ትኩረት ለ ትግራይ ህዝብ‼️
የትግራይ ህዝብ በረሀብ ስቃይ ውስጥ ይገኛል‼️
↘️ የትግራይ ህዝብ ከ4.5 ሚሊዮን በላይ በርሀብ አደጋ ውስጥ ነው!
↘️ የትግራይ ህዝብ አስቸኳይ እርዳታ ካልደረሰ በሚቀጥሉት ቀናት በርሀብ የሞተ ምስል ልናይ እንገደዳለን!
# ኢትዮጵያዊነት_ከዘር_በላይ_ነው !!!
#SHARE
#EthioTelecom
በመቐለ ከተማ እና በማይጨው የሞባይል ድምፅ አገልግሎት ማስጀመር እንደቻለ ኢትዮ ቴሌኮም ማምሻውን ገልጿል።
በመቐለ የሞባይል ድምፅ አገልግሎት የተጀመረው "አማራጭ ኃይል" በመጠቀም ከመሆኑ አንፃር የአገልግሎት መቆራረጥ ሊየጋጥም ይችላል፤ ደንበኞችም ይህን ይገንዘቡ ብሏል።
ኢትዮ ቴሌኮም የጥገና እና የመሰረተ ልማቶች መልሶ የማቋቋም ስራዎች በማከናወን ከኃይል አቅርቦት ጋር በተገናኘ ከኢትዮጵያ ኤላክትሪክ ኃይል ጋር በመስራት የተሟላ የቴሌኮም አገልግሎት ለመስጠት ጥረት እያደረገ እንደሆነ አሳውቋል።
* ዝርዝር መረጃው ከላይ ተያይዟል።
@mebreklink
🇪🇹ጎግል ትውልደ ኢትዮጵያዊቷን የ”አርቴፊሻል ኢንተለጀንስ” ተመራማሪ በማሰናበቱ በሰራተኞቹ ተቃውሞ ቀረበበት🇪🇹
👉ጎግል ትውልደ ኢትዮጵያዊቷን የ”አርቴፊሻል ኢንተለጀንስ” ተመራማሪ ዶክተር ትምኒት ገብሩን በማሰናበቱ በመቶዎቹ የሚቆጠሩ የተቋሙ ሰራተኞች እርምጃውን በመቃወም ግልፅ ደብዳቤ መፃፋቸው ተነገረ።
👉ትምኒት ገብሩ በጎግል የ”አርቴፊሻል ኢንተለጀንስ” ስነ ምግባር ጥናት እና የሰዎችን ማንነት በፊታቸው የሚለየው ቴክኖሎጂ በአተገባበሩ ላይ ያለውን የዘር መድሎ በማጋለጧ ትታወቃለች።
👉ከጎግል እስከተሰናበተችበት ጊዜ ድረስ ትምኒት ገብሩ የተቋሙን “አርቴፊሻል ኢንተለጀንስ” ስነ ምግባር ቡድን አባል ነበረች።
👉ትውልደ ኢትዮጵያዊቷ ትምኒት ባዘጋጀችው የጥናት ወረቀት እና ጎግል ሰራተኞችን በተለይ ከፆታ እና ከቀለም ጋር ተያይዞ የሚያስተናግድበትን መንገድ በተመለከተ ለባልደረቦቿ ያላትን ፍርሃት ከገለፀች በኋላ ተቋሙን እንድትለቅ እንደተገደደች ተናግራለች።
👉ጎግል ዶክተር ትምኒት ካበረከተችው አስተዋፅኦ እና ካላት ልምድ አንፃር ሊንከባከበት ሲገባ የዘር መድሎ፣ ጥናቷን ሳንሱር በማድረግ ብሎም ከስራ እድትሰናበት አድርጓታል ሲሉ ሰራተኞች በፃፉት ደብዳቤ ላይ መግለጻቸውን ኤን ፒ አር በዘገባው ላይ አስፍሯል።
👉ትምኒት ከሌሎች ባለሙያዎች ጋር በመሆን ያዘጋጀችው ጥናት ጎግልን ጨምሮ ሌሎች የቴክኖሎጂ ኩባንያዎች የሚጠቀሟቸው “አርቴፊሻል ኢንተለጀንሶች” በስነ ምግባር እና በአካባቢ ላይ የሚያሳድሩትን ተፅዕኖ የሚያመለክት መሆኑ ተጠቁሟል።
👉ትውልደ ኢትዮጵያዊቷ በዘርፉ ካሉ ውስን ጥቁር ሴት ባለሙያዎች መካከል አንደኛዋ ናት፡፡
@mebreklink
#NBE
ከነገ ጀምሮ በትግራይ ክልል ባሉ ባንኮች አካውንት የከፈቱና ከትግራይ ክልል ውጭ ያሉ ደንበኞች በያሉበት የሀገሪቱ አካባቢዎች ሂሳባቸውን ማንቀሳቀስ እንዲችሉ መፈቀዱ እና ለባንኮችም ይህ መመሪያ መተላለፉን NBE ዛሬ አሳውቋል።
ይህ በፌዴራል ጠቅላይ አቃቤ ህግ በወንጀል ተጠርጥረው ሂሳባቸው እንዳይንቀሳቀስ የተደረጉ ደንበኞችን የሚመለከት አይደለም።
በሌላ በኩል ፦
የፀጥታ ሁኔታ ለባንኮች አመቺ በሆነባቸው የትግራይ ክልል ከተሞች ባንኮች ተከፍተው ስራ እንዲጀምሩ ብሄራዊ ባንክ ከሚመለከታቸው አካላት ጋር እየሰራ መሆኑን አስታውቋል። የፀጥታ ሁኔታ አመቺ ባልሆነባቸው የክልሉ ከተሞች ባንኮች ተዘግተው እንደሚቆዩ NBE ለኢቲቪ ገልጿል።
@mebreklink
በአሮጌው የብር ኖት መገበያየት ከነገ ጀምሮ ያበቃል!
በአሮጌው የብር ኖት መገበያየት ከነገ ኅዳር 22 ቀን 2013 ዓ.ም ጀምሮ ያበቃል።የኢትዮጵያ ብሔራዊ ባንክ ከዚህ ቀደም በህዳር 10 ቀን 2013 ዓ.ም ለኢዜአ በላከው መግለጫ እንዳስታወቀው፣ ከነገ ጀምሮ በአሮጌው የብር ኖት መገበያየት አይቻልም።
የአሮጌው ብር ኖት ቅያሬ ታኅሣሥ 6 ቀን 2013 ዓ.ም እንደሚጠናቀቅም የኢትዮጵያ ብሔራዊ ባንክ በወቅቱ መግለጹ ይታወሳል።ከመስከረም 6 ቀን 2013 ዓ.ም አሮጌ የብር ኖቶች በአዲስ የብር ኖቶች እየተቀየሩ መሆኑ ይታወቃል።
@mebreklink
የኢትዮጵያ አየር መንገድ የኮቪድ-19 ክትባትን ለማጓጓዝና ለማሰራጨት 21 አውሮፕላኖች ማዘጋጀቱን ገለጸ !
