medhanialem | Unsorted

Telegram-канал medhanialem - የቃሊቲ ደብረ መድኃኒት መድኃኔዓለም ቤተክርስቲያን ፈለገዮርዳኖስ ሰ/ት/ቤት

189

Subscribe to a channel

የቃሊቲ ደብረ መድኃኒት መድኃኔዓለም ቤተክርስቲያን ፈለገዮርዳኖስ ሰ/ት/ቤት

💒💒💒 እንኳን ለብርሀነ መስቀሉ አደረሳችሁ ።የአገልግሎት ሰአት 8:00 ሁላችሁም በጊዜ እንድትመጡ ። ሰራተኞች እና መደበኛ አባላትም ወረብ ስለሚከለስ ከተባለው ሰአት ቀደም ብላችሁ እንድትመጡ ።መልካም አገልግሎት ይሁንልን።


ከመዝሙር ክፍል።

Читать полностью…

የቃሊቲ ደብረ መድኃኒት መድኃኔዓለም ቤተክርስቲያን ፈለገዮርዳኖስ ሰ/ት/ቤት

ጠቅላላ የአባላት ስብሰባ ጥሪ
መስከረም 12
ለሰንበት ትምህርት ቤታችን አባላት በሙሉ የፊታችን እሁድ መስከረም 12/2017ዓ.ም ጠቅላላ የአባላት ስብሰባ ስላለ ሁላችንም እንድትገኙ ስንል ጥሪያችንን እናስተላልፋለን።
በዕለቱ
~የ2017ዓ.ም የክፍላት ዕቅድ ይቀርባል።
~አባላት ለ2017ዓ.ም የስራ አፈፃፀም ግብዓት የሚሆኑ ሀሳቦች ይሰበሰባልና።
እንዳይቀሩ
የሰንበት ት/ቤቱ ፅ/ቤት

Читать полностью…

የቃሊቲ ደብረ መድኃኒት መድኃኔዓለም ቤተክርስቲያን ፈለገዮርዳኖስ ሰ/ት/ቤት

ሁላችሁም ሸምድዳችሁ ኑ (ይፃፍም)
እሁድ እንከልሰዋለን
​​🌼የእንቁጣጣሽ መዝሙር🌼
                  🌼🌼

እሠይ /ደስ ደስ ይበላችሁ/(፪)
ቅዱስ ማቲዎስ መጣላችሁ
ደስ ደስ ይበላችሁ

      ደስ ብሎን መጣን ደስ ብሎን(፪)ጌቶች አሉ ብለን
      ደስ ብሎን መጣን ደስ ብሎን(፪)እሜቴ አሉ ብለን

አበባዮሽ 🌼 ለምለም   አበባዮሽ 🌼  ለምለም
እንቆቅልሽ   - -  ንግሥት   ልትፈትል ሄዳ - - ንግሥት
ንግስተ አዜብ - -  ንግሥት   እናት ማክዳ - - ንግሥት
በልቧ ያለውን -  ንግሥት   አጫወታቸው - -   ንግሥት
አሰቀምጣ አበባ🌼  ንግሥት  እያሳየችው - -    ንግሥት
መአዛው የሚሸት  - - ከሁለቱ የቱ ነው አለቸው - -  ለንጉሥ 

          ንግስት ሆይ ለጥያቄሽ ጥበብ አለሽ(፪)
      🌼የአገር አምባር የሚሆነው ከልብ ሽተሽ

እንቆቅልሹ -  -  የሳባ    ከበድም ቢለው -  -🌼 የሳባ
ጥበብ ሰላለው - - ንጉሡ  ሚሥጥሩን ሊያውቀው - - ንጉሡ
ክፈት መስኮቱን - -  ሰለሞን   ቢለው ለሎሌው  - -ሰለሞን
ገቡ ንቦቹ  - -  ሊቀስሙ🌼 ከአባባው አርፈው - - ሊቀስሙ
ብልህ ጠቢቡ  - -   መለሠ     ለተጠየቀው - -  በእውነት
ንጉስ ሰለሞን - -   አለ     አልተሠወረው      🌼     በእውነት

