medhanialem | Unsorted

Telegram-канал medhanialem - የቃሊቲ ደብረ መድኃኒት መድኃኔዓለም ቤተክርስቲያን ፈለገዮርዳኖስ ሰ/ት/ቤት

189

Subscribe to a channel

የቃሊቲ ደብረ መድኃኒት መድኃኔዓለም ቤተክርስቲያን ፈለገዮርዳኖስ ሰ/ት/ቤት

የጉዞ ዋጋ መስተንግዶን ጨምሮ 300ብር

Читать полностью…

የቃሊቲ ደብረ መድኃኒት መድኃኔዓለም ቤተክርስቲያን ፈለገዮርዳኖስ ሰ/ት/ቤት

https://m.tiktok.com/v/7267649660720811270.html?u_code=dchmdmi1iieh42&preview_pb=0&sharer_language=en&_d=dchme1gkk75k0h&share_item_id=7267649660720811270&source=h5_m&timestamp=1711098169&user_id=6832582546871796741&sec_user_id=MS4wLjABAAAAlRZ1G1jUiXS3vV-rgzkXmnum18eSCMasJunD-dA56QopWP3RpkpRBFLDFdqm1rX5&utm_source=telegram&utm_campaign=client_share&utm_medium=android&share_iid=7126025770912515842&share_link_id=4e9614d2-aca2-4234-85ce-dcdab379fda1&share_app_id=1340

Читать полностью…

የቃሊቲ ደብረ መድኃኒት መድኃኔዓለም ቤተክርስቲያን ፈለገዮርዳኖስ ሰ/ት/ቤት

በስመአብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ አሐዱ አምላክ አሜን!!

ሰንበት ትምህርት ቤታችን ለእኛ!!

አንደበታችን ሳይፍታታ ኮልታፋ አንደበታችንን የፈታች። ገና በለጋ እድሚያችን እግዚአብሔር ማመስገን እንድንችል "እምዬ ማርያም ምን ሆናለች፣ መጽሐፍ ቅዱሴን እወዳታለው " በሚሉ እና ሌሎች የጨዋታ መዝሙሮች ምስጋናን እንድንለምድ ያደረገች። መልካም የሆኑ ምንገድ ስንስት መንገድ የሚያስይዙ፣ ሥሥናጠፋ የሚግስጹ፣ ስንዝል የሚያበርቱእና በሀዘንም በደስታችንም ቀን ከማንም በፊት እን ከማንም በላይ የሚሆኑልንን የልብ ጓደኞቻችንን የሰጠችን ምን ብንጥር በሰንበት ትምህርት ቤት ካገኘናቸው ጓደኞቻችን የተሻለ ከሌላ ቦታ ልናገኛቸው የማንችላቸውን ጓደኞች የሰጠች ። ብንቸገር የምንረዳበት ብንታመም የምንጎበኝበት እና ጸሎት እንዲደርግልን መርሐ ግብር ቀርጻ የምትንቀሳቀስ። ምንም አይነት ሙያ እና የስራ ልምድ ሳይኖርህ ሥራ አመራርነትን ( መሪነትን) የሰጠች በስው ሁሉ ፊት ተናግረን መደመጥ የምንችል አይነት ሰዎች እንድንሆን ጠፍጥፋ የሠራች፣ ለሰው አዛኝነትን፣ ሀቀኝነትን ፣ ታጋሽነትን ገንዘባችን እና መገለጫችን እንዲሆን አድርጋ የሠራች። ትጉህ ሠራተኞች እንድንሆን የእግዚአብሔር ምህረት ወደ እኛ እንዲመጣ ምክንያት የሆነች። በኑሯችን ጥሩ ደረጃ እንድንደርስ የደገፈች፤ የመከረች። በልጅ በትዳር እንድንባረክ እና ጥሩ ቤተሰብ እንዲኖረን ምክንያት የሆነች።

አሁን ከብዙ በጥቂቱ ይህን ሁሉ ላደረገች ሰንበት ትምህርት ቤት እንኳን ኖሮን ሳይኖረን ምንስ ብናደርግላት ይቆጫል?
ሀገር ወዳድ ትውልድ እንዲፈጠር ፣ ቤተ ክርስቲያንን ክፉ እንዳያያት እንዳይነካት ለምትደክም ሰንበት ትምህርት ቤት ምንስ ብናደርግ ይቆጫል?



"እኔስ የዛሬ ህፃናት የነገዋ የቤተክርሥቲያን ጠባቂ እና አገልጋዮች የሚሆኑ ትውሎዶችን የምትፈጥረዋን ሰንበት ትምህርት ቤት መማርያ ክፍል እሠራለው።" እናንተስ?


የሠርቲ ደብረ መድኃኒት መድኃኔዓለም ቤተክርስቲያን ፈለገዮርዳኖስ ሰንበት ትምህርት ቤት  የመማሪያ ክፍሎች እጥረት አጋጥሞታል።ይህንንም ለመቅረፍ ይረዳን ዘንድ 3መማሪያ ክፍሎችን ለመስራት አቅዶ እየተንቀሳቀሰ ይገኛል። ስለሆነም አቅማችሁ የፈቀደውን ድጋፍ ታደርጉልን ዘንድ በልዑል እግዚአብሔር ስም እንጠይቃለን።
በገንዘብ ማገዝ ለምትፈልጉ
ኢትዮጵያ ንግድ ባንክ 1000609562319
ህብረት ባንክ     4630412520610015
አቢሲኒያ ባንክ 176147067
ለበለጠ መረጃ
ላቃቸው 0988345695
ሰለሞን 0923079151

Читать полностью…

የቃሊቲ ደብረ መድኃኒት መድኃኔዓለም ቤተክርስቲያን ፈለገዮርዳኖስ ሰ/ት/ቤት

ሰላም ውድ አባላት በቅድሚያ እንኳን ለአቢይ ፆም በሰላም አደረሳችሁ የመጀመረመያ እሁድ ⛪ አገልግሎት ወጣቶች ክፍል ስለሆነ ነገ ማለትም 1/7/216 ጠዋት 1:30 ⛪ተገኝተን የክብር ልብስ ለብሰን የምንወጣበት ሰአት ስለሆነ እንዳታረፍድ ሰላመ አግዚአብሔር ከናንተ ጋር ይሁን።

