሰላም አደረሳችሁ

#የህይወት_እናት_ድንግል_ማርያም_ሆይ ትንሳኤሽ ሳይሆን ሞትሽ ይደንቀኛል፤ እርገትሽ ሳይሆን ወደ መቃብር መውረድሽ ይገርመኛል።


እመቤተ ማርያም ሆይ ያለመጨነቅ ያላፃር ከሥጋዋ ለተለየች ነፍስሽ ሰላምታ ይገባል አነዋወሯም በልጅሽ ቀኝ ጐን በክብር ነው። ድንግል ሆይ ከፈጣሪ ዘንድ የባለማልነትን ግርማ የተጐናፀፍሽ ነሽ። በረድኤትሽ ሰውነቴን ከድካሟ አሳርፊያት። ክብሯም (ኃይሏም) ከድጋግ አባቶቿ ክቡር (ኃይል) ያነሰ አይሁን። መልክአ ቅድስት ድንግል ማርያም።


       #_መልካም_በዓል🙏

አጫጭር ኦርቶዶክሳዊ ትምህርቶች
      •➢ 👇  ለማግኘት // 👇

@meazahaymanot
@meazahaymanot

Читать полностью…

መዓዛ ሃይማኖት በጎ አድራጎትና ጉዞ ማህበር

አስተርእዮ መታየት ወይም መገለጥ የሚል ትርጓሜ ያለው የግእዝ ቃል ነው፡፡በግሪክ ‹‹ኤጲፋኒ›› የሚል ስያሜ አለው፤ የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን ሊቃውንትም ይህን ቃል  በመጠቀም ኤጲፋኒያ እያሉ በዜማ መጻሕፍቶቻቸው ይጠሩታል፡፡
አስተርእዮ የሚለው ቃል አስተርአየ የተባለው ግሥ ራሱን ችሎ ሳይለወጥ በአምስቱ አዕማድ የሚፈታ ብቸኛ ግሥ ነው፡፡ ይህም ማለት፤ ‹አስተርአየ፤ ታየ፤ ተያየ፤ አሳየ፤ አስተያየ፤ አየ› ተብሎ ይፈታል ማለት ነው፡፡ ዘመነ አስተርእዮ ሲያጥር ከጥር ፲፩ ቀን እስከ ጥር ፴፤ ሲረዝም ደግሞ ከጥር ፲፩ ቀን እስከ መጋቢት ፫ ቀን ይሆናል፡፡ በዚህም መሠረት ቀናቱ ሲያጥር ፳፤ ሲረዝም ፶፫ ይሆናሉ ማለት ነው፡፡ጌታችን ኢየሱስ ለሐዋርያት ሕፅበተ እግር ያደረገበት ቀንም (ከጸሎተ ሐሙስ) እስከ ጰራቅሊጦስ ቢቆጠር ፶፫ ቀናት ስለሚሆኑ የእነዚህ ምሳሌዎች ናቸው፡፡ ዮሐንስ በጥምቀት ዕለት ለልዕልና (ጌታ ሰውን ምን ያህል እንዳከበረው) ለማሳየት እጁን ከጌታ ራስ በላይ ከፍ እንዳደረገ፤ ጌታንንም ለትሕትና እጁን ከሐዋርያት እግር በታች ዝቅ አድርጎ እግራቸውን አጥቧቸዋልና ነው፡፡ ጥምቀት የሕጽበት አምሳል ሲሆን፤ ሕጽበት (መታጠብ) ደግሞ በንባብ አንድ ሆኖ ሁለት ምሥጢራት አሉት፡፡
የመጀመሪያው ምእመናን የእንግዳ እግር እንዲያጥቡ ትምህርት ማስተማሩ ሲሆን፤ ሁለተኛው ለሐዋርያት ጥምቀታው መሆኑ ነው፡፡ ሐዋርያት በጸሎተ ሐሙስ ቢጠመቁም መንፈስ ቅዱስ የተቀበሉት የጰራቅሊጦስ ዕለት ነውና፡፡ ቅዱስ ጎርጎርዮስ ዘኑሲስ ስለ ቅዱሳን ሐዋርያት ጥምቀት ቅዱስ ባስልዮስ ዘቂሣርያን እንደ ጠየቀውና ጥምቀታቸው ሕጽበተ እግር መሆኑን እንደ መለሰለት፡፡
በሌላ በኩል ከዘመነ ልደት እስከ ጥምቀት ‹ተወልደ፤ ተሠገወ (ሰው ሆነ)› ይባላል እንጂ ተገለጠ አይባልም፡፡ ከጥምቀት በኋላ ግን አብሮ፣ ተባብሮ ‹ተጠምቀ፤ ተወለደ፤ ተሠገወ፤ አስተርአየ› ይባላል፡፡ ከጥምቀት በፊት አስተርእዮ ለመባሉ በሦስት ነገሮች ነው፡፡
የመጀመሪያው የማይታየው ረቂቅ አምላክ በበረት ተወልዶ፤ በጨርቅ ተጠቅልሎ ቢታይ፤ እንደ ሕፃን ሲያለቅስ ቢሰማም ሰው ሁሉ ሠላሳ ዓመት ሲሞላው ሙሉ ሰው ይሆናል እንደሚባለው፣ ‹አምላክ ነኝ› ብሎ በአንድ ቀን ሳያድግ በጥቂቱ ማደጉንና ስደት እንደ ውርደት ሆኖ እንዳይቆጠር ለሰዎች ስደትን ባርኮ ለመስጠት፤ ሄሮድስም ሊገድለው ይፈልገው ስለነበር ወቅቱ የሚሰደድበት እንጂ የሚታይበት ስላልነበረ ነው፡፡
