medhanialem | Unsorted

Telegram-канал medhanialem - የቃሊቲ ደብረ መድኃኒት መድኃኔዓለም ቤተክርስቲያን ፈለገዮርዳኖስ ሰ/ት/ቤት

189

Subscribe to a channel

የቃሊቲ ደብረ መድኃኒት መድኃኔዓለም ቤተክርስቲያን ፈለገዮርዳኖስ ሰ/ት/ቤት

ከተራ


  ከተራ በዚህ እለት መዕመናን ሁሉ እስከ ምሽት ሰአት ምንም መብል ሳይቅምሱ ይጾሙ ዘንድ የቀደሙት አባቶች ስራዐትን ሰሩ ።አባቶቻችን ይህነን ስራዐት የሰሩበት መክንያትም የልደትና የጥምቀት ቀን በረቡና በአርብ ቢውል በማክሰኞና በሃሙስ ተጹሞ በለላው ቀን እንዲያከብሩ አዘዋል።ልደትና ጥምቀት የጌታችን ታላላቅ በአሎቹ ናቸውና ነው።በተጨማሪነትም አባቶች ከሰባቱ አፁአማት እንደ አንዱ በመቁጠርም ሁሌ በየአመቱ የከተራ እለት እንዲጾም አዘዋል።የዘንደሮ አመት ከተራ ደግሞ በቀዳሚት ሰንበት በመሆኑ ሰዎች ከጥሉላት ብቻ እንዲከለከሉ አዘዋል።ከተራ ከበበ ከሚለው የግዕዝ ግስ የወጣ ሲሆን ፍችው ደግሞ ውሃ መከተር፣ መገደብ ማለት ነው።የጥምቀት ዋዜማ ታቦተ ህጉ ከቤተ መቀደስ ወቶ ውሃ ባለበት አካባቢ ስለሚያድር የአካባቢው ህዝብ እየተሰበሰበ በወንዝ ዳር ወይም በምንጭ ዳር ድንኳን (ዳስ) ይተክላል። የምንጭ ውሃ አነስተኛ በመሆኑ እንዲጠራቀም ይከትሩታል፤ይገድቡታል። ውሃው የሚከተረው በነጋታው ጥር 11 ለህዝቡ መጠመቂያ እንዲሆን ነው።

  ከ1202-1204 ዓ.ም በፃድቁ አቡነ ተከለ ሃይማንት አሳሳቢነት የተጀመረው ስረአተ በአል በአፄ ይኩኖ አመላክ ዘመነ መንግስት /1260-1275 ዓ.ም/በዐሉ ተጠናከሮ እንዲቀጥል በአዋጅ አስነግረዋል ታቦታቱም በህዝቡ ጥበቃና እንክብካቤ በየጥምቀተ ባህሩ እንዲያደሩ ወስነዋል።

  ከዓፄ ገብረ መስቀል ጀምሮ የአደባባይ በዓል የሆነው የጥምቀት በዓል በ15ኛው  ክፍለ ዘመን በደገኛው የኢትዮጵያ ንጉሰ ነገስት ዓፄ ዘርዓ ያእቆብ /1426-1460 ዓ.ም/ አማካኝነት ታቦታቱ ወደ ወንዝ ወርደው እለቱን እንዳይመለሱ በዚህ ፈንታ በጥመቀት ዋዜማ ጥር 10 ቀን ከከሰአት ወደ ባህረ ጥምቀቱ ወርደው እለቱን እንዳይመለሱ አዘዋል።ይሀን ታሪክ በመከተልም ዐፄ ናዖድ /1486-1500 ዓ.ም/ ማንኛውም የኦርቶዶክስ ተዋህዶ እምነት ተከታይ ምዕመን  ታቦተ ህጉ ወደ ባሀረ ጥመቀቱ በሚወርድበት ጊዜ እና ወደ ቤተ መቅደስ በሚመለስበት ጊዜ ሁሉ አጅቦ ወስዶ አጅቦ መመለስ እንዳለበት አዋጅ አስነግረው ነበር። ህዝቡም በእልልታ አጅቦ ከባህረ ጥምቀቱ ከትሞ ማደር ጀመረ።/ሐመር ጥር /የካቲት 1998ዓ.ም/።