የኢትዮጵያ አየር መንገድ ግሩፕ የካርጎና ሎጂስቲክ አገልግሎት ማኔጂንግ ዳይሬክተር አቶ ፍጹም አባዲ ለኢዜአ እንደገለጹት፤ የኮቪድ-19 ክትባትን ለማከማቸት የሚያስችል መሰረተ ልማት ተሟልቷል። ማጓጓዙንና ማሰራጨቱን ስኬታማ ለማድረግም አሰራር መነደፉን ጠቁመዋል።
ክትባቶቹ በባህሪያቸው ቀዝቃዛ ስፍራ የሚፈልጉ በመሆናቸው ይህንን ለማሟላት በቂ የሆነ የመሰረተ ልማት መዘጋጀቱን የጠቆሙት ዳይሬክተሩ፣ የተዘጋጁት 21 አውሮፕላኖችም የክትባቱን ደህንነት በአግባቡ የሚጠብቁ መሆናቸውን አመልክተዋል።
የኢትዮጵያ አየር መንገድ ከዚህ ቀደም የኮቪድ-19 መከላከያ ቁሳቁስ በማሰራጨት ከፍተኛ አስተዋጽኦ ማበርከቱ ይታወቃል።
@mebreklink
ለ8ኛ እና 12ኛ ከፍል ተማሪዎች ቀደም ሲል የተሰጡ ክልላዊ እና ሀገራቀፋዊ ፈተናዎችን በማግኘት በስልክዎ ላይ ለመለማመድ የሚከተሉትን ቅደም ተከተሎች በአግባቡ ይተግብሩ፡፡
1.👆ከላይ ያለውን መተግበርያ ያውርዱ
ከዚያም ከሚመጡት አማራጮች ውስጥ Package installer የሚለውን በመጫን አፕልኬሽኑን ይጫኑ
2.ከዚያም የጫኑትን አፕልኬሽን ሲከፍቱ ከታች ከሚመጣው ውስጥ English የሚለውን በመምረጥ Continue የሚለውን ይምረጡ
3.በመቀጠል ለመጀመሪያ ጊዜ አፕልኬሽኑን የሚጠቀሙ ከሆነ Register የሚለውነ በተን ይጫኑ
4.ከዚያም የሚመጣውን Registration form ይሙሉና Register የሚለውን ይጫኑ
5.በመቀጠል Sign in የሚለውን በመጫን የሚመጣው ፎርም ላይ የተመዘገቡበትን Username and Password ያስገቡ
6.ከዚያም የሚመጣው ፎርም ላይ የክፍል ደረጃና የፈተናውን ዓይነት በመምረጥ ፈተናውን መለማመድ ይቻላል
----------------------------------
#መልካም_የዝግጅት ግዜ
@mebreklink
ለ8ኛ እና 12ኛ ከፍል ተማሪዎች ቀደም ሲል የተሰጡ ክልላዊ እና ሀገራቀፋዊ ፈተናዎችን በማግኘት በስልክዎ ላይ ለመለማመድ የሚከተሉትን ቅደም ተከተሎች በአግባቡ ይተግብሩ፡፡
1.👆ከላይ ያለውን መተግበርያ ያውርዱ
ከዚያም ከሚመጡት አማራጮች ውስጥ Package installer የሚለውን በመጫን አፕልኬሽኑን ይጫኑ
2.ከዚያም የጫኑትን አፕልኬሽን ሲከፍቱ ከታች ከሚመጣው ውስጥ English የሚለውን በመምረጥ Continue የሚለውን ይምረጡ
3.በመቀጠል ለመጀመሪያ ጊዜ አፕልኬሽኑን የሚጠቀሙ ከሆነ Register የሚለውነ በተን ይጫኑ
4.ከዚያም የሚመጣውን Registration form ይሙሉና Register የሚለውን ይጫኑ
5.በመቀጠል Sign in የሚለውን በመጫን የሚመጣው ፎርም ላይ የተመዘገቡበትን Username and Password ያስገቡ
6.ከዚያም የሚመጣው ፎርም ላይ የክፍል ደረጃና የፈተናውን ዓይነት በመምረጥ ፈተናውን መለማመድ ይቻላል
----------------------------------
#መልካም_የዝግጅት ግዜ
/channel/mebreklink/
@mebreklink
Have you checked out Ask Anything Ethiopia yet? It's Ethiopia's first question and answer platform, where you can get answers to your biggest questions from thousands of people! You can join using the link below:
/channel/ask_anything_ethiopia_bot?start=i488204922
የቅድመ ክፍያ የቆጣሪ አገልግሎት ደንበኞች ቅድመ ዝግጅት እንዲያደርጉ የኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ አገልግሎት አሳሰበ
**************
የኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ አገልግሎት የቅድመ ክፍያ የቆጣሪ አገልግሎት ለሚጠቀሙ ደንበኞቹ ከህዳር 05 ቀን 2013 ዓ.ም እስከ ህዳር 07 ቀን 2013 ዓ.ም ድረስ በፊት የነበረው አሰራር ሙሉ በሙሉ ወደ አዲሱ አሰራር ለመቀየር ሲባል የካርድ መሙላትም ሆነ ሌሎች የቅድመ ክፍያ የተመለከቱ አገልግሎቶች እንደማይሰጥ አስታወቀ፡፡
ተቋሙ ጥራት ያለውና በዘመናዊ ቴክኖሎጂ የተደገፈ አገልግሎት ለመስጠት የቅድመ ዝግጅት ሥራዎች እያከናወነ እንደሚገኝ አስታውቋል፡፡
የዚሁ ዝግጅት አካል የሆኑ አንዳንድ ሥራዎች ለማከናወን ሲባል ከጥቅምት 28 ቀን 2013 ዓ.ም እስከ ህዳር 04 ቀን 2013 ዓ.ም ድረስ በሁሉም የአገልግሎት መስጫ ማዕከላት ከኃይል ሽያጭ ወይም ካርድ ከመሙላት ውጭ ሌሎች የቅድመ ክፍያ የተመለከቱ አገልግሎቶች ማለትም የቅድመ ክፍያ ቆጣሪ የማገናኘት፣ የማስተካከል፣ ካርድ የመቀየር ሥራዎች እንደማይከናወኑም አስታውቋል፡፡
https://www.facebook.com/EBCzena/photos/pcb.3846086768756504/3846086025423245/
******************
@mebreklink
ለአትሌት ለተሰንበት ግደይ ድምፅዎን ይስጡ !
