የልደት መፅሀፍ ስጦታ ለሰንበት ትምህርት ቤታችን መስጠት የምትፈልጉ ከእነዚህ መፃህፍት መሀል ለቤተመፃህፍት አስተዋጽኦ ታደርጉ ዘንድ በልዑል እግዚአብሔር ስም እንጠይቃለን።
Читать полностью…እነሆ ሰብዓሰገል ለህፃኑ እጅ መንሻ ወርቅ÷እጣንና ከርቤን ሰጡት የጌታችን የመድኃኒታችን የኢየሱስ ክርስቶስን የልደት በዓል ስጦታ ለህፃናቱ መማሪያ ክፍል ምን ሊሰጡን አስበዋል? ኑ አብረን ከመድኃኔዓለም ልደት በፊት የዚያች የከብቶች በረት ምሳሌ የሆነችውን መማሪያ ክፍል ለፍፃሜ እናብቃ።
ሰንበት ትምህርት ቤቷን በገንዘብ ለማገዝ የምትፈልጉ
የኢ/ያ ንግድ ባንክ 1000639913663 screen shoot በtelegram በ0923079151ስልክ ይላኩልን።
ለበለጠ መረጃ
ሠለሞን 0923079151
ፀጋዬ +251911719353
ኤፍሬም +251920191954
የሰንበት ትምህርት ቤቷ ህንፃ አሰሪ ኮሚቴ
የሰርቲ ደብረ መድኃኒት መድኃኔዓለም ቤተክርስቲያን ፈለገዮርዳኖስ ሰንበት ትምህርት ቤት 3 የመማሪያ ክፍሎችን ገንብቶ በማጠናቀቅ ላይ ሲገኝ አሁን ግን በገንዘብ እጥረት በርና መስኮት ሳንገጥም ቆመናል ስለሆነም ስራችንን ለፍፃሜ ለማብቃት ሲሚንቶ መግዣ ገንዘብ ስለሚያስፈልገን ፈጣሪ የፈቀደላችሁ የበኩላችሁን ትረዱን ዘንድ እንማፀናለን።
Читать полностью…በስመአብ ወወልድ ወመንፈስቅዱስ አሐዱ አምላክ አሜን ።
🔔🔔ማሳሰቢያ 🔔🔔
በ2017ዓ.ም በሰንበት ትምህርት ቤታችን ከሚተገበሩ ተግባር መካከል አንዱ ወርሀዊ ክፍያ ነው ሆኖሞ እየከፈሉ የሚገኙ አባላት ቁጥር በጣም ጥቂት ሲሆን እንድትከፍሉ ስንል እናሳስባለን
የመክፈያ መንገዶች :-
1. ዘወትር እሁድ እሁድ ከ 2:30- 3:30 በሒሳብ ክፍል ቢሮ
2. በሰንበት ትምህርት ቤቷ አኮውንት ቁጥርየ 4960413803933013 በመክፈል የከፈላችሁበትን ደረሰኝ screenshot በማንስት @eyob1005 ይላኩልን
ከሒሳብ ክፍል
ለሰንበት ትምህርት ቤታችን መምህራን በሙሉ የፊታችን እሁድ ታህሳስ 13/2017 ሰንበት ትምህርት ቤታችን መንፈሳዊ ጉዞ ወደ አቡነ እጨጌዮሀንስ ገዳም ጉዞ የሚኬድበት ስለሆነ ከህፃናት እስከ ወጣንያን ክፍል ምንም ዓይነት መርሃግብር የማይኖር መሆኑን እንገልፃለን።
Читать полностью…በአታ ለማርያም
እመቤታችን ማርያም የኢያቄምና የሀና በእርጅና ዘመናቸው ያገኟት የብጽአት(የስለት) ልጅናት