ሁለተኛው፤ ሰው በተፈጥሮም ሆነ በትምህርት አዋቂ ቢሆን ለሚመለከተው ሥራና ደረጃ እስከ ተወሰነ ጊዜ ይህ ሕፃን ለእንዲህ ያለ ማዕረግ ይሆናል አይባልም፤ ተንከባክባችሁ አሳድጉት ይባላል እንጂ ሕፃኑ አዋቂ ነው አይባልም፤ ያውቃል ተብሎም ለትልቅ ደረጃ አይበቃም፡፡ በየትኛውም ኃላፊነት ላይ አይሰጥም፤ ራሱን በመግዛት ይጠበቃል እንጂ፡፡ እንዲሁም ጌታ የመንፈሳዊ እና የሥጋዊ ባለሥልጣን ቢሆንም ፍፁም ሰው ሆኗልና የሰውን ሥርዓት ከኃጢአት በቀር ለመፈጸም በበሕቀ ልሕቀ፤ በየጥቂቱ ዐደገ ይላል፡፡ አምላክ ነኝና ሁሉን በዕለቱ ልፈጽም ሳይል በየጥቂቱ ማደጉን እናያለን፡፡ በዚህም የተነሣ ሰው ሁሉ ፴ ዓመት ሲሆነው ሕግጋትን እንዲወክል እንዲወስን እስከ ፴ ዓመት መታገሡ ስለዚሁ ነው፡፡ ከሠላሳ ዓመት በኋላ ግን ሰው ቢመቸው ይወፍራል፤ ቢከፋው ይከሳል እንጂ ቁመት አይጨምርም፤ አይቀንስም፡፡ ስለዚህ ጌታ ሙሉ ሰው የ፴ ዓመት አዕምሮው የተስተካከለለት ሰው (ጎልማሳ) ሆኖ በመታየቱ ዘመነ አስተርእዮ ተብሏል፡፡
ሦስተኛው፤ በ፴ ዓመት እሱ ሊጠመቅበት ሳይሆን የመጀመሪያ መንፈሳዊ ሕግና ሥርዓት መሠረት የሆኑ ጥምቀትንና ጾምን ሠርቶ በማሳየትና መመሪያ አድርጎ በመስጠት እሱ ሙሉ ሰው ሆኖ ተገልጾ የቃሉን ትምህርት ለመስማት፤ የእጁን ተአምራት ለማየት ይከተለው ለነበረው አምስት ገበያ ያህል ሕዝብ  ትምህርት፣ ተአምራት ያደረገበት፤ ሥራዬ ብሎ የመጣበት መንፈሳዊ ሕግና ሥርዓት የፈጸመበት ዘመን በመሆኑ ነው፡፡  የታየውም ብቻ አይደለም፤ አብ ‹‹ይህ የምወደው ልጄ ነው፤›› ሲል መንፈስ ቅዱስም በእርግብ አምሳል ረቂቁ የታየበት የሥላሴ አንድነትና ሦስትነት ምሥጢር የተገለጠበት ስለሆነ ‹‹ዘመነ አስተርእዮ›› ተብሏል፡፡
በአስተርእዮ ሌሎች በዓሎችም ይጠሩበታል፡፡ ለምሳሌ ቅድስት ድንግል ማርያም ጥር ፳፩ ቀን ነፍሷ ከሥጋዋ ተለይቶ በደመና ተነጥቃ ወደ ገነት በመግባት ለጻድቃን ሰዎችና ለመላእክት በሰማይና በምድር የተሰጣት ጸጋና ክብር የተገለጸበት ዕለት ስለሆነ በዓሉ ‹‹አስተርእዮ ማርያም›› ይባላል፡፡ የኢትዮጵያ ሊቃውንት በዚህ ቃል ሐሳባቸውን ያስተባብራሉ፡፡ ቅዱስ ያሬድ አምላክ በሥጋ ከድንግል መወለዱን በዚህ አካለ መጠን ለዓለም መገለጡን አስተርእዮ ብሎ ሲናገር፤ አባ ጽጌ ብርሃን ደግሞ በማኅሌተ ጽጌ ‹እግዚአብሔር ጽጌ ትንቢት ለቢሶ ሥጋኪ ሥጋ ዚአነ፤ አመ አስተርአየ በምድር ወተአምረ ለነ፤ ንዌድሰኪ እንዘ ንብል ምክሐ ዘመድነ፤ ዮም በፍሥሓ ለማርያም እምነ፤ አስተርእዮ በሰማይ ኮነ፤ የትንቢት አበባ እግዚአብሔር እኛን ሥጋ የሆነውን የአንቺን ሥጋ ለብሶ በምድር እንደተገለጠ ለእኛም እንዲታወቅ ድንግል ሆይ የወገናችን መመኪያ ዛሬ ለእናታችን ለቅድስት ማርያም በሰማይ ፍጹም በደስታ መገለጥ ሆነ እያልን እናመሰግናለን›› ብሏል፡፡ ዳዊትም እንዲህ አለ ‹‹በከመ ሰማዕነ ከማሁ ርኢነ፤ እንደ ሰማን እንዲሁ አየን››፡፡ (መዝ. ፵፯፥፰) በነቢያት ይወለዳል ሲባል የሰማነው በበረት ተጥሎ፤ በጨርቅ ተጠቅልሎ በግዕዘ ሕፃናት ሲያለቅስ ሰማነው እንዲሁም በዮርዳኖስ ሲጠመቅ አየነው፡፡

