<<ኑ 72ቱ አርድዕትን ሆነን ታሪክን እንድገም>>
እንደሚታወቀው በ12ቱ ሀዋርያት የተመሰሉ ታላላቅ ወንድሞቻችን አዳራሽና ቢሮዎችን ሰርተው አስረክበውናል። አሁን ያለን ትውልድ ደግሞ ለመጪው ልጆቻችን የሚማሩበት መማሪያ ክፍል ለመስራት ፕሮጀክት ቀርፀን ተነስተናል። ለዚህም የፈለገ የቁርጥ ቀን ልጆች የሆኑ(50+22)=72ሰራተኞች ብቻ እንፈልጋለን።
>እነዚህም 50ዎቹ ደሞዛቸው ከ2000ብር በላይ የሆነ =250,000ብር የሚያዋጡ
#1ዱ=250,000÷50=5000ብር ሢደርስበት
በ3መንገድ ከፍሎ መጨረስ ይችላል።
1.ከ5-6ወር=5x(1000በወር)
2.በ10-12ወር=10x(500በወር)
3.16ወር=16x(312.5በወር)
ሲሆኑ
>22ቱ ደግሞ 50,000ብሯን በዓመት የሚካፈሏት ሲሆኑ ይህም
#1ዱ=50,000÷22=2273ብር
በዓመት ቢከፍል=2273÷12=(190ብር በወር) ያዋጣል።
ይሆናል። እነዚህ 72ሠራተኞች ሰንበት ትምህርት ቤቷ እውቅናን የምትሰጣቸው ናቸው።
የዚህ ታላቅ የበረከት ስራ ለመሳተፍ የምትፈልጉ 72 የሰንበት ትምህርት ቤታችን የቁርጥ ቀን ልጆች ስማችሁንና ምድባችሁን ከታች ለተጠቀሱት ልጆች በመግለፅ ላኩልን።
ስለሆነም ማገዝ ለምትፈልጉ
ኢትዮጵያ ንግድ ባንክ 10006095662319
ህብረት ባንክ 4630412520610015
አቢሲኒያ ባንክ 176147067
ለበለጠ መረጃ
ፀጋዬ 0911719353
ላቃቸው 0988345695
ሰለሞን 0923079151
ታላቅ የምስራች
ለጨሪና ሰፈራ ኦርቶዶክስ ምዕመናን በሙሉ (የወጣቶች ጉባኤ የካቲት 17/2016 ከቀኑ 5:00)
የሰርቲ(ጨሪ) መድኃኔዓለም ቤተክርስቲያን የጥምቀት ወጣቶች ህብረት ከሰንበት ት/ቤቷ ጋር በመተባበር በየ 15ቀኑ የሚደረገው ጉባኤ የካቲት 17/2016 እሁድ ከ5:00-6:10 ይጀምራልና
ኦርቶዶክስ ምዕመናን ወጣቶች እንዳቀሩ ተጋብዛቹኃል።
እነዴት አመሻችሁ ነገ ጠዋት አወደምህረት አገልግሎት ስላለ ወድ አባላት 1:30 ደብር እንድትገኙ ለምታስቀድሱ ቁርባን ሰአት ለይ መልካም አዳር።
ከመዝሙር ክፍል
ለሰንበት ትምህርት ቤታችን ሰራተኛ አባላት በሙሉ ወርሃዊ የትምህርት ጉባኤያችን(በአዲስ ህይወት መመላለስ ትምህርት) ነገ ጥር 26/2016 ስለሚኖር እንድትገኙ ስንል ጥሪያችንን እናስተላልፋለን።
Читать полностью…ሰላመ እግዚአብሔር ከእናንተ ጋር ይሁን ለሰንበት ት/ቤታችን አባላት በሙሉ ይሄ ሰንበት ት/ቤታችን እሁድ በአባላት ፊርማ አፀድቃ ከዚህ በኃላ የምትተዳደርበት መዋቅር ስለሆነ ትኩረት ሰጥታችሁ አንብቡት።
Читать полностью…እንኳን ለከተራ በአል በሰላም አደረሳችሁ,,,,,,,,,,
ነገ ስትመጡ ነጭ ልብስ አድርጋችሁ እንድትመጡ
ሰአትም አክብሩ መልካም አገልግሎት ይሁንልን ,,,,።
ታላቅ መንፈሳዊ ጉዞ
ወደ ዝቋላ አቡነገብረመንፈስ ቅዱስ ገዳም
አዘጋጅ የሰርቲ/ደ/መ/መድኃኔዓለም ቤ/ክ ፈለገዮርዳኖስ ሰ/ት/ቤት
ትኬቱን የሚያገኙባቸው ስልኮች 0923079151/0943164229
የጉዞ ዋጋ 280ብር (መስተንግዶን ጨምሮ)
መነሻ ጥቅምት 4 ጠዋት 11:00ሰዓት
መመለሻ ጥቅምት 5 ከንግስ መልስ
መነሻ ቦታ ሰፈራ ድልድዩ ጋር
ለጉዞ ሲመጡ ትኬቶንና ውዳሴ ማርያም መያዞን አይርሱ
በደበረ ታቦር በዓል #ቡሄ፣ #ጅራፍ_ማስጮህ፣ #ችቦ_ማብራትና #ሙልሙል_ዳቦ ሃይማኖታዊ ምስጢራቸው ምንድነው?
ደብረ ታቦር ጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ያዕቆብን፣ ዮሐንስንና ጴጥሮስን ይዞ ወደ ታቦር ተራራ ከወሰዳቸው በኋላ በዚያ ብርሃነ መለኮቱን የገለጠበትና ሙሴና ኤልያስን ጠርቶ የህያዋንና የሙታን አምላክነቱን ያሳየበት ከዘጠኙ የጌታ ዓበይት በዓለት ውስጥ አንዱ ነው። ቤተክርስቲያናችንም የተለያዩ ስርዓቶችን በመፈፀም አክብራው ታልፋለች፡፡
በደብረ ታቦር በዓል የሚፈጸሙ (#ቡሄ፣ #ጅራፍ_ማስጮህ፣ #ችቦ_ማብራትና #ሙልሙል_ዳቦ) ትውፊታዊ የሃይማኖት ስርዓቶች ምሳሌዎች ምን እንደሆነ እናያለን፡፡
#ቡሄ
ቡሄ ማለት ብራ፣ ብርሃን፣ ደማቅ ማለት ነው፡፡ ከስሙ ትርጉም እንደምንረዳው ጌታችን ብርሃነ መለኮቱን የገለጠበት በዓል ስለሆነ ብራ፣ ብርሃን ደማቅ የሚል ፍቺ ያለው ስያሜ ተሰጥቶታል፡፡
አንድም ቡሄ ማለት ወቅቱ የክረምት ጨለማ አልፎ የብርሃን ወቅት ስለሚመጣ ሰማይም ከጭጋጋማነት ወደ ብሩህነት የሚለወጥበት የመሸጋገሪያ ወቀት ስለሆነ ብራ ተብሏል፡፡
"ቡሄ ከዋለ የለም ክረም ዶሮ ከጮኸ የለም ሌሊት እንዲሉ"
አንድም ቡሄ…..ቡኮ "/ሊጥ" ማለት ነው፡፡ በዚህ በዓል ቡኮ ተቦክቶ ዳቦ/ሙልሙል/ ተጋርሮ የሚታደልበት በዓል ስለሆነ
ይህ ስያሜ ተሰጥቶታል፡፡
#ሙልሙል_ዳቦ
ሙልሙል ዳቦ አመጣጡ ጌታችን ብርሃናዊ መለኮቱን በገለጠበት በዚህ ዕለት በደብረ-ታቦር አካባቢ የነበሩ ህፃናት እረኞች ቀኑ የመሸ ስላልመሰላቸው /ጌታችን በብርሃን አካባቢውን ሞልቶት ስለነበረ/ በዛው ሆነው ከብትና በጎቻቸውን እየጠበቁ ሲቆዩባቸው የሰዓቱን መግፋት የተመለከቱ ወላጆች በችቦ ብርሃን ተጠቅመው ለልጆቻቸው የሚቀመስ ሙልሙል ዳቦ ይዘው ወዳሉበት መምጣታቸውን ያሳያልና ታሪኩን እየዘከርን በዓሉን እናከብራለን፡፡