  የዋዜማው ቀለም ከቀኑ በ4 ሰዐት በመላው አጥቢያተ ቤተ ክርስቲያን ይጀመራል። ከዛም የዋዜማው ሰረአት ቅዱስ ተበሎ እስከ ሰላም ያለው ቀለም ይደርሳል ።በዕለቱም ቅዳሴ ይቀደሳል ፤ታቦተ ህጉን የሚያነሱት የዕለቱ ተረኛ ካህን ከመግበ ስጋ ተከልክለው የዕለቱን ጸሎት ያደርሳሉ። ታቦቱ የሚንቀሳቀስበት ሰአት ሲደርስ ታቦቱ በካህናት ተይዞ የመጾር መስቀል በያዙ ዲያቆናት ደምቆ ለመሄድ ሲነሱ ደውል የደወላል፤አበው ካህናቱ ታቦታቱን ተከትለው ይሄዳሉ። የሰንበት ት/ቤት ተማሪዎችም “ወረደ ወልድ ፣እግዚኡ መርኃ፣ ሆረ ኢየሱስ” ምዕመናን “ነይ ነይ እምያ ማርያም” እያሉ ጉዞ ወደ ባህረ ጥምቀት ይሆናል።

  የከተራ ማክበሪያ ቦታ እንደደረሱ ታቦታቱ በድነኳኑ አጠገብ ቆመው “ወረደ ወልድ” የሚለው ሰላም ተመርቶ በአገባቡ ከተለዘበ በኋላ ጸሎት ተደርጎ የዕለቱ ት/ትና ዝማሬ ከቀረበ በኋላ ውዳሴ ማርያምና መልክዓ ኢየሱስ ተደግሞ ታቦተ ህጉ ወደተዘጋጀለት ቦታ የገባል።በሁለተኛ የአገልገሎት ክፍል ካህናት ስብሃተ እግዚአብሔር ሲያደርሱ ያደራሉ።በመንፈቀ ለሊትም ቅዳሴው ተጀምሮ ከለሊቱ በ9፡00 ይጠናቀቃል።በበነገታው የሰርዐት ጥምቀቱ መርሃ ግብር ይቀጥላል።

  ሐመር 19ኛ ዓመት ቁጥር 9 ጥር 2004ዓ.ም

Читать полностью…

የቃሊቲ ደብረ መድኃኒት መድኃኔዓለም ቤተክርስቲያን ፈለገዮርዳኖስ ሰ/ት/ቤት

🔔✨🔔✨🔔✨🔔✨🔔

ሰላም ውድ አባላት
እንኳን አደረሳችሁ አደረሰን!!!!
⭐⭐⭐⭐⭐⭐⭐⭐⭐⭐

ነገ ስትመጡ ክርስቲያናዊ አለባበስ እንደተጠበቀ ሆኖ ወንዶች ፀጉር አስተካክላችሁ(ተቆርጣችሁ) ፣ ሴቶች ነጭ ሻሽ ግዴታ ቆብ ሊያያንስ ስለሚችል ለአገልግሎት የማይሆን (የማይመች ጫማ) እንዳታረጉ ፣ ሰአት ይከበር ፣ በቶሎ ታቦተህጉ መንገድ ስለሚጀምር ። አደራ አደራ አደራ ።🧏‍♀🧏‍♀🧏‍♀🧏‍♀

አገልግሎታችንን እግዚአብሔር ይባርክ🙏🙏🙏🙏🙏🙏🙏🙏🙏🙏🙏



💦 ከስርአትና ግንኙነት ክፍል💦

Читать полностью…

የቃሊቲ ደብረ መድኃኒት መድኃኔዓለም ቤተክርስቲያን ፈለገዮርዳኖስ ሰ/ት/ቤት

በስመአብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ አሐዱ አምላክ አሜን!!!