ከእለታት አንቀን እመቤታችን ከሀና ከእናቷ እቅፍ ወርዳ ጠፋች ሀናም በብዙፍለጋ አገኘቻት ። ቅድስት ሀናው ኢያቄምን ይህች ብላቴና ሆዷ ዘመድ ሳይወድ አፏ እህል ሳይለምድ ወስደን ከቤተ መቅደስ እንስጣት አንዳች ብትሆንብን ከልጃችንም ከእግዚአብሔርም ሳንሆን እንቀራለን አለችው እርሱም ፍቅርሽ ይለቅልሽ ብዬ ነው እንጂ የኔማ ፈቃዴነው አላትናወዲያው ወደ ብተመቅደስ ወሰዷት ሊቀካህናቱ ዘካርያስም የምግቧን ነገር እንዴት አደርጋለሁ ብሎ መጥቅዕ (ደወል) መቶ ህዝቡን ሰበሰበ ህዝቡም የምግቧን ነገር እንዴት እንዲያደርጉ ሲጨነቁ መልዐኩ ቅዱስ ፋኑኤል ኅብስት ሰማያዊ ጽዋዕ ሰማያዊ ይዞ ረቦ ታየ።
ዘካርያስ ከዚህ በፊት በስውር ይቀበል ነበርና ለእኔ የመጣ ነው ብሎ ቀረብ አለ መልዐኩም ወደላይ ረቀበት የእግዚአብሔር ነገር አይታወቅም ምናልባት ለዝች ብላቴና የመጣ ይሆናል ብለው ለብቻዋ አድርገውዋት ፈቀቅ አሉ ድንኩል ድንኩል እያለች ሐናን ስትከተል መልዐኩ ፈጥኖ ወርዶ አንድ ክንፉን አንጥፎ አንድ ክንዱን ጋርዶ በሰው ቁመት ልክ ከምድር አስለቅቆ መግቧት እመቤቴሆይ ረኀብ በአስመታሁሽ ይቅር በዪኝ ብሏት ወደሰማይ ዐረገ ዘካርያስም የምግቧ ነገር ከተያዘልንማ ብሎ ከቤተ መቅደስስ አስገብቷታል ።
እመቤታችን ቅድስት ድንግል ማርያምወደ ሁላችን ቤት በረድኤት ትግባ የእመቤታችን ልመናዋ ክብሯ የልጇም ቸርነት በሁላችንምላይ ይደር።
ለሰንበት ትምህርት ቤታችን አባላት በሙሉ የአቡነእጨጌ ዮሀንስ ጉዞ ወደ ታህሳስ 13 ስለተሸጋገረ የፊታችን እሁድ ከቤተክርስቲያን ጉባኤ በኃላ መደበኛው የትምህርት እና የዝማሬ መርሃግብር ስለሚኖር መማርያ መሳሪያ እንድትይዙ ስንል ጥሪያችንን እናስተላልፋለን።
ሰንበት ት/ቤቱ
ከእሁድ እስከ እሁድ በጉልበት ደከመኝ ሰለቸኝ ሳትሉ ስታግዙን የነበራችሁ ዛሬ በመርሀ ግብር መጣበብ ምክንያት በደንብ ያላመሠገናችሁ ከታች ያላችሁና ሌሎች በጉልበት የምታግዙን ፈጣሪ ይስጥልን እያልን የተለመደው ትብብራችሁን እንዳይለየን እያልን ነገ ሰኞና እሮብ ከ10:00 ጀምሮ ኮረት ስለምናስገባና ማክሰኞ የአናፂ ስራ ስላለ እንድትገኙልን።
1. አዛዥ ጠበቃው
2. ምስጋናው ሞላ
3. ናሆም ተሻለ
4. ዲ/ን ታደሰ ክፍሌ
5. ብሩክ ስንታየሁ
6.ምንተስኖት ሙሉ
7.ተመስገን ተስፋዬ
8.ዳኛቸው አሰፋ
9. ታሪኩ ተሾመ
10.መንበሩ በላይ
11. ሚኪያስ አብዮት
12. ሳሙኤል ተስፋዬ
13. ናትናኤል ተስፋዬ
14. ዲ/ን የአብፀጋ
ሲሆኑ ስለምታደርጉልን ትብብር በልዑል እግዚአብሔር ስም እናመሰግናለን።
የህንፃ አሰሪ ኮሚቴ ሰብሳቢ
ሁሩ ወመሐሩ ....