አንድም እንደ ሐዋርያት የምስራች ሲነግሩን ወንጌል ሊሰብኩልን በየደጃፋችን መጥተው "ቢሄ በሉ" የሚሉትን ታዳጊዎችን ይበሉት ዘንድ ይሰጣቸዋል ይህም መጽሐፋዊ ነው ጌታችን ደቀ መዛሙርቱን በደረሳችቡት ሁሉ ተመገቡ /ማቴ 10፥12/ ብሏልና ህፃናቱም የጌታን በዓል ሊያበስሩ ሲመጡ ዳቦ መስጠት ልማዳዊ ብቻ ሳይሆን ህፃናቱም የደቀመዛሙርት ምሳሌ ናቸው፡፡ መዝሙራቸው ደግሞ የምስራች ወንጌል ይዘው የመምጣታቸው ምሳሌ ነው፡፡ ሐዋሪያት በገቡበት ሀገር ሁሉ አስተምረው አጥምቀው የፀጋ ልጅነትን አሰጥተው እንደሚቆዩ ሁሉ ልጆችም ዘምረው አመስግነው መርቀው ውለዱ ክበዱ የመንግስተ ሰማያት ወራሾች ያድርጋችሁ ብለው አመስገነው ይሄዳሉና በሐዋሪያት ህፃናቱ ይመሰላሉ፡፡
#ችቦ_ማብራት
ችቦ የጌታችንን ብርሃነ መለኮት መገለጥን የሚያመለክት ነው፡፡ ጌታችን በደብረ ታቦር መለኮቱን ሲገልጥ ብርሃን አካባቢውን ሞልቶት ነበርና ያንን በዘመናችን ለመግለጥ የበዓሉ ዋዜማ ማታ ችቦ አብርተን አምላካችንን እናመሰግናለን፡፡ አንድም ደግሞ የችቦ ታሪክ ከላይ እንደገለፅነው የእረኞቹ ወላጆች ይዘውት የመጡት ብርሃን ነው፡፡
#የጅራፍ_ምሳሌነት
በደብረ ታቦር በዓል በትውፊታዊ መልኩ የሚታየው ሚስጥር በእየሩሳሌም ስለሚሆነው የጌታችን ሞቱ ምሳሌ ነው፡፡ በዚህ በዓል ጅራፍ መገመዱ እና ማጮሁ ሁለት አይነት ምሳሌ አለው፡፡
#የመጀመሪያው ጌታችን በዕለተ አርብ የደረሰበትን ግርፋትና ህማም እናስብበታለን፣
#ሁለተኛው ደግሞ ድምፁን ስንሰማ የባህሪ አባቱን የአብን የምስክርነት ቃልና በግርማው ሲገለጥ የተሰማውን ነጎድጓድ ያስታውሰናል፡፡ የጅራፍን ትውፊታዊ ውርስ መጽሐፋዊ ትምህርቱንና ምስጢሩን ከትውልድ ጠብቆ ማስተላለፉ ተገቢ ነው፡፡
በአጠቃላይ በዓለ ደብረ ታቦር ከነዚህ ሚስጢር ካላቸው ትምህርቶችና ትርጓሜያቱ ከትውልድ ወደ ትውልድ በቅብብል እንደመጣልን እኛም ሃይማኖታዊ ትውፊቱን ሳይለቅ ማስተላለፍ ይጠበቅብናል፡፡ የዚህ ነገር ባለ ድርሻ አካላት ደግሞ ወጣቶችና ወላጆች ናቸው፡፡ አንዳንድ ጊዜ በቡሄ ጨዋታ የሚሰሙ ግጥሞች ስድብ ፊዝና ሳቅ ይታይባቸዋል ተጫዋቾቹም ከሰጡን እንመርቃለን ካልሰጡን እንራገማለን አይነት መልዕክት ያስተላልፋሉ። የሚብሰው አሳባቢ ነገሩ ደግሞ ኃይማኖታዊ ስርዓቱን ወደ ገንዘብ ማግኛ መቀየሩ ነው፡፡ ስለሆነም ይህን ነገር በተለይ የነገ የሀገር ተረካቢና የቤተክርስቲያን ተተኪ የሆንን ወጣቶች ማስተካከል ይኖርብል፡፡ ወላጆችም ሕፃናት በየደጃፋችን ላይ በዓሉን ሊያበስሩ ሲመጡ አስደንግጦ ከማባረር በሚገባው መልኩ አስተምረን መርቀን ማስተናገድ ይጠበቅብናል ባህሉም እንዳይተው የበኩላችንን አደረግን ማለት ነው።
ከበዓሉ በረከት ያሳትፈን
መንፈሳዊ የአዳር መርሃግብር ዛሬ ሰኔ26
ከምሽቱ 3:00ሰዓት ጀምሮ
የሚቀርቡት መርሃግብራት
መክፈቻ መዝሙር
መንፈሳዊ ስብከት
መንፈሳዊ ግጥም
ግጥማዊ ወግ
መዝሙር በተጋባዥ ዘማርያን
ያሬዳዊ ወረብ
ብሂለአበው
መነባንብ
ጭውውት
ድራማ
የምርጫ ካርዴ ለቅድስት ቤተክርስቲያኔና ለሀገሬ
"አንተም ከህዝብ ሁሉ አዋቂዎችን እግዚአብሔርን የሚፈሩት፥ የታመኑ የግፍን ረብ የሚጠሉትን ሠዎች ምረጥ " ዘፀ 18:21
ሀገርን እንደሶሪያ
ቅድስት ቤተክርስቲያናችንን እንደ ቱርክ እንዳናጣት ባለ ማዕተቦች ያሉበትን ለይተን እንምረጥ።
የምርጫ ድምጻችንን ከመስጠታችን በፊት
ወደ ምርጫ መስጫ ከመሄዳችሁ በፊት የምርጫ ቅስቀሳውን በየቦታው ከተለጠፈው ብርቅርቅ ምስል በላይ በፓርቲዎቹ ውስጥ ያለውን አቋም ፈትሹ በየፓርቲው ውስጥ ያሉትን እጩ ኦርቶዶክሳውያን ለዩ ትላንት ባሳለፍናቸው ሶስት ዓመታት ውስጥ ኦርቶዶክሳውያን ላይ የደረሰውን መከራ አይተው እንዳላዩ ሰምተው እንዳልሰሙ በመከራችን ላይ የተሳለቁብን ባለስልጣናት እንዳትረሱ
ባሳለፍናቸው ሶስት ዓመታት ብቻ
ቡራዩ፣ጅግጅጋ ፣ሻሸመኔ፣ መተከል፣ ወለጋ፣ ጅማ፣ ማይካድራ፣ ትግራይ፣አጣዬ በማንነትና በሃይማኖታቸው ምክንያት ብቻ ወገኖቻችን ተጨፍጭፈዋል
ማተባቸው እየተበጠሰ ጋዝ ተርከፍክፎ ተቃጥለው ወደ ወንዝ ተወርውረው እሬሳቸው አይቀበርም በማለት ለውሻ ተሰጥተዋል
የካህናት ሚስት፣ነብሰጡር እናቶች፣ ለአቅመ ሂዋን ያልደረሱ ህጻናት በግልና በቡድን ተደፍረው ቅስማቸው ተሰብሮ አካላቸው ቆሽሾ ወድቀዋል
ካህናት ዲያቆናት የሰንበት ትምህርት ቤት ተማሪዎች በመንገድ ላይ ተገለው ደማቸው ፈሷል
ቤተ ክርስቲያን ተቃጥላ መቅደሷ ተደፍሯል
ቤተከርስቲያንና ምዕመኗ በየቦታው የአደባባይ በዓላት ማክበሪያ ይዞታ ቦታዋ ተነጥቋል
በኦሮሚያ ክልል ኦርቶዶክሳውያን ቤት ንብረታቸውን ጥለው ተሰደዋል አብያተ ክርስቲያናት ተዘግተዋል
በመንግሥትና በግል ሚድያ ከመንግሥት ባለስልጣን እስከተራ አክቲቪስት በአደባባይ ቤተከርስቲያንን ሰድቧል የቤተከርስቲያኗን ቅዱስ ሲኖዶስ ፓትርያሪከር ዘኢትዮጵያን ዘልፏል
ወደ ምርጫ ጣቢያ ከመሄዳችሁ በፊት የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ከርስቲያን ትልቅ መከራ ውስጥ እንዳለች የቤተከርስቲያንን መከራ የሚያስቆም ለደረሰባት ግፍ ፍትህ የሚሰጥ የሰው ልጅ ሰው በመሆኑ ብቻ ተከብሮ እንዲኖር የሚያደርግ ፓርቲ ማን እንደሆነ አሰላስሉ!