ጥር 7 ቀን 

  በዚህ ቀን ዓለምን ካለመኖር ወደ መኖር ያመጡት የፍጥረታት ሁሉ ገዥ የሆኑት የአጋዕዝተ ዓለም ሥላሴ ክብረ በአላቸው ነው።አንድም ሦስትም ተብለው የሚጠሩት ሚስጢረ  ሥላሴ በእምነት ለማይኖር በትህትና ለማይቀርብ የሚገለጥ አይደለም።በስም ፣በአካል፣በግብር ሦስትነታቸውን ስንናገር በመለኮት፣በአገዛዝ፣በባህሪ፣በህልውና ደግሞ አንድ ናቸው ብለን የምንመሰክርላቸው ሥላሴ  በጥር 7 በዚህ እለትም ስለ ሁለት ነገሮች ይከበራሉ።         
   
1.  ህንፃ ሰናኦርን ያፈረሱበት እለት ነው። ሰናዖር ከሺህ አመታት በፊት በአሁኗ ኢራቅ አካባቢ እንደነበር የሚነገር ግዛት ናት።ታዲያ የዚህ ግዛት ሰዎች ከናመሩድ ክፋት በኋላ ከሰይጣን ጋር ተወዳጁ ከጥፋት ውሃ በኋላ አብረው ሲኖሩ ክፋትን አመጡ፤አሰቡ።በመጠራራትም “ኑ ሳነበታተን ስማችን የሚጠራበትን ስራ እንስራ አባቶቻችንን በጥፋት ውሃ ያጠፋብንን እግዚአብሔርን እንውጋው “ተባባሉ።ሰማይ ጠቀስ ፎቅንም ሰሩ፤ ፎቁ ላይም በመውታት ጦርን ወደሰማይ ወረወሩ በዚህ ጊዜም ሰይጣን ደም እየቀባ ጦሩን ይመለስ ስለነበር ሥላሴን ያገኙ እየመሰላቸው ይደሰቱ ነበር።በዚህ ጊዜ ቅድስት ሥላሴ “ኑ እንውረድ ቋንቋቸውን እንደባልቅባቸው” በማለት ቋንቋቸውን ደባልቀዋል።እናም የሰናኦር ሰዎች አንዱ አካፋ ሲጠይቅ ዶማ እያመጡ መግባባት እንዳጡ ባዩ ጊዜ ተበታተኑ። ሥላሴም ህንፃውን በተኑት ያ ስፈራም ባቢሎን በመባል ተጠራ።

2.  ቅዳሴ ቤታቸው ነው። መናኝ የነበሩት አዲያም ሰገድ እያሱ በኢትዮጽያ በነገሱ በአስረኛው አመት በጎንደር ከተማ ንግስተ አድባራት ቅድስት ሥላሴ ቤ/ክ አሰርተው አተናቀዋል። ጥር 7 ቀን ሊቁ ክፍለ ዮሃንስን ጨመሮ ሌሎች መዕመናን፣መሳፍንት፣ሊቃውንት ባሉበትቅዳሴ ቤታቸው ተከብሯል። ከዚህ ቀን ጀምሮ ቅዳሴ በታቸው ጥር 7 ቀን ይከበራል።

  ወስብሃት ለእግዚአብሔር
▰▰▰▰▰▰▰▰▰▰▰▰▰▰

ፈለገ ዮርዳኖስ ሰንበት ትምህርት ቤት

/channel/+bDYQeUV7ou4wYjU0 ይከታተላሉን

@Senbttemeherbetbot ጻፉልን

Читать полностью…

የቃሊቲ ደብረ መድኃኒት መድኃኔዓለም ቤተክርስቲያን ፈለገዮርዳኖስ ሰ/ት/ቤት

Share 'የጥምቀት አገልግሎት ስምWPS Office.docx'

Читать полностью…

የቃሊቲ ደብረ መድኃኒት መድኃኔዓለም ቤተክርስቲያን ፈለገዮርዳኖስ ሰ/ት/ቤት

የልደት መፅሀፍ ስጦታ ለሰንበት ትምህርት ቤታችን መስጠት የምትፈልጉ ከእነዚህ መፃህፍት መሀል ለቤተመፃህፍት አስተዋጽኦ ታደርጉ ዘንድ በልዑል እግዚአብሔር ስም እንጠይቃለን።