ይህን የትዊተር ሊንክ Retweet በማድረግ ለአትሌት ለተሰንበት ግደይ ድምፅ ይስጡ!
በዚህ Retweet ብዙ ቁጥር ያገኘ አትሌት በአለም አትሌቲክስ (World Athletics) "የወሩ ምርጥ ግዜ" አሸናፊ ይሆናል።
https://t.co/fE5sRDWd3j
*******"""""""**********
@mebreklink
ክራይሲስ ግሩፕ በፌዴራል እና በትግራይ ክልል ጉዳይ ፦
• ዓለም አቀፉ ማህብረሰብ ኢትዮጵያ የገባችበት አጣብቂኝ እንዳይባባስ ከፈለጉ ብሔራዊ መግባባት ላይ እንዲደረስ የበኩላቸውን ሚና መወጣት አለባቸው።
• የዩናይትድ ስቴትስ መንግስት እንዲሁም የአውሮፓ ሕብረት የፌደራል መንግስት ከትግራይ መንግስት ጋር ወደ ውይይት እንዲመጣ ጫና መፍጠር አለባቸው።
• የትግራይ ክልል መንግስት የፌደራል መንግስት እንደ ትንኮሳ የሚመለከተውን መግለጫ ማውጣት እንዲያቆም ዓለም አቀፉ ማህበረሰብ ጫና ማሳደር ይኖርበታል።
• ለኢትዮጵያ ቅርብ የሆኑት ቻይና እንዲሁም የባህረ ሰላጤው አገራትም ሁለቱ አካላት ወደ ጠረጴዛ ዙሪያ እንዲመጡ ጫና መፍጠር አለባቸው።
• በሁለቱ አካላት ዘንድ ተሰሚነት ያላቸው የአፍሪካ ሕብረት የወቅቱ ሊቀ መንበር የደቡብ አፍሪካ ፕሬዝደንት ሲሪል ራማፎሳ ወደ ድርድር እንዲመለሱ ጥረት ማድረግ አለባቸው።
* ችግሮቹ መፍትሄ የማያገኙ ከሆነ በአፍሪካ በሕዝብ ቁጥር ሁለተኛ በሆነችው አገር ኢትዮጵያ 'ጦርነት' ተከስቶ ቀውስ ሊከሰት እንደሚችል ሲል ክራይሲስ ግሩፕ ገልጿል። ምንጭ (BBC)
@mebreklink
ለ6ኛው አገራዊ ምርጫ ከታህሳስ እስከ ጥር ባሉት ጊዜያት የመራጮች ምዝገባ እንደሚካሄድ ተገለጸ!
ለ6ኛው አገራዊ ምርጫ ከታህሳስ እስከ ጥር ባሉት ጊዜያት የመራጮች ምዝገባ እንደሚካሄድ የኢትዮጵያ ብሔራዊ ምርጫ ቦርድ አስታወቀ።ቦርዱ ለ6ኛው አገራዊ ምርጫ በሚከናወኑ ዋና ዋና ጉዳዮች ላይ ከሲቪክ እና ከመገናኛ ብዙሃን አባላት ጋር እየመከረ ነው።በምክክር መድረኩ መክፈቻ ላይ የብሔራዊ ምርጫ ቦርድ ሰብሳቢ ወይዘሪት ብርቱካን ሚደቅሳ እንደተናገሩት ከታህሳስ እስከ ጥር ወር 2013 ዓ.ም ለ6ኛው አገራዊ ምርጫ የመራጮች መዝግባ ይካሄዳል።
"ከጥር የመጀመሪያው ሳምንት እስከ የካቲት አጋማሽ ደግሞ የእጩዎች ምዝገባ እንዲሁም ከየካቲት አጋማሽ ጀምሮ የምረጡኝ ቅሰቀሳ ይጀመራል" ሲሉም ተናግረዋል።በምክክር መድረኩ ላይ የምርጫ ጊዜ ሰሌዳ እና በምርጫ ሂደት ስለሚወሰዱ የኮቪድ-19 የጥንቃቄ እርምጃዎችን በተመለከተ ከሲቪክ ማህበራት እና ከመገናኛ ብዙሃን አባላት ጋር በመወያየት ግብዓት ይወሰዳል ተብሏል።በተጨማሪም ሲቪክ ማህበራት አና መገናኛ ብዙሃንን የሚመለከቱ ዋና ዋና የምርጫ እንቅስቃሴዎች እና ዝግጅቶች ላይ ውይይት እንደሚደረግም ነው የተገለጸው።
እንደ ወይዘሪት ብርቱካን ገለጻ፣ መድረኩ የተዘጋጀው የሲቪክ ማህበራት እና የመገናኛ ብዙሃን የሚያነሷቸውን ሀሳቦች በመጨረሻ ለሚወጣው የምርጫ ጊዜ ሰለዳ እና የአፈጻጸም ዕቅድ ላይ በግብዓትነት ለመጠቀም ታስቦ ነው።በመድረኩ በምርጫ ሂደት የሚተገበሩ የኮቪድ-19 የጥንቃቄ መመሪያ መነሻ ሀሳቦች ቀርበው ውይይት ይደረግባቸዋል።በተጨማሪም ዋና ዋና የምርጫ ተግባራት በሚተገበሩበት ጊዜ የሲቪክ ማህበራት እና የመገናኛ ብዙሃን ያላቸውን ሚና የተመለከቱና ተያያዥ ጉዳዮች ላይ ውይይት ያደረጋል ተብሎ ይጠበቃል።
[ኢዜአ]
@mebreklink
ከድሬድዋ በቅርብ ርቀት ላይ የተገነባ ቄራ ተመረቀ!