ምርጫ ስንመርጥ ቤተ ከርስቲያንን እያሰብን ይሁን ቤተ ከርስቲያን የተባለችው የምዕመናን ሕብረት ናት ሕብረታችንን እናስጠብቅ ድምጻችን ለቤተከርስቲያናችን!!
+++ ከካም መንገድ ተመለሱ +++
* ዛሬ ቤተክርስቲያናችንን እጅግ በጣም እየጎዳት ያለው ከውጪው የጥቃት እንቅስቃሴ ይልቅ የውስጡ ውስብስብ እንቅስቃሴ ነው። በማወቅም ይሁን ባለማወቅ ብዙዎች ቤተክርስቲያንን ክፉኛ እየጎዷት ነው። በአደባባይ ዕርቃኗን እየገለጡ በአሕዛብ ፊት መዘባበቻ ከማድረግ በዘለለ በምእመናን መካከል ጥርጥርና መለያየት እንዲፈጠር እያደረጉ ነው።
* እርግጥ ነው በቤታችን እጅግ በርካታ ችግሮች አሉ። ቢሆንም ችግሮቹ የውስጣችን እንጂ የአደባባይ አይደሉም። ስለዚህ በቤታችን እንጂ በአደባባይ የምንከራከርባቸው፥ የምንተቻችባቸው፥ የምንሰዳደብባቸው፥ የምንጎሻሸምባቸው ወይም የእውቀታችንን ልክ የምናሳይባቸው ወይም የጽሁፍ ችሎታችንን የምናስመሰክርባቸውም አይደሉም።
* ማንም አዋቂ ነኝ ካለ ለምን በአደባባይ የወንጌሉን የምሥራች በመስበክ የቤተክርስቲያንን የአገልግሎት ግዳጅ አያግዝም? ወይም ምእመናን በመንፈሳዊ ሕይወታቸው እንዲበረቱና ወደ ምሥጢራተ ቤተክርስቲያን እንዲቀርቡ አያንጽም?
* ሌላው ደግሞ በእውቀትና በመንፈሳዊነት መካከል የሰማይና የምድር ያህል ልዩነት መኖሩንም መገንዘብ ያስፈልጋል። አዋቂ ሆነህ መንፈሳዊነቱ ላይኖርህ ወይም መንፈሳዊነቱ ተትረፍርፎ እውቀት ላይኖርህ ይችላል። “ፍቅር ለዘወትር አይወድቅም፤ ትንቢት ቢሆን ግን ይሻራል፤ ልሳኖች ቢሆኑ ይቀራሉ፤ እውቀትም ቢሆን ይሻራል።”(1ኛ ቆሮ.13፥8)
* እንደዚሁ ሙያና መንፈሳዊነትም መለየት አለበት። ማንኛውም የሙያ ደረጃና ምስክርነት ካላጣመሩትና ካልኖሩበት በቀር ከመንፈሳዊነት ጋር ተዛምዶ ላይኖራቸው ይችላል። ሰው ሙያው በሥነ መለኮት ዘርፍ ቢሆንም እንኳ ባለሙያ እንጂ መንፈሳዊ ላይሆን ይችላል። ስለ እግዚአብሔር ሊያውቅ እግዚአብሔርን ግን ላያውቅ፤ ስለ ሃይማኖት ሊያውቅ ሃይማኖቱን ግን በሕይወት ላያውቅና ላይኖርበት ላይጠቀምበትም ይችላል።
* በፌስ ቡክና በዩቲዩብ ሚድያዎች የምንዘረግፋቸው የቤተክርስቲያን የውስጥ ጉዳዮች የሚያንጸው ማንን ነው? መእመናንን ነው እንዳንል ምን ያህሉ ኦርቶዶክሳዊ ነው ፌስ ቡክና ዩቲዩብ የሚጠቀመውና የሚከታተለው? ለመሆኑ እየተደረገ ያለው ስብከት ነው? ማንቃት ነው? መካሰስ ነው? መፈራረጅ ነው? ተቆርቋሪነት ነው? ወይስ ዝናንና ክብርን ማሳደግ ነው? ወይስ የቲፎዞ(ተከታይ) ብዛት ፉክክር ነው።
* የቤተክርስቲያንን የውስጥ ጉዳይና ችግር አደባባይ ላይ ማስጣት ዕውቀትም፥ ተቆርቋሪነትም፥ አገልግሎትም ሊሆን አይችልም ከውጭ ኃይሎች ይልቅ ቤተክርስትያንን በራስ እጅ ማፍረስ እንጂ። በካም መንገድ መጓዝ እንጂ።
* እኔ እላለሁ፣ ማናችንም ከቤተክርስቲያን አንበልጥምና አካሄዳችን እንዲህ ከሆነ፥ መንገዳችን የካም ከሆነ ዕውቀታችንም፥ ተቆርቋሪነታችንም፥ አገልግሎታችንም ይቅርባት። በርግጠኝነት ነው የምነግራችሁ በዚህ አንዳች አይጎድልባትም፤ እንዲያውም እፎይ ትላለች። የካም የግብሩ መጨረሻ በፃድቅ አባቱ መረገም እንደሆነ ቅድስት ቤተክርስቲያን እንዳትረግማችሁ ጥንቃቄ አድርጉ።
* አክቲቪስቶችም ብትሆኑ፥ ምንም ታላቅ ብትባሉ፥ ምንም ሚሊየን ተከታይ ቢኖራችሁ፥ በጀመራችሁበት መንገድ እንደ ሀሳባችሁ ሂዱ እንጂ የኦርቶዶክሳዊት ተዋሕዶ አማኝ ብትሆኑም እንኳን በአደባባይ ከምትራቀቁበት የቤተክርስቲያን የውስጥ ጉዳይ ታቀቡ አይደለም ውጡ!!! ይበልጡኑ ደግሞ በናንተ አያምርም። ፖለቲካና ማኅበራዊ ጉዳይ የአደባባይ ነው፤ የቤተክርስቲያን ጉዳይ ግን የአማኞቿ የውስጥ ጉዳይ ብቻ ነው።
* በማኅበራዊ ሚድያ የአድማጭ ተመልካች መድረክ ከፍታችሁ ለቤተክርስቲያን የማይናቅ አስተዋፅዖ እያበረከታችሁ ያላችሁ አገልጋዮችም በዚህ ረገድ ድካማችሁን የሚያመክንና ዓላማችሁን የሚፃረር ድርጊት ውስጥ እንዳትወድቁ ብርቱ ጥንቃቄ እንድታደርጉ በእግዚአብሄር ርኅራኄ እለምናችኋለሁ። መርሐ ግብር ስታዘጋጁ ከቤተክርስቲያን ጥቅም አኳያ በርዕሰ ጉዳዩ የሚገኘውን ትርፍና ኪሳራ አስቀድማችሁ አስሉ። መርሐ ግብራችሁ ለሁሉም ክፍት ስለሆነ ኦርቶዶክሳውያኑን ብቻ አድሬስ የምታደርጉ መስሏችሁ እንዳትዘናጉ። ስለዚህ በርዕሰ ጉዳይ መረጣ ላይ የውስጥ ችግራችን አጀንዳ ሆኖ አደባባይ እንዳይወጣ ብርቱ ጥንቃቄ አድርጉ።
* እንደኔ እንደኔ የቤት ውስጥ መድረክ እንዲዘጋጅና ተቆርቋሪ ነኝ፥ የቤተክርስቲያንን ችግር የሚፈታ የመፍትሄ ሀሳብ አለኝ፥ በዕውቀቴ ማገዝ እችላለሁ የሚል ኦርቶዶክሳዊ ሁሉ ከማኅበራዊ ሚድያ ወርዶ ወደ እልፍኙ ተሰብስቦ እንዲከራከርና በዚህ የጭንቅ ጊዜ በእውነተኛ ልጅነት ቤተክርስቲያንን ከመከራዋ እንዲታደጋት ምክር፥ ቅስቀሳና ግፊት ብታደርጉ ባለውለታ ትሆናላችሁ።
* ስለዚህ በማወቅም ይሁን ባለማወቅ ወይም ባለማስተዋል ቤተክርስቲያንን የማኅበራዊ ሚዲያ ላይ ሰቅላችሁ መከራዋን የምታበዙባት አባቶች ወንድሞችና እህቶች እባካችሁ ከካም መንገድ ተመለሱ፣ ከእርግማንም ራቁ። (ዘፍ.9፥20-27)