ከመዝሙር ክፍል

Читать полностью…

የቃሊቲ ደብረ መድኃኒት መድኃኔዓለም ቤተክርስቲያን ፈለገዮርዳኖስ ሰ/ት/ቤት

<<ኑ 72ቱ አርድዕትን ሆነን ታሪክን እንድገም>>
እንደሚታወቀው በ12ቱ ሀዋርያት የተመሰሉ ታላላቅ ወንድሞቻችን አዳራሽና ቢሮዎችን ሰርተው አስረክበውናል። አሁን ያለን ትውልድ ደግሞ ለመጪው ልጆቻችን የሚማሩበት መማሪያ ክፍል ለመስራት ፕሮጀክት ቀርፀን ተነስተናል። ለዚህም የፈለገ የቁርጥ ቀን ልጆች የሆኑ(50+22)=72ሰራተኞች ብቻ እንፈልጋለን።
>እነዚህም 50ዎቹ ደሞዛቸው ከ2000ብር በላይ የሆነ =250,000ብር የሚያዋጡ
#1ዱ=250,000÷50=5000ብር ሢደርስበት
በ3መንገድ ከፍሎ መጨረስ ይችላል።
1.ከ5-6ወር=5x(1000በወር)
2.በ10-12ወር=10x(500በወር)
3.16ወር=16x(312.5በወር)
ሲሆኑ
>22ቱ ደግሞ 50,000ብሯን በዓመት የሚካፈሏት ሲሆኑ ይህም
#1ዱ=50,000÷22=2273ብር
በዓመት ቢከፍል=2273÷12=(190ብር በወር) ያዋጣል።
ይሆናል። እነዚህ 72ሠራተኞች ሰንበት ትምህርት ቤቷ እውቅናን የምትሰጣቸው ናቸው።
የዚህ ታላቅ የበረከት ስራ ለመሳተፍ የምትፈልጉ 72 የሰንበት ትምህርት ቤታችን የቁርጥ ቀን ልጆች ስማችሁንና ምድባችሁን ከታች ለተጠቀሱት ልጆች በመግለፅ ላኩልን።
ስለሆነም ማገዝ ለምትፈልጉ
ኢትዮጵያ ንግድ ባንክ 10006095662319
ህብረት ባንክ     4630412520610015
አቢሲኒያ ባንክ 176147067
ለበለጠ መረጃ
ፀጋዬ 0911719353
ላቃቸው 0988345695
ሰለሞን 0923079151

Читать полностью…

የቃሊቲ ደብረ መድኃኒት መድኃኔዓለም ቤተክርስቲያን ፈለገዮርዳኖስ ሰ/ት/ቤት

ታላቅ የምስራች
ለጨሪና ሰፈራ ኦርቶዶክስ ምዕመናን በሙሉ (የወጣቶች ጉባኤ የካቲት 17/2016 ከቀኑ 5:00)

የሰርቲ(ጨሪ) መድኃኔዓለም ቤተክርስቲያን የጥምቀት ወጣቶች ህብረት ከሰንበት ት/ቤቷ ጋር በመተባበር በየ 15ቀኑ የሚደረገው ጉባኤ የካቲት 17/2016 እሁድ ከ5:00-6:10 ይጀምራልና
ኦርቶዶክስ ምዕመናን ወጣቶች እንዳቀሩ ተጋብዛቹኃል።

Читать полностью…

የቃሊቲ ደብረ መድኃኒት መድኃኔዓለም ቤተክርስቲያን ፈለገዮርዳኖስ ሰ/ት/ቤት

እነዴት አመሻችሁ ነገ ጠዋት አወደምህረት አገልግሎት ስላለ ወድ አባላት 1:30 ደብር እንድትገኙ ለምታስቀድሱ ቁርባን ሰአት ለይ መልካም አዳር።



ከመዝሙር ክፍል

Читать полностью…

የቃሊቲ ደብረ መድኃኒት መድኃኔዓለም ቤተክርስቲያን ፈለገዮርዳኖስ ሰ/ት/ቤት

ለሰንበት ትምህርት ቤታችን ሰራተኛ አባላት በሙሉ ወርሃዊ የትምህርት ጉባኤያችን(በአዲስ ህይወት መመላለስ ትምህርት) ነገ ጥር 26/2016 ስለሚኖር እንድትገኙ ስንል ጥሪያችንን እናስተላልፋለን።

Читать полностью…

የቃሊቲ ደብረ መድኃኒት መድኃኔዓለም ቤተክርስቲያን ፈለገዮርዳኖስ ሰ/ት/ቤት

ሰላመ እግዚአብሔር ከእናንተ ጋር ይሁን ለሰንበት ት/ቤታችን አባላት በሙሉ ይሄ ሰንበት ት/ቤታችን እሁድ በአባላት ፊርማ አፀድቃ ከዚህ በኃላ የምትተዳደርበት መዋቅር ስለሆነ ትኩረት ሰጥታችሁ አንብቡት።

Читать полностью…

የቃሊቲ ደብረ መድኃኒት መድኃኔዓለም ቤተክርስቲያን ፈለገዮርዳኖስ ሰ/ት/ቤት

ጠቅላላ የአባላት ስብሰባ ጥሪ
እሁድ ጥር 19/2016
ከጠዋቱ 3:00-6:00 ሰዓት

Читать полностью…

የቃሊቲ ደብረ መድኃኒት መድኃኔዓለም ቤተክርስቲያን ፈለገዮርዳኖስ ሰ/ት/ቤት

እንኳን ለከተራ በአል በሰላም አደረሳችሁ,,,,,,,,,,
ነገ ስትመጡ ነጭ ልብስ አድርጋችሁ እንድትመጡ
ሰአትም አክብሩ መልካም አገልግሎት ይሁንልን ,,,,።