Читать полностью…

የቃሊቲ ደብረ መድኃኒት መድኃኔዓለም ቤተክርስቲያን ፈለገዮርዳኖስ ሰ/ት/ቤት

እነሆ ሰብዓሰገል ለህፃኑ እጅ መንሻ ወርቅ÷እጣንና ከርቤን ሰጡት የጌታችን የመድኃኒታችን የኢየሱስ ክርስቶስን የልደት በዓል ስጦታ ለህፃናቱ መማሪያ ክፍል ምን ሊሰጡን አስበዋል? ኑ አብረን ከመድኃኔዓለም ልደት በፊት የዚያች የከብቶች በረት ምሳሌ የሆነችውን መማሪያ ክፍል ለፍፃሜ እናብቃ።
ሰንበት ትምህርት ቤቷን በገንዘብ ለማገዝ የምትፈልጉ
የኢ/ያ ንግድ ባንክ 1000639913663  screen shoot በtelegram በ0923079151ስልክ ይላኩልን።
ለበለጠ መረጃ
ሠለሞን 0923079151
ፀጋዬ +251911719353
ኤፍሬም +251920191954
የሰንበት ትምህርት ቤቷ ህንፃ አሰሪ ኮሚቴ

Читать полностью…

የቃሊቲ ደብረ መድኃኒት መድኃኔዓለም ቤተክርስቲያን ፈለገዮርዳኖስ ሰ/ት/ቤት

የሰርቲ ደብረ መድኃኒት መድኃኔዓለም ቤተክርስቲያን ፈለገዮርዳኖስ ሰንበት ትምህርት ቤት 3 የመማሪያ ክፍሎችን ገንብቶ በማጠናቀቅ ላይ ሲገኝ አሁን ግን በገንዘብ እጥረት በርና መስኮት ሳንገጥም ቆመናል ስለሆነም ስራችንን ለፍፃሜ ለማብቃት ሲሚንቶ መግዣ ገንዘብ ስለሚያስፈልገን ፈጣሪ የፈቀደላችሁ የበኩላችሁን ትረዱን ዘንድ እንማፀናለን።

Читать полностью…

የቃሊቲ ደብረ መድኃኒት መድኃኔዓለም ቤተክርስቲያን ፈለገዮርዳኖስ ሰ/ት/ቤት

በስመአብ ወወልድ ወመንፈስቅዱስ አሐዱ አምላክ አሜን ።

🔔🔔ማሳሰቢያ 🔔🔔

በ2017ዓ.ም በሰንበት ትምህርት ቤታችን ከሚተገበሩ ተግባር መካከል አንዱ ወርሀዊ ክፍያ ነው ሆኖሞ እየከፈሉ የሚገኙ አባላት ቁጥር በጣም ጥቂት ሲሆን እንድትከፍሉ ስንል እናሳስባለን

የመክፈያ መንገዶች :-
1. ዘወትር እሁድ እሁድ ከ 2:30- 3:30 በሒሳብ ክፍል ቢሮ
2. በሰንበት ትምህርት ቤቷ አኮውንት ቁጥርየ 4960413803933013 በመክፈል የከፈላችሁበትን ደረሰኝ screenshot በማንስት @eyob1005 ይላኩልን


ከሒሳብ ክፍል

Читать полностью…

የቃሊቲ ደብረ መድኃኒት መድኃኔዓለም ቤተክርስቲያን ፈለገዮርዳኖስ ሰ/ት/ቤት

ለሰንበት ትምህርት ቤታችን መምህራን በሙሉ የፊታችን እሁድ ታህሳስ 13/2017 ሰንበት ትምህርት ቤታችን መንፈሳዊ ጉዞ ወደ አቡነ እጨጌዮሀንስ ገዳም ጉዞ የሚኬድበት ስለሆነ ከህፃናት እስከ ወጣንያን ክፍል ምንም ዓይነት መርሃግብር የማይኖር መሆኑን እንገልፃለን።