Читать полностью…

መዓዛ ሃይማኖት በጎ አድራጎትና ጉዞ ማህበር

ምክረ አበው ዘቅዱስ ሳዊሮስ ዘአንጾኪያ

የምወዳችሁ ወንድሞቼ ሆይ ስለ አእምሮአችን ሕጸጽ ጸልዩልን፤ጌታ በፍጹም ቸርነቱ እስከ መጨረሻ እስትንፋስ ፍጻሜ ድረስ በቀናች ሃይማኖት ያጽናን ዘንድ ተስፋችን ይህ ብቻ ነው፤ለአብ ለወልድ ለመንፈስ ቅዱስ ለዘለዓለሙ በእውነት ክብር ምስጋና ይገባቸዋል  አሜን
    
መልካም ዕለተ ሰኞ

Читать полностью…

መዓዛ ሃይማኖት በጎ አድራጎትና ጉዞ ማህበር

ታላቅ መንፈሳዊ ጉባኤ በቡራዩ ክ/ከተማ የጠሮ መካነ ቅዱሳን  አቡነ ገብረ መንፈስ ቅዱስ ወቅድስት አርሴማ ቤተክርስቲያን  የገቢ ማሳሰቢያ
ጉባኤው የሚከናወንበት ቦታ: መንበረ ጸባኦት ቅድስት ሥላሴ ቤተክርስቲያን አዳራሽ (አራት ኪሎ)
የጉባኤ ቀን : መጋቢት 15/2016 ዓ.ም

መግቢያ ዋጋ : 100 ብር ብቻ

የመንፈሳዊ ጉባኤውን ትኬት የሚፈልጉ ከሆነ ይደውሉ፡፡        0907610076 0960029538   
ባሉበት ትኬቱ እንዲደርሶ እናደርጋለን፡፡ ሰብሰብ አድርገው ቢገዙ ይበረታታል! እናመሰግናለን

Читать полностью…

መዓዛ ሃይማኖት በጎ አድራጎትና ጉዞ ማህበር

ስንክሳር ዘወርሃ ጥር አሥራ ዘጠኝ(፲፱)
/channel/meazahaymanot

Читать полностью…

መዓዛ ሃይማኖት በጎ አድራጎትና ጉዞ ማህበር

ዓውደ ስብከት

መምህር፣ቀሲስ ህብረት፣የሺጥላ ።
የትምህርቱ ርዕስ =የቅርብ አምላክ ።ትንቢተ ኤርሚያስ 23፣23
የእግዚአብሔር ቃል ለሁሉ ይዳረስ ዘንድ ጸልዩ! ሌሎች እንዲሰሙት Share ያድርጉ
👇👇👇👇👇
@meazahaymanot

Читать полностью…

መዓዛ ሃይማኖት በጎ አድራጎትና ጉዞ ማህበር

ታላቅ መንፈሳዊ ጉባኤ በቡራዩ ክ/ከተማ የጠሮ መካነ ቅዱሳን  አቡነ ገብረ መንፈስ ቅዱስ ወቅድስት አርሴማ ቤተክርስቲያን  የገቢ ማሳሰቢያ
ጉባኤው የሚከናወንበት ቦታ: መንበረ ጸባኦት ቅድስት ሥላሴ ቤተክርስቲያን አዳራሽ (አራት ኪሎ)
የጉባኤ ቀን : መጋቢት 15/2016 ዓ.ም

መግቢያ ዋጋ : 100 ብር ብቻ

የመንፈሳዊ ጉባኤውን ትኬት የሚፈልጉ ከሆነ ይደውሉ፡፡ 0907610076 0960029538
ባሉበት ትኬቱ እንዲደርሶ እናደርጋለን፡፡ ሰብሰብ አድርገው ቢገዙ ይበረታታል! እናመሰግናለን