Читать полностью…

የቃሊቲ ደብረ መድኃኒት መድኃኔዓለም ቤተክርስቲያን ፈለገዮርዳኖስ ሰ/ት/ቤት

ታላቅ መንፈሳዊ ጉዞ
ወደ ዝቋላ አቡነገብረመንፈስ ቅዱስ ገዳም
አዘጋጅ የሰርቲ/ደ/መ/መድኃኔዓለም ቤ/ክ ፈለገዮርዳኖስ ሰ/ት/ቤት
ትኬቱን የሚያገኙባቸው ስልኮች 0923079151/0943164229
የጉዞ ዋጋ 280ብር (መስተንግዶን ጨምሮ)
መነሻ ጥቅምት 4 ጠዋት 11:00ሰዓት
መመለሻ ጥቅምት 5 ከንግስ መልስ
መነሻ ቦታ ሰፈራ ድልድዩ ጋር
ለጉዞ ሲመጡ ትኬቶንና ውዳሴ ማርያም መያዞን አይርሱ

Читать полностью…

የቃሊቲ ደብረ መድኃኒት መድኃኔዓለም ቤተክርስቲያን ፈለገዮርዳኖስ ሰ/ት/ቤት

በደበረ ታቦር በዓል #ቡሄ፣ #ጅራፍ_ማስጮህ፣ #ችቦ_ማብራትና #ሙልሙል_ዳቦ ሃይማኖታዊ ምስጢራቸው ምንድነው?

ደብረ ታቦር ጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ያዕቆብን፣ ዮሐንስንና ጴጥሮስን ይዞ ወደ ታቦር ተራራ ከወሰዳቸው በኋላ በዚያ ብርሃነ መለኮቱን የገለጠበትና ሙሴና ኤልያስን ጠርቶ የህያዋንና የሙታን አምላክነቱን ያሳየበት ከዘጠኙ የጌታ ዓበይት በዓለት ውስጥ አንዱ ነው። ቤተክርስቲያናችንም የተለያዩ ስርዓቶችን በመፈፀም አክብራው ታልፋለች፡፡
በደብረ ታቦር በዓል የሚፈጸሙ (#ቡሄ፣ #ጅራፍ_ማስጮህ፣ #ችቦ_ማብራትና #ሙልሙል_ዳቦ) ትውፊታዊ የሃይማኖት ስርዓቶች ምሳሌዎች ምን እንደሆነ እናያለን፡፡

#ቡሄ
ቡሄ ማለት ብራ፣ ብርሃን፣ ደማቅ ማለት ነው፡፡ ከስሙ ትርጉም እንደምንረዳው ጌታችን ብርሃነ መለኮቱን የገለጠበት በዓል ስለሆነ ብራ፣ ብርሃን ደማቅ የሚል ፍቺ ያለው ስያሜ ተሰጥቶታል፡፡
አንድም ቡሄ ማለት ወቅቱ የክረምት ጨለማ አልፎ የብርሃን ወቅት ስለሚመጣ ሰማይም ከጭጋጋማነት ወደ ብሩህነት የሚለወጥበት የመሸጋገሪያ ወቀት ስለሆነ ብራ ተብሏል፡፡
"ቡሄ ከዋለ የለም ክረም ዶሮ ከጮኸ የለም ሌሊት እንዲሉ"
አንድም ቡሄ…..ቡኮ "/ሊጥ" ማለት ነው፡፡ በዚህ በዓል ቡኮ ተቦክቶ ዳቦ/ሙልሙል/ ተጋርሮ የሚታደልበት በዓል ስለሆነ
ይህ ስያሜ ተሰጥቶታል፡፡

#ሙልሙል_ዳቦ
ሙልሙል ዳቦ አመጣጡ ጌታችን ብርሃናዊ መለኮቱን በገለጠበት በዚህ ዕለት በደብረ-ታቦር አካባቢ የነበሩ ህፃናት እረኞች ቀኑ የመሸ ስላልመሰላቸው /ጌታችን በብርሃን አካባቢውን ሞልቶት ስለነበረ/ በዛው ሆነው ከብትና በጎቻቸውን እየጠበቁ ሲቆዩባቸው የሰዓቱን መግፋት የተመለከቱ ወላጆች በችቦ ብርሃን ተጠቅመው ለልጆቻቸው የሚቀመስ ሙልሙል ዳቦ ይዘው ወዳሉበት መምጣታቸውን ያሳያልና ታሪኩን እየዘከርን በዓሉን እናከብራለን፡፡
አንድም እንደ ሐዋርያት የምስራች ሲነግሩን ወንጌል ሊሰብኩልን በየደጃፋችን መጥተው "ቢሄ በሉ" የሚሉትን ታዳጊዎችን ይበሉት ዘንድ ይሰጣቸዋል ይህም መጽሐፋዊ ነው ጌታችን ደቀ መዛሙርቱን በደረሳችቡት ሁሉ ተመገቡ /ማቴ 10፥12/ ብሏልና ህፃናቱም የጌታን በዓል ሊያበስሩ ሲመጡ ዳቦ መስጠት ልማዳዊ ብቻ ሳይሆን ህፃናቱም የደቀመዛሙርት ምሳሌ ናቸው፡፡ መዝሙራቸው ደግሞ የምስራች ወንጌል ይዘው የመምጣታቸው ምሳሌ ነው፡፡ ሐዋሪያት በገቡበት ሀገር ሁሉ አስተምረው አጥምቀው የፀጋ ልጅነትን አሰጥተው እንደሚቆዩ ሁሉ ልጆችም ዘምረው አመስግነው መርቀው ውለዱ ክበዱ የመንግስተ ሰማያት ወራሾች ያድርጋችሁ ብለው አመስገነው ይሄዳሉና በሐዋሪያት ህፃናቱ ይመሰላሉ፡፡

