medhanialem | Unsorted

Telegram-канал medhanialem - የቃሊቲ ደብረ መድኃኒት መድኃኔዓለም ቤተክርስቲያን ፈለገዮርዳኖስ ሰ/ት/ቤት

189

Subscribe to a channel

የቃሊቲ ደብረ መድኃኒት መድኃኔዓለም ቤተክርስቲያን ፈለገዮርዳኖስ ሰ/ት/ቤት

የምርጫ ካርዴ ለቅድስት ቤተክርስቲያኔና ለሀገሬ

"አንተም ከህዝብ ሁሉ አዋቂዎችን እግዚአብሔርን የሚፈሩት፥ የታመኑ የግፍን ረብ የሚጠሉትን ሠዎች ምረጥ " ዘፀ 18:21

ሀገርን እንደሶሪያ
ቅድስት ቤተክርስቲያናችንን እንደ ቱርክ እንዳናጣት ባለ ማዕተቦች ያሉበትን ለይተን እንምረጥ።

የምርጫ ድምጻችንን ከመስጠታችን በፊት
ወደ ምርጫ መስጫ ከመሄዳችሁ በፊት የምርጫ ቅስቀሳውን በየቦታው ከተለጠፈው ብርቅርቅ ምስል በላይ በፓርቲዎቹ ውስጥ ያለውን አቋም ፈትሹ በየፓርቲው ውስጥ ያሉትን እጩ ኦርቶዶክሳውያን ለዩ ትላንት ባሳለፍናቸው ሶስት ዓመታት ውስጥ ኦርቶዶክሳውያን ላይ የደረሰውን መከራ አይተው እንዳላዩ ሰምተው እንዳልሰሙ በመከራችን ላይ የተሳለቁብን ባለስልጣናት እንዳትረሱ
ባሳለፍናቸው ሶስት ዓመታት ብቻ
 ቡራዩ፣ጅግጅጋ ፣ሻሸመኔ፣ መተከል፣ ወለጋ፣ ጅማ፣ ማይካድራ፣ ትግራይ፣አጣዬ በማንነትና በሃይማኖታቸው ምክንያት ብቻ ወገኖቻችን ተጨፍጭፈዋል
 ማተባቸው እየተበጠሰ ጋዝ ተርከፍክፎ ተቃጥለው ወደ ወንዝ ተወርውረው እሬሳቸው አይቀበርም በማለት ለውሻ ተሰጥተዋል
 የካህናት ሚስት፣ነብሰጡር እናቶች፣ ለአቅመ ሂዋን ያልደረሱ ህጻናት በግልና በቡድን ተደፍረው ቅስማቸው ተሰብሮ አካላቸው ቆሽሾ ወድቀዋል
 ካህናት ዲያቆናት የሰንበት ትምህርት ቤት ተማሪዎች በመንገድ ላይ ተገለው ደማቸው ፈሷል
 ቤተ ክርስቲያን ተቃጥላ መቅደሷ ተደፍሯል
 ቤተከርስቲያንና ምዕመኗ በየቦታው የአደባባይ በዓላት ማክበሪያ ይዞታ ቦታዋ ተነጥቋል
 በኦሮሚያ ክልል ኦርቶዶክሳውያን ቤት ንብረታቸውን ጥለው ተሰደዋል አብያተ ክርስቲያናት ተዘግተዋል
 በመንግሥትና በግል ሚድያ ከመንግሥት ባለስልጣን እስከተራ አክቲቪስት በአደባባይ ቤተከርስቲያንን ሰድቧል የቤተከርስቲያኗን ቅዱስ ሲኖዶስ ፓትርያሪከር ዘኢትዮጵያን ዘልፏል
ወደ ምርጫ ጣቢያ ከመሄዳችሁ በፊት የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ከርስቲያን ትልቅ መከራ ውስጥ እንዳለች የቤተከርስቲያንን መከራ የሚያስቆም ለደረሰባት ግፍ ፍትህ የሚሰጥ የሰው ልጅ ሰው በመሆኑ ብቻ ተከብሮ እንዲኖር የሚያደርግ ፓርቲ ማን እንደሆነ አሰላስሉ!
ምርጫ ስንመርጥ ቤተ ከርስቲያንን እያሰብን ይሁን ቤተ ከርስቲያን የተባለችው የምዕመናን ሕብረት ናት ሕብረታችንን እናስጠብቅ ድምጻችን ለቤተከርስቲያናችን!!

Читать полностью…

የቃሊቲ ደብረ መድኃኒት መድኃኔዓለም ቤተክርስቲያን ፈለገዮርዳኖስ ሰ/ት/ቤት

+++ ከካም መንገድ ተመለሱ +++
* ዛሬ ቤተክርስቲያናችንን እጅግ በጣም እየጎዳት ያለው ከውጪው የጥቃት እንቅስቃሴ ይልቅ የውስጡ ውስብስብ እንቅስቃሴ ነው። በማወቅም ይሁን ባለማወቅ ብዙዎች ቤተክርስቲያንን ክፉኛ እየጎዷት ነው። በአደባባይ ዕርቃኗን እየገለጡ በአሕዛብ ፊት መዘባበቻ ከማድረግ በዘለለ በምእመናን መካከል ጥርጥርና መለያየት እንዲፈጠር እያደረጉ ነው።

* እርግጥ ነው በቤታችን እጅግ በርካታ ችግሮች አሉ። ቢሆንም ችግሮቹ የውስጣችን እንጂ የአደባባይ አይደሉም። ስለዚህ በቤታችን እንጂ በአደባባይ የምንከራከርባቸው፥ የምንተቻችባቸው፥ የምንሰዳደብባቸው፥ የምንጎሻሸምባቸው ወይም የእውቀታችንን ልክ የምናሳይባቸው ወይም የጽሁፍ ችሎታችንን የምናስመሰክርባቸውም አይደሉም።

* ማንም አዋቂ ነኝ ካለ ለምን በአደባባይ የወንጌሉን የምሥራች በመስበክ የቤተክርስቲያንን የአገልግሎት ግዳጅ አያግዝም? ወይም ምእመናን በመንፈሳዊ ሕይወታቸው እንዲበረቱና ወደ ምሥጢራተ ቤተክርስቲያን እንዲቀርቡ አያንጽም?

* ሌላው ደግሞ በእውቀትና በመንፈሳዊነት መካከል የሰማይና የምድር ያህል ልዩነት መኖሩንም መገንዘብ ያስፈልጋል። አዋቂ ሆነህ መንፈሳዊነቱ ላይኖርህ ወይም መንፈሳዊነቱ ተትረፍርፎ እውቀት ላይኖርህ ይችላል። “ፍቅር ለዘወትር አይወድቅም፤ ትንቢት ቢሆን ግን ይሻራል፤ ልሳኖች ቢሆኑ ይቀራሉ፤ እውቀትም ቢሆን ይሻራል።”(1ኛ ቆሮ.13፥8)

* እንደዚሁ ሙያና መንፈሳዊነትም መለየት አለበት። ማንኛውም የሙያ ደረጃና ምስክርነት ካላጣመሩትና ካልኖሩበት በቀር ከመንፈሳዊነት ጋር ተዛምዶ ላይኖራቸው ይችላል። ሰው ሙያው በሥነ መለኮት ዘርፍ ቢሆንም እንኳ ባለሙያ እንጂ መንፈሳዊ ላይሆን ይችላል። ስለ እግዚአብሔር ሊያውቅ እግዚአብሔርን ግን ላያውቅ፤ ስለ ሃይማኖት ሊያውቅ ሃይማኖቱን ግን በሕይወት ላያውቅና ላይኖርበት ላይጠቀምበትም ይችላል።

* በፌስ ቡክና በዩቲዩብ ሚድያዎች የምንዘረግፋቸው የቤተክርስቲያን የውስጥ ጉዳዮች የሚያንጸው ማንን ነው? መእመናንን ነው እንዳንል ምን ያህሉ ኦርቶዶክሳዊ ነው ፌስ ቡክና ዩቲዩብ የሚጠቀመውና የሚከታተለው? ለመሆኑ እየተደረገ ያለው ስብከት ነው? ማንቃት ነው? መካሰስ ነው? መፈራረጅ ነው? ተቆርቋሪነት ነው? ወይስ ዝናንና ክብርን ማሳደግ ነው? ወይስ የቲፎዞ(ተከታይ) ብዛት ፉክክር ነው።

* የቤተክርስቲያንን የውስጥ ጉዳይና ችግር አደባባይ ላይ ማስጣት ዕውቀትም፥ ተቆርቋሪነትም፥ አገልግሎትም ሊሆን አይችልም ከውጭ ኃይሎች ይልቅ ቤተክርስትያንን በራስ እጅ ማፍረስ እንጂ። በካም መንገድ መጓዝ እንጂ።