ጌታችን መድኃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ከሀዋርያት ተለይቶ በሚያርግ ጊዜ ከነገራቸው ትዕዛዛት አንዱ ሂዱና አህዛብን በአብ በወልድ በመንፈስ ቅዱስ ስም እያጠመቃችኋቸው ደቀ መዛሙርቴ አድርጎቸው የሚል ነው።ሐዋርያትም ይህንን ቃል ተቀብለው ደረቅ የሆነውን የሰዎችን ልቦና በወንጌል ቃል አረስርሰዋል፤አልጫ የሆነውንም ዓለም በወንጌል ጨውነት አጣፍጠዋል ።ከሐዋርያት ቀጥለውም ሐዋርያነ አበው፣ ከዚያም ሰማዕታት ፣ቀጥለውም ሊቃውንት ፣እንዲሁም መነኮሳት ይህንን የእግዚአብሔር ቃል ተቀብለው ወንጌልን ለዓለም አድርሰዋል ።
ሰንበት ትምህርት ቤታችን ፈለገ ዮርዳኖስንም የአምላካችንን ቃል በመቀበል ፡በሐዋርያት አስተምሮ፣በሰማዕታት ተጋድሎ ፣በመነኮሳት ኑሮ ፣በሊቃውንት ትርጓሜ መሰረት ላይ ተመስርታ እግዚአብሔር በፈቀደላት መጠን የወንጌል ቃል ስታስተምር ቆይታለች(አሁንም በማስተማር ላይ ትገኛለች )።በዚህም ብዙ ደቀ መዛሙርትን ለእግዚአብሔር አገልጋይ እንዲሆኑ ከዓለም ሐሳብ ለይታ ንጹሕ መስዋዕት አድርጋ አቅርባለች ።ብዙ ሰዎችንም ከወንጀል ሰሪነት ወደ ወንጌል አገልግሎት መልሳለች።ይህንን ሐዋርያዊ አገልግሎት ደግሞ ከጀመረች እነሆ 20 ዓመቷን ዛሬ ህዳር 21 እና ነገ ህዳር 22 በደማቅ ሁኔታ ታከብራለች ።በመሆኑም ሁላችንም ህዝበ ክርስቲያናት በመርሐ ግብሩ ላይ በመገኘት የመርሐ ግብሩ ተሳታፊ ይሆኑ ዘንድ በአክብሮት ተጠርተዋል ።
አናፂዎቻችን ትጥቃቸውን አሟልተው ለጣሪያ ስራ ዝግጁ ሆነዋል። ለፍፃሜው የበረከት ስራ መድኃኔዓለም የፈቀደላችሁ ተገኝቶ የበረከቱ ተሳታፊ መሆን ይቻላል።
Читать полностью…20 አመትሽ ነው?
በ20 ዓመት የሕይወት ጉዞ ውስጥ ብዙ ክረምት አልፎ ብዙ በጋ መጥቷል፣ህጻን ሆነው የተወለዱት ለወጣትነት በቅተዋል ፣ወጣት የሆኑት ጎልምሰዋል፣የጎለመሱት ደግሞ አርጅተዋል ።በ20 ዓመት ውስጥ ብዙ ሰዎች ተወልደው ብዙ ሰዎች ሞተዋል ፣ በዚህች 20 ዓመት ውስጥ ቅናሽ የነበረው ኑሮ አሁን ደግሞ ተወዷል የአንድ ብር ከሀምሳ ምግብ መቶ ሀምሳ ብር ገብቷል ፣ብዙ መንግስታት መጥተው ብዙ መንግስታት አልፈዋል ፣ ብዙ አስተዳዳሪዎች መጥተው አስተዳድረው ሄደዋል።በዚህች 20 ዓመት ውስጥ ነው ታዲያ ከብዙ የህይወት ክንውኖች ውስጥ ፈለገ ዮርዳኖስ ሰንበት ትምህርት ቤት የምትባል እናት የፈለቀችው ።
ሰንበት ትምህርት ቤታችን ፈለገ ዮርዳኖስ የዛሬ 20 ዓመት ነበር በመድኃኔዓለም ፈቃድ፣በወንድሞች እና እህቶች መልካምና በጎ ተነሳሽነት የተወለደችው ።በዮሐንስ መወለድ ለብዙዎች ደስታ እንደሆነ ሁሉ በሰንበት ትምህርት ቤታችንም መወለድ ለብዙዎቻችን ደስታን ሰጥቷናል።በዚህች እናት በሆነች ሰንበት ትምህርት ቤት ውስጥ ነው ታዲያ ህጻናት ሆነን ገብተን ትልቅ ሆነን የወጣንባት ፣ያልተማርን ሆነን ሆነን ሊቆች ሆነን የወጣንባት ፣በመንፈሳዊ ዕውቀት ህጻን ሆነን ገብተን ጎልምሰን የወጣንባት ፣ትምህርት ሳንጀምር ገብተን የተመረቅንባት፣ብቻችንን ሆነን ገብተን የተዳርንባት ፣ልጅ ሆነን መጥተን አባት የሆንባት ፣ ከምንም በላይ የበግ ስጋ በልተን መጥተን የእውነተኛው በግ የክርስቶስን ስጋ ደም እንድንበላ ያደረችን ምርጥ እናታችን ናት።