* ሰላመ እግዚአብሔር ከሁላችን ጋር ይሁን። እንደ ቸርነቱ፥ እንደ ይቅርታውና እንደምኅረቱ እንጂ እንደ ኃጢአታችንና እንደ በደላችን አያድርግብን።
የቅዱስ ሲኖዶስ ዋና ጸሐፊ ብፁዕ አቡነ ዮሴፍ የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተክርስቲያን የቅዱስ ሲኖዶስ ምልአተ ጉባኤ የግንቦት ፲፱ ቀን ፳፻፲፫ ዓ.ም ክንውን አስመልክቶ መግለጫ ሰጥተዋል።
- ቅዱስ ሲኖዶስ ግንቦት ፲፱ ቀን ፳፻፲፫ ዓ.ም በጸሎት ጉባኤውን ጀምሯል፡፡
- በቅድሚያ በትናንትናው ዕለት ውሳኔ የሰጠባቸውን ሁለት አጀንዳዎች ቃለ ጉባኤ ቀርቧል፡፡ በዚህም የቅዱስነታቸውን የመክፈቻ ንግግር ቅዱስ ሲኖዶስ አጽድቆታል፡፡
- ሀገራዊ እና ወቅታዊ ጉዳይን አስመልክቶ በሀገራችን በሚታዩት ወቅታዊ ችግሮች የፖለቲካ አለመረጋጋት፣ ስደትና መፈናቀል ዙርያ በሰፊው ተወያይቶ የመፍትሔ ሐሳብ የያዘ ውሳኔ አሳልፏል፡፡ ውሳኔውም በዝርዝር በሚሰጠው መግለጫ የሚገለጽ ይሆናል፡፡
- በተጨማሪ የቅድስት ቤተክርስቲያን የአምልኮ ሥፍራ የሆኑትን የመስቀል እና የጥምቀት ቦታዎች አስመልክቶ ሰፊ ውይይት በማድረግ ቅዱስ ሲኖዶስ ችግሩ የሚፈታበትን ውሳኔ አሳልፏል፡፡ የውሳኔው ዝርዝር በአጠቃላይ መግለጫው ይቀርባል።
የምሥራቅ ጎጃም ሀገረ ስብከትን አስመልክቶ ፡-
- በምስካበ ቅዱሳን ቆጋ ቅ/ኪዳነ ምሕረት አንድነት ገዳም የተፈጸመውን የዶግማ እና ቀኖና ጥሰት ቅዱስ ሲኖዶስ በሰፊው ከተወያየበት በኋላ ሕገ ወጥ በመሆኑ ውሳኔ አሳልፎበታል፡፡ዝርዝሩ በማጠቃለያ መግለጫው የሚገለጽ ይሆናል፡፡
- በምስራቅ ጎጃም ሀገረ ስብከት የክፍሉ ሊቀ ጳጳስ የነበሩት ብፁዕ አቡነ ማርቆስ ወደ መንበረ ፓትርያርክ ጠቅላይ ቤተክህነት ስብከተ ወንጌል እና ሐዋርያዊ ተልዕኮ መምሪያ የበላይ ኃላፊ ሊቀ ጳጳስ እና የጎፋ ደብረ ብሥራት ቅዱስ ገብርኤል ካቴድራል የበላይ ኃላፊ ሊቀ ጳጳስ ሆነው እንዲያገለግሉ ዝውውር አድርጓል፡፡
- የምሥራቅ ጎጃም ሀገረ ስብከትን በተመለከተ ብፁዕ አቡነ ያሬድ የመንበረ ፓትርያርክ ጠቅላይ ጽ/ቤት ዋና ሥራ አስኪያጅ አርሲ ሀገረ ስብከት የሰበካ ጉባዔ ማደራጃ ሊቀ ጳጳስ በሊቀ ጳጳስነት እንዲመሩት ተወስኗል፡፡
- በሰዋሰወ ብርሃን ቅዱስ ጳውሎስ መንፈሳዊ ኮሌጅ እና በደብሩ መካከል ያለውን አለመግባባት በሰፊው ተመልክቶ ቅዱስ ሲኖዶስ የመፍትሔ ውሳኔ አሳልፏል፡፡
- በአዲስ አበባ ሀገረ ስብከት ላይ የሚቀርበውን የመልካም አስተዳደር ችግር ቅሬታ በሰፊው የተመለከተው ቅዱስ ሲኖዶስ የቀረበው የመልካም አስተዳደር ችግር እርምት እንዲደረግበት ሲል ለሀገረ ሰብከቱ ማሳሰቢያ ሰጥቷል፡፡ ዝርዝሩ በማጠቃለያ መግለጫው ይቀርባል።
- በሀገራችን በተለያዩ ጊዜያት እደረሱ ያሉ ችግሮችን አስመልክቶ ሦስት ብፁአን አበው ሊቃነ ጳጳሳት ለቅዱስ ሲኖዶስ መግለጫ አዘጋጅተው እንዲያቀርቡ መርጧል፡፡
- በመላው ሀገሪቱ እና በዓለም አቀፍ ደረጃ ባሉት ኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ አብያተ ክርስቲያናት እና ገዳማት በሙሉ ስለ ሀገራችን ሰላም ጸሎተ ምኅላ እንዲደረግ ቅዱስ ሲኖዶስ ወስኗል፡፡-
- ቅዱስ ሲኖዶስ በቀረቡት አጀንዳዎች ላይ ነገ የማጠቃለያ ውይይት እና ቃለ ጉባኤ ማጽደቅ ካከናወነ በኋላ ሰኞ ግንቦት 23 ቀን 2013 ዓ.ም መግለጫ ይሰጣል፡፡
ምንጭ EOTC TV
ብፁዕ አቡነ ያሬድ የጠቅላይ ቤተ ክህነት ዋና ሥራ አስኪያጅና የአርሲ ሀገረ ስብከት ሊቀ ጳጳስ ከሚመሩት ሀገረ ስብከት በተጨማሪ የምሥራቅ ጎጃምን ሀገረ ስብከት ደርበው እንዲመሩ ቅዱስ ሲኖዶሱ በዛሬው ዕለት ውሳኔ አሳልፏል።
Читать полностью…የሠርቲ ደብረ መድኃኒት መድኃኔዓለም ቤተክርስቲያን ፈለገዮርዳኖስ ሰንበት ትምህርት ቤት የመማሪያ ክፍሎች እጥረት አጋጥሞታል።ይህንንም ለመቅረፍ ይረዳን ዘንድ 3መማሪያ ክፍሎችን ለመስራት አቅዶ እየተንቀሳቀሰ ይገኛል። ስለሆነም አቅማችሁ የፈቀደውን ድጋፍ ታደርጉልን ዘንድ በልዑል እግዚአብሔር ስም እንጠይቃለን።
በገንዘብ ማገዝ ለምትፈልጉ
ኢትዮጵያ ንግድ ባንክ 10006095662319
ህብረት ባንክ 4630412520610015
አቢሲኒያ ባንክ 176147067
ለበለጠ መረጃ
ላቃቸው 0988345695
ሰለሞን 0923079151
ለሰንበት ትምህርት ቤታችን አባላት በሙሉ። ሰንበት ት/ቤታችን ፈለገዮርዳኖስ የበዓለ ሀምሳ ዕለት ጠቅላላ የአመራር ምርጫ ስለምታደርግ ለቀጣይ 3ዓመታት ሰንበት ትምህርት ቤቷን የሚመሯትን መሪዎች ጥቆማ ከቻላችሁ በአካል ጥቆማ ሳጥን ውስጥ
በአካል መገኘት ያልቻላችሁ ደግሞ
ለወንድማችን ኤፍሬም ስልክ
0920107746 በtelegram inbox ላኩልን።
ክፍሎቹ
ሰብሳቢ
ም/ሰብሳቢ
ፀሀፊ
ሰበካጉባኤ ተወካይ
ትምህርት ክፍል
መዝሙር ክፍል
ቁጥጥር ክፍል
ህፃናት ክፍል
ልማት ክፍል
ንብረት ክፍል
ሂሳብ ክፍል
ገንዘብ ያዥ
ኪነጥበብ ክፍል
ባለፈው ዓመት በሕገወጥ መንገድ "ጵጵስና" ተሹመናል በማለት ሲንቀሳቀሱ የነበሩ አካላት በዛሬው ዕለት በዚሁ ሕገወጥ መንገድ በመቀጠል "መንበረ ጴጥሮስ" የተባለ ሕገወጥ ቤተ ክህነት መሥርተናል አሉ !