* እኔ እላለሁ፣ ማናችንም ከቤተክርስቲያን አንበልጥምና አካሄዳችን እንዲህ ከሆነ፥ መንገዳችን የካም ከሆነ ዕውቀታችንም፥ ተቆርቋሪነታችንም፥ አገልግሎታችንም ይቅርባት። በርግጠኝነት ነው የምነግራችሁ በዚህ አንዳች አይጎድልባትም፤ እንዲያውም እፎይ ትላለች። የካም የግብሩ መጨረሻ በፃድቅ አባቱ መረገም እንደሆነ ቅድስት ቤተክርስቲያን እንዳትረግማችሁ ጥንቃቄ አድርጉ።

* አክቲቪስቶችም ብትሆኑ፥ ምንም ታላቅ ብትባሉ፥ ምንም ሚሊየን ተከታይ ቢኖራችሁ፥ በጀመራችሁበት መንገድ እንደ ሀሳባችሁ ሂዱ እንጂ የኦርቶዶክሳዊት ተዋሕዶ አማኝ ብትሆኑም እንኳን በአደባባይ ከምትራቀቁበት የቤተክርስቲያን የውስጥ ጉዳይ ታቀቡ አይደለም ውጡ!!! ይበልጡኑ ደግሞ በናንተ አያምርም። ፖለቲካና ማኅበራዊ ጉዳይ የአደባባይ ነው፤ የቤተክርስቲያን ጉዳይ ግን የአማኞቿ የውስጥ ጉዳይ ብቻ ነው።

* በማኅበራዊ ሚድያ የአድማጭ ተመልካች መድረክ ከፍታችሁ ለቤተክርስቲያን የማይናቅ አስተዋፅዖ እያበረከታችሁ ያላችሁ አገልጋዮችም በዚህ ረገድ ድካማችሁን የሚያመክንና ዓላማችሁን የሚፃረር ድርጊት ውስጥ እንዳትወድቁ ብርቱ ጥንቃቄ እንድታደርጉ በእግዚአብሄር ርኅራኄ እለምናችኋለሁ። መርሐ ግብር ስታዘጋጁ ከቤተክርስቲያን ጥቅም አኳያ በርዕሰ ጉዳዩ የሚገኘውን ትርፍና ኪሳራ አስቀድማችሁ አስሉ። መርሐ ግብራችሁ ለሁሉም ክፍት ስለሆነ ኦርቶዶክሳውያኑን ብቻ አድሬስ የምታደርጉ መስሏችሁ እንዳትዘናጉ። ስለዚህ በርዕሰ ጉዳይ መረጣ ላይ የውስጥ ችግራችን አጀንዳ ሆኖ አደባባይ እንዳይወጣ ብርቱ ጥንቃቄ አድርጉ።

* እንደኔ እንደኔ የቤት ውስጥ መድረክ እንዲዘጋጅና ተቆርቋሪ ነኝ፥ የቤተክርስቲያንን ችግር የሚፈታ የመፍትሄ ሀሳብ አለኝ፥ በዕውቀቴ ማገዝ እችላለሁ የሚል ኦርቶዶክሳዊ ሁሉ ከማኅበራዊ ሚድያ ወርዶ ወደ እልፍኙ ተሰብስቦ እንዲከራከርና በዚህ የጭንቅ ጊዜ በእውነተኛ ልጅነት ቤተክርስቲያንን ከመከራዋ እንዲታደጋት ምክር፥ ቅስቀሳና ግፊት ብታደርጉ ባለውለታ ትሆናላችሁ።

* ስለዚህ በማወቅም ይሁን ባለማወቅ ወይም ባለማስተዋል ቤተክርስቲያንን የማኅበራዊ ሚዲያ ላይ ሰቅላችሁ መከራዋን የምታበዙባት አባቶች ወንድሞችና እህቶች እባካችሁ ከካም መንገድ ተመለሱ፣ ከእርግማንም ራቁ። (ዘፍ.9፥20-27)

* ሰላመ እግዚአብሔር ከሁላችን ጋር ይሁን። እንደ ቸርነቱ፥ እንደ ይቅርታውና እንደምኅረቱ እንጂ እንደ ኃጢአታችንና እንደ በደላችን አያድርግብን።

Читать полностью…

የቃሊቲ ደብረ መድኃኒት መድኃኔዓለም ቤተክርስቲያን ፈለገዮርዳኖስ ሰ/ት/ቤት

የቅዱስ ሲኖዶስ ዋና ጸሐፊ ብፁዕ አቡነ ዮሴፍ የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተክርስቲያን የቅዱስ ሲኖዶስ ምልአተ ጉባኤ የግንቦት ፲፱ ቀን ፳፻፲፫ ዓ.ም ክንውን አስመልክቶ መግለጫ ሰጥተዋል።

- ቅዱስ ሲኖዶስ ግንቦት ፲፱ ቀን ፳፻፲፫ ዓ.ም በጸሎት ጉባኤውን ጀምሯል፡፡

- በቅድሚያ በትናንትናው ዕለት ውሳኔ የሰጠባቸውን ሁለት አጀንዳዎች ቃለ ጉባኤ ቀርቧል፡፡ በዚህም የቅዱስነታቸውን የመክፈቻ ንግግር ቅዱስ ሲኖዶስ አጽድቆታል፡፡

- ሀገራዊ እና ወቅታዊ ጉዳይን አስመልክቶ በሀገራችን በሚታዩት ወቅታዊ ችግሮች የፖለቲካ አለመረጋጋት፣ ስደትና መፈናቀል ዙርያ በሰፊው ተወያይቶ የመፍትሔ ሐሳብ የያዘ ውሳኔ አሳልፏል፡፡ ውሳኔውም በዝርዝር በሚሰጠው መግለጫ የሚገለጽ ይሆናል፡፡

- በተጨማሪ የቅድስት ቤተክርስቲያን የአምልኮ ሥፍራ የሆኑትን የመስቀል እና የጥምቀት ቦታዎች አስመልክቶ ሰፊ ውይይት በማድረግ ቅዱስ ሲኖዶስ ችግሩ የሚፈታበትን ውሳኔ አሳልፏል፡፡ የውሳኔው ዝርዝር በአጠቃላይ መግለጫው ይቀርባል።

የምሥራቅ ጎጃም ሀገረ ስብከትን አስመልክቶ ፡-

- በምስካበ ቅዱሳን ቆጋ ቅ/ኪዳነ ምሕረት አንድነት ገዳም የተፈጸመውን የዶግማ እና ቀኖና ጥሰት ቅዱስ ሲኖዶስ በሰፊው ከተወያየበት በኋላ ሕገ ወጥ በመሆኑ ውሳኔ አሳልፎበታል፡፡ዝርዝሩ በማጠቃለያ መግለጫው የሚገለጽ ይሆናል፡፡

- በምስራቅ ጎጃም ሀገረ ስብከት የክፍሉ ሊቀ ጳጳስ የነበሩት ብፁዕ አቡነ ማርቆስ ወደ መንበረ ፓትርያርክ ጠቅላይ ቤተክህነት ስብከተ ወንጌል እና ሐዋርያዊ ተልዕኮ መምሪያ የበላይ ኃላፊ ሊቀ ጳጳስ እና የጎፋ ደብረ ብሥራት ቅዱስ ገብርኤል ካቴድራል የበላይ ኃላፊ ሊቀ ጳጳስ ሆነው እንዲያገለግሉ ዝውውር አድርጓል፡፡

- የምሥራቅ ጎጃም ሀገረ ስብከትን በተመለከተ ብፁዕ አቡነ ያሬድ የመንበረ ፓትርያርክ ጠቅላይ ጽ/ቤት ዋና ሥራ አስኪያጅ አርሲ ሀገረ ስብከት የሰበካ ጉባዔ ማደራጃ ሊቀ ጳጳስ በሊቀ ጳጳስነት እንዲመሩት ተወስኗል፡፡

- በሰዋሰወ ብርሃን ቅዱስ ጳውሎስ መንፈሳዊ ኮሌጅ እና በደብሩ መካከል ያለውን አለመግባባት በሰፊው ተመልክቶ ቅዱስ ሲኖዶስ የመፍትሔ ውሳኔ አሳልፏል፡፡

- በአዲስ አበባ ሀገረ ስብከት ላይ የሚቀርበውን የመልካም አስተዳደር ችግር ቅሬታ በሰፊው የተመለከተው ቅዱስ ሲኖዶስ የቀረበው የመልካም አስተዳደር ችግር እርምት እንዲደረግበት ሲል ለሀገረ ሰብከቱ ማሳሰቢያ ሰጥቷል፡፡ ዝርዝሩ በማጠቃለያ መግለጫው ይቀርባል።