Читать полностью…

የቃሊቲ ደብረ መድኃኒት መድኃኔዓለም ቤተክርስቲያን ፈለገዮርዳኖስ ሰ/ት/ቤት

ታህሳስ 13 የሰንበት ትምህርት ቤታችን መንፈሳዊ ጉዞ ቀን ደረሰ ኑ አብረን የበረከቱ ተካፋይ እንሁን

Читать полностью…

የቃሊቲ ደብረ መድኃኒት መድኃኔዓለም ቤተክርስቲያን ፈለገዮርዳኖስ ሰ/ት/ቤት

በአታ ለማርያም

  
     እመቤታችን ማርያም የኢያቄምና የሀና በእርጅና ዘመናቸው ያገኟት  የብጽአት(የስለት)   ልጅናት
ከእለታት አንቀን እመቤታችን ከሀና ከእናቷ እቅፍ ወርዳ ጠፋች ሀናም በብዙፍለጋ አገኘቻት ። ቅድስት ሀናው ኢያቄምን ይህች ብላቴና ሆዷ ዘመድ ሳይወድ አፏ እህል ሳይለምድ ወስደን ከቤተ መቅደስ እንስጣት አንዳች ብትሆንብን ከልጃችንም ከእግዚአብሔርም ሳንሆን እንቀራለን አለችው እርሱም ፍቅርሽ ይለቅልሽ ብዬ ነው እንጂ የኔማ ፈቃዴነው አላትናወዲያው ወደ ብተመቅደስ ወሰዷት  ሊቀካህናቱ ዘካርያስም የምግቧን ነገር እንዴት አደርጋለሁ ብሎ መጥቅዕ (ደወል) መቶ ህዝቡን ሰበሰበ ህዝቡም የምግቧን ነገር እንዴት እንዲያደርጉ ሲጨነቁ መልዐኩ ቅዱስ ፋኑኤል ኅብስት ሰማያዊ ጽዋዕ ሰማያዊ ይዞ ረቦ ታየ።
      ዘካርያስ ከዚህ በፊት በስውር ይቀበል ነበርና ለእኔ የመጣ ነው ብሎ ቀረብ አለ መልዐኩም ወደላይ  ረቀበት የእግዚአብሔር ነገር አይታወቅም ምናልባት ለዝች ብላቴና የመጣ ይሆናል ብለው ለብቻዋ አድርገውዋት ፈቀቅ አሉ ድንኩል ድንኩል እያለች ሐናን ስትከተል መልዐኩ ፈጥኖ ወርዶ አንድ ክንፉን አንጥፎ  አንድ ክንዱን ጋርዶ በሰው ቁመት ልክ ከምድር አስለቅቆ መግቧት እመቤቴሆይ  ረኀብ በአስመታሁሽ  ይቅር በዪኝ ብሏት ወደሰማይ ዐረገ ዘካርያስም የምግቧ ነገር ከተያዘልንማ ብሎ ከቤተ መቅደስስ አስገብቷታል ።
እመቤታችን ቅድስት ድንግል ማርያምወደ ሁላችን ቤት በረድኤት  ትግባ የእመቤታችን ልመናዋ ክብሯ የልጇም ቸርነት በሁላችንምላይ ይደር።
             

Читать полностью…

የቃሊቲ ደብረ መድኃኒት መድኃኔዓለም ቤተክርስቲያን ፈለገዮርዳኖስ ሰ/ት/ቤት

ለሰንበት ትምህርት ቤታችን አባላት በሙሉ የአቡነእጨጌ ዮሀንስ ጉዞ ወደ ታህሳስ 13 ስለተሸጋገረ የፊታችን እሁድ ከቤተክርስቲያን ጉባኤ በኃላ መደበኛው የትምህርት እና የዝማሬ መርሃግብር ስለሚኖር መማርያ መሳሪያ እንድትይዙ ስንል ጥሪያችንን እናስተላልፋለን።
ሰንበት ት/ቤቱ