#ችቦ_ማብራት
ችቦ የጌታችንን ብርሃነ መለኮት መገለጥን የሚያመለክት ነው፡፡ ጌታችን በደብረ ታቦር መለኮቱን ሲገልጥ ብርሃን አካባቢውን ሞልቶት ነበርና ያንን በዘመናችን ለመግለጥ የበዓሉ ዋዜማ ማታ ችቦ አብርተን አምላካችንን እናመሰግናለን፡፡ አንድም ደግሞ የችቦ ታሪክ ከላይ እንደገለፅነው የእረኞቹ ወላጆች ይዘውት የመጡት ብርሃን ነው፡፡

#የጅራፍ_ምሳሌነት
በደብረ ታቦር በዓል በትውፊታዊ መልኩ የሚታየው ሚስጥር በእየሩሳሌም ስለሚሆነው የጌታችን ሞቱ ምሳሌ ነው፡፡ በዚህ በዓል ጅራፍ መገመዱ እና ማጮሁ ሁለት አይነት ምሳሌ አለው፡፡
#የመጀመሪያው ጌታችን በዕለተ አርብ የደረሰበትን ግርፋትና ህማም እናስብበታለን፣
#ሁለተኛው ደግሞ ድምፁን ስንሰማ የባህሪ አባቱን የአብን የምስክርነት ቃልና በግርማው ሲገለጥ የተሰማውን ነጎድጓድ ያስታውሰናል፡፡ የጅራፍን ትውፊታዊ ውርስ መጽሐፋዊ ትምህርቱንና ምስጢሩን ከትውልድ ጠብቆ ማስተላለፉ ተገቢ ነው፡፡

በአጠቃላይ በዓለ ደብረ ታቦር ከነዚህ ሚስጢር ካላቸው ትምህርቶችና ትርጓሜያቱ ከትውልድ ወደ ትውልድ በቅብብል እንደመጣልን እኛም ሃይማኖታዊ ትውፊቱን ሳይለቅ ማስተላለፍ ይጠበቅብናል፡፡ የዚህ ነገር ባለ ድርሻ አካላት ደግሞ ወጣቶችና ወላጆች ናቸው፡፡ አንዳንድ ጊዜ በቡሄ ጨዋታ የሚሰሙ ግጥሞች ስድብ ፊዝና ሳቅ ይታይባቸዋል ተጫዋቾቹም ከሰጡን እንመርቃለን ካልሰጡን እንራገማለን አይነት መልዕክት ያስተላልፋሉ። የሚብሰው አሳባቢ ነገሩ ደግሞ ኃይማኖታዊ ስርዓቱን ወደ ገንዘብ ማግኛ መቀየሩ ነው፡፡ ስለሆነም ይህን ነገር በተለይ የነገ የሀገር ተረካቢና የቤተክርስቲያን ተተኪ የሆንን ወጣቶች ማስተካከል ይኖርብል፡፡ ወላጆችም ሕፃናት በየደጃፋችን ላይ በዓሉን ሊያበስሩ ሲመጡ አስደንግጦ ከማባረር በሚገባው መልኩ አስተምረን መርቀን ማስተናገድ ይጠበቅብናል ባህሉም እንዳይተው የበኩላችንን አደረግን ማለት ነው።

ከበዓሉ በረከት ያሳትፈን

Читать полностью…

የቃሊቲ ደብረ መድኃኒት መድኃኔዓለም ቤተክርስቲያን ፈለገዮርዳኖስ ሰ/ት/ቤት

Ye kidus yohanis ze echege mezimur

Читать полностью…

የቃሊቲ ደብረ መድኃኒት መድኃኔዓለም ቤተክርስቲያን ፈለገዮርዳኖስ ሰ/ት/ቤት

መንፈሳዊ የአዳር መርሃግብር ዛሬ ሰኔ26
ከምሽቱ 3:00ሰዓት ጀምሮ
የሚቀርቡት መርሃግብራት
መክፈቻ መዝሙር
መንፈሳዊ ስብከት
መንፈሳዊ ግጥም
ግጥማዊ ወግ
መዝሙር በተጋባዥ ዘማርያን
ያሬዳዊ ወረብ
ብሂለአበው
መነባንብ
ጭውውት
ድራማ

Читать полностью…

የቃሊቲ ደብረ መድኃኒት መድኃኔዓለም ቤተክርስቲያን ፈለገዮርዳኖስ ሰ/ት/ቤት

ሚያዚያ 13/2016ዓ.ም ያዘጋጀነው የቤዛዊት ማርያም ገዳም ይህን ይመስላል

Читать полностью…

የቃሊቲ ደብረ መድኃኒት መድኃኔዓለም ቤተክርስቲያን ፈለገዮርዳኖስ ሰ/ት/ቤት

በአይነቱ ልዩ የሆነና በሰንበት ተማሪዎች ዝማሬ÷ፀጋው በበዛላቸው መምህራን ትምህርት በተለያዩ መንፈሳዊ ጉባኤያት የታጀበ በተለይ የፈለገ ዮርዳኖስ ሰንበት ትምህርት ቤት ጣእም ቀምሰው የሚያቁ መቼም መቅረት የሌለብዎ ልዩ የፍቅር ጉዞ ወደ ቦሌ አራብሳ ቤዛዊት ማርያም ሚያዚያ 13/2016
ይህን ጉዞ መቅረት ያስቆጫል።

Читать полностью…

የቃሊቲ ደብረ መድኃኒት መድኃኔዓለም ቤተክርስቲያን ፈለገዮርዳኖስ ሰ/ት/ቤት

ታላቅ መንፈሳዊ ጉዞ
ወደ ምሁር እየሱስ ገዳም
መጋቢት 28&29
አዘጋጅ:-የሰርቲ ደ/መ/መድኃኔዓለም ቤ/ክ ፈለገዮርዳኖስ ሰንበት ት/ቤት

Читать полностью…

የቃሊቲ ደብረ መድኃኒት መድኃኔዓለም ቤተክርስቲያን ፈለገዮርዳኖስ ሰ/ት/ቤት

💒💒የመጋቢት መድኃኔዓለም መዝሙራት💒💒

ሰቀሉ ምስሌሁ

ሰቀሉ ምስሌሁ ክልኤተ ፈያተ(2)በየማኑወበፀጋሙ/
ወበማዕከሎሙ ኢየሱስ(4)
ትርጉም ፦ኢየሱስን በመሐል ሁለቱን ወንበዴዎች በግራና በቀኝ አድርገው ከእርሱ ጋር ሰቀሉ።