- በሀገራችን በተለያዩ ጊዜያት እደረሱ ያሉ ችግሮችን አስመልክቶ ሦስት ብፁአን አበው ሊቃነ ጳጳሳት ለቅዱስ ሲኖዶስ መግለጫ አዘጋጅተው እንዲያቀርቡ መርጧል፡፡

- በመላው ሀገሪቱ እና በዓለም አቀፍ ደረጃ ባሉት ኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ አብያተ ክርስቲያናት እና ገዳማት በሙሉ ስለ ሀገራችን ሰላም ጸሎተ ምኅላ እንዲደረግ ቅዱስ ሲኖዶስ ወስኗል፡፡-

- ቅዱስ ሲኖዶስ በቀረቡት አጀንዳዎች ላይ ነገ የማጠቃለያ ውይይት እና ቃለ ጉባኤ ማጽደቅ ካከናወነ በኋላ ሰኞ ግንቦት 23 ቀን 2013 ዓ.ም መግለጫ ይሰጣል፡፡

ምንጭ EOTC TV

Читать полностью…

የቃሊቲ ደብረ መድኃኒት መድኃኔዓለም ቤተክርስቲያን ፈለገዮርዳኖስ ሰ/ት/ቤት

ብፁዕ አቡነ ያሬድ የጠቅላይ ቤተ ክህነት ዋና ሥራ አስኪያጅና የአርሲ ሀገረ ስብከት ሊቀ ጳጳስ ከሚመሩት ሀገረ ስብከት በተጨማሪ የምሥራቅ ጎጃምን ሀገረ ስብከት ደርበው እንዲመሩ ቅዱስ ሲኖዶሱ በዛሬው ዕለት ውሳኔ አሳልፏል።

Читать полностью…

የቃሊቲ ደብረ መድኃኒት መድኃኔዓለም ቤተክርስቲያን ፈለገዮርዳኖስ ሰ/ት/ቤት

https://cl2win.com/NGJldGVu

Читать полностью…

የቃሊቲ ደብረ መድኃኒት መድኃኔዓለም ቤተክርስቲያን ፈለገዮርዳኖስ ሰ/ት/ቤት

https://go2ere.com/NGJldGVu

Читать полностью…

የቃሊቲ ደብረ መድኃኒት መድኃኔዓለም ቤተክርስቲያን ፈለገዮርዳኖስ ሰ/ት/ቤት

በምሥራቅ ጎጃም ሀገረ ስብከት የቅብዓት እምነት አራማጆች 3ተኛ የህገወጥ ጳጳስ ሹመት ይፋ ማድረጋቸው ተገለፀ !!!

*************************************

በምሥራቅ ጎጃም ሀገረ ስብከት በቆጋ ምስካበ ቅዱሳን ኪዳነ ምህረት ገዳም ከአንድ አመት በፊት አባ ኪዳነ ማርያም እና አባ ሄኖክ ፈንቴ የተባሉ መነኮሳት የቅብዓት እምነት አራማጆች ራሳቸውን ጳጳሳት ብለው መሾማቸው ይታወሳል።

ከዚሁ ጋር ተያይዞ የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን ቅዱስ ሲኖዶስ የመነኮሳቱ ሢመት ህገወጥ ተፈፃሚነት የሌለውና ከቀኖና ቤተ ክርስቲያን የወጣ መሆኑን ገልፆ መነኮሳቱ በገዳም ተወስነው እንዲቆዩ ውሳኔ ቢያሳልፍም በምሥራቅ ጎጃም ሀገረ ስብከት ዳተኝነትና ለጉዳዩ ድጋፍ የሚሰጡ የሀገረ ስብከቱ የአስተዳደር አካላት በመኖራቸው የቅዱስ ሲኖዶሱ ውሳኔ ተፈፃሚ ሳይሆን ቀርቷል።

በትናንትናው እለት የህገወጥ ጵጵስና ሹመት ዓመታዊ በዓል በሚል የቅብዓት እምነት አራማጆች ማክበራቸውን ተከትሎ ሌላ 3ተኛ ሹመት ይፋ ማድረጋቸው ተገልጿል።

በምሥራቅ ጎጃም ሀገረ ስብከት አገልጋይ የሆኑት መምህር ሰናይ እንዳለ ለዝግጅት ክፍላችን እንደገለፁት ራሳቸውን "ብፁዕ አባ ዮሐንስ" እና "ፓትርያርክ ቄርሎስ" ብለው ቀደም ተብሎ ከተገለፀው ባሻገር በትናንትና እለት አከበርነው ባሉት በዓለ ሢመት ወቅት መርጌታ ሙሉ የተባለን ግለሰብ በቅርቡ መንኩሶ "ብፁዕ አባ ባስልዮስ" ተብሎ መሾሙ በይፋ መነገሩን ገልፀውልናል።

እንደ መምህር ሰናይ እንዳለው ገለፃ የሀገረ ስብከቱ ጽ/ቤት ለዚህ ህገወጥ ተግባር ተባባሪ መሆኑን የሚያምኑ መሀኑን ጠቅሰው ቅዱስ ሲኖዶስ መላ የሀገረ ስብከቱን ኃላፊዎች ፈትሾ ሊያስተካክል እንደሚገባ ገልፀዋል።

Читать полностью…

የቃሊቲ ደብረ መድኃኒት መድኃኔዓለም ቤተክርስቲያን ፈለገዮርዳኖስ ሰ/ት/ቤት

ለምን እንደምትኖር እወቅ፦

ህይወት ማለት የተሰጠህን ሃላፊነት ለመጨረስ የተሰጠችህ ጊዜ ናት።

ሃላፊነትህ ምንድን ነው?

በህይወትህ ማድረግ የምትፈልገው ነገር ምንድን ነው?

መልሱን ካወቅክ ለህይወት ያለህ አመለካከት ይቀየራል፡፡

@Binisiwe
@Binisiwe
@Binisiwe

ለአሰተያየት @BiniGirmachew_Bot

Читать полностью…

የቃሊቲ ደብረ መድኃኒት መድኃኔዓለም ቤተክርስቲያን ፈለገዮርዳኖስ ሰ/ት/ቤት

ማንን እንደምታገኝ አታውቅምና ለሁሉም ሰው ቅን ሁን፦

ሰዎችን አትናቅ ፤ በየትኛውም አጋጣሚ

ለምታገኛቸው ሰዎች ትክክለኛውን ነገር አድርግ፡፡


@Binisiwe
@Binisiwe
@Binisiwe

ለአሰተያየት @BiniGirmachew_Bot

Читать полностью…

የቃሊቲ ደብረ መድኃኒት መድኃኔዓለም ቤተክርስቲያን ፈለገዮርዳኖስ ሰ/ት/ቤት

የሰዎችን ያለማወቅ አግዝ ፤ ዕውቀትህ ባላወቁት ላይ እንድትኮራና እንድትፈርድ

አያድርግህ የአዋቂ ኩሩ ቁጥሩ ካላዋቂዎች

ነውና ማወቅ ባለዕዳነት እንዳይሆን አላዋቂዎችን እርዳቸው ።

@Binisiwe
@Binisiwe
@Binisiwe

ለአሰተያየት @BiniGirmachew_Bot

Читать полностью…

የቃሊቲ ደብረ መድኃኒት መድኃኔዓለም ቤተክርስቲያን ፈለገዮርዳኖስ ሰ/ት/ቤት

ክፋት አይሙቅህ ፣ መልካም ነገርም ብርድ ብርድ አይበልህ ።

ለክፋት አቅም ካለህ ለበጎ ነገርም አቅም አለህና ተግባርህ የምርጫ ውጤት ነውና አስብበት ።

@Binisiwe
@Binisiwe
@Binisiwe

ለአሰተያየት @BiniGirmachew_Bot

Читать полностью…

የቃሊቲ ደብረ መድኃኒት መድኃኔዓለም ቤተክርስቲያን ፈለገዮርዳኖስ ሰ/ት/ቤት

ከገነተ ጽጌ ቅዱስ ጊዮርጊስ የተነሡ ወጣቶች እና ሌሎች ምዕመናን መንበረ ፓትርያርክ ቅድስተ ማርያም ተከፍቶላቸው ወደ ቅጽረ ቤተክርስቲያን ገብተው ዝማሬ እያቀረቡ ነው።