🌼አደይ ቅድስት ሀገሬ እልል በይ (፪)
🌼 ኢትዩዮጲያ የዝና ስሟ በዓለም ተሠማ (፪)
🌼
ለፈጣሪዋ - - ንግሥት   ምስጋና አቅርባ - -   ንግሥት
ኢትዮጲያዊቷ - - ንግሥት   ንግስተ ሣባ   🌼   ንግሥት
ጥበቡን አይታ - -  ንግሥት   አደነቀችው  - -    ንግሥት
ወርቅ ሸቶውን - -  ንግሥት  ዕንቁ ሰጠችው - -   ንግሥት

      ንግስት ሆይ ምስክር ሆንሽ ለሀገርሽ (፪)🌼🌼
      የአምላክን የፈጣሪያችን ስሙን ጠርተሽ (፪)🌼🌼

የኢትዮጵያ ሠዎች  - -ለንግሥት   ቆሙ በተራ - -ለንግሥት
እደጅ ሆነው     🌼   ለንግሥት   ለዙፋን ክብሯ - - ለንግሥት
በመስከረም ወር - -  ለንግሥት   ሀገር ስትገባ - -  ለንግሥት
ይዘው ሥጦታ - -  ለንግሥት   የፈካ አበባ    🌼ለንግሥት

      🌼አደይ የብርሃን ጮራ በኢትዮጵያ በራ (፪)🌼🌼
      🌼ኢትዮጲያ በታሪክሽ ጥንታዊት ነሽ (፪)🌼🌼

ኢየሩሳሌም - - ንግሥት   ደርሠሽ መጣሽ - -  ንግሥት
እንኳን በክብር - - ንግሥት   ለዚህ አበቃሽ - - ንግሥት
ከአምላክ በረከት - - ንግሥት  ፍሬ አግኝተሽ - - ንግሥት
የዘሽ ስጦታ - -  ንግሥት   ዕንቁ ለጣጣሽ - - ንግሥት

      🌼ንግስት ሆይ ለታሪክሽ ክብር አለሽ (፪)🌼🌼
      🌼ልጆችሽ አበባዮሽ እያልን እናስታውስሽ (፪)🌼🌼

🌼የአባቶች ተስፋ - -   ለፃድቃን   የነቢያት ትንቢት - - ለፅናት
የሙሴ ፅላት - -     ለፀሎት   የአሮን በትር  - -   ለፅናት
የዳዊት መንግስት - - ለፅናት    ይዘሸ የመጣሽ - -   ከጥንት
አምስቱን አውታር - - ለሠጠሽ   ለሀገር መሠረት -    በእውነት🌼🌼

🌼 አደይ ቅድስት ኢትዮጵያ እልል በይ (፪)🌼🌼
      🌼ኢትዮጵያ በልጆችሽ ደስ ይበልሽ (፪)🌼🌼

በህገ ልቦና  - -   ህጉን     ፈጣሪን አውቀሽ - -  ህጉን
ህገ ነቢያትን - -  ከዓለም  ፈጥነሽ ተቀበልሽ - - ከዓለም
በብሉይ ኪዳን   🌼ለጌታ    መስዋዕት አቅርበሽ - -  ለጌታ
ተስፋ ካረጉት - - ከአይሁድ ከአስራኤል - - ከአይሁድ
ህገ ወንጌልን-  -በፊት    ይዘሽ ተገኘሽ    🌼    በፊት

