medhanialem | Unsorted

Telegram-канал medhanialem - የቃሊቲ ደብረ መድኃኒት መድኃኔዓለም ቤተክርስቲያን ፈለገዮርዳኖስ ሰ/ት/ቤት

189

Subscribe to a channel

የቃሊቲ ደብረ መድኃኒት መድኃኔዓለም ቤተክርስቲያን ፈለገዮርዳኖስ ሰ/ት/ቤት

ሁሩ ወመሐሩ ....
ጌታችን መድኃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ከሀዋርያት ተለይቶ በሚያርግ ጊዜ ከነገራቸው ትዕዛዛት አንዱ ሂዱና አህዛብን በአብ በወልድ በመንፈስ ቅዱስ ስም እያጠመቃችኋቸው ደቀ መዛሙርቴ አድርጎቸው የሚል ነው።ሐዋርያትም ይህንን ቃል ተቀብለው ደረቅ የሆነውን የሰዎችን ልቦና በወንጌል ቃል አረስርሰዋል፤አልጫ የሆነውንም ዓለም በወንጌል ጨውነት አጣፍጠዋል ።ከሐዋርያት ቀጥለውም ሐዋርያነ አበው፣ ከዚያም ሰማዕታት ፣ቀጥለውም ሊቃውንት ፣እንዲሁም መነኮሳት ይህንን የእግዚአብሔር ቃል ተቀብለው ወንጌልን ለዓለም አድርሰዋል ።

ሰንበት ትምህርት ቤታችን ፈለገ ዮርዳኖስንም የአምላካችንን ቃል በመቀበል ፡በሐዋርያት አስተምሮ፣በሰማዕታት ተጋድሎ ፣በመነኮሳት ኑሮ ፣በሊቃውንት ትርጓሜ መሰረት ላይ ተመስርታ እግዚአብሔር በፈቀደላት መጠን የወንጌል ቃል ስታስተምር ቆይታለች(አሁንም በማስተማር ላይ ትገኛለች )።በዚህም ብዙ ደቀ መዛሙርትን ለእግዚአብሔር አገልጋይ እንዲሆኑ ከዓለም ሐሳብ ለይታ ንጹሕ መስዋዕት አድርጋ አቅርባለች ።ብዙ ሰዎችንም ከወንጀል ሰሪነት ወደ ወንጌል አገልግሎት መልሳለች።ይህንን ሐዋርያዊ አገልግሎት ደግሞ ከጀመረች እነሆ 20 ዓመቷን ዛሬ ህዳር 21 እና ነገ ህዳር 22 በደማቅ ሁኔታ ታከብራለች ።በመሆኑም ሁላችንም ህዝበ ክርስቲያናት በመርሐ ግብሩ ላይ በመገኘት የመርሐ ግብሩ ተሳታፊ ይሆኑ ዘንድ በአክብሮት ተጠርተዋል ።

Читать полностью…

የቃሊቲ ደብረ መድኃኒት መድኃኔዓለም ቤተክርስቲያን ፈለገዮርዳኖስ ሰ/ት/ቤት

አናፂዎቻችን ትጥቃቸውን አሟልተው ለጣሪያ ስራ ዝግጁ ሆነዋል። ለፍፃሜው የበረከት ስራ መድኃኔዓለም የፈቀደላችሁ ተገኝቶ የበረከቱ ተሳታፊ መሆን ይቻላል።

Читать полностью…

የቃሊቲ ደብረ መድኃኒት መድኃኔዓለም ቤተክርስቲያን ፈለገዮርዳኖስ ሰ/ት/ቤት

20 አመትሽ ነው?