Читать полностью…

መዓዛ ሃይማኖት በጎ አድራጎትና ጉዞ ማህበር

ስንክሳር ዘወርሃ ጥር አሥራ ሰባት(፲፯)
/channel/meazahaymanot

Читать полностью…

መዓዛ ሃይማኖት በጎ አድራጎትና ጉዞ ማህበር

ስንክሳር ዘወርሃ ጥር አሥራ ስድስት(፲፮)
/channel/meazahaymanot

Читать полностью…

መዓዛ ሃይማኖት በጎ አድራጎትና ጉዞ ማህበር

ስንክሳር ዘወርሃ ጥር አሥራ አምስት(፲፭)
/channel/meazahaymanot

Читать полностью…

መዓዛ ሃይማኖት በጎ አድራጎትና ጉዞ ማህበር

በስመአብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ አሐዱ አምላክ አሜን።

**በዛሬው ዕለት(ጥር 14) ታላቋ ሰማዕት ቅድስት ሙሕራኤል(መህራቲ) በሰማዕትነት አረፈች።

በመከራ እና በኃዘን ውስጥ ብንሆንም ነገር ግን እጅግ የምወዳትን የታላቋን ሰማዕት የቅድስት ሙሕራኤልን የተቀደሰ የሰማዕትነት ታሪክ እንብባችሁ በመንፈሳዊ ደስታ ደስ ይበላችሁ።

ታላቋ ሰማዕት ቅድስት ሙሕራኤል የተወለደችው በግብጽ አገር ጣሙህ በሚባል ከተማ ነው። እናትና አባቷ የተቀደሱ እና የተባረኩ እግዚአብሔርን የሚፈሩ ናቸው። አባቷ ካህን ነው ስሙ ዮሐንስ ይባላል እናቷ ኢላርያ ትባላለች።

እናትና አባቷ ልጅ እንዲሰጣቸው አብዝተው ይለምኑ ነበር እግዚአብሔርም ልመናቸውን ሰምቶ ወር በገባ በ 21 ቀን አምላክን በወለደች በእመቤታችን ማርያም ቀን ታላቅ ራዕይን አዩ።

** ባዩት ራዕይ እጅግ ተደነቁ ደስም አላቸው እግዚአብሔርም አመሰገኑት ።ቅድስት ሙህራኤል በተወለደች ጊዜ ጎረቤት ዘመድ ሁሉ እጅግ በጣም ተደሰቱ እንዲሁም ለእግዚአብሔር ምስጋናን አቀረቡ።

ከ3 ዓመት በኋላ የቅድስት ሙሕራኤል ወንድም ታላቁ ሰማዕት ቅዱስ አባሑር ተወለደ((አባሑር ማለት ካህን ወይም ቄስ አይደለም በግብጽ አገር "አባኖብ" "አባሑር" ብሎ ልጆችን መሰየም የተለመደ ነው ሲጠራም አንድላይ "አባሑር" ነው የሚጠራው እንጂ እንደ ካህናት አጠራር "አባ ሑር" ተብሎ ተለያይቶ አይጠራም ))።

** ቅድስት ሙሕራኤል በመንፈሳዊ ሥርዓት በመልካም አስተዳደግ አደገች።ሁል ጊዜም ወደ ቤተክርስትያን ሄዳ ቅዱስ ቁርባን ትቀበል ነበር እንዲሁም በመኝታ ቤቷ ቆልፋ ትጸልይ ነበር አንዳንዴም የአካባቢውን ሕጻናት መዝሙረ ዳዊትና የቤተክርስትያን ሥርዓት ሰብስባ ታስተምር ነበር ገና በልጅነቷ የምትበላው ምግብ ደረቅ ዳቦ እና ጨው ነበር ። የመንደሩ ሰዎች ሁሉ ይወዷት ያከብሯት ነበር። በዘመኑ ጨካኙ ንጉስ ዲዮቅልጥያኖስ ተነስቶ ነበርና ብዙ ክርስትያኖች ሰማዕትነትን ይቀበሉ ነበር።

**ታላቁ ሰማዕት ቅዱስ ኤሲ ወደ እስክንድርያ ለንግድ ሄደ ሄዶም የጨካኙ ንጉስ አዋጅ በክርስትያኖች ላይ ሲፈጸም ባየ ጊዜ አብሮ ሰማዕትነት ለመቀበል ክርስትያኖችን ተቀላቀለ እህቱም ታላቋ ሰማዕት ቅድስት ታክላ በህልሟ ወንድሟ ታላቅ ሰማዕት እንደሚሆን እግዚአብሔር ገለጠላትና ተቻኩላ እና ደንግጣ ወደ እስክንድርያ እሄዳለሁ ልብሴን አዘጋጂ ብላ አገልጋይዋን ነገረቻት አገልጋይዋም አዘጋጀች ።