ከድሬድዋ ከተማ 5 ኪ.ሜ ርቀት ላይ የእንስሳት ሥጋ ምርትን ለውጭ ገበያ ለማቅረብ የሚያስችል ቄራ ተገንብቶ ጠ/ሚ ዐብይ አህመድ በተገኙበት ተመርቆ ተከፍቷል።
ይህ ቄራ በቀን ከ100 በላይ ግመል እና ከ3000 በላይ በግ እና ፍየል በማረድ አቀነባብሮ ለውጭ ገበያ ለማቅረብ የሚያስችል አቅም እንዳለው ጠ/ሚ ዐብይ አስረድተዋል።
''ይህም በአካባቢው ያለውን ሰፊ የቁም እንስሳት ሀብት በመጠቀም የውጭ ምንዛሬ ለማግኘት የሚያስችል ከመሆኑ ባለፈ ለአካባቢው ማህበረሰብ የስራ እድል ለመፍጠር ያግዛል።'' ሲሉ ነው የገለጹት።
@mebreklink
የመንግሥት አገልግሎት መስጠት የሚያስችሉ ዲጅታል የፈጠራ ሥራዎች ውድድር ይፋ ሆነ
***********
የኢኖቬሽንና ቴክኖሎጂ ሚኒስቴር በ2013 በጀት ዓ.ም ከተመድ ልማት ፕሮግራም ጋር በመተባበር በኮቪድ-19 ወረርሽኝ ምክንያት በመንግሥት አገልግሎት አሰጣጥ ላይ የደረሰውን አሉታዊ ተፅዕኖ መቀነስ የሚያስችሉ የኢኖቬሽን እና ቴክኖሎጂ ምርምር ፕሮጀክቶችን በመለየት ለመደገፍ ውድድር ይፋ አድርጓል።
የመንግሥት አገልግሎትን ከዚህ በፊት በነበረው ልክ ወይም በተሻለ ሁኔታ ለመስጠት የሚያስችሉ ዲጅታል መፍትሔዎች ያሏችው የፈጠራ ባለሙያዎች እና ድርጅቶች በቀጣዮቹ ዐሥር ቀናት እንዲመዘገቡም ጥሪ አቅርቧል።
አመልካቾች https://www.et.undp.org/content/ethiopia/en/home/presscenter/articles/2020/covid-19-challenge-grant--digital-solution-for-government-servic.html?fbclid=IwAR3HkJbUZTwwHlc1naSlVOKLLPp1lgExJHUG7TWGNTjuLSV8k5jXHFf7Ohs የሚለውን ማስፈንጠሪያ በመጫን ተጨማሪ መረጃ ማግኘት እንደሚችሉም ገልጿል። https://www.facebook.com/EBCzena/photos/a.542045289160685/3819943411370840/
**********
@mebreklink
#UPDATE
አሜሪካ የፋይዘር/ባዮንቴክ ሰራሹን የኮቪድ-19 ክትባቶቹን "ወደ ሁሉም ግዛቶቿ" ማከፋፈለች መጀመሯን ተገልጿል።
አሜሪካ ዜጎቿን ዛሬ መከተብ የምትጀምር ሲሆን እስከ መጋቢት ማገባደጃ ድርስ 100 ሚሊዮን ሰዎችን ለመከተብ ታቅዷል ተብሏል።
የአሜሪካ ባለስልጣናት ክትባቱን ቅድሚያ የሚያገኙት ለበሽታው የበለጠ ተጋላጭ የሆኑት የጤና ባለሙያዎችና በእንክክብካቤ ማዕከላት የሚገኙ አረጋውያን ናቸው ብለው የነበረ ቢሆንም አሜሪካ መገናኛ ብዙሃን የዋይት ሃውስ ባለስልጣናትን ጠቀሰው እንደዘገቡት የዋይት ሃውስ አባላት ክትባቱን ቀድመው ከሚወስዱ አሜሪካውያን ተርታ ተሰልፈዋል።
ምንጭ፦ BBC
@mebreklink
🇪🇹የአዲስ አበባ የነዋሪነት መታወቂያ የአገልግሎት ዘመን ላይ ማሻሻያ ተደረገ፡፡🇪🇹
👉ቀደም ሲል የከተማዋ የነዋሪዎች መታወቂያ ሊያገለግል ይችል የነበረው 2 ዓመት ሲሆን አሁን ወደ 4 ዓመት ከፍ እንዲል መደረጉን ሰምተናል፡፡
👉4 ዓመት የአገልግሎት ጊዜ የሆነ የነዋሪነት መታወቂያ ከዛሬ ጀምሮ የሚሰጥ መሆኑን የነገሩን የከተማዋ የወሳኝ ኩነት ምዝገባ ኤጀንሲ ምክትል ዳይሬክተር አቶ ዮናስ አለማየሁ የአገልግሎት ክፍያው ላይም ማሻሻያ ተደርጓል ብለዋል፡፡
👉በዚህም ከዚህ በፊት መታወቂያ ለመወሰድ ይከፈል የነበረው ክፍያ 20 ብር ቀርቶ ለአዲስ ማኑዋል መታወቂያ 80 ብር፣ ለዲጂታል መታወቂያ ደግሞ 100 ብር ሆኗል ሲሉም አክለዋል፡፡
👉የዲጂታል መታወቂያውን በሚፈለገው መጠን ለመስጠት አንደኛው ችግር የኔትወርክ መቆራረጥን መሆኑን ሀላፊው ይናገራሉ፡፡
👉ሌላኛው ደግሞ ኤጀንሲው የራሱ የሆነ የዳታ ሴንተር የሌለው መሆኑን የተናገሩት አቶ ዮናስ ይህንን ችግር ለመፍታት ዘንድሮው ዓለም አቀፍ ጨረታ ወጥቶ ኤጀንሲው የራሱን ዳታ ማዕከል እንዲኖረው ለማድረግ መታሰቡን፤ ለዚህም 40 ሚሊዮን ብር ተበጅቷል ብለዋል፡፡
👉ይህም ለነዋሪነት መታወቂያ ብቻ ሳይሆን የልደት ፣ የጋብቻ ፣ የፍቺ ፣የላገባ የምስክር ወረቀቶች በአሻራና በዲጂታል ምዝገባ እንዲሆኑ ያግዛል ብለዋል፡፡
@mebreklink
🇪🇹ኢትዮጵያ በ2017 ለዜጎቿ ሙሉ በሙሉ የኤሌክትሪክ ኃይል ለማቅረብ እየሰራች ነው🇪🇹- ዶ/ር ኢ/ር ስለሺ በቀለ