      🌼ኢትዮጵያ ደስ ይበልሽ ትልቅ ፀጋ አለሽ(፪)🌼🌼
      🌼ስለፈፀምሽ ሦስቱን ህግጋት ለፈጣሪሽ (፪)🌼🌼


ካለፈው ሰህተት - -  ሁላችን    እንድንመለስ - - ሁላችን
አዲሱ ዓመት  - -  ለሁሉም   መጣ ማቴዎስ- -ለሁሉም
ይህም ያልፍና - - በጊዜው    ይመጣል ማርቆስ - - በጊዜው
ሌላው ይተካል - -  በጊዜው    ዘመነ ሉቃስ - - በጊዜው
ወልደነጓድጓድ  - -  በጊዜው  🌼 ሲደርስ ዮሐንስ - - በጊዜው
በየአራት ዓመት -  -  በጊዜው   ለሁሉም ሲደርስ - - በጊዜው
በየዓመቱ  - -  መጥምቁ      ቅዱስ ዩሐንስ - - በጊዜው🌼🌼

      🌼አደይ የብርሃን ጮራ በዮሐንስ በራ(፪)🌼🌼
🌼 ኢትዮጵያ ባሕል ቋንቋሽ የሚያኮራሽ (፪)🌼🌼

ልጅ አበባ ልጅ አበባዬ    🌼     አዬ ውዲቷ እናቴ
ልጅ አበባ 🌼እያለች እማማ      አዬ ውዲቷ እናቴ
ምክሯን ሁሌ እኔ እንድሰማ    አዬ ውዲቷ እናቴ
እያሻሸች እንድሆን ጤናማ     አዬ ውዲቷ እማማ
አዬ ውዲቷ እናቴ (፪)🌼

🌼አበባ ለምለም 🌼 ቀጤማ ለምለም
    🌼ኢትዮጵያ እንዳንቺ የለም (፪)🌼

አብዬ ኧኸ ደግሞም እማምዬ
መጣሁ ለሰላምታ ከቤት አሉ ብዬ🌼
እንኳን ለቅዱስ ዮሐንስ አደረሰዎት ብዬ (፪)
🌼
ይሸታል ዶሮ ዶሮ (፪) ከማምዬ ጓሮ (፪)
ይሸታል የወይን ጠጅ (፪) ከጋሽዬ ደጅ (፪)

      ከበረው ይቆዩ ከብረው 🌼
       አመት አወደ አመት ደርሰው
      ቅን ታዛዥ ልጅን ወልደው
      ትሁት ሰው አክባሪ ሆነው
      የፍቅር ሸማን ለብሰው🌼
      ንስሐ ገብተው ቆርበው
  🌼ከብረው ይቆዩ ከብረው
          
               መዝሙር
      🌼በማህበረ ፊልጶስ🌼

Читать полностью…

የቃሊቲ ደብረ መድኃኒት መድኃኔዓለም ቤተክርስቲያን ፈለገዮርዳኖስ ሰ/ት/ቤት

እንኳን ለጌታችን ለመድኃኒታችን ለኢየሱስ ክርስቶስ ደብረ ታቦር በዓል አደረሳችሁ እያልን ሰንበት ትምህርት ቤታችን ፈለገዮርዳኖስ የፊታችን እሁድ ነሀሴ12/2016 ከቀኑ 8:00 ሰዓት ጀምሮ አገልግሎቱን ከቃሊቲ መናኸሪያ አካባቢ ጀምሮ እስከ ሰፈራ ስለሚከናወን ለዚህ አገልግሎት ሁላችሁም እንድትገኙ ተጠርታችኃል። ለደብረታቦር አገልግሎት መጥተን አገልግለን በመዝሙር ክፍል የተመደብን በክብር ልብስ ከአገልግሎት የራቅን ደግሞ በነጠላ መጥተን እንድናገለግል ሰንበት ትምህርት ቤታችን ጥሪዋን ታስተላልፋለች።