በ20 ዓመት የሕይወት ጉዞ ውስጥ ብዙ ክረምት አልፎ ብዙ በጋ መጥቷል፣ህጻን ሆነው የተወለዱት ለወጣትነት በቅተዋል ፣ወጣት የሆኑት ጎልምሰዋል፣የጎለመሱት ደግሞ አርጅተዋል ።በ20 ዓመት ውስጥ ብዙ ሰዎች ተወልደው ብዙ ሰዎች ሞተዋል ፣ በዚህች 20 ዓመት ውስጥ ቅናሽ የነበረው ኑሮ አሁን ደግሞ ተወዷል የአንድ ብር ከሀምሳ ምግብ መቶ ሀምሳ ብር ገብቷል ፣ብዙ መንግስታት መጥተው ብዙ መንግስታት አልፈዋል ፣ ብዙ አስተዳዳሪዎች መጥተው አስተዳድረው ሄደዋል።በዚህች 20 ዓመት ውስጥ ነው ታዲያ ከብዙ የህይወት ክንውኖች ውስጥ ፈለገ ዮርዳኖስ ሰንበት ትምህርት ቤት የምትባል እናት የፈለቀችው ።

ሰንበት ትምህርት ቤታችን ፈለገ ዮርዳኖስ የዛሬ 20 ዓመት ነበር በመድኃኔዓለም ፈቃድ፣በወንድሞች እና እህቶች መልካምና በጎ ተነሳሽነት የተወለደችው ።በዮሐንስ መወለድ ለብዙዎች ደስታ እንደሆነ ሁሉ በሰንበት ትምህርት ቤታችንም መወለድ ለብዙዎቻችን ደስታን ሰጥቷናል።በዚህች እናት በሆነች ሰንበት ትምህርት ቤት ውስጥ ነው ታዲያ ህጻናት ሆነን ገብተን ትልቅ ሆነን የወጣንባት ፣ያልተማርን ሆነን ሆነን ሊቆች ሆነን የወጣንባት ፣በመንፈሳዊ ዕውቀት ህጻን ሆነን ገብተን ጎልምሰን የወጣንባት ፣ትምህርት ሳንጀምር ገብተን የተመረቅንባት፣ብቻችንን ሆነን ገብተን የተዳርንባት ፣ልጅ ሆነን መጥተን አባት የሆንባት ፣ ከምንም በላይ የበግ ስጋ በልተን መጥተን የእውነተኛው በግ የክርስቶስን ስጋ ደም እንድንበላ ያደረችን ምርጥ እናታችን ናት።

ታዲያ ይህን ሁሉ ውለታ የዋለች እናት ሰንበት ትምህርት ቤታችን 20ኛ ዓመት የምስረታ ልደቷን ከፊታችን ህዳር 21 እና ህዳር 22 ታከብራለች ፤ በመሆኑም በዚህ መርሐ ግብር ላይ በመገኘት የባለ ውለታዋን ውለታ እናስብ ዘንድ በክብር ተጠርተናል።

አዎ

Читать полностью…

የቃሊቲ ደብረ መድኃኒት መድኃኔዓለም ቤተክርስቲያን ፈለገዮርዳኖስ ሰ/ት/ቤት

ሁሩ ወመሐሩ  ፅፋት ቃሉን  ዘሩን ያዙት በቃላችሁ    ያላዛችሁት ካላችሁ  ምትችሉ ማክሰኞ እናሐሙስ መጥታችሁ ፅፋቱን አጥኑ  ሰራተኛ ክፍሎች።

Читать полностью…

የቃሊቲ ደብረ መድኃኒት መድኃኔዓለም ቤተክርስቲያን ፈለገዮርዳኖስ ሰ/ት/ቤት

በወንድማችን ኤፍሬም አስተባባሪነት 3,000ብር ተደርጎልናል እግዚአብሔር ይስጥልን። ወቅቱ የደሞዝ ነውና ወርሃዊ ክፍያችንን እንክፈል።ሌሎችንንም አስተባብረን የሰንበት ት/ቤታችንን መማሪያ ክፍሎች ለፍፃሜ እናብቃ።
የመማሪያ ክፍል ግንባታ አካውንት
ህብረት ባንክ 4960413803933013
የኢ/ያ ንግድ ባንክ 1000639913663
እባክዎ ከላኩ በኃላ screen shoot አድርገው በዚህ ይላኩ። @solomon9151