ጥር 14 ቀን 2016 ዓ.ም (ተ.ሚ.ማ/አዲስ አበባ)
+++
በኦሮሚያ ክልል ፖለቲካዊ ካባ የደረበ አጀንዳ ይዘው የኢትዮጵቻ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያንን ለመከፋፈል እየተንበሳበሱ የሚገኙት በቀድሞ ስማቸው "አባ" ገ/ማርያም ነጋሳ እና ግብረ አበሮቻቸው ሕገወጥ ተግባራቸውን በመቀጠል "መንበረ ጴጥሮስ" የተባለ ቀኖናዊ መሠረት የሌለው እና ሕገወጥ የሆነ ቤተ ክህነት መሥርተናል ሲሉ ስትራቴጂክ አጋሮቻቸው በሆኑ የሚዲያ ተቋማት አማካይነት በሰጧቸው መግለጫዎች አስታውቀዋል።
በቋንቋችን ለመማር እና በነጻነት ለማምለክ ለዘመናት ተከልክለናል በሚል ሀሰተኛ ሽፋን ይህን እንቅስቃሴ እያደረጉ የሚገኙት ነውጠኛ መነኮሳት በመንግስት አደራዳሪነት ችግሩ ተፈትቷል ከተባለ በኋላ የሚያደርጓቸው እንቅስቃሴዎች ስምምነቱን የጣሰ እና በሚዲያዎች እና ቤተ ክርስቲያንን ለማጥፋት በሚጥሩ ኃይሎች ድጋፍ እየተደረገላቸው እንደሚገኝ ማሳያ ነው።
ልክ የዛሬ ዓመት ጥር 14 ቀን 2015 ዓ.ም ሕገኸጥ ሢመተ ኤጲስ ቆጶሳት በመፈፀም የኦሮሚያና የብሔር ብሔረሰቦች ሲኖዶስ በሚል "አብዮታዊ ዴሞክራሲን" እናት ፍልስፍና አድርጎ ተመሠረተ የተባለው የመነኮሳት ስብስብ በአሁኑ ወቅትም ከ5 በማይበልጡ የቀድሞ መነኮሳት የቤተ ክርስቲያንን አንድነት ለማፍረስ የውክልና እንቅስቃሴ ላይ መሆናቸውን በዛሬው ዕለት ይፋ አድርገዋል።
"ለትግራይና ለአማራ ሲኖዶስ እንዲቋቋም ተፈቅዷል" በማለት ሀሰተኛ እና በቤተ ክርስቲያኒቱ ያልተደረገን ነገር ማስተላለፋቸው ሳያንስ "ለ5 ኪሎ ሲኖዶስ" እንዳትገዙ በማለት ጭምር ሕዝብን በሕዝብ ለማነሳሳት ከፍተኛ ቅስቀሳ እና የጦርነት አዋጅ እያወጁ ይገኛሉ።
#Ethiopia
#Tewahedo_Media_Center
#TMC_Addia_Ababa
ተዋሕዶ ሚዲያ ማዕከል
እውነተኛ የተዋሕዶ ድምፅ
የዩቲዩብ ቻናላችንን ሰብስክራይብ ያድርጉ
TMC1" rel="nofollow">https://youtube.com/@TMC1
የቴሌ ግራም ቻናላችንን ይቀላቀሉ ፤ ፈጣን መረጃዎችን ያግኙ /channel/tewahedomediacenter
አጫጭር ትምህርታዊ እና ወቅታዊ መረጃዎችን ለማግኘት የቲክ ቶክ አማራጫችንን ይመልከቱ
https://vm.tiktok.com/ZM8WVucY7/
ብፁዕ አቡነ ሄኖክ የአዲስ አበባ ሀገረ ስብከት ሊቀ ጳጳስ በዓለ ጥምቀትን አስመልክቶ በሀገረ ስብከታቸው ጽ/ቤት መግለጫ ሰጥተዋል !
ጥር 8 ቀን 2016 ዓ.ም
+++
ብፁዕ አቡነ ሄኖክ የአዲስ አበባ ሀገረ ስብከት ሊቀ ጳጳስ በዓለ ጥምቀትን አስመልክቶ በሀገረ ስብከታቸው ጽ/ቤት መግለጫ ሰጥተዋል !
የብፁዕነታቸው ሙሉ መግለጫ ከዚህ እንደሚከተለው ቀርቧል።
በስመ አብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ አሐዱ አምላክ አሜን
“ ወኪያነኒ ይእዜ ያድኅነነ በአርኣያሁ በጥምቀት ።” ጥምቀት ምሳሌ ሆኖ አሁን ያድነናል ። 1ኛ ጴጥ 3፥ 21
በመላው ዓለም የምትገኙ የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን ልጆች ምእመናንና ምእመናት
የሰላም አለቃ ፣ የዘለዓለም አባት ጌታችን አምላካችን መድኃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ እንኳን በሰላም ጠብቆ ለ2016 ዓ.ም በዓለ ጥምቀት በጤና አደረሰን አደረሳችሁ።
የጥምቀት በዓል ነጻነታችን የታወጀበት ፣ የዕዳ ደብዳቤያችን የተፋቀበት የባርነት ቀንበር የተሰበረበት ፣ የሚናፈቀው የእግዚአብሔር ድምፅ የተሰማበት ፣ ምሥጢረ ሥላሴ የተገለጠበት ፣ ልጅነትን የምንቀበልበት ጸጋ የተመሠረተበት ከጌታችን መድኃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ከዘጠኙ ዐበይት በዓላት መካከል አንዱ በመሆኑ በኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን በልዩ ድምቀት ይከበራል።
ይኸውም በመዲናችን አዲስ አበባ ከተማ የቅዱስ ሲኖዶስ ርዕሰ መንበር እና ታላቁ አባታችን ብፁዕ ወቅዱስ አቡነ ማትያስ ቀዳማዊ ፓትርያርክ ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት ዘኢትዮጵያ ሊቀ ጳጳስ ዘአክሱም ወእጨጌ ዘመንበረ ተክለሃይማኖት በተገኙበት በጃን ሜዳ ባሕረ ጥምቀት የሚከበረው በዓል እንደተጠበቀ ሆኖ በጠቅላላ በከተማዋ ውስጥ ከ78 ያላነሱ የጥምቀት በዓል ማክበሪያ ሥፍራዎች ይገኛሉ። በዚህም መሠረት በዓሉ በተቀናጀ መልኩ ለማስኬድ ሲባል በእያንዳንዱ ክ/ከተማ ላይ ግብረ ኃይል በማደራጀት እና ተጠሪነታቸውንም ለሃገረ ስብከቱ ሥራ አስኪያጅ በማድረግ በሰፊው ዝግጅት ተደርጓል በየባሕረ ጥምቀቱም በብዙህ ሺህ የሚቆጠሩ ምእመናን ይሳተፉበታል።
ሀገረ ስብከቱም በዓሉ በሰላም እንዲከበር ከሚመለከታቸው አካላት ጋር በመሆን ያካሄደውን ሰፊ ዝግጅት አጠናቅቋል።
የተወደዳችሁ የመንፈስ ቅዱስ ልጆቻችን
ምእመናንና ምእመናት
ሰላም የጌታ ድንቅ ስጦታ እንደሆነና ደግሞም ማንም እንዳይወስድብን አጽንተን ልንይዘው የሚያስፈልገን የሁሉም መሠረት ነው ፣ ሰላም ከሌለ በዓላትን ማክበር ይቅርና ወጥቶ መግባት ፣ ሠርቶ መብላት የማይቻልበት ሁኔታ ሊፈጠር እንደሚችል መገመት ብቻ ሳይሆን ከጥቂት ዓመታት በፊት በተግባር ያየነው መሆኑ ሊዘነጋ አይገባም።
ኦርቶዶክሳዊት ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያናችን ሰላምን በማስጠበቅ ረገድ እና ለሰላም ዘብ በመቆም ቀዳሚ መሆኗ ይታወቃል።