Читать полностью…

የቃሊቲ ደብረ መድኃኒት መድኃኔዓለም ቤተክርስቲያን ፈለገዮርዳኖስ ሰ/ት/ቤት

/channel/+3uxZm2BmV042OTdk

Читать полностью…

የቃሊቲ ደብረ መድኃኒት መድኃኔዓለም ቤተክርስቲያን ፈለገዮርዳኖስ ሰ/ት/ቤት

ከእሁድ እስከ እሁድ በጉልበት ደከመኝ ሰለቸኝ ሳትሉ ስታግዙን የነበራችሁ ዛሬ በመርሀ ግብር መጣበብ ምክንያት በደንብ ያላመሠገናችሁ ከታች ያላችሁና ሌሎች በጉልበት የምታግዙን ፈጣሪ ይስጥልን እያልን የተለመደው ትብብራችሁን እንዳይለየን እያልን ነገ ሰኞና እሮብ ከ10:00 ጀምሮ ኮረት ስለምናስገባና ማክሰኞ የአናፂ ስራ ስላለ እንድትገኙልን።
1. አዛዥ ጠበቃው
2. ምስጋናው ሞላ
3. ናሆም ተሻለ
4. ዲ/ን ታደሰ ክፍሌ
5. ብሩክ ስንታየሁ
6.ምንተስኖት ሙሉ
7.ተመስገን ተስፋዬ
8.ዳኛቸው አሰፋ
9. ታሪኩ ተሾመ
10.መንበሩ በላይ
11. ሚኪያስ አብዮት
12. ሳሙኤል ተስፋዬ
13. ናትናኤል ተስፋዬ
14. ዲ/ን የአብፀጋ
ሲሆኑ ስለምታደርጉልን ትብብር በልዑል እግዚአብሔር ስም እናመሰግናለን።
የህንፃ አሰሪ ኮሚቴ ሰብሳቢ

Читать полностью…

የቃሊቲ ደብረ መድኃኒት መድኃኔዓለም ቤተክርስቲያን ፈለገዮርዳኖስ ሰ/ት/ቤት

የዛሬውን በዓል በአካል መከታተል ላልቻላችሁ ፅናፅል ሚዲያ ላይ live ይተላለፋል።

Читать полностью…

የቃሊቲ ደብረ መድኃኒት መድኃኔዓለም ቤተክርስቲያን ፈለገዮርዳኖስ ሰ/ት/ቤት

በስመአብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ አሐዱ አምላክ አሜን!!!
የጥምቀት አከባበር
ጥምቀት ጌታችን መድሃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ በባህረ ዮርዲያንኖስ በጥር 11 ቀን መጠመቁን በማጠየቅ እኛ የኦርቶዶክ ተዋህዶ እምነት ተከታዮች በየዓመቱ ጥር 10 ከተራ ጥር 11 ደግሞ የጥምቀት በዓል በማለት በታላቅ ደምቀት እናከብራለን። የበዓሉ ዋዜማ የከተራ በዓልና የፆመ ታሪካዊ እና ሃየማኖታዊ ዳራ ምንድን ነው??

Читать полностью…

የቃሊቲ ደብረ መድኃኒት መድኃኔዓለም ቤተክርስቲያን ፈለገዮርዳኖስ ሰ/ት/ቤት

የሰንበት ት/ቤታችን አባል የሆነው የወንድማችን አብነት የሺዋስ አያት ስላረፉ ቀብር የምንችል እንድንገኝ እንዲሁም ማታ 12:00 ሰዓት ላይ በቤት ጉባኤ ስለሚኖር ሁላችንም ተገኝተን ወንድማችንን እንድናፅናና

Читать полностью…

የቃሊቲ ደብረ መድኃኒት መድኃኔዓለም ቤተክርስቲያን ፈለገዮርዳኖስ ሰ/ት/ቤት

✨✨✨✨✨⚡⚡⚡✨✨✨✨✨ እንኳን ለብርሀነ ጥምቀቱ በሰላም አደረሳችሁ።💦💦💦💦💦💦💦💦💦💦💦💦💦💦💦

ሰላም ውድ አባላት ስም ዝርዝራቹ ያለ ለምታገለግሉ አባላት በሙሉ፣፣፣
⚡⚡⚡
✅ የከተራ ቀን (ቅዳሜ)፦5:00 ሰአት


✅5:00 የክብር ልብስ መሰጠት ይጀምራል ። በስራ እና በት/ት ምክንያት የማትችሉ ልጆች እንዲቀመጥላችሁ እንድታሳውቁ::
💦💦💦💦💦💦💦💦💦💦💦

በተጨማሪ🧏‍♀ ለአገልግሎት ስትመጡ አለባበሳችሁ ክርስቲያናዊ እና ከተቻለ ነጭ ጫማ ቢሆን ።


ሰላመ እግዚአሔሄር ከእናነተ ጋራ ይሁን


በዚህ ስልክ ቁጥር፦0942712658
;-099 172 8624

በinbox አሳውቁ ወይም ደውሉ!! !! !!