Читать полностью…

የቃሊቲ ደብረ መድኃኒት መድኃኔዓለም ቤተክርስቲያን ፈለገዮርዳኖስ ሰ/ት/ቤት

ነገ ማለትም 5-12-16 ቅዳሴ ላይ እና ከቅዳሴ በኋላ አገልግሎት ስላለ ሁላችሁም ትላልቅ አባላት እንድትገኙ ።

Читать полностью…

የቃሊቲ ደብረ መድኃኒት መድኃኔዓለም ቤተክርስቲያን ፈለገዮርዳኖስ ሰ/ት/ቤት

የደብረ ታቦር ወረብ

አሀዜ አለም

አሀዜ አለም ዘእም ሀቤሁ ስብሐቲሁ ወውዳሴሁ እምዚአሁ
ሰይፈ በቀል ውስተ እዴሁ ፍትሀ ግፉአን እም ጽርሑ ይወጽእ

Читать полностью…

የቃሊቲ ደብረ መድኃኒት መድኃኔዓለም ቤተክርስቲያን ፈለገዮርዳኖስ ሰ/ት/ቤት

ነገ ጠዋት አውደ ምህረትና አገልግሎት አለ

Читать полностью…

የቃሊቲ ደብረ መድኃኒት መድኃኔዓለም ቤተክርስቲያን ፈለገዮርዳኖስ ሰ/ት/ቤት

የሰንበት ትምህርት ቤታችን አባል ሀና ሰለሞን ወላጅ አባት ሥላረፉ ዛሬ ማታ17/10/2016 ማታ 11:30 ላይ በቤታቸው የማጽናኛ መርሐ ግብር ስለሚኖረን ሁላችሁም እንድትገኙ

Читать полностью…

የቃሊቲ ደብረ መድኃኒት መድኃኔዓለም ቤተክርስቲያን ፈለገዮርዳኖስ ሰ/ት/ቤት

መልዕክት ለሰ/ት/ቤታችን አባላት
ነገ የቤተክርሥቲያናችንን የሰበካ ጉባኤ አባላት አገልጋዮች የምንመርጥበት ሥለሆነ ሁላችሁም አባላት ከ ጠዋቱ 01:00 እንድትገኙ በጥብቅ እናሳስባለን ።

Читать полностью…

የቃሊቲ ደብረ መድኃኒት መድኃኔዓለም ቤተክርስቲያን ፈለገዮርዳኖስ ሰ/ት/ቤት

ታላቅ መንፈሳዊ ጉባኤ
ቤተክርስቲያናችን የሁለት ቀን መንፈሳዊ ገባኤ
በ 1/9/2016 እና 2/9/2016 ማለትም ቅዳሜ እና እሁድ ጠዋትም ማታም ያዘጋጀች በመሆኗ ከዚህ በታች ስማችሁ የተጠቀሳችሁ የሰንበት ት/ቤት አገልጋዮች እንደ እግዚአብሔር መልካም ፍቃድ መጥታችሁ አገልግሎቱን እንድትፈጽሙ እንላለን ።
ወንድ ሴት

ታሪኩ ሜሮን የሻነው
ናሆም ታሪኳ
ዳኙ ምህረት
ብሩክዋሲሁን ኤልሻዳይ
ሳሙኤል ነፃነት
ላቃቸው ሀይማኖት
ያሬድ አይናለም
ከፈኒ ትግስት
እዮብ ሀና ተመስገን
መንበሩ ሂሩት
ኤርሚያስ ሆሳዕና
ሚኪያስ ሳምራዊት
አዛዠ ሰላም
ተካልኝ ሜሮን ደስታ
ቴድሮስ ፂሆን
ብሩክ ስንታየው ፅጌ
ናትናኤል ገነት
ዳንኤል ባጫ ፀጋ
ዳንኤል ፍቃዱ አዳነች
ፀጋዬ ታደሉ
ኤፍሬም
ዲ/ን ቢንያም አበበች
ሰለሞን ሜሮንሙልጌታ
ጌታሁን
ሀብታሙ
ምስጋናው

ቅዳሜ 11:00 ሰዓት ሰራተኛ ለሆናችሁ እስከ 12:00
እሁድ ጠዋት 01:00 ከቻላችሁ ደግሞ ለቅዳሴ ኑ
እሁድ አመሻሽ 11:00 ሰዓት መገኘት ግዴታ ነወ።