👉 ኢትዮጵያ በ2017 ዓ.ም ለዜጎቿ ሙሉ በሙሉ የኤሌክትሪክ ኃይል ለማቅረብ አቅዳ እየሰራች መሆኑን የውሃ መስኖና ኢነርጂ ሚንስትር ዶክተር ኢንጂነር ስለሺ በቀለ ገለፁ።
👉ዶክተር ኢንጂነር ስለሺ በቀለ በዛሬው እለት በዌቢናር በተካሄደው የዩይትድ ኪንግደምና የአፍሪካ የኢነርጂ ሚንስተሮች ሲምፖዚየም ላይ ነው ይህንን የተናገሩት።
👉በሲምፖዚየሙ ላይ የኢትዮጵያ፣ የሞሮኮ፣ የግብፅ፣ የሞዛምቢክና የሞሪታኒያ ሀገራት የኢነርጂ ሚንስትሮች ንግግር አድርገዋል።
👉183 ባለድርሻዎችም የዌቢናር ውይይቱን መታደማቸውን ከውሃ መስኖና ኢነርጂ ሚንስቴር ያገኘነው መረጃ ያመለክታል።
👉በሲምፖዚየሙ ላይ ንግግር ያደረጉት ዶክተር ኢንጂነር ስለሺ በቀለም፥ ኢትዮጵያ እስካሁን 60 በመቶ የሚሆኑ ዜጎቿ የኤሌክትሪክ ኃይል ተጠቃሚ እንዳልሆኑ ገልፀዋል።
👉የኃይል አቅርት ችግሩ ሌሎች ኢኮኖሚያዊና ማህበራዊ ችግሮችን እያስከተለ መሆኑን የገለፁት ሚኒስትሩ፥ ይህንን ነባራዊ ሁኔታ ለመቀየር ኢትዮጵያ የተለያዩ እቅዶችን በማውጣት እየሰራች መሆኑን አስታውቀዋል።
👉በዚህም በሚቀጥሉት 10 ዓመት ኢትዮጵያ 20 ሺህ ሜጋዋት የኤሌክትሪክ ኃይል ለማመንጨት የሚያስችል አቅም ለመፍጠር አቅዳ እየሰራች መሆኑን ገልጸዋል።
👉በ2017 ዓ.ም (በአውሮፓውያኑ በ2025) ደግሞ ኢትዮጵያ በግሪድና በኦፍ ግሪድ ለዜጎች ሙሉ በሙሉ ሃይል ለማቅረብ ያለመች መሆኑን ጠቁመዋል።
👉ዘርፉ ከፍተኛ የውጭ ምንዛሪና ቴክኖሎጂ የሚጠይቅ በመሆኑ እንደ ዩናይትድ ኪንግደም ያሉ ሃገራት ባለሃብቶች በዘርፉ ገብተው ኢንቨስት እንዲያደርጉ ጥሪ አቅርበዋል።
👉ኢትዮጵያ በኢነርጂ ሴክተሩ ላይ ማሻሻያዎችን በማድረጓ ከውጭ ለሚመጡ ኢንቨስተሮች ምቹ አሰራር መዘርጋቱንም አብራርተዋል።
👉በተለይ ደግሞ ኢትዮጵያ በጂኦተርማል፣ በንፋስ፣ በሶላርና በባዮ ኢነርጂዎች የሏትን እምቅ አቅም ወደ ሃይል ለመቀየር ኢንቨስት እንዲያደርጉም ለዩናይትድ ኪንግደም ባለሃብቶች ጥሪ አድርገዋል።
👉በዚህ የዩናይትድ ኪንግደምና የአፍሪካ የኢነርጂ ሚንስትሮች የዌቢናር ስብሰባ ላይ የኢንግሊዝ ሃገር የልማት ተራድኦ ድርጅት በኦፍግሪድ ሃይል አቅርቦት ስራ ላይ የሚያደርገውን የፋይናንስ ድጋፍም በዚሁ ጊዜ ተነስቷል፡፡
@mebreklink
በትግራይ ክልል በሚገኙ አካባቢዎች ማለትም በዳንሻ፣ በተርካን፣ በሁመራ፣ በሽራሮ፣ ማይፀብሪና እና በማይካድራ በከፊል በአላማጣ ደግሞ ሙሉ በሙሉ የቴሌኮም አገልግሎት መጀመሩን ኢትዮ ቴሌኮም አስታውቋል።
በተቀሩት የትግራይ አካባቢዎች አገልግሎቱን ለማስጀመር የተጎዱ የቴሌኮም መሰረተልማቶችን በመጠገን መልሶ በማቋቋም እንዲሁም መደበኛ የኃይል አቅርቦቶችን በመጠቀም በሁሉም አካባቢዎች አገልግሎቱን ለማስጀመር ጥረት እየተደረገ መሆኑ ተገልጿል።
@mebreklink
🇪🇹የኮሮና ቫይረስን 95 ከመቶ የሚፈውስ ክትባት መገኝቱ ተገለጸ፡፡🇪🇹
👉ሞደሬና የተባለው ፋብሪካ የኮሮና ቫይረስን 95 ከመቶ የሚፈውስ እና የሚከላከል ክትባት ማግኝቱን ሮይተረስ ከደቂቃዎች በፊት በሰበር ዜናው አስነብቧል፡፡
👉ክትባቱ በ30 ሺህ ያህል ሰዎች ላይ ተሞክሮም አመርቂ ውጤት ማምጣቱን ነው የተነገረው፡፡
👉ሞደሬና የተባለው የመድሀኒት አምራች ፋብሪካ ሰሞኑን ፒፍዘር ከተባለው የመድሀኒት አምራች ፋብሪካ ጋር በመተባበር በርካታ ቁጥር ያለው ክትባት ለሀገራት ሊያቀርብ እንደሆነም አስታውቋል፡፡
👉አሁን የተገኝው ከትባት የመጨረሻ የሙከራ ደረጃ ሙሉ በሙሉ ማለፉንና ውጤታማ መሆኑን የገለጸው የህ ፋብሪካ እስከ ፈረንጆቹ አዲስ አመት ድረስ 60 ሚሊየን ብልቃጥ ክትባት አቀርባለሁ ብሏል።
👉በሚቀጥለው አመት የአሜሪካ መንግስት አንድ ቢሊየን ክትባት ለመግዛትም ማዘዙን ዘገባው ጠቁሟል፡፡
👉አሜሪካ አሁን ላይ ውጤታማ ናቸው የተባሉ ሁለት ክትባባቶችን ለአለም አስተዋውቃለች፡፡
🔸@mebreklink
#DrTedrosAdhanom
ዓለም የኮቪድ-19 መከላከያ ክትባት ወደማግኘት እየተቃረበ ቢሆንም የኮቪድ-19 መከላከያዎችን ማላላት የለበትም ሲሉ የዓለም ጤና ድርጅት ዋና ዳይሬክተር ዶክተር ቴድሮስ አድሃኖም አሳሰቡ።
ዶ/ር ቴድሮስ ፥ "የኮሮናቫይረስ (ኮቪድ-19) አሁንም የዛሬ 8 ወር እንደነበረው አስጊ ወረርሽኝ መሆኑን እንደቀጠለ ነው" ብለዋል።