Читать полностью…

የቃሊቲ ደብረ መድኃኒት መድኃኔዓለም ቤተክርስቲያን ፈለገዮርዳኖስ ሰ/ት/ቤት

ተመስገን ሀይሉ=10,000ብር
አልፐራሲም ማህበር=7,000ብር
ማህበረ መድኃኔዓለም=4,000
ጠቅላላ በ21,000ብር=600ብሎኬት ችለውናል ፈጣሪ ያክብርል።
ሌላው ነገ በደብራችን አውደምህረት ምዕመናን ብሎኬት እንዲችሉን አስተዳደሩ ቅስቀሳ ስለሚያደርጉልንና በአውደምህረት መዝሙር ስለምናቀርብ በዛ ያለ አባል አገልግሎት ላይ ስለሚመደብ ማገልገል የምትችሉ ልጆች በጠዋት ተገኙልን።

Читать полностью…

የቃሊቲ ደብረ መድኃኒት መድኃኔዓለም ቤተክርስቲያን ፈለገዮርዳኖስ ሰ/ት/ቤት

https://vm.tiktok.com/ZMh4mNbTd/

Читать полностью…

የቃሊቲ ደብረ መድኃኒት መድኃኔዓለም ቤተክርስቲያን ፈለገዮርዳኖስ ሰ/ት/ቤት

እንደፈጣሪ ፍቃድ የመሰረት ድንጋይ ግንብ ስራ በእናንተ በአባሎቻችን ድጋፍ ጨርሰናል።ቅዳሜና እሁድን ጉልበታችሁን ሳትሰስቱ ላገዛችሁን መድኃኔዓለም ይስጥልን። የጀመርነው ከፍፃሜ ለማብቃት የእናንተ ድጋፍ ያስፈልገናልና የምትችሉ በማቴሪያል ካልሆነም በእነዚህ አካውንቶች ገቢ እንድታረጉልን በልዑል እግዘብሔር ስም እንጠይቃለን።
ህብረት ባንክ 4960413803933013
የኢ/ያ ንግድ ባንክ 1000639913663

Читать полностью…

የቃሊቲ ደብረ መድኃኒት መድኃኔዓለም ቤተክርስቲያን ፈለገዮርዳኖስ ሰ/ት/ቤት

የሰንበት ቤት መጠለያችን ነሽ
መማሪያችን መጠለያችን ነሽ
እኛና አምላክን ያገናኘሽ
አዝ...
በሐጢያት ስንኖር በዓለም ተበታትነን[፪]
ባለማወቅ ጉያ በጨማ ሰጥመን
ኑ ልጆቼ ብለሽ መክረሽ ሰብስበሽ
በፍቅር ታቅፈሽ መጠለያ ሆንሽ
አዝ...
ምስጢረ ሥላሴን ነገረ ማርያምን[፪]
ዶግማና ቀኖና ትእውፊት የአባቶችን
እያቀረብሽልን ጥዑም ቃል ስንበላ
ዘመናትን ቆጠርን በረድኤትሽ ጥላ
አዝ...
ሰው እንዳይሳሳት ትውልድ እንዳይጠፋ[፪]
ወንጌለ ምሥራች በዓለም እንዲስፋፋ
አባቶች ባርከውሽ ያቆሙሽ በጸሎት
የድኅነት መስክ ነሽ ሰንበት ትምህርት ቤት
አዝ.....
የአቡነ ቴዎፍሎስ የሒወት አሻራ[፪]
የነ አቢብ ጊዮርጊስ የተጋድሎ ሥፍራ
እኛም አንለይም ከግንድሽ ቅርንጫፍ
ከአባቶቻችን ጋር ስማችን እንዲጻፍ