ማሳሰቢያ:-ተመድባችሁ ያለበቂ ምክንያት አለማገልገል አይቻልም ምክንያታችሁን ቀድማችሁ ለመዝሙር ክፋል ደውላችሁ ወይ በአካል አሳውቁ።!!
ታሪኳ 0942712658
ዳኙ 0982006549
ታሪኩ 0991728624

መልካም አገልግሎት
ከመዝሙር ክፍል።

Читать полностью…

የቃሊቲ ደብረ መድኃኒት መድኃኔዓለም ቤተክርስቲያን ፈለገዮርዳኖስ ሰ/ት/ቤት

የስብሰባ ጥሪ (ካዕላይ ክፍልና ከዚያ በላይ ለሆናችሁ የሰንበት ትምህርት ቤታችን አባላት በሙሉ)
ሰንበት ትምህርት ቤታችን ፈለገዮርዳኖስ ሰኔ 16/2016ዓ.ም (ከቅዳሴ በኃላ) የስራ አስፈፃሚዎች ምርጫ የሚያካሂድ ስለሆነ ሁላችሁም ተገኝታችሁ ለሰንበት ትምህርት ቤቷ ለቀጣይ 3ዓመታት የሚጠቅሟትን አመራሮች ትመርጡ ዘንድ በልዑል እግዚአብሔር ስም ጥሪያችንን እናስተላልፋለን።
             የሰ/ት/ቤቷ ፅ/ቤት

Читать полностью…

የቃሊቲ ደብረ መድኃኒት መድኃኔዓለም ቤተክርስቲያን ፈለገዮርዳኖስ ሰ/ት/ቤት

🤚🤚🤚ሰላም ውድ አባላት እንዴት ናችሁ የሰርግ ጥናት እህታችን ታደሉ ጋር ነው 11:30 ላይ ይጀመራል ጥናቱ ።

አድራሻ:- ሰፈራ ከሸገር ዳቦወደ ላይ።

Читать полностью…

የቃሊቲ ደብረ መድኃኒት መድኃኔዓለም ቤተክርስቲያን ፈለገዮርዳኖስ ሰ/ት/ቤት

በሰንበት ትምህርት ቤቷ ታሪክ እጅግ ብዙ ምዕመናንና አባላት ቲኬት የቆረጡበት እስከአሁን ካዘጋጀናቸው ጉዞዎች በአይነቱ እጅግ የተለየ ልክ እንደ ሀዊረ ህይወት ሰንበት ት/ቤታችን በቤዛዊት ማርያም ገዳም መንፈሳዊ ጉባኤያትን የምታዘጋጅበት ልዩ መንፈሳዊ ጉዞ 1ቀን ቀረው። ከ10የማይበልጡ ትኬቶች ብቻ ስላሉን ያልቆረጣችሁ(ደውላችሁ ቦታ ያልሳዛችሁ) እስከ ነገ ከሰዓት ቶሎ እንድታሲዙ

Читать полностью…

የቃሊቲ ደብረ መድኃኒት መድኃኔዓለም ቤተክርስቲያን ፈለገዮርዳኖስ ሰ/ት/ቤት

https://vm.tiktok.com/ZMMCjfGPq/

Читать полностью…

የቃሊቲ ደብረ መድኃኒት መድኃኔዓለም ቤተክርስቲያን ፈለገዮርዳኖስ ሰ/ት/ቤት

የቤዛዊት ማርያም ገዳም መንፈሳዊ ጉዞ ወደ ቤዛዊት ማርያም ትኬት መሸጥ ስለጀመረ ከወዲሁ ይህ በሰንበት ት/ቤታችን አባላት የሚደረግ ታሪካዊ ጉዞ እንዳያመልጣችሁ ከወዲሁ በእነዚህ ስልኮች ቦታ ይያዙ።
ላቃቸው +251988345695
ሰሎሞን 0923079151
ፀጋዬ +251911719353