ከላይ እንደተገለጸው በሰላም አምላክ የተመሰረተን እና የተሰጠን ጸጋ ማስጠበቅ የእያንዳንዱ አማኝ ግዴታ ነው። እንዲሁም የጥምቀት በዓል የአደባባይ በዓል እንደመሆኑ መጠን ሰላምን የመጠበቅ እና የማስጠበቅ ድርሻ በእያንዳንዳችን ላይ እንዳለ በመገንዘብ ሐዋርያዊት ፣ ብሔራዊት እና ዓለምአቀፋዊት ለሆነችው የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን በሚመጥን መልኩ በዓሉን ማክበር ያስፈልጋል።
ስለሆነም ይህንን በዓል በምናከብርበት ወቅት ጌታችን መድኃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ የተወልንን ሰላም በመንከባከብ እና በመተግበር ፍፁም ክርስቲያናዊ በሆነ ሥነ ምግባር እና አካሄድ በዓላችንን ልናከብር ይገባናል።
ይህ በእንዲህ እያለ
1. መንፈሳዊ ሰልፋችን ከነአለባበሳችን የጉዞውን ቅደም ተከተል በጠበቀ መልኩ ሥርዓተ ቤተ ክርስቲያንን ማዕከል ያደረገ እና ለበዓሉ ድምቀት የሚሰጥ እንዲሆን
2. ወደ ባሕረ ጥምቀቱ የሚደረገው ጉዞ የጌታችን መድኃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ከገሊላ ወደ ዮርዳኖስ ፤ ከልዕልና ወደ ትህትና መውረዱን የሚያሳይ መንፈሳዊ እሴት ያለበት እንደሆነ የታወቀ በመሆኑ በጉዞው ላይ የሚደረግ እያንዳንዱ ክንውን አስተማሪ ሊሆን ይገባል። ሰልፉም ውበትና መስመር እንዲኖረው ይጠበቃል። በመሆኑም የአምልኮ መርሐግብር እያከናወኑ ዋዛ ፈዛዛ በመከወን የሚደረግ ጉዞ ከቤተ ክርስቲያናችን ቀኖና ጋር ፈጽሞ የሚጣረስ በመሆኑ በተለይ ወጣቶች በዚህ ረገድ ከካህናት አባቶች የሚሰጡ መመሪያዎችን በመቀበል የበዓሉን አከባበር በደመቀ መልኩ ማከናወን እንዲቻል እንዲደረግ።
3. ሰዓትን በተመለከተ ጥር 10 ቀን 2016 ዓ.ም ታቦታተ ምሥዋዕ ከመንበረ ክብር ስለሚነሱበት ሰዓት በወጣው መርሐ ግብር መሠረት ከጠዋቱ 4:00 ሰዓት ዋዜማ ስብሐተ እግዚአብሔር ይቆማል። በማስቀጠል 7 ሰዓት ሲሆን በመላዋ አዲስ አበባ አብያተ ክርስቲያናት ለ10 ደቂቃ የደወል ድምፅ ይሰማና መነሻ ሰዓት ይሆናል።
- የጥር 11 የጥምቀት በዓልና የጥር 12 የቃና ዘገሊላ በዓልን በተመለከተም መነሻ ከጠዋቱ 3:00 ሰዓት እንዲሆንና መድረሻውም ከ 7 - 10 ሰዓት ባለው ጊዜ እንዲሆን እያሳሰብን በዓሉ የትህትና እና የፍቅር እንደመሆኑ መጠን ከእኛ የሚጠበቁ ክንውኖችን በመፈፀም ለበዓሉ በድምቀት መከበር አስተዋጽኦ ልናደርግ ይገባል።
4. አገልግሎታችን ሥርዓተ ቤተ ክርስቲያንን የተከተለ መሆን ስለሚገባው አስፈላጊውን ግብዓት ከማቅረብ በቀር ከአበው ካህናት ውጭ በየትኛውም መልኩ በሌሎች አካላት የሚደረግ ማዕጠንት ተገቢነት የሌለው እና ከቀኖና ቤተ ክርስቲያን ውጭ በመሆኑ እንዳይፈፀም የሚመለከታቸው አካላትም ተገቢውን ክትትል እንዲያደርጉ እንዲሁም በማዕጠንት አገልግሎቱ በካህናት አባቶች በሰፊው እንዲሰጥ ይሁን።
5. በረከተ ጥምቀቱን የማድረስ እና የመርጨት ክንውን የሚፈጸመው በሥርዓተ ቤተ ክርስቲያን መሠረት በካህናት ብቻ መሆኑ ይታወቃል በዚሁ መሠረት ቀኖና ቤተ ክርስቲያን ባለማወቅ ምክንያት ሥርዓቱ እንዳይፈርስ ወጣት ልጆቻችንም ይህን አውቃችሁ ሥርዓቱን እንድትጠብቁና አገልጋዮች ካህናትም ድርሻችሁን እንድትወጡና ሕዝቡን እንድታገለግሉ እናሳስባለን ።
6. ከልክ ያለፉ እና በተደጋጋሚ የተስተዋሉ ከሥርዓት ውጭ በሆነ መልክ ለታቦታቱ ክብር በማይመጥኑ ሥፍራዎች ላይ እንዲቆሙ የሚደረገው ልምድ እንዲታረምና ሁሉም በሕግና በሥርዓት እንዲመራ።
7. ምእመናን እንደተለመደው ራሳችሁን ከሁከትና አላስፈላጊ ነገሮች በማራቅ በትዕግሥት እና በሆደ ሰፊነት በዓሉን እንድናከብር እያሳሰብን ችግሮች ቢፈጠሩ እንኳን ከሚመለከታቸው የጸጥታ አካላት ጋር በመቀናጀት በተናበበ መልኩ እልባት እንዲሰጣቸው ሊደረግ ይገባል።
በመጨረሻም ፦
በዓለ ጥምቀትን ስናከብር በፍፁም ወንድማዊ ፍቅር የተራቡትን በማብላት ፣ የተጠሙትን በማጠጣት ፣ የታረዙትን በማልበስ በተለያዩ ምክንያቶች ከቀያቸው የተፈናቀሉ ወገኖችን በመርዳትና በመደገፍ ፤ የመድኃኒታችን የኢየሱስ ክርስቶስን ትህትና አብነት በማድረግ በመተሳሰብና በመደጋገፍ እንዲሆን እናሳስባለን።
ወስብሐት ለእግዚአብሔር
እግዚአብሔር ኢትዮጵያንና ሕዝቧን ይባርክ አሜን
አባ ሄኖክ
በኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን
የአዲስ አበባ ሀገረ ስብከት ሊቀ ጳጳስ
ጥር 8 ቀን 2016 ዓ.ም አዲስ አበባ፤ ኢትዮጵያ
የጥር 7ወረብ
በፈቃደ
በፈቃ'ደ አቡሁ ወረ'ደ' ተአንገደ ሀበ ማርያም
በድንግልናሀ ንፁሕ' በድንግልናሀ' ንፁሕ እግዚአብሄር ተወልደ
ይህ ' ያለበት ቦታ መርግድ ነው
ሰላም የፈለገ ዮርዳኖስ አባላት በሙሉ ተቋርጦ የነበረዉ የመዝሙር ቅጂ አሁን ይቀጥላል: እናም በፊት እንደምታረጉት አሁንም በደንብ እንድታጠኑ ስንል በተህትና እንጠይቃለን ።
Читать полностью…🔔
ኦርቶዶክሳዊ ያልሆነ ጠባይ !
ኦርቶዶክሳዊ ስብዕና ዓይኖቹ ዘወትር ወደ ቤተክርስቲያን ናቸው፡፡ ከእናቱ ከቤተክርስቲያን በቀር በልቦናው የተሳለ ሌላ ነገር አይኖርም፡፡ በየትኛውም የፈተና ዘመን በቤተክርስቲያን ጸንቶ መኖር ይቻለዋል፡፡ በአገልግሎት ላይ ያሉ የቤተክርስቲያን "መምህራንን" አድናቂና ተከታይ መሆን ኦርቶዶክሳዊ ጠባይ አይደለም፡፡ "መምህራኑንም" በከንቱ ውዳሴ ጠልፎ ለፈተና መዳረግ ነው፡፡ አይሁንና ድንገት ቢስቱና ከሃይማኖት መስመር ቢወጡ በቤተክርስቲያን ላይ ያልታነጹ የግለሰብ አድናቂና ተከታይ የሆኑ ብዙዎች ይሰናከላሉ፡፡ በዘመነ ሃራጥቃ ተሃድሶ የተፈጠረው እንዲህ ያለ ፈተና ነው፡፡ ገና በፈተናና በተጋድሎ ላይ ያሉ ግለሰቦችን ተከታይና አድናቂ መሆን ለብርቱ ፈተና ይዳርጋልና እንዲህ ካለው ነገር እንጠበቅ !