Читать полностью…

የቃሊቲ ደብረ መድኃኒት መድኃኔዓለም ቤተክርስቲያን ፈለገዮርዳኖስ ሰ/ት/ቤት

ሰንበት ትምህርት ቤታችን የመማሪያ ክፍል ግንባታ እንቅስቃሴ ስለጀመርን
በዕቃ ድጋፍ ማድረግ የምትፈልጉ
እጅግ አንገብጋቢው ፍላጎታችን ብሎኬት ነው።
እንዲሁም ሰንበት ት/ቤቷን በገንዘብ ማገዝ የምትችሉ
ህብረት ባንክ 4960413803933013
የኢ/ያ ንግድ ባንክ 1000639913663
በጉልበትና በሀሳብ ማገዝ የምትፈልጉ
ሰለሞን 0923079151
ፀጋዬ +251911719353 በእነዚህ ስልኮች ደውለው ቢያናግሩን

Читать полностью…

የቃሊቲ ደብረ መድኃኒት መድኃኔዓለም ቤተክርስቲያን ፈለገዮርዳኖስ ሰ/ት/ቤት

https://vm.tiktok.com/ZMhQU8qNe/

Читать полностью…

የቃሊቲ ደብረ መድኃኒት መድኃኔዓለም ቤተክርስቲያን ፈለገዮርዳኖስ ሰ/ት/ቤት

ትላልቅ አባላት ነገ ጥዋት አውደ ምህረት አገልግሎት ስላለ በጥዋት እንድትገኙ

17/2/17

Читать полностью…

የቃሊቲ ደብረ መድኃኒት መድኃኔዓለም ቤተክርስቲያን ፈለገዮርዳኖስ ሰ/ት/ቤት

ለሠንበት ትምህርት ቤታችን አባላት በሙሉ የቤተክርስቲያናችን ሰበካ ጉባኤ አባል የሆኑት የወ/ሮ ታደሉ አጉኔ አባታችን አርፎአል እና የማስተዛዘኛ መርሃግብር ነገ 11:30 ጀምሮ ስለሆነ እንድትገኙ ስንል በልዑል እግዚአብሔር ስም እንጠይቃለን።

Читать полностью…

የቃሊቲ ደብረ መድኃኒት መድኃኔዓለም ቤተክርስቲያን ፈለገዮርዳኖስ ሰ/ት/ቤት

ለጨሪ ሰፈራና አካባቢ ላላችሁ የጥምቀት ተመላሽ በሙሉ እንኳን ለ2017ዓ.ም የጥምቀት አገልግሎት ጊዜ አደረሰን አደረሳችሁ እያልን። ለ2017ዓ.ም ጥምቀት ማስተባበር የነጋሪትና የመለከት ጥናትና በመሳሰሉት ጉዳዮች ላይ ለመወያየት የፊታችን እሁድ ጥቅምት 10 ከ5:00 ጀምሮ ውይይት ስላለን ሁላችሁም እንዳቀሩ ስንል በልዑል እግዚአብሔር ስም ጥሪያችንን እናስተላልፋለን።
ሰንበት ትምህርት ቤቷ