Читать полностью…

የቃሊቲ ደብረ መድኃኒት መድኃኔዓለም ቤተክርስቲያን ፈለገዮርዳኖስ ሰ/ት/ቤት

ሰላም ለሰንበት ትምህርት ቤታችን ሰራተኛ አባላት በሙሉ ነገ መስከረም 12/2017 ጠቅላላ የአባላት ስብሰባ ስላለ የሰራተኛ መዝሙር ጥናት ከ3:00-5:00 ስለሆነ በጊዜ እንድትገኙ።

Читать полностью…

የቃሊቲ ደብረ መድኃኒት መድኃኔዓለም ቤተክርስቲያን ፈለገዮርዳኖስ ሰ/ት/ቤት

የመስቀል ወረብ
በመስቀሉ
በመስቀሉ በዓለ በመስቀሉ በዓለ በላዕሉ በሰማያት ወዘነገሰ በምድር (፪)
ዮም መስቀል አብርሃ ለአእዛብ ወለኵሉ ዓለም በፍስሃ ወበሰላም (፪)

Читать полностью…

የቃሊቲ ደብረ መድኃኒት መድኃኔዓለም ቤተክርስቲያን ፈለገዮርዳኖስ ሰ/ት/ቤት

ልዩ የሰፈር ውስጥ አገልግሎታችን ደረሰ
ሰንበት ትምህርት ቤታችን ፈለገዮርዳኖስ የፊታችን እሁድ ነሀሴ12/2016 በዓይነቱ ልዩ የሆነ የሰፈር አገልግሎት ባማረና በደመቀ መልኩ ከቀኑ 8:00 ጀምሮ ተገኝተው በሚማሩና በተለያየ ምክንያት በጠፉ አገልጋዮቿ ታጅባ ዝግጅቷን ጨርሳለች ስለሆነም በጥሪያችን መሰረት ማናችንም ከዚህ አገልግሎት እንዳንቀር በክብር ልብስ ያልተመደብን ነጠላ ለብሰን እንገኝ።

Читать полностью…

የቃሊቲ ደብረ መድኃኒት መድኃኔዓለም ቤተክርስቲያን ፈለገዮርዳኖስ ሰ/ት/ቤት

የሰንበት ትምህርት ቤታችን አባል የሆነችው ሀይማኖት መሀመድ አባቷ ስላረፉ ቀብር ነገ ስለሆነ ተገኝተን እንድናፅናና። ማታ 12:00 ሰዓት በመኖሪያ ቤታቸው ጉባኤ ይኖራል

Читать полностью…

የቃሊቲ ደብረ መድኃኒት መድኃኔዓለም ቤተክርስቲያን ፈለገዮርዳኖስ ሰ/ት/ቤት

የሰንበት ትምህርት ቤታችን ካዕላይ ክፍል አባል የሆነችው የመቅደስ አያቷ ስላረፉ ቀብር ስለምንሄድ እንድትገኙ። እንዲሁም ማታ 12:30 በቤቷ ተገኝተን የማፅናናት ጉባኤ ስላለ እንድንገኝ።

Читать полностью…

የቃሊቲ ደብረ መድኃኒት መድኃኔዓለም ቤተክርስቲያን ፈለገዮርዳኖስ ሰ/ት/ቤት

በስመአብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ      አሐዱ አምላክ አሜን!!

        ሰንበት ትምህርት ቤታችን ለእኛ!!