ለአዳም ዘአግብኦ

ለአዳም ዘአግብኦ ለአዳም ዘአግብኦ ውስተ ገነት/2
ወለ ፈያታዊ ሐረዮ በቅፅበት ሐረዮ በቅፅበት/2
ትርጉም፦አዳምን ወደ ገነት አገባው ወንበዴውንም መረጠው።

በለኒ መሐርኩከ

በለኒ መሐርኩከ በለኒ መሐርኩከ መሐርኩከ በእንተ ማርያም/2/
እስመ አልቦ ዘእንበሌከ ዘይሜሕር ቃለመድኀኔዓለም /2/
ትርጉም፦ በቀራንዮ ላይ የተሰቀልከው መድኃኔዓለም ክርስቶስ ሆይ ስለ ድንግል ማርያም ብለህ ይቅር አልኩ በለኝ ካለ አንተ ይቅር ባይ የለምና።

እም ትካት አይሁድ

እም ትካት አይሁድ በቅንአቶሙ ይፀልኡኪ ጥቀ/2/
በእንተ ዘወለድኪ በድንግልና ወልደ ጻድቀ መድኃኔዓለም /2/
ትርጉም፦ እውነተኛውን ልጅ መድኀኔዓለምን ስለወለድሽ አይሁድ ከጥንት በቅንአት ፈፅሞ ይጠሉሻል።

ምድርም ተነዋወጠች

ምድርም ተነዋወጠች ፀሀይም ጨለመች/2/
በሰቀሉት ጊዜ ጌታችንንበሰቀሉት ጊዜ መድኀኔዓለም ን/2/

Читать полностью…

የቃሊቲ ደብረ መድኃኒት መድኃኔዓለም ቤተክርስቲያን ፈለገዮርዳኖስ ሰ/ት/ቤት

የሠርቲ ደብረ መድኃኒት መድኃኔዓለም ቤተክርስቲያን ፈለገዮርዳኖስ ሰንበት ትምህርት ቤት የመማሪያ ክፍሎች እጥረት አጋጥሞታል።ይህንንም ለመቅረፍ ይረዳን ዘንድ 3መማሪያ ክፍሎችን ለመስራት አቅዶ እየተንቀሳቀሰ ይገኛል። ስለሆነም አቅማችሁ የፈቀደውን ድጋፍ ታደርጉልን ዘንድ በልዑል እግዚአብሔር ስም እንጠይቃለን።
በገንዘብ ማገዝ ለምትፈልጉ
ኢትዮጵያ ንግድ ባንክ 10006095662319
ህብረት ባንክ 4630412520610015
አቢሲኒያ ባንክ 176147067
ለበለጠ መረጃ
ላቃቸው 0988345695
ሰለሞን 0923079151

Читать полностью…

የቃሊቲ ደብረ መድኃኒት መድኃኔዓለም ቤተክርስቲያን ፈለገዮርዳኖስ ሰ/ት/ቤት

Ye kidane mehret mezmur

Читать полностью…

የቃሊቲ ደብረ መድኃኒት መድኃኔዓለም ቤተክርስቲያን ፈለገዮርዳኖስ ሰ/ት/ቤት

ለሰንበት ትምህርት ቤታችን አባላት በሙሉ። ሰንበት ት/ቤታችን ፈለገዮርዳኖስ የበዓለ ሀምሳ ዕለት ጠቅላላ የአመራር ምርጫ ስለምታደርግ ለቀጣይ 3ዓመታት ሰንበት ትምህርት ቤቷን የሚመሯትን መሪዎች ጥቆማ ከቻላችሁ በአካል ጥቆማ ሳጥን ውስጥ
በአካል መገኘት ያልቻላችሁ ደግሞ
ለወንድማችን ኤፍሬም ስልክ
0920107746 በtelegram inbox ላኩልን።
ክፍሎቹ
ሰብሳቢ
ም/ሰብሳቢ
ፀሀፊ
ሰበካጉባኤ ተወካይ
ትምህርት ክፍል
መዝሙር ክፍል
ቁጥጥር ክፍል
ህፃናት ክፍል
ልማት ክፍል
ንብረት ክፍል
ሂሳብ ክፍል
ገንዘብ ያዥ
ኪነጥበብ ክፍል

Читать полностью…

የቃሊቲ ደብረ መድኃኒት መድኃኔዓለም ቤተክርስቲያን ፈለገዮርዳኖስ ሰ/ት/ቤት

የመጋቢት 27 ወረብ
ወጸሐፈ

ወጸሐፈ መጽሀፈ ጲላጦስ ወይብል መጽሐፉ ጲላጦስ መጽሐፈ
ኢየሱስ ናዝራዊ ንጉሥ ናዝራዊ ንጉሠ አይሁድ

Читать полностью…

የቃሊቲ ደብረ መድኃኒት መድኃኔዓለም ቤተክርስቲያን ፈለገዮርዳኖስ ሰ/ት/ቤት

ባለፈው ዓመት በሕገወጥ መንገድ "ጵጵስና" ተሹመናል በማለት ሲንቀሳቀሱ የነበሩ አካላት በዛሬው ዕለት በዚሁ ሕገወጥ መንገድ በመቀጠል "መንበረ ጴጥሮስ" የተባለ ሕገወጥ ቤተ ክህነት መሥርተናል አሉ !