🔔
✤ የአቡነ ሽኖዳ ቢሒሎች ✤
💎ቅዱስ መሆንን ብቻ መፈለግ በቂ አይደለም ቅዱስ የምንሆንበትም መንገድ እውነተኛ መሆን አለበት የሰዎች መንገድ ግን ብዙ ጊዜ የስሕተት ስለሆነ ይወድቃሉ ይነሳሉ።
💎የአገልግሎት ስኬት ብዙ ሕዝብ መሰብሰብ አይደለም ሕይወታቸውን ለውጦ ወደ እግዚአብሔር ማድርስ ነው እንጂ።
💎ከኃጢአት መሸሽ ውጫዊ የሆነ ነገር ነው ከኃጢአት ነጻ መውጣት ግን የልብ ውስጣዊ ሁኔታ ነው።
💎አንተ ታማኝ ሆነህ በፍቃድህ ከምትሰራቸው ኃጢአቶች ከታቀብክ እግዚአብሔር ደግሞ ያለፍቃድህ እንድትሠራቸው ከሚመጡብህ ኃጢአቶች ሁሉ ይጠብቅሃል።
የቅዱስነታቸው በረከታቸው ይደርብን!
🌿🍂🌿🍂🌿🍂🌿🍂🌿
ደብረ ምጥማቅ
ግብጽ በምትገኘው በእመቤታችን ቅድስት ድንግል ማርያም ስም በተሠራችው ደብረ ምጥማቅ ቤተ ክርስቲያን ጉልላት ላይ ድንግል ማርያም ከግንቦት ፳፩ ጀምሮ እስከ ፳፭ ቀናት በተከታታይ በመገለጧ ሕዝበ ክርስቲያን በዓሏን ያከብራሉ፡፡
እመቤታችን ቅድስት ድንግል ማርያም ከልጇ ጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ጋር ወደ ምድረ ግብጽና ኢትዮጵያ በተሰደደች ጊዜ በአሁኑ ጊዜ ደብረ ምጥማቅ ተብሎ በሚጠራው ቦታ ላይ ዐርፈው ነበር:: ጌታችንም ቦታውን ባርኮ የእርሷ መገለጫ እንዲሆን ቃል ኪዳን ገብቶላት ስለነበር ጊዜው በደረሰ ሰዓት ደብረ ምጥማቅ ተገድሞ የበርካታ መነኮሳት በዓት ሆነ:: በደብረ ምጥማቅም እመቤታችንም ቅድስት ድንግል ማርያም ብርሃን ተጎናጽፋና በሠራዊት መላእክት ታጅባ ተገልጣለች፤ በዚያን ጊዜም ሱራፌል ማዕጠንታቸውን ይዘው ሰገዱላት፤ እንዲህ እያሉም አመሰገኗት፤ ‹‹አብ በሰማይ አይቶ እንዳንቺ ያለ አላገኘም፤ ባንቺም ሰው ሆነ፡፡›› (መጽሐፈ ስንክሳር ግንቦት ፳፩ ገጽ. ፫፻፲፰)
ሰማዕታትም እንደየክብራቸው ማዕረግ ለእመቤታችን ድንግል ማርያም ሊሰግዱ ረቂቃን በሆኑ ፈረሶቻቸው ተቀምጠው ወደ እርሷ ቀረቡ፤ በመጀመሪያ ሊቀ ሰማዕታት ቅዱስ ጊዮርጊስ ከሁሉም ቀድሞ ከሰገደላት በኋላ ሌሎቹም በተመሳሳይ መልኩ ሰገዱላት፡፡ ከዚህም በኋላ ቅዱስ መርቆሬዮስ በዱሪ ፈረስ ተቀምጦ ወደ እርሷ በመምጣት ሰገደላት፡፡ ጻድቃን በአንድነት ቀርበው ለክብሯ ሰገዱላት፤ ቀጥሎም በንጉሥ ሄሮድስ በግፍ የተገደሉት ሕፃናት ለእርሷ ሰገዱ፤ በደስታና በፍቅርም ተጫወቱ፡፡ በዚያ የተሰበሰቡትም ክርስቲያኖች፣ እስላሞችና አረማውያን ይህን በአዩ ጊዜ ደስታ ሞልቶባቸው በተለየ ዓለም ያሉ ይመስላቸው ነበር፡፡ (መጽሐፈ ስንክሳር ግንቦት ፳፩ ገጽ. ፫፻፲፰)
አባ ጽጌ ድንግልም በደብረ ምጥማቅ በታላቅ ክብር ለምእመናን የታየችው የአምላክ እናት የድንግል ማርያምን መገለጥ በማኅሌተ ጽጌ ድርሰቱ እንዲህ በማለት ገልጾታል፤ ‹‹አመ ትበርቂ በደብረ ምጥማቅ ኀምሰ ዕለታተ፣ ትእምርተ ገጽኪ ይርአይ እስከ ይትነሣእ ዘሞተ፣ሚ መጠነ ማርያም ታሥተፌሥሒ ትፍሥሕተ፣ ኅድጊሰ ጽጌ ፍቅርኪ በጊዜ ንቃሁ መዓልተ፣ ብፁዕ ዘርእየኪ በሕልሙ ሌሊተ፤ የፊትሽን መልክ ያይ ዘንድ የሞተ ሰው እስኪነሣ ድረስ በደብረ ምጥማቅ ለአምስት ቀናት ያህል በተገለጽሽ ጊዜ ማርያም ምን ያህል ደስ ታሰኚ ኖሯል! በቀን የታየው የፍቅርሽ አበባ ይቅርና ሌሊት በሕልሙ ያየሽ ምስጉን ነው፡፡›› (ማኅሌተ ጽጌ)
በደብረ ምጥማቅ ከተሰበሰቡት ሕዝብ መካከል እናትና አባታቸው፣ ዘመዶቻቸው እንዲሁም ባልንጀሮቻቸው የሞቱባቸው ሰዎች ቅድስት ድንግል ማርያም እንድታሳያቸው በለመኗት ጊዜ እንደ ቀደመ መልካቸው አድርጋ ታሳያቸው ነበር፡፡ አንዳንዶች ደግሞ መሀረባቸውን ወደ ላይ በሚወረውሩት ጊዜ እርሷ የወደደቻቸው እንደሆነ በእጅዋ ተቀብላ መልሳ ትጥልላቸዋለች፤ ሁሉም ለበረከት ይካፈሉታል፡፡ እነርሱም ወደ ቤታቸውም ለመሄድ በሚፈልጉ ሰዓት ተሰናብተውና በተባርከውም ይሄዳሉ፡፡ (መጽሐፈ ስንክሳር ግንቦት ፳፩ ገጽ. ፫፻፲፱)
የደብረ ምጥማቅና የአካባቢዋ ሰዎች እመቤታችን ድንግል ማርያምን ያዩባቸው ቀናት አረማውያኑ ያመኑበት፣ የበደሉት በምልጃዋ ቸርነትን ምሕረትን ያገኙበት፣ ያመኑት ደግሞ የተባረኩበት ዕለታት ነበሩ፡፡ ሕዝቡ እርሷን ተመኝተው ያጡት ወይንም ጠይቀው ያልተፈጸመላቸው ምንም ነገር አልነበረም:: ነቢያት፣ ሐዋርያት፣ ጻድቃን፣ ሰማዕታት፣ ደናግል፣ መነኮሳት መላእክትና ሊቃነ መላእክትም ለድንግል ማርያም ሲሰግዱ ይታዩ ነበር::
ከዚህ በኋላ በዘመናት ይኖሩ የነበሩ ቅዱሳን የአምላክን እናት ለማየት ብዙዎች ተመኝተዋል፤ የመልክአ ማርያም ደራሲ ዓፄ ዘርዓ ያዕቆብ የአምላኩን እናት ቅድስት ድንግል ማርያምን ፊቷን ለማየት ሽቶ ‹‹ሰላም ለመልክእኪ ዘተሠርገወ አሜረ ዘያበርህ ወትረ ፍቅርትየ አንቲ እንተ ታበድሪ ፍቅረ አርእዪኒ ገጸ ዚኣኪ ማርያም ምዕረ ዘኢይሰምዖ ካልእ እንግርኪ ነገረ፤”
ዘወትር የሚያበራ ፀሐይን ጌጥ ላደረገ መልክሽ ሰላምታ ይገባል፤ ፍቅርን የምትመርጪ (የምታስቀድሚ) አንቺ የምወድሽ ማርያም ሌላ የማይሰማው ነገርን እነግርሽ ዘንድ አንድ ጊዜ ያንቺን ፊት ግለጪልኝ (አሳይኝ)›› በማለት ተማፅኗታል፡፡ (መልክአ ማርያም)