☘ከመዝሙር ክፍል🍀

Читать полностью…

የቃሊቲ ደብረ መድኃኒት መድኃኔዓለም ቤተክርስቲያን ፈለገዮርዳኖስ ሰ/ት/ቤት

በስመአብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ አሀዱ አምላክ አሜን።
☘☘☘☘☘☘☘☘☘☘☘☘

የጧፍ አገልግሎትን በተመለከተ
✨✨✨✨✨✨✨✨✨✨✨
✅በ3 በአታ እና በ7 ስላሴ መደበኛ እና ሰራተኞች ክፍል ይገለገላል።
✨✨✨✨✨✨✨✨✨✨✨✨
✅በ6አርሴማ እና በ14አቡነ አረጋዊ
ቀዳማይ እና ካዕላይ ክፍል ይገለገላል።
✨✨✨✨✨✨✨✨✨✨✨
✅በ27 መድኃኒዓለም ሁሉም ክፍላት ይገለገላል
✨✨✨✨✨✨✨✨



🌟እሁድ በ4/5/2017 አጠቃላይ ጥናት የጥምቀት መዝሙራት እና ወረባት ይጠናል ። ለጥምቀት የመጨረሻ እሁድ እንደመሆኑ በአንድነት መጠናት ይኖርበታል ላልሰሙትም አሰምታችሁ እንድመጡ ።
⚡⚡⚡⚡⚡⚡⚡⚡⚡⚡⚡⚡⚡⚡⚡⚡⚡⚡⚡⚡⚡⚡⚡⚡

ሰአት👈3:30 ጀምሮ
ቦታ👈 ትልቁ ህንፃ ቤ/ክ ወይም ትልቁ አዳራሽን
💦💦💦💦💦💦💦💦💦💦💦

ማሳሰቢያ➡ በተቻላቹ አቅም ለጓደኛችሁ ላልሰሙት አሰምታችሁ እንድመጡ::

⚡⚡⚡⚡⚡⚡⚡⚡⚡⚡⚡
💦 መልካም ቀን ከመዝሙር ክፍል💦

Читать полностью…

የቃሊቲ ደብረ መድኃኒት መድኃኔዓለም ቤተክርስቲያን ፈለገዮርዳኖስ ሰ/ት/ቤት

ሰላም ታህሳስ 27 የካዕላይ ክፍል የኢትዮጵያ ቤተክርስቲያን ታሪክ ሚድ ፈተና (ከመግቢያ -በግብፅ እስከ ነገሱ ኢትዮጵያዊያን ድረስ) እና ራብዓይ ክፍል ዮሀንስ ወንጌል አንድምታ ምዕራፍ 3 ፈተና ስለሚኖር ከወዲሁ ተዘጋጁ

Читать полностью…

የቃሊቲ ደብረ መድኃኒት መድኃኔዓለም ቤተክርስቲያን ፈለገዮርዳኖስ ሰ/ት/ቤት

🙋 ውድ አባላት ለወጣንያን እና ቀዳማይ ክፍል በ19/4/2017 ከቀኑ 10:00ጀምሮ ምዘናው ይሆናል ። ለሰራተኞች ክፍል በ20/4/2017 (እሁድ) ምዘና መኖሩ ይታወቃል ሚጀመረው
'ምዘናው ' 3:00 በመሆኑ ቶሎ ለመጨረስ ከወዲሁ ተዘጋጅታችሁ በጊዜ እንድትመጡ ።



ከመዝሙር ክፍል☘☘☘🙏

Читать полностью…

የቃሊቲ ደብረ መድኃኒት መድኃኔዓለም ቤተክርስቲያን ፈለገዮርዳኖስ ሰ/ት/ቤት

ትምህርተ ሀይማኖት ሰራተኞች ክፍል ማጠቃለያ ፈተና እሑድ በ20 ይኖረናል ተዘጋጁ

Читать полностью…

የቃሊቲ ደብረ መድኃኒት መድኃኔዓለም ቤተክርስቲያን ፈለገዮርዳኖስ ሰ/ት/ቤት

እንዳይረሳ ለማስታወስ ያህል

መዝሙር ክፍል

Читать полностью…

የቃሊቲ ደብረ መድኃኒት መድኃኔዓለም ቤተክርስቲያን ፈለገዮርዳኖስ ሰ/ት/ቤት

🖐🖐🖐የጥር ስላሴ ወረብ

+ ነአምን በአብ ወነአምን በወልድ ወነአምን በመንፈስ ቅዱስ.
+አሀዱ ውዕቱ አምላክ ፍፁም አሀዱ ውዕቱ.