Читать полностью…

የቃሊቲ ደብረ መድኃኒት መድኃኔዓለም ቤተክርስቲያን ፈለገዮርዳኖስ ሰ/ት/ቤት

የብዙኃን ማርያም መዝሙር መስከረም21 ቀን

Читать полностью…

የቃሊቲ ደብረ መድኃኒት መድኃኔዓለም ቤተክርስቲያን ፈለገዮርዳኖስ ሰ/ት/ቤት

እንኳን ለእመቤታችን ቅድስት ድንግል ማርያም ህዳር ፅዮንና ለሰንበት ትምህርት ቤታችን 20ኛ ዓመት በዓል አደረሰን።

Читать полностью…

የቃሊቲ ደብረ መድኃኒት መድኃኔዓለም ቤተክርስቲያን ፈለገዮርዳኖስ ሰ/ት/ቤት

አረንጓዴ አሻራ
#የሾላ ዛፍ
ጌታችን በመንገድ ሲያልፍ እርሱን ለማየት ከሚሹ ሰዎች መሀል አንዱ ባለጸጋው እና የቀራጮች አለቃ የነበረው ዘኪዮስ አንዱ ነበር።ነገር ግን ዘኪዮስ ከሰዎች መጨናነቅ የተነሳና በቁመቱ እጥረት ምክንያት ጌታን ለማየት አልተቻለውም ነበር ።ነገር ግን ምንም እንኳን ቁመቱ ቢያጥርና የሰዎች መጨናነቅ ጌታን እንዳያየው ቢያግደውም ፡እጅግ አብዝቶ ጌታን ይወደው ነበርና ወደ ፊት ሮጦ ሄዶ የሾላ ዛፍ ላይ በመውጣት የሚወደውን ጌታን ለማየት ቻለ።ጌታም ያሳየውን ፍቅር እና መሻት ተመልክቶ፡ ሊያየው ብቻ የሚሻውን እርሱን፡ ቤቱ ድረስ በመግባት መሻቱን ፍጹም አደረገለት።

እኛም በህይወት ውስጥ፡ ምንም እንኳን በየቀኑ የጽድቅ ህይወት የመኖር ፍላጎታችንም ቢጨምርም፡ ነገር ግን ብዙ ጊዜ ከነፍስ ፍላጎታችን ይልቅ፡ ሥጋዊ ፍላጎታችን እየበለጠ ማየት የምንፈልገውን አምላክ እንዳናይ አድርጎናል ።እንደ ዘኪዮስ ቁመት ያጠረው ማንነታችን፡ ለብዙ መንፈሳዊ ዝለቶች ዳርጎናል።ኃጢአታችን ፣በደላችን ና ክፋታችን የዕድገት ሆርሞናችንን ገድሎ፡ ይኸው በመንፈሳዊ ህይወት ድንኮች ሆነን መኖር ከጀመርን ቆይተናል ።ከራሳችን ማንነት ጋር ደግሞ እንደምንም ታርቀን ወደ ቤቱ ስንመጣ ደግሞ፡ በአጠገባችን ያሉ ሰዎች በሚናገሩት ንግግር ፣በሚያደርጉት አልባሌ ተግባር ፣በሚያሳዩት አሽሙር ምክንያት ብዙ ጊዜ እርሱን ከማየት ተከልክለናል።ዘኪዮስ ጌታን እንዳያይ ሰዎች እንደጋረዱት ሁሉ፡ እኛም ጌታን እንዳናይ ብዙ ጊዜ ጋርደውናል ።

የዘኪዮስን ጌታን የማየት ፍላጎት ያሟላችለት ባለውለታው ታዲያ፡ ያቺ እርሱን ከፍ አድርጋ ወደ ላይ ያወጣችው የሾላዋ ዛፍ ናት።እኛም ምንም እንኳን ከላይ የገለጽናቸው ችግሮች ጌታን እንዳናየው ቢከለክሉንም ልክ እንደ ሾላዋ ዛፍ ግን እኛንም ከፍ አድርጋ ጌታን እንድንመለከት ያደረገችን የእኛ ሾላ ዛፍ ሰንበት ትምህርት ቤታችን ናት።ሰንበት ትምህርት ቤታችን ኃጢአታችንን ሰውራ ፣በደላችንን ከድና ፣ያለችንን ትንሽ መንፈሳዊ ህይወት ከፍ አድርጋ ፣አገልግሎት በሚባል ዘርፍ ከእግዚአብሔር ጋር እንድንሰራ በማድረግ፡ ጌታን እንድናይ እጅግ አድርጋ ረድታናለች።በሰዎች ተሰናክለን እንዳንወርቅ ፣ የዓለም ጫጫታ ና ግፊያው እዛው እንዳያስቀረን በትከሻዋ ተሸክማ "ኑ ከዓለም ተለዩና እግዚአብሔር እዩ " በማለት እንደ መልካም እናት ከፍ አድርጋ እግዚአብሔር እንድንመለከት አድርጋናለች። ክብር ለሾላ ዛፍችን።