Читать полностью…

የቃሊቲ ደብረ መድኃኒት መድኃኔዓለም ቤተክርስቲያን ፈለገዮርዳኖስ ሰ/ት/ቤት

የቅዱስ ሲኖዶስ ምልዐተ ጉባኤ ነገ ግንቦት 17 ቀን 2013 ዓ.ም ከቀኑ 10 ሰዓት በጸሎት ሥነሥርዓት ይጀመራል ።
***************************

የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤተ ክርሰቲያን ቅዱስ ሲኖዶስ ምልአተ ጉባኤ ነገ ግንቦት 17 ቀን 2013 ዓ.ም ከቀኑ 10 ሰዓት በመንበረ ፓትርያርክ ቅድስተ ቅዱሳን ማርያም ገዳም በሚያካሂደው የጸሎት ሥነሥርዓት ይጀምራል ።

የቅዱስ ሲኖዶስ ምልአተ ጉባኤ ረቡዕ ግንቦት 18 ቀን 2013 ዓ.ም በሚያካሂደው ጉባኤ ቋሚ ሲኖዶስ በምልአተ ጉባኤው መታየት ይገባቸዋል ።በማለት ያዘጋጃቸውን አጀንዳዎች ምልአተ ጉባኤው በሚሰይማቸው ብጹአን አባቶች እንዲታዩ ካደረገ በኋላ መካት ያለባቸው አጀንዳዎች እንዲካተቱ፣ መቅረት የሚገባቸው አጀንዳዎች እንዲቀሩና ሌሎች በአጀንዳነት መታየት የሚገባቸው አጀንዳዎች እንዲጨመሩ በማድረግ ለቅዱስ ሲኖዶስ ምልአተ ጉባኤ በማቅረብ ካጸደቀ በኋላ የጸደቁትን አጀንዳዎች መሰረት በማድረግና በቅደም ተከተል በመወያት ውሳኔ እንደሚያስተላልፍ ይጠበቃል።
በእለቱ ብጹዕ ወቅዱስ አቡነ ማትያስ ቀዳማዊ ፓትርያርክ ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት ዘኢትዮጵያ ሊቀ ጳጳስ ዘአክሱም ወእጨጌ ዘመንበረ ተክለሃይማኖም የጉባኤውን መከፈት በማስመልከት የመክፈቻ መልዕክት እንደሚያስተላልፉ ከቅዱስ ሲኖዶስ ጽህፈት ቤት ያገኘነው መረጃ ያመለክታል ።እኛም በየጊዜው የሚተላለፉ ውሳኔዎችን በወቅቱ በመዘገብ የምናቀርብ መሆኑን ከወዲሁ ለመግለጽ እንወዳለን ።

Читать полностью…

የቃሊቲ ደብረ መድኃኒት መድኃኔዓለም ቤተክርስቲያን ፈለገዮርዳኖስ ሰ/ት/ቤት

የጸሎት ጥሪ ለሰንበት ት/ቤታችን አባላት በሙሉ
እንደሚታወቀው ባለፈው ሳምንት ሰንበት ት/ቤታችን አዳዲስ አመራሮችን መምረጧ ስለሆነም የተመረጥነው አመራሮች ወደ ስራ ከመግባታችን በፊት ፈጣሪ በአገልግሎታችን ከፊት እንዲቀድም የ3 ቀን የፀሎት ሱባኤ ለመያዝ አቅደናል ስለሆነም የፊታችን አርብ ቅዳሜና እሁድ ከጉባኤ በኃላ የፀሎት መርሃግብር ስላለን የምትችሉ አባላት የበረከቱ ተሳታፊ ትሆኑ ዘንድ ጥሪያችንን እናስተላልፋለን።
ሰ/ት/ቤቷ

Читать полностью…

የቃሊቲ ደብረ መድኃኒት መድኃኔዓለም ቤተክርስቲያን ፈለገዮርዳኖስ ሰ/ት/ቤት

👉 ቅዳሜ ወይም እሑድ አያልፈኝም
የምርጫ ካርድ በማውጣት የመራጭነት ምዝገባ አጠናቅቃለው፡፡

👉 ‹‹እመርጣለሁ-በድምጼም የእኔን እና የቅድስት ቤተክርስቲያኔን መብት አስከብራለሁ››

👉 እባክዎ በዙርያዎ ያሉ ኦርቶዶክሳውያን ቅዳሜና እሑድ የምርጫ ካርድ እንዲያወጡ ያድርጉ በሚገባ ይቀስቅሱ፡፡ መምረጥ መብትም ኃላፊነትም ነው!
መብቶን ያስከብሩ፣ ኃላፊዎንም ይወጡ የምርጫ ካርድዎን ይውሰዱ!

Читать полностью…

የቃሊቲ ደብረ መድኃኒት መድኃኔዓለም ቤተክርስቲያን ፈለገዮርዳኖስ ሰ/ት/ቤት

✤ የአቡነ ሽኖዳ ቢሒሎች ✤

💎ቅዱስ መሆንን ብቻ መፈለግ በቂ አይደለም ቅዱስ የምንሆንበትም መንገድ እውነተኛ መሆን አለበት የሰዎች መንገድ ግን ብዙ ጊዜ የስሕተት ስለሆነ ይወድቃሉ ይነሳሉ።
💎የአገልግሎት ስኬት ብዙ ሕዝብ መሰብሰብ አይደለም ሕይወታቸውን ለውጦ ወደ እግዚአብሔር ማድርስ ነው እንጂ።
💎ከኃጢአት መሸሽ ውጫዊ የሆነ ነገር ነው ከኃጢአት ነጻ መውጣት ግን የልብ ውስጣዊ ሁኔታ ነው።
💎አንተ ታማኝ ሆነህ በፍቃድህ ከምትሰራቸው ኃጢአቶች ከታቀብክ እግዚአብሔር ደግሞ ያለፍቃድህ እንድትሠራቸው ከሚመጡብህ ኃጢአቶች ሁሉ ይጠብቅሃል።

የቅዱስነታቸው በረከታቸው ይደርብን!
🌿🍂🌿🍂🌿🍂🌿🍂🌿

Читать полностью…

የቃሊቲ ደብረ መድኃኒት መድኃኔዓለም ቤተክርስቲያን ፈለገዮርዳኖስ ሰ/ት/ቤት

ደብረ ምጥማቅ

ግብጽ በምትገኘው በእመቤታችን ቅድስት ድንግል ማርያም ስም በተሠራችው ደብረ ምጥማቅ ቤተ ክርስቲያን ጉልላት ላይ ድንግል ማርያም ከግንቦት ፳፩ ጀምሮ እስከ ፳፭ ቀናት በተከታታይ በመገለጧ ሕዝበ ክርስቲያን በዓሏን ያከብራሉ፡፡

እመቤታችን ቅድስት ድንግል ማርያም ከልጇ ጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ጋር ወደ ምድረ ግብጽና ኢትዮጵያ በተሰደደች ጊዜ በአሁኑ ጊዜ ደብረ ምጥማቅ ተብሎ በሚጠራው ቦታ ላይ ዐርፈው ነበር:: ጌታችንም ቦታውን ባርኮ የእርሷ መገለጫ እንዲሆን ቃል ኪዳን ገብቶላት ስለነበር ጊዜው በደረሰ ሰዓት ደብረ ምጥማቅ ተገድሞ የበርካታ መነኮሳት በዓት ሆነ:: በደብረ ምጥማቅም እመቤታችንም ቅድስት ድንግል ማርያም ብርሃን ተጎናጽፋና በሠራዊት መላእክት ታጅባ ተገልጣለች፤ በዚያን ጊዜም ሱራፌል ማዕጠንታቸውን ይዘው ሰገዱላት፤ እንዲህ እያሉም አመሰገኗት፤ ‹‹አብ በሰማይ አይቶ እንዳንቺ ያለ አላገኘም፤ ባንቺም ሰው ሆነ፡፡›› (መጽሐፈ ስንክሳር ግንቦት ፳፩ ገጽ. ፫፻፲፰)

ሰማዕታትም እንደየክብራቸው ማዕረግ ለእመቤታችን ድንግል ማርያም ሊሰግዱ ረቂቃን በሆኑ ፈረሶቻቸው ተቀምጠው ወደ እርሷ ቀረቡ፤ በመጀመሪያ ሊቀ ሰማዕታት ቅዱስ ጊዮርጊስ ከሁሉም ቀድሞ ከሰገደላት በኋላ ሌሎቹም በተመሳሳይ መልኩ ሰገዱላት፡፡ ከዚህም በኋላ ቅዱስ መርቆሬዮስ በዱሪ ፈረስ ተቀምጦ ወደ እርሷ በመምጣት ሰገደላት፡፡ ጻድቃን በአንድነት ቀርበው ለክብሯ ሰገዱላት፤ ቀጥሎም በንጉሥ ሄሮድስ በግፍ የተገደሉት ሕፃናት ለእርሷ ሰገዱ፤ በደስታና በፍቅርም ተጫወቱ፡፡ በዚያ የተሰበሰቡትም ክርስቲያኖች፣ እስላሞችና አረማውያን ይህን በአዩ ጊዜ ደስታ ሞልቶባቸው በተለየ ዓለም ያሉ ይመስላቸው ነበር፡፡ (መጽሐፈ ስንክሳር ግንቦት ፳፩ ገጽ. ፫፻፲፰)