ነቢዩ ዳዊት ‹‹ወለገጽኪ ይትመሐለሉ ኲሎሙ አሕዛብ ብዑላነ ምድር፤ የምድር ባለጠጎች አሕዛብ ሁሉ በፊትሽ ይማለላሉ›› በማለት ትንቢትን እንደተናገረላት በርካት ቅዱሳን ሰዎች ቅድስት ድንግል ማርያምን ተገልጻላቸው ለማየት ተመኝተዋል፤ ልመናቸው ተሰምቶላቸው የአምላክ እናት ተገልጻላቸው ፊቷን ለማየትን ክብሯን ለመግለጥ ቅዱሳን አባቶች፣ ጻድቃን ሰማዕታት በቅተዋል፡፡ ይህም የሆነው በፍጹም ልቡናቸው በመማፀናቸውና በፍጹም ትጋት የጌታቸውን እናት ሲያገለግሉ በመኖራቸው እንደሆነ የጻድቃኑ ገድል ምስክር ነው፡፡ እነርሱም ሌት ከቀን ምኞታቸው ይሳካላቸው ዘንድ በጸሎት ይማፀኑ ነበር፡፡ (መዝ. ፵፬፥፲፪)
እመቤታችን ድንግል ማርያምም ጸሎታቸውን ሰምታ ያሰቡትን ትፈጽምላቸው ነበር፤ ምኞታቸው ከተሳካላቸው ቅዱሳን አባቶች መካከል አባ ይስሐቅ አንዱ ነው፤ ይህ ቅዱስ አባትም እመቤታችን ቅድስት ድንግል ማርያምን በፍጹም ልቡናው ይወዳት ስለነበር ለሰባት ዓመታት አምላኩን ክብርት እናቱን ያሳየው ዘንድ በጸሎቱ ተማጸነ፡፡ ዘወትር ከሠርክ ጸሎት በኋላ ሌሎች መነኮሳት ለመኝታ ወደ የበዓታቸው ሲሄዱ አባ ይስሐቅ ወደ ቤተ ክርስቲያን በመሄድ በቅድስት ድንግል ማርያም ሥዕሏ ፊት ቆሞ ሦስት መቶ ስግደትን እየሰገደ ይማፀን ነበር፡፡ ከስግደቱም ጋር ‹‹ኦ እግዚእየ ኢየሱስ ክርስቶስ አርእየኒ እመከ አሐተ ሰዓተ፤ ጌታዬ ኢየሱስ ክርስቶስ ሆይ ለአንዲት ሰዓት እናትህን አሳየኝ›› እያለ ይጸልይ ነበር፡፡ በእንደዚህም ሁኔታ ለሰባት ዓመት ከቈየ በኋላ እመቤታችን ቅድስት ድንግል ማርያም በታላቅ ግርማ ተገለጸችለት፤ የልቡም መሻት ምን እንደሆነ ጠየቀችው፤ አባ ይስሐቅም የርሷን ገጽ ያዩ ዐይኖቹ ሌላ ነገርን ማየት እንደማይሹ ነገራት፤ ከተወደደ ልጇ ኢየሱስ ክርስቶስ እንድታማልደውም ተማጸናት፡፡ ቅድስት ድንግል ማርያምም ልመናውን ተቀበለች፤ ከዚያም በኋላ የዕረፍቱ ቀን ከሦስት ቀን በኋላ መሆኑን አሳወቀችው፤ ባርካውም ወደ ሰማይም በክብር ዐረገች፤ ይህ ቅዱስ አባት ይስሐቅም እርሷን ካየ በሦስተኛው ቀን ዐረፈ፡፡ (መጽሐፈ ስንክሳር ታኀሣሥ ፳፩ ገጽ.፬፻፺፪)
እመቤታችን ቅድስት ድንግል ማርያም በደብረ ምጥማቅ ተገልጣ የሕዝቡን ምኞት እንደፈጸመችላቸው የእኛንም በጎ መሻት ትፈጽምልን፤ አሜን፡፡
© Mahibere Kidusan
ብፁዕ አቡነ ያሬድ የጠቅላይ ቤተ ክህነት ዋና ሥራ አስኪያጅና የአርሲ ሀገረ ስብከት ሊቀ ጳጳስ ከሚመሩት ሀገረ ስብከት በተጨማሪ የምሥራቅ ጎጃምን ሀገረ ስብከት ደርበው እንዲመሩ ቅዱስ ሲኖዶሱ በዛሬው ዕለት ውሳኔ አሳልፏል።
Читать полностью…በምስካበ ቅዱሳን ቆጋ ቅ/ኪዳነ ምሕረት አንድነት ገዳም የተፈጸመውን የዶግማ እና ቀኖና ጥሰት ቅዱስ ሲኖዶስ በሰፊው ከተወያየበት በኋላ ሕገ ወጥ በመሆኑ ውሳኔ አሳልፎበታል፡፡ ዝርዝሩ በማጠቃለያ መግለጫው የሚገለጽ ይሆናል፡፡
••••
በምስራቅ ጎጃም ሀገረ ስብከት የክፍሉ ሊቀ ጳጳስ የነበሩት ብፁዕ አቡነ ማርቆስ ወደ መንበረ ፓትርያርክ ጠቅላይ ቤተክህነት ስብከተ ወንጌል እና ሐዋርያዊ ተልዕኮ መምሪያ የበላይ ኃላፊ ሊቀ ጳጳስ እና የጎፋ ደብረ ብሥራት ቅዱስ ገብርኤል ካቴድራል የበላይ ኃላፊ ሊቀ ጳጳስ ሆነው እንዲያገለግሉ ዝውውር አድርጓል፡፡
••••
የምሥራቅ ጎጃም ሀገረ ስብከትን በተመለከተ ብፁዕ አቡነ ያሬድ የመንበረ ፓትርያርክ ጠቅላይ ጽ/ቤት ዋና ሥራ አስኪያጅ አርሲ ሀገረ ስብከት የሰበካ ጉባዔ ማደራጃ ሊቀ ጳጳስ በሊቀ ጳጳስነት እንዲመሩት ተወስኗል፡፡
••••
በሰዋሰወ ብርሃን ቅዱስ ጳውሎስ መንፈሳዊ ኮሌጅ እና በደብሩ መካከል ያለውን አለመግባባት በሰፊው ተመልክቶ ቅዱስ ሲኖዶስ የመፍትሔ ውሳኔ አሳልፏል፡፡
••••
በአዲስ አበባ ሀገረ ስብከት ላይ የሚቀርበውን የመልካም አስተዳደር ችግር ቅሬታ በሰፊው የተመለከተው ቅዱስ ሲኖዶስ የቀረበው የመልካም አስተዳደር ችግር እርምት እንዲደረግበት ሲል ለሀገረ ሰብከቱ ማሳሰቢያ ሰጥቷል፡፡ ዝርዝሩ በማጠቃለያ መግለጫው ይቀርባል።
••••
በሀገራችን በተለያዩ ጊዜያት እደረሱ ያሉ ችግሮችን አስመልክቶ ሦስት ብፁአን አበው ሊቃነ ጳጳሳት ለቅዱስ ሲኖዶስ መግለጫ አዘጋጅተው እንዲያቀርቡ መርጧል፡፡
••••
በመላው ሀገሪቱ እና በዓለም አቀፍ ደረጃ ባሉት ኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ አብያተ ክርስቲያናት እና ገዳማት በሙሉ ስለ ሀገራችን ሰላም ጸሎተ ምኅላ እንዲደረግ ቅዱስ ሲኖዶስ ወስኗል፡፡
••••
ቅዱስ ሲኖዶስ በቀረቡት አጀንዳዎች ላይ ነገ የማጠቃለያ ውይይት እና ቃለ ጉባዔ ማጽደቅ ካከናወነ በኋላ ሰኞ ግንቦት 23 ቀን 2013 ዓ.ም መግለጫ ይሰጣል፡፡
••••
EOTC TV
••••
📱📲 #ኦርቶዶክሳዊ ሚዲያን #JOIN እንዲሁም #ሼር በማድረግ #ለኦርቶዶክሳውያን #መልዕክቱን እናድርስ።
━━━━⊱✿⊰━━━━
ይ🀄️ላ🀄️ሉን
❤️ የአማኑኤል ልጆች ቴሌግራም ቻናላችን ሊንክ፦
👉 /channel/Terbinos
❤️ የአማኑኤል ልጆች የፌስቡኩ ገፃችን ሊንክ፦
👉 https://www.fb.me/terbinos