በፓሪስ እየተካሄደ በሚገኝ የሰላም ጉባዔ ላይ "በኮቪድ-19 ታክቶን ይሆናል ነገር ግን እርሱ ገና አልሰለቸንም" ብለዋል ዶ/ር ቴድሮስ አድሃኖም።
የአውሮፓ አገራት እየታገሉ ነው ነገር ግን ስርጭቱን ለማቆም የተወሰዱት እርምጃዎች እንዲሁም ቫይረሱ ምንም ለውጥ አላሳየም" ሲሉ ተናገረዋል።
ከሰሞኑን የተለያዩ ሀገራት ተመራማሪዎች "ውጤታማ" የሆነ ክትባት ማግኘታቸውን እየገለፁ ነው።
ዶ/ር ቴድሮስ ገና ደህንነቱ እና ውጤታማነቱ መፈተሽ ባለበት ክትባት ላይ መተማመን አደገኛ መሆኑን ገልፀዋል።
"ክትባት በፍጥነት ያስፈልጋል ፣ ነገር ግን እጃችንን አጣጥፈን ቁጭ አንልም" ብለዋል። (BBC)
@mebreklink
ለ8ኛ እና 12ኛ ከፍል ተማሪዎች ቀደም ሲል የተሰጡ ክልላዊ እና ሀገራቀፋዊ ፈተናዎችን በማግኘት በስልክዎ ላይ ለመለማመድ የሚከተሉትን ቅደም ተከተሎች በአግባቡ ይተግብሩ፡፡
1.👆ከላይ ያለውን መተግበርያ ያውርዱ
ከዚያም ከሚመጡት አማራጮች ውስጥ Package installer የሚለውን በመጫን አፕልኬሽኑን ይጫኑ
2.ከዚያም የጫኑትን አፕልኬሽን ሲከፍቱ ከታች ከሚመጣው ውስጥ English የሚለውን በመምረጥ Continue የሚለውን ይምረጡ
3.በመቀጠል ለመጀመሪያ ጊዜ አፕልኬሽኑን የሚጠቀሙ ከሆነ Register የሚለውነ በተን ይጫኑ
4.ከዚያም የሚመጣውን Registration form ይሙሉና Register የሚለውን ይጫኑ
5.በመቀጠል Sign in የሚለውን በመጫን የሚመጣው ፎርም ላይ የተመዘገቡበትን Username and Password ያስገቡ
6.ከዚያም የሚመጣው ፎርም ላይ የክፍል ደረጃና የፈተናውን ዓይነት በመምረጥ ፈተናውን መለማመድ ይቻላል
----------------------------------
#መልካም_የዝግጅት ግዜ ለጓደኞችዎም ያጋሩ
https://t.me/joinchat/AAAAAEyYjxSHWM66afKljA
@LiyuMereja
90 በመቶ የመከላከል አቅም አለው የተባለው ክትባት በወሩ መጨረሻ እውቅና ሊሰጠው እንደሚችል ተገለፀ።
Pfizer እና BioNTech በተባሉ ሁለት ኩባንያዎች የተመረተው ክትባቱ፤ በስድስት አገራት በ43 ሺህ 500 ሰዎች ላይ መሞከሩ ታውቋል። ምንም አይነት የጤና ደህንነት ዕክል ያልታየበት ክትባቱ፤ ለሳይንስ እና ሰብአዊነት ትልቅ ስኬት እንደሆነ የኦክስፎርድ ዩኒቨርስቲ ተመራማሪዎች ተናግረዋል። Pfizer የተባለው ኩባንያ ብቻ የክትባቱን 50 ሚሊዮን ዶዝ እስከ 2020 መገባጃ እንሚያቀርብ የቢቢሲ ዘገባ ያሳያል። ሌሎች 12 አይነት የኮቪድ-19 ክትባቶች የመጨረሻ ሙከራ ደረጃ ላይ ይገኛሉ ተብሏል።
--- @mebreklink
🇪🇹ግጭቱ በአስቸኳይ እንዲቆም የጋራ ም/ቤቱ ጠየቀ🇪🇹
👉በፌዴራል መንግስት እና በጽንፈኛው ህወሓት መካከል የተፈጠረው ግጭት በአስቸኳይ እንዲቆም እና ሁለቱ ወገኖች ወደ ውይይት እንዲመጡ የኢትዮጵያ የፖለቲካ ፓርቲዎች የጋራ ምክር ቤት ጠየቀ፡፡
👉ምክር ቤቱ ከግጭቱ ሁለቱም ወገኖች የሚያተርፉት ነገር የሌለ ከመሆኑም ባሻገር ሃገሪቱን የሚጎዳ በመሆኑ የተፈጠረው ግጭት እንዲቆም ጠይቋል፡፡
👉የጋራ ምክር ቤቱ የፊታችን ቅዳሜ ሃገራዊ መግባባት ላይ ለመድረስ ህወሃትን ጨምሮ በርካታ የፖለቲካ ፓርቲዎችን ያሳተፈ ውይይት ለማድረግ እቅድ ይዞ እንደነበርም በመግለጫው አስታውቋል፡፡
👉በተለይም በመንግስትና በጽንፈኛው ህወሃት መካከል የተፈጠረውን ውጥረት ወደ ጠረጴዛ ዙሪያ ለማምጣት አጀንዳ ቀርጾ ከማዘጋጀቱም ባሻገር ለፌዴሬሽን ምክር ቤት ደብዳቤ ማስገባቱን ገልጿል፡፡
👉ይሁን እንጂ ባለፈው ማክሰኞ ምሽት ጉዳዩ ወደ ግጭት በማምራቱ እቅዱ ሊሳካ አለመቻሉን አስረድቷል፡፡
👉ግጭቱ እንደ ሃገር ዋጋ እንደሚያስከፍል የጋራ ምክር ቤቱ ገልጾ ችግሩን በውይይት ለመፍታት አሁንም አለመርፈዱን ጠቁሟል፡፡
👉በአለም የፖለቲካ ታሪክ ተደርጎና ተሰምቶ የማያውቅ ተግባር በህወሃት በመፈጸሙ ወደ ግጭት መገባቱን የገለጸው የጋራ ምክር ቤቱ ያም ቢሆን ግን ወደ ውይይት ለመምጣት ሰፊ እድል አለ ብሏል፡፡
👉የጋራ ምክር ቤቱ ሁለቱ ወገኖች በአስቸኳይ የተኩስ አቁም ስምምነት እንዲያደርጉ የሚጠይቅ ባለ ሰባት ነጥብ የአቋም መግለጫ አውጥቷል፡፡
@mebreklink
የትምህርት ትንሽ የለምና ዉሰዱና ተጠቀሙበት