አባ ጽጌ ድንግልም በደብረ ምጥማቅ በታላቅ ክብር ለምእመናን የታየችው የአምላክ እናት የድንግል ማርያምን መገለጥ በማኅሌተ ጽጌ ድርሰቱ እንዲህ በማለት ገልጾታል፤ ‹‹አመ ትበርቂ በደብረ ምጥማቅ ኀምሰ ዕለታተ፣ ትእምርተ ገጽኪ ይርአይ እስከ ይትነሣእ ዘሞተ፣ሚ መጠነ ማርያም ታሥተፌሥሒ ትፍሥሕተ፣ ኅድጊሰ ጽጌ ፍቅርኪ በጊዜ ንቃሁ መዓልተ፣ ብፁዕ ዘርእየኪ በሕልሙ ሌሊተ፤ የፊትሽን መልክ ያይ ዘንድ የሞተ ሰው እስኪነሣ ድረስ በደብረ ምጥማቅ ለአምስት ቀናት ያህል በተገለጽሽ ጊዜ ማርያም ምን ያህል ደስ ታሰኚ ኖሯል! በቀን የታየው የፍቅርሽ አበባ ይቅርና ሌሊት በሕልሙ ያየሽ ምስጉን ነው፡፡›› (ማኅሌተ ጽጌ)

በደብረ ምጥማቅ ከተሰበሰቡት ሕዝብ መካከል እናትና አባታቸው፣ ዘመዶቻቸው እንዲሁም ባልንጀሮቻቸው የሞቱባቸው ሰዎች ቅድስት ድንግል ማርያም እንድታሳያቸው በለመኗት ጊዜ እንደ ቀደመ መልካቸው አድርጋ ታሳያቸው ነበር፡፡ አንዳንዶች ደግሞ መሀረባቸውን ወደ ላይ በሚወረውሩት ጊዜ እርሷ የወደደቻቸው እንደሆነ በእጅዋ ተቀብላ መልሳ ትጥልላቸዋለች፤ ሁሉም ለበረከት ይካፈሉታል፡፡ እነርሱም ወደ ቤታቸውም ለመሄድ በሚፈልጉ ሰዓት ተሰናብተውና በተባርከውም ይሄዳሉ፡፡ (መጽሐፈ ስንክሳር ግንቦት ፳፩ ገጽ. ፫፻፲፱)

የደብረ ምጥማቅና የአካባቢዋ ሰዎች እመቤታችን ድንግል ማርያምን ያዩባቸው ቀናት አረማውያኑ ያመኑበት፣ የበደሉት በምልጃዋ ቸርነትን ምሕረትን ያገኙበት፣ ያመኑት ደግሞ የተባረኩበት ዕለታት ነበሩ፡፡ ሕዝቡ እርሷን ተመኝተው ያጡት ወይንም ጠይቀው ያልተፈጸመላቸው ምንም ነገር አልነበረም:: ነቢያት፣ ሐዋርያት፣ ጻድቃን፣ ሰማዕታት፣ ደናግል፣ መነኮሳት መላእክትና ሊቃነ መላእክትም ለድንግል ማርያም ሲሰግዱ ይታዩ ነበር::

ከዚህ በኋላ በዘመናት ይኖሩ የነበሩ ቅዱሳን የአምላክን እናት ለማየት ብዙዎች ተመኝተዋል፤ የመልክአ ማርያም ደራሲ ዓፄ ዘርዓ ያዕቆብ የአምላኩን እናት ቅድስት ድንግል ማርያምን ፊቷን ለማየት ሽቶ ‹‹ሰላም ለመልክእኪ ዘተሠርገወ አሜረ ዘያበርህ ወትረ ፍቅርትየ አንቲ እንተ ታበድሪ ፍቅረ አርእዪኒ ገጸ ዚኣኪ ማርያም ምዕረ ዘኢይሰምዖ ካልእ እንግርኪ ነገረ፤”
ዘወትር የሚያበራ ፀሐይን ጌጥ ላደረገ መልክሽ ሰላምታ ይገባል፤ ፍቅርን የምትመርጪ (የምታስቀድሚ) አንቺ የምወድሽ ማርያም ሌላ የማይሰማው ነገርን እነግርሽ ዘንድ አንድ ጊዜ ያንቺን ፊት ግለጪልኝ (አሳይኝ)›› በማለት ተማፅኗታል፡፡ (መልክአ ማርያም)

ነቢዩ ዳዊት ‹‹ወለገጽኪ ይትመሐለሉ ኲሎሙ አሕዛብ ብዑላነ ምድር፤ የምድር ባለጠጎች አሕዛብ ሁሉ በፊትሽ ይማለላሉ›› በማለት ትንቢትን እንደተናገረላት በርካት ቅዱሳን ሰዎች ቅድስት ድንግል ማርያምን ተገልጻላቸው ለማየት ተመኝተዋል፤ ልመናቸው ተሰምቶላቸው የአምላክ እናት ተገልጻላቸው ፊቷን ለማየትን ክብሯን ለመግለጥ ቅዱሳን አባቶች፣ ጻድቃን ሰማዕታት በቅተዋል፡፡ ይህም የሆነው በፍጹም ልቡናቸው በመማፀናቸውና በፍጹም ትጋት የጌታቸውን እናት ሲያገለግሉ በመኖራቸው እንደሆነ የጻድቃኑ ገድል ምስክር ነው፡፡ እነርሱም ሌት ከቀን ምኞታቸው ይሳካላቸው ዘንድ በጸሎት ይማፀኑ ነበር፡፡ (መዝ. ፵፬፥፲፪)

እመቤታችን ድንግል ማርያምም ጸሎታቸውን ሰምታ ያሰቡትን ትፈጽምላቸው ነበር፤ ምኞታቸው ከተሳካላቸው ቅዱሳን አባቶች መካከል አባ ይስሐቅ አንዱ ነው፤ ይህ ቅዱስ አባትም እመቤታችን ቅድስት ድንግል ማርያምን በፍጹም ልቡናው ይወዳት ስለነበር ለሰባት ዓመታት አምላኩን ክብርት እናቱን ያሳየው ዘንድ በጸሎቱ ተማጸነ፡፡ ዘወትር ከሠርክ ጸሎት በኋላ ሌሎች መነኮሳት ለመኝታ ወደ የበዓታቸው ሲሄዱ አባ ይስሐቅ ወደ ቤተ ክርስቲያን በመሄድ በቅድስት ድንግል ማርያም ሥዕሏ ፊት ቆሞ ሦስት መቶ ስግደትን እየሰገደ ይማፀን ነበር፡፡ ከስግደቱም ጋር ‹‹ኦ እግዚእየ ኢየሱስ ክርስቶስ አርእየኒ እመከ አሐተ ሰዓተ፤ ጌታዬ ኢየሱስ ክርስቶስ ሆይ ለአንዲት ሰዓት እናትህን አሳየኝ›› እያለ ይጸልይ ነበር፡፡ በእንደዚህም ሁኔታ ለሰባት ዓመት ከቈየ በኋላ እመቤታችን ቅድስት ድንግል ማርያም በታላቅ ግርማ ተገለጸችለት፤ የልቡም መሻት ምን እንደሆነ ጠየቀችው፤ አባ ይስሐቅም የርሷን ገጽ ያዩ ዐይኖቹ ሌላ ነገርን ማየት እንደማይሹ ነገራት፤ ከተወደደ ልጇ ኢየሱስ ክርስቶስ እንድታማልደውም ተማጸናት፡፡ ቅድስት ድንግል ማርያምም ልመናውን ተቀበለች፤ ከዚያም በኋላ የዕረፍቱ ቀን ከሦስት ቀን በኋላ መሆኑን አሳወቀችው፤ ባርካውም ወደ ሰማይም በክብር ዐረገች፤ ይህ ቅዱስ አባት ይስሐቅም እርሷን ካየ በሦስተኛው ቀን ዐረፈ፡፡ (መጽሐፈ ስንክሳር ታኀሣሥ ፳፩ ገጽ.፬፻፺፪)