ጥር 14 ቀን 2016 ዓ.ም (ተ.ሚ.ማ/አዲስ አበባ)

+++

በኦሮሚያ ክልል ፖለቲካዊ ካባ የደረበ አጀንዳ ይዘው የኢትዮጵቻ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያንን ለመከፋፈል እየተንበሳበሱ የሚገኙት በቀድሞ ስማቸው "አባ" ገ/ማርያም ነጋሳ እና ግብረ አበሮቻቸው ሕገወጥ ተግባራቸውን በመቀጠል "መንበረ ጴጥሮስ" የተባለ ቀኖናዊ መሠረት የሌለው እና ሕገወጥ የሆነ ቤተ ክህነት መሥርተናል ሲሉ ስትራቴጂክ አጋሮቻቸው በሆኑ የሚዲያ ተቋማት አማካይነት በሰጧቸው መግለጫዎች አስታውቀዋል።


በቋንቋችን ለመማር እና በነጻነት ለማምለክ ለዘመናት ተከልክለናል በሚል ሀሰተኛ ሽፋን ይህን እንቅስቃሴ እያደረጉ የሚገኙት ነውጠኛ መነኮሳት በመንግስት አደራዳሪነት ችግሩ ተፈትቷል ከተባለ በኋላ የሚያደርጓቸው እንቅስቃሴዎች ስምምነቱን የጣሰ እና በሚዲያዎች እና ቤተ ክርስቲያንን ለማጥፋት በሚጥሩ ኃይሎች ድጋፍ እየተደረገላቸው እንደሚገኝ ማሳያ ነው።

ልክ የዛሬ ዓመት ጥር 14 ቀን 2015 ዓ.ም ሕገኸጥ ሢመተ ኤጲስ ቆጶሳት በመፈፀም የኦሮሚያና የብሔር ብሔረሰቦች ሲኖዶስ በሚል "አብዮታዊ ዴሞክራሲን" እናት ፍልስፍና አድርጎ ተመሠረተ የተባለው የመነኮሳት ስብስብ በአሁኑ ወቅትም ከ5 በማይበልጡ የቀድሞ መነኮሳት የቤተ ክርስቲያንን አንድነት ለማፍረስ የውክልና እንቅስቃሴ ላይ መሆናቸውን በዛሬው ዕለት ይፋ አድርገዋል።

"ለትግራይና ለአማራ ሲኖዶስ እንዲቋቋም ተፈቅዷል" በማለት ሀሰተኛ እና በቤተ ክርስቲያኒቱ ያልተደረገን ነገር ማስተላለፋቸው ሳያንስ "ለ5 ኪሎ ሲኖዶስ" እንዳትገዙ በማለት ጭምር ሕዝብን በሕዝብ ለማነሳሳት ከፍተኛ ቅስቀሳ እና የጦርነት አዋጅ እያወጁ ይገኛሉ።

#Ethiopia
#Tewahedo_Media_Center
#TMC_Addia_Ababa

ተዋሕዶ ሚዲያ ማዕከል
እውነተኛ የተዋሕዶ ድምፅ

የዩቲዩብ ቻናላችንን ሰብስክራይብ ያድርጉ
TMC1" rel="nofollow">https://youtube.com/@TMC1

የቴሌ ግራም ቻናላችንን ይቀላቀሉ ፤ ፈጣን መረጃዎችን ያግኙ /channel/tewahedomediacenter

አጫጭር ትምህርታዊ እና ወቅታዊ መረጃዎችን ለማግኘት የቲክ ቶክ አማራጫችንን ይመልከቱ
https://vm.tiktok.com/ZM8WVucY7/

Читать полностью…

የቃሊቲ ደብረ መድኃኒት መድኃኔዓለም ቤተክርስቲያን ፈለገዮርዳኖስ ሰ/ት/ቤት

ብፁዕ አቡነ ሄኖክ የአዲስ አበባ ሀገረ ስብከት ሊቀ ጳጳስ በዓለ ጥምቀትን አስመልክቶ በሀገረ ስብከታቸው ጽ/ቤት መግለጫ ሰጥተዋል !

ጥር 8 ቀን 2016 ዓ.ም

+++

ብፁዕ አቡነ ሄኖክ የአዲስ አበባ ሀገረ ስብከት ሊቀ ጳጳስ በዓለ ጥምቀትን አስመልክቶ በሀገረ ስብከታቸው ጽ/ቤት መግለጫ ሰጥተዋል !

የብፁዕነታቸው ሙሉ መግለጫ ከዚህ እንደሚከተለው ቀርቧል።

በስመ አብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ አሐዱ አምላክ አሜን

“ ወኪያነኒ ይእዜ ያድኅነነ በአርኣያሁ በጥምቀት ።” ጥምቀት ምሳሌ ሆኖ አሁን ያድነናል ። 1ኛ ጴጥ 3፥ 21
 
በመላው ዓለም የምትገኙ የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን ልጆች ምእመናንና ምእመናት
የሰላም አለቃ ፣ የዘለዓለም አባት ጌታችን አምላካችን መድኃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ እንኳን በሰላም ጠብቆ ለ2016 ዓ.ም በዓለ ጥምቀት በጤና አደረሰን አደረሳችሁ።

የጥምቀት በዓል ነጻነታችን የታወጀበት ፣ የዕዳ ደብዳቤያችን የተፋቀበት የባርነት ቀንበር የተሰበረበት ፣ የሚናፈቀው የእግዚአብሔር ድምፅ የተሰማበት ፣ ምሥጢረ ሥላሴ የተገለጠበት ፣ ልጅነትን የምንቀበልበት ጸጋ የተመሠረተበት ከጌታችን መድኃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ከዘጠኙ ዐበይት በዓላት መካከል አንዱ በመሆኑ በኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን በልዩ ድምቀት ይከበራል።