አንደበታችን ሳይፍታታ ኮልታፋ አንደበታችንን የፈታች። ገና በለጋ እድሚያችን እግዚአብሔር ማመስገን እንድንችል  "እምዬ ማርያም ምን ሆናለች፣ መጽሐፍ ቅዱሴን እወዳታለው " በሚሉ እና ሌሎች የጨዋታ መዝሙሮች ምስጋናን እንድንለምድ ያደረገች። መልካም የሆኑ ምንገድ ስንስት መንገድ የሚያስይዙ፣ ሥሥናጠፋ የሚግስጹ፣ ስንዝል የሚያበርቱእና በሀዘንም በደስታችንም ቀን ከማንም በፊት እን ከማንም በላይ የሚሆኑልንን የልብ ጓደኞቻችንን የሰጠችን ምን ብንጥር በሰንበት ትምህርት ቤት ካገኘናቸው ጓደኞቻችን የተሻለ ከሌላ ቦታ ልናገኛቸው የማንችላቸውን ጓደኞች የሰጠች ። ብንቸገር የምንረዳበት ብንታመም የምንጎበኝበት እና ጸሎት እንዲደርግልን መርሐ ግብር ቀርጻ የምትንቀሳቀስ። ምንም አይነት ሙያ እና የስራ ልምድ ሳይኖርህ ሥራ አመራርነትን ( መሪነትን) የሰጠች በስው ሁሉ ፊት ተናግረን መደመጥ የምንችል አይነት ሰዎች እንድንሆን ጠፍጥፋ የሠራች፣ ለሰው አዛኝነትን፣ ሀቀኝነትን ፣ ታጋሽነትን ገንዘባችን እና መገለጫችን እንዲሆን አድርጋ የሠራች። ትጉህ ሠራተኞች እንድንሆን የእግዚአብሔር ምህረት ወደ እኛ እንዲመጣ ምክንያት የሆነች። በኑሯችን ጥሩ ደረጃ እንድንደርስ የደገፈች፤ የመከረች። በልጅ በትዳር እንድንባረክ እና ጥሩ ቤተሰብ እንዲኖረን ምክንያት የሆነች።

   የሠርቲ ደብረ መድኃኒት መድኃኔዓለም ቤተክርስቲያን ፈለገዮርዳኖስ ሰንበት ትምህርት ቤት  የመማሪያ ክፍሎች እጥረት አጋጥሞታል።ይህንንም ለመቅረፍ ይረዳን ዘንድ 3መማሪያ ክፍሎችን ለመስራት አቅዶ እየተንቀሳቀሰ ይገኛል። የመማሪያ ክፍል ግንባታውን ለመጀመር ከሸገር ከተማ የግንባታ ፍቃድ እስክናገኝ እየጠበቅን ስለነበረ ነው የዘገየነው ሰለሆነም ፍቃዱ እጃችን ላይ እንደገባ በፍጥነት ገንብተን ለመጨረስ ከወዲሁ የእናንተ አባላቶች ድጋፍ ያስፈልገናልና ስለሆያስፈልገናልና አቅማችሁ የፈቀደውን ድጋፍ ታደርጉልን ዘንድ በልዑል እግዚአብሔር ስም እንጠይቃለን።
በተጨማሪም ለመማሪያ ክፍል ግንባታ ስራ የምንጠቀምባቸውን አካውንቶች በእነዚህ የተካናቸው መሆኑን እንገልፃለን
#ያሬድ ሻምበል እና ሰሎሞን ንጉሴ
~ኢት/ንግድ ባንክ 1000639913663
~ህብረት ባንክ 4960413803933013
ለበለጠ መረጃ
ያሬድ 0923258941
ሰለሞን 0923079151

Читать полностью…

የቃሊቲ ደብረ መድኃኒት መድኃኔዓለም ቤተክርስቲያን ፈለገዮርዳኖስ ሰ/ት/ቤት

ነገ ጠዋት አውደ ምህረትና አገልግሎት አለ ። 1:00 አንዳታረፍዱ።

Читать полностью…

የቃሊቲ ደብረ መድኃኒት መድኃኔዓለም ቤተክርስቲያን ፈለገዮርዳኖስ ሰ/ት/ቤት

ለሰንበት ትምህርት ቤታችን አባላት በሙሉ
ቀጣይ ሳምንት ሰኔ 16/2016 ዓ.ም የሰንበት ት/ቤታችን የቀጣይ 3ዓመት የሚመሩ ጠቅላላ የስራ አስፈፃሚ ምርጫ ስላለ ሁላችሁም ከቀዳማይ በላይ የሆናችሁ አባላት እንድትገኙ ጥሪያችንን እናስተላልፋለን።