እመቤታችን ቅድስት ድንግል ማርያም በደብረ ምጥማቅ ተገልጣ የሕዝቡን ምኞት እንደፈጸመችላቸው የእኛንም በጎ መሻት ትፈጽምልን፤ አሜን፡፡

© Mahibere Kidusan

Читать полностью…

የቃሊቲ ደብረ መድኃኒት መድኃኔዓለም ቤተክርስቲያን ፈለገዮርዳኖስ ሰ/ት/ቤት

ብፁዕ አቡነ ያሬድ የጠቅላይ ቤተ ክህነት ዋና ሥራ አስኪያጅና የአርሲ ሀገረ ስብከት ሊቀ ጳጳስ ከሚመሩት ሀገረ ስብከት በተጨማሪ የምሥራቅ ጎጃምን ሀገረ ስብከት ደርበው እንዲመሩ ቅዱስ ሲኖዶሱ በዛሬው ዕለት ውሳኔ አሳልፏል።

Читать полностью…

የቃሊቲ ደብረ መድኃኒት መድኃኔዓለም ቤተክርስቲያን ፈለገዮርዳኖስ ሰ/ት/ቤት

በምስካበ ቅዱሳን ቆጋ ቅ/ኪዳነ ምሕረት አንድነት ገዳም የተፈጸመውን የዶግማ እና ቀኖና ጥሰት ቅዱስ ሲኖዶስ በሰፊው ከተወያየበት በኋላ ሕገ ወጥ በመሆኑ ውሳኔ አሳልፎበታል፡፡ ዝርዝሩ በማጠቃለያ መግለጫው የሚገለጽ ይሆናል፡፡
••••
በምስራቅ ጎጃም ሀገረ ስብከት የክፍሉ ሊቀ ጳጳስ የነበሩት ብፁዕ አቡነ ማርቆስ ወደ መንበረ ፓትርያርክ ጠቅላይ ቤተክህነት ስብከተ ወንጌል እና ሐዋርያዊ ተልዕኮ መምሪያ የበላይ ኃላፊ ሊቀ ጳጳስ እና የጎፋ ደብረ ብሥራት ቅዱስ ገብርኤል ካቴድራል የበላይ ኃላፊ ሊቀ ጳጳስ ሆነው እንዲያገለግሉ ዝውውር አድርጓል፡፡
••••
የምሥራቅ ጎጃም ሀገረ ስብከትን በተመለከተ ብፁዕ አቡነ ያሬድ የመንበረ ፓትርያርክ ጠቅላይ ጽ/ቤት ዋና ሥራ አስኪያጅ አርሲ ሀገረ ስብከት የሰበካ ጉባዔ ማደራጃ ሊቀ ጳጳስ በሊቀ ጳጳስነት እንዲመሩት ተወስኗል፡፡
••••
በሰዋሰወ ብርሃን ቅዱስ ጳውሎስ መንፈሳዊ ኮሌጅ እና በደብሩ መካከል ያለውን አለመግባባት በሰፊው ተመልክቶ ቅዱስ ሲኖዶስ የመፍትሔ ውሳኔ አሳልፏል፡፡
••••
በአዲስ አበባ ሀገረ ስብከት ላይ የሚቀርበውን የመልካም አስተዳደር ችግር ቅሬታ በሰፊው የተመለከተው ቅዱስ ሲኖዶስ የቀረበው የመልካም አስተዳደር ችግር እርምት እንዲደረግበት ሲል ለሀገረ ሰብከቱ ማሳሰቢያ ሰጥቷል፡፡ ዝርዝሩ በማጠቃለያ መግለጫው ይቀርባል።
••••
በሀገራችን በተለያዩ ጊዜያት እደረሱ ያሉ ችግሮችን አስመልክቶ ሦስት ብፁአን አበው ሊቃነ ጳጳሳት ለቅዱስ ሲኖዶስ መግለጫ አዘጋጅተው እንዲያቀርቡ መርጧል፡፡
••••
በመላው ሀገሪቱ እና በዓለም አቀፍ ደረጃ ባሉት ኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ አብያተ ክርስቲያናት እና ገዳማት በሙሉ ስለ ሀገራችን ሰላም ጸሎተ ምኅላ እንዲደረግ ቅዱስ ሲኖዶስ ወስኗል፡፡
••••
ቅዱስ ሲኖዶስ በቀረቡት አጀንዳዎች ላይ ነገ የማጠቃለያ ውይይት እና ቃለ ጉባዔ ማጽደቅ ካከናወነ በኋላ ሰኞ ግንቦት 23 ቀን 2013 ዓ.ም መግለጫ ይሰጣል፡፡
••••
EOTC TV
••••
📱📲 #ኦርቶዶክሳዊ ሚዲያን #JOIN እንዲሁም #ሼር በማድረግ #ለኦርቶዶክሳውያን #መልዕክቱን እናድርስ።
━━━━⊱✿⊰━━━━
ይ🀄️ላ🀄️ሉን
❤️ የአማኑኤል ልጆች ቴሌግራም ቻናላችን ሊንክ፦
👉 /channel/Terbinos
❤️ የአማኑኤል ልጆች የፌስቡኩ ገፃችን ሊንክ፦
👉 https://www.fb.me/terbinos

Читать полностью…

የቃሊቲ ደብረ መድኃኒት መድኃኔዓለም ቤተክርስቲያን ፈለገዮርዳኖስ ሰ/ት/ቤት

https://go2ere.com/NGJldGVu

Читать полностью…

የቃሊቲ ደብረ መድኃኒት መድኃኔዓለም ቤተክርስቲያን ፈለገዮርዳኖስ ሰ/ት/ቤት

ፉክክሩ Digitized ሆኗል
መስቀል አደባባይን ጎግል ማፕ ላይ እየገቡ ኢድ አደባባይ እያሉ ኢዲት እያደረጉት ነው። ይህ ደግሞ የአንድ ሰው ኢዲት ብቻ ሳይሆን ሙስሊሞች እየተረባረቡ ኢዲት እያደረጉ ስለሆነ ጎግል መስቀል አደባባይን ''መስቀል አደባባይ ወይም ኢድ አደባባይ ብሎ ቀይሮታል።
ኦርቶዶክሳወያን መበሳጨት አያስፈልግም ነገሩ ቀላል ነው ሁላችንም እንረባረብና ኢዲት ያደረጉትን እኛም ኢዲት አድርገን ''ወይም ኢድ አደባባይ'' የሚለውን እናጥፋው። እንዲያውም ''Land mark'' የሚለው ላይ ባለቤቱ ኦርቶዶክስ ቤተክርስቲያን ስለሆነች ''Orthodox church'' የሚል እንጨምርበታለን።
በቀላሉ አሻራዎን ያሳርፉ ከቤ/ክ ጎን ይቁሙ ። ይህንን ለማድረግ ስልኮት ላይ ጎግል ማፕ (Google map) ይክፈቱ እና ደረጃ በደረጃ ያዘጋጀሁትን አጭር የ Screen shoot instruction ይመልከቱ።
N.B ይህንን ለማድረግ የGmail account (email) login info ከጠየቀዎ User name እና password ያስገቡ
ከዛም:
1. Google Map Application ይክፈቱ
2. Search Bar ላይ ሄደውMeskel square ብለው ይጻፉ
እና Meskele Square, Addis Ababaን ይምረጡ
3. ቀዩን የ ፒን(📌) ምልክት ይጫኑ
4. ከመጡት አማራጮች ውስጥ Sugest Edit የሚለውን ይምረጡ
5. Change Name or other details ይጫኑ
6. Meskel Square ከሚለው በታች በአማረኛ የተጻፈውን
''መስቀል አደባባይ ወይም ኢድ አደባባይ'' የሚለውን ይንኩ እና ''ወይም ኢድ አደባባይ የሚለውን'' ያጥፉ እና መስቀል አደባባይን የሚለውን ብቻ ያስቀሩ
7. Historical Land mark ላይ የሚለው ላይ ይግቡ (ባለቤቱ የኦርቶዶክስ ቤ/ክ ስለሆነች)
8. ከአማራጮች ውስጥ Religion የሚለውን ይንኩ
9. ''search more category'' የሚለው መፈለጊያ ባር ላይ Orthodox church የሚል ይጻፉ እና Orthodox church የሚለውን አማራጭ ይጫኑ
10. መጨረሻ ላይ ዝርዝሩ ቼክ ያድርጉ
ከላይ በእንግሊዘኛ : Meskel Square
በአማረኛ : መስቀል አደባባይ
Category : Orthodox church
ከዛም ከአናቱ ላይ ያለችውን የቀስት(የ telegram ወይም Send ምልክት) የምትመስለውን ይጫኑ። እርማትዎ ለጎግል ይደርሰዋል።

ጎግል የእርማቱን (Edit) ብዛታ ተመልክቶ ''ወይም ኢድ አደባባይ የሚለውን ከቀናት በኋላ ያጠፋዋል።

እርሶ ወደነበረበት ''መስቀል አደባባይ'' አርመው (Edit) አድረገው መመለስዎ የቤ/ክ ክብርን መመለስዎ እንደሆነ አይርሱ። ሲጨርሱ ይሄንን ፖስት ለኦርቶዶክሳውያን ያጋሩ!