ታዲያ የእኛ ሾላ ዛፍ (ፈለገ ዮርዳኖስ ሰንበት ትምህርት ቤት) የተተከለችበትን 20ኛ ዓመት ህዳር 21 እና ህዳር 22 በደማቅ ሁኔታ ታከብራለች ።ስለዚህ ሁላችንም በመርሐ ግብሩ ላይ በመሳተፍ አብረን ልደቷን እናክብር።

Читать полностью…

የቃሊቲ ደብረ መድኃኒት መድኃኔዓለም ቤተክርስቲያን ፈለገዮርዳኖስ ሰ/ት/ቤት

የዛሬ ብሎኬት ስራ ይህን ይመስላል። የሰንበት ት/ቤታችን ክፍል ግንባታ እንዲህ እየተፋጠነ ይገኛል። ይህን ለፍፃሜ ለማብቃት በገንዘብና በጉልበት አግዙን። የምትችሉ ነገ ከሰዓት እስከ ማታ ስራዎች ስላሉ ብትገኙልን

Читать полностью…

የቃሊቲ ደብረ መድኃኒት መድኃኔዓለም ቤተክርስቲያን ፈለገዮርዳኖስ ሰ/ት/ቤት

የሰንበት ት/ቤታችን ማህበር የሆነው አልፐራሲም ማህበር በድጋሚ 10,000ብር ገቢ አድርገውልናል ፈጣሪ ይስጥልን።

Читать полностью…

የቃሊቲ ደብረ መድኃኒት መድኃኔዓለም ቤተክርስቲያን ፈለገዮርዳኖስ ሰ/ት/ቤት

ዛሬ አባሎቻችን የብሎኬት ስራ ግንባታ ላይ

Читать полностью…

የቃሊቲ ደብረ መድኃኒት መድኃኔዓለም ቤተክርስቲያን ፈለገዮርዳኖስ ሰ/ት/ቤት

ሰላም ነገ ጊዜ ያላችሁ ልጆች በሰንበት ት/ቤታችን ስር ባሉ ማህበራትና ቃል በገቡ ሰዎች ብሎኬት ገዝተን ስለምናመጣ የምትችሉ በጉልበት ብታግዙን

Читать полностью…

የቃሊቲ ደብረ መድኃኒት መድኃኔዓለም ቤተክርስቲያን ፈለገዮርዳኖስ ሰ/ት/ቤት

ሰንበት ትምህርት ቤታችን ህዳር 29/2017 ጉዞ ያዘጋጀበት አቡነእጨጌ ዮሐንስ ገዳም ይህን ይመስላል።

Читать полностью…

የቃሊቲ ደብረ መድኃኒት መድኃኔዓለም ቤተክርስቲያን ፈለገዮርዳኖስ ሰ/ት/ቤት

ታላቅ መንፈሳዊ  የንግስ በዓል ጉዞ
ወደ ዘነበወርቅ አቡነ እጨጌ ዮሀንስ ገዳም ህዳር 29/2017ዓ.ም
የሠርቲ ደ/መ/መድኃኔዓለም ቤተክርስቲያን ፈለገዮርዳኖስ ሰንበት ትምህርት ቤት ህዳር 29/2017 ደርሶ መልስ ጉዞ ወደ አቡነ እጨጌ ዮሀንስ ጉዞ ስላዘጋጀ ሁላችሁም የበረከቱ ተሳታፊ እንድትሆኑ ጥሪያችንን እናስተላልፋለን።
#የጉዞ ገቢ ሙሉ ለሙሉ አዲስ ለሚሰራው መማሪያ ክፍል
ሰንበት ት/ቤቱ
መነሻ ቦታ1:-ከሰፈራ ድልድይ ተነስቶ በጋርመንት
መነሻ ቦታ2:- ከቃሊቲ ቶታል ተነስቶ በቃሊቲ ገብርኤል በማሰልጠኛ