Читать полностью…

የቃሊቲ ደብረ መድኃኒት መድኃኔዓለም ቤተክርስቲያን ፈለገዮርዳኖስ ሰ/ት/ቤት

ሰላም ወድ አባላት
የቅድስት ስላሴ ሐምሌ 7 ወረብ
ነው አጥኑት። ጥናት የመጣችሁ ከልሱት ያልመጣችሁ አጥኑት።

Читать полностью…

የቃሊቲ ደብረ መድኃኒት መድኃኔዓለም ቤተክርስቲያን ፈለገዮርዳኖስ ሰ/ት/ቤት

ለሰንበት ትምህርት ቤታችን ሰራተኛ አባላት በሙሉ በፊታችን የሚከበረውን በዕለተ እሁድ ሐምሌ 7 (የቅድስት ስላሴን) በዓል ባማረ መልኩ ለማክበር ታስቦ ከመጪው እሁድ ጀምሮ ከ3:30-6:00 ስዓት የመዝሙር ጥናት ስለሚጀመር እንዳቀሩ።

Читать полностью…

የቃሊቲ ደብረ መድኃኒት መድኃኔዓለም ቤተክርስቲያን ፈለገዮርዳኖስ ሰ/ት/ቤት

የሰርግ መዝሙር ነው ግጥሙ በቃል ይሸምደድ።

Читать полностью…

የቃሊቲ ደብረ መድኃኒት መድኃኔዓለም ቤተክርስቲያን ፈለገዮርዳኖስ ሰ/ት/ቤት

🌈💒💒💒💒💒💒💒💒💒💒💒💒ክርስቶስ ተንስአ እሙታን .........እንኳን ለዳግመ ትንሳኤ በሰላም አደረሳችሁ። ነገ ጥዋት አውደምህረት አገልግሎት ስላለ 1:30ድረሱ መልካም አዳር።

Читать полностью…

የቃሊቲ ደብረ መድኃኒት መድኃኔዓለም ቤተክርስቲያን ፈለገዮርዳኖስ ሰ/ት/ቤት

የቤዛዊት ማርያም ገዳም መንፈሳዊ ጉዞ  የቀረን ትኬት በጣም ጥቂት ስለሆነ በእነዚህ ስልኮች ደውለው ሳያልቅ ቶሎ ቲኬት ይያዙ።
ላቃቸው +251988345695
ሰሎሞን 0923079151
ፀጋዬ  +251911719353

Читать полностью…

የቃሊቲ ደብረ መድኃኒት መድኃኔዓለም ቤተክርስቲያን ፈለገዮርዳኖስ ሰ/ት/ቤት

እንዴት አላችሁ ውድ የፈለገ ዮርዳኖስ አባላት በሙሉ በነገው ዕለት አጠቃላይ መዝሙር ጥናት ስላለ ሰራተኞችም መደበኛ አባላትም 2:00 ሰዓት ላይ እንድትገኙ ስንል ጥሪያችንን እናስተላልፋለን ።
ለጥናቱ የሚገቡትን መገልገያዎች እንድትይዙ ።

መዝሙር ክፍል

Читать полностью…

የቃሊቲ ደብረ መድኃኒት መድኃኔዓለም ቤተክርስቲያን ፈለገዮርዳኖስ ሰ/ት/ቤት

ውድ የሰ/ትቤታችን አባላት የወንድማችን ጌታሁን ዘሪሁን አባት ስላረፉ ዛሬ ማታ ማለትም ቅዳሜ 12 መኖሪያ እቤታቸው እንድትገኙ ነገ እሁድ ቀብር እንድትሄዱ ።

Читать полностью…
Subscribe to a channel