#መስቀል_አደባባይ

Читать полностью…

የቃሊቲ ደብረ መድኃኒት መድኃኔዓለም ቤተክርስቲያን ፈለገዮርዳኖስ ሰ/ት/ቤት

በትዳር ውስጥ መጋጨት ብቻውን የመጠላላት ምልክት እንዳልሆነ ሁሉ፣

አለመጋጨት ብቻውንም ግን የፍቅር ምልክት አይደለም

@Binisiwe
@Binisiwe
@Binisiwe

ለአሰተያየት @BiniGirmachew_Bot

Читать полностью…

የቃሊቲ ደብረ መድኃኒት መድኃኔዓለም ቤተክርስቲያን ፈለገዮርዳኖስ ሰ/ት/ቤት

መልካም አስብ መልካም ተናገር፦

በመጀመሪያ ሰው ያስተሳሰቡ ውጤት መሆኑን እመን፤

አሁን የምንኖረው ህይወት ያመለካከታችን እና ያስተሳሰባቸን ውጤት ነው።

ይህን ካወቅክ አስተሳሰብህን በጥንቃቄ አጢነው።

ደስተኛ ለመሆን የተመረጠ አስተሳሰብ ሊኖርህ ይገባል።

@Binisiwe
@Binisiwe
@Binisiwe

ለአሰተያየት @BiniGirmachew_Bot

Читать полностью…

የቃሊቲ ደብረ መድኃኒት መድኃኔዓለም ቤተክርስቲያን ፈለገዮርዳኖስ ሰ/ት/ቤት

የሰዎችን ያለማወቅ አግዝ ፤ ዕውቀትህ ባላወቁት ላይ እንድትኮራና እንድትፈርድ

አያድርግህ የአዋቂ ኩሩ ቁጥሩ ካላዋቂዎች

ነውና ማወቅ ባለዕዳነት እንዳይሆን አላዋቂዎችን እርዳቸው ።

@Binisiwe
@Binisiwe
@Binisiwe

ለአሰተያየት @BiniGirmachew_Bot

Читать полностью…

የቃሊቲ ደብረ መድኃኒት መድኃኔዓለም ቤተክርስቲያን ፈለገዮርዳኖስ ሰ/ት/ቤት

ቆንጆዎች ቁንጅናቸው ሁሉን የሚተካ እየመሰላቸው ከዕውቀትና ከትሕትና ይርቃሉ ።

ሁሉንም ሰው በመልካቸው የሚማርኩት ስለሚመስላቸው ኩሩና ተንኮለኞች ይሆናሉ ።

አንተ ግን ቆንጆ ወዳጅን እንጂ ቆንጆ ቁመናን አትሻ ፤ ቆንጆ ትዳርን እንጂ ቆንጆ ሴትን አትመኝ ፤ የላይ ነገር ከንቱና ኀላፊ ነውና በሚፈርስ አካል ፣ ኑሮ በሚለውጠው መልክ አትደለል ።

@Binisiwe
@Binisiwe
@Binisiwe

ለአሰተያየት @BiniGirmachew_Bot

Читать полностью…

የቃሊቲ ደብረ መድኃኒት መድኃኔዓለም ቤተክርስቲያን ፈለገዮርዳኖስ ሰ/ት/ቤት

የዛሬ ግንቦት ፲፰ ቀን ፳፻፲፫ ዓ.ም የቅዱስ ሲኖዶስ ውሎ
በመ/ር ቀሲስ መዝገቡ ጌታቸው
(ኢኦተቤ ቴቪ ግንቦት ፲፰ ቀን ፳፻፲፫ ዓ.ም )
የቅዱስ ሲኖዶስ ዋና ጸሐፊ እና የሲዳማ ጌዲኦ እና ቡርጂ አህጉረ ስብከት ሊቀ ጳጳስ ብፁዕ አቡነ ዮሴፍ የቅዱስ ሲኖዶስ ውሎን አስመልክተው አጭር መግለጫ ሰጥተዋል። በመግለጫቸውም ቅዱስ ሲኖዶስ በትላንትናው ዕለት በጸሎት የጀመረው የግንቦት ርክበ ካህናት ስብሰባ በብፁዕ ወቅዱስ አቡነ ማትያስ ፓትርያርክ ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሣት ዘኢትዮጵያ ሊቀጳጳስ ዘአክሱም ወእጨጌ ዘመንበረ ተክለሃይማኖት ንግግር ተከፍቷል። በዚያም ከብፁአን አበው ሊቃነ ጳጳሳት መካከል በተሰየመ አጀንዳ አርቃቂ ኮሚቴ አማካኝነት ቋሚ ሲኖዶስ ለውሳኔ የተቸገረባቸውን ጉዳዮች ጨምሮ ወቅታዊ ሀገራዊ ጉዳዮችን ያካተተ ፯ አጀንዳ በማጽደቅ ወደ ውይይት እና ውሳኔ ገብቷል። በዚህም መሠረት በ፪ አጀንዳዎች ላይ ውሣኔ የተሰጠ ሲሆን ቃለ ጉባኤው ተፈርሞ እንደተጠናቀቀ ውሳኔው ይፋ ይሆናል። ጉባኤው በመንፈስ ቅዱስ መሪነት በብፁዕ ወቅዱስ አቡነ ማትያስ ርዕሰ መንበርነት ውይይቱን ይቀጥላል።

የዜናው ምንጭ
© EOTC TV



/channel/KeAbawandebet

Читать полностью…

የቃሊቲ ደብረ መድኃኒት መድኃኔዓለም ቤተክርስቲያን ፈለገዮርዳኖስ ሰ/ት/ቤት

Google ላይ የቦታውን ስም ወደ ነበረበት ለመመለስ የሚከተለውን እናድርግ:-

👉1. Google ላይ login አድርገን Google Maps ላይ በመሄድ meskel square ብለን search ማድረግ። ከዚያም በ Map ላይ መስቀል አደባባይ/ ኢድ አደባባይ ብሎ የሚያሳየንን click ማድረግ
👉2. ከሚመጣልን ምርጫ ውስጥ suggest an edit የሚለውን መንካት
👉3. ቀጥሎ ከሚመጣልን ምርጫ ውስጥ change name or other details የሚለውን መጫን
👉4. የሚመጣልን edit ገጽ ላይ የቦታውን ስም ወደ መስቀል አደባባይ ብቻ ማስተካከል
👉5. በቀኝ ጥግ ላይ የምትገኘዋን send ምልክት መጫን።

ማሳሰቢያ:- ብዙ ሰው edit እስኪያደርገው ድረስ አይቀየርም!

Читать полностью…

የቃሊቲ ደብረ መድኃኒት መድኃኔዓለም ቤተክርስቲያን ፈለገዮርዳኖስ ሰ/ት/ቤት

💐🥀💐🥀💐🥀💐🥀💐🥀💐🥀💐🥀💐🥀💐🥀💐🥀💐🥀💐🥀💐
የአዲስ አበባ ሰንበት ት/ቤቶች አንድነት ሥራ አመራር በሀገረ ስብከቱ ከሚገኙ ከ200 በላይ ከሚደርሱ ሰንበት ት/ቤቶች የሥራ አመራር አባላት ጋር በወቅታዊ ጉዳዮች ዙሪያ ውይይት አደረገ!!!
💐🥀💐🥀💐🥀💐🥀💐🥀💐🥀💐🥀💐🥀💐🥀💐🥀💐🥀💐🥀💐

ግንቦት 15/2013 ዓ.ም በሀገረ ስብከቱ ከሚገኙ 200 በላይ ሰንበት ት/ቤቶች የሥራ አመራር አባላት ጋር በተደረገው ግማሽ ቀን የፈጀ ውይይት በሁለት ወቅታዊ አጀንዳዎች ዙሪያ በጥልቀት ፥ በሰፊው ፥ ኃላፊነት በተሞላበት መልኩ ... ውይይት የተደረገ ሲሆን ፦