**ወደ እስክንድርያ የሚሄድ ጀልባ ስታፈላልግ በውስጡ ሁለት ሴት የተቀመጡበት እና ከግራ እና ቀኝ ሁለት ጠባቂዎች የቆሙበት አንድ ጀልባ አገኘች ወደ ጀልባውም ገባችና ምድራዊ ሴቶች መስላቸው "አመሰግናለሁ ስለጠበቃችሁም፤ በጣም ተቻኩዬ ነበር" ብላ ሁለቱን ሴቶች አመሰገነቻቸው ከዚያም ከሁለቱ ሴቶች አንደኛዋ ፊቷ ከጸሐይ ይልቅ ማብራት ጀመረ ቅድስት ታክላም ደነገጠች ማን መሆኗንም አወቀች ጮክ ብላም "የጌታዬ እናት እመቤቴ አሁን በሰማይ ነው ያለነው እንዴ?!" አለች እመቤታችንም "አዎ እኔ ነኝ አሁን በምድር ላይ ነን ነገር ግን በሰማያዊው የልጄ የሰርግ ድግስ አንቺን ለልጄ ሙሽርነት አጭቼሻለሁ እንደ ወንድምሽ አንቺም ሰማዕት ሆነሽ የክብር አክሊል ትሸለሚያለሽ።" አለቻት ቅድስት ታክላም "የጌታዬ እናት እመቤቴ ሆይ ወንደሜ ሰማዕት ከመሆኑ በፊት በምድር ላይ በሕይወት አገኘው ይሆን? እንዲሆም ከአጠገብሽ የተቀመጠችው ሴትስ ማን ነች እዛ እና እዚህ የቆሙት ማን ናቸው?" ብላ እመቤታችንን ጠየቀቻት እመቤታችንም " አዎ ወንድምሽ ሰማዕት ከመሆኑ በፊት በሕይወት ታገኝዋለሽ።"
ብላ እመቤታችን አጠገቧ ወደ ተቀመጠችው ሴት ዘወር አለች ያቺ ሴት ለቅድስት ታክላ "እኔ ኤልሳቤጥ የመጥምቁ ዮሐንስ እናት ነኝ" አለቻት እመቤታችንም መልሳ ለቅድስት ታክላ "በግራ እና በቀኝ ያሉት የመላዕክት አለቆች ሚካኤልና ገብርኤል ናቸው" አለቻት ቅድስት ታክላም እጅግ ተደሰተች።

**እመቤታችን ታላቋ የመጥምቁ ዮሐንስ እናት ቅድስት ኤልሳቤጥን እና ታላቋ ሰማዕት ቅድስት ታክላን ይዛ ከጀልባው ወረደች የወረደችው ከእስክድርያ ከመድረሳቸው በፊት "ጣሙህ" የሚባል አገር ወረዱ ይህም ታላቋ ሰማዕት ቅድስት ሙህራኤል ያለችበት አገር ነው። ከዚያም እመቤታችን ወደ ቅድስት ሙህራኤል ቤት ሄዳ አንኳኳች የቅድስት ሙሕራኤል አባት ከፈተና "እመቤቶች ምን ልርዳችሁ አላቸው" አሁንም የጌታ እናት ፊቷ ከጸሐይ የበለጠ ባበራ ጊዜ "እመቤቴ የጌታዬ እናት ብሎ ጮኸ" ከዚያም በፍርሃትና በደስታ " ግቡ ግቡ ቤታችን አበራች ተባረከች"ብሎ አስገባቸው ቀጥሎም የጌታዬ እናት "እኔን ልትጎበኚ መጣሽ ይህ ድንቅና ዕጹብ ነው" ብሎ እመቤታችንን አመሰገነ እመቤታችንም በፈገግታ "ሙሕራኤል የታለች" አለችው እርሱም "እመቤቴ ሆይ ጸሎት እየጸለየች ነው ልጥራት?!" አለ እርሷም "አትጥራት ጸሎቷን ትቀጥል" አለችው(እመቤታችን ቅድስት ሙሕራኤል ያለችበትን ሳታውቅ ቀርታ ሳይሆን የጸሎትን ታላቅነት ልታሳይ ስለፈለገች ለእኛ ጸሎት አቋርጠን ሰውን ለምናነጋግረው ትምሕርት እንዲሆነ ነው)።

እመቤታችንም " ልጃችሁን ለልጄ ሙሽራ አድርጌ አጭቻታለሁ በልጄ ቅዱስ ስም ሰማዕት ትሆናለች " ብላ ለአባቷ ነገረችው እርሱም "እግዚአብሔር የተመሰገነ ይሁን አንቺም እመቤቴ ምስጋና ይድረስሽ እመቤቴ ሆይ ልጄ በሰማዕትነት ካረፈች በኋላ አካሏ እዚህ የተወለደችበት አገር ነው የሚያርፈው?!" አላት "እርሷም አዎ እዚህ ነው የሚያርፈው በዚህም ቃል ኪዳን እሰጥሐለሁ አለችው ።" ቅድስት ሙህራኤል ጸሎቷን ፈጽማ ይህን ሁሉ ንግግር ሰምታ እግዚአብሔርን አመሰገነች የጌታንም እናት አከበረች። ከዚያም ባርካቸው እመቤታችን ቅድስት ኤልሳቤጥ እና ቅድስት ታክላ ተሰወሩ ።