ታዲያ ይህን ሁሉ ውለታ የዋለች እናት ሰንበት ትምህርት ቤታችን 20ኛ ዓመት የምስረታ ልደቷን ከፊታችን ህዳር 21 እና ህዳር 22 ታከብራለች ፤ በመሆኑም በዚህ መርሐ ግብር ላይ በመገኘት የባለ ውለታዋን ውለታ እናስብ ዘንድ በክብር ተጠርተናል።
አዎ
ሁሩ ወመሐሩ ፅፋት ቃሉን ዘሩን ያዙት በቃላችሁ ያላዛችሁት ካላችሁ ምትችሉ ማክሰኞ እናሐሙስ መጥታችሁ ፅፋቱን አጥኑ ሰራተኛ ክፍሎች።
Читать полностью…ሰላም ታህሳስ 27 የካዕላይ ክፍል የኢትዮጵያ ቤተክርስቲያን ታሪክ ሚድ ፈተና (ከመግቢያ -በግብፅ እስከ ነገሱ ኢትዮጵያዊያን ድረስ) እና ራብዓይ ክፍል ዮሀንስ ወንጌል አንድምታ ምዕራፍ 3 ፈተና ስለሚኖር ከወዲሁ ተዘጋጁ
Читать полностью…🙋 ውድ አባላት ለወጣንያን እና ቀዳማይ ክፍል በ19/4/2017 ከቀኑ 10:00ጀምሮ ምዘናው ይሆናል ። ለሰራተኞች ክፍል በ20/4/2017 (እሁድ) ምዘና መኖሩ ይታወቃል ሚጀመረው
'ምዘናው ' 3:00 በመሆኑ ቶሎ ለመጨረስ ከወዲሁ ተዘጋጅታችሁ በጊዜ እንድትመጡ ።
ከመዝሙር ክፍል☘☘☘🙏
🖐🖐🖐የጥር ስላሴ ወረብ
+ ነአምን በአብ ወነአምን በወልድ ወነአምን በመንፈስ ቅዱስ.
+አሀዱ ውዕቱ አምላክ ፍፁም አሀዱ ውዕቱ.
ትርጉም:- ፍፁም አንድ አምላክ በሚሆን በአብ ቢወልድ በመንፈስ ቅዱስ ስም እናምናለን።
🙋መልካም ጥናት🙏
ከመዝሙር ክፍል
🔔🔔🔔 ሰላም ለሰንበት/ቤታችን አባላት በሙሉ እንኳን ለእናታችን ለሰማዕቷ ለቅድስት አርሴማ አመታዊ በአል በሰላም አደረሳችሁ ። በሰአታችሁም እንድትገኙ።
🙏 ከሰማዕቷ ፀጋና በረከት ያሳትፈንመልካም አገልግሎት ይሁንልን ።🙏
☘ መዝሙር ክፍል🍀
🙏 🙏🙏 መስከረም 29🙏🙏🙏
ሰላም ለሰንበት ትምህርት ቤታችን አባላት በሙሉ የበዓታ ማርያምን ታቦት 1:00 ሰዓት ላይ ከድልድዩ ጋር ጀምረን ስለምናጅብ ሁላችንም 12:30 ላይ ደብር ተገኝተን የምስጋና ልብስ ለብሰን ከማኅበረ ካህናቱ ጋር አብረን በመሆን እንቀበላለን ። ስለዚህም ያያቹ ላላዩት የሰማችሁ ላልሰሙት አሰምታችሁ እንድትገኙ ። መቅረትም ሆነ ማርፈድ ክልክል ነው ።
2ኛ ጴጥሮስ 2:10 ስለዚህ ወንድሞች ሆይ መጠራታችኹንና መመረጣችኹን ታጸኑ ዘንድ ከፊት ይልቅ ትጉ እነዚህን ብታደርጉ ከቶ አትሰናከሉምና።
🙏ከባዕታ ለማርያም ረድኤት በረከት ያሳትፈን🙏
👏 መዝሙር ክፍል 👏
ሰላም ለሰንበት ትምህርት ቤታችን አባላትና ምዕመናን በሙሉ ከደብሩ ፅህፈት ቤት የበዓታ ለማርያም ታቦት የፊታችን ቅዳሜ ተቀብለን እሁድ ትገባለች የሚል መልዕክት ከቤ/ክኗ ስለተላለፈልን የአቡነ እጨጌዮሀንስን ጉዞ ወደ ታህሳስ 13/2017 ያስተላለፍን መሆናችንን ከይቅርታ ጋር እንገልፃለን።
Читать полностью…አረንጓዴ አሻራ