ይኸውም በመዲናችን አዲስ አበባ ከተማ የቅዱስ ሲኖዶስ ርዕሰ መንበር እና ታላቁ አባታችን ብፁዕ ወቅዱስ አቡነ ማትያስ ቀዳማዊ ፓትርያርክ ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት ዘኢትዮጵያ ሊቀ ጳጳስ ዘአክሱም ወእጨጌ ዘመንበረ ተክለሃይማኖት በተገኙበት በጃን ሜዳ ባሕረ ጥምቀት የሚከበረው በዓል እንደተጠበቀ ሆኖ በጠቅላላ በከተማዋ ውስጥ ከ78 ያላነሱ የጥምቀት በዓል ማክበሪያ ሥፍራዎች ይገኛሉ። በዚህም መሠረት በዓሉ በተቀናጀ መልኩ ለማስኬድ ሲባል በእያንዳንዱ ክ/ከተማ ላይ ግብረ ኃይል በማደራጀት እና ተጠሪነታቸውንም ለሃገረ ስብከቱ ሥራ አስኪያጅ በማድረግ በሰፊው ዝግጅት ተደርጓል በየባሕረ ጥምቀቱም በብዙህ ሺህ የሚቆጠሩ ምእመናን ይሳተፉበታል።

ሀገረ ስብከቱም በዓሉ በሰላም እንዲከበር ከሚመለከታቸው አካላት ጋር በመሆን ያካሄደውን ሰፊ ዝግጅት አጠናቅቋል።

የተወደዳችሁ የመንፈስ ቅዱስ ልጆቻችን
ምእመናንና ምእመናት

ሰላም የጌታ ድንቅ ስጦታ እንደሆነና ደግሞም ማንም እንዳይወስድብን አጽንተን ልንይዘው የሚያስፈልገን  የሁሉም መሠረት ነው ፣ ሰላም ከሌለ በዓላትን ማክበር ይቅርና ወጥቶ መግባት ፣ ሠርቶ መብላት የማይቻልበት ሁኔታ ሊፈጠር እንደሚችል መገመት ብቻ ሳይሆን ከጥቂት ዓመታት በፊት በተግባር ያየነው መሆኑ ሊዘነጋ አይገባም።

ኦርቶዶክሳዊት ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያናችን ሰላምን በማስጠበቅ ረገድ እና ለሰላም ዘብ በመቆም ቀዳሚ መሆኗ ይታወቃል።

ከላይ እንደተገለጸው በሰላም አምላክ የተመሰረተን እና የተሰጠን ጸጋ ማስጠበቅ የእያንዳንዱ አማኝ ግዴታ ነው። እንዲሁም የጥምቀት በዓል የአደባባይ በዓል እንደመሆኑ መጠን ሰላምን የመጠበቅ  እና የማስጠበቅ ድርሻ በእያንዳንዳችን ላይ እንዳለ በመገንዘብ ሐዋርያዊት ፣ ብሔራዊት እና ዓለምአቀፋዊት ለሆነችው የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን በሚመጥን መልኩ በዓሉን ማክበር ያስፈልጋል።

ስለሆነም ይህንን በዓል በምናከብርበት ወቅት  ጌታችን መድኃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ የተወልንን ሰላም በመንከባከብ  እና በመተግበር ፍፁም ክርስቲያናዊ በሆነ ሥነ ምግባር እና አካሄድ በዓላችንን ልናከብር ይገባናል።

ይህ በእንዲህ እያለ
1. መንፈሳዊ ሰልፋችን ከነአለባበሳችን የጉዞውን ቅደም ተከተል በጠበቀ መልኩ ሥርዓተ ቤተ ክርስቲያንን ማዕከል ያደረገ እና ለበዓሉ ድምቀት የሚሰጥ እንዲሆን

2. ወደ ባሕረ ጥምቀቱ የሚደረገው ጉዞ የጌታችን መድኃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ከገሊላ ወደ ዮርዳኖስ ፤ ከልዕልና ወደ ትህትና መውረዱን የሚያሳይ መንፈሳዊ እሴት ያለበት እንደሆነ የታወቀ በመሆኑ በጉዞው ላይ የሚደረግ እያንዳንዱ ክንውን አስተማሪ ሊሆን ይገባል። ሰልፉም ውበትና መስመር እንዲኖረው ይጠበቃል። በመሆኑም የአምልኮ መርሐግብር እያከናወኑ ዋዛ ፈዛዛ በመከወን የሚደረግ ጉዞ ከቤተ ክርስቲያናችን ቀኖና ጋር ፈጽሞ የሚጣረስ በመሆኑ በተለይ ወጣቶች በዚህ ረገድ ከካህናት አባቶች የሚሰጡ መመሪያዎችን በመቀበል የበዓሉን አከባበር በደመቀ መልኩ ማከናወን እንዲቻል እንዲደረግ።

3. ሰዓትን በተመለከተ ጥር 10 ቀን 2016 ዓ.ም  ታቦታተ ምሥዋዕ ከመንበረ ክብር ስለሚነሱበት ሰዓት በወጣው መርሐ ግብር መሠረት ከጠዋቱ 4:00 ሰዓት ዋዜማ ስብሐተ እግዚአብሔር ይቆማል። በማስቀጠል 7 ሰዓት ሲሆን በመላዋ አዲስ አበባ አብያተ ክርስቲያናት ለ10 ደቂቃ የደወል ድምፅ ይሰማና መነሻ ሰዓት ይሆናል።

- የጥር 11 የጥምቀት በዓልና የጥር 12 የቃና ዘገሊላ በዓልን በተመለከተም መነሻ ከጠዋቱ 3:00 ሰዓት እንዲሆንና መድረሻውም ከ 7 - 10 ሰዓት ባለው ጊዜ እንዲሆን እያሳሰብን በዓሉ የትህትና እና የፍቅር እንደመሆኑ መጠን ከእኛ የሚጠበቁ ክንውኖችን በመፈፀም ለበዓሉ በድምቀት መከበር አስተዋጽኦ ልናደርግ ይገባል።

4. አገልግሎታችን ሥርዓተ ቤተ ክርስቲያንን የተከተለ መሆን ስለሚገባው አስፈላጊውን ግብዓት ከማቅረብ በቀር ከአበው ካህናት ውጭ በየትኛውም መልኩ በሌሎች አካላት የሚደረግ ማዕጠንት ተገቢነት የሌለው እና ከቀኖና ቤተ ክርስቲያን ውጭ በመሆኑ እንዳይፈፀም የሚመለከታቸው አካላትም ተገቢውን ክትትል እንዲያደርጉ እንዲሁም በማዕጠንት አገልግሎቱ በካህናት አባቶች በሰፊው እንዲሰጥ ይሁን።