**አንድ ቀን ቅድስት ሙሕራኤል ከወንድሟ ከቅዱስ አባሑር ጋር ውሃ ልትቀዳ ወደ ወንዝ ወረደች በጀልባ ላይ አንዲት ኢ-አማኒት ሴት ጽንሷ ለስድስት ቀን ያህል አልወለድ ብሎ ተቸግራ ነበር በምጥ የምትሰቃየው ሴት እናት ተጨንቃ የክርስትያን ቄስ ጥሩ ብላ ጮኸች ቄሱ እስኪመጣ ልጄ ልትሞት ነው ብላ ተጨነቀች።የሴትየዋን ጭንቀት ያየችው ቅድስት ሙሕራኤል ከወንድሟ ጋር ወደ እግዚአብሔር መጸለይ ጀመረች ያ ስድስት ቀን ሙሉ አልወለድ ያለው ልጅ ወዲያወኑ ተወለደ ከዚያም ቅድስት ሙሕራኤል ከንቱ ውዳሴ ሸሽታ ውሃውን ሳትቀዳ ወደ ቤቷ ሮጣ ሄደች። ያደረገችው ተዓምርም አገሩ ሁሉ ሰማ ብዙ የታመሙ ሰዎች ወደ እርሷ እየመጡ ይፈወሱ ነበር።

**ከዚህ በኋላ እመቤታችን በሌሊት ተገልጣላት ወደ "የምወድሽ ልጄ ሙሕራኤል ወደ እኛ የምትመጭበት ጊዜ ስለደረሰ በቀትር ከቅድስት ኤልሳቤጥና ከስድስት ደናግላን ጋር በወንዙ ዳር እጠብቅሻለሁ ነይ" አለቻት። ቀትር በሆነ ጊዜ ሰማዕቷ ቅድስት ሙሕራኤል ወደ ወንዙ ዳር የውሃ መቅጃዋን ይዛ ሄደች በደረሰች ጊዜ በጀልባ ላይ አንድ ሊቀጳጳስ ከ ብዙ ካህናትና ዲያቆናት ጋር ታስሮ አገኘችው " ብጹዕ አባቴ ሆይ ወዴት ትሄዳለህ?!" አለችው እርሱም "ልጄ ኃጥያቴ በዝቶ ይቅር ወደ ምባልበት ቦታ እየሄድኩ ነው።" አላት ይህንን ባላት ጊዜ እመቤታችን ከቅድስት ኤልሳቤጥና ከስድስት ደናግላን ጋር በሰማይ ተገልጣ አየቻት ። ቅድስት ሙህራኤልም የወታደሮቹን አለቃ እኔንም እሰረኝ እና ውሰደኝ አለችው እርሱም አስሮ ያለርህራሄ ወደ ጀልባ ወስዶ ወረወራት ከዚያም ወደ አገረ ገዢው ፊት ቀርበው ክርስትያን መሆናቸውን መሰከሩ ።

Читать полностью…

መዓዛ ሃይማኖት በጎ አድራጎትና ጉዞ ማህበር

🔴 #አዲስ_ዝማሬ ሊቀ መዘምራን ቴዎድሮስ ዮሴፍ

Читать полностью…

መዓዛ ሃይማኖት በጎ አድራጎትና ጉዞ ማህበር

የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተክርስቲያን ሥርዓት፣ ትውፊት እና አስተምህሮ  የጠበቁ ትምህርቶች እና መዝሙሮች እንዲሁም ወረቦችን  ማግኘት የምትፈልጉ የመዓዛ ሃይማኖትን የዩቲዩብ ቻናል ሰብስክራይብ በማድረግ ማኅበሩ ለሚያከናውናቸው አገልግሎቶች አጋዥ እንድትሆኑ በአክብሮት እንጋብዛለን።

https://m.youtube.com/channel/UCKGh-U7U7pnvFUIEGXPOnNw

Читать полностью…

መዓዛ ሃይማኖት በጎ አድራጎትና ጉዞ ማህበር

ስንክሳር ዘወርሃ ጥር ሃያ ሁለት(፳፪)
/channel/meazahaymanot

Читать полностью…

መዓዛ ሃይማኖት በጎ አድራጎትና ጉዞ ማህበር

✞ ሞትማ_ለመዋቲ_ይገባል ✞

ሞትማ ለመዋቲ ይገባል ይገባል(፪)
የድንግል አሟሟት እጅጉን ይደንቃል(፪)

ለልጇ ስትነግር ሞት እንደምትፈራ(፪)
ወሰዷት በሐሴት መላእክተ ሐራ(፪)
ጭንቀቱ ሳይገጥማት ሳታስብ ድንገት(፪)
እንደ እንቅልፍ ወሰዳት ያመልአከ ሞት፪)

         /አዝ = = = = =

ይገርማል ይደንቃል የድንግል ፍልሰታ(፪)
በምስጋና አረገች ከልጇ ተጠርታ
በይባቤ አረገች ከልጇ ተጠርታ
እያሸበሸቡ መላእክተ ሰማይ(፪)
ወስደው አቀረቧት ከልጇ መንበር ላይ(፪)

/አዝ = = = = =

ሱባኤ እንደገቡ እንደ ሐዋርያት(፪)
እኔም ከቤት ወጣሁ አንቺኑ በመሻት(፪)
ትንሳኤሽን በክብር እንዳሳየሻቸው(፪)
እኔንም ለዚህ አብቂኝ ብርሃንሽን እንዳየው(፪)

👉ሊቀ መዘምራን ኪነጥበብ ወልደቂርቆስ

@meazahaymanot

Читать полностью…

መዓዛ ሃይማኖት በጎ አድራጎትና ጉዞ ማህበር

ስንክሳር ዘወርሃ ጥር ሃያ አንድ(፳፩)
/channel/meazahaymanot

Читать полностью…

መዓዛ ሃይማኖት በጎ አድራጎትና ጉዞ ማህበር

አስተርዮ ማለት ምን ማለት ነው?