Afan Oromo / አፋን ኦሮሞ / ትርጉም 1 ኤሳ - የት 2 ዮም - መች 3 ኤኙፊ - ለማን 4 ሲፍ - ላንተ / ላንቺ / 5 ማሊፍ - ለምን 6 ከም - የትኛው 7 ቦሩ - ነገ 8 ዲማ - ቀይ 9 አዲ - ነጭ 10 ጉራቻ - ጥቁር 11 ማገሪሳ አርንጒዴ 12 አባ - አባት 13 ሙጫ - ልጅ 14 ኢጆሌ - ልጆች 15 ዳኢማ - ህፃን 16 መና - ቤት 17 ሲ - አንተ 18 መቃ - ስም 19 ፊራ - ዘመድ 20 ማቲ - ቤተሰብ 21 ከና - ይህ 22 ሰን - ያኛው 23 አስ - እዚህ 24 አች - እዛ 25 - ኬ - ያንተ 26 ኪያ - የኔ 27 ሲገሌ - ገባህ 28 ኛታ - ምግብ 29 መና ኛታ - ምግብ ቤት 30 ሲሬ - አልጋ 31 ሲሬን ጅራ - አልጋ አለ 32 ቢሻን - ወሃ 33 - ጪስ - ተኛ 34 ለጋ - ወንዝ 35 ባዬ . ሄዱ - ብዙ 36 ጋሪ . ደንሳ . ሚሻ - ጥሩ 37 - ኡመታ - ህዝብ 38 ኮቱ - ና 39 ዴም - ሂድ 40 - ከሌሳ - ትናንት 41 በልበላ - በር 42 ኢብሳ - መብራት 43 ኢፋ - ብረሃን 44 - ከራ መንገድ 45 ቦላ - ጉድጓድ 46 ላኮፍሳ - ቁጥር 47 ሜሻ - እቃ 48 በኒ - ክፈት 49 ሴኒ - ግባ / ግቢ / 50 ኦፍ - ንዳ ።።። ላይክ እንደ ሼር ማድረጉን አይርሱ Thank You
🇪🇹ፓስፖርት በ‘ኦንላይን’ እንዴት ማደስ/ማውጣት ይቻላል?🇪🇹
👉የኢሚግሬሽን ዜግነትና የወሳኝ ኩነት ኤጀንሲ ተጠቃሚዎች በድረ-ገጽ አማካኝነት አዲስ ፓስፖርት ለማውጣት እና ለማደስ ቀጠሮ ማስያዝ የሚያስችል ድረ-ገጽ ይፋ አድርጓል።
👉https://www.ethiopianpassportservices.gov.et/#/Information በሚለው የኤጀንሲው ድረ-ገጽ ላይ አዲስ ፓስፖርት ለማውጣት፣ ጊዜው ያበቃ ወይም የተበላሸ ፓስፖርት ለማሳደስ፣ የጠፋ ወይም የተሰረቀ ፓስፖርትን በአዲስ ለመተካት እና ፓስፖርት ላይ የተመዘገበ መረጃ ለመቀየር አገልግሎት የሚፈልግ ወደ ድረ-ገጹ መሄድ ይችላል።
👉የአገልግሎት ፈላጊዎች ቁጥር ከፍ ያለ ሊሆን ስለሚችል የሚፈልጉትን አገልግሎት በወቅቱ ለማግኘት ቀድመው ቀጠሮ ይያዙ። ለምሳሌ ዛሬ ላይ ሆነው ለነገ ቀጠሮ ማግኘት ላይችሉ ይችላሉ።
👉አዲስ ፓስፖርት ለማውጣት በቅድሚያ የሚያስፈልጉ ሰነዶችን ያዘጋጁ። የታደሰ የቀበሌ መታወቂያ እና የልደት ሰርተፊኬት ያስፈልጋል። እነዚህን መረጃዎች ድረ-ገጹ ላይ ስለሚጫኑ ሰነዶቹ ‘ስካን’ መደረግ ይኖርባችኋል።
👉ወደ ድረ-ገጹ ያምሩ። ቅጾቹን በጥንቃቄ ይሙሉ፤ የታደሰ የቀበሌ መታወቂያ እና የልደት ሰርተፊኬት የሚጠይቀው ቦታ ላይ ‘ስካን’ ያደረጉትን ሰነድ ይጫኑ። ከሚቀርቡት ሁለት የክፍያ አማራጮችን አንዱን ይምረጡ። ማመልከቻዎን ካስገቡ በኋላ በስልክዎ ላይ በሚላከው አጭር የጽሑፍ መልዕክት ወይም በኢሜል የሚወጣውን ኮድ ተጠቅመው ክፍያዎን ይፈጽሙ።
👉አዲስ ባለ 32 ገጽ ፓስፖርት 600 ብር የሚከፈልበት ሲሆን፣ ለ ባለ 64 ገጽ ፓስፖርት ደግሞ 2186 ብር ይጠየቃሉ። የቀጠሮዎ ቀን እና ሰዓት የተጠቀሰበትን የማመልከቻዎን የመጨረሻ ገጽ አትመው ይያዙ።
👉በቀጠረዎ ዕለትም የቀጠሮ ወረቀትዎን፣ አስፈላጊ የሆኑ ዋና እና ኮፒ ሰነዶችን ይዘው ይገኙ። ፓስፖርት ለማውጣትና አገልግሎቱ ያበቃ ፓስፖርት ለማሳደስም ተመሳሳይ ቅደም ተከተሎችን ይከተላሉ።
👉በተጨማሪም ፓስፖርትዎን ለማሳደስ አገልግሎቱ ያበቃው ፓስፖርት “ኢንፎርሜሽን ፔጅ” ተብሎ የሚጠራውን አንጸባራቂ ገጽ ፎቶ ኮፒ ያድርጉ። የፓስፖርት “ኢንፎርሜሽን ፔጅ” ማለት ፎቶ ግራፍዎ የታተመበት ገጽ ማለት ነው።
👉በተመሳሳይ ፓስፖርት ለማሳደስ የሚጠየቁት እንደየ ገጹ ብዛት 600 ብር እና 2186 ብር ነው። የጠፋ ወይም የተሰረቀ ፓስፖርትዎን በአዲስ ለመተካት ወደ ኤጀንሲው ድረ-ገጽ በማምራት ቀጠሮ መያዝ ይችላሉ።
✅ፓስፖርትዎን በአዲስ ለመተካት
👉ፓስፖርትዎን በአዲስ ለመተካት አዲስ ፓስፖርት ለማውጣት እንደሚያደርጉት ተመሳሳይ ቅድመ ተከተሎችን ይከተላሉ። ፓስፖርትዎ ለመጥፋቱ/ለመሰረቁ ግን ከፖሊስ ማረጋገጫ ማቅረብ ይኖርብዎታል።
👉የታደሰ የቀበሌ መታወቂያ እና የፓስፖርቱ ኮፒ ካለዎትም ዝግጁ ያድርጉ። በተመሳሳይ በድረ-ገጹ ላይ የሚቀርብልዎትን ቅጽ ይሙሉ። ከፍያውን ይፈጽሙ። በቀጠርዎ ቀን ሰነዶችን ያቅረቡ።