#በእጀንዳ_አንድ ላይ የጃንሆይ (ጃን) ሜዳን እና የመስቀል አደባባይን ጉዳይ የተመለከተ ጥልቅ ውይይት የተደረገ ሲሆን የጃንሆይ (ጃን) ሜዳን ጉዳይ ሀገረ ስብከቱ ከሚመለከታቸው ጋር አበክሮ በመወያየት ጉዳዩ የመጨረሻ መፍትሔ እንዲያገኝ እንዲያደርግ ። ቅዱስ ሲኖዶስም አቋም እንዲይዝበት እንዲጠየቅ ። እንዲሁም በዚሁ እጀንዳ ላይ ወቅታዊው በሀገረ ስብከቱ ምዕመናን በእጅጉ ያሳዘነው የተፈጸመውን ስህተት እና መዋቅራዊ ጥሰት በተመለከተ ጉባዔው የእርምት የመፍትሄ ሐሳቦች አቅጣጫ ያስቀመጠ ሲሆን በተሰጠው አቅጣጫ መሰረት ሀገረ ስብከቱ አስቸኳይ የእርምት ምላሽ እንዲሰጥበት ተጠይቋል:: ይህ የማይፈፀም ከሆነ ግን ጉዳዩን ለቅዱስ ሲኖዶስ በማቅረብ መፍትሔ እንዲወስድበት በቤተ ክርስቲያን ልጅነት መንፈስ አቅጣጫ ተይዟል፡፡

#በእጃንዳ_ሁለት ላይ ብፁዕ ወቅዱስ አቡነ ማትያስ ቀዳማዊ ፓትርያርክ ርእሰ ሊቃነ ጳጳሳት ዘኢትዮጵያ ሊቀ ጳጳስ ዘአክሱም ወእጨጌ ዘመንበረ ተክለ ሃይማኖት ን በተመለከተ እየወጡ ያሉ መረጃዎች ላይ ውይይት ተደርጎል:: ለውይይት በር የከፈተውን ሐሳብ ወደ ጎን ትተን በምንም መልኩ የቤተክርስቲያኒቷን ቀኖናዊ ሥርዓት ለመናድ እየተወራ ያለውን በእንደራሴ ጉዳይ የሚናፈሰውን መረጃ በፍፁም አንቀበልም ፤ ቤተክርስቲያኒቷን እና አባቶችን እንደቀደመው ጊዜ ለመከፋፈል የሚሠራውን ሂደት እንቃወማለን ፤ መንፈስ ቅዱስ እና ቅዱስ ሲኖዶስ የመረጣቸውን ቅዱስ ፓትርያርክ ማንም ከመንበራቸው እንዲነካብን አንፈቅድም ፤ ቅዱሳን አባቶቻችንን ሳይገባ ሰድቦ ለሰዳቢ የሚያጋልጣቸውን ሁሉ በእጅጉ እናወግዛለን ፤ ሰሞኑን በተለያዩ ሚዲያዎች የቅዱስ አባታችንን የክብር ስም በንቀት በማሳጠር እና ባልተገባ መልኩ ለማቅለል እየተሠራ ያለውን ሂደት በፍጹም አንቀበልም ይህን ያደረጉ ሁሉ ክብርት ቤተክርስቲያኒቷን ፥ ቅዱስ አባታችንን እና ምዕመኑን ሁሉ በይፋ ይቅርታ ሊጠይቁ ይገባል ፤ ብፁዓን አባቶቻችንም እንደ አንድ ልብ መካሪ እንደ አንድ ቃል ተናጋሪ ሆነው የቤተክርስቲያንን ክብር እና መብት ፥ ... ለማስጠበቅ ከምንጊዜውም በላይ በቁርጠኝነት በአንድነት እንዲሰሩ በልጅነት መንፈስ የውይይቱ ተሳታፊዎች ጠይቀዋል... በዚህም የመጨረሻ የመፍትሔ ሐሳብ በማስቀመጥ ፤ በቀጣይም አጥቢያ ድረስ የሚደርስ ሰፊ እንቅስቃሴ ለማድረግ ስምምነት ላይ ተደርሷል ::

ማስታወሻ 👉 በውይይቱ ላይ የተወሰኑ ውሳኔዎችን የአንድነቱ ሥራ አመራር በተዋረድ ለቅዱስ ሲኖዶስ ፤ ለሀገረ ስብከቱ ፤ ለምዕመናን እንዲሁም ለሚመለከታቸው ሁሉ በደብዳቤ እና በመግለጫ በቀጣይ የሚያደርስ ይሆናል ::

ግንቦት 15/2013 ዓ.ም
የአዲስ አበባ ሰንበት ት/ቤቶች አንድነት
💐🥀💐🥀💐🥀💐🥀💐🥀💐🥀💐🥀💐🥀💐🥀💐🥀💐🥀💐🥀💐

Читать полностью…

የቃሊቲ ደብረ መድኃኒት መድኃኔዓለም ቤተክርስቲያን ፈለገዮርዳኖስ ሰ/ት/ቤት

‼️ አዋጅ አዋጅ አዋጅ ‼️

•✥ ለ1 ሳምንት ግዴታ ሁሉም ኦርቶዶክስ ነኝ የሚል ካለ ከላይ የላክነው የቅዱስ አባታችን ብፁዕ ወቅዱስ አቡነ ማትያስ ቀዳማዊ ፓትርያርክ ርዕሰ ሊቀነ ጳጳሳት ዘኢትዮጵያ ሊቀ ጳጳስ ዘአክሱም ወእጨጌ ዘመንበረ ተክለሃይማኖት ፎቶ ኃሙስ(5/9/13) ከ1 ሰዓት እስከ ዕረቡ (11/9/13) ድረስ ፕሮፋይል ፒክቸር በማድረግ በአባታችን ላይ እየደረሰ ያለው ጫና እና ተቃውሞ በመንቀፍ ከአባታችን ጎን መሆናችንን ለአባታችን ያለንን ክብርና በኦርቶዶክስ ተዋህዶ እየደረሰ ያለውን ጫና እንቃወም


"በመልክታቸው ላትስማማ ትችላለህ...ክብረ ፕትርክናቸውን ማክበር ውዴታ ሳይሆን መንፈሳዊ ግዴታችን ነው!!!።"

•✥ ሁሉም ኦርቶዶክስ እንዲያደርግና አሕዛብና ከሀዲዎችን ማስገረም አለብን። የሚያስገርመው ነገር ምንድን ነው ካላቹ ሁላችን በተመሳሳይ ሰዓትና ቀን PROFILE PICTURE ማረጋችን ነው። ኦርቶዶክሶች ሲነኩን እንደ ምድር አሸዋ እንደምንበዛ ማሳያም ነው። ነገ 1 ሰዓት ሁሉም ኦርቶዶክስ profile picture በማድረግ ግዴታውን ይወጣ
መልዕክቱን በማስተላለፍ የበኩሉዎን ይወጡ። ለ20 የኦርቶዶክስ ቤተሰብ ፎርዋርድ / SHARE እናድርግ ‼️

•✥ ብፁዕ ወቅዱስ አቡነ ማትያስ ቀዳማዊ ፓትርያርክ ርእሰ ሊቃነ ጳጳሳት ዘኢትዮጵያ ሊቀ ጳጳስ ዘአክሱም ወእጨጌ ዘመንበረ ተክለሃይማኖት ቡራኬዎ ይድረሰን አሜን !

━━━━━━━━━━━━━━━━━━━
ቢያንስ ለ 20 ኦርቶዶክሳውያን SHARE በማድረግ ለሁሉም እናዳርስ ‼️ በየግሩፑ በሁሉም ቦታ ያዳርሱት ‼️

━━━━━━━━━━━━━━━━━━━
💚 •✥• @Z_TEWODROS •✥•💚
💛 •✥• @Z_TEWODROS •✥•💛
❤️ •✥• @Z_TEWODROS •✥•❤

Читать полностью…

የቃሊቲ ደብረ መድኃኒት መድኃኔዓለም ቤተክርስቲያን ፈለገዮርዳኖስ ሰ/ት/ቤት

ለሰንበት ት/ቤታችን አባላት በሙሉ እንደሚታወቀው በመጪው እሁድ ሚያዚያ 10 ጠዋት ከቅዳሴ በኃላ የሰበካ ጉባኤ ምርጫ ስላለ ለቤተክርስቲያናችን የሚበጃትን ሰው በመምረጥ ባለፉት 3ዓመት ቤተክርስቲያናችን ከገባችበት ረመጥ እናውጣት ስንል ጥሪያችንን እናስተላልፋለን።ስንመርጥ የተጀመረውን ህንፃ ቤ/ክ የሚያስጨርስልንን እንጂ ቤ/ክቲያኒቱን የሚቦጠቡጥ እንዳይሆን ልንጠነቀቅ ይገባል።

Читать полностью…
Subscribe to a channel