Читать полностью…

መዓዛ ሃይማኖት በጎ አድራጎትና ጉዞ ማህበር

ስንክሳር ዘወርሃ ጥር ሃያ(፳)
/channel/meazahaymanot

Читать полностью…

መዓዛ ሃይማኖት በጎ አድራጎትና ጉዞ ማህበር

ምክረ አበው  ዘቅዱስ አግናጥዮስ

=>  ጻድቅ የሆነ ሰው የራሱ ከሳሽ ራሱ ነው።እንድትጸድቅ በመጀመሪያ በደልህን ተናገር

=>  ከክፉዎች ጋር ሕብረት  ያለው ማንም ሰው ደግ ሊባል አይችልም።

=>  ራስን ከፍ ከፍ ማድረግን ትዕቢትን ሌሎችን መናቅን ከእናንተ ብታርቁ ከእግዚአብሔር ጋር ፍፁም አንድነትን ታገኛላችሁ

መልካም ቀን

Читать полностью…

መዓዛ ሃይማኖት በጎ አድራጎትና ጉዞ ማህበር

ታላቅ መንፈሳዊ ጉባኤ በቡራዩ ክ/ከተማ የጠሮ መካነ ቅዱሳን  አቡነ ገብረ መንፈስ ቅዱስ ወቅድስት አርሴማ ቤተክርስቲያን  የገቢ ማሳሰቢያ
ጉባኤው የሚከናወንበት ቦታ: መንበረ ጸባኦት ቅድስት ሥላሴ ቤተክርስቲያን አዳራሽ (አራት ኪሎ)
የጉባኤ ቀን : መጋቢት 15/2016 ዓ.ም

መግቢያ ዋጋ : 100 ብር ብቻ

የመንፈሳዊ ጉባኤውን ትኬት የሚፈልጉ ከሆነ ይደውሉ፡፡        0907610076 0960029538   
ባሉበት ትኬቱ እንዲደርሶ እናደርጋለን፡፡ ሰብሰብ አድርገው ቢገዙ ይበረታታል! እናመሰግናለን

Читать полностью…

መዓዛ ሃይማኖት በጎ አድራጎትና ጉዞ ማህበር

ስንክሳር ዘወርሃ ጥር አሥራ ስምንት(፲፰)
/channel/meazahaymanot

Читать полностью…

መዓዛ ሃይማኖት በጎ አድራጎትና ጉዞ ማህበር

#ዓውደ_ስብከት

ለንሰሐ የሚገባ ፍሬ አድርጉ


@meazahaymanot

Читать полностью…

መዓዛ ሃይማኖት በጎ አድራጎትና ጉዞ ማህበር

ዓውደ ስብከት

🛑የኃጥያተኞች መንገድ ትጠፋለች || እጅግ ድንቅ ትምህርት በርእሰ ሊቃውንት አባ ገብረኪዳን ግርማ

Читать полностью…

መዓዛ ሃይማኖት በጎ አድራጎትና ጉዞ ማህበር

የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተክርስቲያን ሥርዓት፣ ትውፊት እና አስተምህሮ  የጠበቁ ትምህርቶች እና መዝሙሮች እንዲሁም ወረቦችን እንዲሁም መንፈሳዊ ቦታዎችን መጎብኘት    የምትፈልጉ join በማለት ይቀላቀሉን ማኅበሩ ለሚያከናውናቸው አገልግሎቶች አጋዥ እንድትሆኑ በአክብሮት እንጋብዛለን።

/channel/meazahaymanot


Share

Читать полностью…

መዓዛ ሃይማኖት በጎ አድራጎትና ጉዞ ማህበር

በመጀመርያ አገረ ገዢው የሰማዕቷን የቅድስት ሙሕራኤል ልጅነት አይቶ ትንሽ ልጅ ስለሆነች በቀላሉ በሥጦታዎች አታሎ ለጣዖት አንድትሰግድ ለማድረግ ሞክሮ ነበር ነገር ግን ታላቋ ሰማዕት ቅድስት ሙሕራኤል በእምነቷ ጸንታ ጣዖታቱን አቃለለቻቸው።

**ትዕግስቱ ያለቀው አገረ ገዢ በታላቅ ቁጣ ሆኖ እንዲያሰቃዯት ለወታደሮቹ ትዕዛዝ አስተላለፈ የቅድስት ሙሕራኤል የሚያምር ፊቷን በስለት ፈተፈቱት ገረፏት በብዙ ስቃዮች አሰቃዩአት ነገር ግን የጌታ መልዓክ እየመጣ ይፈውሳት።በዚህ የተናደደው አገረ ገዢ እንዴት የ12 ዓመት ልጅ ታሸንፈኛለች ብሎ ብዙ መርዛማ እባቦች በሞሉበት ሳጥን ከተዋት ከወታደሮች ጋር አድርገው በጀልባ ወደ ሌላ አገር እንዲልኳት አዘዘ ነገር ግን በዚያ በታሸገ ሳጥን ውስጥ ለብዙ ቀናት ምንም ሳትሆን ለእግዚአብሐር መዝሙር እየዘመረች ቆየች። ያንን ሳጥን የሚጠብቁት ወታደሮች እስኪደነቁ ድረስ መዘመሯን አላቋረጠችም ነበር።