Читать полностью…

የቃሊቲ ደብረ መድኃኒት መድኃኔዓለም ቤተክርስቲያን ፈለገዮርዳኖስ ሰ/ት/ቤት

ይሸምደድ

መዝሙር ክፍል

Читать полностью…

የቃሊቲ ደብረ መድኃኒት መድኃኔዓለም ቤተክርስቲያን ፈለገዮርዳኖስ ሰ/ት/ቤት

ትናንት በጉልበት ተገኝታችሁ ድንጋይ ማጋዝ የጉልበት ስራ ላገዛችሁን እግዚአብሔር ይስጥልን።ዛሬም ከ10:00 ጀምሮ ተጨማሪ ከአካባቢው የገዛናቸው የመሰረት ድንጋዮች ስላሉ የምትችሉ ዛሬ ማታ ድንጋይ የማጋዝ ስራ እና የቁፋሮ ስራ ስለሚኖር ከ10:00 ሰዓት ጀምሮ ስለሚኖር እንድትገኙልን።
እንደወንድማችን ሙሉአባይ ግንባታችንን በtiktok የምታስተዋውቁልን በርቱ

Читать полностью…

የቃሊቲ ደብረ መድኃኒት መድኃኔዓለም ቤተክርስቲያን ፈለገዮርዳኖስ ሰ/ት/ቤት

እንግዲህ የፈለገ የቁርጥ ቀን ልጇ የሚለይበት ጊዜ ደረሰ
ለሰንበት ት/ቤታችን ሰራተኛ አባላት ዘወትር ከሰኞ-ቅዳሜ ከ12:00 ሰዓት በኃላ የምትችሉ ሰዎች ስራ በጉልበት ብታግዙን
ሰንበት ት/ቤቷን በገንዘብ ማገዝ የምትችሉ
ህብረት ባንክ 4960413803933013
በጉልበትና በሀሳብ ማገዝ የምትፈልጉ
ሰለሞን 0923079151
ፀጋዬ +251911719353 በእነዚህ ስልኮች ደውለው ቢያናግሩን

Читать полностью…

የቃሊቲ ደብረ መድኃኒት መድኃኔዓለም ቤተክርስቲያን ፈለገዮርዳኖስ ሰ/ት/ቤት

ኑ አብረን እንገንባ
የሰንበት ትምህርት ቤታችን መማሪያ ክፍል ቁፋሮ ስራ ስለተጀመረ ነገ ከሰራተኛ መዝሙር ጥናት በኃላ የተወሰኑ ስራዎች ስላሉ ሰራተኞች ስትመጡ የስራ ልብስ ለብሳችሁ ኑ

Читать полностью…

የቃሊቲ ደብረ መድኃኒት መድኃኔዓለም ቤተክርስቲያን ፈለገዮርዳኖስ ሰ/ት/ቤት

ለሰንበት ትምህርት ቤታችን አባላት በሙሉ የፊታችን ቅዳሜ ከሰዓት ጀምሮ የመማሪያ ክፍል ግንባታ ስራዎችን ስለምንጀምር ባላችሁ ጊዜ በጉልበት ታግዙን ዘንድ በልዑል እግዚአብሔር ስም እንጠይቃለን።

Читать полностью…

የቃሊቲ ደብረ መድኃኒት መድኃኔዓለም ቤተክርስቲያን ፈለገዮርዳኖስ ሰ/ት/ቤት

የዘመነ ፅጌ መዝሙር ከመስከረም 21-ህዳር 5 ቀን

Читать полностью…

የቃሊቲ ደብረ መድኃኒት መድኃኔዓለም ቤተክርስቲያን ፈለገዮርዳኖስ ሰ/ት/ቤት

የጥቅምት መድኃኒዓለም ፅፍት ነው ቅኝት አዳምጡት🦻🦻🦻🦻🦻🦻

Читать полностью…
Subscribe to a channel