5. በረከተ ጥምቀቱን የማድረስ እና የመርጨት ክንውን የሚፈጸመው በሥርዓተ ቤተ ክርስቲያን መሠረት በካህናት ብቻ መሆኑ ይታወቃል በዚሁ መሠረት ቀኖና ቤተ ክርስቲያን ባለማወቅ ምክንያት ሥርዓቱ እንዳይፈርስ ወጣት ልጆቻችንም ይህን አውቃችሁ ሥርዓቱን እንድትጠብቁና አገልጋዮች ካህናትም ድርሻችሁን እንድትወጡና ሕዝቡን እንድታገለግሉ እናሳስባለን ።

6. ከልክ ያለፉ እና በተደጋጋሚ የተስተዋሉ ከሥርዓት ውጭ በሆነ መልክ ለታቦታቱ ክብር በማይመጥኑ ሥፍራዎች ላይ እንዲቆሙ የሚደረገው ልምድ እንዲታረምና ሁሉም በሕግና በሥርዓት እንዲመራ።

7. ምእመናን እንደተለመደው ራሳችሁን ከሁከትና አላስፈላጊ ነገሮች በማራቅ በትዕግሥት እና በሆደ ሰፊነት በዓሉን እንድናከብር እያሳሰብን ችግሮች ቢፈጠሩ እንኳን ከሚመለከታቸው የጸጥታ አካላት ጋር በመቀናጀት በተናበበ መልኩ እልባት እንዲሰጣቸው ሊደረግ ይገባል።

በመጨረሻም ፦

በዓለ ጥምቀትን ስናከብር በፍፁም ወንድማዊ ፍቅር የተራቡትን በማብላት ፣ የተጠሙትን በማጠጣት ፣ የታረዙትን በማልበስ በተለያዩ ምክንያቶች ከቀያቸው የተፈናቀሉ ወገኖችን በመርዳትና በመደገፍ ፤ የመድኃኒታችን የኢየሱስ ክርስቶስን ትህትና አብነት በማድረግ በመተሳሰብና በመደጋገፍ እንዲሆን እናሳስባለን።

ወስብሐት ለእግዚአብሔር
እግዚአብሔር ኢትዮጵያንና ሕዝቧን ይባርክ አሜን

አባ ሄኖክ
በኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን
የአዲስ አበባ ሀገረ ስብከት ሊቀ ጳጳስ

ጥር 8 ቀን 2016 ዓ.ም አዲስ አበባ፤ ኢትዮጵያ

Читать полностью…

የቃሊቲ ደብረ መድኃኒት መድኃኔዓለም ቤተክርስቲያን ፈለገዮርዳኖስ ሰ/ት/ቤት

የጥር 7ወረብ
በፈቃደ

በፈቃ'ደ አቡሁ ወረ'ደ' ተአንገደ ሀበ ማርያም

በድንግልናሀ ንፁሕ' በድንግልናሀ' ንፁሕ እግዚአብሄር ተወልደ


ይህ ' ያለበት ቦታ መርግድ ነው

Читать полностью…

የቃሊቲ ደብረ መድኃኒት መድኃኔዓለም ቤተክርስቲያን ፈለገዮርዳኖስ ሰ/ት/ቤት

መስቀል ትርኢት የተመደባችሁ አባላት ማክሰኞ፣ሀሙስ ቅዳሜና እሁድ ከ10:00-12:00ሰዓት ጥናት ስለተጀመረ እንድትሄዱ

Читать полностью…

የቃሊቲ ደብረ መድኃኒት መድኃኔዓለም ቤተክርስቲያን ፈለገዮርዳኖስ ሰ/ት/ቤት

Ye tsome fisileta mezimur

Читать полностью…

የቃሊቲ ደብረ መድኃኒት መድኃኔዓለም ቤተክርስቲያን ፈለገዮርዳኖስ ሰ/ት/ቤት

ሰላም የፈለገ ዮርዳኖስ አባላት በሙሉ ተቋርጦ የነበረዉ የመዝሙር ቅጂ አሁን ይቀጥላል: እናም በፊት እንደምታረጉት አሁንም በደንብ እንድታጠኑ ስንል በተህትና እንጠይቃለን ።

Читать полностью…

የቃሊቲ ደብረ መድኃኒት መድኃኔዓለም ቤተክርስቲያን ፈለገዮርዳኖስ ሰ/ት/ቤት

🔔

ኦርቶዶክሳዊ ያልሆነ ጠባይ !

ኦርቶዶክሳዊ ስብዕና ዓይኖቹ ዘወትር ወደ ቤተክርስቲያን ናቸው፡፡ ከእናቱ ከቤተክርስቲያን በቀር በልቦናው የተሳለ ሌላ ነገር አይኖርም፡፡ በየትኛውም የፈተና ዘመን በቤተክርስቲያን ጸንቶ መኖር ይቻለዋል፡፡ በአገልግሎት ላይ ያሉ የቤተክርስቲያን "መምህራንን" አድናቂና ተከታይ መሆን ኦርቶዶክሳዊ ጠባይ አይደለም፡፡ "መምህራኑንም" በከንቱ ውዳሴ ጠልፎ ለፈተና መዳረግ ነው፡፡ አይሁንና ድንገት ቢስቱና ከሃይማኖት መስመር ቢወጡ በቤተክርስቲያን ላይ ያልታነጹ የግለሰብ አድናቂና ተከታይ የሆኑ ብዙዎች ይሰናከላሉ፡፡ በዘመነ ሃራጥቃ ተሃድሶ የተፈጠረው እንዲህ ያለ ፈተና ነው፡፡ ገና በፈተናና በተጋድሎ ላይ ያሉ ግለሰቦችን ተከታይና አድናቂ መሆን ለብርቱ ፈተና ይዳርጋልና እንዲህ ካለው ነገር እንጠበቅ !

🔔

Читать полностью…
Subscribe to a channel