** ከዚህም በኋላ ጌታችን አምላካችን ኢየሱስ ክርስቶስ ተገለጠላትና " የምወድሽ ልጄ ሙሕራኤል ሆይ ሰላም ላንቺ ይሁን ። "ስለተቀበልሽው መከራ ዋጋሽ በሰማይ እጅግ ታላቅ ነው። የከበረች ወላጅ እናቴ ማርያም ለአባትሽ ቃልኪዳን እንደገባችው ሥጋሽ በተወለድሽበት አገር ያርፋል በስምሽ ቤተክርስትያን ያነጸ እኔ ኃጥያቱን እደመስስለታለሁ በሰማያትም ታላቅ አዳራሽ አሰጠዋለሁ የተቀደሰ የተጋድሎሽንም ታሪክ የጻፈም እኔ በሰማያዊት መዝገብ ላይ የእርሱንም የቤተሰቡንም ስም እጽፍለታለሁ በስምሽ በተሰየመው ቤተክርስትያን የሚያገለግሉ ካህናትና ዲያቆናት የተባረኩ ይሆናሉ በንጽሕና እና በቅድስና ይኖራሉ ያገለግላሉ ። የተራበውን የተጠማውን ያበላ ያጠጣ የተቸገውን ልብስ ያለበሰ ዋጋውን በሰማያት እከፍለዋለሁ።" ብሎ ቃል ኪዳን ሰጣትና ወደ ሰማይ ዓረገ። ቅድስት ሙሕራኤል በሰላም አረፈች ሥጋዋም ወደ ጣሙህ ተወሰደ እና በታላቅ ክብር በቤተክርስትያን አሳረፉት።

** የዘጠኝ ዓመት ዕድሜ የሆነው ወንድሟ ቅዱስ አባሑር የእህቱን በሰማዕትነት ማረፍ ባየ ጊዜ " ጌታ ሆይ እህቴን በሰማዕትነት እንዳሳረፍካትና እንደመረጥካት ሁሉ እኔንም ምረጠኝ" ብሎ ጸለየ ጌታም ጸሎቱን ሰምቶ እህቱ ሰማዕትነት ወደ ተቀበለችበት አገር ሄዶ ሰማዕትነት ተቀብሎ ቅዱስ አካሉ እህቱ ጋር አረፈ። የታላቋ ሰማዕት የቅድስት ሙሕራኤል ቅዱስ አካል ታላቅ ተዓምራትን የሚያደርግ ሲሆን ብዙ ህሙማን እየተፈወሱ እስከዛሬ ድረስ በግብጽ አገር አለ።

ለእግዚአብሔር ምስጋና ይሁን እኛንም በታላቋ ሰማዕት በቅድስት ሙሕራኤል እና በታላቁ ሰማዕት በቅዱስ አባሑር ጸሎት ይማረን በረከታቸውም ለዘለዓለሙ ጸንቶ ከእኛ ጋር ይኑር።አሜን። አሜን።አሜን።

Читать полностью…

መዓዛ ሃይማኖት በጎ አድራጎትና ጉዞ ማህበር

ሰማዕቷ ቅድስት ምሕራኤል (ሙራኤል)

Читать полностью…

መዓዛ ሃይማኖት በጎ አድራጎትና ጉዞ ማህበር

አለቀብኝ ብዬ

አለቀብኝ ብዬ እጄ ባዶ ሆነ
ብዬ ሳዝን የሚሞላው አለ
ባዶ ጎተራዬን በፍሬ የሞላው
እግዚአብሔር ከአባትም በላይ ነው/2/
አዝ-----
የማይጥል የማይከዳ
የሚያዝን የሚረዳ
ፍቅር ነው የማይጠላ
እግዚአብሔር ነው ከለላ/2/
አዝ-----
ጉልበታም ነው ክንዱ ጽኑ
ድንቅ የሚያደርግ በየቀኑ
ይሸከማል ነጋ ጠባ
አይቆረቁር የእርሱ ጀርባ/2/
አዝ-----
በእረፍት ውሃ እየመራኝ
በለምለም መስክ አሰማራኝ
አልጨነቅ ለሚመጣው
የኔ ጉዳይ ከሰማይ ነው/2/
አዝ-----
በእርሱ ሞልቷል ማሰሮዬ
አንዳች አይጎድል ማድጋዬ
የእርሱ ቁጥር ቀኑ ሲደርስ
ያደርገዋል ሁሉን አዲስ/2/
አዝ-----
በእርሱ ሞልቷል ማሰሮዬ
አንዳች አይጎድል ማድጋዬ
የእርሱ ቁጥር ቀኑ ሲደርስ
ያደርገዋል ሁሉን አዲስ/2/



🙏🙏አዲስ ዝማሬ በሊቀመዘምራን ቴዎድሮስ ዮሴፍ🙏🙏

Читать полностью…
Subscribe to a channel