ትርጉም:- ፍፁም አንድ አምላክ በሚሆን በአብ ቢወልድ በመንፈስ ቅዱስ ስም እናምናለን።



🙋መልካም ጥናት🙏

ከመዝሙር ክፍል

Читать полностью…

የቃሊቲ ደብረ መድኃኒት መድኃኔዓለም ቤተክርስቲያን ፈለገዮርዳኖስ ሰ/ት/ቤት

🔔🔔🔔 ሰላም ለሰንበት/ቤታችን አባላት በሙሉ እንኳን ለእናታችን ለሰማዕቷ ለቅድስት አርሴማ አመታዊ በአል በሰላም አደረሳችሁ ። በሰአታችሁም እንድትገኙ።

🙏 ከሰማዕቷ ፀጋና በረከት ያሳትፈንመልካም አገልግሎት ይሁንልን ።🙏


☘ መዝሙር ክፍል🍀

Читать полностью…

የቃሊቲ ደብረ መድኃኒት መድኃኔዓለም ቤተክርስቲያን ፈለገዮርዳኖስ ሰ/ት/ቤት

🙏 🙏🙏 መስከረም 29🙏🙏🙏
ሰላም ለሰንበት ትምህርት ቤታችን አባላት በሙሉ የበዓታ ማርያምን ታቦት 1:00 ሰዓት ላይ ከድልድዩ ጋር ጀምረን ስለምናጅብ ሁላችንም 12:30 ላይ ደብር ተገኝተን የምስጋና ልብስ ለብሰን ከማኅበረ ካህናቱ ጋር አብረን በመሆን እንቀበላለን ። ስለዚህም ያያቹ ላላዩት የሰማችሁ ላልሰሙት አሰምታችሁ እንድትገኙ ። መቅረትም ሆነ ማርፈድ ክልክል ነው ።

2ኛ ጴጥሮስ 2:10 ስለዚህ ወንድሞች ሆይ መጠራታችኹንና መመረጣችኹን ታጸኑ ዘንድ ከፊት ይልቅ ትጉ እነዚህን ብታደርጉ ከቶ አትሰናከሉምና።

🙏ከባዕታ ለማርያም ረድኤት በረከት ያሳትፈን🙏

👏 መዝሙር ክፍል 👏

Читать полностью…

የቃሊቲ ደብረ መድኃኒት መድኃኔዓለም ቤተክርስቲያን ፈለገዮርዳኖስ ሰ/ት/ቤት

በዚህ link ሰዎችን በመጋበዝ የሰንበት ትምህርት ቤታችንን የልማት ስራዎች ይደግፉ

Читать полностью…

የቃሊቲ ደብረ መድኃኒት መድኃኔዓለም ቤተክርስቲያን ፈለገዮርዳኖስ ሰ/ት/ቤት

ሰላም ለሰንበት ትምህርት ቤታችን አባላትና ምዕመናን በሙሉ ከደብሩ ፅህፈት ቤት የበዓታ ለማርያም ታቦት የፊታችን ቅዳሜ ተቀብለን እሁድ ትገባለች የሚል መልዕክት ከቤ/ክኗ ስለተላለፈልን የአቡነ እጨጌዮሀንስን ጉዞ ወደ ታህሳስ 13/2017 ያስተላለፍን መሆናችንን ከይቅርታ ጋር እንገልፃለን።

Читать полностью…

የቃሊቲ ደብረ መድኃኒት መድኃኔዓለም ቤተክርስቲያን ፈለገዮርዳኖስ ሰ/ት/ቤት

https://www.youtube.com/live/MhVNeV_abbM?si=QwOj2uvY4QPR8484

Читать полностью…

የቃሊቲ ደብረ መድኃኒት መድኃኔዓለም ቤተክርስቲያን ፈለገዮርዳኖስ ሰ/ት/ቤት

🔔🔔ነገ ጠዋት 1:30 በፍፁም እንዳትቀሩ አገልግሎት አለ።🔔
መዝሙር ክፍል

Читать полностью…
Subscribe to a channel