✅የመረጃ ለውጥ
👉በፓስፖርትዎ ላይ ተመዝግቦ የሚገኝ፣ ለምሳሌ የስም፣ የትውልድ ቀን ወይም የትውልድ ስፍራ፣ መረጃ እንዲቀየር ከፈለጉ፤ የፍርድ ቤት ወረቀት ያስፈልግዎታል።
👉በመቀጠል አዲስ ፓስፖርት ለማውጣት እንደሚያደርጉት ተመሳሳይ ቅድመ ተከተሎችን ይከተላሉ። አስቸኳይ አገልግሎት ለማግኘት ከላይ የተጠቀሱትን አገልግሎትን በአስቸኳይ ማግኘት ከፈለጉ ከዚህ በታች ከተዘረዘሩት አንዱን ማቅረብ ይኖርብዎታል።
👉ከአገር ውጪ ወጥተው መታከም እንደሚኖርብዎ የሚያስረዳ የሐኪም ደብዳቤ (የሕክምና ቀጠርዎ ሊሆን ይችላል)፣ ከተፈቀደላቸው ተቋማት የድጋፍ ደብዳቤ፣ የውጪ አገር መኖሪያ ፍቃድ፣ የግብዣ ደብዳቤ፣ አስቸኳይ የሥራ ጉዞ፣ የትምህርት ዕድል ወይም ዲቪ ሎተሪ እድለኛ መሆንዎን የሚያሳይ ማስረጃ፣ በሃዘን ወይም ደስታ የሚደረግ ጉዞ መሆኑን የሚያሳይ ሰነዶች ሊሆኑ ይችላሉ።
👉አስቸኳይ አገልግሎት ተጨማሪ ክፍያ ይጠየቅበታል። የሚጠየቁትን ተጨማሪ ክፍያ ለመክፈል ዝግጁ ይሁኑ። ያስታውሱ ከላይ የተጠቀሱ አገልግሎቶችን ለማግኘት በአካል መቅረብ ግዴታ ነው።
ይህ መረጃ ያገኘነው ከኤጀንሲው ድረ-ገጽ ላይ ነው።
@mebreklink
የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ለገበታ ለሀገር ፕሮጀክት አንድ ነጥብ አንድ ቢሊዮን ብር አበረከተ!
የገንዘብ ድጋፉን የባንኩ አመራሮች ለጠቅላይ ሚኒስትር አቢይ አህመድ አስረክበዋል።ጠቅላይ ሚኒስትሩ ባንኩ የህዝብ እንደመሆኑ መጠን ለህዝብ የሚጠቅሙ ፕሮጀክቶች ላይ አስተዋጽኦ እያደረገ መሆኑን ገልጸው፤ ለአስተዋጽኦው ምስጋና አቅርበዋል።ከተደረገው ድጋፍ 571 ሚሊዮን ብሩ ከባንኩ ሰራተኞች፤የቦርድ አባላትና ማኔጅመንት የተሰበሰበ ሲሆን ቀሪውን ባንኩ ወጭ ማድረጉ ተገልጿል። የዛሬውን ጨምሮ የፋይናንስ ዘርፉ እስካሁን በአጠቃላይ ለገበታ ለሀገር ፕሮጀክት ግንባታ የ1 ነጥብ 5 ቢሊዮን ብር ድጋፍ ማድረጉ ታውቋል።
ምንጭ
[ኢዜአ]
@YeneTube @mebreklink
ብሔራዊ ምርጫ ቦርድ 1.1 ቢሊዮን ብር ተጨማሪ በጀት ጠየቀ!
የህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት ምርጫው በያዝነው ዓመት (2013 ዓ/ም) እንዲካሄድ መወሰኑን ተከትሎ ቦርዱ የኮቪድ-19 ወረርሽኝ የጥንቃቄ መመሪያ አውጥቶ እየተንቀሳቀሰ እንደሚገኝ አስታውቋል።
ቦርዱ ምርጫው ፍትሀዊ፣ ተአማኝ፣ ግለጽ ከማድረግ ባለፈ ከጤናም አንጻር ጥንቃቄ የታከለበት እንዲሆን ተጨማሪ የሰው ሃይል ከማሰማራት ጀምሮ የተጠናከረ የመራጮች ትምህርት መስጠት እንደሚያስፈልግ ገልጿል።
ቦርዱ ይህ ለማድረግ ተጨማሪ በጀት እንዲጠይቅ ግድ ብሎኛል ሲል አሳውቋል። ምርጫ ቦርድ ባዘጋጀው መመሪያ መሰረት ለመጓዝም 1.1 ቢሊዮን ብር ተጨማሪ በጀት መጠየቁን የቦርዱ ሰብሳሲ ወ/ት ብርትኳን ሚዴቅሳ ተናግረዋል።
ምንጭ Tikvah
@eliasmeseret
#############
@mebreklink
በ1.8 ቢሊየን ብር የሚገነባው የገለልሽ-ደጋሀምዶ መንገድ ስራ ተጀመረ
******************
ዛሬ ሶማሌ ክልል የገቡት ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አህመድ በ1.8 ቢሊየን ብር የሚገነባውን ከጅግጅጋ-ገለልሽ-ደጋሀምዶ የመንገድ ፕሮጀክት አካል የሆነውን የገለልሽ-ደገሀምዶ መንገድ ሥራን አስጀምረዋል።
አጠቃላይ 166 ኪ.ሜ ከሚረዝመው ከዚህ መንገድ ውስጥ 110 ኪ.ሜ የመንገድ ግንባታ በሀገር ውስጥ ኮንትራክተር በሆነው ቢአይካ የሚገነባ ነው።
በሁለት ዓመት ተኩል ግንባታውን ሰርቶ ለማስረከብ እንደሚሠራም ተገልጿል። ይህም ዛሬ በሶማሌ ክልል በ6 ቢሊዮን ብር ወጭ ሊገነቡ የመሠረት ድንጋይ ከተቀመጠላቸው መካከል ነው።
ከጅግጅጋ - ገለልሽ የሚደርሰው 56 ኪ.ሜ የመንገድ ሥራው በ1 ቢሊዮን ብር ተገንብቶ ተጠናቅቆ በጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አህመድ ተመርቆ ለአገልግሎት ተከፍቷል።
በአስማማው አየነው
https://www.facebook.com/EBCzena/photos/a.542045289160685/3822277957804052/?type=3&theater
*********
@mebreklink