#የሾላ ዛፍ
ጌታችን በመንገድ ሲያልፍ እርሱን ለማየት ከሚሹ ሰዎች መሀል አንዱ ባለጸጋው እና የቀራጮች አለቃ የነበረው ዘኪዮስ አንዱ ነበር።ነገር ግን ዘኪዮስ ከሰዎች መጨናነቅ የተነሳና በቁመቱ እጥረት ምክንያት ጌታን ለማየት አልተቻለውም ነበር ።ነገር ግን ምንም እንኳን ቁመቱ ቢያጥርና የሰዎች መጨናነቅ ጌታን እንዳያየው ቢያግደውም ፡እጅግ አብዝቶ ጌታን ይወደው ነበርና ወደ ፊት ሮጦ ሄዶ የሾላ ዛፍ ላይ በመውጣት የሚወደውን ጌታን ለማየት ቻለ።ጌታም ያሳየውን ፍቅር እና መሻት ተመልክቶ፡ ሊያየው ብቻ የሚሻውን እርሱን፡ ቤቱ ድረስ በመግባት መሻቱን ፍጹም አደረገለት።
እኛም በህይወት ውስጥ፡ ምንም እንኳን በየቀኑ የጽድቅ ህይወት የመኖር ፍላጎታችንም ቢጨምርም፡ ነገር ግን ብዙ ጊዜ ከነፍስ ፍላጎታችን ይልቅ፡ ሥጋዊ ፍላጎታችን እየበለጠ ማየት የምንፈልገውን አምላክ እንዳናይ አድርጎናል ።እንደ ዘኪዮስ ቁመት ያጠረው ማንነታችን፡ ለብዙ መንፈሳዊ ዝለቶች ዳርጎናል።ኃጢአታችን ፣በደላችን ና ክፋታችን የዕድገት ሆርሞናችንን ገድሎ፡ ይኸው በመንፈሳዊ ህይወት ድንኮች ሆነን መኖር ከጀመርን ቆይተናል ።ከራሳችን ማንነት ጋር ደግሞ እንደምንም ታርቀን ወደ ቤቱ ስንመጣ ደግሞ፡ በአጠገባችን ያሉ ሰዎች በሚናገሩት ንግግር ፣በሚያደርጉት አልባሌ ተግባር ፣በሚያሳዩት አሽሙር ምክንያት ብዙ ጊዜ እርሱን ከማየት ተከልክለናል።ዘኪዮስ ጌታን እንዳያይ ሰዎች እንደጋረዱት ሁሉ፡ እኛም ጌታን እንዳናይ ብዙ ጊዜ ጋርደውናል ።
የዘኪዮስን ጌታን የማየት ፍላጎት ያሟላችለት ባለውለታው ታዲያ፡ ያቺ እርሱን ከፍ አድርጋ ወደ ላይ ያወጣችው የሾላዋ ዛፍ ናት።እኛም ምንም እንኳን ከላይ የገለጽናቸው ችግሮች ጌታን እንዳናየው ቢከለክሉንም ልክ እንደ ሾላዋ ዛፍ ግን እኛንም ከፍ አድርጋ ጌታን እንድንመለከት ያደረገችን የእኛ ሾላ ዛፍ ሰንበት ትምህርት ቤታችን ናት።ሰንበት ትምህርት ቤታችን ኃጢአታችንን ሰውራ ፣በደላችንን ከድና ፣ያለችንን ትንሽ መንፈሳዊ ህይወት ከፍ አድርጋ ፣አገልግሎት በሚባል ዘርፍ ከእግዚአብሔር ጋር እንድንሰራ በማድረግ፡ ጌታን እንድናይ እጅግ አድርጋ ረድታናለች።በሰዎች ተሰናክለን እንዳንወርቅ ፣ የዓለም ጫጫታ ና ግፊያው እዛው እንዳያስቀረን በትከሻዋ ተሸክማ "ኑ ከዓለም ተለዩና እግዚአብሔር እዩ " በማለት እንደ መልካም እናት ከፍ አድርጋ እግዚአብሔር እንድንመለከት አድርጋናለች። ክብር ለሾላ ዛፍችን።
ታዲያ የእኛ ሾላ ዛፍ (ፈለገ ዮርዳኖስ ሰንበት ትምህርት ቤት) የተተከለችበትን 20ኛ ዓመት ህዳር 21 እና ህዳር 22 በደማቅ ሁኔታ ታከብራለች ።ስለዚህ ሁላችንም በመርሐ ግብሩ ላይ በመሳተፍ አብረን ልደቷን እናክብር።
የዛሬ ብሎኬት ስራ ይህን ይመስላል። የሰንበት ት/ቤታችን ክፍል ግንባታ እንዲህ እየተፋጠነ ይገኛል። ይህን ለፍፃሜ ለማብቃት በገንዘብና በጉልበት አግዙን። የምትችሉ ነገ ከሰዓት እስከ ማታ ስራዎች ስላሉ ብትገኙልን
Читать полностью…